#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ተኝታ አገኛት
የፍፁምን መምጣት በመስኮታቸዉ በኩል አጮልቀዉ ያዩት አከራዩ ከቤታቸዉ በፍጥነት እየወጡ
በር ላይ ቆሞ የቤዛዊትን ቤቱ መጥታት ያስገረመዉን ፍፁም
አቅፈዉ ለመሳም እየዳዳቸዉ እና የያዘዉን ክራንች በአይናቸው
በሀዘኔታ እየተመለከቱ
"ፈጣሪ እንኩዋን አተረፈህ ልጄ ፈፅሞ ይማርህ"
የሀበዛ ልማድ የሆነዉን ከንፈራቸዉ በጥቂቱ ገርበብ አርገዉ
"ምፅ"
የሚልድ ድምፅ እየፈጠሩ
ፍፁም ከልባቸዉ መሆኑ ስለገባዉ እና ሀዘናቸዉ ተሰምቶት
"አሜን አሜን"
ብሎ እያወራ
አከራዩ ወደ ጆሮዉ ጠጋ ብለዉ
"እንኳን ለቤትህ አበቃህ ቤትህን እስከዛሬ ስንጠብቅ ነበረ"
አጮልቀዉ አይናቸዉን ከቆሙበት በረንዳ ወደ ፍፁም ቤት
እያማተሩና እየጠቆሙት
"ደፈርከኝ አትበለኝና እጮኛህን ከፍቼ ያስገባኋት እኔ ነኝ"
"ጥሩ አርገዋል አመሰግናለሁ"
በቆመበት እያስቸገሩት ስለሆነ ቀኑም እየመሸ ስለሆነ
"ሰላም እደሩ እሺ"
አላቸዉና ወደ ቤቱ ዉስጥ ሰተት አለ።
ወደ አልጋዉ ተጠግቶ የተኛችዉን ቤዛዊትን በፍቅር እየተመለከታት ህልም እራሱ የምታይ አትመስልም ጭልጥ ያለ
እንቅልፍ ስለወሰዳት ቀስቅሶ ለማዋራት ያሰበዉን ሀሳብ ትቶ
አልጋዉ ጠርዝ ላይ ተቀመጠ።
የዶክተር መለሰ ሀኪም ቤት ጥበቃ ዞር ሲሉ የጠፋችባቸዉን ሴት አስደንገጣቸዉ ወደ አለቃቸዉ መለሰ ቢሮ እየተበሰጫጩ
አምርተዉ
"በስመአብ ጋሼ ምን ሴጣን እንደሰፈረባት አላዉቅም ልጅቷ
ላይ በር ላይ አላስወጣሽም ብያት ወደ እርሶ ጋር ተከተይኝ
ብያት እየመጣን ለአፍታ ዞሬ ብመለከት እንደ ንፋስ ተበተነሽ"
ግራ የተጋባዉ ዶክተር መለሰ
"ምን.."
ሲላቸዉ
"ጠፋች እያልኳ ጋሼ"
"ማን?የቷ?"
"ያቺ በቀደም ከእርሷ ጋር የመጣችዋ ወጣት ልጅ"
አሉት ጥበቃዉ እንዴት እርሶን አልፋ ወጣች እንዳይላቸዉ እየሰጉ
ዶክተር መለሰ ከወንበሩ ተነስቶ ጥበቃዉን አልፏቸዉ ወደ
ቤዛዊት ክፍል አምርቶ በሩን ከፍቶት ገባ
የተገላለጠ አልጋ ትንሽ እንደመተከዝ ብሎ ወደ መሬት
ሲያቀረቅር መሬት ላይ የተጣለ መድሀኒት ተመለከተ
ለእንቅልፍ ብሎ የሰጣት ነበር
አየተናደደ እና እየተበሳጨ ወደ አባቷ መደወል ጀመረ።
ስዓቱ ከመሸ ቆየ ፍፁም ከተቀመጠበት ተነስቶ በሩን ቀርቅሮት
ወደ አልጋዉ ተመልሶ ቤዛዊትን እንዳይቀሰቅሳት እየተሳቀቀ
ከጎኗ ጋደም አለ ሳያስበዉ በክንዱ ክርን ስለነካት ቤዛዊት
እያኮረፈች ከነቃች በኋላ ወድያዉ ከጎኗ የተኛዉን ፍፁምን
ስታየዉ ፈገግ እያለች በተኛችበት በደረቷ ተስባ የፍፁምን
ጉንጭ ሳመችዉ
"እንዴት ነክልኝ ፍፄ"
"ደህና ነኝ አንቺስ"
ከንፈርዋ ለከንፈሩ ተጠግተዉ የትንፋሽዋ ሙቀት እየተሰማዉ ነዉ
"እንዴት እንደናፈቀኝ.."
አለችና የተኝጨባረረዉን ፀጉሩዋን በስርአቱ ሰብስባዉ
ካስያዘችዉ በኋላ ፍፁም እንዲያቅፋት እጁን ከደረቱ ላይ አንስታ
ከአንገቷ ዙርያ ካሳረፈችዉ በኋላ ተመቻችታ ተንተራሰችዉ
ፍፁም የሚያወራዉ የሚናገረዉ ነገር ጠፍቶበት እና ቀጥሎ
ሊፈጠር የሚችለዉ ነገር እያሳሰበዉ ጣራ ጣራዉን እያየ
ቤዛዊት ከንፈሮቿን ከንፈሩ ላይ አሳረፈቻቸዉ
በቀስታ ባለመስማማት አንገቷን ቀና አድርጎ አያት
የድሮዋ ቆንጆዋ ሳቂታዋ ቤዛዊት ናት አይኗቿ ፍቅርን ተርበዉ
በለሆሳስ ገርበብ ብለዉ ተከፍተዋል ከንፈሮቿም ደግመዉ
ሊስሙት አኮብኩበዋል ስሜቱን ማሸነፍ ስላቃተዉ እሱም እየሳማት የብርድ ልብስ ሙቀት ሳያስፈልጋቸዉ የፍቅራቸዉን
የመጀመርያ ፅዋ አብረዉ ተጓነጩ።
ጠዋት አልጋዉ ላይ ቤዛዊት እና ፍፁም እርቃናቸውን ተኝተዉ
የፍፁም ቤት በር በሀይል ሲደበደብ ሁለቱም በድንጋጤ ነቅተዉ ተያዩ።
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍4❤1
#የሀገሬ_ሰው
“እንደምን አድርጐ እንዴት ነው 'ሚኖረው?
የጽልመቱን ዘመን
በብሩህ ብርሐን ማነው 'ሚቀይረው?
“
ለምንድን ነው?” አለ “ማነው “ሚመልሰው?”
እልፍ አዕላፍ ጥያቄ ጠየቀ የህገሬ ሰው::
በገዛ ሀገሩ ላይ
በሐሳብ መግባባት መስማማት ሲጠፋ
ቂም በቀል ጥላቻ
ሥቃይና በደል ግድያው ሲከፋ
እሥራት እንግልት ስደቱ ሲስፋፋ
ሰላም ተናግቶበት
ፍቅርም መክኖበት ሲቀር ያለ ተስፋ
ጣዕሟ ቢጠፋበት ሕይወት ብትመረው
ዘመኑን በአግባቡ በቅጡ ያልኖረው
ምስኪኑ የሀገሬ ሰው መኖር ቢቸግረው
ለፈጣሪው አለው
“አኗኗሬን ሳይሆን..ሞቴን አሳምረው!!!”
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
“እንደምን አድርጐ እንዴት ነው 'ሚኖረው?
የጽልመቱን ዘመን
በብሩህ ብርሐን ማነው 'ሚቀይረው?
“
ለምንድን ነው?” አለ “ማነው “ሚመልሰው?”
እልፍ አዕላፍ ጥያቄ ጠየቀ የህገሬ ሰው::
በገዛ ሀገሩ ላይ
በሐሳብ መግባባት መስማማት ሲጠፋ
ቂም በቀል ጥላቻ
ሥቃይና በደል ግድያው ሲከፋ
እሥራት እንግልት ስደቱ ሲስፋፋ
ሰላም ተናግቶበት
ፍቅርም መክኖበት ሲቀር ያለ ተስፋ
ጣዕሟ ቢጠፋበት ሕይወት ብትመረው
ዘመኑን በአግባቡ በቅጡ ያልኖረው
ምስኪኑ የሀገሬ ሰው መኖር ቢቸግረው
ለፈጣሪው አለው
“አኗኗሬን ሳይሆን..ሞቴን አሳምረው!!!”
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
አትሮኖስ:
#ጨረቃ_እና_ፀሐይ
ከንጋት ጀምሮ ጀንበሬን ፈንጥቄ
እስከገባሁበት ስማይ ሥር ጠልቄ
ፍቅርን ሳልሰስት በሕይወት ዘመኔ
ብርሐን የቸርኩሽ ፀሐይሽ ነኝ እኔ፡፡
እንደ ክዋክብቱ ከእኔ የተደበቀ
ልዩ ምስጢር ያለሽ ሥውር የረቀቀ
ከፊትሽ በስተቀር ጀርባሽ ያልታወቀ
ቅርፅሽ ተለዋዋጭ የተፈራረቀ
ሲያሰኝሽ ሙሉ ክብ ካሻሽም ተገምሰሽ
አንዳንዴም ተሸርፈሽ በሰማይ ላይ ነግሰሽ
በተውሶ ብርሐን ጽልመት እምትረቺ
የምሽት ላይ ንግሥት ጨረቃ ነሽ አንቺ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ጨረቃ_እና_ፀሐይ
ከንጋት ጀምሮ ጀንበሬን ፈንጥቄ
እስከገባሁበት ስማይ ሥር ጠልቄ
ፍቅርን ሳልሰስት በሕይወት ዘመኔ
ብርሐን የቸርኩሽ ፀሐይሽ ነኝ እኔ፡፡
እንደ ክዋክብቱ ከእኔ የተደበቀ
ልዩ ምስጢር ያለሽ ሥውር የረቀቀ
ከፊትሽ በስተቀር ጀርባሽ ያልታወቀ
ቅርፅሽ ተለዋዋጭ የተፈራረቀ
ሲያሰኝሽ ሙሉ ክብ ካሻሽም ተገምሰሽ
አንዳንዴም ተሸርፈሽ በሰማይ ላይ ነግሰሽ
በተውሶ ብርሐን ጽልመት እምትረቺ
የምሽት ላይ ንግሥት ጨረቃ ነሽ አንቺ፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#ቀብርሽ_ላይ_አትቀሪም
ብትቀየሚኝም
" ቀብርህ ላይ አልደርስም” ፥ ለምን ትይኛለሽ
አንቺ ባትገኝም
የራሴ ቀብር ላይ ፥ አልቀርም ታውቂያለሽ
“ሞት ወሰደው" ብለው
ወዳጆቼ ሁሉ ፥ በእንባ ሲራጩ
ደረት እየደቁ ፥ ፀጉር ቢነጫጩ
አያዩትም እንጂ
የኗሪ ሀዘን ነው ፥ ለሟች የሳቅ ምንጩ።
ሕይወት ያለው ሁሉ
ከዚህ ዓለም ሲለይ ፥ በሞት ተሸፍኖ
ቀብሩ ላይ ይገኛል ፥ ተቀባሪ ሆኖ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ብትቀየሚኝም
" ቀብርህ ላይ አልደርስም” ፥ ለምን ትይኛለሽ
አንቺ ባትገኝም
የራሴ ቀብር ላይ ፥ አልቀርም ታውቂያለሽ
“ሞት ወሰደው" ብለው
ወዳጆቼ ሁሉ ፥ በእንባ ሲራጩ
ደረት እየደቁ ፥ ፀጉር ቢነጫጩ
አያዩትም እንጂ
የኗሪ ሀዘን ነው ፥ ለሟች የሳቅ ምንጩ።
ሕይወት ያለው ሁሉ
ከዚህ ዓለም ሲለይ ፥ በሞት ተሸፍኖ
ቀብሩ ላይ ይገኛል ፥ ተቀባሪ ሆኖ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ
፡
፡
#በክፍለማርያም
....ሁለቱም ተያዩ
ሁለቱም ከተኙበት ቀና እያሉ ተያዩ በሁለቱም ሀሳብ ዉስጥ
የቤዛዊት ቤተሰቦች እሳት ጎርሰዉ በር ላይ የቆሙ ስለመሰላቸዉ
እየተደናገጡ አልጋዉ ጠርዝላይ የተበታተኑ ልብሷቻቸዉን
ማሰስ ጀመሩ
ስላጧቸዉ ከአልጋ ሁለቱም ወርደዉ ብርድ ልብሱን መነቃቀሩት ከአልጋዉ ግርጌ መሬት ላይ ልብሷቻቸዉ ወድቀዉ ስላገኙ እየተቻኳሉ ለባብሰዉ ድጋሜ ተያዩ በሩ መንኳኳቱን ግን አላቆመም ነበር።
የፍፁም በር ላይ ምግብ ይዘዉ የቆሙት አከራዩ በልባቸዉ
"ሞተዋል እንዴ እነዚህ ሰወች"
እያሉ ለመመለስ እያሰብ ፍፁም
በሩን ከፍተላቸዉ
"እንዴት አደራችሁ ምግብ ይዤ ብመጣ ደጅ አስጠናችሁኝ እኮ..."
አከራዩ መበሳጨታቸዉ ፊታቸዉ ላይ እየተነበበ
ቤዛዊት ጆሮዎቿን ቀስራ እያዳመጠች ነዉ የአባቷ ድምፅ
እየመሰላት ዉስጧ እየተረበሸ
ፍፁም አከራዩ በመሆናቸዉ እፎይታ እየተሰማዉ እና ለመዋሸት
እየተንተባተበ
"ስላልሰማን ነዉ ይግቡ"
እያለ እንዲገቡ በሩን ከፈት አረገላቸዉ
"አይ ምኑን ገባሁት ይቺን ቅመሱ እስቲ"
አሉና በዳንቴል የተሸፈነ ትሪ አቀብለዉት
"እግርህንም እንደማይህ እያገገምክ ነዉ ወደ ኋላ መጥቼ እናወራለን"
እያሉት ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ።
ፍፁም የተሸፋፋነዉን ትሪ ሳይገልጠዉ ገና የምግቡ ሽታ ስላወደዉ
በመጠኑ እያነከሰ አልጋዉ ላይ እየተቀመጠ ቤዛዊትም ትላንት
የበላች ስለሆነች ከተቀመጠችበት ተነስታ ከተጣጠበች በኋላ
ፍፁምም እንዲታጠብ እረድታዉ አከራዩን እያመሰገኑ መመገብ ጀመሩ።
የቤዛዊት አባት የዶክተር መለሰን ስልክ አዉርተዉ ከጨረሱ
በኋላ እና ፍፁም ቤዛዊትን ፈልጓ መጥቶ ነበር የሚለዉን
ስለሰሙ ከሱ ቤት ዉጪ ልጃቸዉ ወዴትም እንደማትሄድ አስበዉ ወደ ታላቋ ልጃቸዉ የፍፁምን ቤት እንድታሳያቸዉ
ደወሉ
"ሄሎ ልጄ እንዴት ነሽ"
"ደህና ነኝ አባ"
መለሰችላቸዉ
"የአሰተማሪዉን ቤት የምታዉቂዉ መሰለኝ አሁን እንገናኝ እና
ታሳይኛለሽ"
የቤዛዊት ታላቅ እህት ቤዛዊትን መጥላት ሳይሆን እየፈራቻት
ነዉ ልታረጋት የነበረዉ ነገር አይምሮዋ ዉስጥ ስለተቀረፀ ብቻ ቤዛዊትን ላለማየት የፍፁምን ቤት ብታዉቀዉም
ደብቃ
"ዉይ አላዉቀዉም ቤቱን "
"እኔም ሰዉ ነሽ ብዬ አንቺ ጋር መደወሌ"
አባቷ እየተናደዱ ስልኩን ዘግተዉ ወደ መምህር ፍቃዱ መደወል ጀመሩ።
ፍፁም እና ቤዛዊት ደስታ በደስታ ሆነዋል
ከባዱን ጊዜ እንዳለፉት ቆጥረዉ ጠባቧ የፍፁም ክፍል ዉስጥ
አልጋዉ ላይ ጋደም ብለዉ ስላሳለፉት ነገር ከተያዩበት ቀን ጀምሮ
እስካሁን ስላሳለፉት ነገር በነፃነት እየተያዩ እየተሳሳቁ እያወሩ
ተቃቅፈዉ እየተላፉ እየተሳሳሙ አስደሳች ጊዜ አያሳለፉ ነዉ
ፍፁም ቤዛዊትን መላ አካሏን እየተመለከተ ቆይቶ ከቤዛዊት
ጋር አይን ለአይን ተጋጩ ፈገግ አለች ፊቷ ፍክት ብሏል
የዉስጥ ስሜትን በአብዛኛዉ የሰዉ ፊት ላይ ማየት ይቻላል
በዚህ ሰአት ህመም ያለባት ቀርቶ ታማ የምታዉቅ እንኳን
አትመስልም ክትክት እያለች ትስቃለች ፈገግታዋ ዉስጥ ንፁህነት
የዋህነት ምስኪንነት ይነበባል ተጠጋግተዉ ተቃቅፈዉ እየተያዩ
ቤዛዊት ሳያስበዉ ከአይኖቿ የእንባ ዘለላወች እየወረዱ
"እወድሃለሁ እንዳትርቀኝ ላጣህ አልፈልግም"
አለችዉ ከአይኖቿ የሚፈሱትን እንባወች ለማስቆም እየሞከረች
"አልተዉሽም ቤዚ ከልቤ ነዉ"
እያለ ፍፁም በከንፈሮቹ ከንፈሮቿን ሳማት።
ሁለቱም ደክሟቸዉ በጀርባቸዉ ተኝተዉ እጇቻቸዉን ብቻ አየር ላይ
ዘርጋተዉ በጣቶቻቸዉ እየተቆላለፉ የፍፁም በር በድጋሜ ተንኳኳ
ፍፁም ለመክፈት ቀስ እያለ ተነሳ።
የቤዛዊት አባት እና መምህር ፍቃዱ ተከታትለዉ በፍፁም
ጋባዥነት ወደ ዉስጥ ገቡ የቤዛዊት አባት ልጃቸዉን ስላዩዋት
እየተደሰቱ ከፍፁም ጋር ማደሯን በልባቸዉ ጠርጥረዉ አንጀታቸዉ
እየጨሰ ልጃቸዉን
"ተነሽና ወደ ቤት እንሂድ"
አዘዙ መምህር ፍቃዱ አይኖቹን ከወድህ ወድያ እያንቀዋለለ ቆይቶ
የቤዛዊትን ጡት ማስያዥያ ስላየና ለአባቷ አሳይቶ ነገሮችን
ለማክረር ስላሰበ ቤዛዊትን በፌዝ አስተያየት እያያት
"ያ ነገር ያንቺ ነዉ " ሲል አፋጠጣት

👍2❤1
#እንቆቅልህ_እንቆቅልሽ
ለጠየቅሽኝ እንቆቅልሽ ፥ ሲጠፋብኝ እኔ መልሱ
“ሀገር ስጠኝ” የምትዪኝ ፥ መልስ አታውቂም አንቺ ራሱ!
ሁሉ ሀገሩን ተከፋፍሎ ፥ ክልልሎችን እያጠረ
ኬ'ት አምጥቼ ሀገር ልስጥሽ ? ሀገር ማለት ሰው ነበረ
ሰውም በዘር ተደራጅቶ ፥ ሀገር መሆን አቅቶታል
ገድሎ መኖር ተበራክቶ ፥ ሞቶ ማኖር ከሀገር ጠፍቷል።
ይህን እውነት እያወቅሽው ...
ሀገር ስጠኝ” አትበዪኝ! ፥ በእንቆቅልሽ ልትለውጭኝ
ክልልና ዘር ነው ያለኝ ፥ ውሰጂና ሀገር ስጭኝ !
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ለጠየቅሽኝ እንቆቅልሽ ፥ ሲጠፋብኝ እኔ መልሱ
“ሀገር ስጠኝ” የምትዪኝ ፥ መልስ አታውቂም አንቺ ራሱ!
ሁሉ ሀገሩን ተከፋፍሎ ፥ ክልልሎችን እያጠረ
ኬ'ት አምጥቼ ሀገር ልስጥሽ ? ሀገር ማለት ሰው ነበረ
ሰውም በዘር ተደራጅቶ ፥ ሀገር መሆን አቅቶታል
ገድሎ መኖር ተበራክቶ ፥ ሞቶ ማኖር ከሀገር ጠፍቷል።
ይህን እውነት እያወቅሽው ...
ሀገር ስጠኝ” አትበዪኝ! ፥ በእንቆቅልሽ ልትለውጭኝ
ክልልና ዘር ነው ያለኝ ፥ ውሰጂና ሀገር ስጭኝ !
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ያንቺ ነዉ ሲል አፋጠጣት
ቤዛዊት አንዴ ፍፁምን አንዴ አባቷን አፈራርቃ እያየች
የተረገመ ፍቃዱን በዉስጧ እየረገመች መሬት ላይ የወደቀዉን
ጡት ማስያዣ አንስታ እና ንዴቷ እየተቀሰቀሰ አይኗን
እያጉረጠረጠች
"ያንተ ነዉ ልስጥህ ...አንተ ሴታሴት ወረኛ" ጥፍሮቿን አሹላ ወደ ፍቃዱ ተጠጋችዉ
ፍቃዱ አዋረድኳቸዉ ብሎ መዋረዱ እየታየዉ አመጣጧ እያስፈራዉ ወደ አባቷ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ
"አረ ተረጋጊ ሴትዮ"
አፉ ላይ የመጣለትን ቃል እያወራ
ፍፁም ለመገላገልም አልተነሳም አልጋዉ ጠርዝ ላይ ተቀምጦ
የጥፋተኝነት እና ደግ አረኩ በሚል ሁለት የተቃረኑ ሀሳቦች
ተዉጦ ከሀሳቡ ያነቃዉ ብርጭቆ ከግድግዳ ጋር ሲጋጭ
የሚያሰማዉ ድምፅ ነበር
"ኳኳ ከሽሽሽሽሽ"
ፍቃዱ በሩን በርግዶ እየተንደፋደፈ ወጣ አባቷ በድንጋጤ ተዉጠዉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ እና ፍጥርጣሪዉን ፈርተዉ።
አይናቸዉን ጨፍነዉ ቆይተዉ
ልጃቸዉን በልመና አስተያየት እያዩዋት
"ተረጋጊ ልጄ በቃ"
እያሉ መለመን ጀመሩ መታመሟ እየመሰላቸዉ እየፈሩ
በንዴት የጦፈችዉ ቤዛዊት የወረወረችዉ ብርጭቆ
ፍቃዱን ስላላገኘዉ እና እልኋ ስላሎወጣላት ግላ
"ሁለተኛ ይሄን የተረገመ ሰዉ ማየት አልፈልግም"
እጆቿ እየተንቀጠቀጡ እና የታችኛዉን
ከንፈሯን ወደ አፍዋ ዉስጥ ስባ በጥርሶቿ ነክሳ።
በትክክለኛዉ ስዓት አንዳንዴ ጥፋትን ለመሸፈን ሌላ ጥፋት
ማጥፋት የመጀመርያዉ ጥፋትን ያደበዝዝልናል
ሰዓቱን ካልጠበቀ ደሞ በሁለት ስህተት ቅጣት ያስጠይቀናል
መልካም ነገርም እንደዚህ ነዉ በትክክለኛዉ ስዓት
ጥሩ ነገር ላይ ሌላ ጥሩ ነገር ማስራት እና ድጋሜ ጥሩ ማሰብ
የመጀመርያ ደስታችንን አስረስቶ ወደ እጥፍ ድርብ ወደ ሆነ ደስታ ዉስጥ ይከተናል።
አባቷ ልጃቸዉ ቤዛዊትን እየለመኗት ይዘዋት እየወጡ ነዉ
ዞራ ፍፁምን ተመለከተችዉ ምን ማረግ ይችላል ከአባቷ ነጥቆ ማስቀረት አይችል እየከፋዉ እና እያዘነ ለመሰናበት
እጆቹን አየር ላይ አነሳ እስዋም በአይኖቿ እንባ እየቀረሩ እያየችዉ
አባቷ አቅፈዉ እንደያዟት ወደ ዉጪ ወጣች የቤዛዊት አባት እግሬ
አዉጭን ብሎ የሮጠዉን ፍቃዱን በአይናቸዉ እየፈለጉት ነበር
ቤዛዊት የአባቷ መኪና ዉስጥ ገብታ ስትቀመጥ ወረቀት እና
እስኪርቢቶ ስላገኘች ፊቷ ፈገግ እያለ የሆነ ነገር ሞነጫጭራ ፅፋ
ኪሷ ዉስጥ አባቷ እንዳያዩዋት ከከተተች በኋላ
"የረሳሁት እቃ አለ መጣሁ.."
አባቷን ብላቸዉ ከመኪናዉ ወርዳ ወደ ፍፁም ቤት መሮጥ ጀመረች።
ፍፁም ቤዛዊት እንደወጣች ብቸኝነት ቀንድ አዉጥቶ መልክ ኖሮት
ሰፈረበት ከፋዉ
ወራቶች እያለፉ ስለሆነ በዚህ ወቅት የትም ትምህርት ቤት
ተቀጥሮ ማስተማር እንደማይችል ሲያስበዉ ከአልጋ ወደ አልጋ
ቦታ እየቀያየረ እየመሰለዉ አዘነ
ቤዛዊትም የእሱ ትሁን አትሁን ግራ በገባዉ ሁኔታ ስትታመም
ሲሻላት አብሯት ከጎኗ እንዳይሆን መሰናክል ሲበዛበት
ይባስ ብለዉ ቤተሰቦቿ ጣልቃ እየገቡ እረፍት እና ደስታ ስለነሱት
ተስፋ ወደ መቁረጥ እየሄደ እየተጨነቀ ሲያስብ በሩ ተበርግዶ
ተከፍቶ ቤዛዊት እየፈጠነች ገብታ ሀይሏን በሙሉ ትከሻዉ ላይ
ጥላበት ካቀፈችዉ በኋላ እና ከንፈሩን በፍጥነት ለኮፍ አርጋ
ስማዉ እንደለመደችዉ ከኪሷ የተጣጠፈ ወረቀት አዉጥታ
ሰጥታዉ በገባችበት እየፈጠነች ወጣች።
ከወጣች በኋላ ወረቀቱን ገልጦ አነበበዉ የቦታ ስም ተፅፎበታል
አቅጣጫዉን እና ነገ ሶስት ሰአት እንገናኝ ይላል
አንብቦት ሲጨርስ ደስ እያለዉ በጀርባዉ ጋደም አለ።
ቤዛዊት ቤቷ ስትደርስ መሳቅ መጫወት አበዛች ቤተሰቦቿ
ደስ እያላቸዉ መሽቷ ለእንቅልፍ ወደየአልጋቸዉ ተለያዩ
እስዋ ግን ስለነገዉ እያብሰለሰለች የባንክ ደብተሯን ኪሶ ዉስጥ
ከትታዉ በለበሰችዉ ሱሪ አልጋዋ ላይ ወጣች።
ነፋሻማ አየር ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር መዉጫ መስመር
በአካባቢዉ የበቀሉት ዛፎች በንፋስ ይወዛወዛሉ ዛፎቹ ላይ ያሉት
የወፍ ዝርያወች ቢንጫጩም ዜማ አላቸዉ
እማማ ስንቅነሽ ቤዛዊትን በራቸዉ ላይ ቆማ ሲያገኟት
የሞተች ልጃቸዉ መቃብር ፈንቅላ እንደወጣች ተደስተዉ እያዩዋት
"ልጄ ልጄ የምትመጪ አልመሰለኝም
የኔ የዋህ የኔ ምስኪን"
እያሉ አቀፏት

#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በክፍለማርያም
በነፋሻዉ አየር በንፋሱ ዉልብታ ቅርንጫፎቹን ከወዲህ ወድያ የሚዉረገርገዉን የባህርዛፉን ግንድ ተደግፋ
ቤዛዊት የቀጠረችዉን ፍቅረኛዋን በጉጉት አይኖቿ አሻግረዉ እያዩ ትጠብቃለች።
እማማ ስንቅነሽ ትመጣለች ብለዉ ያልጠበቋትን የበፊትዋን እብድ ጤነኛ ሆና በመምጣቷ እየተደሰቱ እና አምላካቸዉን እያመሰገኑ በጠዋት መጥታ እንግዳ ስለሆነችባቸዉ ቁርስ ቢጤ ሊሰሩላት ደፋ ቀና እያሉ ነዉ።
በእርግጥ ከህልማቸዉ ጠፍታ አታዉቅም እርቃኗን ሆና በብርድ ስትንሰፈሰፍ አይናቸዉ ላይ ስለተቀረፀች
ድቅን ትልባቸዋለች በወለደ አንጀታቸዉ አፈር አልብሰዉ የቀበሯት ልጃቸዉን ያዩ ይመስል ቤዛዊትን
ሲያዩ ስፍስፍ ብለዉ ያዝኑላታል።
ፍፁም ነግቶ ልቡም በጭንቀት እንደተወጠረ ቤዛዊት ካለችዉ ቦታ ለመሄድ ለባብሶ ጨርሶ የአንድ እጁን ክራንች
ትቶ በአንዱ ብቻ እየተጠቀመ በሩን ቆልፎ ከወጣ በኋላ የፃፈችለት ወረቀትን ከኪሱ አዉጥቶ በድጋሜ ተመልክቶ
ኪሱ ዉስጥ መልሶ ሊከተዉ እየሞከረ ከጀርባዉ አከራዩ ጉሮሮአቸውን እየጠረጉ
"እህህ እንዴት አድረሀል አቶ ፍፁም?"
ፍፁም ሳያስበዉ ስለጠሩት ደንገጥ እያለ እና የቤት ኪራይ ቀን መድረሱም ትዝ እያለዉ ኪሱ ዉስጥ ከያዘዉ ዳጎስ
ያለ ገንዘብ መሀል ቆጥሮ እያወጣ ለአከራዩ እየሰጣቸዉ
"ይመስገን"
አላቸውና ስዓት እንዳያረፍድ እና ቤዛዊትን እንዳያጣት አስቦ እየተቻኮለ ወጣ።
የቤዛዊት አባት ቤዛዊት ቦርሳ አንግባ እንደወጣች ከእንቅልፋቸዉ እንደነቁ ሰራተኛቸዉ ስለነገረቻቸዉ ተናደዉ
"እዚች ልጅ ላይ ያለዉ ሴጣን መች ይሆን እረፍት የሚሰጠን"
እያሉ እያጉተመተሙ ወደ ቤዛዊት መኝታ ክፍል ደርሰዉ እንደገቡ መጀመርያ አይናቸዉ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ
ወረቀት ላይ ስለሆነ በእጃቸዉ ሳይነኩት በእርቀት ቆመዉ ለማንበብ አንገታቸዉን ሰገግ አርገዉ አይኖቻቸውን
ሰደዱ
"አትፈልጉኝ በፈጠራችሁ አምላክ ተዉኝ"
የሚሉ ቃላቶችን ሲያነቡ ወረቀቱን አንስተዉ ጨምድደዉ እየወረወሩት
"ጥርግ በያ ለኔ ስትይ ገደል ለምን አትገቢም"
እየጮሁ ተናግረዉ በሀሳብ እና በንዴት እየተዉረገረጉ ወደ ሳሎን አምርተዉ ተለቅ ያለዉ ሶፋ ላይ
ዘፍ ብለዉ ተቀምጠዉ ቤዛዊትን ማማረር እና መራገም ጀመሩ
"የእራሷ ጉዳይ"
አሉና ስለ ቤዛዊት ላለማሰብ ፂማቸዉን በእጇቻቸዉ ሲነካኩ ቆይተዉ አይናቸዉ ከሳሎኑ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለዉ
የቤተሰብ ፎቶ ላይ ተተክሎ ቀረ
እሳቸዉ ባለቤታቸዉን አቅፈዉ ፎቶዉ ላይ ይታያሉ የቤዛዊት ታላቅ እህት እናቷን ተደግፋ ከጀርባ ቆማለች
ፊቷ ላይ ፈገግታ ይነበባል ቤዛዊት ከረሜላ አልገዛልህም እንደተባለ ህፃን አኩርፋ አባቷን ተደግፋ ትታያለች
የቤዛዊት አባት ፎቶዉን እያዩ ቆይተዉ ቤዛዊት ላይ መጨከን እና መተዉ አላስችል ስላላቸዉ
በሀዘን ተዉጠዉ ለአቶ ፍቃዱ እርዳኝ ለማለት ስልካቸዉን አዉጥተዉ መደወል ጀመሩ።
ተንኮለኛ እና ሞኝ ሰዉ አይጥመድህ ከህይወትህ ለማሶጣት በጣርክ ቁጥር የጠራከዉ ይመስለዋል
ስለዚህ ሁሌም ሲከተልህ ይኖራል
ፍቃዱ እየተጣደፈ ስራዉን ትቶ የፍፁምን እና የቤዛዊትን ህይወት ለማመሰቃቀል ወደ ፍፁም የተከራየበት ቤት
አመራ ወደ ግቢዉ ሲደርስ ቤዛዊት ኖራ እንዳትመታዉ እራሱን ለመጠበቅ እየተንሿከከ ወደ ግቢዉ ዉስጥ ዘለቀ።
የፍፁም በር ጋር ሲደርስ ከጀርባዉ ሰዉ መኖር እና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ዙርያዉን ቃኝቶ ጆሮዉን የፍፁም በር
ላይ ለጥፎ ሲያዳምጥ ድምፅ በማጣቱ እየተገረመ በሩን ሲያንኳኳ እና ቆይቶም ለመክፈት ሲታገል ማንም አለመኖሩን ሲያዉቅ እየተበሳጨ ወደ መጣበት ሊመለስ ሲል መሬት ላይ የወደቀ ወረቀት አይቶ ጎንበስ ብሎ
ካነሳዉ በኋላ ለማንበብ ሞከረ
የቦታ አድራሻ የቀጠሮ ሰአት መልሶ መሬት ላይ ጥሎት ሹክክ ብሎ ወደ ዉጪ ወጣ
" የት ሄደዉ ይሆን "
ሲል ብዙ ካሰበ በኋላ ወረቀቱ መልስ ያለዉ ስለመሰለዉ ወረቀቱን ፍለጋ
ወደ ፍፁም ግቢ ፈገግ እያለ ተመለሰ።

👍1
#ነፃነት
በጽልመት ፈርጣማ ክንድ እግር ተወርች ተይዛ
ላፍታም ቢሆን ላለመኖር በባርነት ቅኝ ላትገዛ
ያላንዳች የተኩስ ድምፅ ያላንዳች የጥይት እሩምታ
ፀንታ ታግላ በፀጥታ
ቃታ ሳትስብ የጠመንጃ
ባላንጣዋን ግዳይ ጥላ ነፃነቷን ይፋ አውጃ
ጨረቃ እንኳን . . .
የጋረዳትን ግርዶሽ ጥሳ ከደመና እግረ ሙቅ ተላቃ
ከድቅድቅ ጨለማ ወጥታ ሙሉ ብርሐኗን ፈንጥቃ
በክብር አምራ ደምቃ በነፃነት ኮርታ ስቃ
ለነፃ አየር ስትበቃ
ሰውን ያህል ታላቅ ፍጡር እንዴት ያንሳል ከጨረቃ !?
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
በጽልመት ፈርጣማ ክንድ እግር ተወርች ተይዛ
ላፍታም ቢሆን ላለመኖር በባርነት ቅኝ ላትገዛ
ያላንዳች የተኩስ ድምፅ ያላንዳች የጥይት እሩምታ
ፀንታ ታግላ በፀጥታ
ቃታ ሳትስብ የጠመንጃ
ባላንጣዋን ግዳይ ጥላ ነፃነቷን ይፋ አውጃ
ጨረቃ እንኳን . . .
የጋረዳትን ግርዶሽ ጥሳ ከደመና እግረ ሙቅ ተላቃ
ከድቅድቅ ጨለማ ወጥታ ሙሉ ብርሐኗን ፈንጥቃ
በክብር አምራ ደምቃ በነፃነት ኮርታ ስቃ
ለነፃ አየር ስትበቃ
ሰውን ያህል ታላቅ ፍጡር እንዴት ያንሳል ከጨረቃ !?
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ከመላዕክት_በስተቀር
ሆሄያትን ድርድሬ
ቃላት አሰልፌ
ሐረጋት ዘርግቼ
ስንኝ አዋቅሬ
ሕብረቃል ፈጥሬ
በሰም ቀባብቼ
በወርቅ ለብጬ
በወግ አሳምሬ
ብዘርፍልሽ ቅኔ
አይበቃኝም እኔ፡፡
ከመቅደስ ታድሜ
ቅኔ ማሕሌት ቆሜ
ቃናው በሚጣፍጥ
ልብን በሚመስጥ
ውብ በሆነ ዜማ
በሚያምር ቅላፄ
በወርቃማ ድምፄ
ሌት ተቀን ባሰማ
ከመሳዕከት በስተቀር
አያዳምጡት ካህናት
የኔን ፍቅርማ፡፡
ከደብረ ሰላሙ ከደጃፉ ቆሜ
ብፀልይ ሺ ጊዜ ብሰግድ ደጋግሜ
እቀራለሁ እንጂ በከንቱ ደክሜ.
በየትኛውም ቋንቋ አይገለፅ በቃል
የፍቅሬ ርቀቱ ከሰማይ ይዘልቃል
የፍቅሬ ጥልቀቱ ከውቅያኖስ ይጠልቃል።
ከደሜ ሥር ጠልቆ
ከነፍሴ ሥር ዘልቆ
አቅሌን አስቶ
አደብ አሳጥቶ
ፍቅር ሲያዋልለኝ
“እንዴት ነህ?” ለሚለኝ
ምንስ ምላሽ አለኝ?!
ዝም ብዬ ብቻ አለሁ አለሁ
አለሁኝ እላለሁ
ሌላ ምን እላለሁ?!
ነፍስና ሥጋዬ እንዳልተለያዩ
እንዳልሞትኩ አውቃለሁ፡፡
ካንገቴ የዋለው ያሰርኩት ማተቤ
ሕያው ምስክሬ የህናው በልቤ
ለሕይወቴ ምሥጢር ምክንያቱ የሆነው
ከሰው ወዲያ ለኔ ፍቅር ነው። ፍቅር ነው፡፡
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
ሆሄያትን ድርድሬ
ቃላት አሰልፌ
ሐረጋት ዘርግቼ
ስንኝ አዋቅሬ
ሕብረቃል ፈጥሬ
በሰም ቀባብቼ
በወርቅ ለብጬ
በወግ አሳምሬ
ብዘርፍልሽ ቅኔ
አይበቃኝም እኔ፡፡
ከመቅደስ ታድሜ
ቅኔ ማሕሌት ቆሜ
ቃናው በሚጣፍጥ
ልብን በሚመስጥ
ውብ በሆነ ዜማ
በሚያምር ቅላፄ
በወርቃማ ድምፄ
ሌት ተቀን ባሰማ
ከመሳዕከት በስተቀር
አያዳምጡት ካህናት
የኔን ፍቅርማ፡፡
ከደብረ ሰላሙ ከደጃፉ ቆሜ
ብፀልይ ሺ ጊዜ ብሰግድ ደጋግሜ
እቀራለሁ እንጂ በከንቱ ደክሜ.
በየትኛውም ቋንቋ አይገለፅ በቃል
የፍቅሬ ርቀቱ ከሰማይ ይዘልቃል
የፍቅሬ ጥልቀቱ ከውቅያኖስ ይጠልቃል።
ከደሜ ሥር ጠልቆ
ከነፍሴ ሥር ዘልቆ
አቅሌን አስቶ
አደብ አሳጥቶ
ፍቅር ሲያዋልለኝ
“እንዴት ነህ?” ለሚለኝ
ምንስ ምላሽ አለኝ?!
ዝም ብዬ ብቻ አለሁ አለሁ
አለሁኝ እላለሁ
ሌላ ምን እላለሁ?!
ነፍስና ሥጋዬ እንዳልተለያዩ
እንዳልሞትኩ አውቃለሁ፡፡
ካንገቴ የዋለው ያሰርኩት ማተቤ
ሕያው ምስክሬ የህናው በልቤ
ለሕይወቴ ምሥጢር ምክንያቱ የሆነው
ከሰው ወዲያ ለኔ ፍቅር ነው። ፍቅር ነው፡፡
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
እውነቱን ተናግሮ ፣ በጨለማ ያድራል።”
ጠጠር ሆኖ አግኝቼው ፥ ገዝፌ እንደ ጋን
ያልፈኛል እንደ ቀስት ፥ ስጎብጥ እንደ ደጋን ።
#የጋን_ውስጥ_ጨለማ
አለኝ ተጓዥ ሀሳብ
እግር አውጥቶ ሲሮጥ ፥ በደረት የሚሳብ
በቆመበት ሚገኝ ፥ ክንፍ አውጥቶ ሲበር
ሲወድቅ የሚጠገን ፥ ሲነሳ ሚሰበር
ሲያዝኑለት ሚደሰት ፥ ሚጨክን ሲምሩት
በሲኦል የሚገኝ ፥ በገነት ሲያኖሩት
“ሀሳብ ነበርክና
ወደ ሀሳብ ተመለስ ፥ ብለው ለሚረግሙት
ህያው ሆኖ ሚገኝ ፥ ተለይቶ ከሙት።
አለኝ ተጓዥ ሀሳብ
መንገድ በሌለበት ፥ መሔድ የተካነ
የጋን ውስጥ መብራት
ከጋን ውጪ ላሉት ፣ ጨለማ እንደሆነ
ሲነግረኝ ይኖራል
"የመሸበት ፀሐይ
ይለኛል ሀሳቤ
ይለኛል ምናቤ
ደግፎኝ ቆምኩ ስል
ያልፈኛል እንደቀስት፣ስጎብጥ እንደ ደጋን
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ጠጠር ሆኖ አግኝቼው ፥ ገዝፌ እንደ ጋን
ያልፈኛል እንደ ቀስት ፥ ስጎብጥ እንደ ደጋን ።
#የጋን_ውስጥ_ጨለማ
አለኝ ተጓዥ ሀሳብ
እግር አውጥቶ ሲሮጥ ፥ በደረት የሚሳብ
በቆመበት ሚገኝ ፥ ክንፍ አውጥቶ ሲበር
ሲወድቅ የሚጠገን ፥ ሲነሳ ሚሰበር
ሲያዝኑለት ሚደሰት ፥ ሚጨክን ሲምሩት
በሲኦል የሚገኝ ፥ በገነት ሲያኖሩት
“ሀሳብ ነበርክና
ወደ ሀሳብ ተመለስ ፥ ብለው ለሚረግሙት
ህያው ሆኖ ሚገኝ ፥ ተለይቶ ከሙት።
አለኝ ተጓዥ ሀሳብ
መንገድ በሌለበት ፥ መሔድ የተካነ
የጋን ውስጥ መብራት
ከጋን ውጪ ላሉት ፣ ጨለማ እንደሆነ
ሲነግረኝ ይኖራል
"የመሸበት ፀሐይ
ይለኛል ሀሳቤ
ይለኛል ምናቤ
ደግፎኝ ቆምኩ ስል
ያልፈኛል እንደቀስት፣ስጎብጥ እንደ ደጋን
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#በክፍለማርያም
...ወረቀቱን ፍለጋ ወደ ዉስጥ ተመለሰ
ፍቃዱ ወረቀቱን እያነሳ ድል እንዳረገ ሰው ኮራ እና ጀነን እያለ
"አገኘኋችሁ"
ሲል አጉተምትሞ የወረቀቱን አቅጣጫ ተከትሎ መሄድ ጀመረ።
እማማ ስንቅነሽ ቁርስ ሰራርተዉ ዉጪ ተገትራ የቆመችዉን ቤዛዊትን ወደ ቤት ዉስጥ ገብታ
እንድትበላ ጠሯት አልሰማቻቸዉም ልቧ ከአሁን አሁን መጣ አልመጣም ብላ የምትጠብቀዉ ፍፁም ላይ ነዉ።
ቀረብ ብለዉ እየነኳት
"ልጄ የምትጠብቂዉ ሰዉ አለ እንዴ"
እማማ ስንቅነሽ በሁኔታዋ ተጠራጥረዉ ጠየቋት
"አዎ ግን አሁን አልነግሮትም"
ፈጠን ፈጠን እያለች እያወራች
የእማማን ልብ ለማንጠልጠል አስባ
ነገር ግን እማማ ስንቅነሽ ምንም አልመሰላቸዉም እንደሚያማት ስለሚያዉቁ አብዳ ለይቶላት
ጨርቋን ጥላ ሳይፀየፉ ሰዉ ናት ብለዉ ስላቀረቧት አሁን አሟት ቢሆን እንኳ ሰዉ የምትጠብቀዉ ሊጫኗት አልፈለጉም።
እዉነተኛ ወዳጅም እንደዚህ ነዉ ጥፋትህን ስህተትህን ካወቀ በስህተት በጥፋትህ ተጠቅሞ
ሊጎዳህ አይሞክርም
ያግዝሀል ያበረታሀል እንጂ
እማማ ስንቅነሽም የቤዛዊትን እጅ በፍቅር ይዘዉ ሳብ እያረጉዋት
"በይ ነይና ቁርስሽን በልተሽ ትጠብቂዋለሽ"
ለእሳቸዉ የእሷ ቁርስ መብላት እንጂ ታማ ዉጪ መገተሯ ወይ በጤነኛ አይምሮዋ ሰዉ ቀጥራ
እየጠበቀች መሆኑ ብዙም ትኩረት አይሰጣቸዉም
ቤዛዊት የቀጠረችዉ ሰዓት ሳይደርስ መጨነቋ እየገረማት እና ፍፁምን ምን ያክል እንደምትወደዉ እያሰበች ወደ ቤቱ ዉስጥ ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ተከታትለዉ ገቡ።
እጇ ላይ ያሰረችዉ ሰዓት ይቆጥራል እርግጠኛ ስላልመሰላትም በእማማ ስንቅነሽ በር በኩል
የሚያልፉ እና የሚያገድሙ ሰወችን
"ይቅርታ ሰዓት ስንት ነዉ?"
በሚያሳዝን አስተያየት ትጠይቃለች
"ሶስት ተኩል፣አራት ስዓት .."
እያሉዋት የጠየቀቻቸዉ ሰወች ያልፉሉ
እሷም ያሰረችዉ ሰዓት ግን ትክክል ነበር የሚሰራዉ።
ቤዛዊት ስልኳን ይዛ ባለመዉጣቷ ተበሳጨች ይዛዉ ብትጠፋ ቤተሰቦቿ እየደወሉ የሚጨቀጭቋት ስለመሰላት ነበር ትታዉ የወጣችዉ አሁን ግን ብይዘዉ ኖሮ ስትል
ተመኘች የፍፁም መዘግየት እያሳሰባት ስድስት ስዓት ሊሆን ተቃርቧል።
እማማ ስንቅነሽ በጠራራ ፀሐይ ዉጪ የቆመችዉን ቤዛዊትን ቤት እንድትገባ ለመለመን ከጉዋዳቸዉ ወጡ
"አይ ልጄ ፀሀዩ በረታብሽ እንዳያምሽ ወይ ወደ ቤት ግቢ አልያም በረንዳ ላይ ጥላ ቦታ ተቀመጪ"
"ቀረብኝ እኮ ሶስት ሰዓት ተባብለን ስድስት ሰዓት ሞላ"
"እኮ ይመጣል ብቻ ከፀሐይዋ ራቅ በይ"
እንደዚህ ሲልዋት ቤዛዊት በደስታ ፈገግ እያለች
"የሚመጣዉ ማን እንደሆነ ልንገሮት?"
በእሺታ እማማ ስንቅነሽ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁ
"ጉዋደኛዬ ፍቅረኛዬ ባሌ"
ቀጠል አድርጋም
"ፍፁም ይባላል ሲመጣ አስተዋዉቃችሁዋለሁ"
እማማ በእሷ ደስተኛ መሆን እየተደሰቱ እና እያዋሩ ቤዛዊትን ከፀሀዩ ወደ ጥላ ወስደዋት ነበር።
(ከሰዓታት በፊት)
ፍፁም ሁለት ስዓት ተኩል አካባቢ ከተባለዉ አድራሻ በታክሲ ተሳፍሮ እንደወረደ እና ባለችዉ አቅጣጫ ጥቂት ከተራመደ በኋላ ቦታዉን ለማረጋገጥ ፈልጎ ቤዛዊት የሰጠችዉን ወረቀት ኪሶቹ ዉስጥ ሲፈልግ ስላጣዉ እየተበሳጨ
የት ሊጥለዉ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ።
ቤቱ እየወጣ ለአከራዩ ብር ሲሰጥ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ የቦታዉን እርግጠኝነትን ለማረጋገጥ
ጭንቅላቱን መጠየቅ ተያያዘ
አልተሳሳተም ያለችዉ ቦታ ላይ ደርሷል ነገር ግን እሱ ከቆመበት መንገድ ተሻግሮ ነበር
አንገቱን ቀና አርጎ ለማየት ሞከረ ቤዛዊትን በርቀት አያት
በእድሜ ገፋ ካሉ ሴትዮ ጋር ቆማ ታወራለች
ስላያት እየተደሰተ ግዜ ሳያጠፋ መንገዱን ሊሻገር ሲል በቅርብ እርቀት ከቅድም ጀምሮ ከጀርባዉ
የነበረ የመሰለዉ ሰዉ ስላየ መሻገሩን ተቶ የሰዉየዉን ፊት ለማየት በቀስታ ዞሮ በጨረፍታ አይቶት
መሻገሩን ወደ ቤዛዊት መቅረቡን ትቶ ቀጥታዉን መንገድ ይዞ እየተናደደ እያጉተመተመ መራመድ ጀመረ።
"ከቤት ጀምሮ ሲከተለኝ ነበር ወይስ እንዴት እዚህ ድረስ ሊመጣ ቻለ"
ፍፁም እራሱን እየጠየቀ ከኋላዉ የሚከተለዉን ሰዉዬ ለማምለጥ እየሞከረ ነዉ
"አይ ፍቃዱ ምን አርግ ነዉ ግን የሚለኝ ምን በደልኩት ምን አሰቀየምኩት
ይሄን ያህል የጎን ዉጋት የሆነብኝ"
ፍፁም ከፊት ሲራመድ ፍቃዱ አድፍጦ ከኋላው እየተከተለዉ ነዉ ፍፁም እሮጦ ማምለጥ
ተመኘ ነገር ግን እግሮቹ ለመሮጥ ብቁ አደሉም
ፍፁም እያነከሰ ፍቃዱን ለማምለጥ ክራንቹን ተጠቅሞ ፈጠን ፈጠን ለማለት እየታገለ ነዉ
ከጀርባዉ ያለዉ ፍቃዱ ግን ዘና ብሎ እየተራመደ በፍፁም አረማመድ አነካከስ እየሳቀ እየተከተለዉ ነበር።
አንዳንዴ በህይወት መስመራችን ዉስጥም ከእኛ በብዙ እጥፍ የሚበልጡን በብዙ እጥፍ
የተሻሉ ሰወች አሉ
ነገር ግን አብዛኞቹ ስለበለጡን የሚኮፈሱ ስላነስን የሚንቁን ናቸዉ
ህየወትንም ከባድ የመያረጋት መሮጥ የሚችል ሰዉን በታመመ እግር በክራንች ታግዘዉ ማምለጥ መቻል ነዉ።

❤2👍1
#ኢትዮጵያዊ_ነኝ
በላሊበላ አስቀድሼ፣ ሽህ ሁሴን ባሌ የተገኘሁ፤
በአባ ገዳ ተመራርቄ፣ መካ ላይ እርዝቅ ያገኘሁ፡፡
ሀመር የቡርጆ አደራ
ፈጣሪ ከሰጠኝ በረከት፣ ዘመን አያነጥፈው ወረት፤
የሚገባኝን ለሰጠኝ፣ የሚገባውን የምገመድል ፤
ለሞላልኝ የማላጎድል።
በሲዳማ ጨንበለላ፣
በወላይት ጊይታ፣
ቢያሻኝ በቅዳስ ዮሀንስ፣
የዘመን ጥባት የምከትብ፣ አዲስ አመት የማወድስ፡፡
በጅምላ የማልቀመስ፤
በችርቻሮ የማልረክስ፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ሳነቴ ላይ ውርጭና ጉም፣ ዳሽን ጫፍ ግግር በረዶ፧
ደሎ መና የአዋራ ጭስ፣ ዳሎል ላይ የእሳት እርጎ፡፡
ይርጋለም ያጋጥኳትን ላም፣ ወለጋ ላይ አስጠቅቼ፤
ትኩስ እንገርዋን የጠጣሁ፣ አክሱም ጫፍ ጥገት አስሬ፤
ሰሜን ያለብኩትን ወተት፣ በአርሲ ጮጮ የሞላሁ ፤
ጋምቤላ ወተቱን ንጬ ፣ የሀረሪ ቆንጆ የቀባሁ፡፡ .
ወሰን የለሽ እግረ ፌንጣ፣
ሞተ ሲሉኝ ብን ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
የቅገዠት ምች፣ ህልም ፈቺ፣ ዳነው ሲሉኝ የማገረሽ፤
ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
ጎጥ አይበቃኝ - የሀገር ስፍር ፤
ጎሳ አይገልጠኝ - የሰው ስእል፡፡ .
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ማሳዬ ላይ ገበሬ፤ ምድር አራሽ፣
ድንበሬ ላይ ወቶአደር፣ ጠላት ደምሳሽ፣
ከበሬዬ ቀንበር ከሞፈር፣
ከወገቤ ላይ ዝናር፣
ከጀርባዬ ላይ ዲሞትፈር፣
የማላጣ፤
ለወደደኝ እንዳወዳደዱ፣ ከማሳዬ ፍሬ የማልስስት፤
ለጠላኝ እንደ ድርፈቱ፣ ከጀርባዬ ባሩድ የምግት ; .
እልኸኛ!
እንደምስጥ በቁም የምጥል፤
ተበድዬ የማልተኛ፡፡
ለደፈሩኝ አድዋን ያህል ተራራ፣ ሀውልት ያቆምኩ በሀገሬ
ነጻነቴን ሰንደቄን ያተምኩ፣ ሮም ላይ ተሻግሬ፤
ያውም እንደፈጠረኝ፣ በባዶ እግሬ ፤
ኢትጵያዊ ነኝ!!
እንደ እየሱስ እንጂ በፍቅር፤
ለመርዘኛ የተንኮል ስፍር፣
የማልመች፣ አታጥልሉኝ ባይ፣
ክታብ የአብሮነት ሲሳይ፤
በጅምላ የማልቀመስ ፤
በችርቻሮ የማልረክስ፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ጃውሌ የደንጊያ እጣን፣ ከርቤ ከጊንር ቋጥሬ፤
አቦዳይ ጫት ተዘይሬ፤
ጂማ ካባጁፋር መንደር፣ ከአዎል - በረካ ጀባ ፤
ሶዶ ዋዳ ተዘፍኖልኝ - ጎይ ላይ ቃጢራ አድሬ፤
አፋር ላይ በግመል እንገር፣ ምርቃናዬን የሰበርኩ፤
የሀገሬን ባንዲራ፣ ለአፋር ግመል ማተብ ያሰርኩ፡፡
ወሰን የለሽ፣ እግረ ፌንጣ፣
ሞተ ሲሉኝ ብን - ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
የቅዠት ምች፣ ህልም ፈቺ፣ ዳነው ሲሉኝ የማገረሽ፤
ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
ጎጥ አይበቃኝ - የሀገር ስፍር፤
ጎሳ አይገልጠኝ - የሰው ስእል፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
ግንቦት፣ 2012፣ ኣዲስ ኣበባ፡፡
በላሊበላ አስቀድሼ፣ ሽህ ሁሴን ባሌ የተገኘሁ፤
በአባ ገዳ ተመራርቄ፣ መካ ላይ እርዝቅ ያገኘሁ፡፡
ሀመር የቡርጆ አደራ
ፈጣሪ ከሰጠኝ በረከት፣ ዘመን አያነጥፈው ወረት፤
የሚገባኝን ለሰጠኝ፣ የሚገባውን የምገመድል ፤
ለሞላልኝ የማላጎድል።
በሲዳማ ጨንበለላ፣
በወላይት ጊይታ፣
ቢያሻኝ በቅዳስ ዮሀንስ፣
የዘመን ጥባት የምከትብ፣ አዲስ አመት የማወድስ፡፡
በጅምላ የማልቀመስ፤
በችርቻሮ የማልረክስ፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ሳነቴ ላይ ውርጭና ጉም፣ ዳሽን ጫፍ ግግር በረዶ፧
ደሎ መና የአዋራ ጭስ፣ ዳሎል ላይ የእሳት እርጎ፡፡
ይርጋለም ያጋጥኳትን ላም፣ ወለጋ ላይ አስጠቅቼ፤
ትኩስ እንገርዋን የጠጣሁ፣ አክሱም ጫፍ ጥገት አስሬ፤
ሰሜን ያለብኩትን ወተት፣ በአርሲ ጮጮ የሞላሁ ፤
ጋምቤላ ወተቱን ንጬ ፣ የሀረሪ ቆንጆ የቀባሁ፡፡ .
ወሰን የለሽ እግረ ፌንጣ፣
ሞተ ሲሉኝ ብን ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
የቅገዠት ምች፣ ህልም ፈቺ፣ ዳነው ሲሉኝ የማገረሽ፤
ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
ጎጥ አይበቃኝ - የሀገር ስፍር ፤
ጎሳ አይገልጠኝ - የሰው ስእል፡፡ .
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ማሳዬ ላይ ገበሬ፤ ምድር አራሽ፣
ድንበሬ ላይ ወቶአደር፣ ጠላት ደምሳሽ፣
ከበሬዬ ቀንበር ከሞፈር፣
ከወገቤ ላይ ዝናር፣
ከጀርባዬ ላይ ዲሞትፈር፣
የማላጣ፤
ለወደደኝ እንዳወዳደዱ፣ ከማሳዬ ፍሬ የማልስስት፤
ለጠላኝ እንደ ድርፈቱ፣ ከጀርባዬ ባሩድ የምግት ; .
እልኸኛ!
እንደምስጥ በቁም የምጥል፤
ተበድዬ የማልተኛ፡፡
ለደፈሩኝ አድዋን ያህል ተራራ፣ ሀውልት ያቆምኩ በሀገሬ
ነጻነቴን ሰንደቄን ያተምኩ፣ ሮም ላይ ተሻግሬ፤
ያውም እንደፈጠረኝ፣ በባዶ እግሬ ፤
ኢትጵያዊ ነኝ!!
እንደ እየሱስ እንጂ በፍቅር፤
ለመርዘኛ የተንኮል ስፍር፣
የማልመች፣ አታጥልሉኝ ባይ፣
ክታብ የአብሮነት ሲሳይ፤
በጅምላ የማልቀመስ ፤
በችርቻሮ የማልረክስ፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
ጃውሌ የደንጊያ እጣን፣ ከርቤ ከጊንር ቋጥሬ፤
አቦዳይ ጫት ተዘይሬ፤
ጂማ ካባጁፋር መንደር፣ ከአዎል - በረካ ጀባ ፤
ሶዶ ዋዳ ተዘፍኖልኝ - ጎይ ላይ ቃጢራ አድሬ፤
አፋር ላይ በግመል እንገር፣ ምርቃናዬን የሰበርኩ፤
የሀገሬን ባንዲራ፣ ለአፋር ግመል ማተብ ያሰርኩ፡፡
ወሰን የለሽ፣ እግረ ፌንጣ፣
ሞተ ሲሉኝ ብን - ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
የቅዠት ምች፣ ህልም ፈቺ፣ ዳነው ሲሉኝ የማገረሽ፤
ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
ጎጥ አይበቃኝ - የሀገር ስፍር፤
ጎሳ አይገልጠኝ - የሰው ስእል፡፡
ኢትጵያዊ ነኝ!!
🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘
ግንቦት፣ 2012፣ ኣዲስ ኣበባ፡፡