ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ጨርሰኝ #አትበዪኝ

እጄ እየመረጠ ~ችሎ እንዳይቀባባሽ
እሳሳልሻለሁ ~ መሳሳት ከገባሽ
እኖራለሁ እንጂ
እያብሰለሰልኩሽ ~ እያሰላሰልኩሽ
ጨርሰኝ አትበዪኝ ~ ገና መች ጀመርኩሽ
መች ጀመርኩሽ ውዴ
መች ደገምኩሽ ሆዴ
ቅኔ ነው መውደዴ
ስውር ነው መንገዴ
ከመልመድሽ በፊት ~ ብሩሽና ሸራ
ከመሆንሽ በፊት ~ የጥበቤ አሻራ
የምናቤ ህላዌሽ
ሞልቶ ሳይሞት በፊት ~ በአካል ሳያበቃ
ባለ አቅም ሳይገዛሽ~ሳይቆጥርሽ እንደ እቃ
ገዢ ፊትሽን አይቶ ~ ዋጋ ሳይናገር
የፍቅሬን ቀይ ባህር ~ ከፍሎ ሳይሻግር
* * *
አይንአዋጅ ሆኖበት ~ በምርጫ ተሳክሮ
በድን ግርግዳው ላይ ~ ሳላይሽ ቸንክሮ
እየደጋገመ ~ ላይ ታች አገላብጦ
ከአቻዎችሽ መሀል ~ ከቢጤሽ አማርጦ
ከቤቱ ሳይሰቅልሽ ~ በሚስማር ቀጥቅጦ
ሳልጀምር ጨርሼሽ
ሞላሁ ብለሽ ሳትሄጅ ~ ሳትሰናበቺ
የኔ ብቻ ሁነሽ
መንፈሴ ውስጥ ኑሪ ~ ለአመታት ሰንብቺ
ሰንብቺ በሀሳቤ ~ ክረሚ በጣሙን
ልቅመስ ላጣጥመው ~የመሸሸግ ጣ‘ሙን
ጨርሰኝ አትበዪኝ ~ መጨረስ ለምኔ
የሞላሁሽ እለት ~ እጎድላለሁ እኔ
#ደሞ
አልቀሽ ሊጀምርሽ
ለሚጠባበቀው ~ ሰልፈኛ በሙሉ
መጨረስ አይችልም ~ ትይኛለሽ አሉ
#ቀላል #እችላለሁ
የአይንሽ አቀማመጥ
ጠፍቶኝ እንዳይመስልሽ~ስሜቴን ምታከክ
አልመጣልህ ብሎኝ
ታክቶኝ እንዳይመስልሽ~የአፍንጫሽ መሰልከክ
ከብዶኝም አይደለም
የአንገትሽን እርዝመት~በቀለም ማጥለቅለቅ
ዞማው ፀጉርሽን
ጥቁር መደብ ሰርቶ ~ ሸራ ላይ መለቅለቅ
መች አጣሁት ውዴ
ግንባርሽን ስዬ ~ ገድሽን ማሳመር
መች ጠፋብኝ ሆዴ
የአይኖችሽ ቆብ ቁጥር~የቅንድብሽ መስመር
የፈገግታሽ ለዛ ~ የደም ደም ግባትሽ
ሰምና ወርቅ ያለው ~ ቅኔታዊ ውበትሽ
#ሁሉም እጄ ላይ ነው
ጀምሬሽ ያቆምኩሽ
መስጥሬ የተውኩሽ
እንዳጠፊብኝ ነው ~ እንዳይወስዱሽ ብዬ
እያሰብኩሽ ምኖር ~ በሀሳቤ ከልዬ
ትንሽ ቀረኝ ብዬ ~ በአፌ ብዋሽሽም
እስከምትጨርሽው ~ ልቤ አይጨርስሽም
#የጨረስኩሽ #ለታ
ከባለቀን ሀብታም ~ የበረታው ክንዱ
ከፍሎ ይነጥቀኛል ~ ይወስድሻል አንዱ
== =||= ==
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@peppac
👍21
#አንቺ #የኔ #ሽንኩርት
የቁሌቴ ጅምር ~ የጤንነቴ ፍንጭ
የጣእሜ መሰረት ~ የጥፍጥናዬ ምንጭ
አይተሽ ስትዘጊኝ ~ ሳይሽ ተቅለስልሼ
ስልጥሽ አነባሁ ~ ስገዛሽ አልቅሼ
#ደሞ
ሽንኩርቴ ነሽ ስልሽ ~ አትስጊ ግድ የለም
ውድነትሽን እንጂ ~ እድሜሽን አይደለም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@getem
👍1