#አንቺ ሳትሄጂ
አንቺ ሳትሄጂ
ሰርክ በማለዳ ፤ልታፈካ ሰማይ
ሽቅብ ተንጠልጥላ ፤ቁልቁል እኛን ልታይ
እምትወጣው ጠሀይ ፦
የጠሀይዋን ዳና ፤ዱካዋን ጠብቃ
አመሻሽታ ደሞ ፤ምተካት ጨረቃ፦
አንቺ ሳትሄጂ ፦
ቶሎቶሎ ሚያልቁት ፦ቀናት ሳምንታቱ
ወራት አመታቱ ፤ቀትርና ሌቱ ፦
አንቺ ስትሄጂ ፥
ብቻ ምን አለፋሽ
እነሱም ጠፍተዋል ፤አንቺ ስለጠፋሽ
ጠሀይ አንደጥንቱ ፤በጊዜ አትወጣም
ጨረቃም ሲሻት ነው ፤ካላሻት አትመጣም
ጊዜያቱ እራሱ ፤ተወዛግበው አሉ
ሊያዩሽ ይወጡና ፤ሲያጡሽ ይገባሉ
ብቻ ምን አለፋሽ
ሁሉም ከፍቷቸዋል ፤አንቺ ስለጠፋሽ
አንቺ ሳትሄጂ ፤አብሮኝ የነበረ
ስትሄጂም ያልተወኝ ፤ቃሉን ያልሰበረ
ትዝታሽ ብቻ ነው ፤ከኔ ጋር የቀረ።
✍Anteneh tesfaye✍
@Lula_al_greeko
@getem
@getem
አንቺ ሳትሄጂ
ሰርክ በማለዳ ፤ልታፈካ ሰማይ
ሽቅብ ተንጠልጥላ ፤ቁልቁል እኛን ልታይ
እምትወጣው ጠሀይ ፦
የጠሀይዋን ዳና ፤ዱካዋን ጠብቃ
አመሻሽታ ደሞ ፤ምተካት ጨረቃ፦
አንቺ ሳትሄጂ ፦
ቶሎቶሎ ሚያልቁት ፦ቀናት ሳምንታቱ
ወራት አመታቱ ፤ቀትርና ሌቱ ፦
አንቺ ስትሄጂ ፥
ብቻ ምን አለፋሽ
እነሱም ጠፍተዋል ፤አንቺ ስለጠፋሽ
ጠሀይ አንደጥንቱ ፤በጊዜ አትወጣም
ጨረቃም ሲሻት ነው ፤ካላሻት አትመጣም
ጊዜያቱ እራሱ ፤ተወዛግበው አሉ
ሊያዩሽ ይወጡና ፤ሲያጡሽ ይገባሉ
ብቻ ምን አለፋሽ
ሁሉም ከፍቷቸዋል ፤አንቺ ስለጠፋሽ
አንቺ ሳትሄጂ ፤አብሮኝ የነበረ
ስትሄጂም ያልተወኝ ፤ቃሉን ያልሰበረ
ትዝታሽ ብቻ ነው ፤ከኔ ጋር የቀረ።
✍Anteneh tesfaye✍
@Lula_al_greeko
@getem
@getem
#ንፅፅር
(✍ #አብርሀም_ተክሉ)
አንቺና ሀገሬን ሳመሳስላችሁ
የመጣውን ሁሉ !!
እንዳልክ.....እያላችሁ
ጥርስ የደረደረ ፥ ደባ እያደባችሁ
ባላዋቂ ጮሌ
በዘመን ወፍጮ ላይ ፥ ነገረ አፈጃችሁ ።
ታውቂያለሽ?
ምስኪኗ የኔ አገር
ባንድ መቀመጫ ፥ ሁለት ባል ሲገርፋት
ከፋፍላ ሰጠችው ፥ በጉብታው ስፋት
#አንቺ_ደሞ
ልክ እንደሀገሬ ፥ ነገር ስትዋጂ
የባልሽን አልጋ ፥ ከእልፍኝ ሞገሱ
ለሎሌሽ ማረፊያ ፥ ክብሩ ስታወርጂ
የተንቆራቆዘ
አልጋሽ ወድቆ ከደጅ
የተገላቢጦሽ
አሽሙርሽ ሲበጃጅ
ባንቺው ተንገላትቶ ፥ በግብርሽ ላረጀ
በሰበርከው ምፀት
አይጡ በበላ ፥ ዳዋውን አስፈጀ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
@getem
(✍ #አብርሀም_ተክሉ)
አንቺና ሀገሬን ሳመሳስላችሁ
የመጣውን ሁሉ !!
እንዳልክ.....እያላችሁ
ጥርስ የደረደረ ፥ ደባ እያደባችሁ
ባላዋቂ ጮሌ
በዘመን ወፍጮ ላይ ፥ ነገረ አፈጃችሁ ።
ታውቂያለሽ?
ምስኪኗ የኔ አገር
ባንድ መቀመጫ ፥ ሁለት ባል ሲገርፋት
ከፋፍላ ሰጠችው ፥ በጉብታው ስፋት
#አንቺ_ደሞ
ልክ እንደሀገሬ ፥ ነገር ስትዋጂ
የባልሽን አልጋ ፥ ከእልፍኝ ሞገሱ
ለሎሌሽ ማረፊያ ፥ ክብሩ ስታወርጂ
የተንቆራቆዘ
አልጋሽ ወድቆ ከደጅ
የተገላቢጦሽ
አሽሙርሽ ሲበጃጅ
ባንቺው ተንገላትቶ ፥ በግብርሽ ላረጀ
በሰበርከው ምፀት
አይጡ በበላ ፥ ዳዋውን አስፈጀ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ
@getem
@getem
@getem
ድርሳነ ፍቅር!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
#አንቺ የእኔ ጣዖት!
እኔ ያንቺ አማኝ
የምዕመኑ ጠሎት ቅዳሴና አዛኑ
በየት በኩል ይሰማኝ?
።።።
እሳት ያንቺ ገላ ~ መብረቅ ያንቺ መውደድ
በየት መንገድ ልጓዝ ~ እምን ላይ ልራመድ?
ዓይኖችሽ ጉልላት
ጥርሶችሽ በረዶ
ጣቶችሽ አለንጋ....
ሠንበር የወረሰው ~ ቁስል ልቤን ይዤ
እንደምን አልሰጋ?
።።።።
#እኔ
መድሀኒቴ አንቺ
በሽታዬም አንቺ
አንቺን እየዋጥሁኝ ~ አንቺን የምታመም
ባንቺ እየታመምሁኝ ~ ባንቺ የምታከም
.
ባለ አንድ ድዌያም ~ ባለ አንድ ክኒና
ወይ አልሞት ፥ ወይ አልድን
ወይ አልኖር በደህና!
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
#አንቺ የእኔ ጣዖት!
እኔ ያንቺ አማኝ
የምዕመኑ ጠሎት ቅዳሴና አዛኑ
በየት በኩል ይሰማኝ?
።።።
እሳት ያንቺ ገላ ~ መብረቅ ያንቺ መውደድ
በየት መንገድ ልጓዝ ~ እምን ላይ ልራመድ?
ዓይኖችሽ ጉልላት
ጥርሶችሽ በረዶ
ጣቶችሽ አለንጋ....
ሠንበር የወረሰው ~ ቁስል ልቤን ይዤ
እንደምን አልሰጋ?
።።።።
#እኔ
መድሀኒቴ አንቺ
በሽታዬም አንቺ
አንቺን እየዋጥሁኝ ~ አንቺን የምታመም
ባንቺ እየታመምሁኝ ~ ባንቺ የምታከም
.
ባለ አንድ ድዌያም ~ ባለ አንድ ክኒና
ወይ አልሞት ፥ ወይ አልድን
ወይ አልኖር በደህና!
@getem
@getem
@getem
#የስሌት #ጋብቻ
#አንቺ
ሽማግሌ አዘጋጅ ብለሽ ተናግረሻል
ምን አለው ይሉኛል ብለሽ ተጨንቀሻል
#እኔ
ከቀየው መርጬ
በቂ ሽማግሌ አዘጋጅቻለሁ
የሌለኝ ነገር
ለራሴ አለኝ ብዬ በቃል ሸምድጃለሁ
#እነሱ
ቤተዘመድ መጥቶ
ምን አለው ለማለት ማልዶ ይሰለፋል
ሽማግሌ ከቦ
ምን አለው ለሚባል
የወላጅ ጥያቄ የሐሰት መልስ ይፅፋል
#ውዴ #አትጨነቂ
ያንቺ ብቻ አይደለም የሀገር ነው ችግሩ
እኛም ቤት ብትመጪ ይሔው ነው ነገሩ
#አምና
የታናሽ እህቴ
የልጅነት ፍቅሯ አመት በአል አስታኮ
በፍቅር መርቀን
ፈቅደን እንድንሰጠው ሽማግሌ ልኮ
#መልስ #ሲጠባበቅ
በዚህ ወገን ሆኜ እኔም ጠይቄያለሁ
ማይደርስብኝ መስሎኝ ምን አለው ብያለሁ
በሴት ወገን ስንሆን የወንዱን ባናውቅም
ምን አለው ተብሎ ሰው አይጠየቅም
ሀቅ ተዟዙሮ
ቦታ ተቀያይሮ
የትናንት ተቀባይ ከነገ ወዲያ ይልካል
በሴቷ ጠይቆ በወንድ ይጠየቃል
ሸፋፍነነው እንጂ
ደፍረን ከጠራነው ነገሩ ያሳስባል
በንግድ አጠያየቅ
ምን አለው አይደለም ስንት አለው ነው ሚባል
ባንክ ቤት ስንት አለው በጥሬው ያኖረው
ስንት መኪና አለው የሚያሽከረክረው
ስንት ካሬ መሬት ካርታ የወጣለት
ስንት ክፍል ቪላ የተንጣለለለት
በልጅ የደም ቀለም የሌለንን ስንስል
ልጅ የምንድር ሳይሆን ገዢ ነው ምንመስል
የመመኘት ቀመር
የማዟዟር ብዜት በዘመን ሲጣፋ
ምን አለው ነው እንጂ
ከዬት አመጣው የሚል ሽማግሌ ጠፋ
#እኔ #ምለው ?
የማካፈል ስሌት ዞሮ የመጣ ‘ለት
ምን ያህል ይዘናል ምን አለው ለማለት
#ይልቅ
እግዚአብሔር አድሎት
በጥላቻ ዘመን የሰው ልጅ ሲፋቀር
አፍቃሪ ልብና
ሁሉም ነገር አለው ከሀብት በስተቀር
ሀቁን እያወቅነው ውጠን ከማባበል
ምን አለውን ትተን ምን የለውም እንበል
=====||=====
✍ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@beppa_19
#አንቺ
ሽማግሌ አዘጋጅ ብለሽ ተናግረሻል
ምን አለው ይሉኛል ብለሽ ተጨንቀሻል
#እኔ
ከቀየው መርጬ
በቂ ሽማግሌ አዘጋጅቻለሁ
የሌለኝ ነገር
ለራሴ አለኝ ብዬ በቃል ሸምድጃለሁ
#እነሱ
ቤተዘመድ መጥቶ
ምን አለው ለማለት ማልዶ ይሰለፋል
ሽማግሌ ከቦ
ምን አለው ለሚባል
የወላጅ ጥያቄ የሐሰት መልስ ይፅፋል
#ውዴ #አትጨነቂ
ያንቺ ብቻ አይደለም የሀገር ነው ችግሩ
እኛም ቤት ብትመጪ ይሔው ነው ነገሩ
#አምና
የታናሽ እህቴ
የልጅነት ፍቅሯ አመት በአል አስታኮ
በፍቅር መርቀን
ፈቅደን እንድንሰጠው ሽማግሌ ልኮ
#መልስ #ሲጠባበቅ
በዚህ ወገን ሆኜ እኔም ጠይቄያለሁ
ማይደርስብኝ መስሎኝ ምን አለው ብያለሁ
በሴት ወገን ስንሆን የወንዱን ባናውቅም
ምን አለው ተብሎ ሰው አይጠየቅም
ሀቅ ተዟዙሮ
ቦታ ተቀያይሮ
የትናንት ተቀባይ ከነገ ወዲያ ይልካል
በሴቷ ጠይቆ በወንድ ይጠየቃል
ሸፋፍነነው እንጂ
ደፍረን ከጠራነው ነገሩ ያሳስባል
በንግድ አጠያየቅ
ምን አለው አይደለም ስንት አለው ነው ሚባል
ባንክ ቤት ስንት አለው በጥሬው ያኖረው
ስንት መኪና አለው የሚያሽከረክረው
ስንት ካሬ መሬት ካርታ የወጣለት
ስንት ክፍል ቪላ የተንጣለለለት
በልጅ የደም ቀለም የሌለንን ስንስል
ልጅ የምንድር ሳይሆን ገዢ ነው ምንመስል
የመመኘት ቀመር
የማዟዟር ብዜት በዘመን ሲጣፋ
ምን አለው ነው እንጂ
ከዬት አመጣው የሚል ሽማግሌ ጠፋ
#እኔ #ምለው ?
የማካፈል ስሌት ዞሮ የመጣ ‘ለት
ምን ያህል ይዘናል ምን አለው ለማለት
#ይልቅ
እግዚአብሔር አድሎት
በጥላቻ ዘመን የሰው ልጅ ሲፋቀር
አፍቃሪ ልብና
ሁሉም ነገር አለው ከሀብት በስተቀር
ሀቁን እያወቅነው ውጠን ከማባበል
ምን አለውን ትተን ምን የለውም እንበል
=====||=====
✍ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@beppa_19
[አስቱ]
#አንቺ_ስትቀሪ፣
…
ሽፋን ታቅፊያለው ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
……………
ትመጣለች ይሆን እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
……………
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ
…
እያልኩኝ…
…
…እያልኩኝ
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ
…
አይኔ እሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ
ወዴት ነው ሚጓዘው ወደማን ይሸሻል!?
…
ታዲያ ስትቀሪ የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
……
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በምባዬ
…
"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።
ምክንያቱም
…
እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ
…
አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀና
ድንገት የቀረች'ለት ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና
…
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"
@getem
@getem
@getem
#አንቺ_ስትቀሪ፣
…
ሽፋን ታቅፊያለው ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
……………
ትመጣለች ይሆን እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
……………
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ
…
እያልኩኝ…
…
…እያልኩኝ
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ
…
አይኔ እሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ
ወዴት ነው ሚጓዘው ወደማን ይሸሻል!?
…
ታዲያ ስትቀሪ የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
……
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በምባዬ
…
"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።
ምክንያቱም
…
እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ
…
አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀና
ድንገት የቀረች'ለት ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና
…
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"
@getem
@getem
@getem
👍1
#አንቺ አደይ ሆዬ
💚💛❤️
አደይ ቢጫ ሆዬ ሰልፍሽ ደርሷል አሉ
ቅድስቲቷ ምድር በአበባሽ ተሞሉ
የሞሉት ወንዞችሽ በተስፋ ጎደሉ
ጸደይ ቢጫ ሆዬ
መስኩ የረጠበው ባንቺ አበባ ሞሉ
ኮለል ኮለል ኮለል ምድሯ ስታማልል
ሰማዩ ሲቀና በመሬቷ ውበት በቅናት ሲማልል
ዝናቡም ሊስምሽ ካልዘነብኩብሽ ሲል
ፀሀይም ልትመጥሽ ካንቺ ስትዋልል
ሰው ባንቺ ተገርሞ እጁን ካንቺ ሲጥል
ንቦች በጥዝታ ለማሩ ሲቸኮል
የሚያጓራው ሰማይ በአደብ ሲል ዘንበል
ምድር ስታበራ ፀሀይን ስታቀል
ሌቱ ውብ ሰላሙን በጨረቃ ሲጥል
ውብ አይናማ ሴቶች ሲሉ ለምለም ለምለም
ደሞ አስጨፋሪዋ ኮኮቧን ስትለቅም
ባልንጀራ ሴቶች ሲወጡ ወደ አለም
ጎጃቸው ሲቀለስ እንጨቶች በመልቀም
አጥር የሌላቸው አንድነት በማለም
በአዲስ አመቱ ጭፈራው የሰላም
ሌቱን ከሀገር ጋር ብቸኝነት የለም
ኮለል ኮለል አንቺ ትልቅ አለም
እንቁ ነው ለጣሽ ሰለሞን የሰጠሽ
ብር ነሀስ አይደል ለእጅሽ የሰካልሽ
እንቁ ነሽ ኢትዮጵያ ሚያበራ ውበትሽ
ሁሉ ውብ ነገር ነው ክፋት የለ ቤትሽ
እቴ እቴ አባባ ሽታሽ የአበባ
ቀሚስሽ ነጭ ነው የደረብሽው ካባ
መተኛሽ የሚመች የሞላ በላባ
ሽታሽ ዝባድ ሽቶ ምታምሪ ውቧ የኛ ሳባ
እውዬ እዋውዬ ጌታሽ የሰማዩ የሁሉ ፈጣሪ
መርጦሻል አንቺንስ በተለየ ጥሪ
አስውቦ የሰራሽ እጅግ የምታምሪ
የመላእክት ማረፊያ የቅድሳን ጋሪ
ከብረሽ ቆዪልኝ ከብረሽ ድንግል ንፅይት ነሽ
ማንም ያላረሰሽ ድንግል መሬት ነሽ
ታንፀሽ የቆምሽው በሱ ባምላክሽ
ኢትዮጵያ ንፅህይት የሁሉ እናት ነሽ
ሁሌ እንደ አዲስ አብሪ ባለሽ ዘመንሽ
✍ብላቴናው
(🌼መልካም አዲስ አመት🌼)
@getem
@getem
@getem
💚💛❤️
አደይ ቢጫ ሆዬ ሰልፍሽ ደርሷል አሉ
ቅድስቲቷ ምድር በአበባሽ ተሞሉ
የሞሉት ወንዞችሽ በተስፋ ጎደሉ
ጸደይ ቢጫ ሆዬ
መስኩ የረጠበው ባንቺ አበባ ሞሉ
ኮለል ኮለል ኮለል ምድሯ ስታማልል
ሰማዩ ሲቀና በመሬቷ ውበት በቅናት ሲማልል
ዝናቡም ሊስምሽ ካልዘነብኩብሽ ሲል
ፀሀይም ልትመጥሽ ካንቺ ስትዋልል
ሰው ባንቺ ተገርሞ እጁን ካንቺ ሲጥል
ንቦች በጥዝታ ለማሩ ሲቸኮል
የሚያጓራው ሰማይ በአደብ ሲል ዘንበል
ምድር ስታበራ ፀሀይን ስታቀል
ሌቱ ውብ ሰላሙን በጨረቃ ሲጥል
ውብ አይናማ ሴቶች ሲሉ ለምለም ለምለም
ደሞ አስጨፋሪዋ ኮኮቧን ስትለቅም
ባልንጀራ ሴቶች ሲወጡ ወደ አለም
ጎጃቸው ሲቀለስ እንጨቶች በመልቀም
አጥር የሌላቸው አንድነት በማለም
በአዲስ አመቱ ጭፈራው የሰላም
ሌቱን ከሀገር ጋር ብቸኝነት የለም
ኮለል ኮለል አንቺ ትልቅ አለም
እንቁ ነው ለጣሽ ሰለሞን የሰጠሽ
ብር ነሀስ አይደል ለእጅሽ የሰካልሽ
እንቁ ነሽ ኢትዮጵያ ሚያበራ ውበትሽ
ሁሉ ውብ ነገር ነው ክፋት የለ ቤትሽ
እቴ እቴ አባባ ሽታሽ የአበባ
ቀሚስሽ ነጭ ነው የደረብሽው ካባ
መተኛሽ የሚመች የሞላ በላባ
ሽታሽ ዝባድ ሽቶ ምታምሪ ውቧ የኛ ሳባ
እውዬ እዋውዬ ጌታሽ የሰማዩ የሁሉ ፈጣሪ
መርጦሻል አንቺንስ በተለየ ጥሪ
አስውቦ የሰራሽ እጅግ የምታምሪ
የመላእክት ማረፊያ የቅድሳን ጋሪ
ከብረሽ ቆዪልኝ ከብረሽ ድንግል ንፅይት ነሽ
ማንም ያላረሰሽ ድንግል መሬት ነሽ
ታንፀሽ የቆምሽው በሱ ባምላክሽ
ኢትዮጵያ ንፅህይት የሁሉ እናት ነሽ
ሁሌ እንደ አዲስ አብሪ ባለሽ ዘመንሽ
✍ብላቴናው
(🌼መልካም አዲስ አመት🌼)
@getem
@getem
@getem
👍2😁1
#አንቺ እና ግጥም
....
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ሚጥሚጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ።
.
@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል አስጨናቂ
የሚካኤል አስጨናቂ ተጨማሪ ግጥሞችን ለማግኘት።
https://tttttt.me/MichaelAschenakipoems
....
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ሚጥሚጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ።
.
@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል አስጨናቂ
የሚካኤል አስጨናቂ ተጨማሪ ግጥሞችን ለማግኘት።
https://tttttt.me/MichaelAschenakipoems
#አንቺ እና ግጥም
....(ሚካኤል አስጨናቂ)
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ዳጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ
ጠልቼ አልጠላችሁ!
@getem
@getem
@paappii
#Mikael aschenaki
....(ሚካኤል አስጨናቂ)
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ዳጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ
ጠልቼ አልጠላችሁ!
@getem
@getem
@paappii
#Mikael aschenaki
👍1