#ትንሽ_ወደግራ_ዘምበል...
:
:
#በአሌክስ_አብርሃም
አባቴ ሲራመድ ትንሽ አንከስ ይላል፡፡ ያን ያህል እንኳን አይደለም፡፡ ወታደር ስለነበር ታፋው አካባቢ ጥይት ጨረፍ አድርጋው ነው፡፡ (ለጡረታ ሰበብ ትሆን ዘንድ ከእግዜር የተተኮሰች
ጥይት ይላታል አባቴ ራሱ) !! አንድ አራት እርምጃዎቹ ኖርማል ይሆኑና አምስተኛዋ ላይ
ትንሽ ወደግራ ዘምበል ይላል እንደ እኛ ታሪክ !! የራሳችን ፊደል፣ የራሳችን ቋንቋ፣ አድዋ፣መቅድላ፣ ድርቅ አንከስ ወደ ግራ !! ይሄው ነው !
ታዲያ አባቴን ጥምድ አድርጎ የያዘው የግራ እግሩን በፈንጅ ያጣ ወታደር ጎረቤት አለን ፣ “ለዚች
በየአምስት እርምጃው ለምትከሰት እንከሻው የአካል ጉዳተኛ ተብሎ ጡረታ ይበላል፡፡ ይሄ ለጳግሜ ከመስከረም እኩል ደመወዝ ከመክፈል አይተናነስም አይ እች አገር ! አይ ታሪክ " እያለ ያሸሙረዋል በክራንቹ መሬት እየቆረቆረ…!!
የአባቴን እግር የጨረፈችው ጥይት ለአባቴ ግንባር የተተኮሰች መሆኗን ዘንግቶ፡፡ የተጫረ እግር
ከተቆረጠ እግር እያወዳደረ በጉድለት ቁና የታሪክ ገለባውን ሊሰፍር ይዳዳዋል ፡፡ ጡረታን
የጉዳት ዳረጎት አድርጎ የሚያስብ ከንቱ !! ሰው አንገቱን ተቆርጦ ጡረታ እየተቀበለ መኖር
ቢችል ኖሮ፣ “ለአገራቸው ክብር” አንገታቸውን የተቆረጡቱ “ግራ እግር ምን አላት” ብለው
በተቆረጠው ግራ እግሩ በሳቁበት ነበር ፤ “አንዱ ባንዱ ሲስቅ ጀምሰሯ ጥልቅ” (በጨለማ መሳቅ
የለመደ ህዝብ ስለጀምበር መጥለቅ ምን ገዶት፡፡ ለምን እንጦሮጦስ አትወርድም፡፡ ኮኮቦችን ወላ ጨረቃዋን አስከትላ፡፡)
ቀን ቀን ትሁት፣ የተከበረ፣ የተጣላ የሚያስታርቅ የመንደሩ ዋልታ ነው አባቴ ፡፡ ማታ…. አቤት ቀንና ማታ በአባቴ ባህሪ ሲለኩ ያላቸው ልዩነት፡፡ ጧት የነበረው አባቴ ሌላ ክፍለ ዘመን፣ ማታ የሚከሰተው ደግሞ ሌላ ላይ የተፈጠረ ፤ ሁለት አባት ያለኝ እስኪመስለኝ !! አባቴ
ማታ ማታ ከራሱና ከእነዛ ሁለት ሥዕሎች ጋር ይጣላል ።
ጠጭ ነው:: በየቀኑ ይጠጣል፡፡ ሲጠጣ ቤተሰብ አይረብሽም፡፡ እናቴን አይናገርም፡፡ ቤታችን
ግድግዳ ላይ የተለጠፉት ሁለት ሥዕሎች ጋር ነው ዱላ ቀረሽ ግብ ግብ የሚፈጥረው በቃል !!
አባትህ ስራው ምንድን ነው ?” ብባል፣ “አባቴ ስራው ምን እንደሆነ አላውቅም” ነው መልሴ፡፡
ማሪያምን አላውቅም ! ትምህርት ቤትም እንደዚሁ ብዬ መልሼ ሁሉም ሳቁብኝ፡፡ እኔ ግን ለምን
እንደሳቁ አልገባኝም !! የተማሪዎቹ እሺ ይሁን ምድረ ኩታራ፡፡ ቲቸር ምን አሳቀው ? (ከሳቁ በፊት አንቱ ነበር የምለው፡፡) የቲቸር ሳቅ ስላበሳጨኝ ሆነ ብዬ እንዲህ ስል ሳቁን ተረጎምኩት፣
“አባትህ ቢያጣ ቢያጣ መምህር መሆን ያቅተዋል ?” ማለቱ ነው፡፡” ባይሰማኝም አንጀቴ ራስ፡፡
ይሄን አስቀያሚ መላጣ፣ ኮቱ የተዛነፈ ሂሳብ አስተማሪ ተውትና ስላባቴ ልንገራችሁ..(ሲጀመር
ሂሳብ እስተማሪ ስለአባቴ ሥራ ምን አገባው ደሞ ይስቃል እንዴ!)
ስለአባቴ ሥራ እንዴት ልበላችሁ? አባቴ አሁን ሹፌር ነው ተብሎ አንድ ፌርማታ ሳያልፍ ራፖርት ጸሐፊ ይሆናል፣ እሳቸው የሚጽፉት ማመልከቻ መሬት ጠብ አይልም" ተብሎ ባለጉዳይ
ቤታችን ሲመጣ፣ አባቴ መጋዝና ሜርቴሎውን ይዞ ገና ድሮ አናፂ ሆኗል፡፡ እንግዲህ በክረምት
ጣራችሁ አፍስሶ ወይ የእንጨት አጥራችሁ ወድቆ ትላንት ግንቦት ላይ አናፂ የነበረ አባቴን ሰኔ
አንድ "ጠግንልን” ብላችሁ ብትመጡ አባቴ ከተከመረ የከሰል ጆንያ ኋላ ቆሞ የከሰል ነጋዴ
ሆኖ ታገኙታላችሁ (“ዱቤ ክልክል ነው” ከሚል ፅሁፍ ጋር)..እና አባቴ ሥራው ምንድን ነው ልበል ? ብዙ ሥራ ያለውና ምንም ብር የሌለው አባት !
ብር ከአንዱ ይበደራል፣ የተበደረውን ከሌላ ሰው ተበድሮ ይከፍላል፡፡ ለሌላው ሰው ደግሞ
ከሌላ ሌላ ሰው ተበድሮ ይከፍላል፡፡ ሕፃን እንደነበርኩ ታዲያ ይሄ የአባቴ የመበደርና ብድር የመክፈል ሳይክል መጨረሻ ያለው ስለማይመስለኝ አባቴ እስከዘላለሙ በብድር የሚከሰስ፣ የሚታሰር አይመስለኝም ነበር፡፡ ብድር ይከፍላል፡፡ እጁ ላይ ምንም ብር አይኖረውም፡፡ ብር ለምን ይጠቅማል ቢሉኝ፣ ብድር ለመከፈል፡፡ 'ደመወዝ ለምን ይጠቅማል?' ብባል ብድር
ለመክፈል፤ ታዲያ ለምንድነው ሰዎች 'በባንክ ብድር ቤታቸው ተሸጠ የሚባለው? - እንደኔ
አባት ብልህ ስላልሆኑ ነዋ !!
ሥዕሎቹ፣
1. አባቴ በመጠኑ ሲሰከር (ሞቅ ብቻ ሲለው) ፊት ለፊቱ ቆሞ “ሳተናው ደህና አመሸህ!” የሚላቸው የአፄ ቴዎድሮስ ሥዕል የሽጉጣቸውን አፈሙዝ አፋቸው ውስጥ አስገብተው መቅደላ ጫፍ ላይ ሬሳና ቁስለኛ ከስራቸው ተለሽልሾ የሚታይበት ሥዕል፣ በቀኝ በኩል ከዕቃ መደርደሪያዋ በላይ ግድግዳው ላይ ተለጥፎ ይገኛል፡፡ (አባቴ ከዚህኛው ስዕል ጋር የመረረ ጥል የለውም፣ አልፎ
አልፎ ካልሆነ፡፡)
2. አባቴ ስካሩ ከመደበኛው ስካር ከፍ ሲልና፣ ቀን ከገጠመው የሕይወት ስንክሳር ጌሾ ጋር
ሲቀየጥ ደግሞ ከማይጋጩት ባላጋራ ጋር ይጋጫል፣ “.የጌታ እየሱስ ከርስቶስ” ምሥል ጋር!!
እየሱስ ቀይ መጎናፀፊያ ለብሶ፣ ረዥም ምርኩዙን በብብቱ ስር ይዞ፣ በር እያንኳኳ.. በግራ
በኩል!! አባቴ ከዚህ ሥዕል ጋር ይጣላል (ድፍረቱ ኢይገርምም ?)
አባቴ ገና በር ሲያንኳኳ እናቴ ስካሩ አንደኛ ደረጃው ይሁን ወይም ሁለተኛው ደረጃ ታውቀዋለች ፣ እንዴት ታውቃለች ? እግዜር ይወቅ !! እነዚህ እናቶች በየድራፍት ቤቱ ስለማይደሰኩሩ እንጂ በየሬዲዮና በየቴሌቪዥኑ ስለማይቀባጥሩ እንጂ ስንት ጉድ ተዓምር አለ በውስጣቸው:: ስንት
ጉድ፣ መላ.. :: እንኳን ባላቸው በር ሲያንኳኳ ቀርቶ ዙፋን ላይ ቂብ ሊል ያቆበቆበ ባለተራ ዓይነ ውሀውን አንብበው ክፉ ይሁን ደግ ያውቃሉ ዘመን ምስክር ነው !
ሁለተኛው ዓይነት ስካር ከሆነ እናቴ ተንደርድራ ከክርስቶስ ሥዕል ፊት ትሄዳለች - በፈጣን
አነጋገር፣ “ጌታ ሆይ እባክህ የተናገረውን ሲናገር አትቁጠርበት ይቅር በለው" ብላ የንሰሃ ቀብድ
ታስይዛለች ! (ሙሉውን አባቴ ራሱ ስካሩ ሲበርድለት ያወራርዳል !! ) ከዛ በሩን ትከፍትለታለች!
ፊቱ ወዝቶ አይኑ በአስፈሪ ሁኔታ ጉሽርጥ መስሎ ይገባል:: “ሰላም አመሻችሁ!” የለ ምን የላ!
“የአባትህ ገዳይ እዛ ቤት ተደብቋል፣ በግራ በኩል ከአልጋው በላይ ታገኘዋለህ” ብለው የላኩት ይመስል ዝም ብሎ ይገባና በቀጥታ ወደግራ ታጥፎ ከእልጋው በላይ የተሰቀለው የከርስቶስ ስዕል ፊት ይቆማል ፡፡
ፂሙን እያሻሸ ለረዥም ደቂቃዎች በዝምታ ሥዕሉ ጋር አፍጥጦ ይቆይና ድንገት፣ “አንከፍትም”
ብሎ ይጮሃል፡፡ እናቴ ሽምቅቅ ትላለች፡፡
“ለስንቱ እንከፈት፣ ሲያንኳኩ ስንከፍት ገብተው እኛን ሲያስወጡን፡፡ በጣታቸው ሲያንኳኩ 'ቤት ለእንግዳ' ብለን ስንከፍት በክንዳቸው ሲደቁሱን ከመክፈት ጋር ተጣልተናል ፤ አንከፍትም….”
እናቴ ወደ ጣራው ዓይኗን ልኮ በለሆሳስ ታነበንባለች፡፡ ለከርስቶስ “ቅድም ያልኩህን እንዳትረሳው
አደራ!” የምትል ይመስለኛል፡፡ አባቴ ይንጎማለላል፡፡ ረዥም ነው ቁመቱ፡፡ ብን ተደርጎ የተበጠረ
ጥቁር ከርዳዳ ፀጉሩ ላይ ወደፊት አካባቢ ትንሽ ሽበት ጣል ያደረገበት ፡፡ የጨርቅ ሱሪው የተኩስ መስመር ቀጥ ማለት፣ “ሱሪውን ከለበሰው ጀምሮ ተቀምጦ አያውቅም እንዴ” የሚያስብል በሚገባ የተወለወለ አሮጌ የወታደር ቦት ጫማ ፡፡ ይንጎማለላል ..

👍31❤2