አትሮኖስ
264K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
418 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ይዘዋት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን እዚህ ከመጣች በኋላ ያልጠበቀችውን ነገር ስላየች መገረሟ አልቀረም፡፡ ያየችውን አይታ ከተመለሰች በኋላ ግን በአማርኛ መፀለዩን ትታ በእንግሊዝኛ መፀለይ ጀመረች:: ወላጆች ያልጠበቁት ነገር ስለነበር ግራ ተጋቡ፡፡ እነሱ የጠበቁት ሀገሯ ቆይታ ስለመጣች፤ አማርኛ መናገርንም ቢሆን በመጠኑ አሻሽላ ስለነበርና አገሯን አይታ ከመጣች ብቻ በአማርኛ እንደምትፀልይ ቃል ገብታ ስለነበር በአማርኛ መፀለዩን አጠናከራ ትቀጥላለች እንጂ ከእነ ጭራሹ እንዲህ እርግፍ አድርጋ ትተወዋለች ብለው ስላልገመቱ ግራ ገባቸው:: አባትና እናት በሁኔታው በመናደድ በአማርኛ ብቻ እንድትፀልይ ለመገፋፋት ቢሞክሩም ልጂት ግን ፍንክች አልል ስላለች ግራ የተጋባው አባቷ ማስፈራራቱን ትቶ በለዘብታ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ልጅቷን ይጠይቃል:: እሷም ደረቷን ነፋ አድርጋ፤ “አይ አባዬ ከአሁን በኋላ በእንግሊዝኛ እንጂ በአማርኛ አልፀልይም፡፡ ጌታ የሚሰማው እንግሊዝኛ እንጂ አማርኛ አይሰማም" ትላለች:: አባት ግራ ተጋብቶ "እንዴት አይሰማም? ምን ማለትሽ ነው?' ይላል፡፡

"እግዚአብሄር አማርኛ ስለማይሰማ እንጂ እነዛን ኢትዮጵያኖች የሚበሉት የማይጣፍጥ ምግብ፣ የሚለብሱት ያደፈና የተቦጫጨቀ ልብስ፣ ቤታቸው ደላላ፣ የማያምርና ንፅህና የሌለው፣ ከተማቸው አስቀያሚ ሆና እያለ ተቀምጠው እንደዚያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው፣ ያውም እንደኛ ሳይሆን ያንን 나사 ሰዓት ቆመው እየለመኑት፣ አይጨክንባቸውም ነበር። አማርኛ የሚሰማ ቢሆን ኖሮማ እነሱንና ሀገራቸውን ከድህነት ያወጣቸው ነበር" ብላ ቁጭ፡፡ የመከላከያ ምስክሮች የሚሰሙበት ቀን ደርሶ በተለመደው ሁኔታ እጅ በካቴና ከሌላ እስረኛ ጋር ተቆራኝቶ ወደ ፍርድ ቤት ሄድኩ:: አሁን አሁን እጂ በካቴና ታስሮ ስሄድ ለምን እንደሆን ሊገባኝ ባይችልም መሳቀቁ ግን ትቶኛል:: ምናልባት ወንጀለኛ መሆኔን ተቀብዬው አሊያም ከዚህ በኋላ በከርቸሌ ለማሳልፈው ሕይወት ሰው አየኝ አላየኝ የሚለው ይሉኝታ ትርጉም አልባ ሆኖብኝ ሊሆን ይችላል:: ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ዛሬ ከሌላው ቀን ይልቅ ተረጋግቼ ወደ ፍርድ ቤቱ ያመራሁት:: ወደ ውስጥ እየገባሁ ሳለ ምን እንደሚመሰክሩልኝ ባላውቅም ምስክር ብዬ የጠራኋቸውን ኤልሳንና አለሚቱን እንዲሁም ጠበቃዬን አየኋቸው፡፡ ሳጥኑ ውስጥ ቆሜ ከምስክሮቼ አፍ እኔን ነፃ የሚያወጣ ቃል እንደማላገኝ ስለገባኝ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሰማኝ፡፡ዳኛው መዝገቡን እያዩ በመሀል ደግሞ ቀና እያሉ ይመለከቱኝና መልሰው ንባባቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንደሚመስለኝ ቀና እያሉ የሚያዩኝ የወንጀሉን አስከፊነት እያነበቡ ፊቴ የገዳይ ፊት ዓይነት መምሰል አለመምሰሉን ለማረጋገጥ ሳይሆን አይቀርም :: በመጨረሻም መነፅራቸውን _ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ቤቱን ግራና ቀኝ ሲያማትሩ ከቆዩ በኋላ ጠበቃዬ አለኝ የሚለውን የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርብ ዕድል ሰጡት፡፡ በመጀመሪያ ለምስክርነት የቀረበችው እጮኛው ኤልሳ ስለነበረች ጥያቄ ለመጠየቅ ሲዘገይ በማየቴ፤ ሁለት ፍቅረኛሞችን ጠያቂና ተጠያቂ በማድረጌ ስህተት የፈፀምኩ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ነገር ግን ችግር ቢኖረው ኖሮ የእሷን ስም ስጠራለት ጠበቃዬ አይሆንም ይለኝ ነበር ብዬ ተፅናናሁ፡፡ ኤልሳ በተለመደው ሁኔታ ማንነቷን ከተናገረችና በቃለመሀላ እውነት ብቻ እንደምትናገር ካረጋገጠች በኋላ ጠበቃዬ ጥያቄውን ጀመረ፤ “ወ/ት ኤልሳቤጥ፣ አቶ አማረን የት ነው የሚያውቋቸው?'' “ዩንቨርስቲ አብረን ስንማር ነው'' ።

*ትውውቃችሁ በምን ደረጃ ነበር?" "መጀመሪያ የእኔና የሟች ጓደኛ ነበር፣ በኋላም የእሷ ፍቅረኛ ነበር አለች። “በአቶ አማረና በሟች መካከል የነበረው የፍቅር ግንኙነት እንዴት חל::" *መጀመሪያ ላይ በጣም ይፋቀሩ ነበር፣ በኋላ ግን እሱ ከትምህርት ቤት በመባረሩ የተነሳ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ነበር"። “ግንኙነታቸው በምን ምክንያት እንደተቋረጠ ያውቃሉ'። “በትክክል ለመናገር ይከብደኛል፣ እሷን ስጠይቃት እሱ እንደከዳት፣ እሱን ስጠይቀው ደግሞ እሷ እንደከዳችው ይናገሩ ስለነበር ትክክለኛውን ምክንያት ማረጋገጥ አልቻልኩም':: *ወ/ት ኤልሳቤጥ፤ አልማዝ ዲያሪዋ መጨረሻ ላይ አንድ ነገር ለማጣራት ወደ እርሶ ዘንድ እየመጣች እንደነበር ፅፋለች፣ የምትመጣበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለእርስዎ ነግራዎት ነበር?'' "የምታጣራው ነገር ስላለ እንደምትመጣ ከመንገር ውጪ ለምን እንደምትመጣ አልነገረችኝም" :: “ወደ እርስዎ እንደምትመጣ ከእርሷ ሌላ የሚያውቅ ሰው ነበር? ወይም እርስዎ የነገሩት ሰው ነበር?'' “የሚያውቅ ስው ይኑር አይኑር አላውቅም፣ እኔ ግን ለማንም አልተናገርኩም"፡፡ “ተከሳሹ ይህንን የሚያውቅበት መንገድ ይኖራል ብለው ይገምታሉ?'' “ይህንን በእርግጠኝነት መመለስ ያዳግተኛል"፡፡ ተሾመ እሷ ልካው ከአልማዝ ጋር መገናኘቱን አስመልክቶ የካደው ሳያንስ እሷ ስትደግመው ስሰማ ደግሞ የነበረኝን ጥርጣሬ ይበልጥ አጠናከረው፡፡ አልማዝ ዲያሪዋ ላይ እንደፃፈችው፤ ሁል ጊዜ ተሾመ እየመጣ አልማዝን የሚያስፈራራትና የሚመታት ኤልሳ ምክንያት ፈጥራ ከእሷ ከተለየች በኋላ ነበር፡፡ ያ ማለት ደግሞ ሌላ ሳይሆን ኤልሳ ያኔ ስታደርግ የነበረውን ድርጊት ነው የደገመችው ማለት ነው፡፡ አቃቢ ሕግ ጥያቄውን ቀጠለ፤


...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_19


"እሺ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ፤ ከተከሳሽ ጋር በጓደኝነት ባሳለፋችሁት ግዜ ውስጥ እንደተገነዘቡት ምን ዓይነት ጠባይ ነበረው። “አማረ ትሁት፣ ከአፉ ክፉ ቃል የማይወጣ፤ ተግባቢና ተወዳጅ ልጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አልማዝን በጣም ስለሚወዳት በእሷ ሲመጡበት ብቻ ነው ሲናደድ ያየሁት" በማለት መለሰች፡፡ "አመሰግናለሁ" ብሎ ጠበቃዬ ተቀመጠ። አቃቤ ሕግ በተራው ተነስቶ መስቀለኛ ጥያቄ እየጠየቀ እኔን ወንጀለኛ የሚያደርግ ቃላት ከአንደበቷ ጎትቶ ለማውጣት መታገል ጀመረ:: *ወ/ት ኤልሳቤጥ፤ ቀደም ሲል እንደተናገሩት ከሆነ ሟችና ተከሳሽ በምን እንደተለያዩ አላወቁም፡፡ ተክላሽ ከማች ጋር አልፎ አልፎ ግቢ ውስጥ ይጣሉ እንደነበር ይወራል፣ ይህ በምን ምክንያት ነው"፡፡ “አልፎ አልፎ ሟችን ዶ/ር አድማሱ የተባለ መምህሯ ያስጠናት ስለነበር በብዛት ወደሱ ቤት እየሄደች ታጠና ነበር:: በዚህም የተነሳ እሱም ይህንን ስላልወደደው እሱ ጋ መሄዷን እንድታቆም ይጨቀጭቃት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህም ሆኖ ትምህርት ቤት እያሉ በዚህ ምክንያት ተጣልተው አልተለያዩም"፡፡ *ጥሩ! ምክንያቱ ይህ ካልሆነ፣ ተከሳሽ ከትምህርት ቤት ከተባረረ በኋላ ከእሷ ጋር የተለያየበት ምክንያት ምንድነው?"፡፡ "እኔ አላውቅም"፡፡ “ቅድም እንደነገሩን ተከሳሻ በቅናት የሚጣላ ከሆነ በቂም በቀል ተነሳስቶ ለመግደል የሚስችለው ምክንያት አለ ብለው አያምኑም?" ብሎ ሲጠይቅ፤ ጠበቃዬ ተነስቶ ተቃውሞ አለኝ አለ፡፡ ዳኛው ተቀውሞውን እንዲያሰማ ዕድል ሰጡት፤ “ክቡር ፍ/ቤት፤ ተጨባጭ መረጃ በሌለበት ሁኔታ ምስክሯ በግምት ይህንን ጥያቄ ልትመልሰው መገደድ ስለሌለባት ጥያቄው ውድቅ ቢሆን' አለ፡፡ ዳኛው ተቃውሞውን ተቀብለው ሌላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ አዘዙ፡፡ አቃቤ ሕግም ለዚህ ብዙም ሳይጨነቅ! *ቀደም ሲል እንደተናገሩት ተከሳሽ ትሁት ቢሆንም በአልማዝ ላይ ከመጡበት እንደሚበሳጭ ተናግረዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ አብራችሁ በነበራችሁበት ወቅት ተከሳሽ ከአንድ ተማሪ ጋር ተጣልተው ነበር ይባላል፣ ምክንያቱ ምን ነበር?''

“አዎ! አንድ ጊዜ ብቻ መጣላቱን አስታውሳለሁ፡፡ እሱም አንድ ተሾመ የሚባል ተማሪ ሟችን አፈቀርኩሽ እያለ በግድ ከእሱ ጋር እንድትሆን ያስቸግራት ነበር፡፡ እሷ ግን ፍቃደኛ አለመሆኗን ስለነገረችውና በዚሁ የተነሳ ስለመታት፣ አማረ ተናዶ ከእሱ ጋር መደባደቡ ትዝ ይለኛል" አለች፡፡ አቃቤ ሕግ ይህንን ሲሰማ ጨርሻለሁ በማለት እየተኩራራ ወደ መቀመጫው አመራ፡፡ ከኤልሳቤጥ ምስክርነት ጠበቃዬ ምን ጠቃሚ ነገር እንዳገኘ ለማወቅ ቢያዳግተኝም እኔ ግን የመሰከረችብኝ እንጂ የመሰከረችልኝ መስሉ አልተሰማኝም፡፡ የእሷን የምስክርነት ቃል ከጠበቃዬ ይልቅ አቃቢ ህግ “አልማዝን ላለማጣት የተደባደበ ሰው፣ በፍቅሩ ከመጡበት ሰው ለመግደል አይመለስም" የሚለውን ለማሳየት ተጠቅሞበታል፡፡ ይህንንም ጥያቄ እንዲያነሳ ፍንጭ የሰጠችው እሷ ነች፡፡ የእሷ ምስክርነት አልማዝ ከተሾመ ጋር ተያይዞ በኤልሳ ላይ የነበራትን የቀድሞ ጥርጣሬ እኔ ላይ አስፍኖ በማለፉ የተስፋ መቁረጥና የፍርሀት ስሜት ወረረኝ። ሌላዋ ምስክሬ አለሚቱ ስትሆን እሷም ብትሆን ጥሩ ጠባይ እንዳለኝና አንድ ቀንም ከሰው ጋር ተጣልቼ እንደማላውቅ ከመመስከር ውጪ ምንም የፈየደችው ነገር አልነበረም፡፡ ቢያንስ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቀን ቤት ውስጥ እንደነበርኩ ትመሰክራለች ብዬ ብጠብቅም፤ የዛን ቀን የት እንደዋልኩ እንደማታስታውስ በመናገሯ ለእኔ ምንም የጠቀመኝ ነገር አልነበረም፡፡ ለነገሩ እኔ በወቅቱ ተናደድኩባት እንጂ እንኳን እሷ እኔ ራሴም ብሆን የዛን ቀን የት እንደነበርኩ አላስታውስም፡፡ በመጨረሻም ዳኛው ለመስከረም 15/1981 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተውን ወጣን፡፡ ከፍርድ ቤት ወጥቼ ወህኒ ቤት እንደገባሁ ዙሪያ ገባውን እየቃኘሁ ብዙ ሳሰላስል ከቆየሁ በኋላ በእርግጠኝነት ይህ "ቤቴ" ከደጁ መሻአሉን አረጋገጥኩ፡፡ ቢያንስ እዚህ ያለነው አስተሳሰባችን አንድ ነው:: የምናስበው ስለ ዛሬ ነው እንጂ አንዳችንም ነገ ስለሚሆነው ነገር አንጨነቅም፡፡ ሁላችንም የምንኖረው ለዛሬ ነው:: ለእኛ ህይወት ዛሬ ነች፤ ነገ ግን የሌሎች ናት:: ለዛሬ ስንል ነው ነጥቀን የምንበላው፣ የዛሬ ሆዳችንን ለመሙላት ስንል ነው ሕይወት የምንቀጥፈው፣ ለዛሬዋ የቅጽበት ደስታ ስንል ነው ሴት ደፍረን የምንታሰረው:: አርቆ የሚያስብ ሰውማ እንዴት ወንጀለኛ ሊሆን ይችላል:: ታዲያ እኔም እዚህ በሰላም ያለጭንቀት ለዛሬ ብቻ እኖርና ወደ ውጪ በወጣሁ ቁጥር ግን ዛሬ ማን ይመሰክርብኝ ይሆን? ምን ብሎ ይመሰክርብኝ ይሆን? ይፈረድብኝ ይሆን? በማለት ስለነገ ሕይወቴ መጨነቅ እጀምራለሁ፡፡ አዎ! ይህንን ሳስብ አልማዝ ዲያሪ ላይ ያነበብኩት የሱማሌውና የጤፉ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡

"ያባው! አሊያ አንተ አላህ ሆንክ ወይስ ከአላህ ጋር ተማክረሀል? እንዴት አንድ ዓመት ሙሉ በሕይወት እንደምትኖር እርግጠኛ ሆንክ?" ያለው ያኔ ለኔ ባይታየኝም ትክክለኛ ጥያቄ ነበር። ለካስ እነሱ ሁልጊዜ ለዛሬ ብቻ የሚመገቡትን የሚገዙትና ስለነገ ሲያወሯቸው “ኢንሻ አላህ" የሚሉት፣ ሁል ጊዜ የዛሬን ብቻ ስለሚኖሩ ነበር! የፍርድ ቤቱ ውሎ እንደጠበቅሁት ስላልሆነልኝ እስር ቤት ከገባሁ በኋላ ለጓደኞቼ "ውሎ እንዴት ነበር?" ጥያቄ መልስ ሳልሰጥ ቆዝሜ ተቀመጥኩ፡፡ ጓደኞቼ ማፅናናቱ ሲሰለቻቸው በተለያየ መንገድ ሊያስቁኝ ሞከሩ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ቀልዶች እኔን የሚያስቁ አልነበሩም፡፡ ይልቁንም ቀልዱን ትተው ቁምነገር ማውራት ሲጀምሩ ሳልወድ በግድ ሳቅሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ለዶክትሬት ዲግሪ ጥቁር አንበሳ ይማር የነበረ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ በአንድ ትምህርት ኤፍ (F) የሰጠውን አስተማሪ ውጤቱን እንዲያስተካክልለት እያለቀሰ ቢለምነውም ከመራራት ፋንታ በቀልድ መልክ፤ "አይዞህ አትጨነቅ ወጣት ነህ፣ ገና በመጀመሪያው ዓመት እንዲህ የተልከሰከሰ ነጥብ ይዘህ ቀሪ አምስት ዓመታትን በጭንቀትና በለቅሶ ከማሳለፍ እንደገና ማትሪክ ተፈትነህ ዕድልህን ብትሞክር ይሻሻል" ሲለው በንዴት ራሱን መቆጣጠር ተስኖት በቡጢ ፊቱ ላይ መትቶት ጥርሱን ይሰብረውና እስር ቤት ይገባል፡፡ ይህ እስረኛ እስር ቤት ውስጥ የሚጠራው በስሙ ሳይሆን ዶክተር እየተባለ ነው፡፡ ለአብዛኛው በተለይ ፊደል ላልቆጠረው እስረኛ ዶክተር ማለት ደግሞ የማያውቀው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ታዲያ የዛን ቀን አንዱ እስረኛ የተለያዩ የማያውቃቸውን ጥያቄዎች ይጠይቀው ነበር፡፡ ጠያቂው እስረኛ ቅማል አማሮት ኖሮ ከልብሱ ላይ ቅማል እየገደለ፤ “ስማ እንጂ ዶክተር፤ እነዚህ ቅማሎች እንዴት ነው የሚራቡት? እኔ በየቀኑ እገላቸዋለሁ፣ እነሱ ግን የበለጠ ቁጥራቸው እየበዛ ይፈለፈላሉ፡፡ ለመሆኑ እናትየው በየደቂቃው እያረገዘች መንታ መንታውን ነው እንዴ የምትወልደው?'ይለዋል፡፡ ዶክተሩ ለጥቂት ደቂቃዎች ተንከትክቶ ይስቅና ሲቃ እንደያዘው፤ "ስማ እንጂ፤ ለመሆኑ ማነው ቅማል ታረግዛለች ያለህ? ቅማል አታረግዝም፡፡ እንቁላል እየጣለች ነው የምትራባው" ይለዋል፡፡ _ እስረኛው ስለተሳቀበት ሀፍረት እየታየበት፤ "ውይ! ተወው ረስቼው ነው፡፡ ቅጫም ለካስ የቅማል እንቁላል ነው" ይለዋል፡፡ ሌላኛው እስረኛ ቀበል አድርጎ፤
"አንተ ደግሞ የምትጠይቀው የጅል ጥያቴ ነው፡፡ ከጠየቅህ አይቀር ከበድ ያለ ጥያቄ አትጠይቅም" ይለውና፤ "እሺ ዶክተር እሱን ተወውና መርፌ እንዴት ነው የሚሰራው?” ይለዋል፡፡ ዶክተሩም ጥያቄው አልጥም ስላለው፤ "አላውቅም" ይለዋል፡፡ እስረኛው በአሸናፊነት መንፈስ፣ “አዬ! ለካ ያንተ ዶክተርነት የውሸት ነው! መርፌ እንኳን እንዴት እንደሚሰራ የማያውቅ ዶክተር ምን ዶክተር ይባላል" ብሎ- ሲናገር፣ በመጀመሪያው ጥያቄ አፍኜው የነበረውን ሳቄን መቆጣጠር ተስኖኝ ለቀቅሁት፡፡ ዶክተሩ ለማስረዳት በመሞከር ፋንታ ከእኛው ጋር ይስቅ ጀመር፡፡ ፍርድ ቤት መመላለሴ የቀጠለ ቢሆንም የመጨረሻው ውሳኔ ግን ከመቅረብ ይልቅ ይበልጥ እየራቀብኝ መጥቷል፡፡ በመጀመሪያዎቹ የቀጠሮ ቀናት ፍርድ ቤት በቀረብኩ ቁጥር ፍርዴን የምሰማ እየመሰለኝ እጓጓ እንዳልነበር፤ ዛሬ ግን የምናፍቀው የመጨረሻው ፍርድ እንዲህ በቀላሉ እንደማይገኝና ወደ ፍርድ ቤት የምሄደው የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስማት ሳይሆን ሌላ ቀነ ቀጠሮ ለመቀበል መሆኑ ከገባኝ ሰንብቷል፡፡ ስለዚህም ወደ ፍርድ ቤት መሄድ የሚናፍቀኝ ተናፍሶ ለመምጣት ካልሆነ በስተቀር ሌላ አዲስ ነገር ይዞ እንደማይመጣ ተረድቼአለሁ፡፡ ቀናት በቀናት እየተተኩ፣ ወራት በወራት ላይ እየተደራረቡ ወደ ዓመታት እየተለወጡ ቢሆንም ያ የምናፍቀው ፍርድ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አልሆነም:: ግን ምን ዓይነት ፍርድ ነው የምጠብቀው? የሞት ፍርድ እንደማይሆን ጠበቃዬ ነግሮኛል:: ታዲያ ፍርዱ ምን ሊሆን ይችላል? ዕድሜ ይፍታህ አሊያም በነፃ መለቀቅ እንጂ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም:: ለእኔ ደግሞ ከሁለተኛው ይልቅ የመጀመሪያው አማራጭ የተሻለ ነው:: የአካል ነፃነት ብቻ ለእኔ ትርጉም ስለማይኖረው፡፡ ከአሁን በኋላ ብፈታም አልማዝ በሌለችበት ዓለም ውስጥ መኖር ለእኔ ትርጉም የለውም፡፡ እርግጥ ከአልማዝ ጋር ከተለያየሁ በኋላ ብዙ ጊዜያትን እሷ በሌለችበት ሁኔታ አሳልፌአለሁ፡፡ ግን “አንድ ቀን ትመጣ ይሆናል" የሚለው ተስፋዬ አብሮኝ በመኖሩ በሕይወት መኖር አላስጠላኝም ነበር፡፡ ዛሬ ግን አንድ ቀን ትመጣ ይሆናል የሚለው ተስፋዬ በመጥፋቱ ሕይወቴ ለእኔ ትርጉመ ቢስ እንደምትሆን አልጠራጠርም። በበኩሌ የሕይወቴን ፋይል ከዘጋሁ ቆይቼያለሁ፡፡ ፋይሉን ለመዝጋት የቀፈፈው ግን ፈጣሪ ነው:: ገና ያዘጋጀልኝ ብዙ የሥቃይና የመከራ ሕይውት ስላለ እሱን በተከታታይ ሳልጋት ፋይሉን ዘግቶ ሊያሰናብተኝ አልፈለገም፡፡ እርግጥ ዕድሜ ልክ መታሰሩም ቢሆን ነፃ ከመውጣት ይሻል ይሆናል እንጂ የሥቃይን ምእራፍ የሚዘጋው አልነበረም:: ግን ምን ያደርጋል? እሱንም

ማጣት እንደሌለብኝ ውስጤ የሚያምን ቢሆንም ለኤልሳ እርካታና ለጠበቃዬ ስል ለእኔ የተሻለውን አማራጭ ለማጣት እየተፍጨረጨርኩ ነው። አለሚቱ መምጣቷን ካቆመች ከወር በላይ ሆኗታል:: ቢጨንቀኝ ምን እንደሆነች ኤልሳ አጣርታ እንድትነግረኝ ላኩዋት:: አላገኘቻትም፡፡ ኤልሳም ወደ ቤት ሄዳ ልታገኛት አልቻለችም:: እንደአጣራችው ከሆነ ግን ውዝፍ የቤት ኪራይ በመጠየቋ ያለውን የቤት ዕቃ ሽጣ እና ከፍላ አገሯ መግባቷን ሰማሁ:: ምስኪን ምን ታድርግ! ብታይ ብትጠብቅ የድብቅ ፍቅረኛዋ ለፈታላት አልቻለም:: የእሷ ሩጫ መጨረሻው ባዶ መቅረት መሆኑን ተረድታዋለች፡፡ በቀላሉ ይፈታል ብላ እንዳትገምት ደግሞ የተከሰስኩበት ወንጀል በነፍስ ማጥፋት ነው፡፡ የሚገርመው ግን እሷ ብትሄድም ከሁሉም በላይ የምወደው ንብረቴ መጽሐፍ መሆኑን ስለምታውቅ በጠቅላላ ለአከራዮቼ በመስጠቷ ኤልሳ ተቀብላ እሷ ዘንድ አድርጋልኛለች:: የቀረችኝ አንድ ወዳጀ እሷው ነበረች፡፡ እሷንም አጣሁ:: ኤልሳ ሁኔታውን ስትነግረኝ እምባዬ ዓይኔ ላይ አቀረረ፡፡ እሷም ይህንን ስታይ ለንብረቴ ያዘንኩ መስሏት፤ “አይዞህ አማረ አንተ ነፃ ውጣ እንጂ ጥሩ መ/ቤት አስቀጥርሃለሁ፡፡ ከዚያ ሁሉንም ነገር አሟልተህ ሕይወትን በአዲስ መልኩ ትጀምራለህ፡፡ ንብረት ቢጠፋ በንብረት ይተካል አትዘን" አለችኝ:: እርግጥ ነው ዛሬ እሷ ግብርና ሚ/ር ውስጥ ባለሥልጣን በመሆኗ ለእኔ የሚሆን ሥራ ላታባ ትችላለች፡፡ የጠፋብኝንም ንብረት ስወጣ ልተካው እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ባይገባት ነው እንጂ የእኔ ንብረት መች የሚተካ ሆነና፡፡ በግላጭ ስቅስቅ ተብሎ እርም የሚወጣበት ቢሆን ኖሮ አልቅሼ በተገላገልኩት ነበር፡፡ ነገር ግን ነገሩ የድብቅ ሆነና ውስጥ ለውስጥ ድብን ብሎ መቅረት ብቻ ሆነ፡፡ የመጨረሻ በረከቴ አለሚቱ ነበረች፤ እሷንም አጣሁ:: የእኔ ፉንጋ! ሁሌ የማይከፋት፣ ስፈልግ የምጠራት፣ ስፈልግ የማባርራት፣ ኩርፊያዋ በአንድ መሳም ጥርግ ብሎ የሚጠፋ፣ አለሚቱ ለእኔ የምትተካ በረከቴ አልነበረችምና ከኤልሳ ተሰናብቼ ስሄድ ድምፄን ሳላሰማ አለቀስኩላት፡፡ -//- ከሳምንት በኋላ ጠበቃዬ አስጠራኝ:: በተቻለ መጠን ሁኔታዎቹን እያጣራ እንደሆነና አንዳንድ መረጃዎችን ከእኔ በተጨማሪ ከፖሊስ ጣቢያ ማግኘቱን፤ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች የእኔን ከወንጀሉ ነፃ መሆን የሚያሳምኑት ቢሆንም፤ ዳኞቹን ለማሳመን ግን አሁንም በቂ መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚገባው ነገረኝ:: ቀጠል አድርጎም ስለአልማዝ የአሟሟዋት ሁኔታ ይተርክልኝ ጀመር።

“አቶ አማረ፤ ለማንኛውም የተከሰስክበትን ሁኔታ ማወቁ መረጃ ለመስጠት ሊረዳህ ስለሚችል ስለአልማዝ አሟሟት ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡ አልማዝ የሞተችው አልቤርጎ ውስጥ ተሰቅላ ነው፡፡ የሞተችበት ክፍልም ያው ከዲያሪው ላይ እንዳነበብከው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ ደብረወርቅ እየተባለ በሚጠራ ሆቴል ውስጥ ነው:: እሷ ከቤት ስትነሳ መምጣት የፈለገችው ወደ ኤልሳ ነበር። ግን የሚደንቀው ነገር፤ ፅፋ የተወችው ደብዳቤ የሚተርከው የራሷን ሕይወት በራሷ ማጥፋትዋንና በዚህም የተነሳ ሌላ ሰው እንዳይጉላላ የሚገልፅ ነበር። ፖሊሶችም ይህ የሚታመን ነገር ስላልሆነላቸው የእጅ ጽሑፉን "በአባዲና ፖሊስ የምርመራ ክፍል አስመርምረው የእሷ የእጅ ጽሑፍ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ነገር ግን እራሷን ለመግደል የሚያደርስ በቂ ምክንያት መኖሩን ግን ከዲያሪውም ሆነ ከሌሎች መረጃዎች ላይ ማግኘት አልተቻለም:: አልጋ ላይ ጋደም ብላ ሙዚቃ እያዳመጠች ስለነበር ከመቅጽበት ከአልጋ ላይ አስነስቶ ራሷን እንድታጠፋ የሚጋብዝ ሁኔታ ላይ እንዳልነበረች መረዳት ይቻላል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተን ለማግኘት በመፈለጓና ኤልሳም ከመጣች እንደምታገናኛትና እውነቱን ከአንተ መስማት እንደምትችል ነግራት ከቤት ስለወጣች በአንድ ግዜ ሀሳቧን የሚያስለውጥና ራሷን ለመግድል የሚያነሳሳ ምክንያት አለ ብሎ መናገርም ያዳግታል:: እርግጥ አልማዝ በልጅነቷ ከደረሰባት ችግር ጋር ተያይዞ በጭንቀት የተነሳ የአእምሮ ሕመም ችግር ሊያጋጥማት ከቻለ እራሷን ገድላ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሊከሰት አይችልም ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም በዓለማችን ላይ ራስን የማጥፋት ችግር ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በእንደዚህ ዓይነት ግለሰቦች ላይ ነውና፡፡ ነገር ግን ፖሊስ ራሷን አልገደለችም ብሎ እንዲያምን ያደረገው እሷ የተሰቀለችበት አልቤርጎ የተቆለፈው ከውስጥ መሆን ሲገባው ከውጭ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ ነው:: ምክንያቱም ቁልፉን አልቤርጎው ውስጥም ሆነ ከበሩ ላይ ማግኘት አልተቻለም:: ስለዚህ ከሶስት ነገሮች አንዱ ተከስቶ ሊሆን ይችላል:: አንደኛው፤ ገዳዩ ገብቶ ከመግደሉ በፊት ራሷን እንደገደለች አድርጋ እንድትጽፍ አስገድዶ ካጻፋት በኋላ ሰቅሏት ደብዳቤውን አስቀምጦ ሄዶ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ፖሊስን ሊያሳምን አልቻለም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሊገድላት የመጣ ሰው ራሷን እንደገደለች
አድርጎ ሲያጽፋትና ሲሰቅላት ምንም ቢሆን ትንሽ እንኳ ሳትፍጨረጨር እና ሳትከላከል ትሞታለች ብሎ መገመት አዳጋች ነው:: ነገር ግን የሚገርመው ጥፍሮቿም ላይ ሆነ ሌላ አካሏ ላይ የሌላ ሰው ደም ወይም አሻራ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አልማዝ ራሷን ከመግደሏ በፊት አልቤርጎውን ቆልፋ ቁልፉን ሽንት ቤት ውስጥ አሊያም በመስኮት በኩል ጥላው ራሷን ገድላ ሊሆን ይችላል:: ይህም ከመላምትነት አልፎ በመረጃ የተደገፈ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ቁልፉን በመስኮት ጥላዋለች እንዳይባል ግቢው ውስጥ ስንዝር በስንዝር ተፈልጎ ሊገኝ አልቻለም:: ሽንት ቤትም ጨምራው ይሆናል ተብሎ እንዳይጠረጠር፣ ደብዳቤው ላይ እንደተፃፈው ከሆነ አልማዝ በእሷ ሞት ምክንያት ማንም ሰው እንዳይጉላላ የምትጽፍ ከሆነ ሽንት ቤት ውስጥ ቁልፉ እንዳይገኝ በማድረግ እውነቱን የምትደብቅበት ምክንያት ሊኖር አይችልም:: ሶስተኛው፣ አልማዝ ራሷን ከገደለች በኋላ ምናልባት በወንጀሉ የሌለበት ግለሰብ በአጋጣሚ በሩን ከፍቶ ሲገባ ተሰቅላ መሞቷን ሲያይ ደንግጦ በሩን ከውጪ ዘግቶ ቁልፉን ይዞ ሄዶ ይሆናል የሚለው ተራ መላምት ነው :: ይህም ቢሆን የሚያሳምን አይደለም:: ምክንያቱም ቢያንስ ቢያንስ በበሩ ላይ የግለሰቡ አሻራ መገኘት ነበረበት፡፡ ይህም ሊገኝ አልቻለም:: እንግዲህ ወንጀሉ በረቀቀ መንገድ ተፈፅሟል ማለት ነው፡፡ አልማዝ ራሷን በረቀቀ መንገድ ገድላለች፣ ወይም በሌላ ሰው የረቀቀ ስልት ተገድላለች፡፡ ይህ እንቆቅልሽ ካልተፈታ ያንተን ነፃ መሆን ለዳኞቹ ማሳመን ይከብዳል። እኔ ግን ቢያንስ ኤልሳን ስለማምንና አልማዝ ወደ አንተ እየመጣች መሆኑን በተመለከተ አንተ ምንም መረጃ እንዳልነበረህ ስለማውቅ በንፁህነትህ አልጠራጠርም፡፡ ሌላውን እንዴት ማሳመን እንደምችል ግን ግራ ገብቶኛል::" በማለት በሁለት እጆቹ ጉንጮቹን ይዞ ተክዞ ተቀመጠ። የሰማሁትን ማመን አቃተኝ:: ድርጊቱ የተወሳሰበና ለፈራጅ የሚያስቸግር ነው:: ከዚህ ውስብስብ ወንጀል ውስጥ የእኔን ንፁህነት ፈልቅቆ ማውጣት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ታየኝ፡፡ ምናልባት እንቆቅልሹን መፍታት የሚችል ሰው ካለ ከእኔ በስተቀር ሌላ ሊሆን አይችልም:: ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው እኔ መረጃዎችን የማሰባሰብ ዕድል ኖሮኝ እውነቱን ለማግኘት ስታደል ብቻ ነበር:: ይህንን ለማድረግ ግን አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበረኝም። ሰባተኛው የቀጠሮ ቀን ደርሶ ወደ ፍርድ ቤት ስገባ ከጠበቃዬ ጋር ፊት ለፊት ተገናኘን:: ፊቱን ሳየው ግርማ ሞገሱ ጠፍቶ የተሸናፊነት ስሜት አጥልቶበታል። እርግጥ ነው እንደሚሸነፍ እንኳን እሱና እኔም ጠንቅቄ

አውቄዋለሁ፡፡ የመከላከያ ምስክሮች ተብለው የተጠሩት የሰጡት የምስክርነት ቃል ከእኔ ይልቅ ለአቃቢ ሕግ የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው እያወቅሁ ማሸነፍን ማሰብ ጅልነት ነው፡፡ ጠበቃዬ እኔን ለማፅናናት ሳይሆን አይቀርም፡ “አይዞህ፣ ይፈረድልናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ካልሆነም ይግባኝ እንላለን አለኝ:: ይግባኝ የሚለው ቃል ከአፉ ሲወጣ ተሸናፊነቱን የተቀበለ ስለሚያስመስል ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ሆነ:: ግን ለምን እንደሆነ ባላውቅም ያ ስመኘው የነበረው በእኔ ላይ የመፈረድን ሁኔታ ሳስብ ግን ሽንፈት መስሎ ስለተሰማኝ ፍርሃት ወረረኝ:: በተለይ ዶ/ር አድማሱ ከፊት ለፊት በኩራት ተቀምጦ በእኔ ላይ የሚፈረደውን ፍርድ ለመስማት ሲጠባበቅ ሳየው ሽንፈቱ ፍጹም አልዋጥልህ አለኝ:: ግን ያም ሆነ ይህ አሁን ግዜው አልፏል፡፡ ብዙ ላደርጋቸው የምችላቸውን ነገሮች አላደረኩም፡፡ ከሁሉም በላይ እንቆቅልሹን ልፈታው የምችለው እኔ ሆኜ ሳለ እነሆ ይኸው ራሴን እንደ እየሱስ አሳለፌ ልሰጥ ተዘጋጅቼአለሁ:: እየሱስ እንኳን ራሱን አሳልፎ የሰጠው በደሙ የሰው ልጆችን የኃጢያት እድፍ ሊያጠራ አስቀድሞ ራሱ የገባውን ቃል ለመተግበር ነው:: የኔ ግን እዚህ ግባ በማይሉት የሐሰት ቁልል ምክንያት በከንቱ ራስን ለጠላቴ አሳልፎ ከመስጠት ውጪ ይህ ነው የሚባል ፋይዳ ያለው ጥቅም አልነበረውም:: ዳኛው የሚሰጡትን ውሳኔ ለመስማት ሁሉም ድምጹን አጥፍቶ እያዳመጠ ስለነበር ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ ውሀ እንኳን ጠብ ቢል መስማቱ አይቀርም ነበር፡፡ ዳኛው የክርክሩ ጠቅላላ ሂደት እንዴት እንደነበር ካብራሩ በኋላ ይህ ሁሉ ታዛቢ ሰው በጉጉት የሚጠብቀውን የፍርድ ውሳኔ ማሰማት ጀመሩ!


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
#አላገባህም


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


////
‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡››

‹‹እናቱና እህቱ የሞቱ ቀን ነው የተሰወረው፡፡ሁለቱ በመልክም ሆነ በአመካከት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑት  ወንድማማቾች ከከተማ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ ..ሳሎኑ ፍፁም ትርምስምስ ብሎ ያያሉ ..ግራ በመጋባት  ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ እናታቸው ልቧ ላይ ነጭ አብረቅራቂ ቢላዋ ተሰክቷባት ወለሉ ላይ ዝርግትግት ብላ ተኝታለች..አባትዬው ስሯ በደም በተጨማለቀው እጇቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ደንዝዘዋል….፡፡

‹‹እንዴ አባዬ ምንድነው..?እናቴን ምን አደረካት?›› ብለው ሲጮሁ ከፊት ለፊት  ኮርኒሱን ከደገፈው ብረት ላይ በታሰረ  ሲባጎ  አንገቷ የታነቀው እህታቸው በድኗ 360 ዲግሪ ሲሽከረከረከር ይመለከታሉ፡፡ሁለቱም ወንድማማቸች ወደእህትዬው እየሮጡና ሁለት እግሮቾን አንድ ላይ ይዘው ወደላይ ከፍ ያደርጎታል….‹‹ቶሎ በል ቢላዋ አምጣና ..ገመድን ቁረጥ…››
.ዘሚካኤል ይንደረደርና እናትዬው ደረት ላይ የተሰካውን ቢላዋ ይነቅልና ወንበር ላይ ቆሞ ገመዱን ይበጥሳል…እህትዬው ተዝለፍልፍ ሚካኤል ተከሻ ላይ ታርፋለች… ቀስ ብለው ወለል ላይ አሳርፈው በፍጥነት አንገቷ ላይ ያለውን ገመድ አላቀው ትንፋሿን ቢያዳምጡም በውስጧ የቀረ  ምንም  እንጥፍጣፊ እስትንፋስ አልነበረም….ከዛ ዘሚካኤል ቀጥታ እህቱ የተንጠለጠለችበትን ገመድ የቆረጠበትን እና እናቱ የተገደለችበትን ቢላዋ ይዞ ወደአባትዬው ሲንደረደር…ሚካኤል  በደመነፈስ ሮጠ ይጠመጥበታል…

‹‹ልቀቀኝ..እናቴንና እህቴን ገድሎ እሱ በህይወት አይኖርም››

‹‹አይሆንም….ስለሆነውን ምንም ምናውቀው ነገር የለም››ሲል ይመልስለታል፡፡

‹‹እንዴት አናውቅም..?አታይም እንዴ …?እጁ በደም ተጨማልቆ……ልቀቀኝ ልግደለው›› ሲል ይጋበዛል፡፡

‹‹አባቴንም ማጣት አልፈልግም››

‹‹እንግዲያው ሁለታችሁንም እገድላችኃለው…››ይለውና ድብድብ ይጀምራሉ…ይሄ ሁሉ ሲሆን አባትዬው ደንዝዘው ከተቀመጡበት  ቦታ ንቅንቅ አላሉም ነበር….ወንድማማቾቹ አባቴን ልግደል አትገድልም በሚል ጠብ እርስ በርሳቸው ተቦቅሰውና ተደባድበው ሳይለይላቸው ቤቱ በፖሊስ ይሞላል፡፡

አባትዬ እነሱ ከመድረሳቸው በፊት ስልክ ደውለው ሚስታቸውን  እንደገደሉ ነግሮቸው ነበር፡፡ፖሊሶቹ ወንድማማቾቹን አገላግለው ሶስቱንም ወደእስር ቤት ከወሰዷቸው በኃላ ሬሳዎቹን አንሰተው ለምርመራ ወደሆስፒታል ይልካሉ..በማግስቱ አባትዬው ሚስታቸውንም ሆነ ልጃቸውን የገደሉት እራሳቸው እንደሆነ ቃል ስለሰጡ በዛ መሰረት ሁለቱ ልጇች ይፈታሉ፡፡

ከአራት ቀን በኋላ የእናትና እህታቸውን  ሬሳ ተረክበው ከቀበሩ በሆላ ዘሚካኤል በከተማው አልታየም፡፡‹‹አንተ ያንን አውሬ ሰውዬ ገድዬ የእናቴንና የእህቴን ደም እንዳልበቀል ያደረከኝ ጠላቴ ነህ..ከእሱ በላይ እጠላሀለው ..እና ደግሞ መቼም ቢሆን ይቅር አልልህም፡፡››የሚል ማስታወሻ ለወንድሙ ጥሎ ነበር የጠፋው፡፡ቆይቶ እንደሰማነው ከጓደኞቹ ጋር በቦረና በኩል ወደኬኒያ ከዛም ወደጣልያን ከተሻገረ በኋላ…በፊትም ልጅ እያለ ጀምሮ ይሞካክረው  በነበረው ሙዚቃ ገፋበትና በትምህርትም አሳድጎ ጥሩ ሙዚቀኛ ሆነ ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወት መኖሩን ያወቅነው የዛሬ 3 አመት የሙዚቃ ክሊፑን ሲለቅ ነው፡፡

….የዛን ጊዜ ሚካኤል የተደሰተው መደሰት ያው አንቺም አብረሺን ስለነበርሽ ታውቂዋለሽ፡፡ከዛ በሀገር ውስጥ በጣም ተቀባይነት ስላገኘ ..ጓዙን ጠቅልሎ ገባ፡፡በሙዚቃ ብቻ ሳይሆን በፊልም ትወና ላይ መስራት ቀጠለ…እንግዲህ ባለፉት አምስት አመታት የገነባውን ስምና ዝና  እኩል ነው የምናውቀው፡፡››

‹‹ይገርማል….ግን ከመጣ በኃላ ወንድሙን ለማግኘት አልሞከረም…?››

‹‹ወይ ማግኘት..እኔ አንኳን ላገኘው ሄጄ ስለወንድሙ ሳነሳበት እንዴት እንደተንገሸገሽ እስከዛሬ ሳስበው ይዘገንነኛል..አሁንም ጥላቻው እንዳለ ነው፡፡አልፎ አልፎ በድብቅ እየመጣ የእናቱንና የእህቱን መቃብር እየጎበኘ እንደሚሄድ አውቃለው….በዛው ልክ ስለአባቱም ሆነ ስለወንድሙ ምንም መስማት እንደማይፈልግ እና ቢሞቱም ግድ እንደሌለው አውቃለው፡፡››

‹‹ተይ እንደዛ አትበይ…..››

‹‹ወይ አንቺ ልጅ ስንት ነገር ውስጥ አስገባሺኝ..ስለእሱ ለማወቅ ለምንድነው የፈለግሽው?፡››ስትል ዳግመኛ ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንደምንም ብዬ በሰርጋችሁ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ አስቤለው››

‹‹ምን?››አዲስአለም ክፉኛ ነው የደነገጠችው፡፡

‹‹ምነው መጥፎ ሀሳብ ነው እንዴ?››

‹‹አረ በፍጹም…ግን የሚሳካ እቅድ አይደለም….››

‹‹ከተሳካልኝስ?››

‹‹ከተሳካልሽማ….ለሚካኤል በሰርግ ላይ ሌላ ሰርግ ደገሽለት ማለት ይሆናል….በፊቱንም ይወድሻል በቃ የዘላለም ባለውለታው ነው የምትሆኚው››

ፀአዳ ‹‹ለማንኛውም ጉዳዩ በእኔና አንቺ መሀከል በሚስጥር ይያዝ …..ሚካኤል ሰምቶ ካልተሳካ ቅር እንዲሰኝ
አልፈልግም፡፡››ስትል አስጠነቀቀቻት፡፡

‹‹አታስቢ እኔም ባሌ በሰርጉ ሰሞን እንዲያዝንብኝ ስለማልፈልግ ..አልነግረውም…ለአንቺ ግን እንዲቀናሽ በቻልኩት መንገድ ሁሉ አግዝሻለው፡፡››

በዚህ ሁኔታ ነበር ከአዲስ አለም  ስለዘሚካኤል የተወሰነ ነገር ማወቅ የቻለችው..ከዛ ወደ ሶሻል ሚዲያ ሄደችና እና ስለእሱ የተፃፉ የጋዜጣ አምዶችና በተለያየ ጊዜ የሰጣቸውን ቃለ መጠይቆችን ሰብስባ ማንበብና ማዳመጥ ነው የቀጠለችው…ይሄ ሂደት አንድ ሳምንት ነው የፈጀባት፡፡በዚህ ጊዜ በአምስት አመት ውስጥ ያወጣችውን ሶስት አልበሞችና ፤ከስምንት በላይ ነጠላ ዜማዎችን እየደጋገመች ያደመጠች ሲሆን እሱ የተሳተፈባቸውን ስምንት የሚሆኑ ፊልሞችንም በጽሞና መመልከት ችላለች፡፡

እና በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ለአመታት የምታውቀው የቅርቧ ሰው እንደሆነ እንዲሰማት አድርጎታል..ያንን ስሜት ግራ አጋቢ ነው፡፡‹አይ በጣም የምወደው ወንድሜ የሚካኤል ወንድም ስለሆነ በእሱ እይን  እሱንም ማየት ጀምሬለው ማለት ነው..›ስትል ለራሷ ማብራሪያ መስጠት ብትሞክርም ሊያሳምናት ግን አልቻለም፡፡

ደግሞ ስለሴሰኝነቱ..በየጊዜው ስለሚቀያይራቸው ሞዴል መሳይ ሴቶች፤ ከዝነኛ እንስቶች ጋር ስለሚጀምረው የፍቅር ግንኙነትና ስለመለያየቱ …ከስራው እኩል አንዳንዴም ከስራው በላይ ነው ሚያወራው፡፡እና ለእንደዚህ አይነት ሴት አውል የማይጨበጥ ሙልጭልጭ ወንድ ምን አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው….?መልስ የላትም፡፡ግን አሁን ልታገኘውና ልትጋፈጠው ወስናለች..ዝግጅቷንም ጨርሳለች፡፡
///          
ፀደይ ባደረገችው ጥናት እና በሰበሰበችው መረጃ መሰረት  የሚካኤል መንታ ወንድም የሆነው ዘሚካኤልን ለማናገር አንድ ብቸኛ መንገድ ብቻ እንዳላት ተረድታለች፡፡በሳምንት ሶስት ቀን በሚሰራበት በከተማዋ ታዋቂ  ናይት ክለብ  ተገኝታ እድሏን መሞከር ፡፡ከእሷ ባህሪ አንጻር እንደዛ አይነት ቦታ ተገኝታ የማታውቀውን ሰው ማናገር በጣም ከባድ የቤት ሰራ ነው፡፡ቢሆንም የግድ ልትወጣው የሚገባ ተግባር እንደሆነ እራሷን አሳምናለች፡፡

ባለፉት ሁለት ቀን ውስጥ የተባለው ናይት ክለብ ውስጥ በውድቅት ለሊት በመገኘት እሱ ሲዘፍን እና በቀበጥ አድናቂዎቹ ሲሞገስና ሲሸለም መመልከት ብትችልም  እሱን ተጠግቶ ለማናገር ያደረገችው ሙከራ ግን ሙሉ በሙሉ  አልተሳካላትም ነበር፡፡ዛሬ ግን የግድ ሊሳካላት ይገባል..ምከንያቱም ሰርጉ ከአምስት ቀን  በኃላ  ነው፡፡ዛሬ አግኝታ ካላናገረችው…ወደእዚህ መጥታ ሌላ ሙከራ የምትሞክርበት ሌላ እድል የላትም፡፡
ልክ ስምንት ሰዓት አካባቢ  ወደ ሽንት ቤት ሄደችና  አስባና  አቅዳ  አስመስላ ያሰፋችውን የቤቱን ሴት አስተናጋጆች ልብስ ለበሰችና ሰሞኑን ባጠናችው መሰረት   ሙዚቀኞች ለማረረፊያና ለመዘጋጃ ወደሚጠቀሙበት ከፍል ሄደችና እንደምንም ተሹለክልካ ከጀርባ በኩል አልፋ  ስራ እየሰራች በማስመሰል መጠበቅ ጀመረች፡፡

በመድረክ ላይ የሚያቀርበውን ዝግጅት ካጠናቀቀ በኃላ በሁለት ጋርዶች  ተጅቦ ሲመጣ ተመለከተች…ፈጠን አለችና በረፉን ከፍታ በመግባት መልሳ ዘግታ ዙሪያ ገባውን ተመለከተች፡፡ተንደረደረችና ከግዙፍ ጥቁር ቆዳ ከለበሰው ሶፋ ጀርባ ሄዳ ተወሸቀች…ብዙም ሳይቆይ የበራፍ መከፈትና የእግር ኮቴ ሰማች….የልቧ ድውድውታ ከእራሷም አልፎ ለእሱ የሚሰማ መስሎ ተሰማትና ሰጋች፡፡

‹‹የአንድ ሰዓት ረፍት አለኝ….ትንሽ አረፍ ልበል…አስር ጉዳይ ላይ ቀስቅሱኝ››ከጋርዶቹ ጋር ነው የሚያወራው፡፡

‹‹እሺ..ተኛ እንቀሰቅስሀለን››

አጮልቃ ስታይ ጋርዶቹ ከውጭ በራፉ ላይ ሲቀሩ እሱ ከውስጥ ሆኖ ዘጋባቸው..በራፉን ቀረቀረና…ከላይ የለበሰውን ጃኬት አወለቀ …ወደክፍሉ መሀል ሄደ…ከዛ የለበሰውን ቲሸርት አወለቀ….በተደበቀችበት ሆና መላ ቁመናውና ተመለከተች…ጠንበልል የሚባል ወንዳወንድ ነው፡፡ከወንዶች ይልቅ የሴቶች የሙዚቃ አፍቃሪዎች በእጥፍ እንደሚወዱት ታውቃለች፡፡ይሄ የሆነው ስርቅርቅ ድምፁ ከወንዶች ይልቅ ሴቶችን የማቅለጥ ተፈጥሮው ስውር ችሎታ ስላለው ሳይሆን የሴቶችን ልብ የማቅለጥ አቅም ያለው ወንዳወንድ ቁመናና  አቅልጥ ውበት ስላለው እንደሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ቲሻርቱን ሲያወልቅ ከወገቡ በላይ ርቃኑን ቀረ…ሆዱ በግማሽ በጥቁር ፀጉር የተሸፈነ ነው፡፡በዛ ላይ አብረቅራቂ ሰንሰለት መሳይ ሀብል ስላንጠለጠለበት ቀልብ ይስባል፡፡

በተደበቀችበት ሆና የለበሰችውን የአስተናጋጅ ልብስ አወለቀችና እዛው ስሯ ወለል ላይ ጣለችው፡፡ሱሪውን ለማውለቅ ቀበቶውን መፍታት ሲጀምር ተስፈንጥራ ከተደበቀችበት ወጣችና ከፊት ለፊቱ ተደንቅራ ቆመች፡፡

በከፍተኛ መገረም እነዛ ተንከባላይ ሰማያዊ አይኖቹን ተከለባት፡፡አይኖቹ ልብን በቀላሉ ሰርስረው የሚገቡ አስማታዊ ስለሆኑ መቋቋም ከበዳት፡፡

‹‹አቤት ..እዚህ እንዴት ገባሽ?››የቁጣ  ሳይሆን የመደነቅ ቃና ባለው ድምፀት ጠየቃት፡፡

‹‹በብዙ ድካም ….ተደብቄ..››ስትል ድፍን ያለ መልስ ሰጠችው፡፡

አፈቀርንህ ..እራሳችንን እናጠፋለን ..ምናምን የሚሉ በእሷ እድሜም የሆኑ ከእሷ ያነሱ ወጣቶች በየእለቱ የተላያዩ አይነት ገጠመኞችን በመፍጠር ሊያገኙትና ሊዳስሱት ስለሚሞክሩ ይሄንንም ከዛ የተለየ ነው ብሎ አላሳበም…

ፀደይ የሚንደቀደቀውን የልብ ትርታዋን ለመቆጣጠር እየታገለች  በቀጣይ ምን ብላ ወደመጣችበት ጉዳይ እንደምትገባ እያሰላሰለች ሳለ…ለግላጋ እጁን በመዘርጋት በቀጭን ወገቧ አዙሮ ያዘትና በኃይል ጎትቶ ግማሽ እርቃን ከሆነ ሰውነቱ ላይ ለጠፋት፡፡

ፈፅሞ ይሆናል ብላ ያልጠበቀችው ስለነበረ …አንገቷን ቀና አደረገችና በልምምጥ ተቁለጭላጭ አይኖቾን በተንከባላይ አይኖቹ ላይ ተከለች፡፡በቁመት ቢያንስ በ40 ሳ.ሜትር ይበልጣታል…ስለዚህ እሷ አንጋጣ ስታየው እሱ ደግሞ አዘቅዝቆ ነው የሚያያት፡፡

.. የገባችበት እውነታ አምኖ መቀበል ነበረበት።አስደናቂ ነበር ። እንዲለቃት ልትጠይቀው በጣም ፈልጋለች..ግን ቃላትቱን ከአንደበቷ ማውጣት አልቻለችም፡፡ ይባስ ብሎ አፉን አሞጥሞጦ ወደታች ዝቅ አለና ከንፈሯን በከንፈሩ ጎረሰው…ሳትወድ በግዷ አይኗን ጨፈነች….‹‹ጌታ ሆይ ድረስልኝ››ስትል በውስጦ ልትፀልይ ሞከረች፡፡እንደክንፍ የተዘረጋውን እጇን ያለፍቃዷ ወደ እሱ ላከችና በወገቡ ዙሪያ ጠመጠመች፡፡ምላሱን ጎልጉሎ አፏ ውስጥ ከተተውና  ሲያሽከረከረው..አቃሰተች…ይሄ የመጀመሪያ ጊዜ ገጠመኞ ነው…ገላዋ ከወንድ ገላ ጋር እንዲህ ሲጣበቅና ሲቀልጥ ከስድስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
የዚህ ዝነኛና ሀብታም ድምጻዊ ሴት አውልነት የታወቀና የየእለት የታብሎይዶችና ዩቲዩቦች ማድመቂ ዜና ነው፡፡ለእሱ በእየእለቱ እንደሚመገበው ቁርስና ምሳ  ሴቶችን መቀያየርና በፍቅር በማቅለጥ ከዛም አልፎ ለወሲብ ወደአልጋ ላይ መጎተት ተራና የተለመደ ነገር ነው..ለእሷ ግን ከዛ በጣም የተለየ ነው፡፡ታዲያ አሁን እንዴት ተቃውሞ አልባ ሆነች..?እንዴት ለመሳም ሲያቅፋት ለመታቀፍ እንዲህ ቸኮለች..ሲስማትስ እንዴት መልሳ ሳመችው ?ለአመታት በውስጧ የተዳፈነው የወሲብ ረሀብ ድንገት ገንፍሎ  ከቁጥጥር ውጭ ስላደረጋት ይሆን?፡፡‹‹አይ እንደዚህማ ተራ ሴት አልሆንም…. በፍፅም…እንደምንም ታግላ ከንፈሯን ከከንፈሩ አላቀቀች….ከዛ ከእጆቹ ሾልካ ወጣችና አንድ ሜትር ወደኃላዋ ፈንጠር ብላ  ቆመችና በእጆቾ ጣቶች ለደቂቃዎች ሲሳማት የቆየውን ከንፈሯን እየነካካች  ቆመች ፡፡
እሱም በቆመበት እየተመለከታት ምን እንዳልተመቻት እያሰላሰለ ነው፡፡የሆነ ነገሯ ልቡ በፍጥነት እንዲመታ አድርጎታል፡፡፡ቆንጆ ነች፡፡ግን ደግሞ በእየእለቱ ስዕል ሚመስሉ ብዙ ቆንጆዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ በመልኳ ልታስደምመው አትችልም  ፡፡ማንኛዋም ሴት እሱ ፊት ለመቅረብ ስትመጣ ተበድራም ሆነ ተለቅታ ውድ ልብስ ለብሳ ፤ሜካፖን ተለቅልቃና ተቆነጃጅታ  ነው፤ይህቺ ፊት ለፊቱ ያለችው ልጅ ግን ዝም ያለ ፍዝ አለባበስ ነው ለበሰችው፡፡ኦሞ ቀለም ያለው ጅንስ ሱሪ ከነጭ ቲሸርት ጋር ለብሳለች፡፡፡አንገቷ ላይ ሮዝ ቀለም ያለው ሻርፕ ጣል አድርጋለች፡፡እና ነጭ ስኒከር ጫማ ተጫምታለች በቃ፡፡በዛ ላይ የለበሰችው ጅንስ ሱሪ ጉልበቱ ላይ ተቦጭቋል…ለፋሽን ተብሎ የተቦጨቀ ሳይሆን ምስማር የቦተረፈው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡
ፀደይ ረጅምና   ጥልቅ  ትንፋሽ ወሰደች። መረጋጋት አለባት። እሷ እዚህ ለትልቅ ተልዕኮ ነው የተገኘችው፡፡በጣም አስፈላጊ  ለሆነ ተልዕኮ …. እና በቀላሉ በልብ ድካም ተይዞ ለመዝለፍለፍ ጊዜ አልነበራትም - ይህ የጀመረችው የእብደት  አካሄድ በእቅዷ ላይ ከባድ መፋለስ ይፈጥርባታል።የሁለት ጓደኞቾን የስረግ ካርድ ሰጥታው  ግብዣዋን ላይ መገኘት እንዳለበት ማሳመን አለባት  ፡፡

‹‹ይቅርታ እኔ ለዚህ አልመጣሁም››አለችው፡፡

‹‹ለዚህ ማለት?››በግማሽ መገረምና በግማሽ ፈገግታ ጠየቃት፡፡

‹‹ማለቴ ያው ይገባሀል ..ለመሳሳምና ለ…..››አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እኔ ደግሞ ለዛ መስሎኝ በጣም ተነቃቅቼና ተደስቼ ነበር››አለና ፈገግ አለ፡፡

‹‹ይቅርታ..ስትስበኝ መሳብ..ስትስመኝም መሳም የለብኝም ነበር››

‹‹ግን አድርገሽዋል..እና ሳስበው ደግሞ መጥፎ አይመስለኝም››

‹‹ሊሆን ይችላል…ግን አግባብ ስራ አልነበረም..ይቅርታ…ጊዜህን አልሻማብህ የመጣሁበትን ጉዳይ ልንገርህና ልሂድ››

‹‹ምንድነው..ምን ልርዳሽ?››

የጅንስ ሱሪዋ የኃላ ኪስ ገባችና አንድ ፖስታ አወጣችና አቀበለችው፡፡

‹‹ምንድነው?››እያለ እጁን ዘርግቶ ተቀበላት..ፖስታውን ሲመለከት ወዲያው ወደአእምሮ የመጣለት በሆነ ችግር ለምሳሌ የሆነ ቤተሰብ ታሞባት ለህክምና እርዳታ እየጠየቀች ነበር የመሰለው፡፡

እንደዚህ አይነት ነገር በተለያየ መንገድ ሁል ጊዜ ስለሚደርሱት ብዙም ሚደንቅ አይደለም..በዚህ መንገድ ግን በለሊት ተደብቃና ተሹለክልካ ማረፊያ ክፍሉ ድረስ ገብታ በዚህ መልክ  እርዳታ የጠየቀችው ሴት ስለሌለች ተገርሞበታል፡፡

ወደራሱ አስጠግቶ ሲያየው..ከአሰበው የተለየ ጉዳይ  ነው፡፡‹‹የምን ሰርግ ነው…ልታጋቢ ነው እንዴ..?ሰርግሽ ላይ እንድገኝ ልትጠሪኝ ነው በዚህ መንገድ በዚህ ሰዓት የተገኘሽው?››
በተራዋ ፈገግ አለች፡፡‹‹አይ..አይደለም…የጓደኛዬ አዲስአለም እና የወንድምህ የሚካኤል የጋብቻ ስነስርአት በፊታችን እሁድ በአዳማ ይካሄዳል…በዛ ሰርግ ላይ ተገኝተህ ወንድምህን እንድታስደስተውና እንድታስገርመው እፈልጋለው››፡፡

‹‹እና ለዚህ ነው ….ከአዳማ ድረስ መጥተሸ በዚህ ውድቅት ለሊት ክፍሌ የተገኘሽው?››

‹‹አዎ ..አንተን ለማግኘት ያለፉትን ሶስት ቀናት ስመላለስ ነበር..ይሄን ሁሉ የለፋሁት ያንተ ሰርጉ ላይ መገኘት ለወንድምህ ምን ያህል አስደሳች እንደሚሆን ስለማምንበት ነው››

‹‹በእውነት !!በጣም ነው ያስደመምሽኝ..ወንድም የለኝም እንጂ ቢኖረኝና ብገኝ ደስ ይለኝ ነበር››

‹‹ተው እንጂ..እስከማውቀው ድረስ…አንተም ከእሱ በስተቀር እሱም ካንተ በስተቀር ሌላ ዘመድ የላችሁም…ከዚህ በፊት በምንም ሁኔታ ብትጣሉና ብትቀያየሙ ያለፈውን ይቅር ተባብላችሁ ወደፊት መቀጠል አለባችሁ ..ደግሞ ሰርግና ሞት አንድ ነው ይባል የለ….እባክህ!!››

‹‹አዝናለው..ነገርኩሽ ..እውነቴን ነው… እንዳልሽው  እኔ ምንም አይነት ዘምድ የለኝም  ወንድም ጭምር..ስለዚህ አዝናለው››

‹‹እኔም አዝናለው….በምትዘፍናቸው ዘፈኖች ስለፍቅርና ስለይቅርታ ከደርዘን በላይ ሙዚቃዎችን ተጫውተሀል….ቃላችውን የማይኖሩ ሰዎች ያበሳጩኛል››አለችውና በብስጭት ወደበራፉ መራመድ ጀመረች፡፡

‹‹ይቅርታ ጠብቂኝና የምትሂጂበት ድረስ ሸኝሻለው››

‹‹አይ ይቅርብኝ››አለችና የተቀረቀረውን በራፍ ከፍታ ወጣችና መልሳ ዘግታ በግርምት የሚያዬትን ቦዲ ጋርዶች ገፍትራ ተሰወረች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ //// ‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡›› ‹‹እናቱና እህቱ የሞቱ ቀን ነው የተሰወረው፡፡ሁለቱ በመልክም ሆነ በአመካከት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑት  ወንድማማቾች ከከተማ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ ..ሳሎኑ ፍፁም ትርምስምስ ብሎ ያያሉ ..ግራ በመጋባት  ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ እናታቸው ልቧ ላይ ነጭ አብረቅራቂ ቢላዋ ተሰክቷባት…»
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_20

ዳኛው የሚሰጡትን ውሳኔ ለመስማት ሁሉም ድምጹን አጥፍቶ እያዳመጠ ስለነበር ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ ውሀ እንኳን ጠብ ቢል መሰማቱ አይቀርም ነበር፡፡ ዳኛው የክርክሩ ጠቅላላ ሂደት እንዴት እንደነበር ካብራሩ በኋላ ይህ ሁሉ ታዛቢ ሰው በጉጉት የሚጠብቀውን የፍርድ ውሳኔ ማሰማት ጀመሩ፤ “አቶ አማረ አስረስ መጋቢት 15 ቀን 1980 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አዲስ አበባ፣ ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ደብረወርቅ ሆቴል ውስጥ፣ ሰውን ለመግደል አስበውና አቅደው፣ ሟች ወይዘሪት አልማዝ አስፋውን ከእኔ ሌላ ሰው አፍቅረሻል በሚል ምክንያት በቅናት መንፈስ ተገፋፍተው ፍቅረኛቸውን የለምንም ርህራሄ ራሷን እንደገደለች የሚያስመስል ደብዳቤ እንድትፅፍ ካደረጉ በኋላ ገድለው ሰቅለዋታል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ግለሰቡ ይህንን ሁሉ ወንጀል የፈፀሙ ሆነው ሳለ ወንጀሉን አምነው ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ በወንጀላቸው ሳይፀፀቱ ከወንጀሉ ነፃ ነኝ በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሹ ወንጀሉን በቅናት መንፈስ ተነሳስተው መፈፀማቸው በምስክሮችና በማስረጃ ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ተከሳሹ አቶ አማረ አስረስ ጥፋተኛ ናቸው በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡''

ዳኛው የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ አቃቤ ሕግ በተሰጠው የጥፋተኛነት ውሳኔ ላይ የቅጣት አስተያየት ካለው እንዲሰጥ ጋበዙ፡፡ አቃቤ ሕግም የተሰጠውን ዕድል በመጠቀም ምን ያህል ጭካኔ በተሞላው መንገድ ሆን ብዬና ተዘጋጅቼ ግድያውን እንደፈፀምኩ በማብራራት የመጨረሻው ከባድ ቅጣት እንዲበየንብኝ ዳኛውን በሕግ ቃላት ለማሳመን ጥረቱና ትንቅንቁን አጠናከረ፡፡ በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ዕድል የተሰጠው ተረቺው ጠበቃዬ፤ "እኔን ነፃ ለማውጣት ሲከራከር እንዳልነበር ሁሉ አሁን ግን መረታቱን ተቀብሎ፤ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ወንጀል ሰርቼ እንደማላውቅ በተደጋጋሚ በመጥቀስ የቅጣቱ መጠን እንዲቀልልኝ ተማፀነ፡፡ ዳኛው የቅጣት ማክበጂያና ማቅለያ አስተያቶችን ከሰሙ በኋላ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 19/1982 ዓ.ም ቀን እንድንቀርብ በማዘዝ አሰናበቱን፡፡ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ብዬ ሳስብ እዚሁ ላይ ተጠናቀቀ። ከዚህ በፊት ከስሼም ሆነ ተከስሼ ፍርድ ቤት ቀርቤ ስለማላወቅ የችሎቱ ሂደት የተጠናቀቀበት ሁኔታ ባይገባኝም በአቃቤ ሕግና በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ የማየው የደስታ ሳቅና፣ በኤልሳና በጠበቃዬ ፊት ላይ ያየሁት የመከፋት ስሜት በእርግጠኝነት በእኔ ላይ እንደተፈረደ አመላክቶኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርዱ የሞት ፍርድ፤ ዕድሜ ይፍታህ፤ ወይም የተወሰነ እስር ዘመን መሆኑን ለይቼ ለመረዳትም ይሁን ለመገመት አለመቻሌ ግራ አጋብቶኛል፡፡ እስር ቤት ተመልሼ እንደገባሁ ግን የጥፋተኝነት ውሳኔ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሌላ ቀጣይ የፍርድ ሂደት እንዳለ መረዳት ቻልኩ፡፡ እንደእኔ ከሆነ ግን ጥፋተኛ መሆኔ ከታመነበት ጊዜ ሳይፈጁ ፈርደውብኝ ቁርጤን ቢነገግሩኝ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ነገር ግን እንደሚመስለኝ እንዲህ የፍርድ ሂደቱን በማጓተት እስረኛው ምን ይፈረድብኝ ይሆን? ይገድሉኝ ይሆን? ዕድሜ ልክ ይወሰንብኝ ይሆን? ሃያ ዓመት ያስሩኝ ይሆን? ወዘተ.. እያለ ቀን መጨነቁ፣ ሌሊት እንቅልፍ ማጣቱ ከፍርድ በፊት የሚቀጣው ቅጣት ተደርጎ ሳይወሰድ አይቀርም፡፡ የፍርድ ውሳኔ የሚስጥበት ቀን ደርሶ ፍርድ ቤት ቀረብኩ፡፡ ሐሰት በእውነት ላይ የበላይነት አግኝታና የተተበተበው ሴራ ሳይፈታ፣ እጄ ከተያዘበት ዕለት አንስቶ የሃያ ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደብኝ፡፡ ውሳኔውን ስሰማ ጉልበቴ አካላቴን መሸከም እስከሚያቅተው ድረስ መብረክረክ ጀመረ። ንዴትና ፍርሀትም ሰውነቴ ውስጥ ተቀላቅለው በፈጠሩት ትኩሳት የተነሳ መላ ሰውነቴ በላብ ተዘፈቀ፡፡

እንግዲህ እነሆ ያቺ ስጠብቃት የነበረች ውድ ቀን ደርሳ የጠበቅኋት ውሳኔ ባልጠበቅሁት ሁኔታ ተፈረደች:: እኔም ባልሰራሁት ወንጀል ተፈርዶብኝ የታስርኩበት አራት ዓመት ሲቀነስ ለቀጣይ አስራ ስድስት ዓመታት ልታሰር ተወስኖብኛል። እርግጥ ለእኔ ብዙም ለውጥ የለውም። ከአልማዝ ተለይቼ ያሳለፍኳቸው ዓመታት በሙሉ በብረት አጥር ውስጥ ተከልዬ በፖሊስ እየተጠበቅሁና በአንድ ቦታ ተወስኜ አለመኖሬ ካልሆነ በስተቀር ከእሥር የተለዩ ስላልነበሩ ውጪው ዓለም እስከዚህም የሚያጓጓኝና አጥብቄ የምሻው አልነበረም፡፡ ድሮስ ቢሆን ነፃ በመሆኔና እንደልብ በመንቀሳቀሴ መች ተደስቼ አውቃለሁ? ይልቁንም የተሻለ ደስታን ያገኘሁት እሥር ቤት ውስጥ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ውስጤ ይህንን ይቀበለው እንጂ በዓይኔ የማየው ነገር ህሊናዬን እየተፈታተነ ያበሳጨኝ ጀመር። በፖሊስ ታጅቤ ከችሎቱ በመውጣት ላይ ሳለሁ ድንገት ዓይኔን ወደ ኋላ ወርወር አደረግሁ፡፡ ዶ/ር አድማሱ በደስታ እየተፍለቀለቀ አብረውት ከመጡት ጋር ብቻ ሳይሆን አጠገቡ ከቆሙትና ከማያውቃቸው ሰዎችም ጋር እየተቃቀፈ ይሳሳማል፡፡ በእሱ እምነት የፍቅረኛው ገዳይ በሠራው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት አግኝቷልና ለምን አይደሰት? ለምንስ አይቦርቅ? ወደ እስር ቤት እንደተመለስኩ እስረኛው ሁሉ የተፈረደብኝን እንደሰማ ክፉኛ አዘነ፡፡ ቀደም ሲል በሌሎች ላይ የሞት ፍርድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፍርድ ሲሰጥ እምብዛም የሚያዝን ሰው አልነበረምና ለእኔ ማዘናቸው ገረመኝ:: በተቃራኒው እኔ ከዚህ በፊት የማዝነው እስረኛ ሲፈረድበት ሣይሆን ሲፈታ ነበር፡፡ አለሙና የእሥር ቤቱ ካቦ ሲፈቱ አዝኛለሁ፡፡ ከቤተሰቦቻችን አንድ ሰው ጥሎኝ ወደ ውጪ ሀገር ለዘላለሙ ላይመለስ እንደሄደ ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ከተፈረደብኝ ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ጠበቃዬ አስጠራኝ:: በተፈረደብኝ ፍርድ ተስፋ እንዳልቆርጥ፣ ይግባኝ እንደሚልና እኔን ለማስፈታት የተቻለውን ያህል እንደሚሞክር ቃል ገባልኝ:: ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሳየው ግን ደስ አለኝ፡፡ ምናልባት ሃያ ዓመት እንደተፈረደብኝ ሳውቅ መብረክረኬ አሊያም ጠበቃዬ የሚፈልገውን በማግኘቱ ዳግመኛ አይመጣም ብዬ ገምቼ ስለነበር፣ መምጣቱን እንዳየሁ እውነትም ከልቡ እየተከራከረልኝ ነው ብዬ አስቤ ሊሆን ይችላል፡፡ እርግጥ ፈርቼም ሊሆን ይችላል፡፡ ትንሽ ቆይቼ ይፈቱኛል እንጂ እንዲህ ባልሰራሁት ወንጀል ሀያ ዓመት ይፈረድብኛል ብዬ አስቤ ስላልነበር ውሳኔውን ስሰማ ብፈራ አሊያም ብደናገር የሚደንቅ አልነበረም:: ከዚህ በላይ ደግሞ የመጨረሻው ፍርድ

ሲፈረደብኝ በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ ያየሁትን የደስታ ስሜትና ፈገግታ ላስታውስ መኖርን ፈለግሁ፣ መፈታትንም ተመኘሁ። እስር ቤት ውስጥ እኔና ጠበቃዬ ብቻ በአንዲት ክፍል ውስጥ ፊት ለፊት ተቀምጠን ያንን ሊፈታው ያልቻለውን እንቆቅልሽ መፍታት ላይ እንድረዳው በማሰብ ወደ ኋላ እየተመለሰ ታሪኮቹን በመተረክና በየጣልቃው በዚያው ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል የማውቀው ነገር ካለ ይጠይቀኝ ጀመር። ይህም ቢያንስ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ነገር ካለ እንዳስታውስ በማሰብ መሆኑ ስለገባኝ በጥንቃቄ እያዳመጥኩ መልስ እሰጠው ነበር።ከምስጠው መልስ ውስጥ የሚጠቅመውን አግኝቶ ይሁን ወይም ለእኔ ትኩረት መስጠቱን ለማሳየት እንደሆነ ባይገባኝም እየመረጠ ከጻፈ በኋላ፤ “አቶ አማረ፤ እንግዲህ ከዚህ በፊትም እንደነገርኩህ የአንድ በሽታ የመጀመሪያው ሀኪም ራሱ በሽተኛው ነው፡፡ መድሀኒቱን ባያውቅ እንኳን የቱ ጋ እንደሚያመው ከሀኪሙ በፊት አስቀድሞ የሚናገረው እሱ ነው:: ከዚያ በኋላ ነው ሀኪሙ እዛ ቦታ ላይ ምርመራውን የሚጀምረውና መድሀኒቱንም የሚያዘው:: ስለዚህ አንተም በበኩልህ በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሊሆኑ
የሚችሉ መረጃዎች ካሉ ለማስታወስ ሞክር፡፡ ማለትም ልትረዳኝ ይገባል“ አለ፡፡ እውነቱን ነው፤ እሱ ያለምንም ክፍያ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ላይና ታች ሲል እኔ ግን ላቀረበልኝ ጥያቄ ብቻ መልስና መረጃ ከመስጠት ውጪ ራሴን ለማዳን ያደረኩት ተጨማሪ ጥረት አልነበረም:: አሁን ሁሉም ነገር ካለቀ በኋላ ደግሞ ላደርገው የምችለው ነገር የለም፡፡ ቢኖርም የፈሰሰ ውሀ ለማፈስ የመሞከር ያህል ሆኖ ተሰማኝ፡፡ እሱ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ውትወታውን ቀጠለ፡፡ “አቶ አማረ፤ ለሁላችንም እንቆቅልሽ የሆነ ነገር አለ፡፡ ግን ይህንን እንቆቅልሽ መፍታት ያለብህ አንተ ነህ። እኔ በተፈረደው ፍርድ ላይ ይግባኝ ብያለሁ፡፡ ነገር ግን የማቀርበው አዲስ ነገር ስለሌለ በውስጤ ባዶነትና የተሸናፊነት ስሜት ይሰማኛል። ስለዚህ አንድ ከዚህ ቀደም ያልሰማሁትን አዲስ ነገር መስማትና ያላገኘሁትንና ያልደረስኩበትን አዲስ መረጃ ማግኘት እሻለሁ:: ይህ መረጃ ደግሞ ተዳፍኖ ወይም ተደብቆ ይሆናል እንጂ ጠፍቶ ሊቀር አይችልም:: ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያንዣብብኝ እንጂ ከዚህ ድርጊት ጀርባ እውነት ስለመኖሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እውነቱ ደግሞ የጠፋ እስኪመስል ድረስ ተዳፍኗል፡፡ ስለዚህ እኔ ብቻ ሳልሆን አንተም ይህንን ሐቅ በማውጣትና ሐቁን በመፈለግ በኩል ጠንክረህ ልትረዳኝ ይገባል፡፡ አለበለዚያ ይግባኙ ምንም ዓይነት ውጤት አይኖረውም:: በተለይ ዋናው እንቆቅልሽ ያለው አንተና እሷ ልትለያዩ በቻላችሁበት መንስዔ ላይ ነው:: እሷ አንተ ስለከዳሃት እንደተለያያችሁ ስትናገር፣ አንተ ደግሞ እሷ ስለከዳችህ መለያየታችሁን

ገልጸሃል፡፡ ግን ሁለታችሁም ብትሆኑ ለመለያየታችሁ እኔ መንስኤ ነኝ ብላችሁ አልተቀበላችሁም:: ስለዚህ እዚህ አካባቢ የተሰወረው ወይም የተዳፈነው ሐቅ በግልጽ መውጣት አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ አንተ እውነቱን ሳትደብቅ ልትነግረኝ ይገባል፡፡ ሌላው ቢቀር ላልሆነ ነገር እየለፋሁ ከሆነ የእኒ ልፋት ሊያሳዝንህ ይገባል'' አለኝ፡፡ እኔም ባነጋገሩ እጅግ አድርጌ ከውስጤ አዘንኩ:: አሁንም ከብዙ ጊዜ በኋላ እኔ በነገርኩት ነገር አለማመኑን ስረዳም የእሱ ብቻ ሳይሆን የእኔም ልፋት ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ:: ስለዚህ ባላመነው ነገር ተከራክሮ ነፃ ያወጣኛል ብዬ መገመት ጅልነት መሆኑንም ተገነዘብኩ:: ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? ዕድሌ ሆኖ የምናገረውን የሚያምንም ሆነ ንፁህ መሆኔን የሚቀበል ሰው አላየሁም:: ግን ምን አማራጭ አለ? ወይ እውነቱን ደጋግሞ በመናገር ከተቻለ ማሳመን አለበለዚያ መናገርን ማቆም ነው፡፡ መናገርን ማቆም ማለት ደግሞ ከራሴ በላይ ብዙ የደከመልኝን ጠበቃዬን ጭምር ማስከፋት ነውና ላሳምንበት የምችለው ነገር ካለ ብዬ ማሰላሰሉን ተያያዝኩት:: አእምሮዬ ተንቀሳቀሰ፡፡ ብዙ አወጣሁና አወረድኩ፡፡ ትዝታዎቼን ሁሉ አገላበጥኳቸው፡፡ እሷ የጻፈችው ደብዳቤ ትዝ አለኝ፡፡ ደብዳቤው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝና ከዚያ ወስዶ እንዲያነበው ስነግረው ልክ ያልጠበቀውን ወሬ የሰማ እስከሚመስል ድረስ ከመቀመጫው ተነስቶ ሳይሰናበተኝ ተጣድፎ ወጣ፡፡ ግራ ተጋባሁ! የሚፈልገውን ነገር በማግኘቱ ተደስቶ ይሁን ወይም _ በአመላለሴ ተበሳጭቶ ይውጣ ግን መለየት አልቻልኩም፡፡ ቢደሰት ኖሮ ቢያንስ ተሰናብቶኝ ይወጣ ነበር፡፡ ምናልባት ከእኔ ብዙ ነገር ሲጠብቅ ቆይቶ እኔ ግን አመላለሴ በአጭሩ ስለነበር የማፌዝ መስሎት ይሆን እንዴ? በማለት ተጠራጠርኩ፡፡ ግን ብዙም አልተጨነቅሁ፡፡ በማይሆን አጉል ተስፋ ተሞልቼ ነፃ እወጣለሁ ብዬ ከማሰብ ይልቅ እውነቱን ተቀብዬ ቀሪ ሕይወቴን እንደምኖር ኖሬ ማሳለፉ ሳይሻል አይቀርም ብዬ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ወደ ክፍሌ እንደተመለስኩም በይግባኙ ላይ ተስፋ ቆርጬ የእሥር ዘመኔን መደመርና መቀነስ ጀመርኩ፡፡ አሁን ዕድሜዬ ሰላሳ ሁለት ዓመት ነው፡፡ እዚህ ላይ የታሰርኩበትና የአመክሮ ጊዜ ተቀንሶ ቀሪው አስራ ስድስት ዓመት ሲደመር እሥሬን ስጨርስ አርባ ስምንት ዓመት ይሆነኛል ማለት ነው:: ስለሆነም ከእስራት ስፈታ ቢያንስ ያንን ዶክተር ለመበቀል የሚያስችል በቂ የአካል ብቃት ይኖረኛል ማለት ነው:: ዳሩ ይህንን ማሰቤ ጅልነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለምን ቢሉ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና በጡንቻ መመካት ድሮ ቀርቷል፡፡ ዛሬ አንዲት ትንሽ ጣት ቃታ ከሳበች ተራራ የሚያክል ሰው ትገነድሳለች::ለዚያች የምትበቃ ጉልበት ደግሞ የሰማንያ ዓመት አዛውንትም ቢሆን አያጡም:: ዋናው ነገር ከአምላክ የተጻፈችልኝ ዕድሜ ከአርባ ስምንት

ዓመት በላይ መሆኗን ማረጋገጥ አለመቻሌ ነው:: ይህንን ደግሞ ማረጋገጥ ስለማይቻል፣ እንዲሆን ከመመኘት ውጪ ሊደረግ የሚችል ነገር ባለመኖሩ አማራጩ እውነታውን ተቀብዬ የተለመደ ኑሮዬን መቀጠል ነው:: ያ ካልሆነ ደግሞ የልቤ ሳይደርስ የተዛባ ፍትሕ ስለባ ሆኜ መቅረቴ የማይቀር ነው:: አንድ ሰኞ ዕለት ስሜ ተጠርቶ ወጣሁ:: ጠበቃዬ ተመልሶ መጥቶ ወይም እጮኛው ያስጠራችኝ መስሎኝ ነበር:: ነገር ግን ሌሎች እስረኞችም እየተጠሩ ሲወጡና እንደተለመደው እጃችን የፊጢኝ እየታሰረ ወደ እስረኛ ማጓጓዢያ መኪና ስንገባ ግራ ተጋባሁ፡፡ ወዴት እንደምንሄድ አጠገቤ የነበረውን እስረኛ ጠየቅሁት:: እስረኛው የሚሄድበትን ቦታ በእርግጠኝነት እንደሚያውቀውና የተማከረ በሚመስል ሁኔታ፤ ''ወዴት ይወስዱናል? ይግባኝ ተብሎልህ ከሆነ ያው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነዋ የሚወስዱህ" አለኝ፡፡ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ በመግባት ላይ ላለሁ ኤልሳና ጠበቃዬ ፈንጠር ብለው ቆመው ሰላምታ ሰጡኝ፡፡ አንድ ነገር ገባኝ፡፡ የመጣሁት ጠበቃዬ ይግባኝ ብሎ መሆኑ ላይ እርግጠኛ ሆንኩ:: ይግባኙ አዲስ ነገር የሚፈጥር ባይሆንም በተስፋ መኖርም ጥሩ በመሆኑ ይግባኝ በመጠየቁ ደስ አለኝ፡፡ ምን ይታወቃል ጠበቃዬ እንደጠረጠርኩት ሳይሆን ከልቡ እየደከመልኝ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ተጠራጠርኩት እንጂ ያኔ የተፈረደብኝ ዕለት ከፊቱ ላይ የመከፋት እንጂ የተደበቀ የደስታ ስሜት አላየሁበትም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህንኑ ተቀብሎ በተስፋ መኖር ተስፋ ከማጣት የተሻለ ነውና እውነቱን ተቀብዬ አብሬው ለመጓዝ ወሰንኩ፡፡ አብረውኝ የመጡ እስረኞች በየተራ ወደ ችሎት እየተጠሩ ደርሰው ይመለሳሉ:: አብዛኞቹ እንደ እኔ ይግባኝ ያሉ ናቸው፡፡ ተራዬ ደርሶ እዚያቹ አለመድኳት ሳጥን ውስጥ ገባሁ:: ጠበቃዬ ከፊት ለፊት ተቀምጦ በፈገግታ ይመለከተኛል፡፡ ተስፋ አትቁረጥ ተስፋ አለን የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የሚሞክር መሰለኝ፤ አዘንኩለት፡፡ እኔ በሌላ ሁኔታ ብጠረጥረውም እሱ ግን አልተወኝም:: ፈገግታው ከልብ የመነጨ ስለነበር በውስጤ የተስፋ ጭላንጭል ጫረብኝ: ፍርድ ቤቱ እንደተለመደው በሰዎች ተሞልቷል:: ዛሬ ግን እነዚያ የመስሪያ ቤት ባልደረቦቼ አልተገኙም፡፡ እንደድሮው እስር ቤት እየመጡም

መጠየቁን ትተውታል:: የእኔ ነገር ማክተሙን ስለተረዱ ያላግባብ መድከም አልፈለጉም :: ከሃያ ዓመት በኋላ ለሚፈታ እስረኛ ማን መድከም ይፈልጋል የፍ/ቤቱና የይግባኝ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት የኔን ጉዳይ የያዘው ፋይል ተራ እንደደረስ የዕለቱ የችሎት ማብቂያ ሰዓት በመድረሱ ዳኛው ቀጠሮ ለመስጠት አጀንዳቸውን ሲያገላብጡ፣ ጠበቃዬ ነቃና ላቅ ባለ የትሕትና ስሜት፤ “ክቡር ፍ/ቤት፣ ምንም እንኳን አሁን ማስረጃ የማቅረቢያ ወቅት ባይሆንም ተከሳሹ ወንጀሉን አለመፈፀሙን ማረጋገጥ የሚያስችል ማስረጃ እጄ ውስጥ ገብቷል:: በመሆኑም ፍ/ቤቱ ያላግባብ ደንበኛዬ ባልሰራው ወንጀል ሃያ ዓመት እንዳይታሰርና ጉዳዩም በተጓተተ ቁጥር እውነቱ ተደብቆና ተድበስብሶ እንዳይቀር ሲባል መረጃዎቼንና የማቀርበውን ተጨማሪ የሰው ማስረጃ
እንዳቀርብ እንዲፈቅድልኝ በትህትና እጠይቃለሁ" አለ፡፡ ዳኛው ሰዓታቸውን አይተው ይግባኙን እንዲያቀርብ ሲፈቅዱ፣ አቃቤ ሕግ ከመቀመጪያው ተነስቶ፤ “ተቃውሞ አለኝ፣ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ" አለ:: ዳኛው ተቃውሞውን እንዲያቀርብ ዕድል ሰጡት:: እሱም ቀጠል አድርጎ፤ “ይህ የይግባኝ ሥርዓት እንጂ ማስረጃ የሚታይበት ወቅት ባለመሆኑ ክቡር ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን እንዳይቀበለው እጠይቃለሁ'' አለ፡፡ ዳኞቹ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩና ከጠበቃዬ የቀረበውን ሰነድ በሥነ- ሥርዓት አስጠባቂ በኩል ተቀበሉ፡፡ ጠበቃዬ ምን አዲስ መረጃ እንዳገኘ ባላውቅም ለእኔ ከድካም ውጪ ሊያስገኘው የሚችል ፋይዳ አልታይህ አለኝ:: ጠቃሚ መረጃ ብሎ ሊያቀርበው የሚችለው ባለፈው መጥቶ በነበረ ጊዜ ከፖሊስ ጣቢያ እንዲወስድ የነገርኩት ደብዳቤ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል የታወቀና በኤግዚቢትነት የተያዘ ስለነበር አዲስ ነው ከተባለ ለእሱ እንጂ ለሌላው አዲስ አልነበረም:: በሌላ በኩል ደግሞ እኔን ነፃ የሚያወጣ የሰው ማስረጃ ተገኘ ከተባለም መሆን ያለበት የገደልኳት እኔ ነኝ የሚል ሰው ከተገኘ ብቻ ነው:: እንዲህ ዓይነት ሰውም ከተገኘ እጅግ በጣም መንፈሳዊ አለበለዚያም ቂል ካልሆነ በስተቀር እሱ የሰራው ወንጀል በተሳካ ሁኔታ ተደብቆለትና ለእሱም ጥፋት ለሀያ ዓመታት የሚታሰርለት እስረኛ ተገኝቶ እያለ እኔ ነኝ ገዳይዋ ብሎ ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ የመጠበቅ ያህል ነው:: በመሆኑም ለደስታም ሆነ ለሐዘን አንዳችም ቦታ አልነበረኝም፡፡ ይልቅ የጓጓሁት ዳኞቹ የሚወስኑትን ውሳኔ ለመስማት ነበር።

ጠበቃዬ ያቀረበው ማስረጃ በአባዲና ፖሊስ የምርመራ ክፍል ተመርምሮ ውጤቱ ለመስከረም 5 ቀን 1983 ዓ.ም እንዲቀርብ ወስነው ችሎቱን ተነሳ:: እኔም ክችሎቱ ወጥቼ ወደ እስር ቤቱ መኪና እያመራሁ ላለ ጠበቃዬና ኤልሳ ወደ እኔ እያዩ፤ በእነሱ እይታ በቲ ማስረጃ ስላገኙ ነፃ እንደሚያወጡኝ እርግጠኛ መሆናቸውን በፈገግታ መልዕክት ገለፁልኝ:: በሰማሁት እና ባየሁት ነገር ብዙም ባልደስትም በውስጤ ተስፋ ሰንቂ ወደ እሥር ቤቴ አመራሁ:: ወህኒ ቤት እንደገባሁ ውሎ እንዴት ነበር እያሉ እስረኞች ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ የሆነውን ነገር ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኳቸው:: መቼም እስረኛ ሲባል ሌላ "የሕግ ባለሙያ'' ማለት ነው:: እያንዳንዱ አስረኛ እንዴት ራሱን መከላከል፤ የቱን መካድና የቱን ማመን እንዳለበት የሚያማክሩ የእሥር ቤት የሕግ ምሁራን እዚያው ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ምሁራን ታዲያ በእኔ ጉዳይ ላይ ባልጠቀምበትም ቀደም ሲል እንዴት መካድ እንዳለብኝ አስረግጠው አስረድተውኛል:: መቼም አውጥተው አይናገሩት እንጂ አንዳቸውም በመግደሌ ላይ ጥርጣሬ አልነበራቸውም:: በዚህም የተነሳ ይመስላል እየደጋገሙ እዚህ እውነት ብትናገር ችግር የለውም፤ ዋናው ነገር ፍርድ ቤት ሲሆን ነው መጠንቀቅ ያለብህ፡፡ ይልቁን ገድለሀት ከሆነ አገዳደልህን በደንብ ብታስረዳን እንዴት ራስህን መከላከል እንዳለብህ ስለምናማክርህ እዚህ መናገርህ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም" እያሉ "እውነቱን" እንዳወጣ ይጨቀጭቁኝ ነበር። ዛሬም እንደተለመደው በእኔ ጉዳይ ላይ በራሳቸው የሕግ ትንተና ላይ የተመሰረተ መላ ምት መስጠት ጀመሩ፡፡ “እኔ እንደሚመስለኝ፣ አማረ እንዳለው ንፁህ ከሆነ ሊሆን የሚችለው ቀደም ሲል ያልተገኘ የገዳዩን አሻራ ፖሊስ አግኝቷል ማለት ነው" ሲል፡፡ ሌላው የሕግ ምሁር ቀበል አድርጎ፤ “እንዴት ሊሆን ይችላል? ፖሊስ ቀደም ሲል ያላገኘውን አሻራ እንዴት አሁን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ሊያገኝ ይችላል? አሻራው በሩ ላይ ይኸን ያህል ጊዜ ተለጥፎና ተደብቆ ቆይቶ አሁን ተገኝቶ ይሆናል ልትለን እንዳይሆን?' አለ፡፡ አጅሬ እንዲህ በቀላሉ መረታት ስላልነበረበት፣ “እንዲህ ዓይነት ፍሬከርስኪ ወሬ እያወራሁ አይደለም፡፡ እኔ ማለት የፈለኩት፤ አሻራው በፊት ተገኝቶ ሊሆን ይቻላል፡፡ ግን አሻራው የማን እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቶ አሁን ግን አሻራው የማን እንደሆነ ታውቆ ቢሆንስ? ለዚህም ይመስለኛል እንደገና የአባዲና ምርመራ የተፈለገው'' በማለት መለስ። ሌላኛው "ምሁር" ትራሱን ደገፍ እንዳለ ድምፁን የምሁር ለማስመሰል እያንዳንዷን ፊደል እየቆጠረና በመሀል እ... እ... የሚለውን ድምጽ እየደጋገመ

“እኔ እንደሚመስለኝ እ... እ... ጠበቃው አለኝ ያለው የሰነድና የሰው ማስረጃ እስከሆነ ድረስ እ... እ... አንድ ወንጀሉ ሲፈፀም PP ግለሰብ የአማረ ያላግባብ ተፈርዶበት ወህኒ መውረድ አሳዝኖት ወንጀሉን ማን እንደፈፀመ ማየቱን ገልዖ የፃፈው ደብዳቤ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል፡፡ እ... እ... ደግሞም አቀርበዋለሁ ያለው ማስረጃ ይኼው ግለሰብ የሚሰጠው የምስክርነት ቃል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግለሰብ ምናልባት እንደሚመስለኝ ሆቴል ውስጥ ያለ አስተናጋጅ ወይም ዘበኛ ሊሆንና ገዳዩ ገድሎ ሲወጣ አይቶ ሊሆን ይችላል":: ሌላኛው የቀረበውን የሕግ መከራከሪያ ነጥብ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችለውን ሐሳብ ለማፍለቅ ጣራ ጣራ ሲያይ ቆይቶ፤ “ግን እኮ ይኼ ሊሆን አይችልም ባይባልም፣ በፊት መጥቶ ለአማረ ያልመሰከረ ዘበኛ ወይም አስተናጋጅ አሁን እንዴትና ከየት ሊመጣ ይችላል?" በማለት ቢያንስ በጥያቄ መልክ በቀረበው አስተያየት ክርክሩን መሠረት ለማሳጣት ሲሞክር፣ ሌላው ምሁር ቀበል አድርጎ፣ “ይህማ ሊሆን የሚችለው መጀመሪያ ላይ ፈርቶ ቆይቶ በኋላ ግን አላግባብ የአጅሬ መታሰር እረፍት ነስቶትና ተፀፅቶ እ... እ... ወይም ጠበቃው ሁኔታውን ደርሶበት እንዲመሰክር ወይ አግባብቶት አሊያም አስፈራርቶት ሊሆን ይችላል"፡፡ ይኼንን የክርክር ነጥብ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የመርቻ ሐሳብ የመጣለት ሌላኛው ምሁር፤ “እንዴ! ያበደ ካልሆነ በስተቀር እንዲህማ አያደርግም! ወንጀል ሲፈፀም አይቶ ዝም ማለት በራሱ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እስከአሁን ዝም ብሎ ኖሮ አሁን ሊተነፍስ ቢሞክር ራሱን በገመዱ ማስገባቱ ነው፡፡ ይህንን ያህል ጊዜ ሳይናገሩ መቆየትም በሕግ ያስጠይቃል" ሲል ንግግሩን ቋጨ ፤ “መመስከርማ አለበት እ... እ... እንዲያውም ወንጀል የሚሆነው ከነጭራሹ ደብቆ የኋላ ኋላ የታወቀ እንደሆን ነው:: አሁን ባድራጎቱ ተፀፅቶ በራሱ ተነሳሽነት እውነቱን የሚመሰክር ከሆነማ በሕግ የሚጠየቅ አይመስለኝም' ሲል፤ ሌላው እስካሁን ሳይናገር ክርክሩን ሲያዳምጥ የነበረ እስረኛ፣ “በሕግ መጠየቅማ አለበት፡፡ እስኪ አስቡት፤ እሱ ቀደም ሲል መስክሮ ቢሆን ኖሮ ወንድማችን ይህንን ያህል ጊዜ ባልታሰረና ሊጠግን የማይችል የህሊና ስብራት ባልደረሰበት ነበር፡፡ ስለዚህ ለዚህም በደሉ በሕግ መጠየቁማ

የማይቀር ነው" በማለት በቁጣ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ:: በመጨረሻም ምሁሩ የማሳረጊያ በሚመስል መልኩ፤ “እ... እ... ምንም ይሁን ምን፤ ጠበቃው የታወቀ ጠበቃ እንደመሆኑ መጠን እንደዚህ እርግጠኛ ሆኖ ማስረጃ ላቅርብ ያለው አንድ ሊረታበት የሚችልበት መረጃ አግኝቶ እንጂ እንዲያው ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ ሊሆን አይችልም፡፡ እ... እ...
ደግሞም መረጃው ፋይዳ ቢስ ቢሆን ኖሮ ዳኞቹም ቢሆን በዚህ ወቅት የአሠራር ሥርዓት ስለማይፈቅድ የሚያሳምን ነገር ባያገኙ ኖሮ መረጃውን ተቀብለው ለምርመራ ባልላኩት ነበር። እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የአጅሬ ሃያ ዓመት ፍርድ ወደ ሃያ ቀን መለወጡ ነው ማለት ነው" በማለት ውይይቱን ደመደመ:: ከዚህ የተሻለ የመከራከሪያ ነጥብም ሆነ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበ ስላልነበር ክርክሩ በዚሁ ተቋጨ፡፡ ክርክሩ ለእኔ የሚፈይደው ነገር ባይኖርም፣ ቢያንስ ሁሉም የእኔን ንፁህነት ተቀብለው በመከራከራቸው ደስታ ተሰማኝ፡፡ እራሴ የፈጠርኩት ስሜት እንጂ ለካስ በእኔ ንፁህነት የሚያምን ብዙ ሰው ነበር ማለት ነው በማለት በራሴ መፅናናትም ጀመርኩ፡፡ ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን፣ ፍርድ ቤት ቆሜ ጠበቃዬ ሲከራከር፣ ፈገግ ሲልና አይዞህ ተስፋ አለን እያለ ሲያፅናናኝ ምንም ተስፋ አልታይህ እንዳላለኝ ሁሉ እዚህ ግን ምሁራኑ የተለያየ የመከራከሪያ ነጥቦችን እያነሱ ከተወያዩ በኋላ የደረሱበትን መደምደሚያ ስሰማ እውነት የሆነ ያህል ተስፋ በሰውነቴ ውስጥ ተጫረ። በዚህም የተነሳ የቀጠሮ ቀኑ ደርሶ እውነቱን ማወቅና የሚቀርበው ማስረጃም ምን እንደሆነ ለመስማትና ለማየት ጓጓሁ።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
#አላገባህም


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ዘሚካኤል  ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ ያለውን የሰርግ የጥሪ ካርድ የያዘውን ፖስታ በራፉ አጠገብ በሚገኘው ቆሻሻ ማጠረቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ጨምድዶ ወረወረው፡፡

ለዛች ስሟን እንኳን ላልነገረችው ሴት ልጅ እንደነገራት በዚህ አለም ምንም አይነት  ወንድም ሆነ ቤተሰብ አያስፈልገውም እና ወደ የትኛውም ሰርግ የመሄድ ፍላጎት የለውም። እንደውም ከተቻለው ስለቤተሰብ በውስጡ የቀረውን እንጥፍጣፊ ትዝታ ከልቡ አሟጦ መሰረዝ ነው ፍላጎቱ፡፡

ከወገብ በላይ ራቁቱን መሆኑን ትዝ ሲለው ወደጠረጴዛው ሄደና ያወለቀውን ልብስ መልሶ ለበሰው..መጀመሪያ እቅዱ ቀጣይ የሙዚቃ ማቅረቢያ ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ሻወር ገብቶ ከተለቃለቀ በኃላ 30 ወይም 40 ደቂቃ መተኛትና እረፍት መውሰድ ነበር፡፡አሁን ግን ሻወር የመውሰድም ሆነ የመተኛት ፍላጎቱ ከውስጡ በኖ ጠፍቷል…ቀጥታ ሶፋው ላይ ሄደና ተቀመጠ፡፡ፊትለፊት ካለው ጠረጴዛ ላይ ያለውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳና ከፍቶ በብርጭቆ ቀድቶ እየተጎነጨ ማሰላሰል ጀመረ….

‹‹ይህቺ ልጅ ምኑን ነክታ እንዴት ስሜቱን ድፍርስርስ አድርጋ እንደሄደች አያውቅም…ወንድሙ ላይ የያዘበት ቂምና የተበሳጨበት ብስጭት አሁንም ትኩስ ነው፡፡

‹‹ግን የዛን ጊዜ ፈቅዶልኝ አባቴን በዛ ቢላዋ ጨቅጭቄ ብገድለው ኖሮስ…?››ሁል ጊዜ እራሱን የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡

አዎ ወንድሙ በድብድብ እና በትግል ባያስቆመው ኖሮ እሱም ይሄን ጊዜ የእድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶበት በአባቱ ምትክ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎበት ተስፋ የሌለው ህይወት ይኖር እንደነበረ…እርግጠኛ ነው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ ሚካኤል ወንድምህ የእድሜ ልክ ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም?››አለው አእምሮው፡፡

‹‹ለምን..ያማ እውነት አይደለም….እሱ እኮ  እንደዛ ያደረገው እኔን ከመከራ ለማትረፍ አስቦ ሳይሆን ለዛ ጨካኝ እና ገዳይ አባቱ ለማገዝ ፈልጎ ነው››

‹‹አይ እሱ የአንተ አእምሮ አንሻፎ የተረጎመው ትርጉም ነው…እንደዛም ቢሆን እንኳን በዛ  ታሪክ ውስጥ ዋናው ተጠቃሚ አንተ ነህ፡፡በወቅቱ ዝም ብሎህ ያሰብከውን እንድታደርግ ቢፈቅድልህ ኖሮ ዛሬ በዚህ ጊዜ ዝነኛው ድምፃዊና ተዋናዩ ዘሚካኤል የለም ነበር…ሀመር መኪና የሚነዳው…የተንጣለለ ውድና ውብ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖረው…ከአደባባይ እስከቤተመንግስት የሚታወቀውና የሚጋበዘው የመገናኛ ብዙሀኖች የዜና ማጣፈጫ የሆነው ዘሚካኤል አይኖርም ነበር፡፡››ሲል እራሱን በራሱ በዝርዝር አስረዳ፡፡
የአእምሮው የእርስ በርስ ጭቅጭቅ ከዚህ በላይ ማስቀጠል አልቻለም..ምክንያቱም በንዴትና በቁጭት አእምሮው ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱ እየጋለበት ነው፡፡ጠረጴዛው ላይ ያለውን ብርጭቆ አነሳና ጠቀም አድርጎ ተጎነጨለት እና መልሶ አስቀመጠው፡፡
ከዛ ስለሌላ ነገር ለማሰብ ሞከረ ..ግን አሁንም አእምሮውን የሞላችው ያቺ ከደቂቃዎች በፊት ከሰውነቱ ለጥፎ ያቀፋትና ለሁለት ሰከንድ ሲስማት የነበረችው ሴት ነች፡፡‹‹ቆይ ይህቺ ልጅ ምን የተለየ ነገር ቢኖራት ነው ከአእምሮዬ ልትወጣ ያልቻለችው ?››እራሱን ጠየቀ…‹‹ከንፈሯ ላይ አስማት አለ መሰለኝ…››አለና ፈገግ አለ….‹‹ምን አለ ስሟን እና  የሞባይል ቁጥሯን ብጠይቃት ኖሮ…?››በጣም ተቆጨ፡፡
ደግሞ እሷም እሱን በምንም አይነት ሁኔታ ደግማ  የማግኘት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳይ ሁኔታ ነው የመጣችበትን ጉዳይ ተናግራ የጥሪ ካርድን እጁ ላይ አስቀምጣ ነው ውልቅ ብላ የሄደችው፡፡

‹‹ባለትዳር ትሆን እንዴ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡
ሀሳብን መቋጫ ሳያበጅለት በራፉ በስሱ ተቆረቆረ…ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን ውስኪ ጨለጠና ሶፋውን ለቆ ወደበራፉ ሄደ ..ቀጣይ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜ መድረሱን ለማሳወቅ በራፉን እንደቆረቆሩ ያውቀል..በራፉን ከፍቶ ሲወጣ ንቁ ሆነው የሚጠብቁት ሁለት ወጠምሻ ጋርዶች ከግራና ከቀኝ ከበቡት፡፡ ሁለት እርምጃ ከተራመደ በኃላ የሆነ ነገር ወደኃላ ሳበው…መልሶ ፊቱን ዞረና ወደክፍሉ ተመለሰ….ከውስጥ በኩል ከበራፉ በስተቀኝ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባስኬት አጎነበሰና አጣጥፎ የጣለውን የሰርግ ጥሪ ወረቀት አነሳ ፡፡የሱሪ ኋላ ኪስ ውስጥ ጨመረውና መልሶ ወጣ..ለምን እንዲህ እንዳደረገ ቢጠየቅ ምንም አይነት መልስ የለውም …እንዲሁ በደመነፍስ ያደረገው ነገር ነው፡፡
////
አሁን የዘሚካኤል ምስል ከሙሉ አቋሙ ጋር በአእምሯዋ እየተራወጠ ነው፡፡ሁለቱ ወንድማማቾች ከቁመትና ከፀባይ ውጭ በሌላው ነገር በሚያስደንቅ ሁኔታ ይመሳሰላሉ። የሚካኤል  ባህሪያት ከዘሚካኤል ትንሽ ደብዘዝ ያሉ ነበሩ እና የዓይኑ ቀለም ንፁህ ፣ ጠንከር ያለ ሰማያዊ ነበረ ፣ ግን ሁለቱም ሰዎች ተመሳሳይ ውብ ፈገግታ፣ ክብ የፊት ቅርፅ እና ሰልካካ አፍንጫ.. ወተት ከመሰሉ ነጫጭ ድርድር ጥርሶች ጋር አላቸው፤››
እየሾፈረች ያለችውን ቪታራ መኪና ኤክስፐረስ መንገድ ውስጥ አስገብታ ወደ አዳማ እያሽከረከረች   ሲሆን አሁንም ስለዛ ዘ-ሚካኤል ስለሚባለው ድምጻዊ ነው የምታሰላስለው፡፡ለሊት 8 ሰዓት ላይ ከእሱ ተለይታ እዛው በአቅራቢያው ወደተከራየችው ፕንሲዬን ሄዳ ለመተኛት ብትሞክርም ምንም እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር እንዲሁ ስትበሳጭና ስትገላበጥ ነው ያደረችው፡፡
ስለእሱ ማሰብ   የጀመረችው ቀደም ብላ ታሪኩን ከየጋዜጦችና ከዪቲዩብ ቻናሎች እየሰበሰበች በምታዳምጥበት ጊዜ ነው፡፡እርግጥ ታውቀለች በዩቲዩቭ የቀረበ ዜና ሁሉ በተለይ ስለፍቅርና ፃታዊ ግንኙነት የሚነዙት አብዛኞቹ ተመልካች ለማግኘት የታስቡ…በውሸት የሚፈበረኩ እንደሚሆን ታምናለች..ግን ቢሆንም‹‹ እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም….››በማለት ለሰው ስሜት የማይጨነቅ ጋጠወጥ ወሲባም አድርጋ ስላው ነበር፡፡እና ደግሞ ለሊት እንዳየችው አልተሳሳተችም…በዛ ለሊት እዛ ክፍል ውስጥ ሲያገኛት መጀመሪያ ያደረገው ወደራሱ ስቦ ከንፈሯ ላይ መጣበቅ ነው…..ስለዛች ቅፅበት ስታስብ ከንፈሯ  ተንቀጠቀጠባት….የሚያበሳጨው ደግሞ ለማንም ሴት ግርማ ሞገሱንና ውበቱን ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆነ ሰው መሆኑን በራሷ ማረጋገጧ ነው…ባለፉት ስድስት አመታት በጣም ብዙ ከሆኑ ወንዶች በብዙ የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈታተኗት ሞክረው ሾልካና አሳስቃ ..አንዳንዱንም ተኮሳትራና አስፈራርታ እራሷን ማትረፍ ችላለች..ከእሱ ጋር ግን በአንድ እይታ ነው ተዝለፍልፋ እቅፉ ውስጥ የወደቀችው፡፡
እንደምንም ከእቅፉ ወጥታ ለማምለጥ ወደበራፉ  በምትራመድበት ጊዜ እንኳን ተንደርድሮ መጥቶ እጇን ይዞ  ጎትቶ እንዲያስቀራት እና ተሸክሞ ሶፋው ላይ እንዲጥላት በውስጧ እየተመኘች ነበር፡፡ግን በተመሳሳይ ጊዜ እንደዛ በመመኘቷ እራሷን ስትወቅስና ስትራገም ነበር፡፡
ባይሰማትም  ‹‹ዘሚካኤል  አንተ እብሪተኛ  እና ጅላጅ ሰው ነህ›› ስትል ተሳደበች፡፡ነገር ግን ነገሩን በጥልቀት ስትመረምረው እሱ ብቻ ጥፋተኛ አልነበረም። እሷም  ለተፈፀመው ጥፋት ትልቅ ድርሻ መውሰድ አለባት።
እንዴት እንዲህ ያለ ቸልተኛ እና ኃላፊነት የጎደላት ሴት  ልትሆን ቻለች? እንዴት እንዲህ አይነት ውጥንቅጥ ነገር ልትሰራ ቻለች?በራሷ ተግባር በዚህ ልክ ስትበሳጭ ይሄ የመጀመሪያዋ ነው፡፡
ዘሚካኤል አጥብቆ ና ጨምቆ የያዛት ክንዷን  አሻሸች… በትክክል እንዴት እንደሆነ ታውቃለች። ልክ እሷን እንዳየ ፣ ከንፈሯን  እንደነካ ፣ ጠቅላላ ሰውነቷ ያልተበረዘ የደስታ መጥለቅለቅ ነው ያስተናገደው።
አዳማ እንደገባች ቀጥታ ከአዲስ አለም ጋር ነው ተገናኘችው፡፡እና ሆነችውንና ያጋጠማትን አንድ በአንድ በዝርዝር አስረዳቻት፡አዲስ አለምም አፏን ከፍታ በጉጉት ስታዳምጣት ከቆየች በኃላ
‹‹ታዲያ ምን ያበሳጭሻል …እንደውም በራስሽ መኩራት  ነው ያለብሽ››

‹‹ማለት?››

‹‹ቀሽት የሆነ  ዜና ነው  እኮ እየነገርሺኝ  ያለሽው …ወይ ጉድ ››

‹‹ድንገት እኮ ነው የሆነው …ክፍሉ ውስጥ ተደብቄ ገባሁ….››  ትንፋሽ ወሰደች።‹‹አውቃለሁ  ግድየለሽ እና ኃላፊነት የጎደለው ነገር ነው ያደረኩት››

አዲስ አለም‹‹ አንቺ የሆነ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ገብተሸ …እኔ አላንም›› ብላ ሳቀች።

‹‹ይህ ደደብ  በሰርጉ ላይ እንዲመጣ ላሳምነው ሀሳብ ነበረኝ …እችላለሁ የሚል እምነት ነበረኝ። ››እጆቿን በጭኖቾ መካከል አድርጋ እርስ በርሳቸው ማፋተግ ጀመረ‹‹እርግጥ ..አንቺ እና ሚካኤል  እሱን ምን ያህል እንደምትፈልጉት አውቃለሁ..ያደረኩትን ሁሉ ያደረኩት እናንተን ለማስደሰት ካለኝ ምኞት የተነሳ ነው። ››
‹‹እና መጨረሻው እዴት ሆነ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ምን መጨረሻ አለው..እንደምንም ወደቀልቤ ተመልሼ ራሴን ነፃ አወጣሁና የመጣሁበትን ጉዳይ እስረድቼው ካርዱን ሰጠሁትና ክፍሉን ለቅቄት ወጣው፡፡››ስትል መጨረሻውን ነገረቻት

‹‹ቆይ…. እዚሁ  አብረሺኝ እደሪ ምናምና አላለሽም››

‹‹እንዴት እንደዛ ይለኛል..?ትንሽ ጠብቂኝና የምትሄጅበት ድረስ ልውሰድሽ ብሎኝ ነበር..እኔ ግን ከእሱ መሸሽና እሰከወዲያኛው መገላለል ነበር የፈለኩት፡፡››

‹‹እንዴት ነው አሳሳሙ..ቅልጥ ነው አይደል የሚያደርገው?››ጥያቄው የመጎምዠት ስሜት የተጫነው ነው፡፡

‹‹ሴትዬ በቃሽ …ለራሴ በጣም ተናድጄለው ይበልጥ አታናጂኝ››ፀአዳ ተቆጣች፡፡

‹‹ይገባኛል የእኔ ቆንጆ ..ምንም የሚያፀፅት ነገር እኳ አላደረግሽም…መልከ መልካም ና ቆንጆ የሆነውን ሙዚቀኛና ተዋናይ በቀላሉ አግኝተሸ ሳምሽው ..ስለዚህ ያ ድንቅ ነገር ነው..እንደውም ሚያሸልምሽ ጉዳይ ነው።››

‹‹ዝም በይ ባክሽ?›› ፀአዳ ለጓደኛዋ ትችት  ወጥመድ ውስጥ እንደገባች ተረዳች፡፡

‹‹ግን ምን አይነት ስሜት  እንደተሰማሽ ማወቅ አፈልጋለው።ብቻ ንገሪኝ እስኪ እሱ በፊልሞቹ ላይ እንደሚታየው  በሥጋው ውስጥ ሞቃት ሆርሞን  የሚራወጥበት አቅልጥ ወንድ ነው?››

‹‹አንቺ ባለትዳር እኮ ነሽ…እንደዚያ ማለት አትችይም። በተግባር ያገባሽ ሴት ነሽ..ለዛውም ወንድሙን ያገባሽ።ስትቁላይ ላየሽ ግን አትመስይም››እንደዚህ ጠንከር ያለ ነገር ተናግራት አፏን ልታዘጋት ፈልጋ በስሌት የሰነዘረችው ዓ.ነገር ነው፡፡

‹‹ምን አጠፋው….አገባሁ እንጂ ሴትነቴን አውጥቼ እኮ አልጣልኩትም ..ውበት ማድነቅ እችላለሁ…አማላይ ወንድ ፈርጣማ ሰውነት በአይኔ ላይ ሲንከባለል አይኔን አልጨፍንም….አንቺ ግን በአጋጣሚ በከፊልም ቢሆን  ጾምሽን ፈታሽ ማለት ይቻላል ? እና በህይወትሽ  ያለፉትን ስድስት አመታት ስለአንድ ሰው በመብሰልሰል አባክነሽዋል››

‹‹ምን ለማለት እንደፈለግሽ አላውቅም?። ››

‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ቀሚስ የለበሺው  መቼ ነው?››

‹‹እኔ ቀሚስ አልወድም። አይመቸኝም››አለች።'

‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ሜካፕ የተጠቀምሺውስ  መቼ ነው? ወይ ጭፈራ ቤት ገብተሸ የምታውቂው መቼ ነው?ከአንድ ማራኪ ሰው ጋር የመሽኮርመም ስሜት ተሰምቷሽ የሚያውቀው መቼነው?

››አዲስአለም ንግግሯን ለደቂቃ አቆመች…ከዛ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹ ከዘሚካኤል ጋር በመሳሳምሽ  ለምን ታፍሪያለሽ? ሰውየው የእያንዳንዱ ሴት የሩቅ ህልም ነው ..አንቺስ ገና የ22 አመት ለግላጋ ወጣት አይደለሽ? ለምን ልትስሚው አትፈልጊም?ነው ወይስ የጤንነት መታወክ አለብሽ..?ይሄ አይነጥላ ምናምን የሚሉት››

‹‹በቃ ተይኝ እስኪ››

‹‹ነው ወይስ አሁንም ያ ወታደርሽ ከለሁበት ፈልጎ ያገኘኛል የሚል ምኞት ውስጥ ነሽ?››

‹‹አረ ተይኝ…ምን ብዬ ነው በቁሜ ገድሎኝ የሄደን ሰው መጥቶ ከሙታን ያስነሳኛል ብዬ የምጠብቀው..ስታይኝ ያን ያህል ጅል እመስልሻለው እንዴ?›››ፀደይ እስከአሁን ከተበሳጨችው በላይ ተበሳጨች፡፡

‹‹እኮ እንደዛ ከሆነ ዘና በያ…ገና ለገና አንድ ሸበላ ወንድ ጋር ተሳሳምኩ ብለለሽ እንዲህ አመድሽ የወጣ.. ሱሪሽን ብታወልቂለት ምን ልትሆኚ ነው?››

‹‹በስመአብ በይ!!!››አማተበች፡፡‹ ስለእሱ የምትቀባጥሪው… ምንም ለውጥ አያመጣም….ይልቅ ትርኪ ምርኪውን ተይና ስለዋናው ነገር እናውራ…እኔን ያናደደኝ ዋናው ጉዳዩ ወደ ሰርግ ለመምጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ወንድም የለኝም እያለኝ ማለቱ ነው …እንዴት…..?››ንግግሯን ሳትጨርስ ሚካኤል ድንገት መጥቷ ስለተቀላቀላቸው  አፏን እንደከፈተች ቀረች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe እያደረጋጁ አይደለም 500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ //// ዘሚካኤል  ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ…»
#አላገባህም


#ምዕራፍ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
‹‹ እንዴት ናችሁ.?.የሴት ወሬ ላይ ነበራችሁ መሰለኝ….በመምጣቴ ምቾት አልተሰማችሁም››አለ፡፡

‹‹እንዴ ባልዬው የሴት ወሬ ደግሞ ምንድነው?››ስትል አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው ወንዷችን ማማት ነዋ››ሲል በፈገግታ መለሰላት፡፡

‹‹አንተ እንደዚህማ አትለንም….በዚህ ፀባይህ ላላገባህ እችላለው…የደገስከው ድግስ  ብላሽ እንዳይሆንብህ

ፀአዳ ጣልቃ ገባች‹‹አንቺ እንደዛማ አታስፈራሪውም..እስኪ ልብ ይኑርሽና እምቢ በይው….የልጅ እናቷን ሳይሆን ልጃገረዶችን ነው የማንጋጋለት››ስትል  መለሰች፡፡

‹‹አንቺ እስስት ለሁለታችንም እኮ ነው እየተሞገትኩ ያለሁት››

‹‹ያንቺን ሙግት አልፈልግም …ይልቅ ሚካኤል… አንተን እና አዲስአለምን ይቅርታ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር። ››አለችው ኮስተር ብላ፡፡

‹‹ምነው ምን ተፈጠረ?››ሚካኤል ብቻ ሳይሆን አዲስአለምም ያልጠበቀችው ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡

‹‹ወንድምህን ዘሚካኤል በሰርጋችሁ ቀን እንዲገኝ ለማድረግ የተቻለኝን ጥሬ ነበር…ግን አልተሳካልኝም፣ አሁን የሚመጣበት ምንም ዕድል የለም።››አለችው፡፡

‹‹ለምን ይቅርታ ትጠይቂያለሽ ? እሱ እንደማይመጣ አስቀድመን እናውቅ ነበር፣››በማለት ሚካኤል ተናገረ፡፡

አሁን ግራ የመጋባቱ ተራ የራሷ የፀዳ ሆነ‹‹ቆይ ለመሞከር እንደሄድኩ ታውቅ ነበር እንዴ?››ስትል በጥርጣሬ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡

ፈራ ተባ እያለ በሹክሹክታ‹‹አዎ..አውቅ ነበር››አላት፡፡

ወደአዲስአለም ዞረችና‹‹አንቺ በቃ ሚስጥር የሚባል ነገር አታውቂም..ለዛውም እንዳትነግሪው ብዬ አስጠንቅቄሽ?››

‹‹አንቺ ደግሞ ባልና ሚስት አንድ ሀምሳል አንድ አካል ናቸው ሲባል አልሰማሽም እንዴ? ከገዛ አካሌ ምን ብዬ ነው የምደብቀው?››

‹‹አረ የምትገርሚ ነሽ…ሚኪ ግን በጣም አዝናለው…››

‹‹ምን ያህል እንደሞከርሽና እንደጣርሽ አውቃለው….በእውነት አዲስ በነገረች ቀን እንባ አውጥቼ ነው ያለቀስኩት..ማንም ሰው እዲህ አይነት ነገር ላድርግለህ ብሎኝ አያውቅም ..እህቴ በጣም ነው የምወድሽ …በጣም ነው የማመሰግንሽ››አላት

‹‹እኔም በጣም ነው የምወድህ››አለችና ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችበት፡፡እሱም ተቀብሎ አቀፋት፡፡

‹‹እናንተ እኔንም እኮ አስቀናችሁኝ››አለችና ከተቀመጠችበት ሄዳ ሁለቱንም አንድ ላይ አቀፈቻቸው፡፡
///
መድረስ አይቀርም ለአመታት  ሲታሰብበት እና ለወራት ሲለፋበት የነበር የሰርግ ቀን ደርሶ አዳራሽ ሙሉ እድምተኞች ሙሽሮቹን አጅቦ ሽር ብትን እያሉ ነው፡፡ ፀአዳ በህይወቷ ከዚህ በፊት እንደዚህ  አይነት  ደስታና ፈንጠዝያ  ተሰምቷት አያውቅም?ከሙሽራዋ ጀርባ ሆና በደመቀ ሁኔታ የሚካሄደውን ስነስርዓት እየተከታተለች ነው፡፡በአዲስ አለም የሰርግ ቀሚስ ላይ ያለው የተራቀቀ ዶቃ በመስታወት ላይ ሲያርፍ  በተብረቀረቀ ብርሃን አንጸባርቆ  መልሶ ወደውስጥ ሲረጭ ስትመለከት በተረት አለም ውስጥ ስላሉ ልዕልቶች  እንድታስብ አደረጋት።  የአጋቢውን ፓስተር ድምጽ ላይ ለማተኮር ሞክራለች። እሷ ራሷ የለበሰችው ቀሚስ ልዩ አይነት ስሜት እንዲሰማት አድርጓታል…በህይወቷ መቼ ቀሚስ ለብሳ እንደነበረ አታስታውስም፡፡ ምን አልባት ከቤተሰቦቾ ጠፍታ ከወጣች በኃላ ቀሚስ ጨርሱኑ ለብሳ አታውቅም ይሆናል…ሴት መሆኗ እንዲሰማት አትፈልግም…ጠንካራ ታጋይ ሆና ልጇን ማሳደግና ህይወትና ማሸነፍ ብቻ ነው እቅዷ ..ቀሚስ መልበስ ለስላሳ የሚያደርጋት ይመስላታል…በምን ምክንያት እንደዛ ልታስብ እንደቻለች አታውቅም..ግን ደግሞ ትክክል ነበረች፡፡ ይሄው ዛሬ የተለየ ስሜት እየተሰማት ነው…ሴትነቷ ጎልቶ እየበራ ነው…ይሄ ደግሟ ለሚመለከቷት ሰዎች ብቻ ሳይሆን… ለራሷም በደንብ ታውቋታል፡፡ አዲስአለም የሚካኤልን  እጅ በመያዝ አጋቢው ፓስተሩ የሚላትን ጥምረታቸውን የሚያበስሩ ውብ ቃላትን  ጥርት ባለ ድምፅ ስትደግም ይሰማል… ።

በመከራህም ሆነ በደስታ ጊዜ… ላልለይህ ቃል እገባለው፡፡
በሀዘንህም ሆነ በደስታህ …ጊዜ ከጎንህ ልሆን  ቃል እገባለው፡፡
በጤንነትህም ሆነ በህመምህ ጊዜ …ከጎንህ ላልለይ ቃል እገባልው፡፡

ቀላበቱን አውጥቶ አጠለቀላት እሷም አጠለቀችለት፡፡እርስ በርስ እንዲሳሳሙ ተደረገ….ፀደይ  በምታየው ነገር ሁሉ አንሳፋፊ አይነት  አስካሪ  ስሜት እየተሰማት ነው፡፡

እሷ ከረጅም ጊዜ በፊት ነው በደስታ ማመን ያቆመችው፣ ነገር ግን እዚህ ውብ ቦታ ላይ ሆና አዲስአለም እና ሚካኤል ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ባልና ሚስት መሆናቸውን በፓስተሩ ሲታወጅ ስትሰማ  ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ደስታ ተገፋፍታ ከጣሪያ በላይ ‹‹…እልልልልል….›› ስትል አዳራሹን አናጋችው..በዙሪያዋ ያሉ ሚዜዎችና አጃቢዎች ተቀላቀሏት…ዘፈኑና ጭፈራው ቀጠለ..፡፡
///
ዘሚካኤል አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ወንበር ከያዘ ደቂቆች አልፈውታል፡፡በአይኑ እየፈለጋት ነው፡፡‹‹በፈጣሪ ስም ወዴት ሄዳሽ ነው?››አጉረመረመ፡፡

ቢፌ የተዘረጋበትን የተንቆጠቆጠ የድግስ አዳራሽ ውብ ሆኖ ይታያል፣  የሰርጉ ድግስ አሁን በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው እና ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ እንግዶች በግዙፉ አዳራሽ ሽር ብትን እያሉ እና እየተዝናኑ ነበር።

‹‹አንድ ባልና ሚስት እንዴት በዚህ መጠን ብዙ ጓደኞች እና ወዳጆች ሊኖራቸው ቻለ?››ሲል አሰበ ፡፡ እና  ደግሞ ሁሉም  ወደ እሱ ለመቅረብ እና ከእሱ ጋር ውስን ቃላትን ለመለዋወጥም ፈልገው ሲቁነጠነጡ ታዘበ ። እሱ ግን ቀልቡም አይኑም እየተንከራተተ ያለው አንዲትን ሴት ለማየት ነው ።ድንገት ከመድረክ ላይ ከሙሽሮቹ ጀርባ ሆና ተመለከታት፡፡ ግን ወዲያው ተሰወረችበት ፡፡‹‹ዘሚካኤል አረ እራስህን ሰብስብ ››ሲል ራሱን ገሰፀ…ፊቱን ወደግድግዳ አዞረና በእጁ የያዘውን መጠጥ እየተጎነጨ ዘና ለማለት ሞከረ። ቢያንስ  እንደዛ በማድረጉ በአይኖቻቸው   ሲያሳድዱት የነበሩትን ጎረምሳ ልጃገረዶችን መገላገል ችሏል ፡፡

‹‹ወደዚህ ተንደርድሬ እንድመጣ ያደረገኝ  ምንድን ነው?››እራሱን ጠየቀ፡፡ትላንት አመሻሹ ላይ ወደ ዱባይ የመብረር እቅድ ነበረው፡፡ትኬት ሁሉ ቆርጦ ነበር፡፡ከአምስት ቀን በኃላ የሚጀመርና ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚካሄድ የሙዚቃ ድግስ አለው፡፡ከአምስት ቀን አስቀድሞ የሚጎዘው…ቀደም ብሎ ከአካባቢው ሁኔታና የአየር ጻባይ ጋር ለመለማመድና   ለዝግጅቱ ትኩረት ለመስጠት ስለፈለገ ነበር፡፡እና በፕሮግራሙ መሰረት ሻንጣውና ሸክፎ ወደቦሌ መጓዝ ጀምሮ ነበር..ግን በመንገዱ ላይ የሚያያቸውን ቢል ቦርዶች ሁሉ የልጅቷን ምስል የያዙ እየመሰሉት ሲደነግጥና ፈፅሞ ሊቆጣጠረው የማይችል ስሜት ውስጡ ሲያሸብረው..ወዲያው ስልኩን አውጥቶ ለኤጀንቱ ነበር የደወለው፡፡

‹‹ሄሎ ይቅርታ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆነ ዛሬ መብረር አልችልም››አለው፡፡

‹‹ምነው..ምን ተፈጠረ?››

‹‹እያመመኝ ነው…አሁን ቦሌ አየር ማረፊያ እየተቃረብኩ ነበር..ግን ወደቤቴ ልመለስ ነው…በረራውን ለሌላ ቀን እንዲሸጋገር አድርግ፡፡››

‹‹ለመቼ ለነገ ላድርገው….?››

‹‹ነገ እንደሚሻለኝ በምን አውቃለው…?ምናልባት ተነገ ወዲያ››

‹‹አውቀሀል …?ዝግጅቱ 5 ቀን እኮ ነው የቀረው››
‹‹ሶሪ… ስልኩን ልዘጋው ነው… ከዚህ በላይ ማውራት አልችልም››በማለት ስልኩን ዘጋውና ሹፌሩን ወደቤት እንዲመልሰው አዘዘው፡፡እያደረገ ስላለው ነገር እሱም እየገባው አይደለም…‹ይህቺ ልጅማ የሆነ አስማታዊ ጥበብ ከንፈሯ ላይ አለ፤እንዴት እንዴት እየሆንኩ ነው?››እራሱን ታዘበ….ወደቤት ተመልሶ ለሊቱን ሙሉ ሲገረምና ስለእሷው ሲያስብ አደረ..በጥዋት ተነሳና አምሮና ተሸቀርቅሮ…ልጅቷ የሰጠችውን የሰርግ ጥሪ ካርድ ካስቀመጠበት ቦታ አንስቶ ኪሱ በመክተት ማንም እንዳያገኘው ስልኩን ጠርቅሞ ዘግቶ ግዙፉን ሀመር መኪና እራሱ እያሽከረከረ ወደአዳማ መንዳት ጀመረ፡፡የሆነ ሃይል  ሙሉ ልቡን  ተቆጣጥሮ  አእምሮው የማይፈቅደውን ነገር በግድ እያሰራው እንዳለ ነው እየተሰማው ያለው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe እያደረጋጁ ቤተሰቦች  500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ምዕራፍ_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ /// ‹‹ እንዴት ናችሁ.?.የሴት ወሬ ላይ ነበራችሁ መሰለኝ….በመምጣቴ ምቾት አልተሰማችሁም››አለ፡፡ ‹‹እንዴ ባልዬው የሴት ወሬ ደግሞ ምንድነው?››ስትል አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡ ‹‹ያው ወንዷችን ማማት ነዋ››ሲል በፈገግታ መለሰላት፡፡ ‹‹አንተ እንደዚህማ አትለንም….በዚህ ፀባይህ ላላገባህ እችላለው…የደገስከው ድግስ  ብላሽ…»
#አላገባህም


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ዘሚካኤል ከሰዓታት በፊት የሰርጉን ስፍራ ለቆ መሄድ ነበረበት። ነገር ግን ከፀአዳ ተለይቶ መራመድ አልቻለም። ከሳምንት በፊት በእንጥልጥል የተወውን ጉዳይ መቋጫ ማበጀት አለበት፡፡በልቡ ጭራበት የሄደችው ሲኦል እሳት እየተንበለበለች መላ ሰውነቱ ትኩሳት እንደለቀቀችበት ነው…እንዴትም አድርጎ እንዴት  እሱን  ማስተካከል ያስፈልገዋል. ዛሬ ማታ።

ፀአዳ ለዘሚካኤል ቃል በገባችለት መሰረት ወደእሱ ለመሄድ ከውስጥ ወደአዳራሹ በተመለሰች ጊዜ በብዙ ውብና አማላይ ሴቶች ተከቦ ሲያውካካ ተመለከተችውና  ከመንገዱ  ለመራቅ ወሰነች - ባየችው ነገር ክፍት ነው ያላት…እንደዛ የማድረግ መብት የላትም ..ግን   ከማንም ለመፎካከርና እሱን ሻሞ ለመሻማት ምንም አይነት እቅድ የላትም..እና እግሯና ወደኃላ ጎተተችና  የአስተባባሪነቱን ስራዋን በትኩረት መስራቷን ጀመረች፡፡እራሷን ማሞኘት አልፈለገችም።

እሱ በእጁ ይዞ የነበረውን ባዶ ብርጭቆ በአጠገቡ በሚያልፈው አስተናጋጅ ትሪ ላይ አስቀመጠና ዓይኑን ወደ ህዝቡ መሀከል አንከራተተ። የሙሽሮቹ ዋና ተጠሪ እንደመሆኗ   መጠን መጥፋት አልቻለችም። ግን   እሱን ከእይታዋ ለማስወገድ እየሞከረች እንደሆነ ያስታውቅባታል፡፡‹‹እንደዛ እንድታደርጊማ አልፈቅድልሽም››ሲል ፎከረ፡፡ይሄ በእሱ ልምድ  አዲስ ተሞክሮ ነበር።አንድ በሆነ አጋጣሚ ከንፈሩን የቀመሰች ሴት መልሳ ልታገኘው መከራዋን ስታይና ስትንሰፈሰፍ ነበር የሚያውቀው፣ከከበቡት ልጃገረዶች በዘዴ ተለየና  እሷን ለማግኘት መጣር ጀመረ፡፡

ፀደይ ግራ በመጋባት ያለአላማ ከወዲህ ወዲያ ስትሽከረከር . ድንገት አይን አዲስ ወደእሷ ጠራቻት‹‹እ ምን ፈለግሽ?››

‹‹እኔ ምንም አልፈለኩም… ለምን ከእሱ ትደበቂያለሽ ?››

‹‹ አልተደበቅኩም›› አለች ፀአዳ፡፡

‹‹እሺ እንደዚያ ከሆነ፣ ለምንድነው ከእሱ ጎን ሆነሽ አንድ ብርጭቆ ሻምፓኝ የማትጎነጪው?ምንድነው የሚያስፈራሽ?››

‹‹እንደምታይው እሱ ብቸኛ ሰው አይደለም….ሁሉም ሰው የእሱን እዚህ ሰርግ ላይ ስለመገኘት ነው  የሚያወራው -..እና ወደሰርግ አዳራሹ ከገባበት ደቂቃ አንስቶ በሰው በተለይ በሴቶች እንደተከበበ ነው››

‹‹እና ውድድሩን አላሸንፍም ብለሽ ሰጋሽ …?አዎ  ከባድ ውድድር እንዳለብሽ እኔም ገምታለው።ግን እኮ ይሄንን ለመሰለ ጠንበልል አማቼ… መፋለም መቻል በራሱ እድል ነው?››

‹‹አረ በካሽ…እኔ ፀደይ ነኝ፡፡ ወንድ ለማግኘት ከሌላ ሴት ጋር የምናጠቀው። እንደው እንዳልሺው ፊልሚያ ውስጥ ልግባ ብልስ እሱ ፍላጎት ከሌለው የሚሆን ይመስልሻል…?እናስ ከእነዛ ከከተመዋ አማላይና ስብር ቅንጥስ ከሚሉ ወዳጆችሽ ጎልቼ በአይኑ የምገባ ይመስልሻል...›› በብስጭት ተንዘረዘረች፡፡

‹‹ገባሽ እኮ ..ቀድመሽ በከንፈሩ ገባሽ….ይልቅ አትንቀርፋፊ..በሰርጌ ቀን ካንቺ ጋር ከዚህ በላይ መዳረቅ አልችልም..ባሌ አየጠራኝ ነው፡፡ቻው››ብላት በቆመችበት ጥላት ሄደች፡፡

ፀደይ ለተወሰነ ደቂቃ ድንዘዝዝ አለች‹‹…ምን ላድርግ?››እራሷን ጠየቀች..፡፡ምንም ያህል ችላ ልትለውና ልትርቀው ብትሞክርም ልቧ ግን ልክ እንደማግኔት ወደእሱ እየጎተታት ነው…ወደአለበት  ሄዳ ከሰውዬው ጋር ለመነጋገር ድፍረት አልነበራትም።ፊቷን አዙራም ከእሱ ርቃ ለመሰወር ብትጥርም ከዚህ የበለጠ ተጫማሪ ሳዕታትን ከእሱ ተደብቃ መቆየት እንደማትችል ልቧ ያውቃል፡፡ድንገት ስታየው ብቻውን ሆኖ ስላየችው  ወደኋላ ተመለሰችና ቅዱስን ከሞግዚቷ ተቀብላ በማቀፍ እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ወደእሱ ሄደች፡፡

‹‹እንዴት ነሽ…?መምጣትሽን በናፍቆት ስጠብቅ ነበር››ከአንደበቷ የሚወጡት ቃላት ልቧን በቀላሉ ማቅለጥ አቅም ነበራቸው፡፡

‹‹አልደበረህም አይደል?››

‹‹በመጠኑ…ግን በጣም የሚፈልጉትን ነገር ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥም ሆነው መጠበቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው….እና አልከፋኝም››አላት፡፡

ዝም አለች…ምን እንደምትል ግራ ተገባች‹‹ከወንድምህ ልጅ ከቅዱስ ጋር ላስተዋውቅህ።››አለችው

ዘሚካኤል  በተራው በዝምታ ተዋጠና  ህፃኑን በትኩረት ማየቱን ቀጠለ። የሆነ የማያውቀው መከፋት ስሜት ውስጡን ሲያተረማምሰው ተሰማው፡፡ህፃኑን እቅፉ የተንጠለጠሉትን ውብ ጉንጮቹን እያገላበጠ ቢሰመው ደስ ይለው ነበር፤አዎ እንደዛ አይነት ፍላጎት ነበር የተሰማው፡፡ግን ከተቀመጠበት መነቃነቅ ሆነ እጆቹን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡እንዲህ መሆን የለበትም ነበር፡፡እሱ በቤተሰቡ ላይ ያን አይነት መአት ከመድረሱ በፊት በጣም ሰው ወዳጅ በተለይ ዘመድ ለተባለ ሰው ልቡ ትርክክ የሚል በፍቅር የሞላ ልጅ ነበር፡፡ከክስተቱ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ነው የሆነው፡፡ከዘመድ ጋር መነካካት መርዝ እንደመጎንጨት የሚያንገፈግፈው ነገር ሆኖል…ቢሆንም እንዲህ በጮርቃ ህፃን ላይ እንኳን የተለየ አቋም ሊኖረው አይገባም  ነበር፡፡

‹‹አይዞህ አትጨናነቅ..በሂደት ጥሩ አጎቱ ትሆናለህ››አለችው፡፡

‹‹ልጁን በተመለከተ እንደጨነቀኝ እንዴት አወቀች?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡

‹‹አሁንም ብቻህን ጥዬህ ልሄድ ነው..ግን አልቆይም..ህፃኑን ለእናቱ አስረክቤ መጣሁ…››

በረጅሙ ተነፈሰ‹‹አዎ እንደዛ ይሻላል..አታስቢ ስለአንቺ እያሰብኩ ጠብቅሻለሁ፡፡››አላት፡፡

ፈገግ አለችለትና ህፃኑን ቅዱስን አቅፋ ተነስታ ሄደች፡፡ከኃላ አይኑን ተክሎ ተመለከታት..አቋሞ ልዩ ነው፡፡ተረከዘ ሎሚ የምትባል አይነት ነች..እንዲህ አይነት እግር ያላት ሴት ከድሮውም በጣም ነው የምትማርከው…ደግሞ ከሁሉም በላይ እሱ ጋር ከሚመላለሱት ሴቶች ተቃራኒ በሆነ መልኩ ምንም አይነት መዋቢያና መኳኳያ አትጠቀምም…ለምን እንደሆነ ሊገባው አልቻለም…ብትጠቀም እኮ የበለጠ ውብ ትሆን ነበር?››ሲል አሰበ፡፡‹‹ግን አንኳንም አልተጠቀመች››ሲል ደመደመ፡፡

ልጁን ለሞግዚቷ አስረክባ ብቻዋን  ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ የወንድሙን ሚስት አስከትላ መጣች፡፡

አዲስአለም ‹‹ዘሚካኤል… በመምጣትህ በጣም ደስ ብሎናል … ዛሬ ማታ ቤታችን በተዘጋጀው የእራት ግብዣ  ላይ ብትገኝ እንዴት ደስ ይለናል መሰለህ …ግን ምቾት የማይሰማህ  ከሆነ እንረዳሀለን….እዚህ ስለመጣህ እራሱ በእውነት በጣም ደስተኛ አድርገሀናል….ሰርጋችንም የማይረሳና የታደመው ሰው ሁሉ መቼም የሚያስታወስው እንዲሆን አድርገሀል ።››

ዘሚካኤል ደቂቃ ወስዶ እንደማሰብ ሲያደርግ ፀአዳ ጣልቃ ገብታ‹‹እባክህ እሺ ብለህ ቆይ…አይዞህ እንደአሁኑ  ጣል ጣል አናደርግህም…ቃል እገባልሀለው››አለችው፡፡

ንግግሯን ስታጠናቅቅ አዲስአለምም ሆነች ዘሚካኤል አፍጥጠው እየተመለከቷት ነበር…‹‹ምንድነው የሚያስቀበጥረኝ ?››ስትል በውስጧ እራሷን ወቀሰች፡፡

ዘሚካኤል መናገር ጀመረ‹‹እሺ እቆያለው››ሲል ተናገረ፡፡

አዲስአለም ፊት በደስታ በራ‹‹አመሰግናለው..በቃ አሁን ጥያችሁ ልሂድ …አብረሽው ቆይና ይዘሽውን ነይ››አለችና ተመልሳ ሄደች፡፡

ፀአዳ ከእፍረቷ ሳትላቀቅ በዝግታ ተቀመጠችና፡፡‹‹እሺ ትላለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››አለችው፡፡

‹‹እውነቱን ለመናገር እኔም እሺ እላለው የሚል ግምት አልነበረኝም….ቃልሽን አምኜ ነው እሺ ያልኩት››አላት፡፡

‹‹ማለት የምን ቃል?››

‹‹እንደእስካሁኑ  ብቻህን በመተው እንድትደበር አላደርግህም…ከመጀመሪያው እስከፍጻሜው ከጎንህ አልለይም…›ብለሽ  የገባሽልኝን ቃል ነዋ››

‹‹አንተ ይሄን ሁሉ መቼ ነው የተናገርኩት.››

‹‹.አሁን ከደቂቃዎች በፊት››

‹‹ይሁን..ለማንኛውም ማትቆጭበት ውሳኔ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው››
‹‹እኔም…አሁን ዝግጅቱ አልተጠናቀቀም እንዴ?..ይሄን ቦታ መልቀቅ ፈልጋለው፡››

‹‹ተጠናቋል …ከ10 ደቂቃ በኋላ እንወጣለን››

‹‹ጥሩ….አንቺ ከፊት ለፊቴ አስካለሽ ከ10 ሰዓትም በሃላ ቢሆን ግድ የለኝም፡፡››

ሳታስበው ‹‹እንደወንድምህ አይደለህም…››አለችው፡፡

‹‹ማለት?››

‹‹እሱ አንደበተ ቁጥብ ነው..በምንም አይነት መንገድ ሰውን በውሸት አይሸንግልም››አለችው፡፡

‹‹በውሸት…ለምን እዚህ የመጣው ይመስልሻል?››

‹‹ይሄ ምን ጥያቄ አለው..የወንድምህ ሰርግ ላይ ለመገኘት ነዋ፡፡››

‹‹ተይ እንጂ….በዛ ውድቅት ለሊት በከንፈርሽ ካደነዘዝሺኝ በኋላ ካንቺ ውጭ ስለሌላ ነገር ማስብ አልቻልኩም..ትናንት ማታ ወደዱባይ መብረር ነበረብኝ ..ትኬት ቆርጬ ወደኤርፖርት ሁሉ መሄድ ጀመሬ ነበር..ከዛ ነው ሀሳቤን ቀይሬ  የመጣሁት…ለምን?፡፡››

‹‹በል አሁን  ሰው እየተንቀሳቀሰ ነው ተነስ እንሂድ አለችው…..››እንዳለችው የሆቴሉ ዝግጅት አልቆ ሙሽሮቹን ተከትሎ ሰው ሁሉ እየወጣ ነው፡፡ግን የጀመረውን ንግግርም ልታቋርጠው ስለፈለገች  ነው አጋጣሚውን ተጠቀመችበት፡፡መቀመጫውን ለቆ ተነሳና ክንዷን ጨብጦ ወደመውጫው መጓዝ ጀመረ….በትክክልም መራመድ አቃታት፡፡ከአዳራሹ ውጭ ወጥተው ወደሀመር መኪናው ሲያመሩ ጎዳናው ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በገረሜታና በመደነቅ ሲያቸው ነበር..አንዳንዱም እጆቻቸውን በደስታ እያውለበለቡ ሰላም ይሉት ነበር፡፡የዘሚካኤል ባለግርማ ሞገስ  ሀመር  መኪና ከሌሎች መኪኖች መሀከል ሆኖ  ጎልቶ ይታያል።፡፡የሙሽሮችን ሊሞዚን ተከትሎ ከኃላ እያሽከረከረ ነው፡፡እሷ ከጎኑ ገቢና ሆና  ባልተረጋጋ ስሜት አንዴ የሰርጉን ድባብ ወዲያው ደግሞ በቀጣይ ከእሱ ጋር ስለሚሆነው ነገር ታሰላለስላለች፡፡

እሱ የዚህን ያህል በጣም ታዋቂ እንደሆነ አታውቅም ነበር! እሷ እምብዛም ሙዚቃ አድማጭና ፊልም ተከታታይ አይደለችም፡፡ ስለእሱ ያወቀችው የሚካኤል ወንድም በመሆኑ ነው ..ስለእሱ የተወሰነ መረጃም መሰብሰብ የጀመረችው በዛ ጉዳይ ነው፡፡አሁን ግን እዚህ ሰርግ ላይ ከተገኘ በኋላ እያንዳንዱ ሰው ከህጻናት እስከ አዛውንቶች እሱን ለማየት ሲንጠራሩና ሰላም ለማለት ሲራኮቱበት ስታይ በጣም ነው የተገረመችው፡፡እና ደግሞ በጣምም ነው ያስፈራት፡፡
ቀኝ እጁን ዘርግቶ ትከሻዋን እየነካካ‹‹ቀኑን ሙሉ አልበላሁም እና  ርቦብኛል››አለ በረጋ መንፈስ።

‹‹እንዴ ምሳ ግብዣ ኮ ብፌ ነበረ››

‹‹ባክሽ የእኔ ቀልብ አንቺ  ማግኘት ላይ ስለነበረ ...በወቅቱ ትዝ አላለኝም..አሁን አንቺን ሳገኝሽ ነው እንደራበኝ ያወቅኩት ››አላት፡፡ ..

ምላሽ ስትሰጠው የድምጻን መንቀጥቀጥ  መቆጣጠር አልቻለችም። የአዲስአለምና የሚካኤል መኖሪያ ቤት ለራት ድግስ የተዘጋጀውን ቢፌ  ብቻ ሊውጥ ያሰበ አይመስልም …አይነ ውሀውን ስታስተውል ረሀቡ የምግብ ብቻ አይመስልም…፡፡  ለምን እንደዛ እንደተሰማት  አታውቅም?

እስከምሽቱ  ሁለት ሰዓት ድረስ እነ አዲስአለም ቤት የራት ግብዠው ላይ አብረው አሳለፉ…በጣም አስደሳችና ዘና ያለ ምሽት ነው ያሳለፉት ከዛ ሙሽሮቹን በስነስርዓት ተሰናበተና ፀአዳ ሆቴል ድረስ ትሸኘኝ በማለት ይዞት ወጣ..እሷም ያለምንም ማንገራገር ነበር ተከትላው ወጥታ መኪናው ውስጥ የገባችው፡፡ቀጥታ ቀደም ብሎ ወደያዘው ሀይሌ ሪዞርት ነዳው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ክፍያችን እሱ ብቻ ነው  500 subscribers Please 🙏

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose