#ሆሆ
“ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ።
እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል። ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባት ሳይቀር እንደሚወሰልት እናውቃለን። መቸም የሴት ገላ ማቀፍ እንዴት እንደሚጥም የቀመሰ ያውቀዋል፤ ግን የሚያስከፍለው ዋጋ ከደስታው ጋር አይመጣጠንም፤ አንድ ጣሳ ደስታ ይሰጥህና አንድ በርሚል ጣጣ ያሸክምሃል!!
#አንድ
የሆነ ጊዜ ላይ አሜሪካ ውስጥ ባንድ ከተማ የተከሰተውን ዜና በራሴ መንገድ ስተርተው ይሄን ይመስላል፤
ሰውየው ሚስቱ ማታ ለስራ በሄደችበት ውሽማውን አምጥቶ በተቀደሰው አልጋ ላይ ይፈትጋታል፤ በፍትጊያ መሀል ኮቴ ሰምቶ ቀና ሲል ሚስቱን አያት፤ ውሽምየዋ እንደስፓይደር ውመን በመስኮት ዘልላ ነካችው፤ ባልየው ብቻውን ከሚስቱ ጋር ተፋጠጠ፤ ሚስትዮዋ ለሰይፍ ሩብ ጉዳይ የቀረው ቢላዋ ይዛለች፤ ባሉካ ለመሮጥ ተመኜ ፤ግን እግሩ ቀጤማ ሆነበት፤ በወዛደር አማርኛ እንግለፀው ከተባለ እድሩ የቡልዶዘር ጎማ ሆነበት፤ ሚስትየው ምንም አላለችም፤ አልጋው ላይ እመርር ብላ ወጣችና አገር አማን ነው ብሎ ቆሞ የሚጠብቀውን ብልቱን ጨብጣ ከስሩ መተረችው፤ ከዛ እንደ ቀይ ስር በቁንጮው አንጠልጥላው ወጣችና በቤቱ ጉዋሮ በሚገኘው ዱር ውስጥ ወርውራው ተሰወረች፤
ብዙ ሳይቆይ አምቡላንስ ስልቡን ሰውየ ይዞ ወድ ሆስፒታ መረሸ፤ ያሜሪካ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ፤ ከሲአኤ ጋር በመተባበር አካባቢውን በብረት ለበስ መኪና አጥሮ ተቆርጦ የተጣለውን ወሸላ ፍለጋ ተሰማራ፤፤ ከላይ በሂሊኮፍተር ከታች በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ሰአታትን የፈጀ አሰሳ በሁዋላ የተቆረጠው ብልት የጉንዳን መንጋ ወርሶት ተገኘ፤፤ በመጨረሻ ዶክተሮች ወደ ስልቡ ባል ቀርበው፤ “የጠፋብህ ብልት ይሄ ነውን?” ብለው’ በመስቀልኛ ጥያቄ መርምረው አረጋግጠው፤ በቀዶ ጥገና ተከሉለት፤ትንሽ ከመንሻፈፉ በቀር በድሮው ቦታ ተተከለ ፤እረ እንዴውም ከዱሮው ሳይሻል አይቀርም፤ ሚስት ተብየዋን ደስ አይበላትና ሀኪሞች ፤ እንደ ክንዱ በፈለገ ጊዜ የሚዘረጋውና የሚያጥፈው አድርገው ተከሉለት፤
#ሁለት
ይሄ ደሞ ባልንጀራየ የነገረኝ ነው፤
ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውን የተጋቡበትን አስረኛ አመት በማክበር እየተዝናኑ አመሹ፤ከዚያ ሚስትዮዋ” ቤብ፤ በፍቅራችን ላይ ቅመም የሚጨምር ነገር ላሳይህ ” አለችና ከራቫቱን ፈታችለት፤ አያ ‘ቤብ ‘ ክራቫቱን እያስፈታ ፤ ከታች ስራ እንዳይፈታ፤ ቀበቶውን ፈታ፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ዳር ቆሞ ቫይብሬት የሚያደርግ መኪና ስለተመለከተ ጠጋ ብሎ መስኮቱን አንኩዋኩዋ!
“is there any problem ? officer? “ አለ ባልየው ትንፋሹ እየተቆራረጠ።
“መኪና መሳረር ህገወጥ ስለሆነ ልቀጣችሁ ነው” አለና ፖሊሲ ባልየውን መቶ ዶላር ቀጣው፤ ሚስቲቱን ግን ሁለት መቶ ብር ቅጣት ጣለባት፤
ባልየው ትንሽ ቆይቶ ስለከነከነው ፖሊሱን ተከትሎ ደረሰበትና፤
“ቅጣቱስ ይሁን! ይበለኝ፤ የግሬን ነው ያገኘሁት፤ ግን በምን ምክንያት ነው እኔን መቶ ብር ቀጥተህ ሚስቴን ሁለት መቶ ቀጣሃት?’
ፖሊሱ እንዲህ መለሰ፤
“እ ሷ መኪና ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር ስታደርግ ያገኘሁዋት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤ ለዝያ ነው እጥፍ ያስከፈልኩዋት”😳
ባልየው በድንጋጤ ታሞ ይሄው በጎፈንድ ሚ እያስታመምነው እንገኛለን፤
🔘በውቀቱ ስዩም🔘

👍3
ጓደኛ ነው:: አብርሃም ነው፡፡
ናትናኤል ትክ ብሎ አለቃውን ተመለከታቸው፡፡ አይናቸውን ሰበሩ።
በጎንና በጎን ያንጠለጠሏቸው ክንዶቻቸው የእርሳቸው የራሳቸው እንዳልሆነ
ሁሉ ረዘሙበት፤ ተንዘላዘሉዐት:: እንደገና ቀና ብለው ሲያዩት ኣይኖቻቸው
ውስጥ የሚጋልበውን ያልተገራ ሌጣ ፍርሃት ተመለከተ። አዘነላቸው፡፡
ተፀየፋቸው፡፡
ግድ የለም፡፡ ብቻውን ወደ ጨለማው ይወጣል፡፡ ያለረዳት ብቻውን አድኖ ይይዛቸዋል፡፡ ቀድሞውንም አለቃውን ተማመኖ አልተነሳም፡፡ ቃል ገብቷል ለአብርሃም አልተዋቸውም ብሎታል፡፡ ሞት? ግድ የለውም::አብርሃም እንኳን ልጁን ትቶ ሄዷል፡፡ እሱ አንድ ነው። ብቻውን ነው፡፡ ቢቀርም ቢሄድም ማንንም አይጎዳም፡፡ርብቃ? አዎ፡፡ ግን ቢጤዋን አታጣም፡፡ ቃል ገብቷል፡፡ ከአሁን ወዲያ አይመለስም፡፡ ህግ ፊት እስኪያቀርባቸው፣ በገመድ ተንጠልጥለው ዥው ዥው ሲሉ እስኪያይ አያርፍም፡፡
“የአመት ፈቃዴን አሁን መውሰድ እችላለሁ?” አላቸው አለቃውን አልትናገሩም ጭንቅላታቸውን በ'አዎንታ ነቀነቁለት፡፡ የዘረጉለትን እጃቸውን ሳይጨብጥ ፊቱን መለሰ፡፡ የቢሮአቸውን መዝጊያ ከፍቶ ከመውጣቱ በፊት የበሩን እጀታ እንደጨበጠ ዞር ብሎ አይኖቹን አጥብቦ ተመለከታቸው::
“ዓርብ እለት አንድ መላምት ላይ እንድደርስ ጠይቀውኝ ነበር፡፡ የጠየቁኝ መላምት ላይ ደርሻለሁ…አዲስ ኣበባ ውስጥ አንድ አውሬ ገብቷል፡፡” አላቸው፡፡
ለአንድ አፍታ አገጫቸው የተንጠለጠለ መሰለው፡፡ የቢሮቸውን በር ዘግቶ ወደ ቢሮው አመራ፡፡
ወደ ቢሮው ተመልሶ ጠረጴዛው ላይ የነበረውን ወረቀት ሁሉ እየሰበሰበ በመሳቢያው ወስጥ ያጭቅ ጀመር፡፡ ብዕሮች፣ ወረቀቶች፣ መስፊያዎች፣ የፋይል ትሪዎች አንድ በአንድ እየተነሱ ከታችኛው መሳቢያ ወስጥ ታጎሩ፡፡ ጠረጴዛው እራቁቱን ሲቀር ከወንበሩ ላይ ተቀመጠና ሁለት መዳፎቹን በባዶው ጠረጴዛ ላይ ጫናቸው፡፡ ካልቨርትን አግኝ… ካልቨርትን የአብርሃም ድምፅ ደጋግሞ ተሰማው፡፡
ሙሉ ሃሣቡን አሰባስቦ አንድ ቦታ ማዋል አለበት… ባለው ኃይሉ ፈጥኖ ማስብ አለበት፡፡ ብቻውን ነው::፡ ጠላቶቹ የዋዛ አይደሉም፡፡ አብርሃም እንዳለው እንደ እሳት እራት ወደፍሙ እየተሽቀዳደመ ነው… መቃጠል የለበትም መንደድ የለበትም…መጋየት የለበትም….ሁልጊዜ . መቅደም አለበት ሁሉጊዜ ከፊት መገኘት አለበት… መበለጥ አይችልም… ሁልጊዜ
መብለጥ አለበት፡፡ አለ እንደ አብርሃም ያበቃል አለዛ ያቆማል…ሁሉም ነገር ያከትማል፡፡ ማክተሙን አያፈራም፡፡ ግን እሳቱን ማጥፋት አለበት፡፡ የንፁሃንን ነፍስ እየቀጠፈ በመሃላቸው የሚመላለሰውን አውሬ አጥምዶ መያዝ አለበት፡፡ ከየት ነው መጀመር ያለበት? ለፖሊስ ማስታወቅ? አዎ ፖሊስ ጋ ሂዶ ጉዳቸውን ማፍረጥረጥ! የስውር ክትትል ዘርግቶ አንድ በአንድ ማስለቀም፡፡ ግን…
የአብርሃም አደራ ታወሰው “ካልቨርትን አግኝ.… ካልቨርትን…” ናትናኤል መሳቢያውን ስቦ ነጭ ወረቀት አወጣ፡፡ ከደረት ኪሱ ውስጥ ብዕር፡፡ ነጩ ወረቀት ላይ ሃሣቡን ያሰፍር ጀመር፡፡
#አንድ፡ በአፍሪካ ኤምባሲዎች የሚሰሩ ወታደራዊ አታሼዎች ወደየአገሮቻ
ቸው እየተጠሩ ሄዱ ማለት የየአገሮቻቸው መንግስታት ሊገልፁላቸው፣ ሊያሳውቋቸው፣ ሊያስጠነቅቋቸው የሚገባ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡
#ሁለት፡ አንዳንድ አታሼዎች ሲመለሱ የተቀሩት በሌሎች ተተኩ ማለት…
ገሚሶቹ ለተመደቡበት ሃላፊነት ብቁ ሆነው በመገኘታቸው ሲመለሱ፣
የተቀሩት ለሃላፊነቱ ተስማሚ በሚሆኑ በሌሎች ተተኩ፡፡
#ሶስት፡ ለሥራው ብቁ ተብለው ከተመለሱ አታሼዎች መካከል በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ተገድለው ሲገኙ አንድ የገባበት ጠፋ ማለት...
የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለታቸው አለበለዚያም ብቃት
ስለጎደላቸው በአውሬው ተበሉ…. ሁለት ተወገዱ ፤አንድ ተሰወረ፡፡
#አራት፡ ሁኔታውን መከታተሉና ማጣራቱ ተገቢ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግሥት አካላትም ሆኑ ሌሎች የኣፍሪካ መንግሥታት ነገሩን መሽፋፈን መረጠ ማለት… የአፍሪካ መንግሥታት እንዳይወጣ የሚሉት ምሥጢር ተፈጠረ አለዚያም በዙሪያቸው የተተበተበው የአውሬው መረብ መነቃነቅ ከለከላቸው፡፡
#አምስት: አንዳንዶቹ የጠፋውን የላይቤርያ አታሼ ለማግኘት በግል ያደረ
ጉት ጥረት ኣደጋ ላይ ጣላቸው ማለት... የላይቤርያው አታሼ አድራሻ እንዳይገኝ የሚሉ ወገኖች ምሥጢሩ እንዳይጋለጥ ሲሉ ነፍስ እስከማጥፋት ይደፍራሉ፡፡
ናትናኤል ድንገት አንድ ጥያቄ ተደነቅረበት፡፡ አብርሃም ብቻ አልነበረም የላይቤርያውን አታሽ አድራሻ ያነፈነፈ። እንዳውም በተቃራኒው ነገር ቆስቋሹ እርሱ ራሱ ነበር፡፡ ታዲያ ለምን አብርሃምን ገደሉት… እሱንስ ለምን ተውት....
💫ይቀጥላል💫

👍2
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#ሁለት
..ቅርርቡ የነፍስ ሆኖ ነው መሰል ብዙ ውጣ ውረድ ሳይፈጠረብን ከሙና ጋ ሻይ ቡና ለመባባል በቃን። ከዛማ ማን ያቁመን፤ ከሙና ጋር አንድ ድፍን ዓመት እብድ ባለ ፍቅር ቆየን። እንደው በመተቃቀፍ፣ እንደው በመገባበዝ፣ እንደው በመተያየት፣ እንደው በመጎሻሸም እና በመደዋወል። አንድ ቀን ታዲያ፣
"ሙናዩ" አልኳት።
“ወይ" አለችኝ በዛ በሚነዝረኝ ድምጽ።
ዝም ብዬ አየኋት ገባት !! እናም እንዲህ አለችኝ፣
"አይሆንም፣ ስንጋባ ብቻ !” ቅር አለኝ። ቢሆንም ግን እንደዛው በፍቅር ማበዳቾንን ቀጠልን።
እንደውም የሆነ ጊዜ አንዱን ደንበኛ አቁማ ከእኔ ጋር በስልክ ስታወራ ክስ ቀርቦባት የደመወዟን አስር ፐርሰንት ተቀጣች። ኃላፊዋ ባለጌ ነው፤ ምሳሌው ሁሉ አያምርም። ምን አላት ?
(አረ ያሳፍራል.....)
ስሚ ሙና፣ አንድ የተላከለትን ብር ሊያወጣ ወደ ባንከ የመጣ ኢትዮጵያዊን ለግማሽ ደቂቃ ከማቆም መኝታ ቤት ምንትሱን አቁሞ የሚጠብቅ ፍቅረኛን ሙሉ ቀን ማስጠበቅ ይሻላል” ሙና በሐፍረት ቀይ ፊቷ ቀላ። አሁን እስቲ ከመቆም ጋር የሚያያዝ ስንት ምሳሌ እያለ ሙና ፊት ይሄን ብልግና መናገር ምን
ያስፈልጋል ?
እኔም ከቅጣት አላመለጥኩም። ሥራዬን ትቼ እሷ ጋር ዘና ብዬ በመዋሌ አለቃዬ አምስት ፐርሰንት
ቀጣኝ ባንኮች ከፍ አድርገው የሚቀጡት የብር ጥቅም ስለሚገባቸው መስሎኝ ነበር። ባንድ ፊቱ አስር ፐርሰንት ልቊጣ ብዬ ከሥራ እየጠፋሁ ከሙና ጋር (ሐሙስ ከሰዓት አትሰራም) ስውል አሰቃዬ ምንም ብር ሳይቀጣኝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሚል ደብዳቤ ሰጠኝ። በእርግጥ አለቃዬ ከድርጅቱ ባለቤት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሰው ነበር። “ተያይዘን እንወጣታለን ብዬ
በሆዴ ፎከርኩ። ቀድሞኝ ተባረረ። የቅጣት ደብዳቤዬን ኪሱ ውስጥ አስቀምጦት ነው መሰል ከ
በኋላ የግል ማህደሬም ላይም ይሁን ሌላ ቦታ አልተገኘም፡፡ ይሄ ስድስት ስልሳ ስድስት የሆነ ፍዳ
ሰውሮትም እንደሆነ እንጃ…
ከስድስት ወራቶች በኋላ ሙናን እንደገና ትክ ብዬ አየኋት !!
ከጋብቻ በፊት አታስበው” አለችኝ ቆጣ ብላ። ግን በቁጣዋ መሃል የሆነች ትንሽ መላላት ውልብ ስትል ያየሁ መሰለኝ። ጨለማ ቤት ውስጥ ትንሽ ብርሃን እንደምታሳልፍ ስንጥቅ ዓይነት ቀጭን የይሁንታ ሰርጥ። ቢሆንም በእንቢታዋ ተበሳጭቼ አስር ቀን ዘጋኋት። አበደች!ስልክ ብትደውል፣ ቤት ብትመጣ
በቃ ዘጋኋት። ከአስረኛው ቀን በኋላ መደወል አቆመች፤ ከቤትም ቀረች። ስትቀር እኔ ሄድኩ። ዘጋችኝ
! የምትሰራበት ሄጄ ስቆም ኮስተር አለች፣
“ኧረ ደንበኛ ክቡር ነው አትገላምጪኝ…” አልኳት። ሳቋ ፈነዳ፤ ታረቅን። መልሰን በፍቅር ማበድ ሆነ። እንኳንም ተጣላን ! ፍቅራችን ጠፍታ ከርማ እንደመጣች ውኃ ኃይሏ ጨምሮ ተንዠቀዠቀች
(ፍቅረኞች ሆይ አልፎ አልፎ ተጣሉ … ደመ መራር ሆናችሁ በዛው ተለያይታችሁ እንዳትቀሩ ጠንቀቅ ብላችሁ)
በመጨረሻ ሙናን እንዲህ አልኳት …. (ምን እንዳልኳት እኔጃ ግን ለድፍን አራት ሰዓታት አውራን
አሳመንኳት፣
“ግን ወደ አጉል ነገር ውስጥ ከገባን በኋላ ብትተወኝስ” አለች ዓይኗ ስልምልም ብሎ። ሰውነቷ ሙሉ ለሙሉ ተሸንፎ አፏ ብቻ ነበር የሞት ሽረት ትግል ላይ የነበረው። ሚስ..ኪን!
“የሁሉም ሴቶች ጥያቄ ነው”
“አትቀልድ"
"ይሄ መያዣ ነው እንዴ ? ከተውኩሽ የአያቶቼ አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋኝ ሙናዬ …" ብዬ
ማልኩ። እነዚህ አያቶቻችን ስንቱን ይውጉ ? ደርቡሽን ተወግተውም ፣ ጣሊያንን ወግተው፣ ሱማሌን
ወግተው አሁን ደግሞ..
"እሺ በቃ አትነዝንዘኝ” አለችኝ። አትነዝንዘኝ የምትለው ቃል "እሺ” የምትለዋን ሽንፈት የምትደግፍ
ከዘራ መሆኗ ነው! እሺ የኔ ቆንጆ እናደርገዋለን፣ በደስታ፣ በፍቅር፣ ያውም በሙሉ ልቤ ... ወደፊት”
ቢባል ምን አለበት ? መሆኑ ላደቀር የምን በዘወርዋራው መናገር ነው …. ሃሃሃሃ ኡፍፍፍፍ ብዩ በደስታ እቅፍ።
እንዴዴዴ ! እንትኑ አሁን ነው እንዴ ?” ብላ ሁለታችንም በሳ.…ቅ። ያለነው እኮ የሆነ ካፌ ውስጥ
ነበር። እና ቀን ተቆረጠ። አርብ ማታ እኔ ቤት ትመጣና ታድራለች፣ (በታድራለች ውስጥ ስንት ጉድ
አለ) ቅዳሜ ትውላለች፣ (በትውላለች ውስጥ ቤቴ የጦርነት ዋዜማ ሲመስል ታየኝ -ጦርነት ያለበት ገነት) ከዛ ታድራለች .… እሁድ ወደ ቤቷ። እንዴት ነው የምለያት” ብዬ ካሁኑ ናፈቅኩ።
አርብ ማታ ቤቴን አበባ አስመስዬ ለራሴም ሌላ ሰው ቤት የሄድኩ እስኪመስለኝ አሳምሬ ጠበቅኳት
እየተንቆራጠጥኩ። ኮቴ ሰማሁ፣ የሴት ጫማ ተረከዝ ቋ ቋ ቋ ሙና ናት፣ መጣች !! በሩ ተንኳኳ …
ኳኳኳኳኳኳኳ ኳኳኳኳኳ ኳኳኳኳኳ …. ግማሹ ኳኳታ ልቤ ሲመታ መሆን አለበት።
ሙና በሬ ላይ ቆማለች። በሩን ስከፍት ረዥም ቀይ ቀሚስ በባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ ለብሳ በረዥም ቁመቷ ከላይ ወደታች የሚፈስ ፏፏቴ መስላ (እኔጃ ለምን እንደሆነ እንደዛ መሰለችኝ። አንዳንዴ የሆነ ቅፅበት አለ እዛው ፊታችን ቆሞ ትዝታ የሚመስለን) አየችኝ፣ ተያየን፣ ገባች። አንደወትሮው አልተሳሳምንም፡ አልተቃለድንም፣ አልተሳሳቅንም … ፈርተናል። በጣም ፈርተናል። ተፈራርተናል።በሩን ይዤ እንድታልፍ ወደ ጎን ዘወር ስልላት እንደቆምኩ ታክካኝ አለፈች። ለስላሳ ጠረኗ አፍንጫዬን
አወደው። ጫማዋን እንጀቆመች ስታወልቅ ገድገድ አለች፡ ሁለቱንም ጫማዎቿን አውልቃ ባዶ እግሯ ስትቆም የቀሚሷ ጫፍ ምንጣፉን ነካው።
ቀስ ብላ ገባች። ተከትሏት ወላፈን ገባ። እንደ ኤርታሌ ዓይነት ነገር ቤቴ ውስጥ ተፈጠረ። እቃዎቹ
ሁሉ እየቀለጡ የፈሰሱ መሰለኝ። ሙና ዝም ብላ ተቀመጠች። ሄጄ አጠገቧ ስቀመጥ ሰወነቷ ሽምቅቅ አለ … ፈርተናል! “ፈራን፣ ፍቅር ፈራን” አለ ባለቅኔው።
"እሺ እንዴት ነበር ውሎ" አልኳት ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ። ድምፄ ለዛ ቢስ ሆነብኝ። እጄን ጣል አደረግኩት። ዝም አለች። ሌላኛውን እጄን ትከሻዋ ላይ … ዝም ! ሦስተኛውን እጄን የሆነ ነገሯ ላይ፣ አራተኛውን እጄን ፀጉሯ ላይ፣ አምስተኛውን እጄን …. እጅ በእጅ ሆንኩ። ሁሉንም ነገር ባንዴ
መንካት ስለፈለግኩ ፈጣሪ ይውጣልህ ብሎ ብዙ እጅ ያበቀለብኝ እስከሚመስለኝ። እና ተነስቼ ሳብ አደረግኳት፣ ተከተለችኝ። ድክም ያላት ትመስል ነበር። በሕይወት ውስጥ አለ የሆነ ጊዜ፣ አዕምሯችንን ትተን በወደድነው ሰው አዕምሮ የምንመራበት። ሙና ዝም ብላ እንደማደርጋት ሆነች::
ወደ መኝታ ቤታችን...
ምን እንደሆነ ባይገባኝም አንድ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል። ማለት እንዲህ አልነበረም መጀመርያ ይሰማኝ የነበረው፡፡ ፍላጎቴን የሆነ የማልገልፀው ዓይነት ቅዝቃዜ ወርሮታል። ተሳሳምን ሙና በስሜት አበደች። ደነገጥኩ። እንዲህ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ትመጣለች ብዬ በምን አባቴ ጠርጥሬ ልብሷን ከሰውነቷ ላይ በትብብር እየገፈፍን ጣልነው፣ የእኔንም ልብስ ሽቅብና ቁልቁል ገፈፍን እንደፈጠረን እርቃናችንን ቆምን። በየት በኩል እንደገባን እንጃ ኣንሶላው ወስጥ ተገኘን።
የሆነ ነገር ጎድሏል። አንድ የሆነ ነገር ጎድሏል። ሙና እየቃተተች፣ እንደምትወደኝእየነገረችኝ፣ ሰውነቷ እሳት ሆኖ እኔ ምን እንደነካኝ እኔጃ የሚያስደነግጥ ፍጥነት ቅዝቅዝ አልኩ። ቅዝቅዝ ! የሞትኩ መስሎኝ ነበር። ሙና ለብቻዋ የሆነ ነገር የምትሰራ መስሎ ተሰማኝ። በቃ ለታዛቢነት የተጠራሁ ይመስል የምታደርገውን ግራ በመጋባት ማየት ሆነ ስራዬ። እንዴት የሚያሳቅቅ ነገር ነው ? ምንድን

👍20❤2
#አልሐምዱሉላሒ_ደህና_ናት
፡
፡
#ሁለት(መጨረሻ)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...በተደጋጋሚ ስለአፍራህ ከመስማቴ ብዛት አፍራህን እኔም ላፈቅራት ምንም አልቀረኝም። እውነቱን ለመናገር የዛን ጊዜ ክላስ ውስጥ ከነበርነው ሠላሳ ምናምን ወንዶች አስራ ምናምኑ በአፍራህ ፍቅር የተለከፈ ነበር፤ ሒሳብ አስተማሪያችን ጭምር። መቼም ሒሳብ አስተማሪያችን እያካፈሉም፣ እየደመሩም፣ እየቀነሱም፣ እያባዙም ሳያስቧት አይቀሩም፡፡ አንዳንዴ ቡዝዝ ብለው መላጣቸው ላይ ላብ ፊጭ ፊጭ እያለ ሲመለከቷት ያሳዝኑኝ ነበር። “ወይኔ ምነው ያችን አመዳም አግብቼ አምስት ልጅ
ባልወለድኩ ኖሮ" እያሉ በሚስታቸው የሚቆጩ ነው የሚመስለኝ።
እኔና አል አሚን ወደ ቤት ስንሄድ አፍራህና ጓደኞቿን ከሩቅ በቀስታ ተከትለን ነው። አንድ ቀን
ታዲያ አፍራህ ማስቲካ ገዝታ (ባናና ማስቲካ) ልጣጩን ጥላው ወደ ጓደኞቿ ተቀላቀለች። እኛ
የማስቲካውን ልጣጭ የጣለችበት ቦታ ስንደርስ አል አሚን ተስገብግቦ ቢጫውን የማስቲካ መሸፈኛ ወረቀት አነሳው፡፡ የሆነ ከባድ ቅርስ ወድቆ ያገኘ ነበር የሚመስለው። ለራሴ ማመን እስከሚያቅተኝ ለሁለት ዓመት አካባቢ የማስቲካውን ልጣጭ በክብር፣ በታላቅ ክብር አስቀምጦት ነበር። ለእርሱ ብቻ
በሚታይ ስውር ቀለም የአፍራህ ምስል የታተመበት እሰኪመስለኝ።
አል አሚን እንዲሁ ሲሰቃይ ክረምት ገባ። እፍራህን ለሁለት ወራት መለየት ለአል አሚን የቁም ሞት ነበር። ሱስ ሆናበታለች፡፡ አፍራህ ዓለሙን ሁላ አጨላልማ በነፍሱ ሰማይ ብቻዋን የደመቀች ኮከብ ነበረች። ቢሆንም እንደለመደው በዝናብ ሳይቀር ከረንቦላ ቤት እየሄደ እዛው ቆሞ አፍራህን ስትወጣ ለማየት ይጣጣር ነበር። ለአስራ አምስት ቀናት ጠብቆ ኣላያትም፤ ሊያብድ ሆነ።
ታዲያ በመሀሉ በጣም የምንወዳቸው ሼህ ያሲን የሚባሉ ሰውዬ መንገድ ላይ አገኙኝ። የአል አሚን ቁርአን አስቀሪ ናቸው።
“አቡቹ ደህና ዋልክ?”
“ደህና ዋሉ ሸሃችን "
"አልሃምዱሊላሂ…. እስቲ ወዲህ የማወጋህ ጕዳይ አለኝ” አሉና ከመንገዱ ወደ ዳር ወስደው እንዲህ አሉኝ፣ “ ጓደኛህ አል አሚን ምን ነክቶት ነው ልጄ? ከቀልቡም አይደለም፤ ቁርአን ቤትም መምጣት ካቆመ ስንት ጊዜው! …ተበላሽቷል ይሄ ልጅ ጭራሽ ዛሬ እዛ ቁማር የሚጫወቱበት ቤት ቁሞ አየሁት። ጓደኛው ነህ፤ አትመክረውም? ኧረ ቀልቡ ደረቀ…።” ብለው ነገሩኝ። በአል አሚን አዘንኩ።ማን ያውቃል የልጁን ጉዳት። የዋልንበት ቦታ ሁሉ ያለን እየመሰላቸው ስንቶች በዋልንበት ፈረጁኝ…
አል አሚን አንድ ቀን እየተጣደፈ ቤት መጣ። ከመቸኮሉ ብዛት ድመታችንን በሩ ሥር እንደተኛት
ጀራቷን ረግጦ ካቅሟ በላይ እስጮኻት፤
"አቡቹ…! አቡቹ! አይገርምም የነአፍራህ ቤት ለካ በሩ እኔ ከምቆምበት በኩል አይደለም፤ …
ከኋላ በኩል በዘይት ቤቱ ጋ ነው፤ በዛ በኩል ነው የምትወጣው… ሂሂሂ ተሸውጄ " አለኝ፤ ሲያወራ
በደስታ ፊቱ በርቶ ነበር። “…ዛሬ ባጋጣሚ በታች በኩል ስሄድ ከእናቷ ጋር ሆና ፌ…ት ለፊት፣
እንደዚህና እንደዛ …በቃ ተያየን፣ ወ…ላሂ አቡቹ ግጥምጥም ነው ያልነው፣ አኡዙቢላሂ …ልሮጥ ነበር ሂሂሂሂሂሂሂ አለና ፍርፍር ብሎ ሳቀ። ድንገት ተነስቶ ቆመና ደግሞ “እስኪ እየኝ፣ እንዲህ ሆኜ እኮ ነው ያየችኝ፤ እደብራለሁ እንዴ …?” አለኝ። ሁለት እጆቹን ግራና ቀኝ እንደ ከንፍ ዘርግቶ አንዴ እኔን
እንዴ ራሱን ቁልቁል እየተመለከተ። አሳዘነኝ። የአፍራህን ቅንጡ አለባበስ እና የአላሚንን የተንሻፈፈ
ሸራ ጫማ፣ ያረጀች እና የወየበች ቪ ቅርፅ ቲሸርት በውጤ እያሰብኩ፣
ኧረ እይደብርም!" አልኩት።
እንደ ሕፃን እየተፍነከነከ መጥቶ አጠገቤ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ። “…አይገርምም ከእናቷ ጋር ሆና
በቃ እንደዚህ እና እንደዛ ፊት ለፊት…! እንዴት አምሮባታል አቡቹ ብታያት…ወላሂ ያች የምታውቃት
አፍራህ አይደለችም! በቃ እንደዚህና እንደዛ እኮ ነው…" እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ፤ ዓይኖቹ የደስታ! የሐዘን፣ የሐፍረት፣ የምኞት ብርሃን ይረጫሉ። ፊቱ ላይ ደስታ እንደረበበት ልሸኘው ውጣሁ።
ልንለያይ ስንል፣ “..አቡቹ ሁለት ብር አለህ እንዴ?” አለኝ እየፈራ። አል አሚን እንኳን ደፍሮ ብር
መጠየቅ፣ ያዋሰውን ደብተሩን እንኳን መልሱልኝ ለማለት የሚፈራ ልጅ ነበር፡፡ ብር ስላልያዝኩ…ወደ
ቤት ተመልሰን ከእናቴ ተቀብዬ ሰጠሁት። ደስ ብሎት ሄደ።
ቆይቼ ስሰማ በአዲሱ የእነአፍራህ በር በኩል አንድ ሻይ ቤት አለች! ሻይ ሃምሳ ሳንቲም ነው!
በሰጠሁት ብር ሻይ እያዘዘ ቁጭ ብሎ አፍራሀን ሲጠብቅ ነበር፤ አራቱንም ቀን ግን አላያትም።
እናም ከረንቦላ ቤት አካባቢ ያገኘውን የእነእፍራህን ሰፈር ልጅ ጠይቆ አፍራህ አዲስ ኣበባ ለእረፍት እንደሄደችና ትምሕርት ሲያልቅ እንደምትመጣ አረዳው፡ ቅስሙ ተሰበረ። ቢሆንም እነአፍራህ ሰፈር መሄድ አላቆመም። በየቀኑ ያንን ሰፈር ሳይረግጥ አይውልም። ሸርፍ ተራ ትርምሱ፣ ግርግሩ፣ ጫት
ተራው፣ መኪናው፣ የደሴ አንደኛ “ቀውጢ" ሰፈር… ይሄ ሁሉ ግርግር ግን ከአፍራህ አይበልጥም። አፍራህ ብቻዋን የአንድ ትምሕርት ቤት ወንዶች ነፍስ የተደረደረባት ገበያ አይደለች እንዴ ።
“እሷ ከሌለች ለምን ትሄዳለህ?” እለዋለሁ፤
“እኔንጃ” ነው መልሱ፤ ያሳዝነኛል !!
አንድቀን ደግሞ ቤት መጣና አቡቹ ሥራ ልጀምር ነው" አለኝ፣ በደስታ ፍንክንክ ብሎ።
“የምን ሥራ አልኩት፤
“አይሱዙ መኪና ላይ ረዳትነት”
“ትቀልዳለህ !?"
“ወላሂ እውነቴን ነው። ካአዲስ አበባ ደሴ የሚምሳለስ አይሱዙ ላይ ሥራ ልጀምር ነው። እናቴንም
ነግሬያት ኣሳምኛታለሁ። መኪናው ቅዳሜ ወደ አዲስ አበባ ይወጣል። አብሬው እሄዳለሁ። ብታይ ቀላል እኮ ነው ሥራው።” ፊቱ ላይ ተስፋ ይንቀለቀላል። በቀጫጭን እጆቹ ሸራ ሲጎትት፡ የጎማ ብሎን ሲያጠብቅ አሰብኩት፤ አል አሚን ትንታጉ ተማሪ። ይሄ ፍቅር የሚሉት ነገር ግን ምናይነት ልክፍት ነው
በእግዚእብሔር!!
አልአሚን ገና በመጀመሪያ ጉዞው ከመኪና ላይ ሲወርድ ወድቆ ግንባሩ ተፈንከቶና ከንዱ ተላልጦ
መጣ። ሰው ሁሉ እንኳን አላህ አተረፈህ!” እያለ አዘነለት። እንዲህ ካልተላላጡና ካልተፈነከቱ የልብን
ስብራት፣ የመንፈስን መድቀቅ ዓይቶ የሚያስታምም የለም መቼም። እንዲህ አለኝ፣ አሮጌ ፍራሹ ላይ እንደተኛ “አንተ … አፍራህ ያንን ሁሉ መንገድ አልፋ ነው አዲስ አበባ የሄደችው…? እነዛን ተራራዎች ዓይታቸዋለች…፣ ያንን ገደል እያየች ፈርታለች ፣ ደብረሲና ምሳ በልታለች፤ ቆሎም ገዝታ ሊሆን ይችላል….እዛ ጨለማ ዋሻ ውስጥ ስትገባ በፍርሃት ተንቀጥቃጣም ይሆናልኮ። ኡፍፍፍፍ አንጀቴን
በላው፡፡ ከላይ እንደእቃ ተጭኖ አፍራህ ባረፈችበት መንገድ በማለፉ ምናባዊ ዳናዋን ተከትሎ ሲነጉድ ታየኝ። ሚስኪን አልአሚን !
ቀስ በቀስ አልአሚን ነገሮች ሁሉ ተቀላቀሉበት። አንድ ቀን ትምሕርት ቤት ሄደና ጭርር ያለው በር ላይ ያገኛቸውን የትምሕርት ቤታችን ጥበቃ ጋሽ ደምሴን፣ “ትምሕርት መቼ ነው የሚጀመረው?” አላቸው፤
“ምን አውቄ ብለህ ልጄ” አሉት። ቀጠል አድረገውም…የኔ ልጅ ኳስ ሰራገጥ ይውላል፣ አንተ ትምርት
ናፍቆህ.የወለዱህ ኣባትና እናት ምንኛ ይኮሩ!! እሰይ!! እሰይ!”
ትቷቸው ወደ ቤት ተመለሰ፤ በቃ መረጋጋት አቃተው ተወዛገበ።
8ኛ ክፍል በተመሳሳይ ለአፍራህ ፍቅሩን ሳይነግራት በየቀኑ እያያት በዓይኖቹ ተስፋ ነፍሱን አፋፍቶ
ኖረ። አንድ ቀን ለአፍራህ ስጦታ ልሰጣት አሰብኩ" አለኝ። ገረመኝ ! ወይኔ ፍቅር ጉድለት አይገባው፣ ድህነት እያልኩ ሳስብ አልአሚን አንድ የሃምሳ ብርና ሦስት አስር አስር ብሮች ከኪሱ አውጥቶ አሳየኝ።
“ከየት አመጣኸው?"

👍28👎1
#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ #ትስፋው
፡
፡
#ሁለት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
....የዜድ ፊት ቲማቲም እንደመሰለ እንኳን አልታዘበም አውቃለሁ ስሜ በክፉ ሲነሳ ፊቷ እንዴት እንደሚቀየር እንግዲህ ይሄ ልጅ…ከባለቤቷ የበለጠ አውቃለሁ ብሎ ቡዳ ሲሆን ምን ይባላል? እህታችንን ሲል “ማን ቢወልድ ማን” ትላለች ዙቤይዳ በሆዷ፤ እኔና ዜድ ነቢል ዙቤይዳን እንደሚከጅላት ጠንቅቀን እናውቃለን። እንደውም አንዴ አፍ አውጥቶ ጠይቋታል። አሁን አፉን ሞልቶ እህታችን ሲል አያፍርም ?! እንደውም እዛ ሱቅ ተኮራምቼ ስውል አንዳንዴ ዙቤይዳ እጄን ይዛ ወስዳ “ሻይ ቡና እንበል” ካላለችኝ እግሬን አላነሳም። እንኳን ጫት ቤት ልዞር። እንደው አንዳንዱ ሰው እህ…ብለው ከሰሙት የሚናገረውን አያውቀውም። የነቢል ዘመቻ እንኳን ያው “የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል”
እንደሚሉት ነው ።
ዙቤይዳን ያወቅኳት እዚህ ቄራ አካባቢ ከቡልጋሪያ ከፍ ብሎ የከባድ መኪና እቃ መለዋወጫ ሱቅ ውስጥ በሻጭነት ተቀጥሬ ስሠራ ነበር። ሱቃቸው ከምሠራበት ሱቅ ጎን ሲሆን ሱቆቻችን የድንጋይ ቤቶች ስለነበሩ ይቀዘቅዛሉ። ጧት ወንበር ውጭጋ እናወጣና ፀሐይ እንሞቃለን። እነዙቤይዳ ሱቅ
ስር ላይ የአንድ ትልቅ ሕንፃ ጥላ ስለሚያርፍ ፀሐይ ፍለጋ እኔ ወደምሠራበት ሱቅ በር ጠጋ ብላ
ነበር የምትቀመጠው። እኔም ወንበር አወጣላትና ጎን ለጎን ተቀምጠን ፀሐያችንን እየኮመኮምን እናወራለን…።
አንዳንዴ እህቷም አብራን ትኖራለች። ብዙ ጊዜ ግን ብቻችንን ነን። ይሄ ቅርርብ ስቦ ስቦ ስጋችን
ፀሐይ፣ ነፍሶቻችንም ፍቅር ይሞቁ ጀመረ። አንድ ቀን ዙቤይዳ ከመሬት ተነስታ፣ “ይሄ ፀሐይ ሱስ
ሆነብኝ” አለችኝ ያዝ እንግዲህ ! በኋላ ፍቅራችን ከለየለት በኋላ “አንተን ማየት ሱስ ሆነብኝ ማለቴ
ነበር፤ የማይገባህ ሆንክ እንጂ” ብላ አስቃኛለች። እሷም ስለማይገባት እንጂ እኔም ሱስ ሆናብኝ ነበር። ዙቤይዳ ከቤት ወጥታ የማታውቅ ውብ ልጅ ነበረች። ፀሐይ ሲነካት ታብረቀርቃለች፣ ቆዳዋ ወርቃማ ነው። አላፊ አግዳሚው ባፍጢሙ እስኪደፋ አንገቱን ጠምዝዞ የሚመለከታት ልጅ ነበረች።
እንደው ስለወደድኳት ሳይሆን ዙቤይዳ ከቤተሰቦቿ አንደኛ ቆንጆ ነበረች መመኪያቸው የቤተሰቡ
መመኪያ !ታዲያ ይችን ልጅ ይዤ ነው ሁልጊዜ ሱቃችንን ዘጋግተን በአፍሪካ ኅብረት መንገድ ክንዴን
ተደግፋ በፍቅር የምንንሳፈፈው አቤት ያንን መንገድ ስንወደው!
አባቷ ጋሽ ጀማል ታዲያ መከረውም ዘክረውም በዘመድ አዝማድ ልጃቸውን አስመክረውም አልሆን ሲላቸው ረጋ ብለው ሲያስቡ ቆዩና፣
“ዙቤይዳ!” አሏትልጃቸውን።
“አቤት አባባ!”
“እስቲ ልጁን ጥሪውና እንየው” አሉ። ወንድምና እህቶቿ ተበሳጩ።
“እንዴት አንድ ዱርዬ ቤት ድረስ ይምጣና ላናግር ይላሉ አባባ” አሏቸው።
“እንኳን ፊት ሰጥተውት ልጁ አይናውጣ ነገር ነው አባባ” አለች የዙቤይዳ እህት… ሚሊየን ጊዜ ስለ አይናፋርነቴ ነግራኛለች በፊት ፀሐይ ስንሞቅ ዛሬ ተጣላንና ግዴለም)።
“ቢሆንስ እንየው ማለት ምን ጉዳት አለው? እኔም እናታችሁም እናናግረውና የምንወስነውን
እንወስናለን” ብለው ቆጣ አሉ። ልጆቹም ደንገጥ ብለው ዝም አሉ
“ግን አባባ እስከዛሬ እንዴት አላወቁትም፣ቄራ ሱቃችን ጎን ተቀጥሮ የሚሠራው ልጅ እኮ ነው።” አለች ዘምዘም የምትባለው ሁለተኛዋ ልጅ።
ጋሽ ጀማል አሰቡ አሰቡና፣ “አሃ ይሄ ቀይ መኪና የሚይዘው ልጅነው ?” ብለው ጠየቁ (ቀይ መኪና የሚይዘው አሠሪዬ ነው)።
“ኧረ አባባ እሱ እንኳን መኪና ሊይዝ ለእግሩም ደህና ጫማ የለውም፤ የሆነ አንጀት የራቀው ላንጌሳ ነገር ነው” አለች ዘሐራ።
“አንች እንዲህ አይባልም… ዱኒያ ተአላህ ዘንዳ ነው። የምን ትዕቢት ነው” አሉ የዙቤይዳ እናት በቁጣ።
ዘሐራ ደንግጣ ዝም አለች። ይች ጉረኛ! የዘሐራ ጉራ ልክ የለውም፣ ትዕቢቷም በጓደኞቿ ሁሉ የታወቀ
ነው። ስለ ሁሉም ነገር ከእኔ በላይ አዋቂ የለም የምትል ልጅ ነበረች። እኔንማ ጥምድ አድርጋ ነው
የያዘችኝ። ሴት ልጅ ጉረኛ ስትሆን እንዴት ያስጠላል?! ባይሆን ኩሩ ስትሆን ይሻላል።
የሆነ ሆኖ የዙቤይዳ አባት ሊያናግሩኝ ወስነው እንድጠራ አዘዙ፡፡ ዙቤይዳም ጠራችኝ። አባቷ ሊያምኑ መንገድ መጀመራቸውን ገምታ ነበር። ታዲያ ዜድዬ ጋር ተገናኝተን ወደ ቤታቸው መንገድ ስንጀምር ቀድማ መከረችኝ፣
“አብርሽ!”
“ወይ ዬዜድ!”
“አይዞህ...ቤት ስትገባ ጫማህን አውልቅ እሺ ?”
"እሺ”
“ደግሞ ማስቲካ በአፍህ እንዳትይዝ፤ አባባ ማስቲካ የሚያላምጥ ሰው አይወዱም።”
"እሺ” ብዬ በአፌ የያዝኩትን ማስቲካ ልተፋው ስል፣
“ማን አሁን አለህ? ቤት ስትደርስ ነው ያልኩህ” አለችና ሳቀች። እኔ አልሳቅኩም፣ተጨናንቄ ነበር።
ማስቲካዬን ወደ አፌ መልሼ ምክሯን ማድመጥ ጀመርኩ።
“ደግሞ አብርሽዬ ብዙ እንዳታወራ፣ በእኔ ለምደህ እንዳትቀባጥር የኔ ማር" ፈገግ አለች፤ “እ…ሌላው ነገር…አዎ ነገር ለማለሳለስ ብለህ አንድም ነገር እንዳትዋሽ። የሆነውን የተሰማህን ነገር ብቻ ሃቋን ተናገር።”
"ሃቋን ”
“አዎ ሃቋን ! በተረፈ በጣም ስለምኮራብህና ምንም ነገር ቢፈጠር እኔ ስለማፈቅርህ እንዳትፈራ የኔ ቆንጆ፤ እሺ አብርሽዬ…”
“እሺ…”
"ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ... ውይ እሺ እሺ ስትል አሳዘንከኝኮ የኔ ሚስኪን "ሂሂሂሂ” አለችና ጉንጬን
ግጥም አድርጋ ሳመችኝ። በዙቤይዳ ሙጥቅላ መኪና ወደ ቤታቸው መንገድ ጀመርን። በቃ ልቤን በድፍረት ሞልታ ሳሎናቸው ውስጥ ወደ ቆመው ችሎት ላከችኝ። ቤታቸው ስደርስ ተንሸራታቹ በር እንደባቡር እየተጎተተ ተከፈተ። የመቃብሬ ድንጋይ የተከፈተ ነበር የመሰለኝ ልቤ ይፈራገጣል።
ዙቤይዳ ወደ ግቢው ከመግባታችን በፊት በእጇ እጄን ጭምቅ አድርጋ ለቀቀችኝ። የዜድ እጅ አፍ ሆኖ ተናገረ፣ የእኔ እጅ ጆሮ ሆኖ አደመጠው።
የተናገረችው ሃቅ ነበር !!
ወደ ግቢው ስገባ ደነገጥኩ። እንዲህ ያምራል ብዬ አላሰብኩም ነበር ጀነት ! እንዴት ደስ ይላል።
እዚህ ግቢ አድጎ እንዴት ሰላማዊ አለመሆን ይቻላል። ዘሐራ ሌላ ቦታ መሆን አለበት ያደገችው እች
ነገረኛ። አሁን ትኖር ይሆን ?
የሳሎኑ በር ሲከፈት አስፈሪው ምንጣፍ አዳራሽ ከሚያክል በር ጋር ጠበቀኝ። እናትና አባቷ በግራ
በኩል ከዛም በፊት ከዛም በኋላ አይቼው የማላውቀው አረቢያን መጅሊስላይ ተቀምጠዋል። አረቢያን መጅሊስ ማለት እግር የሌለው ሶፋ ማለት ነው።
ጫማዬን በር ላይ ላወልቅ ሳጎነብስ በአፍጢሜ ልደፋ ነበር። ፍርሐት ከኋላ ገፍቶኝ ሳይሆን አይቀርም..ሳላስነቃ ራሴን ተቆጣጥሬ ጫማዬን አወለቅኩ። ለዚሁ ፕሮግራም የገዛሁት ነጭ ካልሲ እንደበረዶ።ተንቦገቦገ ኡፍፍፍፍፍፍ ፈርቼ ነበር፣በጣም ፈርቼ ነበር!
በዙቤይዳ መሪነት ኳስ ሜዳ በሚያክለው ምቹ ምንጣፍ ላይ እየተራመድኩ አባትና እናቷፊት ቆምኩ። (የቁርጥ ገን ) በፈገግታ ተቀበሉኝ። በአክብሮት ጎንበስ ብዬ በሁለት እጄ አባቷን ጨበጥኳቸው::
እሳቸው ግን የቀኝ እጄን መዳፍ ወደ ራሳቸው ሳብ አድርገው አይበሉባዬን ሳሙኝና እንደተጨባበጥን የእሳቸውን መልሰው ወደኔ አስጠጉ፣ እጃቸውን ሳምኩ፣ መልሰው ሳሙኝ፣ መልሼ ሳምኳቸው

👍24❤1🔥1😁1
#ድንቡጮ_ለምን_ለምን_ሞተ
፡
፡
#ሁለት(መጨረሻ)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...“እደጉ ልጆቸ እድግ በሉ !! ወርቅ ይፍሶስቦት ሟለት ትልቅ በረከት ነውኮ…፤ ከወርቅ በሏይ ሙን አለ…? ቡዙ ተብዛዙ ቁም ነገር ያቡቋችሁ..! አቡነ አረጋዊ ጭንቅላታቹሁን ይከፋፍተውና ትሙሩቱ ይግባዓባችሁ…” ብለው ይመርቁናል። አፋቸው ይጣፍጣል። እማማ ንግሥት ኤርትራዊት ናቸው። ታዲያ በአማርኛ ሲያወሩ አንደበታቸው አይጠገብም። ጥርስ የማያስከድኑ ተጨዋች ናቸው። ሲቆጡም በዚያው ልክ ነው ይባላል ሲቆጡ አይተናቸው አናውቅም እንጂ…!! አባባ መክብብ ታዲያ ሚስታቸውን ሲወዷቸው ልክ የላቸውም። አንድ ቀን እትየ ንግሥት ታመው (የደም ግፊት የሚባል ነገር ነው አሉ) አንቡላንስ ተጠርቶ ጎረቤቱ ሁሉ ሲሯሯጥ አባባ መክብብ እንደ ሕፃን ልጅ በሁለት እጆቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ እና ሲጮሁ አይቻቸዋለሁ ! ሰው ሁሉ እያባበላቸው!
“እትየ ንግሥት ... እናቴ፣ እህቴ፣ ጓደኛዬ ሜዳ ላይ እኔን ጥለሽ ..” እያሉ…
ባልና ሚስቱ አንዲት ልጅ አለቻቸው፤ ህደጋ የምትባል፣ ፈረንጅ አግብታ ውጭ አገር የምትኖር።በየሦስት ዓመቱ እናትና አባቷን ልትጠይቅ ስትመጣ ከታች ሰፈር ጀምሮ እስከላይ ሰፈር ድረስ
ሁሉም ቤት እየገባች ጎረቤቱን ሁሉ ትስምና ሃምሳ ሃምሳ ብር ትሰጣለች። ለትልልቅ ሰዎች ብቻ
ነው የምትሰጠው። ከእኛ መካከል የሃምሳ ብር እጣ የሚወደቅለት ፈንታው ድንቡጮ ብቻ ነበር።
የፈንታው እናት ሚስኪን ናት፤ በሽተኛ ስለሆነች ከአልጋ ላይ አትነሳም። ፈንታው አባባ መክብብ
ግሮሰሪ በረንዳ ሥር ጫማ እየጠረገ እና እየተላላከ ነው እናቱን የሚያስታምመው። አባቱ በደርግ ጊዜ ዘምቶ ይሙት ይትረፍ ሳይታወቅ በዛው ቀልጦ ቀርቷል። ያው የህደጋ ሃምሳ ብር ፈንታው ድንቡጮን የሚያካትተው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም !
አንድ ቀን ታዲያ የስፖርት ትጥቅ ለመግዛት ከመንደርተኛው ሳንቲም እንለምናለን። በአጋጣሚ ፊት
ለፊታችን ህደጋ አሻንጉሊት የመሰለ ልጇን በደረቷ አቅፋ ስትመጣ ተገጣጠምን። ሌላውን መንደርተኛ ሳንቲም ውለድ እያልን ምናስቆም እኛ፣ ህደጋን ለምን እንደፈራናት እንጃ፤ ብቻ ገለል ብለን አሳለፍናት።
በቀጣዩ ቀን ታዲያ አስጠራችንና እንኳን በእውናችን በህልማችንም አስበነው የማናውቀውን የስፖርት
ትጥቅ ከነኳሱ ገዛችልን።
አቤ…ት! እንዴት እንደተደሰትን…! ለስንት ዓመት ታሪክ ሆኖ በመንደራችን ተወራ ! “ኳሱ የት
ይቀመጥ” በሚል በመካከላችን ከባድ ክርክር ተደርጎ እኔጋ እንዲቀመጥ ተወሰነ። የተሰማኝ ደስታ ወደር አልነበረውም። ግን ምን ያደርጋል አንድ ቀን ያ ለብዙ ሕፃናት ህልም የነበረ ኳስ ምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ጠፋ። የጠፋው ከእኛ ቤት ስለነበር በቡድኑ አባላት ዘንድ ክፉኛ አስተችቶኛል።ለረዥም ጊዜ ያኮረፉኝ የሰፈር ልጆችም ነበሩ። በእግር በፈረስ በሰፈራችን ስርቻ ሁሉ ኳሱን ፈልገን ስናጣው በቃ ወደ ጨርቅ ኳሳችን ተመለስን። አሁን ካደግን በኋላ ሳይቀር የኳሱ ነገር ሲነሳ እወቀሳለሁ።
እንደውም አሁን ካደግን በኋላ እድሜያችን ሃያዎቹ ውስጥ ገብቶ ተፈሪ የሚባለው የሰፈራችን ልጅ
(አሁን አዉስትራሊያ የሚኖር) ኢ-ሜይል ሲያደርግልኝ ስለ ኳሱ ጉዳይ አንስቶ እንዲህ ብሎኛል፣
“አቡቹ እዚህ የፈረንጅ ሕፃናት ኳሶች ይዘው ሲጫወቱ ሳይ ያች ህደጋ የገዛችልን የጣልክብን ኳስ ትዘ እያለችኝ ይቆጨኛል ሃሃሃ” አንረሳም እኮ አንዳንዴ !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ድንገት ነበር ነገሮች የተገለባበጡት፤ ልክ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ፣ እንደጎርፍ መጥለቅለቅ ሰፈራችን ውስጥ በአብሮ መኖር የፍቅር ቆሌ የሆኑ ነዋሪዎችን ከሥራቸው እየመነገለ ድራሻቸውን ያጠፋ ድንገቴ
ነውጥ። እንዴት ነው ሰው ድንገት ተነስቶ ትላንት አለፍኩት ወዳለው አረንቋ መልሶ የሚዘፈቀው…?
“ሲደርሱብን ምን እናድርግ” ብሎ ነገር ...
“ኤርትራ ወረረችን…” ተባለ።
“ምናባቷ ቆርጧት ይች የእናት ጡት ነካሽ!” የሚሉ ደምፍላታም ሰዎች ሰፈሩን ሞሉት። ከየት አመጡት አማርኛውን…? መቸስ ታንክ ቢሆን፣ መትረየስ፣ ቦንብ ምናምን ገዙት ይባላል፣ ወይ በእርዳታ አገኙት፤ ስድብ ከየት ተፈበረከ ... ዛቻ መቼ ተረግዞ ነው በዜማ የተወለደው…? ትላንት እንደ ቦብ ማርሌ “ፀበኞች ካልታረቁ!” እያለ ሲያቀነቅን የነበረ ድምፃዊ “ፍለጠው ቁረጠው!” ዘፈኑን ከየት መዝርጦ ቴሌቪዥኑን ሞላው፤ ወይስ ሁሉም ዘፋኝ ለክፉ ጊዜ ያስቀመጠው ዘፈን አለው? ለጦርነት ግጥምና ዜማ መፍጠር ከፍቅር ዘፈን ይቀላል? ከቀበሌ ኪነት ቡድን እስከ አገር አቀፍ ታላላቅ ዘፋኞች ዘፈናቸው አይሄድ አይመጣ አንድ - “በለው ፍለጠው ቁረጠው !!”
በዓይን ርግብግቢት ፍጥነት 'ለደኅንነታችሁ' ብለው ደህና ሰዎች ብለን ያመንናቸውን፣ ስንጣላ አስታራቂ፣ ስንቸገር ደራሽ የነበሩት ጎረቤቶቻችንን ሁሉ በአውቶብስ እየጫኑ አባረሯቸው። እማማ ንግሥትን ጨምሮ። ከመወለዳችን በፊት ኤርትራ የሄዱ የማናውቃቸው ብዙ እማማዎች ከዛም ተባርረው መጡ። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ። ለካስ የመንግሥታት ፍርሃት እንደጅብ ያነክሳል አገርንም ያስነክሳል። አሁን እማማንግሥት ምናቸው ነው ለደህንነት የሚያሰጋው? በሹሩባቸው ውስጥ ቦምብ
እንዳይቀብሩ ነው? ወይስ በድፏቸው ውስጥ ጥይት እንዳይደብቁ ...። እማማ ንግሥት (ለደህንነት ስጋት ናቸው ተብለው የተባረሩ ቀን ማታ ህልም አለምኩ….
ቀኑ ቡሄ ይመስለኛል። የሰፈር ልጆች እንደልማዳችን ተሰባስበን እማማ ንግሥት በር ላይ ቆመን
እንጨፍራለን።
“እዛ ማዶ አንድ በረዶ!
እዚህ ማዶ አንድ በረዶ!
የኔ እማማ ንግሥት!
ፓራ ኮማንዶ ….”
የእማማ ንግሥት በር ድንገት ብርግድ ብሎ ተከፈተና፣ በወርቅና በሐገር ባህል ቀሚስ የምናውቃቸው እማማ ንግሥት፣ የወታደር ልብስና ከስክስ ጫማ ለብሰው አናታቸውም ላይ የብረት ቆብ ደፍተው ድፎ ሳይሆን ዝናሩ የተንዠረገገ መትረየስ ጠመንጃ ደግነው፣ “ አንች ዲቃላ ሁሉ … በሬ ላይ ሙናባሽ ትናጫጫለሽ አቡነ አረጋዊ ድራሽ አባትሽን ያጥፉት!” ብለው ታታታታታታታታታታታታታ
ሲያደርጉብን በተለይ እኔ ሰውነቴ ተበሳስቶ ወንፊት የሆነ ይመስለኛል…፤ እየጮህኩ ከህልሜ ባነንኩ…፤ እናቴ ከትራስጌ በኩል ቆማ “አቡቹ በስማም በል ቅዠት ነው…” ትላለች።
ያየሁትን ህልም ለማሚ ስነግራት ግን ተቆጣች…
“ምን እንደው የዛሬ ልጅ የነገሯችሁን ይዛችሁ ትጋደማላችሁ፣ ቅዠት ይተርፋችኋል ፤ በል አርፈህ
ተኛ”
አባባ መክብብ እትዬ ንግሥት ወደ ኤርትራ ከተባረሩበት ጊዜ ጀምሮ ግራ እግራቸውን ሰብስቦ
ያዛቸው፤ በከዘራ ድጋፍ ሆነ የሚራመዱት። የጢም መላጫቸውም ከእጃቸው ጠፋች። ነጭና ጥቁር ቡራቡሬ ፂም ትንሽ አገጫቸውን ሸፈነው…፤ ተዘናጉ፤ ሰፈሩ ተዘናጋ …። አንድ ቀን በግሮሰሪዋ በኩል ሳልፍ አባባ መክብብ ከዘራው እጀታ ላይ የተነባበረ እጃቸው ላይ አገጫቸውን አሳርፈው አፋቸው
ባዶ ነገር እያኘከ ትክዝ ብለው ተቀምጠዋል በቀስታ ወደ ፊትና ኋላ እየተወዛወዙ። ላልፍ ስል የውሃ ማጠራቀሚያው በርሚል ላይ ዓይኔ አረፈ፤ የሆነ ነገር ቅር አለኝ …፤ በትኩረት በርሚሉን አየሁት፤ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ከበርሚሉ ተነጥላ የማታውቀው የመርቲ ጣሳ በቦታዋ የለችም። ጣሳዋ ትታሰርባት የነበረችው የኤሌክትሪክ ገመድ ባዶዋን ተንጠልጥላ ነፋስ በቀስታ ያወዘውዛታል !

👍21🔥1
#ከሰሀራ_በታች
፡
፡
#ሁለት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ማንም ችኩል ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም፡፡ ፋናን ገና ስመለከታት ልቤ ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ሐውልት ቆሟል፡፡ ማንም ብትሆን ግድ አይሰጠኝም፤ ቤት ውስጥ ምንሽር የታጠቀ፣ ጓንዴ ትራሱ ስር
ያስተኛ ባሏ ቢቀመጥ፣ ሰባት ልጆቿ “እማ እማ!” እያሉ የሚንጫጩ ሴት ብትሆንም ግድ የለኝም፡፡ፋናን አየኋት፣ ወደድኳት በቃ!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እና ይሄን ሁሉ ሴኮንድ፣ ዘላለም የሚያህል ደቂቃ ፋናን አይቼ ባፈቅራት “ቸኮልክ” የሚለኝ ማነው?!.
ቤተሰቦቼ በየወሩ የሚልኩልኝ ብር ከዚህ የተሻለ ቤት እንድከራይ የሚያስችለኝ ቢሆንም ፋና
የምትባል የእግር ብረት ተጠናውታኝ በየት በኩል ! ቤቱ ለአንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ምኑም
የሚመች አልነበረም፡፡ ከእኔ ክፍል ኋላ የታወቀ ጠላ ቤት ነበር፤ ጫጫታው፣ ሁካታው፣ ዘፈኑ፡
ፀቡ ሁሉ ይረብሸኛል ፡፡ በሳምንት ሦስት ቀን !!
የጠላ ቤቱ ጩኸት ጋብ ሲል ኳስ የሚጫወቱ ልጆች ይተካሉ፡፡ ግድግዳየን በኳስ ሲነርቱት
የቤቴ ምርጊት አፈሩ በለጠፍኩት የግድግዳ መሸፈኛ ወረቀት ስር እየተንኮሻኮሻ ሲፈርስ
ይሰማኛል፡፡ ይህን ሁሉ ስችለው ደግሞ የጠላ ቤቱ አሻሮ ሲታመስ ፣ የጠላ ቂጣው ሲጋራ አአአሻሮ አሻሮ የሚሸትት እንኩሮ እንኩሮ የሚተነፍግ ጭስ ጠባብ ክፍሌን ይሞላታል፡፡
ይህ ሁሉ ችግር ግን ቤቱን እንድጠላው አላደረገኝም፡፡ ፋናን ስመለከት ጫጫታው የፍቅር
ሙዚቃ፣ ጭሱ ፍቅርን የሚያጥን
የገነት ከርቤ እስኪመስለኝ ይስማማኛል፡፡
እዚህ ቤት ውስጥ ለስድስት ወራት ስኖር ከፍቅርተ ጋር ተግባባን፤ እማማ አመለ ጋር የእናትና የልጅ ያህል ተቀራረብን፤ ከፋና ጋር ግን ከሰላምታ ውጭ አንዲት ቃል ተለዋውጠን አናውቅም። ፋና እዛው ተቀምጣ አንድ ቤት እየኖርን ትናፍቀኛለች ፤ አትናገር አትጋገር ! ዝም፡፡ ፋና
ቤት ውስጥ አለች ማለት ማንም ቤት ውስጥ የለም እንደማለት ነው፤ ዝምታ ይነግሳል፡፡ የፋናን
ድምፅ አንዳንዴ ለአራት ለአምስት ቀናት አልሰማውም፤ እዛው እያለች፡፡ አይገርምም ? እኔም
በቤተሰቦቼ “እሱ አይናገር አይጋገር ዝም ነው!” እየተባልኩ እሞካሽ ነበር፡፡ ጉዳቸውን ባዩ !
እዚህ ሞት የሚያስንቅ ዝምታ የሰፈረባት ጋግርታም ጋር በፍቅር ወድቄ አንድ ቃል ሲናፍቀኝ፡፡
የፋና ዝምተኝነት የጤና አልመስል ብሎኝ ነበር፡፡ እንጀራ እየበሉ ወጥ ሲያልቅባት እንኳን ወጥ
ጨምሩልኝ አትልም፡፡ ደግነቱ እናቷ እማማ አመለ ዓይናቸው ከፋና ላይ ስለማይነቀል ገና ወጡ
ሲያልቅባት በላይ በላዩ ይጨምሩላታል፡፡ ፋና በቀን ውስጥ የምትናገራቸው ቃላት ሲደመሩ
እህቷ ፍቅርተ በግማሽ ደቂቃ ከምታዘንበው ንግግር እሚበልጡ አይመስለኝም፡፡ ፍቅርተ ሙሉ
ቀን ስታወራ፣ ስትስቅ፣ ስትጫወት ነው የምትውለው፡፡ አንዳንዴ ፈገግታ የሚያጭርብኝ ነገር
ፋናና ፍቅርተ ሲያወሩ መስማት ነበር፡፡ ፍቅርተ ብቻዋን የምታወራ ነው የምትመስለው።ፋና አንድ ቃል አትመልስም፤ ፍቅርተም ብትሆን የእህቷን አመል ያወቀች ይመስል መልስ አትጠብቅም፤ ዝም ብላ ታወራለች ::
የፍቅርተን ወሬ መስማት አይሰለችም፡፡ እንደው ፍቅርተን መልኳን ሳይመለከት ድምጿን ብቻ
ያደመጠ ሰው በዓለም አንደኛዋ ቆንጆ ሴት እየተናገረች ሊመስለው ይችላል፡፡ በተለይ ሳቋ ! የፍቅርተ ውበት ግን ድምጿ ብቻ ነው:: “ስምን መልአክ ያወጣዋል” የሚባለው ብሂል እውነት
ከሆነ የፍቅርተን ስም ያወጣው መልዓክ ድምጿን ብቻ በሆነ መንገድ አድምጦ “ፍቅርተ” ብሎ
ሳይሰይማት አልቀረም፡፡
እማማ አመለወርቅ ብርቱ እናት ነበሩ፡፡ ሁለቱን ሴት ልጆቻቸውን ያሳደጉት ካለ አባት ነው፡፡
ዛፍ ቆራጭ የነበሩ ባለቤታቸው አንድ ቀን ዛፍ ሲቆርጡ የዛፉ ቅርንጫፍ የተላጠ ኤሌክትሪክ
መስመር ጋር የተነካካ ሆኖ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ ያኔ ፋና የሶስት፣ ፍቅርተ
የሁለት ዓመት ሕፃናት ነበሩ፡፡ እነዚህን ሁለት ልጆች ለማሳደግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡
ያለፉበትን አሰቃቂ የድህነት መንገድ ተመልሰው ሲያስቡት ያንገሸግሻቸዋል፡፡ ታዲያ ከተቀራረብንና እኔም ከቤተሰቡ አባል እንደ አንድ ተቆጥሬ ገመናቸውን ተካፋይ ስሆን ማታ ማታ ቡና ተፈልቶ ታሪካቸውን ያወሩልኝ ነበር፡፡ እማማ አመለ ወሬ ይችላሉ፤ አሁን በሐዘን ዐይናችንን በእንባ ሞልተውት ድንገት ጣል በሚያደርጉት ቀልድ ለሐዘን የኳተረ እንባችን በሳቅ ይፈሳል፡፡
የማታ ቡና አብሬያቸው መጠጣት የጀመርኩበት ቀን ትዝ ይለኛል፡፡ በፊት ቡና ሲያፈሉ ፍቅርተ
መጋረጃዬን ገለጥ አድርጋ አንድ ስኒ ታቀብለኝና እጠጣለሁ፤ እጣኑም ቢሆን እየተጥመለመለ
መጋረጃዬን አልፎ ክፍሌ ይደርሳል ፡
“አብዬ” ይሉኛል እማማ አመለ ሲጠሩኝ እንዲህ ነው፤
“አቤት ማዘር !”
"ሁለተኛ ትጠጣለህ?”
“አይ ይበቃኛል ማዘር” እላለሁ፡፡ እየፈራሁ እንጂ ብጠጣ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
አንድ ቀን ታዲያ ቡናው ተፈልቶ፣ እጣኑ ቤቱን ሞልቶት፣ እኔም ነቃ ብዬ ፍቅርተ መጋረጃዬን
ገለጥ አድርጋ ቡናዬን እስክታቀብለኝ ስጠብቅ እማማ አመለ ጠሩኝ፡፡
“አብዬ !”
“አቤት ማዘር”
“እንደው ከሰውም አልተፈጠርክ ? ምናለ ወዲህ ወጣ ብለህ ብትጫወት፣…ጀበናውንም እያየህ ቡና ብትጠጣ፣ እኔም እናትህ ነኝ፣ እነፍቅርዬም እህቶችህ ናቸው” አሉኝ፡፡ ይሄ የመለአክት ጥሪ ነው !
ልብሴን ቀየርኩ፤ (ምርጥ የምላትን ልብስ ነው የለበስኩት፣ ከዚህች እዚች የመጋረጃ ድንበር ለማለፍ
ሽክ!!)፡፡ እናም መጋረጃዬን ገለጥ አድርጌ ብቅ አልኩ፤ ሁሉም በአክብሮት ተቀበሉኝ፡፡ የተዘጋጀችልኝ ኩርሲ ላይ ተቀመጥኩ ፡፡ እዩት እንግዲህ እግዜር ጨዋታውን ሲያሳምረው! ፋና ፊት ለፊቴ ነው የተቀመጠችው፡፡ ከዚህ በፊት ፊት ለፊቴ ተቀምጦ የሚያውቅ ውብ ነገር ምን ነበር?…ምንም !!
በእኔና በፋና መሃል የሲኒ ረከቦት፣ ሲኒዎቹ ስድስት ጨረቃ መስለው፣ ከረከቦቱ ጎን ማጨሻው
እንደ ደመና በቀስታ ሽቅብ ወደ ጠቆረው ጣራ፣ ከሚሳብ የእጣን ጭሱ ጋር፡፡ ከስሱ የእጣን
መጋረጃ ባሻገር ፋና አንገቷን ደፍታ መሬት መሬት እየተመለከተች ተቀምጣለች፡፡ አዲስ ሰው
ስለተቀላቀልኩ ጨንቋታል፡፡ አቤት እንዲህ ፊቷ ተቀምጠው በእጣኑ ጭስ ውስጥ ሲመለከቷት
“ምነው ባልነቃሁ” በሚባልበት እንቅልፍ ውስጥ የተከሰተች ጣፋጭ ህልም ነው የምትመስለው ፋና የኔ ውብ፡፡
ድህነትን አፈር ድሜ ያስጋጠ ውበት በዚህ ጭርንቁስ ቤት ውስጥ ፊት ለፊቴ በእጣን ደመና
ተከብቦ ተቀምጧል፤ እኔም ከእግር ጥፍር እስከራስ ፀጉር በሚነዝር በሚያስረቀርቅ ደስታ
ውስጥ ህያውና ዘላለማዊ ሥዕል ላደርጋት እያጠናኋት ነው ፡፡ነፍሱ በፍቅር ፍላፃ እንደተወጋች
አይደለም የሚያሳምረው፤ የተፈቃሪውን ነፍስ ይመለከታል፤ ነገን ይመለከታል፤ በዝምታ ውስጥ ያለ ሰላምን የሚቃኙ ዐይኖች ይታደላል፡፡ ከተከዘ ፊት ፈገግታን ያወጣል፡፡ እውነትን በዓይነ ህሊናው ይቃኛል! አፍቃሪ ሠዓሊ ነው!
ከዛን ቀን ጀምሮ ፋና ጋር በእጣን ጭስ መሃል መተያየት የዘወትር ተግባራችን ነበር፡፡ የእማማ
አመለ ጣፋጭ ወግ፣ የፍቅርተ የማያባራ ሳቅና ጨዋታ፣ የፋና የማይገሰስ ዝምታና የዝምታዋ
ውበት፣ የውበቷ ግዝፈት እንደ መንፊስ በቤቱ ውስጥ ያረብብ ነበር፡፡ ያችን የድህነት ጎጆ ሙሉ
ያደረገ መልካም ቤተሰባዊ ፍቅራችን ለአራት አመታት አብሮን ኑሯል፡፡

👍27❤4🥰4👎1
#ሚስቴን_አከሸፏት
፡
፡
#ሁለት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...ፌቨን የፈራረሰ ሰፈር፣ የተቆራረሰ ዳቦ ሆናለች ለእኔ። የጎኔ ሽራፊ ሳትሆን ከሙሉነት ጎን የተሸረፈች የዳቦ ሽራፊ። እጠላታለሁ? አዎ ! ቆንጆና በአበባ የተዋበ ግቢውን በግዴለሽነት ያፈራረሰበትን ሰው ማን ይወዳል ?! ፌቨንን በማፈቅራት ልክ ጠላኋት በቃ!
“ማናባቱ ያዘኛል ምን የጎበረበት፣
በገዛ ትዳሬ ውኃ ብደፋበት” ብላለች ዘፋኝዋ!
አራት ዓመት በፍቅር ቆይተናል፤ ከፌቨን ጋር። እድለኞች ነበርን፤ ለድፍን አራት ዓመት ያልቀዘቀዘ
ፍቅር ነበረን። አስር ደቂቃ አብረን ለመቆየት የአንድ ሰዓት መንገድ አቆራርጠን እንገናኛለን። “ዓይንህን ልየው ብዬ ነው የመጣሁት፤ በጣም እቸኩላለሁ” ብላኝ ላባችን ሳይደርቅ ወደየመጣንበት። ላገባት
እፈልግ ነበር። እርሷ ደግሞ አገባኋት አላገባኋት አያሳስባትም። ቀልቧ የትም እንደማልሄድ ነግሯታል። ቀልቧ ታዲያልክ ነበር። ደግሞ ሌላው የእድለኝነታችን ገፅ ሁለታችንም የሚታይ ለውጥ በሕይወታችን እየተከሰተ በሁሉም ነገር ስናድግ ነበር። ፌቨን አካውንቲንግ ተምራ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ሥራ አገኘች። እኔም ልክ ተመርቄ እንደወጣሁ ሥራ ያዝኩ። ትዳር ሲታሰብ አንዳች ኃይል ነገሮችን
ያገጣጥማቸዋል (እግዜር እንዳልል የዛሬውን ፍች ሳስብ ፈርቼ ነው)፤ እናም እንዲህ አልኳት፣
“ፌቪ!”
“ወይዬ” ሁልጊዜ ስጠራት ከዓይኗ ብርሃን ይረጫል። ስሟ ላይ የጨመርኩበት አንዳች ነገር ያለ
ይመስል፣
“ላገባሽ ነው”
“እኔ ... አላምንም… አብረን ልናድር ነው?” ብላ ተጠመጠመችብኝ። አቤት ደስታዋ።በእርግጥ ለሌላ ሰው ይህ አባባሏ ሳያስቀው አይቀርም። ለእኔ ግን የሆነ አስደሳች እና በስሜት የሚንጥ
ነገር ነበረው። አብረን ውለን
“በቃ ልሂድ” ስትል እንዴት ይቀፈኝ እንደነበረ የማውቀው እኔ ነኛ።
አብሮ ማደር የቀለለባቸው ይሄ ተራ ነገር ይመስላቸዋል። ፌቨን ከእቅፌ ውስጥ ቅር እያላት ስትወጣ የዓለም ቅዝቃዜ ሁሉ ወደኔ ይጋልብና አንጀቴ ውስጥ ገብቶ ያንዘፈዝፈኛል። ሸኝቻት ወደቤት ስመለስ ቤቱ ቤት አይመስለኝም፤ በረንዳ።
ለአራት ዓመት በፍቅር ስንቆይ እንኳን ማደር ምሽቱ ምን እንደሚመስል አብረን አይተነው አናውቅም። የፌቨን እናት ናቸው ምክንያታችን ... የሚገርሙ ሴትዮ … ልጆቻቸውን አታምሹ አይሉም፡፡ ግን የእናትነት የፍቅር መብታቸውን በትክክል ተጠቅመውበታል። ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ፌቨን
ቡና ታፈላላቸዋለች (የቤቱ ደንብ ነው)፣ ሁለት ሰዓት ራት ይበላሉ…ልጆቹ ካልተሟሉ ራት አይበሉም
እንደውም ሰዓቱ ካለፈ ልጆቻቸው ቢሟሉም ራት ሳይበሉ ነው የሚያድሩት። ፌቨን ታዲያ ይሄው
ነገር ተከትሏት መጥቶ እኔ ቤት ካልገባሁ እህል በአፉ አይዞርም፤ እንግዲህ ፌቨን ርሃብ እንደማትችል አውቃለሁ። ከራባት እንስፍስፍ ነው የምትለው፤ ዓይኗን እንኳን መግለጥ ያቅታታል!(አቤት ስታሳዝነኝ እንደነበር) ታዲያ እንዴት አባቴ ብዬ ለእራት እዘገያለሁ በጊዜ ወደ ቤቴ ጥድፊያ ነው ! የፌሽን
እናት በእነዚህ የማይዛነፉ ሕጎች ልጆቹን የማይዛነፍ የቤት መግቢያ ሰዓት ድንበር አስምረውላቸዋል።
ካለአባት ስላሳደጓቸው እናታቸውን እንደ አባትም እንደ እናትም ነው የሚያይዋቸው።
ተጋባን ! ትዳራችን በሚያሰክር ፍቅር የተሞላ ነበር ! እድለኛ ነኝ ያልኩት ለዚህ ነው። ልክ እንደ ፍቅረኛ ነበር የምንኖረው። ከቤታችን መውጣት አንፈልግም። ሰውም ወደቤታችን ባይመጣ
ደስታችን.እውነቴን እኮ ነው። ክፉ ሆነን ሳይሆን ፍቅር የሚባለው ስካር አልሰከነልንም ነበር። ሰዓት
አይበቃንም። ቅድም ነግቶ ቁርስ በልተን ምን እንዳወራን ምን እንደሰራን እንኳን ሳናውቀው
እንዳንዴ እንዲያውም ምሳ ሰዓት ሁሉ በየት እንዳለፈ ሳይገባን ብቅ ስንል ማታ ሆኗል። በቃ! እንዲህ
ነበርን እኔና ፌቨን ! “ሁሉም ሲጀምረው እንዲሁ ነው” ይባል ይሆናል፤ ግን ለድፍን ሦስት ዓመት
ስንኖር ደስታችን ሳይሸረፍ፣ ሳቃችን ሳይከስም ፍፁም ደስተኞች ሆነን ነበር።
ደግሞ አማረብን እንጂ !ፌቨን ድሮም ቆንጆ ናት ጭራሽ አበባ መስላ አረፈች። እኔ እንኳን አንድ ሁለት ተብሎ አጥንቴ የሚቆጠር ፍጥረት ትንሽ የተገለበጠች ጎድጓዳ ሰሃን የምታህል ቦርጭ ተከሰተችብኝ ! እንደ አዳምና ሄዋን የቀደመ ሕይወትም ትዝታም ሳይኖረን እዚሁ ቤት በዚሁ እድሜ የተወለድን ይመስል ያለፈውን ዓለም፣ ቤተሰብ፣ ጓደኛ ምናምን ሁሉ ሁለታችንም ረሳነው። የፌቨን እናት ይደውሉና፣ “ኧረ እናንተ ልጆች ድምጣችሁ ጠፋ .በደህናችሁ ነው ?” ይሉናል።
እኔና ፌቪ ታዲያ ልክ ስልኩ ሲዘጋ፣ “በደህናችን ነው ግን ?” ተባብለን እንሳሳቃለን። ከዛ ፕሮግራም እናወጣለን። በቀጣዩ ቅዳሜ የፌቪ እናት ጋር፣ በዛንኛው ደግሞ እኔ ቤተሰቦች ጋር፣ እንዴ ከሰው ተለየንኮ እንባባልና፤ በቀጣዩ ቅዳሜና እሁድ ወፍ የለም !! እንደውም ቅዳሜና እሁድ ማለፉን የምናስታውሰው ሰኞ ነው! እኛ ሌላ ዓለም ውስጥ ነን!
ቢጨንቃቸው የፌቨን እናት ራሳቸው መጥተው ጠየቁን፤ እና መከሩን፣
“ታፍናችሁ አትዋሉ፣ ወጣ እያላችሁ ይንፈስባችሁ ፊታችሁ ፈረንጅ የመሰለው ጠሃይ እጦት እኮ ነው ምቾት እንዳይመስላችሁ።” ምን ያደርጋል ምክራቸው ራሱ ነፈሰበት። ምናባቴ ላድርግ እኔ ራሱ ከቤት
( ስወጣ ገና ትላንት ከገጠር እንደመጣ ሰው እደናበራለሁ። ቤቴ ይናፍቀኛል .ፌቪ ትናፍቀኛለች። ሩቅ አገር የሄድኩ፣ የማልመለስ ይመስለኛል። ት ና ፍ ቀ ኛ ለ ች እንዲህ ዓይነት ትዳር ከመቶው አንድ ነው አሉ። ለምን ግማሽ አይሆንም። የበረከቱ ተካፋዮች እኔና ፌቨን ነበርን።
ሳወራው ያመኛል። ሰዎች የበለጠ በተፋቀሩ ቁጥር እንደስስት መስተዋት ራሳቸውን ከቀላልም
ከከባድም ግጭት መጠበቅ ይኖርባቸዋል። አንዱ ቸልተኛ ሆኖ ሳት ካለው ፍቅር ሲንኮታኮት
ያሰቅቃል። ደግሞ ብቻውን አይንኮታኮትም፤ ጣፋጭ ትዝታንም ይዞ ነው አፈር ድሜ የሚበላው።የጨነገፈ ፍቅርን እንደማሰብ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ምን ሰቆቃ አለ…?
ፌቨንን እወዳት ነበር፣ አከብራት ነበር፣ አፈቅራት ነበር። ትንሽ ነገር፣ ይሄ ነው የማይባል ምክንያት
በውስጤ እሳተ ገሞራ የሚያህል ቅያሜ አፈነዳ። “አሁን ይሄ ምኑ ይካበዳል ? እንኳን ለፍች ተራ
ኩርፊያም አያበቃምኮ” ይባል ይሆናል። “ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል” አሉ።ይሄ ትንሽ የተባለው
ምክንያት ለተመልካች ትንሽ ይምሰል እንጂ ፌቨንን ዓይኗን ማየት ድምፅዋን መስማት የጠላሁት በዚሁ ምክንያት ነው።
ፍቺ ፈለግኩ። ምክንያቱም ፌቨን ፀጉሯን በአጭሩ በመቆረጧ ነበር ...!! በቃ ይሄው ብቻ ነው ምክንያቱ ሚስቴ ፀጉሯን በአጭሩ መቆረጧ። የፌቨን ፀጉር ምን ቢሆን ነው እንዲህ ጉድያ ፈላው፣ ጎጇችንንስ በጭንቅላቱ ያቆመው ?
ፌቨን” አልኳት ሚስቴ ፀጉሯን ተቆርጣ የመጣች ቀን፣
“አቤት”አላለችኝም!!እንደ ወትሮዋ “ወይዬ” አላለችም። ፊቴ ላይ የነበረው ጥላቻ ቅስሟን ሰብሮታል። እንዲህ ሙሉ ስሟን ደግሞ ጠርቻት አላውቅም። ሙሉ ስሟን ከምጠራት ሙልጭ አድርጌ ብሰድባት ይሻላታል። በምርጥ ፍቅረኞች መሀል እኮ በሙሉ ስም ከመጥራት የበለጠ ስድብ የለም።በአገራችን
አቶ፣ ወይዘሮ ምናምን ከሚባሉት ተቀፅላዎች ይልቅ ስማችን ሲቀናጣ ሐሴት ማድረጋችን ሳይታለም የተፈታ ነው። አቶ ጉልማው ከመባል ጉሌ፣ “ጉልዬ” ብንባልም ደስ ነው የሚለን መቼስ። ፍቅረ ቅንጦት !

👍36❤1👎1
#ዶክተር_አሸብር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#ሁለት
....አሸብር ብላ ስም ያወጣችልኝ ከቤታችን በላይ ብዙ ላም የምታረባ ቅሌታም ባልቴት ናት፡፡ ሰው ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ከአቲዬም ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ እኔ ልወለድ አቲዬ ምጥ የተያዘች ቀን የዚህች አቃጣሪ ባልቴት የአሜሪካ ላም ያልታወቀ ነገር በልታ ሆዷ
ተቆንዝሮና አረፋ ደፍቃ እየጓጎረች ነበር አሉ።
የመንደሩ ሰው ከእኔ እናት ምጥ ይልቅ የዚህች የመንደራችን ሀብታም ላም ነፍስ አስጨንቆት
አዋላጇ አልማዝ ሳትቀር ወደዛው ሂደው ነበርና አቲዩ ብቻዋን እኔን ተገላገለች፡፡ ወለደችኝ!!
የቀን ሥራ ያጠነከራት ብርቱ ሴት ባትሆን ኖሮ ሟች ነበረች፡፡ ብቻዋን ወለደችኝ !!"
አንድ የእንስሳት ሀኪም ተጠርቶ የአቃጣሪዋን ዘርፈ ላም ሆድ እስክሪብቶ በሚመስል ነገር
ወግቶ ሲያስተነፍስላትና ላሟ መጓጎሯን ስታቆም መንደርተኛው እልልታውን አቀለጠው!
እልልልልልልልልልል… አቲዬ እልልታውን ከሩቅ ሰምታለች፡፡ በዚህ መሀል አዋላጇ፡ “በሞትኩት ያቺ ሚስኪን ምን ደርሳ ይሆን?” ብላ ወደ ቤታችን ተጣደፈች። አቲዬን የተፈለቀ ወርቅ የመሰለ ወንድ ልጅ አቅፋ አገኘቻት፡፡ ያ የተፈለቀቀ ወርቅ እኔ ነበርኩ ያውም ገና በእሳት ሊፈተን የተዘጋጀ ወርቅ፡፡
ዘርፌ የሚሏት ሀብታም ባለላም የላሟን ደኅንነት ሊጠይቃት ቤቷ ሲጎርፍ የዋለውን ቅቤ አንጓች
ሁሉ ስታስተናግድ ውላ ወደ ማታ አስር እንጀራና ክክ ወጥ ይዛ ቤታችን መጣችና መንደርተኛው
በእኔ ላም በተሸበረበት ቀን ተወልዷልና አሸብር ብዬዋለሁ” አለች፡፡ አሸብር ሆኜ ቀረሁ!! ነገ አድጌ ብረብሽ! ስምን መልዓክ ያወጣዋል የሚል ሒሳብ 'መልዓክ ነኝ ልትል፡፡ እች…ስድብ የማይገልፃት…!ለ 'አንቱታ' የደረሰች ሴትዮ ናት፣ 'አንች የምላት ባትስማኝም ስንቃት ደስ ስለሚለኝ ነው፡፡
እንግዲህ አሸብር የተባልኩት አንዲት ተራ አጋሰስ..የአሜሪካ ላም ባጋበሰችው ፈስታል ታምማ
መንደርተኛውን ባሸበረችበት ቀን በመወለዴ ነው በቃ ! ደግሞ ምኔም የማያሸብር እንደወም
ቅጠል ሲንኮሻኮሽ እቲዬ አሮጌ ቀሚስ ስር የምደበቅ ፈሪ ነበርኩ ስሜን ያወጣው መልዓክ
አይደለም ዘርፌ የምትባል ቀንዳም ሰይጣን ናት!!
እኔኮ ሚያበሳጨኝ.…የዛን ጊዜ ዘመኑ ስላልሰለጠነ ነው ብዪ ውስጤ ከተመረዘበት ጥላቻ
እንዳይሽር፣ ዛሬም ድረስ ጎረቤቶቻችን ስለዛ ጊዜ ሲያወሩ ፊታቸው የተቀመጠችውን አቲዬን….ብቻዋን መውለዷን ከቁምነገር ሳይቆጥሩት ማለፋቸው ሳይበቃ፣ ከሞተች የቆየችውን የአሜሪካ ላም ደግነት፣ ባልዲ ሙሉ መታለብ ፌስታል በልታ ስታቃስት አንጀታቸው መንሰፍሰፉን
እየተቀባበሉ ማውራታቸው ነው፡፡ ደግሞ የሚንሰፈሰፍ አንጀት እንዳለው ሰው፡፡ጎማ አንጀት ሁሉ!!
አቤት ስጠላቸው! ልቤ ተሸንቁሮ የቋጠረው ፍቅር ፈሶ ያለቀበት ይመስል የተረፈኝ አፅናፍ
የለሽ ጥላቻ ብቻ ነው፡፡ ማንንም አልወድም ሁሉንም እጠላለሁ ! ዘርፌ መልዓክ ብትሆን ጥሩ ነበር
ስሜን እንድሆን፤ ይሄን ከመሬት ተነስቶ የሚሸበርና የሚያሸብር አውራና ምንዝር ጎረቤት ሁሉ እንዳሸብረው !! ወይ ነዶ ለሞላ ቦንብ ምናለ አንዲት ኒውክሌር ቦምብ ብትኖረኝ !! ለክፉ ነገር አልጠቀምባትም፣ ቀለመወርቅ ግቢ እወስድና …
አቲዩ ከገጠር ወደ አዲስ አበባ ስትገባ ገና 14 ዓመት እንኳን አሳምሮ አልሞላትም ነበር፡፡ ገጠር
የሚኖሩ ቤተሰቦቿ ምናምኒት የሌላቸው ያጡ የነጡ ድሆች ስለነበሩ በልጅነቷ ነው ልፋት
ዕጣ ፋንታዋ የሆነው ገጠር ስልችት አላት፡፡ ባል አልነበረም የስደቷ መነሻ፡፡ ያላቻ ጋብቻ
ምንትስ ብላ አልነሳረም ወደ ከተማ መኮብለሏ፡፡ የከተማ ሰው ከድህነት የሚያላቅቅ ዓመድሽን
የሚያራግፍ ደግ ነው ብለዋት እንጂ ባል ሽሽት አልነበረም፡፡
ከተሜው ያላቻ ጋብቻ እያለ የሚወተተው ሲያስመስል እኮ ነው፡፡ ለሀብት፥ በዘር፣ በእምነት
አቻ በማሳደድ ሱስ ስለተለከፈ፣ የመከፋፈልና የማግለል ንቅዘቱ ነው የሚያስለፈልፈው፡፡ ተራራ
ተሻግሮ የሚጮኸው ከተሜ ስንት የነቀዘ ባህል፣ የገማ ዓመል ጉያ ውስጥ ሸጕጧል። አሱን ብሎ የመብት ተከራካሪ፣ እሱን ብሎ ታዳጊ፡፡ ምን በወጣሽ ካለ እድሜሽ ማግባት እያለ
የገጠሯን ሴት በአዞ እንባ ሙሾ የሚያስወርድ ከተሜ በየጓዳው ከከፉ ባል ይከፋል፡፡
የልጅነት እግሮቿ ወደ አዲስ አበባ መሯት። ዘርፌ የምትባል ባለ ብዙ ላም ሴት የደሀ መንደር ከእኔ ወዲያ ሀብታም ላሳር' የምትል ክብረ ቢስ ባልቴት ላይ ሰዎች አምጥተው ጣሏት፡፡ ሴትዮዋ
ብዙ የአሜሪካ ላሞች ስለነበሯት አቲዬን በሰራተኝነት ቀጠረቻት፡፡
ገጠር ትታው የመጣችው አዛባ መዛቅና ላም ማላብ እዚህም መሀል አዲሳባ ጠበቃት፡፡ ሰው
እየመሰለው ይሮጣል እንጂ እጣ ፋንታውን በመሽሽ አያመልጠውም፡፡ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ብሂል ጋር ስንተላለፍ እጣ ፉንታችንም አብሮን እያለፈ ከፊታችን ይጠብቁናል፡፡ እንዲያ ነው አቲዩን የገጠማት፣ ከእርሻ ላም ወደ አሜሪካ ላም!! አዲሳባ ራሷ የአሜሪካ ላም ናት፡፡ ብዙ
ላበላት ብዙ የምትታለብ፡፡ አላቢም ታላቢም ግፍ የሞላባት፣ ውጪዋ አብረቅራቂ ቀለም የተቀባ ሰፊ በረት !!
አንዳንድ የአሜሪካ ላሞች ከሰው ልጆች የበለጠ ክብር ይሰጣቸዋል፡፡ የአሜሪካ ላም ስለሆኑ ወይም፣ ላም ብቻ ስለሆኑ አይደለም ወትት ስለሚታለቡ፡፡ ስጋቸው ስለሚበላና ሌላ የምትታለብ ላም የሚታረድ በሬ ስለሚወልዱ፡፡ ይሄ የዓለማችን የደነዘ የምጣኔ ሀብት ቀመር ነው
የበለጠ የሚታለበውን የበለጠ ተንከባከበው !! ይልኻል በአደባባይ በከራቫት በታነቀ ተወካዩ፡፡ በተወካዩ መሪነት የስግብግብነትና የከፋት ኪራላይሶ የሚደግም አህዛብ ከተሜ ይባላል፡፡
አገር ይሁን ሰው ምንም ከሌለው ምናምቴ ነው፡፡ ይገፋል ይረገጣል፡፡ ለጠብታ ነዳጅ አንድ
አገር ሰው ቢፈጅ ዓለም ጭጭ የሚለው ለፅድቅ የሚሆንን መንገድ በግፍ ለመቀየስ ነው ካለወጉ !!ሰብዓዊነት ገደል ይግባ! ብለው ሰው መሆንህን ሊክዱ የሚዳዳቸው ሁሉ፣ በዕድልም ይሁን በችሎታህ አምልጠህ ሰው ስትሆንባቸው ገደል ያስገቧትን ሰብዓዊነት ጎትተው የሚያወጡባትን
ገመድ እንድትሰጣቸው ፊትህ ቁመው ጅራታቸውን ይቆላሉ፡፡ ደግነቱ ጭራቅ ለጭራቅ እስኪበላላ አይጨካከንም የጭራቅ ሕግ አለ፣ የጭራቅ መሀላ በየወንዙ የሚማማሉት ዓይነት፡፡ እንደ አተዬ አይነት ሚስኪን ልፋት የፈጠራት እንደ አህያ ያሻቸውን የሚጭኑባት ፍጥረት የሚማማሉበት ወንዝ ዳር ከተገኘች፣ አደፈረሽብን ከማለት አይመለሱም
እንደሰው ባልቆጠሯት እናቴ ጉልበት ሰው የሆኑ ብዙዎች ሰው ብቻ እንዳልሆኑ፣ ይልቅ በጣም
ሰው እንደሆኑ ሲሰማቸው (ከጣት ጣት ይበላለጣል የሚል ተረት ሁሉ አላቸው፡፡) የአትዬ ወጣት ሰውነት ላይ አይናቸውን ያቁለጨልጩ ጀመረ፡፡ ቀለመወርቅ የሚባል ካፖርትና ክብ ኮፍያ የማይለየው ባለ ትልቅ ቤትና ባለ መኪና ሰው ነበር። እሱስ አሁንም አለ፣ እኔ ውስጥ ከሞተ ቆየ እንጂ ! በውስጤ ሚሊየን ጊዜ ገድየው፣ ሚሊየን ጊዜ ተነስቷል የክፉ ሰው ነፍስ ጣር ይበዛበታል፡፡
ሁሉም ሰው ጋሽ ቀለሙ ነው የሚለው እና ይሄ ካፖርታም ቤታም እና መኪናም አጋሰስ

👍27❤3
‹‹አምስተኛዋ እኔ ነኝ፤አላየኸኝም እንዴ? እኔም እኮ ትናንት እዛ ነበርኩ››ፈገግ አለ፡፡
‹‹እኔ እንጃ፡፡ነበርሽ እንዴ? ምን አልባት በጣም ተጠግተሸኝ ተቀምጠሸ ከሆነ ‹ሎንግ ሳይት› በሽታ ስላለብኝ ቅርቤ ያለውን ነገር አጥርቼ ማየት ይቸግረኛል›› ሲል ተረቧን በተረብ መለሰ፡፡ ‹‹አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረህ››
‹‹እንደ እኔ ግን ሴትዮህ አሮጊቷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ለደቂቃ እንኳን አይኗ ካንተ አይነቀልም፡፡አንተ ስትኮሳተር ፊቷን ታጠወልገዋለች፣ፈገግ ስትል ትገለፍጣለች፡፡ ምራቋን የዋጠች የሠከነች ሚስት እንደሚወጣት እርግጠኛ ነኝ፡፡››
‹‹እሷን እርሻት ባክሽ፡፡አታያትም ጥርሷ እራሱ እንዴት እንደሚገጥ፡፡››
‹‹ምን ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ... አልተውሽም ብለሀታል፤እረሳኸው እንዴ?››
‹‹አረሳሁም፡፡ ግን እንዲህ አይነት ትሁን ማለቴ አይደለም፡፡ ቦርጯን እስቲ እይው? ከሠሎሞን እኮ አትተናነስም፡፡››
‹‹ያቺ ቀጫጫዋስ? ዛሬ ደግሞ ከትናንቱ በተቃራኒ ፈነዲሻ ሆናለች፡፡››
‹‹እሷ እንኳን ምንም አትል ግን ማደናገሪያ ትመስለኛለች፡፡ ስሜቴ እንደዛ ነው የሚነግረኝ፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ይህቺ አንባቢዋ ሳትሆን አትቀርም፡፡››
‹‹ትናንት እኮ እሷ ልትሆን አትችልም ብለኸኝ ነበር፡፡ እሷ ብትሆን የራሷን መፅሃፍ በማንበብ ግልፅ የሆነ ምልክት እንዴት ልታሳጥህ ትችላለች?»
‹‹ታዲያ ምን ላድርግ፤እሺ ንገሪኝ የትኛዋ ነች?>>
«ያቺ ቀዮስ?»
ፊቱን አዞረ፡፡ ሠርቃ ስታየው ተመለከታት‹‹አምጪ አበባውን ..…ታፍኜ አልፈነዳ››
ከቦርሳዋ አውጥታ ሠጠችው፡፡ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ቀለበቱ መኖሩን አረጋጠ፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ በተንቀረፈፈ እርምጃ ወደ ልጅቷ አመራ፡፡
‹‹ሠው አለው?›› ከፊት ለፊቷ ወዳለው ወንበር በጣቱ እያመለከተ፡፡
‹‹የለውም... ከዛ አባረረችህ እንዴ?››
ምንም ሳይመልስላት ተቀመጠ፡፡በዛው ቅፅበት በጨረፍታ ሲመለከት ጠይሟ ወጣት መጽሀፏን ዘግታ ከመቀመጫዋ ለቃ ወደ መውጫው ስታመራ ተመለከታት፡፡ በጥርጣሬ ታፍኖ በአይኑ ሸኛት፡፡ አሮጊቷም አምስት እርምጃ በማይሆን ርቀት ከኃላዋ አንገቷን ደፍታ ተከትላታለች፡፡ ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡ አይኑን ሲመልስ ወርቃማ ፀጉሯን በቀጫጭን ጣቶቿ ወደኃላ እየላገች አፍጣ በመገረም ታየው ነበር፡፡
እንደመርበትበት አለና አይኖቹን ከአይኖቿ አሸሸ፡፡
‹‹የያዝከው አበባ ያምራል፤ የሚቀበልህ አጣህ እንዴ?>>
‹‹አበባውን የሚቀበለኝ ሳይሆን ክራይቴሪያውን የሚያሟላ ነው ያጣሁት፡፡››
‹‹ስላላፈቀርክ ነዋ፡፡››
<<እንዴት?>>
‹‹ክራይቴሪያ የሚኖረው እኮ ከፍቅር በፊት ነው፡፡ ካፈቀርክ ግን የክራይቴሪያ ዘረ ማንዘሮች ተጠራርገው እንጦሮጦስ ይገባሉ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ጉድለቶችን ሁሉ አይቶ የማለፍ ብቃት አለውና፡፡››
‹‹እንደመልክሽ ንግግርሽም ጣፋጭ ነው››
‹‹አመሠግናለሁ፡፡ ግን ያቺን የመሠለች ቆንጆ ብቻዋን አስቀምጠህ እዚህ የመጣኸው ልትጀነጅነኝ እንዳይሆን?››
‹‹ብጀነጅንሽ ምን አለበት?››
‹‹ምንም የለበትም፡፡ ክፋቱ ዛሬ መጀንጀን አላሠኘኝም፤ ለማንኛውም አበባውን ግን እቀበልሀለሁ ፤ልትሠጠኝ ከፈለክ ማለቴ ነው፡፡››
አበባ የያዘ እጁን ወደ እሷ ዘረጋ፡፡ተቀበለችው፡፡ ለደቂቃም በፅሞና ተመለከተችው፡፡ እላዩ ላይ የተለጠፈውን ቁራጭ ወረቀት አነበበች፡፡ ‹‹እንቆቅልሽ›› ጮክ ብላ አነበበችው፡፡ በዝግታ ከጎኗ ያስቀመጠችውን ቦርሳ አነሳችና ጭኗ ላይ አስቀምጣ መክፈት ጀመረች፡፡የሁሴንም ልብ አብሮ መከፈት ጀምሯል፡፡እጇን ቦርሳ ውስጥ ከታ ታተረማምሳለች፡፡
‹‹ቀስ ብለሽ ፈልጊው›› አላት ሳያስበው፡፡
ቀና ብላ አየችውና ፈገግ ብላ ወደ ፍለጋዋ ተመለሠች፡፡ እሱም እጁን ወደ ኪሱ ከቶ ቀለበቱን ባለበት ያፍተለትል ጀመር፡፡ዳግመኛ እጇ ከቦርሳዋ ሲወጣ ግን ይዛ የወጣችው የጓጓለትን ሀብል ሳይሆን ቢዝነስ ካርድ ነው፡፡ ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለትና፡፡ ከወንበሯ ተነሳች፡፡ ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ አድርጋ አበባውን በቀኝ እጇ እንደያዘች <<የኔ ማር ዛሬ ሙዴ ስላልሆነ ነው ፤ያው አድራሻዬ፤ ሌላ ቀን ብትደውልልኝ መገናኘት እንችላለን፡፡ እስከዛው አበባህን ውሃ እያጠጣሁ እንከባከባታለሁ›› በማለት ጎንበስ ብላ ጉንጩን ሳመችውና እየተውረገረገች ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ሁሴን ባለበት ደነዘዘ፡፡ ምንም መናገር አልቻለም፡፡ ምራቁ መረረው፡፡ ትንግርት መጥታ ከጎኑ በመቀመጥ ብታናግረውም አልሠማትም፡፡ትከሻውን እያርገፈገፈች ለማናገር ሙከራዋን ቀጠለች፡፡
‹‹ስማ ነገሮች እኮ አላከተሙም፡፡ ሌላ አንድ እድል እኮ ይቀርሃል፡፡››
‹‹ተይኝ ባክሽ እንዲያውም አንቺ ነሽ›› አንቧረቀባት፡፡
‹‹ደግሞ እኔ ምን አደረግሁ?››
<<አሳሳትሽኛ፡፡ እኔ አሁን ይህቺን ዲቃላ መች አየኋት፡፡ አንቺ ነሽ የጠቆምሽኝ፡፡ ደግሞ አውቀሽ እንድሳሳት ፈልገሽ ነው፡፡››
‹‹እንዴት እንድትሳሳት እፈልጋለሁ?››
‹‹ከእሷ ጋር እንድንገናኝ እንደማትፈልጊ እኮ ከቅድሙ ንግግርሽ ተረድቼያለሁ፡፡ ደግነቱ አሁን ማን እንደሆነች አውቄያታለሁ ነገ ብቻ ይንጋ፡፡ ወደ ኃላ መመለስ አቃተኝ እንጂ ልክ እኔ ወደዚህ ስመጣ ነው እሷ ተበሳጭታ ስትወጣ ያየኋት፡፡››
‹‹እሷ ብቻ እኮ አይደለችም ተበሳጭታ የወጣችው እንዲያውም የእሷን ብስጭት አልተከታተልኩም፡፡ አሮጊቷ ግን አንገቷን ደፍታ ነበር እያዘነች የወጣችው፡፡››
‹‹በቃ ከአሁን በኋላ በራሴ መንገድ መሄድ ነው የምፈልገው ምክርም አልፈልግም፡፡ እንደውም ጥዋት እሸኝሻለሁ፡፡ የመጨረሻውን ፈተና ብቻዬን መጋፈጥ እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ተነሽ ወደ ሆቴላችን እንሂድ..… በጣም መጠጣት አምሮኛል፡፡›› በማለት መቀመጫውን ለቆ ውጪ ወደቆመው መኪና አመራ፡፡ ከኋላው ተከተለችው፡፡ ቀጥታ ያመሩት አልጋ ወደያዙበት ቢሾፍቱ አፋፍ ሆቴል ነበር፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቀጣዩ ክፍል ማታ #ሁለት #ሰዓት ይለቀቃል እስከዛው በብዛት ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ጠብቁኝ ቤተሰቦች 😘
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍104🥰13🔥6❤5