ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
እልልልልልልልልልልል እንኳን አደረሳችሁ
ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ
ገብርኤልን ላከላቸው::
+ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ
ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6
ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ
በተጸነሰ ጊዜ #የአርያም_ንግሥት #ድንግል_እመቤታችን ደጋ
ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት
የእህትማማች ልጆች ናቸው::
+የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው # መንፈስ_
ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ
ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ
በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ
" #ዮሐንስ " ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
+"+ # መጥምቀ_መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ +"+
¤የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ጌታውን ያጠመቀና
¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
+ስለዚሕም #ቤተ_ክርስቲያን # ነቢይ: # ሐዋርያ: #ሰማዕት :
# ጻድቅ : #ገዳማዊ : #መጥምቀ_መለኮት: # ጸያሔ_ፍኖት :
# ቃለ_ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::
እንኩዋን ለቅዱስ #አባ_ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
+ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ( #ወንጌሉ_ዘወርቅ )
ቅዱሱ"ወንጌሉ ዘወርቅ" እየተባለ የሚጠራው ከሌሎች
#ዮሐንስ ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው
ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው: ከእጁ በማይለይ የወርቅ ወንጌል ነው
#ቅዱሳን_ስምዖንና_ዮሐንስ
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ አስደናቂ ታሪክ ካላቸው #ጻድቃን
እነዚህ 2ቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: እርሱስ እንደ ምን ነው
ቢሉ:-
ቅዱሳኑ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ተወልደው
ያደጉ ክርስቲያኖች ናቸው::
ዘመዳሞች ከመሆናቸው ባሻገር አብረው ስላደጉ እጅጉን
ይፋቀሩ ነበር:: የዋሃንም ነበሩ:: ወጣት በሆኑ ጊዜ ትልቁ
#ዮሐንስ ሚስት አገባ:: ታዲያ አንድ ቀን ከጌታችን መቃብር
#ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ #ገዳመ_ዮርዳኖስ አካባቢ
ደረሱ:: እርስ በርሳቸውም "ይህ ገዳምኮ የመላእክት ማደሪያ
ነው" ተባባሉ::
በዚያውም መንነው ለመቅረት አሰቡ:: ፈረስና ንብረታቸውን
ለዘመዶቻቸው ልከው ጸሎት አደረሱ:: ፈቃደ እግዚአብሔርን
ሊረዱም ዕጣ ተጣጣሉ:: ዕጣውም "ወደ ገዳም ሒዱ"
የሚል ስለሆነ ተቃቅፈው ደስ አላቸው::
ወደ ገዳሙ ሲደርሱም አበ ምኔቱ #አባ_ኒቅዮስ ፈጣሪ
አዞት የገዳሙን በር ከፍቶ ጠበቃቸው:: ተቀብሎ
ሲያስገባቸውም አንድ ደግ መነኮስ ሲያልፍ: ቆቡ ቦግ ቦግ
እያለ እንደ ፋና ሲያበራ እና #መላእክት ከበውት አዩ::
ወዲያውም አበ ምኔቱን "እባክህ አመንኩሰን" አሉት::
እርሱም የአምላክ ፈቃድ ነውና በማግስቱ አመነኮሳቸው::
ፍቅረ ክርስቶስ ገዝቷቸዋልና በጥቂት ዓመታት ተጋድሎ
ከብቃት (ከጸጋ) ደረሱ:: 2ቱም ቆመው በፍቅር ሲጸልዩ
የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ይወርድ ነበር:: አካላቸውም
በሌሊት ያበራ ነበር::
እንዲህ ባለ ቅድስና ለዓመታት ቆይተው ከገዳሙ ወደ ጽኑ
በርሃ ሊሔዱ ስለ ፈለጉ የገዳሙ በር በራሱ ተከፈተ:: አበ
ምኔቱ አባ ኒቆን (ኒቅዮስ) እያነባ በጸሎት ሸኛቸው::
በበርሃም በጠባቡ መንገድ: በቅድስና ተጠምደው ለ29
ዓመታት ተጋደሉ:: በዚህ ሰዓት ግን 2ቱን የሚለያይ ምክንያት
ተፈጠረ::
#እግዚአብሔር ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ እንዲገባ: ቅዱስ
ዮሐንስ ግን በዚያው እንዲቆይ አዘዘ:: 2ቱ ለረዥም ሰዓት
ተቃቅፈው ተላቅሰው ተለያዩ:: ከ50 ዓመታት በላይ
ተለያይተው አያውቁም ነበርና::
#ቅዱስ_ስምዖን ወደ ከተማ ሲገባ ክብሩን ይደብቅ ዘንድ
እንደ እብድ ሆነ:: በዚህ ምክንያትም የወቅቱ ከተሜዎች
ይንቁት: በጥፊም ይመቱት ነበር:: (እባካችሁ ብዙ
በየመንገዱ የወደቁ አባቶች አሉና እንጠንቀቅ!) ቅዱሱ ግን
ስለ እነርሱ ይጸልይ ነበር::
በከተማዋ የነበሩ እብዶችን ሁሉንም በተአምራት
ፈወሳቸው:: አንድ ቀን ግን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች
ደብድበውት ደከመ:: የእግዚእብሔር መልአክ ወርዶ "ና
ልውሰድህ" ብሎ ዮሐንስን ከበርሃ: ስምዖንን ከከተማ
በዚህች ቀን ወሰዳቸው:: እነሆ ብርሃናቸው ዛሬም ድረስ
ለሚያምንበት ሁሉ ያበራል::
#ታላቁ_ቅዱስ_መቃርስ
ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ( #መቃሬ ) "ጽድቅ እንደ መቃርስ"
የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ
የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ:
ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም
ጻድቅ ነው::
በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት
በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው
#ቅዱስ_መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ
ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ
ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነንጉሳቸው አጥምቀዋል::
በተሰደዱባት ሃገርም #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ (ስም
አጠራሩ ይክበርና) #እመቤታችንን : #ቅዱሳን_ሐዋርያትን :
#አዕላፍ_መላእክትን : በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን #ዳዊትን:
#ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: #ማርቆስን:_
ዼጥሮስን:_ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል::
በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
ታላቁ ቅዱስ መቃርስና መቃርዮስ ከ2 ዓመታት ስደትና መከራ
በሁዋላ ስደት በወጡባት በዚችው ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ
ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል
ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ
ወጥተዋል::
ይህች ዕለት ለአባታችን መቃሬ በዓለ ፍልሠቱ ናት::
ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት
በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ
ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ
በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት
ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ
ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም
ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ
ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ
እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ
መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት
ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::
በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው
በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን:
ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ
ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ
እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ
ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ
ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ
ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና
በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::
በወቅቱ ደግሞ #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ የንስሃ
ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ
እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ
ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6
ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::
ለ6 ወራት ከቅዱስ #ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ
ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ተጠመቀ::
በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ
እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው
ጠየቀው::
"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል
ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ::
(ሉቃ. 7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ::
ጌታም ከ72ቱ #አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት
ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: (ሉቃ. 10:17)
ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም ከዋለበት
እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር
አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ
ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኩዋል::
በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ #ሐዋርያት
ቅስናን (ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም
#መንፈስ_ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን
ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም::
በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::
በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት
ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7
#ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ
ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ)
ሆኗል::
8ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ
እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን
ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኩዋ እጅግ ፈተና
ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት:
ማሕደረ እግዚአብሔር' ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ.
6:5)
አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት'
ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ
በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ 'በራት
ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ
ዲያቆን ብቻ አይደለም::
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በሁዋላ ለ 1 ዓመት
ያህል 8ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ
ቢጋደል #ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': #ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ
እሰፋ' አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት
መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው' ብለው
አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ
ገደሉት::
እርሱ ግን ፊቱ እንደ #እግዚአብሔር መልአክ እያበራ
ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ
እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ
መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::
ፍልሠት
ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በሁዋላ
በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም
#ሉክያኖስ ይባል ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ
እየተገለጠ "ሥጋየን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ
ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም ደስ ብሎት ካህናትና
ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ # ገማልያል (የመምሕሩ
ርስት ነው) ሔደ::
ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ::
መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ
መላእክትም ተሰማ:: ሕዝቡና ዻዻሱም በቅዱስ
እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ ዝማሬና በሐሴት
ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ #ጽዮን
(በተቀደሰችው ቤት) አኖሩት::
#እለ_እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ ክርስቲያን
አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት በሁዋላም እለ
እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን ስለ
ፍቅሩ አኖሩት:: ሚስቱ ወደ ሃገሯ #ቁስጥንጥንያ
ስትመለስ የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን
ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው::
መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው
ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ አላት:
አምላክ ለዚህ አድሏታልና:: እርሷም ወስዳ ለታላቁ
ንጉሥ #ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም
ታላቅ ሐሴት ተደረገ::
ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም
በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች::
በዚያም ላይ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ
እስጢፋኖስ ሲመቱ ጥቅምት 17: ዕረፍቱ ጥር 1:
ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም 15 ቀን ነው::
Forwarded from ግጻዌ
#የካቲት_18
፫ተኛ መዝሙር ዘምኵራብ ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ ይሁዳ፡፡
#ዘቅዳሴ
#ቆላስ_2:16-ፍጻሜ፡ዑቁ እንከ አልቦ ዘይግእዘክሙ"እንግዲህ በመብልም ቢሆን በመጠጥም ቢሆን በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን በመባቻም ቢሆን በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡...............................................................................ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለውም፡፡"
#ያዕቆብ_2:14-ፍጻሜ፡ምንተ ይበቁዕ አኃዊነ"ወንድሞቻችን ሆይ እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?...........................................................................ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ አንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_10:1-9፡ወሀሎ ፩ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ"በቂሳርያም ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ.........................................................................................ነገሩንም ሁሉ ነግሮ ወደ ኢዮጴ ከተማ ላካቸው፡፡"
#ምስባክ
እስመ ቅንአተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
#ትርጉም
የቤትህ ቅናት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና
ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡
#መዝ_68:9-10
#ወንጌል
#ዮሐንስ_2:12-ፍጻሜ፡ወእምድኅረ ዝንቱ ወረዱ ቅፍርናሆም"ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ....................
................................................የሰውንም ግብሩን ሊነግሩት አይሻም እርሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኵተከ)
@gitsawe
Forwarded from ግጻዌ
#የካቲት_25
፬ተኛ መዝሙር ዘመፃጉዕ አምላኩሰ ለአዳም
#ዘቅዳሴ
#ገላትያ_5:1-ፍጻሜ፡ቁሙ እንከ ወኢትሑሩ ዳግመ"እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ፡፡...........
.................................................ኩሩዎች አንሁን እርስ በርሳችን አንተማማ እርስ በርሳችንም አንቀናና፡፡"
#ያዕቆብ_5:14-ፍጻሜ፡ወእመቦ ዘይደዊ አምኔክሙ"ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቀቡት፡፡...
................................................ኀጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ራሱን ከሞት እንደ አዳነ ብዙ ኀጢአቱንም እንደ አስተሰረየ ይወቅ፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_3:1-12፡ወዐርጉ ምኵራበ ጴጥሮስ"ጴጥሮስና ዮሐንስም በዘጠኝ ሰዓት ለጸሎት በአንድነት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፡፡.....................................................................................ጴጥሮስና ዮሐንስም ይዘውት ወደ መቅደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደንግጠው ወደ ሰሎሞን መመላለሻ ወደ እነርሱ ሮጡ፡፡"
#ምስባክ
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሀለኒ
#ትርጉም
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል
እኔስ አቤቱ ማረኝ
#መዝ_40:3-4
#ወንጌል
#ዮሐንስ_5:1-25፡ወእምድኅረዝ ኮነ በበዓሎሙ ለአይሁድ"ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡......................................................................................እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛል ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይሄድም፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኵተከ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ግጻዌ
#መጋቢት_16
፯ተኛ መዝሙር ዘኒቆዲሞስ ሖረ ኀቤሁ፡፡
#ዘቅዳሴ
#ሮሜ_7:1-12፡ኢተአምሩኑ አኃዊነ ሕገ ንነግረክሙ"ወንድሞቻችን! ሕግን ለሚያስተውሉ እናገራለሁና ሰው በሕይወት ባለበት ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?............
................................................ኀጢአት በዚያች ትእዛዝ ምክንያት አሳተችኝ በእርሷም ገደለችኝ፡፡"
#1ኛ_ዮሐንስ_4:18-ፍጻሜ፡
ወአልቦ ፍርሃት ውስተ ተፋቅሮትነ"በፍቅር መፈራራት የለም ፍጽምት ፍቅር ፍርሀትን ወደ ውጭ ታወጣለች እንጂ ፍርሀት ቅጣት አለባት የሚፈራም በፍቅር ፍጹም አይደለም፡፡.....................
................................................እግዚአብሔርን የሚወድ ሁሉ ወንድሙን ይወድዳል፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_5:34-ፍጻሜ፡
ወተንሥአ ፩ እምውስተ ዐውድ"በሸንጎዉም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የከበረ የኦሪት መምህር ስሙን ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ ተነሣ............................
................................................ሁልጊዜም በቤተ መቅደስና በቤት ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አልተዉም፡፡"
#ምስባክ
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዐመፃ በላዕሌየ
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው፡፡
#ትርጉም
ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ
ፈተንከኝ ምንም አላገኘህብኝም
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡" #መዝ_16:3-4
#ወንጌል
#ዮሐንስ_3:1-12፡ወሀሎ ፩ ብእሲ እምፈሪሳውያን"ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፡፡.............
.................................................እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉንም፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዐ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ግጻዌ
#፴፱_በሆሣዕና ዋዜማ ቅዳሜ ማታ
#ዕብራው_8:1-ፍጻሜ፡እስመ ቀዳሚሁ ለዝንቱ ኵሉ"ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው...................................
..አዲስ ትእዛዝ በማለቱ የቀደመችቱን አስረጃት አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ለጥፋት የቀረበ ነው፡፡
#1ኛ_ጴጥሮስ_1:13-ፍጻሜ፡
ወይእዜኒ ቅንቱ ሐቋ ልብክሙ"ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ..........................
........በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_8:26-ፍጻሜ፡ወነበቦ መልአከ እግዚአብሔር"የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው.....
.................................................በከተማዎችም ሁሉ እየተዘዋወረ ወደ ቂሣርያ እስኪደርስ ድረስ ያስተምር ነበር፡፡"
#ምስባክ
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ
በዕምርት ዕለት በዓልነ
እስመ ሥርዐቱ ለእስራኤል ውእቱ፡፡
#ትርጉም
በመባቻ ቀን በከፍተኛውም በዓላችን ቀን
መለከትን ንፋ
ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና
#መዝ_80:3-4
#ወንጌል
#ዮሐንስ_12:1-12፡ወእምዝ ሖረ ኢየሱስ እምቅድመ ስዱስ"ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን ...
................................................ከአይሁድ ብዙዎች ስለ እርሱ እየሄዱ በጌታችን በኢየሱስ ያምኑ ነበርና፡፡"
@gitsawe
Forwarded from ግጻዌ
#ሰኔ_3(ዘሰንበት)
፲፩ኛ እሁድ ከጰራቅሊጦስ በኋላ መዝሙር ዘምሩ ለእግዚአብሔር፡፡
#ዘቅዳሴ
#1ኛ_ቆሮ_14:1-27፡ዴግንዋ ለተፋቅሮ ወተቃኀዉ"ፍቅርን ተከተሏት ለመንፈሳዊ ስጦታ ይልቁንም ትንቢት ለመናገር ተፎካከሩ፡፡................................................................................በቋንቋ መናገር አላችሁ መተርጎምም አላችሁ ሁሉም ለሚታነጽበት ጥቅም አድርጉት፡፡"
#1ኛ_ዮሐንስ_4:1-9፡አኃዊነ ለኵላ መንፈስ ኢትእመኑ"ወንድሞቻችን ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ............
.................................................ወንድሙን የማያፈቅር እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_10:44-ፍጻሜ፡
ወእንዘ ይነግሮሙ ጴጥሮስ"ጴጥሮስም ይህን ነገር ሲነግራቸው ይህን ትምህርት በሰሙት ሰዎች ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ፡፡............................
................................................በኢየሱስ ክርስቶስም ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው፡፡ከዚህም በኋላ ጥቂት ቀን አብሮአቸው እንዲቀመጥ ጴጥሮስን ማለዱት፡፡"
#ምስባክ
ኢትግድፈኒ እምቅድመ ገጽከ
ወመንፈስከ ቅዱሰ ኢታውፅእ እምላዕሌየ
ዕስየኒ ፍሥሓ ወአድኅኖተከ፡፡
#ትርጉም
ከፊትህ አትጣለኝ
ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ፡፡
የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፡፡
#መዝ_50:11-12
#ወንጌል
#ዮሐንስ_15:17-ፍጻሜ፡ወዘንተ እኤዝዘክሙ ከመ ትትፋቀሩ"እርስ በርሳችሁም እንድትዋደዱ ይህን አዥዣችኋለሁ፡፡..........................................................................እናንተም ትመሰክራላችሁ ከጥንት ጀምሮ ከእኔ ጋር ኑራችኋልና፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘዲዮስቆሮስ፡፡
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ግጻዌ
#ሰኔ_8
ተዝካረ ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያና ለእግዝእትነ ወትምዳ ወውሉዳ ወአረኮን ፲፻ወ፪ ሰማዕታት፡፡
#ዘቅዳሴ
#ኤፌሶን_2:13-ፍጻሜ፡ወይእዜሰ ባሕቱ አንትሙ እለ ትካት"አሁን ግን ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀረባችሁ፡፡.........
................................................እናንተ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ልትሆኑ በእርሱ ታነጻችሁ፡፡"
#1ኛ_ጴጥሮስ_1:10-13፡ይእቲኬ መድኃኒት"ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩ ነቢያት የመረመሩአትና የፈለጉአት መድኀኒት ናት፡፡..........................
.................................................ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_7:44-51፡ወደብተራ ስምዕ እንተ ነበረት"ሙሴን ተናግሮ እንደ አዘዘው በአሳየው ምሳሌ የሠራት የምስክር ድንኳን በአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፡፡....................................................................................ይህን ሁሉ እጆቼ የሠሩት አይደለምን?"
#ምስባክ
ወአስተዮሙ ከመ ዘእምቀላይ ብዙኅ
ወአውኀዘ ማየ ከመ ዘእምአፍላግ
ወአውፅአ ማየ እምእብን፡፡
#ትርጉም
ከጥልቅ እንደሚገኝ ያህል በብዙ አጠጣቸው
ውኃን ከጭንጫ አወጣ
ውኃንም እንደ ወንዞች አፈሰሰ፡፡
#መዝ_77:15-16
#ወንጌል
#ዮሐንስ_4:1-15፡ወአእሚሮ እግዚእነ ከመ ሰምዑ"ጌታችን ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርትን እንደ አበዛና እንደሚያጠምቅ ፈሪሳውያን መስማታቸውን ዐወቀ፡፡................
................................................እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዓ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
💚💛ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር💛❤️
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት
ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ #አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም::
እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ
ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም::
በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም " #ዮሐንስ_ሐጺር -
አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል:: ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ
ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም
ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::

ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ
ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ
መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል::
ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ
ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር
በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ
ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው
ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ
"አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር:: ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::

#አባ_ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ
ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ
ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::

አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ
ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ
መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል:: ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና
ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው
አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ
አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ
ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ
ወስዶ ተከለው:: ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ:: በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው
በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ
ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም:: ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው:- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው::" ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::
መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ
ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው
ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ
ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ
አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
#መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ
ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር::
ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን
ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ
(ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን
#ሊቃነ_መላእክት #ሚካኤል እና #ገብርኤል በግርማ በጌታ
ፊት ቆመው ተመለከተ::
"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ
እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ
ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን
ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ #ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ
ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ
#ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
በ825 ዓ/ም ግን በአባ #ዮሐንስ_ፓትርያርክ ዘመን ክቡር
ሥጋው ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው
ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ
ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ #ቅዱስ_መቃርስ
ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ
ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል:: ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ::
ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ
ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን::
በበረከቱም ይባርከን::
Dn yordanos abebe
🌼መስከረም 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት🌼
1.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
2.ቅዱስ ዳስያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዲዲሞስ ሰማዕት
4.ቅድስት መሪና

🌻ወርኀዊ በዓላት🌻
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
" #‎ጌታ_ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ #‎ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው #‎ኤልያስ ይሕ ነው::
የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ:: " (ማቴ 11፥7-15)
💚💛 አቡነ ተጠምቀ መድኅን 💛❤️

ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::

ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም::

ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::

ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:-

1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል
2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል
3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና)
4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::

ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል::
እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል::
from: d/n yordanos abebe

@senkesar @senkesar

-----------+++++++++++-----------
እንድትከታተሉት የምንጋብዞ ቻናል
1⃣ዓውደ ምህረት
@AwediMeherit

2⃣ ተዋህዶ የወጣቶች ቻናል @Tewahedoyouth

3⃣ሐዊረ ሰላም
@hawireselam
💚💛 ጻድቃን እንድራኒቆስ ወአትናስያ 💛❤️
ሁለቱ ቅዱሳን ባል እና ሚስት (ባለትዳር) ናቸው:: የነበረበት ዘመን 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እስኪ #እግዚአብሔር የቀደሰው ጋብቻ ምን እንደሚመስል እንመልከት::

#እንድራኒቆስና_አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ : ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ:: ዘመኑ ደርሶ በሚገባው የተክሊል ሥርዓት ጋብቻቸውን ፈጸሙ:: 40 ቀን ከተፈጸመ በሁዋላ ከምንም ነገር በፊት 2ቱ ቁጭ ብለው ተወያዩ::

የውይይታቸው ርዕስ ደግሞ "ፈጣሪያችን በምን እናስደስተው" የሚል ነበር:: ውይይታቸው የጠናቀቀው በእነዚህ ውሳኔዎች ነው::
1.ሁልጊዜም እንግዳ መቀበል አለብን::
2.ነዳያን ከቤታችን ሊጠፉ አይገባም::
3.ጸሎት : ጾምና ስግደት በቤት ውስጥ አይቁዋረጥም::
4.አብሮ ለመተኛት መቸኮል የለብንም::

እነርሱ መልካምን አስበዋልና አምላክ የሰጣቸውን ሃብት ሲመጸውቱ ኖሩ:: ከዘመናት የቅድስና ጉዞ በሁዋላ በፈቃደ እግዚአብሔር 2 ልጆችን አከታትለው ወለዱ:: ወንዱን "#ዮሐንስ" : ሴቷን ደግሞ "#ማርያም" አሏት::

እነርሱን ከወለዱ በሁዋላ እንደ ገና ሌላ ውሳኔ አሳለፉ:: "ይህንን ላደረገልን ጌታ ከዚህ በሁዋላ አልጋ እንለያለን" ብለው ለ12 ዓመታት በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::
+ሕጻናቱ ዮሐንስና ማርያም በቅንነት አድገው እድሜአቸው 12 ሲሆን 2ቱም በአንድ ቀን ታመው ሞቱ:: ይህ ለአንድ ወላጅ የመጨረሻው አሰቃቂ ፈተና ነው:: ሁሉቱም (እንድራኒቆስና ሚስቱ አትናስያ) ልጆቻቸውን ታቅፈው ወስደው ቀበሩ::

#እንድራኒቆስ ከቀብር በሁዋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምርር ብሎ አለቀሰ:: ግን እንዲህ አለ:-
"አምላከ #ኢዮብ! አንተ ሰጠኸኝ:: አንተም ነሳኸኝ:: ስምህ ለዘለዓለም ይባረክ" ብሎ ሔደ:: እናት #አትናስያ ግን ከሐዘን ብዛት ልቡናዋ ሊሠወር ጥቂት ቀረው::

የልጆቿ መቃብር ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ቅዱስ መልአክ ልቡናዋን ወደ ሰማይ አሳረገው:: ልጆቿ ዮሐንስና ማርያም በገነት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ሐሴትን ሲያደርጉም ተመለከተች:: ወዲያው ወደ ቤት ተመልሳ ለባሏ እንድራኒቆስ ያየችውን ነገረችውና ደስ አላቸው::

እዛው ላይ "ለዚህ ውለታው ከነፍሳችን ውጪ የምንሰጠው የለም" ብለው ሊመንኑ ተስማሙ:: እጅግ ሃብታሞች ነበሩና ነዳያንን ሰብስበው : ሃብት ንብረታቸውን : ቤት ርስታቸውን አካፍለው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዱ::

እርሷ ከሴቶች ገዳም : እርሱ ደግሞ ከወንዶቹ ገቡ:: ለ12 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ተገዙ:: በእነዚህ ዘመናት ተያይተው : አንዱ ስለ ሌላው ሰምቶ አያውቅም:: በጸሎት ግን ያለማቁዋረጥ ይተሣሠቡ ነበር::

ከ12 ዓመታት በሁዋላ የፍቅር አምላክ በሁለቱም ልቡና በተመሳሳይ ሰዓት : ተመሳሳይ ሐሳብን አመጣ:: እርሱ ከአበ ምኔቱ (#ታላቁ_አባ_ዳንኤል) : እርሷም ከእመ ምኔቷ አስፈቅደው ወደ #ኢየሩሳሌም ከቅዱሳት መካናት ለመባረክ ጉዞ ጀመሩ:: በየፊናቸው ጥቂት እንደተጉዋዙ እርስ በርስ ተያዩ::
+እርሷ ለየችው:: እርሱ ግን ጭራሽ ሊለያት አልቻለም:: ይህም ጥበበ እግዚአብሔር ነው:: 2ቱም እየተጫወቱ : እየጸለዩ በሰላም ተባርከው ወደ ግብጽ ተመለሱ:: በእነዚህ ጊዜያት ቅድስት አትናስያን የሚለያት አልነበረም:: አካሏ በገድል ከመለወጡ ባሻገር የለበሰችው እንደ ወንድ መነኮሳት ነበር::

ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ሲደርሱ ጸጋው ተሰጥቶታልና #አባ_ዳንኤል ባልና ሚስት መሆናቸውን አወቀ:: "ለምን አብራችሁ አትኖሩም?" አላቸው:: "እኛ ደስ ይለናል" አሉት:: ከዚያ እርሷ እያወቀችው: እርሱ ሳያውቃት ለ12 ዓመታት አብረው በቅድስና ኖሩ::

ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላ ግን ሐምሌ 28 ቀን ቅድስት #አትናስያ ታመመች:: አባ ዳንኤል ሥጋውን ደሙን አቀብሏትም ዐረፈች:: ሊገንዟት ሲቀርቡ ቅዱስ #እንድራኒቆስ መልኩዋን ልብ ቢለው ሚስቱ ናት::

በአንድ ጊዜ ሚስቱንና የሚወደውን ባልንጀራ በማጣቱ አለቀሰ:: እርሷን ቀብረው ወደ በዓቱ ተመልሶ "ጌታ ሆይ! ውሰደኝ?" አለ:: እርሱም ተከትሏት ዐረፈ:: አባ ዳንኤል እርሱንም ቀብሮ ጥዑም ዜናቸውን ጻፈ::
From:- dn yordanos abebe
@senkesar @senkesar
ሰላም ለከ #ዮሐንስ : ዘረፈቀ ውስተ ኅጽኑ #ለኢየሱስ

~በጌታ ደረት ላይ ለተጠጋህ::
~እሳቱ ላላቃጠለህ::
~መለኮት ለሳመህ::
~ድንግል ላቀፈችህ::
<ላንተ (ለዮሐንስ) ሰላምታ ይገባሃል!!>>

ከብዙ ጸጋህ . . . ለእኛ ለባሮችህ ጌታንና ድንግል እናቱን መውደድን እንድትሰጠን እንማጸንሃለን !!
አሜን!

@senkesar