#ንፋስ_ወዴት_ነህ_ቢሉት_ማርና #ወተት_ወዳለበት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እማማ አረጋሽ ቤት ሩጫ ልናይ ተሰብስበናል፡፡ ልጃቸው ከውጭ አገር ትልቅ ቴሌቪዥን
ስላመጣችላቸው በሳቸው ቴሌቪዥን ማየት የሩጫ ጥም ይቆርጣል፡፡ መቸስ ቴሌቪዥኑን
ግድግዳ በሉት፡፡ የእማማ አረጋሽ ቤት ከሦስት ግድግዳና ከአንድ ቴሌቪዥን ነው የተዋቀረው
ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ባለቤታቸው አቶ ፈንታው ነፍሳቸውን ይማራቸው ዜና ለምን
በየቀበሌው እንደዞሩ ይሄን ዓለም ሳያዩ ሞቱ፤ ሳያልፍላቸው ሞቱ፡፡ “ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን በማያ ጊዜያቸው ሞቱ” ይላል ጎረቤቱ፡፡
ጀመረ ሩጫው ገንዘቤ ዲባባ፣ አበባ አረጋዊ ቴሌቪዥኑን እየሞሉ ደግሞ ራቅ እያሉ…
እኛም ግንዘብ…ገንዘብዬ…ገንዘባችን ሩጭ አሳያቸው…አይዞሽ” እያልን፣ ያው አበባ አረጋዊ ፈትለክ ብላ ወርቁን ወሰደችው፡፡ ያውም የስዊዲን ማልያ ለብሳ በስዊዲን ባንዲራ ተውባ ! ብዙዎቻችን ቀዝቀዝ ስንል እማማ ወለላ “እልልልልልልልልልልልልልል እሰይ እሰይ” አሉ (ጎረቤት ናቸዉ
“እንዴ ለስዊዲን እኮ ነው የሮጠችው ብንላቸው፣
“ይሁና ልጃችን ናት” አሉ፡፡
እማማ አረጋሽ ታዲያ፣ “አይ ወለላዬ አሁንስ እማማ ፅጌን መሰልሽኝ” አሉ፡፡
ስለ እማማ ፅጌ ለመስማት ጆሯችን ቆመ፡፡
“ማናቸው እማማ ፅጌ ?
እማማ አረጋሽ ስላነሷቸው ሴት ታሪክ አወጉን…
በድሮ ጊዜ እኛ ሰፈር እች አሁን ጋሽ እቁባይ ገፋ አድርገው ያጠሯት ቦታ ላይ አንዲት የእማማ
ፅጌ ድንጋይ የምትባል ጥቁር ድንጋይ ነበረች አጠገቧ ደግሞ የላስቲክ ቤት፡፡ አሁንም አጥሩ
ውስጥ ድንጋዩ አለ፡፡ ታሪክን ሲያጥሩት ያው አጥሩ ውስጥም ሁኖ ቢሆን ይጮሃል፡፡
እማማ ፅጌ አንዲት ልጅ ነበረቻቸው፡፡ መቼስ ቁንጅናዋ አይወራም፡፡ መልአክ፣ መልአክ በሏት፡፡
እንዲት ልጃቸው ናት፣ አባቷ አይታወቅም፡፡ እችው ባልቴት እናቷ እዚህች ድንጋይ ላይ ተቀምጠው
ድንችም ቲማቲምም እየቸረቸሩ አሳደጓት፡፡ በኋላ ህመሙም እርጅናውም ተጫናቸው ግማሽ
ችርችራ፣ ግማሽ ልመና በሆነ ሕይወት ይውተረተሩ ጀመር ::
መቼስ ልጅቱ መንገድ ዳር እየኖረች ልዕልት መሰለች፡፡የመንደሩ ሴቶች ጠርሙስ ሙሉ ቅባት ጨርሰው፣ ያማረ ለብሰው፣ ትኩስ በልተው ጠብ ያላለላቸው መልክ እዚህች መንገድ ዳር
ላስቲክ ከልላ በምፅዋት የምትኖር ልጅ ላይ ፈሰሰ፡፡ ፀጉሯ ተዘናፈለ፣ ዳሌዋ ሞላ ወንዱ ሁሉ
ዓይኑ ይቀላውጣት ጀመረ፡፡
አንድ ምሽት እማማ ፅጌ ኡኡ አሉ፡፡ መንደርተኛው ወደ ላስቲኳ ቤታቸው ተሰበሰበ፡፡ ልጅቱ
የለችም ጠፋች፡፡ መንደርተኛው እማማ ፅጌ ጋር በመሆን ሳምንት ሙሉ ፈለገ፡፡ የለችም፡፡ሀ
ቆንጆዋ፣ ባልቴት እናቷን ትታ ምጥ ትግባ ስምጥ እልም ድርግም አለች፡፡ ጎረቤቱ ተስፋ ቆርጦ
ወደ የራሱ ጉዳይ ሲመለስም ሚስኪኗ ባልቴት ግን ከዛች ቀን ጀምሮ ለአስራ አንድ ዓመታት
ታየች በተባለበት ተንከራተቱ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራቸው ከተማ የተረፋቸው መንደር የለም፡፡
በየደረሱበት የዕለት ጉርሳቸውን እየለመኑ ፅንፍ የለሽ በሆነ የእናት ፍቅር ልጃቸውን ፈለጉ፡፡
በአስራ አንደኛው ዓመት ልጃቸው ውጭ አገር ኖራ እንደተመለሰችና አንድ ባለፀጋ ልታገባ ሰርጉ
እየተደገሰ መሆኑን ከሁነኛ ሰው ሰሙ፡፡ “አይ ልጄ ፈልጋ አጥታኝ ነው” አሉና ወደ አዲሳባ አቀኑ፡፡ አዲሳባ እንደገቡ እንድ ጥግ ላይ ከያዟት ፌስታል ሌት ቀን ብለው ያስቀመጧትንና ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ለብሰዋት የማያውቋትን ቀሚስ አውጥተው ለበሱ፡፡ ራሳቸውን አየት አደረጉና፣ “እመቤት መሰልኩ አይደለም እንዴ፣ ልጄንማ አላዋርዳትም አሉና ፈገግ አሉ፡፡
ልጃቸው አለች ወደተባለበት ቤት ሳያርፉ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ቤተ መንግሥት የመሰለው ቤት
በሁለት ዘበኞች ይጠበቃል፡፡ “የልጄ ቤት” አሉ በኩራት ፊት ለፊት ቆመው፤ ከዛም ጠጋ ሲሉ
እግዜር ይስጥሽ አለ አንዱ ዘበኛ፣ እማ ፅጌ ይሄን ቃል ሺ ጊዜ ሰምተውታል የዛሬው ግን
ለየት አለባቸው፡፡
ሳቅ ሳቅ አላቸው፡፡ ይሄ ጥበቃ ከደቂቃዎች በኋላ ጎንበስ ቀና ሲልላቸው ታያቸው፣
“ልጄዋ እኔ እንኳን የመጣሁት ቢጣዬን ብዬ ነው”
“ቢጣ ማናት?”
“ልጄ ናታ እዚህ ቤት እንደምትኖር ነግረውኛል”
“እንደዛ የምትባል ሴት የለችም እዚህ እማማ”
ጠጋ አሉትና፣ “ሙሽራይቱ ማነው ስሟ
“እሜቴ ስማቸው ብሩክታዊት ነው
ግራ ተጋብተው ከግቢው በር እንደቆሙ ቢጣ ከሸበላ ባለቤቷ ጋር ውሃ በመሰለ መኪና ብቅ
አለች፡፡ ራሷ ናት፣ እናትና ልጅ ፊት ለፊት ተፋጠጡ፡፡ እናት ችለው መቆም አልቻሉም ጉልበታቸው ተብረከረከ፣ “ቢጣዬ ያይኔ አበባ " ብለው ወደ መኪናው በእንብርክክ ቀረቡ ልጅ ኮስተር አለች፣ የመኪናውን መስተዋት ዝቅ አደረገች፣ ጥቁር መነፅሯን ወደ ፀጉሯ ከፍ ራሷን መታ አድርጋ ውብ ፀጉሯን ወደ ጎን አለችና፤
“ምንድነው?” አለች ፊቷን አጨፍግጋ፡፡
ቢጣዬ..እናትሽ ስንከራተት ኖሬ ይሄው መጣሁልሽ፡፡ ሄድኩ አይባልም? ሜዳ ላይ ጣል አድርገሽ ማን አላት ብለሽ…"
“ማነህ ወደዛ ውሰዳት! የማንም ወፈፌ እየመጣ…እንሂድ ሃኒ አለች ቢጣ መኪናውን ወደ
ሚያሽከረከረው ሰው ዞር ብላ…፡፡
“ሃሃሃሃሃሃ ሃኒዩ አትበሳጭ አዲሳባ በነዚህ ዓይነት ፈጣጣዎች ነው የተሞላው ነዳጁን ሰጠና
ፈትለክ፡፡ እማማ ፅጌ ተንበርክከው ቀሩ፡፡ ራሳቸውን አይተው “ልጄ እስክትረሳኝ ተጎሳቁያለ
ማለት ነው” አሉ በልጃቸው አልፈረዱም፡፡
እስከሰርጉ ቀን ከግቢው ፊት ለፊት ካለች በረንዳ ላይ ዝናብና ፀሐይ እየተፈራቀባቸው ልት።
መኪና እንደልብስ እየቀያየረች ስትገባና ስትወጣ እየተመለከቱ በልጃቸው ምቾትና ታላቅ ደረጃ
መድረስ የራሳቸውን መከራ ረስተው ቆዩ፡፡ አንድ ቀን እናቴ ብላ እጄን እንደምትዘረጋላቸው
ተስፋ በማድረግ፡፡ (ልጅ ያላየቻቸው እየመሰለች ስታልፍ ቆየች ከአንድ ወር በላይ !!)
የሰርጉ ቀን፣ እናት ያችን ቀሚስ ከፌስታላቸው አወጡና ለበሱ፣ የኖሩባትን በረንዳ ላጠራረጉ
ፌስታላቸው ውስጥ ያስቀመጧትን ትንሽ ብልቃጥ አወጡና በረንዳው ላይ ባለ መስታወት ዓይናቸውን ተኳሉ፡፡
ከሰዓት ሙሽራዋ በነጭ ቀሚስ ተውብ በክፍት መኪና ስትደርስ ጎረቤቱ፡ ሰርገኛው ሲተረማመስ
መሃል መንገድ ላይ ከሰርጉ መኪና ፊት ለፊት እማማ ፅጌ እስከሰታቸውን አወረዱት፡፡
ሁሉ እብድ መስለውት ለአፍታ ትኩረቱን ወደ ባልቴቷ አዞረ፡፡ ከጫጫታው ኮሙዚቃው በላይ
የገዘፈ ድምፅ ከባልቴቷ ወጣ፡፡
መጣችም ሄደችመ ደሟ ከደሜ ስጋዋ ከስጋዬ የተጨለፈ ልጅ ቢጣዬ እቻት እንኳን ደስ ያለሽ በሉኝ ሙሽራው ልጄን አደራ" አሉና ፈታኝውን እዙረው ወደ በረንዳቸው ሄዱ ከኋላቸው የእድምተኛው ሳቅና ፈዝ እየተከተላቸው::
ሌሊቱን ሲጨፈር ሲደለቅ ታድሮ ጧት ያደረው ሰርገኛ ሲወጣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት
የአስክሬን ማንሻ መኪና ከሰርጉ ቤት ፊት ለፊት ካለ ሱቅ በረንዳ ላይ የአንዲት ባልቴት ሬሳ
ሲያነሱ ታየ፡፡ ሬሳው ከተነሳበት በረንዳ ንፋስ እየገፋ ወደ ሰርግ ቤቱ በር የወሰደው አንድ
ጥቁርና ነጭ ፎቶ ዘበኛው እግር ስር ደረሰ፡፡ እናትና ልጅ የተነሱት ፎቶ ነበር፡፡
ወይ የሰው መመሳሰል.ልጅቱ እትዬን አትመስልም…” አለ ዘበኛው ለጓደኛው፣
እድያ እሱን ወዲያ ጥላህ ይሄን ያዝ!” ብሎ ከሰርጉ የተረፈ ቢራ ሰጠው:: ዘበኛው ፎቶውን
ጥሎ ወደ ቢራው ዞረ፡፡ ነፋሱ ጥቁርና ነጩን ፎቶ ወዳልታውቀ ቦታ እየገፋ ወሰደው::
እኛ ያሳደግናት በማር በወተት" የሰርግ ዘፈን ከግቢው ይሰማል፡፡
✨አለቀ✨

👍39❤6👎1😁1