አትሮኖስ
271K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
437 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ምዕራፍ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
‹‹ እንዴት ናችሁ.?.የሴት ወሬ ላይ ነበራችሁ መሰለኝ….በመምጣቴ ምቾት አልተሰማችሁም››አለ፡፡

‹‹እንዴ ባልዬው የሴት ወሬ ደግሞ ምንድነው?››ስትል አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው ወንዷችን ማማት ነዋ››ሲል በፈገግታ መለሰላት፡፡

‹‹አንተ እንደዚህማ አትለንም….በዚህ ፀባይህ ላላገባህ እችላለው…የደገስከው ድግስ  ብላሽ እንዳይሆንብህ

ፀአዳ ጣልቃ ገባች‹‹አንቺ እንደዛማ አታስፈራሪውም..እስኪ ልብ ይኑርሽና እምቢ በይው….የልጅ እናቷን ሳይሆን ልጃገረዶችን ነው የማንጋጋለት››ስትል  መለሰች፡፡

‹‹አንቺ እስስት ለሁለታችንም እኮ ነው እየተሞገትኩ ያለሁት››

‹‹ያንቺን ሙግት አልፈልግም …ይልቅ ሚካኤል… አንተን እና አዲስአለምን ይቅርታ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር። ››አለችው ኮስተር ብላ፡፡

‹‹ምነው ምን ተፈጠረ?››ሚካኤል ብቻ ሳይሆን አዲስአለምም ያልጠበቀችው ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡

‹‹ወንድምህን ዘሚካኤል በሰርጋችሁ ቀን እንዲገኝ ለማድረግ የተቻለኝን ጥሬ ነበር…ግን አልተሳካልኝም፣ አሁን የሚመጣበት ምንም ዕድል የለም።››አለችው፡፡

‹‹ለምን ይቅርታ ትጠይቂያለሽ ? እሱ እንደማይመጣ አስቀድመን እናውቅ ነበር፣››በማለት ሚካኤል ተናገረ፡፡

አሁን ግራ የመጋባቱ ተራ የራሷ የፀዳ ሆነ‹‹ቆይ ለመሞከር እንደሄድኩ ታውቅ ነበር እንዴ?››ስትል በጥርጣሬ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡

ፈራ ተባ እያለ በሹክሹክታ‹‹አዎ..አውቅ ነበር››አላት፡፡

ወደአዲስአለም ዞረችና‹‹አንቺ በቃ ሚስጥር የሚባል ነገር አታውቂም..ለዛውም እንዳትነግሪው ብዬ አስጠንቅቄሽ?››

‹‹አንቺ ደግሞ ባልና ሚስት አንድ ሀምሳል አንድ አካል ናቸው ሲባል አልሰማሽም እንዴ? ከገዛ አካሌ ምን ብዬ ነው የምደብቀው?››

‹‹አረ የምትገርሚ ነሽ…ሚኪ ግን በጣም አዝናለው…››

‹‹ምን ያህል እንደሞከርሽና እንደጣርሽ አውቃለው….በእውነት አዲስ በነገረች ቀን እንባ አውጥቼ ነው ያለቀስኩት..ማንም ሰው እዲህ አይነት ነገር ላድርግለህ ብሎኝ አያውቅም ..እህቴ በጣም ነው የምወድሽ …በጣም ነው የማመሰግንሽ››አላት

‹‹እኔም በጣም ነው የምወድህ››አለችና ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችበት፡፡እሱም ተቀብሎ አቀፋት፡፡

‹‹እናንተ እኔንም እኮ አስቀናችሁኝ››አለችና ከተቀመጠችበት ሄዳ ሁለቱንም አንድ ላይ አቀፈቻቸው፡፡
///
መድረስ አይቀርም ለአመታት  ሲታሰብበት እና ለወራት ሲለፋበት የነበር የሰርግ ቀን ደርሶ አዳራሽ ሙሉ እድምተኞች ሙሽሮቹን አጅቦ ሽር ብትን እያሉ ነው፡፡ ፀአዳ በህይወቷ ከዚህ በፊት እንደዚህ  አይነት  ደስታና ፈንጠዝያ  ተሰምቷት አያውቅም?ከሙሽራዋ ጀርባ ሆና በደመቀ ሁኔታ የሚካሄደውን ስነስርዓት እየተከታተለች ነው፡፡በአዲስ አለም የሰርግ ቀሚስ ላይ ያለው የተራቀቀ ዶቃ በመስታወት ላይ ሲያርፍ  በተብረቀረቀ ብርሃን አንጸባርቆ  መልሶ ወደውስጥ ሲረጭ ስትመለከት በተረት አለም ውስጥ ስላሉ ልዕልቶች  እንድታስብ አደረጋት።  የአጋቢውን ፓስተር ድምጽ ላይ ለማተኮር ሞክራለች። እሷ ራሷ የለበሰችው ቀሚስ ልዩ አይነት ስሜት እንዲሰማት አድርጓታል…በህይወቷ መቼ ቀሚስ ለብሳ እንደነበረ አታስታውስም፡፡ ምን አልባት ከቤተሰቦቾ ጠፍታ ከወጣች በኃላ ቀሚስ ጨርሱኑ ለብሳ አታውቅም ይሆናል…ሴት መሆኗ እንዲሰማት አትፈልግም…ጠንካራ ታጋይ ሆና ልጇን ማሳደግና ህይወትና ማሸነፍ ብቻ ነው እቅዷ ..ቀሚስ መልበስ ለስላሳ የሚያደርጋት ይመስላታል…በምን ምክንያት እንደዛ ልታስብ እንደቻለች አታውቅም..ግን ደግሞ ትክክል ነበረች፡፡ ይሄው ዛሬ የተለየ ስሜት እየተሰማት ነው…ሴትነቷ ጎልቶ እየበራ ነው…ይሄ ደግሟ ለሚመለከቷት ሰዎች ብቻ ሳይሆን… ለራሷም በደንብ ታውቋታል፡፡ አዲስአለም የሚካኤልን  እጅ በመያዝ አጋቢው ፓስተሩ የሚላትን ጥምረታቸውን የሚያበስሩ ውብ ቃላትን  ጥርት ባለ ድምፅ ስትደግም ይሰማል… ።

በመከራህም ሆነ በደስታ ጊዜ… ላልለይህ ቃል እገባለው፡፡
በሀዘንህም ሆነ በደስታህ …ጊዜ ከጎንህ ልሆን  ቃል እገባለው፡፡
በጤንነትህም ሆነ በህመምህ ጊዜ …ከጎንህ ላልለይ ቃል እገባልው፡፡

ቀላበቱን አውጥቶ አጠለቀላት እሷም አጠለቀችለት፡፡እርስ በርስ እንዲሳሳሙ ተደረገ….ፀደይ  በምታየው ነገር ሁሉ አንሳፋፊ አይነት  አስካሪ  ስሜት እየተሰማት ነው፡፡

እሷ ከረጅም ጊዜ በፊት ነው በደስታ ማመን ያቆመችው፣ ነገር ግን እዚህ ውብ ቦታ ላይ ሆና አዲስአለም እና ሚካኤል ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ባልና ሚስት መሆናቸውን በፓስተሩ ሲታወጅ ስትሰማ  ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ደስታ ተገፋፍታ ከጣሪያ በላይ ‹‹…እልልልልል….›› ስትል አዳራሹን አናጋችው..በዙሪያዋ ያሉ ሚዜዎችና አጃቢዎች ተቀላቀሏት…ዘፈኑና ጭፈራው ቀጠለ..፡፡
///
ዘሚካኤል አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ወንበር ከያዘ ደቂቆች አልፈውታል፡፡በአይኑ እየፈለጋት ነው፡፡‹‹በፈጣሪ ስም ወዴት ሄዳሽ ነው?››አጉረመረመ፡፡

ቢፌ የተዘረጋበትን የተንቆጠቆጠ የድግስ አዳራሽ ውብ ሆኖ ይታያል፣  የሰርጉ ድግስ አሁን በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው እና ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ እንግዶች በግዙፉ አዳራሽ ሽር ብትን እያሉ እና እየተዝናኑ ነበር።

‹‹አንድ ባልና ሚስት እንዴት በዚህ መጠን ብዙ ጓደኞች እና ወዳጆች ሊኖራቸው ቻለ?››ሲል አሰበ ፡፡ እና  ደግሞ ሁሉም  ወደ እሱ ለመቅረብ እና ከእሱ ጋር ውስን ቃላትን ለመለዋወጥም ፈልገው ሲቁነጠነጡ ታዘበ ። እሱ ግን ቀልቡም አይኑም እየተንከራተተ ያለው አንዲትን ሴት ለማየት ነው ።ድንገት ከመድረክ ላይ ከሙሽሮቹ ጀርባ ሆና ተመለከታት፡፡ ግን ወዲያው ተሰወረችበት ፡፡‹‹ዘሚካኤል አረ እራስህን ሰብስብ ››ሲል ራሱን ገሰፀ…ፊቱን ወደግድግዳ አዞረና በእጁ የያዘውን መጠጥ እየተጎነጨ ዘና ለማለት ሞከረ። ቢያንስ  እንደዛ በማድረጉ በአይኖቻቸው   ሲያሳድዱት የነበሩትን ጎረምሳ ልጃገረዶችን መገላገል ችሏል ፡፡

‹‹ወደዚህ ተንደርድሬ እንድመጣ ያደረገኝ  ምንድን ነው?››እራሱን ጠየቀ፡፡ትላንት አመሻሹ ላይ ወደ ዱባይ የመብረር እቅድ ነበረው፡፡ትኬት ሁሉ ቆርጦ ነበር፡፡ከአምስት ቀን በኃላ የሚጀመርና ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚካሄድ የሙዚቃ ድግስ አለው፡፡ከአምስት ቀን አስቀድሞ የሚጎዘው…ቀደም ብሎ ከአካባቢው ሁኔታና የአየር ጻባይ ጋር ለመለማመድና   ለዝግጅቱ ትኩረት ለመስጠት ስለፈለገ ነበር፡፡እና በፕሮግራሙ መሰረት ሻንጣውና ሸክፎ ወደቦሌ መጓዝ ጀምሮ ነበር..ግን በመንገዱ ላይ የሚያያቸውን ቢል ቦርዶች ሁሉ የልጅቷን ምስል የያዙ እየመሰሉት ሲደነግጥና ፈፅሞ ሊቆጣጠረው የማይችል ስሜት ውስጡ ሲያሸብረው..ወዲያው ስልኩን አውጥቶ ለኤጀንቱ ነበር የደወለው፡፡

‹‹ሄሎ ይቅርታ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆነ ዛሬ መብረር አልችልም››አለው፡፡

‹‹ምነው..ምን ተፈጠረ?››

‹‹እያመመኝ ነው…አሁን ቦሌ አየር ማረፊያ እየተቃረብኩ ነበር..ግን ወደቤቴ ልመለስ ነው…በረራውን ለሌላ ቀን እንዲሸጋገር አድርግ፡፡››

‹‹ለመቼ ለነገ ላድርገው….?››

‹‹ነገ እንደሚሻለኝ በምን አውቃለው…?ምናልባት ተነገ ወዲያ››

‹‹አውቀሀል …?ዝግጅቱ 5 ቀን እኮ ነው የቀረው››