አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በአንድ_ሰውነት_ውስጥ

ከልቤ መንጭቶ ደም በሥራ ስሬ ሥርዓት ይዞ ሲፈስ
ሳምባዬ ሲያስችለኝ ንፁህ አየር መተንፈስ
መላው አካላቴ ሥራውን ሲሰራ ያላንዳች መኮፈስ
አብሮ በአንድነት በቀናነት መንፈስ፣
“ነፍሴ” እየታመመ "ሥጋዬ" ሲገዳ
“ሥጋዬ” ሲቆሽሽ ነፍሴ” ስትፀዳ
አንዳንዴ ጊዜ “ነፍሴ ሆኖ የማይረዳ ፣
አንዱ ባንድ ነገር
መላ አጥቶ ሲቸገር
ትርምስምስ ተፈጥሮ
እርስ በርስ መግባቢያ ቋንቋ ሲጠፋበት
“ነፍሴ ለ “ሥጋዬ” አዲስ ሲሆንበት ፣
ለነፍሴም ሲታየው “ሥጋዬ እንደ እንግዳ
እኔው አንዱ ሰውዬ ሳልሰነዳዳ
ለገዛው እራሴ ባንድ ግዜ እሆናለሁ ዘመድና ባዳ፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘