አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የመግቢያ_ፈተና


#በአሌክስ_አብርሃም

አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈትኜ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ ውጤት በማምጣቴ መንደሩ በደስታ አበደ
የበለጠ ወሬውን ያሞቀው ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መመደቤ ነበር፡፡

እሳቷ ኸዋና ከተማው ከባህሩ ዘላ ጥርቅም አለች ተባለልኝ፡፡ ወሬው ሁሉ ስለኔ ሆነ፡፡

“…የእቶ ዘለቀ ልጅ ይንበርስቲ በጠሰ"

“የትኛው"

“ይሄ ባለፈው በሬ ወግቶት የነበረው

“…ኧረረረረረረረ ሰው ሁሉ ሞኛሞኝ መስሎ፤ ለካስ እንዲህ ጥይት ነው ጃል

“ቀለም ዘልቆት ነው ፈዘዝ ያለው አይ…ጎበዝ ነው ከድሮውም አረ፡፡ወሬው ከመንደር መንደር
ተሰራጨ፣ በዛን ሰሞን የመንደሩ ሕፃናት አጥንተን እንሙት አሉ፡፡ ለወትሮው በቅስቀሳ ትምህት
ቤት የሚሄደው ውሪ ሁሉ፣ ሰዓቱ ሳይደርስ ደብተሩን አንጠልጥሉ ቱርርር እያለ ይበር ጀመር፡፡

ሁሉ ነገር ተሰናድቶ ድል ያለ የመሸኛ ግብዣ ተደረገና ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ተሰባስቦ ጨዋታው እንደደራ፣ ከከተማ የመጣው አጎቴ ስለሁኔታው ያወጋኝ ጀመረ!

“መላኩ"

“አባት አጎቴ"

"ከሆነስ ሆነና የትኛው ስፍራ ነው የደለደሉህ ስድስት ኪሎ የማባለው ነው የካቲት 12 ሆስፒታል አጠገብ?

አይደለም እጎቴ አምስት ኪሎ የሚባለው ነው በቃ እዛ የአክስቴ ቤት ጎን ከዪኒበርስቲው ጋር ኩታ ገጠም ናቸው እንዲህ አጥር ነው የሚለያቸው አለች ከመንደራችን
ብቸኛዋ አዲሳባን ሁለት ጊዜ ሂዳባታለች የምትባለው አረጋሽ በእርግጥም ወደ አምስት ወር አዲስ አበባ ቆይታ ተመልሳለች አጎቴ ቀጠለ አምስት ኪሎ የት ነው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይቀርባል መላኩ የሚባለው እውነት ነው።

"ኧረ አጎቴ አይደለም"

“ተዉት በቃ አራት ኪሎ ነው” አለች አረጋሽ፡ ቀጠል አድርጋም፡ እዛው ዝቅ ብሎ እኮ ነው! ከዚህ እንደ አቶ አስራት ቤት ቢሆን ነው፡ አጎቴ ጉግሳ ቤቱ እዛው ስር ነው"
"መላኩ፣ ለመሆኑ አራት ኪሎ በመሆኑ ከፍቶኸል?" አለ እጎቱ ፊቴን እያየ ፡ ፡

እናቴ ፊቴ ላይ ያለውን ቅሬታ አንብባ እንዲህ አለች፡

"አይዞህ የኔ አንበሳ፡ እግርህ አዲሳባን ይርገጥ እንጂ ግዴለም ከአራት ጀምረህ አምስትም፡
ስድስትም ሰባትም ኪሎ ትገባለህ፡፡ ስንቅ ነው; እኔ እናትህ እያለሁ አትቸገርም አለች፡፡
"እናትህ እውነቷን ነው! የትም ብትሆን እንዳትሰጋ!” አለ አባቴ ፉከራ በሚመስል ድምፅ፡፡

አጎቴ ቀላል ሰው አይደለም፡ ጊዜው ራቅ ይበል እንጂ አዲሳባ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን
ሰንብቶ መጥቷል፡፡ እናም ባለችው እውቀት ስለ አራት ኪሎ እንዲህ አለ፡ “ኧረረረ ዋናው ጭንቅላቱ ላይ ነህና፣ ቤተ መንግስቱ ውስጥ በለው በቃ አለ ጋቢውን ወደ ትካሻው ከፍ እያደረገ፡፡

ግምታቸው ምርር ስላደረገኝ እንዲህ አልኩ፡ እኔ የተደለደልኩት ኮሜርስ የሚባል ቦታ ነው፡፡

አጉረመረሙ።

"እሱ ደሞ ወዴት ነው? አዲስ አባ ነው…ሲባልም አልሰማሁ” አለ አጎቴ፡፡

እኔም የት እንደሆነ አላውቅም እቴ፡ ብቻ እዛው አዲሳባ ኣንዱ ግድም ነው አልኩ፡፡
በዕርግጥም አራት ኪሎ፡ እምስት ኪሎ፡ ስድስት ኪሎ ካልተባለ ዩኒቨርስቲ ስለማይመስለኝ
ኮሜርስ ባሉት ነገር ከፍቶኝ ነበር፡፡

“ምንድነው የሚያስተምሩት?” አለ አባቴ፡፡

“የንግድ ስራ ይላል ወረቀቱ ላይ" አልኩ፡፡

“መድሃኒዓለም! ንግድ ምን ትምህርት ይላል? ይሄው እኛ ዝም ብለን እያቀላጠፍነው አይደለም!” አለ አባቴ፣ ታዋቂ የእህል ነጋዴ ነው፡፡

“እንዴዴዴዴዴ ባንክ የምትሰራው የአክስቴ ልጅ የተማረችበት ነው፡ ኧረ ጥሩ ተማሪ ቤት ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ሞት ይርሳኝ! ያ በሪሁን፡ የእናቴ የእህት ልጅ፣ ቤቱ እዛው ነው አለች አረጋሽ፡፡

ጋሽ ዘለቀ የመንደራችን አስቂኝ ሽማግሌ፣ “አረጋሽ እንደው ያንች ዘመዶች ሁሉ ዩኒበርስቲ
እጥር ስር ብቻ ነው እንዴ ቤት የሚሰሩት?!” አሉና ሰዉን አሳቁት፡፡

ሁሉም እንደየአቅሙ የሰማውንም ያየውንም ስለእዲስ አበባ ይመከረኝ ጀመረ፡፡

የመጀመሪያው አጎቴ ነው፣

“መላኩ አዲሳባ እንዲህ ቀላል አገር እንዳይመስልህ ባህር ነው
ባህር…በዛ ላይ ሌባው አይጣል፤ ሴት ወንዱ ሞላጫ ነው፡፡ ሱፉን ግጥም አድርጎ መኳንንት
የመሰለው ሰው፣ ጠጋ ብሎ ከኪስህ ገንዘብህን ይከተልብሀል፡፡ ሴቷ ስትውረገረግ ልብህን ትሰልበዋለች፡፡ አንዳች አፍዝ አደንግዝ አላቸው፡፡ ጠንቀቅ ብለህ እንደወታደር ነው መኖር
የኣዲሳባ ሕዝብ ፈዛዛ አይወድም

አጎቴ አዲስ አበባ የሄደው ለሕከምና ነበር፡፡ ታዲያ ከቆየባቸው አርባ አምስት ቀናት
ሰላሳ ዘጠኙን ጥቁር አንበሳ ተኝቶ ነው ያሳለፈው፤ ሁለት ቀን የካቲት 12 ሆስፒታል...
አንድ ቀን ጦር ኃይሎች…ከህመሙ ጋር እየታገለ ስለአዲሳባ ይሄን ሁሉ ማወቁ ግሩም ነው፡፡

ዙሪያሽ ነበረች ቀጣይ መካሪ፣ “ወይ አዲስ አበባ…ሂሂሂሂ…የጉድ አገር እኮ ናት፣ መንገድ
ስትሻገር ነጭ ነጫን እየረገጥክ ነው፣ ሳት ካለህ መኪናው አያፈናፍንም…”

“ይሄ አዲስአባ ሰፊ አገር ነው አልተባለም እንዴ? የምን የማሪያም መንገድ ነው! ነጩን
ጥቁሩን እንዳሻው ይራመድ እንጂ” አለች እናቴ፡፡

ሂሂሂሂሂ ሕግ ነው፤ እንደኛ አገር ያገኙበት መርገጥ የለም እናቴ፣” ብላ አረጋሽ ቀጠለች፣
እና…መላኩ ዋናው ነገር…ዋናው የአዲስአባ ሴቶች አሳሳቾች ናቸው፤ ያንተ ዓይነቱን ሸበላማ
ካዩ ተከትለውህ ነው የሚመጡት፡፡ ኮስተር በል፣ ፊት አትስጣቸው! ኧረ በድንግሏ ሃፍረት የሚባል አያቃቸውም…”

አንድ ቀን የአክስቴ ልጆች ካማሪካ መጡና እራት እንብላ ብለው ሰብስበው ወሰዱን፡፡ ጉድ አየሁ…ጉድ ሴት እና ወንድ፣ ሴትና ወንድ ሁነው ነው የሚቀመጡት፡፡ አንድ ብቻህን ቁሪር ብሎ መቀመጥ ነውር ነው የተባለ ይመስል…፡፡ ሃዲያ አንድ ጊዜ ይጎርሱና መሳሳም፣ ደሞ ይጎርሱና መሳሳም..እማምላክን እህሉን በውሃ ሳይሆ በመሳሳም የሚያወራርዱት ነው እኮ
የሚመስሉት…ሁሁሁሁ” ብላ በሀፍረት ሳቀች፡፡
“ወላዲት አምላከ!ኸምግብ ቤቱ ነው የሚሳሳሙት?
ፈረሰኛው ጊወርጊስ!”

ሁሉም በወሬው ተገርመው ተንጫጩ፡፡

ቀጠለች አረጋሽ፣ “ደሞ ሴቶቹ እንዲቹ እርቃናቸውን ቁራጭ ልብስ ጣል አርገው እንዲቹ
እንደፈጠራቸው ነው የሚመናቀሩት…የቆዳቸው ልስላሴ…መስተዋት ነው የሚመሳስሉት…
አይበርዳቸውም ወይ? እላለሁ እኔማ አለች፡፡ …ገረመኝ!!
እና መላኩ፣ በሌላ ሌላው እንኳን አንተ አትመከርም፣ በሴቶቹ እንዳትፈትን አደራ!" ብላ
ምከሯን ጨረሰች፡፡

እንደጧት አዲሳባ ልሳፈር ሌሊቱን ሲያቃዠኝ አደረ፡፡ እራት እየበላሁ ይመስለኛል፣ የቆዳዋ ጥራት
መስተዋት የመሰለ ሴት እርቃኗን ጎኔ ተቀምጣ አንዴ በጎረስኩ ቁጥር የምትስመኝ ይመስለኛል፤
ልክ እንደማወራረጃ፡፡ ከዚሁ ፈተናው ጀመረኝ፡፡

አለቀ
👍376😁2