ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
194 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
ከደመና በታች
አዲስ ዝማሬ
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ እሁድ ምሽት
በዩትዩብ ቻናል ላይ ይጠብቁን !!!!

http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405

Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
👆👆👆
Subscrib Here
#Zemari_Dawit_kibru
#ዘማሪ_ዳዊት_ክብሩ
#ከደመና_በታች
#newvideo
#mezmur
#orthodoxmezmur
#ጌታ ሆይ የአንተን ነገር ከመናገር አለመናገር የበለጠ ገላጭ ነው።ከዝምታም ዕንባ የበለጠ ገላጭ ነው።እስከ መጨረሻው አምላክነትህን የገለጥክላቸው አይሁድ በመቃብርህ ወታደሮችን ቢያኖሩ ሞትን ገድለህ በሥልጣንህ የተነሣኸው ሆይ፤እስከ መጨረሻው ወድደህ (ዮሐ 13:1) የሰውን የመጨረሻ ሥልጣን (ልጅነትን) (ዮሐ1:12) የሰጠኸኝን እኔን ዙሪያን የሚዞረኝን ጠላት(1ኛ ጴጥ 5:8) በትንሣኤህ ብርሃን ድል ንሣልኝ!!!

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!!!በዓሉን የ "የፊተኛውን ትንሣኤ" (ራእይ 20:6) የምንነሣበት ያድርግልን!!! አሜን!!!
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን።

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም

ዛሬ ....
#ለክርስቶስ ጸሀይ ምስራቅ ድንግል #ማርያም የተወለደችበት ቀን ነው ።
(አንቲ ምስራቁ ለክርቶስ እንዲል ቅዱስ ህርያቆስ)

#ለክርስቶስ ዝናብ ደመና ድንግል #ማርያም የተዘረጋችበት ነው ።
(አንቲ በአማን ደመና እንተ አስተርያ ለነ ማየ ዝናም እንዲል ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው)

#ለክርስቶስ መብል ፍሬ ድንግል #ማርያም የተተከለችበት ነው ።
(እስመ ወለድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን እንዲል ቅዳሴ ማርያም )

#መልካም_በዓል
#የልደትሽ_ቀን_ልደታችን_ነው
#ስለ_ሀገር_መጸለይን_አታስታጉሉ


©️ ከመምህር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ
ለክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት:- ልደታ ለማርያም

እንኳን አደረሳችሁ!!

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ጥንተ አብሶ ካመጣው ፍዳና መርገም ጠብቋታል:: የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ዓለም በጥንተ አብሶ በነበረበት ዘመን በክርስቶስ ማዳን ዋዜማ ሲያበሥራት ቅድስት ኤልሳቤትም በፅንሰቷ ጊዜ ስታመሰግናት ደጋግመው "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ" "አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ።" እያሉ ይህን እውነት መስክረዋል። (ሉቃ፩:፳፮-፵ በጥንተ አብሶና ውጤቱ (origional sin and its effects) ምክንያት ሰዎች "የእግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል በተባሉበት ዘመን ጸጋን የተመላች ብቸኛ ልዩ እርሷ ነበረች:: ።" (ሮሜ ፫:፳፫) እግዚአብሔር እርሷ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ለመውለድ ፈቃደኛ እንደምትሆን ስለሚያውቅ አስቀድሞ በአካል የሚመስለው በባሕርይ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ አንድያ ልጁን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንድትወልድ ቅድመ ዓለም መርጧታልና የእመቤታችን ልደት (ልደታ ለማርያም) የዓለም መዳን የማይቀር መሆኑ ለታወቀበት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት ነው እንላለን። (The nativity of the blessed virgin Mary prepares the way for the birth of Jesus Christ) እንዳለ ሊቁ። (The book of the nativity of Virgin Mary ,) የጌታችን ሰው መሆን "ከዘላለምና (ቅድመ ዓለም) ከትውልዶች ጀምሮ (ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ) ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው።" (ቆላ፩:፳፮) መባሉም የአምላክ ሰው መሆን እንዲሁም የእርሷ እርሱን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ሕሊና የሚታወቅ መሆኑን ያስረዳናል። (ኢሳ ፯:፲፬ ፱:፮) እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ ነው። (መዝ ፻፴፭:፩ ራእ፲፱:፲፮) እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ፈጣሪ ነው:: "ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች ያለ እርሱ አልሆነም።" (ዮሐ ፩:፫) "መልካሙን ነገር ለማድረግ በክርስቶስ ተፈጠርን።" "የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሁኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና።" እንደተባለ:: (ቆላ ፩:፲፭-፲፮፣ ኤፌ ፪:፲) እርሱ ለቅዱሳን የጸጋ አምላክነትን ክብር የሰጠ ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ የባሕርይ አምላክ ነው:: (ዘጸ ፯:፩፣ መዝ ፹፩:፩፣ ዮሐ፲÷፴፬፣ ሮሜ ፱:፭፣ ፩ተሰ ፫:፲፩፣ ቲቶ ፪:፲፩፣ ፩ዮሐ ፭:፳) እርሱ ቸር ከሆነ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአገዛዝ በሥልጣን በሕልውና በመለኮት አንድ ነው:: (ዮሐ ፲:፴፣ ፲፯:፲፣ ማቴ ፲፩:፳፯-፳፱፣ ዮሐ ፲፬:፮-፰) እርሱ ፀሐይ እናቱ ምሥራቅ ናት:: (ሕዝ ፵፬:፩፣ ዮሐ ፰:፲፪፣ ሚል ፬:፪) ምሥራቅ እናቱን ዘወትር መሻታችን የፀሐይ ክርስቶስን በረከት ፍቅርና ቸርነት ለማግኘት ነው:: እንኳንስ እናቱን ነቢዩ ዳዊት ስለ ወዳጆቹ "ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው ስለዚህም ነፍሴ ፈለገቻቸው።" ብሎ ዘምሯል:: (መዝ ፻፲፰:፻፳፭) እርሱ የባሕርይ አምላክ እርሷ ደግሞ ወላዲተ አምላክ ( Theotokos) ናት:: ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከተፈጠረም በኋላ መቸም መች አምላክን "ልጄ ወዳጄ" ማለት ከቶ ለማን ተችሏል? እርሱ ፈጣሪ እርሷ ደግሞ ወላዲተ ፈጣሪ ኩሉ ዓለም ናት:: እርሱ እውነተኛ ደስታ እርሷ የደስታ መፍሰሻ ናት። (መዝ ፵፭:፭) እርሱ ሕይወት እርሷ ነቅዐ ሕይወት (የሕይወት ምንጭ) ናት። ይህች ብርሃን ሙዳየ መድኃኒት ቤዛዊተ ኩሉ ብርሃንን ትሰጠን ሕይወት ክርስቶስን ትወልድልን ዘንድ ከተቀደሱ ተራሮች ከአብርሃም ከዳዊት ቤት ተወለደች። (መዝ ፹፰(፹፱):፩)

+++ የልደቷ ቀን +++

አንተ የራስህን እንዲሁም የምትወዳቸውን ሰዎች ልደት ሻማ አብርተህ ኬክ አስጋግረህ ወዳጅ ዘመዶችህን ጠርተህ በዳንስ በጭፈራና እስክስታ በመውረግረግ ታከብራለህ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም የተወለደችበትን ቀን በማሰብ በዓለ ልደቷን የሚያከብሩ ሰዎችን ግን ለምን ያከብራሉ ብለህ ትተቻለህ:: ለመሆኑ አንተ ያንተ የሆኑትን ሰዎች ልደት ተገቢ በሆነ መንገድ ብታከብር አምላክ እንደማያዝንብህ ካወቅህ የእናቱን ልደት እርሱን እያመሰገንን እያወደስን እናቱ "ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል።" (ሉቃ ፩:፵፱) እንዳለችም እርሷንም እያመሰገንን "ብርቱ የሆን እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና።" ብላ እንደመሠከረችም በእርሷ ለሰው ዘር የተደረገውን ታላቅ ሥራ እያሰብን ብናከብር የሚያዝንብን ይመስላሃልን? ከማዳኑስ በላይ ምን ታላቅ ሥራ አለ? ዓለም:- የኤድስ ቀን፣ የጉበት ቀን፣ የኩላሊት ቀን፣ የላብ አደር ቀን፣ የውሃ ቀን፣ የአፈር ቀን፣ የእናቶች ቀን፣ የአባቶች ቀን እያለ በልዩ ልዩ መንገድ ሲያከብር ቅር አይለውም የእናቱ የእመቤታችንን ልደት ለማክበር ግን ያመዋል::
ልደታ ለማርያምን ስናከብር

☞ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት በዳንኪራና በአስረሽ ምስናከብር
ሆን በመንፈሳዊ ሥርዓት እናክብረው ያኔ የልጇ በረከት እጥፍ ድርብ ይሆንልናል። (ምሳ ፲:፯፣ ፩ጴጥ ፪:፲፪)
☞ የቤተክርስቲያን ባልሆነ የልደቷን ነገር በማይገልጥ በማይወክል መንገድ በአምልኮ ባዕድ ጨሌን በየዛፉ ዙርያ አረቄና ቡና በማፍሰስ የሚያከብሩትን ሰዎች በማስተማርና ትክክለኛውንና የክርስትናውን መንገድ በተከተለ መንገድ እንዲያከብሩት በማድረግ ድርሻችንን በመወጣት እናክብር ::
☞ ልደቷ "በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ከተባለለት ከዮሐንስ ልደት የሚልቅ መሆኑን እንወቅ። እርሷ የዮሐንስ ፈጣሪ የክርስቶስ እናቱ ናትና። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም " ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ።" እንዳለ:: እርሱ ክርስቶስ "ሁሉን በስሜ አድርጉት" እንዳለን እርሷን በእርሱ ስም ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን ብለን ተቀብለን ልደቷን እንደምናከብር እንረዳ:: (ሉቃ ፩:፲፬)

+++ አድባር +++

አድባር የሚለው ቃል የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም ተራሮች ማለት ነው:: እመቤታችን በሊባኖስ ተራሮች መሐል ተወልዳለችና የልደቷን ወቅት አድባር እንላለን። (መኃ ፬:፰)

🚹የእናቱን በዓለ ልደት ማክበር ማኅበራዊ ፋይዳ 🚹

በዚህ ቀን የአንድ ቀዬ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ጸሎት በማድረግ እግዚአብሔርን በማመስገን እናቱንም በማወደስ ማክበራቸው ከሃይማኖታዊው ፋይዳ ባለፈ በልዩ ልዩ ምክንያት እየደበዘዘና እንደ ዳይኖሰርና ዶዶ ድራሹ እየጠፋ የመጣውን አብሮነት ማኅበራዊ ትስስር የሚያጠነክር መልካም ባሕላችንም ጭምር ነውና አጥብቀን ልንይዘው ይገባናል:: የድንግል ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ የልደት ቀን በረከት ያሳትፈን!!!

©️ መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፲፮ ዓ ም
"ዕርገተ ክርስቶስ"

#ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፤ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ"(መዝ46:5) በማለት ጌታው ሲሆን ልጁ ልጁ ሲሆን ጌታው ስለሚሆን ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ ትንቢት ተናግሯል።

#በዚህ ኃይለ ቃል ያለው ምሥጢረ ተዋሕዶ ምንድን ነው? ቢሉ "አምላክ" ብሎ አምላክነቱን "ዐረገ" ብሎ ሰውነቱን ያስረዳል።ማረግ (ከፍ ከፍ ማለት፣ወደ ሰማይ መውጣት) የሚስማማው ሥጋ ነውና በተዋሕደው "ሥጋ ማርያም" በሁሉ ላለ "ቃል ለሚባል እግዚአብሔር" ዕርገት ተነገረለት።

#ነገሩን ትንሽ ለመግለጥ ያህል፦አምላክ በሁሉ ቦታ (በምልዐት) የሚገኝ ስለሆነ ከዚህ ተነሥቶ እዚያ ደረሰ አይባልም።አምላክ በተዋሕዶ ሰው ሲሆን ግን ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር ለእኛ የሚነገረው ሁሉ ለእርሱም ተነገረለት።ተፀነሰ፣ተወለደ፣ተሰደደ፣ተጠመቀ፣ተሰቀለ፣ሞተ፣ተቀበረ፣ተነሣ፣ዐረገ ተባለለት።ይህ ሁሉ ግን በበጎ ፈቃዱ የተከናወነ ነው ፤ እንደኛ ግዳጅ ያለበት አይደለም።

#ክርስትና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን የእግር አሻራ የመከተል ሕይወት ነውና እርሱ ስለኛ የፈጸማቸውን ሁሉ እንፈጽማለን።ኋላም እርሱ በኃይሉና በሥልጣኑ ተነሥቶ እንዳረገ እንዲሁ እኛንም አስነሥቶ ያሳርገናል።ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ "እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ" ማለቱም ለዚህ ነው።

#ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ ብሎ ጌታችን የነገረን ቃል እኔን በመመሰል እንድታድጉ (Theosis:ሱታፌ አምላክ) አደርጋችኋለሁ ሲል ነው።ይኸውም በመንግሥተ ሰማያት የምንኖረው ኑሮ "ዕርገታዊ" (ከፍ ከፍ የማለት) እንደሆነ ያስረዳል።ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" በማለት ውስጥ እየተቀደስን በጸጋ ላይ ጸጋ በክብር ላይ ክብር በጣዕም ላይ ጣዕም እየተጨመረልን እግዚአብሔርን እየመሰልን ከፍ እንላለን።

ከበዓለ ዕርገቱ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን!!!
"ዕርገተ ክርስቶስ እንደ ሃይማኖት"

#በጸሎተ ሃይማኖታችን ከምንመሰክራቸው ምስክርነቶች አንዱ "በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ" የሚል ነው።በዚህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ በኋላ እንዳረገ ማመናችንን እንገልጣለን።ይህንን ሃይማኖታችንን ያገኘነውም "የእግዚአብሔር መንፈስ ካለባቸው" ቅዱሳት መጻሕፍት ነው።(2ኛ ጢሞ 3:16)

ቅዱስ ዳዊት "በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" (መዝ 67:33) ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ "ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ" (ሉቃ 24:51) ብለውናል።እነዚህም የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነቶች ናቸው።

"ዕርገተ ክርስቶስ በነገረ ማርያም"

#የእመቤታችን ወዳጅ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ" ሲል ያመሰግናታል።ይኸውም ለቃል ርደት(መውረድ (ሰው መሆን) ) ለሥጋ ዕርገት ( ከፍ ማለት (አምላክ መሆን) )ምክንያት ድንግል ማርያም ናት ማለት ነው።ቃል ሥጋ ሲሆን ሥጋም ቃልን በመሆን ከፍ ያለው (ያረገው) በማኅፀነ ድንግል ማርያም ነው።ኋላም ከተነሣ በዐርባኛው ቀን ያረገው ከእመቤታችን ሰው በሆነበት ሥጋ ነው።በዕርገቱ ጊዜ ከእናቱ የነሣው (የተዋሐደው) ሥጋ አልተለየውም።"በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ..." በሚለው ኃይለቃል ውስጥ ያለው "ምሥራቅ" የሚለው ቃልም "ሥጋ ማርያም"ን ያሳያል።ጌታ ፀሐየ ጽድቅ ሆኖ ከእርሷ የወጣባት ምሥራቅ ድንግል ማርያም ናትና።ስለዚህ ኃይለ ቃሉ "በድንግል ማርያም ሥጋ ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" ተብሎ ይተረጎማል።

"ዕርገተ ክርስቶስ በአምልኮአችን"

#ቅድስት ቤተክርስቲያን የምትገለጥበት ትልቁ አምልኮዋ ቅዳሴ ነው።የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በቅዳሴዋ "አሜን" ( አሜን ለሃይማኖት ሲሆን ትክክል/እውነት ማለት ነው) እያለች ከምትናገራቸው ምስክርነቶቿ አንዱ "ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ" (ዕርገትህን እናምናለን ሁለተኛ መምጣትህንም) የሚል ነው።እንዲሁም ካህኑ "አልዕሉ አልባቢክሙ" (ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ) በማለት ከፍ ከፍ ያለውን አምላካችንን ሲያሳስበን ዲያቆኑ ደግሞ "ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ" ብሎ የጌታን በምሥራቅ ማረግ ያስታውሰናል።ልቡናን ከፍ ከፍ ማድረግም በዓይነ ልቡና ከሐዋርያቱ ጋር ጌታን ሲያርግ መመልከት ፤ በዕዝነ ልቡና የቅዱሳን መላእክቱን ዝማሬ ማድመጥ፤ በአንፈ ልቡና መዓዛ ዕርገቱን ማሽተት ፤ በእግረ ልቡና ከሐዋርያቱ ጋር በደብረ ዘይት መቆም፤በአብራከ ልቡና ለጌታችን መስገድና በዚህ ሁሉ መደሰት ነው።"እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ" እንዲል (ሉቃ 24:52)

"ዕርገተ ክርስቶስ በክርስቲያናዊ ሕይወት"

#ጌታችን ወደ ላይ ከፍ ከፍ እንዳለ ክርስትናም ከፍ ከፍ የማለት ሕይወት ነው።ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ "በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል" (1ኛ ዮሐ 2:6) እንዳለ ጌታችን ከፍ ከፍ እንዳለ እኛም በቅድስና ከፍ ከፍ ልንል ይገባናል።ይህ የቅድስና ሕይወትም ከሥጋ ንጽሕና ወደ ነፍስ ንጽሕና ከነፍስ ንጽሕና ወደ ልቡና ንጽሕና የሚደረግ ጉዞ ነው።ከሁሉ አስቀድመን ግን ከስድብ ወደ ምስጋና፣ከጥላቻ ወደ ፍቅር፣ከቂም ወደ ይቅርታ፣ከዓለም ወደ ቤተክርስቲያን፣ከፍልስፍና ወደ ሃይማኖት፣ከገዛ አጉል እሳቤአችን ወደ እግዚአብሔር ሐሳብ ከፍ ከፍ ልንል ያስፈልገናል!!!

"ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ፤ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን።" (2ኛ ተሰ 4:17)

መድኃኔዓለም እንዲህ ያለውን የክብር መነጠቅ በቸርነቱ ያድለን !!!

ሰኔ 07/2016 ዓ.ም

#ኢዮብ ክንፈ
ዛሬ ይለቀቃል !!
በራሴ የዩትዩብ ቻናል ይጠብቁ
ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ለሌሎችም በማጋራትና እዲቀላቀሉ በመጋበዝ ይደግፉኝ!!🙏🙏🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
Forwarded from Eyob kinfe
"ሕይወትን በሚሰጥ አዳኝ በሆነ ከአብ በሠረጸ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን" (ጸሎተ ሃይማኖት)

#እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በዛሬው ዕለት በእሳትና በነፋስ ተመስሎ ለቅዱሳን ሐዋርያት ወረደ።ይኸውም በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት የደስታ መፍሰሻ ወላዲተ አምላክን ከብበው በአንድ ልብ ሲጸልዩ ነው።

#ፍስሕት (ደስተኛዪቱን) ይዘው ቢጸልዩ የደስታ መንፈስ የሆነ መንፈስቅዱስ ወረደላቸው።

#መዝገበ ምሥጢር ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ከሣቴ ምሥጢር (ምሥጢርን የሚገልጥ) መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው።በዚህም በሚያውቁት አንድ ቋንቋ ላይ ሰባ አንድ ቋንቋ ተገልጦላቸው ቅዱስ ወንጌልን ሰብከዋል።

#ናዛዚት (የምታረጋጋ) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ናዛዚ (የሚያረጋጋ) መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቷቸዋል።

#ንጽሕት ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ) መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

#ጽንዕት (የጸናች) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መጽንሒ (የሚያጸና) መንፈስቅዱስን ተቀበሉ።

#መስተሥርዪ ኃጢአት (ኃጢአትን ይቅር የምታስብል) ርኅርኂተ ኅሊና ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ኃጢአትን ይቅር የሚል መንፈስ ቅዱስ በእሳት ተመስሎ ወደ እነርሱ መጣ።

#እናታቸውን ይዘው ምን ሊያጡ ኖሯል?ጽዮንን (እመቤታችንን) ከብበው ቢጸልዩ በደብረ ጽዮን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው።

#ይህቺ ቀን የቅድስት ቤተክርስቲያን የልደት ቀን ናት።ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው እንደ ጌታቸው ሁሉ ጾሙ ጸለዩ።መንፈስ ቅዱስ ያደረበት እንደሚጾም እንደሚጸልይ ያጠይቃል።በዓለም ሁሉ ዞረው ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበኩ።

#አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቸርነቱ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነት ከመፍገምገም ወደ ጽናት ፣ ከኃዘን ወደ ደስታ ፣ ከኃጢአት ወደ ንጽሕና ፣ ከመቅበዝበዝ ወደ መረጋጋት ፣ ከድንቁርና ወደ ዕውቀት ይመልሰን!!! አሜን !!!

#በዓለ ጰራቅሊጦስ

ወርኃ ሰኔ 16 / 2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ
subscribe ያድርጉ 🙏🙏🙏

👇👇👇👇👇👇

http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
+++ ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ! +++

በፍጹም ተዋሕዶ አንድ የኾነ ክርስቶስን እየነጣጠለ በሰውነቱ እንዲህ በመለኮቱ እንዲያ እያለ ሊከፍል የሚሻ አስተሳሰብን ለመንቀፍ ሊቃውንቱ "ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ" በማለት መጻሕፍትን መሠረት አድርገው ከፊደል ላይ ሳይሆን ትርጓሜን መነሻና መድረሻ አድርገው በስፋት ያስተምራሉ "ተዋሕዶ ኹለትነትን አጠፋ" ለማለት። ሥግው ቃል (Incarnated logos) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ አይነጣጠልም አይከፋፈልም!!

በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆኖ በሥጋ ማርያም የተገለጠ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ነው፡፡ ሥጋም ፍጹም በሆነው ተዋሕዶ የመለኮትን ገንዘብ (ግብረ ባሕርዩን፡- ሁሉን ዐዋቂነት ሁሉን ሰጪነት ልዕልና ምሉዕነት ሁሉን ቻይነት ….) ገንዘቡ አድርጓልና "ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው።" ብሎ ተናገረ፡፡ (ዮሐ 16፥15)

ለአብ ያለው ምንድነው? ለአብ ያለው ዕውቀት፣ ቸርነት፣ ከኃሊነት፣ ጥበብ ሁሉ ለወልድም አለውና የወልድም ጥበቡ፣ ዕውቀቱ፣ ቸርነቱ፣ ከኃሊነቱ ተቆጥሮ ተሠፍሮ አያልቅም ፡፡ ለእኛ ጸሎትን ምስጋናን ሊያስተምረን ሥጋም (ሰውነት) በተዋሕዶ መክበሩን በገለጠበት አንቀጹ "አባት ሆይ ያንተ የሆነ ሁሉ የእኔ ነው የእኔውም ያንተ ነው።" በማለት ተናግሯል፡፡ (ዮሐ 17፥10) ጌታችን ክብር ይግባውና ከባሕርይ አባቱ ከአብ ጋር በሥልጣን በሕልውና በአገዛዝም በምልአትም አንድ እንደሆነ በሥጋዌው ወራት ዋና ምሥክርነቱ ነበር፡፡ (ዮሐ 14፥8-11) "የእኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ ባደርገው ግን እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደሆነ እኔም በአብ እንደሆንሁ (በሕልውና፣ በአኗኗር፣ በዕውቀት አንድ እንደሆንን) ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።" ብሎ እንደተናገረ፡፡ (ዮሐ10፥38)

ወልድን መካድ (በወልድ ላይ የክሕደት ንግግር መናገር ) አብን መካድ ነው፡፡ ወልድን በገደምዳሜ ወደ ንስጥሮሳዊ ትምህርት ማስጠጋት አብንም መካድ ነው። ሊቃውንቱ "አብ ሲነክ ወልድ ይነክ።" እንዲሉ። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ "ወልድን የሚክድ አብ እንኳን የለውም በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።" ብሎ የመሠከረውም ይህን ያመለክተናል፡፡ (1ዮሐ 2፥23)

መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ሠኔ 26 ቀን 2016 ዓ ም
https://www.facebook.com/bitwoded.worku?mibextid=ZbWKwL
"ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ።" (ኢሳ 51:2)

    ነቢዩ ይህንን ቃል ቅዱስ አብርሃምንና ቅድስት ሣራን ምሰሏቸው ለማለት ተናግሮታል።

#አብርሃም አበ መናንያን (የመናንያን አባት) ነው።ሁሉን ትቶ እግዚአብሔርን ተከትሎአልና።(ዘፍ 12:1)

#አብርሃም የሙሽሮችም አባት ነው።ሚስቱ ምን መካን ብትሆን አልተዋትምና።

#አብርሃም ለሰብዓ ዓለም (በዓለም ለሚኖሩ ክርስቲያኖች) አባት ነው።በሕገ ልቡና ሁኖ ወንጌልን ፈጽሟልና።አረ ግሩም ነው !!! የእግዚአብሔር እንግዳ ቤቴ ሳይመጣ ግብር አላገባም፤እህል አልቀምስም ማለት እንዴት ያለ ብፅዕና ነው!? ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ እንዴት ቢጸኑለት ነው!?ደጉ አባታችን የእግዚአብሔር ሰው አብርሃም  ወንጌልን ሲፈጽማት ተመልከቱልኝማ!!!

#"በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና"(ማቴ 5:3) ትሑቱ አብርሃም ባለጠጋ ሆኖ ሳለ ለእኔ የሚስማማ ደህነትነው፤ባለጠግነትማ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው በማለት መንፈሱን ዝቅ አድርጎ ራሱን እንዳሳላፊ ቆጥሮ እግዚአብሔር የሰጠውን ለሌሎች ያካፍል ነበር።በዚህም መንግሥተ ሰማያት (የሰማያት መንግሥት) የሆኑ ሥላሴን አስተናግዷል።መንግሥተ ሰማያት የሚባል ጌታም ከእርሱ ዘር ተወልዷል።"የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።"ማቴ 1:1እንዲል

#“የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።”
(ማቴ 5:4) ርኅሩኁ አብርሃም ለሦስት ቀናት ያህል ሰው ቤቱ ስላልመጣ እጅጉን አዝኗል።ሥላሴን በማግኘት ተጽናንቷል።

#"ስለ  ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።"(ማቴ 5:6) መፍቀሬ ሰብእ ደጉ አብርሃም ስለ ሰው ፍቅር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ተርቧል።ጽድቅ የሚባል እግዚአብሔርን በድንኳኑ ተቀብሎም ጠግቧል (ነፍሱ ተደስታለች) ።

#"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።"(ማቴ 5:10) የሃይማኖት ሰው አብርሃም እግዚአብሔር "ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።"(ዘፍ 12:1) ሲለው በፍጹም እምነት ወጥቷል።መንግሥቱንም ወርሷል።

    "አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፤አየም ደስም አለው።" ዮሐ8:56 ማለት እንግዲህ  ይህ ነው።በጨለማው ዘመን ሆኖ ብርሃንን ማየት ወንጌልን መኖር!!!ቅድስት ሥላሴን በቤቱ ተቀብሎ"የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተእመለሳለሁ፤ሣራምልጅንታገኛለች።"ዘፍ18፤14 ባለው ቃል መሠረት ለጊዜው ይስሐቅን እንደሚወልድ ለፍጻሜው ክርስቶስ ከእርሱ እንደሚወለድ ኪዳንን ተቀብሏል።

#በሕገ ልቡና ሕገ ኦሪት በሕገ ኦሪት ሕገ ወንጌል በተሰጠን በእኛ ቅዱስ አብርሃም ይፈርዳል፤ከአብርሃም የሚከብር ጌታ በሥጋ አብርሃም ተወልዶ በጥምቀት ልጅነትን፣በልጅነት መንግሥተ ሰማያትን ሰጥቶን የአብርሃምን ሥራ አልሠራንምና።

        የአብርሃሙ ሥላሴ በሁላችን ቤት ይደሩ!!!

                       ሐምሌ ሥላሴ/2016 ዓ.ም
    #ኢዮብ ክንፈ