አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አምስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ
===
የመጀመሪያ ቀን እይታ የሰው ልብን መአከላዊ ስፍራ ለመያዝ ወይም ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው ይባል የለ፡ይሄንን ፕሪንስፕል ተከትዬ በሕይወቴ የመጨረሻውን መሽቀርቀር ነው የተሸቀረቀርኩት..ምን አልባት ይሄንን መልሼ የምደግመው ከእለታት አንድ ቀን ልቤን የምታቀልጥ ልእልት አግኝቼ ሚስቴ አድርጌ በማገባት ቀን ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡የኢጣሊያን ብራንድ ሱፍ ከእንግሊዝ በልዩ ትዕዛዝ የተገዛ ጫማ ፤በየሰው እፍንጫ ሲደርስ ከልብ ውስጥ ፍቅር ..ሰላምና ፍሰሀን የሚያመነጩትን ህብረ ህዋሳቶችን የሚያነቃቃ ልዩ የፈረንሳይ ሽቶ …..በአጠቃላይ በእጄ ላይ ያደረግኩት ሰዓት በጣቴ ያጠለቅኩት የአልማዝ ቀለበት….በዩኒቨርሲት ከገበየውት ዕውቀት በተጨማሪ ያለውበትን እና የሚገባኝን የህይወት ደረጃ በትክክል የሚያንፀባርቁና የሚያረጋግጡ እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኜ ነው ከቤቴ የወጣውት
አስደማሚውንና የተንጣለለውን ቢሮዬን ተረከብኩ….በመጀመሪያ በአስተዳዳሪው መሪነት በየክፍሉ እየዞርኩ ሰራተኞችን በመተዋወቅ ነበር የጀመርኩት..ተስፋ ሰጪና አበረታች ሁኔታ ነው ያጋጠመኝ…ከወጣት እስከአዛውንት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰራተኞች እኔን በአክብሮትና በመሽቆጥቆጥ እናም ደግሞ በፍራቻ ነበር የተዋወቁኝ ..ይሄ ደግሞ አሪፍ ምልክት ነው..ሁሉን በፈለኩት መጠን ለፈለኩት ተግባር በማሰማራት ተፈላጊውን ውጤት በማምጣት አባቴን አኮራዋለው ..ይሄንን ካምፓኒም ሶስቱንም ባለድርሻ አሳምኜ በዕድሜ ልክ እርስትነት ገዢ ሆኜ እሾምበታለው….፡፡
ቀጥሎ የየክፍሉን ኃላፊዎች ነበር ቢሮዬ ሰብስቤ ስለጠቅላላው የካማፓኒው እንቅስቃሴ ገለጻ እንዲያደርጉልኝ ያደረግኩት….አራት ሰዓት አካባቢ ለሶስት ወር እሰራዋለው ብዬ ከአወጣውት ዕቅድ ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ መስራት የሚገባኝን የስራ ዕቅድ በወረቀት ጫር ጫር አደረግኩና ፀሀፊዎ በኮምፒተር እንድትጽፍልኝ ስለፈለኩ ጠረጰዛዬ ላይ ያለውን መጥሪያ ተጫንኩት…ተላላኪዋ መጣችና ምን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ…
‹‹ፀሀፊዋን ፈልጌ ነበር…››
‹‹ውይ..የለችም››
‹‹የለችም ማለት..?በስራ ሰዓት የት ሄደች…?››ኮስተር ብዬ ጠየቅኩ…..አዎ ከአሁኑ ቆፍጠን እና ጠንከር ካላልኩ ከግማሽ በላይ አዛውንት ያሉበትን ከመቶ በላይ የሆኑ ሰራተኞችን በስርአት ልመራቸው አልችልም…አዎ አንዳይንቁኝ ለማንም ፊት ማሳየት የለብኝም ..ይሄ አቋሜ ነው፡፡
‹‹ጋሼ እኔ እንጃ ..ግን ትናንትም አልመጣችም..ዘመድ ሞቶባታል ሲባል ሰምቼያለው››
‹‹እሺ በቃ …በሩን ዘግተሸ ውጪልኝ››
ሹክክ ብላ ወጣችን በራፉን ዘጋችልኝ፡፡
‹‹አስተዳደሩ ጋ ስልክ ደወልኩ››
‹‹ሄሎ አቶ ሰይፉ››ቆፍጠን ብዬ
‹‹አቤት አቶ ፍሰሀ ምነው ፈለከኝ..? ልምጣ…..?››ተሸቆጠቆጡ
..አይ እቺ ወንበር..ብታዩ እኮ የስልሳ አምስት አመት የሰማይ ስባሪ የሚያህሉ ሰውዬ ናቸው…
‹‹አይ ፀሀፊዋ የለችም አሉኝ ..የሚያቀውቁት ነገር አለ…..?››
‹‹ይቅርታ ሰው መተካት ነበረብኝ..አክስቷ ሞታ የሳምንት እረፍት ወጥታለች፡፡››
‹‹ለአክስት ሞት አንድ ሰማንት…..?ለአክስት ይሄን ያህል ከፈቀዳችሁ እናት ስትሆን ደግሞ ወር ነው ማለት ነው..?››
‹‹አይ እንደሱ እንኳን አይደለም…ለቅሶው መቀሌ ነው …ራቅ ስለሚል ነው….አሁን የእኔን ጸሀፊ እልክልሀለው››
‹‹እሺ ላኩልኝ…ሌላውን በሄደት እናተካክለዋለን፡፡››ስልኩን ዘጋውት…
አያያዜ ለራሴ አስገረመኝ …..በዚሁ ከቀጠልኩማ በቃ አዳሜን ሽር ነው ማደርጋት……‹አያየዙን አይተው ጭብጦውን ቀሙት › የሚለውን ተረት እንዳይተረትብኝ ጥሩ መንገድ ላይ ነው ያለውት …አዎ ለራሴ እንደዛ ነው እየተሰማኝ ያለው …
ከ3 ደቂቃ ቡኃላ በራፉ በጥቂቱ ተንኳኳና ተከፈተ….በእኔው እድሜ አካባቢ ያለች ቸኮሌት ቀለም ያላት ልጅ እንደቀጭኔ የረዘመ አንገቷን አስቀድማ ወደውስጥ ገባች…ከአይኖቾ የሚረጨው ጨረር ልቤን ሲወጋኝ ታወቀኝ …ፀጉሯን አንድ ላይ አስራው ወደፊት በትከሻዋ በማምጣት ለቃው በደረቷ ወርዶ በጡቷቿ መካከል አልፎ እንብርቷ አካባቢ ደርሶል…አለባበሶ መጥፎም ጥሩም የማይባል መካከለኛ አይነት ነው፡፡ ‹ኖ ሜካፓ አትትቀባም ኦል…..›እንደተፈጠረች ምንም ባልነካካው በኦረጂናል ቆዳዋ ነች… ብቻ በድምሩ የሆነ ነገሯ አስደነገጠኝ….ከሁሉ በላይ ቁመቷ ያሰፈዝዛል…<ይሄን ሁሉ ቁመት ያሸከማት ምን እንድታደርግበት ነው.. ? በውስጤ የተፈጠረብኝ ጥያቄ ነበር…
‹‹አቤት ምን ነበር አልኳት››የተጨማደደ ፊቴን ሳልፈታ…. ሙሉ በሙሉ ገባችና በራፉን ዘግታ ወደ እኔ ቀረበች……ወደላይ አንጋጥጬ እያየዋት
‹‹ፊናን እባላለው…..ምንድን ነበር እንዲፃፍልህ የፈለከው..?››አለቺኝ ከእኔ በላይ በሆነ መኮሳተር
‹‹ፀሀፊዋ አንቺ ነሽ››ምንሽም ፀሀፊ አይመስል የሚል መልዕክት በሚያስተላልፍ የድምጽ ቅላፄ
‹‹አዎ ነኝ..››
‹‹ማን መሆኔን አውቀሻል….››አልኳት እስከአሁን መላው ሰራተኞቼ ለእኔ እያሳዩ የነበረውን መሽቆጥቆጥ እሩቡንም ከእሷ ስላላገኘው ስለማንነቴ ከለማወቅ ነው ብዬ በመገመት፡፡
‹‹አቶ ፍሰሀ የኤም.ዲ.ቲ ካንፓኒ ዋና ስራ አስኪያጅ…ፊት ለፊትህ እኮ ከፎቶህ ጋር ተፃፎ ይነበባል…››በሀገራችን ያልተለመደ የሚመስል ሰማያዊ ቀለም ያላቸው የዓይን ብሌን ነው ያላት.. ከሆነ ኮከብ የተሸረፍ የሚመስሉ አደገኛ ዓይኖቾን እያንከባለለችብኝ
‹‹ጥሩ ነው..አንቺ ግን የዚህ ካምፓኒ ሰራተኛ ነሽ…...?ቅድም ሰራተኞችን ስተዋወቅ ተገናኝተናል..?››ትእቢቷን ባለማመን ደግሜ ሌሎች ጥያቄዎች ጠየቅኳት
‹‹አዎ የጋሽ ሰይፉ ----ፀሀፊ ነኝ…በመጣህ ጊዜ ቢሮ አልነበርኩም..ስለዚህ አልተገናኘንም ››
‹‹በይ እዛ ወንበር ላይ ተቀመጪና በራሴ ላፕቶፕ ይሄንን ገልብጪልኝ..በፍጥነት ነው የምፈልገው፡፡
‹‹በፍጥነት ማለት..?፡፡››
‹‹በ15 ደቂቃ››አቀበልኳት….ተቀበለቺኝና ላፕቶፑ ፊት ለፊት ተቀመጠች….መጻፍ ጀመረች….ጨርሳ ስታስረክበኝ ገርሞኝ ሰዓቴን አየው 6 ደቂቃ ብቻ ነው የፈጀባት…
‹‹እየው…››አለቺኝ በተቀመጠችበት ልክ ለድርድር የመጣች ጉረኛ ባለጉዳይ አንደኛውን እግሯን በአንደኛው ላይ አፈናጣ በግምሽ እይታ እያየቺኝ…እግሮቾን በመደራረቦ የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ በመጠኑ ወደላይ ስለተሰበሰበ ወደጭኗ የሚጠቁም የሆነ ሸለቆ አይነት ምስል አይኔ ላይ ብዥታ ፈጠረብኝ..ይህቺ አለሌ ዱርዬ ሳትሆን አትቀርም ደረጃዬን በሚመጥን ሁኔታ እራሴን መቆጣጠር ይገባኛል ›በማለት ከውስጤ ተማከርኩና
‹‹አይ ቀስ ብዬ አየዋለው….ለጊዜው ጨረስን…ስፈልግሽ ጠራሻለው ››ብዬ እንድትወጣልኝ አዘዝኮት
‹‹እሺ ..››ብላኝ ከተቀመጠችበት በመለጠጥ ተነሳችና የሆነ ኪነ-ጥበባዊ በሆነ አረማመድ ወጥታ ሄደች…ይሄ አረማመዶ ተፈጥሮዊ ነው ወይስ የተጠና በልምምደ የተገኘ…..?ሁል ጊዜ የምትጠቀምበት ነው ወይስ ለማጥመድ የፈለገችውን እንደእኔ አይነነት አጎጊ ወንድ በሚያጋጥማት የክት ቀን የምትጠቀምበት…በጊዜ ሄደት የማረጋግጠው ይሆናል፡፡
አምስት ደቂቃ ስለእሷው ሳስብ ቆየውና..ቆይ እስኪ የሰራቸውን ልየው ብዬ ላፕቶፔን ወደራሴ በማስጠጋት ከፍቼ ማየት ጀመርኩ …ልቅም አድርጋ ያለምንም እንከን ነው የሰራችው..ግን ከታች ጻፊ ያላልኳትን ጨምራ ጽፋለች፡፡
‹‹ስለ ዕቅድህ ያለኝ አስተያየት››ብሎ ይጀምራል
1/ይንን ዕቅድ ወደተግባር ለመተግበር ከመሞከርህ በፊት የካምፓኒውን የስራ አካሄዶች፤ከሌሎች ካምፓኒዎች ጋር ተደረጉ የስራ ውሎችንና ስምምነቶችን፤አሁን ካምፓኒው እጅ ላይ ያሉ ስራዎችን ወ.ዘ.ተ ቢያንስ አንድ ሳምንት ወስደህ በደንብ ብታጠና
2/የካናፓኒውን ሰራተኞች
👍6
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሰባት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ

...ከአዳራሹ ሳይሆን ትንሽ ወደኃላ ተመልሼ ልጀምርላችሁ፡፡ እስከ አሁን አዋዋላችን በጣም ግሩም የተባለ ነበር..ከተለያዩ ሰራተኞችም ጋር በየምክንያቱ የመነጋገር ስሜታቸን ማዳመጥ፤ የመቀላለድ እና እስከዛሬ ከነበረው በተሸለ የመግባባት አጋጣሚውን ስንጠቀምበት ነበር የዋልኩት…ከፌናን ጋር ግን ከሩቁ ከመተያየት በስተቀር ፊት ለፊት የመገናኘቱ አጋጣሚ አልነበረም….ምን አልባት ሰላም ያዋልኩትም እንደዛ ስለሆነ ይሆናል..የማታውን ፕሮግራም ለመጀመር አዳራሽ ከገባን ቡኃላ ከቀኑ ከነበረው አለባበሷ በተቃራኒ በጣም ረጅም ግን ደግሞ በተመሳሳይ ውብ ያደረጋትን ደማቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳ ወደመድረኩ ስትወጣ ነበር ያየሆት…
ምትፈልገው የሆነ ዕቃ ኖሮ እሱን ለመውሰድ ወደ መድረክ የወጣች ነበር የመሰለኝ ግን ተሳስቼ ነበር… ፊት ለፊት ቆማ …ልክ ለአመታት የመድረክ ልምድ አንዳለው ፓለቲካኛ በሙሉ በራስ መተማመን ንግግሯን ጀመረች….እኔ እራሱ ምን አይነት እንከፍ ነኝ..እስኪ ቀደም ብዬ ፕሮግራማቸውን ባየው..እርግጠኛ ነኝ ከአስር ደቂቃ ባፊት እንኳን አውቄ ቢሆን እዚህች መድረክ ላይ እንድትወጣ ፈጽሞ አልፈቅድላትም ነበር…. ከመጀመሪያው ንግግሯ ነው የነገር ጦሮን በስውር የወረወረይብኝ..እስኪ እዚህ ሁሉ ሰው መካከል አቶ ፍሰሀና እጮኛቸው ማለት ምን ማለት ነው……..?እጮኛዬ ትሁን አትሁን አልነገርኮት ከየት አባቷ አወቀች…..?አቤት ወስጤ እንደተቃጠለላችሁ ..ሰውነቴ ሁሉ ሲንቀጠቀት ይታወቀኛል…ደግሞ ይህቼ ከጎኔ የተቀመጠችው መፍለቅለቅ ምን የሚሉት ነው…?የማንም ስርዓት አልባ መድረክ ላይ ወጥታ በዘጠና ምናምን ሰዎች ፊት‹‹.. የፍሰሀ እጮኛ… ››ብላ ስለተናገረችላት የእውነት እጮኛዬ የሆነች መሰላት እንዴ..?አናደደቺኝ……..
ከዛ አስተዳዳሪው ወጣ..የካማፓኒውን ሪፖርት እያቀረበ ቢሆንም ምን እንደለ አንዱንም አልሰማው…እያብሰለሰልኩ ያለውት ስለእዛች የተረገመች ልጅ ነው…እንዴት አድርጌ ነው አንገቷን ላስደፋ የምችለው….…እግዜር ይስጠው ሽማግሌው ሪፖርቱን አላንዛዛውም…ጨርሶ አመስግኖ መድረኩን ለዛች እብድ ለቀቀላት….እሷ ማለት ያቺ የተረገመች ወጥታ ስትናገር ብዙም ቁብ አልሰጣዋትም ነበር ..ግን ሽማግሌው ያቀረበውን ሪፖርት እያብራራች እየበታተነች ሳልወድ በግድ እየመረረኝ እንድሰማውና አደረገች…
ከፍተኛ ጥቃት ነው የተፈፀመብኝ ..በእኔ ብቻ አይደለም በካማፓኒውም…..ሰራተኞቹን ጠቃሚ ከሆኑት በላይ ጠቃሚ እንደሆኑ እዲሰማቸው…በትዕቢት ልባቸው እንዲወጣጠርና ነገሮች ለእኔ ከባድ እንዲሆኑብኝ ያሴረችው ሴራ ነው በእያንዳንዱ የዋህ ሰራተኛ አዕምሮ በጥበብ የበተነችው ..አዎ ንግግሯን ሰምተው ያጨበጨብላት ሰራተኞቹ የተናገረችው ሁሉ ለእነሱ አስባ ይመስላቸዋል…የእሷን ሴራ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው…እንደውም እሷን ማባረሬ በጣም ትክክለኛ ውሳኔ ነው..እና ይቅር ብያት እንድትመለስ የማስበውን ነገር ትቼዋለው..ለዚህችማ አይገባትም…ይህቼ ወጥ ረጋጭ ካቅሟ በላይ የምትንጠራራ… መኪና ተከራይታ ወይም ደግሞ ከሹገር ዳዲዋ ተውሳ እዚህ ይዛ በመምጣት ለመጎረር የምትጥር ከአቅም በላይ ለመኖር ስቃዬን ለምታይ ሴት ማዘን…
ወደመድረክ ስትጋብዘኝ የውስጥ ስሜቴ እየተተረማምሰ ነበር…የተዘጋጀውበትን ንግግር ሁሉ ቃላቶች ብትንትን ብለው ከአዕምሮዬ ተሰደዋል…ብቻ በደመነፍስ ወጣውና ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ‹‹በጣም በጣም ባለጌና መሰሪ ልጅ ነሽ ››አልኳት…ቆሽቴን እንዳሳረረቺኝ ቆሽቷን ላሳርርረው ብዬ..እሷ እቴ ምን በወጣት የመረቅኳት ይመስል ፈገግ ብላና ድምጽን ለሁሉም እንዲሰማ አድርጋ ‹‹አመሰግናለው አቶ ፍሰሀ …በእውነት ለካምፓኒዬ እና ለምወዳቸው የስራ ባለደረቦቼ ከዚህ በላይ መናገር ችዬ ብናገርና ባገለግል ደስ ይለኛል››ብላ ጭራሽ ያረረው ቆሽቴ እንዲከስል አድርገ መድረኩን ለእኔ በመልቀቅ ከኃላዬ ቆመች….

❤️ፌናን

የማታውን ፕሮግራም አትጠይቁኝ…ብዙሀኑ የተደሰቱበት እኔና ሰውዬው በየምክንያቱ በተገናኘን ቁጥር ስንጠዛጠዝና ስንነቋቆር ያሳለፍንበት ገራሚ ምሽት ነበር…በተለይ ፍቀረኛው የእኛኑ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ስትከታተልና ስትጠብቀን ነው ያመሸችው…አራት ሰዓት ሲሆን ይዛው ትሂድ ወይም ይዟት ይሂድ አላውቅም ብቻ ተያይዘው ወጡ….ወደ ማደሪያቸው…
እኔም ከ30 ደቂቃ ቡኃላ ቡድኑን ተለይቼ ወደማደሪያዬ ሄድኩ…..ገብቼ አልጋዬ ላይ እንደተዘርርኩ ነበር እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ያለው....ትንሽ መጠጥ የቀማመስኩ ጊዜ እንዲሁ ነው የሚያደርገኝ…ክፋቱ እንቅልፌ ቶሎ ያልቅብኛል…ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ሙለ በሙሉ እንቅልፌን ጨርሼ ፈጠጥኩ…እዛው እየተገላበጥኩ በውስጤ የሚተረማመሰውን ሀሳብ ማመንዠግ ቀጠልኩ… በዚህ ውድቅት ለሊትም ሀሳቤ ስለእሱው ነው….ምን እየሰራው ነው…….?ከልጁ ጋር ምን እንደዚህ አይነት ጫወታው ውስጥ አሰጋባኝ..….? እሱ አልሸነፍ ባይ ስለሆነ ነው..ወይስ እኔ የማሸነፍ ሱስ ስላለብኝ….….?ነው ወይስ ቀጥታ ከአላማዬ ጋር የሚገናኝ ትግል ነው…….?እንዴት እንደዛማ አይሆንም የእኔ ዓላማ በእሱ መሸነፍ ላይ እንደማይመሰረት እርግጠኛ ነኝ..እና ምንድነው ችገሬ…….?ይሄንን ሳስብ የለበስኩትን አንሶላና ብርድልብስ ከላዬ ገፍፌ ከአልጋዬ ወረደኩ….አፍቅሬው ብቻ እንዳይሆን…….?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ…….?ቆይ እስኪ ፍቅር እንዴት ነበር..….? አውቃለው እንዴ…….?
በሀያ አመቴ አካባቢ አንድ ሁለት የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር ፍቅር ፍቅር መጫወት ጀምሬ ነበር..ግን እኩዬቼ ቢሆንም እኔ በማስበው ልክ ሊያስቡልኝ ስላልቻሉ..እኔ ፍቅርን በምተረጉምበት ልክ ሊተረጉሙልኝ ሳላልቻሉ ከአንዱ ጋር አንድ ወር ከሌለኛው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር አብረን መዝለቅ የቻልነው…፡፡ያው ወንዶች ከሴት በእኩል ዕድሜ ሊበስሉ እንደማይችሉ ዘግይቼ ነው የተረዳውት…ማለት ያው የ18 ዓመት ሴት አንድ ቤትን እማወራት ሆና በደንብ ማስተዳደር ትችላለች አንድ የ18 ዓመት ወንድ ግን እራሱንም የማስተዳደር ብቃት ላይ አይደርስም…የድሮ አባቶቻችን እንዲሁ በዘፈቀደ አይደለም ወጣቶችን ሲያጋቡ ቢያንስ ወንዱ ከሴቷ በ5 ዓመት ቢበልጣት ጥሩ እንደሆነ የሚመክሩት እና እንደዛም እንዲሆን በተቻላቸው መጠን የሚጠነቀቁት…
የእሳትነቱን ዘመን ካለፍኩ ቡኃላ ደግሞ ፍቅርን በተመለከተ አንድ ቅድመ ሁኔታ ለራሴ አስቀመጥኩ… የማፈቅረው ሰው እኔ እንደምወደው እሱ ግን እንክትክት እስኪል ድረስ እንደሚያፈቅረኝ እርግጠኛ ስሆን ብቻ ነው እጄን ዘርግቼ ልቀበለው የምችለው፡፡ይሄን ለምን እንዳልኩ ማስረዳት አለብኝ መሰለኝ..ወንድ ልጅ በደንብ እንዳፈቀራት እርግጠኛ ሳትሆን እጇን የሰጠችና ወደጋብቻ የገባች ሴት ብዙ ጊዜ ከሳሪ ነች፡፡ምክንያቱም አብዛኛቹ ወንዶች የፍቅር ጫፍ ላይ የሚደርሱት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ጊዜያቶች ነው…ከዛ ወደግንኙነት ሲገቡ ፤ ከዛም አልፎ ወደ ትዳር ሲሸጋገሩ የማፍቀር መጠናቸው እየወረደ ነው የሚመጣው..ቢያንስ በግንኙነት ፍቅር ላይ የነበረ ስሜቱ ወደ ትዳር ሲገባ መውደድ ላይ አርፎ እንዲረጋጋ ከፍቅር መጀመር አለበት....ለሴት ልጅ ግን ተቃራኒው ነው ፡፡በግንኙነት እና በመላመድ ስሜቷ እያደገና እየጎለበተ ነው የሚመጣው.. ፡፡ በግንኙነት ወቅት መውደድ ከቻለች፤በትዳር ውስጥና በመላመድ ወደላይ ነው የምታሳድገው ወደፍቅር …አብዛኛዋ ሴት እንደዚህ ነች…እና እኔም የምወደውን እና እሱ ደግሞ የሚያፈቅረኝን እንዳገኘው እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ለማንም ልቤን ከፍቼ አልሰጥም፡፡ለዚህ ፍሰሀ ለሚባለውም ቢሆን
👍3
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ
===
እየጎተትኳት መኪናው ጋር ስንደርስ ቀጥ አልኩ…ለካ የመኪናዬን ቁልፍ አልያዝኩም ‹‹ሶሪ ፊናን ሁለት ደቂቃ››
‹‹ምነው››ግራ ገብቷት
‹‹የመኪና ቁልፍ ይዤ መጣሁ…››በማለት እዛው ጥያት በሶምሶማ ወደ መኝታ ቤቴ ሄድኩ…እመቤቲቱን እዳልቀሰቅሳ በቀስታ ከፍቼ ገባውና ወደ ኮመዲኖ ሄጄ የመኪናዬን ቁልፍና ሞባይሌን በቀስታ አንስቼ በዝግታ እየተራመድኩ ልወጣ በራፍ አካባቢ ስደርስ ‹‹ማሬ ››የሚል ድምጽ ወደ ኃላዬ እንድዞር አስገደደኝ..
‹‹ተነሳሽ እንዴ? ››
የተጨናበሰ አይኗን በእጆቾ እያሻሻች ‹‹አዎ ..ወዴት ነው…?››አለቺኝ
እየተንደረደርኩ ወደውስጥ ተመለስኩና ግንባሯን ስሜ ‹‹መጣው ተኝተሸ ጠብቂኝ..ወይንም እታች ወርደሽ ቁርስ መብላትም ትቺያለሽ››
‹‹እንዴ ምን ማለትህ ነው..? ምትሄድበት ቦታ አብሬህ እሄዳለው..አምስት ደቂቃ ጠብቀኝ……››
‹‹አይ ምን አስቻኮለሽ ..ዘና ብለሽ ተነሽ…ብዙም አልቆይም መጣው….››እልኳትና መልሷን ሳልሰማ ተንደርድሬ ወጣሁና በራፍን መልሼ በላይዋ ላይ ዘግቼባት እየተንደረደርኩ የሆቴሉን ደረጃ በመውረድ ወደምትጠብቀኝ አስደማሚዎ ፊናን ተመልሼ ሄድኩ….
ስደርስ‹‹እኔስ ሚስትህ አፍና አስቀረችህ ብዬ ወደ ክፍሌ ልመለስ ነበር››በሚል ሽርደዳ ተቀበለቺኝ
‹‹አይ ተርፌያለው›› አልኩና መኪናዋን ከፍቼ እሷን አስቀድሜ በማስገባት ዞሬ መሪውን በመጨበጥ ግቢውን ለቀን ወጣን… አስፓልቱን እንደያዝን ….‹‹ወዴት እንደምትወስደኝ ለማወቅ ጓጉቼለው››አለቺኝ
‹‹ይገርምሻል በጫወታሽ በመማረክ ከአንቺ ጋር ተጫማሪ የብቻችን ጊዜ ለማሳለፍ ስለፈሉኩ እንጂ ወደየት እንደምወስድሽ ምኑንም አላውቅም…››አልኳት…እውነትም በዚህ ጥዋት ለዛውም በለሊት ልብሷ ያለች ሴት ወዴት ይዣት ልሄድ እንደምችል ምኑንም አላውቅም…ሳቋን ለቀቀችው..ስትስቅ በጣም ታምራለች…ኪሊዬፓትራም ስትስቅ እንዲህ ታምር ነበር እንዴ ..?እሷም ስትስቅ የጁሊዬስ ቄሳር እና የማርክ አንቶኒዬን ልብ አሁን የእኔ ልብ ቀጥ እንዳለው ቀጥ ይልባቸው ነበር እንዴ…‹‹አንተ ይሄ ጥሩ ስነ-ምግባር ነው…?››አለቺኝ በትዝብት
‹‹እንዴት ምን አጠፋው?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት
‹‹ አንተን ብላ ኪሎ ሜትር አቋርጣ አምናህ የመጣችውን ፍቅረኛህን መኝታ ቤት ውስጥ ዘግተህባት ከሌላ ሴት ጋር ለብቻችን ሆነን ማውራት አማረኝ በሚል ተቀባይነት በሌለው ምክንያት እንዲህ ማድረግህ?››
‹‹በነገርሺኝ ታሪክ ነው የተማርኩት…ኪሊዬፓትራ ያፈቀሩት ሁለቱም ጀግኖች ባለትዳር ነበሩ..በእሷ ፍቅር ሲሸነፍ ትዳር ስላለን ይቅርብን አላሉም፡፡››
‹‹ጥሩ ተማሪ ነህ..ክፍ ክፉውን ብቻ መርጠህ አዕምሮ ውስጥ አስቀረህ….ደግሞ ፍቅር ያዘህ እንዴ?››
መኪናውን ዝም ብዬ በሰርክል አድርጌ ወደ ሆራ መስመር እየነዳውት ነው…
‹‹ማ እኔ ካንቺ ፍቅር…?››
‹‹አይ ድንገት እንደው ተሳስተህ አፍቅረኸኝ እንደሆነ ብዬ ነው?››
‹‹አይ እንደዚህ አይነት ስህተትማ አልሳሰትም……››አልኳት.
.እውነት አልተሳሳትኩም እንዴ..ካልተሳሳትኩ ታዲያ ምን እንደዚህ ያደርገኛል …?አንዴት ስለእሷ በየሰዓቱ የተዘበራረቀ አይነት ስሜት ሊሰማኝ ቻለ…?. ስታበሳጨኝ ምበሳጭላት ሳታስቀኝ ምስቅላት ምኔ ስለሆነች ነው ..?እራሴን የጠየቅኩትና በርግጠኝነት መልስ ላገኝላት ያልቻልኩት ጥያቄ ነው፡፡ምክንያቱም ከራስ ልብ ውስጥ እውነተኛ መልስ ማግኘት ከአንደበት ቃላት አውጥቶ ለሌላ ሰው ድንገተኛ መልስ እንደመመለስ ቀላል አይደለም፡፡
መከላከያ ኮሌጅ አካባቢ ስንደርስ ስልኬ ተንጫረረ…ሳየው የአባቴ ነው….‹‹ወይ ዳድ ነው የደወለው ማንሳት አለብኝ››አልኩን መኪናዬን ዳር ላይ አቆምኩ...ከምንቆም ቀይሪኝና አንቺ ንጂ ››አልኳትና ስልኩን አንስቼ እያዋራው ከገቢናው ወጥቼ ዞርኩ እሷም ዞረችና መሪውን በመጨበጥ በዝግታ ትነዳ ጀመር …እኔም አዕምሮዬን ሰብስቤ የናፈቀኝን አባቴን ማዋራት ቀጠልኩ….
‹‹እንዴ ዳድ አበዛሀው እኮ…በጣም ነው የናፈቅከኝ››ተነጫነጭኩበት….
‹‹ልጄ እኔም …..በጣም ነው የናፈቅከኝ››
‹‹አይ አይመስለኝም… ብናፍቅህማ ይሄን ያህል እትቆይም….››
‹‹አሁን መምጫዬ ደርሷል..ለመሆኑ ስራው እንዴት እየሄደልህ ነው፡፡››
‹‹አሪፍ ነው አባዬ…. በጣም አስደሳች እየሆነ ነው….አሁን ሰራተኛችንም ሆነ ስራውን በደንብ ለምጄዋለው… አንዳንድ ውጤታማ ለውጦችንም ለማድረግ እያሰብኩ ነው››
‹‹አይ አሪፍ ነው…ለመሆኑ ሰራተኞቹ በአንተ ላይ እምነት ያሳደሩ ይመስልሀል….መቼም ታውቃለህ ልጄ የምትመራቸውን ሰራተኞች ቀልብ ማሸነፍ ሳትችል ውጤት ማምጣት አትችልም››
‹‹አዎ ትክክል ነህ ዳድ..ሀላፊዎቹም ሆኑ ተራ ሰራተኞች በጣም ታዛዥና ተግባቢ ናቸው..እርግጥ አልደብቅህም አልፎ አልፎ አልታዘዝ ባዬችና ስርአት የሌላቸው ሰራተኞች አሉ ..እነሱንም የሚገባቸውን ትምህርት የሚሰጥ ቅጣት እየቀጣው ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ችያለው››ይሄንን ስናገር በቆረጣ ፊናንን እያየዋት ነው….ምን ያህል ትበሳጫለች የሚለውን ለማየት..በተቃራኒው የሹፈት ሳቅ እየሳቀች እንደሆነ ነው መታዘብ የቻልኩት ፡
‹‹ልጄ ሰራተኞችን በጥበብ ያዝ …ዝም ብለህ ቀጥታ አትላተም…››አባታ ምክሩን ቀጠለ
‹‹አይ አባ …ሁሉን የምታገስ ከሆነም እንዴት ብዬ ነው በሶስት ወር የምትፈልገውን ውጤት ማግኘት የምችለው..በዛ ላይ አንደኛው ወር እያለቀ ነው..››
‹‹ልጄ አሁን የደወልኩልህ ስለዛ ላወራህ ነው…ለዛ የሚሆን ጊዜ የለንም …ስብሰባው ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲደረግ ተወስኗል..››
‹‹ብዥ ነው ያለብኝ….እንኳንም እኔ እየነዳው አልሆነ ….መኪናዋን መንገድን ስቼ ከሆነ ግንብ ጋር እላተም ነበር..
‹‹እንዴ አባ ..በአንድ ወር ምን አይነት ተአምር ልሰራ ነው…እሰከአሁን እኳን ሙሉ በሙሉ የካማፓኒውን አሰራር እና የእያንዳዱን ሰራተኛ ብቃትና ጉድለት አጥንቼ አልጨረስኩም…እነዚህን ነገሮች በጥልቀት ሳላውቅ ደግሞ የካምፓኒው ጥሩ ጎኑንና ለውጥ የሚያስፈልገውን ቦታ ለይቷ ማወቅ ያስቸግረኛል…..በሶስት ወር ምን አይነት የተለየ ነገር ማድረግ እችላለው ብዬ ስጨነቅ ጭራሽ አንድ ወር?፡፡..አልችልም አባ … የእውነት የመጣው ይምጣ እንጄ በአንድ ወር ውስጥ የምትፈልገው ነገር ላሳካው አልችልም ››
‹‹አውቃለው ልጄ..እኔም ያማትችለውን ነገር አድርግ ብዬ ላስጨንቅህ አልፈልግም››
‹‹እና ታዲያ እንሸነፍ…ዕድሜ ልክህን የለፋህበትን ካምፓኒ እጅ ሰጥተን ለሴትዬዋ እናስረክባት…እሷ ለሴት ልጄ ሰጥታ ድርጅታችንን ድምጥማጡን እንድታጠፋው እንፍቀድላት…እንዴ አባዬ አንዴት እንዲህ በቀላሉ ተሸናፊ ሆንክ…?. ህልሜንማ እነዲህ ፍቺ አልባ አታድርገው…››
‹‹ልጄ አሁን መስፈርቱ ተቀይሯል ..አንተም ሆንክ የሴትዬዋ ልጅ የምትወዳደሩት በምታቀርብት ፕሮፕዛል ጥራት እንዲሆን ተወስኗል….ክምፓኒውን በጥልቀት ምን ያህል አውቃችሁታል …ወደፊትስ የት እንዲደርስ ለማድረግ ትችላላችሁ… …በዛ ነው የእያንዳንዳችንን ድምጽ በተለይ ልዩነት የሚያመጣውን የሰውዬውን ድምጽ ማግኘት የምትችሉት››
‹‹እንደዛ ከሆነማ ቀላል ነው…››
‹‹እንዴት ቀላል ነው ልትል ቻልክ.?.››
‹‹እንዴ አባ አንደኛ አሁን በካምፓኒው እንድሰራ እድል በማግኘቴ ምክንያት ብዙ ዕውቀቶችን አግኝቼያለው….ይሄ ደግሞ ለፕሮፖዛሉ በቂ ግብአት እንዳገኝ ያግዘኛል..ሁለተኛ የካምፓኒውን ሀላፊዎች ሆነ ኤክስፐርቶችን ሁሉ ቀኑ እስኪደርስ ድረስ መጠቀም እችላለው፤ ከእነሱ የማገኘው እገዛም ሆነ ግብአት ቀላል አይደለም…ሌላው አስፈላጊወም ከሆን ረዳት
👍7
ቀጥሬ እንዲያግዘኝ ማደረገ እችላልው..ይሄን ሁሉ አድርጌ አንዲት ሴት ማሸነፍ ካቃተኝም ያንተ ልጅ አይደለውም ማለት ነው››የምሬን በብስጭት ፎከርኩ
‹‹እንደምታደርገው አምናለው ልጄ.. ላስጠነቅቅህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ወሳኙን የመለያ ድምጽ የያዙት ሰውዬ ቀላል ሰው እንዳልሆኑ ነው….ሁል ጊዜ የተለየ ነገር ይፈልጋሉ…ከዚህ ቀድመው የማያውቁትን ወይንም በጣም ሊያስደምማቸው የሚችል ነገር ካላገኙ ድምጻቸውን ማግኘትን አታስበው..….በተረፈ ዝርዝሩን ስመጣ እናወራለን..እኔም አግዝሀለው››
‹‹መች ነው የምትመጣው ?››
‹‹ከአስር ቀን ቡኃላ መጣለው››
‹‹እሺ ቻው አባ እወድሀለው››
ስልኩን ዘግቼ አካባቢዬን ስቃኝ ለካ መኪናውን ዳር ይዛ በማቆም በተመስጦ ዝም ብላ እያዳመጠቺኝ ነበር
‹‹እንዴ ምነው መኪናውን አቆምሽ..?››ጠየቅኳት
‹‹አይ እዚህ ትንሽ እድንቆይ ፈልጌ ነው››
‹‹አባቴ እኮ ደውሎ .በጣም ደባሪ ነገር ነው የነገረኝ..››
‹‹ሰማውኮ…ነገሩ በደንብ ባይገባኝም መረበሽህን ከንግግርህ ተረድቼያለው…››
‹‹አዎ ባክሽ ላንቺ መንገር ይኑርብኝ ወይስ አይኑርብኝ አላወቅም እንጂ ትንሽ የሚረበብሽና ያልጠበቅኩት ነገር ነው ..››
‹‹ከደበረህ ተወው…ግን የካማፓኒው ስራ-አስኪያከጅ ለመሆን አንድ ተቀናቃኝ አለችብህ መሰለኝ…ከንግግራችሁ የተረዳውት ያንን ነው…››
‹‹አልተሳሳትሺም…ግን እወጣዋለው››
‹‹ለምን ከሴት ጋር ስለሆነ ፉክክሩ…?.ሴት ደካማ ስለሆነች?››ኮስተርና በስጨት ብላ
‹‹አይ ማለቴ….››የምላት ጠፋኝ
‹‹ለመሆኑ ልጅቷን ታውቃታለህ..?ማለቴ የትምህርት ዝግጅቷን ?የስራ ልምዷን? የተፈጥሮ ብቃቷን..?››
‹‹አይ አላውቅም…ግን ያው በእኔ ዕድሜ አካባቢ እንደሆነች አውቃለው…ስለዚህ ሌላውን መገመት ብዙም አይከብደኝም…››
‹‹ሴት መሆኗን እና በአንተ ዕድሜ ላይ ምትገኝ መሆኗን ብቻ በማወቅህ የእሷን ብቃት ካንተ በታች ዝቅ አድርገህ ለመያት በቂ መረጃ ሆነህ …ብቻ እግዜር ይሁንህ ..፡፡ግን እንደ ምክር ልስጥህ …ማንኛውም ጦረነት ውስጥ ስትገባ ምንም አይነት መንገድ የባለጋራህን ችሎታ ዝቅ አድርገህ አለማየት ይጠቅምሀል በሌላ ጎኑም በራስህ ላይ ያለህን በራስ መተማመንም ማጣት የለብህም…ይሄ ትክክለኛውን ዝግጅት እንድታደርግና በዝግጅትህም መጠን በብቃት እድትፋለም ያግዝሀል፡፡
‹‹ምን አበሳጨሽ አንቺ?›› አልኳት..መበሳጨት ከንግግሯም አልፎ በፊቷ ላይ በግልጽ ስለተነበበ..
‹‹አይ እንዲሁ ነው…ለማንኛውም ይሄ የምታየው ጨለቅለቃ ሀይቅ ነው…የሚደነቁ አይነት ወፎች በአካባቢው አሉ… ለተወሰነ ደቂቃ ወርደን በግር እንራመድ››አለቺኝ
በደስታ ተስማምቼ ወረድኩ መኪናውን በመቆለፍ ወደእሷ በመሄድ የአስፓልቱን ዳር ይዘን ቀኝ እጄን ተከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ አካባቢውን የወረሩት ደግሞ ስንጠጋቸው እየተበተኑ ሰማዩን በውበት እየሞሉ በመንሳፈፍ ዛፎቹ ላይ የሚያርፉትን እንደ ዳክዬ ፤ፓሮት፤ ፍላሚንጎ ፤ ብዙ ስማቸው የማላውቃቸውን የተለያየ እና ገራሚ ዝርያ ያለቸውን ወፎችን እየተመለከትን ስንራመድ..
‹‹ፀጥ አልሽ ምነው?››
‹‹እኔ እንጃ ከአባትህ ጋር ስታወራ አባቴ ናፈቀኝ?››
‹‹አባትሽ…ታዲያ አውሪያቸዋ..›› ስልኬን አቀበልኳት..ስልኩን ተቀብላኝ ቁጥሩን እየመታች ሸርተት ብላ እጆን ከትከሻዬ ላይ አወረደችና ወደኃላ ቀረች..ገባኝ ፡፡የማወራውን ነገር እንድሰማባት አልፈለገችም ማለት ነው…ስለዚህ ፈጠን ፈጠን ብዬ ወደፊት በመሄድ በመሀከላችን የነበረውን ርቀት አሰፋውት
===
❤️ፌናን

ይህ የተረገመ ልጅ በደቂቃዎች ነው ስሜቴን ያደፈራረሰው….ከአባቱ ጋር ያወራው ወሬ በራሱ ግርታ ፈጥሮብኛል በዛ ላይ የእሱ ለሴት ያለውን ዝቅ ያለ ግምት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አናዳጅ ሆኖ ነው ያገኘውት ..…እንደው ወንዶች ምንም ቢማሩ፤ ምንም ያህል ዘመናዊ ነን ቢሉ እብሪት አይለቃቸውም..ስሜቴን መደፍረስ ተከትሎ ዝም በማለቴ ለጠየቀኝ ጥያቄ በሰጠውት መልስ ለአባቴ እንድደውል ስልኩን ሲያቀብለኝ አላቅማማውም…ከእሱ ወደኃላ ቀርቼ አባቴን እያወራውት ነው…
‹‹እንዴ…አንቺው ነሽ ማሬ ..ስደውልልሽ እኮ ስልክሽ ይጠራል አይነሳም…ሳይለንት ላይ አድርገሽው ያላየሽው ነበር የመሰለኝ፡፡››
‹‹አይ አባ መኝታ ቤቴ ረስቼው ከልጆች ጋር ዞር ዞር እያልን ስለሆነ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ነው….በቃ ተዝናኑ ..››
‹‹እሺ አባ .ከመዝጋትህ በፊት ግን እማዬ ደውላ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ ምነው ማታ ደውላ ነበር››
‹‹ያለችህ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹አዎ ከስድስት ወር ቡኃላ ለማድረግ ቀጠሮ ይዛበት የነበረው ወደ ሶስት ወር ዝቅ ብሎል..ከዛሬ ሶስት ወር ቡኃላ የልብ ቀዶ ጥገናውን ታደርጋለች..ስለዚህ ከዛ በፊት ከሀያ ቀን ቡኃላ ወደሀገር ቤት እንደምትመጣ ነግራኛለች..ግን ምነው..?የሰማሺው ነገር አለ እንዴ?››
‹‹አረ የለም ..እንዲሁ በህልሜ ስላየዋት ነው..በል አባ ቻው ..ደውልልሀለው..እና በጣም እድሀለው፡፡›› ስልኩን ዘጋውና ወደ እሱ ፈጠን ብዬ ሄድኩ…..

#ፍሰሀ

ስልኩን አናግራት ጨርሳ ስትመጣ ልክ ፍቅረኛዋን አናግራ እንደመጣች ነገር ነው ከጨገጋት ስሜት ወጥታ እየተፍለቀለቀች የመጣችው….ግን ፍቅረኛውን እንደሆነ ያናገገረችው በምን አውቃለው…››በውስጤ የተጫረ ጥያቄ ነበር..ደግሞ ወዲያውኑ ፍቅረኛዋንስ አናግራ ብትመጣ አንተ ምንህ ተነካ…..››እራሴን የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር… አይ መነካት ሳይሆን ለምን ትዋሸኛለች ?››ለአዕምሮዬ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሞከርኩ..መጥታ ልጥፍ ስትልብኝ ሁሉንም እረሳውትና ጠረኗን እየማግኩ ውቡን ተፈጥሮ፤ የሚያማምሩ ወፎችን ዝማሬ ወደማዳመጥ ተሸጋገርኩ..
ታብራራልኝ ጀመር‹‹ይሄን ሀይቅ በበጋ ብትመጣ አሁን እንዲህ እንደምታዬው አታገኘውም…››
‹‹እንዴት?››
‹‹ይደርቃላ..ባዶ ይሆናል፡፡ከዛ የአካባቢው ሰዎች ለግብርና ስራ ይጠቀሙበታል ….ሽንኩርት፤ ቲማቲም ፤በቆሎ ጭምር ያመርቱበታል..ክረምት ሆኖ ዝናብ መዝነብ ሲጀምር ግን ከከተማው ሁሉ ተሰብስቦ የሚመጣው ጎርፍ ተጠራቅሞ የሚተኛው እዚህ ስለሆነ ተንጣሎ ይተኛል….የሚገርም ሀይቅ ይሆናል..ያንንም ተከትሎ ከዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አህጉር አቋራጭ ወፍች ጭምር እንደምታየው መጥተው እዚህ በጊዜዊነት በመስፈር አካባቢውን የበለጠ ውብ ያደርጉታል….በዛ ላይ አዚህ አካባቢ ቆመህ ፊትህን ወደ ሀይቁ አዙረህ ማዶ አሻግረህ ስታይ የሚገርም የተፈጥሮ እይታ ነው አይንህን የሚሞላው…ያ ተራራ ይታይሀል..ኤረር ተራራ ይባላል፡፡አስር የአዲስአበባ ወጣት አቁመህ ኤረር ተራራ የት ይገኛል ብትል አንድ ሰው ብቻ ቢመልስልህ ነው…
‹‹እኔ እራሴ አላውቅም …››
‹‹ይሄ ተራራ እንደምታዬው አስደማሚ ሰንሰለታማ ተራራ ሲሆን ብቻው እንደሙዚዬም ሊጎበኝ ሚችል ታሪክ ያለው ነው፤በውስጡ ከ300 በላይ ዋሻዎች አሉት ፡፡ከዛም በላይ የአብረሀ አጽብሀ ቤተመንግስተ እና የልብነድንግል ቤተመንገስቶች ነበሩበት..አሁንም ፍርስራሹ ይገኛል…በዛ ላይ በጣም ብዙ ደብሮች በተራራው ላይ እንደነበሩ ታሪክ ይናገራል..ከዛም አልፎ የኢትዬጵያ ማዕከላዊው ስፍራ ወይም እንብርት ይሄ ተራራ እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ..ይሄም አንዱ ድንቅ ሚስጥር ነው፡፡አሁንም ከታሪካዊነቱ በተጨማሪ አካባቢው በአሁኑ ጊዜ በደን የተሸፈነ እና ለፍፁም መደመምና ከራስ ጋር ለመማከር ተመራጩ ቦታ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ከዚህ 9ኪሎ ሜትር ብቻ ብትሄድ ዝቋላ ገዳምን ታገኘዋለህ…ዝቋላ ስትሄድ ታራራ ታገኛለህ ፤
ሀይቁም ታገኛለህ..ሀይቁ የሚገርም ገበቴ ውስጥ ያለ የሚመስል ዙሪያውን በቄጤማ የተከበበ ነው፡፡አካባቢው ዙሪያውን በየአመቱ በሚነሳ ሰደድ
👍102
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ
===
መቼስ ያለውበትን ሁኔታ በጥቂቱም ቢሆን ግንዛቤው ይኖራችሆል ብዬ አስባለው፡፡ለዚህ ለዓላማዬ መሳካት ቁልፍ ለሆነው የፕሮፖዛል ዝግጅት ሙሉ ጊዜዬን ሰጥቼ ጠብ እርግፍ እያልኩ ነው….በሌላ ጎን ደግሞ ይህቺ ፌናን የምትባል ልጅ እራሷን የቻለች የቤት ስራ ሆናብኛለች፡፡በቃ የሆነ ነገር ሳታውቁት ከቁጥጥራችሁ ውጭ በሆነ ስሜት ስተት ብሎ ከደምስራችሁ ጋር በመስረግ በመላ ሰውነታችሁ ጋር ተዋህዶባችሁ ያውቃል…በቃ ልቤ ላይም ፤ አዕምሮዬ ውስጥም፤ እታች የእግሯቼ ጥፍሮች ላይም በእኩል መጠን ያለች ነው የሚመስለኝ..፡፡እንደእዚህ እንዴት ሆነ ……?አላውቅም….፡፡በቃ አፍቅሬያታለው፡፡ማፍቀሬን ደግሞ በውስጤ ስላፈንኩት እየተጎዳው ነው...ህመሙ ልቤ ስር እስኪሰማኝ ድረስ የተጎዳውበት ነው….
ስራውን በተመለከተ ረዳቴ ሆና በጣም እያገዘቺኝ ነው..እርዳታዋ በጣም ጠቃሚና ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ እራሴን እስክታዘብ ድረስ ነበር ስደመምባት የነበረው፡፡ ….አሁን ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ያለው ፕሮፖዛል እሷ ባታግዠኝ ኖሮ በራሴ እሰራው ከነበረው ጋር በሀሳቤ ሳመዛዝነው ደነግጣለው..፡፡ልጅን እንደ ቁጥር አንድ ጀግና በሚያስበው አባቴ ፊት ተዋርጄ ነበር…፡፡አሁን ግን እድሜ ለፌናን አይደለም ከአንዲት ልምድ አልባ ወጣት ሴት ጋረ ይቅርና ከማንም በስራው እድሜ ጠገብ ልምድ ያለው ሰው ጋር ተወዳድሬ ቦታውን በእጄ ማስገባት እችላለው፡፡፡የዛን ያህል በራሴ እንድተማመን አድርጋኛለች ፡፡አሁን በዛ እርግጠኛ ሆኜያለው ፤ ይገርማችሆል ፌናን ጭቅጭቆ እራሱ ሱስ ይሆንባችኃል…….አሁንም ቢሮ ጭቅጭቅ ላይ ነን፡፡ ስለዚሁ የፕሮፖዛል አንዱ ክፍል የሆነ የሰራተኛ ደሞዝን በተመለከተ እየተነጋገርን ነው…
‹‹አሁን ለሰራተኟች እየተከፈለ ያለው ደሞዝ መስተካከል አለበት ..››የሚል ሀሳብ አቀረበች
ወዲያው ነው የተቃወምኳት‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ……?በተመሳሳይ የስራ መደብ በመንግስት ቤት ከሚከፈላቸው ሰራተኞች ጋር ሲነፃፀር ቢያንስ አርባና ሀምሳ ፐርሰንት የእኛ ጭማሪ አለው..እና በዚህ ላይ አሁን በምናደርገው ማሻሻያ ላይ የ5 ፐርሰንት ጭማሪ ማድረጋችን በጣም ምክንያታዊና በቂ ነው ብዬ አስባለው፡፡››
‹‹አልስማማም..››አለቺኝና ንግግሯን ማብራራት ቀጠለች‹‹ይሄውልህ በመጀመሪያ ደሞዝን በተመለከተ የመንግስትን እስኬል ማነፃፀሪያ ማድረግ ትክክል አይመስለኝም፡፡››
‹‹ለምን ………..?መንግስት እንደዛ ለምን እንደሚከፍል ታውቂያለሽ ፡፡ሀገሪቱ ደሀ ስለሆነች ነው፡፡እኛም ደግሞ መክፈል ሰለቻልን ብቻ ዝም ብለን መክፈል የለብንም ….ገበያውን ማበላሸት ነው የሚሆነው››
‹‹ላስቁምህ..ይህቺ ገበያውን ማበላሸት ነው የምትለው ቀሺም ምክንያት ነች ..እዚህ ሀገር ላይ የሰው ጉልበት ዋጋን በተመለከተ በጣም የተዛባ አመለካከት አለ…መንግስት ሀገሪቱ ደሀ ስለሆነች ከዚህ በላይ የተሻለ ደሞዝ መክፈል አልችልም ይላል..ግን እውነቱ ያ ብቻ ይመስልሀል…?፡፡እንደእኔ ግንዛቤ ዋናው ችግሩ ያመለካከት ነው……በየመስሪያ ቤት በቋሚ እና አላቂ ንብረቶች ላይ የሚከሰትን ብክነትና ብልሽትን የተወሰነ ግንዛቤ በመፍጠር እና የተወሰነ የጥንቃቄ እርምጃ በማድረግ ለዓመታዊ ዕቃ ግዢ የሚወጣውን ወጪ በ50 ፐርሰን መቀነስ ብንችል ከዛ በተገኘ ገንዘብ ቢያንስ የእያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ላይ የ25 ፐርሰንት የደሞዝ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለህ ታስባለህ…?.ባለስልጣኗች በሙስና የሚቀራመቱትን ገንዘብ የተወሰኑ ክፍተት ያላቸውን አሰራሮች በማሻሻል እና የተወሰነ ቁጥጥር በማድረግ ቢያንስ 50 ፐርሰንቱን ማስጣል ቢቻል የሰራተኛውን ደሞዝ 200 ፐርሰንት ማሳደግ አይቻልም ትላለህ…?የተቀላጠፈ የስራ ቢሮክራሲ ተፈጥሮ የእያንዳንዱን ሰራተኛ የስራ ውጤታማነትን በተወሰነ ስልተና እና ማነቃቃት በአንድ እጥፍ ማሰደግ ቢቻልና አጠቃላይ የሀገሪቱን ዓመታዊ ምርታማነትን የእውነት 11 ፐርሰንት ማሳደግ ማይቻል ይመስልሀል? እንደዛ ከሆነ ድግሞ በየአመቱ ስንት ፐርሰንት ለሰራተኛ ደሞዝ መጨመር ይቻላል…?አየህ የሀገሪቱን የድህነት ችግር ለመቅረፍ እየሞከርን ያለነው በተሳሳተ የድህነት አመለካከት ነው….
‹‹እኔ እንጃ የምትያቸውን ነገሮች በቀላሉ ማድረግ ይቻላል የሚለውን መቀበል ይከብደኛል››አለኳት…
ተቃውሞዬን ችላ ብላ ቀጠለች‹‹አንዳንዴ ይገርመኛል አንድ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ስንት እና ስንት ለሀገር ደህነንነት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዩችን ሲዳኝ ውሎ፤ የሚሊዬን እና ቢሊዬን ሙስና ወንጀሎችን ሲመረምር ቆይቶ ወደቤቱ የሚወስደው አንድ ቪትስ መኪና እንኳን አጥቶ በታክሲ ሰልፍ ይዞ እየተጋፋ ወይም በባስ ታጭቆ እየተንገላታ ወደቤቱ ሲሄድ የሚፈጥርበት ስሜት ይታይህ…ይሄ ሰው የሚከፈለውስ ደሞዝ ስንት ነው…?ልጁ ቢታመምበት የግለሰብ ሆስፒታል ወስዶ ማሳካም አቅም ይኖረዋል ወይ ….?እና ሄዶ ሄዶ ሙስና ውስጥ ሳይገባ ምን የህል ጊዜ በጽናት መቆየት ይችላል …?በእሱ ላይ የሚመጣውን የድህንት ችግር መታገስ አለበት ብለን እንፍረድበት በልጁ ላይስ ሲሆን …?ክፋቱ ደግሞ ማንም ሰው ለወቅቱ የሚያስፈልገውን ለችግሩ ሚበቃውን ያህል ብቻ ዘርፎ አያቆምም..፡፡አንዴ መዝረፍ ከተጀመራ ሱስ ነው የሚሆነው…ለዛውም አደገኛ የሀሽሽ ሱስ አይነት …፡፡ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ማሟላት ያቃተው ዳኛ ዘራፋ ሲጀምር…ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ማሟላት ያቃተው መሀንዲስ መዝርፈ ሲጀምር…. ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ማሟላት ያቃተው የባንክ ማናጀር መዝረፍ ሲጀምር ..ሀገር ሁሉ በዘራፊዎች መነኸሪያ ሆና ታርፈዋለች….. በጣም የሚያስጠላው ደግሞ መዝረፍ ውስጥ የገባ ሰው በዘረፋው ብቻ አይደለም ሀገሪቱን የሚጎዳው የስራ ሞራሉም ቀን በቀን አየወረደ ስለሚመጣ ነው…ተጫሪ ገንዘብ በቀጥታ ለኪሱ የሚያስገባለት ገንዘብ የማያገኝበትን ስራ ዞር ብሎ ለማየት ፍላጎቱ ወደ ዜሮ እየተንደረደረ ይሄዳል …
አሁን እኮ ለሙሰኞችና ቀማኞች ይቅራታ እንዲባሉ ምክንያት እየሰጠሽላቸው ነው››
በፍጽም እንደዛ አይደለም ..ምንም ሳይቸግረው በስነምግባር ጉድለትና በስግብግብነት በሽታ ብቻ በመጠቃታቸው በሙስና የሚጨማለቁ ቡዙ ዜጎች እንዳሉ አውቃለው…ግን ሳይፈልጉ ችግርና እጦት አንደርድሮ እዛ አዝቅጠት ውስጥ የጨመራቸው የመንግስት ሰራተኞች ቀላል ቁጥር የላቸውም እያልኩህ ነው…እንደዚህ አይነት ሰዎች ደግሞ አንድ ንጽህ ህሊናቸው በሆነ ምክያት ከጨቆየ ይሰባራሉ… በራሳቸውም ስለሚያፍሩ ብኩን ዜጎች እንደሆኑ ይቀራሉ..እያወራውልህ ያለውት ስለእነዛ ሰዎች ነው..በነዛ ጠቃሚ ሰዎች ውድቀት መንግስት የደሞዝ ክፍያ ስርዓትና አሰስተሳሰብ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፡፡እያልኩህ ነው…
‹‹ቆይ…. እንደምታውቂው የሰው ልጅ ፍላጎት ማብቂያ የለውም፡፡የሆነ ነገር በሰጠሸው ቁጥር ሌላ ተጨማሪ ነገር ይጠይቅሻል..ታዲያ ምን ያህል ቢከፈል ነው በቂ ሚባለው?፡፡››
‹‹ለችሎታውና ለአገልግሎቱ የሚመጥነውን ቢያንስ ዝቅተኛውን ክፍያ ማግኘት አለበት….አንድ ምሳሌ ልስጥህ በመዘጋጃ ቤት የሚሰራ መሀንዲስ 5 ሺብር ደሞዝ እየተከፈለው የሀምሳ ሚሊዬን ብር ባጀት ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንፃ እንዲቆጣጠር ይመደባል…. እና መንግስን ወክሎ ባለሀብቱ በተሰጠው ቦታና በፀደቀለት ዲዛይን መሰረት ህንጻውን እየገነባ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚሰማራበት ጊዜ ያገኘውን ስህተት ለባለቤቱ ተናግሮ የማሳገጃ ትዕዛዝ ሊፅፍ ሲል ባለሀብቱ 20 ሺብር ማለት የአራት ወር ደሞዙን በአንድ ቀን ቢሰጠው አልፈልግም ለማለት የሚያስችል ስብዕና ጽናት ከመቶ ሰው
👍1
ውድ አንባብያን ያለፈው ክፍል ላይ በስተት ክፍል 21 22 የተባለው በስተት ነው ምንም የታሪክ መቆራረጥ የለም መልካም ንባብ

#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ

‹‹አሁን ተስማምቼለው››
‹‹አመስግናለው››
‹‹አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር?››
‹‹አለቃ እኮ ለመጠየቅ ፍቃድ አይጠይቅም››
‹‹አሁን እኮ የስራ ሰዓት አይደለም …ስለዚህ አለቃ ምናምን ብሎ ነገር የለም..››አልኳት
‹‹እሺ ጠይቀኝ››አለቺኝ አቀማጧን እያስተካከለች
‹‹የዛን ቀን እሷን ለማናደድ ብለሽ ያደረግሺውን እንደሆነ ባውቅም ግን በምንም አይነት ከአዕምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም….ከአዕመሮዬም ብቻ አይደለም ከህልሜም ማስወገድ አልቻልኩም….ሙሉ አዕምሮዬ በአንቺ ከንፈር ተሞልቷል…ምነው አሁንም አንድ ሰው አበሳጭቷት በሳመቺኝ እያልኩ በየቀኑ ነው የምፀልየው…
‹‹እየቀለድክ ነው አይደል?››አለቺኝ በፈገግታ እና በመኮሳተር መካከል በሚዋልል ስሜት
‹‹አይደለም…››አልኩና እንደምንም እራሴን አደፋፍሬ እጇን በመዶፎቼ መካከል አስገባውና እያሻሸው ንግግሬን ቀጠልኩ..አልተቃወመችኝም፡፡
‹‹አይደለም..እውነቴን ነው…ከህይወቴ አንድ አመት ተቀንሶ ያንን አይነት መሳም አንድ ጊዜ ደግማ ትሳምህ ብባል እስማማለው …እና እባክሽ..››
‹‹እንዲህ አይጠየቅም እኮ …አንድን ሴት እንዴት ልሳምሽ ብለህ ትጠይቃታለህ…ነውር እኮ ነው፡፡ነው ወይስ ውጭ ስለኖርክ ነውር የሚባል ነገር እረስተሀል?››
‹‹እንደዛ ማለቴ አይደለም..ፍቅረኛዬ እንድትሆኚ እየጠየቅኩሽ ነው››
በጥያቄዬ ምንም የመገረም ስሜት አልታየባትም ‹‹ከዛም በፊት ፍቅረኛ አለሽ ወይ ተብሎ ይጠየቃል…በዛ ላይ አንተም ፍቅረኛ አንዳለችህ አውቃለው..ታዲያ ፍቅረኛ ያለችውን ሰው መጥበስ የምፈልግ ይመስልሀል…?››
‹‹የእኔን እርሺው አብቅቶለታል..አንቺን ፍቅረኛ አለሽ ወይ ብዬ ያልጠየቅኩሽ ግን መልሱን ስለፈራው ነው..አለኝ ካልሺኝ ምን እንደምሆን አላውቅም…››
‹‹የእውነት ልንገርህ አለኝ ብልህም ምንም አትሆንም ..ሁሉም ወንዶች አንዱን ሴት ለማሰመን እንዲህ ነው የሚሉት..››
‹‹እወነቴን ነው …ትክክለኛ የሚሰማኝን ነው እየነገርኩሽ ያለውት..እኔ እስከዛሬ የነበሩት የፍቅር ገጠመኞቼ በአጋጣሚ የተከሰቱ ስለነበሩ እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገሮችን አላውቃቸውም…››
‹‹ይሁን ግን የእሳትእራትን የፍቅር ታሪክ ታውቃለህ
አላውቅም እስኪ ንገሪኝ…
የአሳት እራት ፍቅረኛው እየመሰለችው ነው አንፖል በበራ ቁጥር ሲሽከረከር እምታየው ….ሴቷ ለፍቅር ዝግጁ ስትሆን የራሷን ብርሀን ከሰውነቷ አመንጭታ በመርጨት ነው ምልክት የምትሰጠው.. በዛ ብርሀን ተስቦ ወደ እሷ ይሄድና ፍቅሩን ያጣጥማል…እና ይሄ የዋህ አፍቃሪ የሚያምር እና የሚንበለበል ብርሀን ባየበት ሁሉ አፍቃሪ ያገኘ እየመሰላው ተንደርድሮ ምስግ ነው…የሚንበለበል እወነተኛ እሷት ውስጥም ቢሆን ከመግባት ስሜቱን መግታት አይችልም…ከገባና ደግሞ ታውቃለህ እርር ክስም ማለቱ አይቀርም …
‹‹እና ምን ለማለት ነው..››አልኳት ምሳሌዋ ግራ አጋብቶኝ
‹‹ከእኔ ጋር የሚጠብቅህ ፍቅር መንደድ እና መክሰምንም ሊያስከትልብህ ይችላል ብዬ እያመከርኩህ ነው››
‹‹ሰምቼሻለው..እሺ በይኝ እንጄ መንደዱም መክሰሉም አያስጨንቀኝም››
‹‹ወደ እኔ ተሳበች እና ወደ ከንፈሬ ተጠጋች…ከበቀደም ለታው መሳም በላይ የጠለቀ..ከዛ በላይ የሚያደነዝነዝና ረጅም ትንፋሸ አስቋራጭ ነበር… ከተቀመጥኩበት ሶፋ ተንሸራትቼ ወለል ላይ በጉልበቴ እስከምንበረከክ ድረስ አቅል የሚያሳጣ አይነት መሳም ነበር የሳመቺኝ….ቆይ የአሳሳም ጥበብን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚያሰለጥን ተቋም አለ እንዴ…?.እንደዛ ካልሆነማ እንዲህ አይነትን አደንዛዣ አሳሳም ጥበብ ልትጎናፀፍ ትችላለች፡፡
እንደምንም ገፍታ ነበር ከንፈሯን ከከንፈሬ ያለቀቀችው….
ትንፋሽ ወስጄ እራሴን ካረጋጋው ቡኃላ‹‹እና እሺ አልሺኝ ማለት ነው..ፍቅረኛሞች ሆነናል ማለት ነው››ስል በመንሰፍሰፍ አይነት ስሜት ጠየቅኮት
‹‹በፍጽም አልሆንም….ስብሰባው ተካሄዶ የዚህን የፕሮፖዛል ውጤት ካወቅክ ቡኃላ መልሰህ ምትጠይቀኝ ከሆነ የዛን ጊዜ መልሱን ነግርሀለው››
ምን ማለቷ እንደሆነ ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም‹‹ፕሮፖዛሉ ውጤትና የእኔ እና አንቺ ጉዳይን ምን አገናኘው…?.››
ተገናኘም አልተገናኘውም ያልኩህን ከማድረግ ውጭ ምንም ምርጫ የለህም…ከፈለክ ወይም ከዛ ቡኃላም ፍቅርህ የሚኖር ከሆነ እዚሁ አጠገብህ ጋር ስለምገኝ ጠይቀኝ….አንድ ሰምንት አይደል የሚቀረው..?ሳምንት መታገስ ያቅትሀል?
ይብላኝ ላንቺ እንጂ እኔስ ጠብቃለው….ስሜቴ በሳምንት የሚጠፋ መስሎሽ ነው…?ከአመታት ቡኃላም ብትይኝም ተመሳሳይ ጥያቄ ነው የምጠይቂኝ….የፍቅር ጓደኛዬ ሁኚ ብዬ…..
‹‹እናያለን…››አለቺኝ
‹‹እናያለን ››አባባሏ አስፈራኝ..የሆነ እሳት በውስጤ እንዲጫር አደረገብኝ….
❤️ፌናን
===
እለቱ እሁድ ነው…ያው ይሄ ዓረፍተ ነገር ብቻ የሚገልፀው ሀሳብ አለ አይደል…….?እለቱ ዕሁድ ከሆነ ብዙ ነገሮች የሚረጋጉበት ቀን ነው ማለት ነው..፡፡ወከባና መተረማማስ በጣም የሚቀንስበት ቀን…የስራ ስልክ ሲያወሩ ከመዋል ተገላግለው ቤተሰብን ወይም ወዳጅ ዘመድን በመደወል እንዴት ናችሁ….? የሚባልበት ቀን …የታመመ የሚጠየቅበት ፤ያዘነን የሚያፅናኑበት ለመንፈስ የቀረበ ስራ የሚሰራበት ቀን፡፡
በቤታችን ውስጥ ነው ምንገኘው..እኔ አባቴና እናቴ ብቻ ..ወይ ሳልነጋራችሁ እናቴ ከውጭ ተመልሳ ከመጣች ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ደግሞ በዚህ ዘመን ከውጭ ተመልሶ መምጣት ብርቅ ነው እንዴ….? እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለው…
ለማኛውም የዛሬዋ ቀን ልዩ ቀን እንድትሆን ስለፈለኩ ለሁሉም የቤቱ ሰራተኞች ፍቃድ ሰጥቼያቸዋለው…ግን ከመሄዳቸው በፊት ቀኑን ሙሉ ሲያግዙኝ እና ለእለቱ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ሲሰሩልኝ ነው የዋሉት ..ልክ እንደምፈልገው፡፡አሁን ሰዓቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ነው፡፡እናቴ የገዛ መኝታ ቤቷ እንደተኛች ነው..አባቴ ደግሞ ያው እንደልማዱ ላይብረሪው ውስጥ እራሱን ዘግቶ ወይ እያነበበ ነው ወይ ደግሞ እየጻፈ ነው..ብቻ እዛ ነው ያለው፡፡
እኔ ደግሞ የምግብ ጠረጵዛው በምግብ እየሞላው ነው….ልክ እንደጨረስኩና ነገሮች በፈለኮቸው መሰረት እንደተማቻቹና ቀልብ ሳቢ እንደሆኑ ካረጋገጥኩ ቡኃላ ወደእናቴ መኝታ ቤት አመራው
===
..በዝግታ ሳንኳኳ ‹‹ግቡ››የሚል የደከመ ድምጽ ፍቃድ ሰጠኝ… በራፉን ገፋ አድርጌ ገባው…እናቴ አልጋዋን በወረቀት ሞልታ አፍንጫዋ ላይ የሰካችው መነጻር ከፍ ዝቅ አያደረገች አንገቷን አቀርቅራ ወረቀቷቹ ላይ አፍጥጣለች፡፡
‹‹እንዴ እማ የተኛሽ መስሎኝ ነበር እኮ….?››
‹‹በዚህ ሰዓት…….?አረ አልተኛውም››
‹‹ይሄ ሁሉ ወረቀት ምንድ ነው….?››
‹‹የካምፓኒውን የስድስት ወር ሪፖርት ልከውልኝ ነው..እስኑ እያየውት ነው››
‹‹ምነው ተዲያ ተኮሳተርሽ ….….?የጠፋ ነገር አለ እንዴ…….?››
‹‹አይ የለም…..አንድ ብቻ ደስ ያላለኝ ነገር አለ…››
‹‹ልትነግሪኝ ትቺያለሽ….?››
‹‹የሰውዬው ልጅ ስር-አስኪያጅ ከሆነ ምን ያህል ጊዜ ሆነው….?››
‹‹ወር ከሀያ ቀን …››
‹‹እና ምን አድርጎ ነው በዚህ አጭር ጊዜ በጣም የተለየ ትርፍ ሊገኝ የቻለው…….?››
‹‹ጎበዝ ነው ብዬ ነግሬሻለው እኮ….›››አልኳት በፈገግታ ተሞልቼ
‹‹አይ ይሄንን ስራ ጥርሴን የነቀልኩበት ነው..የፈለገ ጎበዝ ቢሆን ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊታይ የሚችል ልዩነት ማምጣት የሚችል ሰው አይኖርም… ምን አልባት ስራውን በደንብ የሚያውቅና ካምፓኒውን ቀድሞ
👍3
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ



#ፍሰሀ
===
በህይወቴ በጣም የተፈተንኩበት አንድ ሳምንት ነው እያሳለፍኩ ያለውት…በጣም አስጨናቂና ትንፋሽ የሚያሳጣ አይነት ሳምንት…. ደግነቱ ስራዎቼን ቀድሜ ማጠናቀቄ በጀኝ እንጂ በዚህ አይነት የጨፈገገ ስሜት እንዴት እሰራው እንደነበር ማሰቡ እራሱ ይከብደኛል ፡፡
ምክንያቱ አለመኖሯ ነው……ይሄው አይኖቼ አይኖቾን ካዩ አንድ ድፍን ሳምንት ተቆጠረ…የቤተሰብ ጉዳይ ስላጋጠመኝ ድሬደዋ ሄጃለው ነበር ያለቺኝ…እኔማ ደርሶ መልስም ቢሆን ልምጠና አንዴ አይቼሽ ልመለስ ብያት ነበር..ብትመጣም አታጋኘኝምና አትልፋ.. ይልቅ ዝግጅትህ ላይ አተኩር ፤ፍልሚያውን በድል ከተወጣህ ቡኃላ ደውልልኝ..እስከዛ እኔም እዚህ ያለውን ነገር ጨርስና እመለሳለው ካልሆነም ያለውበትን አድራሻ እነግርህና ትመጣለህ›› ስላለቺኝ… ምርጫ አጥቼ በናፍቆቷ እየተሰቃየሁ ባለቺው ተስማምቼ እጄን አጣጥፌ ቁጭ አላልኩም፡፡ምናልባት ድሬደዋ የሄደችበትን አድራሻዋን ባገኝ ብዬ ከሶስት ቀን በፊት በፊት ትሰራበት ወደነበረ ከዚህ በፊትም እንዲህ በጠፋችበት ጊዜ ወደአገኘዋት ሜክሲኮ መጽሀፍት ቤት ሄጄ ነበር ……መኪናዬን ቦታ አስይዤ በማቆም ወደ መጻሀፍ መደብሩ አመራው::ሁለት በአስራዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው ያሉት…አንደኛው ደንበኛ እያስተናገደ ስለነበረ ነፃ ወደሆነው ተጠጋሁ…
‹‹ምን መፃሀፍ ልስጥህ…..? ››አለኝ… እዚህ ቤት መፃሀፍ እንጂ ሴት ፍለጋ የሚመጣ ሰው ይኖራል ብሎ ስላልገመተ መሰለኝ ቀጥታ ስለመፃፍ የጠየቀኝ ፡፡
‹‹ፌናንን ፈልጌ ነበር..ሰሞኑን መጥታ ነበር?››
‹‹አይ ቆየች.. አስራ አምስት ቀን ሆኗታል››
‹‹ጓደኛዋ ነኝ …ማለቴ የመስሪያ ቤት ጎደኛዋ..ስልኳ አልሰራ ብሎኝ ነው ..ቢሮ ደግሞ እሷ ብቻ የምትሰራው አፋጣኝ ስራ ነበር..እና እቤቷን ልትጠቁመኝ ትችላለህ፡፡››
‹‹እቤታቸው ቤቴል አካባቢ እንደሆነ ነው እንጂ ትክክለኛውን ቦታ አላውቅም…ግን ትንሽ ብትጠብቅ እኮ ጋሼ ስለሚመጡ ትጠይቃቸዋለህ››
‹‹ጋሼ ማነው…..?››
‹‹አባቷ ናቸዋ››
‹‹እርግጠኛ ነህ ይመጣሉ?››
‹‹አዎ እንደሚመጡ ደውለው ነግረውኛል፡፡››
‹‹አይ እንደዛ ከሆነማ አሪፍ ነው.. እጠብቃቸዋለው ››አልኩ…ግን ደግሞ ወዲያው ሌላ ጥያቄ በውስጤ ተፈጠረ…‹‹ከአባቷ በጣም ትግባባላችሁ ማለት ነው?››ጠየቅኩት
‹‹እንዴ አሰሪዬ አይደሉ ለምን አንግባባም?››ሲለኝ እየገባኝ የመሰለኝ ጉዳይ መልሶ ድንግርግር አለብኝ
‹‹አሰሪዬ ስትል..…..?››
‹‹ይሄ የመፅሀፍ መደብር እኮ የእሷቸው ነው …ሌላም ቦታዎችም አላቸው››ሊያብራራልኝ ሞከረ…
‹‹ይሄ መጻሀፍ ቤት የፌናን አባት ነው?››
‹‹አዎ ››አለኝ ይሄን ሁሉ ሳታውቅ ነው እንዴ ጓደኛዋ ነኝ የምትለው በሚል ስሜት ..
ገረመኝ..ከዚህ በፊት እዚህ ባገኘዋት ጊዜ በትርፍ ጊዜዋ ተቀጥራ እንደምትሰራ ነበር የነገረቺኝ ፡፡ይሄ ሁሉ መዋሸት ለምን አስፈለገ?
በውስጤ የተፈጠረ የመደነቅ ጥያቄ ነበር…
‹‹አባቷ ጎበዝ ናቸው ማለት ነው?››አልኩት ልጁን….ስለእዚህች ሚስጥር ስለሆነች ልጅ ሌላ ተጨማሪ ሚስጥር እንዲነግረኝ በመፈለግ ለመጎትጎት ፈልጌ
‹‹እንዴ…!!!››አለና ዝም አለ
‹‹ምነው…..?››
‹‹ጋሼን አታውቃቸውም እንዴ?››
ነገሮች እንዳይበላሹ ዋሸውት‹‹አውቃቸዋለው››
‹‹አይ ጎበዝ ናቸው ስትል ገርሞኝ ነው››
‹‹ለምን ይገርምሀል…..?››
‹‹ጎበዝ ናቸው ማለት ነው ስትል በጉብዝናቸው ጥርጣሬ ያለብህ ይመስላል..እሷቸው እኮ ይሄንን የከፈቱት እኛንም ለመርዳት ነው እንጂ ጎበዝ ለመሆን አይደለም…አስተማሪነታቸው እና ደራሲነታቸው ብቻ ለጉብዝናቸው በቂ ነው››
‹‹እሱስ እወነትህን ነው››አልኩት ልክ አስተማሪም ሆነ ደራሲ መሆናቸውን እንደማውቅ ሆኜ…‹‹ አሀ የአስተማሪና የደራሲ ልጅ ነሻ?.ለዛ ነው ነገሮችን መበታተን እና መልሶ መሰብሰብ ሚያስደስታት….አሁን ገባኝ››ብዬ በወስጤ አብሰለሰልኩ…አሁን በዘዴ ብዙ ነገር እያወቅኩ ነው…ይበልጥ ለማወቅ ሌላ ዘዴ መጣልኝ፡፡
‹‹እስቲ የእሳቸው መፃሀፍ ይኖራል..…..?››
‹‹የቱን ልስጥህ……..?››
‹‹ሁሉንም የለኝም… አሪፍ ያልከውን …››
በፈገግታ ከዚህም ከዛም አየመዘዘ አምስት መፃሀፍ እጄ ላይ ዘረገፈ…
‹‹እንዴ…? ይሄን ሁሉ እንደፃፍ አላውቅም ነበር››መደነቄን መደበቅ አልቻልኩም
‹‹11 መፃሀፍ እኮ ነው ያላቸው..ይበዛብሀል ብዬ ነው የቅርቦቹን ብቻ መርጬ የሰጠውህ…. ልጁን እያዳመጥኩ ግን ደግሞ መፃሀፎቹን እያገላበጥኩ በማየት ላይ ሳለው አይኖቼ የመፃፍ ጀርባ ላይ የታተመ የደራሲው ፎቶ ላይ አረፈ ..ደነገጥኩ…. እባብ ሱሬው ውስጥ እንደገባበት ሰው አይነት ነው አደነጋገጤ ..ሰውዬውን አውቃቸዋለው፡፡ሌላውን መፃሀፍ ጀርባ ገለበጥኩ ፎቶ የለውም……ሌላውን ገለጥኩ አዎ እራሳቸው ናቸው…ከመቀመጫዬ ተነሳው….
‹‹ሂሳቡ ስንት ነው…..?››
‹‹የየትኛው…..? ››
‹‹የሁሉም››
መፃሀፎቹን ከእጆቼ ወሰደና ጀርባቸው ላይ ያለውን ዋጋ ደምሮ ነገረኝ..ከፍዬ መልስም ሳልጠይቅ ወጣሁ…
‹‹እንዴ አትጠብቃቸውም……..?››ልጁ ግራ ተጋብቶ ጠየቀኝ
‹‹ተመልሼ መጣለው ››ቻው..ተንደርድሬ መኪናዬ ውስጥ ገባውና አሁንም ድጋሜ የመጽሀፉን ጀርባ ላይ ያለውን ፎቶ አየሁት…ንዴትም ደስታም የተቀላቀለበት ስሜት ነው ተሰማኝ፡፡እኚን እኮ ነው ሹገር ዳዲዋ እንደሆኑ የነገረቺኝ ፡፡ለካ አባቷ ናቸው…?ሲያስደስት..ግን እንዴት ነው የምታስበኝ ?ይሄን ሁሉ ውሸት እንዴት ስትዋሸኝ ትከርማለች……? ስለእሷ የማላውቀው ሌላስ ምን አለ……?ይህቺ ልጅ እስከመቼ ነው እየራቀቀችብኝና እየጠለቀችብኝ የምትሄደው…?ለማንኛውም በእሷ በመታለሌ ከተበሳጨውት ይበልጥ ሹገር ዳዲዋ ናቸው ብዬ ለቀናት በንዴት ስንጨረጨር እና እንቅልፍ ሳጣበት የነበረው ጉዳይ ውሸት ሆኖ አባቷ በመሆናቸው የተደሰትኩት በእጥፍ ይበልጣል…
ከዛን ቡኃላም ስልኳ አይሰራም…ካላጋነንኩት ለመቶ የቀረብ መልዕክቶችን ልኬላታለሁ…ምንአልባት ከከፈተችው ወዲያው እድትደውልልኝ በማለት..ግን አንደዛ አልሆነም…ይገርማችሆል አንዳንዴ በውድቅት ለሊት ስምንትና ዘጠኝ ሰዓት ከእንቅልፌ ድንገት በርግጌ እነሳና ስልኬን አንስቼ እሞክርላታለው….ግን የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ዛሬ ግን በተቻለኝ መጠን ስለእሷ ከማሰብ እራሴን መግታትና እና ትኩረቴን ሰብሰብ አድርጌ ስለፍፃሜው ጦርነት ብቻ ማሰብ ነው የምፈልገው፡፡ቀኗ ዛሬ ነች…ማንነቴን ለአባቴም ለሌላውም ሰው የማሳይበት ቀን፡፡ይህቺን ቀን አብራኝ ለወራት የለፋችው ፊናን ከጎኔ ብትሆን ኖሮ የበለጠ ጠንካራ የበለጠ ልበሙሉ እሆን ነበር…አይ የኔ ነገር አሁንም መልሼ ወደእሷ ወሰድኮችሁ አይደል፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ


ብቻ አሁን ከንጋቱ 12 ሰዓት ነው…መኝታዬን ለቅቄ ቢጃማዬን እያወላለቅኩ ወደሻወር ቤት አመራው…የሻወሩን ውሀ ለብ እንዲል አደረግኩና ገባውበት…አዎ ንጹህና ቀለል ብሎኝ መዋል ነው የምፈልገው፡፡
ዛሬ የምለብሰውን ልብስ ከአስር ቀን በፊት ነበር የተዘጋጀው…ሙሉበሙሉ በፌናን ምርጫ በጥንቃቄ ተመርጠው የተገዙ አዳዲስ ናቸው፡፡ከሻወር ወጥቼ እራሴን ካደራረቅኩ ቡኃላ ከቁም ሳጥኔ ውስጥ እያወጣው ሙሉ ቁመናዬን በጥራት የሚያሳየ መስታወት ፊት ቆሜ በጥንቃቄ ለበስኩ፡፡ፀጉሬን አስፈላጊውን ቅባት በተገቢው መጠን በመቀባት አስተካከልኩ፡፡ካሉኝ ሽቶዎች ምርጥ የተባለውን ሽቶ ሳይበዛም ሳያንስም ከተጠቀምኩ ቡኃላ ለመጨረሻ ጊዜ መስታወቱ ፊት አየተሸከረከርኩ..እየቀረብኩ ..እየራቅኩ የጎደለ ወይም የተዛነፈ ነገር ካለ አረጋገጥኩና ስልኬንና የመኪና ቁልፌን ይዤ ከመኝታ ቤቴ ወጣው
በዚህን ጊዜ ለአንድ አስር ጉዳይ ሆኖ ነበር፡፡ፕሮግራሙ የሚጀመረው ሶስት ሰዓት ስለሆነ ገና ቡዙ ጊዜ አለኝ፡፡አባቴ እየተዘጋጀ መሆኑን ለማረጋገጥ ወደእሱ መኝታ ቤት አመራው…፡፡አዎ ተንስቷል… ምክንያቱም መኝታ ቤቱ ገርበብ እንዳለ ነው፡፡እየተቃረብኩ ስመጣ ድምጹን ሰማው …ያወራል፡፡ስልክ ላይ እንደሆነ ገባኝና ልመለስ ስል ከአንደበቱ ወጥተው ጆሮዬ የደረሱ ዓ/ነገር ጭራሽ ተጠግቼ እንዳዳምጥ ገፋፋኝ፡፡የኮቴዬን ድምጽ እንዳይሰማ ተጠንቅቄ ወደ በራፉ ቀረብኩና አጨንቁሬ ወደውስጥ እያየው ጆሮዬን ለጠፍኩ፡፡አባቴ ፊቱን ከበሩ በተቃራኒው አዙሮ የአልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ እያወራ ነው፡፡
‹‹ስሚኝ ክብረወርቅ …ዛሬም ድረስ እንደማፈቅርሽ አትዘንጊ››ይሄንን መስማቴ ነው በፈገግታ ቀሪውን የስልክ ልውውጥ እንዳዳምጥ የገፋፋኝ..‹‹አባዬ ውሽማ አለችው እንዴ..?..የሚገርም ነው….››
ከዛኛው ወገን የሚነገረው ከርቀቱ አንጻር አይሰማኝም…
‹‹ይሄውልሽ…አንቺ ለልጅሽ እንደምታዳይ ሁሉ እኔም ልጄ የፈለገውን እንዲያገኝ የማልፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም››
‹‹አይደለም..ፈፅሞ አንቺን ለመበቀል እየሰራው ያለውት ስራ የለም፡፡እርግጥ ለዓመታት እንድታገቢኝ ስማፀንሽ አሻፈረኝ ስላልሺኝ ሁሌ እንደተበሳጨውብሽ ነው፡፡አሁንም ከንዴቴ ጋር ነው ያለሁት…፡፡ቢሆንም ግን ላንቺ ያለኝ ፍቅር እዛው ድሮ ያለበት ቦታ እንደሆነ ልደብቅሽ የሚያስችል ጥንካሬ አይኖረኝም…
‹‹አዎ ባል እንዳለሽ አንድ ሺ ጊዜ ነግረሺኛል..አውቃለውም…፡፡ግን አንቺ ለእኔ የተፈጠርሽ ሴት ነበርሽ፡፡ባልሽ እኮ ምኑም ካንቺ ጋር አይሄድም፡፡አንቺን የምታህል ሚኒዬነር ነጋዴ አንድ ተራ የሀይ-እስኩል አስተማሪ አግብታ እድሜ ልኳን ከእሱ ጋር……….››
‹‹ይቅርታ ..ሁል ጊዜ ስለእሱ ሳወራ እንደምትበሳጪ አውቃለው፡፡ግን እይውእስቲ…እኔ እና አንቺ በጋራ ይሄን የመሰለ ካምፓኒ መመስረት ችለናል፡፡ለአመታት በጣም ውጤታማ ነን፡፡ይሄንን የቢዝነስ ስኬታችንን ለልጆቻችን አስተላልፈን እኔና አንቺ ወደ ፍቅር ውህደት ማለቴ ወደ ትዳር ብንገባና ቀሪ ዘመናችንን የተረጋጋ እና የሰከነ ኑሮ ብንኖር ደስ ይለኛል፡፡ምንኖረው ሀገር ውስጥም ላይሆን ይችላል ፡፡አንቺ ተስማሚ እንጂ የፈለግሽው የሀገር ጫፍ ብትይ ይመቸኛል፡፡ሰው ማይኖርበት አንታርቲካም ቢሆን ..››
‹‹የምሰማው ንግግር ከአባቴ አንደበት እየወጣ መሆኑን ማመን ተሳነኝ ‹‹…ወይ ጉድ!! ለካ ሼባው አደገኛ የፍቅር አክተር ነበረና…እኔ እንኳን እሱ በሚያወራው መጠን የማወራትና የምጀነጅናት ሴት ኖራኝ አታውቅም….. ደግሞ ተፈቃሪዋ እኮ የካምፓኒው አንዷ ባለድርሻ ነች …ለካ ይህ ጉዳይ ለእሱ ወሳኝ እንደሆነ ለመቶ ምናምነኛ ጊዜ ደጋግሞ ሲነግረኝና ሲያስጠነቅቀኝ የነበረው ሌላ ምክንያት ስላለው ነበር… አዎ አሁን ገባኝ … በመካከላቸው ያለው ጦርነት ቢዝነሳዊ ብቻ ሳይሆን ፃታዊም ነበር ማለት ነው…፡፡
‹‹ቀጥሏል አባቴ››
‹‹…በቃ እንግዲህ ….የልጅሽና የልጄ ፊልሚያ ላይ እንገናኝ፡፡እና የመጨረሻው ደስታ የእኔ ስለሚሆን ፅዋችንን በእኔ ወጪ ነው የምናነሳው…››
‹‹አታስቢ.. የልጄን ዕወቀትና ብቃት ስለማታውቂ ነው…እኔን ስለምታውቂኝ እሱንም ያወቅሽ እንዳይመስልሽ፡፡እኔን ቁጭ አድርጎ ሊያስተምረኝ ሚችል ጀግና ነው››
ከአባቴ አንደበት በዚህ አይነት ሁኔታ የራስን ልጅ ግነታዊ በሆነ ደረጃ ከፍ ከፍ እያደረገ ሲናገር መስማቱን አልወደድኩትም …ከዚህ የባሰ ነገር ተናግሮ ለወራት የገነባውትን ማንነቴን እና በራስ መተማመን እንዲሸረሽርብኝ ስለማልፈልግ ቀስ እያልኩ ወደኃላ አፈገፈግኩና ወደሳሎን ወረድኩ….
ሰራተኛዋ በምግብ ጠረጵዛው ላይ ቁርስ ደርድራ እንደጨረሰች አባቴም መጣ…
‹‹ፐፐፐፐ…ጠቅላይ ሚኒስቴር መስለሀል.››ብሎ ወደኔ ቀረበና ግንባሬን ሳመኝ..ደስ አለኝ…
ሌላውም ሰው እንደእሱ ከተሰማው አሪፍ ነው ስል አሰብኩ…በፌናን ምክር መሰረት አንዱ ነገር ተሳክቷል ማለት ነው…በዝግጅቱ ቀን የገምጋሚዎቹን ቀልብ ሰብስቦ የሚይዝ ፤በራስ መተማመንኔን በራሱ የሚያስረዳ አይነት አለባበስ መልበስ የመጀመሪያ መመሪያዋ ነበር…ሌላው ፕሮፖዛሉ ሙሉ ሰነድ እንደመሆኑ መጠን ከዛ ዋና ዋናውን ሀሳብ በአንድ ሰዓት ውስጥ ለሶስቱ ወሳኝ ሰዎች ለማቅረብ መከተል የሚገባኝን አካሄድ …
*
To make sticky idea you should be focuse on the following criteria
1/simplicity
2/un expected
3/Cridibel
4/concerete
5/Emotional
6/Story ……ትለኛለች
**
ሶስት ቀን ሙሉ ነው ስለእያንዳንዱ ነጥብ ምሳሌ በመስጠት ያስጠናቺኝ…፡፡እናም ጥናቱን ፍሬ ነገር ጨምቄ ቀላልና ግልጽ በሆነ አገላለጽ በገምጋሚዎች ላይ ያልጠበቁትን መደመም በመፍጠር ሚዛን ሚደፍ ሀሳቦችንና በሚያስምን አቀራረብ ሙሉ የጥናቱን ታሪክ በሚያስረዳ መልኩ የተጨመቀውን ሀሳብ በተሰጠኝ አንድ ሰዓት ውስጥ ማቅረብ እንድችል የተቻላትን ያህል አዘጋጅታኛለች… እኔም ብዙ ጊዜ እያፈረስኩ እየገነባው ሳምንቱን ሙሉ ተለማምጄዋለው፡፡እና አሁን ከአንድ ሰዓት ቡኃላ ይሄን የወራት ልፋቴን ውጤት የእኔም ብቻ ሳይሆን በዚህ መጠን እንድዘጋጅና ተፎካካሪዬን በብቃት እንድረታ በሚስችለኝ መጠን እንድዘጋጅ ለረዳችኝ ፊናን ልፋትም ፍሬው የሚለቀምበት ሰዓት ደርሷል፡፡ዝግጅቱን የማቀርብበት ሰዓት ….
በነገራችን ላይ ፕሮግራሙን ሳልነግራችሁ፡፡ከሶስት እስከአራት ሰዓት ባለው ጊዜ እኔ ሙሉ ሰነዱን አስረክቤ የተዘጋጀውበትን ሀሳብ በተሠጠኝ አንድ ሰዓት ውስጥ አቀርባለው…፡፡ከዛ ከአራት ሰዓት እስከ ተኩል ድረስ የምጠየቀውን ጥያቄ የምመልስበት ሰዓት ይሆናል፡፡. ከዛ የሻይ እርፍት ይኖርና፡፡ ከ5 እስከ ስድስት ሰዓት ደግሞ የሴትዬዋ ልጅ ትገባና በተመሳሳይ እንደ እኔ ያዘጋጀችውን ሰንድ አስረክባ በአንድ ሰዓት ውስጥ አቅርባ ስድስት ሰዓት ትጨርሳለች፡፡ከስድስት እስከ ስድስት ተኩል ልክ እንደእኔ በተመሳሳይ የጠየቋትን ጥያቄ የምትመልስበት ወቅት ይሆናል…፡፡
ከዛ አምስታችንም ወደምሳ ፕሮግራም እንሄዳለን፡፡ከ 6:30 እስከ 8 ሰዓት የምሳ ሰዓታችን ነው፡፡ከ8 እስከ 10 ሰዓት ሶስቱ የካምፓኒው ባለቤቶች ለብቻቸው ሰብሰባ ያደርጋሉ፡፡ በሰነዱና በቀረበላቸው ሀሳብ ላይ ይወያያሉ፡፡ለተኩል ሰዓት ሻይ ይወጣና ተፎካካሪዎቹም ባሉበት የመጨረሻ ድምጽ ይሰጣል፡፡የተሰጠው ድምጽ በግልጽ ሁሉም እያየ ይከፈታል አሸናፊው ይለይና ሙሉ ፕሮግራሙ ይጠናቀቃል፡፡
አሁን ከጥዋቱ 2፡40 ሆኗል እኔና አባቴ ቢሮ ደርሰናል፡፡ጋሼ ከበደ ከእኛ አምስት ደቂቃ ዘግይተው
👍4
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ



#ፍሰሀ
===
ልዩ የሆነ ቆይታ ነበር፡፡ሶስቱንም ፈታኞቼን እንዳስደመምኮቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡መድረኩን በስነስርዓት፤ ባጠናውት እና በተዘጋጀውት መጠን ነበር የተወጣሁት፡፡በመጨረሻ ሁሉም ወ/ሮ ክብረወርቅም ጭምር ቆመው ነበር ያጨበጨብልኝ፡፡እኔም በደስታ ሰክሬ ከወገቤ ሽብርክ ብዬ አመሰገንኳቸው፡፡
ለመውጣት ቸኩያለው ቀልቤ ያለው ፌናን ጋር ነው፡፡እስከአሁን ከቤቷ መጥታ ውጭ በረንዳ ላይ ወይም ቢሮዬ ቁጭ ብላ እደምትጠብቀኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡አዎ አይኖቼ መላ እሷነቷን ተርበዋል፡፡ከራሴ በላይ እወደዋለው፡፡ ብዬ የማስበው አባቴ እንኳን ከስድስት ወር ባላይ ተለይቶኝ ሲኖር በዚህ መጠን ናፍቆኝና ተርቤው አላውቅም…
ናፍቆቴ የቱንም ያህል ቢሆን ግን እነሱን ቀድሜ መውጣት በአይን አውጣነት የሚያስፈርጀኝ መስሎ ስለተሰማኝ እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጥሬ እየታገስኩ ነው፡፡እነሱ በእርጋታ የሚንቀሳቀሱትን ሽማጊሌውን አስቀድመው እየተጎተቱ ክፍሉን እስኪለቁልኝ መጠበቅ ግድ ሆነብኝ፡፡ይባስ ብሎ አባቴ ወደእኔ መጣ፡፡ተጠመጠመብኝ ፡፡ምን ላድርግ …?መልሼ በተመሳሳይ አቀፍኩት፡፡ለዚህች ቀን አይደል ስንት ወር ሙሉ ሲወተውተኝ የነበረው?እሱ ያልተደሰተ ማን ይደሰታል……?ግን እሱ ያላወቀው እንዲህ መታቀፍ ያለብኝ እኔ ሳልሆን ፌናን መሆኗን ነው፡፡ግድ የለም ..እሱ እኔን ባቀፈኝ መጠን እኔ ደግሞ ከደቂቃ ቡኃላ እሷን አቅፋታለው፡፡.ጭምቅ አድርጌ አቅፋትና ምስጋናዬን አቀርብላታለው፡፡ምስጋናዬን ብቻ ሳይሆን ዛሬ ማታ አፕል አበረክትላታለው፡፡አዎ ጥንት ግሪካዊያን ለሚያፈቅሩት ሰው አፕል ነበር የሚልኩት አንተም የምታፈቅረኝ ከሆነ ከዝግጅቱ ቡኃላ አፕል ላክልኝ የዛን ጊዜ መልሱን ነግርሀለው አይደለ ያለቺኝ?ዋው..ማታ እራት ጋብዛታለው::ከዛ አፕል እሰጣታለው::አፕሉ ውስጥ ደግሞ ቀለበት ይኖርታል::አብረቅራቂ የአልማዝ ቀለበት::ይህንን በማሰቤ ውስጤ ዘላለማዊ በሚመስል ደስታ ተጥለቀለቀ
‹‹በጣም ነው ያኳራኸኝ…እጅግ በጣም ከጠበቅኩት በላይ ጀግና ሆነህልኛል ለካ?አሁን እርግጠኛ ሆነህ ካማፓኒውን በቋሚነት ለመረከብ ተዘጋጅ..››አለኝ አባቴ ሌሎቹ ሊሰሙት በማይችሉት ዝቅተኛ ድምጽ
‹‹እሺ አባዬ አመሰግናለው፡፡››
‹‹ና እንውጣ›› አለኝና ትከሻዬን በኩራት አቅፎ ወደውጭ ይዞኝ ወጣ::በራፍ ላይ እንደደረስን በሃያ ሜትር ርቀት ፌናን ቀድመውን ከወጡት ጋሽ ከበደ እና ከወ/ሮ ክብረወርቅ ጋር ሲያወሩ ለዛውም እየተሳሳቁ ተመለከትኩ
እኔም አባቴም ሳንነጋገር እርምጃችንን እዛው በራፍ ላይ ገታነው::እንዴት አምሮባታል ?ይህ ሁሉ ውበት እንዲህ ጎልቶ እና ፈክቶ የወጣው ከእራሷ ከአፈጣጠር ነው ወይስ ከአለባበሷ…?ልቤ እንደለመደችው ቅልጥልጥ አለች…ግን ከሰዎቹ ጋር የት ተዋውቃ ነው እንዲህ በመፈንጠዝያና በፈገግታ የምታወራቸው……?
‹‹አንተ ተፋላሚህ መታልሀለች::ደግሞ እንዴት ታምራለች……?ልክ እንደእናቷ ››አባቴ ነው በአድናቆትና በስጋት መሀከል በሚዋልል ስሜት የተናገረው…
‹‹አባ እሷ አይደለችም::ይህቺ እኮ የእኔ ረዳት ነች››አረምኩት
‹‹እርግጠኛ ነህ…?ፎቶዋና እኮ እናትዬው ያሳየቺኝ መሰለኝ..ለማንኛውም ና ወደ እነሱ እንሂድ..››አለኝና ተያዘን ስራቸው ደረስን …ፌናን ዞር ብላ እንዳየችኝ ተሸከርክራ ተጠመጠመችብኝ….በጣም እንደናፈቀቺኝ ያወቅኩት ሁሉም እያዩኝ ያለይሉኝታ ልክ እንደ ህጋዊ እጮኛዬ አቅፌ በአየር ላይ ሳንጠለጥላት ነው….
አባቴ ‹‹ክብረወርቅ ልጅሽ ነች እንዴ…?››ብሎ ሲጠይቅ በጆሮዬ ገባ..
‹‹አዎ ልጄ ነች::ፌናን ሰላም በይው…››የሰማውትን መልስ ማመን አቃተኝ….. ምንድነው እየተካሄደ ያለው..?.ከእሷ ሸሸት እልኩና እናትዬው ላይ አፈጠጠኩባት
<<…ምን ተፈጠረ …?በሚል ግራ በተጋባ አሰተያየት ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንዲህ ምትግባቡ አይመስለኝም ነበር››ለእኔ ነው የምትለኝ ፡፡
‹‹ፌናን ያንቺ ልጅ ነች…?››አንቱነታውንን እረስቼ የአባቴን ጥያቄ መልሼ ደገምኩ
‹‹አዎ ..ፌናን ልጄ ነች..ምነው …?አልነገረችህም እንዴ……?››
ወደ እሷ ተንደረደርኩና ሁለት ትከሻዋን ጨምድጄ ያዝኳት …ሶስትም ደነገጡ‹‹በጣም ባለጌ ነሽ..በጣም አታለሺኛል..መቼም ይቅር አልልሽም….››
ይሄን ሁሉ ስላት እሷ ምንም እንዳልተፈጠረ በግማሽ ፈገግታ እያደማጠቺኝ ነው…ገፍትሬ አባቴ ትከሻ ላይ ወረወርኳትና ወደቢሮዬ ተንደረደርኩ…
‹‹ምንድነው ነገሩ?ልጄን ምን አደረጋችሁት…?››የአባቴ ድምጽ እየተሰማኝ ነው…ቤሮዬን ገባውና ከውስጥ ቀረቀርኩ.. ቢያንኳኩም ልከፍትላቸው አልፈለኩም..ትንሽ ይብረድለት ብለው መሰለኝ ትተውኝ ዞር አሉ….እኔም ምፈልገው ያንን ነበር፡፡
…….ታንቄበት የዋልኩትን ከረባት ከአንገቴ ፈትቼ ጥዬ ኮቴን አውልቄ በመወርወር ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ አንገቴን ጠረጳዛ ላይ ደፍቼ አነባው ጀመር::እንዲህ አይነት ለቅሶ ካለቀስኩ ስንት ዓመት እንዳለፈኝ ትዝ አይለኝም::ንፍጤ እስኪዝረከረክ ድረስ ነው ያለቀስኩት፡፡በህይወቴ አንድ ሰው በዚህ መጠን ተጫውቶብኝና አታሎኝ አያውቅም::እንዴ አምኜያት ነበርኮ..?በአድናቆት ፈዝዤያለት አፍቅሬያትና ብዙ ብዙ ህልም አልሜላት ነበር…?እንዴት አንዲህ ትሰብረኛለች?ይህችን ካምፓኒ ለማስተዳደር ብላ……?እኔ እኮ ከካምፓኒው ስራ በላይ ነበር ያፈቀርኳት…
…እያንዳንዷን የሰራዋትን ጥናት ቃል በቃል ታውቀዋለች፤ ምክንያቱም አብረን ነው የሰራነው.፡፡ስለዚህ የእሷ ዝግጅት የእኔን ጥናት አይታና ከእዛ በበለጠና ያንን በሚያጠቃ መልኩ ለማዘጋጀት እድሉን አግኝታለች… .በዛ ላይ ችሎታዋን አውቃዋለው..እና እንዴት ነው ከእሷ በልጬ ይሄን ቦታ የማገኘው…?ተዋረድኩ….፡፡በቃ ሁሉ ነገር አስጠላኝ ::ስራው አስጠላኝ ..ካምፓኒውም አስጠላኝ ..ያፈቀርኮት ልጅ አስጠላቺኝ…ሀገሬም አስጠላቺኝ …፡፡መመለስ አለብኝ…አዎ ወደመጣውበት ሀገር እመለሰላው..ስደት ይሻለኛል..ስራዬን እየሰራው ሶስትኛ ዲግሪዬን ብማር ይሻለኛል..::እንደውም በተጨማለቀ ሀገር የተጨማለቀ ኑሮ ለመኖር ምንድነው እንደዚህ አፈር የሚያስግጠኝ..…?ወሰንኩ…እንባዬን ከጉንጬ ላይ ጠራረግኩ…ኮምፒተሬን ከፈትኩና መጻፍ ጀመርኩ…ለቦርድ አባላቱ ነው::የካምፓኒውን ስራ ስለማልፈልገው ውድድሩ እንዲቀርና ስራውንም በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን የሚገልጽ ደብዳቤ …ፕሪንት አድርጌ ፈረምኩበትና ኮቴን መልሼ በመልበስ ወጣው…ሰራተኞቹ ሁሉ ለምሳ የወጡ ቢሆንም ጸሀፊዬ ግን ስጠብቀኝ ነበር….
‹‹አሁን የቦርድ አባሎቹ ሲመጡ ይሄንን ማመልከቻ አስገቢልኝ›› አልኩና በካኪ ፓስታ የታሸገውን ማመልከቻ ሰጠዋት
‹‹አባትህ ደጋግመው ሲደውሉ ነበር…ምሳ እየጠበቅንህ ነው ፤ደውልኝ ብለውሀል…››
‹‹ዝም በይው::ስልኬን ዘግቼዋለው …ከደወለ ወጥቼ እንደሄድኩና እንደማልመለሰም ንገሪው……››
‹‹አንተ ግን ሰላም ነህ…?›ሁኔታዬ ስላላማራት መሰለኝ የጠየቀቺኝ
‹‹ሰላም ነኝ ….አመሰግናለው…››ጥያት ወጣው…..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን