አትሮኖስ
269K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
435 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_19


"እሺ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ፤ ከተከሳሽ ጋር በጓደኝነት ባሳለፋችሁት ግዜ ውስጥ እንደተገነዘቡት ምን ዓይነት ጠባይ ነበረው። “አማረ ትሁት፣ ከአፉ ክፉ ቃል የማይወጣ፤ ተግባቢና ተወዳጅ ልጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አልማዝን በጣም ስለሚወዳት በእሷ ሲመጡበት ብቻ ነው ሲናደድ ያየሁት" በማለት መለሰች፡፡ "አመሰግናለሁ" ብሎ ጠበቃዬ ተቀመጠ። አቃቤ ሕግ በተራው ተነስቶ መስቀለኛ ጥያቄ እየጠየቀ እኔን ወንጀለኛ የሚያደርግ ቃላት ከአንደበቷ ጎትቶ ለማውጣት መታገል ጀመረ:: *ወ/ት ኤልሳቤጥ፤ ቀደም ሲል እንደተናገሩት ከሆነ ሟችና ተከሳሽ በምን እንደተለያዩ አላወቁም፡፡ ተክላሽ ከማች ጋር አልፎ አልፎ ግቢ ውስጥ ይጣሉ እንደነበር ይወራል፣ ይህ በምን ምክንያት ነው"፡፡ “አልፎ አልፎ ሟችን ዶ/ር አድማሱ የተባለ መምህሯ ያስጠናት ስለነበር በብዛት ወደሱ ቤት እየሄደች ታጠና ነበር:: በዚህም የተነሳ እሱም ይህንን ስላልወደደው እሱ ጋ መሄዷን እንድታቆም ይጨቀጭቃት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህም ሆኖ ትምህርት ቤት እያሉ በዚህ ምክንያት ተጣልተው አልተለያዩም"፡፡ *ጥሩ! ምክንያቱ ይህ ካልሆነ፣ ተከሳሽ ከትምህርት ቤት ከተባረረ በኋላ ከእሷ ጋር የተለያየበት ምክንያት ምንድነው?"፡፡ "እኔ አላውቅም"፡፡ “ቅድም እንደነገሩን ተከሳሻ በቅናት የሚጣላ ከሆነ በቂም በቀል ተነሳስቶ ለመግደል የሚስችለው ምክንያት አለ ብለው አያምኑም?" ብሎ ሲጠይቅ፤ ጠበቃዬ ተነስቶ ተቃውሞ አለኝ አለ፡፡ ዳኛው ተቀውሞውን እንዲያሰማ ዕድል ሰጡት፤ “ክቡር ፍ/ቤት፤ ተጨባጭ መረጃ በሌለበት ሁኔታ ምስክሯ በግምት ይህንን ጥያቄ ልትመልሰው መገደድ ስለሌለባት ጥያቄው ውድቅ ቢሆን' አለ፡፡ ዳኛው ተቃውሞውን ተቀብለው ሌላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ አዘዙ፡፡ አቃቤ ሕግም ለዚህ ብዙም ሳይጨነቅ! *ቀደም ሲል እንደተናገሩት ተከሳሽ ትሁት ቢሆንም በአልማዝ ላይ ከመጡበት እንደሚበሳጭ ተናግረዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ አብራችሁ በነበራችሁበት ወቅት ተከሳሽ ከአንድ ተማሪ ጋር ተጣልተው ነበር ይባላል፣ ምክንያቱ ምን ነበር?''

“አዎ! አንድ ጊዜ ብቻ መጣላቱን አስታውሳለሁ፡፡ እሱም አንድ ተሾመ የሚባል ተማሪ ሟችን አፈቀርኩሽ እያለ በግድ ከእሱ ጋር እንድትሆን ያስቸግራት ነበር፡፡ እሷ ግን ፍቃደኛ አለመሆኗን ስለነገረችውና በዚሁ የተነሳ ስለመታት፣ አማረ ተናዶ ከእሱ ጋር መደባደቡ ትዝ ይለኛል" አለች፡፡ አቃቤ ሕግ ይህንን ሲሰማ ጨርሻለሁ በማለት እየተኩራራ ወደ መቀመጫው አመራ፡፡ ከኤልሳቤጥ ምስክርነት ጠበቃዬ ምን ጠቃሚ ነገር እንዳገኘ ለማወቅ ቢያዳግተኝም እኔ ግን የመሰከረችብኝ እንጂ የመሰከረችልኝ መስሉ አልተሰማኝም፡፡ የእሷን የምስክርነት ቃል ከጠበቃዬ ይልቅ አቃቢ ህግ “አልማዝን ላለማጣት የተደባደበ ሰው፣ በፍቅሩ ከመጡበት ሰው ለመግደል አይመለስም" የሚለውን ለማሳየት ተጠቅሞበታል፡፡ ይህንንም ጥያቄ እንዲያነሳ ፍንጭ የሰጠችው እሷ ነች፡፡ የእሷ ምስክርነት አልማዝ ከተሾመ ጋር ተያይዞ በኤልሳ ላይ የነበራትን የቀድሞ ጥርጣሬ እኔ ላይ አስፍኖ በማለፉ የተስፋ መቁረጥና የፍርሀት ስሜት ወረረኝ። ሌላዋ ምስክሬ አለሚቱ ስትሆን እሷም ብትሆን ጥሩ ጠባይ እንዳለኝና አንድ ቀንም ከሰው ጋር ተጣልቼ እንደማላውቅ ከመመስከር ውጪ ምንም የፈየደችው ነገር አልነበረም፡፡ ቢያንስ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቀን ቤት ውስጥ እንደነበርኩ ትመሰክራለች ብዬ ብጠብቅም፤ የዛን ቀን የት እንደዋልኩ እንደማታስታውስ በመናገሯ ለእኔ ምንም የጠቀመኝ ነገር አልነበረም፡፡ ለነገሩ እኔ በወቅቱ ተናደድኩባት እንጂ እንኳን እሷ እኔ ራሴም ብሆን የዛን ቀን የት እንደነበርኩ አላስታውስም፡፡ በመጨረሻም ዳኛው ለመስከረም 15/1981 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተውን ወጣን፡፡ ከፍርድ ቤት ወጥቼ ወህኒ ቤት እንደገባሁ ዙሪያ ገባውን እየቃኘሁ ብዙ ሳሰላስል ከቆየሁ በኋላ በእርግጠኝነት ይህ "ቤቴ" ከደጁ መሻአሉን አረጋገጥኩ፡፡ ቢያንስ እዚህ ያለነው አስተሳሰባችን አንድ ነው:: የምናስበው ስለ ዛሬ ነው እንጂ አንዳችንም ነገ ስለሚሆነው ነገር አንጨነቅም፡፡ ሁላችንም የምንኖረው ለዛሬ ነው:: ለእኛ ህይወት ዛሬ ነች፤ ነገ ግን የሌሎች ናት:: ለዛሬ ስንል ነው ነጥቀን የምንበላው፣ የዛሬ ሆዳችንን ለመሙላት ስንል ነው ሕይወት የምንቀጥፈው፣ ለዛሬዋ የቅጽበት ደስታ ስንል ነው ሴት ደፍረን የምንታሰረው:: አርቆ የሚያስብ ሰውማ እንዴት ወንጀለኛ ሊሆን ይችላል:: ታዲያ እኔም እዚህ በሰላም ያለጭንቀት ለዛሬ ብቻ እኖርና ወደ ውጪ በወጣሁ ቁጥር ግን ዛሬ ማን ይመሰክርብኝ ይሆን? ምን ብሎ ይመሰክርብኝ ይሆን? ይፈረድብኝ ይሆን? በማለት ስለነገ ሕይወቴ መጨነቅ እጀምራለሁ፡፡ አዎ! ይህንን ሳስብ አልማዝ ዲያሪ ላይ ያነበብኩት የሱማሌውና የጤፉ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡

"ያባው! አሊያ አንተ አላህ ሆንክ ወይስ ከአላህ ጋር ተማክረሀል? እንዴት አንድ ዓመት ሙሉ በሕይወት እንደምትኖር እርግጠኛ ሆንክ?" ያለው ያኔ ለኔ ባይታየኝም ትክክለኛ ጥያቄ ነበር። ለካስ እነሱ ሁልጊዜ ለዛሬ ብቻ የሚመገቡትን የሚገዙትና ስለነገ ሲያወሯቸው “ኢንሻ አላህ" የሚሉት፣ ሁል ጊዜ የዛሬን ብቻ ስለሚኖሩ ነበር! የፍርድ ቤቱ ውሎ እንደጠበቅሁት ስላልሆነልኝ እስር ቤት ከገባሁ በኋላ ለጓደኞቼ "ውሎ እንዴት ነበር?" ጥያቄ መልስ ሳልሰጥ ቆዝሜ ተቀመጥኩ፡፡ ጓደኞቼ ማፅናናቱ ሲሰለቻቸው በተለያየ መንገድ ሊያስቁኝ ሞከሩ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ቀልዶች እኔን የሚያስቁ አልነበሩም፡፡ ይልቁንም ቀልዱን ትተው ቁምነገር ማውራት ሲጀምሩ ሳልወድ በግድ ሳቅሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ለዶክትሬት ዲግሪ ጥቁር አንበሳ ይማር የነበረ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ በአንድ ትምህርት ኤፍ (F) የሰጠውን አስተማሪ ውጤቱን እንዲያስተካክልለት እያለቀሰ ቢለምነውም ከመራራት ፋንታ በቀልድ መልክ፤ "አይዞህ አትጨነቅ ወጣት ነህ፣ ገና በመጀመሪያው ዓመት እንዲህ የተልከሰከሰ ነጥብ ይዘህ ቀሪ አምስት ዓመታትን በጭንቀትና በለቅሶ ከማሳለፍ እንደገና ማትሪክ ተፈትነህ ዕድልህን ብትሞክር ይሻሻል" ሲለው በንዴት ራሱን መቆጣጠር ተስኖት በቡጢ ፊቱ ላይ መትቶት ጥርሱን ይሰብረውና እስር ቤት ይገባል፡፡ ይህ እስረኛ እስር ቤት ውስጥ የሚጠራው በስሙ ሳይሆን ዶክተር እየተባለ ነው፡፡ ለአብዛኛው በተለይ ፊደል ላልቆጠረው እስረኛ ዶክተር ማለት ደግሞ የማያውቀው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ታዲያ የዛን ቀን አንዱ እስረኛ የተለያዩ የማያውቃቸውን ጥያቄዎች ይጠይቀው ነበር፡፡ ጠያቂው እስረኛ ቅማል አማሮት ኖሮ ከልብሱ ላይ ቅማል እየገደለ፤ “ስማ እንጂ ዶክተር፤ እነዚህ ቅማሎች እንዴት ነው የሚራቡት? እኔ በየቀኑ እገላቸዋለሁ፣ እነሱ ግን የበለጠ ቁጥራቸው እየበዛ ይፈለፈላሉ፡፡ ለመሆኑ እናትየው በየደቂቃው እያረገዘች መንታ መንታውን ነው እንዴ የምትወልደው?'ይለዋል፡፡ ዶክተሩ ለጥቂት ደቂቃዎች ተንከትክቶ ይስቅና ሲቃ እንደያዘው፤ "ስማ እንጂ፤ ለመሆኑ ማነው ቅማል ታረግዛለች ያለህ? ቅማል አታረግዝም፡፡ እንቁላል እየጣለች ነው የምትራባው" ይለዋል፡፡ _ እስረኛው ስለተሳቀበት ሀፍረት እየታየበት፤ "ውይ! ተወው ረስቼው ነው፡፡ ቅጫም ለካስ የቅማል እንቁላል ነው" ይለዋል፡፡ ሌላኛው እስረኛ ቀበል አድርጎ፤