በጊዜው ታዲዬስ እሷን ከሸኘ በኃላ እረፍት አላገኘም…፡፡በምን ዓይነት መንገድ ይህቺን ልጅ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሊረዳት እንደሚችል በቀላሉ ሊገለጽለት አልቻለም፡፡ እንዲሁ በሀሳብ ሲባዝን አምሽቶ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን የቻለው፡፡ሞባይል ስልኩን አነሳና ያሰበውን ወደተግባር ለመቀየር ያግዙኛል ወዳላቸው ሶስት ሰዎች ጋር በተከታታይ የደወለው፡፡እቅዱን ለሁሉም በዝርዝር አስረዳና በእፎይታ እራሱን ለእንቅልፍ አሳልፎ ሰጠ፡፡
በማግስቱ ማለዳ 12 ሰዓት ነበር የአቶ ቂጤሳ ቤት በሶስት ሰዎች የተንኳኳው፡፡ድምፁን ሰምታ በድንጋጤ በመበርገግ በሩን ለመክፈት መኝታዋን ለቃ በራፍ ላይ ቀድማ የተገኘችው መርጊቱ ነች፡፡ ይሄ ያልተለመደ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው?ማን ሞተ..…?‹‹ተልባ ቆይዋ እያለች..ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት››የሚለው ሀገራዊ ብሄል በአዕምሮዋ ተሰነቀረ፡፡እሷን ማን ቀደማት?የትኛው ዘመድ ነው ከእሷ ጋር ፉክክር የገጠመው…?ማነው ቀድሟት የሞተው?ምን አለ አንድ ቀን ዘግየት ብሎ ቢጠብቋት ወይም ምን አለ አንድ ቀን ፈጠን ብትል? በሰከንዶች ሽርፍራፊ ይሄን ሁሉ እያሰላሰለች በራፉን ስትከፍት ሶስት ጎልማሳ ወንዶች በራፉን ሞልተው ቆመዋል፡፡
‹‹ምንድ ነው? ምን ተፈጠረ?››
‹‹ተረጋጊ ሰላም ነው፡፡››
‹‹በዚህን ሰዓት የምን ሰላም?››
‹‹ኧረ ሰላም ነው ፤ አባትሽን ማናገር ፈልገን ነው፤ቤተክርስቲያን ሳይሄዱ ልንደርስባቸው ስለፈለግን ነው በማለዳ የመጣነው፡፡
በድንጋጤ የሚንቀጠቀጠው ሰውነቷ ሳይረጋጋ ከበራፉ ገለል አለችና እንዲገቡ ፈቀደችላቸው፡፡
‹‹ግቡ ..ይቅርታ ቤቱ ግን እንደተዝረከረከ ነው፡፡››
‹‹አረ ግድ የለም፤ይልቅ አባትሽን ቀስቅሺልን፡፡››
‹‹እሺ ››ብላ ዞር ስትል አቶ ቂጤሳ ተነስተው ከመኝታ ቤታቸው በመውጣት ሳሎን ደርሰው ነበር::
መርጊቱ ትታቸው ወደ መኝታ ቤት ገባችና ጆሮዋን ግድግዳ ላይ ለጥፋ ማዳመጡን ቀጠለች፡፡
‹‹ሰዎች ምነው በሰላም ነው? አረ ቁጭ በሉ፡፡››
በተርታ ተገትራው የነበሩት ሶስት ሰዎች በአክብሮት እጅ እንደመንሳት አሉና ‹‹የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር መቀመጥ አንችልም፡፡››
‹‹እኮ ቁጭ በሉና ትናገራላችሁ፡፡››
‹‹ኧረ ግድ የለም ቆመን ይሻላል፡፡››
‹‹እሺ ምን እግር ጣላችሁ?››
‹‹ልጃችሁን ለልጃችን እንድትሰጡን ልንጠይቅ ነው፡፡››
‹‹ልጃችሁን ለልጃችን?››አቶ ቂጤሳ ቃሉን መልሰው ደገሙት፡፡መኝታ ክፍል ሆና ስታዳምጥ የነበረችው መርጊቱ የምትሰማው ነገር የተዓምር ያህል አስደነገጣት፡፡ማን ነው
ላኪው? መቼስ እዚህ ቤት ከእኔ ሌላ ሌላ ሴት የለም፡፡የትኛው አፍቃሪዬ ነው እኔን ሳያማክር ለጋብቻ ሚስኪኑ አባቴ ጋር የላከው? በፍቅር የሚጎመዣትና ስትወጣ ስትገባ የሚለክፏትን አንድ ሶስት ወንዶች በምናቧ መጡላት፡፡ከእነሱ መካከል አንድ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች፡፡ አሳቃትም፣ አሳዘናትም፡፡ሁለቱም ስሜት እኩል ነው የተሰማት፤አንድ ላይ ተዋህዶ አንድ ላይ ተጨፍልቆ፡፡መቼስ እርጉዝ መሆኗን እያወቀች ብትፈልግ እንኳን ይሄንን የጋብቻ ጥያቄ መቀበል አትችልም፤በሀጥያት ላይ ሌላ ሀጥያት አትጭምርም፡፡ጆሮዋን የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ እንደለጠፈች ሳሎን የሚካሄደውን ትዕይንት መከታተል ቀጠለች፡፡
‹‹ለመሆኑ ልጁ ማን ነው?››አባቷ ጠየቁ፡፡
‹‹እኮ ማ ነው? የእሱንና የቤተሰቦቹንም ማንነት ንገሩኝ?››
ያው እርሷ ባያውቁም ልጃችንና ልጆት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ፤ያው አሁን መምጣታችን ነገሩን ሁሉ በእርሷ ፍቃድ እንዲሆን ስለፈለግን ነው፡፡››
‹‹ሰዎች ለምን የጠየቅኳችሁን አትመልሱም..? ልጁ ማን ነው?››ጋሽ ቂጤሳ ትግስት አጠራቸው፡፡
መርጊቱ ደግሞ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የምትሰማው ነገር ግራ አጋባት‹…እንዴ እንዲህ አይነት ውሸት አለ እንዴ?ማነው እንዴህ በድፍረት አይን ያወጣ ውሸት አሲዞ ሽማግሌዎችን የሚልክ?እሱ ተዋርዶ እነሱንም የሚያዋርድ?›› ተንደርድራ ወጥታ ለሽማግሌዎቹም ለአባቷም ምንም አይነት ፍቅረኛ እንደሌላትና ማንንም ማግባት እንደማትፈልግ ነግራቸው ነገሩን ለማሳጠርና ሁሉንም ከድካም ለመገላገል ወሰነችና ወደ ሳሎን ሳሎን ለመግባት መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ አንድ እግሯን ስታነሳ ‹‹ጌታዬ ልጁ ታዲዬስ ነው፡፡››የሚል ድምጽ ከሽማግሌዎቹ ሰማች... ባለችበት ደንዝዛ ቆመች፡፡
‹‹ታዲዬስ….ታዲዬስ የቱ?››
‹‹ታዲዬስ መሀንዲሱ ..እዚሁ እርሶ ቤት የሚኖረው፡፡››
አቶ ቂጤሳ ከመደንገጣቸው የተነሳ በተቀመጡበት እጆቻቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ጫኑና አንገታቸውን ወደ መሬት ደፍተው ማሰላሰል ጀመሩ፡፡‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል?››አንድ ቀን እንኳን የረባ ጫወታ ሲጫወቱ፣ሲቀላለዱ ወይም ሲላፉ አጋጥሞቸው አያውቅም፡፡ሁለቱም እርስ በርስ ከመሳሳብ ይልቅ የመገፋፋት ባህሪ ነበር ዘወትር የሚያታይባቸው፡፡እንዴት ከእሷቸው በዚህን መጠን ግንኙነታቸውን መሰወር ቻሉ?
‹‹እሺ ያላችሁትን ሰምቼያለሁ፤ጉዳዩን ከልጅቷም ከዘመድ አዝማድም ጋር ልማከርበትና መልሱን ለሳምንት ልስጣችሁ፡፡››
በደመነፍስ እግሯን እየጎተተች በጓሮ በር ወጥታ ወደ ታዲዬስ ክፍል አመራች፤አንኳኳች፤ ከፈተላትና ወደ መኝታው ተመለሰ፡፡ ምንም ሳትናገር ወደውስጥ ገባችና በራፉን ዘጋችውና ወደ አልጋው በመውጣት ከውስጥ በመግባት ዝም ብላ ከጎኑ ተኛች፡፡ በአድናቆትና በዝምታ ተመለከታት፡፡ በጣም ደንግጣለች፤ በእንቅልፍ ልቧ እየተጓዘች የመጣች ትመስላለች፡፡ዝም ብሎ አይኖቾ እንባ ያመነጫሉ፡፡ከሃያ ደቂቃ የዝምታ ጊዜ በኃላ << ታፈቅረኝ ነበር እንዴ?››በማለት ያልጠበቀውን አደናጋሪ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
ግራ ተጋባ‹‹ምን አልሺኝ?››
‹‹ታፈቅረኝ ነበር ወይ ?ሳትዋሽ ንገረኝ፡፡››
‹‹በፍቅር እኮ ውሸትም ይሉኝታም አይገባም፤ፈጽሞ አፍቅሬሽ አላውቅም፡፡››
ሰውነቷ በደቂቃዎች እንደበረዶ ቀዘቀዘባት‹‹ታዲያ ለምን?አስበኸዋል ግን? ሰው ያፈቀረውን እንኳን ለማግባት ሞራል ባጣበት ጊዜ አንተ የማታፈቅራትን ለዛውም እርጉዝ የሆነችን ሴት ለማግባት መስዋዕትነትን ለመክፈል የፈለከው ?ነው ወይስ የውሸት ድራማ እየተጫወትክ ነው፡፡?››
‹‹የውሸት አይደለም፤ የእውነት ነው የማገባሽ..ማለቴ እንጋባለን፤አብረን እንኖራለን፡፡…ያለምንም ግንኙነት፤ልጅሽን ወልደሽ ሁኔታዎች ከተስተካከሉ በኃላ አልተስማማንም ብለን እንፋታና አንቺም የፈለግሽውን ማለት የሚያፈቅርሽንና የምታፈቅሪውን ታገቢያለሽ፤ እኔም እንደዛው፡፡››
‹‹እኮ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ለምን ለመግባት ፈለክ?እኔ ምን አድርጌልህ አውቃለሁ? አንድ ቀን እንኳን ልብስህን ልጠብልህ ወይም ቤትህን ላፅዳልህ ብዬህ አላውቅ፡፡››
ስለተደረገልሽ ብቻ አይደለም የሆነ ነገር ማድረግ ያለብሽ፡፡ደግሞም ላንቺ ብዬ አይደለም፤ ለአባትሽ ስል ነው፡፡አንቺ እንዳልሽው በዚህ ዕድሜያቸው ጥለሻቸው ብትጠፊ እርግጠኛ ነኝ ለአንድ ወር በህይወት አይቆዩም፤በመጨረሻ ዕድሜያቸው ለእሳቸው ይሄ አይገባቸውም፡፡››
✨ይቀጥላል✨
ዛሬ በጠዋት ተከስተናል ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ እስከማታ የተወሰነ ሰው #Sebscribe ካደረገ በክፍል #31 እንገናኛለን #Shareም አይረሳ አመሰግናለሁ፡፡
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍120❤12😱5😢2
አየሽ እኔ ስራን የምሰራው ለብር አይደለም እያንዳንዱን የህይወት ዘርፍ ለማጣጣም እንዲያመቸኝ ነው፡፡ሳይት ኢንጂነር
ሆኜ ሰርቼያለሁ፤የሆቴል ማናጀር ሆኜያለሁ፤ተሸካሚ ሆኜ ሰርቼ አውቃለሁ፤ ዌይተርም ነበርኩ፤ አስተማሪም ሆኜ ሰርቼያለሁ..ብዙ ብዙ ነገር፡፡ይሄንን የማደርገው ከነዛ የስራ ዘርፎች የሚገኘውን የህይወት ልምድ ቀጥታ ለማግኘት ስል ነው፡፡››
‹‹የሚገርም ነው!!!የወደፊት እቅድህን ልትነግረኝ ትችላለህ?››
‹‹የወደፊት ዕቅዴ ህዝብና መንግስትን ማሳቀቅ ነው፡፡››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹አየሽ... ሰሞኑን የተዋወቅሻቸው አምስት ልጆቼን በየተሰጥኦዋቸው የመጨረሻው ስኬት ላይ እንዲደርሱ ማገዝ ነው ዋና የህይወት ግቤ፡፡…ያ ሲሆን ደግሞ እነዚህ ልጆች ከበረንዳ ኑሮ ከቆሻሻ ላይ ተነስተው የሀገሪቱ ምርጥ ሰው ሆነው ሲገኙ..መንግስትም ሆነ ማንም ገንዘብ አለኝ የሚል ግለሰብ ስንቱ ምጡቅ
አዕምሮ ያለው ትውልድ በየቆሻሻው ባክኖ እንደቀረ ማሰብና መቆጨት ይጀምራል፡፡ከዛም ከአንድ ሺ መካከል አንድ ሰው እንኳን የእኔን ልጆች ስኬት ተመልክቶ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ቢነሳ ጎዳና ባክኖ የሚቀር አንድ ህፃን እንኳን አይገኝም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ በአጠቃላይ እኔ ይሄንን አድርጌያለሁ ... እናንተስ ?...ለማለት ነው..፡፡የተግባር ስብከት ለመስበክ፡፡››
ቀጣይ ምን እንደምትጠይቀው እያሰላሰለች ሳለ የእሱ ስልክ ድምፅ አሰማ፡፡
<ሄሎ ሰላም::>>
<<ሄሎ>>
<<ምን?>>
‹‹መጣሁ...በቃ ሄለን ሞባይሉን ስጫትና ከኋላ ትከተለው ..ደውዬላት ያሉበት ድረስ ሄዳለሁ፡፡›› ስልኩን ዘጋው፡
‹‹ምነው? ምን ሆንክ?››
‹‹ሙሴ ከግቢ ወጥቷል ...ሂሳብ ክፈይና እንሂድ፡፡››ከቦርሳዋ ብር አወጣችና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ በመነሳት ወደመኪናው አመራች ፡፡እሱም ተከትሏታል፡፡ የተፈጠረው ችግር አልገባትም፡፡
ከግቢው ወጥተው መንገድ እንደያዙ‹‹አልገባኝም..ሙሴ ከግቢ መውጣቱ ችግር አለው?››
‹‹አዎ..ሙሴ ትንሽ ክትትል የሚፈልግ ልጅ ነው፤ከግቢ የሚወጣው ብዙውን ጊዜ የሆነ ነገር ለመስራት አስቦ የሆነ ቁሳቁስ ሲያጣ ፍለጋ ነው፡፡››
‹‹ከየት ነው የሚፈልገው?››
‹‹ከየመንገዱ.፤ከየቆሻሻ መጣያው...የፈለገውን እሲኪያገኝ ድረስ ሲባዝን ነው የሚውለው..ካጣ ደግሞ ስለሚ።በሳጭ ያመዋል፡፡››
‹‹ምንድነው የሚያመው?››
‹‹የሚጥል በሽታ አለበት፡፡ሙሴ ተአምራዊ የሆነ የፈጠራ ብቃት አለው፡፡ ይሁን እንጂ በዛው ልክ ታማሚ፤ከሰው የማይግባባ፤የትምህርት ለመማር የሚያዳግተው የተለየ ልጅ ነው፡፡››
‹‹ቆይ ..አንድ የማይገባኝ ነገር እንዲህ የተለየ የፈጠራ ብቃት እያለው ትምህርት ለመማር እንዴት ይከብደዋል?››
‹‹በዚህ አለም የትምህርት ስርዓት ስትማሪ በካሪኩለሙ በተቀመጠው ልክ ካልተጓዝሽ ደደብ ነሽ፡፡››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ማለቴ ሰነፍም ከሆንሽ…በጣምም ከመጠን ያለፈ ጎበዝ ከሆንሽ በተመሳሳይ ‹ደደብ ነሽ >ነው የምትባይው...ምክንያቱም ሰነፍ ስትሆኚ የእውነት አንቺ አታውቂም ...በጣም ጎበዝ ስትሆኚ ደግሞ አንቺ ባወቅሺው መጠን
ካሪኩለሙም አስተማሪዎችሽም አያውቁም፡፡
የዛን ጊዜ ታዲያ መቼስ ማንም ቢሆን አስተማሪው አያውቅም ማለት ስለማይደፍር አንችኑ ደደብ ነሽ ይልሻል..ያሸማቅቅሻል፡፡
ሙሴን ያጋጠመው እንደዚህ አይነት ሁኔታ
ነው፡፡ለምሳሌ ሁለተኛ ክፍል ሆኖ አንድ ዶሮ ሲደመር ሶስት ዶሮ ስንት ይሆናል ? የሚል ጥያቄ ፈተና ላይ ቀረበለት፡፡ለዚህ ጥያቄ
አስተማሪው ከእሱ የሚጠብቀው መልስ አራት
ዶሮ የሚል ነበር፡፡እሱ ግን ‹መደመር አይቻልም> ብሎ መለሰ፡፡ ኤክስ አገኘ፡፡‹ አልተሳሳትኩም›ብሎ ክርክር አስነሳ << ..አንዱ ዶሮሴት..ሌላው ወንድ..አንዱ ጥቁር ሌላው ቀይ..አንዱ 5 ኪሎ ሚመዝን ሌላው 3 ኪሎ
ሚመዝን ሊሆን ይችላል፤ታዲያ እንዲህ በስም ካልሆነ በስተቀር በምንም የማይመሳሳሉ
የተለያዩ ነገሮች አንድ ላይ ጨፍልቆ አምስት ዶሮዎች ማለት ትልቅ ስህተት ነው ብሎ ሀሳቡን አብራራ፡፡ከእኔ በስተቀር ማንም ሀሳቡን
ሊረዳው የፈለገ ሰው አልነበረም፣አስተማሪዎቹ
ሳይቀሩ እንደጅል ነበር የቆጠሩት፡፡››
‹‹እውነትም እንክብካቤ የሚገባው ልጅ ነው››አለች ዶ/ር ሶፊያ በሙሴ ሁኔታ ውስጧ ተነክቶ፡፡ ታዲዬስም ሄለን ጋር ደወለ የሚገኙበትን ቦታ ነገረችው፤ ተቃርበዋል፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ በጣም ቀንሳችኋል እስካሁን የተወሰነ ሰው ነው #Sebscribe ያደረገው ከዚ ፖስት በኋላ አንድ 20 ሰው እጠቦቃለው ሃሳባችን ከሞላ ጠዋት በክፍል 33 እንገናኛለን አመሰግናለው።

👍104❤12🥰1😱1
ትንግርት ታዲዬስን ለመጨበጥ በአየር ላይ የዘረጋችው እጇን እንዳንከረፈፈች ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ ዶ/ር አዞረች፡፡በህይወቷ መቼም ፊት ለፊት አገኛታለሁ ብላ ለሰከንድ እንኳን አስባ የማታውቀውን ሰው ፊት ለፊት ስታይ አፏን ከፈተች.. ለደቂቃዎች ሁለቱም ደንዝዘው በፀጥታ ተፋጠጡ፡፡ ሶስት ወንዶች ግራ ገባቸው፡፡
በመጋባት ጠየቀ::
‹‹እጅግ በጣም እንተዋወቃለን ››ብላ ስትናገር እና ጠረጴዛ ላይ ያለውን የለስላሳ ጠርሙስ አንስታ ዶክተሯ ጭንቅላት ላይ ስትከሰክሰው አንድ ነበር፡፡በሰከንዶች ቅፅበት በአከባቢው ከፍተኛ ግርግርና ድንጋጤ ተከሰተ፡፡.ዶ/ር ሶፊያ መላ ፊቷ በደም ተሸፍኖ እራሷን ስታ ተቀምጣበት ከነበረበት ወንበር ወደ ኃላዋ ተገነደሰች፡፡
<< ምን ነካሽ አብደሻል እንዴ…?››ኤልያስ
‹‹እንዴ ምነካሽ ?እኛን እንኳን አታከብሪም?››ጋዜጠኛው አመነጫጨቃት፡፡ ታዲዬስ ዶ/ር ሶፊያን በክንዶቹ አቅፎ ግራ በመጋባት ትንፋሿን ያዳምጣል፡፡
ከ5 ደቂቃ በኃላ ታዲዬስ እና ኤልያስ ዶ/ር ሶፊያን ለህክምና ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች በአፋጣኝ ደርሰው ወንጀለኛዋን ትንግርትን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አመሩ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ነው በጣም አመሰግናለው
አሁንም #Sebscribe ያለደረጋቹ እያደረጋቹ #ትንግርት እስከሚያልቅ 500 ##Sebscriber እጠብቃለሁ በቅድምያ ለሁላችሁሜ አመሰግናለሁ።

👍69❤15🤔6😱6