ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ሮሜ 8÷34 " #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡" #ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና…


1ኛ ጢሞቲዎስ 2፥5

"አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም #መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤"

#የክርስቶስ ሰው የመሆን ምክንያት በዚህ መልእክት በሚገባ ሰፍሯል። በአዳም #በደል ምክንያት #ከእግዚአብሄር ፊት የራቀው #የአዳም ዘር ዳግመኛ #የእግዚአብሄርን #ፊት ለማየት የሚያስችል #ንጽህና ያልነበረው በመሆኑ፣ በእርሱ እና በአምላኩ #መካከል ያለውን #ክፍተት የሚሞላ ስላላገኘ፣ "አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን #አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን፥ #አቅና"፣ እጅህን፥ ከአርያም ላክ #አድነኝም" (መዝ 118፥25 ፣ 144፤ 7-8) በሚል በብዙ #ጩኸት ውስጥ ነበር። ክብር ለእርሱ ይሁንና ፍጹም #ሰው ፍጹም #አምላክ በሆነው #በክርስቶስ <<.... #በደሙ የተደረገ #ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም #የበደላችን #ስርየት>> ነው (ኤፌሶን 1፥7)።
" #መካከለኛ እንዲሆን እግዚአብሔር #አንድያ #ልጁን ላከው... [ምክንያቱም ደግሞ <<ወንድም ወንድሙን #አያድንም ሰውም #አያድንም>> እንደሚል(መዝ 49፥7) መጽሀፍ፥ #ሰው(ፍጡርና የአዳም ልጅ) #መካከለኛ ሊሆን... እና #ሊያድን የማይችል ደካማ #ፍጡር ነውና። የሰው ልጅ ብቻም ሳይሆን <<ከሰማይ #መላእክት እንኳ ቢሆን ከምድርም ሰው መካከል አንድስ እንኳ #ለመካከለኝነቱ ብቁ ሆኖ #ሰውና #እግዚአብሔርን #ማስታረቅ የተቻለው አልተገኘም አይገኝምም። "ደም ሳይፈስም ስርየት የለም"(ዕብ9፥22)። #በሰውና #በእግዚአብሄር #መካከል የነበረውን #የጥል #ግድግዳ ለማፍረስ በመካከል የገባ፣ ሁለቱን #ያስታረቀ፣ ሰውን ከሰማያዊ ርስት የቀላቀለ #ጌታ #ኢየሱስ #ብቻ ነው>>።
📖/፤ ብርሃኑ አበጋዝ፤
^ክርስቶስ^ (2007) ገጽ 38።
#ክርስቶስ #የመካከለኛነት ሥራውን የሰራው በመከራ ሞቱ በመሆኑ ሁላችን #በእርሱ #በኩል ወደ #እግዚአብሔር #የመቅረብ መብት እንድናገኝ አስችሎናል ለዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን #በዐዲስና #በሕያው #መንገድ ወደ ቅድስት #በኢየሱስ #ደም በመጋረጃው ማለት #በሥጋው #በኩል እንድንገባ ድፍረት..." እንዳለን የሚያስተምረው (ዕብ 10፤ 19-20)።
#የክርስቶስን #የመካከለኝነት ሥራ ለመቀበል የከበዳቸው ሰዎች ለዚህ ጥቅስ የሚሰጡት መከላከያ #ሐሳብ ቢያጡ ከምንባቡ ውስጥ <<ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ>> የሚለውን መዘው በማውጣት በእርግጥ #ክርስቶስ በዚህ ምድር ሳለ #የመካከለኝነት #ሥራ ሰርቶ ነበር አሁን ግን እንዲህ ያለ ነገር #በእርሱ ዘንድ #የለም የሚል #ሐሳብ ያቀርባሉ። ወገኖቻችን በዚህ ስፍራ ላይ #ሐዋሪያው #ጳውሎስ #ክርስቶስን ^ #ሰው^ ማለቱን አላስተዋሉም ይሆን?? አሁን በሰማያት የእኛን ሥጋ ሥጋው ያደረገ መካከለኛ (ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ) አለን። ለዛም እኮ ነው መጽሀፍቅዱስ፤
""ስለእኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ ገባ"(ዕብ 9፥24 ፣ 28)""
""ስለእኛ የሚማልደው(ሮሜ 8፥34)፤""
""ዘውትር ሊያማልድ...ብሎም በእርሱ በኩል የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል(ዕብ 7፥25)፤""
""እንዲሁም በሰማይ ባለችው መቅደስ አገልጋይ"(ዕብ 8፥2)""
""የአዲስ ኪዳን መካከለኛ(ዕብ 9፥15፣ 12፥24)፤""
""በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ #መካከለኛ #እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል።""(ዕብ 8፥6)
""ዘላለማዊ ሊቀካህን""(ዕብ 2፥17፣ 3፥1፣ 4፥14፣ 6፥20፣ 7፥26፣ 8፥1)....ወ.ዘ.ተ የሚለው።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod