ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ጊዜ የምጣድ ቂጣ ተገልባጭ ባካሉ
አምና ሰነፍ ሆነው ከቤት የሚውሉ
ዘንድሮን ተከብረው ታዛዦች ተባሉ 😄

@getem
@getem
@paappii

#mikael aschenaki
#ዝማሬ ሰብ
።።።።።።።
ከቀፎ ሰገባ ፣ ዋሻ ተሸሽጋ
ከርማ የነበረ ...
ንቢት ይኸው ወጣች ጠሀዩ አማረ
አደይ በመስኩ ላይ ዳግም ተሞሸረ።
ጠል ወጨፉ አልፎ ሰማይ ሲስቅልኝ
ያንተ ቸርነት ነው ሸክሜን የጣለልኝ
እላለሁ! !
እንደጊዜውማ እንደዓመቱ ክፋት
ይህችን አዲስ ጠሀይ ፈክታልኝ ሳላያት
ከአንድ ወጣት ሽመል እግሩ ስር ወድቄ
እንዲህ እንደዛሬው አልታይም ስቄ።
እንደጊዜውማ እንደዓመቱ ጥመት
ወረርሽኝ በሚሉት የደም ውሀ ዥረት
ሳል እያጣደፈ ላብ እያጠመቀኝ
ለአየርህ ርቄ ሞቼ ነበር ምገኝ
ግን ጥላህ ከለለኝ! !
ዛሬ በዓዲስ ተስፋ ...
ሀይቁ ዳር ቆሜ መረቤን ወደርሁት
አፋፉ ላይ ቁሜ ወንጭፌን አሾርሁት
ምድር ከፍሬዋ ዘግና ስትችረኝ
ከአላፊው ርቄ በህላዌ ስገኝ
ያንተ ከለላ ነው እኔን የሚታየኝ ።
እንጂማ እንደ አምናው የመዓት ሰቆቃ
ተስፋና እድሌ በሙቅ ብረት ታንቃ
መራመድ ተስኖኝ እግሬን ሳላነሳ
አንክሼ ነበረ ወቅቱን የማወሳ ።
አሁን ተዚህ ስደርስ.. .
በዓለሟ ሽክርክር ቀናቴን ገርስሼ
ካቀረቀርሁበት
ዳግም ቀና እያልሁኝ ስፍራህን አስሼ
ለአፍ ይምሰል ድርጊት ቃላትን ሳልሰፋ
እንዳለሁ በተስፋ ...
አምላክ የለም ያለኝ የሳይንስ አዋቂ
አንባቢውን አንቂ ...
እመን በሙከራ ...እመን በምርምር ብሎ ሲናገረኝ
ሳልመራመርህ በመረመርከኝ ነው ተገርሜ የምገኝ።
ይልቅ እንካ ውሰድ የድርጎህን ድርሻ
ያንተን ቸርነትን ነው ነገም ላይ የምሻ።
ተመስገን !!

@getem
@getem
@getem

#mikael aschenaki
#አንቺ እና ግጥም
....(ሚካኤል አስጨናቂ)
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ዳጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ
ጠልቼ አልጠላችሁ!

@getem
@getem
@paappii

#Mikael aschenaki
👍1
#ለምን እንደረከስኩ.. . !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
በቀልዴ ስትስቂ.. . ፈገግታሽ ሲገለጥ
ለኔ ደስታ የለም ከዚህ ገኖ 'ሚበልጥ
ስትስቂ ግን ድንገት
ሄጄ በሀሳብ ዥረት.. .
ተመልሼ ድሮ.. . አምናና ካቻምና
ከሌላ ወንድ ጋር አብረሽ ነበርሽና
ለሱም ስቃ ነበር ...በቀልዱ ተገርማ
ብዬ አኮርፋለሁ ... ደስታዬ ሲቀማ ።
.
እንዲሁ እንደ ዘበት
አንዳንድ ቀን ድንገት
በአልጋ ላይ ጨዋታ
ነፍሳችን ተረታ ...
አንገትሽ ስር ባለች.. . መዓዛ ሰክሬ
ሸሽቼ ከቅጥሬ.. .
ስቤ በምምገው ... ቃናሽ ሳልረካ
ሌላም ሰው ደርሶታል ይሄ ሽታም ለካ !
የሚል ሞጋች ሀሳብ እያንገበገበኝ
አንቺን አቅፎ ማደር ገላዬን ሸከከኝ።
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ማሽን ያተኮሰው
እኔ የምወደው.. .
የፀጉርሽ ሽታ
ደርሷል ሌላ ቦታ ...
.
ከፍቶሽ ስታነቢ እንባሽ ሲወርድ ቁልቁል
ሌላም ሰው እንደኔ አፅናንቶሻል እኩል
.
መስታወት ፊት ቆመን
የተንጋደደው የሸሚዝ ኮሌታ
ሲቃና በጣትሽ
ትናንት የሌላ ወንድ ኮሌታ ላይ አርፏል
ይሄ የጣት ፍቅርሽ
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ወይን እየጠጣን የተጨዋወትንበት
ይሄ ቦታ ድንገት
ከሌላ ወንድ ጋር በፊት ነበርሽበት ...
.
መውደድን ያየሁት ባንተ ነው ፍቅሬ
የሚል አፅናኝ ወሬ ...
አይደለም የዛሬ
.
ፅጌረዳ መሳይ አበባው ከንፈርሽ
እንቡጥ ሳለ ድሮ ተስሟል ባፍቃሪሽ
.
ይህን ጊዜ ታድያ ...
ካንቺ ኋላ መጥታ ላወኳት ሌላ ሴት
በቅናት በንዴት ...
ቀልዱን አጋርቻት አየሁ የሷን ሀሴት
አንገቷ ስር ገባሁ... ሳብኩት መዓዛዋን
የተከዘች ጊዜ ክንዴ ስር አቅፌ አበስኩኝ እንባዋን
.
ማሽን ያተኮሰው ጡገሯን አሸተትኩኝ
(ሽታሽ ይብልጣታል .. )
ሸሚዜን ላቃና ከሷ ፊት ዘንድ ቆምኩኝ
ጠጣን አብረን ወይን በኔና አንቺ ቦታ
ከንፈሯን ጎረስኩት ካላንዳንች ይሉኝታ
.
ረከስኩ
ረከስኩ
ለሌላ ሴት ወደኩ!
ከክብር ተናነስኩ!
.
ከዛ ግን ተቃናሁ ... በገላዬ ርኩሰት
ዛሬ አንቺን አቅፌ ... እንዲሁ በድንገት
"ሌላ ወንድ አቅፏታል" የሚል ክፉ ሀሳብ
ውስጤን ሲሞግተኝ...
"እኔ ማን ሆኜ ነው የሌላ ሰው ሀጥያት
ቀድሞ የሚታየኝ ?"
የሚል ምላሽ አለኝ!

@getem
@getem
@paappii

#Mikael aschenaki
👍1
እንቢ በል !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

የሀያላኑ ክንድ ሀይሉ ሲበረታ

በነቀዘ ስንዴ

ሽንገላ ተታለህ ሳትኖር በቸልታ

በጤፉ በስንዴው በእርዳታው ፈንታ

አንተው ዘሪ ሆነህ

አንተው አራሽ ሆነህ ድረስ ለገበታ!

እንቢ በል !

አባትህ ቴዎድሮስ ያ መይሳው ካሳ

የቋራው አንበሳ

ለመንግስቱ ግብር ለርሱ እጅ መንሻ

እህል ሲያቀርቡለት ጠይቋል ማረሻ

እንቢ በል !

ተመፅዋች አድርገው በሴራ ባሻጥር

አርቀህ ለማየት ሲሰጡህ መነጥር

ቅርብህ ተደብቋል ይሄን ብቻ ጠርጥር

እንቢ በል !

ለምለም ምድር ታቅፈህ ውስጡ አረንጓዴ

ለምን ትረዳለህ?  ልጠይቅህ ጓዴ !

ከሞኝ ደዳፍ ሞፈር ይቆረጣል ሚሉት

የአባቶችህ ተረት

አይደለም የዘበት!

ተሻገር እያሉ መርከብን ሲሰጡ

የመርከብ ስሪቱ እውቀት አመጣጡ

ከየት ነው መነሻው ብለህ ነው መጠየቅ

መድረሻ አልባ ጉዞ ለመስጠም መሆኑን

ይሄን ብቻ እወቅ! 
እንቢ በል !

በዘር ጎሳ ስሌት ሰበዝህን ሲመዙ

መሶብ ወርቅ መሆን ነው የውበትህ ወዙ

የቆምክበት ምድር የምታየው አፈር

የስጋ ፍራሽ ነው አብዲሳ ሲገበር

የደሙ ዋጋ ነው ያ ባልቻ ሲቀበር

እንቢ በል !

ተምሳሌት ሲያሳጡህ በታሪክ ፈጠራ

ሚኒልክ ገዳይ ነው ብለህ ሳታጓራ

ስር አልባ ሲያደርጉህ ቁስልህን በመጠቅጠቅ

ከፍለው ሊገዙህ ነው ይሄን ብቻ እወቅ!

እንቢ በል !

የነጭ ለምዳም ተኩላ 

መፅሀፍ አንግቶ ሲያሳልምህ መስቀል

አሜን አሜን ብለህ በእምነት አትታለል

በጎችን የሚነጥቅ የሰይጣን አለቃ

ለኢየሱስ ብሎህ ነው አንተን የሚያጠቃ

እንቢ በል !

የኢትዮጵያዊ ልህቀት የሀበሻ ጀብዱ

ባንዳ ሲወረው ነው የሚለየው ጉዱ

እሺ ለጌታህ ነው ለላይኛው አምላክ

እሱን መታመን ነው ለሱ ብቻ መላክ

ልጠብቅህ ለሚል ለአስመሳይ ቀመር

ዋርካህን አትገድስ ለጠላትህ ሞፈር !

እንቢ በል !

እሺ ማለትህ ነው ተብታቢው ሰንሰለት

እሺ ማለት ላይ ነው አዲሱ ባርነት

እንደ እንስሳ ታስረህ ለገበያ ድምቀት

ዋጋህ ሳይተመን...

ፍቅርህን አደርጀው ለነፍስህ አርነት

እንቢ በል !

አሰብንልህ ሲሉ በእነሱ ቋንቋ

ሀገር አጣህ በቃ !

ልማት አጣህ በቃ!

ለራስ ክብር ለግመህ ስትፈልግ ጠበቃ

መሪህ ጠላት ሆኗም ይሄን እወቅ በቃ! !

@getem
@getem
@getem

#Mikael aschenaki
👍1
33👍21😱6
👍26😱5🎉2🔥1