አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
576 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በክፍለማርያም

...ወደ ሆስፒታል ገሰገሰች
ፍፁም የህክምና ሰወች ተረባርበዉ ትንሽ ነብሱ መለስ አለች
ህመሙን የሚቀንስ መድሀኒት ተሰጥቶት ከዋጠ በኋላ
ከትራሱ ጋር ድጋሜ ጭንቅላቱን አገናኘዉ
እንደ ህመም ከባድ ወቅት የለም በጤነኝነት ስንኖር ዋጋ ሰጥተን
ባናስበዉም ስንታመም እና ስቃይ ዉስጥ ስንሆን ግን ሁሉ ነገራችን ተወስዶ ጤናችን ቢመለስ እንለምናለን
አብዛኞቻችን ለጤናችን አስበን አናዉቅም ጥንቃቄም የለንም
ምኞታችን ብር ላይ ያተኮረ ይሆናል ይለፋል ይለፋል በስተመጨረሻ ጤና ጠፍቶ ስንሰቃይ በህመም እጅ ዉስጥ
ስንወድቅ ብራችንን በሙሉ ለጤናችን መልሰን እናዉላለን
እንደ ፍፁም በአደጋ ህመም ላይ ሲወደቅ ግን ምን ይደረጋል
ሳያስበዉ እና ሳይጠብቀዉ ለዚህ በቃ የዚህ ሁሉ ጦስ ደግሞ
የፍቃዱ ተንኮል በተጨማሪም የቤዛዊት ማገናዘብ አለመቻል ናቸዉ።

እንቅልፍ መተኛት ባይፈልግም አልጋዉ ላይ ጋደም ብሎ
አይኖቹን ያንከራትታል
"እግሬ ለወደፊቱም መራመድ ባይችልስ?"
በድን እግሮቹን ለማንቀሳቀስ እየሞከረ
በፊት ልጅ እያለ ከጉዋደኞቹ ጋር እሩጫ ሲወዳደሩ አንደኛ እንደሚወጣ አስታዉሶ ፈገግ አለ ወደ አሁኑ ያለበት ህይወት ሲያስብ ግን እንባ እና ተስፋ መቁረጥ
ስለሚከቡት ላለማሰብ በብርድ ልብሱ ተጠቅልሎ ተኛ።

ቤዛዊት ብቻዋን እንድትሄድ ቤተሰቦቿ አልፈቀዱላትም ነበር
እህቷ አብራት ነበረች የተኛበትን አልጋም ስለምታዉቀዉ ልታሳያት ተከተለቻት።

ከቦታዉ ደርሰዉ አልጋዉ አጠገብ ቆሙ ተጠቅልሎ የተኛ አካል
በብርድ ልብሱ ቅርፅ ሰርቶ ይታያል ፍፁምን ለማየት የጓጓችዉ
ቤዛዊት እንዲነሳ እግሩን በእጆቿ ነካ ነካ ነረገችዉ አልሰማ አላት

"ፍ ፁ ም ..."

እህቷ የፍፁም እግሮች እንደማይሰሩ እንደማይሰሙ
ብታዉቅም ለመንገር ግን
ከብዷት እህቷ የምታረገዉን በሀዘኔታ ታያለች።

"ፍ ፁ ም ፍፁም..."

የሚሉ ቃላቶች የእዉነት እየሆኑ በቅዠት መልክ ስለተሰሙት
አቤት ለማለት አይኖቹን ከፍቶ ከብርድ ልብሱ ተገለጠ
ፊት ለፊቱ ቤዛዊት ቆማለች የጠቆረች የከሳች የተጎዳች መሰለዉ
ለማማተብ የዘረጋዉን እጁን አይኑን ባለማመን ጠራረገበት
እሷ ፊት ላይ ለስለስ ያለ ፈገግታ እየታየ ቀረበችዉ
ወደ ጉንጮቹ ከመጠጋቷ በፊት እህቷን አየት አርጋት ሳመችዉ
እህቷም ስለገባት እንዲያወሩ ጥላቸዉ ወደ ዉጪ ወጣች
የደረቀ እና የተጣበቀ ከንፈሩን እያለያየ
"እንዴት ነሽ ቤዚ..."
"ደህና ነኝ አንተስ አልተጎዳክም አደል ..."
በእጆቿ እየደባበሰችዉ
"ምንም አልተጎዳሁም..."
ህመሙን ዋጥ እያረገ እሷ ስለመጣች ደስ እያለዉ
ፊቷን አተኩሮ እያየ ፈግታዋ እንደድሮዋ አልደምቅልህ አለዉ
ደህንነቷ አሰጋዉ ጠፍታ ነበር የተባለዉን አስታዉሶ ልጠይቃት
አልጠይቃት እያለ በዉስጡ ማሰብ ጀመረ።

በእስዋ በኩልም ፍፁምን ታሞ አልጋ ላይ ስታየዉ ዉስጧ እርብሽ ብሏል ከትምህርት ቤት እንደተባረረ ወሬ
ስለሰማች በእሷ ምክንያት መሆኑን ገምታለች
የተገጨዉም ይሄኔ እኔን ለማዋራት ትምህርት ቤት ሲመጣ
ነዉ እያለች ሁለቱም በራሳቸዉ ሀሳብ ሰምጠዉ ቆይተዉ
"ቀሚስሽ ደሞ እንዴት ያምራል .."
ጨዋታ ለመጀመር አስቦ ለየት ስላለበት አለባበሷ
"የእማማ ስንቄ ነዉ እንዴት ጥሩ ሰዉ መሰሉክ የሆነ ቀን አብረን ሄደን አስተዋዉቅሀለዉ..."
መራመድ እንደማይችል ትዝ ስላለዉ ማዉራት እየከበደዉ
በመስማማት አንገቱን ነቀነቀ
"ምግብ በልተሀል ለምን ከአልጋ ወርደህ አትቀመጥም "
ፈጠን ያለ ጥያቄ ጠየቀችዉ
"በልቻለሁ.."
ተስፋ በቆረጠ አነጋገር
ቤዛዊት መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ተነስቶ ተቃቅፈዉ
የሆድ የሆዳቸዉን እያወሩ ከሚጨንቀዉ ሆስፒታል
ፍፁምን ይዛዉ ብትወጣ ደስታዋ ነዉ
ነገር ግን ፍፁም መንቀሳቀስ የፈለገ አልመሰላትም
"ተቀይመሀኛል እንዴ መጥቼ ስላልጠየኩህ"
ከንፈሯን እያጣመመች
"አረ አልተቀየምኩሽም"
እጆቹን ሰዶ እጆን ያዛት
"እሺ ተነስ..."
አይኖቹን እስዋ ላይ ተክሎ እግሮቹን ለማንቀሳቀስ መታገል ጀመረ
"እ ህ ..........አ"
እየከበደዉ እልህ እየተናነቀዉ በእጆቹ ታግዞ
አልጋዉ ጠርዝ ላይ በመከራ ተቀመጠ
ቤዛዊት ግራ ተጋብታ እያየችዉ ነዉ ልታግዘዉ እየሞከረች
እንዳትረዳዉ በእጆቹ ምልክት ስላሳያት ፈዛ በሀዘኔታ ታየዋለች
በደንብ አልተሻለዉም በማለት እንባዋን ለመቆጣጠር እየታገለች
ከጀርባዋ ያለዉን ዊልቸር እየጠቆማት
"እሱን ጠጋ አርጊልኝ"
አዘዛት
ላለ ማልቀስ እየታገለች አስጠጋችለት ከአልጋዉ ወርዶ
ዊልቸሩ ላይ ሊቀመጥ ሲል ግን
የዊልቸሩ ጎማወች ስለሚንቀሳቀሱ ለመቀመጥ ሲታገል
ሚዛኑን ሳቶ ከመዉደቅ ቤዛዊት በእጆቿ ደግፋ አተረፈችዉ
ተደናግጠዉ ተያዩ ወድያዉ እንዲቀመጥ ካገዘችዉ በኋላ መሳቅ ጀመሩ።

የቤዛዊት እህት ተመልሳ ወደ ፍፁም እና ቤዛዊት ተጠጋች
ልብ አላሏትም ሁለቱም የሞቀ ጨዋታ ላይ ናቸዉ
እስከ አሁን ይነግራታል ብላ በማሰብ
"እግርህ አሁን ለዉጥ አለዉ..."
ወሬያቸዉን አቋርጠዉ ተመለከቷት
"ጥሩ ነዉ ለዉጥ አለዉ "
አላት እና ፈገግ አለ ቤዛዊት ባትኖር መዉደቁ እንደ ነበር
እያስታወሰ የቤዛዊት እህትም ፊቱ ላይ ፈገግታ ስታይ ሳቀች
ፈገግታዋ ከቤዛዊት ጋር ይመሳሰላል ፍፁም ተገርሞ አያት በልቡ
"ቁጭ ቤዛዊትን" እያለ
ቤዛዊት የእህቷን አሳሳቅ አልወደደችዉም ደስ አላላትም
ዉስጧ ንዴት እየተቀጣጠለ ነዉ ህመሟ መንስኤ ነዉ የሚፈልገዉ
በተለይ የፍፁምንም እህቷን እያየ መሳቁን ስታይ
"እገላታለሁ"
ስትል በታመዉ ህሊናዋ እህቷ ላይ ዛተች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍5
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...ወደ ሆስፒታል ገሰገሰች ፍፁም የህክምና ሰወች ተረባርበዉ ትንሽ ነብሱ መለስ አለች ህመሙን የሚቀንስ መድሀኒት ተሰጥቶት ከዋጠ በኋላ ከትራሱ ጋር ድጋሜ ጭንቅላቱን አገናኘዉ እንደ ህመም ከባድ ወቅት የለም በጤነኝነት ስንኖር ዋጋ ሰጥተን ባናስበዉም ስንታመም እና ስቃይ ዉስጥ ስንሆን ግን ሁሉ ነገራችን ተወስዶ ጤናችን ቢመለስ እንለምናለን…»
#አንቺ_እና_እኔ

#አንቺ
“ጠፊ አላፊ ናቸው ጥላቻና ውበት
ግና ግና
ሕያው ሆኖ ኗሪ ምንግዜም ባለበት
ገንዘብ ማይረታው
ሁኔታ ማይፈታው
ሥፍራ ማይቀይረው ዕድሜ ማይጫጫነው
ፅኑ አምድ በዓለም በፍቅር ማመን ነው፡፡”

#እኔ

ስትዪኝ አምኜ
“ገዳሜ ነሽ ብዬ ባንቺ ሥር መንኜ
እንደጥላሽ ሆኜ
ስትሔጅ ስከትልሽ
አልቅስ አልቅስ ሲለኝ ደስ ደስ ሲልሽ
እንደሰው ኖርሽብኝ፤ እንደሰው ኖርኩልሽ፡፡
አንቺ- እንቆልልህ!.. እኔ - ምናውቅልሽ!..

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ባዶነት

ለሥጋዬ ሳልኖር ወይ ሳልኖር ለነፍሴ
ወይ ካንቺ ጋር ሳልሆን ወይ ሳልሆን ከራሴ
ቅዱስ የነበረው እረክሶ መንፈሴ
በስሜት ናውዤ እንደው ስንጀላጀል
በንፁህ ፍቅር ስም የፈፀምኩት ወንጀል፧
ክብረ-ሕሊናዬን ፅናቴን ቢቀማኝ
ማንነቴ ጠፋኝ
ባዶዬን ቀርቼ ባዶነት ተሰማኝ፡፡

🔘ፈሲል ተካልኝ🔘
19/01 /2000
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በክፍለማርያም

...እህቷ ላይ ዛተች
ፍፁም ቤዛዊት አድራ ልታስታምመዉ ፍቃደኛ ሆና አልሄድም
ከአንተ ጋር አድራለሁ ብላ እህቷን ስታስቸግራት
የእሷንም ሁኔታ ስለሚረዳት ደህና እንደሆነ እና ምን
የሚያስፈልገዉ ነገር እንደሌለ ነግሯት
ከእህቷ ጋር ወደ ቤቷ ሄዳ እንድታርፍ አደረገ።

ቤዛዊት እና ታላቅ እህቷ ወደ ቤት ለመሄድ ከሆስፒታሉ ወጥተዉ
ታክሲ እየጠበቁ ቤዛዊት እህቷን በግልምጫ እያየቻት
"ፍፁምን እያየሽ ለምንድን ነዉ የሳቅሽዉ
ፍፁም ማለት የኔ ብቻ ነዉ አታዉቂም?"
ቆጣ ብላ ጠየቀቻት
"ቤዚ ደሞ መቀናቱ ነዉ ..."
ለፍፁም ምንም አይነት ስሜት የሌላት እህቷ ፈገግ እያለች
እየመለሰችላት ታክሲ ዉስጥ ገብተዉ ጎን ለጎን ተቀመጡ
"ሁለተኛ ከእሱ ጋር እንዳላይሽ"
ምን ሆና ነዉ እያለች ታላቅ እህቷ ቤዛዊትን ሰረቅ አርጋ አየቻት
አይኗ ድፍርስ ብሏል በአጠቃላይ በፊት የምታዉቃት ታናሿ
የደስደስ ያላት ሁሌ ፈገግታ ከፊቷ የማይጠፋዉ እህቷ
ስላልመሰለቻት እና የጠፋች ሰሞን ጥሩ ሁኔታ ላታሳልፍ
ስለምትችል ነዉ የምትነጫነጭብኝ ብላ ለይምሰል

"እሺ"

የሚል መልስ መለሰችላት።
ቤታቸዉ ሲደርሱ ሳሎን ዉስጥ አባት እና እናታቸዉ
ከእንግዳ ጋር ተቀምጠዉ ደረሱ
እህቷ ፈጠን ፈጠን እያለች ተራምዳ እንግዳዉን ሰዉዬ ደመቅ ያለ
ሰላምታ ሰጥታዉ አጠገቡ ተቀመጠች
ቤዛዊት ወደ መኝታ ክፍሏ ለመሄድ ስትሞክር
አባቷ አብራቸዉ እንድትቀመጥ አዘዟት።
እንግዳዉን አይን አይኑን እያየች ተቀመጠች
አሁን ደሞ ምን ሊሉኝ ነዉ በሚል ስሜት ተዉጣ
"ተዋወቂዉ"
አሏት አባቷ ልጃቸዉ ቤዛዊት እያዩ ፈገግታ ፊታቸዉ ላይ ጨምረዉ
በተቀመጠችበት ትንሽ ተንጠራርታ እጇን ዘረጋች

"ቤዛዊት.."

"ዶክተር መለሰ"

ቤዛዊት ያምሻል ያምሻል ሁሌ ስለሚሏት እስዋ ግን የዉሸት
የሚሏት ስለሚመስላት በዶክተር ስም ሊያስጨንቁኝ ነዉ በሚል
አባቷ እና እናቷ ላይ ለመጮህ አፏን ስታሞጠሙጥ
ዶክተር መለሰ ኮስተር ብሎ
"የእህትሽ የወደፊት ባል ነኝ"
የሚል ቃል ጨመረበት
ልትሳደብ የነበረዉን እረስታዉ
"መች ልትጋቡ ነዉ"
ደስ እያላት አንዴ እህቷን አንዴ ዶክተሩን እያየች
"ቀን አልቆረጥንም ሙያዋ ጥሩ ነዉ ፀባይዋ ስላስቸገረኝ
ለቤተሰቦቿ ቅሬታ ላቀርብ ነዉ ዛሬም የመጣሁት"
ያዘነ መስሎ የቤዛዊትን የፊት እንቅስቃሴ እያጠና
"ፀባይዋ እማ ቆንጆ ነዉ ልክ እንደ እኔ"
ብላ ስትስቅ
ሁሉም ተከትለዋት ሳቁ

እህቷ ፍፁም እና ቤዛዊት እንዲያወሩ ሆስፒታል ዉስጥ ጥላቸዉ
ወጣ ስትል ስለ ቤዛዊት አዲስ ዶክተር መረጃ አባቷ በስልክ ነግረዋታል ቤዛዊትን የሚቀርባት እንደ ሀኪም ሳይሆን እንደ አንቺ የፍቅር ጉዋደኛ ነዉ ብለዉ ነግረዋት ነበር።

ዶክተር መለሰ ከነ ቤዛዊት ቤት ከመዉጣቱ በፊት ቤዛዊትን
ለብቻዋ አጊንቷት
"የሁለታችን ሚስጥር አርገሽ ያዢዉ
ስለ እህትሽ አንዳንድ መጥፎ በሀሪያት እነግርሻለሁ አንቺም
በሀሪዋ እንዲስተካከል ትረጂኛለሽ
ቃል ግቢልኝ"
"እሺ"
እያለች የዘረጋዉን እጅ ለመሀላ መትታዉ ወደ ክፍሏ ለመተኛት ገባች።

ፍፁም የነጋ ሳይመስለዉ ሰዓቱ መንጎዱ የገባዉ ከእንቅልፉ
ሳይነቃ ምሳ ሰአት መድረሱን ሲመለከት ነዉ አልጋ እና እንቅልፍ ላይ አብዛኛዉ ሰአት እንደሚያልፍም ዛሬ
ተገለጠለት በህልሙ የሚያስፈራ ነገር ቢያይም ከነቃ በኋላ
ለማስታወስ ሲሞክር ስለጠፋበት በመኪና መገጨት የመርሳት
ችግር ያመጣል እንዴ?
እራሱን ጠየቀ ለመርሳት እና ላለመርሳቱ ማረጋገጫ ሲፈልግ
ቤዛዊት ቦርሳዋን በጀርባዋ አዝላ ፀጉሯ ትከሻዋ ላይ ተነጥፎ
የማያባራ ሳቅ እየሳቀች ፊት ለፊቱ ቆማ በቀኝ አይኗ ስትጠቀሰዉ
አሰበ ጤነኛ መሆኑን ስላረጋገጠ ደስ አለዉ ጭንቅላቱ
እንዳልተጎዳ እያሰበ በዛዉ ፊቱ አካባቢ ያሉትን ቁስሎች ዳበሳቸዉ
ህመም አይሰማዉም ደርቀዉለታልም ዛሬን ቀን ከህመም ስሜት
የነፃ እንደሚሆንለት ተስፋ እያረገ ቤዛዊት እየሳቀች መጥታ
ጉንጩን ልትስመዉ ስትሞክር ተጋጩ
"ቀስ ከመኪና ስተርፍ በቴስታ ልትገይኝ ነዉ"
አላመመዉም ለመቀለድ አሰቦ ነዉ
"ዉይ ይቅርታ አላየሀኝም ስመጣ እንዴ?"
በራሱ ሀሳብ ዉስጥ ሆኖ ልብ አላላትም ነበር።

"እራሴ ሰርቼ ያመጣሁልህ ምግብ"
ልታጎርሰዉ መጠቅለል ጀመረች
ዛሬ ጤነኝነት እየተሰማዉ ስለሆነ ሲዘጋዉ የነበረዉ የምግብ ስሜቱ ዛሬ ተከፍቷል የመጀመርያ ጉርሻዋን ጎረሰ
"ምግቡ በጣም ይጣፍጣል ጉርሻዋ ግን በጣም አነሰች"
ምላሱ ላይ ቁጭ ያረገችዉን እየዋጠ
"እንደዉም እራስክ ጉረስ"ስትለዉ እየሳቀ በእሷ እጅ መጉረሱን
ቀጠለ።
በመሀል የቤዛዊት ስልክ ጠራ
"ቤዛዊት?"
"ነኝ"
አንገቷንም እየነቀነቀች
"ዶክተር መለሰ ነኝ ዛሬ ላግኝሽ?"
እሺ ልበለዉ እንቢ በሚለዉ ሀሳብ አንገራግራ ከፍፁም ጋር አብሮ
ለመዋል
"ዛሬ አይመቸኝም ሌላ ግዜ"ብላዉ ስልኩ ተዘጋ።
ከፍፁም ጋር መቼ ከሆስፒታል እንደሚወጣ ስለ ወደፊት እቅዳቸዉ
እየተመካከሩ ከፊት ለፊታቸዉ ከሚታከመዉ ታማሚ ፊት ለፊት ዶክተር መለሰ ነጭ ገዋን አርጎ ስላየችዉ ደንግጣ እንዳያያት
ፊቷን ተሸፋፈነች ዶከተሩም አይቷት እንዳላየ ወጣ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በክፍለማርያም

...አይቷት እነዳላያት አለፈ
ፍፁም መደባበቋን ሲያይ ማንን እንዳየች ለማወቅ ጠየቃት
"የእህቴ ባል ነዉ ...ማለቴ ሊጋቡ ነዉ ዶክተር ነዉ አሁን ሲያልፍ አይቼዉ ነዉ"
ስለነገረችዉ ደስ አላት እህቷ ከፍፁም ጋር ስትስቅ የያዘችባት
ቂም ከሆዶ ስላልወጣ እህቷ ባል እንዳላት በአቆራጭ እየነገረችዉ ነበር።

እህቷ ከወትሮ በተለየ ተኳኩላ አዲስ የተገዛ ቀሚስ ለብሳ በእጆ
ለፍፁም የሚበላ እና የሚጠጣ ነገር ይዛለት ቤዛዊት እና ፍፁም
ጋር ደርሳ ቆመች ቤዛዊት ትመጣለች ብላ ስላላሰበች በአግራሞት
እና በጥርጣሬ እያየቻት መቀባባቷን እና መዘነጦን በክፋት ተመልክታዉ
"ለምን መጣሽ?ማለት እንዴት መጣሽ"
አለቻት እህቷ ገና ሰላምታ ሰጥታቸዉ ያመጣችዉን እቃ እያስቀመጠች
"አረ እንደዚህ አይባልም ቤዚ"
ፍፁም በመጠኑ ፈገግ እያለና እጆቹን ለሰላምታ ወደ እህቷ እየሰደደ
"ዶክተር መለሰ እዚህ ነዉ የሚሰራዉ እጮኛዬ
እሱን ለማግኘት መጥቼ
እግረ መንገዴን ፍፁምንም ልጠይቀዉ ብዬ ነዉ"
የቤዛዊትን መቀያየር ተመልክታ ግራ እየተጋባች።

ቤዛዊት በሀሳብ ጥላቸዉ ሄዳለች
የሆነ ነገር ያለ መሰላት እህቷ ዶክተሩ እሱን እያብሰለሰለች ፍፁም
እና እህቷ ግንኙነት ያላቸዉም መሰላት እሶ ምን ያክል ቀን እማማ
ስንቅነሽ ጋርም እንደቆየች ስላልታወሳት በመሀል እህቷ ከፍፁም ጋር የጀመረችዉ ነገር እንዳለ የእዉነት መስሏት
እህቷን የእዉነት እየጠላቻት ለመግደል አስባ የነበረዉን አርጊዉ
አጥፊያት ግደያት የሚል የአይምሮዋ የህመም ስሜት እየመከራት።

ህመሞ መንስኤ ይፈልጋል አይምሮዋን ተቆጣጥሮት
እሱ ለማዘዝ የሚፈልገዉ ጥቂት ሀሳቧን የሚገዛ ሀሳብ ሲያገኝ
ሲጀምራት እራሷን በከፊል ታዉቃለች አይኖ መፍዘዝ መደፍረስ
ይጀምራል ደማቁ ፈገግታ የማይጠፋዉ ፊቷ ይደበዝዛል ፅልመት
ይዉጣታል ትለዋወጣለች ሙሉ ለሙሉ ሲቆጣጠራት እራሷን
አታዉቅም የምታረገዉ የሚሆነዉ በሙሉ ከሷ ቁጥጥር ዉጪ ነዉ።

ፍፁም እና እህቷ ሲነጋገሩ ቆይተዉ ዝም ያለችዉን ቤዛዊት
ማዋራት ጀመሩ ነገር ግን እየሰማቻቸዉ አልነበረም
ፍፁም የተቀያየረዉን ፊቷን በፍቅር አስተያየት እያየ
"ምን ነዉ የሆንሽዉ ነገር አለ?"
"ምንም አልሆንኩም"
ንግግሯ ዉስጥ የተደበቀ የሌላ ሰዉ ድምፅ ያለ ይመስል
ተለዋዉጦ
የቤዛዊት እህት ዶክተር መለሰን ደዉላ ጠራችዉ መጀመርያ
ቤዛዊት የነበረችበትን ቦታ ስላየዉ በፍጥነት ከተፍ አለ ሰላምታ
ተለዋዉጠዉ ፍፁም አጠገብ እያበረታታዉ ቆሞ የቤዛዊትን ፊት
በአትኩሮት ያጠናል የሆነ የሆነችዉ ነገር እንዳለ ስለተሰማዉ።

ለማረጋገጥ ሞከረ
አይኗ እህቷ ላይ አልነቀል ስላለዉ በእህቷ መናደዷ ገባዉ በምን ምክንያት?
ሁለተኛዉ መልስ ያላገኘለት ጥያቄ
ፍፁም በሰዉ መከበቡ ደስታ ፈጥሮለት ባይተዋርነኝ ብሎ
ያሰበዉን እረስቷ እያወራ እና እየተጫወተ ነዉ ህመሙን እረስቷ
ቤዛዊት ከዶክተር መለሰ ዉጪ ልብ ያላት ባይኖርም በህመሟ
ተመርታ የክፋት ሀሳብ እያመነጨች ነዉ
እህቷ ለፍፁም ያመጣችለትን ጭማቂ የፔርሙስ ክዳን ፈልጋ
ለፍፁም ስትሰጠዉ ተቀምጣ የነበረችዉ ቤዛዊት በድንገት
ፍንጥር ብላ ተነስታ
"እግዜር ይማርህ"
ምፀት ያዘለ ቃል ተናግራ ቦርሳዋን ማዘል ስትችል እየጎተተችዉ
ወጣች ፍፁም ግራ ተጋብቶ የሚያወራትን ሳትሰማ እህቷ ምን እንደሆነች ለማወቅ ስትከተላት ዶክተር መለሰ እንዳትሄድ
ካስቆማት በኋላ እሱ እየሮጠ ከሆስፒታሉ በመዉጣት ላይ ያለችዉ
ቤዛዊት ጋር ደረሰ።
ጥቂት አብሯት ከተጓዘ በኋላ
"ፍቅረኛዮ ማለትም እህትሽ ከኔ ሌላ ሌላ ወንድ ሳትጀምር አትቀርም..."
የምትመልስለት ስላልመሰለዉ ሌላ ቃላት ሊጨምር ሲል
"አዉቄዋለሁ ኪኪኪ ኪኪ ኪኪ"
እየሳቀች መራመዷን አቁማ የዶክተሩን ፊት እያየች
በመነፅር ከተደበቁት አይኖቹ ዉስጥ እንደሷ የተከዳ ሰዉ ያየች
ይመስል
"ፍፁም እና እህቴ"
እህቴ የሚለዉን ቃል ጠበቅ አርጋ ስታወራ
እንድትረጋጋ ትከሻዋን እየነካ
"አብረን እናጣራ እዉነት መሆኑን እና አለመሆኑን እርግጠኛ
ላንሆን እንችላለን"
ለመቀራረብ እንዲረዳዉ ድጋሜ ተዋወቃት
"መለሰ"
ብለሽ ጥሪኝ ዶክተር የሚባለዉ አያስፈልግም
እየሳቀች መስማማቷን ገለፀችለት
ትንሽ መረጋጋት እንደታየባት ሲያዉቅ ሻይ ቡና እያሉ እንዲያወሩ
ቢጠይቃትም አሁንም ለሌላ ቀን ቀጥራዉ ጉዋደኛ ለመሆን
ተስማምተዉ ተለያዩ።
ምሽቱን አልጋዋ ላይ ሆና እቅዷን እንዴት ማሳካት እንዳለባት
ማሰብ ጀመረች እህቷን መግደል እያሰበች መሆኗን በጤናማ
አይምሮዋ ስታስብ ደግሞ ማሰቧ ፀፀት ተሰማት ነገር ግን ከፊሉ
አይምሮዋ እቅዱን ለማስፈፀም እየሞከረ ነዉ።
ለሊት ታላቅ እህቷ እንቅልፍ አልወስድሽ ስላላት አልጋዋ ላይ
ስትገላበጥ የመኝታ ክፍሏ በር ድምፅ እያመሳ ሲከፈት የሰማች
መስሏት ደንግጣ መብራት አበራች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
2
#የቃል_ቅሌት

ከሚሊዮናት ውስጥ
የቅርብ ዘመድ ጠፍቶ
አንድ ረዳት አጥቶ
ጠባብ ኩሽና ውስጥ
ቢገኝ አንድ አዛውንት
ደርቆ ተኮራምቶ
ከዚህ ዓለም ጣጣ
በሞት ተለያይቶ
በስላም “አረፈ”
“ተገላገለ” እንጂ
እንዴት “ሞተ” ይባላል?!?

ቃል”ም እንደሰው ልጅ
ለካ እንዲህ ይቀላል!!

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#የከርሠ_ምድር_ሰው

በምድር ላይ ሳለሁ
በጀርባ እማይበት ሦስተኛ ዓይን የለኝ
ማን እንደሁ አላወኩም ግፍትሮ የጣለኝ
አሁን ገደል ሥር ነኝ፡፡
እጄን አልሰጠሁም ለመውጣት ሞከርኩኝ
ግድግዳ ቧጠጥኩኝ
እምይዘው አጥቼ የንግልል ወደቅኩኝ፡፡
ተነሳሁ ዳከርኩኝ
ደጋግሜ ጣርኩኝ
ለመውጣት አልቻልኩም ሞክሬ ተሳነኝ
ያለሰው ብቻዬን ብዙ ጊዜ ሆነኝ
ከከርሠ ምድር ውስጥ አሁን ግደል ሥር ነኝ፡፡
የግራና የቀኝ
ግድግዳዎች በቀር ከገደሉ በላይ ፤
ከሩቅ ይታየኛል ተስፋዬ ሰማይ ላይ፡፡
የመውጣቴ ተስፋ
ከውስጤ ሲጠፋ
ላዬ ላይ “ሚወርደው አንዳንዴ እንደግርሻ፤
ተስፋ ይዘራብኛል የሰዎች ቆሻሻ፡፡
ተስፋዬ እንዳይጠፋ
ጭራሽ እንዳይመክን ሰዎቹ ሲጠፉ ፤
እናፍቅ ጀመረ ቆሻሻ እንዲደፉ፡፡
አወጣ አወርዳለሁ
እንደዚህ አስባለሁ፡፡
“ገደል ሥር አዳሪ ቆሻሻ አላሚ
ሆኜ እቀር ይሆን?
ወይስ ያዩኝ ይሆን? ሰዎች በአጋጣሚ፡፡
“አፋልጉኝ" የሚል ስው አንድም እንኳ የለም?
ወይስ ተለይቶ
የእኔ ከዓይን መጥፋት አሳሳቢ አይደለም?
አስጨናቂ አልሆነም ?
ከቢሊዮናት መሐል የእኔ ቁጥር መጉደል፤
ራሴን እማይበት
መስታወት ሆኖኛል የገፊዎች በደል፤
ለካስ ኢምንት ነኝ!
ለዓለም እማላጉል እማልሞላ ጎደል፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#በአንድ_ሰውነት_ውስጥ

ከልቤ መንጭቶ ደም በሥራ ስሬ ሥርዓት ይዞ ሲፈስ
ሳምባዬ ሲያስችለኝ ንፁህ አየር መተንፈስ
መላው አካላቴ ሥራውን ሲሰራ ያላንዳች መኮፈስ
አብሮ በአንድነት በቀናነት መንፈስ፣
“ነፍሴ” እየታመመ "ሥጋዬ" ሲገዳ
“ሥጋዬ” ሲቆሽሽ ነፍሴ” ስትፀዳ
አንዳንዴ ጊዜ “ነፍሴ ሆኖ የማይረዳ ፣
አንዱ ባንድ ነገር
መላ አጥቶ ሲቸገር
ትርምስምስ ተፈጥሮ
እርስ በርስ መግባቢያ ቋንቋ ሲጠፋበት
“ነፍሴ ለ “ሥጋዬ” አዲስ ሲሆንበት ፣
ለነፍሴም ሲታየው “ሥጋዬ እንደ እንግዳ
እኔው አንዱ ሰውዬ ሳልሰነዳዳ
ለገዛው እራሴ ባንድ ግዜ እሆናለሁ ዘመድና ባዳ፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#እፍቅር_መዳፍ_ውስጥ

አበው ቀድመው ሲሉ “የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ።"
እኔ ችላ ብዬ ምክር እማልሰማ ሆኜ ማልጠንቀቅ
አጉል እምራቀቅ፤
“ሀገር” ማለት “ፍቅር”
“ፍቅር” ማለት ሀገር መሆኑን ዘንግቼ
ምሥጢሩ እረቆብኝ ትርጉሙን አጥቼ
ቀልቤን አጥቼያለሁ ቀልቤን ተሰርቄ
ልበቢስ ሆኜያለሁ ልቤን ተነጥቄ፡፡
ይኸው ብሶብኛል
እፍቅር መዳፍ ውስጥ በሰው ልጅ ወድቄ እንፈራገጣለሁ ፤
ደግሞ ለመላላጥ ሰው እናፍቃለሁ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በክፍለማርያም

...ደንግጣ መብራት አበራች
እህቷ በተኛችበት አንገቷን በመጠኑ ቀና አርጋ
ወደ መኝታ ክፍሏ በር ተመለከተች ገርበብ ብሎ ተከፍቷል
አንገቷን ስለከበዳት ተመልሳ ትራሷን እተደገፈች እራሷን ጠየቀች

"ማን ከፈተዉ?"

ማታ ስትተኛ ዘግታዉ እንደነበር ስታስታዉስ ደንግጣ ተነስታ
እየተቀመጠች በመዝጋቷ እርግጠኛ ሆና ማን ከፍቷት ይሆን?
አለች በግርምት አባቷ ቤት ማደር አለማደሯን ሊያረጋግጡ
ከፍተዉ ያዩዋት እየመሰላት
አስራዉ የተኛችዉን ሻሽ መዉለቁን አስተዉላ ከትራስዋ ላይ
አንስታ ፀጉሯን ለመሸፈን ጭንቅላቷ ላይ እያሰረች በቀስታ
ከአልጋዋ ወርዳ ወደ በሯ ተጠጋች
የበሩን እጀታ ይዛ ወደ ዉጪ ስትመለከት ምንም የለም
ፀጥ ረጭ ያለ ድባብ ያለዉ ኮሪደር ጥቂት ድምፅ ለመስማት
ጆሮወቿን ቀስራ ቆይታ ድምፅ ስላልሰማች ተረጋግታ በርዋን
መልሳ ዘግታ ወደ መኝታዋ አመራች።

/ከደቂቃወች በፊት/

ቤዛዊት በለሊት ማን እንደቀሰቀሳት ባታዉቅም የቀሰቀሳት የሆነ
ሀይል አለ እህቷን እንድትገላት ፈልጎ የሚወተዉታት
"ፍፁምን ቀማችሽ"
"እህትሽ ግን አትገርምም እንዴት አንቺን ታስከፋሻለች"
ተመሳሳይነት ያላቸዉ ወቀሳወች
በእህቷ ላይ ተስፋ እንድትቆርጥ የሚያረጉ ሀሳቦች
ገሚሱን እያወቀች ገሚሱን በደመነብስ ሆና በተኛችበት ስስ ልብስ ለእግሯቿ ጫማ ሳያስፈልጋት በባዷ እግሯ
እልህ እና ንዴት ወኔ እየሰጣት ወደ እህቷ ክፍል የእጇን ጥፍር እየበላች ተጓዘች ።

ደርሳ በሩን ከፍታ ወደ ዉስጥ እየገባች በምን ልትገላት
እንደመጣች አይምሮዋ ስለጠየቃት ጥፍሮቿን መብላት አቁማ
ወድያዉ ለመግደያ የሚያገለግላት እቃ ፍለጋ ወደ ማዕድ ቤት አመራች።
ማዕድ ቤቱ ዉስጥ ስትገባ መጀመርያ አይኗ ዉስጥ የገባዉ
ከዚህ በፊት እራሷን ለማጥፋት የሞከረችበት ስለት ያለዉ ቢለዋ
ላይ ነበር
ፈገግ እያለች በቀስታ እና በፍቅር አነሳችዉ
በቀኝ እጇ ይዛዉ ስለቱን ለመረጋገጥ በግራ እጇ የወፍራሙ ጣት
አሻራ ስለቱ ላይ አሳርፋ ለማሸት ስትሞክር ወድያዉ ቆርጧት
ደሞን ስላየችዉ ተደስታ ወደ እህቷ መኝታ ክፍል ስታመራ ከፊት
ለፊት እህቷ አንገቷን ቀስራ በሯ ላይ ቆማ ስታያት መተላለፍያ
ኮሪደሩ ጥግ ጨለማ ዉስጥ ተደበቀች።

/አሁን/

ታላቅ እህቷ በበሯ መከፈት እየተገረመች
የመኝታ ክፍሏን መብራት አጥፍታ ጥቂት አስባ ተኛች።
ከጨለማዉ ዉስጥ አይኗ ብቻ የሚታየዉ የታመመችዉ ቤዛዊት
በለበሰችዉ ስስ ገዋን አልፎ የሚገባዉ ብርድ ሰዉነቷን
እያንዘፈዘፈዉ ቢለዋዉን በተጠንቀቅ ይዛ ፍዝዝ ብላ ቆይታ
በግዳጅ የታዘዘች ይመስል ከተደበቀችበት ወጥታ በፍጥነት
እየተራመደች በድጋሜ የእህቷን በር ከፍታ በጨለማ ዉስጥ አልጋ
ላይ ወደ ተኛችዉ ታላቅ እህቷ አመራች።

ታላቅ እህቷ በሬን ማን ከፈተዉ ብላ አልተጨነቀችም
ምክንያቱም ቤት ዉስጥ ሁሉም ቤተሰቦቿ ናቸዉ ሰራተኛቸዉ
ሳይቀር በዘመድ የመጣች የሩቅ የስጋ ዝምድና ያላት ናት ወድያዉ
ነዉ እንቅልፍ ያሸለባት።
በህይወት አምነነዉ አብሮን እንደሚያድር ሰዉ መልካም ወዳጅ
የለንም ምክንያቱም ከእንቅልፍ እስክንነቃ የእሱ ምርከኞችም ነን
አብረን ለማደር ስንፈራራም ነዉ ጦርነት እና ዉግያ የሚጀምረዉ።

ሰራተኛቸዉ ከማዕድ ቤት እቃ ሲንኳሻኮሽ ስትሰማ የነጋስለመሰላት "ዉይ መች ተኝቼ ነዉ የነጋዉ"
በሚል ስሜት እየተጨናበሰች ተነስታ ወደ ዉጪ ስትወጣ
ጨለማዉ ገና አልገፈፈም
"ተመስገን"
አለች ተመልሳ መተኛቷን ስታስብ
ከመተኛቷ በፊት የሰማችዉን ለማረጋገጥ ወደ ማዕድ ቤት ስትገባ
ከቤዛዊት አዉራ ጣት የፈሰሰዉን ደም ስታይ እየደነገጠችም
የማን እንደሆነም ለማረጋገጥ የደሙን ጠብታ ተከትላ ስትመለከት
ወደ እነ ቤዛዊት እና እህቷ መኝታ ቤት ስለሚጠቁም ፈራ ተባ
እያለች መከተል ጀመረች በየአንዳንዱ እርምጃዋ ያገኘችዉ
ማብራት እያበራች።

ቤዛዊት የእህቷን መኝታ ክፍል ድጋሜ ከፍታ ወደ ዉስጥ ዘለቀች
እህቷ ሀገር አማን ብላ አልጋዋ ላይ ተንሰራፍታ ተኝታለች
ተሸፋፍናዉ የነበረዉ ብርድ ልብስ ስትገላበጥ በከፊል ተገልጦ
ከወገቧ በላይ አካሏ ይታያል ቤዛዊት ቢለዋ በያዘ እጇ በአፏ
በቀስታ እያወራች
"አገኘሁሽ!"
እያለች ተጠግታት ታላቅ እህቷን ፊት አየችዉ
የቤዛዊት እህት በህልሟ ምን እያየች እንደሆነ ባይታወቅም
ጥሩ ነገር እንደሆነ የፊቷ እንቅስቃሴ ይመሰክራል
በተኛችበት ከንፈሮቿ አሞጥሙጠዉ ከጉንጮቿ እንቅስቃሴ ጋር
አፍዋ ዉስጥ ያለዉን ምራቅ አጣጥማ እየዋጠች ነበር።

"አንቺ ይሄኔ ፍፁምን እያለምሽዉ ነዉ!"
አለች ቤዛዊት በህመም ስሜት ቢለዋዉን ከፍ አድርጋ በእህቷ
ግንባር ትይዩ እያረገችዉ።
ታላቅ እህቷ በተኛችበት ግንባሯ ላይ ቀዝቃዛ ነገር ሲያርፍባት
ላለመነሳት እየታገለች ገርበብ አርጋ አይኗን ገለጠች
እህቷን በማየቷ ተገርማ አይኗን ሙሉ ለሙሉ ስትገልጥ
የቤዛዊት ፊት ተለዋዉጦ በቢለዋ ልትወጋት እንደተዘጋጀች
ስታይ በተኛችበት ዉሀ ሆነች።

መነሳት መንቀሳቀስ አቃታት እህቴ ብላ መጥራት መለመን
ብትፈልግም አፍዋን መክፈት አልቻለችም ያላት የቻለችዉ
የመጨረሻ አቅም ግን ማንባት ነበር
ድምፅ አልባ እንባወች
ለትራሷ ቀለብ ሆኑ ምቿት ያለዉ ትራስ በእንባወቿ እርሶ በቃኝ ይላል።

ቤዛዊት የምታለቅሰዉን እህቷን ስታይ እንዳሰበችዉ ቢለዋዉን
የእህቷ አካል ዉስጥ ልትሰካዉ አቅመ አነሳት እያንገራገረች እና
ጥርሷን እያፏጨች
ሰራተኛቸዉ ከኋላ ደርሳ ቤዛዊትን እያየች
"አረ ኡ አረ ጌቶች ድረሱ ኡ ኡ ኡ"
የሚል ጩሀት ስትሰማ ቢለዋዉን መሬት ላይ ጥላዉ ወደ እራሷ አይምሮ ተመለሰች የት እንዳለች ለማረጋገ
እየሞከረች ዲዳ ሆና ደርቃ በፈዘዘ አይን የምታያትን ታላቅ እህቷን ግራ ገብቷት እያየች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በክፍለማርያም

...ደንግጣ እያየቻት
ቤዛዊት ወደ እራሷ ተመልሳለች የያዘችዉን ቢለዋ ጥላዉ
እጇን እንደቆረጨችዉ የታወቃት አሁን ነዉ የቁስሉ ጥዝጣዜ ዉስጦ ድረስ ዘልቆ ስለተሰማት እህቷን ልትገላት መሆኑ ግልፅ
ስለሆነላት ተፀፀተች ግን ምን ታርግ እያሰበች እንደነበረ እንጂ
የእዉነት አርጋዉ እህቷ ክፍል ድረስ ለመግደል እንዴት
እንደመጣች ግራ እየተጋባች እህቷን ላለማየት እያፈረች
እናት እና አባቷ በሰራተኛዋ ጩሀት ተደናግጠዉ ወደ ክፍሉ ሲገቡ አልጋ ላይ በድንጋጤ ዉሀ የሆነችዉ ታላቅ
እህቷ ድምፅ አዉጥታ ሲቃ እየተናነቃት ማልቀስ ጀመረች።

አምቃ የነበረዉን በትራስ የተደበቀዉን
ሀዘኗን ማሰማት ተያያዘችዉ የወለዷትን ቤተሰቦቿን ስታይ ቤዛዊትን እንደቤተሰቧ ለመቁጠር ስላልቻለች በፍርሀት ተዉጣ
አይኖቿን በሰቀቀን ከወድያ ወዲህ እያንከዋለለች
ታላቅ እህቷ ታናሽ እህቷ ቤዛዊት ስትሰድባት ስታንጓጥጣት
ህመሟ ነዉ ወዳ አደለም በማለት ታግሳታለች ብዙ በደል ብትበድላትም አይታ ባላየም አልፋታለችም
ቤዛዊት ሰዉ ፊት እህቷን ብዙ ግዜ አዋርዳታለች
የዛሬ አመት ገደማ ቤዛዊት እንደተለመደዉ አሟት
ከትምህርት ቤት ለታላቅ እህቷ ተደወለላት
እህቷ ናትና ስራዋን ትታ ደንግጣ ከመስርያ ቤቷ
ስትወጣ ያረገችዉ ጫማ ስላልተመቻት ተደናቅፋ ወደቀች
እግሯን ክፉኛ ተመታ እስካሁን የሚያሰቃያት ህመም ያዘች
ጉልበቷ እና እጆቿ ተጋግጦ ህመሞን ችላ
ለቤዛዊት ለመድረስ ወደ ትምህርት ቤቱ እየከነፈች እንደገባች
ቤዛዊት በስድብ ተቀበለቻት
በአስተማሪወች እና በተማሪወች ፊት የቤት ዉስጥ
ገመናዋን ሳይቀር ዘረገፈችባት እንደምንም ታግሳ ግን ሆስፒታል
ወስዳት ነበር ብቸኛዋ ታናሽ እህቴ ብላ ፍቅሯ ተናገረችኝ በሚል
ተልካሻ ምክንያት ሳይቀንስ
ያ ሁሉ መስዋትነቷ ተረስቶ ግን
ያቺ የምትራራላት ታናሽ እህቷ ልትገላት አስባ ቢለዋ በእጇቿ
ጨብጣ እንቅልፍ በወሰዳት በአሳቻ ስዓት መኝታ ክፍሏ ገብታ
ስላየቻት አዝናለች ደንግጣለች ልቧም ተሰብሯል
እየፈራቻትም ነዉ ለህይወቷም ያሰጋታላ
የቤዛዊት አባት እየተደናገጡ ከላይ እርቃናቸዉን ሆነዉ
ከስር በለበሱት ከሰዉነታቸዉ በሰፋ ቁምጣ እየተራመዱ
በደፈረሰዉ አይናቸዉ ሁለቱንም ልጇቻቸዉን እያዩ ደርቃ
እየተንቀጠቀጠቀጠች የቆመችዉን ቤዛዊት አቅፈዋት ወደ ሳሎን
አመሩ ግራ የተጋቡት እናታቸዉ አልጋ ላይ በድን ሆና ወደ ምትነፋረቀዉ
የመጀመርያ ልጃቸዉ ተጠግተዉ እያቀፉዋት ማባበል ጀመሩ
"አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ"
የማይቆመዉን እንባዋን ለማበስ በእጃቸዉ እየሞከሩ
የሚያማት ልጅ ኖሯቸዉ ታመመች ብለዉ መጥላት ባልቻለ
የእናትነት አንጀታቸዉ መሀል ቤት እየተሰቃዩ
"ል እእእ ልትገለኝ እ እ ነበር እእእ እኮ እማ"
የሚያባብሏትን የእናቷን ፍቅር ስታይ ለቅሷዋ እየጨመረ
"አልሞትሽም ልጄ እኔ ልሙት"
እናቷ የልባቸዉን እያወሩ
"እእእ እንዴት ነዉ እ እ ታድያ አብሬያት እ እ እምኖረዉ"
ሳግ እየተናነቃት እያለቀሰች
እናቷ ማሰብ ጀመሩ
በፊት በፊት ቤዛዊት ስትሳደብ ምንም አይመስላቸዉም
ነበር አሁን ግን ሰዉ መግደል ማሰብ ደረጃ አልፋ
በለሌት ልትገላት እንደነበር ሲያስተዉሉ
ገላት ብደርስስ ኖሮ ብለዉ ሲያስቡት
እንባቸዉ ቀደማቸዉ
"አጥቼሽ ነበር አጥቼሽ ነበር"
በማለት እያጉተመተሙ ጠበቅ አርገዉ እያቀፏት
በተቃራኒዉ ቤዛዊትን ምን ሊያረጓት እንደሚችሉ ሲያስቡ
ከጣት እጣት መርጦ መቁረጥ ሆኖባቸዉ ሀዘናቸዉ በዝቶ እየዬ
ማለት ጀመሩ የሚሉ ሄንን ስታይ እሷ ማልቀስ አቁማ እናቷን
ማባበል ጀመረች
በነጋታዉ ቤዛዊት ካደረችበት ሳፋ ወንበር ፀፀት እየገረፋት
ማታ ልታረገዉ በነበረዉ ነገር እያዘነች እህቷን እግሯ ላይ ወድቃ
ይቅርታ ለመጠየቅ
እይኖቿን እያበሰች ስትራመድ እህቷ በሻንጣ
እቃ ይዛ በለቅሶ ብዛት ያበጠ ፊቷን በሻርፕ ተሸፋፍና ልትወጣ
ስትል ፊት ለፊት ተገናኙ
ታላቅ እህቷ ቤዛዊትን ፊቷ ስታያት ደነገጠች
የእዉነትም ያስፈራል
ማታ ሊገልህ የነበረ ሰዉን ተርፈህ ጠዋት ብታገኘዉ
የሚሰማዉ ስሜት ነብስ የማትረፍ የልብ ድንጋጤ እና ትርታ
"ይቅርታ እህቴ ይቅርታ ምንም የማዉቀዉ ነገር አልነበረም"
ቤዛዊት ልመና ጀመረች
እህቷ ግን ልትሰማት ዝግጁ አልነበረችም በእልህ እንድታሳልፋት
ሳትጠይቃት ገፍትራት ቤቱን ለቃ ወጣች።

ፍፁም እያገገመ ነዉ ዊልቸሩን ትቶ በክራንች መንቀሳቀስ ጀምሯል
የሆስፒታሉ ዶክተሮችም መዉጣት እንደሚችል ነግረዉታል
እራሱን እየተንከባከበ እንደሚሻለዉ አዉቋል
በእግሩ መራመድ አለመቻሉን ሲያስብ እና ሲጨነቅ የነበረዉ
ፈጣሪን ማማረሩ አሁን ክራንች ይዞ ሲራመድ ገና ሙሉ ለሙሉ
ሳይድን ተፀፀተ
ነገ የተሻለ እንደሚሆን እና ክራንቹንም ጥሎ ለመራመድ
እንደሚችል አምኖ አምላኩን አመሰገነ
የተዘጋ የሚመስል ነገር ሁሉ ጊዜ ጠብቆ ይከፈታል
አበቃ የተባለም ጊዜ ጠብቆ ይጀምራል
ቤዛዊት መጥታ ከጠየቀችዉ ሁለት ቀን ስላለፈ ተጨንቋ ብዙ
ጊዜ ቢደዉልላትም ስልኳ ስላልሰራ ወደ እህቷ ስልክ ደወለ
ጥቂት ሰላምታ ተለዋዉጠዉ ስለቤዛዊት ሲጠይቃት ስሜቷ
ተለዋዉጦ አይቻት አላዉቅም ስላለችዉ በክራንቹ እየታገዘ
የቤዛዊት ሁኔታ ስላሳሰበዉ
ወደ ቤዛዊት ቤት ለመሄድ ከሆስፒታል ወጣ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...ደንግጣ እያየቻት ቤዛዊት ወደ እራሷ ተመልሳለች የያዘችዉን ቢለዋ ጥላዉ እጇን እንደቆረጨችዉ የታወቃት አሁን ነዉ የቁስሉ ጥዝጣዜ ዉስጦ ድረስ ዘልቆ ስለተሰማት እህቷን ልትገላት መሆኑ ግልፅ ስለሆነላት ተፀፀተች ግን ምን ታርግ እያሰበች እንደነበረ እንጂ የእዉነት አርጋዉ እህቷ ክፍል ድረስ ለመግደል እንዴት እንደመጣች ግራ እየተጋባች…»
#እፀድቅ_ብዬ ..

እምላክ ሆነህ ሳለህ
የሰው እግር ስታጥብ ፥ ትህትናን ተምሬ
ስንቱን ባለስልጣን
እግሩን በትህትና ፥ ሳጥበው ዋልኩኝ ዛሬ።
ታዲያ ምን ያደርጋል
የቀን ፅድቅ ስራ
ጉንፋን ራስ ምታት ፥ ባመሻሽ አደለኝ
በስህተት መንገድ ላይ
ብዙ አመት ተጉዘው ፥ መጥተው ነው መሰለኝ!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የወሬኞች_ወሬ

ወሬን ለወሬኛ ትተናል ለሚሉ
ወሬኞች በሙሉ
በወሬ ነገሩን ወሬ እንደሚጠሉ

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ዓሣ_ጐርጓሪ…”

“ፍቅር ይቅር!”
“ይቅር ፍቅር!" ተባባሉ
ሰው እና ውሻ ተጣሉ
ተያያዙ - ሊጣጣሉ?
ሰው - ውሻዉን ጣለ
ውሻ - ከሥር ወደቀ
ማንቁርቱ ተያዘ
በሰው እጅ ታነቀ
ተስፋውን ቆረጠ
ሽንፈቱን አመነ
ወዲያው እጁን ሰጠ::
ሰው አዘነና አሰበ ሊለቀው
ግና ትዝ ሲለው
ጠቡ ከውሻ ነው::
“ከተውኩት አይለቀኝም!” አለና ሰው
ከሥሩ የተኛውን ውሻውን ነከሰው :
ውሻው ተደሰተ ጥርሶቹን አሾለ
አፉን ከፈተና ለሰው እንዲህ አለ::

አመሰግናለሁ!
የረሳሁትን አስታወስከኝ
አኝኝ!”

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#በር_ሥር

ሕይወቴን በሙሉ ያሻኝን ፈልጌ
ፈልጌ ፈልጌ ወርጄ ወጥቼ
የድካሜን ያህል ሳላገኝ ቀርቼ
ዘመኔን ፈጅር ባክኜ ኑሬያለሁ ፤
ኖሬ ተስፋ አልቆርጥም
ብዬ እጅ አልሰጥም ይኸው እታገላለሁ።
ኳ..ኳ...ኳ...ኳ...ኳ...ኳ

መሻቴን ላሟላ ሌት ተቀን ደክማለሁ ፣
ኳ..ኳ...ኳ...ኳ...ኳ...ኳ

ከሰማይ በር ሥር እነሆ አንኳኳለሁ ፤
ኳ..ኳ...ኳ...ኳ...ኳ...ኳ

ሳንኳኳ ሳንኳኳ ዘመናትን ፈጀሁ ፤
የልቤ ሳይሞላ
ሳይከፈትልኝ በር ሥር አረጀሁ።
እስካልሞትኩኝ ድረስ በሕይወት እስካለሁ
እኔ ተስፋ አልቆርጥም በሩን አንኳኳለሁ፡፡
ኳ..ኳ...ኳ...ኳ...ኳ...ኳ

እየዋለ እያደር በሩ ጠነከረ
የልቤ መሻትም ምኞቴም ጨመረ
እጄም ተበራታ ማንኳኳት ቀጠለ
የኳኳታዬ ድምፅ ሲበዛ አየለ፡፡

ኳ..ኳ...ኳ...ኳ...ኳ...ኳ
ጉልበቴ ሲጣምን እጄ አቅሙን ሲያጣ
በውስጤ ታወቀኝ ድካም እንደመጣ፡፡
ከፋቹ እንዲሰማኝ በብርቱ ፈልጌ
በሃይል እጮህ ጀመር ደምፄን ከፍ አርጌ።

ጮኬ ጮኬ ላንቃዬ ተንቃቃ
ጉሮሮዬ ደርቆ ልሳኔ ተዘጋ።
ትዕግስቴ ተሟጦ ተስፋዬን ቆርጬ
ከሰማይ በር ሥር ከፍቶኝ ተቀምጬ
እንዲህ ስል ጠየ-ኩኝ በሐዘን ተውጬ።
“አካሉ የበደ ነው
ጆሮ ዳባ ብሎ አውቆ የተኛው ማነው?
ብርቱ ኃይለኛ ድምፄ የማይቀሰቅሰው። ያ ሁሉ ኳኳታ ፈጥኖ ያልደረሰው ሰማዩ።ውስጥ ያለው ፈጣሪ ነው ወይ ሰው"

እኔ😳

🔘ፋሲሌ ተካልኝ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በክፍለማርያም

...ከሆስፒታል ወጣ
የገጪዉ ሚስት የተወሰነ ገንዘብ ሰጥታዋለች እያነከሰ በክራንች ተጠቅሞ ለመራመድ ቢሞክርም
ሁሉም ነገር ልምድ ስለሚጠይቅ እና በክራንቹ ታግዞ መራመድ
ስላልቻለ ኮንትራት ታክሲ ለመያዝ አስፓልት ዳር ቆሞ መጠበቅ
ጀመረ
መኪና ማግኘት ሳይችል ቀርቶ ጥቂት ስለቆመ ብቻ እግሮቹ
ብርክ ብርክ አሉበት በቆመበት ላለመዉደቅ ሲታገል ከጎኑ
የሰዉ እጅ ስለደገፈዉ ተመልሶ በመከራ ለመቆም ቻለ

"ምን እየጠበቅክ ነዉ ወንድሜ አሞሀል መሰለኝ "

ጥቁር በጥቁር የለበሰች ሴት ደገፍ አርጋ ይዛዉ በሀዘኔታ እግሮቹን እያየች
"ምን ባክሽ ትራንስፗርት አጥቼ እኮ ነዉ "
ክራንቹን ጠበቅ አረጎ እየያዘ ጠበቅ አርጋ የያዘችዉ የልጅቷ እጅ
ከድጋፍ አልፎ ሰዉነቱን ጨምድዳ ስለያዘችዉ እየጨነቀዉ
ልጅቷ የፊቱን ሁኔታ ስታይ እና እራሱን ችሎ መቆሙን ስታስተዉል
ለቀቅ እያረገችዉ ፊት ለፊታቸዉ የቆመችዉን ቀይ ቀለም የተቀባች
መኪና እየጠቆመችዉ
"የምትፈልግበት ላደርስህ እችላለሁ"
እንዲከተላት ምልክት እየሰጠችዉ የመኪናዉን በር በቀስታ ከፍታ
እንዲገባ ጋበዘችዉ
ፍፁም ጥቂት ካንገራገረ በኋላ እያመነታ ወደ መኪናዉ ዉስጥ ገብቶ ተቀመጠ ክራንቾቹን በእጆቹ አቅፎ እንደያዘ
ልጅቷ የፍፁምን መግባት ስታስተዉል በሩን መዘጋቱን አረጋግጣ
ወደ ሹፌር መግቢያ በር ዞራ ገብታ ከተቀመጠች በኋላ የት መሄድ
እንደፈለገ ጠይቃዉ ስለነገራት የመኪናዉን ሞተር አስነስታ በነገራት
አቅጣጫ መንዳት ጀመረች
ፍፁም የልጅቷን መልካምነት እያስተዋለ
በዚህ ዘመን ማን ሰዉ ያግዛል?ሲል እራሱን እየጠየቀ እና በልቡ
እያመሰገናት በቀስታ አንገቱን አዙሮ መንገዷ ላይ ትኩረት አርጋ
የምትነዳዉን ሴት አያት
ከለበሰችዉ ጥቁር ልብስ እንዳለቀሰች ከሚያስታዉቁት አይኖቿ
እና ከቀሉት ጉንጮቿ የሆነ ነገር ተረድቶ
"ሀዘን ላይ ነሽ መሰለኝ"
ሲል ለስለስ ባለ ድምፅ ጠየቃት
"አዎ"
የሚል አጭር መልስ ሰጥታዉ ፍፁም መጠየቅ እና ማፅናናት
እየፈለገ ነገር ግን የነቤዛዊት ሰፈር ስለደረሱ እና መዉረድ
ስላለበት እየተፀፀተ
"በጣም አመሰግናለሁ አንቻንም ፈጣሪ ያፅናሽ"
የሚል ቃል ከአፉ ወጥተዉ ከመኪናዋ ወርዶ ወደ እነቤዛዊት በር
ጋር ቆሞ ማንኳኳት ሲጀምር ያደረሰችዉ መልካም ሴት መኪናዋን
እያስጓራች አልፋዉ ከአይኑ እራቀች።
ቤዛዊት እህቷ ላይ የመግደል ሙከራ ካረገች በኋላ ዶክተር መለሰ
አባብሎ እና የህክምና ጥበብ ተጠቅሞ እሱ የከፈተዉ የግል
ሆስፒታል ተኝታ እንድትታከም ከቤተሰቦቿ ጋር ተማክሮ ሁሉም
ስለተስማሙ መታከም ጀምራለች።

ብቻዋን በሆነች ቁጥር ግን ዶክተሩም አልተረዳላትም እንጂ
ህመሟ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ነበር።
ዶክተር መለሰ አብሯት ጥቂት ካዋራት እና መድሀኒት ዉጣ እንድትተኛ ካረጋት በኋላ መሻሻል እና ለዉጥ ስላላየባት ምን
አይነት የተለየ ህክምና ሊሰጣት እና ልትድን እንደምትችል እያሰበ
ቤዛዊት የተኛችበትን ክፍል ለቆ ወጣ
ቤዛዊት የዶክተር መለሰን መዉጣት ስትመለከት አፍዋ ዉስጥ
ሳትዉጠዉ የደበቀችዉን ኪኒን በእጇ ከአፏ እያወጣችዉ እና
መሬት ላይ ወርዉራ ጥላዉ ብቻዋን ማዉራት እና መበሳጨት
ጀመረች
ፍፁምን ካየችዉ ሁለት ቀን እንዳለፋት አስታዉሳ ከአልጋዋ ዘላ
ወርዳ በቀስታ እየተራመደች የክፍሏን በር ከፍታዉ አንገቷን
አጮልቃ ተመለከተች
ዶክተር መለሰ ከታማሚ ጋር ፊት ለፊቷ ቆሞ ያወራል እስዋን
ታማሚዉ እያያት ቢሆንም ዶክተር መለሰ
ጀርባዉን ሰጥቷት ስለቆመ ሊያያት አይችልም ያረገችዉ ነጠላ
ጫማ ድምፅ እንዳይፈጥር እየተጠነቀቀች እና የግድግዳዉን
ጠርዝ እየታከከች እያወራ የቆመዉን ዶክተር መለሰን አልፋዉ ወደ
በሩ ከወጣች በኋላ መጠንቀቆን ትታ ስላመለጠችዉ እና
በብልጠቷ እየተደሰተች ከግቢዉ በር ጨርሳ ልትወጣ ስትል
የሀኪም ቤቱ ጥበቃ ፊቷ ቆሟ
"አንቺ ባለፈዉ ከጋሼ መለሰ ጋር የመጣሽዉ ልጅ አደለሽ?"
ብሎ ሲያፋጥጣት እየተናደደች እና ዘበኛዉን እንዴት ሊተዋት
እንደሚችል ካሰበች በኋላ ሀሳብ ስለመጣላት እጆቿን ወደ ኪሷቿ
ከታ
"እቃ ልገዛ ነበር"
አለችና ከኪሷ ያወጣችዉን የብር ኖቶች እያሳየችዉ
ጥበቃዉ በጥርጣሬ እያያት
"ጋሼ አንቺ እንድትወጪ የሚፈቅዱ አይመስለኝም
ተከተይኝ እንጠይቃቸዉ እንጂማ አላሷጣሽም"
እያለ ፊት ፊቷ እየተራመደ ተደብቃ ወደወጣችበት ሊያስገባት
ሲሞክር ሀሳቧ እንዳልተሳካ ያወቀችዉ ቤዛዊት እያወራ
የሚሄደዉን ጥበቃ ሳትከተል ክፍት ወደሆነዉ በር በቀስታ ሄዳ
ከወጣች በኋላ ከአካባቢዉ እስክትርቅ መሮጧን ቀጠለች።

ፍፁም ቤዛዊት ቤት ዉስጥ እንደሌለች እና የዶክተር መለሰ ሀኪም
ቤት እንደሄደች ስለነገሩት ምን ሆና ይሆን በሚል ሀሳብ ተዉጦ
እና ለመራመድ እንኳን እየታገለ ወደ ነገሩት ሀኪም ቤት ሄዶም
ስላጣት እያዘነ ከተዘጋ ሳምንታት ወዳለፉት ወደ ተከራየዉ ቤት
በሀሳብ ተዉጦ በቀስታ እየተራመደ ቤዛዊት የት ልትጠፋ
እንደምትችል እያሰበ ቤቱ ደርሶ የበሩን መከፈት አይቶ እየተገረመ እና እየተደናገጠ ወደ ዉስጥ ሲዘልቅ
መሄጃ ያጣችዉ ግራ የተጋባችዉ ቤዛዊት አልጋዉ ላይ ድብን ያለ
እንቅልፍ ወስዷት ተኝታ አገኛት

(ከሰዓታት በፊት)

ቤዛዊት እሩጫዋን ገታ አርጋ የምትሄድበትን አሰበች
ቤተሰቦቿ እንደማይፈልጓት ስለተሰማት ፍፁምን ፍለጋ
ወደ ተኛበት ሆስፒታል ብታመራም ዛሬ እንደወጣ ስለነገሯት
ወደ ቤቱ ሄዶ ይሆናል በማለት ነበር ወደ ፍፁም ቤት እንዳታጣዉ
እየፀለየች የሄደችዉ ስትደርስ ቤቱ ዝግ ሆኖ አለመኖሩን
ስታስተዉል ይመጣል በሚል ተስፉ በረንዳዉ ላይ ተቀምጣ ብዙ
ስዓት ስለቆየች
የፍፁም አከራይ ታዝበዋት እና ስለፍፁም መጥፋት አሳስቧቸዉ
ከጠየቋት እና የሆነዉን ሁሉ ስትነግራቸዉ እና እጮኛዉ ነኝ ብላ
ስለነገረቻቸዉ በእምነት ቤቱን ከፍተዉ ያስገቧት።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
አትሮኖስ pinned «#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #በክፍለማርያም ...ከሆስፒታል ወጣ የገጪዉ ሚስት የተወሰነ ገንዘብ ሰጥታዋለች እያነከሰ በክራንች ተጠቅሞ ለመራመድ ቢሞክርም ሁሉም ነገር ልምድ ስለሚጠይቅ እና በክራንቹ ታግዞ መራመድ ስላልቻለ ኮንትራት ታክሲ ለመያዝ አስፓልት ዳር ቆሞ መጠበቅ ጀመረ መኪና ማግኘት ሳይችል ቀርቶ ጥቂት ስለቆመ ብቻ እግሮቹ ብርክ ብርክ አሉበት በቆመበት ላለመዉደቅ…»
#ችግር_የለም?”

የተለየ ጠባይ
ሲፈጥረው ያደለው
ሐበሻ አለልህ
በሃይል እረግጠኸው
ክፉኛ አቁስለኸው
እስቲ “ይቅርታ” በለው

ችግር የለም!” ይላል
ሕመሙን ዋጥ አርጉ
በሥቃይ ፈግጐ
የልብህን ሰርተህ
መስለህ የጸጸተህ
ይቅርታ ጠይቀው
ችግር አለ? በለው
ቶሎ ሆድ ሳይብሰው።
ከእግር እስከ ራሱ
መከራ የወረሰው
የትህትናን ቆዳ
ደራርቦ የለበሰው
ከመቻልም በሊይ
ትዕግስት የለገሰው
“ችግር የለም!”
ምስኪኑ ያበሻ ሰው።

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘