ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የተጠናቀቁ #ኮርሶች

👉#ነገረ_ድኅነት(ምዕራፍ አንድ)
👉#የመጻሕፍ ቅዱስ ጥናት
👉#ክርስቲያናዊ ምግባር

❤️ #አዲስ የሚተኩ ኮርሶች

👉 #ነገረ_ድኅነት (ምዕራፍ ሁለት)
👉 #የቤተ_ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
👉 #ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

#ሌሎቹ እዳሉ ይቀጥላሉ ማለት ነው

#ምን_እንጠይቅልዎ ዘወትር ቅዳሜ
👉ፍቅር
👉ንቅሳት
👉ውርጃ
👉የቅርብ ዝምድናና ትዳር
ወዘተ የመሳሰሉት #ከእናንተ_የሚመጡ_ማንኛውም_መንፈሳዊ ጥያቄዎች እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በቂ ምላሽ ይሰጥበታል::
እንዲሰጥ የምትፈልጉት ሌላ የኮርስ ዓይነት ካለ ሀሳባችሁን በ

@abenma
@abenma
ወይም
@YeawedMeherte
@YeawedMeherte
ብትልኩልን #እግዚአብሔር ከፈቀደ ነገሮችን አስተካክለን የምንጨምርላችሁ መሆኑን #በደስታ እንገልጻለን::
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (toolkit)
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን01.3gpp
4.4 MB
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
ክፍል #አንድ

በመምህር #ይትባረክ

#ይዘት
የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትርጉም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን 02.3gpp
5.2 MB
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል ሁለት

#በመምህር #ይትባረክ

#ይዘት
ቤተ ክርስቲያን ምን ትባላለች?

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል ሦስት

#በመምህር #ይትባረክ

#ይዘት
ሥርዓት ለምን አስፈለገ?

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን04.3gpp
4.8 MB
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል አራት

#በመምህር #ይትባረክ

#ይዘት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን መማር ለምን አስፈለገ?

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል አምስት

#በመምህር #ይትባረክ

#ይዘት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የምንለው ምኑን ነው?

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል ስድስት

#በመምህር #ይትባረክ ደንድር

#ይዘት
የሥርዓት ዓይነቶች

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል ሰባት

#በመምህር #ይትባረክ ደንድር

#ይዘት
የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጮች የሲኖዶስ ጉባኤ ውሳኔዎች

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
#ክፍል ሰባት

#በመምህር #ይትባረክ ደንድር

#ይዘት
የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጮች የሲኖዶስ ጉባኤ ውሳኔዎች

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
"እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።" ያዕ 4:15

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ውድ የተዋሕዶ ልጆች የዓውደ ምህረት ዘተዋሕዶ አባላት እንኳን ለጌታችን በዓለ ጥምቀት በሠላም አደረሳችሁ እያልን ከበዓለ ጥምቀት አንድ ሳምንት በኋላ ከጥር 20 ዕለተ ሰኞ ጀምሮ ዕረፍት ላይ የነበሩ የኮርስ ትምህርቶች የሚቀጥሉ ይሆናል። በተጨማሪም በእናንተ ጥያቄ መሠረት #የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን እንደምንጀምር እናስታውቃለን። ይዘናቸው የምንቀርባቸው ትምህርቶች:

#ትምህርተ_ሃይማኖት በወንድማችን #ኢዮብ ክንፈ #ምሥጢረ ቁርባን እና ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን

#የቤተክርስቲያን_ታሪክ_በዓለም_መድረክ ምዕራፍ ሁለት #በዲያቆን #እስጢፋኖስ ደሳለኝ

#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ ምዕራፍ ሁለት በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ክብረ_ቅዱሳን (ዘውትር ረቡዕ) በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

#ሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን ምዕራፍ ሁለት በመምህር ይትባረክ ደንድር

#ልሳነ_ግዕዝ ምዕራፍ አንድ በመሪጌታ #አምሳለ አበበ

የሚሰጡ ይሆናል። እርስዎም ይህንን መልእክት ላልሰሙ ወዳጆችዎ በማጋራት መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያሳውቁ። በተጨማሪ አዲስ ለተቀላቀላችሁን አባላቶቻችን ከዚህ ቀደም የተሰጡትን ተከታታይ ትምህርቶች ሁሉ በቦታችን @Awtztbot ላይ ያገኟቸዋል።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ሥርዓተ_ቅዳሴ

#የትምህርቱ_ዓላማ

ለቤተ ክርስቲያን ተከታዮች የቤ/ክ አገልግሎት ለተከታዮቿ ማሳወቅ ይሆናል።

የትምህርቱ ...ጠቀሜታች ዋናዋናዎቹ እንደሚከተለው ይሆናል።

1. በብሉይ ኪዳን የነበሩትን ንዋየቅድሳትና በሐዲስ ኪዳን ያሉትን ንዋየቅድሳት ጥቅሞችን ያስረዳል፡፡

2. የህንጻ ቤ/ክ ምሳሌያዊ ትርጉም

3. የሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አፈጻጸምና በምስጢራቱ የሚገኙትን ሃብታት (ጸጋዎች) ጥቅሞች እንረዳለን፡፡

3 በብሉይ ኪዳን ስለ ነበረው ቁርባንና በሐዲስ ኪዳን ስላለው ቁርባን

5. በብሉይ ኪዳን ስለ ነበረው ክህነትና በሐዲስ ኪዳን ስላለው ክህነት

6. በብሉይ ኪዳን ስለነበረው መስዋዕትና በሐዲስ ኪዳን ስላለው መስዋዕት

7. በብሉይ ኪዳን የነበረችቱ ቤ/ክ ና በሐዲስ ኪዳን ያለችቱ ቤተክርስቲያን

8. የደብተራ ኦሪት አሰራር እና የሐዲስ ኪዳን ቤ/ክ አሰራር

9. የመቅደሰ ሰሎሞን እና የአሁኗ የሐዋርያው ማርቆስ ቤ/ክ

10. በቤተክርስቲያን ዙርያ የሚሰሩ ቤቶች የሚሰሩበት አቅጣጫ ና አገልግሎታቸው

11. በብሉይ ኪዳን ስለነበሩ ንዋየ ቅድሳትና በሐዲስ ኪዳን ስላሉ ንዋየ ቅድሳት

12. ታቦት በብሉይ ኪዳን ታቦት በሐዲስ ኪዳን.......

የሚሉትን ምሳሌአቸውን ትርጉማቸውን እናያለን...

ትምህርቱ የሚሠጥባቸው መንገዶች
👉 በጽሑፍ
👉 በድምጽ የመምህሩ ማብራሪያዎች
👉 በምስል

መቼ?

➡️ ዘወትር ቅዳሜ ከምሽቱ 4:00

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Deleted Account
አንድ ሰው በተክሊል ማግባት የሚችል ወይም የምችል መቼ ነው? በምን ሁኔታስ ነው?
ተክሊል ማለት ከለለ አከበረ ከሚለው ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ክብር ማለት ነው። ተክሊል ምሥጢር ተብሎ መጠራቱ ሙሽራውና ሙሽሪት በግብር አምላካዊ አንድ የሚሆኑበት የጋብቻ ሥርዓት በመሆኑ ነው። ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም ምሥጢርነት አለው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም "... ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው" ማለቱ ይህንኑ ያረጋግጥልናል።
#የተክሊል አፈጻጸም
እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ /ሥርዓት/ ተክሊል ከሥርዓተ ቅዳሴና ከቅዱስ ቁርባን ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ምሥጢር ነው። እንጂ ብቻውን አይፈጸምም። ጸሎተ ተክሊል ተደርሶ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ከቀረ ግን ተክሊሉ ፍጹም አይደለምና ጋብቻው አይጸናም።
#ሥርዓተ ተክሊል ለማን ይፈጸማል?
ተክሊል የሚፈጸመው ንጽሕናዋን ጠብቃ ከወንድ እርቃ ለኖረች ጥብቅ ልጃገረድ ወይም በሥጋ ድንግልናዋን ለጠበቀች በተግባር ዝሙት ላልፈጸመች ኦርቶዶክሳዊ ሴት ነው። ሴትን በምንጣፍ ተገናኝቶ የማያውቅ ንጽሕናውን ጠብቆ ልኖር ኦርቶዶክሳዊ ወንድ ብቻ የሚፈጸም የጋብቻ መፈጸሚያ አይነት ነው። በአጠቃላይ ተክሊል ከሥጋዊ ድንግል ጋር አብሮ የሚሄድ ምሥጢር መሆኑን ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት መጽሐፍቶች ሁሉ ተባብረው የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ፍትሃ ነገስት እንዲህ ይላል ፦ "ይህ ተክሊል በጋብቻ ጊዜ ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት ይገባል።" ፍትሃ ነገስት 24:906 ከላይ ያነሳነው ሥርዓት ግን በደንብ ካልተብራራ ተክሊልን በተመለከተ የሚነሱትን ጥያቄዎች ከምንጫቸው ማድረግ የሚችል አይሆንም። ሰለዚህ በዚህ ምሥጢር ዙሪያ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንድንችል ድንግልና እንደቤቱ ክርስቲያናችን አስተምህሮ እንዴት ይታያላል /ይብራራል/ የሚለውን በደንብ መመልከት ይገባል።

#ድንግልና ምንድን ነው?
ድንግልና የሚለው ቃል ተደነገለ ተጠበቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም መጠበቅ ማለት ነው። ድንግልና እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ንዑስ ሕዋስን /Hymen/ ለመግለጽ ብቻ ሳይሆን የንጽሕና አኗኗር ለማስረዳት አንድ ድርጊት መፈጸም ወይም አለመፈጸሙን ለማመልከት አገልግሎት ላይ የሚውል ቃል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
ሰለዚህም አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሴት ሥጋዊ የሆነው የድንግል ማሕተም ስላልፈረሰባት ብቻ ሥርዓተ ተክሊል መፈጸም ትችላለች ሌላኛዋ ኦርቶዶክሳዊት ደግሞ ሥጋዊ የድንግልናዋ ማሕተም ሰለፈረሰ ብቻ ተክሊል አይገባትም ማለት አይደለም። በቅድሚያ እዚህ ላይ ያለውን ውዥንብር መደንብ ለማጥራት በሴቶች ተፈጥሮ ውስጥ የሚገኘውን የድንግልና አይነቶችን ማየት ይጠቅማል።
#የሴቶች ድንግልና ተፈጥሮ ዓይነቶች
ማኅተመ ድንግልና ሴት ከወንድ ጋር ሩካቤ አድርጋ አለማወቋን የሚያስረዳ የሥራዋ መገለጫ የአኗኗሯ መታወቂያ ልዩ የተፈጥሮ ምልክትና የድንግልናዊ ኑሮዋ ዘውድ ነው። ይህ ተፈጥሮዊ ማኅተም በሴቶች አፈ ማኅፀን ቀለበት በሚመስል ስስ ሥጋነት በጉልህ ይታወቃል። ይህ ማለት ግን ሩካቤና ሰስሎተ ድንግልና /የድንግልና መወገድ/ የተለያዩና
ራሳቸውን የቻሉ ተግባራት መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል። አንዲት ሴት ማኅተመ ድንግልና ስላላት ብቻ " ሩካቤ አድርጋ አታውቅም" " ወይም ሩካቤ ስላደረች ማኅተመ ድንግልና ሊኖራት አይችልም። ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አለመቻሉን እንረዳለን። በዚህም የተነሳ የድንግልና አይነቶችን ከተክሊል ጋር እያዛመዱ መመልከት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ወንዶች እንደ ሴቶች ተጨባጭና ጉልህ የድንግልና ምልክት ስለሌላቸው ከሴት ጋር ሩካቤ ፈጽመው የማያውቁ ሆነው ሳለ ደናግል አይደሉም ማለት አይቻልም። እንደዚሁ ሁሉ ሩካቤን ፈጽመው የማያውቁ ሴቶች የድንግልና ማኅተም ስለሌላቸው ብቻ ደናግላን
ከመባል አይከለከሉም። በሌላ አቅጣጫ ስንመለከት ወንዶች ሩካቤ ፈጽመው ሳለ እንደ ሴቶች የሚገሠሥ ማኅተመ ድንግልና ስለሌላቸው ድንግልናቸውን አልፈረሰም እንደማይባል ሁሉ ሴቶች ሩካቤ ሥጋ እየፈጸሙ በልዩ ልዩ ምክንያት ማኅተመ ድንግልናቸውን ባይገሠሥም መደበኛ ሩካቤ እስከ ፈጽሙ ድረስ ደናግል ሊባሉ አይችሉም። ለዚህም ነው ሰለድንግልና አይነቶች ማውራት አስፈላጊ ሁኖ የተገኘው ፦
#የድንግልና ዓይነት
የድንግልና መለያ ወይም ስስ የክብር ንጽሕና ሽፋን /Hymen/ ዓይነታቸው አራት ሲሆኑ በሁሉም ሴቶች ላይ የሚኖረው ዓይነት ምንም እንኳን በተፈጥሮ ተወስኖ የተፈጠረ ቢሆንም ግን ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ ድንግልና የሚጠፋባቸው በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ። ይህም ከሴቶች የድንግልና ተፈጥሮ አንጻር ነው።
#አንደኛ ደረጃ_የድንግልና ማኅተም /Hymen/ ምልክቶች ፦ ይህ ድንግልና አይነት ያላቸው ሴቶች ንዑስ ሕዋስ የድንግልና ማኅተም ምልክቱ የሌላቸው ሲሆኑ እነዚህ ምንም እንኳን ከአጠቃላዩ ሴቶች ሲታይ ቁጥራቸው አናሳና አንዳንድ መረጃዎች እንደ ሚጠቁሙት ከሦስት እስከ አምስት በመቶ የማይበልጡ ቢሆኑም የዚህ አይነት ተፈጥሮ ባለ ድርሻ የሆኑ እህቶች የሠርጋቸውን የመጀመሪያውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲዳርጉ ምናሴም እንኳን ሕመም ቢሰማቸውም እንደሌሎቹ የድንግልና አይነቶች ያለ መድማታቸው አይነቱን የተለየ ያደርገዋል። ይህ አይነቱ ድንግልና ያላቸው ወጣት ሴቶች ምንም እንኳን ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁ ራሳቸውን በቅድስናና በንጽሕና ጠብቀው የኖሩ ቢሆኑም ሆኖም ግን በጋብቻቸው ምሽት የመጀመሪያውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ ደም ባለመታየቱ በባላቸው ዘንድ ተአማኒነት የሚያጡበት አሳዛኝ አጋጣሚ የሚከሰትበት አጋጣሚ አለ።
#ሁለተኛ ደረጃ የድንግልና ዓይነት፦ይህ የድንግልና አይነት በተፈጥሮ ያላቸው ሴቶች የድንግልና መለያቸው በጣም ስስነት ያለው ሲሆን እነዚህ አይነት ሴቶች በቁጥር ከአጠቃላዩ ሴቶች ከሃያ አምስት በመቶ ያላነሱ ናቸው። ይህ የድንግልና አይነት ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ በተለያዩ የጥንቃቄ ጉድለቶች ሊወገድ የሚችልባቸውም አጋጣሚዎችም አሉ። በዚህ የድንግልና አይነት የሚኖሩ እህቶች ከባድ በሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ጥንቃቄ በጎደለው አለባበስ የተነሳ ሊወገድ ይችላል። እነዚህ እህቶች በሩካቤ ሥጋ ግንኙነት በዝሙት ተግባር ሳይገኙ ድንግልናቸውን ሊያጡት ይችላሉ።
#ሦስተኛው ደረጃ የድንግልና ዓይነት፦ ይህ የድንግልና ዓይነት መካከለኛ ደረጃ ውፍረት ያለው ሲሆን የድንግልና መለያ ምልክት በአብዛኛው ሴቶች ላይ ማለትም ከአጠቃላዩ ድንግልና ካላቸው ወጣት ሴቶች ከግማሽ በላይ በሚሆኑት ላይ የሚገኝ የድንግልና ማኅተም አይነት ነው። ይህ የድንግልና አይነት እስከ አሁን ካየናቸው የድንግልና ማኅተሞች በጥንካሬና በውፍረት የተሻለ ከመሆኑ በላይ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በስተቀር በሌሎች የጥንቃቄ ጉድለቶች ማለትም ጥንቃቄ በጎደለው ስፖርትና በመሳሰሉት የመወገድ ዕድሉ በጣም ዝቀተኛ ነው።
#አራተኛ ደረጃ የድንግልና ዓይነት ፦ ይህ የድንግልና አይነቶች ጽኑ የሚባል ነው። ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጭ በሌላ በምንድን አይነት መንገድ የሚፈርስ የሚወገድ አይደለም። ተክሊል የሚገባት ሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ፈጽማ ድንግልናዋ ላልፈረሰባት ሴት አይደለም። ይቺ ሴት ምንም እንኳን የሥጋ ድንግልናዋ ቢኖርም የዝሙት ተግባርን ፈጽማለችና ተክሊል አይገባትም። በተለይ አራተኛው የድንግልና አይነት ላይ የሚገኙ ጽን የድንግልና ማኅተም ያላቸው ሴቶች በመጀመሪያው የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት የድንግልና ማኅተማቸው ላይወገድ ይችላል። ይህንን ሩካቤ ሥጋ ግንኙነት የፈጸሙት ከጋብቻ ውጭ ከሆነ ዝሙት ነውና የድንግልና ማኅተም አለኝ ተ