#የከርሠ_ምድር_ሰው
በምድር ላይ ሳለሁ
በጀርባ እማይበት ሦስተኛ ዓይን የለኝ
ማን እንደሁ አላወኩም ግፍትሮ የጣለኝ
አሁን ገደል ሥር ነኝ፡፡
እጄን አልሰጠሁም ለመውጣት ሞከርኩኝ
ግድግዳ ቧጠጥኩኝ
እምይዘው አጥቼ የንግልል ወደቅኩኝ፡፡
ተነሳሁ ዳከርኩኝ
ደጋግሜ ጣርኩኝ
ለመውጣት አልቻልኩም ሞክሬ ተሳነኝ
ያለሰው ብቻዬን ብዙ ጊዜ ሆነኝ
ከከርሠ ምድር ውስጥ አሁን ግደል ሥር ነኝ፡፡
የግራና የቀኝ
ግድግዳዎች በቀር ከገደሉ በላይ ፤
ከሩቅ ይታየኛል ተስፋዬ ሰማይ ላይ፡፡
የመውጣቴ ተስፋ
ከውስጤ ሲጠፋ
ላዬ ላይ “ሚወርደው አንዳንዴ እንደግርሻ፤
ተስፋ ይዘራብኛል የሰዎች ቆሻሻ፡፡
ተስፋዬ እንዳይጠፋ
ጭራሽ እንዳይመክን ሰዎቹ ሲጠፉ ፤
እናፍቅ ጀመረ ቆሻሻ እንዲደፉ፡፡
አወጣ አወርዳለሁ
እንደዚህ አስባለሁ፡፡
“ገደል ሥር አዳሪ ቆሻሻ አላሚ
ሆኜ እቀር ይሆን?
ወይስ ያዩኝ ይሆን? ሰዎች በአጋጣሚ፡፡
“አፋልጉኝ" የሚል ስው አንድም እንኳ የለም?
ወይስ ተለይቶ
የእኔ ከዓይን መጥፋት አሳሳቢ አይደለም?
አስጨናቂ አልሆነም ?
ከቢሊዮናት መሐል የእኔ ቁጥር መጉደል፤
ራሴን እማይበት
መስታወት ሆኖኛል የገፊዎች በደል፤
ለካስ ኢምንት ነኝ!
ለዓለም እማላጉል እማልሞላ ጎደል፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
በምድር ላይ ሳለሁ
በጀርባ እማይበት ሦስተኛ ዓይን የለኝ
ማን እንደሁ አላወኩም ግፍትሮ የጣለኝ
አሁን ገደል ሥር ነኝ፡፡
እጄን አልሰጠሁም ለመውጣት ሞከርኩኝ
ግድግዳ ቧጠጥኩኝ
እምይዘው አጥቼ የንግልል ወደቅኩኝ፡፡
ተነሳሁ ዳከርኩኝ
ደጋግሜ ጣርኩኝ
ለመውጣት አልቻልኩም ሞክሬ ተሳነኝ
ያለሰው ብቻዬን ብዙ ጊዜ ሆነኝ
ከከርሠ ምድር ውስጥ አሁን ግደል ሥር ነኝ፡፡
የግራና የቀኝ
ግድግዳዎች በቀር ከገደሉ በላይ ፤
ከሩቅ ይታየኛል ተስፋዬ ሰማይ ላይ፡፡
የመውጣቴ ተስፋ
ከውስጤ ሲጠፋ
ላዬ ላይ “ሚወርደው አንዳንዴ እንደግርሻ፤
ተስፋ ይዘራብኛል የሰዎች ቆሻሻ፡፡
ተስፋዬ እንዳይጠፋ
ጭራሽ እንዳይመክን ሰዎቹ ሲጠፉ ፤
እናፍቅ ጀመረ ቆሻሻ እንዲደፉ፡፡
አወጣ አወርዳለሁ
እንደዚህ አስባለሁ፡፡
“ገደል ሥር አዳሪ ቆሻሻ አላሚ
ሆኜ እቀር ይሆን?
ወይስ ያዩኝ ይሆን? ሰዎች በአጋጣሚ፡፡
“አፋልጉኝ" የሚል ስው አንድም እንኳ የለም?
ወይስ ተለይቶ
የእኔ ከዓይን መጥፋት አሳሳቢ አይደለም?
አስጨናቂ አልሆነም ?
ከቢሊዮናት መሐል የእኔ ቁጥር መጉደል፤
ራሴን እማይበት
መስታወት ሆኖኛል የገፊዎች በደል፤
ለካስ ኢምንት ነኝ!
ለዓለም እማላጉል እማልሞላ ጎደል፡፡
🔘ፋሲል ተካልኝ🔘