[አስቱ]
#አንቺ_ስትቀሪ፣
…
ሽፋን ታቅፊያለው ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
……………
ትመጣለች ይሆን እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
……………
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ
…
እያልኩኝ…
…
…እያልኩኝ
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ
…
አይኔ እሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ
ወዴት ነው ሚጓዘው ወደማን ይሸሻል!?
…
ታዲያ ስትቀሪ የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
……
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በምባዬ
…
"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።
ምክንያቱም
…
እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ
…
አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀና
ድንገት የቀረች'ለት ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና
…
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"
@getem
@getem
@getem
#አንቺ_ስትቀሪ፣
…
ሽፋን ታቅፊያለው ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
……………
ትመጣለች ይሆን እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
……………
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ
…
እያልኩኝ…
…
…እያልኩኝ
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ
…
አይኔ እሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ
ወዴት ነው ሚጓዘው ወደማን ይሸሻል!?
…
ታዲያ ስትቀሪ የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
……
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በምባዬ
…
"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።
ምክንያቱም
…
እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ
…
አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀና
ድንገት የቀረች'ለት ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና
…
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"
@getem
@getem
@getem
👍1