#ቁጭት
መውደድን አርሰን ቆፍረን.. ፍቅርን ነበር የዘራነው
ትውውቅን ተክለን ኮትኩተን..ደስታን ነበር ያሳደግነው
የጥርጣሬ ነቀዝ በልቶት...ገና ሳይበስል ቆረጥነው::
ለካ መለየት እንዲህ...ሰውን በቁሙ ይበላል?
ለካ 'ሚወዱት ሲርቅ...ዓለም በሙሉ ያስጠላል?
ለካንስ ትርፉ ፀፀት ነው...ብቼኝነትም ያደክማል!?
አጥንቴ ቀረልሽ ፍቅሬ..ወጣሁልሽ ከሰው ተራ
ብቻየን ማውራት ጀመርኩኝ..አበደ ተብሎ ተወራ፡፡
ግዴለም ስጋ ቢስ ልሁን...እብደቴን ሰው ይወቅብኝ
አንቺ ካለሽ ነው ምኖረው -
ብቻ አንቺን ክፉ አይይብኝ
ብቻ አንቺን ክፉ አይንካብኝ፡፡
አንቺ ካለሽ ነው ምኖረው...እላለሁኝ ደሞ አላፍርም
በቁሙ ከሚነገላጀጅ
ሐዘን ደስታውን ከረሳ...የተቀበረ አይሻልም!?
ቢሆንም ሞት አልፈልግም...መንቀዋለሉ ይሻለኛል
ሰማይ ቤት እንዳንቺ ያለ.ፍጥረትስ እንዴት ይገኛል!?
ፍቅራችን ማበብ ሲጀምር....እንዳይከስም ያልደከመ
የፈስስን ውሐ ላያፍስ...የሰማይ ላሙን እያለመ
አለ ስላሙ ሲናጋ..ልቤ ትዝታን እያከመ::
ትዝ ይልሻል መቼም ፍቅሬ.. ፍቅራችን ምን እንደነበር?
ተዝቆ ማያልቅ የሚመስል
ዕልፍ አዕላፍ ደስታ..ከፊታችን ሲደረደር
ተስገብግበን ስንቋደስ
አንቺ በስሜ ትምይ ነበር
እኔ በስምሽ እምል ነበር፡፡
የፍቅር መልአክ ኮርኩሮሽ..ሰማይ እያየሽ ስትስቂ
የመውደድ ብርሐን ተገልጦ.. አይኔን እያየሽ ስትቦርቂ፣
ይመስለኝ ነበር ፅድቅነት
የገባሁ ከምድር ገነት፡፡
ታዲያ አሁን ያ ህልም መሳይ..የህይወት ብርሐን ደብዝዞ
ያልበሰለው የፍቅር እሸት...እንዳይበላ ጎምዝዞ
ብቻየን አስቀረኝ እኔን.. ትዝታሽን ብቻ አስይዞ፡፡
እኔ ምለው የኔ ስስት፣
የኔ ፅልመት፣
የኔ ብርሐን፤
እንዲያ በደስታ እንዳልፈካን
በሳቅ እንዳላውካካን፣
ካንቺ ጋር አብሮ የራቀኝ.. አለኝ የምለው ዘመዴ
ከንፈሬ የማይገለጥ...ሳቅ እምቢ ያለኝ ከሆዴ
የሳቅም ጡር አለው እንዴ!?
ግዴለም ሳቅ ይቅርብኝ...ሳቄ በለቅሶ ይተካ
መኖርሽን በማሰብ ብቻ...ልቤ እያነባ ይፍካ፡፡
በእጅ የያዙት ወርቅ እንዲሉ...ችላ ያልነው እንደዋዛ
ጠብታዋ ባህር ሆና
ያማረን ጎጆ ስታፈርስ...የሞቀውን አቀዝቅዛ፣
የአብሮነት ኑሮ ምቾቱ...የትካዜ ጎርበጥባጣው
የብቼኝነት ህመሙ ሲለያዩ ነው የሚሰማው፡፡
ስጋና አጥንቴ ተጣብቀው...ደስታ ርቆብኝ ቢያዩኝ
ህመምህን ንገረን' ብለው...ጓደኞቼ እንኳን ጠየቁኝ፡፡
ራሴን
ሆዴን
እግሬን
ልቤን.......
አልልም ጉዳታቸው አይሰማኝም
ምንድን ነው ሚያምህ?” አትበሉኝ... እኔኮ ስሜት የለኝም
የሆድ ቁርጠት...ራስ ምታት...ብሎ ነገር አይገባኝም፡፡
አንድ በሽታ ብቻ ያለኝ
አንድ ሐኪም ብቻ የሚያድነኝ
እኔ የሷ በሽተኛ...እኔ የሷ ታካሚ ነኝ፡፡
እናማ የኔ ሐኪም...የኔ ህመም የኔ ፈዋሽ
በእንባየ የታጠበውን...ነጭ ጋዎንሽን ለብሰሽ
እንደ ድሮው ተፍለቅላቂ..ይመርብሽ ልይሽ ደምቀሽ፡፡
እኔ ግን የኔ ሩቅ
ካንቺ ከተለየሁ...ከተራራቅሁ ወዲህ
ሆኛለሁ ቀልበ ቢስ...ሆኛለሁ ልብ ውልቅ
ሲያጫውቱኝ የማለቅስ...ሲሰድቡኝ የምስቅ፡፡
ሆኛለሁ ብቸኛ... ሆኛለሁ ልብ አድርቅ
ሲርቁኝ የማልቀርብ...ሲጠጉኝ የምርቅ፡፡
🔘በሙሉቀን🔘
መውደድን አርሰን ቆፍረን.. ፍቅርን ነበር የዘራነው
ትውውቅን ተክለን ኮትኩተን..ደስታን ነበር ያሳደግነው
የጥርጣሬ ነቀዝ በልቶት...ገና ሳይበስል ቆረጥነው::
ለካ መለየት እንዲህ...ሰውን በቁሙ ይበላል?
ለካ 'ሚወዱት ሲርቅ...ዓለም በሙሉ ያስጠላል?
ለካንስ ትርፉ ፀፀት ነው...ብቼኝነትም ያደክማል!?
አጥንቴ ቀረልሽ ፍቅሬ..ወጣሁልሽ ከሰው ተራ
ብቻየን ማውራት ጀመርኩኝ..አበደ ተብሎ ተወራ፡፡
ግዴለም ስጋ ቢስ ልሁን...እብደቴን ሰው ይወቅብኝ
አንቺ ካለሽ ነው ምኖረው -
ብቻ አንቺን ክፉ አይይብኝ
ብቻ አንቺን ክፉ አይንካብኝ፡፡
አንቺ ካለሽ ነው ምኖረው...እላለሁኝ ደሞ አላፍርም
በቁሙ ከሚነገላጀጅ
ሐዘን ደስታውን ከረሳ...የተቀበረ አይሻልም!?
ቢሆንም ሞት አልፈልግም...መንቀዋለሉ ይሻለኛል
ሰማይ ቤት እንዳንቺ ያለ.ፍጥረትስ እንዴት ይገኛል!?
ፍቅራችን ማበብ ሲጀምር....እንዳይከስም ያልደከመ
የፈስስን ውሐ ላያፍስ...የሰማይ ላሙን እያለመ
አለ ስላሙ ሲናጋ..ልቤ ትዝታን እያከመ::
ትዝ ይልሻል መቼም ፍቅሬ.. ፍቅራችን ምን እንደነበር?
ተዝቆ ማያልቅ የሚመስል
ዕልፍ አዕላፍ ደስታ..ከፊታችን ሲደረደር
ተስገብግበን ስንቋደስ
አንቺ በስሜ ትምይ ነበር
እኔ በስምሽ እምል ነበር፡፡
የፍቅር መልአክ ኮርኩሮሽ..ሰማይ እያየሽ ስትስቂ
የመውደድ ብርሐን ተገልጦ.. አይኔን እያየሽ ስትቦርቂ፣
ይመስለኝ ነበር ፅድቅነት
የገባሁ ከምድር ገነት፡፡
ታዲያ አሁን ያ ህልም መሳይ..የህይወት ብርሐን ደብዝዞ
ያልበሰለው የፍቅር እሸት...እንዳይበላ ጎምዝዞ
ብቻየን አስቀረኝ እኔን.. ትዝታሽን ብቻ አስይዞ፡፡
እኔ ምለው የኔ ስስት፣
የኔ ፅልመት፣
የኔ ብርሐን፤
እንዲያ በደስታ እንዳልፈካን
በሳቅ እንዳላውካካን፣
ካንቺ ጋር አብሮ የራቀኝ.. አለኝ የምለው ዘመዴ
ከንፈሬ የማይገለጥ...ሳቅ እምቢ ያለኝ ከሆዴ
የሳቅም ጡር አለው እንዴ!?
ግዴለም ሳቅ ይቅርብኝ...ሳቄ በለቅሶ ይተካ
መኖርሽን በማሰብ ብቻ...ልቤ እያነባ ይፍካ፡፡
በእጅ የያዙት ወርቅ እንዲሉ...ችላ ያልነው እንደዋዛ
ጠብታዋ ባህር ሆና
ያማረን ጎጆ ስታፈርስ...የሞቀውን አቀዝቅዛ፣
የአብሮነት ኑሮ ምቾቱ...የትካዜ ጎርበጥባጣው
የብቼኝነት ህመሙ ሲለያዩ ነው የሚሰማው፡፡
ስጋና አጥንቴ ተጣብቀው...ደስታ ርቆብኝ ቢያዩኝ
ህመምህን ንገረን' ብለው...ጓደኞቼ እንኳን ጠየቁኝ፡፡
ራሴን
ሆዴን
እግሬን
ልቤን.......
አልልም ጉዳታቸው አይሰማኝም
ምንድን ነው ሚያምህ?” አትበሉኝ... እኔኮ ስሜት የለኝም
የሆድ ቁርጠት...ራስ ምታት...ብሎ ነገር አይገባኝም፡፡
አንድ በሽታ ብቻ ያለኝ
አንድ ሐኪም ብቻ የሚያድነኝ
እኔ የሷ በሽተኛ...እኔ የሷ ታካሚ ነኝ፡፡
እናማ የኔ ሐኪም...የኔ ህመም የኔ ፈዋሽ
በእንባየ የታጠበውን...ነጭ ጋዎንሽን ለብሰሽ
እንደ ድሮው ተፍለቅላቂ..ይመርብሽ ልይሽ ደምቀሽ፡፡
እኔ ግን የኔ ሩቅ
ካንቺ ከተለየሁ...ከተራራቅሁ ወዲህ
ሆኛለሁ ቀልበ ቢስ...ሆኛለሁ ልብ ውልቅ
ሲያጫውቱኝ የማለቅስ...ሲሰድቡኝ የምስቅ፡፡
ሆኛለሁ ብቸኛ... ሆኛለሁ ልብ አድርቅ
ሲርቁኝ የማልቀርብ...ሲጠጉኝ የምርቅ፡፡
🔘በሙሉቀን🔘