#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍስሀ
===
ስልኬን አነሳውና ደወልኩ አስተዳደሩ ቢሮ
‹‹…ሄሎ የሴት ድምጽ ነው››
‹‹ማነች ፀሀፊዋን ቢሮ ባስቸኮይ ነይ በያት››
‹‹ፀሀፊዋ ነኝ››
‹‹እንግዲያው ቶሎ ነይ…ከአለቃሽ ጋር..አሁኑኑ ››ጆሮዋ ላይ ጠረቀምኩባት…ልክ አስገባቸዋለው..ሁለቱንም ለድፍረታቸው ተገቢውን ትምህርት ሰጪ ቅጣት ያገኟታል…
እኛ ኢትዬጵያውያን ለወሬ ያለን ፍቅር ለራሳችን ካለን ፍቅር በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡እንደህዝብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተምረዋል በሚባሉት የህብረተሰብ ደረጃ ጨምር የ<critical thinking >ልምምድ የለንም… የሰማነውን ወሬ ‹‹ለምን?›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹የት?›› ‹‹ መቼ?›› ብለን በመጠየቅ የነገሩን ብልት በታትነን ለማየት የምናደርገው ጥረት ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡የሰማነውን ወሬ ወይም መረጃ በዚህ መጠን መመርመር ደግሞ የመረጃዎችን ጥራት ለመጨመር..እርግጠኝነቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና እወነተኝነቱን በአስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገዶች ናቸው፡፡ ሰምተን ሳንጨርስ ለሌላው መናገር እንጀምራለን፡፡
መጡ‹‹ዝጉትና ቁጭ በሉ…››
ፊት ለፊት ተቀመጡ
‹‹ምን እየተሰራ ነው አቶ ሰይፉ››
‹‹ምን አጠፋን ጌታዬ…››በሚርበተበት አንደበት
‹‹እንደዚህች አይነት ሰራተኛ ይልኩብኛል…ነው ወይስ ይህንን እንድታደርግ እርሶ ነዎት የላኳት››
በቆሪጥ የእሷን መርበትበት ለማየት አይኖቼን ወደእሷ ስልክ ጭራሽ የምለውንም እየሰማች አይመስልም…ዘና ብላ የእጆቾን ጣቶች እየዘረጋችና እያጠፈች ከራሷ ጋር ትጫወታለች፡፡
<አረ እኔ…ለመሆኑ ምን አጠፋች?››
<በቃ ቡኃላ አናግሮታለው ከእሷ ጋር ልጨርስ> አመሰግናለው››
‹‹እሺ አቶ ፍሰሀ››ሹክክ ብለው ወጥተው ሄዱ…
ምን ልበላት እንድትደነግጥ እንዴት ልጩህባት እያልኩ በውስጤ ቃላት ስምርጥ
‹‹አንድ ነገር ልምከርህ›› አለቺኝ….
ይህቺ ልጅማ ጤነኛ አይደለችም…‹‹ምን አልሺኝ››
በምንም አይነት ሁኔታ ተራ ሰራተኞች ፊት የማናጅመንት አባላቶችህን እንዲህ ዝቅ አድርገህ አትናገር..ስህተት ቢሰሩም ጥፋት ቢኖርባቸውም ብቻቸውን ጠርተህ ነው ማነጋገር ያለብህ..ምክንያቱም አንተ ስታበሻቕጣቸው ያየ የበታች ሰራተኛ በትክክል ሊታዘዛቸው አይችልም. ያ ደግሞ ዞሮ ዞሮ የካማፓኒውን እፊሸንሲ ያወርደዋል…ያ ማለት ደግሞ ዞሮ ዞሮ በሰተመጨረሻ ያንተኑ አፈፃፀም ነው የሚጎዳው››
‹‹ጨረሽ››
‹‹አዎ ጨርሼያለው…ለምንድነበር የፈለከኝ?››
‹‹ማን ስለሆንሽ ነው ያለዘዝኩሽንን የሰራሽው?››
‹‹ምነው..? ላግዝህ ብዬ ነው››
‹‹ማን ስለሆንሽ ነው ምታግዤኝ?››
<አንድ ሰውን ለማገዝ እኮ ማንም መሆንን አይጠይቅም …ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው..››
ባክሽ አትቀባጥሪ ..ያ ሽማጊሌ ነው አይደል እንዲህ እንድታደርጊ የነገረሽ?..››…..በጥቂት ቀን ውስጥ ማን መሆኔን አሳየዋለው..አንቺ ግን ለእንጀራሽ ስትይ አደብ ግዤ>>
<<አንተም ለካንፓኒው ህልውና ሆነ ለራስህ የስራ ስኬት ስትል ምክሬን ስማ…..ደግሞ ለሽማግሌው ክብር ይኑርህ..ቅድም በስልክ ስታበሻቅጣቸው ላብ ሲያሰምጣቸው ነበረ…ለእሳቸው ሳይሆን ለራስህ ስትል አክብራቸው ..ደህና ሁን..››ብላኝ መቀመጫዋን ለቃ ወጥታ በራፍን በላዬ ላይ ዘግታ ሄደች…
አሁን አልተናደድኩም ..በጣም ደነገጥኩ…..ምንድነች ይህቺ ልጅ ..?ማንን ተማምና ነው እንዲህ መስመር የለቀቀችው…?እራሴን አመመኝ …ከዚህ በላይ ማሰብ ስላልቻልኩ ቢሮዬን ለቅቄ ወጣው ..ልጠጣና ልረሳት..እና ነገ አባርራታለው››
===
በጥዋት እንደገባው…አስጠራዋት….
‹‹እሺ ይህቺን ደብዳቤ ፃፊልኝ››
ቃል ሳትተነፍስ ተቀበለቺኝና ላፓቶፑ ፊትለፊት ተቀመጠችና መፀፋ ጀመረች…እየተከታተልኳት ነው….ስትባሳጭ ስትደነግጥ ለማየት ነበር በትኩረት እየተከታተልኮት የነበረው…ምንም አይነት የስሜት ለውጥ አልታየባትም …ደብዳቤው ስለ እሷ እንደሆነ አልገባትም ማለት ነው…ስሞን እያነበበች እንዴት አይገባትም…..?
‹‹ለወ/ሪት ፌናን ገመዳ
ጉዳዩ ፡ከስራ መሰናበትን ይመለከታል፡፡
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ካምፓኒውን ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ አንድአንድ ለውጦች ማድረግ የግድ አስፈላጊ ስለሆነና ለለውጡ የሚመጥኑ ሰራተኞችና ማሰማራት የግድ በመሆኑ ይህ ደብዳቤ ከደረሶት ቀን አንስቶ ከስራ የተሰበናበቱ መሆንን አሳውቃለው፡፡
‹ከሰላምታ ጋር›
ፍሰሀ
ዋና ስራ አስኪያጅ
**
ይንን ነበር እንድትጽፍ የሰጠዋት..ለትዕቢተኛ እና ለስረአት አልበኛ ምህረት እንደሌለኝ እሷንም ሆነ ቀሪ ሰራተኞችን ማስተማር እፈልጋለው..እርግጥ የሰራችው ስራ ስህተት መሆኑን ተረድታ ይቅርታ ከጠየቀቺኝ ..በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ልምራት እችላለው..አሁን ሳያት ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ማሰቧን የሚጠቁም ምንም አይነት ምልክት አላየውም፡፡
‹‹ጨርሼያለው ፕሪንት ላድርገው››አለችኝ ጭራሽ የደሞዝ ማሻሻያ ደብዳቤ እንደደረሰው ሰራተኛ ፈገግ ብላ
‹‹አዎ አድርጊውና ልፈርም››
አዘዘችና ወደሚቀጥለው ክፍል ሄደች..ፕሪንተሩ ያለው የሚቀጥለው ክፍል ነው፡፡
ይዛ መጣችና አቀበለቺኝ… ልትወጣ ስትል‹‹ቆይ ልፈርምና መዝገብ ቤት ትወስጂዋለሽ››አልኳት ቆማ ትጠብቀኝ ጀመር..
በዚህ አይነት ስሜት ውስጥም እያለው የተመዘዘ ቁመቷን አለማድነቅ አልቻልኩም…..
ከመፈረሜ በፊት ማንበብ ጀመርኩ…‹‹እንዴ ምንድነው የጻፍሺው…?››እስኪ የሰጠውሽን ረቂቅ ስጪኝ…ወረቀቱን ልታነሳ ጎንበስ ስታል ጡቷቾ ተጋልጠው እይታዬ ውስጥ ገቡ..እርግጠኛ ነኝ ጡት ማስያዥ አላደረገችም….ብታደርግማ ይሄን ሁሉ የጡቶን ክፍል በግልፅ ማየት አልችልም ነበር……ከጠረጳዛው ላይ አነሳችና ሰጠቺኝ….
ከስራ መሰናበትን ይመለከታል ነው የሚለው..አንቺ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ መስጠትን ይመለከታ ብለሽ ነው የጻፍሺው…
ዝም ብለህ በፀባይ ብትጠይቀኝ ኖሮ ከነገ ጀምሮ ቀርልህ ነበር….ግን ነገም በሌላ ሰራተኛ ላይ ተመሳሳዩን ላርግ ስለምትል ህጉን እያስተማርኩህ ነው…‹‹ዝም ብለህ በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ሰራተኛ ማባረር አትችልም….አንደኛ ይሄን ስራ ያንተ ሳይሆን የአስተዳደሩ ስለሆነ ለእሳቸው ብትተውላቸው….በስልጣንህ ተመክተህ አይ እኔ መስራት አለብኝ የምትል ከሆነ ደግሞ አንደኛ የሀገሪቱን የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ሁለተኛ ሰራተኞች ከካንፓኒው ጋር የገቡትን የቅጥር ውል አንብበህ በውሉ ላይ በሰፈረው ህግ እና ደንብ መሰረት ነው እርምጃ መውሰድ የምትችለው…እንደ አንድ ማናጀር ሰውን ሳይሆን ኮንትራትን ነው ማስተዳደር ያለብህ …
በቃ ውጪልኝ..ደብዳቤውን ቀዳድጄ ቅርጫት ውስጥ ከተትኩና ቤሮውን ለቅቄ ወጣው ..በዚህ ስሜት ሌላ ምንም አይነት ስራ መስራት አልችልም….
ምን እየሆንኩ ነው…..አንድ ተራ ፀሀፊ መስመር ማስገባት ያልቻልኩ ሌሎቹን ምክትል ስራአስኪያጁን ጨምሮ የየክፍል ሀላፊዎች እንዴት አድርጌ ልመራ ነው…?አካሄዴንማ ማስተካከል አለብኝ...
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን መልካም ምሽት🙏

👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍስሀ
ምን ነካኝ..? የዓመታት ፍቅረኛዬን
ከወንድ ጋር ስትዳራ እጅ ከፍንጅ የያዝኳት አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ…የሆነ ውስጥ አንጀትን የሚያላውስ አይነት የመረበሽ ስሜት…የሆነ ልብን ድክም የሚያደርግ አይነት የፍርሀት ስሜት…የሆነ ያሳደጋችኃት ለማዳ ወፍ ከእጃችሁ አምልጣ ሰማዩ ተንሳፋ አድማሱን ሰንጥቃ ስትበርባችሁ በዛው ትቀር ይሆን.? ብላችሁ ስትሰጉ የሚሰማችሁ አይነት የእጦት ስሜት …
ሱፐር ማርኬት ልገዛ የመጣውትን ዕቃ ስለጠፋኝ እንደፈዘዝኩ ዝም ብዬ ባዶዬን ነው ወደመኪናዬ የተመለስኩ…... መኪናዬ ውስጥ ገባውና ሞተሩን አስነስቼ የመኪናዋን አፍንጫ ወደ አዲስአባ መለስኩት……
‹‹እንዴ ምን እየሆንክ ነው.?››
‹‹ይቅርታ ለስራ ጉዳይ ስለተደወለልኝ መመለስ አለብን››
‹‹እርግጠኛ ነህ.?››አለቺኝ….
‹‹ማነች እንደዛ ያለችህ.?›› እንዳትሉኝ…ፍቅረኛዬ ነች…ሳሮን ተስፋሁን ትባላለች፡፡አብረን ከሆን አንድ አመት አስቆጥረናል…የዛሬ አመት ለቫኬሽን ከውጭ የመጣው ጊዜ ነበር የተዋወቅነው…አንድ ወር እዚህ ስቆይ አብራኝ ነበረች..ከዛ ለትምህርቴ ወደውጭ ከተመለስኩ ቡኃላም በስልኩም በስካይፒውም ፍቅራችንን እንዲቀጥል ማድረግ ችለናል….አሁን ጨርሼ ከመጣው ቡኃላም እንደዛው…ዛሬ ወደ ደብረዘይት ለአዳር እየሄድን ነበር…. ዘና ብለን ለነገ ስራ በማለዳ ለመመለስ አቅደን ….ግን ይሄው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ አደፍራሽ ስሜት ወደ አዲስአባ እየተመለስኩ ነው…..
‹‹እርግጠኛ ነህ ስትይ ….ምን ለማለት ነው.?››ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኸል ይባላል ..ተቆጣሇት
‹‹የተደወለልህን ስልክ ታሰየኛለህ….?››
‹‹ማለት.? ››
‹‹ስከታተልህ ነበር …ምንም አይነት ስልክ ስታናግር አላየውም..ልጅቷ ማነች...?››
‹‹የቷ ልጅ.?››የምትለው ያልገባኘኝ መስዬ ጠየቅኳት
‹‹እንደዛ ያፈዘዘችህ ነቻ…ለዘመናት የጠፋችብህን ፍቅረኛህን በአጋጣሚ ያገኘህ ነው እኮ የምትመስለው….››
‹‹አትቀባጥሪ….››
‹‹አልተሳሳትኩም ማለት ነው….እንደው ወንዶች ሰትባሉ..››
‹‹በናትሽ አሁን ዝም ልትይልኝ ትቺያለሽ ..ምንም ነገር የመናገር ሙድ ላይ አይደለውም…››
‹‹እንግዲያውም አውርደኝ….››
‹‹የትነው ማወርድሽ.?››ገርሞኝ
‹‹እዚሁ አውርደኝ… ብቻዬን በትራንስፖርት ሄጄ አድሬ መጣለሁ…በስንት ዘዴ እና ውትወታ ቤተሰቤን አሳምኜ ያገኘውትን ከቤት ውጭ የማደር ዕድል ላባክነው አልፈልግም….››
‹‹እወነትሽን ባልሆነ.?››
‹‹እወነቴን ነው ..አውርደኝ አልኩህ እኮ…››አንቧረቀችብኝ
‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው ››ይላል የሀገሬ ሰው….ዳር ይዤ ፍሬኑን ጠርቅሜ ያዝኩና አቆምኩላት… ኮስሞቲኮቾን እና ቅያሬ ልብሶቾን ያጨቀችበትን ቦርሳዋን አንጠልጥላ ወረደች…ኪሴ ገባውና ለመዝናናት ይዥው የነበረ ከእሽጉ ያልተፈታ አምስት ሺ ብር እግሯ ስር ወረወርኩላትና መኪናዬን አስፈንጥሬ ተፈተለኩ……
ከዛ አዳሬን አትጠይቁኝ…ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ቢሮ ነበርኩ..ስደርስ ፅዳቶች እንኳን ስራቸውን አላጠናቀቁም ነበር… አግኝቼ እስካናግራት ቸኩያለው አይገልፀውም…ደግሞ ሳይቸግረኝ ቅዳሜ ለት ከስራ መሰናበቷን የሚገልፅ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፈርሜ ነበር….እርግጥ ከሰዓት ሰራተኞች ከወጡ ቡኃላ ስለፈረምኩ ዛሬ ነው የሚደርሳት…ግን እንዴት አድርጌ ማስተካከል እችላለው.. .?መዝገብ ቤት የሚሰሩት አስተዳዳሪውም ጭምር ደብዳቤውን አይተውታል… በውሳኔው የሚዋልል አሐቃ ደግሞ ማንም አያከብረውም….እንደዛ እንዲያስቡኝ ፈፅሞ አልፈልግም….፡፡ ግን ደግሞ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ…፡፡ብትከሰኝ ጥሩ ነው.. ግን እንዴት ጥሩ ሊሆን ይችላል...?አውቄ ልሸነፍላት ማለት ነው.? ….እሱም ሌላ ጣጣ አለው..‹ በክስ አሸንፍው ተመለሰች› መባሉ ሌላ ውድቀት ነው….አዳሜ ትንሽ በነካዋት ቁጥር ወደክስ እንድትበር መንገድ ማሳየት ነው….፡፡ይልቅ ይቅርታ እዲደረግላት ደብዳቤ ብታስገባ ጥሩ ነው…፡፡አዎ እንደዛ እድታደርግ በዘዴ አግባባታለው…ግን ሳስበው እሷ እንደዛ አታርግም …በፍጽም አንገቷን እንዲህ በቀላሉ የምትደፋ አይነት ልጅ አይደለችም ….
የባጥ የቆጡን ሳስብ 3 ሰዓት ሆነ ..ፀሀፊዬን ጠራዋትና ፌናንን እንድትጠራልኝ ነገርኳት…. ደወለችና….እንዳልገባች ነገረችኝ››
‹‹ምን ማለት ነው … 3 ሰዓት ድረስ አለመግባት….?››ፀሀፊዬ ላይ ነው የጮህኩት
‹‹እኔ እንጃ...?በሞባይሏ ልደውልላት››አለቺኝ እየተሸቆጠቆጠች…፡፡
‹‹አይ ተያት ..እሷን በተመለከተ የተፃፈ ደብዳቤ ከመዝገብ ቤት ታስመጪልኛለሽ.?››
‹‹ቆይ እኔ እራሴ ላምጣ ››ብላ ሄደች
ከሶስት ደቂቃ ቡኃላ ተመልሳ መጣችና ደብዳቤውን እየሰጠቺኝ ‹‹…ያመጣውት ቀሪው ነው ..ዋናውን ፈርማ ወስዳዋለች››አለቺኝ
‹‹ማን ነች የወሰደችው.?››..ሳላስበው ከመቀመጫዬ ተነሳው
‹‹ፌናን ነቻ››
‹‹ምን ጊዜ ወሰደች….? ቅዳሜ ከሰዓት ነበር እኮ የፈረምኩት …ለማንኛው አመሰግናለው..››ብዬ ፀሀፊዋን ሸኘዋትና አስተዳዳሪው ጋር ደወልኩ
‹ደህና አደርክ አቶ ፍሰሀ››
‹‹ሰላም ነኝ..ፌናንን ፈልጌያት ነበር››ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ገባው….
‹‹አልገባችም ››
‹‹አልገባኝም ማለት.?››
‹‹ምትገባ አይመስለኝም …..ያው የተሰናበተችበትን ደብዳቤ ወስዳለች..››
‹‹ትውሰዳ..ዝም ብላ ደብዳቤ ተቀብላ መቅረት ትችላለች እንዴ...?ፎርማሊቲ ምናምን ሚባል ነገር የለም….?››
‹‹አይ ፍቃድ ሞልታለች..እንደዛ እንዲሆን መሰለኝ የተነጋገርነው››
‹‹ከምኔው እንዲህ ተዋክባ ሞላችው.?››
‹‹እኔም አልገባኝ አቶ ፍሰሀ …ደብዳቤውን ጥዋት ስገባ ጠረጳዛዬ ላይ ነው ያገኘውት››አሉኝ እየታዘብኝ መሆኑን በሚያሳብቅባቸው ቃና….
ስልኩን በንዴት ጆሮቸው ላይ ጠረቀምኩት ..እስቲ እሳቸው ምን አደረጉኝ…..
…..መልሼ የጠረጳዛውን መጥሪያ ተጫንኩ…ፀሀፊዬ መጣች…‹‹አቤት ፈለከኝ››
===
‹‹ደውይላት… ሞባይሏ ላይ ደውይላት …››ተመልሳ ሄደችና ሞባይሏን ይዛ መጥታ እያየዋት መሞከር ጀመረች… ትግስቴን በሚፈታተን ሁኔታ ደግማ ደጋግማ ሞከረች…‹‹ጥሪ አይቀበልም ነው ሚለው..ሁለቱም ሲሞ አይሰራም››
‹‹የቤት ወይም የጓደኛ ስልክ የላትም.?››
‹‹እኔ አላውቅም ..ወይ የሚያውቅ ሰው ካለ ልጠይቅልህ….?››ግራ ግብትብት ያላት ፀሀፊዬ መፍትሔ ያለችወን ሀሳብ አመጣች…››
‹‹አይ ተይው..አመሰግናለው…››ሸኘዋት
‹‹ምን እሆንኩ ነው ….?እዚህ ቢሮ ስራ ከጀማርኩ ሁለት ሳምንቴ ነው…፡፡በሁለት ሳምንት ብቻ የማውቃት ሴት እንዴት እንዲህ ውስጤን የማተረማመስ አቅም ኖራት….?ነው ወይስ ከእኔ ዕውቅና ውጭ ለዘማናት በውስጤ በስውር የኖረችበት የተፈጥሮ ምትሀታዊ ሚስጥር ይኖር ይሆን...?አይ እንደዛም አይሆንም አሁን እሷን መፈለግ ነው ወይስ በድያታለው ብዬ ስላሰብኩ መፀፀት የወለደው የጥፋተኝነት ስሜት ነው እንዲህ የሚያደርገኝ….?.በቃ አንዴ ላግኛትና አዋርቻት ይቅርታ ከጠየቅኳት ቡኃላ ይሄ ስሜት ይተወኛል…፡፡አዎ እርግጠኛ ነኝ ይተወኛል…››እራሴን ለማፅናናት ብዙ ጣርኩ…መልሼ የጠረጳዛዬን መጥሬያ አንጫረርኩ..የፈረደባት ፀሀፊዬ በፍጥነት መጣች
‹‹ፋይሎን ታመጪልኝ.?››››
‹‹የማንን.?››
‹‹ሌላ የማን ይሆናል .. .?የፌናንን ነዋ››
…‹‹እሺ›› ብላ ሹክክ ብላ ወጥታ ሄደች
‹‹ሰውዬው አረ ተረጋጋ….አሁን ይህቺ ምስኪን ምን አደረገችህ ….?›› እራሴን ለመገሰጽ ሞከርኩ…ይዛልኝ መጣችና አስረክባኝ ወደ ቦታዋ ተመለሰች …
‹‹ፋይሏን ገልጬ ማየት ጀመርኩ…ዝም ብሎ ስሜቴ ስለገፋፋኝ ወይንም ግራ

😁2👍1👏1
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍስሀ
መፅሃፍ መደብሩ ቆሜያለሁ ነገረ ስራዋን በአትኩሮት እየተከታተልኩ ነው፡፡
ገዢው የሆነ መፃፍ ርዕስ ነገሯት
‹‹እንደዚህ የሚባል መጽሀፍ አለሽ.?››ጠየቃት
‹‹አለኝ ግን ለምን ፈለግከው?››
‹‹አልገባኝም?ልገዛሽ ነዋ.?››
‹‹እሱማ ልትገዛኝ ነው ?ለምን መጽሀፉን ልትገዛው ፈለክ ነው ጥያቄዬ?››
‹‹ለምንስ ብፈልገው አንቺ ምን ይመለከትሻል ?ካለሽ ሽጪልኝ ከሌለሽ የለኝም በይ››
‹‹ስኳር ወይ ሳሙና አይደለም የምትገዛው፤ መጽሀፍ ነው..፡፡መጽሀፍቶች ደግሞ ሳያነቡ የሚያነቡ ለመምሰል ታቅፈዋቸው የሚዞሩ ከንቱዎች እጅ እንዲገቡ አልፈልግም በተለይ እንደጠየቅከው ያለ መጽሀፍ……..፡፡ይሄውልህ እዛ አካባቢ በመደዳ መጽሀፍት ቤቶች አሉ ካላቸው ምክንያት ሳይጠይቁ ይሸጡልኸል….ደህና ሁን››ብላ አሰናበተችው፡፡
ሰውዬው በመገረም እያጉረመረመ ጥሏት ሄደ ..ዞር ስትል እኔን አየቺኝ
‹‹እንዴ አለቃ ምን እግር ጣለህ...?መፅሀፍ ልገዛሽ ነው እንዳትለኝ…?››አለች በመጠኑ ፈገግ ብላ
‹‹ለመሆኑ የትኛው የዋህ ነጋዴ ነው ለመክሰር አንቺን እዚህ ያቆመሽ….?››የእወነቴን ነበር የተናገርኩት
‹‹የሚተማመንብኝ››
‹‹እንዲ ደንበኛ እያበሳጨሽ እያባረርሽበት ነው የሚተማመንብሽ…››
ልትመልስልኝ አፎን ስታስተካክል አንድ ሽበት የወረራቸው ደስ የሚል ግርማ ሞገስ ያላቸው ግን ደግሞ ጎስቆል ያሉ አዛውንት ድምጽ በመሀከላችን ገባ ?››
‹‹ደህና ነሽ የእኔ አለም….?››
‹‹ደህና አደሩ..እንዴት ኖት? ጤናዎትስ?››እኔን ከማውቃት ተቃራኒ በሆነ እርብትብት ትህትና እየተፍለቀለቀች እና እየፈገገች በጋለ ሰላምታ ተቀበለቻቸው፡፡ሰው እንዴት እንዲህ ሁለት ገፃ ይኖረዋል?
‹‹….ሰላም ነኝ ልጄ…፡፡ይመስገነው፡፡››
‹‹አኔ እኮ ሲጠፉብኝ ያመሞት መስሎኝ ሰግቼ ነበር››
‹‹አይ ደህና ነኝ.ባለፈው ያስቀመጥሺልኝን መጽሀፍ ልጆቹ ሰጥተውኝ ወስጄ ነበር..እና መጻሀፎ ስለመሰጠቺኝ ከቤት መውጣት አልቻልኩም ለዛ ነው የጠፋሁብሽ››
‹‹ጨረሱት?››
‹‹ጨረሱት..ሁለት ጊዜ ነው ደግሜ ያነበብኩት…አሁንም አንዴ የምደግመው ይመስለኛል..››
‹‹ስለወደዱት ደስ ብሎኛል..አሁንም ያዘጋጀውሏት መጽሀፍ አለች›› ብላ ከተቆለሉት መጽሀፎቶች ጀርባ እጆን ሰደደችና አንድ ልባሱ አርጀት ያለ መጽሀፍት አውጥታ ሰጣቻቸው ፡፡በመንሰፍሰፍ ተቀበሏት እና ርዕሱን አገላብጠው ካነበብ ቡሃላ እሷን ወደ ራሳቸው ጎትተው ግንባሯን ከሳሟት ቡኃላ ‹‹ ስንትነው የእኔ ልጅ .?››ጠየቋት
‹‹ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ነው የገዛውሎት››
ቀኝ የካፖርት ኪሳቸው ገቡ…የሆነ ባለአስር ብር ዝርዝር ብሮች አወጡ..የካፖርታቸውን ኪስ ከፈቱና ደረት ኪሳቸው ገቡ ሳንቲም ሳይቀር ያለቸውን ብር ከየኪሳቸው እያወጡ ባንኮኒው ላይ ዘረገፍት.በትኩረተ ስከታተላቸው ነበር…ቢቆጠር ከመቶ ምናንም ብር አይበልጥም ቢያንስ የጠየቀቻቸውን ግማሹን አይሸፍንም
‹‹ልጄ በዚህ ላይ አንቺ ሙይልኝ…››አሏት…የልመና ሳይሆን የትዕዛዝ ቃና ባለው የመተማመን ስሜት
‹‹.አይ ይሄ ልጅ የእርሶ አድናቂ ነው… ገና ሲመጡ አይቶት የሚወስዱትን መፃሀፍን እኔ ነኝ የምከፈለው.. አደራሽን እንዳተቀበያቸው ሲለኝ ነበር..አይደል ፍሰሀ?››አለቺኝ ወደእኔ ቀና ብላ አፍጥጣ እያየቺኝ
‹‹አዎ…እባኮት እልኩና ወደኪሴ ገብቼ ዋሌቴን በማውጣት በግምት አንድ ሺ ምናምን ብር ይመስለኛል አወጣውና ይሄው ብሩ የሚችለውን አይነት የሚፈልጉትን መጽሀፍ ስጭልኝ….››
<<አላልኮትም ››አለችና የእሳቸውን ብር ከባንኮኒው ሰብስባ ኪሳቸው መልሳ ጨመረችላቸውና…
‹‹ሌላ ምን ምን መፃሀፍ ነው የሚፈልጉት….?››
‹‹ያው የመጽሀፍ ምርጫዎቼን ታውቂ የለ.››
…ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ መጻሀፎችን መረጠችና በፔስታል አድርጋ ሰጠቻቸው
ሰውዬው ከመሄዳቸው በፊት ወደእኔ ጠጋ አሉ..ብዙ ምርቃት እንደሚያዘንቡብኝ እየጠበቅኩ ነው…‹‹እነዚህን መፃሀፎች አንብቦ ለመጨረስ ሁለት ወር ያህል ይፈጅብኛል…ለቀጣዬቹ ሁለት ወራት እንድኖር የሚያስችል ምክንያት ሰጠተኸኛል ማለት ነው..ምክንያቱም እኔ በምንም አይነት ሁኔታ እጄ ላይ ያሉ መጽሀፎቸን አንብቤ ሳልጨርስ አልሞትምና.››አሉኝ ..ምን ለማለት እንደፈለጉ አልገባኝም..ይህቺ ልጅ ግራ አጋቢ የሆነችው ከእንደዚህ አይነት ግራ አጋቢ ብኩኖች ጋር እየኖረች ነው ስል በውስጤ አሰብኩ.. ሽማግሌው ወደፌናን ዞረው ‹‹የእኔ ትንሽ መላአክ ደህና ሰንብቺልኝ..››ብለው ፊታቸውን አዙረው የመጽሀፍ መደብሩን ለቀው ወጡ
‹‹ምትገርሚ እብድ ነሽ.ለማላውቃቸው ሰው መጽሀፍ ታስገዥኛለሽ…ደግሞ ባዋርድሽስ.?››
‹‹ምን ብለህ ነው የምታዋርደኝ.?››
<<መች አልኩሽ .?››ብልሽስ
‹‹አትልማ ..ለራስህ ያለህን ግምት በደንብ አውቃለው..››
<<እንዴት ነው ምታውቂው ….?በጣም ጉረኛ ነሽ…?ዘመድሽ መስለውኝ ነው..ደግሞ ደስ የሚሉ አዛውንት ናቸው.የሚያነብ ሰው እወዳለው ለዛ ነው…›› አልኩ ቀጥሎ በመሀከላችን ለሚፈጠረው ነገር ጥሩ ስሜት እንዲፈጠር ና ንግግራችን እንዳይከር እየፈራው
‹‹ ማን መሆናቸውን ታውቃለህ?››
‹‹እኔ እንጃ .በምን አውቃለው ፡፡ካለዛሬም አይቻቸው አላውቅም..እዚህ ቦታም ስገኝ የመጀመሪያ ቀኔ ነው››
እንግዲህ እንደዛ እንድታደርግ እድሉን ስላመቻቸውልህ አመስግነኝ…ምክንያቱም ለእሷቸው መፅሀፍ መግዛት ብዙ ሰዎች ቢፈልጉም እድሉን አያገኙምና›› ብላ ማንነታቸውን ነገረቺኝ… ነዘረኝ ከሰማዩ የሚከብድ ስም ያላቸው..ለኢትዬጵያ ብዙ የሰሩ ፤ ብዙ መጽሀፍ የጻፉ ታላቅ ደራሲ ናቸው..አፍሬ አፌን ያዝኩ.ማንነታቸውን ቀድሜ ባውቅ ኖሮ መፅሀፍ ልግዛሎት ብዬ ገንዘብ ከኪሴ ለማውጣት ድፍረት ሚኖረኝ አይመስለኝም
‹‹ስማቸው እና ኪሳቸው ምነው እንዲህ ተራራቀ.››ብዬ የገረመኝን ጥያቄ ጠየቅኳት
‹‹ስማቸውን እኮ በአዕምሮቸው እንጂ በኪሳቸው አይደለም ያገኙት…እሳቸው ለቁሳዊ ሀብት ብዙም ግድ የላቸውም ..ከሚጠቀሙት በላይ ገንዘብ ኪሳቸው እዲከርም አይፈልጉም..ግን አንዳንዴ እንደዛሬ ቀን የሚፈልጉት መፃሀፍ የሚገዙበት ብር ሲጎድላቸው ይበሳጫሉ..››ብላ ልታስረዳኝ ሞከረች፡፡
‹‹ሚገርም ፅናት ነው››አልኩኝ
‹‹ አዎ ነው..አንተ ግን ምን ፈልገህ እዚህ ድረስ መጣህ .?ነው እግረመንገድህን ስታልፍ ድንገት አይተኸኝ ነው?››አለችኝ ኮስተር ብላ..ሞባይሌን ከፈትኩና ሰዓቱን አየው..አምስት ሰዓት ከሩብ ይላል
‹‹ምሳ ልጋብዝሽ ነው አመጣጤ…ምሳ ስንት ሰዓት ነው መውጣት የሚፈቀድልሽ….?››
‹‹ምሳ ምሳ...?››
‹‹አዎ ምሳ..››
ስልኳን አወጣችና ደወለች…‹‹ቶሎ ና ልወጣ ነው…››ብላ መልሳ ዘጋችው…
‹‹የሚቀበለኝ ልጅ እስኪመጣ መኪና ውስጥ ጠብቀኝ ከአስር ደቂቃ ቡኃላ መጣለው››እንዲህ በቀላሉ እሺ ትለኛች ብዬ እልጠበቅኩም ነበር…ሀሳቧን እንዳትቀይር ‹‹እሺ አመሰግናለው›› ብዬ እንደህጻን በውስጤ እየቧረቅኩ በፍጥነት ወደ መኪናዬ ተመለስኩና መሪውን ከሹፌሬ ተቀብዬ እሱ በታክሲ ወደቢሮ እንዲመለስ ልኬው እሷን መጠበቅ ጀመርኩ…ስለእሷ እያሰብኩ…ስንት ሰው እንደሆነች እያሰላው...ከሳምንት በፊት እኛ ካምፓኒ ነበር የምትሰራው…ከዛ ሹፌር ሆና ስትሰራ አገኛዋት አሁን ደግሞ የመፃሀፍት መደብር ሻጭ..ህይወቷን እንዴት እዴት ነው ጢቢ ጢቢ እየተጫወተችበት ያለው.?መስመር የሚያሲዛት ቤተሰብ የላትም ማለት ነው….?እስቲ ትምጣና ለዚህ ሁሉ ጥያቄዎቼ መልስ ትሰጠኛለች….
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍2