ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
4ቱ_ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ
ስማቸው #አባ_አክራ : #አባ_ዮሐንስ : #አባ_አብጥልማ
#አባ_ፊልዾስ ይባላሉ::
እንኩዋን ለቅዱስ #አባ_ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
+ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ( #ወንጌሉ_ዘወርቅ )
ቅዱሱ"ወንጌሉ ዘወርቅ" እየተባለ የሚጠራው ከሌሎች
#ዮሐንስ ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው
ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው: ከእጁ በማይለይ የወርቅ ወንጌል ነው
🙏 እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏

#4ቱ_ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ
ስማቸው #አባ_አክራ : #አባ_ዮሐንስ : #አባ_አብጥልማ
እና #አባ_ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት (ማለትም
በቀደመ ሕይወታቸው) ካህናትና ሃብታሞች ነበሩ:: ሀብቱ ግን
በሥራ ብቻ የተገኘ ነው::
ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ
እየተቀበሉ: ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ
እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ
በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ ግብር
ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት
ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን
ያሰቃዩ ገቡ::
በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር ቤቱ
የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ
መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ:: የራበውን
ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ መድኃኒትን
ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ: ግፉም ከልክ
እያለፈ መጣ::
በዚህ ጊዜ 4ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ
አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ መርጠዋልና:
ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና: የሩጫቸው
መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ::
አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን አካፈሉ::
በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ ከሃብታቸው
አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ
ስምዕ) አደረጉ::
በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ
የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን
አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ::
በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ
ድፍረት ነበር::
መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት
አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም:
በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን
አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ:: በመጨረሻ
ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገድለዋል::
ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና ሰማዕትነታቸው
ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን ተቀብለዋል::
🌻🌻
የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::
🌻🌻
@dn yordnos abebe