🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_20
ዳኛው የሚሰጡትን ውሳኔ ለመስማት ሁሉም ድምጹን አጥፍቶ እያዳመጠ ስለነበር ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ ውሀ እንኳን ጠብ ቢል መሰማቱ አይቀርም ነበር፡፡ ዳኛው የክርክሩ ጠቅላላ ሂደት እንዴት እንደነበር ካብራሩ በኋላ ይህ ሁሉ ታዛቢ ሰው በጉጉት የሚጠብቀውን የፍርድ ውሳኔ ማሰማት ጀመሩ፤ “አቶ አማረ አስረስ መጋቢት 15 ቀን 1980 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አዲስ አበባ፣ ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ደብረወርቅ ሆቴል ውስጥ፣ ሰውን ለመግደል አስበውና አቅደው፣ ሟች ወይዘሪት አልማዝ አስፋውን ከእኔ ሌላ ሰው አፍቅረሻል በሚል ምክንያት በቅናት መንፈስ ተገፋፍተው ፍቅረኛቸውን የለምንም ርህራሄ ራሷን እንደገደለች የሚያስመስል ደብዳቤ እንድትፅፍ ካደረጉ በኋላ ገድለው ሰቅለዋታል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ግለሰቡ ይህንን ሁሉ ወንጀል የፈፀሙ ሆነው ሳለ ወንጀሉን አምነው ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ በወንጀላቸው ሳይፀፀቱ ከወንጀሉ ነፃ ነኝ በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሹ ወንጀሉን በቅናት መንፈስ ተነሳስተው መፈፀማቸው በምስክሮችና በማስረጃ ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ተከሳሹ አቶ አማረ አስረስ ጥፋተኛ ናቸው በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡''
ዳኛው የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ አቃቤ ሕግ በተሰጠው የጥፋተኛነት ውሳኔ ላይ የቅጣት አስተያየት ካለው እንዲሰጥ ጋበዙ፡፡ አቃቤ ሕግም የተሰጠውን ዕድል በመጠቀም ምን ያህል ጭካኔ በተሞላው መንገድ ሆን ብዬና ተዘጋጅቼ ግድያውን እንደፈፀምኩ በማብራራት የመጨረሻው ከባድ ቅጣት እንዲበየንብኝ ዳኛውን በሕግ ቃላት ለማሳመን ጥረቱና ትንቅንቁን አጠናከረ፡፡ በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ዕድል የተሰጠው ተረቺው ጠበቃዬ፤ "እኔን ነፃ ለማውጣት ሲከራከር እንዳልነበር ሁሉ አሁን ግን መረታቱን ተቀብሎ፤ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ወንጀል ሰርቼ እንደማላውቅ በተደጋጋሚ በመጥቀስ የቅጣቱ መጠን እንዲቀልልኝ ተማፀነ፡፡ ዳኛው የቅጣት ማክበጂያና ማቅለያ አስተያቶችን ከሰሙ በኋላ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 19/1982 ዓ.ም ቀን እንድንቀርብ በማዘዝ አሰናበቱን፡፡ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ብዬ ሳስብ እዚሁ ላይ ተጠናቀቀ። ከዚህ በፊት ከስሼም ሆነ ተከስሼ ፍርድ ቤት ቀርቤ ስለማላወቅ የችሎቱ ሂደት የተጠናቀቀበት ሁኔታ ባይገባኝም በአቃቤ ሕግና በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ የማየው የደስታ ሳቅና፣ በኤልሳና በጠበቃዬ ፊት ላይ ያየሁት የመከፋት ስሜት በእርግጠኝነት በእኔ ላይ እንደተፈረደ አመላክቶኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርዱ የሞት ፍርድ፤ ዕድሜ ይፍታህ፤ ወይም የተወሰነ እስር ዘመን መሆኑን ለይቼ ለመረዳትም ይሁን ለመገመት አለመቻሌ ግራ አጋብቶኛል፡፡ እስር ቤት ተመልሼ እንደገባሁ ግን የጥፋተኝነት ውሳኔ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሌላ ቀጣይ የፍርድ ሂደት እንዳለ መረዳት ቻልኩ፡፡ እንደእኔ ከሆነ ግን ጥፋተኛ መሆኔ ከታመነበት ጊዜ ሳይፈጁ ፈርደውብኝ ቁርጤን ቢነገግሩኝ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ነገር ግን እንደሚመስለኝ እንዲህ የፍርድ ሂደቱን በማጓተት እስረኛው ምን ይፈረድብኝ ይሆን? ይገድሉኝ ይሆን? ዕድሜ ልክ ይወሰንብኝ ይሆን? ሃያ ዓመት ያስሩኝ ይሆን? ወዘተ.. እያለ ቀን መጨነቁ፣ ሌሊት እንቅልፍ ማጣቱ ከፍርድ በፊት የሚቀጣው ቅጣት ተደርጎ ሳይወሰድ አይቀርም፡፡ የፍርድ ውሳኔ የሚስጥበት ቀን ደርሶ ፍርድ ቤት ቀረብኩ፡፡ ሐሰት በእውነት ላይ የበላይነት አግኝታና የተተበተበው ሴራ ሳይፈታ፣ እጄ ከተያዘበት ዕለት አንስቶ የሃያ ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደብኝ፡፡ ውሳኔውን ስሰማ ጉልበቴ አካላቴን መሸከም እስከሚያቅተው ድረስ መብረክረክ ጀመረ። ንዴትና ፍርሀትም ሰውነቴ ውስጥ ተቀላቅለው በፈጠሩት ትኩሳት የተነሳ መላ ሰውነቴ በላብ ተዘፈቀ፡፡
እንግዲህ እነሆ ያቺ ስጠብቃት የነበረች ውድ ቀን ደርሳ የጠበቅኋት ውሳኔ ባልጠበቅሁት ሁኔታ ተፈረደች:: እኔም ባልሰራሁት ወንጀል ተፈርዶብኝ የታስርኩበት አራት ዓመት ሲቀነስ ለቀጣይ አስራ ስድስት ዓመታት ልታሰር ተወስኖብኛል። እርግጥ ለእኔ ብዙም ለውጥ የለውም። ከአልማዝ ተለይቼ ያሳለፍኳቸው ዓመታት በሙሉ በብረት አጥር ውስጥ ተከልዬ በፖሊስ እየተጠበቅሁና በአንድ ቦታ ተወስኜ አለመኖሬ ካልሆነ በስተቀር ከእሥር የተለዩ ስላልነበሩ ውጪው ዓለም እስከዚህም የሚያጓጓኝና አጥብቄ የምሻው አልነበረም፡፡ ድሮስ ቢሆን ነፃ በመሆኔና እንደልብ በመንቀሳቀሴ መች ተደስቼ አውቃለሁ? ይልቁንም የተሻለ ደስታን ያገኘሁት እሥር ቤት ውስጥ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ውስጤ ይህንን ይቀበለው እንጂ በዓይኔ የማየው ነገር ህሊናዬን እየተፈታተነ ያበሳጨኝ ጀመር። በፖሊስ ታጅቤ ከችሎቱ በመውጣት ላይ ሳለሁ ድንገት ዓይኔን ወደ ኋላ ወርወር አደረግሁ፡፡ ዶ/ር አድማሱ በደስታ እየተፍለቀለቀ አብረውት ከመጡት ጋር ብቻ ሳይሆን አጠገቡ ከቆሙትና ከማያውቃቸው ሰዎችም ጋር እየተቃቀፈ ይሳሳማል፡፡ በእሱ እምነት የፍቅረኛው ገዳይ በሠራው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት አግኝቷልና ለምን አይደሰት? ለምንስ አይቦርቅ? ወደ እስር ቤት እንደተመለስኩ እስረኛው ሁሉ የተፈረደብኝን እንደሰማ ክፉኛ አዘነ፡፡ ቀደም ሲል በሌሎች ላይ የሞት ፍርድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፍርድ ሲሰጥ እምብዛም የሚያዝን ሰው አልነበረምና ለእኔ ማዘናቸው ገረመኝ:: በተቃራኒው እኔ ከዚህ በፊት የማዝነው እስረኛ ሲፈረድበት ሣይሆን ሲፈታ ነበር፡፡ አለሙና የእሥር ቤቱ ካቦ ሲፈቱ አዝኛለሁ፡፡ ከቤተሰቦቻችን አንድ ሰው ጥሎኝ ወደ ውጪ ሀገር ለዘላለሙ ላይመለስ እንደሄደ ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ከተፈረደብኝ ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ጠበቃዬ አስጠራኝ:: በተፈረደብኝ ፍርድ ተስፋ እንዳልቆርጥ፣ ይግባኝ እንደሚልና እኔን ለማስፈታት የተቻለውን ያህል እንደሚሞክር ቃል ገባልኝ:: ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሳየው ግን ደስ አለኝ፡፡ ምናልባት ሃያ ዓመት እንደተፈረደብኝ ሳውቅ መብረክረኬ አሊያም ጠበቃዬ የሚፈልገውን በማግኘቱ ዳግመኛ አይመጣም ብዬ ገምቼ ስለነበር፣ መምጣቱን እንዳየሁ እውነትም ከልቡ እየተከራከረልኝ ነው ብዬ አስቤ ሊሆን ይችላል፡፡ እርግጥ ፈርቼም ሊሆን ይችላል፡፡ ትንሽ ቆይቼ ይፈቱኛል እንጂ እንዲህ ባልሰራሁት ወንጀል ሀያ ዓመት ይፈረድብኛል ብዬ አስቤ ስላልነበር ውሳኔውን ስሰማ ብፈራ አሊያም ብደናገር የሚደንቅ አልነበረም:: ከዚህ በላይ ደግሞ የመጨረሻው ፍርድ
ሲፈረደብኝ በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ ያየሁትን የደስታ ስሜትና ፈገግታ ላስታውስ መኖርን ፈለግሁ፣ መፈታትንም ተመኘሁ። እስር ቤት ውስጥ እኔና ጠበቃዬ ብቻ በአንዲት ክፍል ውስጥ ፊት ለፊት ተቀምጠን ያንን ሊፈታው ያልቻለውን እንቆቅልሽ መፍታት ላይ እንድረዳው በማሰብ ወደ ኋላ እየተመለሰ ታሪኮቹን በመተረክና በየጣልቃው በዚያው ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል የማውቀው ነገር ካለ ይጠይቀኝ ጀመር። ይህም ቢያንስ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ነገር ካለ እንዳስታውስ በማሰብ መሆኑ ስለገባኝ በጥንቃቄ እያዳመጥኩ መልስ እሰጠው ነበር።ከምስጠው መልስ ውስጥ የሚጠቅመውን አግኝቶ ይሁን ወይም ለእኔ ትኩረት መስጠቱን ለማሳየት እንደሆነ ባይገባኝም እየመረጠ ከጻፈ በኋላ፤ “አቶ አማረ፤ እንግዲህ ከዚህ በፊትም እንደነገርኩህ የአንድ በሽታ የመጀመሪያው ሀኪም ራሱ በሽተኛው ነው፡፡ መድሀኒቱን ባያውቅ እንኳን የቱ ጋ እንደሚያመው ከሀኪሙ በፊት አስቀድሞ የሚናገረው እሱ ነው:: ከዚያ በኋላ ነው ሀኪሙ እዛ ቦታ ላይ ምርመራውን የሚጀምረውና መድሀኒቱንም የሚያዘው:: ስለዚህ አንተም በበኩልህ በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሊሆኑ