አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የአፍሪካ_አናብስት

አምላክ! ት......ልቅ ነገር ለአፍሪካ አድሏታል
አንበሳ 'ሚበላ አንበሳ ሰጥቷታል፡፡

አንት የአፍሪካ መንጋ - አንት የአፍሪካ አንበሳ
ነፍጠኛ ቀርቦሃል በል ነፍጥህን አንሳ፡፡

ካደክበት ቀየ ፣ ካደክበት መንደር
ማዕድን ሲወጣ ፣ መሬትህ ሲቆፈር
ምንድን ነው ማፈግፈግ!?፣ ምንድን ነው ማቀርቀር!?

አይዞህ የኛ አንበሳ!- አይዞህ የኛ ጀግና!
ብዕርህን ጥለህ ነፍጥህን አንሳና፣
እጫካህ ግባና፣
ጨፍጭፍ ወንድምህን፤
ጨፍጭፍ እህትህን፤
ጨፍጭፍ አባትህን፤
ጨፍጭፍ እናትህን፤
ጨፍጭፍ!
ጨፍጭፍ!
ጨፍጭፍ!......
ጨፍጭፋቸው ሁሉን!
ኖረው ካላኮሩን
ዛፍ ይብቀልባቸው አፈር ይሁኑ አሁን፡፡
ተነስ ያዝ ቦንብህን
ይብሱን ጎትታት ጎታታ አገርህን፡፡

ወዲያ የምን ልማት?
የምን ኢንዱስትሪ? ፣ የምን የአገር እድገት?
የጓሮህ ማዕድን
ተቆፍሮ ወጥቶ አገር ከሚያድግበት
አንተ ሽጠውና መሳሪያ ግዛበት፤
መሳሪያ ግዛና ወገን ግደልበት፤
ወገን ግደልና ለስልጣን ተሯሯጥ፤
ያልለፉበት ዳቦ ድሮም ቢሆን አይጣፍጥ፡፡

አንት የአፍሪካ ጀግና አንት የአፍሪካ አንበሳ
ነፍጠኛ ቀርቦሃል -በል ነፍጥህን አንሳ፡፡
ለወንበር ሲሮጡ ለወንበር ተነሳ
ለስልጣን ከቸኮልክ ለሰው ነብስ አትሳሳ፡፡

አየህ አሜሪካን!?
አየህ እነ አውሮጳን!?
ከንቱ ሲጃጃሉ፤
‹ስልጣን በህዝብ እንጂ-
በነፍጥ አናገኝም!›
ብለው ሲማማሉ፡፡

አየህ እነ ህንድን!?
አየህ እነ ቻይናን!?
አየህ ያገር ፈሪ!?
ነፍጣቸውን ጥለው ሲያስፋፉ እንዱስትሪ፡፡

እንትፍ!
ወንድ አሰዳቢዎች ልፍስፍስ እንደ እበት
እነዚህን ነበር
በአንድ ቦምብ ጨፍልቆ ከአለም ማሰናበት፡፡
ቢሆንም እርሳቸው ምንም አይሰሩልህ
ፈንጅ መትረየስ ግን ተቀበል ሲሰጡህ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘