አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በታደለ_አያሌው

...የጃሪም አወጣጥ በኃይል እየቆረቆረኝ ቢሆንም፣ ደስታዬ ግን ጢም እንዳለ ነዉ።

የመሠረት ድንጋዩ በጳጳሳቱ እና ሌሎች ታላላቅ ስዎች ተቀምጦ ከአበቃና የጉባዔዉ አጋፋሪ ‹ሂዱ በሰላም› ካለን ከብዙ ደቂቃዎች በኋላም ቢሆን፣ ችዬ መነሳት አልቻልሁም ነበር፡ ልጄ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ወደ
ተቀመጠዉ የመሠረት ድንጋይ አስጠግቼ፣ በደስታ እንባዬን ሳወርድ ብዙ ቆየሁ፡ ሁኔታዬን ሁሉ እመዋ በሩቁ ስትመለከት ኖሯል መሰለኝ፣ ከእንግዳዉ ጋር መዉጣቷን ትታ ወደ'ኔ መጣች፡

“ደስ እለሽ ዉብዬዋ?” አለችኝ፣ ወደ እቅፏ እየሳበችኝ፡፡

“በጣም!” አልኋት፣ እንባዬን በቀሚሷ እያበስሁ

“እሰይ! እንኳ ንም ደስ አለሽ ልጄ”

“እንደ ዛሬዉም ደስ ብሎኝ አያዉቅ”

“እኔም” አለችኝ፣ ወደ አንገቷ ሥር ጠበቅ አድርጋ እየሳበችኝ ቀና ብዬ
ሳያት፣ እዉነትም ተጫጭኗት የነበረዉን እርጅና ሳይቀር ድል ነስታዉ ታየችኝ: ግንባሯ ላይ በተደረደሩ መስመሮች ሁሉ ደስታ ሲፈስ አየሁ በጣም ደስ ብሏታል። ይኼ ደስታዋ የኔንም ደስታ የትና የት አደረሰዉ።

“የቱናት እናት” አለ ባልቻ፣ እንግዳዉ ቀለል እስከሚልለት ድረስ ሲሸኝ ቆይቶ ወደ እኛ እየመጣ፡ የእሱም ፊት ከእኛ በሚስተካከል ደስታ ተጥለቅልቋል ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አነሳትና የመሠረት ድንጋዩ አናት ላይ ጉብ አደረጋት: “ይኼን ወደ መሰለ ሥፍራ ስጠራት እንዲያ
እንዳልተግደረደረች፣ ደስታ እንዴት እንደሚያደርጋት አየሽልኝ አይደል
ይቺን እናትሽ?” አላት፣ ቱናትን በስስት እየተመለከታት

የመሠረት ድንጋዩ ላይ ከነአልጋዋ ያደረግናትን ቱናትን ለረዥም ጊዜ
ከብበን ከቆየንና፣ ለዚሁ ደስታችንም ወሰን ልናበጅለት ከሞከርን በኋላ እኔና ባልቻ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ከግራ እና ከቀኝ ይዘን ወደ ባልቻ
መኪና ተሳፈርን

“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ከሀገር ርቀን የምንጓዝ ይመስል አቅፋ እየተሰናበተችን፡

“አብረሽን አትሄጅም ወይ እመዋ? ዉቤ እኮ ወደ ሲራክ እየተመለሰች
ያለችዉ ከዓመት በኋላ ነዉ። መቼም በዚህ አንድ ዓመት ዉስጥ
በማዕከላችን የተለዋወጠዉ ነገር ሁሉ እያየች እንደ ጀማሪ ጎብኚ
ይኼ ደግሞ ምንድነዉ እያለች በጥያቄ ማስቸገሯ አይቀርም: ብቻዬን እችላታለሁ ብለሽ ነዉ?” አለ ዓይኖቹን በእኔ፣ በእመዋ እና በቱናት ላይ እያንከባለለ፡፡

“ወደ ሲራክ ነዉ እንዴ የምንሄደዉ?”

“አዎ ምነዉ?” አሉኝ እኩል፣ ድንግጥ ብለዉ፡ ደግሞ ልትለመንብን ነዉ› ብለዉ ነዉ መሰለኝ፣ በቅጽበት አመዳቸዉ ቡንን አለ

“እሺ”

“እኮ! እንዳንቺም በሕጋችን የቀለደበት ሰዉ የለም: እንዲያዉ የቱናት እናት መሆንሽ አተረፈሽ እጂ፣ አንቺስ ደህና አድር ገዉ ቢቀጡሽ ሁሉ የምታጸድቂ ወንጀለኛ ነሽ” አለኝ፣ እንደ መሳቅም በእፎይታ እንደ
መተንፈስም ብሎ፡

“ታዲያ እኔ እምቢ ብዬ ነወይ? ልብ ካላችሁ መቅጣት ነበራ” አልሁት፣ የቱናትን ልብስ እያስተካከልሁ

“ይቀርልሽ መስሎሻል!”

“ቆይ ምን አጥፍቼ ነዉ ግን?”
ያልሰማኝ መስሎ ፊቱን አዞረብኝና፣ እመዋን እንደገና ተሰናበታት፡ እኔም እንደ'ሱ የመኪናዉን መስታዎት ዝቅ አድርጌ ልሰናበታት ስል፣ ሆነ ብሎ
መኪናዉን አንቀሳቀሰብኝ፡፡

“ አየሽልኝ አይደል ምቀኝነቱን እመዋ?” አልኋት፣ ልክ እንደ በባቡር ተጓዥ እጄን እያዉለበለብሁላት፡

እሷን ተለይተን መንገድ ከጀመርን በኋላ፣ ቅድም ያልሰማ መስሎ
ያለፈብኝን ጥያቄዬን እንደገና አነሳሁበት

“እ፣ በል ገረኛ”

“ምኑን?”

“ብቀጣበት የምትጸድቁበትን ጥፋቴን ነዋ”

ፍርጥም ብሎ ጥርሶቹን ገለጠልኝ፡

“እዉነት ጥፋትሽ ጠፍቶሽ ነዉ አንቺ? ሌላዉ ቢቀር፣ አንዲት የሲራክ አባል ብትወልድም እንኳን ፈቃዷ ምን ያህል እንደሆነ አጥተሽዉ ነዉ?”

“ወይ ጉድ… እኔስ አሁንም ወደ ሲራክ እየሄድሁ መሆኑ ደንቆኛል”

ቱናትን ከወለድሁ፣ በተለይም ኋላ በሕክምናዎቿ ጊዜ ያለፈችበትን አበሳ ካየሁ በኋላ፣ ወደ ሲራክ ፯ እመለሳለሁ አላልሁም ነበር፡ እንኳንስ እስከዚህ ድረስ፣ ገዳሜን ከገደምሁበት የእመዋ ቤት አንድም ርምጃ ንቅንቅ የምል አይመስለኝም ነበር፡ ዛሬ ግን ባልቻ ገና ‹እንሂድ› ሲለኝ፣
‹እሺ› ብዬ ከመከተል በቀር ምንም ያሳሰብኝ ነገር የለም፡

በዚህ ሁኔታ ከዋናዉ የማኅበራችን ሕንጻ ደርሰን፣ ጥብቁን እና ረዥሙን የሲራክ ፯ መንገድም አልፈን ከመጨረሻዉ በራፍ አጠገብ ስንደርስ ድንገት ቆመ፡፡ ጭራሽ እንደ መቅለስለስ ብሎ አየኝ፡፡ ይኼ አስተያየቱ
ነበር ቀድሞዉንም እኔን እና እሱን በሌላ ያስጠረጥረን የነበረዉ፡፡ ግራ ገብቶኝ አየሁት፡ በሩ ደግሞ ሲጠም፣ እኛ መሆናችንን አዉቆ በራሱ ጊዜ እንደ ቀድሞዉ ይከፈትልናል ብዬ ብጠባበቀዉም፣ ክርችም እንዳለ ቀረ፡

ምነዉ” አልሁት፣ ዓይን ቢያበዛብኝ፡ “ኧረ አባትዮ፣ እንዴት እንዴት እየሆንህ እንደሆነ ታዉቆሃል ግ?”

“እንዴት እንዴት ሆንሁ?”

“ለራስህ አይታወቀህም?''
መቅለስለሱን ተከትሎ፣ በዚያዉ ሐሳብ ገባዉና፣ ቁዝም ብሎ ቆየብኝ፡

“ምንድነዉ ጉዱ፣ የማትነግረኝ?”
“እንዳትቆጪኝ ፈራሁ እንጂ”

“እንዳትቆጪኝ?”ፈራሁ

“ለእሷ የምትሆኚዉን ሳይ፣ ትንሽ ፈራሁ”

“ማናት ደሞ እሷ?”

ልጅሽ፣ ቱናት” አለኝ፣ የቱናትን አልጋ የያዘ እጄን እያስለቀቀብኝ፡ እሱዐበአንደኛዉ ጎን፣ እኔ ደግሞ በሌላኛዉ ጎን ሆነን ነበር በየእጃችን የያዝናት አሁን ግን የመፈልቀቅ ያህል እጄን አስለቅቆ ለብቻዉ ወደ እቅፉ ወሰዳት አድራጎቱ ሊገባኝ ባይችልም፣ ባልቻ ነዉና ሰዉየዉ ልጄን አትንካብኝ ብዬ ልከላከለዉ አልቻልሁም፡ ትንፋሼን ዉጬ
መጨረሻዉን ጠበቅሁት፡፡ በእርግጥ፣ ደግሞ ሌላ የምሥራች
የተዘጋጀልኝም መስሎኝ ራሴን ለደስታ እያመቻቸሁ ነበር የለመደች ጦጣ አሉ!

“በቃ ዉቤ፤ በቃ ቱናትን ወስጄብሻለሁ” አለ፣ ስለ ራሱ ንግግር ራሱ ሐፍረት እየተሰማዉ፡፡

"እ" አልሁት፣ በግንባሬ፡ ብቻ ያንን የመሰለ ደስታ እንዳይከስምብኝ፡
ዓይኔን በልጥጬ በግርታ አየሁት፡

“አዎ”

“ኧረ አባትዮዉ ተዉ አታስቀኝ” ብዬ፣ እንደ ምንም ጥርሴን ለመግለጥ ሞከርሁ: ሳቄን የሚጋራኝ መስሎኝ ሳቅ ብርቃቸዉ የሆኑት ጥርሶቹ እስኪገለጡ ብጠብቅም፣ እሱ ግን ክርችም እንዳለ ነዉ አሁንም:

“እየቀለድህብኝማ አይደለም: ነዉ እንዴ?”

“በፍጹም! ከእሽቴ ጋርም ተመካክረበታል: ለማኅበራች
ሊቀመንበርም አወያይቼዋለሁ:: ያዉ እመዋንም ቢሆን ጫፍ ጫፏ
አጫዉቻታለሁ: ሁላችንም ጋ ያለዉ ሐሳብ ተመሳሳይ ነዉ''

“ቆይ ቆይ”

“ተዪ ዉቤ: በቃሽ: እዲያዉም ግልጹን ንገረኝ ካልሽኝ፣ ቱናት በዚህ መልኩ የምትጠቅሚያት አይመስለኝም” አለ፣ ቆምጨጭ ብሎ፡ ጭጭ ብዬ ከማዳመጥ በቀር የምሆነዉን እንጃልኝ፡፡

“ስለዚህ ቱናት እየወሰድሁብሽ ነዉ። ከእንግዲህ ቱናትን ለብቻሽ ቤት ዘግተሽባት የብቻሽ ማድረግሽ ይቀርና፣ የሁላችንም ልጅ አድር ገንእናሳድጋታለን። አንቺም ቱናት የምታገኛት እንደ ማናችም አልፎ አልፎ እና ከሥራ ዉጪ ይሆናል ማለት ነዉ። በማኅበራችን የሕጻናት መዋያ ዉስጥ እናስገባት እና እንደ ማንኛዉም ልጅ ጨዋታ እና ግበረ ሕጻናት እየፈጸመች ታድጋለች”

“እንደ ማንኛዉም ልጅ?”
👍27
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


....እሷ ግን፥ከዚህ ሁሉ ሳትደርስ ሚስ ካርላይል የሚጕተመተም ዐመሏ ሲነሳባት ወይ ዝም ብላ ታዳምጣለች " አለበለዚያ ደግሞ በራስ ምታት የሚሠቃየውን
ራሷን በሁለት እጆቿ መኻል ደፍታ ምንም ሳትመልስ ውስጥ ውስጧን እያረረ በሆዷ መቻል እንጂ ለባሏ ስለ ብሶቷ ገልጻለት አታውቅም።

አንድ ቀን በየካቲት ወር ውስጥ አሽከሮች አንድ ስሕተት ሠሩ " ኮርኒሊያ ቀጥታ ሳቤላን ሳይሆን አሽከሮችን ስትሳደብ ስትጮህ ቆየችና ዝም አለች ሁሉም ጸጥ አለ " መንፈሷ ተጨንቆ ተስፋ የቆረጠች መስላ ፍዝዝ ብላ ተቀምጣ የነበረችው ሳቤላ ለራሷ የምትናገር መስላ ሚስ ካርላይል ግን እየሰማቻት « አዬ ! ምነው አሁንስ ቶሎ በመሸ » አለች "

« ለምን ቶሎ እንዲመሽ ፈለግሽ ?» አለቻት"

« አርኪባልድ ወደ ቤቱ እንዲመጣ ብዬ»

ሚስ ካርላይል ደስ የማይል ጉርምርምታ አሰምታ «የደከመሽ ትመስያለሽ .ፈእመቤት ሳቤላ» አለቻት "

« በጣም ደክሞኛል»

« አያስደንቅም " እኔ እንዳንቺ ቀኑን ሙሉ ምንም ሳልሠራ ብውል ለሞት የሚያደርስ ድካም ይይዘኝ ነበር " ሳስበው በሕይወቴ የምቆይ አይመስለኝም " "

« የሚሠራ ነገር እኮ የለም » አለቻት ሳቤላ "

«መሥራት ለሚፈልጉ ምን ጊዜም የሚሠራ ነገር አይታጣም " ለምሳሌ ዝም ብለሽ ከመቀመጥ እነዚህን የገበታ መሐረቦች ስቀመቅም ልትሪጅኝ ትችይ ነበር » አለች ኮርኒሊያ ካርላይል "

« እኔ መሐረብ ልቀመቅም ? » አለች ሳቤላ በመገረም "
« ከዚህ የባሰ ትሠሪ ይሆናል . . እሜቴ » አለች ኮርኒሊያ ካፏ ነጠቅ አድርጋ
« እኔ የዚህ ዐይነት ሥራ አይገባኝም » አለች ሳቤላ ረጋ ብላ
« ሌላውም ቢሆን ካልሞከረው በቀር አይገባወም በበኩሌ እጆቼን አጣጥፌ ከመቀመጥ ጫማ ብሠፋና ባድስ ይሻለኛል " ጊዜ ማባከን ወንጀል ነው "
« ዛሬ እንኳን ጤንነት አልተሰማኝም » አለች ሳቤላ »
« አድካሚ ሥራ መሥራት አልችልም»

« እንደሱ ከሆነ ደግሞ እኔ ብሆን በሠረገላ ወጣ ብዬ አየር እቀበል ነበር ሙሉ ቀን ከቤት ውስጥ ሲጠማረሩ መዋል ለስንኩላንም አይበጃቸውም »

«ግን ባለፈው ሳምንት ፈረሶቹ በርግግው ስለ አስነገጡኝ አርኪባልድ ራሱ ካልነዳ በቀር እንድወጣ አይፈቅድልኝም »

« ጆንም ቢሆን ያንቺን ባል ያህል የመንዳት ልምድ አለው " ፈረሶቹ አንድ ቀን የበረገጉ እንደሆነ ሁለተኛ ይበረግጋሉ ማለት አይደለም በይ አሁንም ጆን
ሠረገላውን እንዲያቀርብልሽ ደውይ " የኔ ምክር ይኸው ነው»

ሳቤላ ራሷን ነቀነቀችና «አይሆንም! በዝጉ ሠረገላ ካልሆነ በቀር ያለሱ እንዳል
ወጣ አርኪባልድ ነግሮኛል " እሱ ስለኔ ብዙ ያስባል " ስለዚህ ፈረሶቹ ቢዶፈደነብሩ እንኳን እሱ አብሮኝ ካለ እንደማልደነግጥ ያውቃል»

« አሁንስ በጣም ሆዶ ባሻ እየሆንሽ ሔድሽ መሰለኝ » አለቻት ኮርኒሊያ "

«ለኔም እየመሰለኝ ነው » ብላ መለሰችላት ሳቤላ « ከወለድኩ በኋላ ደኅና እሆናለሁ እንዳሁን አይጨንቀኝም " ብዙ የሚሠራ ነገር ይኖረኛል »

« ለሌሎቻችንም ብዙ ሥራ ይተርፈናል ብዬ አስባለሁ» ብላ አጕረመረመች ቀና ብላ አዬች
«እንዴ ! ምን ሆኖ ይሆን ? አርኪባልድ መጣ በዚህ ሰዓት ምን
አግኝቶት ይመጣል ? »

« አርኪባልድ ! » አለችና ሳቤላም ሒዳ ጥምጥም አለችበት « አንተን ሳይ ፀሐይ የወጣች ነው የመሰለኝ ፍቅሬ ግን ለምን መጣህ ? »

« በሠረገላ ሽርሽር ልወስድሽ » አላት ደወሎን እየደወለ "

« ጧት አልነገርከኝም »

« ምክንያቱም ለመምጣት መቻሌን አላረጋገጥኩም ነበር . . .ፒተር ! የድንክ
ፈረሶቹን ሠረገላ አምጣልኝ " ፈጠን በል እሱን ነው የምጠብቀው »

« ለምንድነው ? ሠረገላውን ለምን ፈለግኸው ? » አለችው ሚስ ካርላይል ሳቤላ ልብሷን ለመቀየር ስትወጣ።

« ለሽርሽር ትንሽ ወጣ ብለን አየር ተቀብለን ለመምጣት »

« ሽርሽር ? »

« አዎን እስቲ ሳቤላን ተመልከቻት እንደዚህ ሁና እያየሁ አምኜ ያለኔ አላስወጣትም »

«እንደዚህ እየተሆነ ነው ሥራ የሚሠራ በቀን እኩሌታ ሥራ እየጣሎ መውጣት»
አለችው ኮርነሊያ "

« በአሁን ጊዜ ከሥራ የሳቤላ ጤንነት የበለጠ ያሳስባል“ ደግሞ ዲልና ሌሎቹ ጸሐፊዎቼ እኔን ተክተው መሥራት እንደሚችሉ ታውቂያለሽ»

« ጆን ካንተ የተሻለ ሠረገላውን ይነዳ የለ ? »
« እሱም ጥሩ ነጂ ነው" ቁም ነግሩ ግን የሱ መቻል ወይም አለመቻል አደለም» ሳቤላ ለባብሳ ጭንቀቷ ሁሉ ለቋት እየተፍለቀለቀች መጣች " ሚስተር
ካርይል ደግፎ ካሳፈራት በኋላ ' ራሱ እየነዳ ሲሔድ ሚስ ካርላይል ቆማ ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ ቁማ ትመለከታቸው ጀመር።

ሳቤላን የማያስዶስታት ይኸን የመሳሰሉ ብዙ ሁኔታዎች ነበሩ ነገር ግን ከሚስተር ካርላይል ፊት ክፉ ተናግራት አታውቅም » እሱን ሁልጊዜ ብትወርፈውም የለመደው ነገር ነበር » ሳቤላ ግን ከዚያ ንዝንዝ ውስጥ ድርሻዋን የምትቀበል አይመስለውም ነበር "

ወሩ ሚያዝያ ሰዓቱ ማለዳ ነው " ጆይስ ከእመቤት ሳቤላ ካርላይል መልበሻ ውስጥ እጆቿን በጭንቀት እያፋተገች ዕንባዋን በጉንጮቿ እያወረደች ተቀምጣለች በጣም ፈርታ ነበር
የመታመምን ምንነት ደጋግማ ያየች ይሁን እንጂ እንደ ዛሬው የመሰለ ሕመም ግን አጋጥሟት አያውቅም " ጆይስ ተቀምጣ ትጨነቅበት ከነበረው ክፍል ቀጥሎ ሚስዝ ሳቤላ ካርላይል በሕይወትና በሞት መኻል ሆና
ትስቃያለች "

በመተላለፊያው በኩል የሚያስገባው በር ቀስ ብሎ ተከፈተና ሚስ ካርላይል ገባች " በሕይወቷ ዘመን እንደዚያ ተጠንቅቃ በቀስታ ተራምዳ ታውቃለች ለማለት አያስደፍርም » ተደራርቦ በተጠቀጠቀ መደረቢያ ራሷንና ጆሮዋን ሸፍናለች"
ኩምሽሽ ብላ አንድ ወንበር ላይ ተቀመጠች ጆይስ ቀና ብላ ስታያት ፊቷ ልክ ንጋት ጢስ መስሏል"

« ጆይስ » አለቻት በሹhሹhታ
«ያሠጋል? »

« ኧረ የለም ... እሜቴ አይመስለኝም : ማየቱ እንዲህ ከባድ የሆነ ለደረሰበትማ በጣም አስጨናቂ መሆን አለበት »

« እሱ መቸም የጋራችን እርግማን ነው ጆይስ " አንቺና እኔ ግን ከዚህ ዕጣ ጋር የሚያገናኘን መንገድ ባለ መምረጣችን ዕድለኞች ነን » አለችና ትንሽ ዝምአለች »
«አደራውን ከክፉ ይሰውራት እኔ እሷ እንድትሞት ልፈልግም»

ሚስ ካርላይል በጣም ተጨንቃ ቀስ ብላ ነበር የምትናገር ምናልባት ይች ወጣት አዪቷ የሞተች እንደሆነ ጸጸቱ የዕድሜ ልክ የሕሊና ሸክም ሆኖባት እንዳይቀር ፈርታ ይሆናል " እሷ ብትፈልግ ኖሮ አጭሩ የጋብቻ ዘመኗን የደስታና የእፎይታ ጊዜ ልታደርግላት ትችል እንደ ነበር ከባድና የማይወርድ ሸክም ሹክ ይላት እንደሆነ አይታወቅም : በጣም የፈራችና የተጨነቀች ትመስላለች "

« ጆይስ ... እንዲያው የሚያሠጋ ይመስልሻል ? »
«ለምንድነው ስለ ሥጋት የሚያስቡት? ሌሎች እንዴዚህ ታመው አያውቁም እንዴ”

« አይመስለኝም ... ጆይስ የሷ ለየት ያለ መሰለኝ " ለምንድነው
ዶክተር ማርቲን ቶሎ እንዲደርስ
ቴሌግራም ወደ ሊንበራ የተላከ ?»

ጆይስ ከው ብላ ደነገጠች
«ዶክተር ማርቲን ቶሎ እንዲደርስ ? ማን ላክ
«መቸ ተላከበት ? »

« እኔ የማውቀው መልእክት መተላለፉን ብቻ ነው " ሚስተር ዌይንራይት ከጌታሽ ዘንድ ገብቶ ከወጣ በኋላ ጆንን ወደ ዌስት ሊን የቴሌግራም ቢሮ ጋልቦ እንዲሔድ አዘዘው -ፈረሱ ሲጋልብ ኮቴው እንደዚያ ሲጮህ ጆሮህ የት ነበር ? . .

ሲጋልብ ሰምቸ ለምን እንደሆነ ገባኝ " ስለዚህ ፍራት ፍራት አለኝ ሚስተር ካርላይል ዘንድ ሔጄ ብጠይቀው ደግሞ እሱ ምንም እንደማያውቅ ነገረኝና በሩን እፊቴ
ዘጋብኝ "
👍18
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...አሁን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባለው ሚስጥር ላይ ቆሻሻና የሚሸቱ ጨርቆች በሻንጣዎቹ ውስጥ በመክተት ሌላ ሚስጥር ጨመርንበት.

ስለ ሁኔታው አብዝተን ባለማውራታችን ከነገሩ እጅግ አስፈሪ መሆን አመለጥን:
ጠዋት እንነሳና ፊታችን ላይ ውሀ ረጨት እናደርጋለን። ጥርሶቻችንን በባዶ ውሀ እናፀዳለን፤ ጥቂት ውሀ እንጠጣና ትንሽ ወዲያ ወዲህ እንላለን፡ ከዚያ ጋደም ብለን ቴሌቭዥን እናያለን ወይም እናነባለን፡

መንትዮቹ ምግብ ፈልገው ሲያለቅሱ መስማቴ ህይወቴን ሙሉ ልቤ ላይ የሚኖር ጠባሳ አስቀመጠልኝ፡ አያታችንን እንዴት እንደጠላኋት። ያቺ አሮጊት እና እናታችን ይህንን ስላደረጉብን ጠላኋቸው።

የመመገቢያ ሰአታችን ያለ ምግብ ሲያልፍ እንተኛለን፡ ለሰዓታት እንተኛለን::እንቅልፍ ሲወስደን የርሀብ ወይም የብቸኝነት ወይም የምሬት ስቃይ አይሰማንም በእንቅልፍ በውሸት የደስታ ስሜት ውስጥ እንሰምጣለን ከዚያ
ስንነቃ ስለምንም ነገር ግድ አይኖረንም።

እንደ ፈዘዝኩና እንደደከምኩ ጭንቅላቴን ዞር አድርጌ ክሪስንና ኮሪን እያየሁ ነበር ከዚያ ክሪስ ከኪሱ ሰንጢ አውጥቶ የእጁን አንጓ ሲቆርጥ ያለምም
ስሜት ጋደም ብዬ እየተመለከትኩ ነው። የሚደማ እጁን ወደ ኮሪ አፍ አስጠጋና ኮሪ ቢቃወምም እሱ ግን ደሙን እንዲጠጣ አደረገው: ከዚያ የኬሪ ተራ ሆነ ሁለቱ ምንም ነገር ያልበሉ በመሆናቸው፣ የትልቁ ወንድማቸውን ደም ጠጥተው፣ በደበዘዘ፣ በፈጠጠና በተቀባይነት አይን አተኩረው ተመለከቱት።

ማድረግ ባለበት ነገር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰምቶኝ ፊቴን አዞርኩ። ያንን በማድረጉ አድናቆት ተሰምቶኛል። ሁልጊዜ ከባባድ ችግሮችን ማቃለል
ይችልበታል።

ከዚያ ክሪስ ወደኔ አልጋ መጣና፣ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ አይኖቹ ወደተቆረጠው አንጓው ዝቅ
አሉ አሁን መድማቱን አቁሟል። እኔም ደሙን ጠጥቼ ረሀቤን እንዳስታግስ ሌላኛውን ደም ስሩን ለማድማት ሰንጢውን አወጣ እንዳያደርገው ነግሬ ሰንጢውን ቀምቼ ወረወርኩት። ብርታት ለማግኘት ስል የእሱን ደም
እንደማልጠጣ ምዬ ተገዝቼ ብነግረውም መሀላዬን ከቁም ነገርም ሳይቆጥር ሰንጢውን በአልኮል ማፅዳት ጀመረ።

“ተመልሳ ባትመጣ ምንድነው የምናደርገው ክሪስ?" ስል ጠየቅኩት አያታችንን ለሁለት ሳምንት አላየናትም: አይጥ ለማጥመድ ወጥመዱ
ላይ ያደረግነውን ቺዝ የሚላስ የሚቀመስ ባጣን ጊዜ በልተን ጨርሰነዋል።ምግብ የሚባል ሳንቀምስ ሶስት ቀናችን ሆኗል፡ መንትዮቹ እንዲጠጡት
የተውንላቸው ወተትም ካለቀ አስረኛ ቀን ሆኖታል።

“በረሀብ አትገድለንም” አለ ክሪስ አጠገቤ ተኝቶ በደካማ ክንዱ እያቀፈኝ። “እሷ ያንን እንድታደርግ ከፈቀድንላት ደደቦች ነን ማለት ነው ነገ ምግብ ይዛ ካልመጣች ወይ ደግሞ እናታችንም ብቅ ካላለች አንሶላ ተልትለን መሰላል
እንሰራና ወደ መሬት እንወርዳለን” አለ፡

ጭንቅላቴ በደረቱ ላይ ስለሆነ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል። “ምን እንደምታደርግ ታውቃለህ? ስለምትጠላን እንድንሞት ትፈልጋለች። መወለድ የማይገባን
የሰይጣን ልጆች መሆናችንን ስንት ጊዜ ነው የነገረችን?

ካቲ፤ ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ደደብ አይደለችም: እናታችን ካለችበት ከመምጣቷ በፊት ምግብ ይዛ ትመጣለች::”

የተቆረጠ እጁን ላሽግለት ተንቀሳቀስኩ ከሁለት ሳምንት በፊት እኔና ክሪስ ለማምለጥ መሞከር ይገባን ነበር። የዚያን ጊዜ ሁለታችንም ጥንካሬ ነበረን
አሁን ብንሞክር ግን በእርግጠኝነት ወድቀን እንሞታለን፡ መንትዮቹን
በጀርባችን አዝለን ከሆነ ደግሞ የበለጠ ከባድ ይሆንብናል።

በማግስቱ ጠዋት ምንም ምግብ እንዳልመጣ የተመለከተው ክሪስ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል እንድንሄድ አስገደደን፡ እኔና ክሪስ ለመራመድ እጅግ ደክመው
የነበሩትን መንትዮች ተሸከምናቸው የመማሪያ ክፍሉ ጥግ ላይ ስናስቀምጣቸው አቅማቸው ስላልቻለ እንደመተኛት
እያሉ ግድግዳውን ተደግፈው ቁጭ አሉ። ክሪስ መንትዮቹን ጀርባችን ላይ የምናስርበትን ገመድ እያዘጋጀ ነው

“በሌላ መንገድ እናደርገዋለን” አለ ክሪስ እንደገና እያሰበ “በመጀመሪያ እኔ እሄዳለሁ መሬት ስደርስ ኮሪን ታስሪውና ቀስ እያልሽ ወደታች ትለቂዋለሽ
ቀጥሎ ኬሪንም እንደዚያው ታደርጊያለሽ: በመጨረሻ አንቺ ትመጫለሽ ስለ እግዚአብሔር ብለሽ የምትችይውን ጥረት ሁሉ አርጊ! አደጋ በሚደርስበት
ወቅት ከፍተኛ ንዴት ከሰው በላይ የሆነ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ሰምቻለሁ።"

“አንተ የበለጠ ጠንካራ ስለሆንክ እኔ መጀመሪያ ልሂድ” አልኩት በድካም ስሜት “አይሆንም! ድንገት ፈጥነው ከመጡ ለመያዝ ታች መሆን አለብኝ ያንቺ ክንዶች የኔን ያሀል ጥንካሬ የላቸውም: ክብደቱ ሁሉ አንቺ ላይ
እንዳይሆን ገመዱን ጭስ መውጫው ላይ አስርልሻለሁ እና ካቲ ይvህ የአደጋ ጊዜ ነው!”

በአይጥ መያዣ ወጥመዱ ላይ አራት የሞቱ አይጦችን በድንጋጤ ተመለከትኩ።“ትንሽ ጥንካሬ እንድናገኝ እነዚህን አይጦች መብላት አለብን፡” አለ ኮስተር ብሎ፡ “ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን::''

እነዚያን የሞቱ ትንንሽ ወፍራም ነገሮች በመጠየፍ እየተመለከትኩ “ጥሬ ስጋ? ጥሬ አይጥ? አይሆንም!" አልኩ በቀስታ:
በጣም ተናዶና አስገዳጅ በሚመስል አይነት መንትዮቹንም ሆነ ራሴን በህይወት ለማቆየት የሚያስፈልገውን የትኛውንም ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ነገረኝ፡ “ተመልከቺ ካቲ፣ መጀመሪያ እኔ ሁለቱንም እበላለሁ ገመዶቹን
በደንብ ለመቋጠርም የልብስ መስቀያ ስለሚያስፈልገኝ ላምጣ… ታውቂያላሽ ኬቲ እጆቼ አሁን በደንብ አይሰሩም” አለ፡

ሁላችንም በጣም ከመድከማችን የተነሳ የምንንቀሳቀሰው የግዳችንን ነው::

አየት አደረገኝና “በእውነት አይጦቹ በጨውና በበርበሬ በጣም የሚጣፍጡ ይመስለኛል” አለ፡፡

ጭንቅላታቸውን ቆርጦ ቆዳቸውን ገፈፈና አንጀታቸውን አወጣው: ትንንሽ ሆዳቸውን በመሰንጠቅ ረጃጅምና ቀጫጭን አንጀቶቻቸውን እንዲሁም ትንንሽ
ልቦቻቸውንና ሌሎች የውስጥ እቃዎቻቸውን ሲያወጣ እየተመለከትኩት ነበር ሆዴ ባዶ ባይሆን ኖሮ ሊያስመልሰኝ ይችል ነበር።

ክሪስ ጨውና በርበሬ ሊያመጣ ሲሄድ አይኖቼ ቆዳቸው ተገፍፎ ለምግብነት የተዘጋጁት አይጦች ላይ ተተክለው ቀሩ። አይኖቼን ጨፍኜ የመጀመሪያውን
ጉርሻ ለመጉረስ ሞከርኩ እርቦኛል ግን ይህንን ለመብላት የሚያክል አይደለም ረሀቤ።

ወዲያው እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ግንባራቸውን አጋጥመውና አይናቸውን ጨፍነው ጥጉ ላይ የተኙትን መንትዮች አሰብኩ በእናታችን ማህፀን ውስጥም እንደዚህ ተቃቅፈው የነበሩ ይመስለኛል: ምስኪን ልጆች! በአንድ ወቅት በጣም የሚወዷቸው እናትና አባት ነበሯቸው።

እነሱን በደህና መሬት ለማድረስና ከጎረቤት ምግብ ለማግኘት አይጦቹ ለእኔና ለክሪስ በቂ ጥንካሬ እንደሚሰጡን ተስፋ አድርገናል።

ክሪስ ቀስ እያለ ወደኛ ሲመለስ ሰማሁ። በሩ ላይ ቆም ብሎ አመነታ።ሽራፊ ፈገግታ እያሳየ ነው ሰማያዊ አይኖቹ ወደኔ እየተመለከቱ አንፀባረቁ።
በሁለት እጆቹ በደንብ የምናውቀውን ትልቅ የሽርሽር ቅርጫት ይዟል። ቅርጫቱ መክደን እስከሚያስቸግር ድረስ በምግብ ተሞልቷል ሁለት ትልልቅ
ፔርሙዞች አወጣ አንደኛው ውስጥ የአትክልት ሾርባ፣ ሌላኛው ውስጥ ወተት ነበረበት በማየው ነገር ግራ ተጋባሁ። እናታችን አምጥታልን ነው?
ከሆነ ታዲያ ለምን ወደታች እንድንሄድ አልጠራችንም? ለምንስ ደግሞ እኛን ፍለጋ ወደዚህ አልመጣችም?
👍252👏2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡

‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡

ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡

‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡

ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››

ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡

የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡

ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡

ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡

‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡

‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?

‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡

‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››

ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::

‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››

‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡

‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››

‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡

ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡

ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡

‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡

አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡

‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››

“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››

‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::

ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:

በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።

ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡

ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡

የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡

አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡
👍16
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የንጋት ፀሐይ ከወደቀችበት ተነስታ ብርሃኗን ሐመር
ላይ ፈንጥቃለች፡ ካርለት ከወሮ መንደር ሆና ቁልቁል የሐመርን ተፈጥሮ ደኑን የልጃገረድ ጡት መስለው በሰማዩ ደረት የተሰካኩትን የአለሌ  ኤሎ ኤዲ ቢታ… ተራራዎች ስታይ
የምትሆነው ጠፋት ልብ ሰራቂው ተፈጥሮ አነሆለላት እና! ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ወደ ተፈጥሮ ሮጠች ተፈጥሮም ወደ እሷ ገሰገሰች ተቃቀፉ.. አንዱ የሌላውን ሽፋን አወለቀ… አየሩን ሳመችው... መሬቷን አቀፈቻት... ቅጠሉን ሰበሰበችው…ከወፎች ጌር
ሽቅብ ጎነች… ዳመናውን እየበረቃቀሰች በረረች የተፈጥሮ ፍቅር

የሐመር ተፈጥሮአዊ ሕይወት እንደ ቅንቡርስ በውስጧ ገብቶ በሰራ
አካላቷ ተንከላወሰባት ! እንደ እንበሶች ቦረቀች….. ፈነደቀች ከማራኪዋ ተፈጥሮ ጋር እየደጋገመች ተወሳሰበች…..

እንዲህ በደስታ ሰክራ በድካም ጥንዝል ዝርግትግት ብላ
ሳሩ ላይ እንደተንጋለለች የሰው ድምፅ ሰማች፡፡ 'ምን ነበረበት ከእንደዚያ ካለው ዓለም የማይመለሱ ቢሆን!'

ካርለት!

“አቤት" አለች ዞር ብላ እያየች ካርለት፡፡ “ጎይቲ ነይ
እስኪ አጠገቤ ቁጭ በይ"

“ይእ! ምነው እስካሁን ሳትጠይቂኝ ቀረሽ?''

“ምን ብዬ ጎይቲ?

"ይእ! አሁን እውን እሱ የሚረሳ ሆኖ ነው፡ ናፍቆትሽን ውስጥሽ ቀብረሽ ደብቀሽኝ እንጂ…" ያ ሐጫ በረዶ መሳዩን ችምችም
ያለ ጥርሷን እያሳየቻት ጠየቀቻት፡፡

“ደልቲን ነው! ምን ብዬ ልጠይቅሽ? ወሮ እንደማይኖር
አውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ሄጀ ላየው እፈልጋለሁ  ናፍቆኛል!"

ጎይቲ ናፍቆኛል የሚለው አባባል የእሷንም እሳት
ጫረባት ወዲያው ገለባው ልቧ ቦግ ብሎ ነደደ፡

“ይእ! ካርለቴ አያ ደልቲ እኔንም ናፍቆኛል ግን የት ሄጄ ላግኘው" ብላ እንባዋ እንደ በጋ ዝናብ የመጣበት ሳይታወቅ ዥጉድጉድ ብሎ ወረደ፡፡ የሳግ ብርቅታ የውስጣዊ ስሜት
ነጎድጓድ… ጎይቲን ደፈቃት፡፡ ካርለት ደነገጠች ደስታዋ በኦንድ ጊዜ ሙሽሽ አለባት፡፡

“ጎይቲ ምን ሆነ? ካርለትን ጩሂ ጩሂ ብረሪ ብረሪ
አሰኛት፡፡ ጎይቲ ግን ካርለት የጠቀቻትን አልሰማችም! በአይነ ህሊናዎ ጀግናዋ እየተንጎማለለ ሲጓዝ አየችው፡፡ ስታየው አቅበጠበጣት ልቧ ዳንኪራ ረገጠባት… ሊርቃት ሆነ፤ መጥራት ፈለገች፡፡
ካልጠራችው እየተንጎማለላ ሄዶ ጫካው ውስጥ ገብቶ ይጠፋባታል፡፡

“አያ ደልቲ!” ተጣራች ጎይቲ ጮክ ብላ እንዲሰማት፡፡

ምን ሆነ ደልቲ" ካርለት ጎይቲን እየነቀነቀች ጠየቀቻት ጎይቲ ግን የጠራችው አንበሳዋ ዞር ብሎ የጠራውን ሰው በአይኖቹ ሲፈልግ የጡቶችዋ ጫፎች እየቆሙ ሰውነቷን እየነዘራት ወደ እሱ
ስትጓዝ ድንገት ጀግናው እየተንጎማለለ ጫካ ገባ፡፡ ሮጠች! እንቅፋቱ
መታት እሾሁ በልቧ ተሰገሰገ… ጫካው ደልቲን ሸፈነው ዋጠው
ለለቀጠው... ስለዚህ ድምጿን ከፍ አድርጋ ተጣራች፡

“አያ ደልቲ ጮኸች ጎይቲ፡፡ ካርለት ግን የምትሆነው
ጠፋት፡-

“ጎይቲ- ደልቲ ምን ሆነ?" ካርለት ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት
አቅም አነሳት• ድካሟ አገረሸ፡፡ ጎይቲ ደግማ ደጋግማ አለቀሰች
እውነተኛውን ደም መሳዩን እንባ!

ደልቲ ምን ሆነ ደ-ል-ቲ ካርለት እንባዋ ግድብን ጥሶ ወጣ› ጎይቲና ካርት ተቃቅፈው ልቅሶአቸውን አስነኩት፡፡

“አያ ደልቲ" እያሉ ጮሁ፤ የገደል ማሚቶው ግን
ድምፃቸውንም ደልቲንም ዋጠው…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ለምን አለቀስሽ?" አላት ከሎ ሆራ፡፡ ቲማቲም
የመለለ ፊቷን እያዬ:

እንዲሁ ጎይተን ምን እንደሆነ ደጋግሜ ስለጠይቃት…"አቋረጣት ከሎ፡-

“ጎይቲ ምን አለችሽ ታዲያ?

“ምንም"

“እንግዲያው ለምን አለቀስሽ?''

“እንጃ ክፉ ነገር የደረሰበት መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከማጣራቴ በፊት ግን እንደዚህ መሆን አይገባኝም ነበር ይቅርታ! አለች ካርለት፡

ከዚያ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ፡፡

“ከሎ አንተ ግን ለምን አትነግረኝም?"

“ምኑን?

“ስለ ደልቲና ስለ አጋጠመው ሁሉ፡፡"

ካርለት ምን ብዬ ልንገርሽ? ጎይቲ እንደዚያ መሄጃ
መቀመጫ አሳጥታኝ መኪናዋን አስተኛሃት! እያለች ወትውታኝ
ካለረፍት ተጉዘን እዚህ ስንደርስ ደልቲ አልነበረም

“ቡስካ ሄዷል' አሉንና እዚያ ሄደን ስንጠይቅ ዳራ የምትባል የሳላ መንደር ልጃገረድ አብራው እንደተቃበጠችና ደልቲ
መቀመጫውን ሰርቶ እንደሄደ ወይሳ እየነፋ ያም እንደነበርና በእርግጥ አልፎ አልፎ ትክዝ ይል እንደነበር ሰማን፡፡ ከዚያ የላላም
የሻንቆም የቡስካም ሰው ዳግመኛ አለማየቱን ተረዳን፡፡

“ጎይቲ ይህን ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች መጮህና ማልቀስ ጀመረች፡፡ ዳራ በበኩሏ ጎይቲ ስታለቅስ እሷም በተራዋ ትንፈቀፈቅ
ጀመር” ብሎ ከሎ ገጠመኛቸውን ሊቀጥል ሲል፦

“ከዚያስ ተገኘ? ካርለት  ረጅሙን ታሪክ መከታተል
አልቻለችም! ሲቃ ያዛት፡፡

“ከዚያማ ጫማ ጣዮች እንዲተነብዩ ተጠየቀና “ክፉ
አልደረሰበትም፧ ራቅ ብሎ ግን ሄዷል' አሉ፡፡ አንጀት አንባቢዎችም ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ብለው የታያቸውን ተናገሩ፡፡ጎረምሶች ጫካውን ደአሰሱት መልዕክት በየአቅጣጫው ተላከ ከዚያ  በካሮ  ማህበረሰብ በኩል ያሉት የደንበላ መንደር ሰዎች አየነው ብለው መናገራቸውን ሰማን፡፡

እኔም የአንችን መኪና ይዤ በየመንደሩ ለፍለጋ ዞርሁ
አሁን ደንበላ አይተነዋል እሚለውን ስንሰማ ግን እሱን ልፈልግ ወይንስ አንቺን አዲሳባ ሄጄ ላምጣ በሚለው ከሽማግሌዎች ጋር ስማካር አንች መጣሽ?

ከወጣ  ማለቴ ከሄደ ስንት ጊዜ ሆነው?

"ሃያ ቀን በላይ ሆኖታል፡"
እሽ ለምን ነው አንዳንዴ ከፍቶታል የተባለው?"

“ጎይቲን ያፍቅራታል፡ የአንድ ቤተሰብ አባል በመሆናቸው
እንጂ አብሯት ቢኖር ደስታውን አይችለውም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአይኑ
ስትርቅ ላይከፋው ሳይተክዝ አልቀረም። ስለ አንችም ደጋግሞ ያነሳ እንደነበር ሰምቻለሁ የእሷ መባለግ አንሶ ጎይቲንም ይዛት ሄደች!  እያለ እንደሚቆጭ ኮይታውን ከፍሉ እንደጨረሰ አንችን ሲያገባ ያንን
ለስላሳ ገላዋን እገለብጠዋለሁ' እያለም ሲፎክር እንደነበር ሰምቻለሁ" አላት ከሎ ፈገግ ብሎ።

እውነቱን ነው የሐመር ልጃገረድ ነኝ ብዬ ባህሉን
መቀበሌን አሳውቄ! ካለ ሽማግሌ ፈቃድ ያውም ከሐመር ምድር ርቂ መሄዴ በእርግጥ ሊያበሳጨው ይገባል" አለችና በሃሣብ ተውጣ ቆየች፡፡

እንዲህ ካርለትና ከሎ በሃሣብ ተውጠው እንደተቀመጡ ጎይቲ አንተነህ መጣች

“ይእ ምን ሆናችኁል?"
አለቻቸው ሁለቱንም በፍርሃት አየቻቸው ሆዷ ፈራባት “ጎይቲ ምንም አልሆነም፡፡ አንችን
ጠይቄ ልትነግሪኝ ያልቻልሽውን ስለ ደልቲ ከሎን እየጠየቅሁት ነበር"

“እሁሁ… እኔስ ደሞ ምን ሰማችሁ ብዬ የሆንሁትን
አላውቅም" አለችና ሐጫ በረዶ ጥርሶችዋን አሳይታ

“ይእ! የአያ ደልቲን የኦሞ ዳር ጥንቅሽ የቀመስን እኔና
አንች ሌላው ጣምናውን የት ያውቀዋል" ብላ በሣቅ ተፍለቀለቀችና

ነይ በይ አሁን ቡና ጠጭ እህልም ባፍሽ አድርጊ፡፡
የደንበላ ሰዎች “አይተነዋል ብለዋል እንኳን እስካሁን ደና ሆነ እንጂ ከአሁን በኋላስ ከምስጥ ዋሻ ቢገባም አያመልጠን፡፡ ይእ!

አንተስ ና እንጂ  ይኸውልሽ ከመጣን ጀምሮ አበሳውን እያሳየሁት ነው፡፡ ና በል የኔ ጌታ.." አለችውና ከሎን ሶስቱም ተያይዘው በር ወደሌለው የሐመር ጎጆ ሄዱ!
👍291👏1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ከጄኔራሏ ጋር ከአስራ አምስት ቀን በኃላ መገናኘታችን ነው፡፡ በጣም ናቃኛለች፡፡እኔም ሰሞኑን በጣም በተወጣጠረ እና በተጨናነቀ ሁኔታ ላይ ስለነበርኩ ላገኛት አልቻልኩም ነበር…እሷም ለምን እንደሆነ አላውቅም ላግኝህ ብላኝ አታውቅም ፡፡

‹‹እንዴት ነች ልጅህ?››

‹‹ደህና ነች…በጣም ደህና ነች››

‹‹ደህና ነች ስትል ፊትህ ላይ ብርሀን ይረጫል …ታድለሀል፡፡››

‹‹አዎ ..ትክክል ነሽ ታድያለሁ….በተለይ በአካል ካገኘዋት በኃላ ነው በጣም መታደሌን ያወቅኩት፡፡››

‹‹እናትዬውስ…?›

‹‹አናትዬው ምን….?››

‹‹ማለቴ ካየሀት በኃላ አላገረሸብህም?››

‹‹አይ እንዴት ያገረሽብኛል…በሩቅ አየኋት እንጂ በቅርብ አለላወራኋት..በዛ ላይ እህቴ እኮ ነች..››

‹‹መጀመሪያም እኮ እህትህ  ነበረች››

‹‹መጀመሪያማ አለመብሰልና ልጅነት ነው…››

‹‹ብለህ ነው…?››

‹‹አዎ….››

‹‹ይሁንልህ…ለማንኛውም ልሄድ ነው››

‹አልገባኝም….ገና አሁን መምጣትሽ እኮ ነው›

ፈገግ አለችና‹‹ማለቴ ሰሞኑን  መንገድ ልሄድ ነው..››

ይበልጥ ደንግጬ

‹‹ወደየት…?››

‹‹ግብፅ››

‹‹ግብፅ..ለምን …..?››

‹‹አባይን ተከትዬ…››

‹‹አትቀልጂ››

‹‹እሺ ለስራ …››

‹‹የምን ስራ…እዚህ  ስራ ጀምራለው ብለሺኝ አልነበረ እንዴ…?አንተንም አግዝሀለው አላልሺኝም ነበር?››

‹‹አዎ ብዬህ ነበር..ግን…››

‹‹ግን ምን…;?

ያው እንደዛ ከተባባልን በኃላ አንተ ጋር ሆነ እኔ ጋ ብዙ የተቀያየሩ ነገሮች ተፈፅመዋል…..ደግሞ አሁን ያገኘሁትን የስራ እድል በቀላሉ ገሸሽ ላደርው አልፈልግም፡፡››

‹‹ለመሆኑ ምንድነው ስራው…?››

‹‹አንባሳደር ሆኜ ነው የተመደብኩት…››

‹‹ወታደር አምባሳደር……;››
‹‹አዎ፡፡ ምን ችግር አለው…?ብዙ ሰዎች ምታበሽቁኝ ወታደር ተኩሶ ከመግደል ውጭ ሌላ ዕውቀት ያለው አይመስላችሁም….ወታደር እኮ እንደሌላው ሰው ከሙሉ ጭንቅላት ጋር የተፈጠረ ነው፡፡ማንኛውንም ትምህርት ተምሮ የየትኛውም እውቀት ባለቤት የመሆን ብቃትም አቅሙም አለው..እኔም ወታደር ከመሆኔ በተጨማሪ ላይ በውጭ ግንኑነትና ፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪ እንዳለኝ አትርሳ…፡፡››

‹‹አረ አታምርሪ እኔ እንደዛ ማለቴ አይደለም…››

‹‹ባክህ ነው…የንግግር ቃናህ እራሱ ይሻክራል፡፡››

‹‹እሺ እንደዛ እንዲሰማሽ ስላደረኩ ይቅርታ ,.እኔ ግን ባትርቂኝ ደስ ይለኝ ነበር..››

‹‹አይ የምን መራራቅ አመጣህ፡ ከአሁን በኃላ እኮ ልንለያይ የማንችል ዘመዳማቾች ሆነናል፡፡አንተ እኮ የጋሽ አያና ልጅ ነህ..ወንደሜ ማለት ነህ;››
የእውነት ተደንቄም ተበሳጭቼም‹‹ግን የእኔ  እጣ ፋንታ  ምን አይነት ነው?››አልኳት ‹‹ምነው ምን ሆነ? ››

‹‹እንዴት ምን ሆነ ትያለሽ..?ዘላለሜን የማፈቅረው እህቶቼን መሆኑ አይገርምም?››

‹‹የማፈቅረው….ከእኔ ፍቅር ይዞሀል እንዴ?››

‹‹እየቀለድሽ ነው….?ካገኘውሽ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ አንቺን ከማፈቀር ውጭ ሌላ ምን ስራ አለኝ ብለሽ ነው››

ዝም አለች……..አንገቷን አቀረቀረችና ለደቂቃዎች በዝምታ ተውጣ አሰበች…እና እንደምንም ፈገግ ለማለት እየጣረች

‹‹ለማንኛውም ይሄንን ርዕስ ለጊዜው እንርሳው››አለችኝ፡፡

‹‹ለጊዜው ማለት?››

‹‹ለጊዜው ማለትማ …ጊዜ የራሱን መልስ አዘጋጅቶ በየልባችን ሹክ እስኪለን በነበረበት ተከድኖ ይቀመጥ ማለቴ ነው፡፡››

‹‹ይሻላል?›››

‹‹አዎ ይሻላል…ሳረሳው የፊታችን እሁድ እቤቴ ሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቼያለሁ.. ልክ 7 ሰዓት እንድትገኝ››

‹‹እኔ?››

‹‹አዎ አንተ..ዋናው የክብር እንግዳዬ ነህ››

‹‹አረ በፈጣሪ እኔ ፓለቲከኞችና ባለስልጣናት ያሉበት ቦታ መገኘት ይጨንቀኛል፡፡››

‹‹አይዞህ አታስብ…ግብዣው ላይ ሚገኙት ጓዶኞቼ እና ጥቂት ዘመዶቼ ናቸው፡፡ ተጋባዦቹ ከአሰር አይበልጡም፡፡››

‹‹እንደዛ ከሆነ እሺ…››
እጇን ወደ ቦርሳዋ ከተተችና ፖስታ ይዛ ወጣች…ከዛ ሰጠችኝ

‹‹ምንድነው?››

‹‹የጥሪ ካርድ››

‹‹በቃል ነገርሺኝ አይደል…አይበቃም፡፡››

‹‹አይ ለአንተ አይደለም››

‹‹እናስ?››

‹‹ ለአያትህ››

በጣም ደነገጥኩ..እስኪ ምን ሚያስደነግጥ ነገር አለ‹‹እየቀለድሽ ነው…?››

‹‹አንተ ምን  አስጨነቀህ..ብቻ የታሸገውን ፖስታ ሳትነካካ ወስደህ ስጣቸው…. መምጣትና አለመምጣቱን እሳቸው ይወስኑ››

‹‹ቀልደኛ ነሽ…እኔማ ምን
ቸገረኝ እሰጠቸዋለሁ…ውሳኔያቸውን ግን እኔው ልንገርሽ  አይመጡም… አታስቢው፡፡››

‹‹እሺ አንተ ብቻ ስጣቸው፡፡››
ተቀብዬ ኪሴ ከተትኩ
////
በተባለው እሁድ ቀን የልቤ ሰው የሆነችውን የጄኔራሏን የሽኝት በአል ላይ ለመታደም…ለዝግጅቱ የሚመጥን ሽክ ያለ አለባበስ ለብሼ አምሬና ተሸቀርቅሬ በእጄ ደግሞ ይመጥናታል ያልኩትን የማስታወሻ ስጦታና አንድ ጠርሙስ ውስኪ አንጠልጥዬ ልክ ከቀኑ ሰባት ሰዓት መኖሪያ ቤቷ በራፍ ላይ ተገኘሁ፡፡ወደውስጥ ለመግባት ግን ትንሽ አመነታሁ፡፡ውስጥ የማገኛቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ጋር እንዴት ብዬ እንደምግባባቸውና እንዴት አይነት ጊዜ አብሬያቸው ላሳልፍ እንደምችል ሳስበው ጨነቀኝ…በተለይ እኛ ጄኔራል የቀድሞ ወዳጇ ተጠርተው ከሆነ ሙዴ ሁሉ ነው የሚከነተው…ለማንኛውም ምርጫ ስለሌለኝ እራሴን አበረታትቼ ወደግቢው ዘልቄ ገባሁ….በሩቅ በረንዳ ላይ አንድ ታዳጊ ልጅ ትታየኛለች…እየቀረብኩ ስመጣ የማየውን ማመን ነው ያቃተኝ ፡፡ልጅተቷ እኔን ሳታይ ተመልሳ ወደውስጥ ሮጣ ገባች ፡፡
በዛች ቅፅበት ምንም ነገር ማሰብ አልቻልኩም።ልክ ልጅቷ እንደወፍ በራ የምታመልጠኝ ይመስል በሩጫ ተከተልኳት……ታአምር ታምሬ እያልኩ ተንደርድሬ ወደቤት ገባሁ።አንድ እግሬን እቤት ውስጥ አንድ እግሬን በረንዳ ላይ አድርጌ ከነሀስ እንደተሠራ ሀውልት ተገትሬ ቆምኩ።ውስጥ ሳሎኑ ሙሉ ነው። የሚገርመው ደግሞ ሁሉንም ሰዎች አውቃቸዋለሁ… በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንዲህ ግራ ገብቶኝ አያውቅም።ወደኃላ ተመልሼ ሮጬ ማምለጥ ወደፊት ሄጄ ሁኔታዎችን መጋፈጥ.."ሁለቱንም ለማድረግ አእምሮዬን መጠቀም ሰውነቴንም ማዘዝ አልቻልኩም።

ጄኔራሏ  ከሌላኛው ክፍል ወጣችና ቀጥታ ወደእኔ መጣች "እንዴ ግባ እንጂ"
ስሬ ደርሳ ክንዴን ቀጨም አድርጋ ያዘቺኝ እና ጎትታ ከተቸነከርኩበት አነቃነቀችኝ።ከውስጥ አፍጥጠው ከሚያዩኝ ሰዎች መካከል አንድ አዛውንት ወደእኔ መንቀሳቀስ ጀመሩ..ማን እንደሆኑ መገመት አትችሉም፤አያቴ ናቸው።ከሶስት አመት በኃላ እንዴት ክፍላቸውን ለቀው እዚህ ሊገኙ ቻሉ?የጥሪውን ካርድ በሰጠዋቸሁ ቀን ፈፅሞ እንዳላስበው በማያሻማ ቋንቋ ነግረውኝ እኔም አምኜያቸው ነበር….እና ታዲያ እንዴት ሀሳባቸውን ቀየሩ?ይሄ ነገር ህልም  ይሆን እንዴ ?
‹‹ና በል አክስትህን ይቅርታ ጠይቅ።›አያቴ ናቸው የተናገሩት፡

ካለሁበት ድንዛዜ ድንገት ባንኜ በአየር ላይ እንደመንሳፈፍ ተንደርድሬ አክስቴ እግር ስር ድፍት አልኩ… እሷም ፈጥና ልታነሳኝ ትከሻዬን ለመያዝ ብትሞክርም እንደምንም አመለጥኳትና እግሯ ስር ተደፍቼ በእንባ እየታጠብኩ ‹‹እቴትዬ በፈጣሪ ይቅር በይኝ..አሳፍሬሻለሁ.››የመጣልኝን ቀባጠርኩ፡፡

ይቀጥላል
👍1067👏1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ከምሽቱ 5 ሰዓት እቤት ክፍሌ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ስለቃል እያሰብኩ ነው….መቼስ ቃል ቃል ብዬ እናንተንም አሰለቸዋችሁ አይደል  ምን ላድርግ..ተለክፌ እኮ ነው….እንቅልፌ መጥቷል ግን ከመተኛቴ በፊት አሱን ማየት ፈለኩ…ማለቴ በተለያየ ቀን ከመተኛቱ በፊት የፀለያቸውን ያልተለመዱ አይነት ፀሎቶችን እሱ ቤት በቀበርኩት ስውር ካሜራ አማካይነት ቀድቼ ላፕቶፔ ውስጥ አሉ..ከእነሱ መካከል አንድ ሁለቱ ማድመጥ ፈለኩ በዛውም ለእኔም እንደፀሎት ሀኖ ይቆጠልርልኝ ይሆናል…
ይሄ ከዛሬ አስር ቀን በፊት የፀለየው ነው፡፡
///

የዛሬ ሳምንት የፀለየው ደግሞ በእኔ ላይ እየሆነ  ያለው ሁሉ ትክክል ነው…በዙሪዬ ምንም  ገደል የለም…የመታኝ እንቅፋት በንቃት እየተራመድኩ እንዳልሆነ ሊያስታውሰኝ እንጂ ሊያደማኝ ፈልጎ አይደለም፡፡ እየበሰበሰ ያለው ነገር ከመበስበስ ቡኃላ ህይወት መስጠት ስላለ ነው…እየረገፈ ያለው የጠወለገና ደረቅ ቅጠል ለአዲሱና እንቡጠቹ ቅጠሎች ይበልጥ እንዲያቡብና እንዲያፈሩ ነው፡፡በዚህ አለም ላይ  ምንም አይነት የተዘበራረቀ ነገር የለም..እሆነ ያለውነገር ሁሉ አንተ ስለፈቀድክና መሆን ስለሚገባው የሆነ  ነው…ለምለሰሙ ዝናብ ከሰመይ በመርገፍ ምድርን ከጥሞና እንዴያረካት ቀድሞ ሰማዩ በጥቁር ደመና መሸፈንና መዝጎርጎር አለበት…ጨለማው ከሌለ ብሩሆ ጨረቃ የምትተፋውን ብርሀን ፈፅሞ ማየትም ማድነቅም አንችልም….ሁሉ ነገር ድንቅ ነው..ሁሉ ነገር ብሩህ ነው፡፡
አሜን.ብዬ ላፕቶፔን ዘጋሁና መብራቱን አጥፍቼ ተኛሁ፡

///
ከሶደሬ ከተመለሱ ሀያ  ቀን አልፏቸዋል፡፡ዛሬ ለሳምንታት ያቀደችውን ነገር የምትፈፅምበት ቀን ነው፡፡አዎ የምትፈፅመው  ነገር የጽድቅ ስራ አይደለም…አእምሮ የሚጨመድድ ከሳጥናኤል አእምሮ ካልተቀዳ በሰው ሀሳብ የማይታሰብ ነገር እንደሆነ ታውቃለች….ግን ደግሞ በነፃ ሚገኝ  ነገር የለም በሚል እራሷን ለማፅናናት ገፍታበታለች….፡፡‹‹አዎ    ቃልን የራሷ ለማድረግ እሷም መክፈል የሚገባትን መስዋዕትነት በፍቃደኝነት ለመክፈል ቆርጣለች….የልጅነት ጓዳኛዋን፤ የረጅም ጊዜ እጮኛዋ የሆነውን መድህኔን በፍቃደኝነት አሳልፋ ልትሰጥ ነው….አዎ ያንን ለማድረግ ደግሞ የመጨረሻውን ማስፈንጠሪያ የምትጫንበት ቀን ነው…ብቻ እንዲቀናትና ነገሮች በእቅዷ መሰረት እዲከወኑ ለማን መፀለይ እንዳለባት አታውቅም ‹‹እግዚያብሄርን እርዳኝ ብዬ እንዴት ጠይቀዋለሁ….?አረ ያሳፍራል፡፡››አለች ..ብቻ እንዲሁ እንዲቀናት ለራሷ ስኬትን ተመኘች…..በዛው ቅፅበት መኝታ ቤቴ ተንኳኳ፡፡

‹‹ማን ነው?››

‹‹እኔ ነኝ ልዩ..››አለች ከሰራተኛቸው አንዷ፡፡

‹‹እ ..ምን ፈለግሽ?›››

‹‹መድህኔ መጥቷል››

‹‹መጣው ጨርሼያለሁ በይው››

‹‹እሺ….››ብላ ተመልሳ ሄደች፡፡በጣም ተጨንቃ ዝንጥ ብላ ነው የጠበቀችውኩ፤የሚያስፈልጋትን ነገር ሁሉ በቦርሳዋ መጨማመሯን አረጋግጣ ክፍሏን ለቃ ወደታች ወደሳሎን ስትወርድ መድህኔና እናቷ ልክ እንደወትሮቸው አፍ ለአፍ ገጥመው ሲያወሩ ደረሰች፡፡….
እናትዬው ገና እንዳዮት‹‹ወይ ልጄ መልአክ መስለሻል …››አለቻት … መድህኔም ዞር ብሎ ከስር እስከላይ በገምጋሚ አይኖቹ ቃኛትና ፈገግ አለ…..

ከተቀመጠበት ተነሳና‹‹…በቃ ማሚ ሰሞኑን እመጣና በዝርዝር እናወራበታለን›› አላቸው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ልጅ..ነገ ተነገ ወዲያ ቢሆን ደስ ይለኛል…ጊዜ የለንም፡፡››አሉት፡፡
..ምንም እንዳልገባው ሆና‹‹ለምኑ ነው ጊዜ የሌላችሁ?›› ብላ ጠየቀች ..ስለሰራጋቸው እንደሚያወሩ ግልፅ ሆኖላታል፡፡..በዚህ ወቅት በእሷም ሆነ በእሱ ቤተሰቦች ቤት ከእነሱ ሰርግ ውጭ ሌላ አንገብጋቢ አጀንዳ እንደሌለ ታውቃለች፡፡

‹‹አይ የአዋቂ ወሬ ነው….››አላትና አቅፏት ይዟት ወጣ…
ሲሸኞቸው ከኃላ የተከተሏቸው እናቷ‹‹ካደራችሁ ደውሉ››አሏቸው…
‹‹አንደውልም  …ከአሁኑ እወቂው እድራናል›››መለሰችላቸው፡፡
በእሱ መኪና ውስጥ ገብተው ገና ከጊቢ እንደወጡ‹‹በል ጊፍቲ እስቴዲዬም እየጠበቀችን ነው››አለችው..
‹‹እነሱም አብረውን ያመሻሉ እንዴ ..?እኔና አንቺ ብቻ ምንሆን መስሎኝ ?››አላት..ቅር ባለው ፊት፡፡
‹‹አዎ እኔም እንደዛ ነበር እቅዴ ..አሁን ከሀያ ደቂቃ በፊት ደውላ ደብሯት እስቴዲዬም ብቻዋን እዳለች ነገረችኝ ››
‹‹እንዴ  ፍሬንዷ ጋር አትደውልም…?››ሙግቱን ቀጠለ
‹‹ፍሬንዷ ማን ?››
‹‹እያሾፍሽ ነው..?ቃል ነዋ››
‹‹ፍሬንዷ ስትል እኮ ዝም ብሎ ጓደኛዋ የምትል መስሎኝ ነው..ቃልማ ለስራ ክፍለሀገር ወጥቷል….ለዛ እኮ ነው እምቢ ማለት የከበደኝ …አንተ በስራ ቢዚ ሆነህ ችላ በምትለኝ ጊዜ የምታዳብረኝ እሷ አይደለች..አሁን ውለታዬን ልመልስ ነዋ…››አለችው፡፡
‹‹አቤት አቤት..አሁን እኔ መቼ  ነው አንቺ ልታገኚኝ ፈልገሽ ቢዚ የሆንኩት…..ደግሞ የድሮ ጓደኞችሽን እርግፍ አድርሽ  ግንኙነትሽን ጠቅላላ ከእነዚህ ባልና ሚስት ጋር እድርገሻል ምንድነው ?አልገባኝም?…››አላት

በመርማሪ አይኖቹ ፡፡
‹‹ምነው አልተመቹህም እንዴ..?እንደዛ ከሆነ ….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ምን…?››
‹‹ካልተመቹህ ቀስ በቀስ አቆማለኋ…››
‹‹አዎ አልተመቹኝም›› ቢል እንደማታቆም በውስጧ ታውቃለች..ግን ደግሞ ማስመሰል አለባት፡፡  አቁሚ ቢላት እንደውም እልክ ይዞት ጨርቋን ጠቅልላ እነሱ ጋር የምትገባ ሁሉ ይመስላታል፡፡እሱም አመሏን በጥልቀት ስለሚያውቅ እንደእዛ አይነት ቅብጠት አይቃብጥም፡፡
‹‹ኸረ..እንደውም ከእነሱ ገር መዋል ከጀመርሽ በኃላ  አሪፍ ሆነሻል፡፡››
‹‹አሪፍ ስትል?››ተበሳጭች
‹‹በቃ ደስተኛ ሆነሻል..በረባ ባረባው መነጫነጭ ትተሻል ባልልም በጣም ቀንሰሻል .ለምትጠየቂው ጥያቄ ቀና መልሶች  መመለስ እየተማርሽ ነው..አረ ከሁሉም በፊት እንድንጋባ ፍቃደኛ የሆንሽው ከእነሱ ጋር ጓደኛ ከሆንሽ በኃላ እኮ ነው፡፡››ብሏት የቅርብ ጊዜ ለውጧቾን ዘረዘረላት….ምንም የተሳሳተው ነገር የለም…ሁሉንም በአስተውሎት ታዝቦል….ችግሩ ከለውጦቹ ጀርባ የሸሸገችውን ድብቅ ሚስጥራዊ ተልዕኮ አለማወቁ ነው፡፡

‹‹ምን አልባት በእነሱ ፍቅር ቀንቼ ይሆናል…››

‹‹አረ እንኳን  ቀናሽ..እኔ ተጠቃሚ ሆኜያለሁ፡፡››
‹‹ዛሬ እንደውም እንዲህ ተቆነጃጅቼ የወጣሁት የሆነ ነገር ሰጥቼ ሰርፕራይዝ ላደርግህ ነበር..ግን አሁን ፀባይህን ሳየው አይገባህም››

‹‹አይኖቹ በሩ…ምንደነበር ልትሰጪኝ ያሰብሽው…?››
‹‹እስከዛሬ ሰጥቼህ የማላውቀውን››
በደስታ ተፍነከነከ …‹‹በአንድ አፍ….አንዴ አስበሽ ወስነሻል……. ትሰጪኛለሽ፡፡››
‹‹እስኪ እስከምሽቱ ያለህ ፀባይ ታይቶ …ምን አልባት?››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
…በዚህ ጊዜ ስቴዲዬም ደርሰው ነበር ..ጊዬን ሆቴል በራፍ አካባቢ መኪናቸውን አቆሙና ደወሉላት..ቅርብ ስለነበረች መጥታ ተቀለቀለቻቸ….  ወደፒያሳ ነበር የነዳው፡፡


ይቀጥላል
👍11313😁3🤔3🔥1🤩1
#ታአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
""
‹‹ነገርኩሽ እኮ… ዛሬ እሮብ ነው አይደል እስከቅዳሜ አልጋሽን ለቀሽ ያልደረሻቸውን ለቅሶዋችና የታመሙ ወዳጆችሽን እየዞርሽ ትጠይቂያለሽ…››

‹‹እንደአፍሽ ያድርገው››

‹‹እማ እኔ እንዲህ በቁም ነገር ተናግሬ ያልሆነ ነገር አለ…ደግሞ ጀግናዬ ነው መልዕክቱን የነገረኝ…ምን አልባት መድሀኒቱን አባቴ ማለቴ  የድሮ ፍቅረኛሽ ይሆናል በሚስጥራዊ መንገድ  በእሱ በኩል የላከልሽ››

እናትዬዋ በንግግሯ ባለመደሰት ኮስተር ብላ‹‹አባትሽ የድሮ ፍቅረኛዬ ሳይሆን ….የዘላለም ፍቅረኛዬ ነው።››አለቻት፡፡

"እሺ ይሁንልሽ…አሁን ቻው ያዶት ልንሄድ  ነው…ደስ ስላለኝ በዚህ በጥዋት ሂጄ መዋኘት እፈልጋለሁ።››

‹‹እንዴ ቁርስ አፍሽ ላይ ጣል ሳታደርጊ?››

‹‹አይ ስመለስ››ብላ ንስሯን እንዳቀፈች ከቤት ወጣችና ግቢውንም ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

‹‹ጀግናዬ ስላደረጋችሁት ነገር በጣም አመስግናለሁ...ማለት አንተና አባቴ….ቃል በገባሁት መሰረት የዘላለም ውለታችሁ አለብኝ...ግን እናቴ ከአመት በኃላ ቀጣይ ዕድሜ እንዲኖራትስ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ…? መቼስ ከባድ ነገር ነው የሚጠበቅብኝ?››

‹‹አይ ቀላል ነው››

‹‹ቀላል ነው ስትል? 

‹ከእናትሽ ጋር መኖር ማቆምሽ ለእሷ ተጨማሪ ዕድሜ ይሰጣታል፡፡

አንቺ ከተፈጥሮሽ የተነሳ ፍቅርሽ እሷን ለመኖር ያላትን ኃይል ይመጣል….አንቺ ስትወጂም ሆነ ስትጠይ እኩል ነው ሰውን ምትጎጂው….በፍቅርም ሆነ በጥላቻ የተለየ ትኩረት ያሳረፍሽበት ማንኛውንም የሰው ልጅ ኃይሉን ነው ምትመጪበት… ያ ኃይል ደግሞ ከዕድሜው ላይ ይጎመዳል..ምን አልባት እናትሽ አንድ ቀን ከአንቺ ጋር ለማሳለፍ ከእድሜዋ ላይ ሀያ ሰላሳ ቀን መገበር ይጠበቅባት ይሆናል…"
የምትሰማውን ዜና ተቋቁማ ወደፊት መቀጠል አልቻለችም …ከመንገድ ጎራ ብላ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባችና የተደላደለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠች… ንስሯን ከፊት ለፊቷ አስቀመጠችው…. ከንፈር የማይንቀሳቀስበት ፤አፍ ማይከፈትበት ድምፅ አልባ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹.እና አሁን ከእናቴ አልለይም የሆነው ይሁን የምትይ ከሆነ አንድ አመቱን ከእሷ ጋር አሪፍ የምትይውን የደስታ ጊዜ አሳልፊ…አይ እናቴ አርባ ሀምሳ አመት መኖር አለባት የምትይ ከሆነ ግን ዛሬ ነገ ሳትይ ይሄን ሀገር ለቀን መሄድ አለብን፡፡››

‹‹ግን እናቴን ምን እላታለሁ?››
‹‹እውነቱን ንገሪያት..እርግጥ አትስማማም…ግን ቢሆንም ንገሪያትና አንቺ ውሳኔውን ወስኚ።››

‹‹ቆይ ብዋሻትስ?››

‹‹ምን ብለሽ?››

‹‹ለምሳሌ እኔ አብሬአት መኖር ምቀጥል ከሆነ በሽታው ወደእኔ ተላልፎ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደምሞት እንዳወቅኩ ብነግራት የእኔን መሞት ማሰብም ስለማትፈልግ በፍጥነት የምትስማማ ይመስለኛል›"
ላቀረበችው ሀሳብ ከአእምሮው የድጋፍ ወይም የተቃውሞ መልስ ለማንበብ ስትጠብቅ….እሱ በተለየ ብርሀን የደመቁ አይነት ቀለማትን ረጨ.እንዲህ የሚያደረገው በነገሮች ሲደነቅ ወይም ሲደሰት እንደሆነ ታውቃለች፡፡

‹‹ምነው የማይረባ ሀሳብ ነው እንዴ?››

‹‹አረ አባትሽም እንዲህ  አይነት ሸር በዚህ ፍጥነት ማሰብ መቻሉን ስለተጠራጠርኩ አድንቄሽ ነው..››

‹ዲቃላ መሆን ጥቅሙ እኮ ይሄ ነው…ግን አሁን የት ነው የምንሄደው ..ማለቴ የት ሀገር ብንኖር ይሻላል?፡፡››

‹‹ደስ ያለሽ ቦታ..ደስ ያለሽ ሀገር››

‹‹ምን ሰርተን ነው የምንኖረው…ትምህርቴን ገና የ10 ክፍል ማትሪክ እንኳን አልተፈተንኩ..ከብት ከማርባት እና እትክልቶችን ከመንከባከብ ውጭ ምንም ሌላ ማውቀው ሞያ የለኝም››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ አንቺ እኮ ማንኛውንም ሞያ ለመልመድ ከሌላው የሰው ልጅ በመቶ እጥፍ በላይ አቅም ነው ያለሽ....በዛ ላይ ታንዛኒያ የሄድን ጊዜ ኬኒያ ድንበር ያገኘነውን ዳይመንድ አለን....በጣም ሀብታም ነሽ እኮ››

‹‹ማለት አባቴ የሌላ አለም ፍጡር ስለሆነ?››

‹‹አዎ ለሰው ልጆች ጥበብ እና እውቀትን ያስተማሩት እኮ አባትሽ እና ከእሱ ጋር ከገነት የወደቁት ጭምር ናቸው››

‹‹ይሄ ነገር እውነት ነው ማለት ነው?››

"አዎ..በከፊል እውነት ነው››
‹‹በከፊል ስትል.ከፊሉስ እውነት?››

‹እሱን ሌላ ጊዜ..እንድነግርሽ ሲፈቀድልኝ?››

‹‹እንዳልክ …ግን የአባቴ ዘመዶች ለሰው ልጆች ያሰተማሯቸው ዕውቀትንና ጥበብን ብቻ ነው …?››

‹‹አይ እሱማ ክፋትና ተንኮልን…ግድያንና ዘረፋንም ጭምር አስተምረዋል፡፤››

‹‹እና የሰው ልጅ ባለውለታ ናቸው ነው የሚባለው ወይስ ጠላት?››

‹‹አይ እኔ ምለው ማንም ቢሆን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ለማግኘት መክፈል ሚገባው ክፍያ አለ…አባትሽና ወገኖቹ ለሰው ልጆች ያበረከቱት ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ከሰው ልጆችም የነጠቁት መልካምነቶች አሉ››

‹‹ሳስበው ሳስበው የሰው ልጅ ግን ውለታ ቢስ እኮ ነው፡፡

በየቤተክርስቲያኑም ሆነ መስጊዱ ምሰማው የክፋት ሁሉ ምንጭ ሰይጣን እንደሆነ ጥበብና እውቀትን ደግሞ እግዚያብሄር እንዳስተማራቸው  ነው የሚያወሩት››
መልስ ብትጠብቅም ምንም አልመለሰላትም. እዕምሮዋን ዘጋባት

‹‹ምነው? አንተም እግዚያብሄርን ትፈራዋለህ እንዴ?›

አሁንም የተቀየረ ነገር የለም..ለንግግሯ ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት እምሮውን እንደቆለፈ በዛው ገፋበት…ተደነቀች፡፡

‹‹የኃያላን  ኃያል ፤ የጌቶች ሁሉ ጌታ እሱ እግዚያብሄር ነው..የሚል ስብከት መስማቷን አስታወሰችና መልሳ በልቧ አኖረችው…
ሄዶ ሄዶ የሁሉ  ነገር ማሰሪያና የኃይሎች ሁሉ ጥቅል ኃይል እግዚያብሄር ከሆነ ታዲያ የእነ አባቴ ቀድሞ መንፈራገጥ ለምን ይሆን ?ብላ እራሷን ጠየቀችና  ..መልሳ ሌላውን ጥያቄ ተወችና 
‹‹ በል ተነስ እንሂድ.. ወደየት ሀገር እንደምንሄድ አስብበት.››ብላ መንገዷን ስትቀጥል እሱ ክንፍን አማቶና በአየር ላይ ተርገፍግፎ እሷን በመተው በተቃራኒው ወደ ደኑ ውስጥ ገባ..‹‹እርቧሀል ማለት ነው ?››ብላ እሷ ለመዋኘት ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ይቀጥላል
👍12712👎4🥰3👏3
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

የሰው ልጆች የህይወት ጉዞ ልክ እንደ ሸረሪት ድር ነው፡፡እርስ በርሱ የተቆላለፈ.. የተሳሰረ እና የተወሳሰበ፡፡

…ሶፊያ ዲያስፖራ ነች፡፡የኢትጵያውያን ሲያኮሩፉ ሆነ ፈጣን በሆነ የህይወት ጉዞ ወጤታማ መሆን ምኞት በልባቸው ሲፀነስባቸው ግን ደግሞ ያንን ወደ ተግባር
ለመመንዘር የእኔ የሚሏት ሀገራቸው ዕድልና
አጋጣሚውን አላመቻችላቸው ስትል በኩርፊያ መልክ ከሚከትሙባት ሀገረ አሜሪካ ተመልሳ ወደሀገር ቤት ከገባች ገና አራት ወር
አልሞላትም፡፡

የተመለሰችበት ምክንያት ወደ ሀገር ተመልሳ ልማቱን እንድታፋጥን መንግስታዊ ጥሪ ተደርጎላት አይደለም፤ የአሜርካ ኳኳታ ሰልችቷት እንጂ፡፡

የሀገሯ አየር፣የሀገሯ ሰው፣የሀገሯ ፍቅር ናፍቆት
እንጂ፡፡ግን ይሄን እንዲሁ ሰዎች ለምን ተመለሽ
ብለው ሲጠይቋት ምትመልላቸው መልስ
ነው፡፡ትክክለኛው ምክንያቷ ግን እሷ ብቻ ነች ምታውቀው፤ምህረትን ፍለጋ ነው የመጣችው፡፡የዕድሜ ልኳን ፀፀት ከልቧ ለማራገፍ የሚያግዛትን ይቅርታ ለማግኘት፤ግን ከመምጣቷ በፊት እንዳሰበችው መንገዶች ቀላል አልሆኑላትም፡፡ከፀፀት ደዌ ልትፈውሳት የምትችለዋን ሴት በቀላሉ መቅረብ አልቻለችም፡፡

ዶ/ር ሶፊያ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰች በኃላ አንድ ዓለምአቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ ነው ተቀጥራ የምትሰራው፡፡ቋሚ የስራ ቦታዋ አዲስ አበባ ቢሆንም አሁን ወደ ሀዋሳ ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነች ፡፡አንድ አለም አቀፍ ድርጅት ለሶስት ቀናት ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ለመሳተፍ ፡፡

ሁሉንም ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ ብላ እንቅስቃሴ ልትጀምር ስትል ነበር ያላሰበችው እክል የገጠማት፡፡ከግቢው ሳትወጣ መኪናዋ ተበላሸባት፡፡እዛ ጠብራራ አለቃዋ ጋር ደውላ የገጠማትን ችግር በዙሪያ ጥምዝ አስረድታ ሌላ መኪና እንዲቃይርላት ለማሳመን አሰበች፡፡

ግን አስባ ሳትጨርስ ደከማትና ተወችው፡፡

ሴሚናሩ የሚጀምረው ደግሞ ነገ ጥዋት ነው፤ስለዚህ ዛሬ ገብታ ማደር አለባት፡፡

መካኒክ አስመጥታ ለማሰራትም የማይታሰብ
ነገር ነው፡፡ለዛ የሚሆን በቂ ጊዜ የላትም፡፡

በትራንስፖርት ለመሄድ ወሰነች፡፡በሻንጣ ይዛ
የነበረውን ልብስ ወደ ቤት መለሰችና አስፈላጊ የሆኑትን ብቻ ወደ ቦርሳዋ ቀነሰች፡፡ አንድ መኪና ያለው የቅርቧ የሆነ ሰው ጋር ደውላ ቃሊቲ መነኸሪያ ድረስ ስለሸኛት ሚኒባስ ተሳፍራ ወደ ሀዋሳ ጉዞ ጀመረች፡፡ቢሾፍቱን አልፈው ሞጆን ተጠምዝዘው ቆቃን ተሸግረው መቂ አካባቢ ሲደርሱ ረዳቱ ሂሳብ መሰብሰብ ጀመረ….፡፡

ዶ/ሶፊያ ጋር ደረሰ ‹‹ሂሳብ›› አላት፡፡ቦርሳዋን ከፈተች... ፈለገች... በረበረች.. የእጅ ቦርሳዋ የለም፡፡
ረዳቱ‹‹እህት ሂሳብ ››ሲል ጥያቄውን ደገመው፡፡

‹‹እዚ ውስጥ ነበር.. ቤት ረስቼው መጣሁ መሰለኝ››በጣም ደነገጠች፡፡ጠይም ፊቷ ላይ ላቧ ቸፍ አለባት፡፡

‹‹ገንዘብ አልያዝኩም..።››

‹‹ባክሽ ሙድ አትያዢ፡፡››

‹‹እውነቴን ነው፡፡ ሞባይሌም፣ገንዘቤም፣ የእጅ ቦርሳዬ ውስጥ ነበር..እዚህ ውስጥ የከተትኩት መስሎኝ ነበር፡፡››

‹‹እኔ ጭቅጭቅ አልፈልግም…ሂሳቤን ስጪኝ፡፡››ረዳቱ ፊት ነሳት፡፡

‹‹ወንድም አንዴ ሞባይል ብታውሰኝ››ስትል ከጎኗ የተቀመጠውን ወጣት ጠየቀችው፡፡ ጥቁር ቆዳ ጄኬት ለብሶ ጥቁር መነፅር ፊቱ ላይ የሰካ ደልደል ያለ ሰው ነው፡፡

‹‹ይቅርታ ባትሪ ዘግቷል››አላት፡፡ይሄንን የሰማው ከፊት ለፊት የነበሩ አንድ አዛውንት ሰጧት፡፡
ደወለች‹‹ሄሎ ሰኒ ..ሶፊያ ነኝ፡፡››

‹‹የእጅ ቦርሳዬ አለ..?እስቲ እይልኝ፡፡››

‹‹አዎ በናትሽ ....ባንክ ደብተሬም መታወቂያዬም ውስጡ ነው፡፡››

‹‹ምንም ብር አልያዝኩም፡፡››

‹‹ምን ማድረግ እደምችል አላውቅም፡፡ ብትልኪልኝ እራሱ እንዴት አወጣለሁ..? መታወቂያ የለኝም..፡፡››

‹‹በቃ ለማንኛውም ከፈለኩሽ ሚስኮል አደርግልሻለሁ..››ብላ ስልኩን ዘጋችና ለባለቤቱ በመመለስ ‹‹ወንድም ሀዋሳ የማውቃቸው ሰዎች አሉ፤ እንደደረስን እሰጥሀለሁ››ስትል መልሳ ወያላውን መለማመጥ ቀጠለች፡፡

‹‹ባክሽ ..ዝዋይ ላይ ትወርጂልኛለሽ››ውሳኔውን አሳወቃት፡፡

በጣም ተጨናነቀች፡፡አንገቷ ላይ ያንጠለጠለችው የእናቷን ማስታወሻ ሀብል ትዝ አላት፡፡ ከዚህ በላይ መጨነቅ እንደሌለባት ወሰነች ፤ሀብሉን የማስያዝ ሀሳብ መጣላት፡፡ ኔትወርኩ በመሀል ከሰራላት ለምታውቃቸው ሰዎች ደውላ መነኸሪያ እንዲጠብቋት በማድረግ ሀብሏን ታስለቅቃለች፡፡ እስከእዛ ግን እራሷን ከስቃይ ለማላቀቅ ወሰነች፡፡

ሀብሉን ከአንገቷ አወጣችና‹‹ እንካ ይሄንን ያዝ፡፡ ሀዋሳ ደርሰን ብርህን ስሰጥህ ትመልስልኛለህ፡፡››በማለት እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡ መቼም ይሄ ሁሉ ተሳፋሪ እያየ አይክደኝም ስትል ተስፋ አደረገች፡፡

የሰጠችውን ሀብል በእጆቹ ላይ እያገላበጠ ፈተሸና‹‹ሲስቱ ..አርቴ እንዳይሆን ብቻ፡፡፡››አላት፡፡

‹‹ባክህ ሃያ አራት ካራት ሆኖ 14 ግራም ወርቅ ነው፤ይልቅ በጥንቃቄ ያዘው፡፡››አለችው፡፡ በዚህን ጊዜ ከጎኗ ተቀምጦ የነበረው

እስከአሁን ነገሮችን በዝምታ ሲከታተል የቆየው ባለ ጥቁር መነፅሩ ወጣት ሁለት ድፍን የመቶ ብር ኖት አወጣና ሠጣት፡፡

‹‹ክፈይና ሀብልሽን ተቀበይው፡፡ለእኔ እዛ ስትደርሺ ትሰጪኛለሽ፡፡››

የወጣቱን ንግግር የሰማው ረዳት ተበሳጨበት፡፡እጁ የገባውን ዕድል ነው የነጠቀው<<የሆነ ምጥማጥ መልክ..የእርጐ ዝንብ ››በውስጡ አጉረመረመ፡፡

‹‹እግዜር ይስጥልኝ፡፡አመሰግናለሁ፡፡››በማለት ተቀበለችውና ለወያላው ወርውራለት ሀብሏን ተቀበለች፡፡ሠማንያ ብር መለሰላት፡፡ መልሱን ለወጣቱ ስትሰጠው‹‹ለውሃ ምናምን መግዣ ይሆንሻል..ያዢው፡፡ አንድ ላይ ትመልሺልኛለሽ፡፡››

‹‹የት ድረስ ነው የምትሄደው?››

‹‹ሀዋሳ ድረስ፡፡››

‹‹እንደደረስን እሰጥሀለሁ፡፡››

‹‹በማግስቱም ልትሰጪኝ ትችያለሽ፡፡››

እስኪሪፕቶና ወረቀት ከቦርሳዋ አውጥታ ሙሉ ስሟን ፤ ምትሰራበትን ቦታ እና ሁለቱንም የስልክ ቁጥሮቿን ፅፋ አቀበለችው፡፡ተቀበላትና እስኪሪፕቶውን ከእጇ በመውሰድ ወረቀቱን ገልብጦ ባልተፃፈበት በኩል የራሱን ጻፈና አጣጥፎ አቀበላት፡፡››

‹‹ምንድነው?››

‹‹ሲመችሽ አንቺው ደውይና ትሰጪኛለሽ፡፡››

ግራ ገባት ‹‹ባልደውልልህስ..?ብሸውድህስ?››

‹‹ብትደውይም አይደንቀኝ ..ባትደውይም አይገርመኝም፡፡››

‹‹አልገባኝም..፡፡››

‹‹ሁለቱም የሰው ልጅ ባህሪዋች ናቸው፡፡››ብሎ ብዙም ማውራት እንዳልፈለገ በሚገልፅ ስሜት ፊቱን ወደመስታወቱ አዙሮ ውጭ ውጩን ማየት ጀመረ፡፡

‹‹ሀብታም ወይም የሀብታም ልጅ ቢጤ ነው መሰለኝ፡፡ለዛ ነው የሚንጠባረርብኝ፡፡›› ስትል በውስጧ አሰበች፡፡

‹‹አይ አሁን ይህቺን ሁለት መቶ ብር አበደርኩሽ ብሎ በጅንጀና ያደርቀኛል፡፡›› ስትል ገመተች፡፡ ቆዳውን አዋዶ የእሷን ትኩረት
ለመሳብ እንዳቀደ እርግጠኛ ሆናለች፡፡‹‹ወንዶች እንኳን ይህቺን አይነት መግቢያ መንገድ አግኝተው ቀርቶ ድሮም ድሮ ናቸው፡፡›.አለች በልቧ፡፡

ዝዋይ ደረሱና ሚኒባሷ ለሻይ እረፍት ቆመች፡፡ ተሳፋሪዎች ሁሉ ወረዱና ሚያስፈልጋቸውን ነገር ገዛዝተው በመመለስ ጉዞው ቀጠለ፡፡ እሷም ወርዳ ውሀና መስቲካ ገዝታ ነበር፡፡አንድ ውሃ እና አንድ መስቲካ እያቀበለችው ‹‹በብድር ብር የተገዛ ቢሆንም እስኪ ልጋብዝህ፡፡››አለችው፡፡

ውሀውን ተቀበለና‹‹ጣፋጭ ነገር አልወድም፤ለውሀው ግን አመሰግናለሁ፡፡ >> አላት፡፡
👍899😁4🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ  እጅ  አወጣች…በስልጠናው  እየተሰጠ  ባለው  የዕለቱ  ትምህርት  በጣም ተመስጣለች…እና በውስጧ የሚጉላላ ጥያቄ ስለነበረ እሱን ለመጠየቅ ነው  እሺ ሳባ ጠይቂ

‹‹አንድ  ሴት  ከወንዱ  ጋር  ወሲብ  ስትፈፅም  እሱን  ማርካት  ላይ  ነው  ማተኮር ያለባት ወይስ ለራሷም የእርካታ ስሜት.መጨነቅ ይጠበቅባታል››
በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳሽው፡፡ የሴቶች ቆዳ ከወንዶች 10 እጥፍ በላይ ንቁ ነው፡፡ ወንዱ በወሲብ አማካይነት ከስሜቱ ይገናኛል፤በስሜቱ አማካይነት ደግሞ ወደነፍሱ ይመለሳል ሴቷ ግን በአብሮነት ውስጥ ድጋፍ እንዳገኘች ሲገባት ልቧ ውስጥ ተቀብሮ የነበረው ፍቅር ፈንቅሎ ይወጣና በዛ መንገድ መንፈሳዊ ፍላጎቶቿ ሲሟሉላት ወሲባዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት መዘጋጀት ትጀምራለች፡፡ ሴቷ የወሲብ እርካታ ለማግኘት ከወንዱ እጥፍ የሆነ ጊዜ ያስፈልጋታል ቢያንስ ለ20-30  ደቂቃ ያስፈልጋታል፡፡ የወንድ  ልጅ  መንፈስ ግን ለወሲብ ከተነቃቃ በኋላ መተንፈስ ካልቻለ መንፈሱ ብቻ  ሳይሆን አካሉም ምቾት ያጣል ሴቷ ግን  ባትረካም  በወሲብ  አማካይነት በሚፈጠረው ቅብ ብቻ ጥሩ ስሜት ሊሰማትና ደስተኛ ልትሆን ትችላለች፡፡
እንግዲህ ምን ማለት ነው የወንድና የሴት የወሲብ ዝግጅት ቆይታና እይታ ጭምር ይለያያል ማለት ነው፡፡ እና ወሲብ የምትፈፅሚው  ከምን  አይነት ሰው ጋር ነው እንዴት ነው ወንድዬውን ከጥድፊያ እንዲወጣና ነገሮችን በስክነትና በእርጋታ እንዲያደርግ ማድረግ ትችያለሽ.. አንቺስ ፈጥነሽ ወደ ወደሪቲሙ ለመግባት ምን ምን ዘዴዎችን መጠቀም አለብሽ እነዚህን መሰረታዊ መልስ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው ምክንያቱም ወንዱ በፍጥነት ይግላል በፍጥነት ይበርዳል አንቺ ዝግ ብለሽ ትግያለሽ ዘግየት ብለሽ ትበርጂያለሽ፡፡ ከእሱ ቀነስ  ከአንቺ  ጨመር  አድርጋችሁ  መሀከል  ላይ ስትገናኙ ነው  እኩል  መርካት  የምትችሉት፡፡ ግን  ምንም  አደረጋችሁት ምንም ሁል ጊዜ  ሴቷ  ከወንድ  እኩል  መርካት  አትችልም ቢሆንም  ያ ችግር የለውም ምክንያቱም ሴቷ ከእርካታው በላይ ለፕሮሰሱ ትልቅ ትርጉም ትሰጣለች፡፡ ዋናው ነገር በወሲብ ጥምረታቸው ግንኙነታቸው ይበልጥ መጠንከሩና ፍቅራቸውም ይበልጥ  እየጎለበት መሄዱ ነው፤ያ  ከእርካታ እኩል ውስጣዊ ደስታን ይፈጥርላታል፡፡ ለዛሬ እዚህ ላይ እናቁምና በተከታታይ  ቀናቶች  ብዛት  ያላቸውን  በወሲብ  ላይ  የተሰሩ  ዶክመንተሪ ፊልሞችን እየተመለከትን እያንዳንዱን በጥልቀት እንፈትሸዋለን፡
‹‹ሌላ ጥየቄ ያለው አለ?›› ሌላኛዋ ሴት እጅ አነሳች
‹‹አንድ ጥያቄ ነበረኝ…ፍቅረኛዬ ሌላ ሀገር ነው የሚኖረው በሶስት ወርም ሆነ በአራት ወር ይመጣል.. እና እንደመጣ እሱ ዘሎ ወሲብ ላይ ጉብ ማለት ነው የሚፈልገው እኔ ደግሞ እንዲያወራኝ እፈልጋለሁ ከሱ ውጭ ስላሳለፍኩት ልነግረው እፈልጋለሁ..እሱም እንዲነግረኝ እፈልጋለሁ…እና  ይሄ  ሰው እኔ ናፍቄው ሳይሆን የወሲብ ስሜቱን ለማርካት ይሆን እንዴ የሚመጣው ብዬ በማሰብ ቅሬታ ውስጥ እገባለሁ…ይሄ ነገር ሊብራራ ይችላል፡››

አሰልጣኟ ‹‹ጥሩ ጥያቄ ነው…››፡፡በማለት ማብራራቷን ቀጠለች


‹‹ሁለት ጥንዶች ከቀናቶች በኋላ ተነፋፍቀው ሲገናኙ ወንዱ ተጣድፎ ወደወሲብ ጫወታ መግባትያፈልጋል፤እንደዛም ለማድረግ ይቁነጠነጣል ሴቷ  ደግሞ ተቀምጦ ማውራትና በጫወታቸው መንደርደሪያነት ናፍቆትን መወጣት ትፈልጋለች፡፡ ቶሎ ክንዷን ጨምድዶ ወደ አልጋው ይዟት ከሄደ…ልክ ከውጥረቱ ለመርገብ እንደመጠቀሚያ እየተገለገለባት እንደሆነ እንድታስበ ያደርጋታል፡፡ በተቃራኒው የእሷ ወደአልጋ ለመሄድ ዳተኛ መሆን  ለእሱ  ሌላ  ትርጉም ይሰጠዋል…ብዙም እንዳልፈለገችው…በመመለሱ ብዙም ግድ እንዳልሰጣት በመገመት የመገፋት ስሜት ያስተናግዳል፡፡ ይሄንን በወንድና በሴትነት ምክንያት ያለን የባህሪ ልዩነት መረዳት ግን ለሁለቱም በመተጋገዝ ወደመሀል እንዲመጡና እርስ በእርስ የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት በግንኙነታቸው ላይ ጥቁር ነጥብ እንዳይጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ሴት ለወሲብ ልቧን ለመክፈት ፍቅር እንደሚያስፈልጋት ሁሉ ወንዱም ወደ ፍቅር ስሜት ዘልቆ ለመግባት ወሲብ እንደሚያስፈልገው መታወቅ አለበት፡፡ ወንድም ሆነ ሴት የመንፈስ ረሀብ አለባቸው፡፡ ግን ከዚህ ረሀባቸው ለመርካት የሚመገቡት የምግብ አይነት ግን የተለያየ ነው፡፡ ሴቷ ፍቅርን በመመገብ ከመንፈስ ርሀቧ ስታገግም ወንድ ደግሞ ወሲብን ተመግቦ ነው ረሀቡን የሚያባርረው፡፡ ከዛ ሴቷ ፍቅርን ተመግባ ከመንፈስ ርሀቧ ከጠገበች በኋላ ለማወራረጃ ቆንጆ ወሲብ ስታገኝ በጣም ደስተኛና ፍፁም የረካች ሴት ትሆናለች፡፡ በሌላ ጎኑ ወንዱም ሆድን ከሚቆርጠውና አጨናንቆት ከነበረው የመንፈስ ረሀብ ወሲብን ከተመገበ በኋላ ተነፈስ ይልና ቀጥታ በውስጡ የሚንቆረቆረውን የጋለ ፍቅር ልክ እንደውሀ በላዩ ላይ መከለስ ይጀምራል…ከዛ አጅግ ደስተኛ፤ዘና ያለና አይኖቹ የሚያበሩ ይሆናል፡፡ አለችና የእለቱን ትምህርት ዘጋች፡፡ ከዛም እንዳለችው ለ10 ቀናት  ያላዩት የወሲብ ፊልም፤ ያላወሩትና ያልተወያዩበት የወሲብ አይነት አልነበረም ሙሉ በሙሉ ነበር ስለወሲብ የነበራትን እይታ የቀየረባት፡፡ ወሲብ እሷ ከምታስበው በጣም በሰፋና በጠለቀ ሁኔታ በሰው ልጅ ዘመናት ታሪክ ሂደት  ውስጥ አስኳል ድርሻ እንዳለው ተረዳች አሁን ለዚህች አለም እንደጨው. እንደሆነ. ተገነዘበች ...ወሲብ. ለፍቅር፤ ወሲብ. ለገንዘብ፤ወሲብ.ለደስታ፤ወሲብ.ለስለላ…ወሲብለአምልኮ..ወሲብ.ዘርን.ለማስቀጠል…ወሲብ.ለበቀል….ብዙ ብዙ
   በሚቀጥለውም ወደመጨረሻው የሰልጠና ርዕስ ተሸጋገሩ

ተግባቦት ማለት በሁለት አዕምሮዎች መካከል ወይም በአንድ አዕምሮ ከሌሎች ብዛት ያላቸው አዕምሮዎች ጋር የሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከሌላው እንስሳት የተሻለ ነው የሚባለው በመግባባት ችሎታው ራሱን በመግለፅና በማስረዳት ክህሎቱ ነው፡፡፣አብዛኛው እንስሳት እርስ በርሱ ይግባባል…ከእኛ ከሰው ልጅ የሚጠበቀው የመግባባት ችሎታ ግን እንስሳቱ ከሚያደርጉት በላይ የላቀ እና ከዚህ በላይ የመጠቀ መሆን አለበት….ለአንድ ሰው ሀሳባችሁንና ፍላጎታችሁን ስትገልፁ አፋችሁን ከፍታችሁ ከንፈራችሁን አንቀሳቅሳችሁ በቋንቋ ብቻ በመጠቀም መሆን የለበትም፡፡ ከምንናገረው ቋንቋ ጋር አብሮ የሚሄድ የፊት ገለፃ፤የእጅ አንቅስቃሴና  የመሳሳሉት  መጣመርና  ተመሳሳይ  መልዕክት ማስተላለፍ አለባቸው፡፡

በጣም የሚወዳችሁ ሰው አበባ ይዞ ያላችሁበት ድረስ መጥቶ ‹‹የእኔ ፍቅር በጣም አፈቅርሻለሁ›› ሲላችሁ ምንድነው የምታደርጉት?፡፡ አንድም አበባውን ቀና ብላችሁ ሳታዩት ሰውዬውን ባለበት ጥላችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ ሁለተኛ  ስላፈቀርከኝም ሆነ ይሄንን አበባ በስጦታ መልክ ልታበረክትልኝ ስለመጣህ አመሰግናለሁ….ግን አዝናለው አልችልም ሌላ ፍቅረኛ አለኝ ብላችሁ በተከዘ  ፊትና በአዘነ የድምፅ ቃና ትመልሱለታላችሁ፡፡ ሌላው አማራጭ ደግሞ አበባውን ትቀበሉና ግን ፊታችሁን አጨማዳችሁ በሻከረ የድምፅ ቃና እኔም እወድሀለሁ...አመሰግናለሁ ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ ወይ ደግሞ አበባውን ተቀብላችሁ በሚፍለቀለቅና በደስታ በሰከረ ፊት አጅባችሁ የእኔ ማር!! በጣም ደስ የሚል አበባ ነው…በእውነት ነፍሴን ነው ያስደሰትካት...እኔም ውደድድ ነው የማደርግህ ››ትሉታላችሁ ወይ ደግሞ አበባውን ትቀበሉና እጆቻችሁን እንደክንፍ ዘርግታችሁ ትከሻው ላይ  በመንጠልጠል ጉንጮቹን አገላብጣችሁ በመሳም…‹‹የእኔ ፍቅር ይህቺን ቀን ስጠብቅ ነበር
👍6111👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ  ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው  ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን ወለል ላይ ተቀምጦ ይታያል…እሬሳውን ጭኖ ወደኢትዬጵያ የሚበረው አውሮፕላን በሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ይታያል…እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ለዘላለም አሸልባ  የተኛችው ምስራቅ ነች፡፡

ናኦል እና ኑሀሚ ከዳግላስ ወጥመድ አምልጠው የሲኦል ወጥመድ ከሆነው ከእዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ወጥተው እንሆ አስተማማኝን ቦታ ላይ ቆመዋል…ከአንድ ሰዓት በኃላ በአገራቸው አየር መንገድ ወደሀገራቸው ለመብረር ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል…ግን እዚህ ለመድረስ የከፈሉት መሰዋዕትነት ሁለቱንም እስከወዲያኛው ያፈራረሳቸው ነው፡፡አሁን በድናቸው ነው የሚንገዋለለው፡፡እግዚያብሄር በእድሜያቸው መጀመሪያ በዛ በህፃንነታቸው ጊዜ  ሚወዱዋቸውን ወላጆቻቸውን በመንጠቅ አሸማቆቸው ነበር  በእድሜያቸው አጋማሽ ደግሞ በእድሜ ልካቸው አብራቸው የነበረችውን፤ ከጎዳና አንስታ ህይወት የሰጠቻቸውን፤የተዘረፈውን  የወላጆቻቸውን ንብረት ያስለመለሰልችላቸውን.. እናም ከዛም አልፍ እሷን ለማትረፍ አህጉር አቆርጣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የገባችላቸውን የዚህችን  ሴት ህይወት ማጣት ለሁለቱም ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ለናኦል ደግሞ ነገሩ የተለየ ነው….ይህቺን ሴት ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ እዛ በረንዳ ፤ላይ ካያት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ይወዳት ነበር…እዚህ ነገር ውስጥ ያስገባት እራሱ ነው፡፡እህቴ ጠፋችብኝ አፋልጊኝ ብሎ ደወላላት..እሱን ለመርዳ ከጎሬዋ ወጣች..ለብቻው ልትተወው ስላልፈለገች አህጉር አቋርጣ ተከትላው መጣች ..አንድ ወር ሊደፍን ትንሽ ቀን ለቀረው ቀናት በመከራና በስጋት ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እጅግ ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ህይወት አሳልፈዋል….የህይወትን ጣእም እና የፍቅርን ትርጉም አሳይታዋለች ..አስተምራዋለች፡፡….ከእሷ ጋር የመሰረቱት የውሸት ትዳር ለእሱ በህይወቱ ካጋጠመው ተጨባጭ እውነቶች መካከል ምን እልባትም ዋነኛው  ነው…በሰላም ወደሀገራቸው ሲመለሱ ለምኖና እግሯ ላይ ወድቆ ጋብቻቸው ባለበት እንዲቀጥልና በእሷ እቅፍ ውስጥ ለዘላለም መቅለጥ ነበር የሚፈልገው፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር….ብቸኛ ምኞቱም ያ ነበር..፡፡ግን አሁን ሁሉ ነገር እንዳልነበረ ሆኗል….፡፡በሰልም እየሰቀችና እተፍለቀለቀች አብራው የመጣችው ሴት ይሄው ህይወት አልባ በድን እሬሳ ሆነ  በሳጥን ውስጥ ታሽጋ  ወደሀገሯ እየተመለሰች ነው፡፡እና ደግሞ በጣም እያበሳጨው ያለው ነገር  ምንም እንዳልተፈጠረ በህይወት ቆሞ አየር እየሳበ መሆኑን ሲያስብ ነው….ደግሞ እኮ የእሱን ሞት ነው ሞተችው፡፡
ነገሩ እጌት ነው  የተከሰተው  ብለን ወደኃላ ዞረን ስናስታውስ……
..
ከአራት ቀን በፊት  ነው፡፡ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ  የታገቱበት ክፍል ተከፈተ….የመጣው  የተለመደው የዳግላስ ተላላኪ ነው፡፡
ወደኑሀሚ አትኩሮ እየተመለከተ ‹‹ጌታዬ እየጠበቀሽ ነው››አላት፡፡

ኑሀሚ ከ30 ደቂቃ በፊት አምጥቶ የሰጣትን ውብ የራት ቀሚስ ለብሳና ተዘጋጅታ  የጠበቀችው ነበር፡፡ምስራቅንና ወንድሟ ናኦልን ተራ በተራ ጉንጫቸውን ሳመችና በዝግታ እርምጃ ልጁን ተከትላ ወጣች፡፡ቀደም ብሎ የተላከላትን ቀሚስ ለብሳ ወደታባለችው የእራት ግብዣ መሄድ የምርጫ ጉዳይ አይደለም…ግዴታ ነው..፡፡በሰዓቱ እያስጨነቃት የነበረው  ከእራት ቡኃላስ ሚለው ነበር?….ወደአልጋ እንሂድ ቢለኝስ?እንደዛ ስታስብ ዝግንን የሚያደርግ ቀፋፊ ስሜት ነበር የተሰማት፡፡እሷ ግን እኮ እንደዛ አልነበረችም፡፡ለአላማዋ ጥቂትም ጥቅም ይኑረው እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ተጋድሞ ወሲብ መፈፀም ልክ እንደካርታ ጫወታ  ዘና ብላ ምትፈፅመው ቀላልና ትርጉም የማይሰጣት ጉዳይ ነበር…ደግሞም በሰላይነት ሕይወቷ እንዲጠቅማት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ በቂ ስልጠና ወስዳለች…አሁን ግን አንድ ነገር ገብቷታል..ለካ በዛን ጊዜ ነገሩ ቀላልና የማያስጨንቅ ሆኖ የሚታያት  ስለሰለጠነችበት ብቻ አልነበረም…ልቧ ኦናና ባዶ ስለነበረ ነበር እንጂ፡፤አሁን ግን አንድ ሰው ገብቶበታል…ያ ሰው ደግሞ እሷን ለማዳን በቅርብ ርቀት ባለ ጫካ ውስጥ ሆኖ እቅዱን ስለሚያሳካበት ዘዴ እየተጨነቀና እያሰበ ነው…እና  እሷ ካለፍላጎቷም ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ወደአልጋ የመሄድን ጉዳይ በቀላሉ ምታየው አይደለም….ይሄ ነው ያስጨነቃት…የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ ስትገባ ግዙፉ ጠረጴዛ በምግብና በመጠጥ ተሞልቶ ተመለከተች፣አንድ ሴትና ሁለት ወንድ አስተናጋጆች ፈንጠር ብለው ግድግዳውን ተደግፈው ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው…እንደገባች ዳግላስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተራመደ…ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው…ከላይ ሰማያዊ ሸሚዝ ከዳለቻ ጅንስ ሱሪ ጋር አድርጎል…በፈገግታ ተጠጋትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት…ፈራ ተባ እያለች እጇን ሰነዘረችና ጨበጠችው፡፡

እጇን ሳይለቅ እየጎተተ ወደ ጠረጴዛው ወሰዳትና  ወንበር ስቦ አስቀመጣት..ከዛ ራመድ አለና  ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ወዲያው ለአስተናጋጆች በእጁ ምልክት ሲያሳይ ተንደርድረው መጡና ብርጭቆቸውን በመጠጥ ሞልተውላቸው ወደቦታቸው ተመለሱ፡፡
ከተቀዳለት መጠጥ አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ‹‹እንዴት ነው ቆይታ ?››ሲል ጠየቃት፡፡
ያለምንም ማስተባበል‹‹በጣም አሰልቺ ነው››ስትል ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ለስራ ጉዳይ ወጣ ማለት ነበረብኝ…አሁን ግን ተመልሼለው…ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ፍፅም ደስተኛ እንድትሆኚ የተቻለኝን አደርጋለሁ…ከነገ ጀምሮ የአማዛንን ድንቅ ውበት ጎዲያ ጎድጓዳዋን እያዞርኩ አሳይሻለው..እንስሳቱን ፤ወፎችን ፤ፏፏቴዎችንና ወንዙን ሁሉንም አንድ በአንድ አሳይሻለው..እናም ከቦታው ጋር በፍቅር እድትተሳሰሪ የተቻለኝን እጥራለው..ከቦታው ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር ፍቅር እንዲይዝሽ እፈልጋለው››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ ከአንተ ፍቅር እንዲይዘኝ ማድረግ ትችላለህ?››
‹‹እንግዲህ እቅዴ እንደዛ ነው››
‹‹ጥሩ ነው››ብላ በአጭሩ መለሰችለት
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››በጫወታው እንዲገፉበት ስለፈለገ ጥያቄውን ቀጠለበት፡፡
‹‹እስከማውቅህ ድረስ ሁሉንም ነገር    በጉልበትና በማስግደድ ነው የምታደርገው…..ቡኃላ እንዳፈቅርህ ማድረግ ሲያቅትህ እንዳትተኩስብኝ ነው የምፈራው…፡፡››ስትለው ከጣሪያ በላይ ተንከትክቶ ሳቀ..‹‹በይ በባዶ ሆዴ ከዚህ በላይ መሳቅ አልችልም ..እራት እንብላና ወደበረንዳ ወጣ ብለን መጠጣችንን እየተጎነጨን የጀመርነውን ጫወታ እንጨርሰዋለን…››አለና ሰሀን አነሳ …እሷም እንደእሱ አደረገኝ..እራት በልተው አስኪያጠናቅቁ ሀያ ደቂቃ አካባቢ የፈጀባቸው ሲሆን በዛን ጊዜ ውስጥ ብዙም የረባ  ነገር እልተነጋገሩም…፡፡.እራቱ እንደተጠናቀቀ ዳጋላስ እጁን ሊታጠብ ቀድሞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ …ወዲያው ከአስተናጋጆቹ አንዱ እቃ የሚያነሳሳ መስሎ ተጠጋት እና ጎንበስ ብሎ‹‹ነገ በዚህን ሰዓት››አላት፡፡፡አልገባትም‹‹ዋት››አለችው፡፡ደገመላት‹‹ነገ በዚህን ሰዓት..ተዘጋጁ››ብሎ የተበላበትን  ሰሀን ሰበሰበና እንዳቀረቀረ ከሳሎን ወጥቶ ሄደ፡፡
👍817👎2🥰1👏1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞንና የበፀሎት ቤተሰቦችን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አካባቢውን ያለውን እያንዳንዱን መስህብ በመጎብኘት ነው የሚያሳልፉት….እያንዳንዱ ውይይትና ምክረ-ሀሳብም በመዝናናት ውስጥ ሆነው የሆነ ቦታ አረፍ ሲሉ ወይም ቡና ለመጠጣት የሆነ ካፌ ሲቀመጡ በውይይትና በጫወታ መልክ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቢሾፍቱ አስጨናቂና ጭንቅላት የሚይዝ አይነት አልነበረም፡፡

በወንጪ ኢኮ ቱሪዝማ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት እና ለጉብኝት ዝግጁ ከሆኑት ዋና ዋና አይን ሳቢና ቀልብ አስደንጋጭ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
ጎሮ በሚባለው ስፍራ የተገነባው ጎሮ ካልቸራል ሴንተር የወንጪ ኢኮቱሪዘም ፓርክ አንዱ መገለጫና ውበት ነው፡፡ በህንፃው ላይ ባህላዊ ምግቦች የሚገኙበት ውብ የሆነ ሬስቶራንት..ባህላዊ የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶች የሚሸጥባቸው ሱቆች…የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት የሚያገለግል እስከ 3መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ውብ የሆነ አምፊ ትያትር ከአካባቢው ከሚገኙ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እና አካባቢው ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደታች ሀይቁንና ከማዶው ያለውን ተራራ ሲያዩት ልብን ስውር የሚያደርግ የተለየ አይነት አስደማሚ እይታ አለው፡፡

ከጎሮ 2.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ነዲ ካልቸራል ሴንተር ደግሞ ሌላው ልብ ሰዋሪ ቦታ ነው፡፡ነዲ ከስሙም መረዳት እንደሚቻለው በአካባቢው የሚመረት የወንጪ ማር እና የማር ውጤቶች እንደብርዝና ጠጅን ጨምሮ መሸጫ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ህንጻ ነው…የህንፃው ጠቅላላ ዲዛይን አገልግሎቱን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ውብ ነው፡፡በማር እንጀራ ቅርፅ የተሰራ ሁለት ሶስት ጓደኛሞች ተቀምጠው ቁልቁል ሚታየውን ውብ እይታ ዘና እያሉ ወሬያቸውን የሚጠረቁበት ውብ ስፍራ አለ፡፡

ሙለታ ወንጪ ሬስቶራንት ሌላው በስፍራው የሚገኝ ውብ ቦታ ነው …በዚህ ስፍራ ሬስቶራንቶችና ሱቆች የፈረስ ማስዋቢያና ባህላዊ እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች ሲኖሩ ኩኪስ ብስኩት የመሳሰሉትም ቀላል ምግቦችን ማግኘት ይቻላል ፡፡
ነዲ ሰስፔንድድ የመስታወት ቴራስ ሌላው በአካባቢው ያለ ውብ ህንፃ ነው፡፡ይህ የመስታወት ወለል ግማሽ ክብ አይነት ቅርፅ ሲኖረው በሶስት ድርብርብ ተደርጎ የተሰራና እላዩ ላይ ወጥታው በመስታወቱ አሻግረው ወደታች ሲመለከቱ ከስር የሚታየው አስፈሪ ገደል መሳይ ግን በአረንጓዴ ሳርና ተክሎች የተሸፈና ውብ ስፍራ በማዶ የሚገኘው የጠራ ሀይቅ …በቃ አስፈሪ ግን ደግሞ አስደሳች እይታ ነው፡፡ይህ የመስታወት ቴራስ በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 400 ኪ.ግራማ የመሸከም አቅም እንዳለው ቢታወቅም በርከት ያለ ሰው ከወጣበት ግን ከአሁን አሁን መስታወቱ ተፈርክሶ ሾልከን ወደገደሉ ብንንከባለልስ? የሚል የፍራቻ ስሜት ሰቅዞ የሚያሲዝ አይነት ነው፡፡ከዚህ አስደማሚ የመስታወት ቴራስ ጎን አምፊትያትር ያለ ሲሆን በተያያዥነትም…ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካፍቴሪያ አለ፡፡ከዚህ ስፍራ ቀጥታ ወደሎጅ የሚወስድ የመኪና መንገድ ከላይ የመስታወት ቴራሱ ላይ ሆነው ከስር ማየት ይቻላል፡፡
ከዛ ደግሞ የተፈጥሮ ፍል ውሀ ያለበት በደን የተሸፈነ ሲሆን በአካባቢው ጉሬዛ ፤ጦጣ አእዋፍት ፤አምቦ ውሀ የተፈጥሮ ፏፏቴ ይገኛል …ጎን ለጎን ያሉ ሙቅና ቀዝቃዛ ኩሬ የኬብል ድልድይ ፤ወንዝ ..ብዙ ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ ነገር ይገኛል፡፡የነዲ መዝነኛ ስፍራን እና የተፈጥሮ ፍል ውሀን የሚያገናኝ በብረት የተሰራ እስካይ ብሪጅ አለ፡፡ብሪጁ 72 ሜትር ርዝመትና ኖሮት ሀምሳ ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ አስፈሪ ግን ደግሞ የራሱ የሆነ ውበትና የተለየ ስሜት የሚያጭር ልዩ ድልድይ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ባለፈው አንድ ሰምንት ውስጥ የጎበኞቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ለበፀሎት ደወለላት
‹‹ሄሎ..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ…ገነት ገብቼለሁ››
‹‹ወደድሽው ማለት ነው››

‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ …?አካባቢው እኮ እንኳን እንደእኔ አፍጥጠው የሚያዩ ሁለት አይኖች ላሉት ሰው ይቅርና አይነ-ስውር ቢመጣበት እንኳን ውበቱ በሽታ ሳይቀር ይታወቀዋል፡፡››
‹‹ዋው ድንቅ አገላለፅ ነው….በጣም ማርኮሻል ማለት ነው…እኔንም አንድ ቀን ወስደሽ እንደምታስጎበኚኝ ትስፋ አለኝ፡፡››
‹‹በደንብ እንጂ…ለዛውም በቅርብ ነዋ››
‹‹አሁን የት ነሽ…?ላለፉት አንድ ሰዓት ለሊሴ ጋር በሳይክል አካባቢውን ስናካልል ነበር.. አሁን ድክም ብለን ነዲ ካልቸራል ሴንተር የሚባለው ስፍራ ላይ ነን ፡፡
‹‹ምነው…ጠጅ እየጠጣችሁ ነው እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ትኩስ ወለላ ማር እየበላን››
‹‹በቃ ..ሰዓታችሁን አልውሰድባችሁ…..ዘና በሉ››
‹‹እሺ ቸው…ለሊሴ ሀይ እያለችህ ነው፡፡››
‹‹ሀይ በይልኝ‹‹ስልኩ ተዘጋ፡፡
‹‹አንቺ ሀለቃዬን ምን ልታደርጊው ነው?››ለሊሴ በመገረም ውስጥ ሆና ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አደረኩብሽ…?››
‹‹እንዴ እያየሁ…ከተዋወቃችሁ ገና ሳምንት ነው..ግን ይሄውና በየቀኑ ይደውልልሻል፣ ገባሽለት እንዴ?››
‹‹አረ አንቺ ደግሞ…››በፀሎት እንደማፈር ብላ ተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምነው..ቢሆን ደስ ይለኛል..ምርጥ ሸበላና የተማረ ሰው ነው..በዛ ላይ ትህትና አለው…እና አንቺን እህቴን ብድርለት በጣም ደስ ይለኛል››
‹‹በይ አንቺ ካዳመጡሽ …ብዙ ታወሪያለሽ››

ለደቂቃዎች ሁለቱም ዝም ተባባሉና በየግላቸው ሀሳብ መብሰልሰል ጀመሩ፣…በፀሎት ድንገት‹‹አካባቢው ግን አያስደንቅም?››ብላ አዲስ የመወያያ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹ በጣም እንጂ…እያንዳንዱ ስፍራ የራሱ የሆነ እይታ አለው…አሁን ጎሮ ጋር ሆነሽ ቁልቁል ስታይ የተለየ አይነት እይታ..ከሊበን ሆነሽ ስታይው ደግሞ የተለየ አይነት እንደምታይው እዚህ ሆነሽ ስትመለከቾ ደግሞ ሌለ አይነት…በእውነት ይሄ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ቦታ በቀየርሽ ቁጥር የምታይውም ነገር ይቀየራል…››
‹‹አዎ እንግዲህ …አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም….››
‹‹እውነት ነው አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም››የሚል ጣልቃ ገብ ዓ.ነገር  ሁለቱንም ከተቀመጡበት በርግገው እንዲነሱ አደረጋቸው፡፡ሌላ ሰው ነበር ከጀርባቸው የተናገረው፡፡
‹‹አንተ….እንዴት?››
‹‹ያው እንደዚህ››አለና ሁለቱንም በየተራ ሰላም አላቸው፡፡ተያይዘው ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ሆነህ ነበር እንዴ የምትደውልልኝ…?››በፀሎት በገረሜታና ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ…››
‹‹እኔ ደግሞ ምን አይነት ሞኝ ነኝ ..የት ነሽ ስትለኝ ያለሁበትን በየዋህነት መዘርዘሬ››
‹‹ምነው ስለመጣው ከፋሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም››
የሰለሞንንና የበፀሎትን የማያቆርጥ ጥያቄና መልስ በዝምታ እየታዘበች በውስጦ እነዚህ ሰዎች ምንድነው እንዲህ ያቀራረባቸው..?ሰውዬውስ እሷን ፍለጋነው እንዴ እዚህ የመጣው
?እያለች በውስጦ ተብሰለሰለች ፡፡ልክ ልቧን እንዳነበበ ለጥያቄዎቾ መልስ ይሰጣት ጀመር…‹‹ያው ባለፀጋዎቹ ደንበኞቼ እዚህ ካልመጣን ሲሉ ተከትያቸው መጠሁ..ያው አስገድደው ሲያስደስቱኝ ምን ላድርግ..እየመጣሁ ሳለሁ ደግሞ እናንተ እዚህ እንዳላችሁ ትዝ ሲለኝ..የበለጠ ዘና አልኩ››
‹‹እና ታዲያ ሰዎችህ የታሉ?››በፀሎት ከወላጆቾ ጋር ድንገት ፊት ለፊት የመፋጠጥ ስጋት አስጨንቋት ጠየቀች

‹‹አሁን ክፍላቸው አረፍ ብለዋል….ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ሰዓት እረፍት ነኝ….›› በፀሎት‹‹እና ታዲያ ወደፍል ውሀ ለምን አንሄድም?››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡
👍6914
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


===============

በሶስተኛው ቀን አለማየሁና ሰሎሜ  ተደዋውለው  ተገናኙ፡፡ማታ አስራሁለት ሰዓት አካባቢ ሆቴል ነው የተገናኙት…ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው፡፡በሞቀና በጋለ ሰላምታ ተቀበላት ፡፡ምግብ አዘው በልተው መጠጥ እየተጎነጩ ወሬ ጀመሩ ፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነሽ..?ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ለጫወታ መጀመሪያ የሚሆን አ.ነገር ሰነዘረ፡፡
‹‹ቆይ እስኪ የእኔ ጉዳይ ይቆይ…ለመሆኑ አንተ እንዴት ነህ?››መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማለት..እኔ ደግሞ ምን እሆናለሁ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ማለቴ በቀደም ሳልጠይቅህ ….አገባህ እንዴ?››
‹‹አረ..በፍጽም፣ባገባ ኖሮ ቢያንስ ለእቴቴ ነግራት ነበር..ለእሷ ከነገርኩ ደግሞ ያው ልጇ ስለሆንሽ አትደብቅሽም ነበር፡፡››
‹‹አውቄዋለሁ….!!››
‹‹እንዴት .?ምኑን ነው ያወቅሽው?››
‹‹አንተ በቀላሉ የምትጨበጥ ወንድ አይደለህማ..አንድ ሴት አንተን አሳምና ወደ ጋብቻ ለመውሰድ በጣም ነው የሚከባዳት፡፡እርግጠኛ ነኝ ለማንም ሴት ከባድ ነው የሚሆንባት ፡፡››
‹‹እንዴ ያን ያህል አስቸጋሪ ሰው ነኝ እንዴ?››እሱን በተመለከተ በሰጠችው  አስተያየት የእውነት ገርሞት  ነው የጠየቃት ፡፡
‹‹አዎ እኔ እስከማውቅህ ድረስ፣ሀሳብህና ፍላጎትህ በደቂቃ ውስጥ  ነበር የሚቀያየረው…መቀሌም  ሞያሌም በአንድ ጊዜ መገኘት የምትፈልግ ለመረዳት አስቸጋሪ አይነት ሰው ነህ፡፡ማለቴ ነበርክ..አላውቅም ምን አልባት ባለፉት አምስት.. ስድሰት አመታት ተቀይረህ ሊሆን ይችላል..እኔ የማውቀው አሌክስ  ግን እንደዛ ነበር፡፡››
‹‹በእውነትን እንደዛ አይነት ሰው መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ደግሞም አንድ እህት ወንድሟን በተመለከተ ይሄንን የመሰለ አስተያየት መስጠት ያልተለመደ አይነት ነው፡፡፡››
‹‹እንዴት  ..ትክክለኛ ባህሪህን እኮ እየነገርኩህ ነው፡፡ለምሳሌ አስራሁለተኛ ክፍል ጨርሰን ማትሪክ እንደወሰድን  አብረን ተማክረን  ተግባረእድ ተመዝግበን  ነበር፡፡ትምህርት ሲጀመር ግን ብን ብለህ ቤቱንም ከተማውንም ለቀህ ጠፋህ .ፖሊስ  ለመሆን ተመዝግበህ  ማሰልጠኛ መግባትህን እንኳን ለእኔ መንገር አልፈለክም..ከእናቴ ነበር የሰማሁት፡፡ሁል ጊዜ የሆነ ነገር አብረን እናቅዳለን..ትግበራው ላይ ግን ድንገት ታፈነግጣለህ፡፡በዚህ በዚህ ሁሴንና አላዛር ካንተ በጣም የተሻሉ ናቸው፡፡እነሱ በቃላቸው ይፀናሉ…በተለይ አላዛር››
‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ..ለገዛ ባልሽ እያደለሽ ነው..?ለመሆኑ ሁሴን አሁን የት ነው ያለው?››
‹‹ያው ከመሀካላችን የተሻለ ጭንቅላት ያለው እሱ ነበር ፡፡አሁን  እንግሊዝ ሀገር የህክምና ዶክተር ሆኖ እየሰራ ነው…ግን በቅርብ ሳይመጣ አይቀርም፡፡››
‹‹አዎ ውጭ መሄዱንማ ሰምቼለሁ….ለማለት የፈለኩት ትደዋወላላችሁ ወይ ለማለት ነው?››
‹‹ከአላዛር ጋር እስክንጋባ ድረስ እንደዋወል ነበር፡፡ከዛ በኃላ ግን  ደውሎልኝ አያውቅም፡፡.እኔም አንድ ሁለቴ ልደውልለት ሞክሬ ነበር ስልኩን ቀይሮታል መሰለኝ አልሰራ አለኝ፡፡››
‹‹ተበሳጭቶብሽ ነዋ?››
‹‹ምን ያበሳጨዋል?››
‹‹በጣም  ያፈቅርሽ ነበር እኮ…!!››
‹‹ያፈቅርሽ ነበር ወይስ ይወድሽ ነበር?››
‹አንቺ ደግሞ …ሶስታችንም ነበር የምናፈቅርሽ..ይሄንን ደግሞ አንቺም በደንብ ታውቂያለሽ፡፡›.
የመደንገጥና ግራ የመጋባት ስሜት በፊቷ ላይ ተንፀባረቀባት ‹‹ምን እያልከኝ ነው…? እየቀለድክ ነው አይደል?››
‹‹አንቺ ነሽ እንጂ እየቀለድሽ ያለሽው…፡፡ ሶስታችንም ገና ማፍቀር እራሱ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በፊት እናፈቅርሽ ነበር፡፡እድሜያችን በሙሉ ማነው በይበልጥ ሚያፈቅራት እያልን ስንፎካከለርብሽ  ነው ያሳለፍነው፡፡››
‹‹እኔ ትምህርት ጨርሰን እስክንበታተን ድረስ አራታችንም እርስ በርስ የምንዋደድ የልብ ጓደኛሞች እንደሆን ብቻ ነበር የማውቀው፣በተለይ አንተ ወንድሜም ጭምር ስለነበርክ  በዚህ መልኩ ላስብህ አልችልም፡፡ ››
‹‹ይሄን አላዛር እስከአሁን እንዴት ሳይነግርሽ…?ለነገሩ ምን ብሎ ይነግርሻል፤ አውቀሽ እሱ እንዳይከፋ በማሰብ ያላወቅሽ መስለሽ እንደምታስመስይ ነው የሚያስበው፡፡››
‹‹እሺ የሁሴንስ ይሁን ..አንተ የእውነት ታፈቅረኝ ነበር?››
‹‹ለዛውም ልክ በሌለው መጠን ነዋ….ለአንቺ ስል የማላደርገው ምን አለ..ቢያንስ የሞዴሱ ታሪክ ትዝ አይልሽም?››
‹‹አንተ ..ደግሞ ታስታውሰኛለህ እንዴ?ስንት አመት ሙሉ አንተ ምትገዛልኝ እየመሰለኝ አንጀቴን ስትበላው ኖረህ…አለችና በሳቅ ፈረሰች..እሱም ተከተላት፡፡
ሁለቱም በምናባቸው ወደኃላ ተጓዙና ትካዜ ውስጥ ገቡ
ሰሎሜ የወር አበባዋ የመጣው በ14 አመቷ ነበር፡፡ያንን ደግሞ ከግሩፑ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቀው አለማየሁ ነበር፡፡የዛም ምክንያት ከሰሎሜ ጋር አንድ ቤት በመኖራቸው ነው፡፡ወር በመጣ ቁጥር ግን ለሞዴስ የሚሆን ብር እናትዬውን መጠየቅ እያሳቀቃት ስትበሳጭ ይሰማና ..ይሄንን ችግር የሚፈታበትን ዘዴ ማሰላሰል ይጀምራል፡፡
ከዛ ፡አላዛር በዛን ጊዜ   ከትምህር ሰዓት ውጭ የሱቅ ስራ ይሰራ ስለነበረ ወደእዛው ነው የሄደው፡፡
‹‹እሺ ቱጃሩ እንዴት ነህ?››
‹‹ያሄው እንደምታየው ነው....ምነው ብቻህን?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰሎሜን ወይም ሁሴንን አስከትለህ ይምትመጣ መስሎኝ ነበር፡፡››
ከሁለቱን ማንን ይዤ ብመጣ ነበር የምትደሰተው?››ሲል መልሱን እያወቀው ጠየቀው፡፡
‹‹ምን ለማለት ነው…?ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው …ለምን መርጣለሁ?››
‹‹ተው እንጂ …አታስመስል፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ…!››ብሎት ዝም አለ
‹‹ቆይ ..ሞዴስ አለህ እንዴ?››
አላዛር ደንግጦ‹‹የምን ሞዴስ?››ሲል ነበር መልሶ የጠየቀው፡፡
‹‹ሞዴስ ነዋ ..ሴቶች የወርአበባ ሲመጣባቸው ሚጠቀሙበት፡፡››ሲል ብራራለት፡፡
‹‹የለኝም፡፡››
‹‹ለምን አታመጣም..ሴቶች አይጠይቁህም?››
‹‹እሱማ አልፎ አልፎ ይጠይቁኛል፡፡››
‹‹እና ለምን አታመጣም?››
‹‹እንዲሁ…ብዙም አስቤበት አላውቅም…ግን አልገባኝም. .እንዴት ልትጠይቀኝ ቻልክ?፡››
‹‹አይ ሰሎሜ እኮ አላዛር ሞዴስ የሚሸጥ ቢሆን እኮ በየወሩ አንድአንድ ይሰጠኝ ነበር…በየወሩ እቴቴን አላስቸግርም ነበር ስትል ሰምቼት ነው፡፡››
በመደነቅ‹‹በእውነት እንደዛ አለች…?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ ብላለች››ሲል  ነበር ፍርጥም ብሎ የዋሸው፡፡
‹‹ግን የወር አበባ ታያለች ማለት ነው?››
‹‹እንዴ ለምን አታይም ሴት አይደለች?››
‹‹ማለቴ ገና ልጅ ነች ብዬ እኮ ነው፡፡››
‹‹ምነው አንተ መርጨት አልጀመርክም እንዴ?››
‹‹አንተ ደግሞ ታበዛዋለህ፡፡››
‹‹እንደውም ቆየች ..ባይሎጂ ላይ አልተማርክም እንዴ ..?አንድ ሴት እኮ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ የወርአበባ ልታይ ትችላለች፡፡››
‹‹እሱማ አውቃለሁ…በቃ አሁን አደገች ማለት ነው?››
‹‹አዎ ..በደንብ እያደገችልን ነው፡፡››
‹‹በቃ…ከነገ ጀምሮ አመጣለሁ፡፡››
‹‹ጥሩ ..ለዚህ ወር ተገዝቶላታል..ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ትሰጣታለህ፡፡››
‹‹አዎ..ምንም አታስቢ በላት፡፡››
‹‹እሺ እላታለሁ..የወር አበባዋ የሚመጣው በ22 ወይም በ23 አካባቢ ነው…ስለዚህ በ20 በ20 እየመጣሁ ወስድላታለሁ፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ግን እራሷ መጥታ ለምን አትወስድም፡፡››
👍458