አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በጊዜው ታዲዬስ እሷን ከሸኘ በኃላ እረፍት አላገኘም…፡፡በምን ዓይነት መንገድ ይህቺን ልጅ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሊረዳት እንደሚችል በቀላሉ ሊገለጽለት አልቻለም፡፡ እንዲሁ በሀሳብ ሲባዝን አምሽቶ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን የቻለው፡፡ሞባይል ስልኩን አነሳና ያሰበውን ወደተግባር ለመቀየር ያግዙኛል ወዳላቸው ሶስት ሰዎች ጋር  በተከታታይ የደወለው፡፡እቅዱን ለሁሉም በዝርዝር አስረዳና በእፎይታ እራሱን ለእንቅልፍ አሳልፎ ሰጠ፡፡

በማግስቱ ማለዳ 12 ሰዓት ነበር የአቶ ቂጤሳ ቤት በሶስት ሰዎች የተንኳኳው፡፡ድምፁን ሰምታ በድንጋጤ በመበርገግ በሩን ለመክፈት መኝታዋን ለቃ በራፍ ላይ ቀድማ የተገኘችው መርጊቱ ነች፡፡ ይሄ ያልተለመደ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው?ማን ሞተ..…?‹‹ተልባ ቆይዋ እያለች..ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት››የሚለው ሀገራዊ ብሄል በአዕምሮዋ ተሰነቀረ፡፡እሷን ማን ቀደማት?የትኛው ዘመድ ነው ከእሷ ጋር ፉክክር የገጠመው…?ማነው ቀድሟት የሞተው?ምን አለ አንድ ቀን ዘግየት ብሎ ቢጠብቋት ወይም ምን አለ አንድ ቀን ፈጠን ብትል? በሰከንዶች ሽርፍራፊ ይሄን ሁሉ እያሰላሰለች በራፉን ስትከፍት ሶስት ጎልማሳ ወንዶች በራፉን ሞልተው ቆመዋል፡፡

‹‹ምንድ ነው? ምን ተፈጠረ?››

‹‹ተረጋጊ ሰላም ነው፡፡››

‹‹በዚህን ሰዓት የምን ሰላም?››

‹‹ኧረ ሰላም ነው ፤ አባትሽን ማናገር ፈልገን ነው፤ቤተክርስቲያን ሳይሄዱ ልንደርስባቸው ስለፈለግን ነው በማለዳ የመጣነው፡፡

በድንጋጤ የሚንቀጠቀጠው ሰውነቷ ሳይረጋጋ ከበራፉ ገለል አለችና እንዲገቡ ፈቀደችላቸው፡፡

‹‹ግቡ ..ይቅርታ ቤቱ ግን እንደተዝረከረከ ነው፡፡››

‹‹አረ ግድ የለም፤ይልቅ አባትሽን ቀስቅሺልን፡፡››

‹‹እሺ ››ብላ ዞር ስትል አቶ ቂጤሳ ተነስተው ከመኝታ ቤታቸው በመውጣት ሳሎን ደርሰው ነበር::

መርጊቱ ትታቸው ወደ መኝታ ቤት ገባችና ጆሮዋን ግድግዳ ላይ ለጥፋ ማዳመጡን ቀጠለች፡፡

‹‹ሰዎች ምነው በሰላም ነው? አረ ቁጭ በሉ፡፡››

በተርታ ተገትራው የነበሩት ሶስት ሰዎች በአክብሮት እጅ እንደመንሳት አሉና ‹‹የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር መቀመጥ አንችልም፡፡››

‹‹እኮ ቁጭ በሉና ትናገራላችሁ፡፡››

‹‹ኧረ ግድ የለም ቆመን ይሻላል፡፡››

‹‹እሺ ምን እግር ጣላችሁ?››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን እንድትሰጡን ልንጠይቅ ነው፡፡››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን?››አቶ ቂጤሳ ቃሉን መልሰው ደገሙት፡፡መኝታ ክፍል ሆና ስታዳምጥ የነበረችው መርጊቱ የምትሰማው ነገር የተዓምር ያህል አስደነገጣት፡፡ማን ነው
ላኪው? መቼስ እዚህ ቤት ከእኔ ሌላ ሌላ ሴት የለም፡፡የትኛው አፍቃሪዬ ነው እኔን ሳያማክር ለጋብቻ ሚስኪኑ አባቴ ጋር የላከው? በፍቅር የሚጎመዣትና ስትወጣ ስትገባ የሚለክፏትን አንድ ሶስት ወንዶች በምናቧ መጡላት፡፡ከእነሱ መካከል አንድ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች፡፡ አሳቃትም፣ አሳዘናትም፡፡ሁለቱም ስሜት እኩል ነው የተሰማት፤አንድ ላይ ተዋህዶ አንድ ላይ ተጨፍልቆ፡፡መቼስ እርጉዝ መሆኗን እያወቀች ብትፈልግ እንኳን ይሄንን የጋብቻ ጥያቄ መቀበል አትችልም፤በሀጥያት ላይ ሌላ ሀጥያት አትጭምርም፡፡ጆሮዋን የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ እንደለጠፈች ሳሎን የሚካሄደውን ትዕይንት መከታተል ቀጠለች፡፡

‹‹ለመሆኑ ልጁ ማን ነው?››አባቷ ጠየቁ፡፡

‹‹እኮ ማ ነው? የእሱንና የቤተሰቦቹንም ማንነት ንገሩኝ?››

ያው እርሷ ባያውቁም ልጃችንና ልጆት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ፤ያው አሁን መምጣታችን ነገሩን ሁሉ በእርሷ ፍቃድ እንዲሆን ስለፈለግን ነው፡፡››

‹‹ሰዎች ለምን የጠየቅኳችሁን አትመልሱም..? ልጁ ማን ነው?››ጋሽ ቂጤሳ ትግስት አጠራቸው፡፡

መርጊቱ ደግሞ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የምትሰማው ነገር ግራ አጋባት‹…እንዴ እንዲህ አይነት ውሸት አለ እንዴ?ማነው እንዴህ በድፍረት አይን ያወጣ ውሸት አሲዞ ሽማግሌዎችን የሚልክ?እሱ ተዋርዶ እነሱንም የሚያዋርድ?›› ተንደርድራ ወጥታ ለሽማግሌዎቹም ለአባቷም ምንም አይነት ፍቅረኛ እንደሌላትና ማንንም ማግባት እንደማትፈልግ ነግራቸው ነገሩን ለማሳጠርና ሁሉንም ከድካም ለመገላገል ወሰነችና ወደ ሳሎን ሳሎን ለመግባት መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ አንድ እግሯን ስታነሳ ‹‹ጌታዬ ልጁ ታዲዬስ  ነው፡፡››የሚል ድምጽ ከሽማግሌዎቹ ሰማች... ባለችበት ደንዝዛ ቆመች፡፡

‹‹ታዲዬስ….ታዲዬስ የቱ?››

‹‹ታዲዬስ መሀንዲሱ ..እዚሁ እርሶ ቤት የሚኖረው፡፡››

አቶ ቂጤሳ ከመደንገጣቸው የተነሳ በተቀመጡበት እጆቻቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ጫኑና አንገታቸውን ወደ መሬት ደፍተው ማሰላሰል ጀመሩ፡፡‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል?››አንድ ቀን እንኳን የረባ ጫወታ ሲጫወቱ፣ሲቀላለዱ ወይም ሲላፉ አጋጥሞቸው አያውቅም፡፡ሁለቱም እርስ በርስ ከመሳሳብ ይልቅ የመገፋፋት ባህሪ ነበር ዘወትር የሚያታይባቸው፡፡እንዴት ከእሷቸው በዚህን መጠን ግንኙነታቸውን መሰወር ቻሉ?

‹‹እሺ ያላችሁትን ሰምቼያለሁ፤ጉዳዩን ከልጅቷም ከዘመድ አዝማድም ጋር ልማከርበትና መልሱን ለሳምንት ልስጣችሁ፡፡››
በደመነፍስ እግሯን እየጎተተች በጓሮ በር ወጥታ ወደ ታዲዬስ ክፍል አመራች፤አንኳኳች፤ ከፈተላትና ወደ መኝታው ተመለሰ፡፡ ምንም ሳትናገር ወደውስጥ ገባችና በራፉን ዘጋችውና ወደ አልጋው በመውጣት ከውስጥ በመግባት ዝም ብላ ከጎኑ ተኛች፡፡ በአድናቆትና በዝምታ ተመለከታት፡፡ በጣም ደንግጣለች፤ በእንቅልፍ ልቧ እየተጓዘች የመጣች ትመስላለች፡፡ዝም ብሎ አይኖቾ እንባ ያመነጫሉ፡፡ከሃያ ደቂቃ የዝምታ ጊዜ በኃላ << ታፈቅረኝ ነበር እንዴ?››በማለት ያልጠበቀውን አደናጋሪ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ግራ ተጋባ‹‹ምን አልሺኝ?››

‹‹ታፈቅረኝ ነበር ወይ ?ሳትዋሽ ንገረኝ፡፡››

‹‹በፍቅር እኮ ውሸትም ይሉኝታም አይገባም፤ፈጽሞ አፍቅሬሽ አላውቅም፡፡››

ሰውነቷ በደቂቃዎች እንደበረዶ ቀዘቀዘባት‹‹ታዲያ ለምን?አስበኸዋል ግን? ሰው ያፈቀረውን እንኳን ለማግባት ሞራል ባጣበት ጊዜ አንተ የማታፈቅራትን ለዛውም እርጉዝ የሆነችን ሴት ለማግባት መስዋዕትነትን ለመክፈል የፈለከው ?ነው ወይስ የውሸት ድራማ እየተጫወትክ ነው፡፡?››

‹‹የውሸት አይደለም፤ የእውነት ነው የማገባሽ..ማለቴ እንጋባለን፤አብረን እንኖራለን፡፡…ያለምንም ግንኙነት፤ልጅሽን ወልደሽ ሁኔታዎች ከተስተካከሉ በኃላ አልተስማማንም ብለን እንፋታና አንቺም የፈለግሽውን ማለት የሚያፈቅርሽንና የምታፈቅሪውን ታገቢያለሽ፤ እኔም እንደዛው፡፡››

‹‹እኮ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ለምን ለመግባት ፈለክ?እኔ ምን አድርጌልህ አውቃለሁ? አንድ ቀን እንኳን ልብስህን ልጠብልህ ወይም ቤትህን ላፅዳልህ ብዬህ አላውቅ፡፡››
ስለተደረገልሽ ብቻ አይደለም የሆነ ነገር ማድረግ ያለብሽ፡፡ደግሞም ላንቺ ብዬ አይደለም፤ ለአባትሽ ስል ነው፡፡አንቺ እንዳልሽው በዚህ ዕድሜያቸው ጥለሻቸው ብትጠፊ እርግጠኛ ነኝ ለአንድ ወር በህይወት አይቆዩም፤በመጨረሻ ዕድሜያቸው ለእሳቸው ይሄ አይገባቸውም፡፡››


ይቀጥላል

ዛሬ በጠዋት ተከስተናል ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ እስከማታ የተወሰነ ሰው #Sebscribe ካደረገ በክፍል #31 እንገናኛለን #Shareም አይረሳ  አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12012😱5😢2