ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እንደው ጊዜው ከፍቶ ብንጨካከንም
የዘር ክፍፍሉ ለወሬ ባይመችም
ኢትዮጵያን ተዳፍሮ ገፍቶ ለሚመጣ
ሀበሻ መልስ አለው በቅኔ 'ሚቀጣ
ብዙ ናቸው አትበል
ልዩም ናቸው አትበል
ሁሉም ከዳር ቆመው ስድብ ሲላላኩ
በክፉ ቀናት ነው
የሀበሻ ፍቅር ፥ የሚታየው ልኩ..
ሀገሩን አትንኩ !!
።።።።።።
#ሚካኤል አስጨናቂ

@getem
@getem
@getem
#ሰውኛ እውነቶች!
።።።።።።።
በላይ በሰማይ ቤት ፣ በሰፊው አዳራሽ
ከንጉስ ፊት ቆመው ፣ ለፍርዳቸው ምላሽ
ሲኦል አንጣልም ፣ ሰይጣን ባሳሳተን
እሱ በሚያጠፋው ፣ እኛ የምን ቤት ነን?
ቢለው ሚሟገቱ ፣ ምክንያት የሚሰጡ
ለክፉ ስራቸው ፣ ከዋኝ ሲያማርጡ
ለፍርድ ቢፋለሙም ...
ገነት ግቡ ተብለው ፍርዳቸው ቢረጋ
መልዓክት በሰሩት በመልካሙ ዋጋ
እኛ የምን ቤት ነን.. ገና የምንገባ ?
ብለው አይጠይቁም !

@getem
@getem
@getem

#ሚካኤል አስጨናቂ
አጭሬ
.
የወረቀት ክምር ፍራሽ ሆኖ ደልቶኝ
እኔን አሳስቆ ለምቾቱ ጥሎኝ
በእንቅልፍ እያዋዛ በሙቀት ሳይገለኝ
የሰው ልጅ ትንፋሹ.. .
የአፉ እፍታ ፥ እኔን ቀሰቀሰኝ።
።።።።
#ሚካኤል አስጨናቂ

@getem
@getem
@getem
#ገለባ አይደለሁም !
አውሎ ነፋስ ደርሶ ~ የሚያርገበግበኝ
ወንጭፍም አይደለሁ
ማንም እያሾረ ~ የሚወዘውዘኝ
እኔ ደራሽ ውሀ
የመንፈስ አምሀ
እሳቱን የሀሜት ~ ምላስ የማከስም
ድኩማኗን ነፍሴን ~ በተጣፉ ቃላት
በፊደል የማክም...
ወጀቡን ነፋሱን ~ የማልፋቸው ጥዬ
አጎንብሼ 'ማልቀር ~ መንፈሴን አ..ዝዬ
ገለባ ነው ሲሉኝ ~ ፍሬ የማፈራ
ሊከስም ነው ሲሉኝ ~ ከርሞ 'ምጎመራ
የርግማን ውርጅብኝ ~ ከቶ የማልፈራ
በጭብጨባ ብዛት ~ ደንቆኝ የማልኮራ
የዝምታው ዳኛ...
በሸክላ ገላና ~ ብረት ልብ ያነፀኝ
እንደ እያሪኮ ግንብ.. .
በጩኸት የማልፈርስ የእጆቹ ስራ ነኝ።
#ሚካኤል አስጨናቂ

@getem
@getem
@getem
#የእንቢታሽ ሱሰኛ!

።።።።።።።።።።
አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ

ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ

ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ

ስምሽን በቦርሳ ጀርባዬ ላይ አንግቼ

እንደ አሞራ ዙሬሽ በላይ አንዣብቤ

ስትሄጅ ተራምጄ ... ስትቆሚ ቆሜ 

ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ

ከእድሜ ከጊዜዬ ዓመታት ቆንጥሬ

ከእንቢታሽ ጋራ በእልህ ሰክሬ

ስንኞችን ጭሬ.. .

አንቺን በመጀንጀንጀን ልማድ ተጠፍሬ

በሚጣፍጥ ህመም ...

ብቻዬን በአርምሞ ሳብሰለስል ኖሬ

ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር 

ቃላት ድል ነስተውሽ በሀይላቸው በትር

እወድሀለሁ ብለሽ የነገርሽኝ ለታ 

ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋ ትዝታሽ ተረታ።

@getem
@getem
@getem

#ሚካኤል አስጨናቂ
🤩1
#የድሀ ትሩፋት!

.

ሀብታም ሆኜ ሳለው ...

ጨብራራ ጎረምሳ ፥ ኑሮ ያሸመደው

ሸራውን ወድሮ ፥ ቀለሙን ሲያፈሰው

እብድ እየመሰለ ፥ ገርሞ እየታየኝ

አብስትራክት ብሎ ፥ ስዕሉን ቢያሳየኝ

ይበልጡን ደበረኝ!

አሁን ይሄ ራስታ ... 

የሀሳብ ከርታታ...

በቀላም ጭቃዎች ፥ ተለውሶ ቆሞ

ብሩሽ እያነሳ.. . የሚለቀልቀው 

አብስትራክት ያለው ስዕሉ ምንድነው?

እኔን የሚገባኝ አብስትራክት ማለት 

ነው ስራ ፈትነት !

ዓላማ ቢስነት !

በውስኪዎች ፈንታ ቀለማትን መርጨት

ከሴት ጋር ተቀምጦ እንደመጉረስ ከንፈር 

በወጣኒ እድሜ ... በግዑዝ መደበር 

ካልጠፋ መዋቢያ ... መፈሸንን ንቆ

በዝተት አልባሳት.. . ገላውን አላሽቆ

ሳየው ይገርመኛል..

ስዕል እየሳለ ስዕል ይመስለኛል ።

...

ሀብታም ሆኜ ሳለው ...

በጫት ቅጠል ነፍዞ ...በሲጃራ ጥንባት

እድፋሟን ስከርቭ.. . አንገቱ ላይ ጥሏት

ውዴ ፍቅሬ ግና.. . ጨረቃና ፀሀይ

የደመናው ንጣት.. .ደግሞም ይሄ ሰማይ

ምናምን እያለ የሚፈላሰፈው 

ያ ምስኪን ገጣሚ እውነት ጤነኛ ነው ?

እያልኩ አስባለሁ ።

አሁን ለዚህ ወጣት ... 

ድህነቱ ገዝፎ ... ፊቱን ላገረጣት

ሰማይ ፀሀይ ብሎ ስንኝ ከሚቋጥር

ምናል ስራ ሰርቶ እህል በልቶ ቢያድር?

እያልሁኝ ኖሬያለሁ ብዙ ዓመታትን

እኔም ድሀ ሆኜ እስካያት ጥበብን።

..

አሁን የሚገርመኝ.. .

በመፅሀፍት ፈንታ ዳሌ የሚያነበው

ቀለም እንደመርጨት ውስኪ የሚያፈሰው

መኪና ሲቀይር ... ሀሳብ ያልቀየረው

ከግጥም ተጋብቶ እንደመኖር አብሯት

ይህችን ብርቅ ዓለም ከሴት ጋር ጨርሷት

የሚኮፈሰው ነው ያ ከርታታ ሀብታም

የጥበብ ስስታም.. .

አብስትራክት ስሎ.. . ስዕል ሳይደረድር

ዓለምን መስጥሮ ... መፅሀፍትን ሳይጭር 

ለሙዚቃው ቅኝት.. . ክራሩን ሳይወድር

ነፍስያን መበደል ... ገንዘብ ብቻ መርጦ

አያስጠላውም ወይ ... መኖር ከሀሳብ ዘቅጦ?

እያልሁ አስባለሁ.. .

የድህነት ትርፉ.. .ጥበብ ነው አውቃለሁ።
....

@getem
@getem
@paappii

#ሚካኤል አስጨናቂ....
👍3
____የኔታ_________

ከውድቀትህ ተማር ብለው ያሉኝ ለታ
ዜመኛውን ያሬድ በምሳሌ ጠቅሰው
ከትል ተማረ አሉኝ ታሪኩን አስውበው።
አይደለም የኔታ
ሰባት ጊዜ ድሀ ሰባት ጊዜ ወድቃ
ኋላም ለመነሳት ያቺ ትል ስትበቃ
በሂደቷ መሀል ንፋስ ባይኖር ኖሮ
ያሬድ ይቀር ነበር ሳይማር ደንቁሮ
አይደለም!
አይደለም!
ያሬድ ምሳሌዎ
ከንፋስ ነው እንጂ...ከትል አልተማረም።

@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል አስጨናቂ...
ለሰርግሽ አልቀርም!
.
#ያኔ !
በጠባብ ቤታችን ... ስንኖር ተጣምረን
ወርቁ ሰውነትሽ ... በመዳብ ሲተመን
ምንድን ነበር ያልሽኝ?
በእጅህ የያዝከው ወርቅ ... ስስ መዳብ ሆኖብህ
ካጣኸኝ በኋላ.. . ማጌጥ እንዳይሳንህ
የጣልከው ሲነሳ ...
የፀፀት ንፋሱ ... ወጀብ እንዳይወስድህ
በያዝከው ተጠንቀቅ
ባለህ አትሳለቅ።
ስትይኝ.. .
ምክር ስትለግሽኝ።
ምንድን ነበር ያልኩሽ?
አስካለ ብትሄድ ትመጣለች ዘውዴ
ይሄ ነው ስሌቴ ይሄ ነው መንገዴ ።
እያልኩኝ ስመካ ...እያልኩሽ ስኮፈስ
አይመስለኝም ነበር ይሄ ቀን የማይደርስ።
ዛሬ !
ዘውዴን እያቀፍኩኝ ጉያዋ ሰምጬ
አንቺን ነው የምራብ ከሷ አስበልጬ
ለካ ወርቄ ነበርሽ !
አምሮብኝ የነበር ለካስ ባንቺ ጌጥ ነው
ይሄንን ያወቅሁት ከጎኔ ሳጣሽ ነው ።
አሁን ላጊጥ ብዬ
ነጭ ጥጥ ፈትዬ
የሚያምር ፀዓዳ ከላይ ብደርብም
ማንም ተውበሀል ብሎ አይነግረኝም።
ለካ ጌጤ ነበርሽ ...
የአንገት ሀብሌ.. . አይን ማሳረፊያ
የራስ ዘውድ አክሊሌ ... የሹሜ መታያ
ሳጣሽ ነው ያወኩት ... ምሉዕ እንደነበርኩ
ይሄ ባይሆን ኖሮ
አንድ ገላ አቅፌ ለምን አንቺን ና'ፈኩ ?
ዛሬ እንዲህ እላለሁ...
የላክሽልኝን ካርድ አተኩሬ እያየሁ
.
አሁን ይሄ ባልሽ ... አንቺን የነጠቀኝ
ክፉ ጠላት ሳይሆን ወዳጅ ነው የሆነኝ
እሷን ባትገፋ
ደርሰህ ባትደነፋ
በመዳብ ለማጌጥ ወርቅህን አትሸጥም
የሚል ትምህርትን ነው ያሻረኝ በልቅም
.
ሰርግሽ ጉባኤ ነው ያደባባይ ውግዘት
እሷን በመተውህ ሰርተሀል ስህተት
ብሎ የሚለፍፍ
እኔን የሚነቅፍ
ስለዚህ መጥቼ ... ባልሽኝ ተገኝቼ
ግጥም እያቀበልሁ ...ዜማ አሰናድቼ
ሀይሎጋ እያልሁኝ ቆሜ እደርሻለሁ
ደስታው ሽፋን ሆኖ በሚታይ ሀዘኔ ልቤን አነፃለሁ።
.
ሽንፈቴ አይደለም ሰርግሽ ላይ መገኘት
ለኔ ንሰሀ ነው
በደሌን የሚያሽር ያፅድቆቴ ጥምቀት ።
.....................


@getem
@getem
@paappii

#ሚካኤል አስጨናቂ....
👍32
#አንቺ እና ግጥም
....
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ሚጥሚጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ።
.

@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል አስጨናቂ


የሚካኤል አስጨናቂ ተጨማሪ ግጥሞችን ለማግኘት።
https://tttttt.me/MichaelAschenakipoems
#ከአንድ_ትውልድ_የበለጠ
( አዲሱ ጉግሳ )

ለአራዳዎቹ ለኛ ባኖ መንቃት
ጭስ ሆኖ ተራቆ መብቃት
ባህር ተሻግሮ ቀድሞ መማር
ከዛ አምጥቶ ደምቆ ማማር

አዎ ለኛ መሰልጠን መራቀቅ
ከራስ ባህል ተፋቶ መላቀቅ
አፋልጎ ለምኖ መጣበቅ

አዎ ለኛ ጀግንነት
አዎ ለኛ አራድነት
ቁስ ይዞ ቅል ሆኖ መገኘት
በቂቤ አፍ በወሬ መዳኘት
ሃብት አካብቶ በገንዘብ መዋኘት

አዎ ለኛ ሠልጥነን ላወቅነው
ትላንትን ክደን ዛሬን ከነገ ለተበደርነው
ክቡር ንቀታችን በጥቁርነቱ ያፈረው
ቅንቅናም ጥጋብችን ባለመገዛቱ ያኮረፈው
አተላው ዕውቀታችን ባለመረገጡ የሚቆጨው
ከንቱ ናፍቆታችን ብገዛ ብሎ ለነጭነት እራሱን ያጨው
እንዲህ በተከበረበት ወርዶ ያቀጨጨው

የጠፋብን ልብ ቢኖር ነው የተሰወረ
የራሱን ክብር አርቆ የወረወረ
የአያቱን ታሪክ ገፍቶ የቀበረ

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ
የሚባል ተረት የሆነው ሞቱ!
አዲስ ትውልድማ መቷል በትላንቱ የሚስቅ
አዲስ ዘመንማ ቆሟል ታሪኩን የሚንቅ

ከዘር ዘራችን የተጣባ
ከደም ደማችን የተጋባ
አዲስ ትውልድማ ደርሷል የሚንቅ ትላንቱን
አዲስ ዘመንማ ጠብቷል የበላ እትብቱን

ምንም ባያረግም ጉራው መከራ
ምንም ባንፈይድም ወሬው ጠንካራ
ባህር ተሻግሮ ለምኖ ለመኖር
ከሰው በታች ሆኖ ለማደር በነውር
ለእሳት አባቱ አመድ ልጁ ደርሷል
ከአያቱ ጠላት ስጋ ልጁ ብሷል
የቤቱን ሞት ከጠላት ተውሷል

ግና ፦
አንዱ ምርቃት በቅን ተወርቶ
ቃል ተሰተካክሎ ተዘርቶ
ቀለም ተስተካክሎ ተቀብቶ
ኩርማን ትውልድ አለ በአያቱ ተባዝቶ
ጀግንነት ያማረው በአባቱ ተስማምቶ

በሚገፋው ዘመን ውስጥ
ከሚበላው የቃል ምስጥ
ከሚያሾፈው የስም ወዳጅ
ከሚሸጠው የወገን አራጅ

ከሁሉም ከሁሉም የነቃ
ለሃገር ምድሩም የበቃ
መነሻውን ያወቀ
በትውፊቱ የደመቀ
ቆሞ የመሞትን ዘመን ያመለጠ
የከረፋን ትውልድ የበለጠ
ዛሬን ወደ ትላንት ይዞ የፈረጠጠ

ከሚያኮራው ታሪክ ላይ የተቀመጠ
ላስከበረው ገድል የተመሰጠ
አንድ ልጅ አለ ብቻውን አንድን ትውልድ የበለጠ
----------------

#ሚካኤል_ሚሊዮን እግርህ በረገጠበት ሁሉ አድናቂው ማንነቴ አበሮህ ነው። from addis gugsa!

@getem
@getem
@paappii
(ሚካኤል ኤርሚያስ)

"እጠብቅሻለው"
******
(ሚካኤል ኤርሚያስ)

በቀለመ ቀንዲል ፍቅርሽን ሳማስል
ከዝርጉ ብራና መዉደድን ሳንጓልል
ለአፍታ ሳይደክመኝ አንዴም ሳይሰለቸኝ
እቴ አንቺን እንዳልኩኝ ላንቺ እንደማሰንኩኝ
ጀንበሯ ጠለቀች
ጨረቃ መንገሧን በሰማይ አወጀች
አላፋት ከዋክብት አብረዋት ወገኑ
ስትደሰት ስቀዉ ስታለቅስ አዘኑ
ይሄ ሁላ ሲሆን
የተስፋ ሽዉታ አንዳችም ሳይቃኘኝ
ጨረቃዋ ፀልማ ፀሀይ ወጣችብኝ
ንጋት ተበሰረ
መኖር እንደገና ባንቺ ተቀመረ
....... አንቺ ግን የለሽም ......
....እኔም ተስፋ አልቆርጥም.........
ዳግም እንደገና
በጨረቃ ሹመት ከዋክብቱ ደምቀዉ
እ..ጠ..ብ..ቅ..ሻ..ለ..ዉ ::

ግና ውዴ
አንቺ ስትመጪ ......

ጥቁር የጉም
ብርድ ልብስ ከሰማይ ላይ ይጠልላል
አፈሩ በካፊያ ሽቶ ርሶ አየሩን ያውዳል
ዛፎች እና ቅጠሎች የዛር ዳንኪራ ይረግጣሉ
አበቦች
ባንቺ ፀዳል ፍንጣቂ ዳግም ህይወት ይዘራሉ

አንቺ ስትመጪ
ይብላኝ ለኔ እንጂ
ጨረቃዋስ ጉም ውስጥ ገብታ ትደበቃለች
ፀሀይስ ብትሆን
ልማዷ ነው ስለክብርሽ ታረግዳለች

አንቺ ስትመጪ

ይብላኝ ለኔ...

እንደ በጋ ዝናብ
እንባዬ በወፍራሙ ለሚንጠባጠብ
አቅሌን አቅበዝብዤ ሌት'ና ቀን አንቺን ለማስብ
ህይወት
መንጋጋዋ መሀል ሰልቃ ለምታላምጠኝ
በልቤ ድውድውታ አሀዝ
መምጫ ቀንሽን ለቆጠርኩኝ

ይ ብ ላ ኝ ለ ኔ

ምንም ሆይ
አልገባሽ ብሎ'ንጂ
እንደ ባህር ሞገድ ተስፈን በሚሰቅዝ
በሲቃ እንጉርጉሮ ሌት'ተቀን ምተክዝ
መናገር ሚጨንቀኝ ማድመጥ ሚሰለቸኝ
ባማተረኝ ሁሉ እብድ ነው ያሰኘኝ
አልገባሽም እንጂ
አንቺ የሄድሽ ለታ ያኔ ነው የጀመረኝ

አየሽ.. ያ ኔ..
መለየትሽ እውን ሲሆን ብቻ መቅረቴ ሲመጣ
መኖር ከሚሉት ፅዋዬ እሬት አንቆርቁሬ ስጠጣ
እንደማይቀር የሆነ ቀን መመለስሽ
ያ ፅገሬዳ እንቡጥ መሣይ ከንፈርሽ
ነግሮኝ ነበር ስትስሚኝ ነግሮኝ ነበር ስስምሽ

እናም ....
ያቺ ቀን መቼ ትሆን
ብዬ ልበ ኦናሽን በልቦናዬ ብጠይቀው
ልክ አንደ እለተ ምፀዐት እሱም ቢሆን አላወቀው

ታዲያ ምንም
መምጫ ቀንሽን ጣኦት ልብሽ ካልተረዳው
ምናልባት
ህቃቆቱን እግዜሩ ይሆን የደበቀው ...?
ልጠይቀው ...?
ወይስ ልተው.....?
እንጃ...

ብቻ አንቺ ስትመጪ ....
ይብላኝ ለኔ እንጂ.....
:
#ሚካኤል ኤርሚያስ
@getem
@getem
@getem
👍4
አይተሽኛል አይቼሻለሁ
"---------------------"
(ሚካኤል ኤርሚያስ)

አይቼያለሁ .....
በአውሎ ንፍስ ፍጥነት በሰረገላ መንጠቅ
ውበት ማማር ሴትነትሽ በሙዚቃ ኖታ ሲረቀቅ

አይቼያለሁ....
ሀሰት የገተራቸው የምኞት ሀውልቶች እርቃን ሲቀሩ
ሀገሬን ትመስይ አንቺን አይተው ሲያፍሩ

አይቼያለሁ ....
እንደሎሬቱ ግጥም መገን ባይሽ በርክቶ ስነ ቃልሽ ሲቀመር
የጠመጠመ ጠቢብ ሊፈታሽ ዋሸራ ውሎ ዲማ ሲያድር


አይቼያለሁ .....
ርጋፊ ጥላ ላይሽ ላይ ሲያጠላ
ፀሀይ እንዳትነካሽ ሊሆንሽ ከለላ

አይቼያለሁ .....
ሰማይ አሸብርቆ ጥቁር ቀን ሲፈካ
ሀዘን በርኖስ ለብሶ በደስታ ሲተካ

አይቼያለሁ.......
በጠረንሽ ከርቤ በወጣት መአዛሽ እጅ'ና እግሩ ታስሮ
ክፍት ሲመሽበት ጥላቻ ሲያላዝን እንጦርጦስ ተቀብሮ

አይቼያለሁ......
በእርቃን ገላሽ አውታር በማቃሰትሽ መዝሙር
ሰርከ ጥበብሽ ሲረቀቅ በበገና ድርድር

አይቼያለሁ....
አንድዬ...
በአልማዝ እንደታጀለ ኮኮብ አንፀባራቂ ሰላም ሲያለብስሽ
ፀሀይ ሁከት ስታስነሳ ሽራፊ ጨረቃ ስታኮርፍሽ

አይቼያለሁ ....
ፀጉርሽ ደረትሽ ላይ ሲበተን ትከሻሽ ላይ ሲነሰነስ
ንጉስ ክብሩን ሲዘነጋ ላንቺነትሽ ሲያጎነብስ

አዎን
ይሄ ሁላ ሲሆን
ቀናይነትሽ ሲቀነቀን ...

አይቼያለሁ..
ገርመሽኛል
አጀብ እንጂ
ምን ይባላል

የኔ..
ተፈጥሮን ማዘዝሽ
ለአፍታ ሳይደንቅሽ
መታበይ ሳያምርሽ
ኩራት ሳይከጅልሽ
እቅፍቴን ናፍቀሽ
ክንዴን ተንተርሰሽ
በለሆሳስ ሹክሽኩታ
በአይን ጨዋታ
አንድ ነገር ስትይ
ርግቧን ስትመስይ

አ.ይ. ቼ .ሻ .ለ. ሁ ኝ ...
:
...አዎን...
አ.ይ.ተ.ሽ.ኛ.ል .....
ከትኩስ ሴትነትሽ
ውብ ከቀላ ጉንጭሽ
በርብትብት ከናፍር
ከእርቃን ገላሽ ላይ
መለመላ አካሌ
ፍቅርሽን ሲደውር

እፍረት የታባቱ
ማፈር ምናባቱ
የምድር የሰማይ
አንቺ ነሽ ንግስቱ
ስልሽ
ሳወራልሽ
ከአንገትሽ ስር ሆኜ
በአፌ እንፍሎት ጆሮሽን ሳሞቀው
ትዝ ይለኛል ፍቅሬ
አዎን አይተሽኛል አዎ አይቼሻለው ::

#ሚካኤል ኤርሚያስ
@getem
@getem
@getem
👍1
"ቢኖር ደስ ይለኝ ነበረ"
**********
የኔ..ቢኖር ደስ ይለኝ ነበረ.......
እንደኔ አለሙን በሙሉ ስላንቺ የኖረ
አንቺን... ፅላቱ አድ'ርጎ ተሸከሞ የዞረ
ፋቅሬ.. ቢኖር እወድ ነበረ.......
በሻከረ እጁ ሙቀት ወበቅ ችሎ
ልም አፈሩን ዘግኖ ስለፋቅርሽ መኖ
መቅደስሽን ሚያጥን በልብሠ ተክኖ
ቢኖር........
በመዉደድሽ ዛር ከዋሻ የገባ
ስላንቺ የፀለየ ስላንቺ ያነባ
ደስ ይለኝ ነበረ........
እንደኔ ........
ያን መሳይ ሰዉ ቢገኝ ምኞቴ ነበረ
አንቺ አዘዝሺኝ ብሎ የምድር አሸዋ
በእጁ የቆጠረ
በመዳፉ እፋኝ ጉም የዘገነ
ባንቺ የኮሰመነ ስላንቺ የገነነ
ግን ከወዴት ይገኛል..
ፋቅርሽ እኔን ብቻ
ከምስኪኑ ልቤ ዉበትሽ
ዝናሩን እያግተለተለ
ሲያሻዉ ይማርከኛል
ሲለዉ ይፈጀኛል ....
ፋቅርሽ እኔን ብቻ ........::
#ሚካኤል ኤርሚያስ
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል ኤርሚያስ)

እንዴት ባዳ ሆንን....?
እንዴትስ አልገባን የሚበልጥብንን
እንዴትስ አላየን የሚያሻግረንን

ከህይወታችን መፀሀፍ ላይ
ከተገነጠለች አንዲት ነጠላ ገፅ
ብላፍ ብዳክር
ብወጣና ብወረድ ላወጣበት ህፀፅ

አንዳች አላገኘው ጎሪጥ ሚያተያየን
ኸረግ አልገባኝም ምንድነው የለየን

እፎይ ማ'ያ ጎጆ ብንናፍቅ
ከእ'ኛ ወዲያ ላንል ፈቀቅ

ምን ባትጨክኝ ባትሸሺ ሕም ባልርቅሽ
እኔም አንቺም ባዳ ለፍቅሬ ለፍቅርሽ

እንዴት ሆነ ይሄ......?

ትዝ ይልሽ እንደሆን ...
ንጋት ...
ከወፎች ጋር ተሻምተን
ጠይም ጠሀይ ስትወጣ
በለሆሳስ እንዳላቀነቀንን
ምሽት ...
ባለጅራታሙን የሰሜንኮከብ ተመልክተን
አፍችንን በእጃችን ገርበብ አድርገን
አጃኢብ ብለን ተፈጥሮን እንዳላደነቅን

ትዝ ይልሽ እንደሆን ......

እወድሻለሁኝ ስል
ያልነበረችገደል ማሚቱ ለእኔ ስትል መጥታ ድምፀቴን እንዳላስተጋባች
ምነው ዛሬ ስንበክን እንዴት አሁን ስንመክን ልትሸመግለን አልመጣች

ታ.ዘ.ብ.ኳ.ት

ያኔ ...
ናፍቆተ እንባን ስናነባ
ፍቅር በእሳት ልምጭ ሲገረፈን
ስለመውደድ ደረታችንን እየደቃን
ሀዘን ሳይሰብረን ተፍነክንከን
መከፍት ላይ እንዳልሳቅን
ስንቱን እንዳልተሻገርን

የመነጠልን ቅዝምዝም ዱላ
በትእግስት እንዳልመከትነው
አሁን ...ፅኑ ፍቅራችንን
ምንድን አቅሙን ነፈገው ....?

መልስ አለሽ ?
እኔ የ.ለ.ኝ.ም
ኸረግ አ ል ገ ባ ኝ ም ....

ቀድሞ..
የነፍስ ሀቅሽ ከነፍስ ሀቄ ተዋዶ
አንቺነትሽ ከእኔነቴ ተጋምዶ
መጠላለፍችን ላይጥለን
ሀረግ ይመስል እንዳላጎለበተን
አሁን...
ለነጠላ መጋፈጡን
ለየቅል ኩታ ብርድና ውርጩን ማሳለፉን
እንዴት ቻልን.......?

ለፍቅርሽ ለፍቅሬ እንዴት ባዳ ሆንን....
መልስ አለሽ ...
እኔ የለኝም
ኽረ እነደውም ...አልገባኝም ...
መልስ አለሽ ...

#ሚካኤል ኤርሚያስ

@getem
@getem
@getem
👍3
"ወርቅ ቅብ"
***
እኔማ.......
ወርቅ መምሰያ ቅብሽ
ጥቂት አየለና አይኔን ቢጋርደው
በቀይ እንቁው ሚዛን
አንቺን ቅባቅቧን እመዝንሻለው
ከዛ.....
ላላፊ አግዳሚው
እሳቱን ይመስል ወርቅ ናት እላለው
:
ምንም ቢገዝፋ ቅባቅብሽ
ወርቅ እማ ወርቅ ነሽ ለኔለአፍቃሪሽ
እስኪ አስቢው .....አሁን ምን ይሉታል......?
በቀይ እንቁ ሚዛን ቅባ ቅብ መመዘን
በይሁንታ ምኞት
ወርቅ ናት እያሉ በአንደበት ማላዘን
ልብን እያራዱ በልበ ኦና ማዘን
ንፍገተ ክብርሽን በላይሽ ላይ መድፍት
በፍቅርሽ ታፍሮ
ሀሰትሽን ታቅፎ ሀቅ ላይ መደንፍት
እኮ ይሄን ምን ይሉታል......?
በእሳቤ ጥጋጎት ወደላይ ማንጋጠጥ
የፈጠረሽ ጌታን
ወርቅ አድርግልኝ ብሎ ዘውትር መለማመጥ
እስኪሰማኝ ድረስ ሌላ አለማዳመጥ
በህላዌ አንድምታ
በጥቀርሻ ጥፍር አይምሮንመቧጠጥ
ወርቀ ቅባ ቅብነትሽ ታጥቦ እንዲለቅሽ
ማሳበቅ ላምላኬ ማሳበቅ ላምላክሽ
እሱ..ምንም ማይሳነው ..
ወርቁን እንዲያደርግሽ
መማፀን በእግዜሩ ቤት ስምሽ
:
ይሄ ብቻ መስሎሽ........
:
የኔ የልብ መሻት....
ከምመዝንበት
ከቀይ እንቁ አክብሬሽ በጥበብ ሰውሬሽ
እስከ ዐለም እጥፍት ነበር ፍላጎቴ በልቤ ላኖርሽ
ይሄ የኔ መሻት ነው .........
እሷ ግን ......
አሁን ያልኩት ሁሉ ለሷ እንዲሆንላት
ማንጋጠጤን አይቶ እንዲፈፅምላት
ቅባቅቧን ነስቶ ወርቁን እንዲያለብሳት
በጥበብ ሞሽሮ ከልቤ እንዲያውላት
ምለምንበትን ልብ ምልበትን
እኔነቴን ሰልባህቃቆቴን ነስታ
ቀልበ ቢስ ትላለች ማረሻ ስለቴን
አቀቀርቅራ እያየች ከጎኔ ተኝታ።

#ሚካኤል ኤርሚያስ

@getem
@getem
@getem
👍3
"አትዋሹን"
*
በቀረና ልሳን
ነጠላ አጣፋታ ዳዊት የምትደግም
በከረፍ ምናብ
ቁራን እየቀራች ፈጣሪን ምታልም
ጥንትም ሆነ ዛሬ
ያቺን መሳይ ሀገር እኛ የለችንም ::

አ.ላ.ወ.ረ.ሱ.ን.ም!!!!

ምን
ከመቻል ምጣዷ ጠኔ እያሰፉባት
በውቂያዋ ማግስት ሀገሬን ቢርባት
ምን
በጠለሸ መውደድ
የጨቀየ ፍቅር ሰርክ እየጨለፉ
ጨለማ እንዲነግስ
መቅረዞቿ ቢያልፋ
ምን
ጣር ጠምቀው ግፍ ግፍ ቢግቷተት
ምትልስ ምትቀምሰው እሬት ቢሆንባት
ምን
ትውልዱን ማርትሬዛ ሸሽቶት ጠገራ ቢርቀው
ማጣት በምንዱባን እጁ ዘሩን ቢያስቆጥረው
ምን
ጨቅላ ሀሳበኞች በግርድፉ ዘምተው
አንዱ ያነፀውን ሌላኛው ቢያፈርሰው
ምን
ውድቀቷን የሚሹ ሺ ቢፈለፈሉ
የአንድነት አካሏን ከፍፍለው ቢስሉ

እሷም ብትሆን
መጣፈጧን ረስታ መምረርን ብትመርጥም
ያቀናት ብርቱ ነው
ያፀናት ፅኑ ነው ሀገሬ አትፈርስም::

#ሚካኤል ኤርሚያስ

@getem
@getem
@getem
👍5
በ'ያ በጥቀርሻ ልብሽ
በ'ያ በሰባራ ሚዛን
ሀቅሽ ስንት ይደፍል
እውነት ምን ያህ'ላል
በይ ሰፍረሽ ጠቁሚኝ መዘነቺኝ እንድል
መቸስ ቁስ ሆኛለሁ
እኔ ያንቺ ጥሬ እኔ ያንቺ ብስል

እቴ ያንቺ ልሳን
እውነት ያውቅ እንደሆን
ስንት ነኝ.... እኔ ያ አንቺ ስሆን

ላድምጥ ተናገሪ...

ን'ሺ አመልክቺኝ....
ስፈሪኝ መትሪኝ ...
እኔስ አውቀዋለሁ
አንቺ ይሄንነህ በዪኝ

ደሞ ....

እይታሽ ከልቤ በስንት ይራራቃል
ኩርፊያሽ ስንት አክስሞ ስንቱንስ ያፀድቃል
ስንቱን ሞገስ ችሮ ስንቱንስ ያሳጣል
ምን ያህል አብቅሎ ምን የክል ያጠፍል

ሳቅሽስ የዕውነት ይሆን

(ግራ ቢገባኝ ነው እኔስ መጠየቄ )

ባይሆንም..
ግድ የለም ይህ ልቤ
ይቻል ፀያፍሽን ይመን ሀሰትሽን
ስትስቂ ልሳቅ ጥርስሽ ጥርሴ ይሁን
አለ ዐይደል
ስቄ ነበር እንድል
ላንቺም ደስታሽ እንዳይበክን
ብቻ ተፍነክነኪ ፈገግታሽ ሙሉ ይሁን
አሜን.. አሜን.. አሜን

(ምንም እየከፋኝ)

በፈግታሽ ግርዶሽ ሀዘኔን ልሸፍን
በደሌን ልገንዝ ማዘኔን ልከፍን

(እንደምንም ብዬ)

ምንም የመዐተብ ባይሆን
እሱን ማን አየበት ....
ላይጣፍጠኝ ህይወት
አንቺ የሌለሽበት

ባይሆን ....

የኔና አንቺን ነገር
ነበር ማለት ይቅር
ዛሬ አሁን ይሁን መልሴ
ለጠየቀኝ ሁሉ
አለች አለች ልበል ነሽና እስትንፋሴ

(መኖር ማን ይጠላል )

ፀሀዬ ነሽና
ደርሰሽ ምታሞቂኝ
ጭጋግ ምትገፊልኝ
ሲልሽ ምታነጂኝ
ጨረቃ ነሽና
ሲፀልም መንገድ የምትመሪኝ
ብረሀን ምትሆኚኝ
ስትጨክኝ አጋልጠሽ ምትሰጪኝ

( አውቅሽ የለ እኔ ስትግዪም ስትበርጂም)

እንኪ ይ'ኽው
መፀደቄን ፅደቂ መርከስሽን ልርከስ
በኔ ፀሎት እንባ በደልሽ ይታበስ

እኔ እንደው
ያቆሸሺኝ አንቺ ያረከሰኝ ፍቅርሽ
ከገላሽ ያዋለኝ ያኖረኝ ከስርሽ

አንቺ እንደው

ገላሽ ማቅ አያምረው አመድ አያገድፈው
ወትሮም ቆሻሻ ነሽ ማንም ሚፀየፈው
ዳሩ ግድ አይሰጥሽ ...

(ይሄን በሆዴ ነው ያልኩሽ ያው ስታናድጂኝ )

እናም ...
ከእግዜር ደጅ አትሂጂ
ተዪ አትደፊ እኔ ወድቅልሻለሁ
የት አውቀሺው ይማር
የሚያውቀው እኔን ነው

(ፃድቅ ስሆንብሽ
ስመፃደቅብሽ )

እርሱ ከዋልሽበት አይውል
ልማራችሁ እንጂ ጨክኛለሁ አይል

(ዳሩ አንቺ አትማሪ )


ይልቅ ...
ልጠይቅሽ...

(ይሄን ካልኩኝ ሗላ)

እንዴት ነው ሰፈርሺኝ
እንዴት ነው መዘንሺኝ ሀቄንስ አሰላሽ
ልኬቴን ንገሪኝ
ደርሶአያገባውም
በኔ ና አንቺ ፍቅር ሂያጅና ተመላሽ

እችልሽም የለ ...እንደምድር ሆኜ
እሳትህም ናት ሲሉኝ
ውሀህም ናት ሲሉኝ ሁሉንም አምኜ ።

#ሚካኤል ኤርሚያስ

@getem
@getem
@paappii
👍9
ማንም አልነበረም

ፀሀይ እንዳቆረናው የበረሀ ባልጩት
ነፍረን ግለን ስንዋትት ስንቃትት
ገላሽ ትኩስ ገላዬ ትኩስ ሲሆን
እርቃናችንን አዋጥተን መለመላችንን ስንሸፍን

ማንም አልነበረም ...

ድምፃችን ሲሰል'ል ልባችን እየዘለለ ሲፈርጥ
ፍቅር እንደማር ከልበ ቀፎዐችን ሲቆረጥ
በነብሰ ምላሴ ልሼሽ ትጣፍጫለሽ ስልሽ
በእጄ በከንፈሬ በሁለ ነገሬ ስቀምስሽ

አልጠገብኩሽም ስል
ስልምልም ዐይኔ ሲዋልል
ገፅሽ መራብሽን ሲያሳብቅ
ከናፍሬ መበላትን ሲናፍቅ
የፍቅር ሳግ እያነቀን
አልጋችን ሲጠበን

ኩታዬ ሲሸነፍ ነጠላሽ ሲረታ በእርቃናችን
ማንስ አየኝ ማንስ አየሽ አንቺን ..?

ማንም አልነበረም ...

የባህል የወግ ክርን ሳይደቁሰን
በዐለማችን ተወስነን ተቆፍድደን
ካለቋንቋ በጥቅሻ ሳናግርሽ
ስንማፀን ቀን እንዲመሽ ቀን እንዲሸሽ

ከለጋ ጨረቃ ጋር እያወጋን
ለፍቅራችን እማኝ ሁኚልን ስንላት
አለሁላችሁ ስትለን
ነግቶ ፀሀይ እስክትገፈትራት
ስናዝንላት
ስታዝንልን
ለኛ ከእኛ ውጪ ማን ነበረን
ወገ ለሊታችንን የታዘበን ...

ማንም አልነበረም..

ጭንቀት ሲቀጋን ሲወቅረን
ልባችን ደረታችንን ሲረግጠን
ህሊናችን አፍለኝ እንባ ሲያነባ
ለጋርዮሽ ቀኝም ግራም ስንጋባ

ስንማማል
ጥምረታችን
እንደ ጥቅምት ማር ሰንብቶ ላይመረን
አሀዱ ብለን ተቀማምሰን ጣፍጠን ጥመን
የደስታ ከበሮ ስንደልቅ
ከረግረጉ በሀሪያችን
ምንጨ ንፁ ሆነን ስንፈልቅ
ማን ነበረ
ሀቅ ነው ባይ መስካሪ
ለኔ ለዐንቺ ከሸንጎው ፊት ተናጋሪ ...

ማንም አልነበረም...

የአድማስ ስር የፀሀይ ስርቅታ
ወደ ጎሬዋ ስትጠልቅ እኛን አይታ
በመጥለቋ ተከፍተን
የምንምነት ጅራፍ ሲገርፈን
ቆዪ ማለት ሲሳነን

ከኛ ሆና ለ'ዐፍታ
ከኛ ርቃ በ'ዐፍታ
(እቺ የፀሀይ ሽፍታ)
ነገ ትመጣ ትሆን ብለን
በልቤ በልብሽ ጠይቀን
አዎ ስንል በደቦ መልሰን
ተስፍ ጥለን ተስፍ አንገትን
በዕቅፍችን ትከሻችንን
ስ ን ጎ ነ ጉ ን
ፀሀየ ስርቅታን ስንናፍቅ
ማንስ ከፍው የቱስ ነበር ሚስቅ ..?

ማንም አልነበረም.....

እኔ እና አንቺ ብቻ ልብሽ እና ልቤ
አትድከሚ እቴ
ጠንቅቄዋለሁኝ ኹሉንም አስቤ

ማንም የለም በቃ

#ሚካኤል ኤርሚያስ

@getem
@getem
@getem
👍325👎1
በመፅሀፍ የሚገኝ ደስታ
ብሄራዊ ትያትር.. . Tommorow afternoon local 7.00
ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው ። መነሻችን የሰው ማህፀን መድረሻችን የሰውነት ስሪት ቀመር ነው።
ከሰው ማህፀን ተፈጥረን በሰውነት አፈር ውስጥ እንደበቃለን።
መድሀኒቴ እናንተ ናችሁ ... ስፅፍ የምናቤ ግብዓት ናችሁ ።
የፅሁፌ ትርፍ ገንዘብ አይደለም...አንድ መፅሀፍ ፅፈህ.. .ሀገር ምድሩ እስኪታዘብህ ፕሮሞት አድርገህ.. . ለሳምንት ምሽቶች መዝናኛ የሚሆን ትርፍ እንኳ አታገኝበትም።
ብዙ ደራሲዎች ለምን ትፅፋላችሁ ብትሏቸው መልሳቸው ምንም ነው። ስነ ፅሁፍ ልክፍት ነው... እያንዳንዱን ስራህን ቅርፅ አስይዘህ መሬት ስታወርደው አዲስ ፍጥረት ፕላኔቷ ላይ ያመጣህ ያህል ይሰማሀል።
ትርፍህ የሰው ሀሴት ነው። ለምሳሌ ሸግዬ ሸጊቱን ያነበቡ ሰዎች ሲደውሉ አንተ በፈጠርካቸው ታሪኮች ላይ በስሜትና ደስታ ሲያጫውቱህ የሚሰማህን እርካታ ብዬ ልገልፅልህ እችላለሁ?
...
ሸግዬዋን ነገ እንመርቃታለን። ሁላችሁንም ጋብዣችኋለሁ...ለብዙዎች በስልክም በቴክስትም እንዳትቀሩ ብያለሁ። ሌሎቻችሁም በስጋ ስራ ተወጥሬ ዘንግቻችሁ ቢሆን ይሄን ተረድታችሁ ነገ ተገኙልኝ።
ስትገኙ ከእናንተ የሚጠበቀው ፅሞናችሁን ይዛችሁ መምጣት ብቻ ነው።
ትኬትም ገንዘብም አልሻም...እናንተ መጥታችሁ በታላላቅ ገጣምያን እና ደራሲያን ስራዎች ተደስታችሁ መሄዳችሁ ብቻ ለኔ ክብር ነው ።
አክብሬ ጋብዣችኋለሁ።
አደራ !!
#ሚካኤል አስጨናቂ
👍15🔥3
‘’ይሄስ ቀን ባለፈ
ፅልመት በገፈፈ
ጥለሽኝ ብትሄጂ
በወጣሽ ከቤቴ
ጉዷ ባለቤቴ …
እህህ እያልኩኝ
እንዲህ እያማጥሁኝ
አደባባይ መኃል
የማልናገረው …
ብዙ ህመም ነበረ
ደሜን ያመረረው ።’’
በማለት የፃፈ
አንድ ባል ነበረ !
‘ምን ሆነህ ነው? ‘ ስለው
እየተማረረ …
'ላንተ ከተናገርኩ
ስንቱን እንደቻልሁት
ይሄን ግጥም ታድያ
ለምን ነው የፃፍኩት ? '

ብሎ መለሰልኝ !

(ፈርቷት ነው መሰለኝ🙄)

#ሚካኤል

@getem
@getem
@getem
30👍14😁12