ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
1ኛ ጢሞቲዎስ 2፥5 "አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም #መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤" #የክርስቶስ ሰው የመሆን ምክንያት በዚህ መልእክት በሚገባ ሰፍሯል። በአዳም #በደል ምክንያት #ከእግዚአብሄር ፊት የራቀው #የአዳም ዘር ዳግመኛ #የእግዚአብሄርን #ፊት ለማየት የሚያስችል #ንጽህና ያልነበረው በመሆኑ፣…


ዕብራውያን 5፤ 7-10

<< እርሱም #በስጋው #ወራት #ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ #ጩኸትና #ከእንባ ጋር ጸሎትንና #ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።>>

አንዳንዶች ይህን #ጥቅስ አንስተው #ክርስቶስ #ከእኔ #ተማሩ ያለ #መምህር በመሆኑ #ለአብነት ብሎ ነው ቢሉም፣ #ሐዋርያው ግን #ምሳሌ ሆነ ሳይሆን <<እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት>> ነው የሚለው።

#ሐዋርያው #በሥጋው #ወራት የተቀበለው #መከራም #በሥጋ መሆኑ #ይታወቅ ዘንድ #ጌታችን #ጸሎትና #ምልጃን #ከእንባ ጋር አቀረበ አለ /1ኛ ጴጥ 4፥1/። ይህንን የተናገረው #ሐዋርያው #ጌታችን #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል #መከራ መቀበሉን፣ የተቀበለው #መከራም #እውነት መሆኑን #ለማረጋገጥና #መከራው #መሪር(መራራ) መሆኑን ለማሳየት ይህንን ተናገረ። #ብርቱ #ጩኸት #ዕንባና #ጸሎት የሚለው ቃል #የመከራውን #ክብደት #ለማሳየት የተናገረው ቃል ነው። #ግኖስቲኮች እንደሚሉት #ሥቃዩ #የማስመሰል አካሉም ምትሐት አይደለም። #በእውነት #በሥጋ #ተሠቃይቶ ዐዘነ፣ ጸለየ።
📖/፤ ታደለ ፈንታው (ዲያቆን) (ትርጉም)፣ የዕብራውያን ትርጓሜ (2004) ገጽ 87።
ይህም #በሉቃስ #ወንጌል #ምዕራፍ 22፥44 ላይ ከሰፈረው ጋር ያላቸውን #ተግባቦት ለማስተዋል ይረዳል።
#እውነቱን ላለመቀበል (ለመቃወም) #መጽሐፍ #ቅዱስ ላይ ያሉትን ቃላት እስከ #መለወጥ ድረስ የተጓዙት አንዳንዶች ይህንንም #ጥቅስ #አሜን ብለው ለመቀበል #ዐመፀኛው #ልባቸው #ፈቃደኛ አልሆነምና << #ጌታችንና #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ በሥጋው ወራት የፈጸመውን #ከቤዛነት (ከአስታራቂነት) ሥራው አንዱ የሆነውን #ምልጃን ይዘን አሁንም #በልዕልናው ያለውን #አምላክ #አማላጅ ማለት ተገቢ አይደለም>> ይላሉ።
📖/፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምእመናን የቅዱስ እስጢፋኖስ ጉባኤ፣ <ፍኖተ ብርሃን> (ጥቅምት 1990) ገጽ 16።

ይህ ሐሳብ ግን #ክርስቶስ #በሥጋው #ወራት ሳለ #በልዕልናው አልነበረም የሚል ይመስላል። እርሱ #ሰው #ከመሆኑም በፊት፣ #ሰው ሆኖም በአገልግሎት በነበረበት ጊዜም ሆነ ፣ #ከዕረገት #ቡኃላ #ከልዕልናው አልጎደለም። ስለዚህ #በአገልግሎት ዘመኑም #ፍጹም #ሰው #ፍጹም #አምላክ ሆኖ ከሆነ ሲያማልድ የነበረው አሁንም ያማልዳል ለማለት ምን ይከለክላል?? እርሱ ሰው ከመሆኑም በፊት #አምላክ ነበር ሰው በሆነም ጊዜ #አምላክ ነበር <አሁንም ፍጹም #ሰው ፍጹም #አምላክ> ነውና።

በአንድምታ ትርጓሜው ላይ፤
<<የሰውነት ሥራ በሠራበት ወራት ጸሎትን እንደ ላም፤ ስኢልን(ልመናን) እንደ በግ፤ አድርጎ አቀረበ። በፍጹም ኅዘን። በብዙ ዕንባ አቀረበ። የልቡና ነውና፤ ግዳጅ ይፈጽማልና፤ አንድ ጊዜ ነውና፤ በዐቢይ ገዐር ወአንብዕ(በብርቱ ጩኸትና እንባ) አለ። ከሞት ሊያድነው ወደሚቻለው ወደ አብ አቀረበ። የምእመናንን ድኅነት ለራሱ አድርጎ ኅበ ዘይክል አድኅኖቶ እሞት (ከሞት ሊያድነው ወደሚችል) አለ። አንድም ምእመናንን ከሞት ሊያድንለት ወደሚቻለው ወደ አብ አቀረበ። ቁርጥ ልመናውንም ሰማው።
📖/፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 425።
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፤ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 632።

በሚል የሰፈረውን #ክርስቶስ #ስለ #ሰው ልጆች መከራ በተቀበለበት ሰዓት ወደ #አብ እንዴት #ይጸልይ እንደ ነበር መመልከት ይቻላል። ታዲያ በዚህ #ሰዓት #አምላክ አልነበረም ማለት ነው? እርሱስ #ፍጹም #አምላክ ነበር።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ዕብራውያን 5፤ 7-10 << እርሱም #በስጋው #ወራት #ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ #ጩኸትና #ከእንባ ጋር ጸሎትንና #ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።>> አንዳንዶች…


ዕብራውያን 7፤ 20-28

<< እነርሱም ያለ #መሐላ #ካህናት ሆነዋልና፤ #እርሱ ግን። ጌታ። አንተ #እንደ #መልከ ጼዴቅ ሹመት #ለዘላለም #ካህን ነህ ብሎ #ማለ #አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት #ከመሐላ ጋር #ካህን ሆኖአልና ያለ #መሐላ #ካህን እንዳልሆነ መጠን፥ እንዲሁ #ኢየሱስ #ለሚሻል #ኪዳን #ዋስ ሆኖአል። #እነርሱም እንዳይኖሩ #ሞት ስለ ከለከላቸው #ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ #እርሱ ግን #ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ #የማይለወጥ #ክህነት አለው፤ #ስለ እነርሱም #ሊያማልድ #ዘወትር #በሕይወት #ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ #በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ #ሊያድናቸው ይችላል። #ቅዱስና ያለ #ተንኮል ነውርም #የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ #ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ #ሊቀ #ካህናት ይገባልና፤ #እርሱም እንደነዚያ #ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ #ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ #ኃጢአት #ዕለት #ዕለት #መሥዋዕትን ሊያቀርብ #አያስፈልገውም፤ ራሱን #ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ #ፈጽሞ #አድርጎአልና። ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች #ሊቀ #ካህናት #አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ #የመሐላው #ቃል ግን ለዘላለም #ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።>>


<<ለሚሻል ኪዳን ዋስ>> የሆነው #ክርስቶስ እስከሚመጣ ድረስ #ሞት #በአገልግሎታቸው እንዳይቀጥሉ #የከለከላቸው 83 #ሊቃነ #ካህናት ተሹመው ነበር። በቀደመው ኪዳን ውስጥ የነበሩ #ሰዎች አገልግሎት ፈልገው <<አንድ ሰው ተቸግሮ #ካህን ፍለጋ ምናልባት ይሄዳል። ሲድርስ ግን < #ኸረ ሞቶአል! እሌላ ዘንድ መሀድ ያስፈልግሀል> ይባልና ሰውዬው #ዐዝኖ ይሄዳል። #በኢየሱስ ግን እንደዚ የለም፤ #በፈለግህበት ጊዜ ፣ #ባለህበት ቦታ #እርሱ በዚያ አለ>>።
📖/፤ ዳ.እ፣ የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ እብራውያን ትርጓሜ (ጎንደር፣ 1995 - 5ተኛ እትም) ገጽ 53።
📖/፤ GBV፣ የዕብራውያን መልእክት አንድምታ (ትርጓሜው ከነንባቡ)፣ (1998) ገጽ 61።

#በእግዚአብሄርና #በሰው መካከል እንዲሆኑ #ተስፋ የምናደርጋቸው (የካህኑን ሥራ እንዲሠሩ የምንጠብቀቸው) በሙሉ #በምድር በነበሩ ጊዜ (ከሥጋ ሞታቸው በፊት) በነበረው #አገልግሎታቸው እርሱን ሲያከብሩና #በእርሱ #የክህነት #አገልግሎት ሲጠቀሙ የነበሩ ናቸው። ምናልባት እነዚህ #ሰዎች #በአገልግሎት #ዘመናቸው #ካህናት የነበሩ ቢሆኑም እንኳ አሁን ግን #ሞት ከዚህ አገልግሎታቸው #ሽሯቸዋልና #ከእንግዲህ በዚህ በኩል #ሊያገለግሉ አይችሉም። ስለዚህ #ሞት ወደማይያዘው፣ #ክህነቱም #ዘለዓለማዊ ወደ ሆነው #ጌታ መጠጋት የተሻለ #ውሳኔ ነው።
#መድኃናችን @ክርስቶስ <<አስቀድሞ ስለራሱ ኃጢአት>> ያቀረበው #መስዋእት የለም። ምክንያቱም እርሱ #ቅዱስ#ንጹሕ#ነቀፋ የሌለበት፣ #ጻድቅ ነውና #ክህነቱም ነቀፋ የለበትም። እንዲህ ያለው #ቅዱስ ስለእኛ #በደል ራሱን #መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ <<ምንኛ #የከበረ #መሥዋዕት ነው፤ ለሰዎች ሁሉ #ደኅነንትን ለመስጠት #ኢየሱስ #ሕይወቱን #መሥዋዕት አደረገ። ኢየሱስ ወደዚህ #ዓለም የመጣው #ሕይወቱን ለብዙዎች #ቤዛ አድርጎ #ለመስጠት ነው (ማርቆስ 10፥45)። በመጨረሻም ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት <<ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ #የዐዲስ ኪዳን #ደሜ ነው> አለ (ማርቆስ 14፥24)። ለዚህ ነው #በኢየሱስ #ሞት፥ ባፈሰሰው #ክቡር #ደም ድነናል ብለን የምንመሰክረው>>።

በቀደመው ኪዳን አንዱ #ካህን #ሞቶ ሌላው #እስከሚሾም ድረስ #ካህን የማይኖርበት ጊዜ መፈጠሩ እርግጥ ነው። ይህ ደግሞ #በካህኑ አማካይነት ይደረግ የነበረው #የዕርቅ #ሥርዐት ምን ያህል #ችግር ያለበት እንደ ሆነ አመላካች ነው። የእኛ #ሊቀ ካህናት #ኢየሱስ ግን #ዘላለም #በቦታው ስላለ በእርሱ የሚያምኑት #ካህን የሚያጡበት ምንም #ምክንያት የለም። እኛስ ከዚህ #ታላቅ #ሊቀ ካህን ወደ የት እንሄዳለን? መጽሀፉም << #ቅዱስና ያለ #ተንኮል #ነውርም የሌለበት #ከኃጢአተኞችም የተለየ #ከሰማያትም #ከፍ #ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ #ሊቀ #ካህናት ይገባልና፤>> የሚለው ለዚሁ ነው(ቁ.26)።

ምንባቡ <ፍጹም ሰው> ስለሆነው ስለ #ኢየሱስ እየተናገረ፤ ለዚህም ደግሞ በቀደመው ኪዳን እና #በእርሱ #ክህነት መካከል ያለውን #ልዩነት እያቀረበ <<ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የተገለጠ ነው>> እያለ (ቁ.14) << #በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ #ሊያድናቸው ይችላል>> ብሎ እያስተማረ (ቁ.25) መሆኑን እየተመለከቱ፤ <<በመቀጠል "ውውእቱስ ይነብር ለዓለም እስመ ኢይሠዐር ክህነቱ" (እርሱ ግን #ለዘላለም ይኖራል፤ ክህነቱ አይሻርምና) በማለት የካህናተ ሓዲስ አለቃ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ግን <ዘለዓለማዊ አምላክ> ነውና መሻር መለወጥ የሌለበት ክህነቱም የማይለወጥ እንደሆነ ጻፈልን>> የሚሉ ሰዎች ክፍሉ ስለ #ክርስቶስ #አምላክነት እንደማይናገር ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን #ነገረ #ምልጃውን #ለመሸፈን መሆኑ ግልጽ ነው።
📖/፤ ሮዳስ ታደሰ (መጋቤ ዐዲስ)፣ ነገረ ክርስቶስ ክፍል 1 (የካቲት 2008) ገጽ 491።

ሐዋርያው አይሻርም ያለው #ክህነቱን እንጂ #መንግስቱን እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ደግሞስ በራሳቸውም ሆነ በ2000 በታተመው 80 አሀዱ <<ለዘላለም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል>> የሚል መስፈሩን እንዴት አላዩት ይሆን? በአንድምታውስ <<በእሱ አስታራቂነት ወደ እግዚአብሔር። የቀረቡትን ማዳን ይቻለዋል። ፈጽሞ ሕያው ነውና። ተንበለ ሲል፤ አንድም በቁሙ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ እስከ ምጽአት ድረስ ሲያድንበት የሚኖር ስለ ሆነ>> መሆኑን መስፈሩን ምነው ሳያነቡት ቀሩ?
📖/፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 434
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፣ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 647።
(⁉️ ተንበለ ፦ <<መለመን፣ መጸለይ፣ መማለድ፣ ማማለድ፣ ማላጅ፣ አማላጅ መሆን፣ ዕርቅ ፍቅር ይቅርታ መፈለግ፣ ማረኝ ማርልኝ ማለት>>
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ (አለቃ) መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ(1948) ገጽ 900)።
ታድያ #በ80 አሀዱም ሆነ #በአንድምታው ላይ #አስታራቂ መሆኑ የሰፈረው እርሱ ራሱ #አምላክ አይደል እንዴ? ከማን ጋር ነው #የሚያስታርቀው? (ይታረቃቸዋል ሳይሆን ያስታርቃቸዋል የሚለው አገላለጽ ዕርቁ የሚከናወነው ከሌላ አካል ጋር እንደ ሆነ ነው የሚያስረዳው)

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod