ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ
ምድረ ግብፅ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች
አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኩዋን ለስደተኛ በቤቱ
ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት
ያውቀዋል::
ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት
ድንግል እመቤታችን ውሃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች :
ግን ጥርኝ እንኩዋ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች::
ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች
ወስደውት ደረሰች::
ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውሃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም
አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው
ሕይወትነት ያለው ማይ (ጸበል) ፈለቀ:: # ጌታችን :
#እመቤታችን : #ዮሴፍና_ሰሎሜ ከውሃው ጠጥተጠዋል::
ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) :
ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
ከመቶዎች ዓመታት በሁዋላም ጌታ ጸበል ያፈለቀበት :
ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን
ስም #ቤተ_ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል::
ጸበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::
ምድረ ግብፅ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች
አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኩዋን ለስደተኛ በቤቱ
ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት
ያውቀዋል::
ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት
ድንግል እመቤታችን ውሃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች :
ግን ጥርኝ እንኩዋ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች::
ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች
ወስደውት ደረሰች::
ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውሃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም
አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው
ሕይወትነት ያለው ማይ (ጸበል) ፈለቀ:: # ጌታችን :
#እመቤታችን : #ዮሴፍና_ሰሎሜ ከውሃው ጠጥተጠዋል::
ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) :
ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
ከመቶዎች ዓመታት በሁዋላም ጌታ ጸበል ያፈለቀበት :
ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን
ስም #ቤተ_ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል::
ጸበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::
✞✞✞ ♥እንኩዋን ለቅድስት #ቤተ_ክርስቲያን ዓመታዊ
የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ♥ ✞✞✞
አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው
በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ200 ዓመታት
እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ265 ዓ/ም
የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም::
የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት (ዲዮቅልጢያኖስና
መክስምያኖስ) ዓለምን ለ2 ተካፍለው ክርስቲያኖችን
የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ::
በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት
እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ
አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ
ተሰጠ:: ለ40 ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች
ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ:
አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ::
#እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል"
ሲል በ305 ዓ/ም ታላቁ # ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ ነገሠ::
መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው
ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ
ከዓመታት በሁዋላ (በ313 ዓ/ም) ታላቁ ቆስጠንጢኖስ
የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ
ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው
ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ::
+በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ
አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ
ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት (የደስታ ቀን)" ተብላ
ትከበራለች::
የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ♥ ✞✞✞
አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው
በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ200 ዓመታት
እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ265 ዓ/ም
የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም::
የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት (ዲዮቅልጢያኖስና
መክስምያኖስ) ዓለምን ለ2 ተካፍለው ክርስቲያኖችን
የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ::
በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት
እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ
አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ
ተሰጠ:: ለ40 ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች
ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ:
አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ::
#እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል"
ሲል በ305 ዓ/ም ታላቁ # ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ ነገሠ::
መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው
ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ
ከዓመታት በሁዋላ (በ313 ዓ/ም) ታላቁ ቆስጠንጢኖስ
የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ
ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው
ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ::
+በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ
አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ
ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት (የደስታ ቀን)" ተብላ
ትከበራለች::
♥ ቅዱስ ሚናስ ♥
(ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው)
¤በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ
¤በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ
¤በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ
¤ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ
¤በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት
ሰማዕት ነው::
እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ
ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::
♥ ✝ ✝ ♥
በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ
ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ:: ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: #ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል
በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ
በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " #መርዩጥ "
ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ
#ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ
ተከብሯል::

♥እልልልልልልልልልልል እንኳን አደረሳችሁ ♥
ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ
ገብርኤልን ላከላቸው::
+ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ
ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6
ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ
በተጸነሰ ጊዜ #የአርያም_ንግሥት #ድንግል_እመቤታችን ደጋ
ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት
የእህትማማች ልጆች ናቸው::
+የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው # መንፈስ_
ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ
ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ
በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ
" #ዮሐንስ " ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
+"+ # መጥምቀ_መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ +"+
¤የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ጌታውን ያጠመቀና
¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
+ስለዚሕም #ቤተ_ክርስቲያን # ነቢይ: # ሐዋርያ: #ሰማዕት :
# ጻድቅ : #ገዳማዊ : #መጥምቀ_መለኮት: # ጸያሔ_ፍኖት :
# ቃለ_ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

♥ጻድቁ ቅዱስ ዮሐንስ♥
ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር አድሮበታልና ሕይወቱ ግሩም
ነበር:: በሕጻን ገላው ይጾምና ይሰግድ : በልጅ አንደበቱም
ተግቶ ይጸልይ ነበር:: ወላጆቹ ወደ እረኝነት ባሰማሩት ጊዜም መፍቀሬ ነዳያን ነውና ቁርስና ምሳውን ለነዳያን እያበላ እርሱ ጾሙን ይውል ነበር:: አባቱ የሚያደርገውን ሰምቶ ለማረጋገጥ ተከተለው:: እንዳሉትም እናቱ ጋግራ የሰጠችውን ትኩስ ዳቦ ለነዳያን ሲሰጥ አየው::
+ሊቆጣው ፈልጐ "ዳቦህ የታለ?" ቢለው ሕጻኑ ቅዱስ
ዮሐንስ "በአገልግሉ ውስጥ አለ" ሲል መለሰለት:: አባት
ለመቆጣት እንዲመቸው አገልግሉን ሲከፍተው ግን
ያየውን ማመን አልቻለም:: በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ
ዳቦዎቹ ትኩስ እንደሆኑ ተገኙ::
አባትም ወደ ቤቱ ወስዶ "ልጄ! አንተ የእግዚአብሔር
ሰው ስለሆንክ እኛን ሳይሆን እርሱን አገልግል" ብሎ ወደ
#ቤተ_ክርስቲያን ላከው::
♥ አቤቱ ከአባቶቻችን ገድል አትራፊ አድርገን♥

❖♥እንኩዋን ለቅድስት #እናታችን_ማርያም_መግደላ
ዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❖♥
✝#ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት✝
ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ
"መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት
(ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:-
በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ
ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች
በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::
ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና
ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7
አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር::
በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና
ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::
በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት
የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም
ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት
አልዘገየችም::
ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ
ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ
መርጦ ተከታዩ አደረጋት::
ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች::
እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ
ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::
ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::
ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ
#መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ
ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን
ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::
እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም
ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር
አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን
አልፈራችም:: ጌታችንም #ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት
ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ
አደላት::
በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን
( #ሚካኤልና_ገብርኤልን ) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ
የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም"
አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::
ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ
መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት::
"ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን
ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::
#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ
ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን : #ትምሕርተ_ኅቡዓትን
ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ
ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ
አገልግሎት ነበራት::
ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን
ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን
ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ
የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ
ነበረች::
እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ
በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል::
እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ
ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ
ይመግባቸው ነበር::
እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም
የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን
#ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች::
ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና
ግርፋትን ታግሳለች::
በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን
መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን
ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ
በቀር) ያከብሯታል::

❖✝ እንኩዋን ለሰማዕታት ቅዱስ #እንጣዎስ እና ቅዱስ
#ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝❖
#ቅዱስ_እንጣዎስ_አሞራዊ ይሕ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን የሚጠላ
አስቸጋሪ አረማዊ ነበር:: ሃገሩ #ሶርያ ( #ደማስቆ ) ሲሆን
ግብሩ ጣዖት ማምለክና መስረቅ ነበር:: በቅድስት ቤተ
ክርስቲያንና በምዕመናን ላይም ግፍን ፈጽሟል:: በሥጋዊ
ጉልበቱ ኃይለኛ ስለ ነበር የተፈራ ነው::
ሁልጊዜ በጠዋት ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ይሔዳል::
የሚሔደው ግን ንዋያተ ቅድሳትን ለመዝረፍ: አንድም
ካህናትን ለመደብደብ ነበር:: የሚገርመው ግን የወቅቱ
ምዕመናንና ካህናት ይህን ሁሉ እያደረገባቸው አይጠሉትም::
ይልቁኑ ይጸልዩለት ነበር እንጂ:: ምክንያቱም ክርስትና ማለት
ጠላትን መውደድ ነውና:: (ማቴ. 7)
የእግዚአብሔር ትዕግስትና የምዕመናን ጸሎት ተደምሮው
አንድ ቀን ፍሬ አፈራ:: እንጣዎስ እንደ ለመደው ለክፉ ሥራ
ወደ # ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ይሔዳል:: ከዚያም
እንደ ደረሰ ወደ ውስጥ ገብቶ: የሚማታውን ተማቶ:
የሚዘርፈውንም ዘርፎ: የተረፉትን ንዋያተ ቅድሳት በእሳት
አቃጠላቸው::
#እግዚአብሔር ከዚህም በላይ ታጋሽ ነውና አላጠፋውም::
"ዘኢይፈቅድ ለኃጥእ ሞቶ" እንዲል የኃጢአተኛውን መመለስ
እንጂ መሞቱን አይፈልግም:: ለዚያም ነው ዛሬ ይሔ ሁሉ
ግፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተሠራ እግዚአብሔር
እንደማያይ ዝም የሚለው:: ለሁሉም ቀን አለውና በፈረደ ቀን
ግን በፊቱ የሚቆም አይኖርም::
እንጣዎስ ግን የሠራውን ሠርቶ እወጣለሁ ሲል
አልተሳካለትም:: ከበሩ አካባቢ ሲደርስ: ከወደ ሰማይ
አካባቢ ድምጽ ሰምቶ ቀና ሲል መላእክት እንደሱ ዓይነት
ኃጢአተኞችን አሰልፈው በጦርና በቀስት ሲወጉአቸው
ተመለከተ::
ድንገት ግን ከመላእክቱ አንዱ ዘወር ብሎ አንድ ቀስት ወደ
እንጣዎስ ወረወረ (ተኮሰ):: ቀስቷ አካሉ ውስጥ ገብታለችና
እንጣዎስ መሬት ላይ ወድቆ ለሞት ደረሰ:: ላበቱ በግንባሩ
ላይ በጭንቅ እየፈሰሰ ጮኸ::
"ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ማረኝ? ራራልኝ? ይቅር
በለኝ? በድፍረት ባለ ማወቅም በድየሃለሁ:: ይቅር በለኝና
ላምልክህ: ስምህንም ልሸከም" ሲል በጭንቀት ውስጥ ሆኖ
አሰምቶ ጸለየ:: በዚያ የነበሩ ምዕመናን ማን: በምን እንደ
ወጋው ባያውቁም ባዩት ነገር ግን እጅግ ደስ አላቸው::
እነርሱም የፈጉትና የጸለዩለት ነገር ይሔው ነበርና::
ወዲያው ግን እንጣዎስ ከሞት ጫፍ ተመልሶ ተነሳ::
መጀመሪያ በቦታው የነበሩ ካህናትና ምዕመናንን "ይቅር
በሉኝ?" አለ:: ቀጥሎም ወደ ዻዻስ ዘንድ ሔዶ "አጥምቀኝ"
ሲል ጠየቀ:: እርሱ በሚጠመቅበት ቀን ብዙ አሕዛብና
ክርስቲያኖች ተሰብስበው ነበር::
እርሱ በከተማዋ ዝነኛ ነበር:: ሥርዓቱ ሁሉ ተደርሶ ቅዱሱ
ወደ ውሃ ገንዳው ሲገባ ሁሉ እያዩ የብርሃን ምሰሶ ከሰማይ
ወረደ:: ይህንን በገሃድ የተመለከቱ ከ10,000 በላይ አሕዛብ
ወዲያውኑ በክርስቶስ አምነው አብረውት ተጠምቀዋል::
ቅዱስ እንጣዎስ ከዚህ በሁዋላ ምስጉን ክርስቲያን ሆነ::
ስለ ቀደመ ሕይወቱ ፈንታ ጾምን: ጸሎትን: ፍቅርን: ምጽዋትን
ገንዘብ አደረገ:: ሕይወቱም ለብዙ ሰዎች መስታውት ሆነ::
#እመቤታችን ድንግል ማርያምንም ይወዳት ነበርና ወደ
ቅዱሳን ማሕበር ( #ኢየሩሳሌም ) ወስዳው በሥጋዊ አንደበት
ተከናውኖ ሊነገር የማይቻል ምሥጢርን ገልጣለታለች::
እነዚህን የቅድስና ጊዜያት በስኬት ያሳለፈው ቅዱስ
እንጣዎስ መጨረሻው ሰማዕትነት ሆነ:: አረማውያን ወገኖቹና ቀድሞ የሚያውቁት ወደ ቀደመ ክፋትና
ክህደት እንዲመለስ ጠየቁት:: "አይሆንም" አላቸው::
በአደባባይ ለፍርድ አቅርበው ደሙ እስኪፈስ ገረፉት::
ጥርሶቹን በሙሉ በድንጋይ አረገፏቸው:: ደሙና ጥርሶቹ
መሬት ላይ ተዘሩ:: ነገር ግን ይሕ ስቃይ ቅዱሱን ከፍቅረ
ክርስቶስ ሊለየው አልቻለም:: አሕዛብም ተስፋ ቆርጠው
በዚህች ቀን ገድለውታል:: ቅዱስ እንጣዎስም ከሁዋለኛው
ዘመን #ሰማዕታት እንደ አንዱ ተቆጥሯል::

💚💛ቅዱስ_ሚናስ ምዕመን ሰማዕት💛❤️
ቅዱስ ሚናስ ( #ማር_ሚና ) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን
ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::
ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::
ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና
በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር
80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው::
አባቶቻችንና እናቶቻችን #ኢትዮዽያውያን_ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-
¤በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ
¤በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ
¤በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ
¤ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ
¤በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው::
እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::
የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::
በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም::
ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ
ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች::
#ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " #መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ
#ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል::
አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን::
from:- d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar

💚💛ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ 💛❤️
ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " #ዓምደ_ሃይማኖት- የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ (ግብጽ) በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ #አባ_ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: #መንፈስ_ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::
ከዚያም በ412 ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም 24ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ #ቤተ_ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::
በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው #እመቤታችንንየአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት!)
ነገሩን #ቅዱስ_ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም #በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 #ቅዱሳን_ሊቃውንት ተገኙ::
የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር (ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት #ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: #ድንግል_ማርያምም #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::
የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::
ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም " #ታኦዶኮስ(የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን:-
¤የአምላክ እናት:
¤ዘላለማዊት ድንግል:
¤ፍጽምት:
¤ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::
እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::
ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ32 ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ444 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::
From:- d/n yordanos abebe