+♥#አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ ♥+
ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ
ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ
ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው
ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::
ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር
አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ
በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን
እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::
+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር
አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ
ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ::
በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም
የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::
አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ
ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ
አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን
በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና
ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::
ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ
አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን
አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው::
ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት
ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::
ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን
የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ
ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው
ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ
ውጪም ጣሉት::
እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን
መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ
ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ
ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው
እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::
ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ
አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን
አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ
እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ
አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::
የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር
በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት
የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ
መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን
በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም
ለመኑት::
ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም
#በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ
ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና
ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ ( #ስብሐት_ብጡል
) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው
ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::
+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና
አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ
መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት
ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::
ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት
ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ::
በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ::
ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::
በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ
አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ
መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና
ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::
ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት::
ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ
ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ
አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::
በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም
ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ
እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ
አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ
ኑሯል::
በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን
ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና
ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ
ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ
ተቀብሯል::

❖♥እንኩዋን ለቅድስት #እናታችን_ማርያም_መግደላ
ዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❖♥
✝#ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት✝
ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ
"መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት
(ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:-
በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ
ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች
በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::
ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና
ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7
አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር::
በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና
ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::
በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት
የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም
ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት
አልዘገየችም::
ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ
ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ
መርጦ ተከታዩ አደረጋት::
ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች::
እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ
ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::
ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::
ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ
#መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ
ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን
ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::
እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም
ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር
አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን
አልፈራችም:: ጌታችንም #ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት
ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ
አደላት::
በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን
( #ሚካኤልና_ገብርኤልን ) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ
የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም"
አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::
ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ
መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት::
"ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን
ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::
#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ
ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን : #ትምሕርተ_ኅቡዓትን
ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ
ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ
አገልግሎት ነበራት::
ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን
ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን
ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ
የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ
ነበረች::
እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ
በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል::
እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ
ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ
ይመግባቸው ነበር::
እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም
የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን
#ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች::
ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና
ግርፋትን ታግሳለች::
በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን
መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን
ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ
በቀር) ያከብሯታል::

#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
✝ከግራ ቁመት:
✝ከገሃነመ እሳት:
✝ከሰይጣን ባርነት:
✝ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
✔ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ ✔ እንዳለ
ሊቁ::
✝ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
✝እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
✝ #ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
✝ #ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
✝ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
✝ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
✝ # የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
✝ # ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
✝በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
✝ #ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
✝አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
✝ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
✝በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
✝ከግራ ቁመት:
✝ከገሃነመ እሳት:
✝ከሰይጣን ባርነት:
✝ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
✔ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ ✔ እንዳለ
ሊቁ::
✝ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
✝እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
✝ #ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
✝ #ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
✝ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
✝ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
✝ # የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
✝ # ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
✝በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
✝ #ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
✝አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
✝ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
✝በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::
+"+ # ቅዱስ_ይሁዳ ሐዋርያ +"+
=>በዘመነ ሐዋርያት # ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው
# ቅዱስ_ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ #ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ
ቢሆንም ገና በልጅነቱ # ድንግል_ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች::
አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር::
+ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ
ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን # ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: (ዮሐ.
14:22)
+ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ
አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና
ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል::
አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው::
¤ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ
ደርቧል::
+"+ ቅዱሳን # ዺላጦስና_አብሮቅላ +"+
=>ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ #መጽሐፍ_ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል
ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት
የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ
ላይ አያበቃም::
+ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ
ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን
በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ
ተሠይፏል::
=>ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ
ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::

🌼እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው🌼
እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት
በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ : ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

#ሥርዓተ #ማኅሌት #ዘግንቦት #ልደታ #ለማርያም " #ግንቦት ፩" ፨
@senkesar
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡
በአሐቲ ቃል።
❤️ መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል። ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል። እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል። ተፈጸመ ተስፋ አበው #በማርያም_ድንግል ።
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
❤️ ዚቅ
#ለማርያም ዘምሩ: #ለማርያም ዘምሩ: መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትጸውሩ።
❤️ ነግሥ
ሰላም ለልሣንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል። ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል። ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል። አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣሕል። እንበለ ባሕቲታ እኅትከ #ማርያም_ድንግል ።
❤️ ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት #ለማርያም_ድንግል።
❤️ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ህይወት #ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
❤️ዚቅ
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ: ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርስኪ ፆርኪ: እምአንስት ቡርክት አንቲ: ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር: አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት
ፀምር: ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።
ነግሥ ፪ቱ አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ። ረከቡ ወለተ ዘታስተሠሪ ጌጋየ። ለወንጌላውያን ኲልነ ዘኮነተነ ምስካየ። ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ። ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ።
❤️ዚቅ
ምሥራቀ ምሥራቃት መፃአ ፀሐይ: እግዝእትነ ዘመና ሙዳይ: ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ።
❤️ መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ። እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ። #ማርያም_ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ። ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ። ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
❤️ዚቅ
በሐኪ #ማርያም ዘገነት ኮል: ዕፀ ጳጦስ መዝገቡ ለቃል: ዕለተ ልደትኪ ዮም በጽድቅ ናብዕል።
❤️ ወረብ
በሐኪ #ማርያም ዘገነት ኮል/፪/
"ዕፀ ጳጦስ"/፪/ መዝገቡ ለቃል/፪/
መልክዐ ማርያም ሰላም ለልሳንኪ ሙኃዘ ኀሊብ ወመዓር። ዘተነብዮ ወፍቅር። #ማርያም_ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር። ኅብዕኒ እምአይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር። እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ
ወምድር።
❤️ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን: ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።
❤️ወረብ
"መሠረታቲሃ"/፪/ ውስተ አድባር ቅዱሳን/፪/
"ወብእሲ ተወልደ" በውስቴታ/፪/
❤️መልክዐ ማርያም
ሰላም ለአእዳውኪ እሳተ መለኮት እለ ገሠሣ። አውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለሥርጋዌሆን ኢኃሠሣ። #ማርያም_ድንግል ለመካን ሕንባበ ከርሳ። አንጽሕኒ እግዝእትየ ለፍትወተ ዓለም እምርኲሳ። በዲበ ሥጋየ ኢትንብር ነጊሣ።
@senkesar
❤️ዚቅ
ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነሰ ዘተፀነስኪ: አላ በሩካቤ ዘበሕግ: እምሐና ወኢያቄም
ተወለድኪ።
❤️ወረብ
"እምሐና ወኢያቄም"/፪/ ተወለድኪ/፪/
አላ በሩካቤ ዘበሕግ/፪/
❤️መልክዐ ማርያም
ሰላም ዕብል ለድንግልናኪ ዕጽው። እንተ እምኔሁ ሠረቀ ፀሐየ መለኮት ኅትው።
#ማርያም_ድንግል ዘስነ ንጽሕኪ ፍትው። ለኀዲር በበፍናው በአሕጉር ወበድው። ዕቀብኒ ወለቶሙ ለኄራን አበው።
❤️ዚቅ
ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ #ማርያም: እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ #ማርያም: ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ ዕደ ሰብእ: ዕጹብ ግብረ መናሥግተ ሥጋ ኢያርኃወ: ዕጹብ ግብረ።
❤️ወረብ
ወለቶሙ ለነቢያት እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ #ማርያም/፪/
"ደብተራ" ፍጽምት/፪/ እንተ ኢገብራ ዕደ ሰብእ/፪/
❤️መልክዐ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ። ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ። ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ። #ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ። ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ።
❤️ዚቅ
ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቊ ድዳ: ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ: ተወልደት ዮም በምድረ ይሁዳ።
ርቆት ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቊ ድዳ ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ ወዘጳዝዮን/፪/
ዮም ተወልደት በምድረ "ይሁዳ"/፪/ በምድረ ይሁዳ ተወልደት።
አሥርቆት ሰላም ለልደትኪ እማኅጸነ ድክምት ሥጋ። ድኅረ ኃለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ። ማርያም ሥመሪ ወጺሐኪ እንበለ ንትጋ። ለማየ ንጽሕኪ ትረስዪኒ ፈለጋ። እስመ ንጽሕ ይሁብ
ሞገሰ ወጸጋ።
❤️ዚቅ
ሐመልማላዊት ሐመልማላዊት ሐመልማላዊት ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና: እግዝእትየ ሙዳዩ ለመና: ተወልደት ዮም እምነኢያቄም ወሐና።
❤️ወረብ
"ሐመልማላዊት"/፪/ ዕፅ ሙሴ ዘርእያ በደብረ ሲና/፪/
ተወልደት ዮም እምነኢያቄም ወሐና/፪/
❤️ምልጣን
ዮም ፍሥሃ ኮነ በእንተ ልደታ #ለማርያም እምሐና ወኢያቄም: ከመ ትቤዙ ነቢያተ
ወጻድቃነ: አማን ተወልደት እመብርሃን።
❤️አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ተወልደት እመብርሃን/፬/
❤️ወረብ
ኮነ ዮም በእንተ ልደታ #ለማርያም /፪/
ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ ነቢያተ ከመ ትቤዙ/፪/
❤️እስመ ለዓለም
ልሳንየ ላዕላዕ ይሴብሐኪ: እግዝእትየ እብለኪ አዳም ንባብኪ ወመሠረቱ ወመሠረቱ
ለዓለም አንቲ: ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ: እምአንስት4 ቡርክት አንቲ: ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር: አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር: ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።
❤️አመላለስ
አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር/፪/
ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል/፪/

💚💛 ጻድቃን እንድራኒቆስ ወአትናስያ 💛❤️
ሁለቱ ቅዱሳን ባል እና ሚስት (ባለትዳር) ናቸው:: የነበረበት ዘመን 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እስኪ #እግዚአብሔር የቀደሰው ጋብቻ ምን እንደሚመስል እንመልከት::
#እንድራኒቆስና_አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ : ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ:: ዘመኑ ደርሶ በሚገባው የተክሊል ሥርዓት ጋብቻቸውን ፈጸሙ:: 40 ቀን ከተፈጸመ በሁዋላ ከምንም ነገር በፊት 2ቱ ቁጭ ብለው ተወያዩ::
የውይይታቸው ርዕስ ደግሞ "ፈጣሪያችን በምን እናስደስተው" የሚል ነበር:: ውይይታቸው የጠናቀቀው በእነዚህ ውሳኔዎች ነው::
1.ሁልጊዜም እንግዳ መቀበል አለብን::
2.ነዳያን ከቤታችን ሊጠፉ አይገባም::
3.ጸሎት : ጾምና ስግደት በቤት ውስጥ አይቁዋረጥም::
4.አብሮ ለመተኛት መቸኮል የለብንም::
እነርሱ መልካምን አስበዋልና አምላክ የሰጣቸውን ሃብት ሲመጸውቱ ኖሩ:: ከዘመናት የቅድስና ጉዞ በሁዋላ በፈቃደ እግዚአብሔር 2 ልጆችን አከታትለው ወለዱ:: ወንዱን "#ዮሐንስ" : ሴቷን ደግሞ "#ማርያም" አሏት::
እነርሱን ከወለዱ በሁዋላ እንደ ገና ሌላ ውሳኔ አሳለፉ:: "ይህንን ላደረገልን ጌታ ከዚህ በሁዋላ አልጋ እንለያለን" ብለው ለ12 ዓመታት በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::
+ሕጻናቱ ዮሐንስና ማርያም በቅንነት አድገው እድሜአቸው 12 ሲሆን 2ቱም በአንድ ቀን ታመው ሞቱ:: ይህ ለአንድ ወላጅ የመጨረሻው አሰቃቂ ፈተና ነው:: ሁሉቱም (እንድራኒቆስና ሚስቱ አትናስያ) ልጆቻቸውን ታቅፈው ወስደው ቀበሩ::
#እንድራኒቆስ ከቀብር በሁዋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምርር ብሎ አለቀሰ:: ግን እንዲህ አለ:-
"አምላከ #ኢዮብ! አንተ ሰጠኸኝ:: አንተም ነሳኸኝ:: ስምህ ለዘለዓለም ይባረክ" ብሎ ሔደ:: እናት #አትናስያ ግን ከሐዘን ብዛት ልቡናዋ ሊሠወር ጥቂት ቀረው::
የልጆቿ መቃብር ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ቅዱስ መልአክ ልቡናዋን ወደ ሰማይ አሳረገው:: ልጆቿ ዮሐንስና ማርያም በገነት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ሐሴትን ሲያደርጉም ተመለከተች:: ወዲያው ወደ ቤት ተመልሳ ለባሏ እንድራኒቆስ ያየችውን ነገረችውና ደስ አላቸው::
እዛው ላይ "ለዚህ ውለታው ከነፍሳችን ውጪ የምንሰጠው የለም" ብለው ሊመንኑ ተስማሙ:: እጅግ ሃብታሞች ነበሩና ነዳያንን ሰብስበው : ሃብት ንብረታቸውን : ቤት ርስታቸውን አካፍለው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዱ::
እርሷ ከሴቶች ገዳም : እርሱ ደግሞ ከወንዶቹ ገቡ:: ለ12 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ተገዙ:: በእነዚህ ዘመናት ተያይተው : አንዱ ስለ ሌላው ሰምቶ አያውቅም:: በጸሎት ግን ያለማቁዋረጥ ይተሣሠቡ ነበር::
ከ12 ዓመታት በሁዋላ የፍቅር አምላክ በሁለቱም ልቡና በተመሳሳይ ሰዓት : ተመሳሳይ ሐሳብን አመጣ:: እርሱ ከአበ ምኔቱ (#ታላቁ_አባ_ዳንኤል) : እርሷም ከእመ ምኔቷ አስፈቅደው ወደ #ኢየሩሳሌም ከቅዱሳት መካናት ለመባረክ ጉዞ ጀመሩ:: በየፊናቸው ጥቂት እንደተጉዋዙ እርስ በርስ ተያዩ::
+እርሷ ለየችው:: እርሱ ግን ጭራሽ ሊለያት አልቻለም:: ይህም ጥበበ እግዚአብሔር ነው:: 2ቱም እየተጫወቱ : እየጸለዩ በሰላም ተባርከው ወደ ግብጽ ተመለሱ:: በእነዚህ ጊዜያት ቅድስት አትናስያን የሚለያት አልነበረም:: አካሏ በገድል ከመለወጡ ባሻገር የለበሰችው እንደ ወንድ መነኮሳት ነበር::
ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ሲደርሱ ጸጋው ተሰጥቶታልና #አባ_ዳንኤል ባልና ሚስት መሆናቸውን አወቀ:: "ለምን አብራችሁ አትኖሩም?" አላቸው:: "እኛ ደስ ይለናል" አሉት:: ከዚያ እርሷ እያወቀችው: እርሱ ሳያውቃት ለ12 ዓመታት አብረው በቅድስና ኖሩ::
ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላ ግን ሐምሌ 28 ቀን ቅድስት #አትናስያ ታመመች:: አባ ዳንኤል ሥጋውን ደሙን አቀብሏትም ዐረፈች:: ሊገንዟት ሲቀርቡ ቅዱስ #እንድራኒቆስ መልኩዋን ልብ ቢለው ሚስቱ ናት::
በአንድ ጊዜ ሚስቱንና የሚወደውን ባልንጀራ በማጣቱ አለቀሰ:: እርሷን ቀብረው ወደ በዓቱ ተመልሶ "ጌታ ሆይ! ውሰደኝ?" አለ:: እርሱም ተከትሏት ዐረፈ:: አባ ዳንኤል እርሱንም ቀብሮ ጥዑም ዜናቸውን ጻፈ::
From:- dn yordanos abebe
@senkesar @senkesar