አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከ.........እስከ

የሐበሻ ሕይወት==የኢትዬጵያ ኑሮ
በንፍሮ ያበቃል == በገንፎ ጀምሮ

🔘ሙሉቀን🔘
#ሕይወት

ሕይወት ከተማ ናት
ብዙ መንገድ ያላት
ሞት ገብያ ናት
አንድ ቀን የምንገናኝባት።
#የድሃ_ልደት

መሬት ላይ እየተኙ እግር ስር እየወደቁ
ኑሮ በሚባል ከስክስ ጫማ ተረግጠው እየደቀቁ፣
“አለን ይመስገን ይላሉ
በሰው ጥላ ስር እየዋሉ፡፡

ምቹ ማረፊያ ያጣን ተንሳፋፊ ብናኞች
ፍርፋሪ ፍለጋ የሰው ፊት ምናይ ትንኞች ፧
ይኼንም ኑሮ አልነውና
አንድ ቀን እንኳ ሳይደላን አንድ ቀን እንኳ ሳንዝናና፣
ስጋ ውስጥ ነብስ ተፈጥሮ
በእስትንፋስ ዕድሜ ተቆጥሮ ፤
ሃምሳ አመት ሞላው ይባላል
ሰው በቁጥር ይደለላል፡፡

ወዲያ የድሃ ልደት፣
ወዲያ የደሃ ኑሮ!
የቁጥር ብቻ ቋጠሮ፡፡

🔘ሙሉቀን🔘
#የታካሚው_ማስታወሻ(ህመም አልባው በሽታ)


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)

1.ቅድመ ታሪክ

ከአንድ ዓመት ስራ መፍታት በኋላ፣ እንደገና ስራ ልጀምር ነው። በማኔጅመንት ሁለተኛ ድግሪና ከአስር ዓመት በላይ የስራ ልምድ አለኝ። ያለ ስራ በቆየሁበት ግዜ፣ ያጠራቀምኩትን ገንዘብ ጨርሼ
ንብረቶቼን ሸጥኩ፡፡ አሁን መኪናዬን ለመሸጥ በማሰብ ላይ ሳለሁ ስራ
አገኘሁ፡፡ ከባድ ግዜ ነበር፡፡ ንብረት ከማጣት በተጨማሪ፣ የስነ ልቦና ጉዳቱ ይሄ ነው ሚባል አይደለም፡፡ በራሴ ያለኝ መተማመን በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሏል፡፡ ከዚህ በፊትም፣ በተመሳሳይ ስራ ለቅቄ እስክፀፀት
ተቸግሬ አውቃለሁ፡፡ ሁለተኛ ብዬ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ቃሌን መጠበቅ አቅቶኝ፣ ይኸው ለአመት ተንከራተትኩ፡፡

የመጨረሻው ድርጅቴ በጣም ጥሩ ክፍያን ይከፍለኝ ነበር፡፡በተጨማሪም፣ ለሙያዬ እድገት የሚረዱኝ የተለያዩ የስልጠና እድሎችን በሃገር ውስጥና በውጪ ሃገራት ያመቻችልኝ ነበር፡፡ በጣም ደስተኛ ሆኜ ነበር፡፡ ብዙ እንደምቆይበት ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ከተወሰነ ግዜ በኋላ ግን፣ሰራተኛው የተከፋፈለና በየቀኑ የሚካሰስ እንደሆነ እየተሰማኝ መጣ፡፡እኔ ደግሞ እንደ አስተዳደር ስራዬ መዳኘት ነው፤ አንዱን በዳይ፣አንዱን ተበዳይ አድርጎ መፍረድ፡፡ እኔ ደግሞ፣ ከመፍረድና ከመቅጣት ይልቅ፣ ችግሩን በማስታረቅ መፍታት የተሻለ መስሎ ተሰማኝ፡፡ እንደዛ ሞከርኩ። አይሳካም፡፡ ጭራሽ ወደኋላ አምስት፣ አስር ዓመት
ተመልሰው፣ “እርሱ/እርሷ፣ ባለፈውም እንዲህ በድሎኝ/ላኝ፣” እያሉ ሌላ
የክስ ቱባ ይተረትራሉ።

ጓደኛ ሆኜ ቀርቤያቸው፣ መሰረታዊ የፀባቸውን መንስኤ ለማወቅ
ሞከርኩ፡፡ ከአሉባልታ የዘለለ፣ ይሄ ነው የሚባል የከፋ ነገር የላቸዉም፡፡ክሶቻቸው ከጥርጣሬና፣ ሳይቀድመኝ ልቅደመው ከማለት የሚመነጩ ናቸው። እኩል ቀርቤ፣ እንደ ድልድይ ላቀራርባቸው ሞከርኩ፡፡ የሚሆን አይደለም፡፡ ያለበቂ ምክንያት፣ ላይታረቁ ተጣልተዋል፡፡ ለተጣላ ሰው ደግሞ፣ መካሰሻ ምክንያት አሽዋ ነው፡፡ መዳኘት ስራዬ ቢሆንም፣
ሰለቸኝ፡፡ ሁሉም ተበደልኩ ባይ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ደስታዬ ተነነ፣ ሳቄና ጨዋታዬም ጠፋ፡፡ ብስጩና ነጭናጫ ሆንኩ፡፡ ወደ ስራዬ መሄድ ይሰለቸኝና ይጨንቀኝ ጀመረ። ስራተኛውና ድርጅቱ አንገሸገሹኝ፡፡ ካሁን በኋላ ስራ በፍፁም አለቅም ብዬ የገባሁትን ቃል መጠበቅ አቃተኝ፡፡ ሌላ ስራ እንኳን ሳላገኝ እንደዘበት መልቀቂያ አስገብቼ ጠፋሁ፡፡ ለአመት ተንከራተትቼ አዲስ ስራ አገኘሁ፡፡ አሁንም፣ እንደገና አይለምደኝም ብዬ
ስራ ልጀምር ነው፡፡

#እንደገና
“..ቋ..ቋ...ቋ...” ከአለቃዬ ቢሮ እንደወጣሁ፣ ኮሪደሩ ላይ፣ የሂል
ጫማ ድምፅ ተቀበለኝ፡፡ ድምፁን ወደሰማሁበት ቀና ብዬ ተመለከትኩ።
ፈዘዝ ያለ ቢጫ ቦዲ፣ በጥቁር ጨርቅ ሱሪ፣ የሚያምር የሰውነት ቅርፅ፣በረጅም ሂል ጫማ የተጫማች ልጅ ወደኔ አቅጣጫ እየመጣች ነው።ከአለቃዬ ቢሮ፣ የኔ ቢሮ ሩቅ ሚባል አይደለም፡፡ የጎረምሳ ነገር ልጅቷን በቅርበት ሳላያት ወደቢሮዬ መግባት አልፈለኩም፡፡ እንድትደርስብኝ እንደ ኤሊ ተጎተትኩ፡፡ አልተሳካም! ቢሮዬ በር ደረስኩ፡፡ ይሄኔ የሚመጣው
ሰው ማልፈልገው ሆኖ እንዳላየ ለመግባት ብጣደፍኮ ኖሮ.....። መጠበቅ
አለብኝ፡፡ ከአለቃዬ የተቀበልኩትን ወረቀት፣ የቢሮዬ በር ላይ ቆሜ
ማንበብ ጀመርኩ፡፡
ሄይ! አዲሱ ስታፋችን?” እጇን ዘረጋችልኝ..

“አዎ! ያቤዝ እባላለሁ፡፡” እጇን ጨብጬ ከላይ እስከታች በዐይኔ እየዳበስኳት፡፡

“ማሂ ቆንጆ እባላለሁ፡፡”

“እመሰክራለሁ! በጣም ቆንጆ ነሽ!፡፡”

ኪ.ኪ...ኪ...፣ አመሰግናለሁ፡፡ እንኳን ደህና መጣህ፡፡
በስርዓት አቀባበል እናደርጋለን፡፡” ብላ፣ የቆምኩበት ትታኝ፣ ወደ አለቃዬ
ቢሮ መሄድ ጀመረች፡፡

“አመሰግናለሁ!” እያልኩ፣ የጀርባ ውበቷን ለማረጋገጥ ካንገቴ ዞሬ በዐይኔ ተከተልኳት፡፡ ትንሽ እንደተራመደች እያየኋት እንደሆነ ለማረጋገጥ ይመስል፣ ድንገት ዞር ስትል ዐይን ለዐይን ተጋጨን፡፡ ወደ ቢሮዬ ተስፈንጥሬ ገባሁ፡፡ ሃሳቤ ግን ተከትሏት ሄዷል፡፡ ውበቷ ሙጫ ነው፣ ተጣብቆ የሚቀር፡፡ ማራኪ ነች፡፡ በዛ ላይ በደንብ ተኳኩላለች።ቢሆንም፣ ሲፈጥራትም ልቅም ያለች ቆንጆ ነች፡፡ ሃም...፣ ጥሩ ጥቅማ ጥቅም ያለው አሪፍ መስሪያ ቤት ነው የገባሁት፡፡ ይሄንን ቢነግሩኝ ኖሮ፣መች ደሞዙን እንደዛ እጨቃጨቃቸው ነበር፡፡ ምን ክፍል ይሆን
ምትሰራው...?”

ቢሮዬን ዝም ብዬ ተመለከትኩት፡፡ የሰለቸው የወንደ ላጤ ቤት መስሎ ተዝረክርኳል፡፡ እዚህ ቢሮ ውስጥ በቀን ስምንት ሰዓት መቆየት በራሱ ያደክማል፡፡ የጠረጴዛና ወንበሮቹ አቀማመጥ በዘፈቀደ ነው።ማስተካከል ጀመርኩ፡፡ ለስራ በሚመቸኝና ቢሮው የተሻለ እይታ
እስኪኖረው መላልሼ አዟዟርኳቸው፡፡ ማልፈልጋቸውን ወረቀቶች አስወገድኩ፤ ያስፈልጋሉ ምላቸውን፣ በየዘርፍ በየዘርፍ አድርጌ ፋይል ውስጥ አስቀመጥኳቸው፡፡ ስሰራ ሃሳቤ እንዲሰረቅ አልፈልግም፡፡ ቢሮ ውስጥ ያሉ ኮተቶችና ምስቅልቅሎች ሃሳብን ያናጥባሉ። በነፃነትና በትኩረት ስራዬን ለመስራት፣ በምችለው መጠን ቢሮዬን ስርዓት ያለውና ነፃ አደረኩት፡፡ ይህ በቀደሙት መስሪያ ቤቶቼም የምከውነው የመጀመሪያ ቀን ተግባሬ ነው፡፡ ጎንበስ ቀና ያልኩበት፣ እቃዎቹን
የጎተትኩበት ድካም ተሰማኝ፡፡ እርጅና ሊመጣ ነው፡፡ ትንፋሽ ለመውሰድ
ወንበር ላይ አረፍ አልኩ፡፡ ሰዓቴን ስመለከት የሻይ ሰዓት ደርሷል።
ሻይ በኋላ የቀረውን አስተካክለዋለሁ ብዬ እያሰብኩ፤

“ጤና ይስጥልኝ!...” ብለው አለቃዬ ወደ ቢሮዬ ገቡ። እጄን ጨብጠው ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ አለቃዬ መልከ መልካም፣ እድሜያቸው ጎልማሳነትን የዘለለ ይመስላሉ፡፡

“እንኳን ደህና መጡ!”

“ደግሞ ከመቼው ቢሮውን እንዲህ አሳመርከው...?፣ ይሄ ቢሮ እንዲህ ያምር ነበር እንዴ...?” በፈገግታ ጥርሳቸውን ፈልቀቅ አድርገው፡፡

“እንዲመቸኝ ትንሽ ነው የነካካሁት፡፡”

“ሌላ ቢሮ አስመስለህ አሳምረከዋል እንጂ፡፡ አይ ወጣት! መቼም ውበት ትወዳላችሁ! በል ና አሁን ቡና ልጋብዝህ፤ በዛውም ስታፎቻችንን ላስተዋውቅህ፤” ብለውኝ ከቢሮዬ ወጡ፡፡

“እሺ!” ብዬ ቢሮዬን ቆልፌ ተከተላኳቸው፡፡

ካፍቴሪያ ስንደርስ፣ ክብ ሰርተው እየተንጫጩ ሻይ ቡና የሚጠጡ ሰዎች ጋር ወስደው ቀላቀሉኝ፡፡ እየጮሁ ያወራሉ፤ እየጮሁ ይሳሳቃሉ፡፡ ይህ የግቢው አውራ ቡድን እንደሆነ ሁኔታቸው ይናገራል፡፡እየተሸቀዳደሙ ያወራሉ፤ ከፍ አድርገው ይስቃሉ፤ ያሽካካሉ፤ ሌላ ሰው
ይሰማናል፣ እንረብሻለን፣ ምን ይሉናል ሚሉት ነገሮች ሚያሳስቧቸው አይመስሉም፡፡

“ጎበዝ አዲሱ አድሚናችንን ትተዋወቁት ዘንድ ይዤው መጥቻለሁ፡፡ ያቤዝ ይባላል፡፡ እናንተ ደግሞ እራሳችሁን አስተዋውቁት፧”ብለው ወንበር ስበው ተቀመጡ፡፡ ጫጫታቸውን አቁመው፣ ፀጥ ብለው ካዳመጡ በኋላ፣ በአንድ ላይ፣ “እንኳን ደህና መጣህ! ዌል ካም!›› ብለው አልጎመጎሙ:: አራት ሴትና ሶስት ወንድ ናቸው፡፡ ሴቶቹ ወጣትና ቆነጃጅት ሲሆኑ፣ ወንዶቹ በእድሜ ከፍ ከፍ ያሉና፣ ሙሉ ሰውነት ያልደረሱ ጎልማሶች ናቸው።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3👏2
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ(ህመም አልባው በሽታ) ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD) 1.ቅድመ ታሪክ ከአንድ ዓመት ስራ መፍታት በኋላ፣ እንደገና ስራ ልጀምር ነው። በማኔጅመንት ሁለተኛ ድግሪና ከአስር ዓመት በላይ የስራ ልምድ አለኝ። ያለ ስራ በቆየሁበት ግዜ፣ ያጠራቀምኩትን ገንዘብ ጨርሼ ንብረቶቼን ሸጥኩ፡፡ አሁን መኪናዬን ለመሸጥ በማሰብ ላይ ሳለሁ ስራ አገኘሁ፡፡ ከባድ ግዜ ነበር፡፡…»
አበባ:
#እውነት_እናውራ_ካልሽ

“በይ” ስልሽ .. “ወዶኝ ነው”
“ተይ” ስልሽ .. “ቀንቶ ነው!”
ባልሽበት አንደበት፥

ዝም ስል .. “ንቆኝ ነው!”
ብትይ ምናለበት ?!

🔘በዮሐንስ🔘
#ሰላቢ

ተበልተናል ስንል==ሰምተው እንደዋዛ
ቡዳ ላለመባል ==የሚተፋው በዛ

🔘ሙሉቀን🔘
#የአፍሪካ_አናብስት

አምላክ! ት......ልቅ ነገር ለአፍሪካ አድሏታል
አንበሳ 'ሚበላ አንበሳ ሰጥቷታል፡፡

አንት የአፍሪካ መንጋ - አንት የአፍሪካ አንበሳ
ነፍጠኛ ቀርቦሃል በል ነፍጥህን አንሳ፡፡

ካደክበት ቀየ ፣ ካደክበት መንደር
ማዕድን ሲወጣ ፣ መሬትህ ሲቆፈር
ምንድን ነው ማፈግፈግ!?፣ ምንድን ነው ማቀርቀር!?

አይዞህ የኛ አንበሳ!- አይዞህ የኛ ጀግና!
ብዕርህን ጥለህ ነፍጥህን አንሳና፣
እጫካህ ግባና፣
ጨፍጭፍ ወንድምህን፤
ጨፍጭፍ እህትህን፤
ጨፍጭፍ አባትህን፤
ጨፍጭፍ እናትህን፤
ጨፍጭፍ!
ጨፍጭፍ!
ጨፍጭፍ!......
ጨፍጭፋቸው ሁሉን!
ኖረው ካላኮሩን
ዛፍ ይብቀልባቸው አፈር ይሁኑ አሁን፡፡
ተነስ ያዝ ቦንብህን
ይብሱን ጎትታት ጎታታ አገርህን፡፡

ወዲያ የምን ልማት?
የምን ኢንዱስትሪ? ፣ የምን የአገር እድገት?
የጓሮህ ማዕድን
ተቆፍሮ ወጥቶ አገር ከሚያድግበት
አንተ ሽጠውና መሳሪያ ግዛበት፤
መሳሪያ ግዛና ወገን ግደልበት፤
ወገን ግደልና ለስልጣን ተሯሯጥ፤
ያልለፉበት ዳቦ ድሮም ቢሆን አይጣፍጥ፡፡

አንት የአፍሪካ ጀግና አንት የአፍሪካ አንበሳ
ነፍጠኛ ቀርቦሃል -በል ነፍጥህን አንሳ፡፡
ለወንበር ሲሮጡ ለወንበር ተነሳ
ለስልጣን ከቸኮልክ ለሰው ነብስ አትሳሳ፡፡

አየህ አሜሪካን!?
አየህ እነ አውሮጳን!?
ከንቱ ሲጃጃሉ፤
‹ስልጣን በህዝብ እንጂ-
በነፍጥ አናገኝም!›
ብለው ሲማማሉ፡፡

አየህ እነ ህንድን!?
አየህ እነ ቻይናን!?
አየህ ያገር ፈሪ!?
ነፍጣቸውን ጥለው ሲያስፋፉ እንዱስትሪ፡፡

እንትፍ!
ወንድ አሰዳቢዎች ልፍስፍስ እንደ እበት
እነዚህን ነበር
በአንድ ቦምብ ጨፍልቆ ከአለም ማሰናበት፡፡
ቢሆንም እርሳቸው ምንም አይሰሩልህ
ፈንጅ መትረየስ ግን ተቀበል ሲሰጡህ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)


ከሁሉም ወንዶች በእድሜ ወጣት እንደሆንኩ ተስማኝ፡፡ እየዞርኩ :
እየጨበጥኩ መተዋወቅ ጀመረኩ...::

“ኤፍሬም፣ እንኳን ደህና መጣህ!”

“ማሂ ቆንጆ፣ ቅድም ተዋውቀናል፡፡”

“ሳሚ፣ እንኳን ደህና መጣህ!”

“ቤቲ፣ እንኳን ደህና መጣህ!”

“ግርማ፣ እንኳን ደህና መጣህ!”

ፌቨን፣ እንኳን ደህና መጣህ...?”

“ሜሪ፣ እንኳን ደህና መጣህ...?”

ሁሉም በፈግታና አክብሮት በተሞላ ሁኔታ ሰላምታ ሰጥተው ተዋወቁኝ፡፡ ሳምሶን ከጎኑ እንድቀመጥ ወንበር ስቦ ጋበዘኝ፡፡ አስተናጋጇ :ስትመጣ፣ እንደኔ ጠቆር ያለ ማኪያቶ ብዬ አዘዝኩ፡ ሴቶቹ ዞር ብለው
የፊት ቀለሜን ተመለከቱ፡፡ እኔም እንደዛ ብዬ ያዘዝኩት ይሄን ፈልጌ ነበር፡፡ ወደ ጫጫታቸው ተመለሱ፡፡ እኩል እየጮሁ ያወራሉ። ማንን ማዳመጥ እንዳለብኝ ግራ እስኪገባኝ፣ ይሽቀዳደማሉ፤ ይበሻሸቃሉ፣ በጣም ይስቃሉ፤ ፊታቸው ላይ የሚነበበው ደስታና እርካታ ያስቀናል። ማሂ ቆንጆ በጣም ታወራለች። ትስቃለች፡፡ በየመሃሉ በዐይኗ ተጫወት
ትለኛለች፡፡ አለቃዬ እየተሳሳቁ ትንሽ ከተጫወቱ በኋላ፣ “በሉ አስለምዱት!” ብለው ተነስተው ወደ ቢሮ ሄዱ። አሪፍ መስሪያ ቤት እንደገባሁ ሁለት ማስረጃዎች አገኘሁ፤ ደስ የሚል አለቃና ፍቅርና እርካታ የተሞሉ ሰራተኞች፡፡ አለቃማ እንደዚህ ነው፤ ለሰራተኞቹ ያለው
ቀረቤታና አክብሮት ሚያስቀና ነው፡፡ በውስጤ 'ዋ ው! ፀዴ መስሪያ ቤት
ነው የገባሁት፤' አልኩኝ፡፡ ከቀድሞው መስሪያ ቤቴ ጋር አነፃፅሬ ውስጤ
በደስታ ሞቀ። እዚህ ፍቅራቸው የሚያስቀና፣ በመስሪያ ቤታቸው ደስተኛ
የሆኑ፣ በመልክ ተመርጠው የተቀጠሩ የሚመስሉ፣ የውብ ሴቶች ጥርቅም፡፡ ያወራሉ፤ ይስቃሉ፣ በየመሃሉ “ተጫወት!” ይሉኛል፡፡ ቀስ ብዬ የሴቶቹን የግራ እጆቻቸውን ተመለከትኩ፡፡ ጣቶቻቸው ላይ ቀለበት የለም፡፡ 'ያብ ከእነዚህ ውስጥ ሚስት ካላገኘህ፣ መቼም አታገኝም፡፡' ብዬ
ወደ ውስጤ አንሾካሾኩ፡፡

ከሻይ በኋላ ወደ ቢሮ ስመለስ፣ ግቢውን በደንብ ተመለከትኩት፡፡ ወደ ፋብሪካው፣ ወደ እስቶር፣ ወደ ዋናው ቢሮ የሚወስዱትን መንገዶች በሚገባ ዲዛይን ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ በባለሙያ የተያዘ ሚመስለው አረንጓዴ ቦታ በፈኩ አበቦች ደምቋል፡፡ እኮርነር ላይ በግማሽ ጎጆ ቅርፅ የተሰራው ነፋሻማ የሰራተኛ ክበብ፣ መሀል ላይ ለግቢው ሞገስ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራው፣ ነጨ ባለ አንድ ፎቅ የአስተዳደር ህንፃ የመዝናኛ
ቦታ ይመስላል፡፡ ቢሮዬ እንደተመለስኩ፣ የቀረኝን እንደምፈልገው አስተካክዬ ጨረስኩ፡፡ የተሰጠኝን ኮምፒውተር ከፍቼ፣ ስለመስሪያ ቤቱ የተሻለ ምስል ይስጡኛል ያልኳቸውን መረጃዎች ለማግኝት ፋይሎች እየከፈትኩ በማንበብ ተጠመድኩ፡፡ ድርጅቱ ትልቅ ራዕይ እንዳለው ተረዳሁ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ የመሆንና በሀገራችን ላሉ .
ተመሳሳይ የጨርቃ ጨርቅ ድርጅቶችም የልህቀት ማዕከል መሆን ራዕዩ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ ለዚህ ደግሞ ታታሪና ውጤታማ የሆኑ ሰራተኞችን ዋንኛ ግብአት ብቻ ሳይሆኑ፣ ምሰሶና ማገር ናቸው ብሎ ይተነትናል። ሰራተኞቹ ለምን እንደዛ ደስተኛ እንደሆኑ አሁን
ተገለፀልኝ፡፡ አስር ሰዓት ተኩል ሲሆን፣ እንደ አዲስ ጎጆ ወጪ፣ ሳይመሽ
አንድ አንድ ያልገዛኋቸውን የቤት እቃዎች ለመግዛት ቀድሜ ወጣሁ፡፡እቃዎቹን ገዛዝቼ፣ እራት በልቼ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ ደስ ሚል ቀን ነበር፡፡ደክሞኝ ስለነበር እንቅልፍ ቶሎ ወሰደኝ፡፡

።።።።።

ስራ ከጀመርኩ ልክ አንድ ወር ሞላኝ፡፡ ስራውና የስራ ከባቢዬ ተስማምቶኛል፡፡ የስራ ፍላጎቴና ተነሳሽነቴ ተመልሶ ከፍ ብሏል፡፡ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዬን በፍጥነት ለማወቅና ለመረዳት
ችያለሁ፡፡ የተለያዩ ፋይሎችን፣ ደብዳቤዎችን አገላብጬ አነበብኩ።
ከሰዎችና ከሰራተኞች ጋር የመተዋወቅና የመቀራረብ ፍላጎቴም ከፍ ብሎ፣ ሰራተኞችን በየክፍሉ እየዞርኩ እየተዋወኩ አናገርኩ፡፡ የስራ ቅልጥፍናዬ ከሰራተኛው ጋር ያለኝ መግባባትና የስራ ተነሳሽነቴ
በአለቃዬም ሆነ በሰራተኛው ከጠበኩት ፍጥነት በላይ ታማኝነትና ከበሬታን አስገኘልኝ፡፡ በየቀኑ ከማከናውናቸው የዕለት ተዕለት ስራዎች በተጨማሪ፣ ድርጅቱ ያስቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት፣ ይጠቅማል ያልኳቸውን ለመስራት እሞክራለሁ፡፡

ሰራተኛውንም የድርጅቱን ራዕይ ተገንዝቦ፣ በዛው መጠን እንዲተጋ አነቃቃለሁ፤ እመክራለሁ፡፡ከስኞ እስከ ቅዳሜ እንሰራለን፡፡ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ስለሆነ፣
ከነሳሚ ጋር ተያይዘን እንወጣለን፤ ምሳ በልተን እየጠጣን መጫወት ልምድ ሆኗል፡፡ አለቃዬ አንዳንዴ አብረውን ወጥተው ይጋብዙናል፡፡ከቆነጃጅቶች አንዷን ለማጥመድ፣ በደፈናው ሁሉም ላይ መረቤን ዘርግቻለሁ፡፡ ወጣትነቴንና ወንደላጤነቴን እንደ የመጫወቻ ካርድ
አድርጌ እየተጠቀምኩበት ነው፡፡ አሁን በስራዬም በህይወቴም ደስተኛ
ሆኛለሁ፡፡ ዛሬ ሰኞ ነው፡፡ ሁሌ ሰኞ እንደምለብሰው፣ ሙሉ ሱፍ በከረባት
ለብሻለሁ፡፡ የመጀመሪያ ወርሃዊ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከእቅድ ጋር
እያነፃፀርኩ እየሰራሁ ነው፡፡

“መግባት ይቻላል...?” ማሂ ቆንጆ ነች፡፡

ሎርድ...!” ሳላስበው ከአፌ አመለጠኝ፡፡ ዛሬ ደግሞ ብሶባታል፡፡ጥቁር ቀሚስ፣ በጥቁር ሂል ጫማ አድርጋለች፡፡ ፀጉሯን ሂውማን ሄር በደንብ ተሰርታለች፡፡ ያልተሸፈኑት ታፋዎቿ ቀይ ፍም መስለው
ተቃቅፈዋል፡፡ እመሃል ግባ ግባ የሚል ስሜት ድንገት ነዘረኝ፡፡

“ምን አልከኝ ያቡ?" አለችኝ፣ ፈገግ ብላ፡፡

“መጠየቁስ ነው ያልኩሽ...”

“ሳይጠየቅማ አይገባም! ሌላ ሰው ቢኖርስ?” ፈገግ አለች፡፡

“ውይ ለካ እንደዛም አለ፡፡ ያለቃ ፀሃፊ መሆንኮ።”ሰምታኝ ይሆን? ተንተባተብኩ፡፡

“ይሄን ደግሞ ማን ነው የሰጠህ?”

“የቱን?” እንዳልገባኝ አብሪያት ዞሬ እያየሁ፡፡

“አበባውን ነዋ፡፡ በናትህ ማናት ያመጣችልህ? ኪ.ኪ.ኪ.”

“እንዴ...! ለምን ማናት አልሽኝ? ምን ማለት ፈልገሽ ነው?”

“ያው ሰሞኑን፣ የግቢውን ሴቶች አየር ስለተቆጣጠርከው፣ አንዷ
አምጥታልህ ይሆናል ብዬ ነዋ! ኪ.ኪ.ኪ...”

“አንቺ ደግሞ ትቀልጂያለሽ፡፡ እራሴ ነኝ ያመጣሁት፡፡ እንዳንቺ ያለች አበባ ምትመስል ፀሀፊ ባይመድቡልኝም፣ ቢሮዬን በአበባ ላሳምር ብዬ ነው፡፡”

“እረ ባክህ..! ኪ.ኪ.ኪ... እኔ ምልህ ያቡ፣ በናትህ ዛሬም ላስቸግርህ?”

“ምን ልታዘዝ? ደግሞ ላንቺ...”

“ማታ ስንወጣ ምሄድበት ነበረኝ፤ ታደርሰኛለህ? እንዲህ ለብሼ በታክሲ መሄድ...” ብላ ዝቅ ብላ ዳሌዋንና ጫማዋን በዐይኗ ጋበዘችኝ፡፡ዕይኖቿን ተከትዬ ቀያይ ታፋዎቿ መሃል ገባሁ፡፡

ድንገት የታፋዎቼ መሃል ሙቀት ሲጨምር፣ እመሃሉ እሳተ ሲለኮስ ተሰማኝ፡፡ ሳላስበው፣

“ግን ዛሬ ትንሽ አመሻለሁ፤” አልኩኝ፡፡

“እስከ ስንት ሰዐት?”

“እስከ አስራ ሁለት፣” ካፈርኩ አይመልሰኝ፡፡

“ችግር የለም እጠብቅሃለው።”

ካላስመሸሁሽ፣ እሺ እሽኝሻለሁ።”

ከማሂላ ጋር ተቀራርበናል፡፡ በፍጥነት ቤተሰብ አድርጋኛለች፡፡በተደጋጋሚ እንድሸኛት ጠይቃኝ፣ አድርሻታለሁ፡፡ ሻይ ቡናም፣ እራትም ጋብዤያታለሁ፡፡ እንድገባ በሯን እንደከፈተችልኝ ገብቶኛል፡፡ እንዳልገባኝ አልፈዋለሁ፡፡ ማታ ሸኝቼያት ስትወርድ በከፊል ከንፈሬን ስማኝ
ትወርዳለች፡፡ ምንም እንዳልተፈጠረ ደና እደሪ ብያት እሄዳለሁ።መጀመሪያ ቀን የደነገጠላት ልቤ ስትቀርበኝ ቀዝቀዝ አለ፡፡ ከእርሷ ይልቅ ወደ ሜሪ እንዳደላ ይሰማኛል፡፡ ከሜሪ ጋር ብዙ የመገናኘት እድል የለኝም፡፡ በአካል አንዴ ብቻ ነው አግኝቼ ሻይ ቡና ያልኳት፡፡ በስልክ
ግን ብዙ እናወራለን፡፡ ፍላጎት እንዳላት፣ ቢጫ መብራት አሳይታኛለች፡፡ ውስጤ ለሜሪ ስላደላ
እርሷን ለመጠበቅ፣ የማሂን የተከፈተ በር እንዳላየ፣ እንዳልገባው፣ አልፈዋለሁ፡፡ ዛሬ ግን በጣም ልዩ ሆናለች፡፡ ስሜቴን አላወሰችው። እንኳን ተከፍቶ፣ አንኳኩቶም መግባትን
ያስመኛል፡፡ ቀኑ አልመሽ አለኝ፡፡ ተሰምቶኝ የማያውቅ የቅንዝረኝነት ስሜት ቀኑን
ሙሉ ሲላወስብኝ ዋለ፡፡ ሊበርድልኝ ልቀዘቅዝ አልቻልኩም፡፡

እንደምንም ከስሜቴ ጋር ታግዬ ሃሳቤን አሰባሰብኩና መስራት ጀመርኩ፣ ኮሪደሩ ላይ ጫጫታ ተሰማኝ፡፡ ጆሮዬን ጣል አድርጌ አዳመጥኩ፡፡ የኤፍሬም ድምፅ ነው፡፡ ጫጫታው ሲበዛ ተነስቼ ወጣሁ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👏1
Forwarded from 📱SAMSUNG Mobile Store (SMS) (DERAMING)
የእርዳታ ጥሪ

በእግዚአብሄር በአላህ ሼር አድርጉት ‼️😭

• እናቷ እያለቀሰችየነገረችን 😭

• በጎላ ሠፈር ዮሴፍ ሞተር ቤት ፊትለፊት መንደር የምትኖር እፁብ አየለ ትባላለች የ15 ዓመት ወጣት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነች በጭንቅላት ቲቢ እና በጭንቅላት እጢ መሠቃየት ከጀመረች 6 ወሯ ነው ቅ/ጳውሎስ ሆስፒታል ከተኛች 3 ወሯ አትሰማም አትናገርም ! የእናትን ነገር ታቁታላቹ ቀን ሌሊት እያለቀሰች ነው !

ወላጅ እናቷ እዛው እየዋለች እያደረች የምታስታምም ስትሆን አሁን ግን መድሀኒት መግዣ መንቀሳቀሻ ቀለብ ቀሪ ቤተሠብ ማስተዳደር አልቻልኩም ልጄን የተሻለ ሕክምና የተሻለ መድሀኒት እንድታገኝ በሀሳብም በገንዘብም እርዳታችሁ በፈጣሪ ስም አይለየኝ ትላለች ወላጅ እናቷ እያለቀሠች

094 021 5213 ንብረት በሬቻ / እናቷ
1000030804398 ንብረት በሬቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD) ከሁሉም ወንዶች በእድሜ ወጣት እንደሆንኩ ተስማኝ፡፡ እየዞርኩ : እየጨበጥኩ መተዋወቅ ጀመረኩ...:: “ኤፍሬም፣ እንኳን ደህና መጣህ!” “ማሂ ቆንጆ፣ ቅድም ተዋውቀናል፡፡” “ሳሚ፣ እንኳን ደህና መጣህ!” “ቤቲ፣ እንኳን ደህና መጣህ!” “ግርማ፣ እንኳን ደህና መጣህ!” ፌቨን፣ እንኳን ደህና መጣህ...?” “ሜሪ፣…»
#ቁጭት

መውደድን አርሰን ቆፍረን.. ፍቅርን ነበር የዘራነው
ትውውቅን ተክለን ኮትኩተን..ደስታን ነበር ያሳደግነው
የጥርጣሬ ነቀዝ በልቶት...ገና ሳይበስል ቆረጥነው::

ለካ መለየት እንዲህ...ሰውን በቁሙ ይበላል?
ለካ 'ሚወዱት ሲርቅ...ዓለም በሙሉ ያስጠላል?
ለካንስ ትርፉ ፀፀት ነው...ብቼኝነትም ያደክማል!?

አጥንቴ ቀረልሽ ፍቅሬ..ወጣሁልሽ ከሰው ተራ
ብቻየን ማውራት ጀመርኩኝ..አበደ ተብሎ ተወራ፡፡
ግዴለም ስጋ ቢስ ልሁን...እብደቴን ሰው ይወቅብኝ
አንቺ ካለሽ ነው ምኖረው -
ብቻ አንቺን ክፉ አይይብኝ
ብቻ አንቺን ክፉ አይንካብኝ፡፡

አንቺ ካለሽ ነው ምኖረው...እላለሁኝ ደሞ አላፍርም
በቁሙ ከሚነገላጀጅ
ሐዘን ደስታውን ከረሳ...የተቀበረ አይሻልም!?
ቢሆንም ሞት አልፈልግም...መንቀዋለሉ ይሻለኛል
ሰማይ ቤት እንዳንቺ ያለ.ፍጥረትስ እንዴት ይገኛል!?

ፍቅራችን ማበብ ሲጀምር....እንዳይከስም ያልደከመ
የፈስስን ውሐ ላያፍስ...የሰማይ ላሙን እያለመ
አለ ስላሙ ሲናጋ..ልቤ ትዝታን እያከመ::

ትዝ ይልሻል መቼም ፍቅሬ.. ፍቅራችን ምን እንደነበር?
ተዝቆ ማያልቅ የሚመስል
ዕልፍ አዕላፍ ደስታ..ከፊታችን ሲደረደር
ተስገብግበን ስንቋደስ
አንቺ በስሜ ትምይ ነበር
እኔ በስምሽ እምል ነበር፡፡

የፍቅር መልአክ ኮርኩሮሽ..ሰማይ እያየሽ ስትስቂ
የመውደድ ብርሐን ተገልጦ.. አይኔን እያየሽ ስትቦርቂ፣
ይመስለኝ ነበር ፅድቅነት
የገባሁ ከምድር ገነት፡፡
ታዲያ አሁን ያ ህልም መሳይ..የህይወት ብርሐን ደብዝዞ
ያልበሰለው የፍቅር እሸት...እንዳይበላ ጎምዝዞ
ብቻየን አስቀረኝ እኔን.. ትዝታሽን ብቻ አስይዞ፡፡

እኔ ምለው የኔ ስስት፣
የኔ ፅልመት፣
የኔ ብርሐን፤
እንዲያ በደስታ እንዳልፈካን
በሳቅ እንዳላውካካን፣
ካንቺ ጋር አብሮ የራቀኝ.. አለኝ የምለው ዘመዴ
ከንፈሬ የማይገለጥ...ሳቅ እምቢ ያለኝ ከሆዴ
የሳቅም ጡር አለው እንዴ!?

ግዴለም ሳቅ ይቅርብኝ...ሳቄ በለቅሶ ይተካ
መኖርሽን በማሰብ ብቻ...ልቤ እያነባ ይፍካ፡፡

በእጅ የያዙት ወርቅ እንዲሉ...ችላ ያልነው እንደዋዛ
ጠብታዋ ባህር ሆና
ያማረን ጎጆ ስታፈርስ...የሞቀውን አቀዝቅዛ፣

የአብሮነት ኑሮ ምቾቱ...የትካዜ ጎርበጥባጣው
የብቼኝነት ህመሙ ሲለያዩ ነው የሚሰማው፡፡

ስጋና አጥንቴ ተጣብቀው...ደስታ ርቆብኝ ቢያዩኝ
ህመምህን ንገረን' ብለው...ጓደኞቼ እንኳን ጠየቁኝ፡፡
ራሴን
ሆዴን
እግሬን
ልቤን.......
አልልም ጉዳታቸው አይሰማኝም
ምንድን ነው ሚያምህ?” አትበሉኝ... እኔኮ ስሜት የለኝም
የሆድ ቁርጠት...ራስ ምታት...ብሎ ነገር አይገባኝም፡፡

አንድ በሽታ ብቻ ያለኝ
አንድ ሐኪም ብቻ የሚያድነኝ
እኔ የሷ በሽተኛ...እኔ የሷ ታካሚ ነኝ፡፡

እናማ የኔ ሐኪም...የኔ ህመም የኔ ፈዋሽ
በእንባየ የታጠበውን...ነጭ ጋዎንሽን ለብሰሽ
እንደ ድሮው ተፍለቅላቂ..ይመርብሽ ልይሽ ደምቀሽ፡፡

እኔ ግን የኔ ሩቅ
ካንቺ ከተለየሁ...ከተራራቅሁ ወዲህ
ሆኛለሁ ቀልበ ቢስ...ሆኛለሁ ልብ ውልቅ
ሲያጫውቱኝ የማለቅስ...ሲሰድቡኝ የምስቅ፡፡

ሆኛለሁ ብቸኛ... ሆኛለሁ ልብ አድርቅ
ሲርቁኝ የማልቀርብ...ሲጠጉኝ የምርቅ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

እንደምንም ከስሜቴ ጋር ታግዬ ሃሳቤን አሰባሰብኩና መስራት ጀመርኩ፣ ኮሪደሩ ላይ ጫጫታ ተሰማኝ፡፡ ጆሮዬን ጣል አድርጌ አዳመጥኩ፡፡ የኤፍሬም ድምፅ ነው፡፡ ጫጫታው ሲበዛ ተነስቼ ወጣሁ፡፡

“አንቺ እኔን ሌባ እያልሽኝ ነው? የእንትን ልጅ! እገልሻለሁ እገልሻለሁ! እኔ ወንድ አይደለሁም!”

“ልቀቀኝ! ልቀቀኝ! እደፋታሁ! ልታሰራ! ልታሰር...! ልቀቀኝ ባክህ!” ሳሚ ኤፍሬምን ከእነርሱ ቢሮ እጆቹና ወገቡን እንደማቀፍ ይዞ እየገፋ ያስወጣዋል። ሁሉም በቢሮው በር ብቅ ብቅ ብሎ ይመለከታል።ሳሚ ኤፍሬምን ከህንፃው አረጋግቶት፣ አስወጥቶ፣ እየሳቀ ተመለሰ፡፡

“ምንድ ነው? ከማን ጋር ነው?”

“ሆ ...! ከቤቲ ጋር ነዋ፡፡ ባልተባለው ነገር እኮ ነው ሚጮኸው።ሰሞኑን ደግሞ ወፈፌነቱ ተነስቶበታል፡፡” አለኝ ወደ ቢሮው እየተመለሰ፡፡ቢሮዬ ገባሁ፡፡ ሳሚ ከተናገረው “ወፈፌነቱ ተነስቶበታል፤” ያለው አረፍተ ነገር ውስጤ ቀረ፡፡ ኤፍሬም ከእሩቅ ሲያዩት የተረጋጋ ሰው ይመስላል፡፡
ቀረብ ሲሉት ግን በጣም ብስጩና በቀላሉ ወደ ፀብ ሚገባ ባህሪ አለው።
ይህን እንደኔ ሌላም ሰው ተገንዝቦታል ማለት ነው? ለኔ ግን ጭንቅላቱ
ከባህሪው ይበልጥብኛል፡፡ እንደባህሪው ተለማምጬ አሰራዋለሁ፡፡ ይህን
ፀባዩን ማረቅ ቢቻል ጥሩ ደረጃ ሚደርስ ልጅ ነው፡፡ እስከ አስራ አንድ ሰአት እንደነገሩ እየሰራሁ ቆየሁና ለማሂ ደወልኩላት፡፡

“ማሂላ አንወጣም?”

“እንዴ! አስራ ሁለት ሰዓት አላልክም ነበር?”

“ጨረስኩኛ፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ናፈቅሺኝ...”

“እሺ መጣሁ፤ ጠብቀኝ! አስር ደቂቃ ብቻ!” ቢሮዬን ዘግቼ እርሷን መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ አልቆየችም፡፡ ከቢሮ እየወጣን፣

“የት ነው ግን ወይን ምጋብዝሽ?”

“እንዴ... እምሄድበት አለኝ ብዬሃለው እኮ!”

“እሱማ ብለሺኛል፡፡ እኔ ግን እንዲህ አምሮብሽ ሳልጋብዝሽ ዝም ብዬ አልሸኝሽም፡፡”

“እንዴ... ማልቀርበት ቀጠሮኮ አለኝ፡፡”

“ማን ቅሪ አለሽ? ትንሽ ቆይተሽ ትሄጂያለሽ፡፡ የት ልጋብዝሽ?

ኤግልስ?”

“ደረቅ ነህ እሺ፡፡ ግን ትንሽ ነው ምንቆየው።”

“ችግር የለውም፡፡”

ዛሬ ግን ምን ሆነህ ነው እንዲህ በጣም የተሟዘዝከው?”

ፍቅር ይዞኝ!”

“ምን...? አንተን...? ኪ.ኪ.ኪ...” ቆማ ሳቋን ለቀቀችው:: .

“ምነው? እሺ መኪና ውስጥ ግቢና ትስቂያለሽ፡፡ ከዚ ግቢ ቶሉ እንውጣ፡፡” ገብታ እንደተቀመጠች፣

የመኪናህ ሽታ ደስ ሲል! ደግሞ ሁሌም ንፁህ ነች፡፡ ጎበዝ ነህ ቢሮ አያያዝህም፣ እንደ ወንዶች አይደለህም፡፡” መኪናዋን እንደሚገዝ ሰው ዞራ እያየች፡፡

“ቆይ ግን ምን ለማለት ነው? ወንድ ልጅ ንፁህ ነገር አይወድለትም?”

“አልወጣኝም! ግን የሳሚን መኪና አታያትም? የቆሻሻ ቅርጫት አስመስሏት... ኪ.ኪ...ኪ...”

“እሺ ቆይ፣ እኔ አላምርም እንዴ? ሁሌም ቢሮህ፣ መኪና ምናምን ምትዪኝ፡፡ ለነገሩ አንችን የመሰለች፣ ግማሽ መላዕክ፣ ግማሽ ሰው፣ የሆነች ቆንጅዬ ጭኜ ከሄድኩኝ፣ ባላምርም አምራለሁ።”

ኪ.ኪ.ኪ... ኧረ መሞጣሞጥ...፣ ዝምተኛ አልነበርክ እንዴ...? ሳሚ አጋባብህ ማለት ነው...?”

“ምን ያጋባብኛል.…? ስራ ቦታ ነው ብዬ ዝም አልኩ እነጂ፣ በውስጤ ከገባሽ ቆየሽ፡፡”

“ምን ማለት ነው?”

“እንግዲ ዛሬ አፈነዳዋለሁ፡፡ ካለመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል፡፡ በደንብ ተመችተሽኛል፤ ወድጄሻለሁ...”

“ምን...?!”

“አዎ! እስካሁንም ፈርቼሽ ነው!”

“እንዴ አንተ ግን የ'ውነት ሳትዋሽ ሚስት ወይም ፍቅረኛ የለችህም?”

“አዎ! እግዚአብሄር ይመስገን የለኝም።”

“ኪ.ኪ.ኪ... አንተ..? ጭራሽ “እግዚአብሄር ይመስገን የለኝም፡፡'?››

“እውነቴን ነዋ...!፡፡ ቆይ ኖሮኝ ቢሆን፣ አሁን አንቺን የመሰለች ልዕልት ምን አደርግ ነበር? እንኳን አልኖረኝ! አዎ እግዚአብሄር ይመስገን!”

“...ኪ...ኪ...፣ኧረ የዛሬ ምላስ...?”

“ምነው? ባለፈው በጌታ ምን ሆነህ ነው እንዲህ ዝም ምትለው እንዳላልሽኝ፣ ዛሬ ደግሞ፣ በጌታ ስም ይዤሃለው ዝም በልልኝ ልትዪኝ ነው እንዴ?”

| “..ኪ..ኪ...ኪ ኧረ አልልህም! እዚህ ግቢ እንኳን ዝም ተብሎ፣ ተቃጥለንም አልቻልንም፡፡ ግን እንዴት አንተን የመሰለ ልጅ እስካሁን ቢያንስ ፍቅረኛ የለውም?”

“ውይ እንደዛ ከሆነማ፣ እንቺን የመሰለች ልዕልት አግብተሻል ማለት ነው፡፡”

ኪ.ኪ.ኪ...፣ ፍሬቻ አብራ እንጂ፣ በዚህ ጋር ወደ ቀኝ ነንኮ ጠፋብህ እንዴ?”

መኪና አቁመን፣ አንደኛ ፎቅ ላይ ሸሸግ ያለቦታ መርጠን ተቀመጥን፡፡ እራት በልተን ወይን እየጠጣን የሞቀ ጨዋታ ያዝን። ምትሄድበት አልነበረም ወይም እረስታዋለች፡፡ እኔም እንዳላስታወስ ሰው
በጨዋታ ላይ ጨዋታ እያመጣሁባት ዝም አልኳት። ዛሬ እንድትሄድብኝ አልፈለኩም፡፡ እየመሸ ሲመጣ የቤቱ ብርሃን መደብዘዝ ጀመረ። ቀን
እንደዛ ምራቄን ስውጥ የዋልኩበት ታፋዎቿን በሳቆቼ እያሳበብኩ
እዳብሳቸው ጀመር፡፡ መጠጡ ሞቅ እያለኝ ሲመጣ፣ ከመዳበስ አልፌ
እጄን መሃል ለመሃል ወሸኩት፡፡ ምንም እንዳልተፈጠረ ትጫወታለች፣ትስቃለች፡፡ ታፋዎቿ ያቃጥላሉ፡፡ ውስጤ በስሜት ነደደ፡፡

ሂሳብ ከፍዬ ወደ ቤት ወጣን፡፡ መኪናዬ ውስጥ እንደገባን፣

“ዛሬ ካንቺ መለየት አልፈልግም!” አልኳት፡፡

“ኪ.ኪ.ኪ...፣ እና ምን ልታደርግ ነው?”

“ወይ እቤትሽ አብሬሽ ሄዳለሁ ወይም አብረሽኝ እቤቴ ትሄጂያለሽ፡፡ ዛሬ ካንቺ ተለይቼ ማደር አልችልም፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ. ቆይ ምንድነው አላማህ? አከራዬ ቤቴ ጎረምሳ አመጣሽብኝ ብለው በጥዋት ከቤት እንዲያባርሩኝ ነው?”

“እኔ ቤት እናድራለታን እንጂ፣ እንድትባረሪብኝማ አልፈልግም፡፡” ወደ እኔ ቤቴ መንዳት ጀመርኩ፣

“አንተ ደግሞ፣ ዝም ተብሎ በድንገት ወጥቶ ማደር አለ እንዴ?” አንገራገረች፡፡ መኪናውን ድንገት መንገድ ዳር አቁሜ፣ ፊቷን ላለማየት መሪው ላይ ተጎንብሼ፣ መለመን ጀመርኩ፤

“ንግስትዬ ፕሊስ፣ እንደዚህ ሆኜ አላውቅም! በጣም ከባድ ስሜት
እየተሰማኝ ነው፡፡ ፕሊስ?!” ብያት ማላውቀውን እያልኩ ለመንኳት፡፡

“እሺ፣ ነገ ስራ ምን ለብሼ ገባለሁ? ይሄን ለብሼ?
ምን ይሉኛል? ውጪ እንዳደርኩ ያስታውቃልኮ፣ አላደርገውም፡፡”


“ንግስትዬ ለሱ ችግር የለውም፤ ከፈለግሽ አሁኑኑ ሌላ ልብስ
ገዝተን እንግባ፡፡”

“ያምሃል እንዴ አንተ? በዚህ ሰዐት የምን ክፍት ሱቅ አለ? ሰዐቱን አይተኸዋል?”
“እሺ በቃ፣ እኔ ጥዋት በፈለግሽው ሰዐት እቤት አደርስሽና ቀይረሽ ስራ እንገባለን፡፡

እስከዛሬ ፈርቼሽ፣ ስሜቴን አፍኜው ስለቆየሁ ነው? ፕሊስ ውቢት ተረጂኝ፡፡” እትት በረደኝ ብዬ ዘፈንኩላት፡፡ ፍቅርሽ
ሆዴ ገብቶ ያንዘፈዝፈኛል አልኳት፡፡ በመጨረሻም ተስማማች፣ እኔ ጋር
አደረች፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍41🤔1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)

በመጨረሻም ተስማማች፣ እኔ ጋር
አደረች፡፡ በተከፈተልኝ በር ወስኜ መግባት እንዳልከበደኝ፣ አለባበሷና የወይኑ ስሜት ተደማምሮ፣ በድንገት ሰተት ብዬ ገባሁ፡፡ የመጀመሪያ ቀን አይቻት ስደነግጥ እንዲህ በቀላሉ ማገኛት፣ እኔ ላይ እንዲህ ፍላጎት አሳይታ እሺ ምትላኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ በጥዋት ወደ ቤት ሳደርሳት እንደዚህ ያለ ነገር ውስጥ፣ ስራ ቦታዬ ላለመግባት ወስኜ እንደነበር፣
ነገር ግን፣ የእርሷ ውበት ከምቆጣጠረው በላይ እንደሆነብኝና የሆነው ድንገት እንደሆነ ነገርኳት፡፡ ስራችን ላይ ተፅዕኖ እንዳይኖር፣ ሰው እንዳያውቅ ጠየኳት፣፥ ግቢ ውስጥ እንድንጠነቀቅ አሳሰብኳት፡፡ እርሷም እንደዛ እንደማትፈልግና እንደምትጠነቀቅ አረጋገጠችልኝ፡፡
ህይወት ቀና ሆነችልኝ፡፡ በጣም ደስተኛ ሆንኩ፡፡ ስራዎችን በሚገባ አቅዳለሁ! አፈፃፀማቸውን እከታተላለሁ! ለአለቃዬ ሁሉንም በግዜው ሪፖርት አደርጋለሁ፡፡ ሁሉም በስራዬ ደስተኛ ሆኑ፡፡ በተለይ
አለቃዬ ያበረታቱኛል። በውስጤ ብዙ እምቅ አቅም እንዳለ ይነግሩኛል፡፡
ስለ ስራ ልምዳቸው፣ ከፍተኛ ትምህርት ውጪ ሃገር ሄደው ስለመከታተላቸው፣ እኔም እንደዚህ ጠንክሬ ከሰራሁ ትልቅ ደረጃ እንደምደርስ በተገናኘን ቁጥር ይነግሩኛል፡፡ ብዙ ስራተኛ ይፈራቸዋል፡፡
ቁጡና ሃይለኛ ናቸው ይላሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ድርጅቱ የዘመዳቸው ስለሆነ፣ ፈላጭ ቆራጭ ናቸው ይላሉ፡፡ በዚህም፣ ሰራተኛው እንዳሻው ብሎ የቅፅል ስም አውጥቶላቸዋል፡፡ እኔ ግን ነገሮችን በፍጥነት የመረዳት አቅማቸው፣ ልምዳቸውን ለማካፈልና ሰውን ለማሳደግ ያላቸው ቀናነትን ስመለከት እያደር በጣም እንዳደንቃቸው አድርገውኛል፡፡

ዛሬ ቅዳሜ ነው፡፡ ቅዳሜ ብዙ ስራ የለም፡፡ ስራተኞች እንደገቡ ካረጋገጥኩና ምርት በሚጠበቀው እየተመረተ እንደሆነ ካየሁ በኋላ፣ሰዓት እስኪደርስልኝ በየቢሮው እየተንቀሳቀስኩ ምልከታ አደርጋለሁ፡፡
ጨርሼ ቢሮዬ እንደተቀመጥኩ፣ ማሂ እንደተለመደው መጥታ ሸኘኝ አለችኝ፡፡ ለመውጣት እየተዘጋጀን፣ ሳሚ በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ ሳሚ የሂሳብ ክፍል ሃላፊ ነው፡፡ ረጅምና ግዙፍ ተክለ ሰውነት ያለው ሲሆን፣ በባህሪው ሳቂታና ብቻውን መሆን ሚከብደው አይነት ሰው፡፡ ሰላምታ
ከተለዋወጥን በኋላ፣

“ዛሬ ትልቅ ደስታ አለኝ፡፡ ምን እንደሆነ አልናገርም፡፡ ግን የደስደ

ሱን ልጋብዛችሁ ፍቃደኛ ነኝ፡፡ ፈቃደኛ ናችሁ?” ፈገግ ብሎ
ቁልቁል እየተመለከተ ጠየቀን፡፡

ተገኝቶ ነው?፣ ያውም በደስታ ነዋ!” አልኩት፡፡

በሉ እንውጣ!”

“እንዴ ቆይ እኔንም ጠብቁኛ፣ ቢሮ ዘግቼ ልምጣ?” ማሂ መልስ ሳትጠብቅ ወጥታ ሄደች፡፡ ቢሮ ቆልፈን፣ ማሂን ለመጠበቅ ቀስ ብለን እየተራመድን፣ ከነጩ
ህንፃ በር ላይ. ግርማና ቤቲ ቆመው አየናቸው፡፡ ቤቲ ሂሳብ ክፍል ምትሰራ የግቢያችን አንዷ ቆንጆ ነች፡፡ ለሴት ረጅም የሚባል ቁመና ያላት፣ ቀይ፣ ተግባቢና ደፋር ልጅ ናት፡፡ ትውልዷም እድገቷም አዳማ ነው፡፡ አሁንም ከቤተሰቧ ጋር ትኖራለች፡፡ ጥርሷ እንዳብዛኛው ያገሩ ሰው፣ የበዛ ባይሆንም፣ ለፈገግታዋ ውበት የሆነ ትንሽ ብልዝ አለባት፡፡በግሩፓችን፣ ወርቃማው ፈገግታ ጎልደን ስማይል እንላታለን፡፡ ማታ ላይ በስልክ አልፎ አልፎ አወራታለሁ፡፡ መስሪያ ቤት ግን ከስራ ውጪ ብዙም አላዋራትም፡፡ እርሷ ግን፣ ስትፈልግ ቢሮዬ ድረስ ሰተት ብላ
ትመጣለች፡፡ ከሳሚ ጋር አንድ ቢሮ ናቸው፡፡ ክፍላቸው ብዙ ሰራተኛ
ስላለና ስለማይመቸው፣ እኔ ቢሮ ሲያገኛት እወድሻለሁ፣ ካልሳምኩሽ
እያለ ይላፋታል፡፡ ከስራ በኋላ ካልጋበዝኩሽ ብሎ ደጋግሞ ሲጠይቃትም ሰምቻለሁ፡፡ እሺ አትለውም፡፡ እኔ ደግሞ፣ እንከኗ ይሄ ነው ባልልም፣ ስምጥ ብላ አልገባችልኝም፡፡ የሆነ ሚጎረብጥ ነገር እንዳላት ይሰማኛል፡፡ ዛሬ ቤቲ አብራን ከወጣች የሳሚ የደስ ደስ እርሷ ናት፤ ብዬ አሰብኩ፡፡
“እንውጣ፣ ኮተት እንዳይበዛ፡፡” አለ ሳሚ ወደ መኪናዋ እየሄደ የመኪናውን የሪሞት ቁልፍ ተጭኖት፡ የግቢው መኪና ማቆሚያ ውስጥ ተደርድረው ከቆሙት መኪኖች ጥቁሯ ቪታራ፣ ዋይ ዋይ ማለት
ጅመረች፡፡

“አንድ ሰው ካንተ ጋር ይሁና?” አለኝ ሳሚ፣ የከፈተውን የጋቢናውን በር ተደግፎ፡፡

“እሺ!”

ወዲያው ማሂ መጥታ መኪናዬ ውስጥ ገባች፡፡ የተለመደው ስጋ ቤት ስደርስ፣ ሳሚ እያቆመ ነው፡፡ አጠገቡ ሄጄ አቆምኩ፡፡ ስጋ ቤቱ እንደተለመደው ደርቷል፡፡ ባለቤቱ ገና እንዳየን ሚያብለጨልጭ መላጣውን እያሻሽ ወደ ጓሮ ይዞን ገባ፡፡

“ማነህ፣ ና እስቲ! እዚህ ጋር ሁለት ወንበር ጨምርላቸው፡፡”ጮኸ፡፡ ሳሚ ለቤቲ ከጎኑ ወንበር አስተካክሎ፣ ጎንበስ ብሎ እንድትቀመጥ ጋበዛት፡፡ ተቀመጠች፡፡ ግርማ ከቤቲ ጎን ተቀመጠ፡፡ ማሂ ቀጠለች፣ እኔ ክቡን ለመሙላት በማሂና በሳሚ መሃከል ወንበር አስተካክዬ
ተቀመጥኩ፡፡

“ጠፍታችኋል፣ በሰላም ነው?” ባለቤቱ የግሩፑን መሪ ሳሚን ጠየቀው፡፡ ሳሚ ጭር ሲል ማይወድ፣ ነገር ቶሎ ሚረብሽውና ነገርን እንደጦር ሚሸሽ ነው፡፡ ወሬ ሚያቋርጠውን ሰው አይወድም፡፡እንደሚፈልገው ስለምሆንለት፣ ከኔ ጋር መሆን የበለጠ ነፃነት ይሰጠዋል፡፡ ጨዋታ ደምቆ ደስ ካለው ደግሞ፣ ድንገት ተነስቶ ጋባዥ
ነኝ ማለት ይወዳል።

“ምን እንጠፋለን፣ ቅዳሜ መጥተን አልነበር?”
“እሺ ስንት ልዘዝላችሁ? ሁለት
ላድርገው...?”

“አድርገው፡፡”

“የሚጠጣ፣ ያ የተለመደውን?”

“እሺ፡፡ ደግሞ ከረሜላ ላክልን፤ አሪፍ ይሁን ሳሚ የተለመደውን ትዕዛዙን አስከተለ፡፡

ሰውዬው እንደሄደ፣ ጫጫታው
መድረኩን ተረከቡት፡፡ የጀማው ድርሻ የነሱ ሃሳብ ላይ መጨመር፣ አስተያየት መስጠት ወይም መሳቅ ብቻ ነው፡፡ ሚያስቁ ትዝታቸውን፣ ቀልዶችን እያወሩ ይበሻሽቃሉ፤ ያስቁናል፡፡ ከረሜላው ከአዋሽ ተከሽኖ ጋር መጣ፡፡ ጥብሱ ተከተለ፡፡ መጠጡ በፍጥነት ያልቃል፡፡ ከሁለተኛው በኋላ፣ ማን እንደሚያዝ እንኳ አይታወቅም፡፡ ቦታው ሰወር ያለ
በመሆኑ፣ እንደፈለግን ለመንጫጫት ተመችቶናል፡፡ አንዱ ወሬ ሲያልቅ
ሌላ ይቀየራል፡፡ ያኛውስ፣ እንትን” እያሉ ሳሚና ማሂ ይሽቀዳደማሉ።አንዳንዴ አልደማመጥ ሲሉ፣ ማሂ ወደኔ ትዞራለች፡፡ ሳሚ አጠገቡ ላለችው ቤቲ ያወራል። መልሰው በጋራ አንድ ወሬ ይጀምራሉ፡፡ አሁን የቤቲም የግርማም ድምፅ ጎልቶ መሰማት ጀምሯል፡፡

“ሳሚ፣ ሳሚ፣ አንተ...” ማሂ ጮኸች፡፡
“ወይዬ፣ቆንጆ”

ነገ ሶደሬ እንሂድ?”

“ዛሬ ካልደከምን፣ አይተን እንደሙዳችን።”
“እንሂድ በናትህ ... ኪ.ኪ.ኪ...”

“ምንድን ነው? መረጫጨት ነው እንዴ?”

“እንደፈራሁት አይደለም ናፍቆኛል...፡፡ ኪ.ኪ.ኪ...” ማውራት እስኪያቅታት ትስቅ ጀመር፡፡ እሱም አብሯት መንከትከት
ጀመረ።

“እንዴ ንገሩን እና እኛም አብረን እንሳቅ እንጂ..ሃይ!” በመሃል ገባሁ፡፡

“ይኸውልህ ያቡ፣ ባለፈው ከስራ ስንወጣ ሶደሬ ካልሄድን ብሎኝ ሄድን፡፡ ከዛ ካልዋኘሁ ብሎ ተከፍሎ ሚዋኝበት ስንሄድ፣ ስው ሚባል የለም፡፡ እዋኛለሁ ብሎ ገባ፡፡ ከዛ ወዲያው ብቅ ጥልቅ መጫወት አይጀምርም...፡፡ ኪ.ኪ.ኪ..
ደንግጬ እጄን ብሰጠው፣ ብጠራው
ሊሰማኝ ነው...፡፡ ከዛ ኡ...ኡታዬን አስነካሁታ፡፡ ኪ.ኪ.ኪ...ሁላችንም ተከትለናት እንስቃለን፣ እሱም አብሮን ይስቃል...።

“በናትሽ ከዛስ?”

“ከዛማ የሆኑ ሰዎች መጥተው አወጡት፡፡ ኪ.ኪ.ኪ...። አቤት ያስመለሰው ውሃ ብዛቱ... ኪ...ኪ...ኪ... ከመቼው ያን ሁላ ውሃ እንደጠጣ... ኪ.ኪ.ኪ...፣ ደግሞኮ ሲገባ፣ ገንዳው ቆሽሿል ምናምን ሲለኝ፣ ሊጠጣ እንደሚገባ እኔ መች ገባኝ... ኪ.ኪ.ኪ...” ማውራት እሰኪያቅታት ትስቃለች፡፡ ሳሚም ይስቃል፣ እኛም ተከትለን
👍6👏2🔥1
እንስቃለን፡፡ወሬውን ሊያስቀይራት ቢልም፣ አላቆም ስትለው አስተናጋጁን ድንገት፣

“ና እስቲ ሚጠጣ ጨምርልን!” አለው፡፡

“ደግሞኮ፣ በጣም ያሳቀኝ፣ስንመለስ መኪና ውስጥ፣
ኪ......ኪ....ኪ...... እንዴት ነህ?' ስለው፣ “እንደፈራሁት አይደለም አይለኝም... ኪ.ኪ...ኪ...”

ካ..ካ..ካ... ከዛ በላይ፣ ምን ነበር የፈራው...?” እኔም መሃል ገባሁ፡፡

“እንደዛ የተንቀለቀለው፣ ውሃ ጠምቶት ነው ለካ ኪ.ኪ.ኪ. እንደዚህ እየተጫወትን ቤት ሳንቀይር መሸ፡፡ ሰዓቴ ከምሽቱ
ሶስት ሰዓት ይላል፡፡ ሁሉም ሞቅ ያለው ይመስላል፡፡ የሳሚ ግንባሩ ደም ስር ተወጣጥሯል፡፡ ፊቱ ወዝቷል፡፡ እንደዛ አየተሳሳቅን ድንገት ግርማና ቤቲ ይጨቃጨቃሉ። ሳሚ ጨዋታውን አቁሞ ሊያግባባቸው መሃል ገባ፡፡ ነገሩ ጭራሽ ጦዘ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD) በመጨረሻም ተስማማች፣ እኔ ጋር አደረች፡፡ በተከፈተልኝ በር ወስኜ መግባት እንዳልከበደኝ፣ አለባበሷና የወይኑ ስሜት ተደማምሮ፣ በድንገት ሰተት ብዬ ገባሁ፡፡ የመጀመሪያ ቀን አይቻት ስደነግጥ እንዲህ በቀላሉ ማገኛት፣ እኔ ላይ እንዲህ ፍላጎት አሳይታ እሺ ምትላኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ በጥዋት ወደ ቤት ሳደርሳት እንደዚህ ያለ…»
#ሰመመን


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

የፍልስፍናወኑ መምህር ዮናታን እጅጉ የተማሪዎቻቸውን ወረቀት በማረም ላይ ሳሉ አንድ በግዴለሽነት የተሰራ የጥናት ጽሑፍ ገጠማቸው ። ጽሑፉ የአቤል ሙሉዬ መሆኑን ማመን ስላቃታቸው እቢሯቸው ድረስ አስጠርተው ጠየቁት ።

“ እቤል ይህ የጥናት ጽሑፍ ያንተ ነውን ?
አዎ ! የኔ ነው ። ”
“ ስትሰራው ተቻኩለህ ነበር መሰለኝ ? ”

አቤል ስለ ተደናገጠ ዝም አለ። ቶሎ መልስ አልሰጣቸውም ። ዮናታንም ድንጋጤውን ከገጽታን ላይ ስላነበቡ አነጋገራቸውን ለማቅለል ሞከሩ።

“ማለቴ ለዝግጅቱ የሰጠኋችሁ ጊዜ አንሶአችሁም ሊሆን ይችላል ።”

አሁንም አቤል መልስ አልሰጠም ። የይድረስ ይድረስ ሥራ መሥራቱን ልቡ ያውቃል ። ጊዜ አንሶትም አልነበረም ። እንዲያውኑም ከተሰጠው ጊዜ አንድ ሳምንት ቀድም ነው ያስረከበው ።
በመሰረቱ መምህሩ በሰጡት የጊዜ
ገደብ ውስጥ የጥናት ጽሁፍ ተሰርቶ መቅረብ አለበት ።ከዚያ በኋላ የመምህሩ ድርሻ እንደ ሥራው ጥራትና ይዘት ውጤት መስጠት ነው ። አስተዋዩ ዮናታን ግን ፥ በተበላሸው የአቤል ወረቀት ላይ ሳያመዛዝኑ ርምጃ መውሰነድ አልፈለጉም ዐይናቸውን ወረቀት ላይ ተክለው በሐሳባቸው የአቤልን ለውጥ ለማጥናት ተገደዱ ።

በአዲስ አበባው ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የዓመቱ ተመራቂዎች ሰባት ናቸው ። ከሰባቱ መሐል አንዱ አቤል ሙሉዬ ነው ። መምህር ከማናቸውም ይልቅ በአቤል ላይ ያላቸው እምነት ላቅ ያለ ነው ። የሶስቱን ዓመት
የዩኒቨርስቲ ትምህርት እያጠናቀቀ የመጣው ከፍ ባለ ውጤት ነው።
ከዚህም በላይ በክፍል ውስጥም ሆነ በውጭ በግል የሚያቀርበው ጥልቅ ዲያሎግ በዮናታን ልብ ውስጥ ትልቅ
ቦታ ነበረው ። የዮናታን ምኞት አቤል በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆ የበለጠ ከፍተኛ ትምህርት እንዲከታተል ነው ።
...ታዲያ ይህ የአፋፍ ላይ እንቅፋት ምን ይሆን ? ” ሲሉ ዮናታን ራሳቸውን ጠየቁ ።

ካቀረቀሩበት ወረቀት ቀና ብለው መነጽራቸውን በጣታቸው ሽቅብ ገፋ እያደረጉ ፡ ለአቤል ድንገተኛ ጥያቄ
አቀረቡለት ።

“ ዕድሜህ ስንት ነው ? ”

“ ሃያ አንድ ። ”

“ ገና ወጣት ነህ ” አሉት የደረሰበትን የትምህርት ደረጃ ከዕድሜው ጋር በማነጻጸር ።

“ በአንደኛና በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ ሦስት ያህል ክፍሎች በእጥፍ ነበር ያለፍኩት፤
ለዚህ ነው በጊዜ ዩኒቨርስቲ የገባሁት ” አላቸው መግረማቸዉን በማየት።

ወላጆችህ በቅርብ ናቸው ? ”

ይህ ድንገተኛ ጥያቄ አቤልን ቢያስደነግጠውም ከጥናት ጽሁፉ ጉዳይ ወጣ ያለ አርዕስት በመሆኑ ወዶታል ። ይሁንና በተዘዋዋሪም ቢሆን ለዚህ ጥያቄ መንሥኤው የጥናት መበላሸት መሆኑን ሳይገምት አልቀረም ።

“ በቅርብ እንኳ የሉም ። ጎንደር ክፍለ ሀገር ናቸው ።ሲል መለሰ ።

የኑሮ ደረጃቸው እንዴት ነው? ”

“ መቼም ጎርሰው ያድራሉ ። ቋሚ የገቢ ምንጭ ግን የላቸውም ” ካለ በኋላ ' ድንገት ግልፍ ብሎት ፥ “ ያው እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያውያን ወላጆች የእኔኑ እጅ ተጠባባቂዎች ናቸው ” ሲል አከለበት

ይህ ከጥያቄአቸው ውጭ ቢሆንም አንድ አቤል የተቸገረበት ጉዳይ መሆኑን ከአነጋገሩ ለመረዳት ዮናታን ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም ። ሆኖም የእሳቸው መንደርደሪያ በአቤል ውስጥ በቅርብ የደረሰ አደጋ ወይም አጋጣሚ እንዳላ
ለመረዳት ነበር ። በዚህ ረገድ ቀጥተኛ መልስ ባያገኙም ጥርጣሬአቸውን ለማስወገድ ችለዋል ።

ታዲያ... ብለው ዮናታን መናገር ያሰቡትን
ሳይጨርሱ አጠገባቸው ያለው ስልክ አቃጨለ ። የስልክ ጥሪው የማን መሆኑን በልባቸው ገመቱ ።

“ ሁሉ ... ሊብሊንግ ” አሉ አንዳች ነገር እንደሚጠብቁ ሁሉ ፊታቸው ላይ ጉጉት እየተነበበ ።

የደወለችው ሚስታቸው ሞኒካ ነበረች ። ንግግራቸው በጀርመንኛ ስለሆነ አቤል ከዮናታን አፍ ምንም ነገር ሊረዳ አልቻለም ነገር ግን የዮናታን ሚስት ጀርመናይት መሆኗን በዩኒቨርስቲው አካባቢ ሲወራ ይሰማ ስለ ነበር ፥ ዮናታን አሁን የሚነጋገሩት ከሷ ጋር መሆኑን ገመተ።

ሰሞኑን በርሊን ውስጥ የሚገኘው የሞኒካ ወንድም በጠና ታሞ ከባድ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግለት እየተጠባበቀ ነበር ።
ዮናታንና ሚስታቸውም ይህንኑ ጉዳይ በቴሌፎን በመከታተል አብረው ሲጨነቁ ነው የከረሙት ። የተጠቀሰው ዕለት
ደርሶ ሦስት ሰዓት ያህል የፈጀ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ ወንድሟ በሰላማዊ ሁኔታ እንደሚገኝ ዘመዶቿ ከበርሊን ደውለው ለሞኒካ ይነግሯታል ። ሞኒካም ወደ ዮናታን የደወለችው ይህንኑ ልታበሥራቸው ነበር ።

ዮናታን ቴሌፎኑን ከዘጉ በኋላ በደስታ ስሜት ፊታቸው ፈካ ። ከአቤል ጋር ጀምረውት የነበረውን አርዕስት
በዜናው ጣልቃ ገብነት ለማሳጠር ተገደዱ ።

“...እስቲ ለማንኛውም እንደገና እየው” አሉት ፥ በሚያባብል ድምፅ ።

አቤል በእሽታ ራሱን ናጠ ።
“ ሐሳብ ውስጥ ገብተህ ወይም ተቻኩለህ ይሆናል እንጂ አንተ እንዲህ ዓይነት ሥራ እንደማትሠራ እተማመናለሁ” እያሉ ለአቤል ወረቀቱን መልሰው ሰጡት
ወረቀቱን ሲቀበላቸው ፊቱ ላይ አንድ ስሜት አነበቡ ።ሰሜቱ የገባቸው ይመስል “ አይዞህ የሦስት ሳምንት ጊዜ ሰጥቼሃለሁ ። ረጋ ብለህ ሥራው » አሉት
አቤል ሲወጣ ከእንድ እሱነቱ ውስጥ ሁለት ስሜት እየተጓተቱ ነበር ።
ስማ አቤል ! አሁን ወረቀቱን መልስህ የተቀበልካቸው ምን ልትጨምርበት ነው ? የተቻለህን ያህል ሠርተሃል ፡ ይልቅ ፡ የማውቀው ይህን ያህል ነው በቃ ” በልና
መልስላቸው ፤ ያሻቸውን ውጤት ይስጡህ ይላል አንዱ ስሜቱ ።

ይህን ማመንታትህን ትተህ እንደ ገና በደንብ አጥርተህ ለመሥራት ሞክር : ተፍጨርጨር። የመጨረሻ ዓመትህ መሆኑን አትርሳ ። ወላጆችህም በተስፋ የአንተኑ እጅ ጠባቂዎች መሆናቸውን አትርሳ ። የሚወዱህን መምህርም
አታስቀይማቸው ...” ይላል ሌሳው ስሜቱ

የወላጆችህም ችግር ሆነ የመምህርህ ፍቅር ከችሎታህ ህና ከአቅምህ በላይ ሊያደርግህ አይችልም ። የምትችለው
ያንን ያህል ነው ፥ በቃ !... ”

እስቲ ለማንኛውም እንደ ገና እየው
እንዲህ ስሜቶቹ እየተሟገቱ ከመኝታ ክፍሉ ደረሰ ።
ሶስቱም የመኝታ ክፍል ጓደኞቹ እዚአው ውስጥ ነበሩ ።
አቤል ምንም ሳይነግራቸው በቀጥታ ወደ አልጋው ሔዶ በአንድ ጎኑ ዐረፍ አለ ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አቤል ለመኝታ ክፍል ጓደኞቹ ወሬ ማካፈል ቀርቶ ፥ አብረውት መሆናቸውም እያስጠላው ነበር ።
ብቸኝነት እያጠቃው ስለ መጣ ብቸኛ ክፍል ወስጥ ቢሆን ምንኛ በወደደ !... ከራሱ ጋር በመጣላቱ የፈጠረው ጥላቻ እንጂ ፥ ከአንዳቸው ጓደኞቹ ጋር ግጭት አልነበረውም ።

እስክንድር ማንደፍሮ አቤልን ተደራራቢ አልጋ የሚጋራው የመኝታ ክፍል ጓደኛው ነው ። በዩኒቪርስቲው ውስጥ
ሦስት ዓመት አብረው ቆይተዋል ። ከመኝታ ክፍል ጓደኝነታቸወም ሌላ ፥ ሁለቱም የፍልስፍና ተማሪዎች ናቸው ። እስክንድር ከአቤል በዕድሜ ላቅ ያለ ሲሆን ፥ በአቤል የትምህርት ጉብዝና ሳይ ጤናማ የሆነ ቅናት አለው ።

ሰሎቹ ሁለቱ የመኝታ ክፍል ጓደኞቹ ሳምሶን ከልሌ እና አስራት ጣሰው ናቸው ሁለቱም በግቢው ውስጥ የሚታወቁት በቅጽል ስማቸወ ነው " ሳምሶን ከስሙ ጋር ጉልቤው ” የሚል ቅጥያ ስም ወጣለት ማንኛውም ተማሪ ሲጠራው ሳምሶን ጉልቤውን ? እያሉ ነው ። አሥራት
ደግሞ የሚታወቀው “ ድብርት ” በሚል ቅጽል ስም ነው በተማሪው ዘንድ ትክክለኛ ስሙ ጭራሽ ተረስቷል
ማለት ይቻላል ።

ሳምሶን ጉልቤው ” እነ አቤል መኝታ ክፍል የመጣው በዚ ዓመት ነው ። እስክድር ጋር የአንድ ሰፈር ልጆች ስለሆኑ አንድ የፍልስፍና ተማሪ ፈተና
👍2
ወድቆ ከወጣ በኋላ ክፍላቸው ውስጥ ትርፍ መኝታ መኖሩን አይቶ ነው የመጣው ። የሁለተኛ ዓመት የምጣኔ ሀብት ተማሪ ነው ።በአንደኛ ዓመት ትምህር ፡ ባገኘው ዝቅተኛ ውጤት "ማስጠንቀቂያ ” ውስጥ "ቢገባም ስፖርቱን አላቋረጠም ። ስፖርትና ምግብ በጣም ይወዳል ። የዚያኑ ያህልም ሰውነቱን ስላዳበረ ። አፍላነቱ ይፈታተነዋል ። ለዚህ ነው “ጉልቤው” የሚል ቅጥያ የወጣለት ። በዚህ ዓለም ላይ ማንም ሰው የሚያሸንፈው አይመስለውም ። እንኳን እሱን ቀርቶ ጓደኞቹን የሚደፍር ከመጣ ፡ ማነው እሱ ? እናቱን ፤ ” ብሎ ማፍጠጥ
ነው ። “ ጥርሱን ነው የማመልቀው ! ” ሴትም ከሆነች “ጥርሷን ነው የማወልቀው ! ” የጡንቻ መፈክሮች
ናቸው ። ሁሌ ሁሉን ሰው እንዳንቀጠቀጠ
ነወ።አንድ ቀን ብቻ በአንድ የግቢው ወጣት ተደፍሮአል።

ስምሶኦን የምግብ እዳራሽ ሰልፍ አይወድም ሁሌ ጥሶ ነው የሚገባው
አንድ ቀን እንደ ለመደዉ ሰልፍ ጥሶ ሊገባ
ሲል ከፊት የነበረ በዕድሜው በሰል ያለ ወጣት በአድራጎቱ በሽቆ ጭንቅላት እያለህ ለምን በጡንቻህ ታስባለህ ? በጡንቻው የሚያስብ አህያ ብቻ ነው ” አለው• ። ሳምሶን ጉልቤው ” ይህን ሰውና ቃላቱን እስከ መቼውም አይረሳውም
ካልተደባደኩ ብላ ለጊዜው ቢጋበዝም
ከዚያ በኋላ ባላቸው ግኑኝነት ለራሱም በማይገባው ስሜት ወጣቱን ያከብረው ነበር ።

አሥራት ፍጹም ዝምተኛ ነው ብሶትም አለበት እዛው ለዚያው ያልጎመጎማል እንጂ በወጉ አይናገርም ጣእም የሌለው
ዝምታው በጣም ያስጠላል መሃበርያዊ ኑሮ ውስጥ ያለ አይመስልም።“ድብርት ” የሚል ቅጽል ያወጡለትም ለዚህ ነው።

💥 ይቀጥላል 💥
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

...ሳሚ ጨዋታውን አቁሞ ሊያግባባቸው መሃል ገባ፡፡ ነገሩ ጭራሽ ጦዘ፡፡

“አንተ ለሷ መደረብህ ነው? ምን አገባህ! ምታመዛዝን ትልቅ ሰው ትመስለኝ ነበር! እንደዚህ የወረድክ መሆንህን ባውቅማ፣ ወይኔ...!” ግርማ እየጮኸ ያወራል፡፡ ነገሩ አላምርህ ሲለኝ አስተናጋጅ ጠርቼ ሂሳብ
አምጣልን አልኩት።

“ተረጋጋ! ቀስ ብለኸ አውራ! ” ሳሚ ሊያረጋጋው ሞከረ፡፡

“አንተ ስለእርሷ ምን አገባህ?!” ግርማ ነገሩን በጣም አከረረው፡፡ከደቂቃዎች በፊት ሳቅና ጨዋታ የነበረው ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ተለወጠ፡፡

“በቃ ተነሱ፤ ሂሳብ ተከፍሏል እንሂድ” ሳሚ ተነስቶ ወጣ፣ተከተልነው፡፡

“አንተ ምን ስለሆንክ ነው ምትከፍለው?! ሂሳቡን አሳየኝ የራሴን እከፍላለሁ!” ግርማ ሳሚን እየተከተለው፣ ተጨቃጭቀው፡፡ ሳሚ ሪሲቱን አሳየው፡፡ ግርማ የሆነ ብር ሰጠውና ተለያዩ፡፡

“አሁን እንዴት ነው የምንሄደው? እኔ ቤቲን አደርሳታለሁ ፤አንተ ሁለቱን ታደርሳቸዋለህ” አለኝ ሳሚ መኪናውን እየከፈተ፤

“እሺ! ችግር የለም አደርሳቸዋለሁ።”

“ኖ!..ኖ! እኔ በባጃጅ ሄዳለሁ፤ አልፈልግም!” ብሎ ግርማ ጥሎን
ሊሄድ ሲል፣ ተከሻውን ያዝ አደረኩና አረጋግቼ ከማሂ ጋር መኪና ውስጥ አስገብቼ ልሽኛቸው ወደ ዋናው መንገድ መንዳት ጀመርኩ፡፡

“ማሂላ መጀመሪያ ግርምሽን እናድርሰው አይደል?” ማሂ አጠገቤ ብትሆንም ግርማ እንዲሰማ ጮክ ብዬ ጠየኳት፡፡ ስንመለስ ብቻችንን እንድንገናኝ እንደምትፈልግ አውቃለሁ፡፡ ማሂ ቆንጆ ብቻ ሳትሆን ፈጣንና ተግባቢ ናት፡፡ ከጠበኩት በላይ በፍጥነት ነው ተግባብተን ግንኙነት የጀመርነው፡፡ ስንመለስ አብረን እንድናድር እንደፈለኩ
ገብቷታል፡፡

“በፍፁም አይሆንም! መጀመሪያ ለሴት ነው። ቢመሽም እኔ ወንድ ነኝ፣ እርሷን እናስቀድም፤” አለ ግርማ፡፡
“አይ ችግር የለውም ግርምሽ፡፡ የኔ ቤት መንገድ ዳር ስለሆነ እሱም ሲመለስ እንዳይቸገር፣ መጀመሪያ አንተ ቅደም፡፡ ስላስቀደምከኝ ግን በጣም አመሰግናለሁ!” ብላ ከመጨረሷ፣ ቀበል አድርጌ፧

“የት ሰፈር ነህ ግርምሽ?” አልኩት ሌላ ክርክር እንዳያመጣ፡፡

ቀበሌ አስራ አንድ፡፡ ፖስታ ቤት ጀርባ፡፡ ግን አስቸገርኩህ፣በባጃጅ መሄድ እችላለሁኮ...”
“እረ ችግር የለውም! ደግሞ አብረን ወጥተን ተለያይቶ መግባት ደስ አይልም፡፡”

“እሺ ካላቹ፤” ብሎ ስለቤቲና ሳሚ እያማረረ እቤቱ አደረስነው፡፡ስንመለስ፣ ወደ መብራት ሃይል እየነዳሁ ፤
“መቼም በቅዳሜ፣ በዚህ ሰዓት እንግባ እትዪኝም፡፡”

“ደስ ወዳለህ ንዳው፣ እኔም መዝናናት ፈልጌያለሁ፡፡”

ጭፈራ ቤት እየቀያየርን፣ ቢራና ውሲኪ እያፈራረቅን ጠጣን፣በደስታና በመጠጥ ሰክረን ጨፈርን፡፡ የሚያቀን ሰው ቢያየንስ ሳንል፣ በየመሃሉ እንሳሳማለን፡፡ ያለልጓም እስኪወጣልን ተዝናናን፡፡ ሲደክመን
ወደቤት ለመሄድ ወጣን፡፡ ማሂም እንደኔው በግንኙነታችን ደስተኛ የሆነች ትመስላለች፡፡ በየምክንያቱ እኔ ጋር ማደር ልማድ ሆኗል፡፡ ዛሬ ደግሞ እቤት እስክንደርስም አላስቻላትም፡፡ እየነዳሁ ትስመኛለች፡፡ ስንደረስ፣ ማላቃት እስኪመስለኝ፣ የፍቅርና የእልህ በሚመስል መልኩ፣ ዝለን እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ ግንኙነት አደረግን፡፡ ጥዋት አንድ ሰዓት ሲሆን እንደተለመደው እቤቷ አደረስኳት፡፡

####

ባልጠበኩት መልኩ ጥሩ ስራና ቆንጅዬ ልጅ በአንዴ አግኝቼ፣አንድ ቀን ሳይከፋኝ አንድ አመት አለፈኝ፡፡ በሁሉም ነገር ደስተኛ ነኝ፡፡ከማሂ ጋር በጀመርኩት ግንኙነትም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ይሁን እንጂ፣ አሁንም ከማሂ ጋር ያለኝ ግንኙነት በሚስጥር እንዲቀጥል
እፈልጋለሁ፡፡ አሁንም ልቤ ሜሪ ጋር ነው፡፡ በስልክ ምናደርገውን ግንኙነት አላቋረጥኩም፡፡ ግን ሽማግሌ ሳይላክ ምንም አይነት ግንኙነት መጀመር እንደማትችል ነግራኛለች፡፡ እዚህ መስሪያ ቤት ከገባሁ በኋላ፣ ህይወት ብርሀን፣ ፍካት፣ ጣፋጭ እና አጓጊ ሆናልኛለች፡፡ ተስፈኛ ሰው ነኝ! ዛሬም እንደተለመደው በሙሉ ሱፍ ነኝ፡፡ ሱፍ ያምርብሃል
ቢሉኝም፣ እኔ ሱፍ ማዘወትረው የስራ ዩኒፎረሜ ስለሚመስለኝ ነው::ካለሱፍ ስሄድ እረፍት ላይ ያለሁ ይመስለኛል፡፡

ከሆነ ግዜ ጀምሮ ግን አለቃዬ ባህሪያቸው እየተቀየረብኝ መጥቷል። እንደዛ እንዳላከበሩኝና በስራዬ እንዳልኮሩብኝ፣ ከስራዬ እንከን
እየፈለጉ ይዘልፉኝ ጀምረዋል፡፡ በአሽሙር እኔን መቅጠራቸው ትልቅ ስህተት እንደሆነ በሰዎች መሃል ይናገራሉ፡፡ እንዳልገባኝ እሆናለሁ።ቢሯቸው ለጉዳይ ከሄድኩ፣ ስራ እንደያዙ በምልክት እያሳዩ
እንድወጣላቸው ያደርጋሉ፡፡ ስንዝናና እንኳ፣ እኔ ካለሁ ምክንያት ፈጥረው ይሄዳሉ፡፡ ቅሬታቸው ለሰዎች እስኪገለጥ በገሃድ አደረጉት።ለኔ ግን ምን እንዳጠፋሁ እንኳ አልነገሩኝም፡፡ ሲደጋገምብኝ፣ ቢሯቸው ሄጄ ጋሼ ብዬ፣ ምን አጥፍቼ እንዲህ እንደተለወጡብኝ እንዲነግሩኝ ጠየኳቸው፡፡ ከስራ ውጪ ሚያገናኘን እንደሌለና ሁለተኛ እንደዚህ
አይነት ጥያቄ እንደማይፈልጉ፣ እንደውም ስራ እንደረበሽኳቸው ነግረውኝ፣ ከቢሯቸው እንድወጣ አደረጉኝ፡፡ ባህሪያቸው ይሆናል ብዬ ወደስራዬ አተኩሬ መስራቴን ቀጠልኩ፡፡ውስጤ ግን ማብሰልሰል ጀመረ።

“ምነው በጥዋት በሃሳብ ሄድክ፣ ና ተነስ ቡና ልጋብዝህ!” ማሂ ናት፡፡ አሁን አሁን ሰው እስኪጠረጥር ቢሮዬ መመላለስ አብዝታለች፡፡በሻይ ሰዓት ደጋግማ እየመጣች ከእርሷ ጋር አብረን እንድንወጣ ታደርጋለች፡፡ እሺ ብያት ስንወጣ፣ ከፊታችን ግርማን አየነው፡፡

“ቀስ በል፣ ይሄ ማቶ እንዳያየን፤” አለች ወደ ግርማ በአገጯ እየጠቆመች።

“እንዴ! ቢያየንስ፣ ምን ችግር አለው?”

“ኧረ ባክህ? በዚህ ጥዋት ማን የሱን ዝብዘባ ይሰማል፡፡ ምኑን ከምን እንደሚያገናኘውኮ? በዛ ላይ ሲያወራ
ነን ስቶፕ፡፡”

“ማለት?”

“እንጃ ግርማ የሆነ ትንሽ የላላ ነገር አለው፡፡ ከፈሱ የተጣላ ነው፡፡” ከካፍቴሪያ ጀርባ ተቀምጠን ቡና አዘዝን፡፡

“ከፈሱ የተጣላ ማለት?”

“በጣም ተጠራጣሪ ነዋ፡፡ ባለፈው ማታ ከቤቲ ጋር የተጣሉት ቢራ ብርጭቆዬን ቀየርሽብኝ ብሎ አይደል እንዴ.. ሆ..:: እዚህ ግቢ ከሰው ጋር ሁሉ ተናክሶ ጨርሷል፡፡ ሰው ሁሉ እሱን ሚሰልለው
ይመስለዋል፡፡ ወሬው ሁሉ እከሌ እንዲህ አስወርቶብኝ፣ እንዲህ አስደርጎኝ.. ምናምን ነው፡፡ በተለይ ይቺን እንዲህ ብታደርጋት፤ ብለህ አስተያየት ከሰጠኸው...፣ አለቀልህ፡፡”

“ማለት?”

“አንተ እረስተኸው ሁላ፣ ያለህበትን በእግር በፈረስ አፈላልጎ ይመጣና፣ አንተ ግን ቅድም ምን አስበህ ነው እንደዚህ ያልከኝ?፣ ማን ነው እንደዛ በል ያለክ?፣ ምናምን እያለ አይፋታህም፡፡ አዛ ያደርግሃል።

በዚህ ባህሪው ከብዙ እስታፍ ጋር ተጣልቷል፡፡ ለማንኛውም ተጠንቀቅ፡፡

‹‹እሺ፡፡ እጠነቀቃለሁ፡፡››

ቡናችንን ጠጥተን፣ እያወራን እኔ ቢሮ ድረስ ሽኘችኝ፡፡ ከቢሮ ልትወጣ ስትል፣ ሳሚ ሳታስበው ገብቶ ከኋላዋ አቀፋት፣

“እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?”

“ያቡን ምን ጎደለህ ልለው...”

“እርሱ ምን ስለሆነ...? እኔን መጥተሽ መች እንደ ትይኛለሽ...?” እየሳቀ ጉንጫን ለመሳም ይታገላታል። ሳሚ ልማዱ
ነው፡፡ ሴቶቹን አየዞረ ጉንጫቸውን መሳም አመል ሆኖበታል፡፡ አብዛኞቹ ይተባበሩታል፡፡

“አንተስ ከመቼ ጀምሮ ነው፣ ፋይናንስና አድሚንን እኩል ያደረከው...?፡፡" ከእቅፉ ሾልካ አመለጠችው፡፡

“ደግሞ እንዲህም መከፋፈል ጀመራችሁ? እኛም ከአድሚን
ስራተኛ ጋር አንድ መሆን አንፈልግም...!” እያላት ከላይ እስከታች ተመለከታት፣

“አቤት... ዛሬ ደግሞ፣ ውበትሽን ገልጠሽዋል፡፡ ደግሞ ማንን
ልታጠምጂ ይሆን..?”
👍3