ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ሮሜ 8÷34 " #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡" #ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና…


1ኛ ጢሞቲዎስ 2፥5

"አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም #መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤"

#የክርስቶስ ሰው የመሆን ምክንያት በዚህ መልእክት በሚገባ ሰፍሯል። በአዳም #በደል ምክንያት #ከእግዚአብሄር ፊት የራቀው #የአዳም ዘር ዳግመኛ #የእግዚአብሄርን #ፊት ለማየት የሚያስችል #ንጽህና ያልነበረው በመሆኑ፣ በእርሱ እና በአምላኩ #መካከል ያለውን #ክፍተት የሚሞላ ስላላገኘ፣ "አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን #አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን፥ #አቅና"፣ እጅህን፥ ከአርያም ላክ #አድነኝም" (መዝ 118፥25 ፣ 144፤ 7-8) በሚል በብዙ #ጩኸት ውስጥ ነበር። ክብር ለእርሱ ይሁንና ፍጹም #ሰው ፍጹም #አምላክ በሆነው #በክርስቶስ <<.... #በደሙ የተደረገ #ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም #የበደላችን #ስርየት>> ነው (ኤፌሶን 1፥7)።
" #መካከለኛ እንዲሆን እግዚአብሔር #አንድያ #ልጁን ላከው... [ምክንያቱም ደግሞ <<ወንድም ወንድሙን #አያድንም ሰውም #አያድንም>> እንደሚል(መዝ 49፥7) መጽሀፍ፥ #ሰው(ፍጡርና የአዳም ልጅ) #መካከለኛ ሊሆን... እና #ሊያድን የማይችል ደካማ #ፍጡር ነውና። የሰው ልጅ ብቻም ሳይሆን <<ከሰማይ #መላእክት እንኳ ቢሆን ከምድርም ሰው መካከል አንድስ እንኳ #ለመካከለኝነቱ ብቁ ሆኖ #ሰውና #እግዚአብሔርን #ማስታረቅ የተቻለው አልተገኘም አይገኝምም። "ደም ሳይፈስም ስርየት የለም"(ዕብ9፥22)። #በሰውና #በእግዚአብሄር #መካከል የነበረውን #የጥል #ግድግዳ ለማፍረስ በመካከል የገባ፣ ሁለቱን #ያስታረቀ፣ ሰውን ከሰማያዊ ርስት የቀላቀለ #ጌታ #ኢየሱስ #ብቻ ነው>>።
📖/፤ ብርሃኑ አበጋዝ፤
^ክርስቶስ^ (2007) ገጽ 38።
#ክርስቶስ #የመካከለኛነት ሥራውን የሰራው በመከራ ሞቱ በመሆኑ ሁላችን #በእርሱ #በኩል ወደ #እግዚአብሔር #የመቅረብ መብት እንድናገኝ አስችሎናል ለዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን #በዐዲስና #በሕያው #መንገድ ወደ ቅድስት #በኢየሱስ #ደም በመጋረጃው ማለት #በሥጋው #በኩል እንድንገባ ድፍረት..." እንዳለን የሚያስተምረው (ዕብ 10፤ 19-20)።
#የክርስቶስን #የመካከለኝነት ሥራ ለመቀበል የከበዳቸው ሰዎች ለዚህ ጥቅስ የሚሰጡት መከላከያ #ሐሳብ ቢያጡ ከምንባቡ ውስጥ <<ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ>> የሚለውን መዘው በማውጣት በእርግጥ #ክርስቶስ በዚህ ምድር ሳለ #የመካከለኝነት #ሥራ ሰርቶ ነበር አሁን ግን እንዲህ ያለ ነገር #በእርሱ ዘንድ #የለም የሚል #ሐሳብ ያቀርባሉ። ወገኖቻችን በዚህ ስፍራ ላይ #ሐዋሪያው #ጳውሎስ #ክርስቶስን ^ #ሰው^ ማለቱን አላስተዋሉም ይሆን?? አሁን በሰማያት የእኛን ሥጋ ሥጋው ያደረገ መካከለኛ (ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ) አለን። ለዛም እኮ ነው መጽሀፍቅዱስ፤
""ስለእኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ ገባ"(ዕብ 9፥24 ፣ 28)""
""ስለእኛ የሚማልደው(ሮሜ 8፥34)፤""
""ዘውትር ሊያማልድ...ብሎም በእርሱ በኩል የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል(ዕብ 7፥25)፤""
""እንዲሁም በሰማይ ባለችው መቅደስ አገልጋይ"(ዕብ 8፥2)""
""የአዲስ ኪዳን መካከለኛ(ዕብ 9፥15፣ 12፥24)፤""
""በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ #መካከለኛ #እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል።""(ዕብ 8፥6)
""ዘላለማዊ ሊቀካህን""(ዕብ 2፥17፣ 3፥1፣ 4፥14፣ 6፥20፣ 7፥26፣ 8፥1)....ወ.ዘ.ተ የሚለው።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ዕብራውያን 5፤ 7-10 << እርሱም #በስጋው #ወራት #ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ #ጩኸትና #ከእንባ ጋር ጸሎትንና #ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።>> አንዳንዶች…


ዕብራውያን 7፤ 20-28

<< እነርሱም ያለ #መሐላ #ካህናት ሆነዋልና፤ #እርሱ ግን። ጌታ። አንተ #እንደ #መልከ ጼዴቅ ሹመት #ለዘላለም #ካህን ነህ ብሎ #ማለ #አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት #ከመሐላ ጋር #ካህን ሆኖአልና ያለ #መሐላ #ካህን እንዳልሆነ መጠን፥ እንዲሁ #ኢየሱስ #ለሚሻል #ኪዳን #ዋስ ሆኖአል። #እነርሱም እንዳይኖሩ #ሞት ስለ ከለከላቸው #ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ #እርሱ ግን #ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ #የማይለወጥ #ክህነት አለው፤ #ስለ እነርሱም #ሊያማልድ #ዘወትር #በሕይወት #ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ #በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ #ሊያድናቸው ይችላል። #ቅዱስና ያለ #ተንኮል ነውርም #የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ #ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ #ሊቀ #ካህናት ይገባልና፤ #እርሱም እንደነዚያ #ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ #ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ #ኃጢአት #ዕለት #ዕለት #መሥዋዕትን ሊያቀርብ #አያስፈልገውም፤ ራሱን #ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ #ፈጽሞ #አድርጎአልና። ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች #ሊቀ #ካህናት #አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ #የመሐላው #ቃል ግን ለዘላለም #ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።>>


<<ለሚሻል ኪዳን ዋስ>> የሆነው #ክርስቶስ እስከሚመጣ ድረስ #ሞት #በአገልግሎታቸው እንዳይቀጥሉ #የከለከላቸው 83 #ሊቃነ #ካህናት ተሹመው ነበር። በቀደመው ኪዳን ውስጥ የነበሩ #ሰዎች አገልግሎት ፈልገው <<አንድ ሰው ተቸግሮ #ካህን ፍለጋ ምናልባት ይሄዳል። ሲድርስ ግን < #ኸረ ሞቶአል! እሌላ ዘንድ መሀድ ያስፈልግሀል> ይባልና ሰውዬው #ዐዝኖ ይሄዳል። #በኢየሱስ ግን እንደዚ የለም፤ #በፈለግህበት ጊዜ ፣ #ባለህበት ቦታ #እርሱ በዚያ አለ>>።
📖/፤ ዳ.እ፣ የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ እብራውያን ትርጓሜ (ጎንደር፣ 1995 - 5ተኛ እትም) ገጽ 53።
📖/፤ GBV፣ የዕብራውያን መልእክት አንድምታ (ትርጓሜው ከነንባቡ)፣ (1998) ገጽ 61።

#በእግዚአብሄርና #በሰው መካከል እንዲሆኑ #ተስፋ የምናደርጋቸው (የካህኑን ሥራ እንዲሠሩ የምንጠብቀቸው) በሙሉ #በምድር በነበሩ ጊዜ (ከሥጋ ሞታቸው በፊት) በነበረው #አገልግሎታቸው እርሱን ሲያከብሩና #በእርሱ #የክህነት #አገልግሎት ሲጠቀሙ የነበሩ ናቸው። ምናልባት እነዚህ #ሰዎች #በአገልግሎት #ዘመናቸው #ካህናት የነበሩ ቢሆኑም እንኳ አሁን ግን #ሞት ከዚህ አገልግሎታቸው #ሽሯቸዋልና #ከእንግዲህ በዚህ በኩል #ሊያገለግሉ አይችሉም። ስለዚህ #ሞት ወደማይያዘው፣ #ክህነቱም #ዘለዓለማዊ ወደ ሆነው #ጌታ መጠጋት የተሻለ #ውሳኔ ነው።
#መድኃናችን @ክርስቶስ <<አስቀድሞ ስለራሱ ኃጢአት>> ያቀረበው #መስዋእት የለም። ምክንያቱም እርሱ #ቅዱስ#ንጹሕ#ነቀፋ የሌለበት፣ #ጻድቅ ነውና #ክህነቱም ነቀፋ የለበትም። እንዲህ ያለው #ቅዱስ ስለእኛ #በደል ራሱን #መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ <<ምንኛ #የከበረ #መሥዋዕት ነው፤ ለሰዎች ሁሉ #ደኅነንትን ለመስጠት #ኢየሱስ #ሕይወቱን #መሥዋዕት አደረገ። ኢየሱስ ወደዚህ #ዓለም የመጣው #ሕይወቱን ለብዙዎች #ቤዛ አድርጎ #ለመስጠት ነው (ማርቆስ 10፥45)። በመጨረሻም ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት <<ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ #የዐዲስ ኪዳን #ደሜ ነው> አለ (ማርቆስ 14፥24)። ለዚህ ነው #በኢየሱስ #ሞት፥ ባፈሰሰው #ክቡር #ደም ድነናል ብለን የምንመሰክረው>>።

በቀደመው ኪዳን አንዱ #ካህን #ሞቶ ሌላው #እስከሚሾም ድረስ #ካህን የማይኖርበት ጊዜ መፈጠሩ እርግጥ ነው። ይህ ደግሞ #በካህኑ አማካይነት ይደረግ የነበረው #የዕርቅ #ሥርዐት ምን ያህል #ችግር ያለበት እንደ ሆነ አመላካች ነው። የእኛ #ሊቀ ካህናት #ኢየሱስ ግን #ዘላለም #በቦታው ስላለ በእርሱ የሚያምኑት #ካህን የሚያጡበት ምንም #ምክንያት የለም። እኛስ ከዚህ #ታላቅ #ሊቀ ካህን ወደ የት እንሄዳለን? መጽሀፉም << #ቅዱስና ያለ #ተንኮል #ነውርም የሌለበት #ከኃጢአተኞችም የተለየ #ከሰማያትም #ከፍ #ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ #ሊቀ #ካህናት ይገባልና፤>> የሚለው ለዚሁ ነው(ቁ.26)።

ምንባቡ <ፍጹም ሰው> ስለሆነው ስለ #ኢየሱስ እየተናገረ፤ ለዚህም ደግሞ በቀደመው ኪዳን እና #በእርሱ #ክህነት መካከል ያለውን #ልዩነት እያቀረበ <<ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የተገለጠ ነው>> እያለ (ቁ.14) << #በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ #ሊያድናቸው ይችላል>> ብሎ እያስተማረ (ቁ.25) መሆኑን እየተመለከቱ፤ <<በመቀጠል "ውውእቱስ ይነብር ለዓለም እስመ ኢይሠዐር ክህነቱ" (እርሱ ግን #ለዘላለም ይኖራል፤ ክህነቱ አይሻርምና) በማለት የካህናተ ሓዲስ አለቃ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ግን <ዘለዓለማዊ አምላክ> ነውና መሻር መለወጥ የሌለበት ክህነቱም የማይለወጥ እንደሆነ ጻፈልን>> የሚሉ ሰዎች ክፍሉ ስለ #ክርስቶስ #አምላክነት እንደማይናገር ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን #ነገረ #ምልጃውን #ለመሸፈን መሆኑ ግልጽ ነው።
📖/፤ ሮዳስ ታደሰ (መጋቤ ዐዲስ)፣ ነገረ ክርስቶስ ክፍል 1 (የካቲት 2008) ገጽ 491።

ሐዋርያው አይሻርም ያለው #ክህነቱን እንጂ #መንግስቱን እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ደግሞስ በራሳቸውም ሆነ በ2000 በታተመው 80 አሀዱ <<ለዘላለም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል>> የሚል መስፈሩን እንዴት አላዩት ይሆን? በአንድምታውስ <<በእሱ አስታራቂነት ወደ እግዚአብሔር። የቀረቡትን ማዳን ይቻለዋል። ፈጽሞ ሕያው ነውና። ተንበለ ሲል፤ አንድም በቁሙ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ እስከ ምጽአት ድረስ ሲያድንበት የሚኖር ስለ ሆነ>> መሆኑን መስፈሩን ምነው ሳያነቡት ቀሩ?
📖/፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 434
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፣ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 647።
(⁉️ ተንበለ ፦ <<መለመን፣ መጸለይ፣ መማለድ፣ ማማለድ፣ ማላጅ፣ አማላጅ መሆን፣ ዕርቅ ፍቅር ይቅርታ መፈለግ፣ ማረኝ ማርልኝ ማለት>>
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ (አለቃ) መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ(1948) ገጽ 900)።
ታድያ #በ80 አሀዱም ሆነ #በአንድምታው ላይ #አስታራቂ መሆኑ የሰፈረው እርሱ ራሱ #አምላክ አይደል እንዴ? ከማን ጋር ነው #የሚያስታርቀው? (ይታረቃቸዋል ሳይሆን ያስታርቃቸዋል የሚለው አገላለጽ ዕርቁ የሚከናወነው ከሌላ አካል ጋር እንደ ሆነ ነው የሚያስረዳው)

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ዕብራውያን 9፥15 እና 24 <<ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት #የዘላለምን #ርስት #የተስፋ #ቃል እንዲቀበሉ እርሱ ፨የአዲስ ኪዳን #መካከለኛ፨ ነው። . . . ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን #ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን #በእግዚአብሔር #ፊት #ስለ #እኛ #አሁን #ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ #ሰማይ…


ወደ ዕብራውያን 10፤ 10-12

<< በዚህም ፈቃድ #የኢየሱስ #ክርስቶስን #ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ #በማቅረብ ተቀድሰናል። #ሊቀ #ካህናትም ሁሉ #ዕለት #ዕለት እያገለገለ #ኃጢአትን #ሊያስወግዱ ከቶ #የማይችሉትን እነዚያን #መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤ #እርሱ ግን #ስለ #ኃጢአት #አንድን #መሥዋዕት #ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥>>

ሐዋርያው ከሌሎች #መልእክቶቹ በተለየ ሁኔታ #ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው በዚህ #መልእክቱ #ክርስቶስ #አንድ ጊዜ በሠራው ሥራ ስላገኘነው #ቅድስና#ጽድቅ እና #መዳን ደጋግሞ ይናገራል። ይህንንም #ከቀደመው ኪዳን(ብሉይ ኪዳን) #መሥዋዕት ጋር #በማስተያየት ያቀርባል። በዚህም ምዕራፍ ይህንኑ መመልከት ይቻላል።

#የተቀደስነው #የክርስቶስን #ሥጋ #በማቅረብ ነው ይላል፤ <ማቅረብ ምን ማለት ነው?> በተደጋጋሚ እንደ ተባለው #በብሉይ #ኪዳን አንድ #በደለኛ(ኅጢአተኛ) እስራኤላዊ #ለሠራው #በደል #ይቅርታን ለማግኘት የበደል #መሥዋዕት #ማቅረብ ይኖርበታል (ዘሌዋውያን 5፥6)። <<የኃጢአት ደሞዝ #ሞት ነውና>> (ሮሜ 6፥23) እንዲሁም <<ኅጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ #ትሞታለች>> (ሕዝ 18፥4፣ 20) ተብሏልና #ኅጢአት የሠራ ሰው #በሕይወት #መኖር አይችልም። ስለዚህም #በኀጢአተኛው እስራኤላዊ #ምትክ ምንም #በደል #የሌለበት #እንስሳ #ኃጢአተኛ ሆኖ ሲሞት በበደሉ እግዚአብሔርን ያሳዘነው እስራኤላዊ #ንጹሕ ነው ይባላል። <ደም ሳይፈስ #ስርየት የለም> (ዕብ 9፥22-23)

ልክ እንደዚሁ #በበደላችን #ሙታን የነበርን(ኤፌ 2፥2) እኛ ምንም በደል የሌለበት #ክርስቶስ ስለ እኛ በደል #በመሞቱ(2ቆሮ 5፥21) ምክንያት <<የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ #አንድ #ጊዜ ፈጽሞ #በማቅረብ #ተቀድሰናል>>። ይህም #ከእኛ በሆነ ነገር ሳይሆን #ከእርሱ የሆነ በመሆኑ #ክብሩን መልሰን ለእርሱ እንሰጣለን።

ይህ ብቻም አይደለም፤ <<እርሱ ግን ስለ #ኅጢአት #አንድን #መሥዋዕት #ለዘላለም #አቅርቦ #በአብ ቀኝ #ተቀመጠ፤>> በማለት #ለዘላለም #የቀረበው ይህ #መሥዋዕት እስከ ምጽአቱ ድረስ #የምልጃን #ሥራ ሲሰራ፣ #በደለኞችን #ከእግዚአብሄር ጋር #ሲያስታርቅ#በንስሐ #ለተመለሱት ሰዎች #ሲታይ ይቆያል(ዕብ 9፥24፣ 28)። ይህ ነው #የክርስቶስ #ምልጃ። አታወሳስቡት!!

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod