🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_18
“ታዲያ እንዲህ የሚዝቱ ከነበረና ከሟች ጋር አብረው ያመሹ ከሆነ ያንን ዛቻዎትን ላለመፈጸምዎ ምን ማስረጃ አለዎት?” "በመጀመሪያ ደረጃ ያኔና ዛሬ የተለያዩ ጊዜያቶች ናቸው። ያኔ በየዋህነት ያበላሸሁትን ህይወቴንና በዛ ምክንያት የደረሰብኝን ስቃይ እንኳንስ ልደግመው ላስበውም አልፈልግም፡፡ እኔ ዛሬ በጣም የምወዳት እጮኛ የአለችኝና የራሴን ቤተሰብ መስርቼ የተደላደለ ኑሮ ለመኖር የሚስችለኝ ገቢ ያለኝ ሰው ሁኜ ሳለ፤ ያ በወጣትነት ዘመን የነበረው የአፍላነት የፍቅር ስሜት ገፋፍቶኝ በቂም በቀል ህይወቴን የማበላሽበት ምክንያት በፍፁም የማይታሰብ ነው፡፡ ወደ ተጠየቅሁት ጥያቄ ለመመለስ፤ የዛን ዕለት ከእሷ ጋር በሰላም ስንጫወት አምሽተን በሰላም ተለይቼ እንደሄድኩና ከዛ በኋላ ችግሩ እንደተፈጠረ አስተናጋጁ በግልጽ አይቷል፡፡ ፖሊስም ባደረገው የማጣራት ሥራ እኔ ነፃ መሆኔን በማረጋገጡ ለቆኛል" በማለት መለሰ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠበቃዬ እጅግም የማይረቡ ጥያቄዎችን ብቻ ጠይቆ አመሰግናለሁ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ሌላው ቀርቶ አልማዝ ወደነበረችበት አልቤርጎ ድረስ ሄዶ መልዕክት እንዲነግር ኤልሳ እንደላከችው ዲያሪው ላይ አንብቦ ላለ ይህንን እንኳን ለመጠየቅ አልፈለገም፡፡ ዳሩ እሱ እጮኛውን የሚያስወነጅል ጥያቄ እንዲጠይቅ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ውሸት በውሸት ላይ ሲደራረብ በመስማቴ ወንጀሉ እዚህ አካባቢ ተፈፅሟል የሚል ጥርጣሬዬ እየጠነከረ መጣ። ቀጥሎ ለምስክርነት የተጠራው የሆቴል ቤቱ አስተናጋጅ ነው፡፡ የአስተናጋጁን የምስክርነት ቃል ስሰማ በጣም ደነቀኝ፡፡ ተሾመ እሷን ተሰናብቶ ከሄደ በኋላ አንድ ቢራ እንዲያመጣላት ሟች አዝዛው ስለነበር ይህንኑ ይዞ ሲሄድ እኔ ተካሳሹ አብሬ ተከትዬ እንደመጣሁና ለእሱ በሩን ስትከፍት እኔ ገብቼ ከውስጥ በሩን መቆለፌን፡፡ እሱም በሁኔታው ተጠራጥሮ በር አንኳክቶ ሟችን ችግር ይኖር እንደሆን እንደጠየቃትና ከገባውም ሰውዬ ጋር እንደሚተዋወቁና ችግር እንደሌለ ስለነገረችው ጥሎ መሄዱን አስተናጋጁ መሰከረ፡፡ በጣም _ የሚገርመው ግን አንድ ጊዜ ብቻ ካየኝ እንዴት በእርግጠኝነት እኔ መሆኔን ሊያውቅ እንደቻለ ሲጠየቅ፣ ቀኑን በሙሉ እየተመላለስኩ መምጣትና አለመምጣቷን እጠይቅ ስለነበር እንደማይረሳኝና፤ ሟች ከተሾመ ጋር እየተጫወተች ሳለ አንድ ጥግ ቦታ ላይ ተቀምጬ ስከታተላቸው እንደነበር መሰከረ፡፡ ከዛም በኋላ ትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ የእኔና የእሷ ሦስት ጓደኞች በየተራ እየተጠሩ ሲመሰክሩ የአንዳንዶቹ ለስለስ ይበል እንጂ ምስክርነታቸው የእኔን ነፃነት ከማረጋገጥ ይልቅ ወንጀለኝነቴን የሚያጠናክር ነበር። ሁሉም በጣም እንዋደድ እንደነበርና በኋላ ግን ሟች ከዶ/ር አድማሱ
ጋር በፈጠረችው ቅርርብ የተነሳ እኔ በከፍተኛ ሁኔታ እተና እንደነበር መሰከሩ። ስለዚህም ቅናቴ ለመግድል የሚያነሳሳ ስለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ አልነበራቸውም:: በእነሱም ግምት ሟች ጥሩ ጠባይ የነበራትና ከማንም ሰው ጋር ተጣልታ የማታውቅ በመሆኑ ይህንን ይፈፅማል ብለው የሚጠረጥሩት ሌላ ሰው እንደሌለ መሰከሩ:: ይህ ሁሉ ታዲያ የእኔን ወንጀለኝነት የሚያጠናክር እንጂ የሚያቀል አልነበረም:: ዳኛው ጠበቃዬ የመከላከያ ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ለሚያዚያ 5 ቀን 1981 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተው አሰናበቱን:: በዚያችው በተለመደች እሥር ቤት ውስጥ በተለመደው መልኩ ኑሮዬን ለመቀጠል ከፍርድ ቤቱ ወጣሁ:: እስር ቤት እንደገባሁ እራሴ እስኪፈነዳ ድረስ ሰው ሳላናግር ጥግ ቦታ ላይ ቁጭ ብዬ የተሰጡትን የምስክርነት ቃሎች አንዱን ከአንዱ ጋር በማዛመድና በመተንተን የሴራውን ምንነት ለማወቅ መጣር ጀመርኩ፡፡ በእርግጥም እኔን ለመወንጀል ዲያሪው ላይ ከሰፈረው ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ ቅንብር እንደተሰራና ይህንንም እውነት ለማስመሰል አስተናጋጁ ተገዝቶ ሊመሰክር እንደመጣ እርግጠኛ ሆንኩ፡፡ ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ በተሾመና በኤልሳ ተቀነባብሮ በጠበቃዬ አማካሪነት የመጨረሻ ቅርፁን የያዘ ሴራ ነው፡፡ እንደሚመስለኝ ኤልሳ _ ሆን ብላ ከተሾመ ጋር በመመካከር፣ እኔን እንዳገኘች በማስመሰል ደብዳቤ ፅፋ አልማዝ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ካደረገች በኋላ ተሾመ እንዲያገኛት ወደ ሆቴሉ የላከችው እሷ ራሷ መሆን አለባት፡፡ ምናልባት ለክፋት ሳይሆን ከእኔ መለያየቷን ስለምታውቅ እና ዶ/ሩን ከምታገባ ከአክስቷ ልጅ ጋር እንድትጋባ ለማድረግ ብላ ያደረገችው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንንም ትምህርት ቤት ውስጥም ስታደርገው ስለነበር አሁን አታደርገውም ማለት አይቻልም፡፡ እንግዲህ አጅሬ እዚያ ሄዶ ዕድሉን ይሞክራል፡፡ ነገር ግን አሁንም ያው የለመደው መጥፎ አቀባበል ሲገጥመው፣ ጥንትም እንደዛተው በንዴት መኝታ ቤቷ ውስጥ ገብቶ ገድሏት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ኤልሳም በተባባሪነት ልትወነጀል ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም መዋሸት አለባቸው፡፡ እነሱ ነፃ እንዲወጡ ደግሞ የግድ አንድ ሰው መወንጀል አለበት፡፡ ያም ሰው ሌላ ሰው ሳይሆን እኔው ነኝ ማለት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ተከራክሬ ነፃ እንዳልወጣ እነሱ ለእኔ ተከራካሪ ሆነው ቀርበው እውነትን ማዳፈን ነበረባቸውና ይህንኑ ለማሳካት በመፍጨርጨር ላይ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አሁን የማየው የይስሙላ "ተጠየቅ ልጠየቅ" እኔንና ሌላውን ለማሳመን የሚደረግ ትርዒት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡
ቀደም ሲልም ህሊናዬን አንዳች ነገር አሳውሮት ነው እንጂ፣ ኤልሳ እኔ መታሰሬን እንዴት አውቃ ጥብቅና ልትቆምልኝ መጣች? ብዬ መጠራጠርም ነበረብኝ፡፡ እንዲያውም ሊሆን የሚችለው እኔን ጠቁመው ካስያዙ በኋላ ጥብቅና በመቆም ሀቅን አዳፍኖ ለማስቀረት የነደፉት የረቀቀ ሴራ ነው፡፡ እንግዲህ ሴራው ይኼ ከሆነ ደግሞ አራጆቹን ተከትሉ እንደሚሂድ በሬ ሆኛለሁ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ወጥመድ ለመውጣት ደግሞ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ብገነዘብም ምን ላደርግ እንደምችል ግን አንዳችም መፍትኄ ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ ጊዜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር _ አለሚቱ አለፍ አለፍ እያለች መምጣቷ ቀርቶ እጅግ እየዘገየች ብቅ ማለት ጀመረች፡፡ የቤቱን ዕቃ በየተራ እየሸጠች ለራሷም ሆነ ለእኔ የሚያስፈልገንን ነገር እንድታደርግበት ነግሬያታለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የሚሸጠው ነገር ቀስ በቀስ እየሳሳ በመምጣቱና እኔም እንዲህ በቀላሉ እንደማልፈታ ስለተገነዘበች በቁጠባ መጠቀሟ ነበር:: አልፎ አልፎ የመስሪያ ቤት ባልደረቦቼ እየመጡ ገንዘብ ሲሰጡኝ ያቺኑ ሰብስቤ የምሰጣት ቢሆንም፤ ይህም ለእኔና ለእሷ ቀለብ ሆኖና የቤት ኪራይ ለመክፈል የሚበቃ ስላልነበር አጠቃቀሟን መቆጠቧ አግባብነት ነበረው:: ጓደኞቼ እየመጡ ቢጠይቁኝም ነፍሰ ገዳይ አድርገው ስለሚመለከቱኝ ሳይሆን አይቀርም በአንዳቸውም ፊት ላይ የሀዘን ስሜት አላይም፡፡ ሁሉም ሰው ፍቅረኛውን እንደገደለ ቀናተኛ አፍቃሪ እንደሚገምተኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ እያንዳንዱ ስለእኔ ያለው ግምት እንዲህ ይሆናል፣ እንደዚያ ይሆናል ብዬ ከመገመት ውጪ ከሌሎች የምሰማው ነገር አልነበረም፡፡ በአንጻሩ የእሥር ቤት ጓደኞቼ እስከዚህም ስለዚህ ጉዳይ ለማወቅ የሚጨነቁ አልነበሩም፡፡ መግደል ምን እንደሆነና ምን ያህል ሊያጋጥም የሚችል ቀላል ነገር መሆኑን አብዛኛዎቹ አይተውታል፤ ያላዩትም ደጋግመው ሰምተውታልና አይደንቃቸውም:: ያልገደለ ቢኖር እንኳን ያው በሥርቆት የተያዘው ነው:: ከእነርሱም ውስጥ ከፊሉ ጥሩ አጋጣሚ ካጋጠመውና ብዙ ገንዘብ የሚያገኝበት ዕድል ካገኘ ለመግደል ወደ ኋላ የሚል አልነበረም፡፡ እዚህ በተወሰኑ ሰዎች ዘንድ ሰው ገደለ የሚለው ቃል