አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ችግር_የለም?”

የተለየ ጠባይ
ሲፈጥረው ያደለው
ሐበሻ አለልህ
በሃይል እረግጠኸው
ክፉኛ አቁስለኸው
እስቲ “ይቅርታ” በለው

ችግር የለም!” ይላል
ሕመሙን ዋጥ አርጉ
በሥቃይ ፈግጐ
የልብህን ሰርተህ
መስለህ የጸጸተህ
ይቅርታ ጠይቀው
ችግር አለ? በለው
ቶሎ ሆድ ሳይብሰው።
ከእግር እስከ ራሱ
መከራ የወረሰው
የትህትናን ቆዳ
ደራርቦ የለበሰው
ከመቻልም በሊይ
ትዕግስት የለገሰው
ችግር የለም!”
ምስኪኑ ያበሻ ሰው።

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘