ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
"እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።" ያዕ 4:15

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ውድ የተዋሕዶ ልጆች የዓውደ ምህረት ዘተዋሕዶ አባላት እንኳን ለጌታችን በዓለ ጥምቀት በሠላም አደረሳችሁ እያልን ከበዓለ ጥምቀት አንድ ሳምንት በኋላ ከጥር 20 ዕለተ ሰኞ ጀምሮ ዕረፍት ላይ የነበሩ የኮርስ ትምህርቶች የሚቀጥሉ ይሆናል። በተጨማሪም በእናንተ ጥያቄ መሠረት #የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን እንደምንጀምር እናስታውቃለን። ይዘናቸው የምንቀርባቸው ትምህርቶች:

#ትምህርተ_ሃይማኖት በወንድማችን #ኢዮብ ክንፈ #ምሥጢረ ቁርባን እና ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን

#የቤተክርስቲያን_ታሪክ_በዓለም_መድረክ ምዕራፍ ሁለት #በዲያቆን #እስጢፋኖስ ደሳለኝ

#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ ምዕራፍ ሁለት በመምህር #ማርቆስ አለማየሁ

#ክብረ_ቅዱሳን (ዘውትር ረቡዕ) በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

#ሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን ምዕራፍ ሁለት በመምህር ይትባረክ ደንድር

#ልሳነ_ግዕዝ ምዕራፍ አንድ በመሪጌታ #አምሳለ አበበ

የሚሰጡ ይሆናል። እርስዎም ይህንን መልእክት ላልሰሙ ወዳጆችዎ በማጋራት መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያሳውቁ። በተጨማሪ አዲስ ለተቀላቀላችሁን አባላቶቻችን ከዚህ ቀደም የተሰጡትን ተከታታይ ትምህርቶች ሁሉ በቦታችን @Awtztbot ላይ ያገኟቸዋል።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#የነገረ_ድኅነት ጥያቄ #መልሶች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ ሐሰት
#ምክንያቱም :-ሰው ለመዳን ከማመን ያለፈ የተግባር ሰው (ምግባራትን እና ምሥጢራትን የሚፈጽም) መሆን አለበት:: ምግባራት የሚባሉትም በዋናነት #ጾም #ጸሎት #ስግደት #ምጽዋት ሲሆኑ ምሥጢራቱም #ምሥጢረ_ሜሮን #ቅዱስ_ጥምቀት እና #ቅዱስ_ቁርባን ይጠቀሳሉ #ሃይማኖት ያለ #ምግባራት ጥቅም አልባ የሞተ ነው::
"፤ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ #ከሥራ (ከምግባራት )የተለየ እምነት የሞተ ነው።" (የያዕቆብ መልእክት 2: 26)


#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :-በተለየ አካሉ #ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሶ ነፍስን ተስቶ በፍጽም ተዋህዶ #ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና:: #በምስጢረ ሥላሴ ትምህርታችን #አብ አባት #ወልድ ልጅ #መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ብለን ተምረናል እንዲህም እናምናለን:: ቅዱሳት መጻሕፍትም በተዋህዶ ተወልዶ ያዳነን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በስፋት ይነግሩናል:: ለምሳሌ "እግዚአብሔር አንድያ #ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶልና" ዮሐ3÷16

#ኛ ሐሰት

#ምክንያቱም :- ምንም እንኳን ድኅነት በዕለተ አርብ በቀራኒዮ አደባባይ አንድ ጊዜ ተፈጽሞ ለሰው ልጆች የተሰጠ ቢሆንም ከዚህ ከተሰጠው ድኅነት ግን ለመካፈል ሰው የራሱን ጥረት ማድረግ ይገባዋል። ድኅነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተፈጸመ ስለሆነ ብቻ ሰው ሁሉ ያመነውም ያላመነውም በግዴታ ይድናል ማለት አይደለም:: ለመዳን የወደደ ብቻ ከተፈፀመለት የድኅነት ሥራ በምግባራት ተሳትፎ ድኅነትን ያገኛል:: ስለዚህ በድኅነት ውስጥ ሰውም ሊፈጽመው የሚገባ ሂደት ነው::
"፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ #እንደ_ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ፤"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 12)

ልናስተውለው የሚገባን #የታዘዛችሁትን_በመፈጸም የምትለዋ እና #የራሳችሁን_መዳን_ፈጽሙ የምትለዋን ነው

በመሆኑም የእራሳችንን መዳን መፈጸም የምንችለው እና ከተሰራልን የድኅነት ሥራ የምንካፈለው የታዘዝነውን በመፈፀም ነው:: #የታዘዝነውም 10ቱ ትዕዛዛት 6ቱ ቃላተ ወንጌል ናቸው እነዚህን ለመፈፀም ደግሞ ጊዜ ዘመን ያስፈልገናል:: ይህ ደግሞ ድኅነት በሂደት የሚፈፀም እንጂ በአንድ ቀን በአንድ ቦታ በሰዓት ጌታን በመቀበል ብቻ አለመሆኑን ያስገነዝበናል:: በጥቅሉ ለመዳን ሰው የራሱ ድርሻን መወጣት ይገባዋል።

#ኛ እውነት

#ኛ ሐሰት
ምክንያቱም:-ያልተመለሰለት ጸጋ የለምና::
ፀጋ:-
ልጅነትን:- ከእንግዲ ወዲ ባሮች አትባሉም
ወራሽነትን:-
ገዢነትን(ሥልጣንን):- ግዛ ንዳ የተባለሁ ዓለምና በዓለም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ዛሬም ሰው ከትዕዛዙ ካልራቀ ሕጉን ከጠበቀ ከተፈጥሮ ሁሉ በላይ መግዛት መንዳት የሚችልና ሥልጣኑ ያለው መሆኑን በቅዱሳን ሕይወት መመልከት ይቻላል::


#በአጭሩ መልሱ

#ኛ #ስለ_ፍጽም_ፍቅሩ
#ለካሳ ለቤዛ
#የዲያብሎስ ጥበብ #በጥበቡ #ለመሻር
#ለምሳሌነት_ለአራያነት
#ድኅነት ሥርዓት ስላለው…

#ኛ #ማመን
#ሥራ (ምግባራት)
#ምሥጢራትን መፈጸም ማር 16:16 ዮሐ 6:54


#ኛ "፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ #በእርሱም ቍስል #እኛ ተፈወስን።"

(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 5)
"፤ #እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ #ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም #የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53: 6)

ነብዩ ስለ እኔ ብቻ አላለም #እኛ ብሎ አብዝቶ ተናገረ እንጂ:: እኛ ብሎ አብዝቶ መናገሩ የዓለምን ኃጢያት የተሸከመ የዓለም መድኀን መሆኑን ሲገልጥ ነው::

"እነሆ #የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር_በግ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1: 29)


#ኛ #መንግስቱን_ሲወርስ_ስሙን_ሲቀድስ


#ኛ ማዳን የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው ማለት እንጂ ቅዱሳን አያድኑም ወይም መድኀኒት አይባሉም ለማለት አይደለም:: በቅዱስ መጽሐፍ ሰዎች ሆነው አዳኝ ተብለው የተጠሩ አሉ #ለምሳሌ "፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ #እግዚአብሔርም_የሚያድናቸውን_አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ #ጎቶንያልን_አስነሣላቸው።"
(መጽሐፈ መሳፍንት 3: 9) ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎችን አዳኝ መድኀኒት አድርጎ እንደሚያስነሳ ነው:: መዳን በሌላ በማንም የለም ማለቱ የቅዱሳን አዳኝነት (መድኀኒትነት) ጠፍቶት አይደለም:: ቅዱሳን የጸጋ አዳኝ ናቸው:: ጸጋ ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ፣የተቸረ ፣የተለገሰ ስጦታ ማለት ነው:: ስለዚህ ቅዱሳን መድኀኒት ቢባሉ በስጦታ ያገኙት ነው። "#እድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን #ሌላ ስም የለም" ማለቱ ደግሞ ቅዱሳን ሲያድኑም በእራሳቸው ኃይል ሳይሆን ማዳንን በሰጣቸው በፈጣሪያቸው ስም ነው ማለቱ ነው:: ቅዱሳን መላእክት አዳኝ (መድኅኒት )ናቸው። ስማቸው ስመ እግዚአብሔር ተሸክሞልና:: ስለሆነም ቅዱስ ሚካኤል አዳነ ማለት እግዚአብሔር አደነ ማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ (ቅዱሳን ሰዎችም) ቢያድኑ የፈጣሪን ስሙን ጠርተው ነው "፤ ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ #በናዝሬቱ_በኢየሱስ_ክርስቶስ_ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።"
(የሐዋርያት ሥራ 3: 6)
ከዚህም ባሻገር ቅዱሳን ወደ ቅድስና ሲጠሩ ስማቸው ይለወጣል ስመ እግዚአብሔርም ይሆናል:: በመሆኑ እነርሱም በስማቸው ማዳን ይቻላቸዋል "፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ #በእኔ_የሚያምን_እኔ_የማደርገውን_ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ #ከዚህም_የሚበልጥ_ያደርጋል፥" (የዮሐንስ ወንጌል 14: 12)
ከእርሱ አብልጦ የሚሰራ የለም ነገር ግን በስሙ ላመኑ እርሱ ያደረገውን ሁሉ የማድረግ ሥልጣን አላቸው ማለቱ ነው።

ይቆየን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በዓለ #ወልድ በዓለ #እግዚአብሔር
#የፈጣኑ_ሰው መልስ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
#ምሥጢረ ተዋሕዶ የአምላክ ልጅ የሰው ልጅ የሰው ልጅ የአምላክ ልጅ ብሎ ያለ መነጣጠል ማመን ነው:: #ለዚህ ነው ስለ ሰው ልጅ ተጠይቆ ስለ አምላክ ልጅ መልሶ ትክክል የሆነው ::
#ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብም የድንግል ማርያምም የበኩር ልጅ ነው::

ነሐሴ 29/2012ዓ.ም
ኃ/ማርያም
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit