አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
“ወንድ ልጅ ሲጎረምስ ፂም ማውጣት የተለያየ የሰውነት ክፍሉ ላይ ፀጉር ማብቀል.…እና ድምፁ
መጎርነን ይጀምራል ገባችሁ ?"
ስምረት እጇን ታወጣለች፣ “ፀጉር የሚወጣባቸው የተለያዩ አካላት የትኞቹ ናቸው ቲቸር?"

“ውይ አንች ደግሞ ፈተና ላይ የማይመጣ ነገር ምን አጠያየቀሽ ? ትልና ታፍራለች እትዬ፤ ሁላችንም እንስቃለን፡፡

መስፍን እጁን ያወጣል በተራው፣ የመስፍን ማውጣት ይገርመናል፤ በገመድ አስረውም
ቢጎትቱት እጁ የማይዘረጋ ልጅ ዛሬ እጁን ሲያወጣ ይገርመናል፡፡ ሽባ የተተረተረ ያህል በግርምት
እንመለከተዋለን፡፡

"ሴት ስትጎረምስስ ምን ምልክት ይታይባታል ?” ብሎ ይጠይቃል፤ ክፍሉ በሳቅና በጩኸት
ይደበላለቃል፡፡ እትዬ ታፍራለች፡፡
“ዝም በሉ ልክ ነው ጥያቄው የምን መገልፈጥ ነው፡፡ እስቲ ከእናንተ ይህን ጥያቄ የሚመልስ”
ትልና እኛኑ ታጋፍጠናለች፡፡ ቶማስ እጁን ያወጣል “ሴት ስትጎረምስ ያው…አለ አይደል..” ብሎ
ደረቱ ላይ እጆቹን ያሳርፍና እንደ ጡት ያጎብጣቸዋል፡፡ የከፍሉ ተማሪ በሳቅ ያውካካል፡፡

እትዬ በሃፍረት መግቢያው ይጠፋባታል፤ ድንገት አንድኛችንን ትጣራለች፡፡

"አብርሃም !

"አቤት!” እላለሁ በድንጋጤ፤"

“የሴት ልጅ ጉርምስና ምልክቶች ምን ምን ናቸው?”

በፍርሃት ላብ ላብ እያለኝ እየፈራሁ ሞከርኩ “ስ…..ልክ”

“ምን ”

“ስልክ ማለት የአባዬ ስልክ” ከፍሉ በሳቅ ተንጫጫ፤

“ጥያቄው አልገባህም." ብላ እንድቀመጥ ምልክት አሳየችኝ፡፡ “መልሱ ስላልገባት ጥያቄው
አልገባህም ትላለች እንዴ!”ብዬ አኮረፍኩ፡፡

አጎጠጎጤ፣ የድምፅ መስረቅረቅ፣ የዳሌ መስፋት እና የወር አበባ ማየት የሴት ልጅ ጉርምስና
ምልክቶች መሆናቸውን ባዮሎጂው ነገረን፡፡


ትዕግስት የምትባል የክላስ ልጅ የወደድኩት በዛው ሰሞን ነበር፡፡ ትዕግስት ቆንጆ፣ በነፃነት
ያደገች የሃብታም ልጅ ናት፡፡ ቤታቸው ስልክ አላቸው ፡፡ ብቸኛ ችግሯ አውርታ የማትጠግብ፣
ሳታቋርጥ ሙሉ ቀን የምታወራ ወሬኛ መሆኗ ነበር፡፡ ስታወራ በጣም ትጮሃለች፡፡ በቃ ቀስ
ብሎ ማውራት አትችልም ፡፡
ሁሉን ነገር ለመሞከር የቸኮለች ከመሆኗ ብዛት ጓደኛ እንሁን ብዬ በጠየቅኳት በቀጣዩ ቀን

ከክፍላችን ኋላ ተቀምጠን ጉንጬን ስማኝ አስነዘረችኝ፡፡ ከምር ነዘረኝ፡፡በቀጣዩ ሳምንት ከንፈሬን ስማ ንዝረቱን ከፍ አደረገችው በጣም ስለወደድኳት ከትምህርት ቤት ውጭ ላወራት ፈልጌ እኔም የአባዬን ስልክ ቁጥር ሰጠኋት።


አንድ ቀን ከወደ አባዬ ቤት ስሜ ተጠራ፣

"አብርሽ ስልክ"

“አቤት መጣሁ " አለቸ እናቴ!

"ጋሼ አይደለም አብርሽን የሚፈልግ ሌላ ሰው ነው አለች ሚጣ፡፡ ልላ ሰው የታወቀ ነው የታወቀ ነው ትርጉሙ

አባዬ ቤት ስደርስ የገጠመኝ ነገር አስደንጋጭ ነበር፡፡ ቀኑ የኪዳነምህረት ቀን ነበር፤ አባዬ ቤት ዝክር ተደርጎ ፀበል ጸዲቀ ስለነበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበው ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ ግጥም ብሎ ያውካካል፡፡ መራመጃ እንኳን አልነበረም፡፡ ግጥም ብሎ በሰው ተሞልቷል ቤቱ ደግሞ ለክፋቱ ስልኩ ስር ያለች ኩርሲ ላይ እማማ በላይነሽ የሚባሉት የሰፈራችን ነገረኛ ባልቴት ተቀምጠዋል) ገና ከመግባቴ ለከፉኝ፡፡

“አብቹ አንተም መጣህ ና እለፍ በዚህ!” አሉኝ፡

የደወለችው ትዕግስት ነበረች፡፡ በሆነ ነገር ተደባብረን ስለነበር አትደውልም ብዬ ነበር፡፡ ትዕግስት
በባህሪዋ ጫሂ ናት፡፡ እንክዋን የሚጮህ ስልከ ጋር ተዳምራ! የስልክ ንግግር ሳይሆን ለዛ ሁሉ
ስው አዋጅ የምታወጅ ነበር የምትመስለው፡፡

“አብርሽዬ?"

“አቤት" አልኩ ኮስተር ብዬ፡፡ ፀበል ቀማሹ ሁሉ ወሬ ቅመስ ተብሎ የተጠራ ይመስል ጭጭ ብሎ ጆሮውን ቀሰረ፡፡

“አብርሽ ምነው ጨዋ ሆንክ?” አለችኝ ትዕግስት፡፡ ልክ እንደ ራዲዮ ድራማ ፀበልተኛው ይሰማል፡፡

"እ"

“አብርሽ ችግር አለ..? ትላንት ከንፈርህን ስለሳምኩህ ደበርኩህ?”

እግዚኦኦኦኦኦኦኦኦ! ስልኩ አጠገብ የኪዳነ ምህረት ስዕል ተቀምጧል፤
ኪዳነምህረት የዚችን ልጅ አፍ ወይም የፀበልተኛውን ጆሮ ከዘጋሽልኝ የዛሬ ወር አንድ ፓኮ
ሻማ ብዩ ተሳልኩ፡፡ ስልኩን በጆሮዬ ለማፈን ወደ ጆሮዬ ጥብቅ እድርጌ አስጠጋሁት፡፡
ትዕግስት ትቀባጥራለች፡፡

አብርሽ እኔኮ ሴክስ እናድርግ ስትለኝ እንቢ ያልኩህ ፈርቼ ነው፤ በናትህ አብርሽ…እሽ በቃ
አርብ እክስቴ ቤት አድሬያለሁ ልበልና አንተም አመቻችተህ…”

እማማ በላይነሽ ወሬ እያዳመጡ ፉት ያሉት ጠላ ሰርናቸው ውስጥ ገብቶ ትን አላቸው፡፡ከኩርሲያቸው ላይ እስኪፈነገሉ ተንፈራፈሩ፡፡ “…ውሃ ውሃ ስጧቸው ! ጀርባቸውን ምቷቸው!” ይል ጀመረ ፀበልተኛው፡፡ እኔም የአባዬን ስልከ ዘግቼ ቀስ ብዬ ወጥቼ ተፈተለኩ፤ ወደ ቤቴ፡፡

"ወዲያው ሰፈሩ ውስጥ ዝናዬ በመወራቱ እናቴ አበደች"

“እንዴት ታዋርደኛለህ! እንዲህ ላገር መሳቂያ ታደርገኛለህ፣ አብረሃም?! ... አባቱ ሳይኖር ሴት
ቢያሳድገው ልታስብለኝ ....” እያለች እንባ እየተናነቃት ስትገስፀኝ በመሐሉ ቢጣ ተጣራች፡፡

“ሶስና…ሶሲ ..ስልክ ጋሼ አይደለም ! ሌላ ሰው ነው !፡፡ እናቴ በድንጋጤ ውሃ ሆነች፤ ሶስና
ትንሿ እህቴ ናት፡፡ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ፤ ሶሲ ጎረመሰች ፤ በእህቴ መጎርመስ እኔ እና እናቴ
መደፈር ተሰማን፡፡ አናግራ ስትመለስ ልንወርድባት ተዘጋጀን!

አለቀ
👍36😁18🔥3
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከሲልቪ ቤት ወጥቼ ወደ
ሲቴ አመራሁ፡፡ ትላንት “ማታ ባህራም ኪሴ ውስጥ ያስቀመጠውን ወረቀት መንገድ ላይ አነበብኩት፡፡ ኒኮል የፃፈችለት ደብዳቤ ነው
«ውድ ባህራም
«እንዴት ልጀምር? አስቸጋሪ ነው። እወድሀለሁ፣ ከልቤ እወድሀለሁ። አሁን የምነግርህ ነገር የማልወድህ ሊያስመስለኝ
ይችላል። ግን እወድሀለሁ፤ ከልቤ አፈቅርሀለሁ
«ያለሬቮሉሽን መኖር አትችልም። ከኔ ጋር መኖር አትችልም። ስለዚህ እኔን ትተኸኝ መሄድ አለብህ
«እኔ ስለሪቮሉሽን በጭራሽ ሊገባኝ የማይችል ብዙ ብዙ ነገር
አለ። ለምሳሌ ደም ማፍሰስ። ብዙ ተከራክረንበታል፣ ታስታውሳለሁ::
ደጋግመህ አይገባሽም! ስለሪቮሉሽን በጭራሽ አይገቤሽም ብለኸኛል። እውነትክን ነው:: አይገባኝም። ግን በደምብ የገባኝ አንድ ነገር አለ። አንተ ያለ ሬቮሉሽንህ መኖር አትችልም። ስለዚህ መለያየት አለብን።

“ከዚህ ቀጥሎ የምነግርሀ ሊገባህ አይችልም። ስለዚህ እንዲገባህ ለማድረግ አትሞክር። ዝም ብለህ እመነው። ይኸው የማፈቅረው አንተን ነው። የተረገዘው ልጅ ግን ያንተ አይደለም። የሉልሰገድ ነው። ልነግርህ ሞክሬ ነበር። ብዙ ጊዜ ሞከርኩ፣ አቃተኝ፡፡ አሁንም
ቢሆን መነፅራሙ ጓደኛህ ባያግዘኝ ኖሮ አልችልም ነበር

አዝናለሁ:: ስላደረስኩብህ ሁሉ ችግር በጣም አዝናለሁ።
ብትችል በልብህ ይቅር በለኝ። ባትችል ጥላኝ፡፡ ብቻ ሂድና
ሬቮሉሽንህ ውስጥ ኑር። ደስታ ሊስጥህ የሚችል እሱ ብቻ ነው።
በሄድክበት ይቅናህ፡፡ ደህና ሁን።
ያንተ ኒኮል።
P S ልታገኘኝ አትሞክር። አታገኘኝም። ልሰናበትህ ባለመቻሌ አዝናለሁ። ግን ፊትህ ላይ ቂም ማየት እፈራለሁ። ደህና ሁን። ይህን ደብዳቢ ሶስት ጊዜ ደጋግሜ አነበብኩት፡፡ ኒኮል ለምን
ፃፈችው ይህን? ቀዳደድኩት። ቁርጥራጮቹን በተንኳቸው:: ሲቲ ሄጄ ገላዬን ታጥቤ፣ ልብሴን ቀይሬ ወደ ኒኮል ቤት ሄድኩ አልጋዋ ላይ ተጋድማ ሲጋራ እያጨሰች ሙዚቃ ትሰማለች ታቹን ነጭ ክሮሽ እንደ ሸማኔ ጥለት የከበበው ቡና አይነት ቀሚስ ለብሳለች። ስገባ ፈገግ እያለች
«እንኳን መጣህ! ጭር ብሎኝ ነበር» አለችኝ
ደህና ነሽ?
«ደህና ነኝ፡፡ በጣም ደህና ነኝ። ግን ሌላ ሰው ማየት
አልፈልግም። እባክህን በሩን ቆልፈው።
ቆልፌው ስመጣ፣ የተጋደመችበት አልጋ ላይ እንድቀሙጥ በእጇ አመለከተችኝ። ጥፍሮቿ ሀምራዊ ተቀብተው ያብለጨልጫሉ።
ተቀመጥኩ፣ አየሁዋት። በጣም የተለወጠች መሰለኝ፡፡ ከንፈሮቿ እንደ ጥፍርቿ ሀምራዊ መሳይ ቀለም ተቀብተዋል፡ ቅንድቦቿን ወደ ሰማያዊ የሚወስድ ጥቁር ቀለም አድምቋቸዋል፣ ከግምባሯ ንጣት ጋር ሲታዩ በጣም ያምራሉ። የአይኖቿ ቆዳ ልክ የአይኖቿን
የሚመስል ውሀ እረንጓዴ ኩል ተቀብቶ፣ አይኖቿ ውስጥ ተነክሮ
የወጣ ይመስላል። ከመጠን በላይ አምሮባታል። ከጥንታዊት
ግብፃዊት ጋር ያለሁ መሰለኝ። ፀጉሯ እንደ ድሮው አመዳም
አይደለም፡ ንፁህ ቡናማ ቀለም ተነክሯል
«ምን ነካሽ?» አልኳት
«ምነው?»
«እንደዚህ የምታምሪ አይመስለኝም ነበር»
"Merci
«እውነት ግን ምንድነው?» አልኳት
«እንደዚህ ነኝ፡፡ ሳዝን ሰው እንዲያውቅብኝ አልፈልግም። አሁን
ያዘንኩ እመስላለሁ?»
በጭራሽ
«ለዚህ ነው አይኔንም የተኳልኩት፣ ፀጉሬንም የተነከርኩት»
«አዝነሻል?»
«እንደ ዛሬም አዝኜ አላውቅ፡፡ ሲሄድ ደህና ዋል አለህ?»
«አዎን»
የፃፍኩለትን አሳየህ?»
«አዎን፡፡ ለምን ፃፍሽው?»
«እንዴት እንደፃፍኩት ልንገርህ?»
«ንገሪኝ»
«ከትላንት ወድያ ማታ፣ እንደዚህ ተጋድሜ ሙዚቃ ስሰማ፣
አንድ ሰው መጣ፡ መልኩ ሰው ይመስላል እንጂ እንደኔና እንዳንተ
ህዋሳቱ ውስጥ ደም እንደሚፈስ ልምልልህ አልችልም። ምናልባት
ከነሀስ የተሰራ ሰው ሊሆንም ይችላል። ረዥም ቀጭን ነው፡ መነፅር ያረጋል። ግምባር የለውም፡ ከአይኑ ቀጥሎ አናቱ ይመጣል፡፡ ድምፁ ወፍራም ከመሆኑ የተነሳ ከሆዱ እንጂ ከጉሮሮው የሚወጣ
አይመስልም»
«ጠልተሽዋል እ?»
«መጥላት አይደለም፡፡ ፈራሁት። ቀፈፈኝ፡፡ አየህ፣ ገባና
በወፍራም ድምፁ
ኮል ማለት እርስዎ ነዎት?» አለኝ
ነኝ» አልኩት
“ጥሩ። እኔ ከኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ተልኬ የመጣሁ ነኝ
«ታድያ እኔ ከኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ምን አለኝ?
«እርስዎ አይናገሩ፡፡ ጊዜ የለኝም» አለኝ፡፡ ድምፁ በጭራሽ
አይለዋወጥም፡፡ ምንም ነገር ሲናገር በዚያው በወፍራም ድምፅ ነው
“የኢራን ኮሙኒስት ፓርቲ ባህራምን ይፈልገዋል፡፡ በጣም
ይፈልገዋል። እኔን ፓርቲው ልኮኛል። ከትእዛዝ ጋር፡፡ ወያም
ባህራምን ይዘኸው ና፣ ወይም ገድለኸው ተመለስ ተብያለህ
ግደለው? ለምን?» አልኩት
ቀላል ምክንያት፡፡ የኛን ምስጢር ያውቃል፡፡ ምስጢራችንን
በሙሉ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፣ ወይም ከኔ ጋር ይምጣል፡ ወይም
ይሞታል። ሌላ ምርጫ የለም፡፡ ግን አንድ ነገር አለ» አለኝ
ምን?»
ባህራም አልመጣም የሚለው በእርስዎ ምክንያት ነው:: እርስዎ
ባይኖሩ ይመጣል፡፡ ስለዚህ እርስዎ እንዳይኖሩ ማድረግ፡፡»
ሆዱ እየፈራ፤ «እንዴት?» አልኩት
«መግደል» አለኝና፣ ከኪሱ አንድ የታጠፈ ጩቤ አወጣ፡፡ ጫን
ሲለው ጩቤው እንደ ብልጭታ ክፍት አለ ሻህን ልግደለው!' አለኝና፤ ያንን የኢራን
ስእል አመለከተኝ፡፡ ባህራም ነው እዚያ የለጠፈው፡፡ ልተኛ ስልና ልነሳ ስል፣ ሻህ እንዲታየኝ እፈልጋለሁ ብሎ ሰቀለው::»
ግድግዳው ላይ የኢራን ሻህ የጦር ጠቅላይ አዛዥ የማእረግ
ልብሱን ለብሶ ቆሞ በከለር የተነሳው ትልቅ ፎቶ አለ
"ለምሳሌ ሻህ እርስዎ ነዎት። ጉሮሮውን ይመልከተቱ" አለና
ጩቤዋን ወረወራት። የሻህ ጉሮሮ ላይ ስክት አለች። ሰውየው ወደ
ስእሉ ሄዶ ጩቤውን ነቀለና አጥፎ ኪሱ ከተተ መንገድ ላይ እርስዎ ሲራመዱ ወይም ሲሮጡ እኔ በፈጣን መኪና እየሄድኩ ጩቤ ብወረውር፣ ጉሮሮዎትን እልስተውም፡፡ ገባዎት?» አለኝ። በድምፁ ሊያስፈራራኝ በጭራሽ አልሞከረም፡ ልክ የጂኦሜትሪ ፕሮብሌም እንደሚያስረዳኝ ያህል ነበር ገባኝ» አልኩት። እንደዚያን ጊዜ ፈርቼ አላውቅም
«ለባህራም ይንገሩት»
«ምን ብዩ?»
«ያረገዝኩት ካንተ አይደለም፣ ይበሉት
«ታድያ ከማን ነው ልበለው?»
« እንደፈለጉ። ለምሳሌ እጀምሺድ ወይም ከሉልሰገድ ነው
ሊሉት ይችላሉ፡፡ እነሱን ሊጠይቃቸው አይችልም»
«እሺ» አልኩና ደብዳቤውን ፃፈኩ። አጣጥፎ ኪሱ ሲከተው
«ባሀራም ይህንን ካነበበ በኋላም ከርስዎ ጋር መሄድ ባይፈቅድስ?»
አልኩት
«እምቢ አይልም»
«ቢልስ?»
«እገድለዋለሁ። ደህና እደሩ» አለኝና ወጣ። እንደሱ ያለ
ከሰውነት የራቀ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም
ኒኮል ዝም አለች፡፡ ዝም ብዬ እየኋት። በጣም ታምራለች።
ውሀ እረንጓዴ ኩሏና ሀምራዊ የከንፈር ቀለሟ የፈርኦን ዘመን
ግብፃዊት አስመስሏታል። ሳቅ አለች
«ምነው ትኩር ብለህ ታየኛለህ?»
«አማርሽኝ» አልኳት። ውስጡን ደነገጥኩ። እንደዚህ ለማለት
አላሰብኩም ነበር። ውሀ አረንጓዴ ቆዳ ሽፍን ግልጥ በሚያደርጋቸው
ውህ እረንጓዴ እይኖቿ አየችኝ፡፡ ሀምራዊ ከናፍሯ በፈገግታ
ተላቀቁ። እጄን ጉልበቷ ላይ አሳረፍኩ፣ አልከለከለችኝም
«ጫማዬን ላወልቅ ነው» አልኳት
👍285
ኮቴንም ኣውልቄ አጠገቧ ተጋደምኩና እጄን አንተራስኳት
“ደራሲ መሆን እንደምፈልግ ታውቂ የለ?» አልኳት
«አውቃለሁ፡፡ ልትጠይቀኝ " ምትፈልገው ጉዳይ እንዳለም
አውቃለሁ»
“ታውቂያለሽ?
«አዎን፡፡ ለምሳሌ፣ ልጄ ምን ይሆናል? አይደለም አንዱ
ጥያቄህ?»
«ካልፈለግሽ አትመልሺ»
“ብነግርህ ግድ የለኝም። መሀን ለሆኑ ሰዎች አራስ ልጆችን
የሚሰጥ ድርጅት አለ። ወልጄ ልጄን ለድርጅቱ አስረክባለሁ፡፡»
«ለምን አላስወረድሽውም?
«ለምን ገድለዋለሁ? ቢኖር እይሻለውም? እኔኮ በህይወት
አምናለሁ፡፡ አንተስ አታምንም?»
«አምናለሁ፡፡ በህይወትም በውበትም አምናለሁ» አልኩና
ጉንጫን ሳምኳት። ራሴን በለስላሳው ወደዚያ እየገፋች
«ቆይ» አለችኝ
«ምነው?»
«ሌላ ነገር እያሰቡ ሲስሙኝ አይመቸኝም፡፡ መጀመሪያ ጥያቄህን
ሁሉ ልመልስልህ»
«እሺ»
«የሚቀጥለው ጥያቄሀ፣ ልጁ የማን ነው? ነው:: እርግጠኛ
አይደለሁም። የጀምሺድ ወይም የባህራም ሊሆን ይችላል። ግን
የሉልሰገድ አይመስለኝም፡፡ የመጨረሻ ጥያቄ፣ ባህራምን እወደዋለሁ
ወይ? አዎን 'ወደዋለሁ። ከልቤ 'ወደዋለሁ፣ አፈቅረዋለሁ። እንግዲያው ለምን ጀምሺድንና ሉልሰገድን ጠቀለልኳቸው? አላውቅም። ግን
አይቆጨኝም፡፡ የተጋደሉት በኔ ምክንያት ይመስለኛል። አሳዘኑኝ።
በወጣትነታቸው በመቀጨታቸው አዘንኩላቸው:: ግን እዚህ ውስጥ
እኔ ጥፋተኛ ነኝ ብዬ አንድ ጊዜ እንኳ አምኜ አላውቅም፡፡ ገና ለገና
ሁለቱ ተኝተውኛል ተብሎ፣ ከዚህ በኋላ፣ እኔን ነፃነትና ምርጫ
እንዳላት ሴት ሳይሆን፣ እንደ ንብረት ቆጥረው ተጣሉብኝ፡፡ ስለዚህ የራሳቸው ጉዳይ ነው»
አየኋት። ስለምንም ግድ የሌላት፣ በጣም ጠንካራ፣ በጣም ቆንጆ
ሴት ናት። በሀይል ደስ አለችኝ።
“Tuten fouts, eh?” አልኳት ደንታ የለሽም፣ እ?»)
“Epédument?” (ብጭራሽ» አለችና፣ እንደተጋደምኩ ብድግ
ብላ፣ በክርኗ ትራሱ ላይ ተደግፋ ወደታች እየችኝ። ጎምበስ ብላ
አይኖቼን ተራ በተራ ሳመቻቸው። ፈገግ እያለች
«ስላንተም ቢሆን ደንታ የለኝም፡፡ ስለኔ ምንም ብታስብ የራስህ
ጉዳይ ነው:: ብቻ ደስ ትለኛለህ፡፡ በሀይል ደስ ትለኛለህ፡፡ እንዴት
ቆንጆ ነህ!» አለችና ጎምበስ ብላ ታምራዊ ኣፏን ኣፌ ላይ ደቀነች፡፡
አቀፍኳት። ውብ ብልግና ተጀመረ
ያቺ ልጅ መንግስተ ሰማያትን እጣጥፋ ጠቅላ በጭኖቿ
ውስጥ ደብቃ ነው " ምትዞረው ልልህ እችላለሁ . . . እኔ ምለው፡
እንደ ኒኮል ያለች ሴት እየተኙ ሁለት አመት ኖረው ቢሞቱ
ምናለበት? ቢሰነብቱ ትርፉ ማርጀት አይደለም? እርጅና መጥቶ፣ አጥንቶቼን አኮራምቶ፣ ጅማቶቼን ሽምቅቆ፣ ቆዳዬን አጨማዶ፣ አይኔን አጨናብሶ፣ ጠረኔን ሰርቆ በቁሜ በኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች ሽታ ከሚገንዘኝ፣ ኒኮልዬ ጭኖች መሀል ገብቼ ሙቀቱ ውስጥ ቀልጬ፣ ርጥበቱ ውስጥ ሟሙቼ ጥፍት ብል እመርጣለሁ።
የሰው ልጅ መጨረሻውን መምረጥ ቢችል' መጨረሻዬ ኒኮል ውስጥ ቢሆንልኝ እመርጣለሁ. . .»

💫አለቀ💫

ውድ አንባብያን ሆይ
ይህን በነፃነት ተኑሮ፣በነፃነት ተፅፎ፣በነፃነት የታተመውን ልብ ወለድ እየተዝናናችሁ አልፎ አልፎም እየሳቃችሁ እንዳነበባችሁት በመተማመን እጆቼን(ሁለቱንም) በቡራኬ እየዘረጋሁ
"ኑሩ በሰላም "

ስብሐት ለአብ
👍25🥰1
አትሮኖስ pinned «#የአባዬ_ስልክ_እና_ባዮሎጂ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እንዲህ እንደዛሬው በየሰዉ ኪስ ሳይልከሰከስ በፊት ስልክ ተዓምራዊ የሀብት መለኪያ ነበር፡፡ አቤት ስልክ እንዴት እንደሚከበር ! እንደሚፈራ.! ያኔ ኔትወርክ እንጂ ስልክ አልነበረም፡፡ዛሬ ግን ስልክ እንጂ ኔትወርክ የለም። እንግዲህ በሰፈራችን አንድ የቤት ስልክ ብቻ ነበረ ያለው፤ ስሙ ደግሞ “የአባዬ ስልክ”፤ ብዙው የሰፈር ሰው የእኔን እናት…»
#ትንሽ_ወደግራ_ዘምበል...
:
:
#በአሌክስ_አብርሃም

አባቴ ሲራመድ ትንሽ አንከስ ይላል፡፡ ያን ያህል እንኳን አይደለም፡፡ ወታደር ስለነበር ታፋው አካባቢ ጥይት ጨረፍ አድርጋው ነው፡፡ (ለጡረታ ሰበብ ትሆን ዘንድ ከእግዜር የተተኮሰች
ጥይት ይላታል አባቴ ራሱ) !! አንድ አራት እርምጃዎቹ ኖርማል ይሆኑና አምስተኛዋ ላይ
ትንሽ ወደግራ ዘምበል ይላል እንደ እኛ ታሪክ !! የራሳችን ፊደል፣ የራሳችን ቋንቋ፣ አድዋ፣መቅድላ፣ ድርቅ አንከስ ወደ ግራ !! ይሄው ነው !

ታዲያ አባቴን ጥምድ አድርጎ የያዘው የግራ እግሩን በፈንጅ ያጣ ወታደር ጎረቤት አለን ፣ “ለዚች
በየአምስት እርምጃው ለምትከሰት እንከሻው የአካል ጉዳተኛ ተብሎ ጡረታ ይበላል፡፡ ይሄ ለጳግሜ ከመስከረም እኩል ደመወዝ ከመክፈል አይተናነስም አይ እች አገር ! አይ ታሪክ " እያለ ያሸሙረዋል በክራንቹ መሬት እየቆረቆረ…!!

የአባቴን እግር የጨረፈችው ጥይት ለአባቴ ግንባር የተተኮሰች መሆኗን ዘንግቶ፡፡ የተጫረ እግር
ከተቆረጠ እግር እያወዳደረ በጉድለት ቁና የታሪክ ገለባውን ሊሰፍር ይዳዳዋል ፡፡ ጡረታን
የጉዳት ዳረጎት አድርጎ የሚያስብ ከንቱ !! ሰው አንገቱን ተቆርጦ ጡረታ እየተቀበለ መኖር
ቢችል ኖሮ፣ “ለአገራቸው ክብር” አንገታቸውን የተቆረጡቱ “ግራ እግር ምን አላት” ብለው
በተቆረጠው ግራ እግሩ በሳቁበት ነበር ፤ “አንዱ ባንዱ ሲስቅ ጀምሰሯ ጥልቅ” (በጨለማ መሳቅ
የለመደ ህዝብ ስለጀምበር መጥለቅ ምን ገዶት፡፡ ለምን እንጦሮጦስ አትወርድም፡፡ ኮኮቦችን ወላ ጨረቃዋን አስከትላ፡፡)

ቀን ቀን ትሁት፣ የተከበረ፣ የተጣላ የሚያስታርቅ የመንደሩ ዋልታ ነው አባቴ ፡፡ ማታ…. አቤት ቀንና ማታ በአባቴ ባህሪ ሲለኩ ያላቸው ልዩነት፡፡ ጧት የነበረው አባቴ ሌላ ክፍለ ዘመን፣ ማታ የሚከሰተው ደግሞ ሌላ ላይ የተፈጠረ ፤ ሁለት አባት ያለኝ እስኪመስለኝ !! አባቴ
ማታ ማታ ከራሱና ከእነዛ ሁለት ሥዕሎች ጋር ይጣላል ።
ጠጭ ነው:: በየቀኑ ይጠጣል፡፡ ሲጠጣ ቤተሰብ አይረብሽም፡፡ እናቴን አይናገርም፡፡ ቤታችን
ግድግዳ ላይ የተለጠፉት ሁለት ሥዕሎች ጋር ነው ዱላ ቀረሽ ግብ ግብ የሚፈጥረው በቃል !!

አባትህ ስራው ምንድን ነው ?” ብባል፣ “አባቴ ስራው ምን እንደሆነ አላውቅም” ነው መልሴ፡፡
ማሪያምን አላውቅም ! ትምህርት ቤትም እንደዚሁ ብዬ መልሼ ሁሉም ሳቁብኝ፡፡ እኔ ግን ለምን
እንደሳቁ አልገባኝም !! የተማሪዎቹ እሺ ይሁን ምድረ ኩታራ፡፡ ቲቸር ምን አሳቀው ? (ከሳቁ በፊት አንቱ ነበር የምለው፡፡) የቲቸር ሳቅ ስላበሳጨኝ ሆነ ብዬ እንዲህ ስል ሳቁን ተረጎምኩት፣
“አባትህ ቢያጣ ቢያጣ መምህር መሆን ያቅተዋል ?” ማለቱ ነው፡፡” ባይሰማኝም አንጀቴ ራስ፡፡
ይሄን አስቀያሚ መላጣ፣ ኮቱ የተዛነፈ ሂሳብ አስተማሪ ተውትና ስላባቴ ልንገራችሁ..(ሲጀመር
ሂሳብ እስተማሪ ስለአባቴ ሥራ ምን አገባው ደሞ ይስቃል እንዴ!)

ስለአባቴ ሥራ እንዴት ልበላችሁ? አባቴ አሁን ሹፌር ነው ተብሎ አንድ ፌርማታ ሳያልፍ ራፖርት ጸሐፊ ይሆናል፣ እሳቸው የሚጽፉት ማመልከቻ መሬት ጠብ አይልም" ተብሎ ባለጉዳይ
ቤታችን ሲመጣ፣ አባቴ መጋዝና ሜርቴሎውን ይዞ ገና ድሮ አናፂ ሆኗል፡፡ እንግዲህ በክረምት
ጣራችሁ አፍስሶ ወይ የእንጨት አጥራችሁ ወድቆ ትላንት ግንቦት ላይ አናፂ የነበረ አባቴን ሰኔ
አንድ "ጠግንልን” ብላችሁ ብትመጡ አባቴ ከተከመረ የከሰል ጆንያ ኋላ ቆሞ የከሰል ነጋዴ
ሆኖ ታገኙታላችሁ (“ዱቤ ክልክል ነው” ከሚል ፅሁፍ ጋር)..እና አባቴ ሥራው ምንድን ነው ልበል ? ብዙ ሥራ ያለውና ምንም ብር የሌለው አባት !

ብር ከአንዱ ይበደራል፣ የተበደረውን ከሌላ ሰው ተበድሮ ይከፍላል፡፡ ለሌላው ሰው ደግሞ
ከሌላ ሌላ ሰው ተበድሮ ይከፍላል፡፡ ሕፃን እንደነበርኩ ታዲያ ይሄ የአባቴ የመበደርና ብድር የመክፈል ሳይክል መጨረሻ ያለው ስለማይመስለኝ አባቴ እስከዘላለሙ በብድር የሚከሰስ፣ የሚታሰር አይመስለኝም ነበር፡፡ ብድር ይከፍላል፡፡ እጁ ላይ ምንም ብር አይኖረውም፡፡ ብር ለምን ይጠቅማል ቢሉኝ፣ ብድር ለመከፈል፡፡ 'ደመወዝ ለምን ይጠቅማል?' ብባል ብድር
ለመክፈል፤ ታዲያ ለምንድነው ሰዎች 'በባንክ ብድር ቤታቸው ተሸጠ የሚባለው? - እንደኔ
አባት ብልህ ስላልሆኑ ነዋ !!

ሥዕሎቹ፣
1. አባቴ በመጠኑ ሲሰከር (ሞቅ ብቻ ሲለው) ፊት ለፊቱ ቆሞ “ሳተናው ደህና አመሸህ!” የሚላቸው የአፄ ቴዎድሮስ ሥዕል የሽጉጣቸውን አፈሙዝ አፋቸው ውስጥ አስገብተው መቅደላ ጫፍ ላይ ሬሳና ቁስለኛ ከስራቸው ተለሽልሾ የሚታይበት ሥዕል፣ በቀኝ በኩል ከዕቃ መደርደሪያዋ በላይ ግድግዳው ላይ ተለጥፎ ይገኛል፡፡ (አባቴ ከዚህኛው ስዕል ጋር የመረረ ጥል የለውም፣ አልፎ
አልፎ ካልሆነ፡፡)

2. አባቴ ስካሩ ከመደበኛው ስካር ከፍ ሲልና፣ ቀን ከገጠመው የሕይወት ስንክሳር ጌሾ ጋር
ሲቀየጥ ደግሞ ከማይጋጩት ባላጋራ ጋር ይጋጫል፣ “.የጌታ እየሱስ ከርስቶስ” ምሥል ጋር!!

እየሱስ ቀይ መጎናፀፊያ ለብሶ፣ ረዥም ምርኩዙን በብብቱ ስር ይዞ፣ በር እያንኳኳ.. በግራ
በኩል!! አባቴ ከዚህ ሥዕል ጋር ይጣላል (ድፍረቱ ኢይገርምም ?)

አባቴ ገና በር ሲያንኳኳ እናቴ ስካሩ አንደኛ ደረጃው ይሁን ወይም ሁለተኛው ደረጃ ታውቀዋለች ፣ እንዴት ታውቃለች ? እግዜር ይወቅ !! እነዚህ እናቶች በየድራፍት ቤቱ ስለማይደሰኩሩ እንጂ በየሬዲዮና በየቴሌቪዥኑ ስለማይቀባጥሩ እንጂ ስንት ጉድ ተዓምር አለ በውስጣቸው:: ስንት
ጉድ፣ መላ.. :: እንኳን ባላቸው በር ሲያንኳኳ ቀርቶ ዙፋን ላይ ቂብ ሊል ያቆበቆበ ባለተራ ዓይነ ውሀውን አንብበው ክፉ ይሁን ደግ ያውቃሉ ዘመን ምስክር ነው !

ሁለተኛው ዓይነት ስካር ከሆነ እናቴ ተንደርድራ ከክርስቶስ ሥዕል ፊት ትሄዳለች - በፈጣን
አነጋገር፣ “ጌታ ሆይ እባክህ የተናገረውን ሲናገር አትቁጠርበት ይቅር በለው" ብላ የንሰሃ ቀብድ
ታስይዛለች ! (ሙሉውን አባቴ ራሱ ስካሩ ሲበርድለት ያወራርዳል !! ) ከዛ በሩን ትከፍትለታለች!
ፊቱ ወዝቶ አይኑ በአስፈሪ ሁኔታ ጉሽርጥ መስሎ ይገባል:: “ሰላም አመሻችሁ!” የለ ምን የላ!
“የአባትህ ገዳይ እዛ ቤት ተደብቋል፣ በግራ በኩል ከአልጋው በላይ ታገኘዋለህ” ብለው የላኩት ይመስል ዝም ብሎ ይገባና በቀጥታ ወደግራ ታጥፎ ከእልጋው በላይ የተሰቀለው የከርስቶስ ስዕል ፊት ይቆማል ፡፡
ፂሙን እያሻሸ ለረዥም ደቂቃዎች በዝምታ ሥዕሉ ጋር አፍጥጦ ይቆይና ድንገት፣ “አንከፍትም”
ብሎ ይጮሃል፡፡ እናቴ ሽምቅቅ ትላለች፡፡
“ለስንቱ እንከፈት፣ ሲያንኳኩ ስንከፍት ገብተው እኛን ሲያስወጡን፡፡ በጣታቸው ሲያንኳኩ 'ቤት ለእንግዳ' ብለን ስንከፍት በክንዳቸው ሲደቁሱን ከመክፈት ጋር ተጣልተናል ፤ አንከፍትም….”

እናቴ ወደ ጣራው ዓይኗን ልኮ በለሆሳስ ታነበንባለች፡፡ ለከርስቶስ “ቅድም ያልኩህን እንዳትረሳው
አደራ!” የምትል ይመስለኛል፡፡ አባቴ ይንጎማለላል፡፡ ረዥም ነው ቁመቱ፡፡ ብን ተደርጎ የተበጠረ
ጥቁር ከርዳዳ ፀጉሩ ላይ ወደፊት አካባቢ ትንሽ ሽበት ጣል ያደረገበት ፡፡ የጨርቅ ሱሪው የተኩስ መስመር ቀጥ ማለት፣ “ሱሪውን ከለበሰው ጀምሮ ተቀምጦ አያውቅም እንዴ” የሚያስብል በሚገባ የተወለወለ አሮጌ የወታደር ቦት ጫማ ፡፡ ይንጎማለላል ..
👍312
“አንከፍትም ! እድሜ ልኬን በርህን ሳንኳኳ የከረቸምክብኝ፣ እንዴት ነው የኔን ልብ ዛሬ የምከፍትልህ፡፡ የገቡትንም ማስወጪያ አጥተናል እንኳን አዲስ ለሚያንኳኳ ልንከፍት አንከፍትም''
ይንጎራደዳል፡፡ አንዳንዴ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀለውን ቁጣ ላይ፣ “በቃ ገንጥሎ ጣለው ክርስቶስዬ
ጉዱ ፈላ” እላለሁ፡፡ ይሄ ሥዕል ከድሮ ጀምሮ ግድግዳችን ላይ ስለተለጠፈ ነው መሰለኝ ክርስቶስ
ከእኛ ቤት ሌላ መሄጃ ያለው አይመስለኝም ነበር፡፡ እናቴና ክርስቶስ የአባቴን ባህሪ ችለው
የኖሩት ሌላ መሄጃ ስለሌላቸው ይመስለኝ ነበር፡፡እኔ፣ ክርስቶስና እናቴ የአባቴን ባህሪ ችለን
የተቀመጥነው ሌላ መሄጃ ስለሌለን ይመስለኝ ነበር.

"አንከፍትልህም ይህቺ ሚስኪን (ወደናቴ እየጠቆመ) ለስንቱ ሃብታም፣ ለስንቱ ጀግና፣ ለስንቱ ባለ ሥልጣን የከረቸመችውን ልቧን ለኔ ከፈተች፡፡ ምን ተጠቀመች ? ምንም !! እድሜ ልኳን ጡረታ የወጣ ወታደር ባሏ ሰከሮ ሲመጣ በር ከፋች ሆና ቀረች .." (ስለሌላ ባል እንጂ ስለራሱ የሚያወራ አይመስልም፡፡) “እሷን ተዋት..እቺ አገር ራሷ..እቺ እጇን ወደአንተ ትዘረጋለች የተባለችው... ሃሃሃ ..እቺ ኢትዮጵያ .…ጓደኞቼን ዋጥ ስልቅጥ ያደረገችው አገር ራሷ...ለንጉሥ ልቧን ስትከፍት፣
ለወታደር ልቧን ስትከፍት፣ ለወንበዴ ልቧን ስትከፍት፣ ለሶሻሊዝም፣ ለምናምኒዝም ልቧን
ስትከፍት ይሄው መከፈት መዘጋት የሰለቸው በሯ ተገንጥሎ ክፍቷን ቀረች፡፡እናስ ? ምናችን
ጅል ነው የምንከፍትልህ ?..አንከፍትም !! አንከፍትም !! በከፈትን ቁጥር እየገባ የታጨቀብንን
ጣጣ ባስወጣህልን ይልቅ !.ላንተም አይመችህ .ውስጣችን ነድዷል፣ ከሰሏል የተቃጠለ ቤት
ውስጥ ለመኖር ይሄን ያህል ስታንኳኳ መኖር..ኤዲያ" እናቴ እንባዋ ጠብ ሲል ይታየኛል፡፡

ልቤ ይታፈናል፡፡ ልብ ድካም የሚባለው ይሄ ይሆን ? ቤታችን ይታፈናል፡፡ በጣም ብዙ
መላዕክት ቤታችን ውስጥ ታጭቀው፣ “ኧረ ጌታ ሆይ ይሄ ሰውዬ አበዛው፣ ፍቀድልንና ወደዛ
ቦጫጭቀን ሲኦል እንወርውረው…” እያሉ እየሱስን የሚያስፈቅዱ ይመስለኛል፡፡
“እስቲ ተዉት…እሱ ያለፈውን መከራ ማን አለፈ ? ..የዚህን ሚስኪን ልጄን ቀንበር ማን ተሸከመ?
እስከመጨረሻው እለምነዋለሁ!” የሚላቸው ይመስለኛል በሩን ማንኳኳቱን ሳያቋርጥ፤ ክርስቶስ
የኔ ልብ አዋቂ ! አባቴ እያነሰ ክርስቶስ እየገዘፈ ይሄድብኛል አሁን ደግሞ ለአባቴ እሰጋለሁ፡፡

ጎምለል ጎምለል...“እንከፍትም !!
አናውቅም እንዴ…ወላ መስኮት ወላ በሩ በተዘጋ ቤት ሰተት
ብለህ ገብተህ ሰላም ለእናንተ ስትል? አሁን ምን ያዘህ?.ግባ… ይሄው በግድግዳው ግባ፡፡
መቼም ዓይናችን እያየ አንከፍትልህም…” እያጉተመተመ ልብሱን ያወላልቃል፡፡ መጀመሪያ
ኮቱን ገበሩ ተቀዳዷል፡፡ እያጣጠፈ ያጉተመትማል - “ወይ መክፈት… " ሱሪውን በሥርዓት
አልጋው ላይ ዘርግቶ በእጁ እየተኮሰ ያጣጥፋል፡፡ ቢሰክርም ባይሰክርም ልብሱን በመስመሩ
ማጠፍና በሥርዓት ማስቀመጥ አይረሳም፡፡ ሊተኛ ሲል ያየኛል፡፡ ልክ የአልጋ ልብሱን ገለብ
ሲያደርግ ኩርምት ብዬ እናቴ ስር፡፡ “አይዞህ አንበሳዬ…ምነው ከኔ ከምትፈጠር በቀረብህ...
የማይረባ አባት ለአንድ ልጁ እንኳን የማይሆን ወይ አባት አላየንም አባት እንደለማዳ
ውሻ ስምህን ተከትሎ ከሚጮህ ስሜ ሌላ ምን አወርስሃለሁ ቤሳቤስቲን..” እየተናገረ አልጋ
ልብሱ ውስጥ ገብቷል፡፡ በብርድ ልብሱ የታፈነ እንቅልፍ የተጫጫነው ድምፁ ያጉተመትማል፣ከንቱ…ለራሴ ከንቱ ሆኜ የሰው ሰው ከንቱ አድርጌያት ቀረሁግራ ገብቶኝ ግራ ረዥም
ዝምታ፣ የተኛ እስኪመስለን :: ድንገት፣ “አለሜ..እራት በልታችኋል” ይላታል እናቴን፡፡

“ጠዎ ወይም “አልበላንም” አትልም፡፡ ሁልጊዜ መልሷ ይገርመኛል፣
“ቆንጆ ወጥ ሰርቻለሁ ፡ ትንሽ ልስጥህ እስቲ.." ትለዋለች፡፡ ገና ቅድም ተነስታ ጓዳው በር
ላይ ደርሳለች፣

“አ..ይ.. ይላል ስልል ባለ ድምፅ፡፡ አንዳንዴ “አይ” ብሏትም ታቀርብለታለች፣ ተነስቶ
ይበላል፡ አንዳንዴ "አይ…" ካለ ትመለሳለች፡፡ በሁለቱ 'አይ'ዎች መሃል ያለውን ልዩነት ብዙ ጊዜ
ለማጥናት ሞከርኩ፡፡ በድምፅ ርዝመት፣ በቅላፄ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እናቴ ግን በሁለቱ 'አይ'ዎች መሃል የአባቴን መሻት በቀላሉ ታውቃለች፣ አለመሻቱንም፡፡ (አለመሻቱ እንኳን አይ ካለ አይ ነው :: ግን እንዴት አይ ያለ ሰው አይ ያለበትን ጉዳይ እንደፈለገው ማወቅ ቻለች ??????)

አማርኛ አስተማሪያችን “ልጆች ቋንቋን ከቤተሰብ ከማኅበረሰብ ይማራሉ” አሉኝ እንጂ ቋንቋን
የምንማረው ከሕይወት፣ ለዛውም መተሳሰብ፣ መከባበረ እና መፈቃቀር ካለበት የሕይወት
ልምዳችን ብቻ ነው:: አማርኛ አስተማሪያችን ራሳቸው፣ አባባ “አይ” ሲል እራት “አቅርቢልኝ”
ማለት መሆኑን በጭራሽ አያውቁም፡፡ ከማህበረሰቡ ይሄን አልተማሩማ !! ስሜትና ስዋሰው
ለየቅል ናቸው !!
ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ ታዲያ ብቻዬን ነኝ፡፡ እናትና አባቴ ቤተ ክርስቲያን ሄደዋል፡፡ የክርስቶስ
ሥዕል ግን አሁንም አለ፡፡ ቆይ አባቴ ከሌለ ማን እንዲከፍትለት ነው የሚያንኳኳው ? በብርድ
ልብሴ ተጠቅልዬ ሥዕሉን እያየሁ አስባለሁ፣ “አባታችሁን ታዘዙ፣ ቤተሰቦቻችሁ የማይወዱትን
በመሥራት አታሳዝኗቸው” ይሉን የለ የሰንበት አስተማሪያችን ? ስለዚህ...

“አልከፍትም !!” እላለሁ ቀስ ብዬ

አለቀ
👍17😁4👏2
#ምንዱባን


#ክፍል_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

ቀና ሰው

በ1815 መሴ ቻርለስ ብየንቬኑ መሪል የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ነበሩ፡፡ እድሜያቸው 75 ሲሆን የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሁነው የተሾሙት በ1806 ዓ.ም ነበር፡፡ ጳጳሱ ወደ ሀገረ
ስብከታቸው ሲመጡ እህታቸው ወ/ት ባፕቲስታን አብረዋቸው ነበር
የመጡት:: እህትዬዋ ምንም እንኳን ትዳር ባይዙም እድሜ የጠገቡ ሲሆኑ ወንድማቸውን በአሥር ዓመት ይበልጧቸዋል፡፡

ከጳጳሱ ቤት ውስጥ ሌላም ሴት ነበሩ፡፡ እኝህ ሴት የወ/ት ባፕቲስታን እኩያ ናቸው:: ሴትዬዋ ወ/ሮ ማግልዋር ይባላሉ:: ሴትዮዋ ቀደም ሲል የሌላ ሰው አገልጋይ ሆነው ሠርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የወ/ት ባፕቲስታንና
የጳጳሱ ቤት ጠባቂ ሁነው ተቀጥረው ይሠራሉ፡፡

ጳጳሱ ከሀገረ ስብከታቸው እንደደረሱ በሀገሩ ደምብ መሠረት ከፊልድ ማርሻል ቀጥሎ ያለውን ሹመት ይሰጣቸዋል፡፡ የክፍለ ሀገሩ መሪና የማዘጋጃ ቤቱ ሹም ከቤታቸው ሄደው «እንኳን ደህና መጡ» በማለት እጅ ይነስዋቸዋል፡፡ አቡኑም በተራቸው ከዚያ ለተገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡ የከተማው ሕዝብ በአጠቃላይ አዲስ የተሾሙለትን ጳጳስ
ለማየት በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር፡፡

የጳጳሱ ቤት ከአንድ ሆስፒታል አጠገብ ሲሆን ቤቱ እጅግ በጣም
ሰፊና ያማረ ነው:: ሆስፒታሉ ይገኝ የነበረው ከረባዳ ሥፍራ ላይ ሲሆን ግቢው እንደ ጳጳሱ ቤት አይሰፋም:: ጳጳሱ ወደዚያ ሲሄዱ በሦስተኛው ቀን ሆስፒታሉን ይጎበኛሉ:: ከጉብኝቱ በኋላ የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ ከቤታቸው
ድረስ መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ይጋብዙታል:: አስተዳዳሪው ከጳጳሱ ቤት ይሄዳል::

በሆስፒታሉ ውስጥ «ስንት በሽተኞች አሉ? » ሲሉ አስተዳዳሪው ጠየቁ::

«ሃያ ስድስት» ሲል መለሰላቸው::

«ልክ እኔ እንደቆጠርኳቸው ናቸው አልተሳሳትክም» አሉ ጳጳሱ::
ጳጳሱ የቤታቸውን አዳራሽ በዓያናቸው ቃኙ:: አመለካከታቸው
አዳራሹን በዓይነ ሕሊናቸው የሚለኩና የሚያከፋፍሉ ይመስሉ ነበር ።

«ይህ ክፍል ብቻ ሀያ አልጋ ይይዛል» አሉ እርስ በራሳቸው? ሲነጋገሩ።
ከዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቀጥለውን ተናገሩ::

«ወዳጄ የምለውን አጢነህ ስማኝ፡፡ እዚህ ቦታ አንድ ስህተት የተፈጸመ ይመስላል፡፡ እናንተ አምስት ወይም ስድስት ጠባብ ክፍሎች ናቸው ያሏችሁ::
ከዚያ ውስጥ ሃያ ስድስት ሰዎች ይተኛሉ፡፡ እኛ እዚህ ሦስት ሰዎች ብቻ ነን፡፡ ያለው ቦታ ግን ለስልሣ ሰው የሚበቃ ነው:: ታዲያ ይህ የአደላደል ስህተት አይመስልህም? የእኔን ቤት አንተ ብትወስድ ፤ የአንተን ደግሞ እኔ
ብወስድ ይሻላል፡፡›

በሚቀጥለው ቀን ሃያ ስድስቱ በሽተኞች ወደ ጳጳሱ ቤት ተዛወሩ፡፡
ጳጳሱም ሆስፒታሉን ተረከቡ:: ወሬው በከተማው ተነዛ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጳጳሱን በጎ ምግባር በመከተል ለበጎ ተግባር የሚውል እርዳታ ይጎርፍ ጀመር፡፡ በየቀኑ ከጳጳሱ ቤት በር የሚያንኳኳ ሰው ቁጥር እየበዛ
ሄደ፡፡ ሆኖም የሚመጣው ሰው ሁሉ እርዳታ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ምፅዋት ለመቀበልም ነበር፡፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጳጳሱ የብዙ ችግረኞች ቀላቢ፣ ምፅዋት ሰጪና ገንዘብ ሰብሳቢ ሆነ፡፡ ብዙ ገንዘብም ከጳጳሱ እጅ እየገባ ለድሃ ይሰጥ ጀመር:: የሚገኘው ገቢ ግን ልክ ከደረቀ
አፈር ላይ እንደሚፈስ ውሃ ገና ከመገኘቱ ወጪ ሆኖ በቶሎ ያልቃል፡፡ጳጳሱ ገንዘብ ቢያገኙም ከተገኘው ገቢ ጥቂቱን እንኳን ለራሳቸው ወደኋላ አላሉም፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው የራሳቸውንም ይዞ ይሄድ ጀመር፡፡
ጳጳሳትን ከስማቸው አስቀድሞ ንጽህናቸውን ለማረጋገጥ ብፁዕ ወቅዱስ እያሉ መጥራት የተለመደ ቢሆንም በዚያ አካባቢ ይገኙ የነበሩት ነዳያን ፍቅራቸውንና ቅርበታቸውን ለመግለጽና የጳጳሱን ደግነት ለማውሳት ብፁዕ ወቅዱስ በማለት ፈንታ «አባ ደጉ» እያሉ ይጠርዋቸዋል፡፡

እኚህ ደግ ሰው በ1815 ዓ.ም ምንም እንኳን 75 ዓመት ቢሞላቸወም ከስልሣ ዓመት በላይ የሆናቸው አይመስሉም ነበር:: ቁመታቸው እጅግም ረጅም ሳይሆን መጠነኛ ሆኖ ሰውነታቸው ደልዳላ ነው:: ክብደታቸውን
ለመቆጣጠር በእግር መሄድ ያዘወትራሉ:: ሲራመዱ መሬት በኃይል እየረገጠ ከወገባቸው ትንሽ ጎበጥ ይላሉ::

የልጅ ፈገግታ በተጎናጸፈ አንደበት ሲናገሩ ከግርማ ሞገሳቸው ብዛት
የሰማቸው ሁሉ የመንፈስ እርካታን ያገኛል:: ከመላ ሰውነታቸው ደስታ
የሚንፀባረቅ ይመስላል፡፡ ደግነት የተቆራኘው አካላቸውና ወተት የመሰለው ጥርሳቸው ፈገግ ሲል እኚያ «ጨዋ ሰው ፤ እድሜ የተቸረ ሽማግሌ፤ ደግ ሰው» በማለት ለደጋግ ሰዎች የምንሰጠው ቅጻል ሁሉ በእኚህ ሰው ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ላያቸው እንኳን ስለብቃታቸውና
ስለደግነታቸው አይጠራጠርም:: ነገር ግን አንድ ሰው ለጥቂት ሰዓት ከጳጳሱ ጋር ቢቆይና በአሳብ ባህር ተወጠው ቢያያቸወ ቀስ በቀስ
መለወጣቸውን ይገነዘባል፡: ግርማ ሞገሳቸው በቃላት ለመግለጽ በማይቻል ሁኔታ ያስፈራል፡፡ ሰፊውና ኮስታራው ፊታቸው እንዲሁም ሻሽ የመሰለው
ፀጉራቸው ክብር የተጎናጸፈ ለመሆነ በግልጽ ይታያል:: ግርማ ሞገስ ከውስጣቸው እየፈለቀ ሲወጣ የሚያልቅ ቢመስልም የእንዐባራቂነት ኃያል
እንዳለው አያጠራጥርም:: እንዲያውም አንድ ሰው ሁኔታቸውን በጥሞና ሲመለከት «አንድ መልአክ በፈገግታ አጊጦ ያየኛል» የሚል ስሜት
ያድርበታል፡፡ እኚህ ሰው የሚያሰላስሉት ስለ ክቡር ጉዳይ እንጂ ስለርካሽ ነገር ላለመሆኑ ጥርጣሬ አይገባውም::

ጸሎት ማድረስ፤ ምፅዋት መስጠት፧ የመንፈስ ስቃይ የደረሰበትን ማጸናናት፤ ወንድማማችነትን መስበክ፤ ራስን ለሌሎች መስዋዕት ማድረግ፤
በእምነት ራስን መግራት የጳጳሱ የእለት ተዕለት ኑሮ ሲሆን ይህም ኑር በበጎ አሳብ፤ በምርጥ ቃላትና በበጎ ተግባር የተሞላ ነበር፡፡

ክረምት ይሁን በጋ ሁለቱ ሴቶች ሲተኙ ብፁዕነታቸው ወደ ጓሮ
ሄደው አትክልት ውስጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ሰዓት ፈጣሪያቸውን በማሰብ ከዚያ ካልቆዩ ኑሮአቸው የተሟላ አይመስላቸውም:: አሳባቸውን
ሰብስበውና የመንፈስ እርጋታን አግኝተው የምሽቱን ሰላምና ፀጥታ ከሰዎች የመንፈስ እርካታ ጋር እያነፃፀሩ የከዋክብትን ብዛት በመመልከት ከአትክልቱ
ውስጥ ይንሸራሸራሉ፡፡

በዚያች ሰዓት አበቦች ያለመስገበገብ የሚለግሱትን መልካም መዓዛ እየማጉ ጥቅጥቅ ካለ ጨለማ ውስጥ እንደበራ ሻማ ብቻቸውን በፍጥረታት
መካከል በደስታ የተዋበው ነፍሳቸውን ዘርግተው ይቆማሉ:: አእምሮአቸው ውስጥ ምን እንዳለ ራሳቸውን ቢጠይቁ መልሱን አያውቁትም:: ሆኖም ከሰውነታቸው ውስጥ አንድ ነገር ወጥቶ እንደሚሄድና አንድ ነገር ደግሞ ከሰውነታቸው ላይ እንደሚያርፍ ይሰማቸዋል ፤ አንድ ዓይነት ምሥጢር መከናወኑን ይገነዘባሉ::

እኚህ እድሜ የጠገበና ፈጣሪያቸውን የቀረበ ሰው የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ቀን ቀን አትክልት በመኮትኮት ሲሆን ማታ ማታ ደግሞ ፈጣሪያቸውን በጸሎት በማመስገን ስለሆነ ሌላ የሚፈልጉት
ነገር አልነበረም:: ምድሩ በአበባ ፤ ሰማዩ ከከዋክብት በማጌጡ የመንፈስ እርካታ ይሰጣቸዋል::

ውድቀት

ጊዜው 1815 ዓ.ም ወሩ ጥቅምት ነው:: ፀሐይዋ ልትጠልቅ አንድ ሰዓት ያህል ሲቀራት አንድ በእግሩ የሚጓገዝ ሰው ወደ ሞንቴስ ሱር ሞንቴስ
👍47😁3👏2👎1🔥1
ትንሺቱ ከተማ ይገባል፡፡ በየመስኮቶቻቸውና በየቢሮዎቻቸው አጠገብ የቆሙ
ጥቂት ሰዎች ይህን መንገደኛ ይጠራጠሩታል፡፡ ሆኖም ከእርሱም ይበልጥ የተሰቃየ ሌላ ሰው ለማግኘት እንደማይቻል ፊቱ ይመሰክራል፡፡ ቁመቱ መካከለኛና አጥንተ-ወፍራም ሲሆን የሰውነቱ አፈጣጠር ግዙፍ ነው::
በእድሜው ሙሉ ሰው ይመስላል፡፡ ምናልባት አርባ ስድስት ወይም አርባ
ሰባት ዓመት ሳይሆነው አይቀርም:: የፀሐይ ጨረር፣ ነፋስና ከሰውነቱ የወጣው ላብ ያጠቆረውና ያንገላታው ቆብ ግማሽ ፊቱን ሸፍኖበታል::

ቀደም ሲል የፈሰሰው ላቡ ከፊቱ ላይ ደርቆ አዲሰ ደግሞ ከፊቱ ላይ
ሲወርድ ድካሙን በግልጽ ያሳያል:: የለበሰው ሸካራና ቢጫ ሸሚዝ ከብዙ ቦታ ላይ በመቦጫጨቁ የደረቱን አጥንት ለፀሐይ ዳርጎታል:: ሸሚዙ በነፋስ
ኃይል እንዳይሄድ ሳይሆን አይቀርም ከረባትና አሮጌ መስቀል በተንጠለጠለበት
ገመድ አሲዞታል፡፡ የተቀዳደደ ሰማያዊ ሱሪ ታጥቋል:: ሱሪው አንደኛው ጉልበቱ ላይ ሳስቶ ሲነጣ ሌላው ላይ ተቀዳድዶአል፡፡ ከአንድ ጎኑ ላይ አረንጓዴ ጨርቅ የተጣፈበትና ግራጫ መልክ ያለው አሮጌ ሰደርያ ደግሞ
ደርቦአል:: በምናምን የተሞላ አዲስ አቆማዳ በዱላ በማያያዝ በጀርባው አንጠልጥሎአል፡፡ በእጁ ደግሞ ሌላ ባለትልቅ ቋር ዱላ ይዟል:: የተንሻፈፈና
ከጎኑ የተቀደደ አሮጌ ጫማ ያለካልሲ አጥልቆአል:: ፀጉሩን ተላጭቶት የበቀለ ሲሆን ጢሙ ግን በኃይል አድጓል:: ላቡና የሰውነቱ መዛል በእግር ብዙ መጓዙን ያረጋግጣል:: ከላዩ ላይ የሰፈረው አዋራ ለሰውዬው መጎሳቆል ሌላው ማስረጃ ነው::

ይህ ሰው ወደ ከተማው እንደገባ ወደ ግራ ታጥፎ ወደ ማዘጋጃ ቤት
ያመራል:: ከዚያም ከማዘጋጃ ቤት ሹም ቢሮ ገብቶ ከሩብ ሰዓት በኋላ ከቢሮው ይወጣል፡፡
በከተማው ውስጥ ጥሩ ማረፊያ ቤት ነበር፡፡ መንገደኛው ወደዚያች
ማረፊያ ቤት ሄደ፡፡ ማረፊያ ቤቱ በከተማው የታወቀና ምርጥ የተባለ ነበር፡፡ በቀጥታ ወደ ወጥ ቤት ሄደ:: የወጥ ቤቱ የጓሮ በር ወደ ዋናው ጉዳና የሚያስወጣ ሲሆን መንገደኛው የገባው በዚህ በኩል ነበር፡፡ ወጥ ቤቱ ወስጥ ከአብዛኞቹ ምድጃዎች ላይ እንጨት በኃይል ተያይዞ እሳቱ
ይንቦገቦጋል፡፡ የወጥ ቤቱ ኃላፊ እሳቱ ከሚነድበት በችኮላ እየተራመደ ሄዶ የምግቡን ሁኔታ ይቃኛል:: የምግቡን መዳረስ የሚጠብቁ ለሎች መንገደኞች
ቀጥሎ ከነበረው ክፍል ውስጥ ሲስቁና ሲንጫጩ ይሰማል:: የሚዘጋጀው ምግብ መልካም ቃና፧ እንኳን ለሚቀምሰውና ለሚያሸትተው ይቅርና
መንገደኛውን ከሩቅ የሚጠራ ዓይነት ስለነበር እንግዶቹ፣ ምን ዓይነት ሰዎች እንደነበሩ ለመገመት አያዳግትም::

የወጥ ቤቱ ኃላፊ በር ሲከፈት ሰምቶ እንግዳ መግባቱን ስለተገነዘበ አንገቱን ቀና ሳያደርግ «ጌታዬ ምን ይፈልጋሉ?» ሲል ይጠይቃል፡፡
‹‹የሚላስ፧ የሚቀመስና ማደሪያ ነው የምፈልገው» ይላል እንግዳው::
«ከዚህ የቀለለ ምን ነገር አለ!» ብሎ ኃላፊው ከተናገረ በኋላ አንገቱን ቀና አድርጎ ባይተዋሩን በመመልከት ‹‹ግን ይከፈላል» ይለዋል:: ሰውዬው
ከኪሱ ወስጥ ትልቅ ቦርሳ አውጥቶ ገንዘብ አለኝ» ሲል መለሰለት::
«እንግዲያውስ» አለ አስተናጋጁ ፧ «ምን ልታዘዝ?»
ሰውዬው ቦርሳውን መልሶ ከኪሱ ውስጥ ከተተ:: ስልቻውን ከጫንቃው ላይ አውርዶ ከመሬት ላይ ወረወረው:: ዱላውን እንደያዘ እሳቱ አጠገብ
ከነበረው ወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ከተማው የተሠራው ከተራራ ጫፍ ላይ በመሆኑና ወሩም ጥቅምት ስለነበር የአካባቢው አየር በጣም ቀዝቃዛ ነበር፡፡
የቤቱ ባለቤት ወዲህና ወዲያ ባለ ቁጥር መንገደኛውን አተኩሮ
ይመለከተዋል::
«ምግብ ደርሷል?» ሲል መንገደኛው ጠየቀ፡፡
«ተቃርቧል» አለ ኃላፊው::
እንግዳው ጀርባውን ለእሳት ሰጥቶ ሲሞቅ የሆቴሉ ባለቤት ቁራጭ
እርሳስ ከኪሱ ካወጣ በኋላ ከመስኮት አጠገብ ከነበረው አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ
ተቀምጦ ከነበረው የማስታወሻ ደብተር አንዲት ቅጠል ቀደደ:: ምናምን ጻጽፎ ወረቀቱን በአቅራቢያው ለነበረውና እንደ ተላላኪም፧ እንደ ቤት
ጠራጊም ይሠራ ለነበረው ልጅ ሰጠው:: የሆነ ነገር በጆሮው ለልጁ ሹክ ካለው በኋላ ልጁ ወደ ማዘጋጃ ቤት ሹም ቢሮ አቅጣጫ ይሮጣል:: ይህ ሲሆን ግን መንገደኛው አላየም::

«እራት ደርሷል?» ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀ::

«አዎን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ማቅረብ እንጀምራለን» አለ የቤቱ
ጌታ::

ልጁ ወረቀቱን በእጁ እንደያዘ ተመለሰ፡፡ የሆቴሉ ባለቤት ቸኩሉ
አስቸኳይ መልስ ለመስማት እንደሚጓጓ ሰው ሁሉ የተጣጠፈውን ወረቀት ከፈተ፡፡ በጥሞና ማንበብ ጀመረ:: ከዚያም በአንድ እጁ አገጩን ይዞ እንደማሰብ አለ:: በአሳብ ባህር የተዋጠ ወደሚመስለው መንገደኛ ተጠጋ::

«ጌታዬ» አለ፤ «ልረዳዎት ባለመቻሌ አዝናለሁ:: ያልተያዘ ክፍል ያለ መስሎኝ ነበር፤ ግን የለም፡፡»

«ታዲያ» አለ መንገደኛው «አልጋ እንኳን ባይኖር የትም ቢሆን ሳር:
ተጎዝጉዞልኝ ልተኛ ለማንኛውም ከእራት በኋላ እንወያይበታለን::

«እራትም ልሰጥዎት አልችልም፡፡»

መንገደኛው ይህን ሲሰማ «ይህስ ለነገር ነው» ይላል፡፡ከተቀመጠበት
ብድግ አለ፡፡

«እህ.... እህህ፤ ታዲያ እኔ እኮ በጣም ስለራበኝ ጠኔ ይዞኛል::»

«ምንም የለኝም» አለ የሆቴሉ ጌታ::

ሰውዬው ሳቁን ለቀቀው:: ወደ እሳት ማንደጃው ዞር ብሎ የተጣደውን ምግብ ሁሉ ተመለከተ፡፡

«ምንም የለኝም! ያ ሁለ ምግብ እያለ!»

«ያ ሁሉ ምግብ ለሌላ ሰው ነው የተዘጋጀው::

ሰውዬው እንደገና ቁጭ አለ፡፡ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ‹‹ሆቴል ቤት
ውስጥ ነው ያለሁት፤ ተርቤአለሁ፤ እኔ ደግሞ እዚሁ ነው የማድረው»
አለ፡፡

የሆቴሉ ባለቤት አንገቱን ዝቅ አድርጎ ንዴት እየተናነቀው «ሰውዬ
ውጣ» ይላል፡፡

መንገደኛው ወደሚነደው እሳት ጠጋ ብሎ ትርኳሽ እንጨቶችን
በያዘው ዱላ ወደ እሳቱ ረመጥ እያስጠጋ ሳለ «ውጣ» የሚል ቃል ሲሰማ መልስ ለመስጠት ፊቱን ያዞራል፡፡ የሆቴሉ ጌታ አፍጥጦ እያየው ለመናገር እድል ሳይሰጠው «ቢበቃን ይሻላል ፤ በመጀመሪያ ማንንም ቢሆን በትህትና ማናገር ልማዴ ነው ፤ ሰውዬ ያለ ጭቅጭቅ መንገድህን ብትቀጥል ይሻልሃል»ይለዋል::

ሰውየውን እጅ ከነሳ በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቤቱ ወጥቶ ሄደ፡፡

አውራ ጎዳናውን ይዞ ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ የሀፍረት ሽማውን ተከናንቦ እንደ አዘነተኛና እንደተዋረደ ሰው እየታሸማቀቀ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ያስጠጉኝ እንደሆነ በማለት የየቤቱን በር አንኳኳ፡፡ ግባ የሚለው ቢያጣ ፊቱን ሳይመልስ ቀጥ ብሎ ወደፊት ተጓዘ፡፡ ከሆቴል ቤቱ ቢመለስ ኖሮ
የሆቴሉ ባለቤት እዚያ ቤት ውስጥ ከነበሩት እንግዶችና ከተላላፊ መንገደኞች ጋር ቆሞ በጣቱ እየጠቆመ ስለእርሱ በጉጉት ሲያወራቸው ያይ ነበር፡፡
ቢያያቸው ኖሮ ደግሞ የእርሱ ወደዚያ መምጣት የከተማው ወሬ እንደሚሆን ከሁናቴያቸውና ከአመለካከታቸው ሊገምት ይችል ነበር፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መንገደኛው አላየም:: ከችግር ማጥ ውስጥ
የሚዋትቱ ሰዎች ወደኋላ መለስ ብለው አይመለከቱም፤ ሰንኳላ እድል እንደሚከተላቸው ያውቃሉና:: ከአውራ ጎዳናው ሳይወጣ ለጥቂት ጊዜ
እንደተጓዘ ከማያውቀው ሰፈር ደረሰ፡፡ በሀዘን የተዋጠና የተከፋ ሰው ድካም እንደማይሰማው ሁሉ ድካሙ አልተሰማውም:: ግን በድንገት ረሃብ ሞረሞረው:: ሐሞቱ ሲንሰፈሰፍ ተሰማው:: ምሽት ተቃርቧል።
👍345
ከተባረረበት ሆቴል ቤት ጀምሮ ከወደኋላው ይከተሉት የነበሩት
ሕፃናት ድንጋይ ወረወሩበት:: በቁጣ ወደ እነርሱ ዞሮ በያዘው ዱላ ሲያስፈራራቸው እንደ ወፍ መንጋ ተበተኑ፡፡ የእስር ቤት በራፍ እንዳለፈ ከደወል ጋር ተያይዞ ከበር ላይ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት አየ:: መለስ ብሎ ደወሉን ደወለው:: በሩ ተከፈተ::
«ቤቶች» አለ ቆቡን አውልቆ በትህትና እጅ እየነሳ ፤ ለዛሬ ብቻ ከዚህ ያሳድሩኛል?»

«እስር ቤት ሆቴል ቤት አይደለም ፤ ወንጀል ሠርተህ ከመጣ በሩን
እንከፍትልሃለን» አለ አንድ ድምፁ ከሩቅ:: በሩ ተመልሶ ተዘጋበት:: የዘበኞች ኃላፊ ነበር የተናገረው:

ጊዜው እየመሸ ነው:: ቀዝቃዛ አየር ከተራራው ወደ ነበረበት ሰፈር
ይነፍሳል:: እግሩ እየከበደው ቢሄድም መራመዱን ቀጠለ፡፡ ከከተማው ትንሽ ወጣ ሲል ለማደሪያ የሚሆነው የትልቅ ዛፍ ከለላ ወይም የተከመረ
ድርቆሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደረገ፡፡ አንገቱን አቀርቅሮ ጉዞውን ተያያዘው::ሰው ከሚኖርበት አካባቢ የወጣ ስለመስለው አንገቱን ቀና አድርጎ አካባቢውን
በዓይኑ ቃኘ፡፡ ከእርሻ ሜዳ ደርሷል:: ከፊት ለፊቱ ከሚገኘው ጉብታ ላይ የነበረው እህል ታጭዶ የሚታየው ቀሪው ገለባ ብቻ ነው:: አካባቢው በአጠቃላይ የተላጨ ፀጉር መስሉአል:: ሰማዩ ጨልሞ ደመና ዞሮበታል፡፡ የደመናው ብዛት በአካባቢው የሚገኙት ኮረብታ ላይ ያረፈ አስመስሎታል፡፡
ሆኖም ከአንዳንድ ሥፍራ የሚታዩት ዋክብት ነፋስ ይዞት እንደሚሄድ ኩራዝ ደፋ ቀና ይላሉ:: ጨረቃውም ሳሳ ካለው ደመና ላይ ነጭ መስመር የዘረጋች ይመስል ብልጭ ድርግም ትላለች:. አልፎ አልፎ መስመሩን
የሚዘረጋው ጨረቃና ደፋ ቀና የሚሉት ከዋክብተ አካባቢው ጨርሶ ጨለማ እንዳይሆን ረድተዋል :: ስለዚህ የመሬቱን የሰማዩን ያህል አልጨለመም:: ሆኖም አካባቢው በጣም ያስፈራል፡፡.....

💫ይቀጥላል💫
👍20
አትሮኖስ pinned «#ምንዱባን ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ ቀና ሰው በ1815 መሴ ቻርለስ ብየንቬኑ መሪል የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ነበሩ፡፡ እድሜያቸው 75 ሲሆን የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሁነው የተሾሙት በ1806 ዓ.ም ነበር፡፡ ጳጳሱ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲመጡ እህታቸው ወ/ት ባፕቲስታን አብረዋቸው ነበር የመጡት:: እህትዬዋ ምንም እንኳን ትዳር ባይዙም እድሜ…»
#እገዛላታለሁ ... !!


#በአሌክስ_አብርሃም


ቆንጆ ማለት ለዓይን የሚማርክ፣ ለጆሮ የሚጥም፣ የሚያምር፣ የሚያስደስት፣ የሚያማልል፣ ሰው፣እንስሳ፣ ሳር፣ ቅጠል፣ አየር፣ ውሃ፣ ቃል፣ ሁኔታ፣ ድርጊት ሌላም መዓት ትርጉም ይኖረዋል፡፡
አሻሚ ነው ቃሉ፡፡ ውብ የሚለው ቃል ግን አያሻማም አያደናግርም፣ “ውብ” ማለት “እናቴ” ማለት ናት ! የእኔ እማማ ብቻ !!

አዎ እናቴ ውብ ናት !! በችግር የማይፈታ ውበት፡፡ ማንም በአድናቆት ቃል በእንቶፈንቶ ድለላ
ውሉን እጁ አስገብቶ የማይተረተረው ነጭ ቱባ ናት እማማ ፤ ፈገግ ስትል ከጥርሶቿ ድል ማድረግ በአካቤቢው ይነዛል፡፡ እንደ እናቴ ፈገግታ ልብ የሚሰነጥቅ ሳቅ አላየሁም፤ የእናቴ ፈገግታ ብርታቴ ነው፡፡ ሰውነቴ በፈገግታዋ ይታደሳል፡፡ የተፈጥሮ ፍልውሃ ነው ፈገግታዋ !!

ሕይወት ወገቧን አስራ ልታስለቅሳት ድንጋይ ስትፈነቅል እናቴ እማምዬ.የኔ ፀሐይ...በአንዲት
የአሽሙር ፈገግታ ትደቁሳታለች ፤ ሕይወት የጨለማ አረሟን በቤታችን ላይ ስትዘራ እናቴ
በፈገግታዋ ትመነጋግለውና የደስታ እና የሐሴት አዝመራ ቤታችን ይዘናፈላል፡፡እዛ ማሳ ውስጥ እኔ እቦርቃለሁ፡፡አውቆም ይሁን ሳያውቅ አባቴ ቤታችንን የምድር ዋልታ ላይ በበረዶ ገነባው፤ እናቴ በፈገግታ ገመድ ጎትታ መሃል አዲስ አበባ፣ አራት ኪሎ፣ ፀሐይ የሞላበት አመጣችው ቤቱን ከነግቢው ከነዛፉ !! እንደዛ ነው የሚሰማኝ፡፡

አባቴ በውትድርና ኤርትራ ሄደ፡፡
“እነከሌ አገር ሊገነጥሉ፣ መሬት ሊሸርፉ ነውና ሄደህ ልክ
አግባቸው!” በሚል ትዕዛዝ ከእኔ ከአንድ ልጁና ከሚወዳት ሚስቱ ተነጥሎ ሄደ :: “.…አቤት
ቁመና ! አቤት የትጥቅ ማማር !” እያለ ጎረቤቱ ሸኘው፡፡ አምሮ ሊገድል፣ አምሮ ሊሞት አባቴ፡፡
ሕፃን ነበርኩ፤ ብዥ ያለ ነው ትዝታዬ፡፡ አባቴ ሄደ፤ (ዘመተ ይሉታል)፡፡ ስልክ የለም፤ ደብዳቤ
የለም፤ ሄደና ጠፋ፡፡

እናቴ ታዲያ በፍፁም ንፅህና
ስድስት ዓመት ጠበቀችው:: ያውም በደጃችን፡ በእናቴ ውበት
መቶ ጀኔራል እየሸለለ፣ ሺ ካድሬ እየቋመጠ፣ ሚሊዩን አብዮት ጠባቂ ምራቁን እየዋጠ !!
"ንፅህናዋን በምን አወቅክ ?” ስድስት ዓመት ሙሉ ማታ ማታ አንዲት ቀን ሳታቋርጥ ፎቶው
ፊት ተንበርክካ ምን እያለች ትፀልይ እንደነበር እናንተ ታውቃላችሁ ? የአባቴን ፎቶ አቧራ ዝር እንዳይልበት በቀን ስንት ጊዜ ትወለውለው እንደነበርስ…?
ከቤታችን ዕቃዎች ውድ የተባለው መደርደሪያ ላይ ምን ይቀመጥ እንደነበርስ ? የአባቴ ፎቶ !! በዛ ናፍቆት በረበበት፣ ምስኪን እናትና ልጅ ምዕመን በሆኑበት፣ የብቸኝነት ቤተ መቅደስ ውስጥ የአባቴ ፎቶ ፅላት ነበር፡፡
አባቴ ፎቶ ጎን ተሳስቼ ደብተሬን ሳስቀምጥ ሳታስደነግጠኝ ቀስ ብላ ታነሳዋለች ፡፡ ቤት ለማዘጋጀት
እንዳይመስላችሁ፣ አባቴ ፎቶ አጠገብ ምንም እንዳይቀመጥ እንጂ !! እማማ የቃል ኪዳን
ቀለበቷን ሽጣ ምን ገዛች? ለኔ ቆንጆ ጫማና ልብስ ፣ ምድረ የትምህርት ቤት ማቲ የቀናበት
የደብተር መያዣ ቦርሳ ፣ ለአባቴ ፎቶ ወርቃማ የብረት ከፈፍ ያለው ባለመስታዋት የፎቶ ማስቀመጫ፤ በተረፈችው የቃል ኪዳን ቀለበቷን የምትመስል አርቴፊሻል ቀለበት ፡፡ በእንቁ ልብና በአርቴፊሻል ቀለበት ቃል ኪዳኗን አጠረች፤ ከእኔ በስተቀር ይሄንን ማንም አያውቅም::ለራሷስ ምን ገዛች?…ምንም !! እች ናት እናቴ!!

ስድስት ዓመት አባቴን ጠበቀችው ይሄ ሊመጣ ይችላል ተብሎ እዛም እዚህም እየተባለ የሚጠበቀው ዓይነት ጥበቃ ሳይሆን 'መቼ ሄደና' ብሎ ክችች የሚሉት አይነት የመንፈስ አብሮነት
በሌሉበት ማከበር !! ..ይሄ የመጀመሪያው ዓመት ላይ “ሄደብኝ የኔ ጌታ የልቤ ቁራሽ የደሜ ጭላፊ…" እያሉ ጎረቤት እንዲያባብል ድራማ መስራት፣ ዓመት በጨመረ ቁጥር 'አሁን ተፅናናች ሰው መቅረብ ጀመረች የሚባለው አይነት መጠበቅ ሳይሆን፣ ትላንትም ዛሬም ዓመታት ጉልበቱን በማይሰልቡት ጥልቅ መሻት ጠበቀችው:: ይህች ናት እናቴ!!

ስለ ኤርትራ በተወራ ቁጥር ኪሎ ስጋ ከአካሏ እየተገነጠለ ጠበቀች :: “ከኤርትራ የመጣ ሰው
በኮተቤ አለፈ" ሲሏት ነጠላዋን አንጠልጥላ ኮተቤ ትገኛለች፡፡” እንዲት ኤርትራዊት ተፈናቃይ
አቃቂ ኪዬስክ ከፈተች” ሲባል ከአራት ኪሎ እየተመላለሰች የስሙኒ ሻይ ቅጠል ለመግዛት
ደንበኛ የምትሆን ሴት ካለች እናቴ ብቻ ነበረች፡፡ እች ናት እማማ!!

እርጋታዋ የእኔ እማማ በእልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል” ተረት እልፍኛቸው ውስጥ ተሳላፊ እንደሚያበዙ ሴቶች አይደለችም ፤ ማንም የቃል ኪዳን መስመሯን አያልፍም፤ አገር ያውቃል፡ቤታችን ቤተ መቅደስ ነው፡፡ የፍቅር ፅላት በቅዱሰ ቅዱሳን እማማ ልብ ውስጥ አለ፡፡ እርጋታዋ ታማኝነቷን ይነግረኛል፡፡ ዓይኗ ከአባቴ ፎቶ ላይ ከተነቀለ ቀጥሎ ማረፊያው እኔ ላይ ነው፡፡
ጆሮዋ ወደ ውጭ አይቀሰርም፡፡ የኔን አርቲ ቡርቲ ወሬ እንደወንጌል በጥሞና መስማት የነፍሷ
እርካታ ነው፡፡ አባባ መጽሐፍ ቅዱስ፣ እኔ ዮሐንስ ራዕይዋ ታነበኛለች፣ ሰባት ቀንድ፣ እስራ
ስድስት ምላስ፣ ምንም ጆሮ የሌላቸው ልዩ ፍጥረቶች መሐል እናቴ ጆሮ ብቻ ሆና ትሰማኛለች ...!!

ጥቁር ፀጉሯ ሲዘናፈል፣ እንደማር የለሰለሰ ቆዳዋ አላፊ አግዳሚ ሲጠራ፣ ረጋ ባለ እርምጃ እንደ
ደመና ስትንሳፈፍ፣ “ፈዛዛ ውበቷን አቀለጠችው” ይሏታል፡፡ “ጎታታ እንደ ኤሊ ስትንቀረፈፍ
እድሜዋን ፈጀች” ይሏታል፡፡ በሌጣ ልባቸው ሮጠው ምናምን ስለቃረሙ የፈጠኑ የመስላቸው
የመንደራችን ከንቱ ሐሜተኞች፡፡ የፍቅር መስቀል ተሸክማ ዳገት የምትወጣ እናቴን ኤሊ ይሏታል፤
አፍ አውጥተው ኤሊ ይሏታል፡፡ የድንጋይ ልባሷ አንደነሱ ቀሚስ የትም ለማንም አለመገለቡ
እያበገናቸው፣ ተኳኩለው የሚጠብቋቸው ወታደር ውሽሞቻቸው ያልተኳኳለች እናቴን እያዩ
«ማናት ይህች ቆንጆ ?” ሲሏቸው እየበሸቁ…::

እማማዬ ስድስት ዓመት ጠበቀችው አባቴን፡፡ “ይኼኔ ባሏ ከአስመራ ቆንጆዎች ጋር አሸሼ ገዳሜ እያለ ነው፣ እሷ እዚህ ጉልበቷን አቅፋ ትጠራሞታለች” እያሏት ጎረቤቶቻችን፤ አስመራ አድረው ጧት አዲስ አበባ የገቡ ይመስል፡፡ “ለታመነልህ ታመን” የቆሸሸ ዲስኩራቸው “በአልታመኑልንም” ሰበብ ባሎቻቸውን እንዲክዱ፣ ፍቅረኞቻቸውን እንዲቀጥፉ መንገድ እየጠረገላቸው፣ ለውስጣቸው ግልሙትና ጥቅስ እየሆነላቸው፣ “የአስመራን ግልሙትና በአዲስ አበባ ግልሙትና መበቀል ፅድቅ
ነው" የተባለ ይመስል እማምዬን “ባልሽ ወንድ ነው አትመኝው” ይሏታል፡፡

እንድ ማለዳ በራችን ተንኳኳ፡፡ እማማ ከፈተች፡፡ ጎረቤቶቻችን አንድ የተጎሳቆለ ወታደር
አስከትለው መጡና “ባልሽ ሞቷል” አሏት :: “በዚህ ወርዶ በዚያ ሂዶ፣ መድፍ ተኩሶ፣ ታንክ
ማርኮ፣ በጀግንነት ሞተ !” አሏት፡፡ ዝም ብላ ሰማቻቸው፡፡ “ሰው ቀጥ ብሎ የማያይ ጨዋ፣ለትዳሩ ታማኝ፣ ወታደሩ ሁሉ እዛና እዚህ ሲል ባልሽ ግን የአንቺን ፎቶ ከደረት ኪሱ ሳይለይ
በየበረሃው ለእዝ ሲፋለም ኖሮ ሞተ” አሏት፡፡ ዝም ብላ ሰማቻቸው፡፡

አባቴ ሲሞት “ከጎኑ ነበርኩ” ያለው ጎስቋላ ወታደር ከአባቴ ሬሳ ኪስ ውስጥ አገኘሁት ያለውን
ፎቶ ሰጣት፡፡ እናቴና አባቴ ጎን ለጎን ሆነው የተነሱት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ነበር፡፡ ልክ መሀላቸው
👍30🔥1👏1
ላይ በጥይት የተቦደሰ ፎቶ እማማ እጅ ላይ እንዳለ በትከሻዋ ተንጠራርቼ ፎቶውን አየሁት፡፡
እንዴ ! በመድፍ ጥይት ነው እንዴ ፎቶውን የበሉት? እና እንዴት አንዲት ጥይት በቤተሰብ
መካከል ይሄን የሚያህል በደም ነጠብጣብም የተከበበ ሽንቁር ትፈጥራለች? ገረመኝ፡፡
“ባለቤትሽ ደረቱ ኪስ ነበር ፎቶውን የያዘው፡፡ ከጠላት የተተኮሰ ጥይት ፎቶ ባስቀመጠበት ኪሱ በኩል ደረቱን መታችው” አለ ድምፁ የሰለለው ወታደር፡፡ እማማ ፎቶውን በትኩረት አየችው፤ ረዥዥዥም ሰዓት ዝም ብላ አየችው፤ አላለቀሰችም፡፡ ፊቷም ላይ ምንም ለውጥ አልታየም፡፡ ከፎቶው ይልቅ ሽንቁሩን የምታይ መሰለኝ፡፡ አንዴ በረዥሙ ተነፈሰችና ፊት ለፊት መደርደሪያው ላይ የተቀመጠውን የአባባን ፎቶ ተመለከተች ፡፡

"አሁን ውሻ ሞት በከፈተው ቀዳዳ ጅብ ወንዶች ዘው ሊሉ አሰፈሰፉ፡፡ “አይዞሽ ሰው መቼስ ዘላለም አይኖር ምናምን…” ብለው በማስተዛዘን ስም ወደ ቤተ መቅደሳችን ዘው ሊሉ፡፡ እናቴ
“ማንም ለቅሶ እንዳይደርሰኝ” አለች፡፡ መንደሩ “ለየላት አበደች…” ብሎ አወራ፡፡

እማማ የእኔ መልአክ እኔንም ግራ አጋባችኝ ፡፡ አባቴ ሞቷል ወይስ አልሞተም ? ቢሞትም
እማማ “አልሞተም” ካለች አልሞተም፡፡
ቀኑ የአባባ መርዶ የመጣበት ሰኞ ነበር፡፡ ረጋ ብላ ቁርስ ሰራችልኝ፤ የሚጣፍጥ ጨጨብሳ
ስኳሩ በዛ ካለ ሻይ ጋር :: እሷ አልበላችም፡፡

በእጇ የያዘቻትን የሻይ ማንኪያ እየነቀነቀች በጥልቀት ታየኛለች፡፡ ዓይን ዓይኔን እያየችኝ ጥርግ
አድርጌ በላሁ፡፡

ጉንጬን ስማኝ ወደ ትምህርት ቤት ሸኘችኝ፡፡ ጉንጬን ነው ያልኩት ? በልምድ ብዙ ወላጆች
“የልጆቻቸውን ጉንጭ ይስማሉ” እንላለን እንጂ እንደ እኔ እናት ከሆነ ግን ወላጆች የልጆቻቸውን
ነፍስ ነው የሚስሙት ፡፡ አዎ እማምዬ ነፍሴን ስማ ነው የምትሸኘኝ!! ብዙ ከሄድኩ በኋላ
ወደ ቤታችን ዞር ስል አረንጓዴ ቢጃማዋን ለብሳ የበሩን ጣውላ ተደግፋ ቆማ እያየችኝ ነበር፡
የደከማት ትመስላለች፡፡ እማማን እንዲህ ከሩቁ ሳያት “ተመለስ ተመለስ.. እቅፍ አድርጋት
ከጎኗ አትለይ…” ይለኛል፡፡ ሁለት ሰው እሆናለሁ፤ እግሬ ወደፊት እየሄደ ልቤ ወደ እማማ
ወደኋላ ይሮጣል ፡፡

ዓይኖቿ ብርታቶቼ ናቸው:: ከኋላዬ ስትቆም እልፍ አእላፍ መላዕክት ከነሰይፋቸው፣ ከነእሳት ሰረገላቸው እኔን ሊጠብቁ የቆሙ ይመስለኛል፡፡ በምድር ላይ ያለ የጦር ሰራዊት ከነመሳሪያው
ያጀበኝ እናትዬ ከኋላዬ ስትቆም ሰማይ ይቀርበኛል፤ ደመና ባጭር የተቆረጠ ፀጉሬን ሲዳስሰኝ
ይሰማኛል፤ የእግዜር እግር ስር የቆምኩ ይመስለኛል፡፡ የምረግጠው ምድር በእግሮቼ ብርታት የሚናጥ፣ ድንጋዮቹ የሚፈነቃቀሉ ይመስለኛል፡፡ የእማማን የዕይታ ጥሩር ከለበስኩ ማንንም አልፈራም ፡፡ተራሮች ምንድናቸው? በእግሬ እንደማንከባልለው የጨርቅ ኳስ ናቸዋ !! ጨጨብሳ ባልበላም በጠረኗ ሺ ዓመት እኖራለሁ፤ በፈገግታዋ ዘላለም!!
እማምዬ የፍቅር ጥግ፣ የእናትነት አልፋና ኦሜጋዬ፡፡ እናንተ “ሴት እናት ናት! ሴት እህት ናት!” የምትሉ በደፈናው ኃይማኖተኛ ሁሉ መነኩሴ ነው እያላችሁ ነውና ይቅር ይበላችሁ፤
ሴትነት እናትነት አይደለም፡፡ “ሴት ከውስጧ የወጣ ገዳም ውስጥ ስትመንን እናት ትሆናለች”
ሴት…“ልጅ” የሚባል መስቀል ተሸክማ የሕይወትን ቀራንዬ ስትወጣ እናት ትባላለች ፤ ሴት
ልጅ የራሷን ዘመን ይቅርብኝ ብላ የልጆቿ የዘመን መስቀል ላይ በፍቅር ስትቸነከር ወደ እናትነት
ከፍታ ታርጋለች፡፡

እማማን ዞሬ አየኋት፡፡ የምትወደው ባሏን መርዶ ቅድም የሰማች ሴት በር ላይ ቆማለች፤ አይገርምም ? እናት የላትም፣አባት የላትም፣…ዘመድ የላትም፣ እኔ ብቻ ነኝ ያለኋት፡፡ የማላውቀው
ስሜት ወረረኝ፡፡ በአንድ ጊዜ ጀግናም ፈሪም ሆንኩ እኩል! “ማንም የላት” እና “እኔ አለሁላት”
የሚሉ ኃሳቦች ተጋጩብኝ፡፡

ትምህርት ቤቴ እስከምደርስ እንባዬ ጉንጮቼ ላይ እየፈሰሰ እንዲህ እያልኩ ለብቻዬ አነበንብ ነበር

“ሳድግ ለእማማ አዲስ አበባ ሱቆች ውስጥ ያሉትን ቀሚሶች ሁሉ እገዛላታለሁ፡፡ ፒያሳ ወርቅ
ቤቶች ወስጥ የተደረደሩትን ያልተ ደረደሩትንም የወርቅ ቀለበቶች ፡ ሃብሎች ጉትቻዎች ሁሉንም
ለእማማዬ እገዛላታለሁ፡፡ ለእናትዬ ትልቅ ቤት እገዛላታለሁ፡፡ ትልቅ ግቢ እገዛላታለሁ ...:

ባለ ሚሊዮን ፎቅ፡ ዛፉ ጨረቃን የሚነካ ሕንፃ እገዛላታለሁ፡፡ በመጨረሻው መስኮት ብቅ ብላ
የአባቴን ፎቶ ከነ ወርቃማ ፍሬሙ ጨረቃ ላይ ታስቀምጠዋለች፡፡ ማንም እንዳይደርስበት !
ሳድግ ለእማምዬ ሰፈራችንን አራት ኪሎን እንዳለ እገዛላታለሁ፡፡ ከነሐውልቱ፡ ከነዩኒቨርስቲው፣
ከነቤተመንግስቱ.…!!

ሳድግ ለእማማ፣ ለእኔ ደግ፣ ለእኔ ሩህሩህ አዲስ አበባን እገዛላታለሁ፡፡ ሳድግ ለኔ ትሁት፣ ለኔ ቃልኪዳን አክባሪ ኢትዮጵያን እገዛላታለሁ !! ከነሕዝቡ፣ ከነኃይማኖቱ፣ ከነቤተ ክርስቲያኑ፡
ከነ መስጊዱ እገዛላታለሁ፡፡
ሳድግ ኢትዮጵያን..ከነተራራው፣ ከነራስ ዳሽኑ፣ ከነሸለቆው፣ ከነጫካው፣ ከነዋልያና ጭላዳው፣
ከነአዋሹ፣ ከነጫሞ እና አብያታው፣ ከነሶፍዑመሩ፣ ከነላሊበላው፣ ከነፋሲለደሱ፣ ከነጣናው፣ ከነአባቱ፣ ከነአክሱሙ እ ገ ዛ ላ ታ ለ ሁ!!

እዎ እገዛላታለሁ !! “አልፈልግም የኔ እንቦቀቅላ ይሄ ሁሉ ምን ያደርግልኛል ?” ብትልም
እልሰማትም፣ እገዛላታለሁ...!!!
ሳድግ…ትልቁ የልቧ ስባሪ፣ የነፍሷ ቀንዲል፣ የፍቅሯ ስር፣ የእኔም አለኝታ እንደቀልድ የወደቀባትን
ምድር






እገዛላታለሁ ! ለ እ ማ ም ዬ !!


አለቀ
27👍24
#ምንዱባን


#ክፍል_ሁለት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....አልፎ አልፎ መስመሩን
የሚዘረጋው ጨረቃና ደፋ ቀና የሚሉት ከዋክብተ አካባቢው ጨርሶ ጨለማ እንዳይሆን ረድተዋል :: ስለዚህ የመሬቱን የሰማዩን ያህል አልጨለመም:: ሆኖም አካባቢው በጣም ያስፈራል፡፡.

ከጉብታውና ከተንጣለለው ሜዳ ላይ ከአንድ ቅርጸ ቢስ ዛፍ ሌላ
ምንም አልነበረም፡፡ ዛፉ መንገደኛው ከደረሰበት ሩቅ አልነበረም:: ሁናቴው ስላላማረው መንገደኛው ወደመጣበት ተመለሰ፡፡

ከምሽቱ ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ ሆኖአል፡፡ አካባቢውን ስለማያውቅ
መንገድ እንደመራው ብቻ ዝም ብሎ ተጓዘ፡፡ የከንቲባውን ቤት እንዳለፈ ከትምህርት ቤት አካባቢ ደረሰ፡፡ ትምህርት ቤቱን አልፎ እንደ ሄደ ቤተክርስቲያን አጋጠመው:: ገና ቤተክርስቲያኑን ሲያይ እጁን ጨብጦ ዓይኑን ወደላይ አንጋጠጠ፡፡

ከቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አንድ ማተሚያ ቤት አለ፡፡ ሰውዬው
ድካም አወራጭቶት ስለነበር ከዚህ የተሻለ ሥፍራ ሳይፈልግ ከማተሚያ ቤቱ አጠገብ ከነበረው የድንጋይ አግዳሚ መቀመጫ ላይ ተጋደመ::

ወዲያው እንደተጋደመ አንዲት አሮጊት ከቤተክርስቲያኑ ወጡ፡፡
«ወዳጄ ከዚህ ምን ታደርጋለህ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡

«አየሽ የእኔ አዛኝ፤ መተኛቴ ነዋ!» አሊ በቁጣና በድፍረት የማይሆን
መልስ መስጠቱ ሳይታወቀው:: ክብር የሚገባቸው አዛኝዋና ደግዋ ሴት ማዳም ላ ማርኩዚ ይባላሉ::

«እንዴ! ከድንጋይ ላይ!» አሉ፤ «ሌሊቱን በሙሉ ከድንጋይ ላይ
ተኝተህ ሊነጋልህ አይችልም:: ረሃብ እንዳንገላታህና ብርድ እንዳጠቃህ ሰውነትህ ይመስክራል፡፡ የሚያስጠጋ አላገኘህም?»

«ብዙ ቤት ሞከርኩ፤ የየቤቱን ደጃፍ አንኳኳሁ::»

«እና!»

‹‹ሁሉም ሰው ከበራፌ ሂድ አለኝ::
ደግዋ ሴት የሰውዬውን ጀርባ እየመቱ፡ ከአደባባዩ ባሻገር የሚታየውንና ከጳጳሱ ቤት አጠገብ የነበረውን ቤት ጠቆሙት፡፡
«ያንን ቤት ሞክረሃል?» ሲሉ ጠየቁት::

«አዎን::»

«ከዚያ ማዶ ከሚታየው ቤት አንኳኩተሃል?»

«የለም::»

«እዚያ ሞክር እስቲ፡፡»

እናያ ደገ ጳጳስ ከተማ ወስጥ ሲዘዋወሩ በመቆየታቸው ስለደከማቸው ያን እለት ማታ ከክፍላቸው ሳይወጡ ብዙ ቆዩ:: በተጨማሪም ብዙ ስራ
ስለነበራቸው «ሥራዩን ሳልጨርስ አልነሳም» በማለት አእዚያው አመሹ::

ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን እዚያው ሥራቸው ላይ ነበሩ:: በብጣሽ ወረቀትና በማስታወሻ ደብተር ላይ ጉልበታቸውን እያስደገፉ ሲፅፉ
እንደተለመደው አልጋቸው አጠገብ ከነበረው ቡፌ ከብር የተሠራ ሣህን ለማውጣት መዳም ማግልዋር ይገባሉ:: ሴትዬዋ ከተመለሱ በኋላ ጥቂት
ቆይቶ ገበታ እንደቀረበና እህታቸው እንደሚጠብቋቸው በመገመት ጳጳሱ ወደ ምግብ ቤት ሄዱ:: ምግብ ቤቱ፡ የአራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ዓይነት ሆኖ የእሳት ማንደጃ አለው:: ቢፈለግ ወደ አውራ ጎዳናው የሚያስወጣ በርም አለው:: በአትክልቱ በኩል መስኮት አለ፡፡

ማዳም ማግልዋር ገበታውን ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ጠረጴዛውን እያስተካከሉ ከመድምዋዚል ባፕቲስታን ጋር ይጫወታሉ:: ገበታው አጠገብ
ሻማ ከትንሽ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ እየተቀጣጠለ ነው:: ከማንደጃው ውስጥ
የተቀጣጠለው እሳት ፍም ብዛት ስለነበረው ክፍሉ ይሞቃል፡፡ የቤታቸው በር እንዴት መቆለፍ እንዳለበት መዳም ማግልዋር ሲያወሩ ጳጳሰ ይገባሉ፡፡

ማዳም ማግልዋር ለእራት የሚሆን ሸቀጣሸቀጥ ለመግዛት ወደ ገበያ ሄደው ሳለ አንድ መግቢያ ያጣ ማጅራት መቺ ከተማ መግባቱንና ይህ ሰው
በጊዜ ከቤታቸው በማይገቡ ሰዎች ላይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ሲወራ ይሰማሉ፡፡ ሁለቱ ሴቶች ስለዚሁ ጉዳይ ሲያወሩ ጳጳስ ስለገቡ «አባታችን
መዳም ማግልግር የሚናገሩትን ይሰማሉ?» በማለት ጠየቅዋቸው::

«የምትሉት ነገር ግልጽ ባይሆንልኝም ሰምቼአለሁ» አሉ ጳጳሱ፡፡ከዚያም ፊታቸውን ወደሚነድደው እሳት በማዞርና እጆቻቸውን ከጉልበታቸው
ላይ በማሳረፍ ሠራተኛቸውን እያዩ

«ታዲያስ ፤ ምንድነው ጉዳዩ? የሚያስፈራ ነገር አለ እንዴ?» ሲሉ ጠየቁ፡፡

ይህን ጊዜ መዳም ማግልዌር ሳያስቡት ታሪኩን በማጋነን አዋሯቸው::
«ያለመጫሚያ ባዶ እግሩን የሚጓዝ ማጅራት መቺ፧ ሌባ፤ ቀማኛ ከተማ ገብቷል» አሉ፡፡ «ክዊን ላባር ሄዶ ማረፊያ ቢጠይቅ ባለቤቱ አልፈቀደለትም::
ከመሸ በኋላ ከተማ ውስጥ ሲዘዋወር ታይታል:: ስልቻውን በገመድ አስርና ተሸክሞ ይዞራል:: መልኩ ደግሞ በጣም የሚያስፈራ ነው::

«እውነትሽን ነው?» ሲሉ ጳጳሱ ጠየቁ፡፡

ጳጳሱ በታሪኩ የተመሰጡና ፍርሃትም ያደረባቸው ስለመሰላቸው

መዳም ማግልዋር ታሪካቸውን በኩራት ይቀጥላሉ:: «አዎን አባታችን፤ እውነት ነው:: ዛሬ ማታ ከተማ ውስጥ አንድ ነገር ይሆናል፡፡ ከተማው ሁሉ ይህንኑ ነው የሚያወራው:: መድምዋዜል ባፕቲስታን ደግሞ እንደምትለው...» በማለት ሴትዬዋ ንግግርዋን ስትቀጥል «እኔ» በማለት የጳጳሱ እህት ጣልቃ ገብተው «ያልኩት ነገር የለም» ይላሉ፡፡

ተቃውሞውን እንዳልሰሙ መስለው መዳም ማግልዋር ልፍለፋቸውን ቀጠሉ፡፡

«የዚህ ቤት ደህንነት ይህን ያህል አስተማማኝ አይደለም:: አባታችን
ቢፈቅዱልኝ ሄጄ ቁልፍ ለሚሠሩት ሰወዬ የድሮዎቹን መቀርቀሪያዎች
መልሰው እንዲገጥሟቸው ልንገራቸው:: መቀርቀሪያዎቹ ስላሉ በደቂቃ ይሰርዋቸዋል፡፡ ለዛሬ ማታ ብቻ እንኳን ባይሆን ለወደፊቱም ጥሩ ነው፤
በራችን ጠንካራ መቀርቀሪያ ይግባለት:: በቀላሉ የሚከፈት በር እጅግ አደገኛና አስፈሪ ነው:: አባታችን እንደሆነ ይቅርታ ቢደረግልኝ እኩለ ሌሊት
እንኳን ቢሆን ቤት ለእንግዳ፤ ይግቡ የማለት ልምድ አለብዎት:: ግን መቼም ለዚህ ፈቃድ መጠየቅ እንኳን አስፈላጊ» ሴትዮዋ አሳባቸውን ሳያጠቃልሉ በር በኃይል ይንኳኳል፡፡ «ይግቡ» አሉ ጳጳሱ፡፡

በሩ ተከፈተ:: ኣንድ ሰው ሰዎቹ ከነበሩበት ክፍል ውስጥ ገባ፡፡
ያ የምናውቀው ማደሪያ ፍለጋ ከቤት ቤት ፤ ከሥፍራ ሥፍራ
ይንከራተት የነበረው መንገደኛ ነበር፡፡ ሰውዬው በሩን መልሶ ሳይዘጋ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዶ ቆም አለ፡፡ ስልቻውን በጀርባው ተሽክሞ ዱላውን
በእጁ እንደያዘ ነው:: የእሳቱ ውጋጋን ከፊቱ ላይ ሲያርፍ ሻካራውና ድካም ያጎሳቆለው ፊቱ የጭካኔ ምልክት እንዳለበት አጉልቶታል፡፡ ሆኖም ያ ስሜት ወደ ውስጥ የተቀበረ እንጂ በግልጽ የወጣ ኣልነበረም:: የመናፍስት
በአካል መታየት ነበር የሚመስለው::

ማዳም ማግልዋር ለመጮህ እንኳን አቅም አልነበራቸውም፡፡ እንደቆሙ እየተንቀጠቀጡ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ፡፡
መድምዋዜል ባፕቲስታን ዞር ሲሉ ሰውዬው ወደ ውስጥ ሲገባ አዩ፡፡
በፍርሃት ተውጠው ከመቀመጫቸው ብድግ አሉ፡፡ ከዚያም ዝግ ብለው ወደሚነድደው እሳት ዞረው ወንድማቸውን ተመለከቱ፡፡ ፊታቸውን ሲያዞሩ ትንሽ መንፈሳቸው ተረጋጋ፡፡

ጳጳሱ ሰውዬውን በጥሞና ተመለከቱት:: ምን እንደሚፈልግ ሊጠይቁት አፋቸውን እንደከፈቱ ለመናገር እድል ሳይሰጣቸው የያዘውን ዱላ በሁለት
እጁ በመመርኮዝ ከዚያ የነበሩትን ሰዎች አንድ በአንድ ከቃኘ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ መናገር ጀመረ::

«ተመልከቱኝ! ስሜ ዣን ቫልዣ ይባላል፡፡ የተፈረደብኝ ወንጀለኛ
👍27
ነኝ:: ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እሥር ቤት ነበርኩ፡፡ ከአራት ቀን በፊት
ተፈታሁ:: ወደ ፓንታልዩ ነው የምሄደው:: የተፈታሁ እለት ከቱሉን ተነስቼ በእግሬ እየተጓዝኩ ዛሬ ከእዚህ ደርሻለሁ:: በዛሬው ቀን ብቻ ወደ 55 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዤአለሁ:: ማምሻውን ወደዚህ ከተማ እንደገባሁ
ወደ ሆቴል ቤት ሄጄ ማደሪያ እንዲሰጡኝ ጠየቅሁ:: ከእሥር ቤት የተሰጠኝ መታወቂያ ብቻ በመያዜ ከዚያ ላድር አልቻልኩም:: ወህኒ ቤት ሄጄ እንዲያሳድሩኝ ብጠይቃቸው ከእዚያም አባረሩኝ:: ከከተማ ወጣ ብዬ ከዛፍ
ስር ለማደር ፈልጌ ነበር፡፡ ሆኖም ጨለማውን ፈራሁት:: ደመናውም
ስላንገበበ ይዘንባል ብዬ ስለሰጋሁና ደግ አምላክ ኖሮም ዝናቡን ያቆማል ብዬ ስላላመንሁ መጠጊያ አገኛለሁ በማለት ወደዚች ከተማ ተመለስኩ፡፡
ከከተማው መካከል ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ከድንጋይ ላይ ተጋደምኩ፡፡
እንደተጋደምኩ አንዲት ደግ ሴት ቤታችሁን ጠቁማ 'ከእዚያ ቤት አንኳኳ' አለችኝ:: መጥቼም አንኳኳሁ:: ይህ ቤት የማን ቤት እንደሆነ ብትነግሩኝ፡፡
ሆቴል ቤት ነው? ከሆነ ገንዘብ አለኝ:: እሥር ቤት ውስጥ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ሠርቼ 109 ፍራንክና 15 ሱስ ያህል አጠራቅሜአለሁና ሂሣቡን እከፍላለሁ:: በጣም ደክሞኛል:: 55 ኪሎሜትር በአንድ ቀን በእግር መጓዝ ማለት ምን ያህል አድካሚ እንደሆነ ሳትገነዘቡ አትቀሩም:: ደግሞም በጣም ርቦኛል:: ታሳድሩኛላችሁ?»

«መዳም ማግልዋር» አሉ ጳጳሱ፤ «ሌላ ሳህን አምጪ፡፡»
ሰውዬው ጥቂት ራመድ ብሉ ከጠረጴዛው ላይ ተቀምጦ ይነድ
ወደነበረው የሻማ መብራት ጠጋ አለ፡፡ ሰዎቹ ችግሩን ያላወቁለት ስለመሰለው
«ቆዩ» ሲል ጮክ ብሎ በቁጣ ከተናገረ በኋላ «እሱን አይደለም የምለው ፤
ተግባብተናል? የመርከብ ቀዛፊ ባሪያ፤ ወንጀለኛ ነኝ:: ያንን አድካሚ የመቅዘፍ ሥራ ስሠራ ኖሬ ነው የምመጣው:: መታወቂያዩን ተመልከቱ:: የወንጀለኛ መታወቂያ ነው:: ሌላ መታወቂያ ስለሌለኝ የትም ብሄድ ያባርሩኛል::
ወሰዱት! ሰው ሁሉ እንደሆነ አባርሮኛል፡፡ እናንተስ ትቀበለኛላችሁ? ይህ ቤት ለመሆኑ ሆቴል ቤት ነው? የምቀምሰው ነገር ትሰጡኛላችሁ? ማደሪያስ
ትፈልጉኛላችሁ? የፈረሶች ጋጣ እንኳን ቢሆን አልጠየፍም:: ››

«ማዳም ማግልዋር አለ ጳጳሱ፤ «ከእኔ መኝታ ቤት አጠገብ ካለው
ክፍል ውስጥ ያለው አልጋ ይነጠፍ፡፡»
ማዳም ማግልዋር ትእዛዙን ለመፈጸም ወጡ፡፡ ጳጳሱ ፊታቸውን
ወደ እንግዳው አመሩ፡፡
«ልጄ አረፍ በልና ሰውነትህን አማሙቅ፡፡ በቶሎ ገበታ እንቀርባለን፡፡
እራታችንንም እስክንበላ መኝታው ይዘጋጅልሃል፡፡

በመጨረሻ ሰውዬው ገባው:: ያ አስፈሪና ጭጋግ የመሰለው ፊቱ
ተፈታ፡፡ የደስታ ውጋጋን ፊቱ ላይ ያበራ ጀመር፡፡ «እውነትም ሊያሳድሩኝ ይሆን» ሲል ራሱን ጠየቀ:: ከደስታ ብዛት እንደ እብድ ይቀባጥር ጀመር::
«እውነት ነው? እንዴት? ልታሳድሩኝ ነው? ወይስ አታሳድሩኝም?
ወንጀለኛውን! ሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ 'አንተ ውሻ፣ ከዚህ ውጣ' በማለት ፋንታ ልጄ እያሉ በአክብሮት ጠሩኝ እኮ! አሁን ከልብዎ ነው? ከዚህ
እንዳድር ፈቅደውልኛል? ጥሩ ሰዎች ናችሁ:: እኔ ደግሞ ገንዘብ ስላለኝ በሚገባ እከፍላችኋለሁ:: ይቅርታ ብቻ ፤ ድፍረት ባይሆንብኝ፤ የሆቴሉ
ባለቤት እርስዎ ይመስለኛል:: » ስምዎን ልጠይቅ! የጠየቁኝን እከፍላለሁ::
ጥሩ ሰው ነዎት፡፡ የሆቴሉ አስተዳዳሪና ባለቤት ነዎት ወይስ አይደለም?»
«ከእዚህ ቤት የምኖር መነኩሴ ነኝ» አሉ ጳጳሱ በፈገግታ ::
«መነኩሴ» አለ ሰውዩው:: «እህ... ፍጹም መነከሴ! እንግዲያውስ
ገንዘብ አያስከፍሉማ? የተጎዳን የሚረዱ ፤ የተጠቃን የሚያጸናኑ፤ ለነፍስዎ ያደሩ ሰው ነዎታ! አይደለም? የዚያ ትልቅ ቤተክርስቲያን ቄሰ ገበዝ
መሆንዎ ነዋ! አዎን፧ መሆን አለብዎት:: እንዴት ያለሁ ደደብ ሰው ነኝ፤እንዴት ቆብዎን ልብ አላልኩም::

ሰውዩው የባጥ የቆጡን እያለ ስልቻውንና ዱላውን ከአንድ ጥግ
አስቀምጦ መታወቂያውን ወደ ቦርሳው ከመለሰ በኋላ ቁጭ አለ፡፡
«አባቴ፤ ሰብኣዊ ርህራሄና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረብዎት ሰው
ነዎት:: እኔን እንደሌለች ሰዎች አላንቋሸሸኝም:: የካህናት ምሳሌ ነዎት፡፡ እንደ እርስዎም ያለ ካህን ያለ አይመስለኝም:: እንግዲያማ ገንዘብ አይቀበለኝም ማለት ነው?»
«የለም» አለ ጳጳሱ፤ «ገንዘብህን ያው» ካለ በኋላ በኃይል ተነፈሰ፡፡

ሰውየው ልፍለፋውን ቀጠለ፡፡ «አባ፡ ብፁዕ ወቅዱስ ለነፍስዎ ያደሩ ነዎታ! ከእዚያ ከነበርኩበት እስር ቤት እንዳንድ ቀን ትምህርት ይሰጠን ነበር፡፡ አንድ ቀን አንድ ጳጳስ አየሁ:: ሰዎች 'አባታችን' እያሉ ሲጠርዋቸው ሰምቼአለሁ:: ማርሴይ ከተባለ ሥፍራ የመጡ ሲሆን የዚያ አገር ሊቀ ጳጳስ
እንደነበሩ ተነግሮናል:: ጳጳሱ የጳጳሶች ጳጳስ ናቸው ብለውናል:: እዩ እንደት እንደምዘባርቅ:: እኔ እንደሆንክ ምኑንም አልያዝኩም ፧ አልገባኝም ነበር፡፡
ይቅርታ ያድርጉልኝ:: እኛ መሐይሞች እኮ ምንም አናዉቅም:: አንድ ቀን
ከቤተመቅደሱ ውስጥ ሆነው ቀዳሲውን መሩ:: አንድ ሾል ያለና ከወርቅ የተሰራ ነገር ራሳቸው ላይ አጥልቀህ የፀሐይ ጨረር ከላዩ ላይ ሲያርፍ፡በጣም የሚያብረቀርቅ ነገር ነበር:: በሰልፍ፡ እንድንቆም ስለተደረገና ብዙም ብርሃን ስላልነበረ ጳጳሰ በግልጽ አልታዩንም:: ንግግር አድርገውልናል:: ግን በመካከላችን ርቀት ስለነበረ የሚሉትን በግልጽ ለመስማት አልቻልንም::
ጳጳስ ማለት እንግዲህ ይኸው ነው መሰለኝ::»
እንግዳው ሲናገር ጳጳሱ የተበረገደውን በር ዘጉ:: መዳም ማግልዌር ተጨማሪ አንድ ሣህን ይዘው መጥተው ከጠረጴዛ ላይ አኖሩ፡፡

«መዳም ማግልዋር» አለ ጳጳሱ ፤ «አሁን ያመጡትን ሳህን እሳቱ
ከሚነድበት ቀረብ ኣድርገው ቢያኖሩት:: ከዚያም ወደ እንግዳው ዞር ብለው
«የውጪ አየር በጣም ይቀዘቅዛል፤ ሳይበርድህ አልቀረም ልጄ?» አሉት::

ጳጳሱ ረጋ ባለ መንፈስና በሚጋብገዛ ድምፅ ልጄ› ብለው በጠሩት ቁጥር የሰውዬው ፊት ፈገግ ይላል:: የተፈረደበት ወንጀለኛን ልጄ' ብሎ
መጥራት ማለት ባህር ላይ ቁጭ ብሎ በውሃ ጥም ሊሞት ለተቃረበ ሰው አንድ ብርጭቆ ንጹህ ውሃ እንደመስጠት ያህል ነበር፡፡ ሰው የናቀው ክብር ይጠማዋል::
«ፋኖሱ በቂ ብርሃን የለውም» አለ: ጳጳሱ::
መዳም ማግልዋር ገባቸው:: ወደ ጳጳሱ መኝታ ቤት ሄደው ሁለት
ከብር የተሠሩ ረጃጅም የሻማ ማብሪያ አመጡ:: ሻማ ለኩሰው ከሻማ ማብሪያው ላይ ካደረጉ በኋላ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጥዋቸው::
«አባቴ» አለ ሰውዬው፤ «ጥሩ ሰው ነዎት ፤ እኔን አይንቁኝም፤
አያንቋሽሹኝም:: ከቤትዎ ከማስጠጋት አልፈው በትህትና ያናግሩኛል::
ለእኔ ክብር ብለው ተጨማሪ ሻማ እንዲበራ አዘዙ፡፡ እኔም የሕይወት
ታሪኬን ሳልደብቅ ከየት እንደመጣሁና ምን ያህል የተሰቃየሁ መሆኔን
ገለፅኩልዎት::»
ከአጠገቡ ተቀምጠው የነበሩት ሰው ቀስ ብለው እጁን ይዘው
የሚከተለውን ተናገሩ፡፡
«ማን እንደሆንክ እንድትነግረኝ እያስፈልግም:: ይህ የእኔ ቤት
አይደለም፤ የክርስቶስ ቤት ነው:: እርሱ ማንኛውንም ባይተዋር ችግር፧ መከራና ስቃይ እንዳለበት እንጂ ማን እንደሆነ አይጠይቅም:: አንተ መከራን
👍24
ቀምሰሃል፧ ተርበሃል ፤ ተጠምተሃል:: ስለዚህ ቤቴ ቤትህ ነው:: ለዚህም እንድታመሰግነኝ አልፈልግም:: አስጠጋኝም ብለህ አትጠይቀኝ:: ይህ ቤት
ማረፊያ ለሚፈልግ ፤ ለተቸገረ እንጂ የማንም ቤት አይደለም:: ማነው መንገደኛው? ማነው እንግዳ? እመነኝና አንተ ከእኔ ይበልጥ ቤተኛ ነህ::
ከእዚህ ቤት ያለው ነገር ሁሉ ያንተ ነው፡፡ ያንተን ስም ማወቅ ለምን
ያስፈልገኛል? ከዚህም በላይ አንተ ሳትነግረኝ እኔ አውቄዋለሁ::»
ሰውዬው በመገረም አፉን ከፈተ::
«እርግጥ ነው?:: ማን እንደሆንኩ አውቀዋል?»
«አዎን» አሉ ጳጳሱ፤ «
ስምህ ወንድሜ ነው::»
«በቃ…. በቃ አባቴ» ሲል ሰውዬው ጮኸ፡፡ «ከዚህ ቤት ስገባ ጠኔ
ይዞኝ ነበር፡፡ ግን የደግነትዎ ብዛት ይሁን እኔ እንጃ! ምን እንደነካኝ
አላውቅም፧ ምንም ሳልበላ ያ ሁሉ ረሃብ ተወግዶልኛል፡፡»
ጳጳሱ እንደገና አትኩረው ከተመለከቱት በኋላ «ብዙ መከራና ስቃይዐደርሶብሃል» አሉት::

«እወይ! ያቺ ቀይዋ ጥብቆ ፤ የብረቱ ሰንሰለት፧ የእንጨቱ መኝታ!
ሙቀቱ፤ ብርዱ፤ ግርፋቱ፤ ከዚያ የነበሩ ባሮች.. ኧረ ምን ቅጡ፤ አንድ ቃል ቢተነፍሱ የጨለማ ቤቱ ፧ በታመሙ ጊዜ እንኳን ከዚያ ጨለማ ቤት በብረት ሰንሰለት ተጠፍር መኖሩ! ውሾች፧ ውሾች እንኳን ከዚያ የተሻለ ኑሮ ነው የሚኖሩት:: አሥራ ዘጠኝ ዓመት! አርባ ስድስት ዓመቴ ነው።
አሁን ደግሞ መታወቂያዬ የወንጀለኛ ነው:: ይኸው ነው ታሪኩ፡፡»
«ይሁን» አሉ ጳጳሱ፤ «የስቃይና የመከራን ቤት ለቅቀህ መጥተሃል፡፡ አሁን ግን ስማኝ ያንን አስፈሪና አሳዛኝ ቦታ በሰዎች ላይ ጥላቻንና ቁጣን
አሳድሮብህ የምትላቅቀው ከሆነ የሚታዘንልህ ሰው ነህ፡፡ በበጎ ፈቃድ! በጨዋነትና በሰላም የምትለቀው ከሆነ ግን ከሁላችንም ትበልጣለህ፡፡»
በዚህ ጊዜ መዳም ማግልዋር ገበታ መቅረቡን ያበስራሉ፡፡ ከቀረበው
ገበታ ሾርባ፤ ሥጋ፣ አይብና ዳቦ ይገኛል፡፡ የሚወጣ ቪኖም ነበር፡፡
ጳጳሱ የደስታ፣ የእርካታ ስሜትና «እንኳን ደህና መጣህ» የሚል
ፈገግታ እየታየባቸው «እራት ቀርቦአል» አሉ ወደ እንግዳው እየተመለከቱ፡፡

እንግዳወን ከቀኛቸው አስቀመጠት:: መድምዋዚዬል ባፕቲስታን
ከበስተግራቸው ተቀመጡ:: ጳጳሱ ማዕዱን ከባረኩ በኋላ ከሾርባው ለራሳቸው አወጡ፡፡ ሰውዬው ምግቡ ላይ ተረባረበ፡፡
«ገበታው ላይ ኣንድ ነገር የጎደለ መሰለኝ» አሉ ጳጳሱ በድንገት፡፡
መዳም ማግልግር ገበታ ሲያቀርቡ ያዘጋጁት ለጊዜው አስፈላጊ የነበሩትን ሦስት ከብር የተሠሩ ሣህኖችን ብቻ ነበር፡፡ በዚያ ቤት ባህል እንግዳ በመጣ ቁጥር ስድስቱንም ከብር የተሠሩ ሣህኖች ከገበታው ላይ
መደርደር ነበረባቸው:: ለጉራ ሳይሆን ሌላም እንግዳ ቢመጣ ደስ ይለናል በማለት ቸርነታቸውን ለማሳየት ነው::
መዳም ማግልዋር የጳጳሱ አስተያየት ስለገባቸው ወዲያው ከመቅጽበት የተቀሩት የብር ሣህኖች መጥተው ከእያንዳንዳቸው ትይዩ ተቀመጡ፡፡
ከእራት በኋላ ጳጳሱ እህታቸውን ተሰናብተውና አንድ ሻማ ለራሳቸው፣ አንድ ሌላ ደግሞ ለእንግዳው ለመስጠት ሁለት ሻማ ይዘው ተነሱ፡፡
ከዚያም «ልጄ ክፍልህን ላሳይህ» አሉት:: ሰውዬው ተከተላቸው::
ለእንግዳው የተዘጋጀው ክፍል በጳጳሱ መኝታ ቤት አልፎ ነበር
የሚገኘው:: እንግዳው ልክ ከጳጳሱ መኝታ ቤት ሲያልፍ መዳም ማግልዋር
እነዚያ የሚያማምሩ የብር ሣህኖች ከብፁዕነታቸው መኝታ ቤት ውስጥ ይገኝ ከነበረው ቡፌ ውስጥ እያስቀመጡ ስለነበር ዣን ቫልዣ ተመለከተ፡፡ዘወትር ማታ ማታ መዳም ማግልግር ከመተኛታቸው በፊት ሣህኖቹን
አጣጥበው ከቡፌው ውስጥ ነው የሚያስቀምጧቸው::

የእንግዳው አልጋ ከነበረበት ክፍል ደረሱ:: ሰው ያልታኛበት ንጹህ
ነጭ አንሶላ ነው የተነጠፈው:: ሰውዬው ሻማውን አስተካክሉ ከአንዲት አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠ፡፡
‹‹መልካም እንቅልፍ፤ ነገ ጠዋት ከመሄድህ በፊት ላሞች ስላሉን
ትኩስ ወተት ጠጥተህ ትሄዳለህ» አሉ ጳጳሱ::
«አመሰግናለሁ አባታችን» አለ እንግዳው::የምስጋና ቃሉን እንደደረደረ ወዲያው ከመቅጽበት እነዚያ ሁለት ሴቶች ከዚያ ሲኖሩ ውሃ ሊያደርጋቸው ይችል የነበረ ነገር ይናገራል:: ወደ
ጳጳሱ ዞር ብሉና ፊቱን ለዋውጦ በሻከረ ድምፅ ጮክ እያለ «አሁን ጥሩ ነው ፤ ከመኝታ ቤትዎ አጠገብ ነው ያስተኙኝ:: ለመሆኑ በነገሩ አስበውበታል?
ነፍሰ ገዳይ አለመሆኔን ማን ነግሮት?» ሲል ጠየቃቸው::»
«እግዚአብሔር ያውቃል» ሲሉ በእርጋታ መለሰለት::
ከዚያም ምንም ሳይጨነቁና ድምፅ ሳያሰሙ ከራሱ ጋር እንደሚነጋገር ወይም በጥሞና ጸሎት እንደሚያደርስ ሰው ከንፈራቸውን ካነቃነቁና
ሰውዬውን ከባረኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ክፍላቸው ሄዱ፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከዚያ ቤት የነበረ ሰው ሁሉ እንቅልፍ ወሰደው::

እኩለ ሌሊት ላይ ዣን ቫልዣ ነቃ::

💫ይቀጥላል💫
👍34
#ንፋስ_ወዴት_ነህ_ቢሉት_ማርና #ወተት_ወዳለበት


#በአሌክስ_አብርሃም

እማማ አረጋሽ ቤት ሩጫ ልናይ ተሰብስበናል፡፡ ልጃቸው ከውጭ አገር ትልቅ ቴሌቪዥን
ስላመጣችላቸው በሳቸው ቴሌቪዥን ማየት የሩጫ ጥም ይቆርጣል፡፡ መቸስ ቴሌቪዥኑን
ግድግዳ በሉት፡፡ የእማማ አረጋሽ ቤት ከሦስት ግድግዳና ከአንድ ቴሌቪዥን ነው የተዋቀረው
ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ባለቤታቸው አቶ ፈንታው ነፍሳቸውን ይማራቸው ዜና ለምን
በየቀበሌው እንደዞሩ ይሄን ዓለም ሳያዩ ሞቱ፤ ሳያልፍላቸው ሞቱ፡፡ “ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን በማያ ጊዜያቸው ሞቱ” ይላል ጎረቤቱ፡፡

ጀመረ ሩጫው ገንዘቤ ዲባባ፣ አበባ አረጋዊ ቴሌቪዥኑን እየሞሉ ደግሞ ራቅ እያሉ…

እኛም ግንዘብ…ገንዘብዬ…ገንዘባችን ሩጭ አሳያቸው…አይዞሽ” እያልን፣ ያው አበባ አረጋዊ ፈትለክ ብላ ወርቁን ወሰደችው፡፡ ያውም የስዊዲን ማልያ ለብሳ በስዊዲን ባንዲራ ተውባ ! ብዙዎቻችን ቀዝቀዝ ስንል እማማ ወለላ “እልልልልልልልልልልልልልል እሰይ እሰይ” አሉ (ጎረቤት ናቸዉ
“እንዴ ለስዊዲን እኮ ነው የሮጠችው ብንላቸው፣
“ይሁና ልጃችን ናት” አሉ፡፡
እማማ አረጋሽ ታዲያ፣ “አይ ወለላዬ አሁንስ እማማ ፅጌን መሰልሽኝ” አሉ፡፡

ስለ እማማ ፅጌ ለመስማት ጆሯችን ቆመ፡፡

“ማናቸው እማማ ፅጌ ?

እማማ አረጋሽ ስላነሷቸው ሴት ታሪክ አወጉን…

በድሮ ጊዜ እኛ ሰፈር እች አሁን ጋሽ እቁባይ ገፋ አድርገው ያጠሯት ቦታ ላይ አንዲት የእማማ
ፅጌ ድንጋይ የምትባል ጥቁር ድንጋይ ነበረች አጠገቧ ደግሞ የላስቲክ ቤት፡፡ አሁንም አጥሩ
ውስጥ ድንጋዩ አለ፡፡ ታሪክን ሲያጥሩት ያው አጥሩ ውስጥም ሁኖ ቢሆን ይጮሃል፡፡
እማማ ፅጌ አንዲት ልጅ ነበረቻቸው፡፡ መቼስ ቁንጅናዋ አይወራም፡፡ መልአክ፣ መልአክ በሏት፡፡

እንዲት ልጃቸው ናት፣ አባቷ አይታወቅም፡፡ እችው ባልቴት እናቷ እዚህች ድንጋይ ላይ ተቀምጠው
ድንችም ቲማቲምም እየቸረቸሩ አሳደጓት፡፡ በኋላ ህመሙም እርጅናውም ተጫናቸው ግማሽ
ችርችራ፣ ግማሽ ልመና በሆነ ሕይወት ይውተረተሩ ጀመር ::

መቼስ ልጅቱ መንገድ ዳር እየኖረች ልዕልት መሰለች፡፡የመንደሩ ሴቶች ጠርሙስ ሙሉ ቅባት ጨርሰው፣ ያማረ ለብሰው፣ ትኩስ በልተው ጠብ ያላለላቸው መልክ እዚህች መንገድ ዳር
ላስቲክ ከልላ በምፅዋት የምትኖር ልጅ ላይ ፈሰሰ፡፡ ፀጉሯ ተዘናፈለ፣ ዳሌዋ ሞላ ወንዱ ሁሉ
ዓይኑ ይቀላውጣት ጀመረ፡፡

አንድ ምሽት እማማ ፅጌ ኡኡ አሉ፡፡ መንደርተኛው ወደ ላስቲኳ ቤታቸው ተሰበሰበ፡፡ ልጅቱ
የለችም ጠፋች፡፡ መንደርተኛው እማማ ፅጌ ጋር በመሆን ሳምንት ሙሉ ፈለገ፡፡ የለችም፡፡ሀ
ቆንጆዋ፣ ባልቴት እናቷን ትታ ምጥ ትግባ ስምጥ እልም ድርግም አለች፡፡ ጎረቤቱ ተስፋ ቆርጦ
ወደ የራሱ ጉዳይ ሲመለስም ሚስኪኗ ባልቴት ግን ከዛች ቀን ጀምሮ ለአስራ አንድ ዓመታት
ታየች በተባለበት ተንከራተቱ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራቸው ከተማ የተረፋቸው መንደር የለም፡፡

በየደረሱበት የዕለት ጉርሳቸውን እየለመኑ ፅንፍ የለሽ በሆነ የእናት ፍቅር ልጃቸውን ፈለጉ፡፡

በአስራ አንደኛው ዓመት ልጃቸው ውጭ አገር ኖራ እንደተመለሰችና አንድ ባለፀጋ ልታገባ ሰርጉ
እየተደገሰ መሆኑን ከሁነኛ ሰው ሰሙ፡፡ “አይ ልጄ ፈልጋ አጥታኝ ነው” አሉና ወደ አዲሳባ አቀኑ፡፡ አዲሳባ እንደገቡ እንድ ጥግ ላይ ከያዟት ፌስታል ሌት ቀን ብለው ያስቀመጧትንና ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ለብሰዋት የማያውቋትን ቀሚስ አውጥተው ለበሱ፡፡ ራሳቸውን አየት አደረጉና፣ “እመቤት መሰልኩ አይደለም እንዴ፣ ልጄንማ አላዋርዳትም አሉና ፈገግ አሉ፡፡

ልጃቸው አለች ወደተባለበት ቤት ሳያርፉ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ቤተ መንግሥት የመሰለው ቤት
በሁለት ዘበኞች ይጠበቃል፡፡ “የልጄ ቤት” አሉ በኩራት ፊት ለፊት ቆመው፤ ከዛም ጠጋ ሲሉ
እግዜር ይስጥሽ አለ አንዱ ዘበኛ፣ እማ ፅጌ ይሄን ቃል ሺ ጊዜ ሰምተውታል የዛሬው ግን
ለየት አለባቸው፡፡

ሳቅ ሳቅ አላቸው፡፡ ይሄ ጥበቃ ከደቂቃዎች በኋላ ጎንበስ ቀና ሲልላቸው ታያቸው፣
“ልጄዋ እኔ እንኳን የመጣሁት ቢጣዬን ብዬ ነው”

“ቢጣ ማናት?”

“ልጄ ናታ እዚህ ቤት እንደምትኖር ነግረውኛል”

“እንደዛ የምትባል ሴት የለችም እዚህ እማማ”

ጠጋ አሉትና፣ “ሙሽራይቱ ማነው ስሟ

“እሜቴ ስማቸው ብሩክታዊት ነው
ግራ ተጋብተው ከግቢው በር እንደቆሙ ቢጣ ከሸበላ ባለቤቷ ጋር ውሃ በመሰለ መኪና ብቅ
አለች፡፡ ራሷ ናት፣ እናትና ልጅ ፊት ለፊት ተፋጠጡ፡፡ እናት ችለው መቆም አልቻሉም ጉልበታቸው ተብረከረከ፣ “ቢጣዬ ያይኔ አበባ " ብለው ወደ መኪናው በእንብርክክ ቀረቡ ልጅ ኮስተር አለች፣ የመኪናውን መስተዋት ዝቅ አደረገች፣ ጥቁር መነፅሯን ወደ ፀጉሯ ከፍ ራሷን መታ አድርጋ ውብ ፀጉሯን ወደ ጎን አለችና፤

“ምንድነው?” አለች ፊቷን አጨፍግጋ፡፡

ቢጣዬ..እናትሽ ስንከራተት ኖሬ ይሄው መጣሁልሽ፡፡ ሄድኩ አይባልም? ሜዳ ላይ ጣል አድርገሽ ማን አላት ብለሽ…"

“ማነህ ወደዛ ውሰዳት! የማንም ወፈፌ እየመጣ…እንሂድ ሃኒ አለች ቢጣ መኪናውን ወደ
ሚያሽከረከረው ሰው ዞር ብላ…፡፡

“ሃሃሃሃሃሃ ሃኒዩ አትበሳጭ አዲሳባ በነዚህ ዓይነት ፈጣጣዎች ነው የተሞላው ነዳጁን ሰጠና
ፈትለክ፡፡ እማማ ፅጌ ተንበርክከው ቀሩ፡፡ ራሳቸውን አይተው “ልጄ እስክትረሳኝ ተጎሳቁያለ
ማለት ነው” አሉ በልጃቸው አልፈረዱም፡፡

እስከሰርጉ ቀን ከግቢው ፊት ለፊት ካለች በረንዳ ላይ ዝናብና ፀሐይ እየተፈራቀባቸው ልት።
መኪና እንደልብስ እየቀያየረች ስትገባና ስትወጣ እየተመለከቱ በልጃቸው ምቾትና ታላቅ ደረጃ
መድረስ የራሳቸውን መከራ ረስተው ቆዩ፡፡ አንድ ቀን እናቴ ብላ እጄን እንደምትዘረጋላቸው
ተስፋ በማድረግ፡፡ (ልጅ ያላየቻቸው እየመሰለች ስታልፍ ቆየች ከአንድ ወር በላይ !!)
የሰርጉ ቀን፣ እናት ያችን ቀሚስ ከፌስታላቸው አወጡና ለበሱ፣ የኖሩባትን በረንዳ ላጠራረጉ
ፌስታላቸው ውስጥ ያስቀመጧትን ትንሽ ብልቃጥ አወጡና በረንዳው ላይ ባለ መስታወት ዓይናቸውን ተኳሉ፡፡

ከሰዓት ሙሽራዋ በነጭ ቀሚስ ተውብ በክፍት መኪና ስትደርስ ጎረቤቱ፡ ሰርገኛው ሲተረማመስ
መሃል መንገድ ላይ ከሰርጉ መኪና ፊት ለፊት እማማ ፅጌ እስከሰታቸውን አወረዱት፡፡
ሁሉ እብድ መስለውት ለአፍታ ትኩረቱን ወደ ባልቴቷ አዞረ፡፡ ከጫጫታው ኮሙዚቃው በላይ
የገዘፈ ድምፅ ከባልቴቷ ወጣ፡፡

መጣችም ሄደችመ ደሟ ከደሜ ስጋዋ ከስጋዬ የተጨለፈ ልጅ ቢጣዬ እቻት እንኳን ደስ ያለሽ በሉኝ ሙሽራው ልጄን አደራ" አሉና ፈታኝውን እዙረው ወደ በረንዳቸው ሄዱ ከኋላቸው የእድምተኛው ሳቅና ፈዝ እየተከተላቸው::

ሌሊቱን ሲጨፈር ሲደለቅ ታድሮ ጧት ያደረው ሰርገኛ ሲወጣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት
የአስክሬን ማንሻ መኪና ከሰርጉ ቤት ፊት ለፊት ካለ ሱቅ በረንዳ ላይ የአንዲት ባልቴት ሬሳ
ሲያነሱ ታየ፡፡ ሬሳው ከተነሳበት በረንዳ ንፋስ እየገፋ ወደ ሰርግ ቤቱ በር የወሰደው አንድ
ጥቁርና ነጭ ፎቶ ዘበኛው እግር ስር ደረሰ፡፡ እናትና ልጅ የተነሱት ፎቶ ነበር፡፡

ወይ የሰው መመሳሰል.ልጅቱ እትዬን አትመስልም…” አለ ዘበኛው ለጓደኛው፣

እድያ እሱን ወዲያ ጥላህ ይሄን ያዝ!” ብሎ ከሰርጉ የተረፈ ቢራ ሰጠው:: ዘበኛው ፎቶውን
ጥሎ ወደ ቢራው ዞረ፡፡ ነፋሱ ጥቁርና ነጩን ፎቶ ወዳልታውቀ ቦታ እየገፋ ወሰደው::

እኛ ያሳደግናት በማር በወተት" የሰርግ ዘፈን ከግቢው ይሰማል፡፡

አለቀ
👍396👎1😁1
#የመግቢያ_ፈተና


#በአሌክስ_አብርሃም

አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈትኜ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ ውጤት በማምጣቴ መንደሩ በደስታ አበደ
የበለጠ ወሬውን ያሞቀው ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መመደቤ ነበር፡፡

እሳቷ ኸዋና ከተማው ከባህሩ ዘላ ጥርቅም አለች ተባለልኝ፡፡ ወሬው ሁሉ ስለኔ ሆነ፡፡

“…የእቶ ዘለቀ ልጅ ይንበርስቲ በጠሰ"

“የትኛው"

“ይሄ ባለፈው በሬ ወግቶት የነበረው

“…ኧረረረረረረረ ሰው ሁሉ ሞኛሞኝ መስሎ፤ ለካስ እንዲህ ጥይት ነው ጃል

“ቀለም ዘልቆት ነው ፈዘዝ ያለው አይ…ጎበዝ ነው ከድሮውም አረ፡፡ወሬው ከመንደር መንደር
ተሰራጨ፣ በዛን ሰሞን የመንደሩ ሕፃናት አጥንተን እንሙት አሉ፡፡ ለወትሮው በቅስቀሳ ትምህት
ቤት የሚሄደው ውሪ ሁሉ፣ ሰዓቱ ሳይደርስ ደብተሩን አንጠልጥሉ ቱርርር እያለ ይበር ጀመር፡፡

ሁሉ ነገር ተሰናድቶ ድል ያለ የመሸኛ ግብዣ ተደረገና ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ተሰባስቦ ጨዋታው እንደደራ፣ ከከተማ የመጣው አጎቴ ስለሁኔታው ያወጋኝ ጀመረ!

“መላኩ"

“አባት አጎቴ"

"ከሆነስ ሆነና የትኛው ስፍራ ነው የደለደሉህ ስድስት ኪሎ የማባለው ነው የካቲት 12 ሆስፒታል አጠገብ?

አይደለም እጎቴ አምስት ኪሎ የሚባለው ነው በቃ እዛ የአክስቴ ቤት ጎን ከዪኒበርስቲው ጋር ኩታ ገጠም ናቸው እንዲህ አጥር ነው የሚለያቸው አለች ከመንደራችን
ብቸኛዋ አዲሳባን ሁለት ጊዜ ሂዳባታለች የምትባለው አረጋሽ በእርግጥም ወደ አምስት ወር አዲስ አበባ ቆይታ ተመልሳለች አጎቴ ቀጠለ አምስት ኪሎ የት ነው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይቀርባል መላኩ የሚባለው እውነት ነው።

"ኧረ አጎቴ አይደለም"

“ተዉት በቃ አራት ኪሎ ነው” አለች አረጋሽ፡ ቀጠል አድርጋም፡ እዛው ዝቅ ብሎ እኮ ነው! ከዚህ እንደ አቶ አስራት ቤት ቢሆን ነው፡ አጎቴ ጉግሳ ቤቱ እዛው ስር ነው"
"መላኩ፣ ለመሆኑ አራት ኪሎ በመሆኑ ከፍቶኸል?" አለ እጎቱ ፊቴን እያየ ፡ ፡

እናቴ ፊቴ ላይ ያለውን ቅሬታ አንብባ እንዲህ አለች፡

"አይዞህ የኔ አንበሳ፡ እግርህ አዲሳባን ይርገጥ እንጂ ግዴለም ከአራት ጀምረህ አምስትም፡
ስድስትም ሰባትም ኪሎ ትገባለህ፡፡ ስንቅ ነው; እኔ እናትህ እያለሁ አትቸገርም አለች፡፡
"እናትህ እውነቷን ነው! የትም ብትሆን እንዳትሰጋ!” አለ አባቴ ፉከራ በሚመስል ድምፅ፡፡

አጎቴ ቀላል ሰው አይደለም፡ ጊዜው ራቅ ይበል እንጂ አዲሳባ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን
ሰንብቶ መጥቷል፡፡ እናም ባለችው እውቀት ስለ አራት ኪሎ እንዲህ አለ፡ “ኧረረረ ዋናው ጭንቅላቱ ላይ ነህና፣ ቤተ መንግስቱ ውስጥ በለው በቃ አለ ጋቢውን ወደ ትካሻው ከፍ እያደረገ፡፡

ግምታቸው ምርር ስላደረገኝ እንዲህ አልኩ፡ እኔ የተደለደልኩት ኮሜርስ የሚባል ቦታ ነው፡፡

አጉረመረሙ።

"እሱ ደሞ ወዴት ነው? አዲስ አባ ነው…ሲባልም አልሰማሁ” አለ አጎቴ፡፡

እኔም የት እንደሆነ አላውቅም እቴ፡ ብቻ እዛው አዲሳባ ኣንዱ ግድም ነው አልኩ፡፡
በዕርግጥም አራት ኪሎ፡ እምስት ኪሎ፡ ስድስት ኪሎ ካልተባለ ዩኒቨርስቲ ስለማይመስለኝ
ኮሜርስ ባሉት ነገር ከፍቶኝ ነበር፡፡

“ምንድነው የሚያስተምሩት?” አለ አባቴ፡፡

“የንግድ ስራ ይላል ወረቀቱ ላይ" አልኩ፡፡

“መድሃኒዓለም! ንግድ ምን ትምህርት ይላል? ይሄው እኛ ዝም ብለን እያቀላጠፍነው አይደለም!” አለ አባቴ፣ ታዋቂ የእህል ነጋዴ ነው፡፡

“እንዴዴዴዴዴ ባንክ የምትሰራው የአክስቴ ልጅ የተማረችበት ነው፡ ኧረ ጥሩ ተማሪ ቤት ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ሞት ይርሳኝ! ያ በሪሁን፡ የእናቴ የእህት ልጅ፣ ቤቱ እዛው ነው አለች አረጋሽ፡፡

ጋሽ ዘለቀ የመንደራችን አስቂኝ ሽማግሌ፣ “አረጋሽ እንደው ያንች ዘመዶች ሁሉ ዩኒበርስቲ
እጥር ስር ብቻ ነው እንዴ ቤት የሚሰሩት?!” አሉና ሰዉን አሳቁት፡፡

ሁሉም እንደየአቅሙ የሰማውንም ያየውንም ስለእዲስ አበባ ይመከረኝ ጀመረ፡፡

የመጀመሪያው አጎቴ ነው፣

“መላኩ አዲሳባ እንዲህ ቀላል አገር እንዳይመስልህ ባህር ነው
ባህር…በዛ ላይ ሌባው አይጣል፤ ሴት ወንዱ ሞላጫ ነው፡፡ ሱፉን ግጥም አድርጎ መኳንንት
የመሰለው ሰው፣ ጠጋ ብሎ ከኪስህ ገንዘብህን ይከተልብሀል፡፡ ሴቷ ስትውረገረግ ልብህን ትሰልበዋለች፡፡ አንዳች አፍዝ አደንግዝ አላቸው፡፡ ጠንቀቅ ብለህ እንደወታደር ነው መኖር
የኣዲሳባ ሕዝብ ፈዛዛ አይወድም

አጎቴ አዲስ አበባ የሄደው ለሕከምና ነበር፡፡ ታዲያ ከቆየባቸው አርባ አምስት ቀናት
ሰላሳ ዘጠኙን ጥቁር አንበሳ ተኝቶ ነው ያሳለፈው፤ ሁለት ቀን የካቲት 12 ሆስፒታል...
አንድ ቀን ጦር ኃይሎች…ከህመሙ ጋር እየታገለ ስለአዲሳባ ይሄን ሁሉ ማወቁ ግሩም ነው፡፡

ዙሪያሽ ነበረች ቀጣይ መካሪ፣ “ወይ አዲስ አበባ…ሂሂሂሂ…የጉድ አገር እኮ ናት፣ መንገድ
ስትሻገር ነጭ ነጫን እየረገጥክ ነው፣ ሳት ካለህ መኪናው አያፈናፍንም…”

“ይሄ አዲስአባ ሰፊ አገር ነው አልተባለም እንዴ? የምን የማሪያም መንገድ ነው! ነጩን
ጥቁሩን እንዳሻው ይራመድ እንጂ” አለች እናቴ፡፡

ሂሂሂሂሂ ሕግ ነው፤ እንደኛ አገር ያገኙበት መርገጥ የለም እናቴ፣” ብላ አረጋሽ ቀጠለች፣
እና…መላኩ ዋናው ነገር…ዋናው የአዲስአባ ሴቶች አሳሳቾች ናቸው፤ ያንተ ዓይነቱን ሸበላማ
ካዩ ተከትለውህ ነው የሚመጡት፡፡ ኮስተር በል፣ ፊት አትስጣቸው! ኧረ በድንግሏ ሃፍረት የሚባል አያቃቸውም…”

አንድ ቀን የአክስቴ ልጆች ካማሪካ መጡና እራት እንብላ ብለው ሰብስበው ወሰዱን፡፡ ጉድ አየሁ…ጉድ ሴት እና ወንድ፣ ሴትና ወንድ ሁነው ነው የሚቀመጡት፡፡ አንድ ብቻህን ቁሪር ብሎ መቀመጥ ነውር ነው የተባለ ይመስል…፡፡ ሃዲያ አንድ ጊዜ ይጎርሱና መሳሳም፣ ደሞ ይጎርሱና መሳሳም..እማምላክን እህሉን በውሃ ሳይሆ በመሳሳም የሚያወራርዱት ነው እኮ
የሚመስሉት…ሁሁሁሁ” ብላ በሀፍረት ሳቀች፡፡
“ወላዲት አምላከ!ኸምግብ ቤቱ ነው የሚሳሳሙት?
ፈረሰኛው ጊወርጊስ!”

ሁሉም በወሬው ተገርመው ተንጫጩ፡፡

ቀጠለች አረጋሽ፣ “ደሞ ሴቶቹ እንዲቹ እርቃናቸውን ቁራጭ ልብስ ጣል አርገው እንዲቹ
እንደፈጠራቸው ነው የሚመናቀሩት…የቆዳቸው ልስላሴ…መስተዋት ነው የሚመሳስሉት…
አይበርዳቸውም ወይ? እላለሁ እኔማ አለች፡፡ …ገረመኝ!!
እና መላኩ፣ በሌላ ሌላው እንኳን አንተ አትመከርም፣ በሴቶቹ እንዳትፈትን አደራ!" ብላ
ምከሯን ጨረሰች፡፡

እንደጧት አዲሳባ ልሳፈር ሌሊቱን ሲያቃዠኝ አደረ፡፡ እራት እየበላሁ ይመስለኛል፣ የቆዳዋ ጥራት
መስተዋት የመሰለ ሴት እርቃኗን ጎኔ ተቀምጣ አንዴ በጎረስኩ ቁጥር የምትስመኝ ይመስለኛል፤
ልክ እንደማወራረጃ፡፡ ከዚሁ ፈተናው ጀመረኝ፡፡

አለቀ
👍376😁2
#ምንዱባን


#ክፍል_ሶስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


.....ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከዚያ ቤት የነበረ ሰው ሁሉ እንቅልፍ ወሰደው::

እኩለ ሌሊት ላይ ዣን ቫልዣ ነቃ::

ዣን ቫልዣ ገጠሬ ሲሆን የተወለደው ብሬ በመባል ከታወቀ ደሃ ቤተሰብ ነው። በልጅነቱ ትምህርት ቤት ገብቶ የመማር እድል ባለማግኘቱ መሐይም ነው ከአደገ በኋላ ከተማ ውስጥ በአትክልተኝነት ሥራ ጀመረ

ዣን ቫልዣ በተፈጥሮው ለሰው አሳቢ እንጂ አዛኝ አልነበረም፡፡ ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ነው የሞቱት:: እናቱ የሞቱት ታምመው ሲሆን አባቱ ከዛፍ ላይ ወድቀው ነው:: አባቱም እንደ እርሱ አትክልተኛ ስለነበሩ ዛፍ ለመከርከም
ከትልቅ ዛፍ ላይ ወጥተው ሳለ በድንገት ወድቀው ነው ሕይወታቸው ያለፈው:: ከቤተሰቡ መካከል በሕይወት የቀረች ከእርሱ ሌላ አንዲት እህት
ነበረችው:: የእህቱ ባል ሰባት ልጆች ጥሎባት ይጠፋል፡፡ ዣን ቫልዣን ያስጠጋችው እህቱ ስትሆን ባልዋ እስከጠፋ ድረስ ተንከባክባ ነበር ያሳደገችው::
ባልዬው ሲሞት የትልቁ ልጃቸው እድሜ ስምንት ዓመት ሲሆን የመጨረሻው ልጅ እድሜ አንድ ዐመት ነበር፡፡ ዣን ቫልዣ በዚያን ጊዜ 25 ዓመቱ ነበር::
እርሱ በተራው የልጆቹን አባት ተክቶ እህቱንና ልጆችዋን ይረዳ ጀመር::የወጣትነት ዘመኑን አዳጋችና አድካሚ ግን ብዙ ገቢ በማያስገኝ ሥራ ላይ ነበር ያሳለፈው:: በጊዜ ማጣትና ድኅነት ምክንያት በአፍላ ዘመኑ የከንፈር ወዳጅ እንኳን አልነበረውም:: እንዲያውም ከነአካቴው ለፍቅር ጊዜ
አልነበረውም ማለት ይቻላል፡፡

ማታ ማታ ከመሸ በኋላ ከቤቱ ተመልሶ ቃል ሳይናገር ያገኘውን
ይበላል፡፡ አንዳንድ ቀን ያቸን የምስኪን እራቱን ሲበላ እህቱ ከቀረበለት ምግብ ጥቂቱን እንደገና እየወሰደች ለልጆችዋ ትሰጥበታለች:: ይህ ሲሆን
በረጅም ፀጉሩ ፊቱን ሸፍኖ በዝምታ የተረፈችውን ይበላል:: ምንም ነገር እንዳልሆነ በመቁጠር ራሱን ለማታለል ይሞክራል:: ምርጫም አልነበረውም::

ዛፍ በሚገረዝበት ወራት በቀን እስከ 18 ሱስ ያገኛል:: ሥራ ሳይመርጥ ያገኘውን ይሠራል። እህቱም ትሠራለች:: ቢሆንም ራሳቸውን ያልቻለ ሰባት ልጆችን ማሳደግ ቀላል አልነበረም:: ገንዘቡ ስላልበቃቸው ቤተሰቡ
ችግር ቀስ በቀስ እያለ የሚያሳድደው አሳዛኝ ቤተሰብ ሆነ
የአንድ ዘመን ክረምት በጣም የከፋ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ዣን ቫልዣ ሥራ አ፣ልነበረውም:: በዚህ የተነሣ ቤተሰቡ የሚላስ ወይም የሚቀመስ ነገር ያጣል:: አንድ ቀን እሑድ ማታ የአንድ ዳቦ መጋገሪያ ቤት ባለቤት ሊተኛ ሲል የዳቦ ቤቱ መስታወት ሲሰበር ይሰማል፡፡ የሰውዬው መኖሪያ ቅጥር
ግቢው ውስጥ ስለነበር በጊዜ በመድረሱ በተሰበረወ መስታወት በኩል አንድ ሰው እጁን አሾልኮ ዳቦ ሲሰርቅ ያየዋል:: ሌባው ዳቦውን ይዞ ሮጠ፡፡የዳቦ ቤቱ መስታወት የሰበረው በቡጢ ስለነበር እጁ ይደማል:: ስለዚህ
ዳቦው የተወሰደው በሌባ ለመሆነ ሌላ ማስረጃ አላስፈለገም:: ሌባ
ሰውዬ ዣን ቫልገ ነበር፡፡

ይህ የሆነው በ1795 ዓ.ም መጨረሻ ነው:: ዣን ቫልዣ የተዘጋ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ ሰብሮ ለመስረቅ በመሞከሩ «ወንጀለኛ ነው» ተብሎ ተፈረደበት:: ብያኔው ለአምስት ዓመታት በባርነት የመርከብ ቀዛፊ
ሆኖ እንዲሠራ ነበር፡፡

ዣን ቫልዣ አንገቱ በብረት ሰንሰለት ታስሮ ቱሉን ወደተባለ እስር
ቤት ተወሰደ:: ጉዞው ሃያ ሰባት ቀን ወሰደበት፡፡ የተጓዘው በእንስሳ በሚጎተት ጋሪ ነበር፡፡ ከተወሰነለት ሥፍራ እንደደረሰ ጥብቆ አለበሱት:: ያለፈው ታሪኩ ፤ ስሙ እንኳን ሳይቀር ተለወጠ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስሙ ዣን ቫልዣ ሳይሆን ቁጥር 24 ሺህ 601 ሆነ::

ከዚያ በኋላ እህቱ ምን ሆነች? ሰባት ልጆችዋስ ምን ደረሱ? ስለዚህ ጉዳይ ራሱን ያስጨነቀ አልነበረም:: ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፎች ከትልቅ ዛፍ
ግንድ ሲቆረጥ ማነው ስለቅርንጫፎቹ የሚጨነቀው?
አራተኛ ዓመቱን ሲያገባድድ ዣን ቫልዣ ከእስር ቤት አምልጦ
ነፃነቱን የማግኘት እድል አጋጠመው:: ከእንደዚያ ባለ አስፈሪ ቦታ ያለ ሰዎች ዘወትር እንደሚተባበሩ ሁሉ የእርሱም የሥራ ጓደኞች ረድተውት
አመለጠ፡፡ ለሁለት ቀናት በየጥሻውና በእርሻ ቦታ እየተሽሎከሎከ ቆየ፡፡
በሁለተኛው ቀን ግን ወደማታ እንደገና ተያዘ፡፡ ለ36 ሰዓት ያህል እህል አልቀመሰም:: እንቅልፍም አልተኛም:: ለማምለጥ በመሞከሩ የእሥራት ዘመኑን በሦስት ዓመት ፍርድ ቤቱ አራዘመበት:: በጠቅላላው ስምንት ዓመት ሆነበት ማለት ነው:: በስድስተኛው ዓመት እንደገና ለማምለጥ
ሞክሮ ሳይሳካለት ቀረ:: ማታ ስም ሲጠራ 'አቤት' ሳይል በመቅረቱ
ጥሩምባ ተነፋ፡፡ ማታውኑ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ከመርከብ ስር ተሸሽጎ አገኙት፡፡ ዘበኛው ሊይዘው ሲል ተናነቀው፡፡ ወንጀሉ እጥፍ ሆነ፡፡ ለማምለጥ
በመሞከሩና ዘበኛ በመተናነቁ ለዚህ ጥፋቱ አምስት ዓመት ተፈረደበት::
አሥራ ሦስት ዓመት ሆነ፡፡ በአሥረኛው ዓመት እንደገና ለማምለጥ ሞክሮ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ:: ለዚህም ሙከራው ሦስት ዓመት ተፈረደበት::አሥራ ስድስት ዓመት! በመጨረሻም በአሥራ ሦስተኛ ዓመቱ ይመስለኛል
እንደገና ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ ከአራት ሰዓት በኋላ እንደገና ተያዘ፡፡
ለአራት ሰዓት ከእስር ቤት በመጥፋቱ አሁንም አራት ዐመት ተፈረደበት:: ሃያ ዓመት! ዳቦ በመሰረቁ ከእስር ቤት የገባው በ1796 ዓ.ም ሲሆን ከአሥራ
ዘጠኝ ዓመት እሥራት በኋላ ግን ለማምለጥ ቻለ፡፡

መርከብ ቀዛፊዎች ከሚታሰሩበት ሲገባ እየተንቀጠቀጠና እያለቀሰ
ነበር:: ያን ሥፍራ ሲለቅ ግን ልቡ ደንድኖ ነበር የወጣው:: ከዚያ ሲገባ ተስፋ ቆርጦ ነበር የገባው፧ ሲወጣ ግን ተስፋ ቢስ ብቻ ሳይሆን ጨካኝም ሆኖ ነው የወጣው::

ታዲያ የዚህ ነፍስ ሕይወት ምን ይሆን!

ታሪኩን ለማውሳት እንሞክር እስቲ፡፡ የሰውዬው ችግር በሕብረተሰቡ የተፈጠረ ስለሆነ ይኸው ሕብረተሰብ እነዚህን ነገሮች አጢኖ መመልከት
ይኖርበታል፡፡

ቀደም ሲል እንዳልነው ዣን ቫልዣ አላዋቂ ነው:: ግን ደደብ አይደለም:: በተፈጥሮው ጭምት ነው:: ሰንኳላው እድሉ ደግሞ በይበልጥ እንዲጨምትና
እንዲያስተውል ገፋፍቶታል፡፡ ሲገረፍ፤ በሰንሰለት ሲጠፈር፤ ጨለማ ቤት ሲታሰር ሰውነቱ በድካም ብዛት ዝሏል፡፡ የሌሊት ቁር ሲያቆራምደው፤ የቀን ፀሐይ ሲያወራጨው፤ እንዲሁም ከእንጨት ላይ ተኝቶ ዘወትር
ከአሳብ ውስጥ እየዋኘ ከኅሊናው ጋር ሲሟገት የኖረ ሰው ነው::

ራሱን እንደ ፍርድ ቤት ስለቆጠረ ምርመራውን በመጀመሪያ ከራሱ
ይጀምራል:: ያለ አግባብ የተቀጣ የዋህና ቀና ሰው አለመሆኑን ኅሊናው ያውቃል:: ሕገ ወጥ ተግባር መፈጸሙን አይክድም፡፡ ምናልባት ያንን አንድ ዳቦ ቢለምን ኖሮ አይነፈግም ነበር ይሆናል፡፡ አዛኝ ወይም አሠሪ እስኪያገኝ
ድረስ ደግሞ መታገስ ነበረበት፡፡ ለእነዚያ የትም በትኖአቸው ለቀረው ምስኪኖችም ይኸው ይበጅ ነበር፡፡ ስለዚህ የፈጸመው ተግባር የሞኝ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ አንድ አርቆ ለማየት የማይችል ድሃ ዓለምን በጉልበት
አሸንፋለሁ ብሉ ቢጋፈጥ ወይም ችግሮችን በሌብነት እወጣለሁ ብሎ ቢታለል ስህተተኛነቱን ገሃድ ያወጣል፡፡
👍213
ነገር ግን በአሳዛኝ ታሪኩ ውስጥ ስህተት የፈጸመው ዣን ቫልዣ ብቻ
ነው? እንደ እርሱ ያለ ትጉህ ሠራተኛ ሥራ አጥቶ መንከራተቱና ዳቦ ማጣቱ የሚያሳዝን አይደለም? ስህተት ፈጽሞ ጥፋተኛነቱን ቢያምንም
ቅጣቱ ግን ቅጥ ያጣና የአውሬዎች ብያኔ መሆነ አግባብ ነው? ወንጀለኛ ወንጀል ለመሥራት ካለው ፍላጎት ይበልጥ ሕግን አንተርሶ ቅጣትን የማክረር ባህርይ ትክክል ነው? የቅጣት ክብደት ወንጀልን ለማጥፋትና
በውጤቱ ሁኔታዎችን ለማሻሻል ሳይሆን የተበዳዮችን ስህተት ለማጉላትና በቸልተኞች ስህተት ለመቀየር፤ ወንጀለኞችን ከሚገባው በላይ ለማሰቃየት
አበዳሪን በባለዕዳ ለመለወጥ ከሆነ ይህ ተገቢ ነው?

ዣን ቫልዣ ይህን እያሰላሰለ «እውነቱ ቢወጣ ማነው ጥፋተኛ?» ሲል ራሱን ይጠይቃል፡፡

ሕብረተሰቡ አንድ ጊዜ በምክንያት ባልተደገፈ ግድየለሽነት፤ በሌላ
ጊዜ ደግሞ ርህራሄ በተለየው ዓይን እያየ በአባሎቹ ላይ ተመሳሳይ ፍርድ የመበየን ኃይል ቢኖረውም ሕብረተሰቡ ውስጥ እድል በሚያፈራው ሀብት
እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ድርሻ የሚደርሳቸው ምስኪኖችን እጅግ አድርጎ ማሳደድ የጭካኔ አይደለም?

ዣን ቫልዣ እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች እየጠየቀ በሕብረተሰቡ
ላይ ፈርዶ ብያኔ ይሰጣል፡፡ ብያኔው በሕብረተሰቡ ላይ የከረረ ጥላቻን ማሳደር ነበር፡፡ በሕይወት ዘመኑ የደረሰበት ፈተናና ስቃይ የሕብረተሰቡ ውጤት መሆኑን አመነ፡፡ ምናልባት አንድ ቀን እድል ቢገጥመው ሕብረተሰቡን
እንደሚበቀል ለራሱ ቃል ይገባል፡፡
የሕብረተሰቡ አባሎች ሕይወቱን አበላሹበት:: ከቁጡ ፊታቸው ሌላ
ያሳዩት ነገር አልነበረም፡፡ ማንም ቢሆን ለመላላጥ ካልሆነ በስተቀር ፍቅርን አላሳየውም:: ከሕፃንነቱ ማለት ከእናቱና ከእህቱ ከተለየ ጀምሮ ማንም ቢሆን ርህራሄ በተለየው በክፉ ቃል እንጂ በጥሞናና በሰላም ያነጋገረው
የለም፡፡ በስቃይ ላይ ስቃይ እየታከለበት በሄደ ቁጥር ሕይወት ጦርነት መሆኑን አመነ፡፡ በጦርነቱም እርሱ ድል እንደተመታ አወቀ፡፡ ከጥላቻ በስተቀር ሌላ የተማረው ነገር አልነበረም:: እስር ቤት እያለ ይህን ትምህርቱን
ለማጠናከርና ከዚያም ሲወጣ ይዞት እንደሚወጣ ወሰነ፡፡ ዣን ቫልዣ በዚህ ሳይቆም ለስቃዩ ምክንያት የሆነውን ሕብረተሰብ ለፍርድ አቅርቦ በእርሱ ላይ ብያኔ መስጠት ብቻ ሳይሆን ሕብረተሰቡን የፈጠረውንም አምላክ ጭምር አወገዘ፡፡

ዣን ቫልዣ ከታሠረበት ቱሉን ከተባለ ቦታ እንደ እርሱ ያሉ ምስኪኖች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ራሳቸውን ለሌሎች መስዋዕት በሚያደርጉት ጥቂት ግለሰቦች ተከፍቶ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትምህርትና ንቃት ለተንኮልና
ለክፋት በር የሚከፍቱ ቢሆነም በአርባ ዓመቱ ትምህርት ቤት ገብቶ መጻፍና ማንበብ ተማረ::
እነዚያ 19 የስቃይና የባርነት ዘመን ይህ ነፍስ በአንድ ጊዜ እየሞተና
በሌላ ጊዜ ሕይወት እየዘራ ነው የኖረው:: የሕይወቱ ግድግዳ በአንድ በኩል ብርሃን ሲገባው በሌላ በኩል ጨለማ ቦርቡሮታል፡፡

ዣን ቫልዣ በተፈጥሮው ክፉ ሰው አልነበረም:: ከእስር ቤቱ ሲደርስ
ልቡ ቀና ነገር ነበር የሚያስበው:: እነዚያ ውስጥ እያለ ግን ሕብረተሰብን ጠልቶ እርሱም ክፉ ሰው እንደሆነ አመነ፡፡

አንድ መዘንጋት የሌለብን ነገር አለ:: ይኸውም ዣን ቫልዣ እስር
ቤት ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ በአካል ጥንካሬና ጉልበት እጅግ የላቀ እንደነበረ ነው:: ከባድ ስሪ በመስራት፤ ጠንካራ ሽቦ በመጠምዘዝ ክብደት ያለውን ነገር በማንሳት የአራት ሰዎች ጉልበት አይስተካከለውም አንድ ጊዜ የቤት ጥገና ሥራ እየተካሄደ ሳለ ተንጠልጣይ ግምብን ደግፎ ይዞ የነበረው ብረት ሾልኮ ግንቡ ሊፈርስ ሲል በአጋጣሚ እዚያ
የነበረው ዣን ቫልዣ ሰዎች እስኪደርሰለት ድረስ ብቻውን ግንቡን ደግፎ እንዳቆመ ይነገራል፡፡

ቅልጥፍውና የሰውነቱ መታዘዝ ጉልበቱን የሚያስንቅ ነበር::
የወንጀለኞች የዘወትር ሕልም የማምለጥ እቅድ ማውጣት ሲሆን ይህም አንዳንድ ጊዜ ጉልበት ከችሎታ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ በአእዋፍና በዝንቦች ዘወትር እንደቀኑ የሚኖሩት እስረኞች እንደ እነርሱ መብረር ይፈልጋሉ::
ዣን ቫልዣ የዚህ ዓይነት ቅናት ስላደረበት የማይሞክረው ነገር አልነበረም::ከማዕዘንና ከቋጥኝ ላይ እየዳሁ መውጣት፣ በጀርባ መንሸራተት፤ ከረጅም ከፍታ መዝለልና የመሳሰሉትን መፈጸም ለዣን ቫልዣ የእለት ተእለት
ተግባር ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እርሱ የሚሠራቸው ነገሮች ታምራዊ እንጂ ማንም ሰው የሚሠራው አይመስልም ነበር፡፡ አንዳንድ ቀን እንዴት እንደወጣ ሳይታወቅ ከፎቅ ቤት ጣራ ላይ ወጥቶ ይገኛል፡፡

ብዙ አይናገርም፡፡ ሁልጊዜም እንደተኮሳተረ ነው፡፡ ጥርሱን አሳይቶ አያውቅም፡፡ የእስረኞች የጭንቀት ድምዕ ስሜቱን ይነካው እንደሆነ እንጂ ሌላ ነገር ስሜት አይሰጠውም:: ለተመለከተውና ላጤነው ዘወትር ሳያቋርጥ
በአስፈሪ የአሳብ ባህር የተዋጠ ለመሆኑ ከፊቱ ላይ ይነበባል፡፡

ብቅ ጥልቅ በሚልና ባልተሟላ ሕይወት ታፍኖ በተያዘ እውቀት
አማካይነት በጭላንጭል ለማየት እንደሚሞከር ነፍስ አድን አስፈሪ የሆነ ግዙፍ አካል እንደተጫነው ይሰማዋል፡፡ ከዚያ ይቅርታቢስና አስፈሪ ከሆነው፤ ከተጫነው ነገር ለማምለጥ ኣንገቱን ቀና አድርጎ ዓይኖቹን ለመግለጥ
ሲሞክር ሥልጣኔ ብለን የምንጠራው ነገር ያስገኛቸው ነገሮች ፤ ሕጎች! የሰዎች አስከፊ ገጽታዎችና ሥራቸው ተከማችተውና ከቁጣና ከፍርሃት
ጋር ተደባልቀው በአሳብ ያያቸዋል:: ቀስ በቀስ ግን ከእርሱ እየራቁ ወደላይ አሻቅበው ወጥተው ከፊቱ ሲሰወሩ ይመለከታል፡፡

ዣን ቫልዣ በዚህ ዓይነት ተጨባጭ ዓለም አስፈሪ በሆነ መናፍስት ተሞልቶ ፧ አስፈሪው የመናፍስት ዓለም ደግሞ በእውን ነገር ተተክቶ በቃላት ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ በአካሉ ውስጥ እየተቀረጸበት የኖረ ሰው ነው::

አንዳንድ ጊዜ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ድንገት ሥራውን አቁሞ ማሰብ ይጀምራል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ፤ አሁን ግን የዋዠቀው የማመዛዘን ችሎታው ጨርሶ እየጠፋ በእርሱ ላይ የደረሰው ሁሉ ከሥርዓት ውጪ!
በአካባቢው የሚያየው ነገር ሁሉ ያልሆነና የማይሆን ይመስለዋል፡፡ «ይህ ሁሉ ሕልም ነው» እያለ እርስ በራሱ ይነጋገራል:: ከእርሱ ጥቂት ርቆ የቆመውን የእስር ቤት ኃላፊን አተኩሮ ይመለከታል፡፡ ኃላፊው አንድ ዓይነት መንፈስ አንጂ ሰው ሆኖ አይታየውም:: ሆኖም ይህ መንፈስ በድንገት በዱላ ይጠልዘዋል፡፡

ለእርሱ የምናየው ዓለም እውንነት ኣጠራጣሪ ነው:: እንዲያውም
ከአነካቴው ለዣን ቫልዣ «ፀሐይ የለችም ፤ ክረምትና በጋ አይፈራረቁም፤ጠፈር የሚባል ነገር የለም» ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም፡፡ ለእርሱ የአካሉ መጀመሪያና መጨረሻ የሰው ልጆች ያወጡት ሕግና የሰውን ዘር
በአጠቃላይ መጥላት ሲሆን የዚህም ውጤት ማን፣ ምን ሳይባል በሕይወት ያለን ማንኛውንም ፍጡር የማጥፋት ምኞት ነው:: የዚህ ዓይነቱ ጥላቻ
በተወሰነ ወቅት በመለኮት ኃይል ካልተገታ በስተቀር አደገኛ ነው:: ስለዚህ ዣን ቫልዣን «እጅግ አደገኛ ሰው» ብሎ መናገሩ ስህተት አልነበረም፡፡

ከዓመት ዓመት ይህ ሰው ቀስ በቀስ እያለ በይበልጥ በአደገኛ ሁኔታ እየደነደነና እየጨከነ ሄደ፡፡ ይህም ደንዳና ፍጡር የደረቀ ዓይን ነበረው::

ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እስር ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ኣንድ ቀን እንኳን እንባ አልወጣውም::

💫ይቀጥላል 💫
👍271
#ቆጠራ_ላይ_ስለሆንን_መግባት
#ክልክል_ነው_ኮሚቴው !!


#በአሌክስ_አብርሃም


“ይሄ የተከበረና የታፈረ ቤተሰብ ተዋርዷል ! ተቃልሏል ! አገር ከመቃጠሉ በፊት አሁኑኑ ይሄን ጉድ አጣርታችሁ ንገሩኝ” አለ እባቴ እኔንና እህቶቼን ሰብስቦ፡፡ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀለው
ብስጭት አቤት ሲያስፈራ፡፡ አባቴ እንዲህ ሲሆን እይቼው አላውቅም፡፡ ጉዳዩን ከሰማን በኋላ ወዲያው ኮሚቴ ተቋቋመ…፡፡

የኮሚቴው አባላት፣
አብርሃም (ቅፅል ስም የለውም)… ትልቅ ወንድም፣ የቤተሰቡ ብቸኛ ወንድ ልጅና የኮሚቴው ሰብሳቢ፡፡
ኖአሚን (ቹቹ)የቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ ለእረፍት ከአሜሪካ የመጣች፣ የኮሚቴው ጸሐፊ::
ሮዛ (ቢጢቃ)…የአብርሃም ታናሽ እህት የሁለተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ፣ ገንዘብ ያዥ፡፡
መቅደስ(ባርቾ) .…የአክስት ልጅ፣ ለአባቴ ጥሪ ለዚሁ ጉዳይ ከናዝሬት የመጣች…“ሙድ ያዥ እና አባል፡፡

ኮሚቴው በቀጥታ ተጠሪነቱ ለአባቴ ሲሆን፣ የስራ ዘመኑም ይህ ጉዳይ እስኪጣራ ብቻ ይሆናል።

አገር ሊያቃጥል የተፎከረበት ጉዳይ
አባቴ እሁድን የሚያሳልፈው በማንበብና በመፃፍ ነው፡፡ ሁልጊዜ የሚያነበው፣ የደጃዝማች ወንዱ በቀለ የጦር ውሎ የሚል መጽሐፍ ሲሆን የሚፅፈው ደግሞ ማመልከቻ !! ለቀበሌ ለክፍለ ከተማ…ለዕድር…ለጡረታ ሚንስቴር…
አንድ ቀን ታድያ ማመልከቻ ፃፈና ልክ
ፊርማው ላይ ሲደርስ እስክሪብቶው አቋረጠ፡፡
አብራሀም እቲ እስኪሪብቶ እምጣ” አለኝ እየተጣደፈ፡፡
አረ አልያዝኩም አባባ
ኤድያ የተማረ ሰው እንዴት እስኪሪብቶ ከኪሱ ይጠፋል፤ ጠመንጃ የሌለው ወታደር ማለት ነው ብሎ ከተማረረ በኋላ ህፃኗን እህቴን
(ራሴን አሞኝ ስለነበር የከባባ ንዝንዝ አልተመቸኝም፡፡)
ቢጡ እስኪሪብቶ እምጭልኝ አላት::
እሺ ብላ አሻንጉሊቷን ለእኔ አሳቅፋኝ ሮጠች(ፈጣን የኬጂ ተማሪ ነች)፡፡
እሰይ የኔ አንበሳ፡ ካንተ ትሻላለች“ አለ ወደኔ እያየ፡፡
ቆይታ ቆይታ ተመለሰችና፣ “አባባ ቀይ እስክሪብቶ ነው"
የሆነው ይሁን… አላት ስስቅ ወደኔ በብስጭት እያየ፡፡
ቆይታ ቆይታ መጣች፡ “ይሄው…" ያመጣችው እርሳስ ነበር፡፡
አይ…ይሄ ምን ያደርግልኛል? እስከሪብቶ ነው ያልኩሽ” አለ አሁን እሱም ሳቁ መጥቶ ነበር፡፡

ከተሳሳተብህ ታጠፋዋለህ ብዬ ነዋ ! ላጲስ አለው ይኸው::”

"ሂጂ ሀና መኝታ ቤት ፈልጊና አምጪ.አይ ቢጣዬ ፊርማ በላጲስ ቢጠፋ የብድር ሰነድ ላይ የፈረምነውን ስንት ጉድ ፊርማ ባጠፋነውና አገር እፎይ ባለች፡፡”

ቢጡ ወደ ሀና መኝታ ቤት ሮጠች (ሀና የ2ኛ ክፍል ተማሪ እህቴ ነች፡፡ ጨዋ፣ ጎበዝ ተማሪ…)
አቤት አባባ ሲወዳት ሀና ትሙት" ካለ አበቃ !!
ቢጡ የሀናን ቦርሳ ተሸክማ መጣች፡፡
ኤልከፈትም አለኝ አባባ፡፡"
አባባ ቀስ ብሎ ቦርሳውን ከፈተና እስከሪብቶውን ፍለጋ ጀመረ፡፡ ድንገት ትንሽ ፓኬት ነገር እጁ ላይ ዱብ አለች፡፡ ወደ ዓይኑ ጠጋ አድርጎ አያት፡፡ ራቅ ቀረብ…እንደገና ራቅ…
አሃ አብርሃም ! አጠራሩ ከመጥበቁ የተነሳ ስሜ የሚሰበር እስከሚመስለኝ፡፡

“አቤት አባባ"
ሂድ መነፅሬን አምጣልኝ…ቶሎ በል"
እ አልኩ ግራ ገብቶኝ፡፡
መነፅሬን አምጣ እኮ ነው የምለው… ጩኸቱ እስበረገገኝ፡፡

አባባ መነፅርህን እኮ አድርገኸዋል አልኩ፡፡ እጁን ወደ ዓይኑ ልኮ መነፅሩ ዓይኑ ላይ መኖሩን አረጋገጠና፣
“አንቺ ወደ ውስጥ ግቢ…" አላት ቢጡን በቁጣ
“እሺ” ብላ ሮጠች፡፡
“ይሄ ምንድን ነው?”
እኔም ደነገጥኩ፣ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ፖስት ፒል፣ አባባ አውቆታል፡፡
እኔንጃ ምንድን ነው ?”
“ምን ትጠይቃኛለህ እንብበዋ"
አየት እድጌ፣ “መድኃኒት ነው…ያው ራሷን አሟት ምናምን ሊሆን ይችላል፡፡

“ዝም በል፡፡ እንካ ራሴን አመመኝ ስትል አልነበረም፣ እንካ ዋጠው የራስ ምታት ከሆነ፡፡ እህቶችህን ጥራ አለ በጩኸት፡፡ ሁሉም ተሰባሰቡ፡፡ ሀና የለችም ነበር፣ ላይብረሪ ብላ ሄዳለች

አባባ አጭርና ታሪካዊ ንግግር አደረገ (የሁላችንም ልብ በሐዘን ተነከቶ ነበር፡፡) ይሄን ሁሉ ሴት ሲያሳድግ የዚህ ዓይነት ውርደት ደርሶበት እንደማያውቅ፡፡ በተለይ ይሄን ጉዳዩ ልዩ የሚያደርገው፣ መድኃኒቱ ትልቅ ተስፋ በሚጥልባትና በሚኮራባት ልጁ ሀና ቦርሳ ውስጥ በመገኘቱ
መሆኑን በተጎዳ ድምፅ ከገለፀ በኋላ፣
'በጥብቅ የሀና መኝታ ቤት እንዲበረበር ትዕዛዝ ሰጠን፡፡

አብርሃም እህቶችህ ባሉበት ይሄን ጉዳይ አንተ ራስህ እየመራህ መርምር፤ ባይልልህ ነው እንጂ ቤተሰብ መሪ መሆኛህ ነበር…ወይ ውርደት !” ብሎ ጠረጴዛውን ደቃው፣ እንደ ፍርድ ቤት
መዶሻ የዕለቱ ስብሰባ መዝጊያ ተደርጎ ተወሰደ፡፡

የምርመራ ቡድኑ ከላይ በጠቀስኩት ኮሚቴ በማዋቀር (አባቴ ደውሎ የጠራት የአክስታችን ልጅ በማካተት) ወደ ሀና መኝታ ቤት ዘመተ፡፡ እናቴ የኮሚቴው አባል ልትሆን ብትጠይቅም
የእናት አንጀት በማዘንም ይሁን በሌላ ምክንያት ሊያዳላና የኮሚቴውን ስራ ተዓማኒነት ሊያሳጣው ይችላል በማለት ሳትካተት ቀረች፡፡

ኮሚቴው ገና ከጅምሩ ፀብ ጀምሮ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እኔ እንደቀልድ የወረወርኳት ጥያቄ ነበረች፣ “ምናልባት ሀና ቦርሳ ውስጥ ከእናንተ አንድኛችሁ አስቀምጣችሁባት ይሆን? ሁሉተም
ተንጫጩ፡፡ እንደምንም አረጋግቻቸው (የሕዝብና የመንግስት ኃላፊነት ስላለብን) ስራችንን ቀጠልን፡፡

የሀኒ መኝታ ቤት ሲፈተሽ መሳቢያዋ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ የወንድ ፎቶዎች ማግኘት አስደነገጠን፡፡ ጨዋዋ ሀኒ እየዞረች ፎቶ ማንሳት ጀምራ ይሆን ? ሲቀጥል የባሰው መጣ፡፡ " ወላ በጡት ማስያዣ፡ ወላ ከወንዶች ጋር:: ብቻዋን ሀይቅ ዳርቻ ላይ፡፡ ቆይ አዲስ አበባ ሀይቅ
አለ እንዴ ታዲያ የት ሄዳ ተነስታ ነው : በጀልባ ታይታኒከኛ ፎቶ)፡፡ ከቤት ወጥታ የማታውቅ ልጅ በምን ከንፍ በራ ሀይቅ ዳር ተገኘች ? ኧረ ጉድ ጭፈራ ቤት ማታ በሚኒስከርት (ሀናን በሚኒስከርት እየናት ከሚሉኝ፣ አንተን በሚኒስከርት አየንህ ቢሉኝ አምን ነበር ዓይኔ ይሆን መነፀሬ አምጣ አለ አባባ፡፡ እውነቱን ነው፤ ኧረ መነፅሬን አምጡ አለ ያልነው ሲጠፋ ልይበት ሆኖ አረፈው። እኛ ሳሎን ተቀምጠን፣ ዘራፍ የነሉሲ፣ የእነ ማንትስ
ልጆች የመይሳው ደም አባይን ገደብነው ስንል መኝታ ቤታችን፣ የታሪክ የወግና ባህል ግድባችን ፈርሶ አገር ተጥለቅልቋል
ጎበዝ መነፅራችንን ስጡን፡፡ 11፡30 ቤቷ የምትከተት ልጅ ጭፈራ ቤት።

የሀና ላፕቶፕ ተከፈተ (ብልግና ተከፈተ ቢባል ይሻላል፡፡) የወሲብ ፊልም ከአፍ እስከገደፉ፣ በቃ አባባን ካሁኑ መሰናበት አለብን ደም ግፊቱ… ታላቅ ታሪካዊ አደራ የተጣለብኝ ሰው ባልሆን ኖሮ ባለቀስኩ ነበር ግን ስራዬን ቀጠልኩ፤ የወንዶቹ ፎቶ እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ ለሪፖርት እዲመች ይቆጠር ብለን መቁጠር ጀመርን፡፡ መኝታ ቤቱ በር ላይ፣ “ቆጠራ ላይ ስለሆንን መግባት ክልክል ነው ኮሚቴው !! የሚል ጽሑፍ ለጠፍን፡፡ ከፎቶዎቹ ኋላ ስማቸው ተፅፎል 43 ዘሩ.…43 ሚኪ 44 ፒተር ፈረንጅ ነው (የአክስቴ ልጅ ምራቋን ስትውጥ ጉሮሮዋ
ሲንገራገጭ ሰማሁት፡፡ ፈረንጁን የዋጠችው ነው የምትመስለው፡፡)
45 ሸምሰዲን (የሰፈራችን ባለሱቅ ) ትልቅ ደንበኛዬ ነው ትላለች ሀኒ፡፡ አይ ሀኒ አዚህ ሚስኪን ቤተስብ ላይ ቅኔ ስትዘርፍበት ነው የኖረችው፡፡ ግዴለም ! 46 ሀውቹባን (ቻይናዊ)፡፡ እቺ ልጅ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ጠርታ ነው እንዴ?

« ዊ መስት ኮል 911 ኢሚዲየትሊ” አለች ለዕረፍት ከአሜሪካ የመጣችው ትልቋ እህታችን ፊቷ በድንጋጤ አመድ መስሎ፣ እንባዋ በዓይኗ ሞልቶ፡፡ …ኮሚቴው በሳቅ ፍርስስስስስ፡፡ ከሳቂታ ኮሚቴ ጋር አብሬ በመስራቴ ኩራት ተሰማኝ፡፡
👍312