አትሮኖስ
282K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
490 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ልጄ እንግዲህ የተነጋገረነውን አስብበት….የእግዚያብሄር ፍቃድ ከሆነ የዛሬ ወር በሰላም እንደምንገናኝ አምናለው…እናም ከዚህ የተሻለ ቆይታ እንደሚኖረን እተማመናለው፡፡›› ብለው ወደበራፉ ሄዱ …ጠባቂው ቀድሞ ከፍቶ ተቀበላቸው…እሳቸውን አስወጣና ወደ ቅጣው ሄደ …ሰንሰለቱን ይዞ እየጎተተ ይዞት ወጣ …በራፍ ላይ መሳሪያ ደቅኖ የሚጠብቀው ሌላ ጠባቂ ወደክፍሉ መለሱትና መልሰው ሰንሰለቱን ከተቀበረው ብረት ጋር አያይዘው ከቆለፉት በኃላ የውጩን በራፍ  መልሰው ዘግተው ጭለማው ክፍል ውስጥ ጥለውት ሄዱ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍395
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_16

ኤልሳ ተሰናብታኝ ከፖሊሱ ጋ ተከታትለው እየወጡ ላለ ውስጤ ሆኖ ስለሚያስጨንቀኝ የአልማዝ አሟሟት ልጠይቃት ፈልጌ ስሟን ተጣራሁ፡፡ ዞር ስትል እምባ ከዓይኖችዋ ይወርድ ስለነበር አማራጭ አልነበረኝምና፤ "አይ ተዪው" አልኳት፡፡ ቀጥ ብላ ቆማ በርህራኄ ዓይን አየችኝ፡፡ እነሱ እንደወጡ ምርመራው ክፍል _ ውስጥ የቀረነው እኔና ጠበቃው ብቻ ነበርን:: ፊት ለፊቴ ተቀምጦ ዓይን ዓይኔን ሲያይ ምን ብዬ እንደማነጋግረው ሳወጣና ሳወርድ፣ እሱ ራሱ ዝምታውን ጥሶ፤ “አቶ አማረ፤ እኔ ሣሙኤል ገድሉ እባላለሁ፡፡ የኤልሳ ጓደኛ ነኝ፣ ማለትም እጮኛዋ ነኝ፡፡ እሷ ላንተ ያላት ፍቅር ልዩ ነው፡፡ በንፁህነትህና ባልፈጸምከው ወንጀል እንደታሰርክ ምንም ጥርጣሬ የሚባል ነገር የላትም:: ባልሰራኸው ሥራ እንደተከሰስክ ስለምታምንም አንተን መርዳት ትፈልጋለች:: በቀደም ዕለት ብቻህን ያለ ጠበቃ መቆምህን እንዳየች በጣም አዝና እኔ እንድቆምልህ ስለጠየቀችኝ፣ ጥብቅና ልቆምልህ ተስማምቼያለሁ:: እርግጥ ነው ከዚህ በላይ ደግሞ እኔ ላንተ ጥብቅና ለመቆም የወሰንኩት ኤልሳ ባንተ ንጽህና ላይ ያላትን እምነት በመረዳቴና በመጋራቴ ነው:: እኔ ለማልረታበት ነገር ጥብቅና መቆም አልፈልግም:: ስለዚህ ፍቃድህ ከሆነ እኔ ጠበቃህ ለመሆን ዝግጁ ነኝ' አለኝ፡፡ ጠበቃዬ ዕድሜው በግምት አርባ ዓመት አካባቢ የሚደርስ በመሆኑ ከኤልሳ ጋር ሲተያይ በጣም ይልቃታል፡፡ ኤልሳ የእኔ እኩያ በመሆኗ ዕድሜዋ ከሰላሳ ዓመት አይበልጥም፡፡ እርግጥ ቦርጫምና ወፍራም በመሆኑ ምክንያት ምናልባት ልጅ ሆኖ ነገር ግን በዚሁ የተነሳ ጠና ያለ ሊመስል ይችላል፡፡ በተረፈ መልከመልካምና ከእሷ በትንሹ ፈገግ ያለ ጥቁር ፊት አለው፡፡ ሲያወራ በየመሀሉ ፈገግ ስለሚል ሁኔታው ሁሉ የሚከብድ ዓይነት አይደለም፡፡ እኔኑ ለመርዳትና ጥብቅና ሊቆምልኝም መጥቶ ፍቃደኛ መሆኔን በትህትና ሲጠይቀኝ በማየቴ ለሰው አክብሮት ያለው በመሆኑ ጨዋ ሰው ነው ብዬ ደመደምኩ፡፡

“እንግዲህ እኔ ጥብቅና የምቆምልህ አንትን ወክዬ በመሆኑና እውነቱንም ማወቅ ስላለበኝ፣ የሆነውን ነገር ሁሉ ሳትደብቅ ንገረኝ" በማለት የተለያዩ ጥያቄዎችን ያዥጎደጉድብኝ ጀመር። እንዳንዶቹን ጉዳዮች እኔ ራሴ የማላውቃቸው ስለነበሩና እንዲያውም በተቃራኒው እኔ ኤልሳን ልጠይቃት የተዘጋጀሁበት ጥያቄ ስለነበር ራሴው ተመልሼ ተጠያቂ ስሆን ደነገጥኩ:: የጠየቀኝም የማላውቀውን ታሪክ ነበርና ብዙ አውጥቼና አውርጀ:: “እውነት ለመናገር ከሆነ፣ የምትጠይቀኝን ነገር እኔ ራሴ አላውቀውም፡፡ የአልማዝንም ሞት የሰማሁት እዚህ እስር ቤት ውስጥ ነው:: ከትምህርት ቤት ከተባረርኩ ጀምሮ አይቻት አላውቅም” አልኩት:: ግራ በተጋባ ሁኔታ ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆየና፤ “ማለት እዚህ ስትመጣ ለምን እንደመጣህ አታውቅም ነበር ማለት ነው" አለኝ:: ሆን ብዬ ላለመናገር የማደርገው ነገር ስለመሰለው በአመላለሴ ቅር መሰኘቱ ከፊቱ ላይ ይነበብ ነበር፡፡ ያለኝ አማራጭ ሁኔታውን በዝርዝር ማስረዳት ብቻ ስለነበር እንዴት እዚህ እንደመጣሁ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሬ ዘክዝኬ ነገርኩት:: የሚፈልገውን መረጃ ፅፎ ከጨረሰ በኋላ በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት እንደሚመጣ ነግሮኝ ተሰናብቶኝ ወጣ፡፡ በሦስተኛው ቀነ ቀጠሮ ስሜ እንደተጠራ በፖሊስ ታጅቤ ዳኞች ፊት ቀረብኩ:: የእጄ ላይ ሰንስለት ተፈትቶ ሳጥኔ ውስጥ ገባሁ:: ጠበቃዬ ከፊት ለፊት ከአቃቤ ሕጉ በተቃራኒ ቆሞ ባለበት አንገቱን ጎንበስ በማድረግ ሰላምታ ስጠኝ፡፡ ኤልሳ ከፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ ተቀምጣ በማዘን መልክ አንገቷን ወደ ጎን ዘንበል አድርጋ ትመለከተኛለች:: ጥቂት የመስሪያ ቤት ጓደኞቼም ጥግ ላይ ተቀምጠዋል:: መሃል ዳኛው በያዙት መዶሻ ጠረጴዛውን ጠልዘው "ፀጥታ” ካስጠበቁ በኋላ፤ የክሱን ዝርዝር ልክ ስገድል እዚያ የነበሩ በሚመስል መልኩ በንባብ ማሰማት ጀመሩ፡፡ እስር ቤት ውስጥ እያለሁ ለአንድም ደቂቃ ቢሆን አለወንጀሌ መታሰሬን አስቤ እና ተበሳጭቼ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ዛሬ እዚህ ሳጥን ውስጥ ገብቼ ስቆም የሆነውን ነገር በፀጋ መቀበል ተስኖኝ ተበሳጨሁ፡፡ ንፁህ የፍቅር ሰው እንደወንጀለኛ ስንት ነፍሰ ገዳይ ገብቶ በተፈረደበት ሳጥን ውስጥ ገብቼ ካለጥፋቴ ስወነጀልና ያልፈፀምኩት የወንጀል ታሪክ ሲተረክ ብሎም ባልፈፀምኩት ወንጅል ሊፈረድብኝ እዚህ መምጣቴን ሳስብ እምባ ተናነቀኝ። ነገር ግን ማልቀሱ ከፍርሐት የመነጨ እንጂ ባልፈፀምኩት ወንጀል በመታሰሬ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ስለማይኖር እንደምንም ታግዬ መለስኩት፡፡ ይህንንም ሁኔታ ሳስብ በዚች ዓለም ላይ ምን ያህሉ ሰው እንደእኔ ያለኃጢአቱ ተወንጅሎ እዚህ ሳጥን ውስጥ ቆሞ በግፍ ተፈርዶበት ይሆን በማለት ማሰላሰል ጀመርኩ።

ዳኛው ምን እንደሚሉ ባይገባኝም ያ አቃቤ ሕግ የጠቀሰውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር ተጠቅሶ ጭካኔ በተሞላው መንገድ የፈፀምኩት ግድያ ድራማዊ በሆነ አቀራረብ ይተረክ ጀመር፡፡ እኔ በጉጉት ስጠባበቅ የነበረው አልማዝ እንዴት እንደሞተች ለማወቅ ነበር። ግን ምን ያደርጋል የዚያችን ከራሴ በላይ የምወዳትንና የምሳሳላትን የውድ ፍቅረኛዬን አሟሟት በንባብ ስሰማ ምነው ይህንንስ ባልሰማሁት ኖሮ ማለቴ አልቀረም። እንካን ሰው የሚጎዳ ድርጊትን ማድረግ ቀርቶ አንድም ቀን ከአፋ ክፉ ቃል ወጥቶ የሚያውቅ ፍቅረኛዬ የተገደለችበትን ጭካኔ የተሞላበት አገዳደል እንደስማሁ ራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ ድምፅ እያሰማሁ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ በሁኔታው ቢደናገጥም፣ እኔ እንዲያ የምሆነው ግን የሚያጋጥመኝን የቅጣት ውሳኔ መጠን ፈርቼ እንጂ ለእሷ ሲል ነው የሚያለቅሰው ብ እንደማያስብ እርግጠኛ ስለነበርኩ ብዙም ደንታ ሳይሰጠኝ ለቅሶዬን ቀጠልኩ፡፡ ዳኛው ልቅሶዬን እንዳቆም አዘው ትረካቸውን ቀጠሉ፡፡ ዩንቨርስቲ ውስጥ ተዋደን በፍቅር ስንኖር እኔ በትምህርቴ በመድከሜ የተነሳ መባረሬን፣ ከዛ በኋላ እሷ እዛ በቆየችበት ወቅት ዶ/ር አድማሱ ከተባለ የዩንቨርስቲ መምህር ጋር ተዋዳ ፍቅር መጀመሯን፣ በዚህም የተነሳ ከእኔ ጋር ቅራኔ ውስጥ በመግባቷ መለያየታችንን፡፡ ከዛም እኔ በቂም በቀል ተነሳስቼ አመቺ ጊዜና ቦታ ጠብቄ ሕይወቷን በማጥፋቴ በመግደል ወንጀል ተከስሼ መቅረቤን በመግለፅ ድራማውን አጠናቀው መጋረጃውን ዘጉ፡፡ ለእኔ ታሪኩ የተፈፀመ ድርጊት ሳይሆን የሆነ አንድ ልብ ወለድ ታሪክ በድራማ መልክ ተሰርቶ የማይ እስከሚመስለኝ ድረስ ፈዝዤ አዳመጥኩ:: ፍቃደኛነቴ ሳይጠየቅ በቲያትሩ ውስጥ የምሳተፍና መሪ ተዋናይ ሆኜ ከአልማዝ ጋር እንደምንተውን ያህልም ሆኖ ተሰማኝ:: በመጨረሻም ጥፋተኛ መሆንና አለመሆኔን የእምነትና ክህደት ቃሌን እንድሰጥ መድረኩ ተለቀቀልኝ:: በምሰጠው መልስ ላይ ከራሴ ጋር ግብግብ ገጠምኩ:: ሁለት አማራጮች አሉ፣ እየተተወነ ያለው ድራማ፣ ድራማ ሳይሆን በእውነት የተፈፀመ ድርጊት በመሆኑ ድርጊቱን አምኖ ማረጋገጥ፣ አሊያም ትያትሩ ትያትር እንጂ ከዚህ ያለፈ እውነተኛ ድርጊት አለመሆኑን ማረጋገጥ፡፡ የቀረበው ትያትር እንጂ በውን የተፈፀመ ድርጊት አለመሆኑን ለማሳመን ደግሞ ድርጊቱን አለመፈፀሜን በተጨባጭ ማስረዳት አለብኝ፡፡ ነገር ግን አልገደልኩም ብዬ ለመናገር ድፍረቱን አጣሁ፡፡ ምክንያቱም ይህንን ቃል እየደጋገምኩ ተናግሬዋለሁ፤ ግን አንድ ሰው እንኳ ላሳምን አልቻልኩም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ዳኛው በማራኪ አነጋገር እንዲህ አጣፍጠው ወንጀለኛ መሆኔን ለዚያ ሁሉ ባለጉዳይና ታዛቢ ካቀረቡ በኋላ በዚያ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህ የተባለው ፍጹም ውሸት ነው ብሎ ለማሳመን
👍381
መሞከር ጉንጭ ማልፋት ካልሆነ በስተቀር ምንም ፋይዳ የሚኖረው አልነበረም፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የቀረበው ድራማ ሳይሆን እውነተኛ ታሪክ ነው ብዬ ለመቀበልም ፍጹም አዳጋች ሆነብኝ። ምክንያቱም እውነት ነው ብዬ ብቀበልና ገደልኩ ብዬ ባምን እንኳ ወደ ፊት ለሚጠብቀኝ መስቀለኛ ጥያቄ መልስ የማገኝ መሆኔ ላይ እርግጠኛ አልነበርኩም:: ከዚህ ውጪ ደግሞ የኤሌሳንና የጠበቃዬን ጭንቀት ሳይ እኔው ራሴ ተመልሼ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ:: ሁለቱም የመማፀን ያህል አንገታቸውን ግራና ቀኝ በማወዛወዝ ጥፋተኛ ነኝ ብዬ እንዳላምን በከፍተኛ ጭንቀት አሻግረው ይለምኑኝ ነበር:: ዳኛው ቶሎ አምኜላቸው መገላገልን ፈልገው ይሁን ወይም ዝምታዬን ሲያዩ ሳይገድላት አይቀርም ብለው ጠርጥረው እንደሆነ ባይገባኝም፣ ብቻ በተቻኮለ መልኩ በድጋሚ የእምነት ክህደት ቃሌን እንድሰጥ ሲጠይቁኝ ፈጥኜ መልስ ለመስጠት አፌ አልላቀቅ አለ፡፡ በመጨረሻም በውስጤ የነበረው የእውነት ኃይል አሸንፎ “ጥፋተኛ አይደለሁም" የሚለውን ቃል እየቀፈፈኝ ከአፌ አወጣሁት:: ፀጥ ብሎ የነበረው ታዛቢ ብዙ አስቤ ያወጣሁትን ቃላት ሲሰማ የጠበቀውን ይሁን ወይም ያልጠበቀውን ነገር በመስማቱ ባይገባኝም፣ በአንድ ግዜ ማንሾካሾኩን ተያያዘው:: በእርግጠኝነት ለመናገር ግን፣ የዳኛውን ትረካ የሰማና የእኔንም ያን ያህል ተጨንቀ ያወጣሁትን እውነት ያዳመጠ፣ ምናልባትም ከኤልሳና ከጠበቃዬ ውጪ ያለ ማንኛውም ሰው የማይታሰብ ነው፡፡ የእውነቱን እውነትነት ይቀበላል ብሎ ማሰብ ፍጹም ዳኛው ሕዝቡ ፀጥ እንዲል ካዘዙ በኋላ ቀጠል አድርገውም ጠበቃዬ መናገር የሚፈልገው ነገር ካለ በማለት እድል ሰጡት፡፡ “ክቡር ፍርድ ቤት፤ ተከሳሹ ባልፈፀመው ወንጀል መጉላላት ስለሌለበት ውጪ ሆኖ እንዲከራከር የዋስ መብት እንዲፈቀድለት" በማለት ጠበቃዬ በትህትና ጠየቀ፡፡ አቃቤ ሕግ ይህችማ ቀላል ጥያቄ ነች! በሚል ሁኔታ ይመስላል በስሜት ተነሳና፤ “ክቡር ፍ/ቤት፣ ተጠርጣሪው የተከሰሰበት ወንጀል የዋስ መብት የሚያስጥ ባለመሆኑ ሊፈቀድለት አይገባም'' አለ፡፡ ለነገሩ ነው እንጂ እንኳን እሱ የሕጉ ሰው ቀርቶ እኔም ብሆን የዋስ መብት ጥያቄው የማይመስል ጥያቄ መሆኑን እውቃለሁ፡፡ ዳሩ ዋስስ ቢባል ከየት ላመጣ ነው፡፡ እንዲያውም ለእኔ ነፃነቴን ሳላረጋግጥ ወጥቼ ማንም ሲጠቋቆምብኝ ከማይ እዚያው እስር ቤት ውስጥ ከምወዳቸውና ከሚቀሉኝ ሰዎች ጋር ግዜዬን ማሳለፉ የተሻለ ነበር:: እዚያ ለአብዛኛው እስረኛ ወንጀል

ምንም አዲስ ነገር ስላልሆነ "ፍቅረኛውን የገደለ ነው እያለ የሚንሾካሽክብኝ የለም:: ያም ሆነ ይህ ዳኛው አቃቢ ሕግ አለኝ የሚለውን ምስክር እና ተጨማሪ ማስረጃ ካለ ይዞ ጥር 20 ቀን 1981 እንዲቀርብና እስከዛው እኔ ወህኒ ቤት ሆኜ ክሴን እንድክታተል በመወሰን አሰናበቱን:: ከፍርድ ቤቱ ልወጣ ስል ኤልሳ በር ላይ ጠብቃ፤ “አመስግናለሁ አማረ፤ አይዞህ በእግዚአብሄር ረዳትነት ተከራክረን ነፃ እናወጣሀለን" አለችኝ:: ራሴን ለመከላከል አልገደልኩም ብዬ በመናገሬ ማመስገኗ ቢገርመኝና ለእኔ መጨነቋ ቢያስደስተኝም፣ ሐሳቧ ተሳከቶላት ከእሥር ብታሰፈታኝም ነፃ ግን ልታወጣኝ እንደማትችል ስለማውቅ አዘንኩላት:: ምናልባት ያልተጠበቀው ነገር በተአምር ተፈጥሮ በድን አካሌን ከእሥር ልታስፈታውና ነፃ ልታደርገው ብትችልም፣ መንፈሴ ግን ለዘላለሙ የአልማዝ ፍቅር አይቻላትም:: እስረኛ በመሆኑ ከእንግዲህ ወዲህ ነፃ ልታወጣው ከአንድ ቀን አዳር በኋላ ወደ ወህኒ መውረድ ስለነበረብኝ የእስር ቤት ጓደኞቼን ተሰናብቼ በፖሊስ ታጅቤ ወደ ተዘጋጀልኝ የእስረኛ መኪና ገባሁ። ስገባ ሌላ ክፍል ውስጥ ከነበሩና ወደ ወህኒ ቤት አብረውኝ ከሚሄዱ እስረኞች ጋር ተገናኘሁ፡፡ ለአየር ማስገቢያ ብቻ ቀዳዳ በተተወለት መኪና ውስጥ ተዘግቶብን እየተጓዝን ስለነበርና ከውጪ ስንገባ ዓይናችን ጨለማውን እስከሚላመደው ድረስ ምን ያህል ሰው እንዳለ ለማየት ያዳግታል፡፡ መኪናው ውስጥ ያለነው ብዙ እስረኞች ብንሆንም አንድም የሚያወራ እስረኛ አልነበረም፡፡ ለማውራትም የሚመች ቦታ አልነበረም፡፡ አማራጭ አልነበረምና ለአየር ማስገቢያ በተተወች ቀዳዳ በኩል አለፍ አለፍ እያልኩ ውጪውን መመልከት ጀመርኩ፡፡ በናፍቆት መንፈስ ከተማውንና መንገደኛውን አየሁት፡፡ ከርቸሌ ውስጥ ምንም የተለየ ነገር አላጋጠመኝም፡፡ በእርግጥ እዚህ ጠያቂ የሚገባው እሁድ ብቻ ስለሆነና ከጠያቂ የሚመጣው ምግብ፣ መጠጥና ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡ ቦታው ለእኔ የተለየ ቢሆንም የተለየ ሕይወት ግን አልነበረም። እዚህ ያሉትም ተመሳሳይ ሰዎችና ተመሳሳይ ሕይወት ነበር። እዚህም ከዛሬ ውጪ ላለ ሕይወት የማይጨነቅ ሰው፣ ለመግባባት ብዙ ግዜ የማይፈጅበት፣ በጠባብ ክፍል ውስጥ ታፍኖ ሕይወቱን እየገፋ ቢሆንም፣ በነፃው ዓለም እንደልቡ እየተዘዋወረ ከሚኖረው ህዝብ በተሻለ ሁኔታ እውነታውን ተቀብሎና ተለማምዶ በደስታ እየኖረ ያለ ስው የሚገኝበት ቦታ ነበር። እዚህ አንተ ለምትኖረው ሕይወት የሚጨነቅልህ አንተ ሳትሆን ሌላው ነው:: ነገ ምን እለብሳለሁ፣ምን እበላለሁ፣ የቤት ኪራይ ከየት አምጥቼ እከፍላለሁ ወዘተ የሚሉ የነፃውን ዓለም ሰው የሚያስጨንቁ ሐሳቦች ወደዚህ በብረት አጥር ወደ ታጠረውና በመትረየስ ወደሚጠበቀው

የተሞላች ነች:: የሚያጣላ፣ የሚያነጫንጭና የሚያስጨንቅ ብዙ ነገር የለም:: ግቢ አልፈው መግባት አይቻላቸውም:: እዚህ ሕይወት በሳቅና በደስታ እግዜር ይህንን ወስዶ ደስታና ፍቅርን በምትኩ ሰጥቶናል:: እየቆየሁ ስሄድ እስር ቤቱን ከመለማመዴ የተነሳ እኔ ራሴ አሁን አሁን አዲስ እስረኛ ሲመጣ አለማማጅ ሆኜአለሁ:: በተለይ በጣም የሚያረካኝ ነገር እያንዳንዱ እስረኛ የታሰረበትን ጉዳይ ጠጋ እያሉ ማዳመጥ ነበር:: ይህም ከብዙ አስረኛ ጋር በአጭር ግዜ ውስጥ እንድተዋወቅ ረድቶኛል:። ደግሞስ በእሥር ቤት ውስጥ ከዚህ የተሻለ ምን መዝኛኛ ሊኖር? በተለይም የክፍላችን ካቦ በጣም ርህሩህ ከመሆኑ የተነሳ እወደው ስለነበር፣ ይህ ምስኪን ሰው ወንጀል ስርቶ ሳይሆን እንደእኔ በማያውቀው ነገር ተወንጅሎ ሊሆን ይችላል ብዬ ስለማስብ የታሰረበትን ምክንያት ለማወቅ በጣም እጓጓ ነበር:: አዲስ የገባ እሥረኛን ማረጋጋት እንጂ ማስደንገጥ አይፈልግም:: የሻማ ሲጠይቅም ሥርዓት በተሞላ ሁኔታ ስለነበር አብዛኛው ሰው እስጣለሁ ብሉ ያላሰበውን ይሰጠዋል፡፡ ገንዘብ የሌለውን እስረኛ እንኳን ቢሆን ጠያቂ ዘመድ ካለው ጠይቆ ገንዘብ እንዲያመጣ ሲናገር ትህትና በተሞላበት ሁኔታ ነበር:: ቤተሰብ የለንም የሚሉ እሥረኞች ሲያጋጥሙት ገንዘብ ካላመጣችሁ እያለ የሚያስጨንቅ ሰው አልነበረም:: ይሁን እንጂ ማንኛውም እስረኛ ቤተሰብ የለኝም ብሎ የሻማ ሲያስቀር አይቼ አላውቅም፡፡ ከየትም ከየትም ብሎ ማንም ሳያስገድደው አምጥቶ ይከፍላል:: በዚህ ላይ ደግሞ ዞሮ ዞሮ ብሩን አብዛኛው እስረኛ ይጠቀምበታል እንጂ እሱ እምብዛም የብር ችግርም ሆነ ፍላጎቱ ያለው አልነበረም። ይህ ርህሩህ ሰው በምን እንደታሰረ ማወቅ በመፈለጌ ቀስ በቀስ ተግባባሁትና ለመጠየቅ ወሰንኩ:: በመሀከላቸው ተማሩ ከሚባሉት ጥቂት እስረኞች መሀል አንዱ በመሆኔ፣ ስለሚያከብሩኝና ከእኔም ጋር መቀራረብ ስለሚፈልጉ፣ እሱንም ቢሆን መቅረብ ብዙም አላስቸገረኝም፡፡ ታሪኩን ስሰማ ግን ከጠበቁት ውጪ ስለነበር በጣም ተገረምኩ፡፡ የካቦአችን መደበኛ ሥራ ሌብነት ነው፡፡ ታዲያ ሌብነት ሲባል አዲስ አበባ ፖሊስ እንዳገኘሁት እንደመርሀቤቴው እስረኛ የተሰጣ ፓንት ማውረድ ሳይሆን ረቀቅ ያለ ሌብነት ነው:: የሚሰርቀው ደሀውን ኢትዮጵያዊ ሳይሆን የውጪ ዜጎችን
👍291
ነው:: ብዙ ጊዜ ትላልቅ ሆቴሎች አካባቢ ይጠባበቅና እንግዶች በተለይ ተላላፊ መንገደኞች (Transit Passengers) ሲገቡ አብሮ ተደባልቆ ገብቶ አልጋ ይይዛል:: ማታ ሲዝናኑ አብሮ ሲዝናና ያመሽና አመቺ ሁኔታ ጠብቆ፣ አሊያም እንግዶቹ ወጣ ሲሉ አልቤርጎውን በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍቶ ይሰርቃል:: ሁል ጊዜ አልጋ እየያዘ ስለሚያድር የአብዛኛውን አልቤርጎ ክፍሎች ቁልፍ በወረቀት ላይ ስሎ ያሰቀርፃል:: አጋጣሚ ሆኖ ቢያዝ

እንኳን እንግዳው ግፋ ቢል በነጋታው አሊያም በሁለተኛው ቀን ወደ ሀገሩ ስለሚሄድና የተያዘው የመረጃ ገንዘብም ይሁን ጌጣ ጌጥ ለእግዚቢትነት ጥሎ ስለማይሄድ ለመፈታት አይቸገርም:: በዚህ ላይ ደግሞ መያዝ የሚባል ነገር የሚያጋጥመው አልፎ አልፎ ሲሆን አንዳንድ ተልከስካሽ ፖሊሶችንም ባገኘ ቁጥር እጁን ስለሚዘረጋላቸው ያውቁታልም፣ ይወዱታልም:: በቂ መረጃ በማይኖርበትና ቀደም ሲል ያዘጋጁት የመርማሪ ዘመድና ወዳጅ በማይታጠበት አገር ለሱ አስር ግፋ ቢል ከጥቂት ቀናት የማይበልጥ አሊያም ከሳምንት የሚዘል አልነበረም:: በአሁኑ ጊዜ የታሰረባት የተፈጠረችው ግን እንዲህ ነበር፡፡ መጥፎ አጋጣሚ አንድ ቀን እንደተለመደው መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውቶቢስ መጥተው ወደ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲገቡ ተቀላቅሎ ገብቶ አልጋ ይይዛል፡፡ ማታ የመዝናኛ ሰዓት ደርቶ እንግዶች ለመዝናናት፤ እሱ ለመስረቅ በቦታው ላይ ይገኛሉ፡፡ ሙዚቃው ሲደራና ሰዉ ሞቅ እንዳለው አጅሬ ከሚያውቃቸው የመንገድ ላይ ኮረዶች አንዷን ደንበኛውን አስነስቶ መደነስ ይጀምራል፡፡ ለመስረቅ አመቺውን እንግዳ እያማተረ ሳለ ቀልቡ እንደድንገት አንዱ ፈረንጅ ላይ ያርፋል:: የኋላ ኪሱ በገንዘብ በተሞላ ቦርሳ ተወጥሮል፡፡ ፈረንጁ እሱ ከሚያውቃት ከአንዲት ውብ ኢትዮጵያዊት ጋር ይደንሳል፡፡ እሷም እሱ ወደ እነሱ ጋ ጠጋ ሲል ለምን እንደመጣ ስለምታውቅና ከቀናውም ስለሚያንበሸብሻት ሰውየውን ወደራሷ እስጠግታ ቀልቡን ለመስረቅ ታዋራዋለች፣ ትተሻሸዋለች፡፡ አጅሬ ከሰውዬው ጋር እየተጋፋ መደነስ ይጀምራል፡፡ አመቺ ሁኔታ አገኘና እጁን ሰደድ አድርጎ የሰውዬውን ቦርሳ ይመዛታል፡፡ ግን ቀኑ ገዳፋ ነበርና ከቦርሳው ጋር አብረው የተያያዙ ቁልፎች ይወጡና ወለሉ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ፈረንጁ ድምፅ ሰምቶ ዞር ከማለቱ አጅሬ ቦርሳውን ይጥልና የሚረዳው በማስመሰል ቦርሳውንና ቁልፉን አንስቶ ይሰጠዋል:: ፈረንጁ አመስግኖ _ ቦርሳውን ኪሱ ቢከትም በአካባቢው የነበሩ የደህንነት ሰዎች ሁኔታውን ይከታተሉ ስለነበር ወዲያው ይይዙትና ፖሊስ ጣቢያ ይወረውሩታል፡፡ አጅሬ ግን በነጋታው እፈታለሁ ብሎ ስላሰበ ብዙም አልተጨነቀም ነበር። ይሁን እንጂ እንዳሰበው ቶሎ መውጣት አልቻለም፡፡ ሰውዬው ተላላፊ መንገደኛ ሳይሆን አሜሪካ ኤምባሲ ውስጥ የሚሰራ ዲፕሎማት ኖሮ ገንዘቡን በኤግዚቪትነት አስይዞ ክሱን መከታተል በመጀመሩ ለአጅሬ እንደተለመደው በቀላሉ መውጣት የማይታሰብ ሆነ:: ይኸው አንድ ዓመት ተፈርዶበት ግማሹን አገባዷል፡፡


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍411
#አላገባህም


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


////
ፀአዳ የ21 ዓመት አዋቂ ሴት ነች፡፡አገላለጹ ይጋጫል አይደል?የ22 አመት ወጣት ሆኖ አወቂ ሴት ነች ሲባል  ፡፡አዎ እሷ የ15 አመት እና የ9 ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ድብን ያለ ፍቅር ያዟት ነበር፡፡በ16 ዓመት የልደት በአሏ በሚከበርት ቀን በወቅቱ የ19 ዓመት ጎረምሳና የ11 ክፍል ተማሪ ለነበረው የልቧ ሰው በፍደኝነት ድንግልናዋን አስረከበች፡፡ከሁለት ወር በኃላ ማርገዟን አወቀች… ነገረችው፡፡ከሳምንት በኃላ እሷን ሳይሰነበታት.. ደግሞ ሳይስማት…ደግሞ ቀሚስሽን ላውልቅ ፤ ጡትሽን ልጥባ ሳይላት  እሷንም ሆነ ከተማዋን ጥሎ ውትድርና ተቀጥሮ ሄደ…ያንን የመሰለ አስቀያሚ ዜና የሰሚ ሰሚ ከሰው ነው የሰማችው፡፡ያንን የሰማች ቀን ሰማይ ምድሩ ነበር የዞረባት፡ያልጠና ጮርቃ ልቧ ስንጥቅጥቅ አለ….ደነዘዘች…… ፡፡በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ  ማርገዞን አወቀች…ሰማይ ምድሩ ዞረባት…እና በወቅቱ ሁለት ምርጫ ነበር የታያት ..አንድም በሆነ ዘዴ መርዝ በመጠጠት ወይም በገመድ ተንጠልጥሎ ብቻ በሆነ ዘዴ እራሷን ማጥፋት ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ብን ብላ ሀገሯን ጥላ ወደማታውቀው ሀገር ሄዳ ህይወት እንዳደረጋቻት መሆን፡፡

….በምን አሳማኝ ምክንያት እንደሆነ ባታውቅም ሁለተኛውን መረጠችና ከተወለደችበትና ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ከሚኖርበት ዶዶላ ከተማ በአንድ አነስተኛ ሻንጣ ልብሷና እና ይጠቅሙኛል ያለችውን  ዶክመንት ይዛ ወደአዳማ የሚሄድ መኪና ውስጥ ተሳፈረች፡፡እንግዲህ የህይወት ዘመን ባለውለታዋን የሆነውን ሚካኤልን የተዋወቀችው እዛ መኪና ላይ ነበር፡፡በወቅቱ አጋጣሚ ሆኖ ጎን ለጎን ነበር የተቀመጡት፡፡የተወሰኑ ቃላቶች እየተለዋወጡ ከተግባቡ በኃላ ድንገት ወዳልታሰበ ቁምነገር ያለው ውይይት ውስጥ ገቡ፡፡

‹‹አዳማ ነው የምትሄጂው  ወይስ ወደአዲስ አበባ ታልፊያለሽ?
››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አላውቅም…››ስትል በደፈናው መለሰችለት፡፡

‹‹አልገባኝም››

‹‹እኔ እንጃ ..ከተመቸኝ አዳማ እቀራለው…ከለበለዚያ ወደአዲስ አበባ ሄዳለው…እድል እንዳደረገቺኝ ነው የምሆነው››

‹‹ማለት …ቤተሰብ ጋር ነው የምትሄጂው?››ጥያቄውን አሻሽሎ ጠየቃት፡፡

‹‹አይደለም…ስራ ፍለጋ ነው የምሄደው››

‹‹ስራ ፍለጋ….ምን አይነት ስራ?››

‹‹የተገኘውን ስራ፡፡››

‹‹ምነው… ቤተሰቦችሽ የት  ናቸው?››

‹‹ዶዶላ ነበር የሚኖሩት  …ማለት እናቴ ና እኔ ብቻ ነበር..አሁን እናቴ ስለሞተች ብቻዬን ቀረው…እናቴ የሞተችበት ሀገር ደግሞ ተረጋግቼ መኖር አልቻልኩም..ስለዚህ የእድሌን ልሞክር ብዬ ዝም ብዬ ነው እየተጓዝኩ ያለሁት….››ንግግሯን ተከትሎ ከአይኖቾ እንባዋ እየተንከባለለ ፊቷን በማጠብ ወደታች ይወርድ ጀመር፡

የሚካኤል አይኖቸ እንባ አቀረሩ‹‹በጣም አዝናለሁ….አይዞሽ እሺ››

‹‹አረ ችግር የለውም…መኖር ካቃተኝ መሞት አያቅተኝም››ስትል የበለጠ አስደንገጭ ነገር ነገረችው፡፡እሱ ደግሞ እራስን ማጥፋትን በተመለከት እህቱንና እናቱን በቅርብ ያጣ ሰው ስለነበር በቀላሉ ነው ስሜቱ የተነካው፡፡እና በተቻለው መጠን ሊረዳት ወዲያው ነው በውስጡ ውሳኔውን የወሰነው፡፡

‹ኸረ በፍጽም እንደዛ አታስቢ…ቆይ ትምህርት ተምረሻል?››

‹‹አዎ ግን.. ገና ዘጠነኛ ክፍል ነኝ››

‹‹እንግዲያው ለአንቺ የሚሆን ስራ አለኝ››በማለት ያልጠበቀችውን የሚያስፈነጥዝ የምስራች አበሰራት፡፡ማመን አልቻለችም‹‹እየቀለድክብኝ አይደለም አይደል?››

‹‹አይ እውነቴን ነው…አዳማ ላይ ቡቲክ አለኝ…ፍቅረኛዬ ነች የምትሰራው..ግን በቅርብ ትምህርት ስለምትጀምር የሚረዳት ሰው ያስፈልጋታል…እና ሰው ለመቅጠር እያፈላለግን ነበር››

‹‹በጣም ደስ ይለኝ ነበር…ግን ምንም አይነት ተያዥ እኮ የለኝም..ያለኝ መታወቂያ እንኳን የትምህርት ቤት ብቻ ነው››ስትል ስጋቷን ያለምንም መሸፋፈን በግልፅ ነገረችው፡፡

‹‹ችግር የለውም..እኔ ዋስ እሆንሻለው››ሲል ከስጋቷ ገላገላት፡፡

እንባዋን መገደብ ስላልቻለች ለሁለተኛ ጊዜ ማለቀስ ጀመረች..ያሁኑ ለቅሶ ግን የደስታ ነበር፡፡

‹‹ኸረ አታልቅሺ..በፈጣሪ እኔ ሰው ሲያለቅስ ማየት አልፈልግም››ብሎ  ከኪሱ ሶፍት አወጣና አቀበላት…..ተቀበለችና ፊቷን ጠረረገችበት፡፡

እንዳለው አዳማ እንደወረዱ ቀጥታ ይዟት ወደ ቤት ሄደ… ወስዶ ከፍቅረኛው ጋር አስተዋወቃት፡፡በመሰራት ላይ ካለው ጅምር ቤቱ አንድ ክፍል ቤት አስተካከለና ዕቃ አሟልቶ አስረከባት፡፡ሰው ሳይሆን መላአክ መስሎ ተሰማት፡፡እሱም ብቻ ሳይሆን ፍቅረኛው አዲስ አለምም በልዩ ሁኔታ እንደጓደኛ ብቻ ሳይሆን እንደታናሽ እህት ተቀብላ ወደደቻት….በዚህም ፀአዳ ለረጅም ወራቷች ስታማርረው የነበረውን ፈጣሪዋን ይቅርታ ጠይቃ ማመስገን ጀመረች፡፡

በዚህ ሁኔታ ነው ሚካኤል እና ፀአዳ የተዋወቁት..፣ከዛ ብዙም ሳትቆይ ከቤተሰብ ጠፍታ የመጣችበትን ትክክለኛ ምክንያት ለሚካኤል እና  ለፍቅረኛው ለአዲስአለም  ነገረቻቸው…እንደዛ ያደረገችው ሆዷ እየገፋ ሲሄድ የግድ መጋለጧ የማይቀር መሆኑን ስለተገነዘበች ነው፡፡
ከዛ ልጇን በእጇቸው ላይ ወልዳ ከእሷ እኩል እየተንከባከቡ አሳድጉላት፡፡ዛሬ ላይ እነሱም አንድ ቤት ተጠቃለው መኖር ከጀመሩ አራት አመት ያለፋቸውና የሶስት አመት ልጅ ያላቸው ሲሆን በተለያየ ምክንያት በዚህ ወር ይሁን… በሚቀጥለው አመት እያሉ ሲያዘዋወሩት የነበረው ሰርጋቸውን  ለመደገስ አሁን ቀን ተቆርጦ በጀት ተመድቦለት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ 

እና  ፀአዳም ይሄንን የወዳጆቾን ሰርግ ልዩ እና በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የሚያስታውሱት እንዲሆን ትፈልጋለች፡፡ለዛ ነው ምንም ነገር እንዳይጎድል ለወራት ቀንና ለሊት እንቅልፍ አጥታ ስትለፋ የሰነበተችው ፡አሁን አንድ ነገር ብቻ ይቀራታል፡፡በዚህ ሰርግ ላይ ለሚካኤል ብቸኛ ዘመድ የሆነውን አንድ ወንድሙን እንደምንም አሳምና ሰርጉ ላይ እንዲገኝ በማድረግ  ሰርፕራይዝ  በማድረግ  ደስታውን ሙሉ ልታደርግለት እቅድ አውጥታለች፡፡ሚካኤል  ለረጅም ጊዜ አውርቶትና አግኝቶት የማያውቀው  ወንድሙ ዘሚካኤል  በሆነ ተአምር በሠርጋቸው ላይ እንዲገኝ  ለማድረግ  ከልቧ ቆርጣ ተነስታለች።

ይህንን ሀሳብ በአእምሮዋ ስታሰላስልና ስትዘጋጅበት ከወር በላይ ነው የቆየችው፡፡በጣም በብዙ ጥረትና በብዙ ድካም መውጫ መግቢያውን ፕሮግራሞቹንና ልምዶቹን ስታጠና ነበር ሰነበተችው፡፡በቋሚነት በሚኖርበት አዲስአበባ እሱን ለማግኘት ፈተና ነው፡፡ በትክክል እንዴት እሱ በሀሳቧ እንዲስማማ ለማድረግ እንደምትችል እስካአሁን ድረስ በትክክል አላወቀችም።ምክንያቱም ዘሚካኤል እንደማንኛውም ሰው በቀላሉ አግኝተውት  የሚያናግሩትና የሚያሳምኑት አይነት ሰው አይደለም፡፡እሱ ሚሊዬኖች የሚያብዱለት ከሀገሪቱ ዝነኛ ድምጻዊያን መካከል ከዋናዎቹ አንደኛው ነው፡፡በዛው ልክ ፕሮግራሞቹ የተጣበቡ..አጃቢዎች የበዙ ሰው ነው፡ቢሆንም ይሄንን ማድረግ አለባት፡፡ይሄ ለምትወዳቸው ና የእድሜ ዘመን ባለውለታዋ ለሆኑት ባልና ሚስቶች እንደስጦታ አድርጋ ልታቀርብላቸው ያሳበችው ትልቅ ስጦታ ነው፡፡፡
👍7610👏3🔥2👎1
እሱን አግኝታ አንድ ነገር እንዲያደርግ ለማሳመን ይቅርና ወደ አንድ እንግዳ ሰው ለመጨረሻ ጊዜ የሄደችው መቼ ነበር? የማሳመን አቅሟ ከወንዶች ያነሰ ነበር።መለመን ….ማባበል..  ..በምንድነው ቀልቡን ስባ የምትናገረውና ማዳመጥ እንዲችል የምታደርገው በመልኳ፣ በንግግር ብቃቷ ወይም ሌላ በምን…?ሌላው ይቅር እሱ ጋር በልበ ሙሉነት ለመቅረብ የሚያስችል ጥራት ያለው  ልብስ እንኳን  አልነበራትም። ወደእሱ ከመቅረቧ በፊት ስለእሱ ባህሪ ስለሚወዳቸውና ስለሚጠላቸው ነገሮች ማወቅ እንዳለባት ወሰነች፡፡መጀመሪያ ያደረገችው ስለዘሚካኤል አዲስአለምን መጠየቅ ነው፡፡

‹‹አማችሽ ምን አይነት ሰው ነው?››

‹‹እኔ እንጃ …ያ ሰቅጣጭ አደጋ ተከስቶ በሚስቱና በአንድ ሴት ልጅ ግድያ ተጠርጥሮ እስርቤት እስኪገባ ድረስ በጣም መልካም ሰው ነበር….ጎበዝ ሰራተኛ..ለብዙዎች ህይወት መቃናት ምክንያት የሆነ ሰው እንደነበረ ነው የማውቀው…እኔ ብቻ ሳልሆን  ለሳምንት እንኳን ሚያውቁት ሰዎች በምን አንጀቱ ያንን ወንጀል እንደፈፀመ ይገረማሉ….››

‹‹አይ እኔ እንኳን ያልኩሽ ሰለሚካኤል አባት አልነበረም ስለወንድሙ እንድትነግሪኝ ነው፡፡››

‹‹ወይ!! ስለዘሚካኤል ነው…››አይኖቾ በሩ፡፡

‹‹አዎ ስለዘሚካኤል››

በቴሌቪዝን ሆነ በየፖስተሩ ላይ እንደምታይው ውብና ጠንበልል ወንዳወንድ ነው፡፡ ሲመለከት አይኖቹ ሲስቅ ጥርሶቹ …ሲኮሳተር ወንድነቱ…ሲያወራ ቀልዱ ሁሉም ነገር የተሞላለት ኣማላይ ወንድ ነው…ግን ስለእሱ ለማወቅ ለምን ፈለግሽው?››ስትል በጥርጣሬ ጠቀቻት፡፡

‹‹እሱን ቀስ ብዬ ነግርሻለው…ግን ያንቺ ገለፃሽ ስለአማችሽ ምታወሪ ሳይሆነ በስውር ስላፈቀርሽው የድብቅ ፍቅረኛሽ ምታወሪ ነው የሚመስለው››

‹‹ምነው ስለእሱ ያጋነንኩ መስሎሽ ነው?››

‹‹አይ አጋነንሽ አላልኩም..ገለፃሽ ግን መጎምዠት የተቀላቀለበት ወሲባዊ አይነት ሆነብኝ››

‹‹ጉረኛ አንቺ ደግሞ ስለመጎምዠትና ስለወሲብ ምን ምታውቂው ነገር አለ…?የከተማ ባህታዊት እኮ ነሽ…ለማንኛውም በእኔን በአንቺ መሀከል ይቅርና እኔ መጀመሪያ የአይን ፍቅር የያዘኝ ከዘሚካኤል ነበር፡፡ሚካኤልን የቀረብኩት  ወደዘሚካኤል የሚያቀርበኝ አቋራጭ መንገድ ነው ብዬ ነበር….ግን እኔ ከሚካኤል በደንብ ተዋውቄና ጥሩ ጓደኛው ሆኜ ወደዘሚካኤል ለመዝለል እግሮቼን እያፍታታው ሳለ…በቤታቸው እንደዛ አይነት ትራጄዲ ተፈጠረ፡፡አባትዬው ከርቸሌ ሲወረወሩ ዘሚካኤል ደግሞ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ጠፋ….፡፡በዚህ ጊዜ የሚካኤል አጽናኝና አማካሪ ሆኜ ቀረው፡፡በወቅቱ ሚካኤል እንኳን ቀርቦ ጓደኛ ለሆነው ሰው ይቅርና በሩቅ ታሪኩን ለሚሰማ ሰው እራሱ በጣም የሚያሳዝንና አንጀት የሚበላ ሰው ነበር፡፡እናቱንና እህቱን ቀብሮ..አባቱ እስር ቤት ተወርውረው…ወንድሙ ጠፍቶበት…የሚሰማው ሀዘንና ስቃይ ገምቺው.. በዛ ላይ ቤተሰቡን ሀብትና ንብረት ከብክነት መጠበቅና በዛ እድሜው ከሶስት በላይ ድርጅቶችና የማስተዳደር ኃላፊነት ነበረበት…የጠፋውን ወንድሙን ከሀገር ሀገር እየተንካራተተ መፈለግም ይጠበቅበት ነበር…አብዛኛውን ነገር አንቺም ታውቂዋለሽ፣ በወቅቱ ነገሮች በጣም  ከባድ ነበሩ….እና በዛ ሁኔታ ውስጥ ዘሚካኤል ላይ የነበረኝን እቅድ ሳላስበው ሙሉ በሙሉ ረሳሁትና በሚካኤል አሳዛኝ ልብ ውስጥ ቀልጬ ቀረው ››

‹‹እግዜር ይወድሻል?››

‹‹ማለት ?››

‹‹እንዴ!! ይሄንን አተራማሽ አፍቅረሽ  ቢሆን ኖሮ ከሺ ሴቶች ጋር ነበር ሻሞ የምትቦጨቂው….እግዚያብሄር አተረፈሽ….ሚካኤል እኮ ባል ብቻ ሳይሆን አባት ነው…ከሚሊዬን ወንድ መካከል ሚገኝ አንድ ምርጥ ባል ነው››

‹‹እሱስ እውነትሽን ነው…ግን ዘሚካኤልም እኮ ድሮ እኔ ሳቀው እንዲህ አይነት ሰው አልነበረም››

‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡››

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍61👏135
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ //// ፀአዳ የ21 ዓመት አዋቂ ሴት ነች፡፡አገላለጹ ይጋጫል አይደል?የ22 አመት ወጣት ሆኖ አወቂ ሴት ነች ሲባል  ፡፡አዎ እሷ የ15 አመት እና የ9 ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ድብን ያለ ፍቅር ያዟት ነበር፡፡በ16 ዓመት የልደት በአሏ በሚከበርት ቀን በወቅቱ የ19 ዓመት ጎረምሳና የ11 ክፍል ተማሪ ለነበረው የልቧ ሰው በፍደኝነት ድንግልናዋን…»
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_17

ይኸው አንድ ዓመት ተፈርዶበት ግማሹን አገባዷል፡፡ እንግዲህ በዚሁ ክቡር ነው በሚለው የሌብነት ስራው ለእናትና አባቱ ቤት መሥራት ዓላማው እንደነበርና ያንን ቀደም ሲል እንዳሳካ፣ ወደፊት ለራሱ የሚሆን መኖሪያ ቤትና መቋቋሚያ ገንዘብ እንዳገኘ ይህን የሚወደውን ሥራ እንደሚለውጥ ነገረኝ:: የሚገርመው መው ሚስቱን ያገባው ሳትወድ በግድ

አባቷን በሽጉጥ አስፈራርቶ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ታዲያ ባለቤቱ በየጊዜው ጥሩ ጥሩ ምግብ እየያዘች ትመጣና አልቅሳ ትሄዳለች፡፡ ምንም እንኳን እንደካቦአችን ዘወትር እየመጣች የምታለቅስልኝ ቆንጆ ሚስት እንድትኖረኝ የታደልኩ ባይሆንም፤ አለሚቱ ግን አልፎ አልፎ ምግብ ይዛ ትጠይቀኝና አለቃቅላ ትመለስ ነበር፡፡ ለመጠባበቂያ ብዬ ያስቀመጥኩትን ገንዘብ ከሳጥን እያወጣች እንድትጠቀም ነግሬያት ስለነበርና አልፎ አልፎም የመሥሪያ ቤት ጓደኞቼ እየመጡ ገንዘብ ስለሚሰጡኝ ችግሩ ብዙም አልጠናብኝም ነበር:: ነገር ግን በመጡ ቁጥር "ምን ሆነህ ታሰርክ? እንዴት ነው በቅርቡ የመፈታት ተስፋ አለህ?" ወዘተ.. ለሚለው ተደጋጋሚና አስቸጋሪ ጥያቄያቸው ለጊዜው መልስ ስለማላገኝለት አእምሮዬን ክፉኛ ያስጨንቀው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ በተለይ አንዳንዶቹ ባይመጡ ይሻለኝ ነበር። ጠበቃዬ በየመሀሉ እየመጣ ጠቃሚ ነው ያለውን መረጃ ለማሰባሰብ በተለመደው መልኩ በጥያቄ ያጣድፈኛል፡፡ ይሁን እንጂ ከእኔ የሚያገኘው መረጃ እንዳሰበው ስለማይሆንና ብዙም ልረዳው ዝግጁ ስላልነበርኩ አልፎ አልፎ መበሳጨቱ አልቀረም፡፡ “ስማ አቶ አማረ! እኔም እንደ ኤልሳ በአንተ ንጽህና ላይ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ግን የእኛ ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም:: ለዳኞች እውነቱን ፈልቅቀን ማሳየትና ማሳመን መቻል አለብን:: ለዚህ ደግሞ አንተ አእምሮ ውስጥ ያለውን እውነት ምንም ሳትቀያይርና ሳታድበሰብስ ልትነግረኝ ይገባል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ እኔ አንተን ወክዬ በመቆም ተከራክሬ ማሸነፍ እችላለሁ:: አለበለዚያ ግን ንፁህ ሆነህም ቢሆን የአንተ ንጽህና እያነሰና እየመነመነ ከሄደና ባንጻሩ ደግሞ አንተን ወንጀለኛ የሚደርጉ ነገሮች ጎልተው ከወጡ ባንተ ላይ ሊፈረድ ይችላል፡፡'' አለኝ:: እንደነገረኝ ከሆነ አልማዝ እኔን ትታ ሌላ በመውደዷ የተነሳ ገድሏት ሊሆን ይችላል ተብሎ በፖሊሶች በኩል እንደሚጠረጥሩኝና እስካሁን ድረስም አልማዝን ገድሎ ይሆናል ሊባል የሚችል ከእኔ የተሻለ ሌላ ተጠርጣሪ አለ ተብሎ እንደማይታሰብ ገለጸልኝ፡፡ ስለዚህም ይህንን ግምትና አስተሳሰብ ለመለወጥ ከእኔ ብዙ እንደሚጠበቅብኝም ሊያስረዳኝ ሞከረ፡፡ እኔ ግን ሌሎች ይህንን በማሰባቸው አልፈረድኩባቸውም፡፡ ምክንያቱም እነሱ እኔ ለእሷ ያለኝን ፍቅር እንዴት ሊረዱ ይቻላቸዋል? በእኔ ሕሊና ውስጥ ለአልማዝ ፍቅር እንጂ ለጥላቻ የሚሆን ቦታ የለም፡፡ ጊዜያዊ ስሜቴ በአንዳንድ ሁኔታዎች የተነሳ ላይ ላዩን ቢጠላትም ውስጤ ግን ይወዳታል፡፡ እንኳን ሳትበድለኝ ቀርቶ ምንም ያህል በደል ብትፈጽምብኝ ያንን አጋጠማት የተባለውን ሁኔታ ለእሷ በፍፁም አልመኘውም:: የጥንት ጥላቻዬም ቢሆን የመጥላት ሳይሆን

የፍራቻዬ መገለጫ ነው፡፡ ያም የሌላ ሳይሆን እያስታወስካት ከመሰቃየት ይልቅ ጥላቻን እየራገብኩ ከፍቅር ለመራቅ የማደርገው ግብግብ ነበር። ያም ሆነ ይህ ታሪካችን ይኸው መሆኑንና የመከላከያ ምስክር ይሆኑኛል ያልኳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር፤ የጮኛውን የኤልሳን ስም ጨምሬ ስጠሁትና ተለያየን፡፡ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች የሚሰሙበት ቀን ደርሶ ወደ ፍርድ ቤት አመራሁ፡፡ምስክሮቹ በየተራ እየወጡ የእኔን ገዳይነት ቆመው ያዩ ወይም መግደያ ያቀበሉ እስኪመስል ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ እየማሉ መሰከሩ። ሲገድላት አይተናል ማለት ቢቀራቸውም ከአነጋገራቸው እንደተረዳሁት ስለመግደሌ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ አልነበራቸውም። አቃቤ ሕግ የሚፈልገውን ጠቦት አግኝቶ ለማረድ ቢላ ያቀበሉት ያህል ተሰምቶት በድል አድራጊነት በቁሙ ተፍነከነከ፡፡ ቢላው እጁ ገብቶለታል፤ ነገር ግን በእኔ ደም መጨማለቅ ያልፈለገ ይመስል ዳኛው ይህንን የሕሊናና የፍርድ ሃላፊነት እንዲወስዱለት ለማድረግ፣ በደሌንና ጭካኔዬን ከምስክሮች አፍ በሚፈልገው መልኩ በጥያቄ እያውጣጣና እያጣጣመ እሱ ግን እንደጲላጦስ ከደሙ ንፁህ ለመሆን እያመቻቸ ያቀርብላቸዋል:: ፍርድ ቤቱ ውስጥ የተቀመጡት ሰዎች ዓይኖች እሳት ሆነው የሚያቃጥሉ ቢሆን ኖሮ ጨርቄን አልፎ አጥንቴን አመድ ያደረገው ነበር፡፡ ሁሉም በሆዱ ያቺን የተማረች ምስኪን ጭካኔ በተሞላው መንገድ ስገድላት ይታየዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ጭካኔ ፈፅሞ እንዴት ራሱን አያጠፋም? አሁን ይህንን ሁሉ በደል ፈፅሞ ነፃ መውጣት ያምረው ይሆናል እኮ? አይገርምም! እያለ በውስጡ ሳያሰላስል አልቀረም:: አንዳንዱ ሩህሩህ ደግሞ “ ፊቱን እንኳን ሲያዩት ገዳይ አይመስልም፣ ግን ምን እንዲህ አስጨከነው? ምናልባት ማን ያውቃል የከፋ በደል አድርሳበት ሊሆን ይችላል" ብሎ አስቦም ሊሆን ይችላል:: ያም ሆነ ይህ እውነቱን ግን የምናውቀው እሱ አንድየ አምላክና እኔ ብቻ ነን። የእኔን እውነት ደግሞ የሚሰማ ወይም ለመስማት የሚጓጓ ጆሮ ተፈልጎ የሚገኝ አይደለም:: አምላክ ደግሞ በእውነት ውስጥ ሰርጾ እንጂ መቼም ቢሆን እንዲህ በገሀድ መሬት ወርዶ ስለማይመሰክር እውነት በአደባባይ እስከምትታይ ድረስ ዞሮ ዞሮ እውነት የሚባል ነገር ያው ሌሎች እንደሚያስቡትና እንደሚገምቱት በመሆኑ ወደድኩም _ ጠላሁም የእኔን ወንጀለኝነት መቀበል የግድ ነው፡፡ ብዙ የውሸቶች ዓይነቶች በሰፈኑባት በዚህች ዓለም ውስጥ ውሸቶች ተደጋግመው ሲሰሙ "እውነት" ይሆናሉ እንዲሉ፣ ጥቂቱ እውነት ካለም ወይ ይደበቃል ወይ ጠፍቶ ይቀራል፣ አሊያም ራሱ ውሸት ይሆናል።

ከአቃቢ ሕግ ምስክሮች መሃል የዶ/ር አድማሱ ስም ሲጠራ ክው ብዬ ደነገጥኩ፡፡ አዎ እዚህ ወንጀለኛ መቆሚያ ሳጥን ውስጥ መቆሜ የማይቀር መሆኑን ባውቅ ኖሮ መግባት የነበረብኝ ይህንን ሰው ገድዬ መሆን ነበረበት:: በፍቅራችን መሀል ገብቶ ለእኔና ለአልማዝ መለያየት ብሎም ለእሷ ሞትና ለእኔም እንዲህ መስቃየትና መንከራተት ከዚህ ሰው ውጪ ሌላ ቀዳሚ ተጠያቂና ምክንያት ሊኖር አይችልም:: ባለፉት ዓመታት ብዙ ግዜ ይህንን ከይሲ መበቀል እፈልግና ፈርቼ እተወው ነበር። ፍርሀቴና ስጋቴ ላለመታሰር ቢሆንም እነሆ ያሰብኩትን ሳልፈፅም ግን መታሰሬ አልቀረም:: እኔ ወኔ ኖሮኝ ልገድለው ባልችልም እሱ ግን ሁለት ጊዜ ገድሎኛል፡፡ በመጀመሪያ ፍቅሬን ነጠቀኝ፣ ቀጥሎም በዚሁ የተነሳ ወንጀለኛ ሳልሆን ወንጀል እንደሰራሁ ተቆጥሬ በማላውቀው ነገር ለእስር ዳረገኝ:: ይህ አልበቃ ብሎት ይኸው ደግሞ ዛሬ ቀሪውን የድህነትና የመከራ ሕይወቴን እንኳ በሰላም እንዳልኖር በሐሰት ሊመሰክርብኝ መጣ። ዶ/ር አድማሱ የሚመስክረው እውነትና እውነት ብቻ መሆኑንና ከእኔ ጋር ዝምድናም ሆነ ጠብ የሌለው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ቀርቦለት ከማለ በኋላ ውሸትና ውሸት ብቻ መናገሩን ተያያዘው፡፡ አቃቤ ሕጉ እንደተለመደው በልበ-ሙሉነት ቆሞ ጥያቄውን ይጠይቅ ጀመር። እኔ ወንጀለኛ መሆኔን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነገር ባገኘ ቁጥር ወደ ዳኛው እየዞረና ጥያቄውን ደጋግሞ እየጠየቀ ዳኛው ሳይስሙት እንዳያልፉ ለማድረግ ይሞክራል፡፡ “እሺ ዶ/ር አድማሱ እርሶ እሷን ወደ ቤት እየወሰዱ ሲያስጠኑ፣ እሱ እንደሚቀናና እርሶ ጋ እንዳትመጣ እንደሚጨቀጭቃት ከነገረችዎ ለመሆኑ ከእሱ ከተለየች በኋላ እንዳይበቀላት አትፈራም ነበር?"፡፡ ዶክተሩ የሚፈልገውን ጥያቄ ያገኘ ይመስል በጥድፊያ ከአፉ ላይ ቀበል
👍282
አድርጎ፣ “አዎ ትፈራ ነበር! እንዲያውም አንድ ጊዜ ደብዳቤ ዕፎ እንደሚገድላት እንደዛተባት፣ እየደወለም እንደሚያስፈራራት ነግራኛለች:: ደብዳቤውን እኔ ዘንድ ትታው ስለነበር ይዤው ለመምጣት ፈልጌ ለጊዜው ግን ላገኘው አልቻልኩም::'' “ሁኔታውን ለፖሊስ አላሳወቃችሁም?'' ብሎ አቃቤ ሕግ ሲጠይቀው፣ ዶ/ሩ በቀጣፊ ምላሱ፤ “አይ _ አላሳወቅንም፣ በጣም ይወዳት ስለነበር እንደዚህ ጨክኖ ይገድላታል ብለን ስላላሰብን ችላ አልነው፡፡ አሁን ነው ምን ያህል ስህተት እንደሰራን የተረዳሁት" ብሎ የአዞ እንባውን ማፍሰስና ዓይኑን በመሀረብ

መጥረግ ጀመረ። አቃቢ ሕጉ ለቅሶውን እስከሚጨርስ ጠብቆ ያለፈ ነገር አስታውሶ ላደረሰበት ሐዘን ይቅርታ ከጠየቀው በኋላ "ማለት ይህንን ሲሉ እሱ ነው የገደላት ብለው ያምናሉ ማለት ነው? በማለት ሲጠይቅ፤ ጠበቃዬ እጅግ በነቃ ስሜት ክቡር ፍ/ቤት ጥያቄው ላይ ተቃውሞ አለኛ አለ፡፡ ዳኛው ዕድሉን እሰጥሃለሁ በሚል ሁኔታ ራሳቸውን በመነቅነቅ ገለጹለትና የመቃወሚያ ምክንያቱን ሳይጠይቁ አቃቤ ሕግ ሌላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ አዘዙ:: አቃቤ ሕጉ ግን፤ “ጨርሻለሁ" ብሎ ተቀመጠ፡፡ ጠበቃዬ በቦታው ተተክቶ መጠየቅ ጀመረ። "ዶ/ር አድማሱ፤ ሟች ከተከሳሽ ጋር የተለያየችበትን ምክንያት ነግራዎት ታውቃለች?" “አዎን፤ ተከሳሽ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የቅናት መንፈስ ስለነበረበትና በሆነው ባልሆነው ሁሉ ስለሚጠረጥራትና ስለሚጨቀጭቃት፣ ይህ ልትታገሰው ከምትችለው በላይ ስለሆነባት ከእሱ መለያየቱን እንደመረጠች ነግራኛለች::" “ይህ እርሶ ከሟች ጋር በነበረዎት ቀረቤታ የተነሳ የተፈጠረ ይሆን?" “አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ግን በዚህ ብቻ ሳይሆን ከተማሪዎች ጋርም ለምን አየኋት ብሎ ይጣላ ነበር፡፡ እኔ በፊት አስተማሪዋ ስለነበርኩና ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች አንዳንድ ነገሮች ሲቸግሯት እረዳት ነበር፡፡ ልጅቷ የተለያዩ ችግሮች የነበሩባት በመሆኑና ድጋፍ ካልተደረገላት ያላት ከፍተኛ አቅም አላግባብ ሊባክን ይችላል ብዬ በመገመቴ እቤቴ ድረስ እየመጣች አስጠናት ነበር፡፡ በወቅቱ በእኔና በእሷ መካከል የነበረው ግንኙነት ከዚህ የዘለለ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ያው እሷ እንደነገረችኝ ከሆነ ተከሳሹ ከእሱ በስተቀር ከሌላ ወንድም ሆነ ሴት ጓደኛ ጋር እንድትሄድ ስለማይፈልግና ሁሌም ይቀና ስለነበር ለመለያየታቸው ብቸኛው ምክንያት ይህ ብቻ ባይሆንም አንዱ ምክንያት ግን ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ' አለ፡፡ ጠበቃዬም ይህንኑ መነሻ በማድረግ፤ “ከሟች ጋር ከዚህ ውጪ የፍቅር ግንኙነት አልነበረዎትም?'' ብሎ ሲጠይቅ አቃቤ ሕግ ጥያቄው አግባብ አይደለም በማለት ዳኛው እንዲያስቆሙ ጠየቀ:: ይሁን እንጂ ጠበቃዬ የጥያቄው መመለስ ያለውን ፋይዳ በማስረዳቱ፣ ዶ/ር አድማሱ ለጥያቄው መልስ እንዲሰጥ ዳኛው አዘዙ፣

“አዎ፣ እርግጥ ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት በመጀመሪያ የነበረን ግንኙነት በተማሪና አስተማሪነት እንጂ ከዚህ ውጪ አልነበረም። ወያ. መጨረሻ ላይ ግን አቶ አማረ ሌላ ሚስት ማግባቱን ከነገራት በኋላ ተረTEG ስለነበርና ራሷን ለማጥፋት በመፈለጓ እኔም የግድ ማዕናናትና መከታተል ስለነበረብኝ በተከታታይ እኔ ጋ እየመጣች አፅናናት ነበር:: ቀስ በቀስ በሁለታችን መካከል የፍቅር መንፈስ እያየለ በመምጣቱ ለመጋባት ወስንን ይሁን እንጂ ጋብቻችንን መፈፀም የፈለግነው ትምህርቷን ስትጨርስ ስለነበር ሳንጋባ ቆየን፡፡ ምን ያደርጋል ይኸው ህልማችን እውን ሳይሆን በመሃሉ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ተፈጠረ::" በማለት መለስ:: ራሴን መቆጣጠር እስከሚሳነኝ ድረስ መላ አካሌ በንዴት ተቀጣጠለ፡፡ ጠበቃዬ ጥያቄ መጨረሱን ለፍ/ቤቱ ገልጾ ተቀመጠ፡፡ ከዚች ደቂቃ በኋላ መኖር እንዳለብኝ ወሰንኩ። ቢያንስ አንዲት የነጻነት ቀን እፈልጋለሁ አንዲት ቀን ለብቀላ ታስፈልገኛለች፡፡ ቀጣዩ ምስክር ተሾመ ነበር። አፍ አውጥቼ አልናገር እንጂ MO አልማዝን ሊገድል ይችላል ብዬ ከምጠረጥራቸው ሰዎች አንዱ ተሸመ ነው፡፡ በእሷ ምክንያት ከትምህርት ቤት ስለተባረረና ድሮም ቢሆን ሌላ የምታገባ ከሆነ እገድልሻለሁ እያለ ይዝትባት ስለነበር እሱ የሚለውን ለመስማት ቸኮልኩ፡፡ ተሾመ ዓይኑን እኔ ላይ እንደተከለ ወደ ውስጥ ገባና እውነት ለመናገር ቃለ መሀላ ፈፀመ:: "እሺ አቶ ተሾመ፣ ከተከሳሽ ከአቶ አማረና አሟች ከወ/ት አልማዝ ጋር ትውውቅ ነበራችሁ?'' በማለት አቃቤ ሕጉ ጠየቀ፡፡ "አዎን ነበረን"። "ምን ዓይነት ትውውቅ ነበራችሁ?" "ከተከሳሽ ጋር ዩንቨርስቲ _ እያለን _ እንተዋወቅ ነበር፣ ሟችም ኤልሳቤጥ የምትባል የአክስቴ ልጅ ጓደኛ ስለነበረች እንቀራረብ ነበር'፡፡ የሰማሁትን ማመን አቃተኝ፡፡ ኤልሳ የጎረቤት ልጅ ነው እያለች ለአልማዝ የምትነገራት ለካስ የአክስቷን ልጅ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ተሾመ አልማዝን እንዲያፈቅር ሆን ብላ እየሰራች ነበር ማለት ነው፡፡ "ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም* ነው የሚባለው፡፡ ለማንኛውም ገና ብዙ የምሰማው ነገር ስለሚኖር ጆሮዬን አሹዩ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡

"እርሶ ከሟች ጋር የነበረዎት ግንኙነት የአክስትዎ ልጅ ጓደኛ カカパンチロチロ?" "አይደለም፤ ከዛ በላይ እሷ ባትወደኝም እኔ በጣም እወዳት ነበር። "እሷ ለምንድነው ልታፈቅርዎት ያልቻለችው?" "ይህንን መመለስ ቢያዳግተኝም፤ እንደሚመስለኝ ከተከሻስ ጋር ከፍተኛ ፍቅር ስለነበራት ለእኔ የሚሆን ትርፍ ቦታ አልነበራትም በማለት መልስ ሲሰጥ፣ ፍ/ቤቱ ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ መሳቅ ሲጀምር እኔም ላልወድ በግድ ፈገግ አልኩኝ:: "ዩንቨርስቲ እያላችሁ ከተከሳሽ ጋር በዚሁ የተነሳ ተጣልታችሁ ነበር ይባላል እውነት ነው?'' አለ አቃቤ ሕጉ፡፡ "አዎ፣ በዚሁ የተነሳ አንድ ቀን ወደ ከተማ በምወጣበት ግዜ ተአሣሽ ሳላስበው መትቶ ከጣለኝ በኋላ እየረጋገጠ ሊገድለኝ ሲል ሰዎች መጥተው አስጥለውኛል፡፡ "ሟች በተገደለችበት ዕለት እርሶ ከእሷ ጋር አምሽተው ነበር፤ ለመሆኑ እንዴት ልትገናኙ ቻላችሁ? " "እኔ ወደ እዛ አካባቢ እየሄድኩ ስለነበር፣ ወደ ተከራየችው ሆቴል ስትገባ በአጋጣሚ አየኋት፡፡ ዝም ብያት ለመሄድ ስላላስቻለኝ ተከትያት ገብቼ ስንገባበዝና ስንጫወት አመሽተን በሰላም ተሰናብቼያት ሄድኩ፡፡ ከዛ በኋላ በነጋታው ፖሊስ ለጥያቄ ሲጠራኝ ነው በሰው መገደሏን የሰማሁት" ብሎ ሲመልስ፤ አቃቤ ሕግ የሚፈልገውን በማግኘቱ "ጨርሻለሁ" በማለት መድረክ ለቀቀ፡፡ ጠበቃዬ በተራው ተነስቶ፣ "እሺ አቶ ተሾመ፣ ያው ቀደም ብለው እንደነገሩን ለሟች ፍቅር ቢኖሮትም እሷ ግን ለእርስዎ ፍቅር አልነበራትም፡፡ በዚህም የተነሳ ሌላ ብታገባ እንደሚገድሏት ይዝቱ ነበር ይባላል፡፡ ይህ እውነት ነው?" "አዎ፣ በጣም እወዳት ስለነበር እገድልሻለሁ ባልልም ከእኔ ውጪ ሌላ ብታገባ እንደምበቀላት አዝትባት ነበር፡፡ ይህ በጉርምስና ስሜት ምክንያት፣ ከእብደት ባልተናነሰ መልኩ ፍቅር ይዞኝ በነበረበት ወቅት አስፈራርቼ ወደ እኔ እንድትመጣ የማደርገው ጥረት እንጂ ሆን ብዬ በክፋት ከልቤ አስቤበት የምናገረው አልነበረም፡፡ እውነት የማደርገው ቢሆን ኖሮ ያኔ በእሷ ምክንያት ከግቢው ስባረር ባደረኩት ነበር"፡፡

"ታዲያ እንዲህ የሚዝቱ ከነበረና ከሚች ጋር አብረው ያመሹ ከሆነ ያንን ዛቻዎትን ላለመፈጸምዎ ምን ማስረጃ አለዎት?"

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍526👏1
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_18


“ታዲያ እንዲህ የሚዝቱ ከነበረና ከሟች ጋር አብረው ያመሹ ከሆነ ያንን ዛቻዎትን ላለመፈጸምዎ ምን ማስረጃ አለዎት?” "በመጀመሪያ ደረጃ ያኔና ዛሬ የተለያዩ ጊዜያቶች ናቸው። ያኔ በየዋህነት ያበላሸሁትን ህይወቴንና በዛ ምክንያት የደረሰብኝን ስቃይ እንኳንስ ልደግመው ላስበውም አልፈልግም፡፡ እኔ ዛሬ በጣም የምወዳት እጮኛ የአለችኝና የራሴን ቤተሰብ መስርቼ የተደላደለ ኑሮ ለመኖር የሚስችለኝ ገቢ ያለኝ ሰው ሁኜ ሳለ፤ ያ በወጣትነት ዘመን የነበረው የአፍላነት የፍቅር ስሜት ገፋፍቶኝ በቂም በቀል ህይወቴን የማበላሽበት ምክንያት በፍፁም የማይታሰብ ነው፡፡ ወደ ተጠየቅሁት ጥያቄ ለመመለስ፤ የዛን ዕለት ከእሷ ጋር በሰላም ስንጫወት አምሽተን በሰላም ተለይቼ እንደሄድኩና ከዛ በኋላ ችግሩ እንደተፈጠረ አስተናጋጁ በግልጽ አይቷል፡፡ ፖሊስም ባደረገው የማጣራት ሥራ እኔ ነፃ መሆኔን በማረጋገጡ ለቆኛል" በማለት መለሰ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠበቃዬ እጅግም የማይረቡ ጥያቄዎችን ብቻ ጠይቆ አመሰግናለሁ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ሌላው ቀርቶ አልማዝ ወደነበረችበት አልቤርጎ ድረስ ሄዶ መልዕክት እንዲነግር ኤልሳ እንደላከችው ዲያሪው ላይ አንብቦ ላለ ይህንን እንኳን ለመጠየቅ አልፈለገም፡፡ ዳሩ እሱ እጮኛውን የሚያስወነጅል ጥያቄ እንዲጠይቅ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ውሸት በውሸት ላይ ሲደራረብ በመስማቴ ወንጀሉ እዚህ አካባቢ ተፈፅሟል የሚል ጥርጣሬዬ እየጠነከረ መጣ። ቀጥሎ ለምስክርነት የተጠራው የሆቴል ቤቱ አስተናጋጅ ነው፡፡ የአስተናጋጁን የምስክርነት ቃል ስሰማ በጣም ደነቀኝ፡፡ ተሾመ እሷን ተሰናብቶ ከሄደ በኋላ አንድ ቢራ እንዲያመጣላት ሟች አዝዛው ስለነበር ይህንኑ ይዞ ሲሄድ እኔ ተካሳሹ አብሬ ተከትዬ እንደመጣሁና ለእሱ በሩን ስትከፍት እኔ ገብቼ ከውስጥ በሩን መቆለፌን፡፡ እሱም በሁኔታው ተጠራጥሮ በር አንኳክቶ ሟችን ችግር ይኖር እንደሆን እንደጠየቃትና ከገባውም ሰውዬ ጋር እንደሚተዋወቁና ችግር እንደሌለ ስለነገረችው ጥሎ መሄዱን አስተናጋጁ መሰከረ፡፡ በጣም _ የሚገርመው ግን አንድ ጊዜ ብቻ ካየኝ እንዴት በእርግጠኝነት እኔ መሆኔን ሊያውቅ እንደቻለ ሲጠየቅ፣ ቀኑን በሙሉ እየተመላለስኩ መምጣትና አለመምጣቷን እጠይቅ ስለነበር እንደማይረሳኝና፤ ሟች ከተሾመ ጋር እየተጫወተች ሳለ አንድ ጥግ ቦታ ላይ ተቀምጬ ስከታተላቸው እንደነበር መሰከረ፡፡ ከዛም በኋላ ትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ የእኔና የእሷ ሦስት ጓደኞች በየተራ እየተጠሩ ሲመሰክሩ የአንዳንዶቹ ለስለስ ይበል እንጂ ምስክርነታቸው የእኔን ነፃነት ከማረጋገጥ ይልቅ ወንጀለኝነቴን የሚያጠናክር ነበር። ሁሉም በጣም እንዋደድ እንደነበርና በኋላ ግን ሟች ከዶ/ር አድማሱ

ጋር በፈጠረችው ቅርርብ የተነሳ እኔ በከፍተኛ ሁኔታ እተና እንደነበር መሰከሩ። ስለዚህም ቅናቴ ለመግድል የሚያነሳሳ ስለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ አልነበራቸውም:: በእነሱም ግምት ሟች ጥሩ ጠባይ የነበራትና ከማንም ሰው ጋር ተጣልታ የማታውቅ በመሆኑ ይህንን ይፈፅማል ብለው የሚጠረጥሩት ሌላ ሰው እንደሌለ መሰከሩ:: ይህ ሁሉ ታዲያ የእኔን ወንጀለኝነት የሚያጠናክር እንጂ የሚያቀል አልነበረም:: ዳኛው ጠበቃዬ የመከላከያ ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ለሚያዚያ 5 ቀን 1981 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተው አሰናበቱን:: በዚያችው በተለመደች እሥር ቤት ውስጥ በተለመደው መልኩ ኑሮዬን ለመቀጠል ከፍርድ ቤቱ ወጣሁ:: እስር ቤት እንደገባሁ እራሴ እስኪፈነዳ ድረስ ሰው ሳላናግር ጥግ ቦታ ላይ ቁጭ ብዬ የተሰጡትን የምስክርነት ቃሎች አንዱን ከአንዱ ጋር በማዛመድና በመተንተን የሴራውን ምንነት ለማወቅ መጣር ጀመርኩ፡፡ በእርግጥም እኔን ለመወንጀል ዲያሪው ላይ ከሰፈረው ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ ቅንብር እንደተሰራና ይህንንም እውነት ለማስመሰል አስተናጋጁ ተገዝቶ ሊመሰክር እንደመጣ እርግጠኛ ሆንኩ፡፡ ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ በተሾመና በኤልሳ ተቀነባብሮ በጠበቃዬ አማካሪነት የመጨረሻ ቅርፁን የያዘ ሴራ ነው፡፡ እንደሚመስለኝ ኤልሳ _ ሆን ብላ ከተሾመ ጋር በመመካከር፣ እኔን እንዳገኘች በማስመሰል ደብዳቤ ፅፋ አልማዝ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ካደረገች በኋላ ተሾመ እንዲያገኛት ወደ ሆቴሉ የላከችው እሷ ራሷ መሆን አለባት፡፡ ምናልባት ለክፋት ሳይሆን ከእኔ መለያየቷን ስለምታውቅ እና ዶ/ሩን ከምታገባ ከአክስቷ ልጅ ጋር እንድትጋባ ለማድረግ ብላ ያደረገችው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንንም ትምህርት ቤት ውስጥም ስታደርገው ስለነበር አሁን አታደርገውም ማለት አይቻልም፡፡ እንግዲህ አጅሬ እዚያ ሄዶ ዕድሉን ይሞክራል፡፡ ነገር ግን አሁንም ያው የለመደው መጥፎ አቀባበል ሲገጥመው፣ ጥንትም እንደዛተው በንዴት መኝታ ቤቷ ውስጥ ገብቶ ገድሏት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ኤልሳም በተባባሪነት ልትወነጀል ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም መዋሸት አለባቸው፡፡ እነሱ ነፃ እንዲወጡ ደግሞ የግድ አንድ ሰው መወንጀል አለበት፡፡ ያም ሰው ሌላ ሰው ሳይሆን እኔው ነኝ ማለት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ተከራክሬ ነፃ እንዳልወጣ እነሱ ለእኔ ተከራካሪ ሆነው ቀርበው እውነትን ማዳፈን ነበረባቸውና ይህንኑ ለማሳካት በመፍጨርጨር ላይ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አሁን የማየው የይስሙላ "ተጠየቅ ልጠየቅ" እኔንና ሌላውን ለማሳመን የሚደረግ ትርዒት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡

ቀደም ሲልም ህሊናዬን አንዳች ነገር አሳውሮት ነው እንጂ፣ ኤልሳ እኔ መታሰሬን እንዴት አውቃ ጥብቅና ልትቆምልኝ መጣች? ብዬ መጠራጠርም ነበረብኝ፡፡ እንዲያውም ሊሆን የሚችለው እኔን ጠቁመው ካስያዙ በኋላ ጥብቅና በመቆም ሀቅን አዳፍኖ ለማስቀረት የነደፉት የረቀቀ ሴራ ነው፡፡ እንግዲህ ሴራው ይኼ ከሆነ ደግሞ አራጆቹን ተከትሉ እንደሚሂድ በሬ ሆኛለሁ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ወጥመድ ለመውጣት ደግሞ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ብገነዘብም ምን ላደርግ እንደምችል ግን አንዳችም መፍትኄ ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ ጊዜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር _ አለሚቱ አለፍ አለፍ እያለች መምጣቷ ቀርቶ እጅግ እየዘገየች ብቅ ማለት ጀመረች፡፡ የቤቱን ዕቃ በየተራ እየሸጠች ለራሷም ሆነ ለእኔ የሚያስፈልገንን ነገር እንድታደርግበት ነግሬያታለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የሚሸጠው ነገር ቀስ በቀስ እየሳሳ በመምጣቱና እኔም እንዲህ በቀላሉ እንደማልፈታ ስለተገነዘበች በቁጠባ መጠቀሟ ነበር:: አልፎ አልፎ የመስሪያ ቤት ባልደረቦቼ እየመጡ ገንዘብ ሲሰጡኝ ያቺኑ ሰብስቤ የምሰጣት ቢሆንም፤ ይህም ለእኔና ለእሷ ቀለብ ሆኖና የቤት ኪራይ ለመክፈል የሚበቃ ስላልነበር አጠቃቀሟን መቆጠቧ አግባብነት ነበረው:: ጓደኞቼ እየመጡ ቢጠይቁኝም ነፍሰ ገዳይ አድርገው ስለሚመለከቱኝ ሳይሆን አይቀርም በአንዳቸውም ፊት ላይ የሀዘን ስሜት አላይም፡፡ ሁሉም ሰው ፍቅረኛውን እንደገደለ ቀናተኛ አፍቃሪ እንደሚገምተኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ እያንዳንዱ ስለእኔ ያለው ግምት እንዲህ ይሆናል፣ እንደዚያ ይሆናል ብዬ ከመገመት ውጪ ከሌሎች የምሰማው ነገር አልነበረም፡፡ በአንጻሩ የእሥር ቤት ጓደኞቼ እስከዚህም ስለዚህ ጉዳይ ለማወቅ የሚጨነቁ አልነበሩም፡፡ መግደል ምን እንደሆነና ምን ያህል ሊያጋጥም የሚችል ቀላል ነገር መሆኑን አብዛኛዎቹ አይተውታል፤ ያላዩትም ደጋግመው ሰምተውታልና አይደንቃቸውም:: ያልገደለ ቢኖር እንኳን ያው በሥርቆት የተያዘው ነው:: ከእነርሱም ውስጥ ከፊሉ ጥሩ አጋጣሚ ካጋጠመውና ብዙ ገንዘብ የሚያገኝበት ዕድል ካገኘ ለመግደል ወደ ኋላ የሚል አልነበረም፡፡ እዚህ በተወሰኑ ሰዎች ዘንድ ሰው ገደለ የሚለው ቃል
👍422
በላ ወይም ጠጣ እንደሚለው ተራ ነገር ነው የሚታየው:: ስለዚህ ስለእኔ መግደል የሚጠራጠር ባይኖርም ስለሁኔታው ለማወቅ ግን የሚጨነቅ አልነበረም:: አብዛኛው ይህንን እንደ ተራ ነገር ስለሚመለከተውና ስለእኔ እስር መነሻ ለማወቅ የሚያስጨንቀኝ ባለመሆኑ ደስተኛ ነኝ:: ከዚህ ውጪ ለእኔም ቢሆን ንጽሕናዬን ለሌላው ለማሳየት ከመጨነቅ ይልቅ እንደገደልኩ አምኜ ማሳመኑ ይቀለኝ ነበር። -148-

ጠበቃዬ እየጣረ ያለው እኔን ነፃ ለማውጣት ይሁን ወይም እስሬን ለማጠናከር ባይገባኝም፣ በየቀኑ አዳዲስ የቤት ሥራ ይዞ ይመጣል:: ለግማሹ ከእኔ መልስ የሚያገኝ ሲሆን ለቀሪው ደግሞ ዲያሪውንና ደብዳቤውን እያነጻጸረ ማስረጃ ሲሰበስብና ሲያጠናቅር ይውላል:: ይህን የሚያደርገውን ጥረት ላይ ደግሞ ጥርጣሬዬ የተሳሳተ ይሆን እንዴ ማለቴ አልቀረም። በእርግጥ ጠበቃዬ ለዚህ ድካሙ ከእኔ የሚያገኘው ምንም ነገር አልነበረም:: በእርግጥም ለእኔ ነፃነት ሲል እየደከመልኝ ከሆነ ግፋ ቢል ሊሆን የሚችለው ሂደቱን በሽንፈት ሳይሆን በማሸነፍ ከደመደመው ለእጮኛው ያለውን ፍቅር ሊገልፅላት የሚችልበት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወንጀላቸውን ለማዳፈን እየጣረ ከሆነ ግን እጮኛውን ከአደጋ ማዳን በመቻሉና ከፊቱ የተጋረጠውን አደጋ በማስወገዱ የሚያገኘው እርካታ ብቻ ነው:: ያም ሆነ ይህ፤ እኔ አሁን ላደርገው የምችለው ነገር ስለሌለ፣ ለክፉም ይሁን ለደግ የፈለገው ጉዳይ እስኪሳካለት ድረስ ላግዘው ወሰንኩ፡፡ ሌላው ቢቀር ከእኔ የሚፈልገው እውነቱን ማወቅ ነውና እውነቱን በመንገር ልተባበረው አሰብኩ፡፡ ከራሴ አንፃር ግን በክርክሩ ቢያሸንፍም ቢሸነፍም ለእኔ ደንታዬ አልነበረም፡፡ ለእኔ ውጪውም ሆነ እሥር ቤቱ ከአሁን በኋላ ለውጥ የለውምና! ለሱ ግን ማሸነፍም _ ሆነ _ መሸነፍ ትልቅ ትርጉም እንዳለው በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ:: አንድ ቀን ጠበቃዬ መረጃ ካገኘሁ በማለት በጥያቄ ሲያዋክበኝ ከቆየ በኋላ ተሰናብቶኝ እንደወጣ፣ በውስጤ ተቀብሮ የሚከነክነኝ ነገር ውጤት ቢኖረውም ባይኖረውም ተንፍሼው መገላገል አለብኝ ብዬ በመወሰኔ ፖሊሱ እንደገና እንዲጠራልኝ ነገርኩት፡፡ ጠበቃዬ ተመልሶ ፊት ለፊት ተቀምጦ ምን ሊነግረኝ ይሆን እያለ ዓይን ዓይኔን ሲያይ፣ "ይቅርታ ደግሜ አስጠራሁህ፡፡ በውስጤ ተቀብሮ የሚከነክነኝ ነገር አለ፡፡ ነገር ግን እርግጠኛ ባልሆንኩበት ነገር ሰውን መጠርጠር ኃጢያት ነው ብዬ ስላሰብኩ መናገር አልፈለኩም ነበር፡፡ በቀደም ተሾመ ሲመሰክር ልብ ብለህ ሰምተኸው ከሆነ ዩንቨርስቲ እያለሁ በአልማዝ ምክንያት ተጣልቼው ነበር፡፡ እሱ እያለ አልማዝን ከእሱ በስተቀር ማንንም ማግባት እንደማትችልና ይህ ሆኖ ቢያይ ግን እንደሚገድላት ይዝት ነበር፡፡ አልማዝ ከእሱ ጋር ከተደባደብኩ በኋላ ዳግም እንዳንጣላ በማለት ለእኔ ባትነግረኝም፤ እኔ እያለሁም ሆነ ከዩንቨርስቲ ከተባረርኩ በኋላ ማለትም፣ ከዶ/ር አድማሱም ጋር ሆናም፣ ከእሱ ከተሾመ ውጪ ሌላ ብታገባ እንደሚገድላት ይዝት እንደነበር ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ምናልባት ገድሏት ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለኝ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአልማዝ ዲያሪ ላይ እንደተፃፈው አልማዝ ወደ ክፍለ ሀገር መሄዷን ያረፈችበት ሆቴል ድረስ ሄዶ እንዲያገኛትና ሲያጫውታት እንዲያመሽ ተሾመን የላከቺው ኤልሳ ነች፡፡ እሱም እዛ ከደረሰ በኋላ በመጀመሪያ አለሳልሶ ከቀረባት በኋላ ቀስ በቀስ የድሮውን እወድሻለሁ የሚል ንዝንዙን በመጀመሩ ጥላው ወደ አልቤርጎው መኝታ ክፍሏ ገብታለች፡፡ እሱ ግን የዛን ቀን አልማዝን በአጋጣሚ እንዳገኛት እንጂ ኤልሳ እንደላከችው አልተናገረም፡፡ በዚህ ላይ አስተናጋጁ በገንዘብ ተገዝቶ እንጂ እኔን በምንም ተአምር እዛ ሊያየኝ አይችልም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ውሸት ጀርባ አንድ የተደበቀ ወንጀል አለ ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ ምናልባት የሚጠቅምህ ከሆነ ብዬ ነው?" አልኩት፡፡ ጠበቃዬ እንደመሳቅ እያለ፤ "አቶ አማረ፣ ሰውን መጠርጠር ኃጢያት ነው የተባለው የትኛው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነማ እኛና ፖሊስ የማንጠረጥረው ሰው ስለሌለ ተጠራርገን ሲዖል መግባታችን ነው ማለት ነው፡፡ መጠርጠር ማለት መወንጀል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ ጠቃሚ መስሎ ከታየህ እስከአሁን ሳትነግረኝ መቆየትህ ትክክል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ አሁን የሰጠኸኝ መረጃ የሚጠቅም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ፖሊስ ከዲያሪው ላይ ካገኘው መረጃ በመነሳት አንተ ከመታሰርህ በፊት መጀመሪያ በጥርጣሬ የያዘው እሱን ነበር፡፡ ነገር ግን ወንጀሉን መፈጸሙን የሚያሳይ ምንም መረጃ ሳላላገኘ ይልቁንም ንጹህነቱን የሚያረጋግጥ መረጃ ሰጥቶ ለቆታል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተል የጥርጣሬው ሚዛን ወደ አንተ በማጋደሉ አንተን ወደ መያዙ ተኬዷል፡፡ ነገር ግን እኔም ብሆን የተሾመን ንፁህነት አረጋግጧል የተባለው መረጃ ምን እንደሆነ ስለማላውቅና ማረጋገጥ ስላለብኝ ለማጣራት እሞክራለሁ" ብሎ ትከሻዬን መታ መታ አድርጎ ተሰናብቶኝ ወጣ፡ እኔ በእርግጠኝነት ከዚህ ወንጀል ጀርባ ተሾመ ይኖርበታል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ግን እንዴት? የት? መቼ? ተብዬ ብጠየቅ የምመልሰው አይኖረኝም፡፡ ይህንንም እምነቴን አፍኜ ቆይቼ ለጠበቃዬ ስነግረው ይደሰታል ብዬ ብገምትም እሱ ግን ይህንን ከቁብ አልቆጠረውም፡፡ ያ ማለት ደግሞ ክርክሩ ለይስሙላ ካልሆነ በስተቀር የሚፈይደው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ላደርገው የምችለው ነገር ስለሌለ ተስፋ ቆርጬ የእስር ቤት ህይወቴን ማጣጣሙን ተያዝኩት፡፡ እስር ቤት ውስጥ ሁሌ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች የሆኑ አዳዲስ ቀልዶች ስለሚቀርቡ በተለይ ምሽቱ ይናፍቀኛል:: በየዕለቱ የሚገባው አዳዲስ እስረኛ የየራሱን ተውኔት ይዞ ስለሚቀርብ ራሱን የቻለ የማይከፈልበት መዝናኛ ነው:: አንዳንዱ ዘፈን ሲዘፍን የሚያወጣውን ድምፅ ሲሰሙት ይህንን ድምፅ ይዞ ከሚሰርቅ ምነው ዘፍኖ ቢበላ ያሰኛል::

አንዳንዱም ድራማ ሲሰራና የተዋጣለት አርቲስት ሆኖ ሲቀርብ አፍH ያስቀራል:: ባጠቃላይ እዚህ የሌለ ነገር ማግኘት ሳያስቸግር አይቀርም:: በተለይ አንድ ሀሚድ የሚባል እስረኛ "ሰበርታ" የሚለውን የሱዳን ዘፈን ሲጫወት መስማትን የማይናፍቅ እስረኛ አለ ማለት ይቸግራል፡፡ ሁሌ ይዘፍንልናል ግን ሁሌም ደጋግመን ስንሰማው አዲስ ይሆንብናል፡፡ ምናልባት ሬዲዮ ስለማንሰማና ቴሌቪዥን ስለማናይ ዘፋኝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠፍቶብን ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንድ ሰኞ ለት ካቦአችን አየለ እና አፀላያቺን አለሙ የሚፈቱበት ቀን ስለነበር በቤቱ ውስጥ ድብርት ሰፈነ:: በየተራ የሚፈቱ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ባልተጨነቅን ነበር፡፡ ካቦአችን የስንቱን እስረኛ የተለያየ አመል ችሎ እንደ መልካም አስተዳዳሪ እስር ቤቱን ሲያስተዳድር የነበረ፣ ተጫዋች፤ ተግባቢና አዝናኛችን በመሆኑ እሱን ማጣት ለሁላችንም ትልቅ ጉዳት ሲሆን፣ የሁላችንም የመንፈስ አባት የሆነው አፀላያችን አብሮ መፈታት ደግሞ ለእስረኛው ትልቅ ድንጋጤና ሐዘንን መፍጠሩ አልቀረም፡፡ በመፈታታቸው ደስ ቢለኝም እነሱ ከሄዱ በኋላ ግን እስር ቤቱ እንደ ድሮው ሊሆንልኝ አልቻለም፡፡ በተለይ አለሙ እንደሚፈታ በእርግጠኝነት ተናግሮ ሄዶ እንደተናገረውም ተፈታ፡፡ እንደሚፈታ እንኳን እሱ ልምድ ያለው እስረኛ ቀርቶ እኔም አውቄ ነበር። ምክንያቱም ወንጀለኛ ቢሆንም ማስረጃውን በልቶታልና፡፡ ይህ አስደናቂ ጓደኛዬ የተከሰሰው በፎርጂድ ብር ነበር። ከትክክለኛ ብር መሀል ፎርጅድ ብሮችን እየቀላቀለ እቃ ሲገዛና ሲዘረዝር ተይዞ ነበር የታሰረው:: የሚገርመው በተያዘበት ዕለት ከእስር ቤት ወደ ምርመራ ክፍል ይጠራል:: ፖሊሱ
👍263
በኤግዚብትነት የያዘበትን አንድ ባለ መቶ ብር ኖት ይዞ እውነተኛ ቃሉን እንዲሰጥ ይጠይቀዋል:: አጅሬ ግን ልምድ ያለው በመሆኑ እውነቱን ሊያወጣለት ስላልቻለ ሊያስፈራራው በማሰብ በኤግዚቢትነት የተያዘውን ፎርጅድ ብር ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ መግረፊያ ሊያመጣ ይሄዳል፡፡ ከዚያ እንደተመለሰም ኮቱን እንዲያወልቅ ይነግረዋል:: አጅሬ ኮቱን አውልቆ ጠረጴዛ ላይ በነበረው ብር ላይ ጣል ያደርገዋል:: ከዛም መርማሪው ወደ ጓዳ አስገብቶ ለማስፈራራት ያህል አንድ ሁለቴ ሾጥ ሾጥ እየደረገ እውነቱን እንዲያወጣ ለማድረግ ቢሞክርም ሊሳካለት ባለመቻሉ፤ “በል ውጣ! በኋላ ዋጋህን ታገኛለህ፡፡ ብታምን ግን ቶሎ ተፈትተህ ወደ ቤትህ እንድትሄድ አደርግ ነበር" ብሎ ያሰናብተዋል፡፡ አጅሬ ኮቱን ሲያነሳ ፎርጅድ ብሩንም በዘዴ አብሮ አንስቶ ይዞ ይወጣና ወደ እሥር ቤት እየሄደ ሳለ ደብቆ የያዛትን ፎርጅድ ብር ጨባብጦ አፉ ውስጥ ይከትታል፡፡ በምራቅ እንደራሰችም በዝግታ አላምጦ ይውጣታል:: መርማሪው ትንሽ ቆየት ብሎ

ብሩን እንዳላነሳ ትዝ ይለውና ጠረጴዛው ላይ የተወው መስሎት ይፈልጋል! ግን ሊያገኘው አልቻለም:: ፖሊስ ጣቢያውን በሙሉ በልዩ ልዩ ሁኔታ ቢፈትሽና ቢያስፈትሽም ያጣዋል:: ከዚያም ከዓለሙ ውጪ ሌላ ሰው ስላልገባና ከእሱ ውጪ ሌላ ሰው ሊወስደው የሚችል የለም በማለት በንዴት ወደ እስር ቤት ይሄዳል:: እንደገባም እርግጠኛ እንደሆነ በሚያሳይ ሁኔታ የወሰደውን ኤግዚቢት እንዲያመጣ ይጠይቀዋል:: አጅሬ ግን ዓይኔን ግንባር ያድርገው አላየሁም ይላል:: እስረኞቹና እስር ቤቱ በሙሉ ምንጥር ተደርጎ ይፈተሻል፡፡ ነገር ግን ገንዘቡ የገባበት ሊታወቅ አልቻለም:: መርማሪው እንደተናደደ እስረኛውን ወስዶ ደህና አድርጎ እየገረፈ ለማስፈራራት ቢሞክርም አጅሬ ፍንክች የሚል አልሆነም:: በመጨረሻ መግረፉ ሲደክመጡ እስር ቤት ውስጥ ይወረውረዋል:: በነጋታው ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረበትና ይቀርባል፡፡ አጅሬ ልብሱን አውልቆ “ጌታዬ፣ በግል ቂም በቀል ከመንገድ ላይ ያለምንም ጥፋቴ አስሮ ሲቀጠቅጠኝ አደረ፡፡ ይኸው ገላዬን ይመልከቱት" ብሎ በግርፋት የቆሰለውን ሰውነቱን ማሳየት ይጀምራል:: ዳኛው ባዩትና በሰሙት ነገር እጅግ ተናደው፣ “ምነው መርማሪ፤ ፖለቲካ ውስጥ የሌለ ተራ እሥረኛ እንዴት እንዲህ አድርገህ ትደበድባለህ፡፡ ለመሆኑ ለምንድነው የመታኸው?'' ብለው ይጠይቁታል፡፡ “ጌታዬ ይህ ግለሰብ እጅግ በጣም አደገኛ ወንጀለኛና በተደጋጋሚ ተፈርዶበት ታስሮ የተፈታ ነው፡፡ በፎርጅድ ይዤው እየመረመርኩት ሳለ ስለተናነቀኝና በቀላሉ ሊለቀኝ ስላልፈለገ ነው የመታሁት" ይላል :: ዳኛውም አለኝ የሚለውን ማስረጃ ይዞ እንዲመጣ ነገር ግን በተደጋጋሚ ወንጀል እየሰራ የታሰረ ስለሆነ ሳይፈታ ወህኒ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ይወስናሉ፡፡ መርማሪው እንደተባለው በሳምንቱ ሊያቀርበው የሚችል መረጃ ስላልነበረው እስረኛውን ለሁለት ወር ደብቆ አስቀመጠው:: ከሁለት ወር በኋላ ሀላፊዎች እየተዘዋወሩ እስር ቤቱን በጎበኙበት ወቅት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ይህንን ያህል ጊዜ መታሰሩን አስመልክቶ አቤቱታ በማሰማቱ፣ አዛዦቹ በሰጡት ጥብቅ ትዕዛዝና ማስጠንቀቂያ ወደ ፍርድ ቤት ቀረበ። መርማሪው ግን ፍርድ ቤት የሚያቀርበው መረጃ አልነበረውም፡፡ ዳኛው መርማሪውን መረጃ እንዲያቀርብ ሲጠይቁት “መረጃውንም ስርቆታል ብሎ ሲናገር፣ ፍርድ ቤቱ ውስጥ የነበረው ሰው ሁሉ በሳቅ ፈነዳ። ዳኛው በመገረም፤

“መረጃውንም ሰረቀ ነው የምትለው? የሚገርም ነገር ነው፡፡ ለመሆኑ እንዴት መረጃውን ሊያገኘው ቻለ? ነው ወይስ አደራ እንዲያስቀምጥልህ ሰጥተኸው ነበር?" በማለት ቤቱን በሳቅ ላይ ሳቅ ደረቡለት:: መርማሪው ደንግጦ ከመቆም ውጪ ይህ ነው የሚባል የረባ የመከራከሪያ ነጥብ ሊያቀርብ ባለመቻሉ ዳኛው እስረኛውን በነፃ አሰናበቱት:: "አይ ይህቺ የምትገርም ዓለም" አልኩ:: በአብዛኛው ለአጭበርባሪ እንጂ ለንፁሃን ስታደላ አትታይም፡፡ ግን በአንድ በኩል ደግሞ እሱ ንፁህ ሰው ነው ብዬ ራሴን አሳመንኩ:: ሲፀልይና ሲያፀልየን ከልቡ መሬት ላይ ተደፍቶ ነው፡፡ አምላኩን እንዲያስፈታው ሲለምንም ከልብ አምኖና እንደሚያስፈታው ሳይጠራጠር ነው:: እንደእኔ በከፋው ቁጥር አምላኩን አያማርርም ወይም መኖሩን አይጠራጠርም:: አንዴ ትዝ ይለኛል ፀሎት ሲፀልይ አየሁና አፀላለዩ ገርሞኝ፣ “ስማ እንጂ ዓለሙ፤ እንደዚህ እየሰረቅህና ወንጀል እየሰራህ፣ እንዲህ ተመስጠህ ከልብህ ጌታን የምትለምነው ይሰማኛል ብለህ ነው? ባይሆን እንኳን ሌብነትህን እርግፍ አድርገህ ትተህ ቢሆን ኖሮ ሊሰማህ ይችል ይሆናል'' አልኩት፡፡ እሱም በእኔ እንደመገረም እያለ፤ “አይ አማረ _ ለካ _ የዋህ ነህ፡፡ ምን መሰለህ፤ ጌታ ኃጢያተኛ መሆናችንን ያውቃል፣ ግን ከልብ አምነንና አዝነን ከለመነው ይቅርታ ያደርግልናል፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ ወንጀል እየሰራሁና እየሰረቅሁ ተይዤያለሁ፡፡ ግን ሁል ጊዜ የምፈታበትን መንገድ እሱ ያመቻችልኛል፡፡ ጌታ መሐሪ ነው፡፡ እንኳን እኛን ቀርቶ ሰባ ነፍስ ያጠፋውን በላየሰብ "ስለመቤቴ ውሀ ስጠኝ" ላለው ሰው ጠብታ ውሀ በመስጠቱ በማርያም አማላጅነት ይቅር ብሎታል" ያለው ትዝ ይለኛል፡፡ እንዳለውም ጌታ ከእኛ ከንፁሃኑና በሱ ላይ የሳሳ እምነት ካለን ይልቅ፣ ወንጀል እየፈፀሙም ቢሆን በሱ አምነው ከልብ ይቅርታ ለለመኑት ያደላልና ይኸው ነፃ እያወጣቸው ነው:: የእነዚህ እስረኞች መፈታት ባይገርመኝም ወንጀለኛው ሲፈታና ንፁህ ሰው እስረኛ ሆኖ ሲቀር ማየቴ ግን አሳዘነኝ፡፡ የእውነት እንዲህ መሸፈንና የጌታም "ኢፍትሀዊ" መሆን አስደነቀኝ:: ይህንን ሳስብ አንድ ሁሌ የሚደንቀኝ ነገር ትዝ አለኝ:: እኛ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች በድህነት የሚማቅቁ ሀገራት ሕዝቦች፣ በሀብት ብዛት ከሚንደላቀቁ _ ሀገራት ሕዝቦች እጅግ በተለየ መልኩ ሀይማኖታችንን እናጠብቃለን፡፡ ሁሌ በችግር ውስጥ ሆነንም ቢሆን "ተመስገን አምላኬ" ሳንል አንተኛም:: ነገር ግን በበለፀጉ ሀገራት የሚኖር ህዝቦች ሀይማኖት የላቸውም ባይባልም እንዲህ እንደኛ ጥብቅ አድርገው ለሀይማኖታቸው ሳይጨነቁ

በተቃራኒው ሀብትን በሀብት ላይ፣ ደስታን በደስታ ላይ እየጨመረላቸው ተንደላቀው ይኖራሉ፡፡ እኛ ያመለጠን ወይም የተረፈንን ቅንጣት ምግብ ከእጃችን ቢወድቅ፤ አፈሩን አራግፈን፤እፍ ብለንና ስመን "የምግብ ጡር አለው" በማለት ግፍን ፈርተን ስንጠነቀቅ፣ እነሱ ግን በተረፋቸው ምግብ ላይ ሲጋራ ተርኩሰው፣ በሚበሉት ቸኮላት ቤት ሰርተው እያስጎበኙና በቲማቲምም እየተደባደቡ የምግብ ጡር አይነካችውም፡፡ ይልቁንም ምግብ በምግብ ላይ እየተከመረላቸው በረሀብ ሳይሆን በጥጋብ ይሞታሉ፡፡ እንዲያውም ከእነርሱም አልፎ ተርፎ ለእኛም ይበጁናል:: እኛ ግን በአንፃሩ የምንከባከበው ምግብ ፊቱን ሳይሆን ጀርባውን ሰጥቶን በረሀብ እንረግፋለን፡፡ ታዲያ እንደኔው ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእግዚአብሔር "ኢፍትሃዊነት' አልዋጥ ያላት አንድ ፈረንጅ ሀገር ተወልዳ ያደገች ኢትዮጵያዊት ታሪክን ስሰማም መገረሜ አልቀረም:: ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ቤተሰቦቿ ውጪ ሀገር እያለች አማርኛ እንዳትረሳ በማለት ሁል ጊዜ በአማርኛ እንድትፀልይ ያደርጋሉ፡፡ እሷም ምክንያቱ ባይገባትም እናትና አባቷን ለማስደሰት ስትል በእነዚያ አይታቸው በማታውቃቸው ሰዎች ቋንቋ እየተንተባተበች ትፀልያለች፡፡ ነገር ግን ጠዋትና ማታ በማታውቀቸው ህዝቦች ቋንቋ የምትፀልይበትን ምክንያት ለመረዳት ወላጆችዋ አገርሽ የሚሏትን አገር ካላሳይዋት በስተቀር ሁለተኛ በዛ ቋንቋ እንደማትፀልይ ማስፈራራት ስለጀመረች ሳይወዱ በግድ ትምህርት ቤት ሲዘጋ
👍333
ይዘዋት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን እዚህ ከመጣች በኋላ ያልጠበቀችውን ነገር ስላየች መገረሟ አልቀረም፡፡ ያየችውን አይታ ከተመለሰች በኋላ ግን በአማርኛ መፀለዩን ትታ በእንግሊዝኛ መፀለይ ጀመረች:: ወላጆች ያልጠበቁት ነገር ስለነበር ግራ ተጋቡ፡፡ እነሱ የጠበቁት ሀገሯ ቆይታ ስለመጣች፤ አማርኛ መናገርንም ቢሆን በመጠኑ አሻሽላ ስለነበርና አገሯን አይታ ከመጣች ብቻ በአማርኛ እንደምትፀልይ ቃል ገብታ ስለነበር በአማርኛ መፀለዩን አጠናከራ ትቀጥላለች እንጂ ከእነ ጭራሹ እንዲህ እርግፍ አድርጋ ትተወዋለች ብለው ስላልገመቱ ግራ ገባቸው:: አባትና እናት በሁኔታው በመናደድ በአማርኛ ብቻ እንድትፀልይ ለመገፋፋት ቢሞክሩም ልጂት ግን ፍንክች አልል ስላለች ግራ የተጋባው አባቷ ማስፈራራቱን ትቶ በለዘብታ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ልጅቷን ይጠይቃል:: እሷም ደረቷን ነፋ አድርጋ፤ “አይ አባዬ ከአሁን በኋላ በእንግሊዝኛ እንጂ በአማርኛ አልፀልይም፡፡ ጌታ የሚሰማው እንግሊዝኛ እንጂ አማርኛ አይሰማም" ትላለች:: አባት ግራ ተጋብቶ "እንዴት አይሰማም? ምን ማለትሽ ነው?' ይላል፡፡

"እግዚአብሄር አማርኛ ስለማይሰማ እንጂ እነዛን ኢትዮጵያኖች የሚበሉት የማይጣፍጥ ምግብ፣ የሚለብሱት ያደፈና የተቦጫጨቀ ልብስ፣ ቤታቸው ደላላ፣ የማያምርና ንፅህና የሌለው፣ ከተማቸው አስቀያሚ ሆና እያለ ተቀምጠው እንደዚያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው፣ ያውም እንደኛ ሳይሆን ያንን 나사 ሰዓት ቆመው እየለመኑት፣ አይጨክንባቸውም ነበር። አማርኛ የሚሰማ ቢሆን ኖሮማ እነሱንና ሀገራቸውን ከድህነት ያወጣቸው ነበር" ብላ ቁጭ፡፡ የመከላከያ ምስክሮች የሚሰሙበት ቀን ደርሶ በተለመደው ሁኔታ እጅ በካቴና ከሌላ እስረኛ ጋር ተቆራኝቶ ወደ ፍርድ ቤት ሄድኩ:: አሁን አሁን እጂ በካቴና ታስሮ ስሄድ ለምን እንደሆን ሊገባኝ ባይችልም መሳቀቁ ግን ትቶኛል:: ምናልባት ወንጀለኛ መሆኔን ተቀብዬው አሊያም ከዚህ በኋላ በከርቸሌ ለማሳልፈው ሕይወት ሰው አየኝ አላየኝ የሚለው ይሉኝታ ትርጉም አልባ ሆኖብኝ ሊሆን ይችላል:: ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ዛሬ ከሌላው ቀን ይልቅ ተረጋግቼ ወደ ፍርድ ቤቱ ያመራሁት:: ወደ ውስጥ እየገባሁ ሳለ ምን እንደሚመሰክሩልኝ ባላውቅም ምስክር ብዬ የጠራኋቸውን ኤልሳንና አለሚቱን እንዲሁም ጠበቃዬን አየኋቸው፡፡ ሳጥኑ ውስጥ ቆሜ ከምስክሮቼ አፍ እኔን ነፃ የሚያወጣ ቃል እንደማላገኝ ስለገባኝ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሰማኝ፡፡ዳኛው መዝገቡን እያዩ በመሀል ደግሞ ቀና እያሉ ይመለከቱኝና መልሰው ንባባቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንደሚመስለኝ ቀና እያሉ የሚያዩኝ የወንጀሉን አስከፊነት እያነበቡ ፊቴ የገዳይ ፊት ዓይነት መምሰል አለመምሰሉን ለማረጋገጥ ሳይሆን አይቀርም :: በመጨረሻም መነፅራቸውን _ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ቤቱን ግራና ቀኝ ሲያማትሩ ከቆዩ በኋላ ጠበቃዬ አለኝ የሚለውን የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርብ ዕድል ሰጡት፡፡ በመጀመሪያ ለምስክርነት የቀረበችው እጮኛው ኤልሳ ስለነበረች ጥያቄ ለመጠየቅ ሲዘገይ በማየቴ፤ ሁለት ፍቅረኛሞችን ጠያቂና ተጠያቂ በማድረጌ ስህተት የፈፀምኩ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ነገር ግን ችግር ቢኖረው ኖሮ የእሷን ስም ስጠራለት ጠበቃዬ አይሆንም ይለኝ ነበር ብዬ ተፅናናሁ፡፡ ኤልሳ በተለመደው ሁኔታ ማንነቷን ከተናገረችና በቃለመሀላ እውነት ብቻ እንደምትናገር ካረጋገጠች በኋላ ጠበቃዬ ጥያቄውን ጀመረ፤ “ወ/ት ኤልሳቤጥ፣ አቶ አማረን የት ነው የሚያውቋቸው?'' “ዩንቨርስቲ አብረን ስንማር ነው'' ።

*ትውውቃችሁ በምን ደረጃ ነበር?" "መጀመሪያ የእኔና የሟች ጓደኛ ነበር፣ በኋላም የእሷ ፍቅረኛ ነበር አለች። “በአቶ አማረና በሟች መካከል የነበረው የፍቅር ግንኙነት እንዴት חל::" *መጀመሪያ ላይ በጣም ይፋቀሩ ነበር፣ በኋላ ግን እሱ ከትምህርት ቤት በመባረሩ የተነሳ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ነበር"። “ግንኙነታቸው በምን ምክንያት እንደተቋረጠ ያውቃሉ'። “በትክክል ለመናገር ይከብደኛል፣ እሷን ስጠይቃት እሱ እንደከዳት፣ እሱን ስጠይቀው ደግሞ እሷ እንደከዳችው ይናገሩ ስለነበር ትክክለኛውን ምክንያት ማረጋገጥ አልቻልኩም':: *ወ/ት ኤልሳቤጥ፤ አልማዝ ዲያሪዋ መጨረሻ ላይ አንድ ነገር ለማጣራት ወደ እርሶ ዘንድ እየመጣች እንደነበር ፅፋለች፣ የምትመጣበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለእርስዎ ነግራዎት ነበር?'' "የምታጣራው ነገር ስላለ እንደምትመጣ ከመንገር ውጪ ለምን እንደምትመጣ አልነገረችኝም" :: “ወደ እርስዎ እንደምትመጣ ከእርሷ ሌላ የሚያውቅ ሰው ነበር? ወይም እርስዎ የነገሩት ሰው ነበር?'' “የሚያውቅ ስው ይኑር አይኑር አላውቅም፣ እኔ ግን ለማንም አልተናገርኩም"፡፡ “ተከሳሹ ይህንን የሚያውቅበት መንገድ ይኖራል ብለው ይገምታሉ?'' “ይህንን በእርግጠኝነት መመለስ ያዳግተኛል"፡፡ ተሾመ እሷ ልካው ከአልማዝ ጋር መገናኘቱን አስመልክቶ የካደው ሳያንስ እሷ ስትደግመው ስሰማ ደግሞ የነበረኝን ጥርጣሬ ይበልጥ አጠናከረው፡፡ አልማዝ ዲያሪዋ ላይ እንደፃፈችው፤ ሁል ጊዜ ተሾመ እየመጣ አልማዝን የሚያስፈራራትና የሚመታት ኤልሳ ምክንያት ፈጥራ ከእሷ ከተለየች በኋላ ነበር፡፡ ያ ማለት ደግሞ ሌላ ሳይሆን ኤልሳ ያኔ ስታደርግ የነበረውን ድርጊት ነው የደገመችው ማለት ነው፡፡ አቃቢ ሕግ ጥያቄውን ቀጠለ፤


...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍502🥰1
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_19


"እሺ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ፤ ከተከሳሽ ጋር በጓደኝነት ባሳለፋችሁት ግዜ ውስጥ እንደተገነዘቡት ምን ዓይነት ጠባይ ነበረው። “አማረ ትሁት፣ ከአፉ ክፉ ቃል የማይወጣ፤ ተግባቢና ተወዳጅ ልጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አልማዝን በጣም ስለሚወዳት በእሷ ሲመጡበት ብቻ ነው ሲናደድ ያየሁት" በማለት መለሰች፡፡ "አመሰግናለሁ" ብሎ ጠበቃዬ ተቀመጠ። አቃቤ ሕግ በተራው ተነስቶ መስቀለኛ ጥያቄ እየጠየቀ እኔን ወንጀለኛ የሚያደርግ ቃላት ከአንደበቷ ጎትቶ ለማውጣት መታገል ጀመረ:: *ወ/ት ኤልሳቤጥ፤ ቀደም ሲል እንደተናገሩት ከሆነ ሟችና ተከሳሽ በምን እንደተለያዩ አላወቁም፡፡ ተክላሽ ከማች ጋር አልፎ አልፎ ግቢ ውስጥ ይጣሉ እንደነበር ይወራል፣ ይህ በምን ምክንያት ነው"፡፡ “አልፎ አልፎ ሟችን ዶ/ር አድማሱ የተባለ መምህሯ ያስጠናት ስለነበር በብዛት ወደሱ ቤት እየሄደች ታጠና ነበር:: በዚህም የተነሳ እሱም ይህንን ስላልወደደው እሱ ጋ መሄዷን እንድታቆም ይጨቀጭቃት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህም ሆኖ ትምህርት ቤት እያሉ በዚህ ምክንያት ተጣልተው አልተለያዩም"፡፡ *ጥሩ! ምክንያቱ ይህ ካልሆነ፣ ተከሳሽ ከትምህርት ቤት ከተባረረ በኋላ ከእሷ ጋር የተለያየበት ምክንያት ምንድነው?"፡፡ "እኔ አላውቅም"፡፡ “ቅድም እንደነገሩን ተከሳሻ በቅናት የሚጣላ ከሆነ በቂም በቀል ተነሳስቶ ለመግደል የሚስችለው ምክንያት አለ ብለው አያምኑም?" ብሎ ሲጠይቅ፤ ጠበቃዬ ተነስቶ ተቃውሞ አለኝ አለ፡፡ ዳኛው ተቀውሞውን እንዲያሰማ ዕድል ሰጡት፤ “ክቡር ፍ/ቤት፤ ተጨባጭ መረጃ በሌለበት ሁኔታ ምስክሯ በግምት ይህንን ጥያቄ ልትመልሰው መገደድ ስለሌለባት ጥያቄው ውድቅ ቢሆን' አለ፡፡ ዳኛው ተቃውሞውን ተቀብለው ሌላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ አዘዙ፡፡ አቃቤ ሕግም ለዚህ ብዙም ሳይጨነቅ! *ቀደም ሲል እንደተናገሩት ተከሳሽ ትሁት ቢሆንም በአልማዝ ላይ ከመጡበት እንደሚበሳጭ ተናግረዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ አብራችሁ በነበራችሁበት ወቅት ተከሳሽ ከአንድ ተማሪ ጋር ተጣልተው ነበር ይባላል፣ ምክንያቱ ምን ነበር?''

“አዎ! አንድ ጊዜ ብቻ መጣላቱን አስታውሳለሁ፡፡ እሱም አንድ ተሾመ የሚባል ተማሪ ሟችን አፈቀርኩሽ እያለ በግድ ከእሱ ጋር እንድትሆን ያስቸግራት ነበር፡፡ እሷ ግን ፍቃደኛ አለመሆኗን ስለነገረችውና በዚሁ የተነሳ ስለመታት፣ አማረ ተናዶ ከእሱ ጋር መደባደቡ ትዝ ይለኛል" አለች፡፡ አቃቤ ሕግ ይህንን ሲሰማ ጨርሻለሁ በማለት እየተኩራራ ወደ መቀመጫው አመራ፡፡ ከኤልሳቤጥ ምስክርነት ጠበቃዬ ምን ጠቃሚ ነገር እንዳገኘ ለማወቅ ቢያዳግተኝም እኔ ግን የመሰከረችብኝ እንጂ የመሰከረችልኝ መስሉ አልተሰማኝም፡፡ የእሷን የምስክርነት ቃል ከጠበቃዬ ይልቅ አቃቢ ህግ “አልማዝን ላለማጣት የተደባደበ ሰው፣ በፍቅሩ ከመጡበት ሰው ለመግደል አይመለስም" የሚለውን ለማሳየት ተጠቅሞበታል፡፡ ይህንንም ጥያቄ እንዲያነሳ ፍንጭ የሰጠችው እሷ ነች፡፡ የእሷ ምስክርነት አልማዝ ከተሾመ ጋር ተያይዞ በኤልሳ ላይ የነበራትን የቀድሞ ጥርጣሬ እኔ ላይ አስፍኖ በማለፉ የተስፋ መቁረጥና የፍርሀት ስሜት ወረረኝ። ሌላዋ ምስክሬ አለሚቱ ስትሆን እሷም ብትሆን ጥሩ ጠባይ እንዳለኝና አንድ ቀንም ከሰው ጋር ተጣልቼ እንደማላውቅ ከመመስከር ውጪ ምንም የፈየደችው ነገር አልነበረም፡፡ ቢያንስ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቀን ቤት ውስጥ እንደነበርኩ ትመሰክራለች ብዬ ብጠብቅም፤ የዛን ቀን የት እንደዋልኩ እንደማታስታውስ በመናገሯ ለእኔ ምንም የጠቀመኝ ነገር አልነበረም፡፡ ለነገሩ እኔ በወቅቱ ተናደድኩባት እንጂ እንኳን እሷ እኔ ራሴም ብሆን የዛን ቀን የት እንደነበርኩ አላስታውስም፡፡ በመጨረሻም ዳኛው ለመስከረም 15/1981 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተውን ወጣን፡፡ ከፍርድ ቤት ወጥቼ ወህኒ ቤት እንደገባሁ ዙሪያ ገባውን እየቃኘሁ ብዙ ሳሰላስል ከቆየሁ በኋላ በእርግጠኝነት ይህ "ቤቴ" ከደጁ መሻአሉን አረጋገጥኩ፡፡ ቢያንስ እዚህ ያለነው አስተሳሰባችን አንድ ነው:: የምናስበው ስለ ዛሬ ነው እንጂ አንዳችንም ነገ ስለሚሆነው ነገር አንጨነቅም፡፡ ሁላችንም የምንኖረው ለዛሬ ነው:: ለእኛ ህይወት ዛሬ ነች፤ ነገ ግን የሌሎች ናት:: ለዛሬ ስንል ነው ነጥቀን የምንበላው፣ የዛሬ ሆዳችንን ለመሙላት ስንል ነው ሕይወት የምንቀጥፈው፣ ለዛሬዋ የቅጽበት ደስታ ስንል ነው ሴት ደፍረን የምንታሰረው:: አርቆ የሚያስብ ሰውማ እንዴት ወንጀለኛ ሊሆን ይችላል:: ታዲያ እኔም እዚህ በሰላም ያለጭንቀት ለዛሬ ብቻ እኖርና ወደ ውጪ በወጣሁ ቁጥር ግን ዛሬ ማን ይመሰክርብኝ ይሆን? ምን ብሎ ይመሰክርብኝ ይሆን? ይፈረድብኝ ይሆን? በማለት ስለነገ ሕይወቴ መጨነቅ እጀምራለሁ፡፡ አዎ! ይህንን ሳስብ አልማዝ ዲያሪ ላይ ያነበብኩት የሱማሌውና የጤፉ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡

"ያባው! አሊያ አንተ አላህ ሆንክ ወይስ ከአላህ ጋር ተማክረሀል? እንዴት አንድ ዓመት ሙሉ በሕይወት እንደምትኖር እርግጠኛ ሆንክ?" ያለው ያኔ ለኔ ባይታየኝም ትክክለኛ ጥያቄ ነበር። ለካስ እነሱ ሁልጊዜ ለዛሬ ብቻ የሚመገቡትን የሚገዙትና ስለነገ ሲያወሯቸው “ኢንሻ አላህ" የሚሉት፣ ሁል ጊዜ የዛሬን ብቻ ስለሚኖሩ ነበር! የፍርድ ቤቱ ውሎ እንደጠበቅሁት ስላልሆነልኝ እስር ቤት ከገባሁ በኋላ ለጓደኞቼ "ውሎ እንዴት ነበር?" ጥያቄ መልስ ሳልሰጥ ቆዝሜ ተቀመጥኩ፡፡ ጓደኞቼ ማፅናናቱ ሲሰለቻቸው በተለያየ መንገድ ሊያስቁኝ ሞከሩ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ቀልዶች እኔን የሚያስቁ አልነበሩም፡፡ ይልቁንም ቀልዱን ትተው ቁምነገር ማውራት ሲጀምሩ ሳልወድ በግድ ሳቅሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ለዶክትሬት ዲግሪ ጥቁር አንበሳ ይማር የነበረ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ በአንድ ትምህርት ኤፍ (F) የሰጠውን አስተማሪ ውጤቱን እንዲያስተካክልለት እያለቀሰ ቢለምነውም ከመራራት ፋንታ በቀልድ መልክ፤ "አይዞህ አትጨነቅ ወጣት ነህ፣ ገና በመጀመሪያው ዓመት እንዲህ የተልከሰከሰ ነጥብ ይዘህ ቀሪ አምስት ዓመታትን በጭንቀትና በለቅሶ ከማሳለፍ እንደገና ማትሪክ ተፈትነህ ዕድልህን ብትሞክር ይሻሻል" ሲለው በንዴት ራሱን መቆጣጠር ተስኖት በቡጢ ፊቱ ላይ መትቶት ጥርሱን ይሰብረውና እስር ቤት ይገባል፡፡ ይህ እስረኛ እስር ቤት ውስጥ የሚጠራው በስሙ ሳይሆን ዶክተር እየተባለ ነው፡፡ ለአብዛኛው በተለይ ፊደል ላልቆጠረው እስረኛ ዶክተር ማለት ደግሞ የማያውቀው ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ታዲያ የዛን ቀን አንዱ እስረኛ የተለያዩ የማያውቃቸውን ጥያቄዎች ይጠይቀው ነበር፡፡ ጠያቂው እስረኛ ቅማል አማሮት ኖሮ ከልብሱ ላይ ቅማል እየገደለ፤ “ስማ እንጂ ዶክተር፤ እነዚህ ቅማሎች እንዴት ነው የሚራቡት? እኔ በየቀኑ እገላቸዋለሁ፣ እነሱ ግን የበለጠ ቁጥራቸው እየበዛ ይፈለፈላሉ፡፡ ለመሆኑ እናትየው በየደቂቃው እያረገዘች መንታ መንታውን ነው እንዴ የምትወልደው?'ይለዋል፡፡ ዶክተሩ ለጥቂት ደቂቃዎች ተንከትክቶ ይስቅና ሲቃ እንደያዘው፤ "ስማ እንጂ፤ ለመሆኑ ማነው ቅማል ታረግዛለች ያለህ? ቅማል አታረግዝም፡፡ እንቁላል እየጣለች ነው የምትራባው" ይለዋል፡፡ _ እስረኛው ስለተሳቀበት ሀፍረት እየታየበት፤ "ውይ! ተወው ረስቼው ነው፡፡ ቅጫም ለካስ የቅማል እንቁላል ነው" ይለዋል፡፡ ሌላኛው እስረኛ ቀበል አድርጎ፤
👍34
"አንተ ደግሞ የምትጠይቀው የጅል ጥያቴ ነው፡፡ ከጠየቅህ አይቀር ከበድ ያለ ጥያቄ አትጠይቅም" ይለውና፤ "እሺ ዶክተር እሱን ተወውና መርፌ እንዴት ነው የሚሰራው?” ይለዋል፡፡ ዶክተሩም ጥያቄው አልጥም ስላለው፤ "አላውቅም" ይለዋል፡፡ እስረኛው በአሸናፊነት መንፈስ፣ “አዬ! ለካ ያንተ ዶክተርነት የውሸት ነው! መርፌ እንኳን እንዴት እንደሚሰራ የማያውቅ ዶክተር ምን ዶክተር ይባላል" ብሎ- ሲናገር፣ በመጀመሪያው ጥያቄ አፍኜው የነበረውን ሳቄን መቆጣጠር ተስኖኝ ለቀቅሁት፡፡ ዶክተሩ ለማስረዳት በመሞከር ፋንታ ከእኛው ጋር ይስቅ ጀመር፡፡ ፍርድ ቤት መመላለሴ የቀጠለ ቢሆንም የመጨረሻው ውሳኔ ግን ከመቅረብ ይልቅ ይበልጥ እየራቀብኝ መጥቷል፡፡ በመጀመሪያዎቹ የቀጠሮ ቀናት ፍርድ ቤት በቀረብኩ ቁጥር ፍርዴን የምሰማ እየመሰለኝ እጓጓ እንዳልነበር፤ ዛሬ ግን የምናፍቀው የመጨረሻው ፍርድ እንዲህ በቀላሉ እንደማይገኝና ወደ ፍርድ ቤት የምሄደው የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስማት ሳይሆን ሌላ ቀነ ቀጠሮ ለመቀበል መሆኑ ከገባኝ ሰንብቷል፡፡ ስለዚህም ወደ ፍርድ ቤት መሄድ የሚናፍቀኝ ተናፍሶ ለመምጣት ካልሆነ በስተቀር ሌላ አዲስ ነገር ይዞ እንደማይመጣ ተረድቼአለሁ፡፡ ቀናት በቀናት እየተተኩ፣ ወራት በወራት ላይ እየተደራረቡ ወደ ዓመታት እየተለወጡ ቢሆንም ያ የምናፍቀው ፍርድ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አልሆነም:: ግን ምን ዓይነት ፍርድ ነው የምጠብቀው? የሞት ፍርድ እንደማይሆን ጠበቃዬ ነግሮኛል:: ታዲያ ፍርዱ ምን ሊሆን ይችላል? ዕድሜ ይፍታህ አሊያም በነፃ መለቀቅ እንጂ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም:: ለእኔ ደግሞ ከሁለተኛው ይልቅ የመጀመሪያው አማራጭ የተሻለ ነው:: የአካል ነፃነት ብቻ ለእኔ ትርጉም ስለማይኖረው፡፡ ከአሁን በኋላ ብፈታም አልማዝ በሌለችበት ዓለም ውስጥ መኖር ለእኔ ትርጉም የለውም፡፡ እርግጥ ከአልማዝ ጋር ከተለያየሁ በኋላ ብዙ ጊዜያትን እሷ በሌለችበት ሁኔታ አሳልፌአለሁ፡፡ ግን “አንድ ቀን ትመጣ ይሆናል" የሚለው ተስፋዬ አብሮኝ በመኖሩ በሕይወት መኖር አላስጠላኝም ነበር፡፡ ዛሬ ግን አንድ ቀን ትመጣ ይሆናል የሚለው ተስፋዬ በመጥፋቱ ሕይወቴ ለእኔ ትርጉመ ቢስ እንደምትሆን አልጠራጠርም። በበኩሌ የሕይወቴን ፋይል ከዘጋሁ ቆይቼያለሁ፡፡ ፋይሉን ለመዝጋት የቀፈፈው ግን ፈጣሪ ነው:: ገና ያዘጋጀልኝ ብዙ የሥቃይና የመከራ ሕይውት ስላለ እሱን በተከታታይ ሳልጋት ፋይሉን ዘግቶ ሊያሰናብተኝ አልፈለገም፡፡ እርግጥ ዕድሜ ልክ መታሰሩም ቢሆን ነፃ ከመውጣት ይሻል ይሆናል እንጂ የሥቃይን ምእራፍ የሚዘጋው አልነበረም:: ግን ምን ያደርጋል? እሱንም

ማጣት እንደሌለብኝ ውስጤ የሚያምን ቢሆንም ለኤልሳ እርካታና ለጠበቃዬ ስል ለእኔ የተሻለውን አማራጭ ለማጣት እየተፍጨረጨርኩ ነው። አለሚቱ መምጣቷን ካቆመች ከወር በላይ ሆኗታል:: ቢጨንቀኝ ምን እንደሆነች ኤልሳ አጣርታ እንድትነግረኝ ላኩዋት:: አላገኘቻትም፡፡ ኤልሳም ወደ ቤት ሄዳ ልታገኛት አልቻለችም:: እንደአጣራችው ከሆነ ግን ውዝፍ የቤት ኪራይ በመጠየቋ ያለውን የቤት ዕቃ ሽጣ እና ከፍላ አገሯ መግባቷን ሰማሁ:: ምስኪን ምን ታድርግ! ብታይ ብትጠብቅ የድብቅ ፍቅረኛዋ ለፈታላት አልቻለም:: የእሷ ሩጫ መጨረሻው ባዶ መቅረት መሆኑን ተረድታዋለች፡፡ በቀላሉ ይፈታል ብላ እንዳትገምት ደግሞ የተከሰስኩበት ወንጀል በነፍስ ማጥፋት ነው፡፡ የሚገርመው ግን እሷ ብትሄድም ከሁሉም በላይ የምወደው ንብረቴ መጽሐፍ መሆኑን ስለምታውቅ በጠቅላላ ለአከራዮቼ በመስጠቷ ኤልሳ ተቀብላ እሷ ዘንድ አድርጋልኛለች:: የቀረችኝ አንድ ወዳጀ እሷው ነበረች፡፡ እሷንም አጣሁ:: ኤልሳ ሁኔታውን ስትነግረኝ እምባዬ ዓይኔ ላይ አቀረረ፡፡ እሷም ይህንን ስታይ ለንብረቴ ያዘንኩ መስሏት፤ “አይዞህ አማረ አንተ ነፃ ውጣ እንጂ ጥሩ መ/ቤት አስቀጥርሃለሁ፡፡ ከዚያ ሁሉንም ነገር አሟልተህ ሕይወትን በአዲስ መልኩ ትጀምራለህ፡፡ ንብረት ቢጠፋ በንብረት ይተካል አትዘን" አለችኝ:: እርግጥ ነው ዛሬ እሷ ግብርና ሚ/ር ውስጥ ባለሥልጣን በመሆኗ ለእኔ የሚሆን ሥራ ላታባ ትችላለች፡፡ የጠፋብኝንም ንብረት ስወጣ ልተካው እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ባይገባት ነው እንጂ የእኔ ንብረት መች የሚተካ ሆነና፡፡ በግላጭ ስቅስቅ ተብሎ እርም የሚወጣበት ቢሆን ኖሮ አልቅሼ በተገላገልኩት ነበር፡፡ ነገር ግን ነገሩ የድብቅ ሆነና ውስጥ ለውስጥ ድብን ብሎ መቅረት ብቻ ሆነ፡፡ የመጨረሻ በረከቴ አለሚቱ ነበረች፤ እሷንም አጣሁ:: የእኔ ፉንጋ! ሁሌ የማይከፋት፣ ስፈልግ የምጠራት፣ ስፈልግ የማባርራት፣ ኩርፊያዋ በአንድ መሳም ጥርግ ብሎ የሚጠፋ፣ አለሚቱ ለእኔ የምትተካ በረከቴ አልነበረችምና ከኤልሳ ተሰናብቼ ስሄድ ድምፄን ሳላሰማ አለቀስኩላት፡፡ -//- ከሳምንት በኋላ ጠበቃዬ አስጠራኝ:: በተቻለ መጠን ሁኔታዎቹን እያጣራ እንደሆነና አንዳንድ መረጃዎችን ከእኔ በተጨማሪ ከፖሊስ ጣቢያ ማግኘቱን፤ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች የእኔን ከወንጀሉ ነፃ መሆን የሚያሳምኑት ቢሆንም፤ ዳኞቹን ለማሳመን ግን አሁንም በቂ መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚገባው ነገረኝ:: ቀጠል አድርጎም ስለአልማዝ የአሟሟዋት ሁኔታ ይተርክልኝ ጀመር።

“አቶ አማረ፤ ለማንኛውም የተከሰስክበትን ሁኔታ ማወቁ መረጃ ለመስጠት ሊረዳህ ስለሚችል ስለአልማዝ አሟሟት ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡ አልማዝ የሞተችው አልቤርጎ ውስጥ ተሰቅላ ነው፡፡ የሞተችበት ክፍልም ያው ከዲያሪው ላይ እንዳነበብከው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ ደብረወርቅ እየተባለ በሚጠራ ሆቴል ውስጥ ነው:: እሷ ከቤት ስትነሳ መምጣት የፈለገችው ወደ ኤልሳ ነበር። ግን የሚደንቀው ነገር፤ ፅፋ የተወችው ደብዳቤ የሚተርከው የራሷን ሕይወት በራሷ ማጥፋትዋንና በዚህም የተነሳ ሌላ ሰው እንዳይጉላላ የሚገልፅ ነበር። ፖሊሶችም ይህ የሚታመን ነገር ስላልሆነላቸው የእጅ ጽሑፉን "በአባዲና ፖሊስ የምርመራ ክፍል አስመርምረው የእሷ የእጅ ጽሑፍ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ነገር ግን እራሷን ለመግደል የሚያደርስ በቂ ምክንያት መኖሩን ግን ከዲያሪውም ሆነ ከሌሎች መረጃዎች ላይ ማግኘት አልተቻለም:: አልጋ ላይ ጋደም ብላ ሙዚቃ እያዳመጠች ስለነበር ከመቅጽበት ከአልጋ ላይ አስነስቶ ራሷን እንድታጠፋ የሚጋብዝ ሁኔታ ላይ እንዳልነበረች መረዳት ይቻላል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተን ለማግኘት በመፈለጓና ኤልሳም ከመጣች እንደምታገናኛትና እውነቱን ከአንተ መስማት እንደምትችል ነግራት ከቤት ስለወጣች በአንድ ግዜ ሀሳቧን የሚያስለውጥና ራሷን ለመግድል የሚያነሳሳ ምክንያት አለ ብሎ መናገርም ያዳግታል:: እርግጥ አልማዝ በልጅነቷ ከደረሰባት ችግር ጋር ተያይዞ በጭንቀት የተነሳ የአእምሮ ሕመም ችግር ሊያጋጥማት ከቻለ እራሷን ገድላ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሊከሰት አይችልም ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም በዓለማችን ላይ ራስን የማጥፋት ችግር ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በእንደዚህ ዓይነት ግለሰቦች ላይ ነውና፡፡ ነገር ግን ፖሊስ ራሷን አልገደለችም ብሎ እንዲያምን ያደረገው እሷ የተሰቀለችበት አልቤርጎ የተቆለፈው ከውስጥ መሆን ሲገባው ከውጭ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ ነው:: ምክንያቱም ቁልፉን አልቤርጎው ውስጥም ሆነ ከበሩ ላይ ማግኘት አልተቻለም:: ስለዚህ ከሶስት ነገሮች አንዱ ተከስቶ ሊሆን ይችላል:: አንደኛው፤ ገዳዩ ገብቶ ከመግደሉ በፊት ራሷን እንደገደለች አድርጋ እንድትጽፍ አስገድዶ ካጻፋት በኋላ ሰቅሏት ደብዳቤውን አስቀምጦ ሄዶ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ፖሊስን ሊያሳምን አልቻለም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሊገድላት የመጣ ሰው ራሷን እንደገደለች
👍271🥰1
አድርጎ ሲያጽፋትና ሲሰቅላት ምንም ቢሆን ትንሽ እንኳ ሳትፍጨረጨር እና ሳትከላከል ትሞታለች ብሎ መገመት አዳጋች ነው:: ነገር ግን የሚገርመው ጥፍሮቿም ላይ ሆነ ሌላ አካሏ ላይ የሌላ ሰው ደም ወይም አሻራ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አልማዝ ራሷን ከመግደሏ በፊት አልቤርጎውን ቆልፋ ቁልፉን ሽንት ቤት ውስጥ አሊያም በመስኮት በኩል ጥላው ራሷን ገድላ ሊሆን ይችላል:: ይህም ከመላምትነት አልፎ በመረጃ የተደገፈ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ቁልፉን በመስኮት ጥላዋለች እንዳይባል ግቢው ውስጥ ስንዝር በስንዝር ተፈልጎ ሊገኝ አልቻለም:: ሽንት ቤትም ጨምራው ይሆናል ተብሎ እንዳይጠረጠር፣ ደብዳቤው ላይ እንደተፃፈው ከሆነ አልማዝ በእሷ ሞት ምክንያት ማንም ሰው እንዳይጉላላ የምትጽፍ ከሆነ ሽንት ቤት ውስጥ ቁልፉ እንዳይገኝ በማድረግ እውነቱን የምትደብቅበት ምክንያት ሊኖር አይችልም:: ሶስተኛው፣ አልማዝ ራሷን ከገደለች በኋላ ምናልባት በወንጀሉ የሌለበት ግለሰብ በአጋጣሚ በሩን ከፍቶ ሲገባ ተሰቅላ መሞቷን ሲያይ ደንግጦ በሩን ከውጪ ዘግቶ ቁልፉን ይዞ ሄዶ ይሆናል የሚለው ተራ መላምት ነው :: ይህም ቢሆን የሚያሳምን አይደለም:: ምክንያቱም ቢያንስ ቢያንስ በበሩ ላይ የግለሰቡ አሻራ መገኘት ነበረበት፡፡ ይህም ሊገኝ አልቻለም:: እንግዲህ ወንጀሉ በረቀቀ መንገድ ተፈፅሟል ማለት ነው፡፡ አልማዝ ራሷን በረቀቀ መንገድ ገድላለች፣ ወይም በሌላ ሰው የረቀቀ ስልት ተገድላለች፡፡ ይህ እንቆቅልሽ ካልተፈታ ያንተን ነፃ መሆን ለዳኞቹ ማሳመን ይከብዳል። እኔ ግን ቢያንስ ኤልሳን ስለማምንና አልማዝ ወደ አንተ እየመጣች መሆኑን በተመለከተ አንተ ምንም መረጃ እንዳልነበረህ ስለማውቅ በንፁህነትህ አልጠራጠርም፡፡ ሌላውን እንዴት ማሳመን እንደምችል ግን ግራ ገብቶኛል::" በማለት በሁለት እጆቹ ጉንጮቹን ይዞ ተክዞ ተቀመጠ። የሰማሁትን ማመን አቃተኝ:: ድርጊቱ የተወሳሰበና ለፈራጅ የሚያስቸግር ነው:: ከዚህ ውስብስብ ወንጀል ውስጥ የእኔን ንፁህነት ፈልቅቆ ማውጣት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ታየኝ፡፡ ምናልባት እንቆቅልሹን መፍታት የሚችል ሰው ካለ ከእኔ በስተቀር ሌላ ሊሆን አይችልም:: ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው እኔ መረጃዎችን የማሰባሰብ ዕድል ኖሮኝ እውነቱን ለማግኘት ስታደል ብቻ ነበር:: ይህንን ለማድረግ ግን አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበረኝም። ሰባተኛው የቀጠሮ ቀን ደርሶ ወደ ፍርድ ቤት ስገባ ከጠበቃዬ ጋር ፊት ለፊት ተገናኘን:: ፊቱን ሳየው ግርማ ሞገሱ ጠፍቶ የተሸናፊነት ስሜት አጥልቶበታል። እርግጥ ነው እንደሚሸነፍ እንኳን እሱና እኔም ጠንቅቄ

አውቄዋለሁ፡፡ የመከላከያ ምስክሮች ተብለው የተጠሩት የሰጡት የምስክርነት ቃል ከእኔ ይልቅ ለአቃቢ ሕግ የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው እያወቅሁ ማሸነፍን ማሰብ ጅልነት ነው፡፡ ጠበቃዬ እኔን ለማፅናናት ሳይሆን አይቀርም፡ “አይዞህ፣ ይፈረድልናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ካልሆነም ይግባኝ እንላለን አለኝ:: ይግባኝ የሚለው ቃል ከአፉ ሲወጣ ተሸናፊነቱን የተቀበለ ስለሚያስመስል ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ሆነ:: ግን ለምን እንደሆነ ባላውቅም ያ ስመኘው የነበረው በእኔ ላይ የመፈረድን ሁኔታ ሳስብ ግን ሽንፈት መስሎ ስለተሰማኝ ፍርሃት ወረረኝ:: በተለይ ዶ/ር አድማሱ ከፊት ለፊት በኩራት ተቀምጦ በእኔ ላይ የሚፈረደውን ፍርድ ለመስማት ሲጠባበቅ ሳየው ሽንፈቱ ፍጹም አልዋጥልህ አለኝ:: ግን ያም ሆነ ይህ አሁን ግዜው አልፏል፡፡ ብዙ ላደርጋቸው የምችላቸውን ነገሮች አላደረኩም፡፡ ከሁሉም በላይ እንቆቅልሹን ልፈታው የምችለው እኔ ሆኜ ሳለ እነሆ ይኸው ራሴን እንደ እየሱስ አሳለፌ ልሰጥ ተዘጋጅቼአለሁ:: እየሱስ እንኳን ራሱን አሳልፎ የሰጠው በደሙ የሰው ልጆችን የኃጢያት እድፍ ሊያጠራ አስቀድሞ ራሱ የገባውን ቃል ለመተግበር ነው:: የኔ ግን እዚህ ግባ በማይሉት የሐሰት ቁልል ምክንያት በከንቱ ራስን ለጠላቴ አሳልፎ ከመስጠት ውጪ ይህ ነው የሚባል ፋይዳ ያለው ጥቅም አልነበረውም:: ዳኛው የሚሰጡትን ውሳኔ ለመስማት ሁሉም ድምጹን አጥፍቶ እያዳመጠ ስለነበር ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ ውሀ እንኳን ጠብ ቢል መስማቱ አይቀርም ነበር፡፡ ዳኛው የክርክሩ ጠቅላላ ሂደት እንዴት እንደነበር ካብራሩ በኋላ ይህ ሁሉ ታዛቢ ሰው በጉጉት የሚጠብቀውን የፍርድ ውሳኔ ማሰማት ጀመሩ!


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍28
#አላገባህም


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


////
‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡››

‹‹እናቱና እህቱ የሞቱ ቀን ነው የተሰወረው፡፡ሁለቱ በመልክም ሆነ በአመካከት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑት  ወንድማማቾች ከከተማ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ ..ሳሎኑ ፍፁም ትርምስምስ ብሎ ያያሉ ..ግራ በመጋባት  ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ እናታቸው ልቧ ላይ ነጭ አብረቅራቂ ቢላዋ ተሰክቷባት ወለሉ ላይ ዝርግትግት ብላ ተኝታለች..አባትዬው ስሯ በደም በተጨማለቀው እጇቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ደንዝዘዋል….፡፡

‹‹እንዴ አባዬ ምንድነው..?እናቴን ምን አደረካት?›› ብለው ሲጮሁ ከፊት ለፊት  ኮርኒሱን ከደገፈው ብረት ላይ በታሰረ  ሲባጎ  አንገቷ የታነቀው እህታቸው በድኗ 360 ዲግሪ ሲሽከረከረከር ይመለከታሉ፡፡ሁለቱም ወንድማማቸች ወደእህትዬው እየሮጡና ሁለት እግሮቾን አንድ ላይ ይዘው ወደላይ ከፍ ያደርጎታል….‹‹ቶሎ በል ቢላዋ አምጣና ..ገመድን ቁረጥ…››
.ዘሚካኤል ይንደረደርና እናትዬው ደረት ላይ የተሰካውን ቢላዋ ይነቅልና ወንበር ላይ ቆሞ ገመዱን ይበጥሳል…እህትዬው ተዝለፍልፍ ሚካኤል ተከሻ ላይ ታርፋለች… ቀስ ብለው ወለል ላይ አሳርፈው በፍጥነት አንገቷ ላይ ያለውን ገመድ አላቀው ትንፋሿን ቢያዳምጡም በውስጧ የቀረ  ምንም  እንጥፍጣፊ እስትንፋስ አልነበረም….ከዛ ዘሚካኤል ቀጥታ እህቱ የተንጠለጠለችበትን ገመድ የቆረጠበትን እና እናቱ የተገደለችበትን ቢላዋ ይዞ ወደአባትዬው ሲንደረደር…ሚካኤል  በደመነፈስ ሮጠ ይጠመጥበታል…

‹‹ልቀቀኝ..እናቴንና እህቴን ገድሎ እሱ በህይወት አይኖርም››

‹‹አይሆንም….ስለሆነውን ምንም ምናውቀው ነገር የለም››ሲል ይመልስለታል፡፡

‹‹እንዴት አናውቅም..?አታይም እንዴ …?እጁ በደም ተጨማልቆ……ልቀቀኝ ልግደለው›› ሲል ይጋበዛል፡፡

‹‹አባቴንም ማጣት አልፈልግም››

‹‹እንግዲያው ሁለታችሁንም እገድላችኃለው…››ይለውና ድብድብ ይጀምራሉ…ይሄ ሁሉ ሲሆን አባትዬው ደንዝዘው ከተቀመጡበት  ቦታ ንቅንቅ አላሉም ነበር….ወንድማማቾቹ አባቴን ልግደል አትገድልም በሚል ጠብ እርስ በርሳቸው ተቦቅሰውና ተደባድበው ሳይለይላቸው ቤቱ በፖሊስ ይሞላል፡፡

አባትዬ እነሱ ከመድረሳቸው በፊት ስልክ ደውለው ሚስታቸውን  እንደገደሉ ነግሮቸው ነበር፡፡ፖሊሶቹ ወንድማማቾቹን አገላግለው ሶስቱንም ወደእስር ቤት ከወሰዷቸው በኃላ ሬሳዎቹን አንሰተው ለምርመራ ወደሆስፒታል ይልካሉ..በማግስቱ አባትዬው ሚስታቸውንም ሆነ ልጃቸውን የገደሉት እራሳቸው እንደሆነ ቃል ስለሰጡ በዛ መሰረት ሁለቱ ልጇች ይፈታሉ፡፡

ከአራት ቀን በኋላ የእናትና እህታቸውን  ሬሳ ተረክበው ከቀበሩ በሆላ ዘሚካኤል በከተማው አልታየም፡፡‹‹አንተ ያንን አውሬ ሰውዬ ገድዬ የእናቴንና የእህቴን ደም እንዳልበቀል ያደረከኝ ጠላቴ ነህ..ከእሱ በላይ እጠላሀለው ..እና ደግሞ መቼም ቢሆን ይቅር አልልህም፡፡››የሚል ማስታወሻ ለወንድሙ ጥሎ ነበር የጠፋው፡፡ቆይቶ እንደሰማነው ከጓደኞቹ ጋር በቦረና በኩል ወደኬኒያ ከዛም ወደጣልያን ከተሻገረ በኋላ…በፊትም ልጅ እያለ ጀምሮ ይሞካክረው  በነበረው ሙዚቃ ገፋበትና በትምህርትም አሳድጎ ጥሩ ሙዚቀኛ ሆነ ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወት መኖሩን ያወቅነው የዛሬ 3 አመት የሙዚቃ ክሊፑን ሲለቅ ነው፡፡

….የዛን ጊዜ ሚካኤል የተደሰተው መደሰት ያው አንቺም አብረሺን ስለነበርሽ ታውቂዋለሽ፡፡ከዛ በሀገር ውስጥ በጣም ተቀባይነት ስላገኘ ..ጓዙን ጠቅልሎ ገባ፡፡በሙዚቃ ብቻ ሳይሆን በፊልም ትወና ላይ መስራት ቀጠለ…እንግዲህ ባለፉት አምስት አመታት የገነባውን ስምና ዝና  እኩል ነው የምናውቀው፡፡››

‹‹ይገርማል….ግን ከመጣ በኃላ ወንድሙን ለማግኘት አልሞከረም…?››

‹‹ወይ ማግኘት..እኔ አንኳን ላገኘው ሄጄ ስለወንድሙ ሳነሳበት እንዴት እንደተንገሸገሽ እስከዛሬ ሳስበው ይዘገንነኛል..አሁንም ጥላቻው እንዳለ ነው፡፡አልፎ አልፎ በድብቅ እየመጣ የእናቱንና የእህቱን መቃብር እየጎበኘ እንደሚሄድ አውቃለው….በዛው ልክ ስለአባቱም ሆነ ስለወንድሙ ምንም መስማት እንደማይፈልግ እና ቢሞቱም ግድ እንደሌለው አውቃለው፡፡››

‹‹ተይ እንደዛ አትበይ…..››

‹‹ወይ አንቺ ልጅ ስንት ነገር ውስጥ አስገባሺኝ..ስለእሱ ለማወቅ ለምንድነው የፈለግሽው?፡››ስትል ዳግመኛ ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንደምንም ብዬ በሰርጋችሁ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ አስቤለው››

‹‹ምን?››አዲስአለም ክፉኛ ነው የደነገጠችው፡፡

‹‹ምነው መጥፎ ሀሳብ ነው እንዴ?››

‹‹አረ በፍጹም…ግን የሚሳካ እቅድ አይደለም….››

‹‹ከተሳካልኝስ?››

‹‹ከተሳካልሽማ….ለሚካኤል በሰርግ ላይ ሌላ ሰርግ ደገሽለት ማለት ይሆናል….በፊቱንም ይወድሻል በቃ የዘላለም ባለውለታው ነው የምትሆኚው››

ፀአዳ ‹‹ለማንኛውም ጉዳዩ በእኔና አንቺ መሀከል በሚስጥር ይያዝ …..ሚካኤል ሰምቶ ካልተሳካ ቅር እንዲሰኝ
አልፈልግም፡፡››ስትል አስጠነቀቀቻት፡፡

‹‹አታስቢ እኔም ባሌ በሰርጉ ሰሞን እንዲያዝንብኝ ስለማልፈልግ ..አልነግረውም…ለአንቺ ግን እንዲቀናሽ በቻልኩት መንገድ ሁሉ አግዝሻለው፡፡››

በዚህ ሁኔታ ነበር ከአዲስ አለም  ስለዘሚካኤል የተወሰነ ነገር ማወቅ የቻለችው..ከዛ ወደ ሶሻል ሚዲያ ሄደችና እና ስለእሱ የተፃፉ የጋዜጣ አምዶችና በተለያየ ጊዜ የሰጣቸውን ቃለ መጠይቆችን ሰብስባ ማንበብና ማዳመጥ ነው የቀጠለችው…ይሄ ሂደት አንድ ሳምንት ነው የፈጀባት፡፡በዚህ ጊዜ በአምስት አመት ውስጥ ያወጣችውን ሶስት አልበሞችና ፤ከስምንት በላይ ነጠላ ዜማዎችን እየደጋገመች ያደመጠች ሲሆን እሱ የተሳተፈባቸውን ስምንት የሚሆኑ ፊልሞችንም በጽሞና መመልከት ችላለች፡፡

እና በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ለአመታት የምታውቀው የቅርቧ ሰው እንደሆነ እንዲሰማት አድርጎታል..ያንን ስሜት ግራ አጋቢ ነው፡፡‹አይ በጣም የምወደው ወንድሜ የሚካኤል ወንድም ስለሆነ በእሱ እይን  እሱንም ማየት ጀምሬለው ማለት ነው..›ስትል ለራሷ ማብራሪያ መስጠት ብትሞክርም ሊያሳምናት ግን አልቻለም፡፡

ደግሞ ስለሴሰኝነቱ..በየጊዜው ስለሚቀያይራቸው ሞዴል መሳይ ሴቶች፤ ከዝነኛ እንስቶች ጋር ስለሚጀምረው የፍቅር ግንኙነትና ስለመለያየቱ …ከስራው እኩል አንዳንዴም ከስራው በላይ ነው ሚያወራው፡፡እና ለእንደዚህ አይነት ሴት አውል የማይጨበጥ ሙልጭልጭ ወንድ ምን አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው….?መልስ የላትም፡፡ግን አሁን ልታገኘውና ልትጋፈጠው ወስናለች..ዝግጅቷንም ጨርሳለች፡፡
///          
ፀደይ ባደረገችው ጥናት እና በሰበሰበችው መረጃ መሰረት  የሚካኤል መንታ ወንድም የሆነው ዘሚካኤልን ለማናገር አንድ ብቸኛ መንገድ ብቻ እንዳላት ተረድታለች፡፡በሳምንት ሶስት ቀን በሚሰራበት በከተማዋ ታዋቂ  ናይት ክለብ  ተገኝታ እድሏን መሞከር ፡፡ከእሷ ባህሪ አንጻር እንደዛ አይነት ቦታ ተገኝታ የማታውቀውን ሰው ማናገር በጣም ከባድ የቤት ሰራ ነው፡፡ቢሆንም የግድ ልትወጣው የሚገባ ተግባር እንደሆነ እራሷን አሳምናለች፡፡

ባለፉት ሁለት ቀን ውስጥ የተባለው ናይት ክለብ ውስጥ በውድቅት ለሊት በመገኘት እሱ ሲዘፍን እና በቀበጥ አድናቂዎቹ ሲሞገስና ሲሸለም መመልከት ብትችልም  እሱን ተጠግቶ ለማናገር ያደረገችው ሙከራ ግን ሙሉ በሙሉ  አልተሳካላትም ነበር፡፡ዛሬ ግን የግድ ሊሳካላት ይገባል..ምከንያቱም ሰርጉ ከአምስት ቀን  በኃላ  ነው፡፡ዛሬ አግኝታ ካላናገረችው…ወደእዚህ መጥታ ሌላ ሙከራ የምትሞክርበት ሌላ እድል የላትም፡፡
👍6213🥰3👏1
ልክ ስምንት ሰዓት አካባቢ  ወደ ሽንት ቤት ሄደችና  አስባና  አቅዳ  አስመስላ ያሰፋችውን የቤቱን ሴት አስተናጋጆች ልብስ ለበሰችና ሰሞኑን ባጠናችው መሰረት   ሙዚቀኞች ለማረረፊያና ለመዘጋጃ ወደሚጠቀሙበት ከፍል ሄደችና እንደምንም ተሹለክልካ ከጀርባ በኩል አልፋ  ስራ እየሰራች በማስመሰል መጠበቅ ጀመረች፡፡

በመድረክ ላይ የሚያቀርበውን ዝግጅት ካጠናቀቀ በኃላ በሁለት ጋርዶች  ተጅቦ ሲመጣ ተመለከተች…ፈጠን አለችና በረፉን ከፍታ በመግባት መልሳ ዘግታ ዙሪያ ገባውን ተመለከተች፡፡ተንደረደረችና ከግዙፍ ጥቁር ቆዳ ከለበሰው ሶፋ ጀርባ ሄዳ ተወሸቀች…ብዙም ሳይቆይ የበራፍ መከፈትና የእግር ኮቴ ሰማች….የልቧ ድውድውታ ከእራሷም አልፎ ለእሱ የሚሰማ መስሎ ተሰማትና ሰጋች፡፡

‹‹የአንድ ሰዓት ረፍት አለኝ….ትንሽ አረፍ ልበል…አስር ጉዳይ ላይ ቀስቅሱኝ››ከጋርዶቹ ጋር ነው የሚያወራው፡፡

‹‹እሺ..ተኛ እንቀሰቅስሀለን››

አጮልቃ ስታይ ጋርዶቹ ከውጭ በራፉ ላይ ሲቀሩ እሱ ከውስጥ ሆኖ ዘጋባቸው..በራፉን ቀረቀረና…ከላይ የለበሰውን ጃኬት አወለቀ …ወደክፍሉ መሀል ሄደ…ከዛ የለበሰውን ቲሸርት አወለቀ….በተደበቀችበት ሆና መላ ቁመናውና ተመለከተች…ጠንበልል የሚባል ወንዳወንድ ነው፡፡ከወንዶች ይልቅ የሴቶች የሙዚቃ አፍቃሪዎች በእጥፍ እንደሚወዱት ታውቃለች፡፡ይሄ የሆነው ስርቅርቅ ድምፁ ከወንዶች ይልቅ ሴቶችን የማቅለጥ ተፈጥሮው ስውር ችሎታ ስላለው ሳይሆን የሴቶችን ልብ የማቅለጥ አቅም ያለው ወንዳወንድ ቁመናና  አቅልጥ ውበት ስላለው እንደሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ቲሻርቱን ሲያወልቅ ከወገቡ በላይ ርቃኑን ቀረ…ሆዱ በግማሽ በጥቁር ፀጉር የተሸፈነ ነው፡፡በዛ ላይ አብረቅራቂ ሰንሰለት መሳይ ሀብል ስላንጠለጠለበት ቀልብ ይስባል፡፡

በተደበቀችበት ሆና የለበሰችውን የአስተናጋጅ ልብስ አወለቀችና እዛው ስሯ ወለል ላይ ጣለችው፡፡ሱሪውን ለማውለቅ ቀበቶውን መፍታት ሲጀምር ተስፈንጥራ ከተደበቀችበት ወጣችና ከፊት ለፊቱ ተደንቅራ ቆመች፡፡

በከፍተኛ መገረም እነዛ ተንከባላይ ሰማያዊ አይኖቹን ተከለባት፡፡አይኖቹ ልብን በቀላሉ ሰርስረው የሚገቡ አስማታዊ ስለሆኑ መቋቋም ከበዳት፡፡

‹‹አቤት ..እዚህ እንዴት ገባሽ?››የቁጣ  ሳይሆን የመደነቅ ቃና ባለው ድምፀት ጠየቃት፡፡

‹‹በብዙ ድካም ….ተደብቄ..››ስትል ድፍን ያለ መልስ ሰጠችው፡፡

አፈቀርንህ ..እራሳችንን እናጠፋለን ..ምናምን የሚሉ በእሷ እድሜም የሆኑ ከእሷ ያነሱ ወጣቶች በየእለቱ የተላያዩ አይነት ገጠመኞችን በመፍጠር ሊያገኙትና ሊዳስሱት ስለሚሞክሩ ይሄንንም ከዛ የተለየ ነው ብሎ አላሳበም…

ፀደይ የሚንደቀደቀውን የልብ ትርታዋን ለመቆጣጠር እየታገለች  በቀጣይ ምን ብላ ወደመጣችበት ጉዳይ እንደምትገባ እያሰላሰለች ሳለ…ለግላጋ እጁን በመዘርጋት በቀጭን ወገቧ አዙሮ ያዘትና በኃይል ጎትቶ ግማሽ እርቃን ከሆነ ሰውነቱ ላይ ለጠፋት፡፡

ፈፅሞ ይሆናል ብላ ያልጠበቀችው ስለነበረ …አንገቷን ቀና አደረገችና በልምምጥ ተቁለጭላጭ አይኖቾን በተንከባላይ አይኖቹ ላይ ተከለች፡፡በቁመት ቢያንስ በ40 ሳ.ሜትር ይበልጣታል…ስለዚህ እሷ አንጋጣ ስታየው እሱ ደግሞ አዘቅዝቆ ነው የሚያያት፡፡

.. የገባችበት እውነታ አምኖ መቀበል ነበረበት።አስደናቂ ነበር ። እንዲለቃት ልትጠይቀው በጣም ፈልጋለች..ግን ቃላትቱን ከአንደበቷ ማውጣት አልቻለችም፡፡ ይባስ ብሎ አፉን አሞጥሞጦ ወደታች ዝቅ አለና ከንፈሯን በከንፈሩ ጎረሰው…ሳትወድ በግዷ አይኗን ጨፈነች….‹‹ጌታ ሆይ ድረስልኝ››ስትል በውስጦ ልትፀልይ ሞከረች፡፡እንደክንፍ የተዘረጋውን እጇን ያለፍቃዷ ወደ እሱ ላከችና በወገቡ ዙሪያ ጠመጠመች፡፡ምላሱን ጎልጉሎ አፏ ውስጥ ከተተውና  ሲያሽከረከረው..አቃሰተች…ይሄ የመጀመሪያ ጊዜ ገጠመኞ ነው…ገላዋ ከወንድ ገላ ጋር እንዲህ ሲጣበቅና ሲቀልጥ ከስድስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
የዚህ ዝነኛና ሀብታም ድምጻዊ ሴት አውልነት የታወቀና የየእለት የታብሎይዶችና ዩቲዩቦች ማድመቂ ዜና ነው፡፡ለእሱ በእየእለቱ እንደሚመገበው ቁርስና ምሳ  ሴቶችን መቀያየርና በፍቅር በማቅለጥ ከዛም አልፎ ለወሲብ ወደአልጋ ላይ መጎተት ተራና የተለመደ ነገር ነው..ለእሷ ግን ከዛ በጣም የተለየ ነው፡፡ታዲያ አሁን እንዴት ተቃውሞ አልባ ሆነች..?እንዴት ለመሳም ሲያቅፋት ለመታቀፍ እንዲህ ቸኮለች..ሲስማትስ እንዴት መልሳ ሳመችው ?ለአመታት በውስጧ የተዳፈነው የወሲብ ረሀብ ድንገት ገንፍሎ  ከቁጥጥር ውጭ ስላደረጋት ይሆን?፡፡‹‹አይ እንደዚህማ ተራ ሴት አልሆንም…. በፍፅም…እንደምንም ታግላ ከንፈሯን ከከንፈሩ አላቀቀች….ከዛ ከእጆቹ ሾልካ ወጣችና አንድ ሜትር ወደኃላዋ ፈንጠር ብላ  ቆመችና በእጆቾ ጣቶች ለደቂቃዎች ሲሳማት የቆየውን ከንፈሯን እየነካካች  ቆመች ፡፡
እሱም በቆመበት እየተመለከታት ምን እንዳልተመቻት እያሰላሰለ ነው፡፡የሆነ ነገሯ ልቡ በፍጥነት እንዲመታ አድርጎታል፡፡፡ቆንጆ ነች፡፡ግን ደግሞ በእየእለቱ ስዕል ሚመስሉ ብዙ ቆንጆዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ በመልኳ ልታስደምመው አትችልም  ፡፡ማንኛዋም ሴት እሱ ፊት ለመቅረብ ስትመጣ ተበድራም ሆነ ተለቅታ ውድ ልብስ ለብሳ ፤ሜካፖን ተለቅልቃና ተቆነጃጅታ  ነው፤ይህቺ ፊት ለፊቱ ያለችው ልጅ ግን ዝም ያለ ፍዝ አለባበስ ነው ለበሰችው፡፡ኦሞ ቀለም ያለው ጅንስ ሱሪ ከነጭ ቲሸርት ጋር ለብሳለች፡፡፡አንገቷ ላይ ሮዝ ቀለም ያለው ሻርፕ ጣል አድርጋለች፡፡እና ነጭ ስኒከር ጫማ ተጫምታለች በቃ፡፡በዛ ላይ የለበሰችው ጅንስ ሱሪ ጉልበቱ ላይ ተቦጭቋል…ለፋሽን ተብሎ የተቦጨቀ ሳይሆን ምስማር የቦተረፈው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡
ፀደይ ረጅምና   ጥልቅ  ትንፋሽ ወሰደች። መረጋጋት አለባት። እሷ እዚህ ለትልቅ ተልዕኮ ነው የተገኘችው፡፡በጣም አስፈላጊ  ለሆነ ተልዕኮ …. እና በቀላሉ በልብ ድካም ተይዞ ለመዝለፍለፍ ጊዜ አልነበራትም - ይህ የጀመረችው የእብደት  አካሄድ በእቅዷ ላይ ከባድ መፋለስ ይፈጥርባታል።የሁለት ጓደኞቾን የስረግ ካርድ ሰጥታው  ግብዣዋን ላይ መገኘት እንዳለበት ማሳመን አለባት  ፡፡

‹‹ይቅርታ እኔ ለዚህ አልመጣሁም››አለችው፡፡

‹‹ለዚህ ማለት?››በግማሽ መገረምና በግማሽ ፈገግታ ጠየቃት፡፡

‹‹ማለቴ ያው ይገባሀል ..ለመሳሳምና ለ…..››አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እኔ ደግሞ ለዛ መስሎኝ በጣም ተነቃቅቼና ተደስቼ ነበር››አለና ፈገግ አለ፡፡

‹‹ይቅርታ..ስትስበኝ መሳብ..ስትስመኝም መሳም የለብኝም ነበር››

‹‹ግን አድርገሽዋል..እና ሳስበው ደግሞ መጥፎ አይመስለኝም››

‹‹ሊሆን ይችላል…ግን አግባብ ስራ አልነበረም..ይቅርታ…ጊዜህን አልሻማብህ የመጣሁበትን ጉዳይ ልንገርህና ልሂድ››

‹‹ምንድነው..ምን ልርዳሽ?››

የጅንስ ሱሪዋ የኃላ ኪስ ገባችና አንድ ፖስታ አወጣችና አቀበለችው፡፡

‹‹ምንድነው?››እያለ እጁን ዘርግቶ ተቀበላት..ፖስታውን ሲመለከት ወዲያው ወደአእምሮ የመጣለት በሆነ ችግር ለምሳሌ የሆነ ቤተሰብ ታሞባት ለህክምና እርዳታ እየጠየቀች ነበር የመሰለው፡፡

እንደዚህ አይነት ነገር በተለያየ መንገድ ሁል ጊዜ ስለሚደርሱት ብዙም ሚደንቅ አይደለም..በዚህ መንገድ ግን በለሊት ተደብቃና ተሹለክልካ ማረፊያ ክፍሉ ድረስ ገብታ በዚህ መልክ  እርዳታ የጠየቀችው ሴት ስለሌለች ተገርሞበታል፡፡

ወደራሱ አስጠግቶ ሲያየው..ከአሰበው የተለየ ጉዳይ  ነው፡፡‹‹የምን ሰርግ ነው…ልታጋቢ ነው እንዴ..?ሰርግሽ ላይ እንድገኝ ልትጠሪኝ ነው በዚህ መንገድ በዚህ ሰዓት የተገኘሽው?››
👍677
በተራዋ ፈገግ አለች፡፡‹‹አይ..አይደለም…የጓደኛዬ አዲስአለም እና የወንድምህ የሚካኤል የጋብቻ ስነስርአት በፊታችን እሁድ በአዳማ ይካሄዳል…በዛ ሰርግ ላይ ተገኝተህ ወንድምህን እንድታስደስተውና እንድታስገርመው እፈልጋለው››፡፡

‹‹እና ለዚህ ነው ….ከአዳማ ድረስ መጥተሸ በዚህ ውድቅት ለሊት ክፍሌ የተገኘሽው?››

‹‹አዎ ..አንተን ለማግኘት ያለፉትን ሶስት ቀናት ስመላለስ ነበር..ይሄን ሁሉ የለፋሁት ያንተ ሰርጉ ላይ መገኘት ለወንድምህ ምን ያህል አስደሳች እንደሚሆን ስለማምንበት ነው››

‹‹በእውነት !!በጣም ነው ያስደመምሽኝ..ወንድም የለኝም እንጂ ቢኖረኝና ብገኝ ደስ ይለኝ ነበር››

‹‹ተው እንጂ..እስከማውቀው ድረስ…አንተም ከእሱ በስተቀር እሱም ካንተ በስተቀር ሌላ ዘመድ የላችሁም…ከዚህ በፊት በምንም ሁኔታ ብትጣሉና ብትቀያየሙ ያለፈውን ይቅር ተባብላችሁ ወደፊት መቀጠል አለባችሁ ..ደግሞ ሰርግና ሞት አንድ ነው ይባል የለ….እባክህ!!››

‹‹አዝናለው..ነገርኩሽ ..እውነቴን ነው… እንዳልሽው  እኔ ምንም አይነት ዘምድ የለኝም  ወንድም ጭምር..ስለዚህ አዝናለው››

‹‹እኔም አዝናለው….በምትዘፍናቸው ዘፈኖች ስለፍቅርና ስለይቅርታ ከደርዘን በላይ ሙዚቃዎችን ተጫውተሀል….ቃላችውን የማይኖሩ ሰዎች ያበሳጩኛል››አለችውና በብስጭት ወደበራፉ መራመድ ጀመረች፡፡

‹‹ይቅርታ ጠብቂኝና የምትሂጂበት ድረስ ሸኝሻለው››

‹‹አይ ይቅርብኝ››አለችና የተቀረቀረውን በራፍ ከፍታ ወጣችና መልሳ ዘግታ በግርምት የሚያዬትን ቦዲ ጋርዶች ገፍትራ ተሰወረች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍564
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ //// ‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡›› ‹‹እናቱና እህቱ የሞቱ ቀን ነው የተሰወረው፡፡ሁለቱ በመልክም ሆነ በአመካከት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑት  ወንድማማቾች ከከተማ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ ..ሳሎኑ ፍፁም ትርምስምስ ብሎ ያያሉ ..ግራ በመጋባት  ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ እናታቸው ልቧ ላይ ነጭ አብረቅራቂ ቢላዋ ተሰክቷባት…»