አትሮኖስ
280K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ልክ ዐይታው እንደማታውቅ ሰው እጆቿን ስትዘረጋለት ተመለከትኩ፡፡

ረጅም፣ ጠይም፣ ደልዳላና ዱባ ከንፈር ያለው ቢገፋ ቢገፋ ከሠላሳ
ሦስት የማይዘል ሰው ነው፡፡በሳምኳት ቁጥር ሥሥ ከንፈሮቼን መንከስ የጀመረችው ይሄን ዱባ ከንፈሮቹን ያገኘች እየመሰላት ይሆን?

እንዲህ አቅርባ የምታወራውን
ለሁሉም እንደምታደርገው በማቀፍና መሳም ፈንታ እጆቿን ለመጨባበጥ
ስትዘረጋለት፤ ቤቴ፣ ቤቴ ሳይሆን የብሄራዊ ቲያትር መድረክ፣
እነሱም ሊተውት የመጡ የኪነት ሰዎች ሆነው ታዩኝ፡፡

“በረከት ባሌን ተዋወቀው...” አለችና ቀድማው ወደ እኔ መጣች፡፡
ስትሰናዳበት እንደቆየችው ቂጡዋን በእሱ የዕይታ ማእቀፍ ውስጥ
አድርጋ እየተወዘወዘች ስትመጣ፣ እንደማፈር ብሎ እያያት ሲከተላት ተመለከትኩ፡፡

“ሙሉጌታ...” አልኩት፣

የጨበጠኝ እጁን ጭምቅ አድርጌ
ጨብጬ... የገዛ ስሜ አፌ ውስጥ ዝገት ዝገት እያለኝ...

ቤታችን ከሚፈቅደው በላይ የተነጋገሩ በሚመስል ሁኔታ ተራርቀው ተቀመጡ፡፡(በዚህ ጊዜ ቢሆን #ኮረና ይባል ነበር) አልፎ አልፎ ካልሆነ አይተያዩም፡፡

ዐየኋት፡፡

ዐይቶና ነክቷት እንደማያውቅ ሁሉ እጆቹን ባፈረ ሰው አኳኋን አጣምሮ ሷፏው ላይ እየተቁነጠነጠ ተቀምጧል።

ቀሽም ተዋናዮች!

የግብዣውን ቡፌ አጋምሶ ሆዱ ጢቅ እስኪል ከበላ በኋላም የጠገበ
አልመሰላትም መሰለኝ...

“በረከት ይኼ ዳቦ እኮ ልክ አንተ እንደምትወደው ነው... ያዝ እንጂ...”

“ኧረ ጎመን በስጋውን መች ነካኸው በረከት...”

“ላዛኛው ከውጪ የመጣ መስሎህ ነው.? በረከት ሙት... እኔው
ራሴ ነኝ እኮ የሠራሁት... ባለሙያ እኮ ነኝ ሃሃ”

ምሳው አብቅቶ ለቡና ስንቀመጥ እንደገና ዐየኋቸው፡፡

በዐይኑ ይነካታል፡፡

በዐይኑ ልብሷን ያወልቃል፡፡

በዐይኑ ይተኛታል፡፡

በዐይኖቿ ትስመዋለች፡፡

በዐይኖቿ ትዳራዋለች፡፡

በዐይኖቿ የአልጋ ላይ ጨዋታ እንደሰመረላት ሴት
እየተስለመለመች ትሞትለታለች፡፡

ያለ ቃል፣ ያለ አልጋ፣ ፊት ለፊቴ ሲዳሩ ደሜ ከፍ አለ፡፡ ሲጋራ ላጭስ ብዬ ወጣሁ፡፡

አርባ አራት ሲጋራ ይመስለኛል አጭሼ ስመለስ ጭኮ ቀርቧል፡፡ ይሄ ሰው ሚስቴን ብቻ ሳይሆን ጓዳዬንም ሊዘርፍ ነው የመጣው?

“ብላ በናትህ... እንደ ወለጋ ጭኮ ባይሆንም አሪፍ ነው....”
አለችው፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብዬ ስቀመጥ፣

“ስቃኝ ሳምሪ....” ተግደረደረ፡፡

“እስቲ እሱን ነገር ለእኔ ስጪኝ...” አልኩ ንዴቴ ጢም ብሎ ሲሞላ፡፡ ዐየችኝ፡፡

“ምነው...ጭኮ እንደምወድ ታውቂያለሽ... ስጪኝ እንጂ?” አልኩ
መልሼ፡፡

“እኔ እኮ ለበረከት የገዛሁት 'ደምቢዶሎ የምበላው የእናቴ ጭኮ እያለ ሲያወራ ሰምቼ አሳዝኖኝ ነው፡፡

አንተማ አይፈቀድልህም.... ሃሃ” ሣቀች፡፡

ጥርስሽ ይርገፍ፡፡

“ተይ እንጂ... በቤቱ አትከልክይው...” አለች ቃል ከዳን፣ ተነስታ ሰሀኑን እያመጣች፡፡ መምጣቷን ብቻ ሳይሆን መፈጠሯንም ረስቼው ነበር፡፡

“ተይ ቃል.... ወድጄ እኮ አይደለም የከለከልኩት.. ቦርጩን
አታይም...? ያወፍረዋል... በረከት እኮ ቢያንስ ጂም ይሠራል... የኔ ባል ግን ሰነፍ ነው... ለእሱ አስቤ እኮ ነው...”

አላበዛችውም?
*
ከአንድ ሳምንት በኋላ...
የበረከት ስም በድንገት ሊባል በሚችል ሁናቴ ከሚስቴ አፍም፧ከቤታችንም ተለየ፡፡ ፈጽሞ አትጠራውም፡፡ ጨርሶ አታነሳውም፡፡በነገሩ ስገረምም ስብሰለሰልም ከረምኩና፣ አንዱን ማታ የመጣው ይምጣ ብዬ፣

“እኔ የምልሽ...” አልኳት፡፡

“አንተ የምትለኝ...?”

“ያ በረከት ደህና ነው...? ምነው ስለእሱ ስታወሪ አልሰማም - ይህን
ሰሞን?” አልቆዘመችም፡፡ ለማሰብ ጊዜ አልወሰደችም፡፡

ለጥያቄው እንደተዘጋጀች ሁሉ፣

“ኡፍ... እሱ ልጅ እንዳስጠላኝ...” አለችኝ፡፡

“ምነው ምን አደረገ?” እያቁነጠነጠኝ ጠየቅኩ፡፡

“አይ... ምንም.... ማለት እኔን ምንም አላደረገኝም ....ግን አንዳንድ
ሰው ደህና ይመስልና ስታውቀው ይደብርሃል... አይደል? እንደዛ
ነው.... በቃ አለ አይደል...”

ወሬዋን ሳትቋጭ አቀርቅራ ወደ ማእድ ቤት ሄደች፡፡ ስታውቀው ይደብርሃል?

ምን ተፈጥሮ ነው? ተኝቷት ዐይንሽን ላፈር አላት?

ሌላ ዐየባት? ተደብሮባት ወደ ዩኤን ሄደ? እጁን ስመው ተቀበሉት?

ሲያዝንባትና ሲጠየፋት የከረመ ገላዬ
ተኮማተረ፡፡ የበጠሰችው አንጀቴ ደነደነ፡፡

በነጋታው እንቅልፍ ያላየ ዐይኔን እያሻሽሁ ሳሎን ሆኜ ፤ ንግስቴን፣
“ከልቤ ዙፋን ተባረሻል” ብዬ ለመንገር እሰናዳለሁ፡፡ ለምን እንደበቃኝ
ላስረዳት እዘጋጃለሁ፡፡
ሐሳቤን ሳልቋጭ መጣች፡፡
ጸጉሯን በቅድመ በረከት ዘመን እንደነበረው ፤ ጨብራራ ፍሪዝ
አድርጋ፣ የምወደውን ዘልዛላ ሰፊ ሱሪዋን እና ታኮ የለሽ ክፍት ጫማዋን ተጫምታ ሜክአፕ ያልዞረበትን የምወደውን ፊቷን ይዛ ከመኝታ ቤት መጣች፡፡

ዐየኋት፡፡

.ልቤ አንገራገረ፡፡

የጎዳችው ልቤ አንገራገረ፡፡

አንገራገረ።

አንገራገረ።

በኛ በኩል አልቋል እናንተ ከፈለጋቹ ቀጥሉበት😃

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ #ፍክት ያለ ቅዳሜ ይሁንላቹ ደሞ #Share አድርጉ እንጂ 🙏
👍3
#በኔ_የደረሰ


#ክፍል_ሰባት (የመጨረሻው ክፍል)


#በጥላሁን

ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ሲሆን አባዬ ትዝ ብሎኝ ወደቤቴ ካልሸኘሽኝ ብዬ ቤቱን ባንድ እግሩ አቆምኩት በወሰደኝ መኪና ተመልሼ ልክ ግቢያችን በር ላይ ስደርስ ስካሬ ብን ብሎ ጠፋ።

ሹክክ ብዬ እንደወጣሁት ሹክክ ብዬ በመግባት ተጠቀለልኩ።
አይነጋ የለ ነጋ ። ጥዋት 2:30 አከባቢ እማዬ የክፍሌን በር አንኳክታ ሰለሞኔ ተነስ ቁርስ ቀርቧል እየጠበቅንህ ነው ስትለኝ ።መብረቅ ክፍሌ ላይ የወረደባት ይመስል ክው አልኩላችሁ።

ለካ እሄም አለ አሁን እኔ ለሊት እዛ ሁሉ ጉድ ውስጥ አሸሸ ገዳሜ ስል አድሬ እንዴት ነው ከሽማግሌው አባቴና ከአረጊቷ እናቴ ጋር መአድ ባንድ ላይ ቀርቤ እምበላው ••••
እምለው እማረገው ሁሉ ጨነቀኝ ቀና ብዬ እዛው አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩና ሁለቱን እጄቼን ወደ ፊት ዘርግቼ እያየኋቸው •••
ማታ እንዳልተለከፍኩ በምን እርግጠኛ ነኝ እራሴን ጠየኩት?
በምንም ደሞ ጉሮሮህ አከባቢ ህመም እየተሰማህ ነው ይዞህ ይሆን እንዴ ? አለኝ ውስጤ
ጉሮሮዬ እንኳን ማታ ብዙ አይነት መጠጥ እየቀላቀልኩ ስለጠጣሁ ሊሆን ይችላል ያመመኝ ።

ላይሆንም ይችላል በሽታውም አንዱ ምልክቱ እንደዛ ነው?
እስቲ አስበው በዚህ እጅህ ስንቱን ነገር ነክተሀል፣ ከስንቱ ጋር ተጎራርሰህ በልተሀል ፣ከስንቱ ጋር እየተቀባበልክ ጠጥተሀል ፣ ስንቱ የተቀባበለውን ቢራ መክፈቻ ተጠቅመሀል
ውስጤ ሌላ ሰው ተቀምጦ የሚያስፈራራኝ መሰለኝ በሁለት ሀሳብ ተከፍዬ ከራሴ ጋር ስከራከር እራሴን አመመኝ።
አንድ ሰው የማንፈልገውን ወይም የሚረብሸንን ወሬ ቢያወራብን ዝም እንዲል አልያም ወሬ እንዲቀይር እንነግረዋለን ካልሆነ ካጠገቡ ተነስተን እንሄዳለን ከሚድያ ላይ የሚወራውን መስማት ካልፈለግን ተነስተን እንጠረቅመዋለን።
ከደጅ የሚመጣን ጩኸት መስማት ካልፈለግን ጆሮአችንን እንይዛለን
ከውስጣችን የሚመጣውን ጩከት መስማት ባንፈልግ ምናችንን እንይዘዋለን ወዴትስ እንሸሻለን?
እማዬ ድጋሚ የክፍሌን በር አንኳኩታ "ኧረ አባትህ እየጠበቀህ ነው ሰለሞኔ ቁርስ ቀርቧል እኮ!" አለችኝ።
ወጥቼ ሻወር ቤት ገባሁና ከሰዉነቴ ክፍሎች ሁሉ እጄን ደጋግሜ ታጠብኩት።
"ውስጥህንስ በምን ታጥበዋለህ ይዞህ ከሆነ በትንፋሽም እኮ ይተላለፋል አለኝ ከበሽታው በላይ ውጋት የሆነብኝ የውጤ ሀሳብ ነው።

እናባዬ ወዳሉበት ሳሎን ገባሁ ። ግን ሳልጠገቸው ፈንጠር ብዬ ብቻዬን ተቀመጥኩ።
"ዛሬ ምን ሆኗል ልጄ ና እንጂ ቁርስ እንብላ አንተን አይደለም እንዴ የምንጠብቀው" አለ አባዬ።
አይ አይሆንም አባ ካሁን ቡሀላ እሄ ክፉ በሽታ ከሀገራችን ተጠራርጎ እስኪወጣ ምግብም ቢሆን አብረን ለመብላት ስንል መቀራረብ የለብንም ። ለብቻዬ ብታቀርብልኝ ይሻላል አይሻልም አባ? ስል•••
እማ ጣልቃ ገብታ " አበስኩ ገበርኩ የደጁን ይሁን ስል ልጆቼንም ከጉያዬ ሊያርቅብኝ ነው እሄ በሽታ ከመች ወዲህ ነው ልጄ መአድ ተነጣጥለን በልተን የምናውቀው መአድ በአንድ ላይ ቀርቦ መብላት ፍቅርን ያደረጃል ልጄ።
ደሞ በኛ መሀል ኬት ይመጣል ከቤት ወጥተን አናውቅ የምንፈልገውን እቃ እንኳን የባታችሁ ወንድም ነው ገዝቶ የሚያመጣልን እቃ ገዝቶ መጥቶ እንኳን በር ላይ አስቀምጠህ ሂድ እንጂ ግባ ብሎት አያውቅ አባታችሁ።
ዛሬ ድንገት ተነስተህ ለብቻዬ አቅርቡልኝ ማለቱን ምን አመጣው ጥሩ ህልም አላየህም ልጄ እስቲ ንገረኝ?" ብላ ዝም ብዬ ሳያት እኔን ትታ ወደአባዬ ፍቷን መለሰችና
"፣እሄው ልጆቼን የፀሀይ ብርሀን እስኪናፍቃቸው ድረስ አላላውስ ብለህ ተጭነህ ስታስጨንቃቸው በጭንቀት ብዛት የልጄን አይምሮ እንዲቃወስ አድርገከው አረፍክ " ብላ ስታፈጥበት
ደና ነኝ እማዬ ምንም የሆንኩት ነገር የለም አባንም እንደዛ ማለት የለብሽም አባ ልክ ነው ። በቃ ተራራቁ ተብሏል እንራራቅ ነው ያልኩት ቀለል አርጋችሁ እዩትና እሺ በሉኝ እናንተ አንድ ላይ ብሉ ለኔ ለብቻዬ ስጪኝ። ስል እህቴ ከነበረችበት ተነስታ •••
"ባክህ የሌለ ነገር እያወራህ አታጨናንቃቸው ተነስና እንብላ!" እያለች እጄን ይዛ ልትጎትተኝ ነው መሰለኝ ወደኔ ስትጠጋ
ከተቀመጥኩበት ተፈናጥሬ በመነሳት እንዳትጠጊኝ እህቴ ነግሬሻለሁ እንዳትጠጊኝ በቃ ስል አባም ግራ ተጋብቶ ተነስቶ ሲቆም
ተጠግቶ ሳይዘኝ ቤቱን ጥየላቸው ብን ብዬ ልጠፋ አሰብኩና እናቴ ልጄ አበደ ብላ እራሷን ከማጥፋት እንደማትመለስ ሳስበው ፈራሁ።
አንተም እንዳትጠጋኝ አባ በቃ ተረዱኝ አትጠጉኝ አልኩ አትጠጉኝ እያልኩ ወደ ክፍሌ በመግባት ከውስጥ ዘጋሁት።
በስንት ውዝግብ አሳምኛቸው ምግብ መስኮት ላይ እየተደረገልኝ በልቼ አጥቤ እየመለስኩ ስምንት ቀን ሆነኝ ። በዘጠነኛው ቀን ጥዋት ጋደኛዬ ደውሎ
የነ ሊሊ ቤተሰቦች በሽተኛ እቤት ውስጥ መኖሩ ተጠቁሞባቸው ቤተሰቡን በሙሉ አፋፍሰው ካስገባቸው ቡሀላ በምርመራ ሌሎቹ የቤተሰብ አባላት ላይም ስለተገኘ ያን ቀን የሊሊ ልደት ላይ የተገኙት በሙሉ እየታደኑ ወደማቆያ እየተወሰዱ ነው አሉ እኛ ጋም መምጣታቸው አይቀርም አልቆልናል ሶል!"
ሲለኝ እኔ እዛው በተኛሁበት አለቀልኝ ። የተኛሁበት በላብ ሲዘፈቅ ትዝ ይለኛል ካልጋዬ ላይ መነሳት አቃተኝ ካንድ ቀን ቡሀላ ብንን ስል መስኮት ላይ ያስቀመጡትን ምግብ ወስጄ አለመብላቴ ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቼ እህቴን በመስኮት አዘልለው በማስገባትና ከውስጥ እንድትከፍት በማረግ አልጋዬ ላይ ዙሪያዬን ከበውኝ እስክነቃ በጭንቀት ሲጠባበቁ ተመለከትኩ ። በሂወቴ እንደዛች ቅፅበት መሪር ሀዘን እና የነብሰ ገዳይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ። እርርይ አልኩ።
በንጋታው ሁላችንንም ወደ ማቆያ ወሰዱን ከቀናት ቡሀላ የምርመራ ውጤቱ ሁላችንም እንዳለብን አመለከተ።
ውጤቱን ስሰማ በተለይ ቤተሰቦቼን በመሉ ማስያዜን ስሰማ ድጋሚ እራሴን ሳትኩ ከሳምንታት ቡሀላ ወደራሴ ስመለስ እና ስነቃ እቤታችን ውስጥ ነኝ።
ሶስታችን አገገምን አባዬ ግን ከመሀላችን
ጎድሏል ።
በነበረበት ስኳር እና ሌላ ተጓዳኝ ህመም ምክንያት በሽታውን መቋቋም አቅቶት በሀገራችን በዚህ በሽታ ከሞቱት ሰዎች መሀል አንዱ ሆነ ።
ይህ ሁሉ በኔ ነው በኔ የደረሰ በማንም አይድረስ!!

💫ተፈፀመ💫

እስቲ ሁላችሁም ይቺን ፅሁፍ በዚች ደቂቃ እያነበባችሁ ያላችሁ #ኮረና የመጣ ጊዜ #ጥንቃቂያችሁ እንዴት ነበር#አሁንስ መልሱን ለራሳችሁ
ግን አሁንም በሽታው ምንም የተቀየረ ነገር የለም መድሃኒት አልተገኘለትም አሁንም የኛ ብቻ ሳይሆን የአለም ስጋት ነው። በየቤታችን እስኪገባ አንጠብቅ እናም ይሄ ታሪክ አንድ ሰው ያስተምራልና #Share እያደረጋቹ።

🛑አሁንም ግን🛑

#እርቀታችንን_እንጠብቅ
#ማክስ_በአግባቡ_እናድርግ
#እጃችንን_በአግባቡ_እንታጠብ
#ከቻልን_ቤት_እንቆይ #ውዶቼ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏