#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....መንፈሷ ላይድን ቆስሎ፧ ሃሣቧ እዚህም እዚያም እየባከነ፤በተኛችበት ሆና በእንባ እየታጠበች ሁለት ቀን በጓደኛዋ ቤት ካሳለፈች በኋላ፤ ተነሣች፡፡
አካሏ ጠንካራ ቢመስልም፤ መንፈሷ ግን ደካማና የተረበሽ ነበር።በዚህች በሁለት ቀን ውስጥ ከዚህ ዓለም የተገለለች ዓይነት ሰሜት ይስማታል፡፡
የእናቷ፡ የወንድሟና፤ የሻምበል ብሩክ ሁኔታ ከፊቷ ድቅን ይልባታል፡፡
እናቷን ለሁለት ቀን ሳታያት በመቅረቷ ሁለት ዓመት የተለያቻት ያህል በናፍቆት ተቃጥላለች፡፡
“እንዴት ሆና ይሆን?” እያለች ሌሊቱን ስትጨነቅ ነው ያደረችው፡፡እናቷን በህልሟ አይታታለች፡፡ በዚያው ጐን ለጐን የሻምበል ብሩክ ጉዳይ አለ፡፡ ዛሬ እሁድ ስለሆነ ሻምበል ብሩክ እየጠበቃት ነው፡፡ ስለዚህ እሱን ማግኘት አለባት፡፡ ካላየችው ጤነኛ የምትሆን አልመሰላትም፡፡ልቧ ከውስጥ ደም ቢያለቅስም፤ ጥርሶቿ ግን እውነተኛ ስሜቷን በመደበቃቸው፤አዜብ ተጽናናች፡፡
“በቃ እንሂድ”አለቻት ለአዜብ ልብሷን ለባብሳ እንደጨረሰች፡፡
እሺ ትሁት፡፡ መጣሁ ጠብቂኝ” አለችና ሄዳ የታክሲ ገንዘብ ይዛ መጣች፡፡ ከቤት ሲወጡ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ ዕለቱ እሁድ ነው :: ተያይዘው በታክሲ ወደ የካቲት አስራ ሁለት ሆስፒታል በረሩ...
በዚህ ቀን ሻምበል ብሩክ ከአሁን አሁን ትመጣለች በማለት በጉጉት እየተጠባበቃት ነበር፡፡ ትዕግስት መራራ ነች ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ነው የሚለውን ብሂል በሃሣቡ እያውጠነጠነ ፣ትዕግስት አልባ በመሆን ስህተት እንዳይፈጽም ከራሱ ጋር እየተሟገተ ይገኛል፡፡
ከዚህ በፊት ከትዕግስት ውጭ በመሆን ከሱ የማይጠበቅ ድርጊት በመፈጸሙ ተፀፅቶ፤ ለራሱ የገባውን ቃል ዘነጋና፤ ባለፈው ስልክ የደወለችለት ዕለት፤ በድጋሚ ስህተት ፈጸመ፡፡በዚያን ሰዓት ትህትና በሁኔታው ተደናግጣ...
ምን ሆነሃል ብሩኬ?“ ነበር ያለችው፡፡ በአነጋገሩ የድሮው ሻምበል ብሩክ መሆኑ ፍጹም አጠራጥሯት፡፡
ሻምበል ብሩክ እንደበረዶ ቀዝቅዞ ነበር ያነጋገራት :: ይህንን ስህተት መፈጸሙን ያወቀው ግን ስልኩን ከዘጋ በኋላ ነው፡፡
ስልኩን አንስቶ ሲያነጋግራትና፤ሲሰናበታት በነበረው ሁኔታ ተደናግጣ ተደናግጣ “ምን ሆነብኝ?“ በማለት ተጨንቃ፤ ምን እንዳጋጠመው ለማወቅ ፤ እሁድ
አልደርስልሽ አላት፡፡ ሻምበል ብሩክም ስልኩን ከዘጋ በኋላ ምን ያደርግ እንደነበር ሲረዳ ተደናገጠና፤ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፋው፡፡
“ ምን ዐይነት እራሴን መቆጣጠር የማልችል ደደብ ነኝ?” ሲል በራሱ አማረረ
"እሺ አሁን ምን ይሻላል?“ በሚል ጭንቀት ተውጦ ለፈፀመው ስህተት ምክንያት ሲፈልግ አንድ ሃሣብ መጣለት፡፡
ሻምበል ስሜቱ በሁለት ተቃራኒዎች መካከል መዋዠቅ ጀምሯል፡፡ወደር የሌለው ፍቅር በአንድ በኩል፤ የጥላቻ ስሜት በሌላ በኩልእንደከበሮ ወጥረው ይሞግቱታል፡፡
በቃላት ሊገልጸው በማይችለው ሁኔታ ያፈቅራታል፡፡ የዚያን ዕለቱ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር እጅ ለእጅ ተቆላልፋ ወደ ቤቱ ይዟት ሲገባ የነበረው ሁኔታዋ
ከፊቱ ላይ ድቅን ሲልበት ደግሞ፤ ከአንጀቱ ይጠላታል፡፡
ለማንኛውም ይህ ፍቅሩ ጥላቻውን የሚያጠፋበት፣አሊያም ጥላቻው
ፍቅሩን ከውስጡ ጠራርጉ የሚያስወግድበት፤ እውነተኛው ሰዓት
እስከሚደርስ ድረስ በትዕግስት ለመቆየትና የዚያ የውሽት ልጃገረድነት
ጭምብል ወልቆ እውነተኛው ማንነቷ የሚረጋገጥበትን ጊዜ በጉጉት
መጠባበቁን መረጠ፡፡
በሱ እምነትና ግምት ያ ቀን እሁድ እለት እንዲሆን ወስኗል፡፡ሻምበል እሁድ ዕለት ደርሶለት ይሄ ጥርጣሬና ጥላቻው አንድም የሚወገድበት፤አሊያም ከትህትና ጋር የሚቆራረጥበት ዕለት በመሆኑ የአሁኑ እሁድ ከምንግዜውም የበለጠ ናፈቀው፡፡
ትህትና ደግሞ በበኩሏ ሻምበል ብሩክ እንደዚያ ቅዝቅዝ ብሎና ተለውጦ በስልክ ሲያነጋግራት ተረብሻ፣የመገናኛቸው ዕለት ደርሶላት ሄዳ ምን እንደሆነ እስከምትጠይቀው ድረስ ቸኩላ፤ እሁድን እየተጠባበቀች ነበር፡፡
ሁለት ልቦች በየግል ምክንያቶቻቸውን አምቀው፤ ሰዓቱን በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም፤ ሰዎች በፈለጉት መንገድ ሳይሆን፤ ጊዜ በራሱ ህግና ስርዓት የሚመራ ነውና፤ እሁድ የራሱን አዲስ ክስተት ይዞ ብቅ አለ፡፡
ሰው በጊዜ ቢያቅድም ጊዜ የሰው ተጐታች አይደለምና የታቀደ ሁሉ
አይሳካም :: በተገላቢጦሽ ደግሞ ሰው የጊዜ ተጉታች ነውና፤ አንዳንድ የሰዎች ዕቅድ ጊዜው ካልፈቀደ በዕቅድነቱ ይቀርና ጊዜ የራሱን አዲስ ክስተት ይዞ ይመጣል፡፡
ትህትና ድንበሩ በአበራና በአለሌው እንደሻው አማካይነት በተቀነባበረ ሴራ፤ በአካሏ ላይ ጉዳት ስለደረሰባትና ፤በቀሪ ህይወቷ ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥል ወንጀል ስለተለፈፀመባት፤ በናፍቆት የተጠባበቀችው እሁድ ቢመጣም ያ ቀን ከደረሰባት ዱላና አስገዳጅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጉዳት ያገገመችበት ቀን ሆኖ ዋለ፡፡
እንደዚያ የምታፈቅረው ጓደኛዋ ናፍቋት፤ እናቷን ለሁለት ቀናት ያህል ስትለያት የምታደርገው ጠፍቷት፤ በእንባ እየታጠበች በዚያች በሁለት ቀን ውስጥ ወዟ ምጥጥ ብሎ፤ አካሏ ጠውልጉና ውበቷ ተገፍፎ ስትታይ፤ ትህትና ነች ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነበር፡፡ውበት የስሜት
ነጸብራቅ የመሆኑ እውነታ ከፊቷ ይነበብ ነበር፡፡
ለዚያውም አዜብ ከአጠገቧ ሳትለይ በማንኛውም ረገድ ባታፅናናትና
ባትንከባከባት ኖሮ፤ ጉዳቷ ከዚህም የከፋ ይሆን ነበር፡፡ከዚህ ሁሉ በኋላ በሁለተኛው ቀን ላይ ሰውነቷን ተጣጥባ፤ በቅባት ፊቷን አባብሳ፤ የአዜብን ምርጥ ቀሚስ ለብሳ ፤ ሰው መስላ ተነሣች፡፡
ሞራሏ እንዳይነካና ያለፈውን እንድትረሣ አዜብ ያላደረገችላት ጥረት አልነበረም፡፡ ትህትናም ጓደኛዋን ለማስደሰት ያህል ብቻ ልቧ ከውስጥ ደም እያለቀስ፤ ከላይ ከላይ ፈገግታ እያሳየቻት ተነሳች፡፡
በተለይም በዚያን ዕለት ጨረቃዋ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ፤ ከሻምበል ብሩክ ጋር ባሳለፈችው አስደሳች ምሽት የተናገረችው ትዝ ይላትና እረፍት ይነሳታል፡፡ ያንን የሚያሰቃይ ስሜቷን ውጣ በፍጹም ጤነኛና ደሰተኛ መስላ ልብሷን ለባብሳ እንደጨረሰች...
"እንሂድ አዜቢና” አለቻት፡፡
እናቷ ይህችን ሁለት ቀን ልጇ ሳትመጣ በመቅረቷ እዚያ ሆስፒታል ውስጥ በእንባ እየታጠበች አንዱአለምን ካልወለድካት እያለች ስታስጨንቀው፤ በሁለተኛው ቀን ላይ የት እንዳለች ቁርጡን ነገራት፡፡
አንዱዓለም እህቱ የት እንዳለች የሰማው ከአዜብ ነው፡፡
• ትሁት ሻምበል ጋ ነች፡፡ ሁለት ቀን እዚያ ስለምትቆይ አንተ ከእናትህ እንዳትለይ አደራህን” ብላ በሚስጥር ስለነገረችው፤ አንዱአለም ዜናውን በደስታ ተቀብሎ ለደቂቃ ከእናቱ እንደማይለይ በገባላት ቃል መሠረት ከዚያ አካባቢ ውልፍት ሳይል ነው የቆየው፡፡
ትህትና በዚህች በሁለት ቀን ውስጥ ሁለት ዓመት እንደተለያቻች ሁሉ ናፍቃት፤ ሆስፒታል ስትደርስ እየሮጠች ሄዳ እናቷ ላይ ድፍት ብላ አለቀሰች፡፡ አዜብ የጓደኛዋን ሁኔታ ስትመለከት አንጀቷ ተላወሰ፡፡አልቻለችም፡፡ አብራት አለቀሰች፡፡
እናቷም ልጇ ላይ ጥምጥም ብላ በስስት እያገላበጠች ሣመቻትና..
በጤናሽ ነው ትሁቴ? አለሽልኝ የኔ እናት? ” ዐይን ዐይኖቿን በጉጉት እያየች፡፡
“ደህና ነኝ እማይዬ አንቺስ እንዴት ነሽ?” እናቷን እያሻሸች በዐይኗ አንዱአለምን ስትፈልግ እሱም የሆነ ነገር ሊነግራት ፈልጐ ምልክት ሲሰጣት አየችና ልትስመው ሄደች.....
“ሻምበል ጋ እንደነበርሽ ነግሬአታለሁ” አላት ድምፁን ዝቅ አድርጉ፡፡
ትንሽ ሣቅ ብላ......
“እሺ" አለችው::
ከዚያም በኋላ ከእናቷ አጠገብ የተኙትን በሽተኛ አዛውንት ጤንነታቸውን ጠይቀው፣ እናቷን ከበው ተቀመጡ፡፡ እናቷ የልጇን
ዐይን፤ዐይን፤በስስት ስትመለከት ሆዷ ቡጭ ቡጭ

👍1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....ታክሲው ውስጥ የሚጮኸው ሙዚቃ ጭንቅላቱን በጠበጠው፡፡ማታ እንቅልፍ አልወስድህ ብሎት ሲጨነቅ ነበር ያደረው::
“ምንድነው የሆንከው? ለምን አትነግረኝም?” አለች ዘውዲቱ
ከሆቴል ገዝታ ካመጣችው ምግብ እያጎረሰችው፡፡ “ምስኪን አሁንስ ሚስትህ
ናፈቀችሁ መሰለኝ::
ያጎረሰችውን እያላመጠ ዝም አላት:: ወሬ አላሰኘውም:: ምግቡም እንዳያስከፋት ብሎ ነው እንጅ ቢቀርበት በወደደ፡፡
እራት በልተው ተጣጥበው መብራቱን አጥፍተው አልጋ ላይ ከወጡ በኋላ ናትናኤል በጀርባው እንደተንጋለለ አያኖቹን ጣሪያው ላይ ተክሎ ቀረ፡፡
ምን ሆና ይሆን? እንዴት ሁለት ቀን ሙሉ ስራ ሳትገባ ትቀራለች በጤናዋ ባትሆን ነው እንጅ:: ደግሞ ምህረት እቤቷ: ደወዬ
የሚያነሳ አጣሁ ማለቷ ምን ማለቷ ነው? ቤቷን ዘግታ የት ትሄዳለች? ምናልባት አሟት ወላጆቿጋ ሄዳ ይሆን እንዴ? የወላጆቿን ቤት ደግሞ አያውቀውም ! ጉለሌ እንደሆኑ ነግራዋለች፡፡ ግን በደፈናው ጉለሌ ተብሎ አይኬድ፡፡ ቤቷ ሄዶ ይሞክር ይሆን?
ሌሊቱን ሲጨነቅ አደረ፡፡ አሁን ደግሞ ታክሲው ውስጥ ያለው ሙዚቃ አይሉት ጩኽት
“ሲጋራ ፋብሪካ ነው ያሉኝ?” አለው ባለታክሲው፡፡
“እ? አዎ የኔ ልጅ፡፡ ከዚህ ይበቃኛል፡፡” ናትናኤል የታክሲውን በር ከፍቶ ወረደ፡፡
“አባ ገንዘበስ?!” ባለታክሲው የመኪናውን ጥሩንባ ተጭኖ ጮኹ፡፡
“ይቅርታ! ይቅርታ!” አለ ናትናኤል ከሄደበት ተመልሶ ከጋቢው ስር
ከደረት ኪሱ ገንብ እያወጣ “ይቅርታ የኔ ልጅ፡፡ ሃሳብ ገብቶኝ ተዘንግቶኝ
ነው::” ገንዘቡን ለባለታክሲው አቀበለው
ዘውዲቱ የገዛችላት ላስቲክ ቦት ጫማ መንገደኛ ቢያስመስለውም እላይ ከፈፉ እግሩን ከርክሮት ክፉኛ አቁስሎታል። በተራመደ ቁጥር የጫማው ክፈፍ ቁስሉን ሲነካበትና ሲፈትግበት ይለበልበዋል፡፡
ከመንገዱ ባሻገር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ህንፃ ብቻውን ተገትሯል ... ሥራ ፈት፡፡ ናትናኤል ይህንን ፎቅ ሲመለከት ምንም ትርጉም አይሰጠውም በፎቁ ቅርፅ ውስጥ መልዕክት ካለ አንድ የሚል መሆን አለበት ቀጥ ያለ ፎቅ እንድ፡፡
ናትናኤል አይኖቹን ከፎቁ ላይ ነቅሎ ሃሳቡን አሰባሰሰ፡፡ ለጥያቄው መፍትሄ የሚያገኝለት ካልቨርትን ቢያገኝ ብቻ እንደሆነ ከተረዳ ቆይቷል፡፡
ካልቨርትን : እግኝቶ የአውሬውን ማንነት ይፋ እስካላወጣ ድረስ የተደበቀውንና የተሸሸገውን ምሥጢር እስካላዝረከረከው ድረስ አንድ ቀን ከአንዱ ጥግ ነው የሚደፉት፡፡አብርሃምን እንደደፉት፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት ካልቨርትን ማግኘት አለበት፡፡ ግን ካልቨርትን ለማግኘት ከየት ሀ ብሎ እንደሚጀምር እንቆቅልሽ ሆነበት::
መረጃ የውስኪ ጠርሙስ ሾፌር ቤላ
መጠጥ ቤት…ሴት ሞሳድ ኤም አይ
ስድስት…ካዛንቺስ ወዳጁ ቤት… የሴት ልብስ ለብሶ ተሰወረ::
ቁልፉ የግድ እዚህ ውስጥ መሆን አለበት መፍትሄው እዚህ ውስጥ ከሌለ ካልቨርትን ሊያገኘው አይችልም:: ምክንያቱም እሱ የሚያውቀው ይህን ብቻ ነው አብርሃም የነገረውን፡፡
ያለጥርጥር ካልቨርት እንዲሰወር የካዛንቺሷ ወዳጁ ረድታዋለች፡፡ በመጨረሻ የታየው ከእሷ ቤት ሲወጣ ነው፡፡ ምናልባት የት እንደሚገኝም
ታውቅ ይሆናል፡፡ በተቻለው መንገድ ሴትየዋን ማግኘት አለበት:: ካልቨርትን
ለረዳው እንደሚፈልግ ሊያሳምናት ይገባል፡፡ ትጠረጥረው ይሆናል፡፡ ግን
ሊያሳምናት ከቻለና ካልቨርት ያለበትን ቦታ ከነገረችው ድብብቆሹ አበቃ ማለት ነው፡፡ ያን ጊዜ ያለጥርጥር አውሬውን መረቡ ውስጥ ይከተዋል፡፡
ካልቨርት የሚያውቀው ነገር እንደሌለስ? ማወቅ አለበት ምንም የማያውቅ ከሆነ ለምን ተሸሽገ? ያውቃል፡፡ ለሕይወቱ የሚያሰጋው ምሥጢር ይዟል፡፡ ያንን ምስጢር ማግኘት አለበት፡፡ ካልቨርትን ለማግኘት ደግሞ መጀመሪያ የካዛንቺሷን ሴት አግኝቶ ማሳመን፤ ማግባባት ማሽነፍ፡፡፡ እሷ ብቻ ነች ዕድሉ፡፡
ግን አውሬው ለምን ሴትየዋን አቆያት? ያለጥርጥር ወደ ካልቨርት
የምትመሪ መንገድ ነች:: ይህንን ደግሞ አውሬው ሳያውቀው የሚቀር አያደለም:: ታዲያ ለምን አሰነበታት? ለምን አስገድዶም በሆን የካልቨርትን
እድራሻ አላወጣጣትም? ወያም ለማንኛውም ወገን ምሥጢሩን የካልቨርትን አድራሻ እንዳትጠቁም ለምን እንደ አብርሃም አሳስወገዳትም?
ምናልባት ሴትየዋ ራሷ ወጥመድ እንደሆነችስ? የካልቨርትን አድራሻ የሚያነፈንፍ፡ አይጥ ወደ ካዛንቺስ እንዲመጣና ከወጥመድ እንዲገባ
የተንጠለጠለች የሥጋ ቁራጭ እንደሆነችስ? ካዛንቺስ ከመድረሱ እንገቱን ቆርጠው ቢጥሉትስ?'፡ ናትናኤል ሰጋ:ዠ ኣብርሃም ያለው ትዝ አለው
“… ሁለቱን የክትትል ሰዎች ባሰማራን በሶስተኛው ቀን አንደኛው ሰዋችን በስለት ታርዶ እዛው ካዛንቺስ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ.…”
ህ! “እዛው ካዛንቺስ” ወጥመድ
ያለጥርጥር ካዛንቺስ ወጥመድ ተጠምዶለታል፡፡ ቢሆንም ምርጫ
የለውም፡፡ ወደ ካልቨርት ሊቀርብ የሚችለው የካዛንቺሏን ሴት ሲያገኝ ብቻ
ነው:: የግድ ካዛንቺስ መሄድ አለበት፡፡
'ካዛንቺስ፡፡ ካዛንቺስ ምኑጋ? ካዛንቺስ ስንት አውራ መንገዶች አሉ?… ካዛንቺስ ስንት መጠጥ ቤቶች አሉ? የትኛዋ ነች የካልቨርት ወዳጅ? “የፈጣሪ ያለህ!' የካዛንቺስ ስፋቱና የቀሚስ ለባሹ ብዛት ታየው::
ሌላ ጥያቄ! እንዴት ሊያገኛት ይችላል? ማን ሊመራው ይችላል? አብርሃም ምንድነው ያለው.…?
የቅብብሎሹን ሠንሠለት መስበር ነው
ካልቨርት የሰረቀውን መረጃ…በውስኪ ጠርሙሶች…በሾፌርነት ለማያገለግል ኢትዮጵያዊ ያቀብላል..ሹፌሩ ቤላ መጠጥ ቤት ላላት.…”
ሹፌሩ ሹፌሩ ሌላ መጠጥ ቤት ያላትን ሴት ያውቃታል ማለት ነው፡፡ የካዛንቺሷንስ? ሊያውቃት ይችላል? ምናልባት ካልቨርት የሚቀርበው ከሆነ ሊያውቃት ያችላል፡፡ ያለው ምርጫ ሾፌሩ ነው:: ሾፌሩን አአግኝቶ የካዛንቺሷን ሴት እድራሻ እንዲሰጠው መጠየቅ::
ሾፌሩ የኛ ሰወ ነው በእሱ በኩል ነው
መረጃውን የምናገኘው...” ነበር ያለው
አብርሃም::
ሌላ ወጥመድ፡፡ ሾፌሩም አደገኛ ነው፡፡ ካዛንቺስ ያለችውን የካልቨርትን ወዳጅ ሆቴል ኣሳየኝ።” ሲለው መቼም መጠራጠሩ አይቀርም፡፡
“እሺ ና” ብሎ ገመድ አንገቱ ቢያስገባለትስ? መሬት ለመሬት እያንሻተተና እየጎተተ ቢያስይዘውስ? እርግጥ ያለው ምርጫ ወደ ካዛንቺሷ እመቤት የሚደርሰው ብቸኛ መንገድ የላይቤርያው ኤምባሲ ሾፌር ብቻ ነው:: ለይቶ የሚያውቀው አድራሻ የእርሱን ብቻ ነዋ! ቢሆንም ሰውየውን በአካል
መገናኘት የለበትም፡፡አንድ ዘዴ መፍጠር አለበት፡፡ ናትናኤል ለበርካታ ቀናቶች ሲያወጣ ሲያወርድ መልስ ሲሻለት የቆየው ጥያቄ ይህ ነበር፡፡መልሱን
አግኝቷል። አቅዶ ወጥኖ ጨርሷል፡፡ ትከሻው ላይ አላርፍልህ ያለውን ጋቢ
እያስተካከለ ከመንገድ ወዳለ ትንሽ ቁርስ ቤት ገባ፡፡
“የኔ ልጅ እባክሽ ስልክ ታስደውይኝ…እከፍላለሁ::ችግር አጋጥሞኝ ነው ልጅ ታማብኝ፡፡” አላቸው እናቱ የሚሆኑትን የቁርስ ቤቷን ባለቤት ጠጋ ብሎ። ያቀደውን ደረጃ በደረጃ ይፈጽም ጀመር፡፡
ሴትየዋ ስልክ ማስደወሉን ባይወዱትም ከቄስ ጋር! ከእግዚኣብሄር ሰው ጋር ክፉ መነጋገሩን አልፈለጉትም፡፡ ከባልኮኒው ስር አንድ ሰማያዊ ስልክ አውጥተው ቄሱ ፊት ቆለሉትና “ያው” ብለው ፊታቸውን አዙረው ሄዱ፡፡ · ደረታቸው ላይ የተቆለለው የጡት ተራራ የዘውዲቱን ጋራ
ያስንቃል፡፡
ናትናኤል ሴትየዋ ዞር እንዳሉለት የስልኩን መነጋገሪያ አንስቶ በመጀመሪያ ወደ ማዞሪያ ደውሎ የላይቤርያ ኤምባሲን የስልክ ቁጥር ከጠየቀና ካገኘ በኋላ ወደ ኤምባሲው ደወለ። በላይቤርያው ኤምባሲ ውስጥ ከአንድ በላይ ሾፌር ሊኖር ይችላል የትኛውን አቅርቡልኝ ሊል ነው? ብቻ ማናቸውም ቢሆኑ የካልቨርት

👍3❤2🥰1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ዴሪክ ዊሊያምስ ከሀይ ሆፕ ካፌው ወጥቶ ስምንት ብሎክ ወደሚቀርበው ሴንተሊና ውስጥ ወደሚገኘው ቢሮው ለመሄድ መኪናውን ሲያሽከረክር ከጠዋቱ አራት ሰዓት አልፎ ነበር። ቢሮው 12 ጫማ በ 8 ጫማ ስፋት ያለው ሆኖ መስኮት አልባ ነው፡፡ ነገር ግን ኪራዩ በጣም ርካሽ ስለሆነ እና የዋይፋይ ኢንተርኔቱ ጥሩ ስለሆነ ቢሮው ተስማምቶታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከፎቁ ሥር የሚገኙት ወዳጆቹ የብረት ጎማ ስላላቸው ደምበኞቹ አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጉለታል፡፡
የአሁኗ ደንበኛው ያን ያክል አስቸጋሪ አይደለችም፡፡ ለሦስት ሰዓታት ያህል ቁጭ ብላ ስታወራው ዴሪክ ሦስት ነገሮች ለመገንዘብ ችሏል፡፡
የመጀመሪያው ነጥብ በትክክል እጁ ላይ ያለውን ካርዶችን በአግባቡ የሚጫወትበት ከሆነ በሥራው በጣም ብዙ ገንዘብ ያገኝበታል፡፡
ሁለተኛው ነገር ደግሞ ዕድሉ ከሆነ እና ከተሳካለት የድሮ ጠላቶቹ የሆኑትን የሎስ አንጀለስ ፖሊስ ዲፓርትመንት መበቀል ያስችለዋል::
ሦስተኛው ነገር ደግሞ ይሄ ጉዳይ ራሱን አደጋ ውስጥ ሊከተው የሚችል ነገር መሆኑ ነው።
ከሦስቱ ጉዳዩች በዋነኝነት የሳበው ነገር ቢኖር የሦስተኛው ጉዳይ ነው:: በጣም ከረዥም ጊዜ በኋላ ራሱ ላይ አደጋን የሚፈጥር ጉዳይ ሊገጥመው ነው። ትዳር ከመመስረቱ በፊት እንደዚህ ያሉ አደገኛ ጉዳዮች ላይ ነበር ይሰራ የነበረው። እናም ዛሬ ዶክተር ኒኪ ሮበርትስ
ጉዳይዋን እንዲመረምርላት ስታናግረው የድሮው ማንነቱን ምን ያህል እንደናፈቀው
ነበር የተረዳው።
ማታ ላይ የጠጣው መጠጥ እና ጠዋት ላይ የበላው ቁርስ ሆዱ ውስጥ ቁጭ ስላለበት፣ እንዲፈጭለት ሁለት የአልካ ሲልትዘርን በትልቅ ብርጭቆ ውስጥ በሚገኝ የቧምቧ ውሃ ላይ ጨምሮ ጭልጥ አድርጎ ጠጣው። ከዴስኩ
ውስጥም የድሮ የማስታዋሻ ደብተር አውጥቶ መፃፍ ጀመረ፡፡ እንደ
ሁልጊዜም ሁሉ ሠረዝ ሠረዝ እያደረገ ከማንኛውም ደምበኛው የመጀመሪያ
ስብሰባ ካደረገ በኋላ በዚህ መልኩ ይፅፋል።
ወዲያውንም ገፆችን እየሞላ ማስታወሻውን መያዝ ጀመረ።
ኒኪ ሮበርትስ የምታስገርም ሴት ናት። በተለይ ደግሞ ለፖሊሶች ያልነገራቻቸውን ሚስጥሮቿን ለእሱ መንገሯ ጉዳይዋን ከፖሊሶቹ ቀድሞ ሊቋጭላት ያስችለዋል። እሷ እንዲፈታላት የፈለገችውን ነገር ለሁለት ከፍሎ ምርመራ መጀመሩ
ገቢውን ስለሚጨምርለት የተደራደራት። እሷም በእሱ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ተስማምታ ሌሎች ሰዎችን
በዚህ መልኩ ነበር ከሚያስከፍለው በእጥፍ ሂሳብ ሲጠይቃት ጭምር ያለማንገራገር ለዚያውም ከነ ቦነሱ ነበር ቼክ የፃፈችለት።
“ባልሽ ከትዳር ውጪ ስላለው የፍቅር ግንኙነት ለማወቅ ትፈልጊያለሽ አይደል? ማለትም ሴትየዋ ማን እንደሆነች፣ እንዴት እንደተገናኙ እና ከእሷ ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ማወቅ እፈልጋለሁ ብለሻል?” ብሎ ጠየቃት።
“ልክ ነው” ብላ መለሰችለት ኒኪ
“መልካም እሱ የመጀመሪያው ጉዳይሽ ነው። ሌላኛው ደግሞ ግድያዎቹን
በተመለከተ እና አንቺ ላይ የግድያ ማስፈራሪያ እየተደረገብሽ ስላለ ጉዳይ
ነው። ከእነዚህ ግድያዎች በስተጀርባ ያለውን ሰው ልታውቂ ትፈልጊያለሽ።
ይሄ ደግሞ እኔ የኤል.ኤ.ፒ.ዲ ሥራን እንድሠራላቸው ትፈልጊያለሽ ማለት
ነው?”
“በትክክል”
“ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ጉዳይሽ ነው” ብሎ ለእያንዳንዱ ጉዳዮቿ ዋጋ አውጥቶ ሲጠይቃት ኒኪ የወር ወጪውን በእጥፍ ዋጋ ነበር ቼኳ ላይ ፅፋ የሰጠችው። በዚህም የተነሳ ይህቺን ሴት በእውነቱ ሳይወዳት አይቀርም፡፡
ቢሮው ገብቶ ስለ ሁለቱ ጉዳዮች ሲያስብ የመጀመሪያው ባሏ ውሽማ ጉዳይ ገንዘብን የሚያልብበት ጉዳዩ እንደ ሆነ ገባው:: ምክንያቱም የኤል.ኤፒዲ ፖሊሶች ስለ ዶውግ ውሽማ ማንነት የሚያጣሩበት አንድም ምክንያት የላቸውም እና እሱ ጉዳዩን እስከፈለገው ጊዜ ድረስ በመጎተት የማያቋርጥ የገቢ ምንጩ ማድረግ ይችላል። በምዕራባዊ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በዝሙት ዙሪያ ያሉ ጉዳዮች በሙሉ በጣም ምርጥ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙለት ጉዳዮቹ ናቸው እና አምላኩን ያመሰግናል።
በግድያዎቹ ዙሪያ ላይ የሚያደርገው የግል ምርመራ ግን ያን ያህል የብዙ ጊዜው አስተማማኝ የገቢ ምንጩ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም
ምናልባት ይህንን ወር እንኳን ሳይጨርስ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ የሊዛ ፍላንገን እና
የትሬቨን ሬይሞንድን ገዳዮችን ይዘው ለፍርድ ማቅረብ ይችላሉ። ምናልባት
ፖሊሶቹ በፍጥነት ጉዳዩን እንዳይቋጩ የሚያደርጋቸው ነገሮች ቢኖሩ
ዶክተሯን በመኪና ገጭቶ ሊያመልጥ የሞከረውን ገዳይ መከታተል ችላ
ማለታቸው አንደኛው ነው፡፡ ሁለተኛው ነገር ደግሞ ኒኪ በፖሊሶቹ ላይ
ሙሉ እምነት ስለሌላቸው የግድያ ማስፈራሪያ የኢ-ሜይል መልዕክቷን
እንኳን አምጥታ ለእሱ (ላዊሊያምስ) ማስረከቧ ነው።
ይሄ ደግሞ ሌላ ምርጥ ምልክት ነው፡፡ በጣም ብዙ መረጃዎችን በጉዳዩ
ዙሪያ መሰብሰብ እስከቻለ ድረስ ከኤል.ኤ.ፒ.ዲ ቀድሞ ምርመራውን በድል ማጠናቀቅ የሚችልበትን ዕድል ይፈጥርለታል፡፡
ከባሏ ውሽማ ይልቅ የሊዛ እና የትሬይ ግድያዎች ጉዳይ እሱን በደንብ የሳበው ሌላኛው ነገር ነው:: እንደ ሁሉም የሎስ አንጀለስ ነዋሪ ሁሉ ዴሪክም ቢሆን የግድያዎቹን ዜናዎች በደንብ ይከታተል ነበር፡፡ የኒኪ ሮበርትስ ታካሚ የሆነችው ቆንጆዋ ሞዴል ሊዛ ፍላንገን በአሰቃቂ ሁኔታ ሰውነቷ ተቆራርጦ እና ልቧ ላይ በጩቤ ተወግታ ህይወቷ አልፏል። ሊዛ
ትሬይ ሊዛ አፍሪካ አሜሪካዊው
ከተገደለች ከሦስት ቀናት በኋላም
በተገደለችበት በተመሳሳይ ሁኔታ ለመገደል በቅቷል። በመጀመሪያ ላይ በሊዛ ጥፍር ውስጥ የተገኘው የሞተ ሰው ህዋስን በማስመልከት ዞምቢው ነፍሰ ገዳይ በሚል ርዕስ በየማህበራዊ ገፆች ላይ ሲሰራጭ የነበረው ዜና
በመጨረሻ ላይም በዋነኛ የሚዲያ ተቋማት ላይ በዜና መልክ ቀርቦም
ተመልክቶታል፡፡ ሰዎች በእውነተኛው ዓለም ላይ እንደዚህ አይነት ነገር አለ
ብለው ማመናቸውን በወቅቱ ዴሪክን አስቆት ነበር፡፡ ያም ቢሆን ግን እስከ
አሁን ድረስ ጉዳዩን አወሳስቦታል።
“እና እስከ አሁን ድረስ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ በግድያው ጠርጥሮ የያዘው አንድም
ሰው የለማ?” ብሎ ዴሪክ ኒኪን ጠየቋት ነበር፡፡
“እስከ አሁን ድረስ የለም። እንዲያውም አንደኛው ጆንሰን የተባለው መርማሪ ፖሊስ እኔን እንደ ገዳይ ሁሉ ይጠረጥረኛል፡፡ ባገኘኝ እና ባወራኝ
ቁጥርም እኔን የሚያወራኝ ልክ እንደ ወንጀለኛ ነው::”
“ይሄንን ባያደርግ አይገርመኝም፡፡ ሁሉም ፖሊሶች ባለጌዎች ናቸው፡፡” ብሎ ዴሪክ መለሰላት፡፡
“ሁሉም እንኳን አይደሉም ብላ ኒኪ አሰበች፡፡ ይህን ሀሳቧን ግን ለዊሊያምስ አልነገረችውም። በመቀጠልም ዊሊያምስን ያስገረመ አንድ ነገር
እንደደበቀቻቸው ነገረችው።
“ብራንዶን ግሮልሽ የሚባል ልጅ አውቅ እንደሆነ ጠይቀውኝ ነበር። ነገር
ግን አላውቅም ብዬ ነው የመለስኩላቸው፡፡ ልጁን አውቀው ነበር። ባለቤቱ እኔ ህክምና እንዳደርግለት ወደ እኔ ቢሮ ይዞት መጥቶ ነበር::”
“ለምንድነው ስለ እዚህ ልጅ የጠየቁሽ? አንቺስ ለምን ዋሸሻቸው?” ብሎ
ዊሊያምስ ጠየቃት፡፡
ኒኪም ትከሻዋን ሰበቀች እና “ለምን እንደጠየቁኝ አላውቅም። ምናልባት
ግን ልጁ ከግድያዎች ጋር የተያያዘ ነገር አለው ብለው እንደሚያስቡ ገምቻለሁ። ይሄውልህ ይሄ ብራንዶን የተባለ ልጅ እንደዚህ አይነት ነገርን የማድረግ አቅም የለውም፡፡ ልጁ በጣም ጨዋ እና መልካም ልጅ ነበር::" ብላ ፈገግ በማለት
አሁን ላይ ሳስበው ግን ልጁን አላውቀውም ብዬ የዋሸሁለት ከእነርሱ
ልከላከለው አስቤ ይመስለኛል”
“ፖሊሶቹ መዋሸትሽን ቢደርሱበት መረጃን በመደበቅ

👍7
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
በሐሰት ተገንብቶ በተለበጠ አካባቢ ሁሉ አንድ ግለሰብ ብቻውን ተገንጥሉ ልዩ ትክክለኛ አካባቢ ለመፍጠር ከፍ ያለ ችግር ያጋጥመዋል።ሁሉም በየበኩሉ የየራሱን የኑሮ ማሳ እያዳበረ በሚያርስበትና በሚያዘምርበት
ትክክለኛ ዓላማና ግብ ማምራት እንጂ፣ ይኸ እንዲህ ነው፣ ያኛው እንዲያ
አካባቢ፣ የራስን ዶማ እና መሣሪያ ይዞ በመቀላቀል ቀስ በቀስ ወደሚመኙት
ነው እያሉ መጃጃል ወደፊት መራመድ ሳይሆን ወደኋላ ማፈግፈግ ነው:: ልክ
ያልሆነው ነገር ሁሉ ወለል ብሎ ቢታየኝም በግል ስክበው የሰነበትኩት
አስተሳሰብ ለጊዜውም ቢሆን በአካባቢዬ አሮጌ ልማድ ተዋጠ።
ባለሁበት ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ተርፎታል፣ ሞልቶታል፣ እየተባለ ነገር ግን ዝቅ ብሎ መታየትን የመሰለ አሳሳቢ ነገር የለምና የአካባቢን አስተያየትና ግምት ለመለወጥ ሲባል የሚደረግ ልዩ ልዩ ጥረት አንድም ፈጽሞ መውደቂያ ወይም ለጊዜው ቀጥ ብሎ መቆሚያ ሊሆን ይችላል፡፡ ግላዊ ስምና ክብርን ለመጠበቅና ለማስከበር ሲባል የሚደረግ የስግብግብነት ውጣ ውረድ ሁሉ በሰው ሕይወት ውስጥ ትልቅ የሥቃይ ሸክም ነው::
በግል ሀብት ጥሪት ፍላጎት የቆሰለና የበለዘ ሕሊናን ለማንጻትና ለማዳን የሚደረግ ጥረት መሪርና አድካሚ ነው:: ከቤተሰቦቼ የሚደርስብኝን ትችትና የወጪ ገቢ ሐሜት ለመከላከል ያህል የሕሊናዬን ዓላማ ቅንጣት ታህል ችላ ብዪ ሕይወት ኣልባ ተራ ስሜን ለማዳን ስል አንዲት የተለየች የሐሳብና የተግባር ዘመቻ ጀመርኩ። ሌሎችን ለመምሰልና ላይ ላዩን እኩል ሆኜ ለመታየት ስል አንዲት ባገልግሎት ላይ ከዋለች አራት ዓመት ያህል ያለፋት ቮልስዋገን መኪና ከስንት የደላላ ንትርክ በኋላ ገዛሁ፡፡ በክፍያው ላይ እኔና ጉልላት ተረባረብንበት፡፡ የጠንቃቃ ሰው ንብረት ስለ ነበረች በየጊዜው በመሰናከል አላስቸገረችኝም፡፡
ኑሮዬን መለስ ብዬ እያየሁ «የሕይወት ቀላል ፍቺ ይህች ትሆን? ወይስ ራስን የማታለያ ስሕተት» እያልኩ ማሰብ አዲሱ ልማዱ ሆነ፡፡ መስሎ መታየትና በጉራ ተኮፍሶ መወጣጠርን ከዚህም ከዚያም ቀሠምኩ፡፡ አንዳንድ ቀን ያን መበስበሱ እየታወቀ ቀለም እንደተቀባ ግንድ ላይ ላዩን ያሽበረቀ አስመሳይ ኑሮዬን መለስ ብዬ ሳየው ጎምዛዛ ኀዘን ይስማኝና በረጅሙ እተክዛለሁ። በሳምንት አንድና ሁለት ቀን እያመሽሁ መግባትና ሳይበዛም
መጠጥ መጎንጨትን ኣዘወተርኩ፡፡ አንድ ቀን እሑድ ከጧቱ ሁለት ሰዓት የወጣሁ ጥምብዝ ብዬ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል ገባሁ።
የወዲያነሽ ያጋጠማትን ያልታሰበ ችግር ችላ «አይ ጌትዩ! ስንቱን ለፈለፍከው ! መንጋት አበይለው ነጋ» አለችኝ ሰክሬ በገባሁ ማግሥት አብረን ቁርስ ስንበላ፡፡ ከዚያ በመጥፎ ልማዳዊ እምነት ተበክሎ ካደገው ልቦናዩ ምን አስነዋሪ ነገር ወጥቶ ይሆን በማለት በጣም ሠጋሁ፡፡ ከጎኔ ተነሥታ በስተጀርባዬ ቆመች፡፡ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ሁሉ ፊት ለፊቴ ባለው የቁም ሳጥን መስታዋት እመለከት ነበር። እሷም ይህችኑ ብልሃቴን ደርሳበት ኖሮ በመስተዋቲቱ ውስጥ ስታየኝ ዐይን ለዐይን ተጋጨን። የያዝኩትን
የእንቁላል ጥብስ ለመጉረስ አፈን ከፈት ላደርግ ሣቄ አመለጠኝና ተንከተከትኩ፡፡ እጄን ስባ ጎረሰችብኝ፡፡ 'ጌትዬ” አለችኝ ጉርሻዩን ቀምታ የልቧን ካደረሰች በኋላ፡፡ «ይኸው ዛሬ አምስተኛህ መሆኑ ነው መሰል ካንተ አላውቅምና ለምኑም ለምኑም ቢሆን ጥሩ አይደለም። ጌታነህ ሰክሮ እንዲህ አለ መባል ደግሞ አንዳች የሚያህል ነውር ነው። በዚያ ላይ ውርደቱ? ቅሌቱ... ጌትዬ አፈር ስበላልህ! ባንዲት እንጨት ስሔድ አትጠጣ፡ መቼም
ይኸን ጉድህን ጋሼ ጉልላት ኣልሰማም እንጂ ቢሰማማ....» ብላ አዘኔታና
ምክሯን አደባልቃ ከነገረችኝ በኋላ የተዳፈረችኝ ስለ መሰላት ሳይታወቃት
ትከሻዬን በግንባሯ ጠረግ ጠረግ እድርጋ ልትሸሽ ስትል እጅዋን ይዤ
አስቀረኋት፡፡
«ለመሆኑ ክፉ ነገር ተናገርኩ እንዴ? ሆድ ያባውን... የሚሉት ነገር ነበረበት?... አልኳት።
«የተናገርከው ሁሉ ምኑም አልገባኝ። እነዚያኑ ቤተሰቦችህን ስትሰድብና ስታጥላላ ነው ያደርከው:: እኔንም አይዞሽ በርቺ ድሉ ያንቺ ነው፤ ያባትሽ ስም አሸናፊ ነው እንቺም አሸናፊ ትሆኛለሽ እያልክ
ስታጫውተኝ አመሽህ» ብላ እጅዋን ነጥቃኝ ወደ ጓዳ ገባች፡፡
የገዛ ስሕተቴን ለማስተባበል ሳይሆን ለማመኻንት ያህል ከጓዳ መለስ
እንዳለች «ትላንትም በል በል ብለው፣ አጠጥተውኝ ነው እንጂ ከእንግዲህ
ወዲህ መጠጥ በረበት ኣልዞርም» አልኳትና ወደ ሥራዬ ሄድኩ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሌሊቱ አብዛኛውን ክፍል በሐሳብ ስገላበጥ አሳለፍኩት፡፡ እሑድ ጧት ከቁርስ በኋላ ሽር አልኩ። ሰበሰቡ ላይ ቆም ብዬ የወዲያነሽን ጠራኋት።
ከወደ ውስጥ ከተፍ አለች፡፡ የምትለውን ለመስማት ያህል 'አይቆርጡን አይፈልጡን ነይ እስኪ ወላጆቼ ቤት ይዤሽ ልሂድ? እኔ እያለሁ ምንም
እትሆኚ» አልኳት፡፡
ከልቤ ስለ መሰላት ክው ብላ ደነገጠች፡፡ «እንዲህ ንገረኝና ይለይልኝ
እንጂ! እጄን ይዘህ አስገድለኛ! እንኳንስ ካንተ ጋር አብሬ እዚያች ቤት
ገብቼላቸውና መንገድ ላይ ያዩን ይሆን እያልኩ አካላቴ ይበጠቃል። ምን
ቅብጥ ልጄ! ይልቅስ ሂድ ይቅናህ!» ብላ በእርሷ አስተሳሰብ የልቧን ተናግሬ
እንዳበቃች መንገድ ገባሁ፡፡ ጠምዛዛው መንገድ ከዐይኗ እስከ ሰወረኝ ድረስ
የአጥር ግቢውን በር ተደግፋ በዐይኖቿ ሸንችኝ፡፡ መኪናዬን ከቀበና ድልድይ
በላይ አቁሜ በእግር ቀጠልኩ። የወላጆቼን ቤት ከረገጥኩ ሦስት ወር ያህል አልፎኝ ስለ ነበር በዱሮው ዘበኛ በአቶ በየነ ምትክ ሌላ ሰው ተቀጥረዋል።
አጠር ብለው ከወደ ዐይናቸው ላም ያሉ ጸጉረ ገብስማ ሽማግሌ ናቸው::
አያውቁኝም። ለመግባት ፍቃድ ጠየቅሁ። ደረታቸውን ለረፋዷ ፀሐይ ሰጥተው
ማንን ነው የምትፈልገው? ጌቶችና አሜቴ እንደሁ ቤተስኪያን ሊስሙ እንደ
ኤዱ አልተመለሱም፡፡ ቆየት ብለህ ተመልሰሀ ናና ነግሬልህ ትገባለህ» ብለው ፊታቸውን አዙረው ችላ አሉኝ፡፡ ቸልታቸው ስላበሳጨኝ ልጃቸውስ የለችም
እንዴ? እሷም ካለች ያው ነው» ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ በጥፊ የመታኋቸው ያህል
ብው ብለው ተናደዱ፡፡ «እንዴ! እንዴ! መች አበድኩና! አንተ ስለ እኔ
እንጀራ ምንቸገረህ! የዋዛ ቤት መስሎሃል! እዚች ቦታም አያውሉኝ!» አሉና ነገሩኝ፡፡ ቀባጥሬም ሆነ ማንነቴን አስረድቼ መግባት ስላልፈለግሁ ደጅ ደጁን እያልኩ ለመቆየት ወሰንኩ፡፡ በዚያው አካባቢ መለስ ቀለስ ስል የውብነሽ ባዘቶ የመሰለ ነጭ ጋቢ ለብሳ ስትመጣ አየኋት።አመጣጧ በእኔው ኣቅጣጫ ስለ ነበር ቆሜ ጠበቅኋት። ከሩቅ የጀመረው ፈገግታዋ አጠገቤ ስትደርስ ተራውን ለውብ ጥርሶቿ ለቀቀ፡፡ ከጋቢው ሥር እጅዋን ብቅ አድርጋ ጨበጠችኝ፡፡ ስሜቷን ለመሸንገል ያህል ሳምኳት፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሽማግሌው ኣጠገብ ደረስን፡፡ ቀና ብለው ከእግር እስከ ራሴ አዩኝ። ይኸ ደግሞ የማን ነው? በሚል አስተያየት እየገረመሙኝ አልፈናቸው ገባን፡፡
በምድረ ግቢው ያሉት አበቦችና አትክልቶች በጣም ያማሩ መሰለኝ፡፡
ከየውብነሽ ጋር እያወራሁ ዐይኖቼ ካትክልቶቸ ላይ አልተነቀሉም፡፡ እነዚያ
ምን ጊዜም ሌላ መሄጂያና መግቢያ የሌላቸው የሚመስሉት ነባር ሠራተኞች
ናፍቆትን በሚገልጽ ፈገግታ እጅ ነሡኝ፡፡ ውስጥ ውስጡን ግን ዛሬ የጌቶች
ልጅ ከየት መጡ?” እንደሚሉ ታወቀኝ፡፡ አንደኛዋ ሠራተኛ እማማ ወለተሩፋኤልማ በወላጆቼ ቤት ውስጥ ከ30 ዓመታት በላይ አገልግለዋል፡፡ እኔ ግን ገና ከልጅነቴ ጀምሮ አልወዳቸውም ነበር፡፡ ኣብሮ ከመኖር ብዛት የተነሣ
እናትና አባቴ እንደ "ገረድ አያዩዋቸውም፡፡

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....በአርሲ ጠቅላይ ግዛት በጭላሎ አውራጃ በሄጦሳ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ኛሮ እንኳን ለአንድ ሽፍታ ይቅርና ለእልፍ አእላፍ ሽፍቶች መሽሽጊያ ሊሆን የሚችል ሰፊ ባህር ነው፡፡ ከትንንሽ ቁጥቋጦ ጀምሮ ሶስት ሰው እጅ ለእጅ ተያይዞ ቢያቅፋቸው የማይሞሉ ከመቶ አመታት በላይ እድሜን ያስቆጠሩ ግዙፍ አገር በቀል ዛፎች የተጠቀጠቁበት ዱር ከመሆኑም በላይ በውስጡ ያሉት እጅግ በርካታ የዱር አራዊቶች ላኛሮ አስተማማኝ የሽፍታ መኖሪያነት በቂ ምስክር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዘላይ አራዊት፣
በደረት የሚሳቡ፣ በጉድጓድ የሚኖሩ፣ በየድንጋዩ ውስጥ የሚሹሎከሎኩ
በብዛት ይገኙበታል።አጋዘን፣ ድኩላ፣ የሜዳ ፍየል፣ ሚዳቋ፣ ነብር፣
ከርከሮ፣ ሰስ፣ ቀበሮ፣ ጅብ፣ እባብ፣ ዘንዶ... የሚርመሰመሱበት የቀለጠ
ዱር ...
የሳለን ተራራ እንደሰንሰለት ተያይዞ ሽቅብ ሲታይ ሰማዩን አቅፎና ደግፎ ያቆመው ሲመስል ኛሮ ደግሞ የታችኛው የቆላው አገረ ገዥነቱን ያለተቀናቃኝ ይዞ ተንሰራፍቷል። የተማመነበትን ሙጥኝ ያለበትን ሽሽቶ የተደበቀበትን አሳልፎ እንደማይሰጥ በኩራት ደረቱን ነፍቶ የሚመሰክር ዱር..
ኛሮ ዳገቱ ላይ ቡልቅ እያለ ከመሬት ውስጥ የሚወጣው የእሳተ ገሞራው
ሲስ በአካባቢው አጠራር “አርቱ” ይባላል። መሬቱ ማስ፣ ማስ ይደረግና ጉድጓድ ከተበጀ በኋላ የጉድጓዱ አፍ በጋቢ ወይንም በቁርበት ይሽፈናል። ከዚያ ምን ያስፈልጋል? ከውስጡ ቁጭ ማለት ነው።በዚያ ትኩስ እሳተ ገሞራ ጢስ እየተቀቀሉ እንደ ቅቤ ሲቀልጡ እንደ ዥረት የሚንቆረቆረው ላብ ቆሻሻውን ሙልጭ አድርጎ ይዞት ይወጣል። በዘመናዊ አጠራር “ሳውና ባዝ እንደሚባለው መሆኑ ነው። ኛሮ ለቤተሰብ አባሎቹ ለተለያዩ የዱር አራዊቶች ገነት ነው፡፡ እንደ ፍላጎታቸው ሁሉንም ችሎ
አቻችሎ ይዟቸዋል፡፡ የሚጋጥ ሳር ለሚጠይቀው ከጨሌው ጀምሮ የሰው
አንገት እስከሚውጠው ሰንበሌጥ ድረስ አብቅሎለታል። ሥጋ ለሚፈልገው በውስጡ ያቀፋቸው ሳር በል አራዊቶች በሽበሽ ስለሆኑ አድፍጦ ጉብ ማለት ብቻ ነው የሚያስፈልገው እንጂ በኛሮ በኩል የተጓደለ ነገር የለም፡፡ ኛሮ የገባን ፈልጎ ማግኘት ቀይ ባህር ውስጥ የወደቀ ቀለበት ለማግኘት እንደመፈለግ ሆኖ ዋሻነቱ ይጋነንለታል፡፡
ፀሀይዋ ደማቅ ጨረሯን በመለገሷ ሙቀቷን ለመቋደስ የሚፈልጉ አራዊ
ቶች ከየዋሻው፣ ከየጢሻውና ከየድንጋዩ ውስጥ እየወጡ ብቅ ብቅ ማለት
ጀምረዋል። ከእነዚህ መካከል ኛሮ በአይነቱም ሆነ በአፈጣጠሩ ለየት
ያለውን በሁለት እግሩ ቆሞ የሚራመደውን አውሬ ከነጀሌዎቹ በቤተሰብ አባልነት ከመዘገባቸው ውሎ አድሯል። ጎንቻ ዘረፋውን በስውር በሌሊት ያከናውንና ወደ ሐሮ ጫካ ተመልሶ ይሰምጣል። ከተራ ሌብነት በደረጃ ዕድገት ሽፍታ ተብሏል፡፡
“ጎንቻ! ጎንቻ ጎንቻ” በበርካታ ሰዎች
አንደበት በፍርሃት የሚጠራ ገናና ስም ሆኗል። በድንገት እየተከስተ መአተ ቁጣውን ካወረደው በኋላ በፍጥነት ስለሚሰወር ስሙ ሲጠራ በፍርሃት የሚርበደበዱና ብርክ የሚይዛቸው ሰዎች ቁጥር እየበራከተ ሄዷል። የጎንቻ ስም ሲጠራ ወንዱ ሱሪው ሊከዳው ይዳዳዋል፡፡ ሴቱ ደግሞ “የጎንቻ አምላክ” ብሎ በፍርሀት ያመልክበት ጀምሯል፡፡ በዚህ ሁኔታ የጎንቻ ዝና ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ፡፡ ያንን አስከፊ ወንጀል እያፋፋመው ሲሄድ በቸልታ የተመለከተው ሁሉ ቀስ በቀስ በመቅሰፍት ጅራፉ
እየተሸነቆጠ ነው፡፡ የሌላው ህመም ያልተሰማው “እኔ እስካልተነካሁ ድረስ ምን አገባኝ?” በሚል መንፈስ ተሸብቦ የኖረው ሁሉ ከባድ ችግር ውስጥ እየወደቀ መጥቷል። ገና በእንጭጩ በቁጥጥር ስር ማዋል ሲቻል ጎንቻን የቂም መበቀያ ለማድረግ የሁለት፣የሶስት፣ የአስርና የሃያ ዓመት ቂም እየፈለጉ “እገሌ በሙግት ከመሬቴ ከእርስቴ ነቅሎኛልና ንቀልልኝ ቢቻል በራሱ ላይ ባይቻል በንብረቱ፣ በልጆቹ፣ ወይንም ደግሞ በሚስቱ ላይ አደጋ ጣልልኝ፣ እገሌ በህዝብ ፊት ሰድቦ አዋርዶኛልና አዋርድልኝ።
ይህን ያክል ዋጋ እከፍልሃለሁ” የሚሉ አማላጅ የሚልኩ ስዎች እየበዙ
መጡና በትዕቢት ልቡን አሳበጡት። ጎንቻም በድርድር ገንዘብ እየተቀበለ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ባደረገው ጥረት የብዙዎችን አንጀት አራሰ፡፡
አሁን ጎንቻ የዋሻውን ኑሮ እጅግ እየተላመደው መጥቷል። ከሰው ይልቅ
የአራዊት ጠረን ተዋህዶታል፡፡ ከሞቀ ቤት፣ ከሞቀ አልጋ ይልቅ አስፈሪውን ጨለማ፣ዋሻና ጢሻውን የሚመርጥ ሆኗል። ለሰው ልጅ ህይወት ያለው ግምት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዶ የወፍ ያክል እንኳ ዋጋ ሊሰጠው አልቻለም፡፡ ምንም ቢሆን ግን ከአውሬነት ባህሪው ውስጥ ሰው የመሆን ፍጥረቱ ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም ነበረና ዘወትር ዓለሚቱን ያስ
ታውሳታል፡፡ ዘወትር ዓለሚቱን ይራባል፡፡ ይናፍቃታል፡፡ ኛሮ ዋሻ ከገባ በኋላ አንድ ሁለት ጊዜ ጨለማን ተገን አድርጎና ራሱን ለውጦ ጎብኝቷታል፡፡ ይሄ ግን ለሱ በቂ አልነበረም፡፡ ምኞቱና ፍላጎቱ ምንግዜም ከአጠገቡ እንዳትለየው አብራው ጫካ እንድትኖር ነው። እሱ የጫካው ንጉሥ
እሷ ደግሞ ንግስት ሆና ያለ አዛዥ ያለተቆጣጣሪ እያዘዙ እየተቆጣጠሩ
እየነጠቀ እየቀማ በድሎት አብሯት መኖር ይፈልጋል። እንደፈለገው እየበላ እየጠጣ ጥጋብ ሲያንጠራራው፣ እንደ ተዋጊ ኮርማ እያነጠነጠ የወሲብ ፍላጎቱ ሲቀሰቀስ የዓለሚቱ ገላ አእምሮውን እስከሚስት ድረስ በዐይኑ ላይ ይሄድበታል...
በኛሮ ጫካ ውስጥ በጎኑ ጋደም ብሎ፣ ጎፈሬውን ወደ ፊትና ወደ ኋላ
አመሳቅሎ፣ ጠመንጃውን እንደሚሰስቱለት ህፃን ልጅ በደረቱ ሸጉጦ የጠዋቷን ፀሀይ ሙቀት በመጋራት ስለሚያከናውናቸው ተግባራት እቅድ
ያወጣል፣ ያወርዳል። የመልኩ ጥቁረት አይነሳ! ከጥቁር አዝሙድ ጋር ይቀራረባል፡፡ ቁመቱ ረዥም ነው፡፡ ጎንቻ! ጎንቻ!! ጎንቻ! የፍርሀት ጌታ!!... የሰቀቀን አምላክ! በበርካታ ህዝብ አንደበት የሚነገረው ዝናው ሰው መሆኑን እንዲጠራጠር አድርጎታል። “ቀላል እና ከባድ ዘረፋን በመለየት ቀላሉን የዘረፋ ትርዒት የሚንቅ ከባዱን የሚወድ፣ ፈታኝ በሆነ ዘረፋና ግድያ የሚረካ በጥቃቅን
ዘረፋና ሌብነት ላይ እጁን የማያስገባ ዝናው የተፈራ ሽፍታ ሆኖ ለመኖር
ራሱን አሳምኗል፡፡ ከኛሮ አልፎ ግዛቱን ወደ ሌላ አስፋፍቶ፣ ጀሌዎቹን
በእጥፍ ድርብ አበራክቶ ዘረፋውን በማጧጧፍ ሀብታም መሆንን እየተመኘ ነው።
ይሄ ምኞቱ እንደሚሳካ ደግሞ ጥርጥር አልነበረውም፡፡ በተለይ ሰሞኑን
መልእክት የላከበት ባላባት ምን ያክል ለቁም ነገር ተፈላጊ ሰው እየሆነ
መምጣቱን አረጋግጦለታል። ወላጅ አባቱ በቶላ ሞት ምክንያት ተበሳጭተው ራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ መሆናቸውን ከጀሌዎቹ አንደበት በሰማበት ዕለት የቀለደው ቀልድ ጀሌዎቹን ጭምር ያስደነገጠ ነበር። ተበድሮ
ያልመለሰለትን ገንዘብ ሊቀበለው ነው አብሮት የሄደው ከተቀበለው በኋላ
ተመልሶ ይመጣልና አታስቡ በማለት ሊያረጋጋቸው መሞከሩ አለቃቸው
ምን ያክል ጨካኝ ሰው እንደሆነ አረጋግጦላቸዋል። ጎንቻ በደም ስሩ
ውስጥ የሚዘዋወረው የወንጀል ዕፅ የመረዘው መራራ ደም ነበረና የባላባቱን ነገር ሲያብሰለስል ከቆየ በኋላ በአፋጣኝ ሄዶ ማንነቱን ሊያስመስ ክር ፈለገ፡፡ ከዚያም ወደ ጀሌዎቹ ዘወር አለና በደፈረሱት ዐይኖቹ አካባቢውን በመቃኘት ጊርቦን አናገረው፡፡
“ስማ ጊርቦ! የሽማግሌው ጉዳይ?!” አለው፡፡ ጊርቦ አለቃው ጎንቻን በጣም የሚያከብር የሚፈራም ሰው ነው፡፡ በተዘረፈ ንብረት ተሸካሚነትና በወንጀል ተባባሪነት ብቻ ሳይሆን ጠቃሚ መረጃዎችን በመስብስብ በኩል ለጎንቻ ቀኝ እጁ ነው፡፡

👍3
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...አስቻለው ከተንጋለለበት ብድግ ብሎ ሔዋን ሳማት እሷም ሳመችው። ግን ደግሞ ሁለቱም ሆዳቸው ባባና ተላቀሱ።
ቀጣዬቹ ቀናት የአስቻለው የጉዞ ዝግጅት ጊዜ ሆኑ። ከሁለቱ በፊት የደምወዙን ውክልና ለበልሁ ሰጠ። ቀጥሎም ሔዋንና ትርፌን አስቀምጦበት የሚሄደው ቤት ከግለሰብ የተከራየው በመሆኑ እሱ በሌለበት ችግር እንዴይፈጠርባየው ከባለቤቱ ጋር የቃልም ሆነ የፅሁፍ ውል ማሰር ነበረበትና ጥረቱን ጀመረ።
የቤቱ ባለቤት አቶ ከድር አህመድ በቀበሌ ዜሮ ሰባት ውስጥ የኖራሉ።የሚኖሩበት ቤት ከመጥበቧ የተነሳ ከአንድ ፍራሽ የተረፈችው የሳሎን ቦታ ሌላ
ፍራሽ አታዘረጋም ከጫት መቃምያ ፍራሻቸው ፊት ለፊት ሁለት ወይም ሶስት የዱካ መቀመጫዎች ብቻ ተደርድረዋል። አስቻለውና ሔዋን በተወያዩ በሁለተኛው ቀን ከምሽቱ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ አስቻለውና በልሁ አብረው ሄዱ ከአቶ ከድር ቤት ሲገቡ ከባለቤታቸው ጋር ፍራሽ ላይ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ጫት ሲቅሙ አገኛቸው።
«ምን እግር ጣላችሁ ዛሬ ልጆች?» ሲሉ አቶ ከድር አስቻለውና በልሁን ጠየቋቸው።አቶ ከድር በጣም ጥቀር ከመሆናቸው የተነሳ ነጭ ጥርሳቸውን ገለጥ ሲያደርጉት
የሰው ዝጉርጉር መስለው ይታያሉ፡፡ በዚያ ላይ ሰፌድ የሚያህል የእይታ መነጽራቸው ግማሽ ፊታቸውን ሸፍኖት ሲታዩ ሁኔታቸው ያስፈራራል። እድሜአቸው ወደ ሰባ ዓመት የሚጠጋ ሲሆን ሰውነታቸውም መጨማደድ ጀምሯል።
«ስለ ቤት ጉዳይ ላነጋግርዎት ነበር፡፡» አላቸው አስቻለው ከፊት ለፊታቸው ባለች ዱካ ላይ ከበልሁ ጎን ተቀምጦ፡፡
«ልትለቅ ነው?»
“አይ! አይደለም፡፡»
«እንግድያማ ኪራይ ልትጨምር ማሰብህን ልትነግረኝ ነው የመጣኸው ሲሉ አቶ ከድር ቀለዱ፡፡ ጎንበስ ብለው ፈገግ በማለት ጫት ይቀነጣጥባሎ፡፡
«ቢሆንስ ምን ችግር አለው?» አለ አስቻለው በፈገግታ እየተመለከታቸወ፡፡
«ጎሽ የኔ ምሁር አፍክን በዳቦ»
በዚህ ጊዜ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰሚራ አሊ ጭምር በቢቱ ውስጥ ያሉት በሙሉ ሳቁ፡፡
«ለአንድ ስድስት ወር ያህል ወደ ሌላ አገር በጊዜያዊነት ልሄድ ስለሆነ ቤቴ ውስጥ አስቀምጫቸው ስለምሄደው ሰዎች ጉዳይ እንድንጋገር ብዬ ነው የመጣሁት አላቸው አስቻለው ወደ ቁም ነገሩ በመመለስ፡፡
የት ልትሄድ ነው!»
ወደ ኤርትራ ነው ፤ ዘመቻ!»
«አኪምነቱን ትተህ ወታደር ሆንክ እንዴ?» እሉ አቶ ከድር በዚያ
መነፅራቸው ውስጥ ቀና ብለው እያዩት። አስቻለው የአስተሳሰባቸው ከቅጣጫ እንደ
መገረም ብሎት በልሁን እያየ ፈገግ ካለ በኋላ፡-
«አይ ለሌላ ሥራ ነው::» አላቸው፡፡
«ወደዚያ የሚኬደው ለጦርነት ስለሆነ ብዬ ነዋ» ካሎት በኋላ «ታዲያ ማንን ልታስቀምጥበት ፈለግህ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡
«ሰራተኛዬንና እጮኛዬን!»
«ሁለቱም ሴቶች ?»
«አዎ» አለና አስቻለው ወደበልሁ እያመለከተ «ይሄ ወንድሜ የቤት ኪራዩን እቤቶ ድረስ እያመጣ ይከፍሎታል።»
«አዬ..» አሉና እንደማቅማማት አሉ። ወደ ባለቤታቸው ዞር በማለት «ይኸን ነገር እንዴት ታይዋለሽ ሰሚራን» ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እርጅና ወደቅ ያለባቸው ቀይ ፋታቸው ጨምደድ ማለት የጀመረው ወይዘሮ ሰሚራ ሙሉ ሰውነታቸውን በሰፊና ረጅም ቀሚሳቸው ሸፍነው በቀይና ነጭ ቡራቡሬ ጉፍታ አንገትና ጭቅላታቸውን ተከናንበው በመቀመጥ ጫት ይቅማሉ። ጀበናና የሲና ረከቦት ከፊታቸው ደርድረዋል።
«እኔ ደሞ ምን አውቄ!» አሏቸው አቶ ከድርን ማየት ከፊታቸው
ያለውን ከሰል እሳት ቆሰቆስ እረጉት፡፡
«ችግር እኮ የለውም አባ አድር!» አላቸው አስቻለው የባልና ሚስቱ
ምልልስ ትንሽም ቢሆን ወደ ስጋት ስሜት ወሰድ አደረገውና ለማስተማመን::
«ስማ የኔ ልጅ!» አሉ አቶ ከድር አጎንብሰው “ጫታቸውን እየቀነጣጠቡ።
«አቤት»
«የሴት ነገር ያው የሴት ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ አንተ የምትሄደው ወደ ጦር ሜዳ ነው።
ድንገት መጃለፍም ሊኖር ይችላል። በመሀል ታድያ ችግር የተፈጠረ እንደሆነ ሰዶ ማሳደድ አይሆንም ብለህ ነው?» ሲሉ ጥያቄ አዘል አስተያየት ሰጡና ቀና ብለው ተመለከቱት፡፡
በዚህ ጊዜ በልሁ ንድድ ብሎት በሆዱ ምን ዓይነት ፈልፈላ ሽማግሌ ነው አለና « የሆነው ቢሆን በእርስዎ ቤት ላይ ምን ይመጣል ብለው ፈሩ፣» ሲል ኮስቴር ብሎ ጠየቃቸው፡፡
«አይደለም! አይደለም! መፍራት ጥሩ ነው። ባይሆን ሰሞኑን ከሰሚራ ጋር ተነጋግረን የደረሰበትን ሁኔታ እንገልጥላችሁ
እንዲሆን እንጂ…» ብለው ነገራቸውን ጎተት ሲያደርጉት በልሁ ድንገት ከተቀመጠበት ብድግ አለና፡
«ቢቃ ጌታዬ! ምንም አያስፈልግም፣ ነገ መጥተው ቤትዎን ይረከቡ፡፡» አለና
ወደ እስቻለው ዞር ብሎ «ተነስ እንሂድ!» ብሎት ቀድሞ ከቤት ወጣ::
አስቻለው በአቶ ከድር ሁኔታ ሆዱ እየበሽቀ ነገር ግን በልሁ ምን አስቦ እንደሆነ ግራ እየገባው ብድግ ብሎ ተከተለው፡፡ ከደረሰበትም በኋላ ምንም የተለየ
አማራጭ አልነገረውም። ብቻ «ና ወደ ታፈሡ ጋ ሄደን በጋራ እንነጋገርበታለን::»
ብሎት ሁለቱም ዝም ብለው ወደ ታፈሡ ቤት አመሩ፡፡ በልሁ ገና ሔዋን ከሸዋዬ ቤት መውጣት እንዳለባት ሀሳብ ከቀረበ ጀምሮ
ምናልባት እሺ ብላ ከወጣች በማለት ስለምትኖርበት ቤት አንድ ነገር ሲያሰላስል ቆይቷል። በእሱ እምነት የሸዋዬና የአስቻለው ቤት ተቀራራቢ በመሆኑ ሽዋዬ ነጋ
መሽ እየተመላለሰች ሰላም ልትነሳት ትችላለች። የእሱ ቤት ደግሞ በዜሮ ሁለት ቀበሌ ውስጥ ለዚያውም ዙሪያው በግንብ የታጠረና የተከበረ የትልቅ ሰው ግቢ ነው:: ለርቀቱም ለፀጥታውም ምቹ ስለሆነ ሔዋንን ከትርፌ ጋር እዚያ አስገብቶ
እሱ በአስቻለው ቤት ውስጥ የመኖር ሀሳብ ነበረው። አቶ ከድር ግን እቅዱን አበላሹበት።
በልሁ ይሄንኑ እያሰበ ከአስቻለው ጋ ተጉዞ ከታፈሡ ቤት ደረሱ ሁለቱም ገብተው ከታፈሡ ጋር ቁጭ ሲሉ በልሁ አንድ ነገርም ብቻ ለሁለቱም ነገራቸው።
«ስለ ቤት ጉዳይ ምንም አታስቡ፡፡ ቢቻል ነገ ካልሆነ ግን ከነገ ወዲያ
ሔዋን ጓዟን ጠቅልላ ከሸዋዬ ቤት የምትወጣበትን ሁኔታ ብቻ አስቡ፡፡ ሌላውን ነገር ለኔ ተውት አላቸው።
የሆነውም ይኸው ነበር፡፡ በልሁ ያንዕትን ልብሶችና የመጽሐፍ መደርደሪያ ይዞ ከአንድ ሆቴል ውስጥ ኮንትራት አልጋ ይዞ ገባ፡፡ ሔዋንም እንኳንስ ጫማ እና ልብሶቿ!! የአለቀ የእስክሪብቶ ቀፎ እንኳ ሳይቀራት ጓዟን ጠቅልላ በሚቀጥለው ቀን ወደ ታፈሡ ቤት መጣች፡፡ ያ ቀን ማግስት ምሽት ላይ ደግሞ ከትርፌ ጋር በበልሁ ቤት ውስጥ 'ቤት ለንሞባሳ ብለው ገቡ።
የዚያኑ ዕለት ለአስቻለው አጠር ያለ ሽኝት ተዘጋጀ። አዎ! ለነገሩ ጥሩ ምግብ ተበላ መጠጦች በያይነቱ ተጠጡ።። ነገር ግን መስፈሪያ ኖሮት የሚለካ ቢሆን ኖሮ በሽኝቱ እለት ሲወርድ ያመሸው እንባ ምን ያህል ከመያዣው ተርፎ በፈሰሰ ነበር፡፡ ሔዋን በሰቀቀን "እየዮ” ስትል አስቻለው በቁጭት "እህህ" ሲል
አፆናኝና ጋባዦቹ ታፈሡ በልዑና መርዕድም ከእጃቸው ላይ መሀረብ ሳይለይ ሌሊቱ ወለል ብሎ ነጋ።
አስቻለው በጠዋት በማለዳ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ዋለና በሶስተኛው ቀን ቀትር ላይ ደግሞ በአይሮፕላን ወደ አስመራ።

👍11
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
...የዛን ዕለት ጠዋት ኢያሱ ቤተመንግሥት እጅ ሊነሳ
ሲገባ ይኽ ሰው እንዲኽ መልከ መልካም ኑራል እንዴ? ያለችው ትዝ አላት።ምናልባትም እኮ እዝጊሃር ሊያመላክተኝ የፈለገው ነገር ይኖራል። ኸለዛ ኸሰው መኻል ስለምን እሱን በእልሜ ያመጣዋል? ነው አለወትሮየ
በእልሜ የመጣው? እያለች፣ አወጣች አወረደች። ተመልሳ ለመተኛት ሞከረች። እንቅልፍ አልወስድ ብሏት ስትገላበጥ ቆየች። ነገሩን የበለጠ
አሰበችበት፤ ከነከናት። እረ ስለምነው እንደዝኸ ለእልም መጨነቄ!ለዳግም ስለዝኸ ጉዳይ ማሰብ የለብኝም እያለች ስታሰላስል ነጋ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢያሱን ከሐሳቧ ማውጣት አቃታት። ጭንቅላቷ
ከእሱ ሌላ ማሰብ ተሳነው። ይኸ ሰው እኮ የጃንሆይ እት ልዥ ነው።
እንዴት ሁኖ ነው ኸሱ ጋር ሰውስ ምን ይላል? ይቅርብኝ ይኸ ነገር፡
አግባብ ማዶል። የጃንሆይ አጥንት ይወቅሰኛል። ለስሜም ለልዥም
ክብር ተገቢ ማዶል። ልዝም ቢሆን ሲያድግ ያባቴ ክብር ተነካ
ብሎ መቀየሙ አይቀርም፡፡ አምላኬ ምነው እንደዝኸ ያለ መፈታተኛ ሰጠኸኝ? እያለች አምላኳን ሞገተች።
የራሷን ፍላጎትና የሰዉን አመለካከት ስታወዳድር፣ ስታመዛዝን፣ስትጨነቅ፣ ልቧ ሲማስን ወራት አለፉ። ኢያሱ፣ መጥቶ እንደወትሯቸው
እንዳይጫወቱ ምክንያት እየሰጠች ከቤተመንግሥት እንዲርቅ አደረገችው። ውስጧ ለሚንቀለቀለውም ስሜት ልጓም ልታበጅለት ፈለገች። ኅሊናዋ አንዴ ሲከሳት፣ ሌላ ጊዜ ሲፈርድባት፣ አንቺ የቁስቋሟ፡
ይኸን ነገር ኸልቤ አውጭልኝ እያለች ማርያምን ተማፀነች።
ልቧ ግን ወደ እሱ አዘነበለ። የፍቅርን ዕርከን እያዘገመ ወጣ። እንደ እምቡጥ ጽጌሬዳ ራሱ የፈነዳና የአበበ ንፁህ ፍቅር በውስጡ ሰረፀ። በሠራ አካላቷ ተበተነ፣ ዐዲስ ሕይወት በመላ ሰውነቷ ውስጥ አንሰራራ፣
የጎደለው ልቧ ሞላ።
ኢያሱም ቢሆን አጎቱ ከሞቱ በኋላ፣ ቤተመንግሥት አዘውትሮ
መምጣቱ አለነገሩ እንዳልሆነ ገባት። የእሱም ልብ መዋለሉን ተረዳች።ከሰው መሀል ዝምታው ሲያነጋግራት፣ ዐይኖቿ የፍቅር ግብር ሲልኩ፣ገፅታው ጥያቄዎቿን ሲመልስላት ልቧ ከልቡ እንደተጣመረ አወቀች።
ኅሊናዋ መሞገቱን ተወ። ጭራሽ ገፋፋት፤ አሻፈረኝ፣ ባህልና ሥርዐት አያግደኝ በይ አላት።
የወደደ የተሸሽገን አያጣውም እንዲሉ፣ ኢያሱን ለብቻው እልፍኟ
ማስጠራት ጀመረች። ሲመጣ፣ እንደ ማንኛውም ሰው ማውራትና
መጫወት ትፈልጋለች። ዘውዷን አውርዳ፣ ካባዋን ወርውራ፣ እቴጌ
ሳትሆን ሰው ሆና ትጠብቀዋለች።
መስተዋት ፊት ስትቆም፣ ዕድሜ አካሏ ላይ ያመጣውን ለውጥ
ለመፈተሽ ወደ መስተዋቱ ስትጠጋ፣ ያቺ ቋራን ስትለቅ ዐዲስ የፈነዳ አበባ የመሰለችው ወጣት ዛሬ ዕድሜ ሰውነቷን ሞልቶ፣ አካሏንና አእምሮዋን አዳብሮ በውበት ላይ ውበት አክሎላት ገና የደረሰ ፍሬ መምሰሏ አልታወቅ ይላታል። ግንባሯን ፈታ፣ ጨምደድ አድርጋ፣ ወደ መስተዋቱ ጠጋ፣ ራቅ ስትል ያሉትም የሌሉትም መስመሮች ይታይዋታል። እህል በልቶ የሚያውቅ የማይመስለውን ወገቧን ወደ ጎን፣ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እያለች ትመለከትና ያች የቋራዋ ጉብል ኣልመስል ትላታለች፡፡
ያን ሰዐት ግዝየ ሌባ ነው ትላለች።
ኢያሱን ለብቻው ማግኘት ስትጀምር፣ ወሬው ከቤተመንግሥት ባለሟሎች ሹክሹክታ አልፎ መሣፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ካህናቱ፣ ሊቃውንቱና
ወይዛዝርቱ መሃል፣ ብሎም ሕዝቡጋ ደረሰ፤ “እቴጌ ኸባላቸው እት ልዥ ጋር ወዳጅነት ያዙ” እየተባለ ተናፈሰ።
ምንትዋብ ግን ወሬውን ከቁብም አልቆጠረችው።
ጭራሹን ከኢያሱ ጋር በድብቅ ተጋቡ። ጐንደሬዎች “ምልምል
የሚል ቅጽል ስም... የተመረጠው ለማለት... አወጡለት። ምንትዋብ
ምልምል እንዳይሉት ግራዝማች አለችው። ግራዝማች ኢያሱ የሰጣትን ዐዲስ የተገኘ ነፃነት ወደደችው። በልጅነቷ ቤተመንግሥት ገብታ ሕይወቷ በወግ ታጥሮ ቆይቶ አሁን እንደ ተራ ሰው መወደድ እናት መወደድ መቻሏ ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ሰጠው።
አንድ ቀን ግን ይህንን ትርጉም የሚገዳደር፣ ነፃነቷን የሚያውክ ነገር ተፈጠረ። ጠዋት ላይ እልፍኟ ተቀምጣ በሐሳብ ዥው ብላለች፤ ከፊሉን ጊዜ ስለ ኢያሱ፣ ከፊሉን ጊዜ ደግሞ ስለ ግብር አዳራሽ ግንባታ ታስባለች።
ዋና የእልፍኝ አስከልካዩ አርከኤድስ ለጥ ብሎ እጅ ነሳና፣ “አንድ መነኩሴ ኸነማይ መልክት ይዤ መጥቻለሁ ብለው በር ላይ ናቸው።
የውጭ በር ላይ አላስገባ ብለዋቸው መመላለሳቸውን ብሰማ፣ ግቢ እንዲገቡ አርጌ አነጋገርኳቸው። 'ስመላለስ ከረምሁ፣ ብዙም ተጉላላሁ።
አገሬ መመለሻ ግዝየ በመጉላላት አለፈ። ለእቴጌ በእጅ ስጥ ተብየ
ይዤ የመጣሁትን መልክት እንዴት አድርጌ ይዤ መለሳለሁ እያልሁ
ኸዝሁ ከረምሁ እያሉ ቢጨነቁ ይጠብቁ ብያቸው መጣሁ” አላት።
“ኸነማይ?” አለች፣ ምንትዋብ ተገርማ። ከነማይ ማን መልዕክት
ሊልክላት እንዲሚችል መገመት አቅቷት።
“አዎ... ዘመድ ልኮኝ ነው አሉ። የተጠቀለለ ነገር ይዘዋል። “ለእቴጌ በጃቸው በቀር ለሌላ እንዳትሰጥ ብለው አስምለውኝ ነው ያመጣሁት ይላሉ።”
የማናቸው መነኩሴ? እያለች ትንሽ ካሰበች በኋላ፣ “ይግቡ!" አለችው።
አዛዥ አርከሌድስ እጅ ነስቶ ወጣ። ጥቂት ቆይቶ በእሱ መሪነት
ቆብ የደፉ፣ ረጅምና ሰፊ ቀሚስ ያጠለቁ፣ ሽማግሌ ሰው ገብተው
መሬት ሊስሙ ሲያጎነብሱ፣ “ግድ የለም አባቴ ይቀመጡ” አለቻቸው፣ ምንትዋብ።
ፈንጠር ብለው ወንበር ላይ ተቀመጡ።
“አባቴ ኸየት መጡ? ደሞስ ማን ልኮዎት ነው የመጡ?” አለቻቸው። መነኩሴው ከተቀመጡበት ተነሥተው ለጥ ብለው እጅ ነሱ። “እቴጌ ዝናዎን ስሰማ ቆይቸ ዛሬ እርሶን ለማየት ያበቃችኝ ኪዳነ ምረት
ምስጋና ይግባት። እቴጌ ኸነማይ ነው የመጣሁ። ደፈጫ ኪዳነ ምረት ስለት ነበረኝና እሱን ላደርስ መኸዴ ነው ብየ ስነሳ አንድ ኸኛ ዘንድ ሚመላለሱ ሰው፣ '
እኼን ለእቴጌ እንደምንም ብለው አድርሱልኝ። ዐደራ በእጅ ይስጡልኝ። ዘመድ ነኝ ቢሉኝ አመንኳቸው።”
“ሰውየው ማን ይባለሉ?”
“እቴጌ ዕቃውን ሲያዩ ማን እንደሆንሁ ያቃሉ ብለውኛል” ብለው ጥቅሉን አሳዩ።
ምንትዋብ፣ አርከሌድስን፣ “ተቀበልና ፍታው” አለችው።
“እቴጌ ኸርሶ በቀር ለሌላ አትስጥ ተብያለሁ” አሉ፣ መነኩሴው፣
ብድግ ብለው።
“ይቀመጡ... ይስጡትና እኔ ፈታዋለሁ።”
ጥቅሉን ለአርከሌድስ ሲሰጡት ተቀብላ ስትፈታው ዐራት ማዕዘን
እንጨት ላይ የተሣለ የራሷ ምስል ነው። ነጠላ ተከናንባ ወፍታ ጊዮርጊስ ደጀሰላም ላይ ነው። መብረቅ የመታት ያህል ክው ብላ ቀረች።
መነኩሴው የፊቷን መለዋወጥ አይተው ደነገጡ። ከተቀመጡበት
ተነሱ። “እቴጌ... ክፉ ነገር ኑሯል?” ሲሉ ጠየቋት።
የለ፣ ደግ ነው። ብቻ ያልጠበቅሁት ነገር ሁኖብኝ ነው። የላክሁ
ሰውየ ስማቸው ማነው ነበር ያሉኝ?”.
ስማቸውን ስንኳ አላወቅሁም። እኔ ብዙ ግዝየን ኸሰው ስለማልገናኝ
ስለሰዎች እምብዛም አላውቅም። 'እነማይ ለጉዳይ መጠቼ፣ ጐንደር“
ይኸዳሉ ሲሉ ብሰማ ተላኩኝ ብየ ነው። ለእቴጌም ዘመድ ነኝ። የእቴጌ አያቶች እኮ ትውልዳቸው ኸዝሁ ኸኛው ዘንድ ነው ቢሉኝ ምን ከፋኝ ብየ ይዤ መጣሁ።”
“ወደ እነማይ በቅርቡ ይመለሳሉ?”
“ለርሶ መልክቴን ካደረስሁ እንግዲህ ነገ እነሳለሁ።”
“እንግዲያማ ደሕና ግቡ። ለላኩዎም ሰው ባክዎን ወደ ጐንደር ብቅ ይበሉ። እንደርሶ ያለ ሠዓሊ ፈልጋለሁ ይበሉልኝ” አለቻቸው።

👍8
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
....ከዚህ በፊት መፅሀፌ " እምቢ
ሲለኝ፣ አንተን አባርሬ ምን ነበር የማረገው መሰለህ?»
«ከመፅሀፍሽ ጋር የምትታገዪ ነበር የሚመስለኝ»
ተሳስተሀል። በየቀኑ ከምሳ በኋላ ማርሰይ እወርድና፡ ከሰአት
በኋላውን፣ ማታውን፣ አንድ አራት አምስት ወንድ ተኝቶኝ፣ ወደ
እኩለ ሌሊት ላይ ድክም ብሎኝ ወደ ኤክስ እመለሳለሁ:: በቀን
በቀኑ ይህን አረጋለሁ። አንድ ቀን ልሄድ ስዘጋጅ ፃፊ ፃፊ ይለኛል፡፡
መፃፍ እጀምራለሁ፡፡ ወንዶቹ በቁኝ ማለት ነው። በፊት እንዲህ ነበር
የማረገው
«አሁንስ?»
“አሁንም ላደርገው ተነሳሁ። ማርሰይ ወረድኩ። ግን ምንም
ሳላረግ ተመለስኩ።
«ወንዶችሽ እምቢ አሉሽ?»
በጉሮሮዋ ውስጥ ቅንዝረኛ ሳቋን እየሳቀች
“ትቀልዳለህ?» አለችኝ ተለውጬ ነው እንጂ። ወንድ መሄድ
ሱስ መሆኑ ቀረ»
«ሱስ መሆኑ ቀረ እንጂ መደረጉ ግን አልቀረም፣ እ?»
«መደረጉማ ለምን ይቀራል? የስሜት ደስታ አይደለም እንዴ?»
ይህን ጊዜ ቤቷ ልንደርስ አንድ መቶ ሜትር ያህል ቀርቶናል፡፡
ታሻሽው የነበረውን እጄን ለቀቀችና
ማን ይቅደም?» ብላ ትታኝ ሮጠች፡፡ እንዳልቀድማት ብዬ
ጫማዬን በሀይል እያስጮህኩ ተከተልኳት። እሷ እየጮኸች፣ እኔ
እየሳቅኩ ቤቷ ጋ ስንደርስ፣ በሩን ቀድማኝ በእጇ ነካችው
ቀደምኩህ!» አለችና በሩን ተደግፋ ቁና ቁና ስትተነፍስ፣
ጉንጮቿን በእጆቼ ይዤ ግምባሯን ሳምኳት እንደዚህ ለዋውጠኸኝ፣ በኋላ ያላንተ እንዳት ልሆን ነው?»
አለችኝ፡፡ በሀይል አሳዘነችኝ፡፡ ሆዴ ሽምቅቅ አለ፡፡ ወደኔ አስጠግቼ
ራሷን እየደባበስኩ ውይ የኔ ቆንጆ! እንድተውሽ አትፈልጊም እንዴ?» አልኳት
«አልፈልግም አልፈልግም አልፈልግም!» እያለች በጣም
ተጠጋችኝ፡ ራሷን አንገቴ ውስጥ ሸሸገች፡፡ እምባዋ አንገቴን ነካኝ
«እኔም ልተውሽ አልፈልግም፣ የኔ ቆንጆ፣ አልተውሽም፡፡
እስከመቼም አልተውሽም፡፡ ምንም ቢመጣ አልተውሽም» አልኳት
«እፈራለሁ፡፡ ካንት መለየቱን ሳስበው እፈራለሁ፡፡ አንተ አገርህ
ትሄድና፣ ከዚያ በኋላ አንገናኝም። እስከመቸም አላይህም፡፡ በቃ
ለዘለአለም?! ውይ! እቀፈኝ! እቀፈኝ!. . . መኖር እንዴት አስቸጋሪ
ነው!»
«አይዞሽ አንለያይም፣ የኔ ሲልቪ»
«አንለያይም?»
«አንለያይም። አይዞሽ አታስቢ። አሁን እንግባ»
አልጋ ውስጥ ላዬ ላይ አደረግኳትና፣ ጀርባዋንና አንገቷን
ጭንቅላቷን እየደባበስኩ ብዙ ጊዜ ከቆየን በኋላ፤
«አሁን ተለያይተን በወድያኛው ህይወት የምንገናኝ እንኳ
ቢሆን፣ ምናልባት እችለው ነበር» አለችኝ ግን መለያየቱ ለዘለአለም
ቢሆን፡ አንድ ጊዜ አይህና ከዚያ በኋላ ለዘለአለም ለዘለአለም
እስከመቸም የማንተያይ ስንሆን፣ በጣም ያስፈራኛል!» ብላ ተጠመጠመችብኝ
«አይዞሽ እንለያይም»
«አንለያይም?»
በሩ ተንኳኳ። ድንግጥ አለች
«አይዞሽ አይዞሽ»
በሩ እንደገና ተንኳኳ
«ማነው በይ» አልኳት
«ማነው?» አለች ጮክ ብላ
«ባህራም!»
ድንጋጤዋ ወደ ብሽቀት ተለወጠ። እየተነጫነጨች ተነስታ የሌሊት ካፖርቷን ራቁት ገላዋ ላይ ጣል አርጋመቀነቱን እየታጠ
ቀች ሄዳ በሩን ከፈተች
ባህራም «ይቅርታ በዚህ ሰአት ስላስቸገርኩ» እያለ ገባ። ጥቁር
ሙሉ ሱፍ ልብስ፣ ውሀ ሰማያዊ ሸሚዝ፣ ደማቅ ሰማያዊ ክራቫት::
ፂሙን ተላጭቶ፣ ፀጉሩን ወደ ኋላ አበጥሯል፡፡ ከጎንና ከጎን የበቀለው
ሽበት' የእርጅና ምልክት መሆኑ ቀርቶ ልዩ ጌጥ መስሏል፡፡ የድል
አድራጊነት ፈገግታ የሚጨፍርበት ፊቱ ወጣትነት ተላብሷል መጥቶ የተጋደምኩበት አልጋ አጠገብ ወምበር ላይ ሲቀመጥ
«እንዲህ ዘንጠህ የት ልትሄድ ነው? » አልኩት
ሲልቪ መጥታ ከጎኔ አልጋው ውስጥ ገባች
«እገሬ መግባቴ ነው» ከለ
“ልሰናበታችሁ ነው የመጣሁት»
«መሄድህ ነው በቃ?» አለችው ሲልቪ
“አዎን"
«ቆይ ዊስኪ ላምጣልህ» ብላ፣ ከአልጋው ወጥታ ወደ ወጥ ቤት
ሄደች፡፡ ቶሎ ከኪሱ አንድ ወረቀት አውጥቶ፣ ወምበር ላይ
የተሰቀለው ኮቴ ኪስ ውስጥ ከተተና፣ በሹክሹክታ
«ለብቻህ አንብበህ ቅደደው » አለኝ
"ላንተም ላምጣልህ? » አለች ከወጥ ቤቱ
«ለኔም ላንቺም አምጪ» አልኳት
ይዛ መጣች። ከልጋ ውስጥ ገባች። ዊስኪውን አነሳሁና ባሀራምን
«መልካም ጉዞ!» አልኩት
ፉት አልን
«ከመሄዴ በፊት ጥቂት ልነግርህ የሚገባኝ ነገር አለ» አለኝ።
ሲልቪ ትታን ልትሄድ ስትል «ካንቺ የሚደበቅ ያለበት አይደለም»
አላት
«እሺ» አልኩት
ብዙ ልነግርሀ በፈቀድኩ። ግን አብዛኛው የኢራን ኮሙኒስት
ፓርቲ ምስጢር ነው፡፡ አንተን አምንሀለሁ፡፡ ግን ፓርቲው
እንድነግርህ አይፈቅድልኝም»
«ይገባኛል፡፡ ምንም መናገር የለብህም»
«አውቃለሁ፡፡ ሁለት ነገር ብቻ በጠቅላላ ባጭሩ ልንገርህን
«ሁለት አመት ሙሉ በይሩት ነበርኩ፡፡ ግን ዩኒቨርሲቲው
ውስጥ የህክምና ትምህርት አልተማርኩም፡፡ ሌላ ስራ ነበረኝ። በቅርብ ምስራቅ ውስጥ ያሉትን የኢራን ኮሙኒስቶች ሳደራጅ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደሞ ከሻህ ሰላዮችና ከሲ.አይ.ኤ ጋር ረዥም ጦርነት ስናካሂድ ነበር። ሲ.አይ.ኤ ሊገድለኝ ሲሆን ጊዜ፣ ቱዴህ (የኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ) እንድሸሽ አዘዘኝ። ወደ ኤክስ መጣሁ። እውነተኛ ስሜን
ልነግርህ አልችልም፡ ግን ባህራም አይደለም። ባሀራም ከፍሻር
በይሩት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ህክምና ይማር ነበር። በሱ ስም የውሽት ፓስፖርት አውጥቼ ነው፡፡
«ቤቶችህ ይህን ያውቃሉ?»
«ታላቅ ወንድሜ ያውቃል። ስም በቀየርኩ ቁጥር አዲስ ስሜን
በደብዳቤ ነግረዋለሁ፣ ከቤት ገንዘብ ሲመጣልኝ እሱ በአዲሱ ስሜ እየላከው ነው፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር አለኝ የምነግርህ»
ምን?»
«ደጋግመህ መልክህ የኢራንን ሻህ ይመስላል ብለኸኛል።
እውነትክን ነው:: ሻህ የስጋ ዘመዴ ነው»
አጭር ዝምታ
«ላሳየኸኝ ጓደኝነትና ለዋልክልኝ ውለታ ላመሰግንህ አልችልም፡፡
ስለዚህ ሳላመሰግንህ መሄዴ ነው» አለኝና ተነሳ፡፡ በቁሙ ዊስኪውን ጨልጦ፣ ብርጭቆውን ኮሞዲኖ ላይ አኖረው:: ልሸኘው ካልጋ ልነሳ ስል
«አትነሳ። ማኑ እዚህ ውጭ ይጠብቀኛል። አብረኸኝ ብትመጣ
ያለቅስብኛል፡፡ እሱ ሁልጊዜ እንደተጠነቀቀ ነው። ወዴት በኩል
እንደምንሄድ አንተ'ንኳ እንድታውቅ አይፈልግም» ይስቃል፡፡ ማኑን
ስለሚወደው ይስቅበታል። ከማኑ ጋር ለመሆን በመቻሉ እጅግ ደስ
ብሉታል፡፡ ወጣትነቱን እንደገና አግኝቷል። እጄን ዘረጋሁ:: ጨበጠኝ። በኔ በኩል ተንጠራርቶ ሲልቪን ሳማት። ሊሄድ ወደ በሩ በኩል ከዞረ በኋላ
«ለመሆኑ አልኩት ዞረ። ፊቱ ላይ ፈገግታ የለም፡፡ የኢራንን ሻሀ ይመስላል።አፍንጫው ትልቅ ነው
«ለመጀመሪያ ጊዜ
ሳገኝህ ሶስት አሜሪካኖች
ይዘውህ ሊደበድቡህ መጀመራቸው ነበር» አልኩት
“A bas les Yankecs!” አለኝ እየሳቀ
“A bas!" አልኩት
ሰአቱን አየ፡፡ ቸኩሏል
“ሊደበድቡህ ይዘውህ ሳለ፣ ማኑ ያስተማረሀን የመከላከል ዘዴ
ለምን አልተጠቀምክበትምን» አልኩት
«ተማሪዎች ይሁኑ ወይ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ይሁኑ እርግጠኛ አልነበርኩም። ምናልባት እኔን ፍለጋ የመጡ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች ቢሆኑስ? ያን አይነት ያምባጓሮ ዘዴ ማወቄን ካወቁ ባህራም አለመሆኔን ይጠረጥራሉ። ለዚህ ነው:: በሎ ደህና ሁኑ። ማኑ ይጠብቀኛል»

👍30🥰1👏1😁1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...የማሪየስ አባት በየሁለትና ሃ'ስት ወር ፓሪስ ከተማ እየመጣ ልጁ
ከአያቱ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ያየዋል:: የገባውን ቃል አፍርሶ ስለሆነ የሚያየው ሰው እንዳያየው ተጠንቅቆ ከአሳቻ ሥፍራ በመደበቅ ነበር ልጁን የሚያየው።
ማሪየስ እንደማንኛውም ልጅ ትምህርት ቤት ገብቶ ይማራል። የታወቀ ጎበዝ አስተማሪ ከቤት ተቀጥርለት ትምህርቱን በሚገባ ይከታተላል: ኮሌጅ ከጨረሰ በኋላ የሕግ ትምህርት ለመከታተል ከሕግ ትምህርት ቤት ገባ፡፡
ለአያቱ ብዙም ፍቅር የለውም:: የአያቱ፡ አሽሙርና ንቀት ልቡን አቁስሎታል፡፡የወላጅ አባቱ ጉዳይ ግን ዘወትር ያሳስበዋል:: ልጁ በተፈጥሮው ጨዋ ረጋ ያለ ፤ በራሱ የሚተማመን ኩሩ ልጅ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ፈሪሃ
እግዚአብሔር ያደረበት ነው፡፡ በ1827 ዓ.ም ማሪየስ የአሥራ ስምንት ዓመት ወጣት ነው:: አንድ ቀን ማታ አያቱ ከነበሩበት ክፍል ሲገባ ደብዳቤ በእጃቸው ይዘው ደረሰ፡፡
«ማሪየስ» አሉ መሴይ ጊልኖርማንድ ነገ ጠዋት ወደ ቬርኖን ትሄዳለህ፡፡»
«ለምን?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ::
«አባትህን ለማየት::»
ማሪየስ ደነገጠ፡፡ አንድ ቀን ከአባቴ ጋር እገናኛለሁ የሚል ሀሳብ
በእውኑም ሆነ በሕልሙ አስቦት አያውቅም:: ምንም ነገር ከዚህ ይበልጥ አስደንጋጭና ያልተጠበቀ ሊሆንበት አይችልም ነበር፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ ስለነበረው የፖለቲካ አቋም የተቃውሞ አሳብ
ሊኖረውም እያቱ እንደሚሉት አባቱ የቡርዥዋን አገዛዝ የሚቃወም
የማይረባ ወታደር» ነው:: በዚህ የተነሣ ለአባቱ የነበረው ፍቅር ይህን ያህል አልነበረም:: ከዚህም በላይ ወላጅ አባቱ እርሱን ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠቱ ጭካኔ ስለመሰለው ጠላው:: «አባቴ አይወደኝም» ሲል አምነ።
ይዞ በዚህ እንዳለ በዚያች ቅጽበት ያልጠበቀው ጥያቄ ከአያቱ ስለመጣዐበመደንገጡ የአዎንታም ሆነ የእምቢታ መልስ ለመስጠት አልቻልንም። አያቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡
«አባትህ ታሟል መሰለኝ፤ ሊያይህ ይፈልጋል::
በሚቀጥለው ቀን ጀምበር ልትጠልቅ ስትል ማሪየስ ክሼርኖን ከተማ ደረሰ በመጀመሪያ ያገኘውን ሰው «የመሴይ ፓንት መርሲ ቤት የት እንደሆነ ያውቃሉ?ሲል ይጠይቃል::
ተጠያቂው ቤቱን ያውቅ ኖሮ አመላከተው:: ከቤቱ ሲደርስ በሩን
በመደብደብ አንኳኳ፡፡ አንዲት ሴት በሩን ከፈተችለት::
«መሴይ ፓንትመርሲ አሉ?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ::
ሴትዮዋ ደንግጣ መልስ ሳትሰጠው ዝም ብላ ቆመች::
«አሉ እንዴ?» ሲል እንደገና ጠየቀ፡፡
ለመኖሩ ግምባርዋን ወደ ላይ በመግፋት አረጋገጠችለት::
«ላነጋግራቸው እችላለሁ?»
እንደማይቻል ጭንቅላትዋን በመነቅነቅ ገለጸችለት::
«እኔኮ ልጃቸው ነኝ» አለ ማሪየስ፡፡ «እንደምመጣ ደግሞ ስለሚያወቁ
ይጠብቁኛል፡፡»
«ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቅህም» አለች ሴትዮዋ፡፡
በዚህ ጊዜ አተኩሮ ሲመለከታት ቀደም ሲል ታለቅስ እንደነበር አወቀ።
ወደ አንድ ክፍል ባመለከተችው ጊዜ ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ ክፍሉ
ውስጥ ሦስት ሰዎች ነበሩ፡፡ አንዱ ቆሞአል፤ ሌላው ተንበርክኮአል፡፡ ሦስተኛ ከመሬት ላይ ተንጋልሎ ተኝቷል፡፡ ተጋልሎ የተኛው አባቱ ነው::ከሁለቱ ሰዎች አንደኛው ሐኪም ሲሆን ሌላው ጸሉት የሚያደርሱ ቄስ ነበሩ፡፡
ኵሎኔሉ በጠና ከታመመ ሦስት ቀን ሆኖታል። ወዲያው ሕመሙ
እንደጀመረው ነበር ልጁ እንዲመጣለት በመልክተኛ ደብዳቤ ለመሴይ ጊልኖርማንድ የላከው:: ደብዳቤውን እንደላከ ሕመሙ እየጠናበት ሄደ።
ማሪየስ ቬርኖን በደረሰበት እለት ልጁ ከመድረሱ በፊት «ልጄ አልመጣም?
እሱ ካልመጣ እኔ ሄጄ እገናኘዋለሁ» እያለ ካልጋው ዘሎ ይወርዳል፡፡
ሠራተኞች ሊይዙት ቢሞክሩም ሊይዘት ባለመቻላቸው ከክፍሉ ወጥቶ ከበረዳ ሲደርስ ይወድቃል፡፡ እዚያው እንደወደቀ ሕይወቱ አለፈች፡፡
ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ሐኪም እንዲመጣ ሰዎች ተራራጡ፡፡
ነገር ግን ሐኪሙ ከመድረሳቸው በፊት ኰሎኔሉ ሞተ:: ቄሱም ቢሆኑ ነፍሱ ከወጣ በኋላ እንጂ አስቀድመው አልደረሱም:: ልጁ ግን የደረሰው ዘግይቶ ነው::
ክፍሉ ውስጥ የነበረው መብራት ደብዛዛ ቢሆንም ከኩሎኔሉ ጉንጭ
ላይ ከመሞቱ በፊት እምባ መውረዱ ያስታውቃል፡፡ እንዲያውም እምባው
ጨርሶ አልደረቀም:፡ ያለቀሰው ልጁ በጊዜው ስላልደረሰለት ነበር፡፡
ማሪየስ ሰውዬውን አፍጥጦ ተመለከተው:: ለመጀመሪያና
ለመጨረሻ ጊዜ ነበር አባቱን ያየው:: የአባቱ ዓይኖች ሲገለጡም እርሱ ያያቸዋል እንጂ እነርሱ አያዩትም:: የአባቱ እጅ ተገልጦ ስለነበረ የጦር
ሜዳ ቁስሎቹ ጠባሳ በብዛት ይታያሉ፡፡ ከፊቱም ላይ ትልቅ ጠባሳ አለ፡፡
አባቱ እንደሆነና ሕይወቱ እንዳለፈች ማሪየስ አወቀ፡፡ በድንጋጤ ክው ስላለ
ከነበረበት አልተነቃነቀም:: ያዘነው ሀዘን ወደር አልነበረውም፡፡ እንኳን
የወለደው አባቱ ማንም ሰው ቢሆን እንደዚያ ተዘርሮና ሞቶ ቢያይ በጣም ማዘኑ አይቀርም።
ሀዘን፤ መሪር ሀዘን ከዚያች ክፍል ውስጥ ሰፍኖአል፡፡ ሠራተኛዋ
ከጥግ ቆማ ታነባዋለች፡፡ ቄሱ ይጸልያሉ፤ ግን እየጸለዩ ሲንሰቀሰቁ ይሰማል፡፡
ሐኪሙ ወዲያው፧ ወዲያው ዓይናቸውን በመሐረብ ይጠርጋሉ፡፡ ሬሳውም
ቢሆን የሚያለቅስ ይመስላል::
ሐኪሙ፤ ቄሱ፤ ሴትዬዋ ቃል ሳይተነፍሱ ማሪየስን አዩት:: ከውጭ የመጣ እንግዳ እሱ ብቻ ነው:: ማሪየስ ከነበረበት ትንሽ ነቅነቅ አለ። በጣም እፍረት ተሰማው፡፡ ያደረገውን ቆብ አውልቆ በእጅ ይዞት ስለነበር
ሳይታወቀው ከእጁ አምልጦ ከመሬት ወደቀ፡፡ ነገር ግን በጣም ከማዘኑ የተነሣ ቆቡን እንኳን ለመያዝ አቅም እንደሌለው ለማሳየት እንጂ እውነትም
አምልጦት አልነበረም::
ስለአባቱ የነበረውን አመለካከትና ግምት አስታውሶ ተጸጸተ::
መጸጸት ብቻ ሳይሆን ራሱን በጣም ነቀፈ:: ግን ጥፋቱ የእርሱ ነው? ኰሎኔሉ ወደኋላ የተወው ሀብት አልነበረም:: ከቤቱ ውስጥ የነበሩት እቃዎች ተሽጠው ለቀብሩ የወጣውን ወጪ እንኳን ለመሸፈን አልቻሉም፡፡ሠራተኛዋ አንዲት ወረቀት አግኝታ ለማሪየስ ሰጠችው:: ኩሎኔሉ ከመሞቱ
በፊት የጻፈው ማስታወሻ ሲሆን ቃሉም የሚከተለው ነው፡፡
«ለምወድህ ልጄ ፤ ዋተርሉ ጦር ሜዳ ላይ በተደረገው ጦርነት
ስለፈጸምኩት ጀብዱ የባሮንነት ማዕረግ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ማዕረጉን በደሜ የዋጀሁት ስለሆነ ለልጄ ማውረስ እችላለሁ፡፡ እኔ አሁን ማዕረጉ ይገባዋል
ወይም አይገባውም ብዬ መናገር የለብኝም:: ከወረቀቱ ጀርባ ላይ ኲሉኔሉ የጻፈው ማስታወሻ ደግሞ ‹‹በዚሁ በዋተርሉ ጦርነት አንድ የሃምሣ አለቃ ሕይወቴን አድኖአል:: ስሙ ቴናድዬ ይባላል:: ከፓሪስ ከተማ ወጣ ብሎ
ሞንትፌርሜ ከተባለ ሥፍራ አንዲት አነስተኛ ሆቴል እንደነበረው አውቃለሁ:: ድንገት ካገኘኸው በተቻለህ እርሱን እርዳልኝ» የሚል ነበር፡፡
የአባቱ ፍቅር አስገድዶት ሳይሆን «የሞተን አክብር.» ብሎ በሚገፋፋን ውስጣዊ ኃይል ተመስጦ ማሪየስ ወረቀቱን በኃይል ጨመደደው::
ስለኩሎኔሉ ከዚያ በኋላ የታወቀ ነገር የለም:: ዩኒፎርሙንና
ጉራዴውን መሴይ ጊልኖርማንድ ለውራጅ እቃ ሸማች ሸጡት፡፡ ኰሎኔሉ የተከላቸውን አበቦች ጎረቤቱ ቀጥፈውና አትክልቱን አበላሽተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ድራሹን አጠፉት::
ማሪየስ ለሁለት ቀን እዚያው ቬርኖን ቆይቶ ከቀብሩ ሥነሥርዓት
በኋላ ወደ ፓሪስ ተመለሰ፡፡ ከዚያም የአባቱ መሞት ብዙም ሳይረብሸው ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ ኵሎኔሉ በሞተ በሁለተኛው ቀን ተቀበረ፤ በሦስተኛ ቀን ተረሳ፡፡
ማሪየስ ለጥቂት ቀናት ከኮቱ ኮሌታ ላይ ጥቁር ጨርቅ አደረገ፡፡
የሀዘን ምልክት መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ የተደረገ ነገር አልነበረም::

👍12
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...ለአንዳፍታም ቢሆን እንኳን ቱናትን መለየት ያሸብራል፡ መቼስ እንዲህ የሚያደርገኝ ልጅነቷ ወይም መላመዳችን ወይ ደግሞ ገዳሜ ስለሆነች ብቻ አይመስለኝም፡ ታዲያ ምንድነዉ?
ብቻ ክብድ ብሎኛል፡
ደረስሁ።
ከጨዋታ ይልቅ ለዝምታ የሚያመቸዉን በትላልቅ ሀገር በቀል ዛፎች የተሞላዉን ግቢ፣ በተለያየ ዕድሜ የሚገኙት ሕጻናት ይቦርቁበታል። አንዳንዶች ክብ ሠርተዉ፣ አንዳንዶች በመስመር ሆነዉ፣ ሌሎች ዝብርቅርቅ ብለዉ የልባቸዉን ይጫወቱበታል፡ አለፍ ብሎ ባለዉ ሜዳ ላይ ሰፊ ምንጣፍ ተነጥፎላቸዉ ጨቅላዎች ይንከባለላሉ ከእነሱ በወራት
ዕድሜ ከፍ ያሉት ደግሞ ራሳቸዉን ችለዉ ለመቆም ይዉተረተራሉ
የሕጻናቱ ተንከባካቢዎች እንደየምድባቸዉ የሚቆሙት ቆመዉ፣ ያቀፉት ደግሞ ተቀምጠዉ በየትዕይንቱ ይደሰታሉ።
መሥራትስ እንደ እነሱ ነዉ› አልሁኝ፣ በቅናት።
ሆኖም ሥጋቴ ሊያልፍልኝ አልቻለም: እንዲሁ ከመኪናዬ ወረድሁና ቱናትን ከአልጋዋ አንስቼ አቀፍኋትና፣ የግቢዉ አማካይ የሚሆን ሥፍራ ላይ ቆምሁ፡፡ በየትኛዉ ቢሮ የትኛዉን ሰዉ ማናገር እንዳለብኝ በዓይኖቼ
ወዲያ ወዲህ ስል አንዲት በልተት ያሉ ሴትዮ ቀረቡኝ፡
“እንኳን በደህና መጣችሁ” አሉ፣ ልብ በሚሞላ ፈገግታ እኔንም
ቱናትንም አይተዉ ይበልጥ እየቀረቡን፡፡
“እንኳን ደህና አገኘኋችሁ” አልሁ፣ አንገቴን ወደ ጉልበታቸዉ
በመስበር ለትሕትናቸዉ ጭምር አክብሮት እየሰጠሁት፡
እዉነትም እነ እመዋ ነገሮችን ጨራርሰዉልኝ ኖሮ፣ ማነሽ የሚለኝ ሰዉ ቀርቶ ቅጽ እንድሞላ እንኳን የጠየቀኝ ሰዉ የለም፡ ቀድሜ ያገኘኋቸዉ ሴትዮ ለቱናት የተመደበላትን ማደሪያ ክፍል፣ ክፍሉን የሚጋሯትን
ሕጻናት፣ ያለማስታጎል እንዲከታተላት የተመደበላትን ነርስ፣ የምግቦቿን ዝርዝር መርሐ ግብር፣ልብሶቿን እና ሌሎች ነገሮችን በዚያዉ በማይለዋወጥ ትሕትናቸዉ ከገለጹልኝ በኋላ፣ ሥጋት ወይም አስታያየት
ይኖረኝ እንደሆነ ጠየቁኝ፡፡
“እንግዲያዉ መዋእለ ሕጻናት ብቻ አይደለማ ይኼማ?” አልኋቸዉ:
“ትክክል። ያዉ እንደምታዉቂዉ” አሉ፣ ደጋገሜ አንቺ እንዲሉኝ
የለመንኋቸዉን እንደ ምንም ተስማምተዉልኝ፡ “ያዉ እንደምታዉቂዉ አብዛኛዉ የማኅበራች አገልጋዮች ሌት ከቀ ሥራ ላይ ናቸዉ። በዚህም
የተነሳ ለልጆቻቸዉ በቂ እክብካቤ ለማድረግ ይቸገራሉ። ይኼ የሕጻናት መዋያ ከተከፈተ ወዲህ ግን እንደየአገልግሎት ጸባያቸዉ፣ ሙሉ ኃላፊነቱን ለእኛ ለመተዉ የተፈቀደላቸዉ አገልጋዮች አሉ: ሥራቸዉ ፋታ የሚሰጣቸዉ ያሉ እንደሆነ ግን ኃላፊነት የም ወስድላቸዉ ወይ ቀኑን ወይ ማታዉን ብቻ ይሆናል ማለት ነዉ” አሉኝ፣ ቱናትን ባዘጋጁላት
አልጋዋ ላይ እያሳረፏት፡
“ታዲያ” አልሁኝ፣ ከሁሉም ቅድሚያ ለቱናት የሚበላ እንዲሰጡልኝ ለመጠየቅ እንደገና እየዳዳሁ የአንገት ሰላምታ በርቀት ሰጥተዉኝ ከነበሩት ሴቶች አንደኛዋ፣ የልቤን አዉቃልኝ ይሁን የቱናትን ቡዝዝ ማለት አይታ እንደሆነ እንጃ፣ ትኩስ የሥጋ ፍትፍት አመጣችላት። ደቀቅ
ያለዉን የሥጋ አመታሮ በቀይ እንጀራ ፈትፍታ አምጥታ ስታጎርሳት እኔ ምራቄን ብዉጥም፣ቱናት ግን እምቢ አለች: ለማጫወት ብትሞክራት ሁሉ ለማልቀስ ተነፋነፈች።
“ግድ የለም” አሉ፣ ባልቴቷ። “ግድየለም፤ እንግድነት ተሰምቷት ነዉ። ትንሽ ትፋሽ ትዉሰድና እኔ አጫዉቼ አበላታለሁ”
“አይ አልሁኝ፣ ሥጋቴን መደበቅ እያቃተኝ፡
“ግድ የለሽም”
“እንዲያዉ ዛሬ እምብዛም ሳትበላ ነዉ የዋለችዉ”
“ሐሳብ አይግባሽ፤ አጫዉቼ አበላታለሁ”
“እንግዲህ ምን እላለሁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ከማለት በቀር አልኋቸዉ ኹለቱንም፣ ስለ በጎ አድራጎታቸዉ፡
"ተዪ ተዪ: እኛ ነን ማመስገን ያለብን: እንኳንም እግዚአብሔር ልዩ አድርጎ የሰጠሽ ልጅሽ እንድናገለግላት ዕድሉን ሰጠሸን”
“አይ… እንዲያዉ ወድጄ እንኳን አይደለም ያመጣኋት: ልጄ ከብዳኝ ወይ ደግሞ ከእሷ የሚበልጥብኝ ሥራ ኖሮብኝም አይደለም”
“ይገባኛል”
“የሆነዉ ሆኖ እንግዲህ ከኹለት ወይ ከሦስት ሰዓት በላይ
አላስቸግራችሁም”
“ማስቸገር? የለም የለም: ለእሷ ከምናደርግላት ይልቅ፣ እሷ ለእኛ
የምታደርግልን ይበልጥብናል። ከባሪዎቹ እኛዉ ነን''
“ይሁን” ብዬ፣ ወጣሁ።
ለቅሶዋን ከኋላዬ እየሰማሁ፣ እንደ ምንም ጨክኜ ወጣሁ ወደ ጦር ሜዳ እየኼድሁ እንደሆነ ነዉ የሚሰማኝ፡ ከወንድሞቼ እና
ከእህቶቼ፣ በተለይም ከጃሪም ጋር ፊት ለፊት እስከምገጥም ቸኩያለሁ።እሱም ቢሆን ሌላ ምንም ምርጫ አልተዉልኝም፡፡
‹ምን ይሉት ፍርጃ ነዉ ግን? ኧረ እንደ ዋዛ የት ነዉ የደረስነዉ
በማርያም? እያልሁ እንዲችዉ እንደ ተብሰለሰልሁ፣ በአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ዋናዉ ግቢ በኩል ባለዉ ቁልቁለት ወረድሁ።
ለነገሩ ለምን በእነሱ ብቻ እፈርዳለሁ? ጥፋቱ የራሴም ጭምር አይደል?እነሱ ሆኑብኝና ተለማመጥኋቸዉ፡ የእኔ በሕይወት መኖር በእነሱ ፈቃድ እስኪመስል ድረስ ግፊያቸዉን ሁሉ ቻልሁላቸዉ᎓ የጃሪም ወንድምነት
ቢቀርብኝ እሞት ይመስል፣ ያለ ጥፋቴ ጭምር ማረኝ ማረኝ አልሁት።
ቆይ፤ እዉነት ግን አልሞትም? ያለ ጃሪም ወንድምነት፣ ያለ እህቶቼ
እህትነት ምንድን ነኝ እኔ?
ወደ ማኅበራችን ሕንጻ የሚያደርሰኝን መንገድ እንደ ተያያዝሁት፣ የዛፍ እና የንብ ሽርክና በልቡናዬ ክችች አለብኝ፡፡
ሠራተኛዋ ንብ ለማኅበረ ንቧ የሚሆነዉን ምግብ ለመቅሰም አበባ ወዳለው ዛፍ ታርፋለች:: ከአበባዉ ላይ የምታገኘዉን ዕጩ ማር ከቀሰመች በኋላ ተጨማሪ ፍለጋ ወደ ሌላ ባለ አበባ ዛፍ ትሄዳለች: ነገር ግን ከዛፋ
በምትነሳበት ጊዜ፣ የአበባዉ ወንዴ ዘር በጸጉራም አካሏ ላይ ተሳፍሮ ይከተላታል። ወደ ቀጣዩ የአበባ ዛፍ በምታርፍ ጊዜም፣ ያ ከዚያኛዉ ዛፍ ያመጣችዉ ወንዴ ዘር፣ እዚህኛዉ ዘንድ ካለዉ የአበባዉ ሴቴ ዘር ጋር ይገናኛል፡ በዚህም ምክንያት፣ ንቧ ምግቧን ፍለጋ ከዛፍ ዛፍ ባረፈች
ቁጥር፣ የአበባ ዛፎች እንዲራቡ ታደርጋለች ማለት ነዉ ንብ ያለ አበባ ማለት እንግዲህ ያለ ምግብ፤ አበባም ያለ ንብ ማለት ደግሞ ያለ መራባት ስለሆነ ተከላክለዉ አያዉቁም:: እርስ በእርስ ቢከላከሉ፣ አንዳቸዉም መኖር እንደማይችሉ ኹለቱም ጠንቅቀዉ ያዉቁታል።
ስለዚህ ንብ እና አበባ አይለማመኑም:: አለመለማመን ብቻም ሳይሆን፣ ነፍሳቸዉ እስኪገባ ድረስ ይዋደዳሉ
እንደ እዉነቱ፣ እኔና ጃሪምም ሆንን ከሌሎች እህትና ወንድሞቻችንም
ጋር ግን፣ አበባና ንብ ብቻ አይደለንም፡፡ ወይ ንብ እና ንብ፣ ወይ አበባና አበባ ነን፡ ያዉም ወይ የአንድ እናት ንብ እናት አበቦች ነን፡፡ እንዲያዉ እሱም አጉል ሆኖ ቢፈርስ ግን፣ ቢያንስ ንቦች፣ ወይ ደግሞ የአንድ እንደ አበባና ንብ እንኳን መሆን እንዴት ያቅተናል?
የእኔም እጅ አለበት፡፡
አዎ፣ አለበት!
እኔ ያለ እነሱ መኖር እንደማልችል ብቻ እንጂ፣ እነሱም ያለ እኔ መኖር
እንደማይችሉ ነግሪያቸዉ አላዉቅም አበባ የንብን ጥቅም ባያዉቅ ኖሮ አያከብረዉም: የማያከብረዉን ደግሞ የሚወድ የለም፡ መናቅን እንጂ፣በእጄ ነሽ፣ ብለቅሽ ያልቅልሻል፣ ተሸከምሁሽ፣ በደልሽኝ ማለትን እንጂ
እንደ'ኔ ማለትን ያስተዋል፡፡ እህትነቴ እንዲተናነቃቸዉ፣ እነ ጃሪም እዚህ እንዲደርሱ የእኔም ሚና አለበት፡፡
“የት ናት?” አልሁት ባልቻን፣ ከራሴ ጋር እንዲህ እየተዋቀስሁ ወደ
ሲራክ ፯ ማዕከል ደርሼ ቢሮዉ ዉስጥ ያገኘሁት ከኹለት ሰዎች ጋር እየተነጋገረ ቢሆንም፣ ምንም ሳይመስለኝ፡

👍31👏2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
..."ባርባራ ” አለች ሚስዝ ሔር " " የዛሬ ቀን ደስ ማለቱን አየሺው ?”
አዎን በጣም ደስ የሚል ቀን ነው እማማ "
“ ወጣ ብዬ ብመለስ የሚሻለኝ መሳለኝ "
“ በርግጥ ይሻልሻል እማማ !ቶሎ ቶሎ ብትወጭማ ኖሮ ጥቅሙን ታውቂው ነበር ቀኑ እንደ ዛሬ ጥሩ ሲሆን መውጣት ጥሩ ነው ”
“ አባትሽ ከጓሮ አለና እስኪ ይመቸው እንዶሆነ ጠይቂው "
ዳኛው ሔር ከፊት ለፊት የነበረውን አታክልት እየጎበኘ በትእዛዙ መሠረት ያልተሠራውን ለአትክልተኛው ለብንያም ያሳያል " ብንያም ሠረገላ ነጅ የፈሬሶቹ
ባልዶራስ ከመሆኑም ሌላ ከዚያ በሚተርፈው ጊዜም በአትክልተኝነት ይሠራል "
ትዳር አለው ማልዶ በመግባትና አምሽቶ በመጣት ከሠራበት እየተመግበ ! ከራሱ ቤት ይኖራል ጀስቲስ” ሔር ሰው ሠራሽ ጠጉር አጥልቆ የቤት ልብስ ለብሶ
በብንያም እየተቆጣ ሳለ ባርባራ ደረሰች " ከሦስት ልጆቹ ውስጥ አባቷን ደፈር የምትል እሷ ነበረች ሆኖም እንደ ሌሎቹ ባትርበተበትም አጠግቡ ደርሳ በአክብሮት ፍርሃት ቆመች "
“ አባባ ! ”
“ ምን ፈለግሽ ? አላት ግዙፍ ሰውነቱን በማዞር "
እማማ ወጣ ብላ ነፋስ ለመቀበል ትፈልጋለች " ሠረገላ ትፈቅድልናለህ ?”
ዳኛው መልስ ከመስጠቱ በፊት ሰማዩን ቀና ብሎ አየና “ወዴት ለመሔድ ትፈልጋለች ? አለ "
“ ወደ ሱቅ ብቅ ብለን አንዳንድ ነገችን ለመግዛት እንፈልጋለን ከዌስትሊን አንወጣም "
ሚስተር ሔር በሣሩ ውስጥ እየተንጐራደደ ወደ ምግብ ቤቱ ሔደና መስኮቱን ገፋ አድርጐ ከፍቶ ' ' ዛሬ ወደ ሱቅ ለመሔድ ፈለግሽ እንዴ አን ? አላት "
“ እኔ የግድ ዛሬ አላልኩም ” አለችው እየፈራች - “ምን ጊዜም ሊሆን ይችላል " ሠረገላውን የማትፈልገው ከሆነ ግን ፡ቀኑ ሞቃት ስለሆነ ትንሽ ወጣ ብዬ ልመለስ ፈልጌ ነበር " በዚያውም ባርባራ የበጋ ልብሷን ትገዛለች « ”
“ እሷ ሁልጊዜ ልብስ እንደ ገዛች ነው !” ብሎ አጉረመረመ "
“ ኧረ አባባ ! እኔ . . .
ዝም በይ እመቤቲቱ የሚያስፈልግሽ እጥፍ አለሽ ”
“ ምናልባት ሠረገላውን ካልፈቀድክልኝ በእግሬም ቢሆን ቀስ ብዬ ትንሽ ከሔድኩ በኋላ ሲደክመኝ መመለስ እችላለሁ " "
ከዚያ ሳምንት ሙሎ አልጋ ለመያዝ ነው !? በእግር ዌስትሊን ደርሶ መመለስ ? ዕብዶት ነው ” አለና እሺም እምቢም ሳይል መስኮቱን ዘግቶ ወደ ቤንጃሚን ተመለሰ "
" ባርባራ... አባትሽ ሠረገላውን ወዴት ሊሄድበት አስቧል? አለች ሚስስ ሔር
ማንንም መቃወም ዐመል ብሎት ነው እንጂ እሱስ የትም የሚሔድ አይመስለኝም " በእግርሽ መሔድ የምትችይ ይመስለኛልስንመለስ በኪራይ ሰረግላ እንመጣለን።
በርግጥ በእግሬ መሔድ እችላላሁ " አባትሽ ሳይፈቅድ ግን ለመሞከር
አልቃጣውም "
ባርባራ በመስኮት ስትመለከት ቤንጃሚን ያትክልት መሣሪያዎቹን ሰብስቦ አስቀምጦ ጋጦቹ ወደ ነበሩበት ወደ ቤቱ ጀርባ ሲያመራ አየችው " በዚህ ጊዜ በአቋራጭ ሮጣ ቀዶመችውና አባባ በሠረገላ እንድትወስዶን ያዘዘህ ነገር አለ ቤንጃሚን ? ” አለችው "
“ አዎን አንቺንና እሜቴን ዌስትሊን አድርሺ እንድመልሳችሁ ታዝዣለሁ
አላት " እንደገና ተመልሳ የደስ ደሱን ለናቷ ነገረቻት " ከዚያም እህል መሳሪይ አቅርባ ትንሽ አቀመስቻትና ተሣፍረው ሚስተር ሔር በነበረበት በኩል ሲያልፉ ምስጋናዋን በፈግታ ገለጸችላት እሱም “ ልብ በይ ለራት ሰዓት እንድትደርሱ ባርባራ ደግሞ ብዙ ገንዘብ እንዳታጠፉ ተጠንቀቁ ” አላት ከዚያ መንገዳቸውን ቀጠሉ
ዌስትሊን ደርሰው ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ፊት ለፊት ከነበረው የጨርቃ ጨርቅ ሱቅ አጠግብ አቁመው ሠረገላውን ከዚያ ትተውት ገቡ "
ከሱቅ ገብተው ሲመርጡ ሲያገላብጡ ' ዋጋ ሲወጋወጉ አንድ ሰዓት ያህል ከቆዩ በኋላ ሚስዝ ሔር ቦርሳዋን አጣችው "
“ ከሠረገላው ውስጥ ትቸው ሳይሆን አይቀርም ... ባርባራ- ሔደሽ ብታመጭልኝሳ የኔ ልጅ ? የሐሩ ናሙናም ከውስጡ ነው ያለው "
ባርባራ ወጥታ ሔደች ሠረገላው ቤንጃሚና ጸጉረ ለስላሳው አሮጌ ፈረስ ፀጥ ብለው ይጠብቃሉ " ባርባራ በዐይኗ ፈልጋ ቦርሳውን ስታጣው አሽከርዮው አዘዘችው።
የእማማን ቦርሳ ፌልገው ቤንጃሚን ከሠረገላው ውስጥ አንዱ ጋ ተወሽቆ ይሆናል።
ቤንጃሚን ከመቀመጫው ወርዶ መፈለግ ጀመረ " ባርባራ በመንግዱ ቁልቁል እየተመለከተች ትጠብቃለች " ፀሐይዋ በጣም ደምቃለች " አንድ ሰውዬ በድንጋይ ንጣፉ መንገድ ይንሸራሸራል " በሰደሪያው የተጋደመው ወፍራም ሰንሰለትና
ከሱ ጋር የተያዙት ልዩ ልዩ ጌጦች hፀሐይዋ ጨረር ጋር ይንቦጋቦጋሉ የሸሚዙ የወርቅ ቁልፎችም ለብቻቸው ያበራሉ " ጓንቲ ባላጠለቀው እጁ ሪዙን ሲያሻሽ የእጁ ንጣት ከሩቅ ይታያል በተለይ ደግሞ ጣቱ ላይ የሰካው ያልማዝ ቀለበት ያንጸባርቃል ባርባራ ወንድሟ ሪቻርድ የነገራትን የዚያን ጌጣጌጥ ወዳድ ሰዬ ነገር ትውስ አላት።
ሲጓዝ ተመለከተችው " ዐይኑና ጸጉሩ ጥቁር ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ዕድው በኻያ ሰባትና ስምንት የሚገመት መልከ መልካም ጐበዝ ነበር ከፍል "ከፍየል ቆዳ የተሠሩ ብጫ ብጤ ጓንቲዎች አንዷን ከግራ እጁ አጥልቋል ሌውን ቀስ ብሎ እያፏጨ በመተከዝ ሲያወዛውዝ አየችው ደማቅ ፀሐይ ባይኖር ኖሮ ባርባራ የወርቁ
ጉጥ አታየውም ወይም ከዚያ አሳዛኝ ምስጢር ጋር በልቧ አታዛምደውም ነበር "
እንዴ ቶርን አንተነህ እንዴ ? እስቲ ወዲህ ተሻገር !
ከመንገድ ወዲያ ማዶ ሆኖ የተናገረው ኦትዌይ ቤተል ሲሆን የተጣራውም ያን በልዩ ልዩ ፈርጥ ያጌጠውን ጎበዝ ነበር » ሰውየው ግን በሐሳብ ተውጦ ስለ አልሰማው እንደገና ጮኽ ብሎ ጠራው ።
“ ካፒቴን ቶርን !
አሁን ሰማውና ራሱን በአዎንታ ነቅንቆ መንገዱን ተሻገረ ባርባራ ሕልም ውስጥ ያለች መሰላት አንጎሏ ' ልቧ ' ሐሳቧ ' አንድ ላይ ተቀላቀሎባት
“ ቦርሳው ይኸውና ሚስ ባርባራ " በሠረግላው የሥጋጃ እጥፋቶች | ውስጥ ገብቶ አገኘሁት " አለና ቤንጃሚን ወደሷ ሲዘረጋላት ልብ አላለችውም » የሆሊጆንን እውነተኛ ገዳይ ማየቷን ያለ ጥርጥር ስለ አረጋገጠች ከዚህ ጉዳይ ውጭ የሆነውን ነገር ሁሉ ረስታዋለች በሁለመናው ሪቻርድ ከነገራት ገለጻ ጋር ተስማማላት"
ረጅም ' በጣም ነጭ ያልሆነ መልከ መልካም ' እጀ ለስላሳ በጌጣ ጌጥ የተንቆጠቆጠና . . . ስሙ ደግሞ ካፒቴን ቶርን ! እሱ ለመሆኑ ምንም አልተጠራጠረችም ፊቷ ባንድ ጊዜ ተለዋወጠ " ልቧ ያለ መጠን ዘለለ
“ ቦርሳው ይኸው ሚስ ባርባራ !” ደገመ ብንጃሚን።
ባርባራ ቤንጃሚንን ከነቦርሳው ጥላው ሔደች » የቀዶ ጥገና ሐኪሙን ሚስተር ዌይንራይትን ከሩቅ አየችውና ወይሱ በረረች
ሚስተር ዌይንራይት . . . ያ ከኦትዌይ ቤተል ጋር የሚነጋግር ሰው ይታይዎታል . . . ማነው ?”
ሚስተር ዌይንራይት ' መልስ ከመስጠቱ በፊት መነጽሩን ከአፍንጫው ቁብ ማድረግ ነበረበት " ምክንያቱም ዐይኑ እሩቅ ነገር አስተካክሎ አያይለትም ነበር «ያ ነው? ካፔቴን ቶርን ይሉታል " የሔርበርትን ቤተሰብ ለማየት የመጣ መሰለኝ "
መኖሪያው የት ነው ? አሁንስ ከየት ነው የመጣው ?

👍16