አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆጠራ_ላይ_ስለሆንን_መግባት
#ክልክል_ነው_ኮሚቴው !!


#በአሌክስ_አብርሃም


“ይሄ የተከበረና የታፈረ ቤተሰብ ተዋርዷል ! ተቃልሏል ! አገር ከመቃጠሉ በፊት አሁኑኑ ይሄን ጉድ አጣርታችሁ ንገሩኝ” አለ እባቴ እኔንና እህቶቼን ሰብስቦ፡፡ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀለው
ብስጭት አቤት ሲያስፈራ፡፡ አባቴ እንዲህ ሲሆን እይቼው አላውቅም፡፡ ጉዳዩን ከሰማን በኋላ ወዲያው ኮሚቴ ተቋቋመ…፡፡

የኮሚቴው አባላት፣
አብርሃም (ቅፅል ስም የለውም)… ትልቅ ወንድም፣ የቤተሰቡ ብቸኛ ወንድ ልጅና የኮሚቴው ሰብሳቢ፡፡
ኖአሚን (ቹቹ)የቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ ለእረፍት ከአሜሪካ የመጣች፣ የኮሚቴው ጸሐፊ::
ሮዛ (ቢጢቃ)…የአብርሃም ታናሽ እህት የሁለተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ፣ ገንዘብ ያዥ፡፡
መቅደስ(ባርቾ) .…የአክስት ልጅ፣ ለአባቴ ጥሪ ለዚሁ ጉዳይ ከናዝሬት የመጣች…“ሙድ ያዥ እና አባል፡፡

ኮሚቴው በቀጥታ ተጠሪነቱ ለአባቴ ሲሆን፣ የስራ ዘመኑም ይህ ጉዳይ እስኪጣራ ብቻ ይሆናል።

አገር ሊያቃጥል የተፎከረበት ጉዳይ
አባቴ እሁድን የሚያሳልፈው በማንበብና በመፃፍ ነው፡፡ ሁልጊዜ የሚያነበው፣ የደጃዝማች ወንዱ በቀለ የጦር ውሎ የሚል መጽሐፍ ሲሆን የሚፅፈው ደግሞ ማመልከቻ !! ለቀበሌ ለክፍለ ከተማ…ለዕድር…ለጡረታ ሚንስቴር…
አንድ ቀን ታድያ ማመልከቻ ፃፈና ልክ
ፊርማው ላይ ሲደርስ እስክሪብቶው አቋረጠ፡፡
አብራሀም እቲ እስኪሪብቶ እምጣ” አለኝ እየተጣደፈ፡፡
አረ አልያዝኩም አባባ
ኤድያ የተማረ ሰው እንዴት እስኪሪብቶ ከኪሱ ይጠፋል፤ ጠመንጃ የሌለው ወታደር ማለት ነው ብሎ ከተማረረ በኋላ ህፃኗን እህቴን
(ራሴን አሞኝ ስለነበር የከባባ ንዝንዝ አልተመቸኝም፡፡)
ቢጡ እስኪሪብቶ እምጭልኝ አላት::
እሺ ብላ አሻንጉሊቷን ለእኔ አሳቅፋኝ ሮጠች(ፈጣን የኬጂ ተማሪ ነች)፡፡
እሰይ የኔ አንበሳ፡ ካንተ ትሻላለች“ አለ ወደኔ እያየ፡፡
ቆይታ ቆይታ ተመለሰችና፣ “አባባ ቀይ እስክሪብቶ ነው"
የሆነው ይሁን… አላት ስስቅ ወደኔ በብስጭት እያየ፡፡
ቆይታ ቆይታ መጣች፡ “ይሄው…" ያመጣችው እርሳስ ነበር፡፡
አይ…ይሄ ምን ያደርግልኛል? እስከሪብቶ ነው ያልኩሽ” አለ አሁን እሱም ሳቁ መጥቶ ነበር፡፡

ከተሳሳተብህ ታጠፋዋለህ ብዬ ነዋ ! ላጲስ አለው ይኸው::”

"ሂጂ ሀና መኝታ ቤት ፈልጊና አምጪ.አይ ቢጣዬ ፊርማ በላጲስ ቢጠፋ የብድር ሰነድ ላይ የፈረምነውን ስንት ጉድ ፊርማ ባጠፋነውና አገር እፎይ ባለች፡፡”

ቢጡ ወደ ሀና መኝታ ቤት ሮጠች (ሀና የ2ኛ ክፍል ተማሪ እህቴ ነች፡፡ ጨዋ፣ ጎበዝ ተማሪ…)
አቤት አባባ ሲወዳት ሀና ትሙት" ካለ አበቃ !!
ቢጡ የሀናን ቦርሳ ተሸክማ መጣች፡፡
ኤልከፈትም አለኝ አባባ፡፡"
አባባ ቀስ ብሎ ቦርሳውን ከፈተና እስከሪብቶውን ፍለጋ ጀመረ፡፡ ድንገት ትንሽ ፓኬት ነገር እጁ ላይ ዱብ አለች፡፡ ወደ ዓይኑ ጠጋ አድርጎ አያት፡፡ ራቅ ቀረብ…እንደገና ራቅ…
አሃ አብርሃም ! አጠራሩ ከመጥበቁ የተነሳ ስሜ የሚሰበር እስከሚመስለኝ፡፡

“አቤት አባባ"
ሂድ መነፅሬን አምጣልኝ…ቶሎ በል"
እ አልኩ ግራ ገብቶኝ፡፡
መነፅሬን አምጣ እኮ ነው የምለው… ጩኸቱ እስበረገገኝ፡፡

አባባ መነፅርህን እኮ አድርገኸዋል አልኩ፡፡ እጁን ወደ ዓይኑ ልኮ መነፅሩ ዓይኑ ላይ መኖሩን አረጋገጠና፣
“አንቺ ወደ ውስጥ ግቢ…" አላት ቢጡን በቁጣ
“እሺ” ብላ ሮጠች፡፡
“ይሄ ምንድን ነው?”
እኔም ደነገጥኩ፣ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ፖስት ፒል፣ አባባ አውቆታል፡፡
እኔንጃ ምንድን ነው ?”
“ምን ትጠይቃኛለህ እንብበዋ"
አየት እድጌ፣ “መድኃኒት ነው…ያው ራሷን አሟት ምናምን ሊሆን ይችላል፡፡

“ዝም በል፡፡ እንካ ራሴን አመመኝ ስትል አልነበረም፣ እንካ ዋጠው የራስ ምታት ከሆነ፡፡ እህቶችህን ጥራ አለ በጩኸት፡፡ ሁሉም ተሰባሰቡ፡፡ ሀና የለችም ነበር፣ ላይብረሪ ብላ ሄዳለች

አባባ አጭርና ታሪካዊ ንግግር አደረገ (የሁላችንም ልብ በሐዘን ተነከቶ ነበር፡፡) ይሄን ሁሉ ሴት ሲያሳድግ የዚህ ዓይነት ውርደት ደርሶበት እንደማያውቅ፡፡ በተለይ ይሄን ጉዳዩ ልዩ የሚያደርገው፣ መድኃኒቱ ትልቅ ተስፋ በሚጥልባትና በሚኮራባት ልጁ ሀና ቦርሳ ውስጥ በመገኘቱ
መሆኑን በተጎዳ ድምፅ ከገለፀ በኋላ፣
'በጥብቅ የሀና መኝታ ቤት እንዲበረበር ትዕዛዝ ሰጠን፡፡

አብርሃም እህቶችህ ባሉበት ይሄን ጉዳይ አንተ ራስህ እየመራህ መርምር፤ ባይልልህ ነው እንጂ ቤተሰብ መሪ መሆኛህ ነበር…ወይ ውርደት !” ብሎ ጠረጴዛውን ደቃው፣ እንደ ፍርድ ቤት
መዶሻ የዕለቱ ስብሰባ መዝጊያ ተደርጎ ተወሰደ፡፡

የምርመራ ቡድኑ ከላይ በጠቀስኩት ኮሚቴ በማዋቀር (አባቴ ደውሎ የጠራት የአክስታችን ልጅ በማካተት) ወደ ሀና መኝታ ቤት ዘመተ፡፡ እናቴ የኮሚቴው አባል ልትሆን ብትጠይቅም
የእናት አንጀት በማዘንም ይሁን በሌላ ምክንያት ሊያዳላና የኮሚቴውን ስራ ተዓማኒነት ሊያሳጣው ይችላል በማለት ሳትካተት ቀረች፡፡

ኮሚቴው ገና ከጅምሩ ፀብ ጀምሮ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እኔ እንደቀልድ የወረወርኳት ጥያቄ ነበረች፣ “ምናልባት ሀና ቦርሳ ውስጥ ከእናንተ አንድኛችሁ አስቀምጣችሁባት ይሆን? ሁሉተም
ተንጫጩ፡፡ እንደምንም አረጋግቻቸው (የሕዝብና የመንግስት ኃላፊነት ስላለብን) ስራችንን ቀጠልን፡፡

የሀኒ መኝታ ቤት ሲፈተሽ መሳቢያዋ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ የወንድ ፎቶዎች ማግኘት አስደነገጠን፡፡ ጨዋዋ ሀኒ እየዞረች ፎቶ ማንሳት ጀምራ ይሆን ? ሲቀጥል የባሰው መጣ፡፡ " ወላ በጡት ማስያዣ፡ ወላ ከወንዶች ጋር:: ብቻዋን ሀይቅ ዳርቻ ላይ፡፡ ቆይ አዲስ አበባ ሀይቅ
አለ እንዴ ታዲያ የት ሄዳ ተነስታ ነው : በጀልባ ታይታኒከኛ ፎቶ)፡፡ ከቤት ወጥታ የማታውቅ ልጅ በምን ከንፍ በራ ሀይቅ ዳር ተገኘች ? ኧረ ጉድ ጭፈራ ቤት ማታ በሚኒስከርት (ሀናን በሚኒስከርት እየናት ከሚሉኝ፣ አንተን በሚኒስከርት አየንህ ቢሉኝ አምን ነበር ዓይኔ ይሆን መነፀሬ አምጣ አለ አባባ፡፡ እውነቱን ነው፤ ኧረ መነፅሬን አምጡ አለ ያልነው ሲጠፋ ልይበት ሆኖ አረፈው። እኛ ሳሎን ተቀምጠን፣ ዘራፍ የነሉሲ፣ የእነ ማንትስ
ልጆች የመይሳው ደም አባይን ገደብነው ስንል መኝታ ቤታችን፣ የታሪክ የወግና ባህል ግድባችን ፈርሶ አገር ተጥለቅልቋል
ጎበዝ መነፅራችንን ስጡን፡፡ 11፡30 ቤቷ የምትከተት ልጅ ጭፈራ ቤት።

የሀና ላፕቶፕ ተከፈተ (ብልግና ተከፈተ ቢባል ይሻላል፡፡) የወሲብ ፊልም ከአፍ እስከገደፉ፣ በቃ አባባን ካሁኑ መሰናበት አለብን ደም ግፊቱ… ታላቅ ታሪካዊ አደራ የተጣለብኝ ሰው ባልሆን ኖሮ ባለቀስኩ ነበር ግን ስራዬን ቀጠልኩ፤ የወንዶቹ ፎቶ እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ ለሪፖርት እዲመች ይቆጠር ብለን መቁጠር ጀመርን፡፡ መኝታ ቤቱ በር ላይ፣ “ቆጠራ ላይ ስለሆንን መግባት ክልክል ነው ኮሚቴው !! የሚል ጽሑፍ ለጠፍን፡፡ ከፎቶዎቹ ኋላ ስማቸው ተፅፎል 43 ዘሩ.…43 ሚኪ 44 ፒተር ፈረንጅ ነው (የአክስቴ ልጅ ምራቋን ስትውጥ ጉሮሮዋ
ሲንገራገጭ ሰማሁት፡፡ ፈረንጁን የዋጠችው ነው የምትመስለው፡፡)
45 ሸምሰዲን (የሰፈራችን ባለሱቅ ) ትልቅ ደንበኛዬ ነው ትላለች ሀኒ፡፡ አይ ሀኒ አዚህ ሚስኪን ቤተስብ ላይ ቅኔ ስትዘርፍበት ነው የኖረችው፡፡ ግዴለም ! 46 ሀውቹባን (ቻይናዊ)፡፡ እቺ ልጅ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ጠርታ ነው እንዴ?

« ዊ መስት ኮል 911 ኢሚዲየትሊ” አለች ለዕረፍት ከአሜሪካ የመጣችው ትልቋ እህታችን ፊቷ በድንጋጤ አመድ መስሎ፣ እንባዋ በዓይኗ ሞልቶ፡፡ …ኮሚቴው በሳቅ ፍርስስስስስ፡፡ ከሳቂታ ኮሚቴ ጋር አብሬ በመስራቴ ኩራት ተሰማኝ፡፡
👍312