አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
490 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_20

ዳኛው የሚሰጡትን ውሳኔ ለመስማት ሁሉም ድምጹን አጥፍቶ እያዳመጠ ስለነበር ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ ውሀ እንኳን ጠብ ቢል መሰማቱ አይቀርም ነበር፡፡ ዳኛው የክርክሩ ጠቅላላ ሂደት እንዴት እንደነበር ካብራሩ በኋላ ይህ ሁሉ ታዛቢ ሰው በጉጉት የሚጠብቀውን የፍርድ ውሳኔ ማሰማት ጀመሩ፤ “አቶ አማረ አስረስ መጋቢት 15 ቀን 1980 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አዲስ አበባ፣ ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ደብረወርቅ ሆቴል ውስጥ፣ ሰውን ለመግደል አስበውና አቅደው፣ ሟች ወይዘሪት አልማዝ አስፋውን ከእኔ ሌላ ሰው አፍቅረሻል በሚል ምክንያት በቅናት መንፈስ ተገፋፍተው ፍቅረኛቸውን የለምንም ርህራሄ ራሷን እንደገደለች የሚያስመስል ደብዳቤ እንድትፅፍ ካደረጉ በኋላ ገድለው ሰቅለዋታል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ግለሰቡ ይህንን ሁሉ ወንጀል የፈፀሙ ሆነው ሳለ ወንጀሉን አምነው ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ በወንጀላቸው ሳይፀፀቱ ከወንጀሉ ነፃ ነኝ በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሹ ወንጀሉን በቅናት መንፈስ ተነሳስተው መፈፀማቸው በምስክሮችና በማስረጃ ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ተከሳሹ አቶ አማረ አስረስ ጥፋተኛ ናቸው በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡''

ዳኛው የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ አቃቤ ሕግ በተሰጠው የጥፋተኛነት ውሳኔ ላይ የቅጣት አስተያየት ካለው እንዲሰጥ ጋበዙ፡፡ አቃቤ ሕግም የተሰጠውን ዕድል በመጠቀም ምን ያህል ጭካኔ በተሞላው መንገድ ሆን ብዬና ተዘጋጅቼ ግድያውን እንደፈፀምኩ በማብራራት የመጨረሻው ከባድ ቅጣት እንዲበየንብኝ ዳኛውን በሕግ ቃላት ለማሳመን ጥረቱና ትንቅንቁን አጠናከረ፡፡ በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ዕድል የተሰጠው ተረቺው ጠበቃዬ፤ "እኔን ነፃ ለማውጣት ሲከራከር እንዳልነበር ሁሉ አሁን ግን መረታቱን ተቀብሎ፤ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ወንጀል ሰርቼ እንደማላውቅ በተደጋጋሚ በመጥቀስ የቅጣቱ መጠን እንዲቀልልኝ ተማፀነ፡፡ ዳኛው የቅጣት ማክበጂያና ማቅለያ አስተያቶችን ከሰሙ በኋላ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 19/1982 ዓ.ም ቀን እንድንቀርብ በማዘዝ አሰናበቱን፡፡ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ብዬ ሳስብ እዚሁ ላይ ተጠናቀቀ። ከዚህ በፊት ከስሼም ሆነ ተከስሼ ፍርድ ቤት ቀርቤ ስለማላወቅ የችሎቱ ሂደት የተጠናቀቀበት ሁኔታ ባይገባኝም በአቃቤ ሕግና በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ የማየው የደስታ ሳቅና፣ በኤልሳና በጠበቃዬ ፊት ላይ ያየሁት የመከፋት ስሜት በእርግጠኝነት በእኔ ላይ እንደተፈረደ አመላክቶኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርዱ የሞት ፍርድ፤ ዕድሜ ይፍታህ፤ ወይም የተወሰነ እስር ዘመን መሆኑን ለይቼ ለመረዳትም ይሁን ለመገመት አለመቻሌ ግራ አጋብቶኛል፡፡ እስር ቤት ተመልሼ እንደገባሁ ግን የጥፋተኝነት ውሳኔ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሌላ ቀጣይ የፍርድ ሂደት እንዳለ መረዳት ቻልኩ፡፡ እንደእኔ ከሆነ ግን ጥፋተኛ መሆኔ ከታመነበት ጊዜ ሳይፈጁ ፈርደውብኝ ቁርጤን ቢነገግሩኝ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ነገር ግን እንደሚመስለኝ እንዲህ የፍርድ ሂደቱን በማጓተት እስረኛው ምን ይፈረድብኝ ይሆን? ይገድሉኝ ይሆን? ዕድሜ ልክ ይወሰንብኝ ይሆን? ሃያ ዓመት ያስሩኝ ይሆን? ወዘተ.. እያለ ቀን መጨነቁ፣ ሌሊት እንቅልፍ ማጣቱ ከፍርድ በፊት የሚቀጣው ቅጣት ተደርጎ ሳይወሰድ አይቀርም፡፡ የፍርድ ውሳኔ የሚስጥበት ቀን ደርሶ ፍርድ ቤት ቀረብኩ፡፡ ሐሰት በእውነት ላይ የበላይነት አግኝታና የተተበተበው ሴራ ሳይፈታ፣ እጄ ከተያዘበት ዕለት አንስቶ የሃያ ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደብኝ፡፡ ውሳኔውን ስሰማ ጉልበቴ አካላቴን መሸከም እስከሚያቅተው ድረስ መብረክረክ ጀመረ። ንዴትና ፍርሀትም ሰውነቴ ውስጥ ተቀላቅለው በፈጠሩት ትኩሳት የተነሳ መላ ሰውነቴ በላብ ተዘፈቀ፡፡

እንግዲህ እነሆ ያቺ ስጠብቃት የነበረች ውድ ቀን ደርሳ የጠበቅኋት ውሳኔ ባልጠበቅሁት ሁኔታ ተፈረደች:: እኔም ባልሰራሁት ወንጀል ተፈርዶብኝ የታስርኩበት አራት ዓመት ሲቀነስ ለቀጣይ አስራ ስድስት ዓመታት ልታሰር ተወስኖብኛል። እርግጥ ለእኔ ብዙም ለውጥ የለውም። ከአልማዝ ተለይቼ ያሳለፍኳቸው ዓመታት በሙሉ በብረት አጥር ውስጥ ተከልዬ በፖሊስ እየተጠበቅሁና በአንድ ቦታ ተወስኜ አለመኖሬ ካልሆነ በስተቀር ከእሥር የተለዩ ስላልነበሩ ውጪው ዓለም እስከዚህም የሚያጓጓኝና አጥብቄ የምሻው አልነበረም፡፡ ድሮስ ቢሆን ነፃ በመሆኔና እንደልብ በመንቀሳቀሴ መች ተደስቼ አውቃለሁ? ይልቁንም የተሻለ ደስታን ያገኘሁት እሥር ቤት ውስጥ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ውስጤ ይህንን ይቀበለው እንጂ በዓይኔ የማየው ነገር ህሊናዬን እየተፈታተነ ያበሳጨኝ ጀመር። በፖሊስ ታጅቤ ከችሎቱ በመውጣት ላይ ሳለሁ ድንገት ዓይኔን ወደ ኋላ ወርወር አደረግሁ፡፡ ዶ/ር አድማሱ በደስታ እየተፍለቀለቀ አብረውት ከመጡት ጋር ብቻ ሳይሆን አጠገቡ ከቆሙትና ከማያውቃቸው ሰዎችም ጋር እየተቃቀፈ ይሳሳማል፡፡ በእሱ እምነት የፍቅረኛው ገዳይ በሠራው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት አግኝቷልና ለምን አይደሰት? ለምንስ አይቦርቅ? ወደ እስር ቤት እንደተመለስኩ እስረኛው ሁሉ የተፈረደብኝን እንደሰማ ክፉኛ አዘነ፡፡ ቀደም ሲል በሌሎች ላይ የሞት ፍርድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፍርድ ሲሰጥ እምብዛም የሚያዝን ሰው አልነበረምና ለእኔ ማዘናቸው ገረመኝ:: በተቃራኒው እኔ ከዚህ በፊት የማዝነው እስረኛ ሲፈረድበት ሣይሆን ሲፈታ ነበር፡፡ አለሙና የእሥር ቤቱ ካቦ ሲፈቱ አዝኛለሁ፡፡ ከቤተሰቦቻችን አንድ ሰው ጥሎኝ ወደ ውጪ ሀገር ለዘላለሙ ላይመለስ እንደሄደ ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ከተፈረደብኝ ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ጠበቃዬ አስጠራኝ:: በተፈረደብኝ ፍርድ ተስፋ እንዳልቆርጥ፣ ይግባኝ እንደሚልና እኔን ለማስፈታት የተቻለውን ያህል እንደሚሞክር ቃል ገባልኝ:: ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሳየው ግን ደስ አለኝ፡፡ ምናልባት ሃያ ዓመት እንደተፈረደብኝ ሳውቅ መብረክረኬ አሊያም ጠበቃዬ የሚፈልገውን በማግኘቱ ዳግመኛ አይመጣም ብዬ ገምቼ ስለነበር፣ መምጣቱን እንዳየሁ እውነትም ከልቡ እየተከራከረልኝ ነው ብዬ አስቤ ሊሆን ይችላል፡፡ እርግጥ ፈርቼም ሊሆን ይችላል፡፡ ትንሽ ቆይቼ ይፈቱኛል እንጂ እንዲህ ባልሰራሁት ወንጀል ሀያ ዓመት ይፈረድብኛል ብዬ አስቤ ስላልነበር ውሳኔውን ስሰማ ብፈራ አሊያም ብደናገር የሚደንቅ አልነበረም:: ከዚህ በላይ ደግሞ የመጨረሻው ፍርድ

ሲፈረደብኝ በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ ያየሁትን የደስታ ስሜትና ፈገግታ ላስታውስ መኖርን ፈለግሁ፣ መፈታትንም ተመኘሁ። እስር ቤት ውስጥ እኔና ጠበቃዬ ብቻ በአንዲት ክፍል ውስጥ ፊት ለፊት ተቀምጠን ያንን ሊፈታው ያልቻለውን እንቆቅልሽ መፍታት ላይ እንድረዳው በማሰብ ወደ ኋላ እየተመለሰ ታሪኮቹን በመተረክና በየጣልቃው በዚያው ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል የማውቀው ነገር ካለ ይጠይቀኝ ጀመር። ይህም ቢያንስ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ነገር ካለ እንዳስታውስ በማሰብ መሆኑ ስለገባኝ በጥንቃቄ እያዳመጥኩ መልስ እሰጠው ነበር።ከምስጠው መልስ ውስጥ የሚጠቅመውን አግኝቶ ይሁን ወይም ለእኔ ትኩረት መስጠቱን ለማሳየት እንደሆነ ባይገባኝም እየመረጠ ከጻፈ በኋላ፤ “አቶ አማረ፤ እንግዲህ ከዚህ በፊትም እንደነገርኩህ የአንድ በሽታ የመጀመሪያው ሀኪም ራሱ በሽተኛው ነው፡፡ መድሀኒቱን ባያውቅ እንኳን የቱ ጋ እንደሚያመው ከሀኪሙ በፊት አስቀድሞ የሚናገረው እሱ ነው:: ከዚያ በኋላ ነው ሀኪሙ እዛ ቦታ ላይ ምርመራውን የሚጀምረውና መድሀኒቱንም የሚያዘው:: ስለዚህ አንተም በበኩልህ በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሊሆኑ
👍301👏1
የሚችሉ መረጃዎች ካሉ ለማስታወስ ሞክር፡፡ ማለትም ልትረዳኝ ይገባል“ አለ፡፡ እውነቱን ነው፤ እሱ ያለምንም ክፍያ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ላይና ታች ሲል እኔ ግን ላቀረበልኝ ጥያቄ ብቻ መልስና መረጃ ከመስጠት ውጪ ራሴን ለማዳን ያደረኩት ተጨማሪ ጥረት አልነበረም:: አሁን ሁሉም ነገር ካለቀ በኋላ ደግሞ ላደርገው የምችለው ነገር የለም፡፡ ቢኖርም የፈሰሰ ውሀ ለማፈስ የመሞከር ያህል ሆኖ ተሰማኝ፡፡ እሱ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ውትወታውን ቀጠለ፡፡ “አቶ አማረ፤ ለሁላችንም እንቆቅልሽ የሆነ ነገር አለ፡፡ ግን ይህንን እንቆቅልሽ መፍታት ያለብህ አንተ ነህ። እኔ በተፈረደው ፍርድ ላይ ይግባኝ ብያለሁ፡፡ ነገር ግን የማቀርበው አዲስ ነገር ስለሌለ በውስጤ ባዶነትና የተሸናፊነት ስሜት ይሰማኛል። ስለዚህ አንድ ከዚህ ቀደም ያልሰማሁትን አዲስ ነገር መስማትና ያላገኘሁትንና ያልደረስኩበትን አዲስ መረጃ ማግኘት እሻለሁ:: ይህ መረጃ ደግሞ ተዳፍኖ ወይም ተደብቆ ይሆናል እንጂ ጠፍቶ ሊቀር አይችልም:: ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያንዣብብኝ እንጂ ከዚህ ድርጊት ጀርባ እውነት ስለመኖሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እውነቱ ደግሞ የጠፋ እስኪመስል ድረስ ተዳፍኗል፡፡ ስለዚህ እኔ ብቻ ሳልሆን አንተም ይህንን ሐቅ በማውጣትና ሐቁን በመፈለግ በኩል ጠንክረህ ልትረዳኝ ይገባል፡፡ አለበለዚያ ይግባኙ ምንም ዓይነት ውጤት አይኖረውም:: በተለይ ዋናው እንቆቅልሽ ያለው አንተና እሷ ልትለያዩ በቻላችሁበት መንስዔ ላይ ነው:: እሷ አንተ ስለከዳሃት እንደተለያያችሁ ስትናገር፣ አንተ ደግሞ እሷ ስለከዳችህ መለያየታችሁን

ገልጸሃል፡፡ ግን ሁለታችሁም ብትሆኑ ለመለያየታችሁ እኔ መንስኤ ነኝ ብላችሁ አልተቀበላችሁም:: ስለዚህ እዚህ አካባቢ የተሰወረው ወይም የተዳፈነው ሐቅ በግልጽ መውጣት አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ አንተ እውነቱን ሳትደብቅ ልትነግረኝ ይገባል፡፡ ሌላው ቢቀር ላልሆነ ነገር እየለፋሁ ከሆነ የእኒ ልፋት ሊያሳዝንህ ይገባል'' አለኝ፡፡ እኔም ባነጋገሩ እጅግ አድርጌ ከውስጤ አዘንኩ:: አሁንም ከብዙ ጊዜ በኋላ እኔ በነገርኩት ነገር አለማመኑን ስረዳም የእሱ ብቻ ሳይሆን የእኔም ልፋት ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ:: ስለዚህ ባላመነው ነገር ተከራክሮ ነፃ ያወጣኛል ብዬ መገመት ጅልነት መሆኑንም ተገነዘብኩ:: ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? ዕድሌ ሆኖ የምናገረውን የሚያምንም ሆነ ንፁህ መሆኔን የሚቀበል ሰው አላየሁም:: ግን ምን አማራጭ አለ? ወይ እውነቱን ደጋግሞ በመናገር ከተቻለ ማሳመን አለበለዚያ መናገርን ማቆም ነው፡፡ መናገርን ማቆም ማለት ደግሞ ከራሴ በላይ ብዙ የደከመልኝን ጠበቃዬን ጭምር ማስከፋት ነውና ላሳምንበት የምችለው ነገር ካለ ብዬ ማሰላሰሉን ተያያዝኩት:: አእምሮዬ ተንቀሳቀሰ፡፡ ብዙ አወጣሁና አወረድኩ፡፡ ትዝታዎቼን ሁሉ አገላበጥኳቸው፡፡ እሷ የጻፈችው ደብዳቤ ትዝ አለኝ፡፡ ደብዳቤው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝና ከዚያ ወስዶ እንዲያነበው ስነግረው ልክ ያልጠበቀውን ወሬ የሰማ እስከሚመስል ድረስ ከመቀመጫው ተነስቶ ሳይሰናበተኝ ተጣድፎ ወጣ፡፡ ግራ ተጋባሁ! የሚፈልገውን ነገር በማግኘቱ ተደስቶ ይሁን ወይም _ በአመላለሴ ተበሳጭቶ ይውጣ ግን መለየት አልቻልኩም፡፡ ቢደሰት ኖሮ ቢያንስ ተሰናብቶኝ ይወጣ ነበር፡፡ ምናልባት ከእኔ ብዙ ነገር ሲጠብቅ ቆይቶ እኔ ግን አመላለሴ በአጭሩ ስለነበር የማፌዝ መስሎት ይሆን እንዴ? በማለት ተጠራጠርኩ፡፡ ግን ብዙም አልተጨነቅሁ፡፡ በማይሆን አጉል ተስፋ ተሞልቼ ነፃ እወጣለሁ ብዬ ከማሰብ ይልቅ እውነቱን ተቀብዬ ቀሪ ሕይወቴን እንደምኖር ኖሬ ማሳለፉ ሳይሻል አይቀርም ብዬ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ወደ ክፍሌ እንደተመለስኩም በይግባኙ ላይ ተስፋ ቆርጬ የእሥር ዘመኔን መደመርና መቀነስ ጀመርኩ፡፡ አሁን ዕድሜዬ ሰላሳ ሁለት ዓመት ነው፡፡ እዚህ ላይ የታሰርኩበትና የአመክሮ ጊዜ ተቀንሶ ቀሪው አስራ ስድስት ዓመት ሲደመር እሥሬን ስጨርስ አርባ ስምንት ዓመት ይሆነኛል ማለት ነው:: ስለሆነም ከእስራት ስፈታ ቢያንስ ያንን ዶክተር ለመበቀል የሚያስችል በቂ የአካል ብቃት ይኖረኛል ማለት ነው:: ዳሩ ይህንን ማሰቤ ጅልነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለምን ቢሉ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና በጡንቻ መመካት ድሮ ቀርቷል፡፡ ዛሬ አንዲት ትንሽ ጣት ቃታ ከሳበች ተራራ የሚያክል ሰው ትገነድሳለች::ለዚያች የምትበቃ ጉልበት ደግሞ የሰማንያ ዓመት አዛውንትም ቢሆን አያጡም:: ዋናው ነገር ከአምላክ የተጻፈችልኝ ዕድሜ ከአርባ ስምንት

ዓመት በላይ መሆኗን ማረጋገጥ አለመቻሌ ነው:: ይህንን ደግሞ ማረጋገጥ ስለማይቻል፣ እንዲሆን ከመመኘት ውጪ ሊደረግ የሚችል ነገር ባለመኖሩ አማራጩ እውነታውን ተቀብዬ የተለመደ ኑሮዬን መቀጠል ነው:: ያ ካልሆነ ደግሞ የልቤ ሳይደርስ የተዛባ ፍትሕ ስለባ ሆኜ መቅረቴ የማይቀር ነው:: አንድ ሰኞ ዕለት ስሜ ተጠርቶ ወጣሁ:: ጠበቃዬ ተመልሶ መጥቶ ወይም እጮኛው ያስጠራችኝ መስሎኝ ነበር:: ነገር ግን ሌሎች እስረኞችም እየተጠሩ ሲወጡና እንደተለመደው እጃችን የፊጢኝ እየታሰረ ወደ እስረኛ ማጓጓዢያ መኪና ስንገባ ግራ ተጋባሁ፡፡ ወዴት እንደምንሄድ አጠገቤ የነበረውን እስረኛ ጠየቅሁት:: እስረኛው የሚሄድበትን ቦታ በእርግጠኝነት እንደሚያውቀውና የተማከረ በሚመስል ሁኔታ፤ ''ወዴት ይወስዱናል? ይግባኝ ተብሎልህ ከሆነ ያው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነዋ የሚወስዱህ" አለኝ፡፡ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ በመግባት ላይ ላለሁ ኤልሳና ጠበቃዬ ፈንጠር ብለው ቆመው ሰላምታ ሰጡኝ፡፡ አንድ ነገር ገባኝ፡፡ የመጣሁት ጠበቃዬ ይግባኝ ብሎ መሆኑ ላይ እርግጠኛ ሆንኩ:: ይግባኙ አዲስ ነገር የሚፈጥር ባይሆንም በተስፋ መኖርም ጥሩ በመሆኑ ይግባኝ በመጠየቁ ደስ አለኝ፡፡ ምን ይታወቃል ጠበቃዬ እንደጠረጠርኩት ሳይሆን ከልቡ እየደከመልኝ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ተጠራጠርኩት እንጂ ያኔ የተፈረደብኝ ዕለት ከፊቱ ላይ የመከፋት እንጂ የተደበቀ የደስታ ስሜት አላየሁበትም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህንኑ ተቀብሎ በተስፋ መኖር ተስፋ ከማጣት የተሻለ ነውና እውነቱን ተቀብዬ አብሬው ለመጓዝ ወሰንኩ፡፡ አብረውኝ የመጡ እስረኞች በየተራ ወደ ችሎት እየተጠሩ ደርሰው ይመለሳሉ:: አብዛኞቹ እንደ እኔ ይግባኝ ያሉ ናቸው፡፡ ተራዬ ደርሶ እዚያቹ አለመድኳት ሳጥን ውስጥ ገባሁ:: ጠበቃዬ ከፊት ለፊት ተቀምጦ በፈገግታ ይመለከተኛል፡፡ ተስፋ አትቁረጥ ተስፋ አለን የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የሚሞክር መሰለኝ፤ አዘንኩለት፡፡ እኔ በሌላ ሁኔታ ብጠረጥረውም እሱ ግን አልተወኝም:: ፈገግታው ከልብ የመነጨ ስለነበር በውስጤ የተስፋ ጭላንጭል ጫረብኝ: ፍርድ ቤቱ እንደተለመደው በሰዎች ተሞልቷል:: ዛሬ ግን እነዚያ የመስሪያ ቤት ባልደረቦቼ አልተገኙም፡፡ እንደድሮው እስር ቤት እየመጡም

መጠየቁን ትተውታል:: የእኔ ነገር ማክተሙን ስለተረዱ ያላግባብ መድከም አልፈለጉም :: ከሃያ ዓመት በኋላ ለሚፈታ እስረኛ ማን መድከም ይፈልጋል የፍ/ቤቱና የይግባኝ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት የኔን ጉዳይ የያዘው ፋይል ተራ እንደደረስ የዕለቱ የችሎት ማብቂያ ሰዓት በመድረሱ ዳኛው ቀጠሮ ለመስጠት አጀንዳቸውን ሲያገላብጡ፣ ጠበቃዬ ነቃና ላቅ ባለ የትሕትና ስሜት፤ “ክቡር ፍ/ቤት፣ ምንም እንኳን አሁን ማስረጃ የማቅረቢያ ወቅት ባይሆንም ተከሳሹ ወንጀሉን አለመፈፀሙን ማረጋገጥ የሚያስችል ማስረጃ እጄ ውስጥ ገብቷል:: በመሆኑም ፍ/ቤቱ ያላግባብ ደንበኛዬ ባልሰራው ወንጀል ሃያ ዓመት እንዳይታሰርና ጉዳዩም በተጓተተ ቁጥር እውነቱ ተደብቆና ተድበስብሶ እንዳይቀር ሲባል መረጃዎቼንና የማቀርበውን ተጨማሪ የሰው ማስረጃ
👍36🥰2🔥1
እንዳቀርብ እንዲፈቅድልኝ በትህትና እጠይቃለሁ" አለ፡፡ ዳኛው ሰዓታቸውን አይተው ይግባኙን እንዲያቀርብ ሲፈቅዱ፣ አቃቤ ሕግ ከመቀመጪያው ተነስቶ፤ “ተቃውሞ አለኝ፣ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ" አለ:: ዳኛው ተቃውሞውን እንዲያቀርብ ዕድል ሰጡት:: እሱም ቀጠል አድርጎ፤ “ይህ የይግባኝ ሥርዓት እንጂ ማስረጃ የሚታይበት ወቅት ባለመሆኑ ክቡር ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን እንዳይቀበለው እጠይቃለሁ'' አለ፡፡ ዳኞቹ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩና ከጠበቃዬ የቀረበውን ሰነድ በሥነ- ሥርዓት አስጠባቂ በኩል ተቀበሉ፡፡ ጠበቃዬ ምን አዲስ መረጃ እንዳገኘ ባላውቅም ለእኔ ከድካም ውጪ ሊያስገኘው የሚችል ፋይዳ አልታይህ አለኝ:: ጠቃሚ መረጃ ብሎ ሊያቀርበው የሚችለው ባለፈው መጥቶ በነበረ ጊዜ ከፖሊስ ጣቢያ እንዲወስድ የነገርኩት ደብዳቤ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል የታወቀና በኤግዚቢትነት የተያዘ ስለነበር አዲስ ነው ከተባለ ለእሱ እንጂ ለሌላው አዲስ አልነበረም:: በሌላ በኩል ደግሞ እኔን ነፃ የሚያወጣ የሰው ማስረጃ ተገኘ ከተባለም መሆን ያለበት የገደልኳት እኔ ነኝ የሚል ሰው ከተገኘ ብቻ ነው:: እንዲህ ዓይነት ሰውም ከተገኘ እጅግ በጣም መንፈሳዊ አለበለዚያም ቂል ካልሆነ በስተቀር እሱ የሰራው ወንጀል በተሳካ ሁኔታ ተደብቆለትና ለእሱም ጥፋት ለሀያ ዓመታት የሚታሰርለት እስረኛ ተገኝቶ እያለ እኔ ነኝ ገዳይዋ ብሎ ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ የመጠበቅ ያህል ነው:: በመሆኑም ለደስታም ሆነ ለሐዘን አንዳችም ቦታ አልነበረኝም፡፡ ይልቅ የጓጓሁት ዳኞቹ የሚወስኑትን ውሳኔ ለመስማት ነበር።

ጠበቃዬ ያቀረበው ማስረጃ በአባዲና ፖሊስ የምርመራ ክፍል ተመርምሮ ውጤቱ ለመስከረም 5 ቀን 1983 ዓ.ም እንዲቀርብ ወስነው ችሎቱን ተነሳ:: እኔም ክችሎቱ ወጥቼ ወደ እስር ቤቱ መኪና እያመራሁ ላለ ጠበቃዬና ኤልሳ ወደ እኔ እያዩ፤ በእነሱ እይታ በቲ ማስረጃ ስላገኙ ነፃ እንደሚያወጡኝ እርግጠኛ መሆናቸውን በፈገግታ መልዕክት ገለፁልኝ:: በሰማሁት እና ባየሁት ነገር ብዙም ባልደስትም በውስጤ ተስፋ ሰንቂ ወደ እሥር ቤቴ አመራሁ:: ወህኒ ቤት እንደገባሁ ውሎ እንዴት ነበር እያሉ እስረኞች ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ የሆነውን ነገር ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኳቸው:: መቼም እስረኛ ሲባል ሌላ "የሕግ ባለሙያ'' ማለት ነው:: እያንዳንዱ አስረኛ እንዴት ራሱን መከላከል፤ የቱን መካድና የቱን ማመን እንዳለበት የሚያማክሩ የእሥር ቤት የሕግ ምሁራን እዚያው ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ምሁራን ታዲያ በእኔ ጉዳይ ላይ ባልጠቀምበትም ቀደም ሲል እንዴት መካድ እንዳለብኝ አስረግጠው አስረድተውኛል:: መቼም አውጥተው አይናገሩት እንጂ አንዳቸውም በመግደሌ ላይ ጥርጣሬ አልነበራቸውም:: በዚህም የተነሳ ይመስላል እየደጋገሙ እዚህ እውነት ብትናገር ችግር የለውም፤ ዋናው ነገር ፍርድ ቤት ሲሆን ነው መጠንቀቅ ያለብህ፡፡ ይልቁን ገድለሀት ከሆነ አገዳደልህን በደንብ ብታስረዳን እንዴት ራስህን መከላከል እንዳለብህ ስለምናማክርህ እዚህ መናገርህ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም" እያሉ "እውነቱን" እንዳወጣ ይጨቀጭቁኝ ነበር። ዛሬም እንደተለመደው በእኔ ጉዳይ ላይ በራሳቸው የሕግ ትንተና ላይ የተመሰረተ መላ ምት መስጠት ጀመሩ፡፡ “እኔ እንደሚመስለኝ፣ አማረ እንዳለው ንፁህ ከሆነ ሊሆን የሚችለው ቀደም ሲል ያልተገኘ የገዳዩን አሻራ ፖሊስ አግኝቷል ማለት ነው" ሲል፡፡ ሌላው የሕግ ምሁር ቀበል አድርጎ፤ “እንዴት ሊሆን ይችላል? ፖሊስ ቀደም ሲል ያላገኘውን አሻራ እንዴት አሁን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ሊያገኝ ይችላል? አሻራው በሩ ላይ ይኸን ያህል ጊዜ ተለጥፎና ተደብቆ ቆይቶ አሁን ተገኝቶ ይሆናል ልትለን እንዳይሆን?' አለ፡፡ አጅሬ እንዲህ በቀላሉ መረታት ስላልነበረበት፣ “እንዲህ ዓይነት ፍሬከርስኪ ወሬ እያወራሁ አይደለም፡፡ እኔ ማለት የፈለኩት፤ አሻራው በፊት ተገኝቶ ሊሆን ይቻላል፡፡ ግን አሻራው የማን እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቶ አሁን ግን አሻራው የማን እንደሆነ ታውቆ ቢሆንስ? ለዚህም ይመስለኛል እንደገና የአባዲና ምርመራ የተፈለገው'' በማለት መለስ። ሌላኛው "ምሁር" ትራሱን ደገፍ እንዳለ ድምፁን የምሁር ለማስመሰል እያንዳንዷን ፊደል እየቆጠረና በመሀል እ... እ... የሚለውን ድምጽ እየደጋገመ

“እኔ እንደሚመስለኝ እ... እ... ጠበቃው አለኝ ያለው የሰነድና የሰው ማስረጃ እስከሆነ ድረስ እ... እ... አንድ ወንጀሉ ሲፈፀም PP ግለሰብ የአማረ ያላግባብ ተፈርዶበት ወህኒ መውረድ አሳዝኖት ወንጀሉን ማን እንደፈፀመ ማየቱን ገልዖ የፃፈው ደብዳቤ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል፡፡ እ... እ... ደግሞም አቀርበዋለሁ ያለው ማስረጃ ይኼው ግለሰብ የሚሰጠው የምስክርነት ቃል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግለሰብ ምናልባት እንደሚመስለኝ ሆቴል ውስጥ ያለ አስተናጋጅ ወይም ዘበኛ ሊሆንና ገዳዩ ገድሎ ሲወጣ አይቶ ሊሆን ይችላል":: ሌላኛው የቀረበውን የሕግ መከራከሪያ ነጥብ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችለውን ሐሳብ ለማፍለቅ ጣራ ጣራ ሲያይ ቆይቶ፤ “ግን እኮ ይኼ ሊሆን አይችልም ባይባልም፣ በፊት መጥቶ ለአማረ ያልመሰከረ ዘበኛ ወይም አስተናጋጅ አሁን እንዴትና ከየት ሊመጣ ይችላል?" በማለት ቢያንስ በጥያቄ መልክ በቀረበው አስተያየት ክርክሩን መሠረት ለማሳጣት ሲሞክር፣ ሌላው ምሁር ቀበል አድርጎ፣ “ይህማ ሊሆን የሚችለው መጀመሪያ ላይ ፈርቶ ቆይቶ በኋላ ግን አላግባብ የአጅሬ መታሰር እረፍት ነስቶትና ተፀፅቶ እ... እ... ወይም ጠበቃው ሁኔታውን ደርሶበት እንዲመሰክር ወይ አግባብቶት አሊያም አስፈራርቶት ሊሆን ይችላል"፡፡ ይኼንን የክርክር ነጥብ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የመርቻ ሐሳብ የመጣለት ሌላኛው ምሁር፤ “እንዴ! ያበደ ካልሆነ በስተቀር እንዲህማ አያደርግም! ወንጀል ሲፈፀም አይቶ ዝም ማለት በራሱ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እስከአሁን ዝም ብሎ ኖሮ አሁን ሊተነፍስ ቢሞክር ራሱን በገመዱ ማስገባቱ ነው፡፡ ይህንን ያህል ጊዜ ሳይናገሩ መቆየትም በሕግ ያስጠይቃል" ሲል ንግግሩን ቋጨ ፤ “መመስከርማ አለበት እ... እ... እንዲያውም ወንጀል የሚሆነው ከነጭራሹ ደብቆ የኋላ ኋላ የታወቀ እንደሆን ነው:: አሁን ባድራጎቱ ተፀፅቶ በራሱ ተነሳሽነት እውነቱን የሚመሰክር ከሆነማ በሕግ የሚጠየቅ አይመስለኝም' ሲል፤ ሌላው እስካሁን ሳይናገር ክርክሩን ሲያዳምጥ የነበረ እስረኛ፣ “በሕግ መጠየቅማ አለበት፡፡ እስኪ አስቡት፤ እሱ ቀደም ሲል መስክሮ ቢሆን ኖሮ ወንድማችን ይህንን ያህል ጊዜ ባልታሰረና ሊጠግን የማይችል የህሊና ስብራት ባልደረሰበት ነበር፡፡ ስለዚህ ለዚህም በደሉ በሕግ መጠየቁማ

የማይቀር ነው" በማለት በቁጣ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ:: በመጨረሻም ምሁሩ የማሳረጊያ በሚመስል መልኩ፤ “እ... እ... ምንም ይሁን ምን፤ ጠበቃው የታወቀ ጠበቃ እንደመሆኑ መጠን እንደዚህ እርግጠኛ ሆኖ ማስረጃ ላቅርብ ያለው አንድ ሊረታበት የሚችልበት መረጃ አግኝቶ እንጂ እንዲያው ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ ሊሆን አይችልም፡፡ እ... እ...
👍282👎1🔥1
ደግሞም መረጃው ፋይዳ ቢስ ቢሆን ኖሮ ዳኞቹም ቢሆን በዚህ ወቅት የአሠራር ሥርዓት ስለማይፈቅድ የሚያሳምን ነገር ባያገኙ ኖሮ መረጃውን ተቀብለው ለምርመራ ባልላኩት ነበር። እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የአጅሬ ሃያ ዓመት ፍርድ ወደ ሃያ ቀን መለወጡ ነው ማለት ነው" በማለት ውይይቱን ደመደመ:: ከዚህ የተሻለ የመከራከሪያ ነጥብም ሆነ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበ ስላልነበር ክርክሩ በዚሁ ተቋጨ፡፡ ክርክሩ ለእኔ የሚፈይደው ነገር ባይኖርም፣ ቢያንስ ሁሉም የእኔን ንፁህነት ተቀብለው በመከራከራቸው ደስታ ተሰማኝ፡፡ እራሴ የፈጠርኩት ስሜት እንጂ ለካስ በእኔ ንፁህነት የሚያምን ብዙ ሰው ነበር ማለት ነው በማለት በራሴ መፅናናትም ጀመርኩ፡፡ ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን፣ ፍርድ ቤት ቆሜ ጠበቃዬ ሲከራከር፣ ፈገግ ሲልና አይዞህ ተስፋ አለን እያለ ሲያፅናናኝ ምንም ተስፋ አልታይህ እንዳላለኝ ሁሉ እዚህ ግን ምሁራኑ የተለያየ የመከራከሪያ ነጥቦችን እያነሱ ከተወያዩ በኋላ የደረሱበትን መደምደሚያ ስሰማ እውነት የሆነ ያህል ተስፋ በሰውነቴ ውስጥ ተጫረ። በዚህም የተነሳ የቀጠሮ ቀኑ ደርሶ እውነቱን ማወቅና የሚቀርበው ማስረጃም ምን እንደሆነ ለመስማትና ለማየት ጓጓሁ።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍25
#አላገባህም


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ዘሚካኤል  ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ ያለውን የሰርግ የጥሪ ካርድ የያዘውን ፖስታ በራፉ አጠገብ በሚገኘው ቆሻሻ ማጠረቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ጨምድዶ ወረወረው፡፡

ለዛች ስሟን እንኳን ላልነገረችው ሴት ልጅ እንደነገራት በዚህ አለም ምንም አይነት  ወንድም ሆነ ቤተሰብ አያስፈልገውም እና ወደ የትኛውም ሰርግ የመሄድ ፍላጎት የለውም። እንደውም ከተቻለው ስለቤተሰብ በውስጡ የቀረውን እንጥፍጣፊ ትዝታ ከልቡ አሟጦ መሰረዝ ነው ፍላጎቱ፡፡

ከወገብ በላይ ራቁቱን መሆኑን ትዝ ሲለው ወደጠረጴዛው ሄደና ያወለቀውን ልብስ መልሶ ለበሰው..መጀመሪያ እቅዱ ቀጣይ የሙዚቃ ማቅረቢያ ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ሻወር ገብቶ ከተለቃለቀ በኃላ 30 ወይም 40 ደቂቃ መተኛትና እረፍት መውሰድ ነበር፡፡አሁን ግን ሻወር የመውሰድም ሆነ የመተኛት ፍላጎቱ ከውስጡ በኖ ጠፍቷል…ቀጥታ ሶፋው ላይ ሄደና ተቀመጠ፡፡ፊትለፊት ካለው ጠረጴዛ ላይ ያለውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳና ከፍቶ በብርጭቆ ቀድቶ እየተጎነጨ ማሰላሰል ጀመረ….

‹‹ይህቺ ልጅ ምኑን ነክታ እንዴት ስሜቱን ድፍርስርስ አድርጋ እንደሄደች አያውቅም…ወንድሙ ላይ የያዘበት ቂምና የተበሳጨበት ብስጭት አሁንም ትኩስ ነው፡፡

‹‹ግን የዛን ጊዜ ፈቅዶልኝ አባቴን በዛ ቢላዋ ጨቅጭቄ ብገድለው ኖሮስ…?››ሁል ጊዜ እራሱን የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡

አዎ ወንድሙ በድብድብ እና በትግል ባያስቆመው ኖሮ እሱም ይሄን ጊዜ የእድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶበት በአባቱ ምትክ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎበት ተስፋ የሌለው ህይወት ይኖር እንደነበረ…እርግጠኛ ነው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ ሚካኤል ወንድምህ የእድሜ ልክ ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም?››አለው አእምሮው፡፡

‹‹ለምን..ያማ እውነት አይደለም….እሱ እኮ  እንደዛ ያደረገው እኔን ከመከራ ለማትረፍ አስቦ ሳይሆን ለዛ ጨካኝ እና ገዳይ አባቱ ለማገዝ ፈልጎ ነው››

‹‹አይ እሱ የአንተ አእምሮ አንሻፎ የተረጎመው ትርጉም ነው…እንደዛም ቢሆን እንኳን በዛ  ታሪክ ውስጥ ዋናው ተጠቃሚ አንተ ነህ፡፡በወቅቱ ዝም ብሎህ ያሰብከውን እንድታደርግ ቢፈቅድልህ ኖሮ ዛሬ በዚህ ጊዜ ዝነኛው ድምፃዊና ተዋናዩ ዘሚካኤል የለም ነበር…ሀመር መኪና የሚነዳው…የተንጣለለ ውድና ውብ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖረው…ከአደባባይ እስከቤተመንግስት የሚታወቀውና የሚጋበዘው የመገናኛ ብዙሀኖች የዜና ማጣፈጫ የሆነው ዘሚካኤል አይኖርም ነበር፡፡››ሲል እራሱን በራሱ በዝርዝር አስረዳ፡፡
የአእምሮው የእርስ በርስ ጭቅጭቅ ከዚህ በላይ ማስቀጠል አልቻለም..ምክንያቱም በንዴትና በቁጭት አእምሮው ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱ እየጋለበት ነው፡፡ጠረጴዛው ላይ ያለውን ብርጭቆ አነሳና ጠቀም አድርጎ ተጎነጨለት እና መልሶ አስቀመጠው፡፡
ከዛ ስለሌላ ነገር ለማሰብ ሞከረ ..ግን አሁንም አእምሮውን የሞላችው ያቺ ከደቂቃዎች በፊት ከሰውነቱ ለጥፎ ያቀፋትና ለሁለት ሰከንድ ሲስማት የነበረችው ሴት ነች፡፡‹‹ቆይ ይህቺ ልጅ ምን የተለየ ነገር ቢኖራት ነው ከአእምሮዬ ልትወጣ ያልቻለችው ?››እራሱን ጠየቀ…‹‹ከንፈሯ ላይ አስማት አለ መሰለኝ…››አለና ፈገግ አለ….‹‹ምን አለ ስሟን እና  የሞባይል ቁጥሯን ብጠይቃት ኖሮ…?››በጣም ተቆጨ፡፡
ደግሞ እሷም እሱን በምንም አይነት ሁኔታ ደግማ  የማግኘት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳይ ሁኔታ ነው የመጣችበትን ጉዳይ ተናግራ የጥሪ ካርድን እጁ ላይ አስቀምጣ ነው ውልቅ ብላ የሄደችው፡፡

‹‹ባለትዳር ትሆን እንዴ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡
ሀሳብን መቋጫ ሳያበጅለት በራፉ በስሱ ተቆረቆረ…ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን ውስኪ ጨለጠና ሶፋውን ለቆ ወደበራፉ ሄደ ..ቀጣይ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜ መድረሱን ለማሳወቅ በራፉን እንደቆረቆሩ ያውቀል..በራፉን ከፍቶ ሲወጣ ንቁ ሆነው የሚጠብቁት ሁለት ወጠምሻ ጋርዶች ከግራና ከቀኝ ከበቡት፡፡ ሁለት እርምጃ ከተራመደ በኃላ የሆነ ነገር ወደኃላ ሳበው…መልሶ ፊቱን ዞረና ወደክፍሉ ተመለሰ….ከውስጥ በኩል ከበራፉ በስተቀኝ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባስኬት አጎነበሰና አጣጥፎ የጣለውን የሰርግ ጥሪ ወረቀት አነሳ ፡፡የሱሪ ኋላ ኪስ ውስጥ ጨመረውና መልሶ ወጣ..ለምን እንዲህ እንዳደረገ ቢጠየቅ ምንም አይነት መልስ የለውም …እንዲሁ በደመነፍስ ያደረገው ነገር ነው፡፡
////
አሁን የዘሚካኤል ምስል ከሙሉ አቋሙ ጋር በአእምሯዋ እየተራወጠ ነው፡፡ሁለቱ ወንድማማቾች ከቁመትና ከፀባይ ውጭ በሌላው ነገር በሚያስደንቅ ሁኔታ ይመሳሰላሉ። የሚካኤል  ባህሪያት ከዘሚካኤል ትንሽ ደብዘዝ ያሉ ነበሩ እና የዓይኑ ቀለም ንፁህ ፣ ጠንከር ያለ ሰማያዊ ነበረ ፣ ግን ሁለቱም ሰዎች ተመሳሳይ ውብ ፈገግታ፣ ክብ የፊት ቅርፅ እና ሰልካካ አፍንጫ.. ወተት ከመሰሉ ነጫጭ ድርድር ጥርሶች ጋር አላቸው፤››
እየሾፈረች ያለችውን ቪታራ መኪና ኤክስፐረስ መንገድ ውስጥ አስገብታ ወደ አዳማ እያሽከረከረች   ሲሆን አሁንም ስለዛ ዘ-ሚካኤል ስለሚባለው ድምጻዊ ነው የምታሰላስለው፡፡ለሊት 8 ሰዓት ላይ ከእሱ ተለይታ እዛው በአቅራቢያው ወደተከራየችው ፕንሲዬን ሄዳ ለመተኛት ብትሞክርም ምንም እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር እንዲሁ ስትበሳጭና ስትገላበጥ ነው ያደረችው፡፡
ስለእሱ ማሰብ   የጀመረችው ቀደም ብላ ታሪኩን ከየጋዜጦችና ከዪቲዩብ ቻናሎች እየሰበሰበች በምታዳምጥበት ጊዜ ነው፡፡እርግጥ ታውቀለች በዩቲዩቭ የቀረበ ዜና ሁሉ በተለይ ስለፍቅርና ፃታዊ ግንኙነት የሚነዙት አብዛኞቹ ተመልካች ለማግኘት የታስቡ…በውሸት የሚፈበረኩ እንደሚሆን ታምናለች..ግን ቢሆንም‹‹ እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም….››በማለት ለሰው ስሜት የማይጨነቅ ጋጠወጥ ወሲባም አድርጋ ስላው ነበር፡፡እና ደግሞ ለሊት እንዳየችው አልተሳሳተችም…በዛ ለሊት እዛ ክፍል ውስጥ ሲያገኛት መጀመሪያ ያደረገው ወደራሱ ስቦ ከንፈሯ ላይ መጣበቅ ነው…..ስለዛች ቅፅበት ስታስብ ከንፈሯ  ተንቀጠቀጠባት….የሚያበሳጨው ደግሞ ለማንም ሴት ግርማ ሞገሱንና ውበቱን ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆነ ሰው መሆኑን በራሷ ማረጋገጧ ነው…ባለፉት ስድስት አመታት በጣም ብዙ ከሆኑ ወንዶች በብዙ የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈታተኗት ሞክረው ሾልካና አሳስቃ ..አንዳንዱንም ተኮሳትራና አስፈራርታ እራሷን ማትረፍ ችላለች..ከእሱ ጋር ግን በአንድ እይታ ነው ተዝለፍልፋ እቅፉ ውስጥ የወደቀችው፡፡
እንደምንም ከእቅፉ ወጥታ ለማምለጥ ወደበራፉ  በምትራመድበት ጊዜ እንኳን ተንደርድሮ መጥቶ እጇን ይዞ  ጎትቶ እንዲያስቀራት እና ተሸክሞ ሶፋው ላይ እንዲጥላት በውስጧ እየተመኘች ነበር፡፡ግን በተመሳሳይ ጊዜ እንደዛ በመመኘቷ እራሷን ስትወቅስና ስትራገም ነበር፡፡
👍616👏1
ባይሰማትም  ‹‹ዘሚካኤል  አንተ እብሪተኛ  እና ጅላጅ ሰው ነህ›› ስትል ተሳደበች፡፡ነገር ግን ነገሩን በጥልቀት ስትመረምረው እሱ ብቻ ጥፋተኛ አልነበረም። እሷም  ለተፈፀመው ጥፋት ትልቅ ድርሻ መውሰድ አለባት።
እንዴት እንዲህ ያለ ቸልተኛ እና ኃላፊነት የጎደላት ሴት  ልትሆን ቻለች? እንዴት እንዲህ አይነት ውጥንቅጥ ነገር ልትሰራ ቻለች?በራሷ ተግባር በዚህ ልክ ስትበሳጭ ይሄ የመጀመሪያዋ ነው፡፡
ዘሚካኤል አጥብቆ ና ጨምቆ የያዛት ክንዷን  አሻሸች… በትክክል እንዴት እንደሆነ ታውቃለች። ልክ እሷን እንዳየ ፣ ከንፈሯን  እንደነካ ፣ ጠቅላላ ሰውነቷ ያልተበረዘ የደስታ መጥለቅለቅ ነው ያስተናገደው።
አዳማ እንደገባች ቀጥታ ከአዲስ አለም ጋር ነው ተገናኘችው፡፡እና ሆነችውንና ያጋጠማትን አንድ በአንድ በዝርዝር አስረዳቻት፡አዲስ አለምም አፏን ከፍታ በጉጉት ስታዳምጣት ከቆየች በኃላ
‹‹ታዲያ ምን ያበሳጭሻል …እንደውም በራስሽ መኩራት  ነው ያለብሽ››

‹‹ማለት?››

‹‹ቀሽት የሆነ  ዜና ነው  እኮ እየነገርሺኝ  ያለሽው …ወይ ጉድ ››

‹‹ድንገት እኮ ነው የሆነው …ክፍሉ ውስጥ ተደብቄ ገባሁ….››  ትንፋሽ ወሰደች።‹‹አውቃለሁ  ግድየለሽ እና ኃላፊነት የጎደለው ነገር ነው ያደረኩት››

አዲስ አለም‹‹ አንቺ የሆነ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ገብተሸ …እኔ አላንም›› ብላ ሳቀች።

‹‹ይህ ደደብ  በሰርጉ ላይ እንዲመጣ ላሳምነው ሀሳብ ነበረኝ …እችላለሁ የሚል እምነት ነበረኝ። ››እጆቿን በጭኖቾ መካከል አድርጋ እርስ በርሳቸው ማፋተግ ጀመረ‹‹እርግጥ ..አንቺ እና ሚካኤል  እሱን ምን ያህል እንደምትፈልጉት አውቃለሁ..ያደረኩትን ሁሉ ያደረኩት እናንተን ለማስደሰት ካለኝ ምኞት የተነሳ ነው። ››
‹‹እና መጨረሻው እዴት ሆነ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ምን መጨረሻ አለው..እንደምንም ወደቀልቤ ተመልሼ ራሴን ነፃ አወጣሁና የመጣሁበትን ጉዳይ እስረድቼው ካርዱን ሰጠሁትና ክፍሉን ለቅቄት ወጣው፡፡››ስትል መጨረሻውን ነገረቻት

‹‹ቆይ…. እዚሁ  አብረሺኝ እደሪ ምናምና አላለሽም››

‹‹እንዴት እንደዛ ይለኛል..?ትንሽ ጠብቂኝና የምትሄጅበት ድረስ ልውሰድሽ ብሎኝ ነበር..እኔ ግን ከእሱ መሸሽና እሰከወዲያኛው መገላለል ነበር የፈለኩት፡፡››

‹‹እንዴት ነው አሳሳሙ..ቅልጥ ነው አይደል የሚያደርገው?››ጥያቄው የመጎምዠት ስሜት የተጫነው ነው፡፡

‹‹ሴትዬ በቃሽ …ለራሴ በጣም ተናድጄለው ይበልጥ አታናጂኝ››ፀአዳ ተቆጣች፡፡

‹‹ይገባኛል የእኔ ቆንጆ ..ምንም የሚያፀፅት ነገር እኳ አላደረግሽም…መልከ መልካም ና ቆንጆ የሆነውን ሙዚቀኛና ተዋናይ በቀላሉ አግኝተሸ ሳምሽው ..ስለዚህ ያ ድንቅ ነገር ነው..እንደውም ሚያሸልምሽ ጉዳይ ነው።››

‹‹ዝም በይ ባክሽ?›› ፀአዳ ለጓደኛዋ ትችት  ወጥመድ ውስጥ እንደገባች ተረዳች፡፡

‹‹ግን ምን አይነት ስሜት  እንደተሰማሽ ማወቅ አፈልጋለው።ብቻ ንገሪኝ እስኪ እሱ በፊልሞቹ ላይ እንደሚታየው  በሥጋው ውስጥ ሞቃት ሆርሞን  የሚራወጥበት አቅልጥ ወንድ ነው?››

‹‹አንቺ ባለትዳር እኮ ነሽ…እንደዚያ ማለት አትችይም። በተግባር ያገባሽ ሴት ነሽ..ለዛውም ወንድሙን ያገባሽ።ስትቁላይ ላየሽ ግን አትመስይም››እንደዚህ ጠንከር ያለ ነገር ተናግራት አፏን ልታዘጋት ፈልጋ በስሌት የሰነዘረችው ዓ.ነገር ነው፡፡

‹‹ምን አጠፋው….አገባሁ እንጂ ሴትነቴን አውጥቼ እኮ አልጣልኩትም ..ውበት ማድነቅ እችላለሁ…አማላይ ወንድ ፈርጣማ ሰውነት በአይኔ ላይ ሲንከባለል አይኔን አልጨፍንም….አንቺ ግን በአጋጣሚ በከፊልም ቢሆን  ጾምሽን ፈታሽ ማለት ይቻላል ? እና በህይወትሽ  ያለፉትን ስድስት አመታት ስለአንድ ሰው በመብሰልሰል አባክነሽዋል››

‹‹ምን ለማለት እንደፈለግሽ አላውቅም?። ››

‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ቀሚስ የለበሺው  መቼ ነው?››

‹‹እኔ ቀሚስ አልወድም። አይመቸኝም››አለች።'

‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ሜካፕ የተጠቀምሺውስ  መቼ ነው? ወይ ጭፈራ ቤት ገብተሸ የምታውቂው መቼ ነው?ከአንድ ማራኪ ሰው ጋር የመሽኮርመም ስሜት ተሰምቷሽ የሚያውቀው መቼነው?

››አዲስአለም ንግግሯን ለደቂቃ አቆመች…ከዛ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹ ከዘሚካኤል ጋር በመሳሳምሽ  ለምን ታፍሪያለሽ? ሰውየው የእያንዳንዱ ሴት የሩቅ ህልም ነው ..አንቺስ ገና የ22 አመት ለግላጋ ወጣት አይደለሽ? ለምን ልትስሚው አትፈልጊም?ነው ወይስ የጤንነት መታወክ አለብሽ..?ይሄ አይነጥላ ምናምን የሚሉት››

‹‹በቃ ተይኝ እስኪ››

‹‹ነው ወይስ አሁንም ያ ወታደርሽ ከለሁበት ፈልጎ ያገኘኛል የሚል ምኞት ውስጥ ነሽ?››

‹‹አረ ተይኝ…ምን ብዬ ነው በቁሜ ገድሎኝ የሄደን ሰው መጥቶ ከሙታን ያስነሳኛል ብዬ የምጠብቀው..ስታይኝ ያን ያህል ጅል እመስልሻለው እንዴ?›››ፀደይ እስከአሁን ከተበሳጨችው በላይ ተበሳጨች፡፡

‹‹እኮ እንደዛ ከሆነ ዘና በያ…ገና ለገና አንድ ሸበላ ወንድ ጋር ተሳሳምኩ ብለለሽ እንዲህ አመድሽ የወጣ.. ሱሪሽን ብታወልቂለት ምን ልትሆኚ ነው?››

‹‹በስመአብ በይ!!!››አማተበች፡፡‹ ስለእሱ የምትቀባጥሪው… ምንም ለውጥ አያመጣም….ይልቅ ትርኪ ምርኪውን ተይና ስለዋናው ነገር እናውራ…እኔን ያናደደኝ ዋናው ጉዳዩ ወደ ሰርግ ለመምጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ወንድም የለኝም እያለኝ ማለቱ ነው …እንዴት…..?››ንግግሯን ሳትጨርስ ሚካኤል ድንገት መጥቷ ስለተቀላቀላቸው  አፏን እንደከፈተች ቀረች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe እያደረጋጁ አይደለም 500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍705
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ //// ዘሚካኤል  ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ…»
#አላገባህም


#ምዕራፍ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
‹‹ እንዴት ናችሁ.?.የሴት ወሬ ላይ ነበራችሁ መሰለኝ….በመምጣቴ ምቾት አልተሰማችሁም››አለ፡፡

‹‹እንዴ ባልዬው የሴት ወሬ ደግሞ ምንድነው?››ስትል አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው ወንዷችን ማማት ነዋ››ሲል በፈገግታ መለሰላት፡፡

‹‹አንተ እንደዚህማ አትለንም….በዚህ ፀባይህ ላላገባህ እችላለው…የደገስከው ድግስ  ብላሽ እንዳይሆንብህ

ፀአዳ ጣልቃ ገባች‹‹አንቺ እንደዛማ አታስፈራሪውም..እስኪ ልብ ይኑርሽና እምቢ በይው….የልጅ እናቷን ሳይሆን ልጃገረዶችን ነው የማንጋጋለት››ስትል  መለሰች፡፡

‹‹አንቺ እስስት ለሁለታችንም እኮ ነው እየተሞገትኩ ያለሁት››

‹‹ያንቺን ሙግት አልፈልግም …ይልቅ ሚካኤል… አንተን እና አዲስአለምን ይቅርታ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር። ››አለችው ኮስተር ብላ፡፡

‹‹ምነው ምን ተፈጠረ?››ሚካኤል ብቻ ሳይሆን አዲስአለምም ያልጠበቀችው ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡

‹‹ወንድምህን ዘሚካኤል በሰርጋችሁ ቀን እንዲገኝ ለማድረግ የተቻለኝን ጥሬ ነበር…ግን አልተሳካልኝም፣ አሁን የሚመጣበት ምንም ዕድል የለም።››አለችው፡፡

‹‹ለምን ይቅርታ ትጠይቂያለሽ ? እሱ እንደማይመጣ አስቀድመን እናውቅ ነበር፣››በማለት ሚካኤል ተናገረ፡፡

አሁን ግራ የመጋባቱ ተራ የራሷ የፀዳ ሆነ‹‹ቆይ ለመሞከር እንደሄድኩ ታውቅ ነበር እንዴ?››ስትል በጥርጣሬ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡

ፈራ ተባ እያለ በሹክሹክታ‹‹አዎ..አውቅ ነበር››አላት፡፡

ወደአዲስአለም ዞረችና‹‹አንቺ በቃ ሚስጥር የሚባል ነገር አታውቂም..ለዛውም እንዳትነግሪው ብዬ አስጠንቅቄሽ?››

‹‹አንቺ ደግሞ ባልና ሚስት አንድ ሀምሳል አንድ አካል ናቸው ሲባል አልሰማሽም እንዴ? ከገዛ አካሌ ምን ብዬ ነው የምደብቀው?››

‹‹አረ የምትገርሚ ነሽ…ሚኪ ግን በጣም አዝናለው…››

‹‹ምን ያህል እንደሞከርሽና እንደጣርሽ አውቃለው….በእውነት አዲስ በነገረች ቀን እንባ አውጥቼ ነው ያለቀስኩት..ማንም ሰው እዲህ አይነት ነገር ላድርግለህ ብሎኝ አያውቅም ..እህቴ በጣም ነው የምወድሽ …በጣም ነው የማመሰግንሽ››አላት

‹‹እኔም በጣም ነው የምወድህ››አለችና ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችበት፡፡እሱም ተቀብሎ አቀፋት፡፡

‹‹እናንተ እኔንም እኮ አስቀናችሁኝ››አለችና ከተቀመጠችበት ሄዳ ሁለቱንም አንድ ላይ አቀፈቻቸው፡፡
///
መድረስ አይቀርም ለአመታት  ሲታሰብበት እና ለወራት ሲለፋበት የነበር የሰርግ ቀን ደርሶ አዳራሽ ሙሉ እድምተኞች ሙሽሮቹን አጅቦ ሽር ብትን እያሉ ነው፡፡ ፀአዳ በህይወቷ ከዚህ በፊት እንደዚህ  አይነት  ደስታና ፈንጠዝያ  ተሰምቷት አያውቅም?ከሙሽራዋ ጀርባ ሆና በደመቀ ሁኔታ የሚካሄደውን ስነስርዓት እየተከታተለች ነው፡፡በአዲስ አለም የሰርግ ቀሚስ ላይ ያለው የተራቀቀ ዶቃ በመስታወት ላይ ሲያርፍ  በተብረቀረቀ ብርሃን አንጸባርቆ  መልሶ ወደውስጥ ሲረጭ ስትመለከት በተረት አለም ውስጥ ስላሉ ልዕልቶች  እንድታስብ አደረጋት።  የአጋቢውን ፓስተር ድምጽ ላይ ለማተኮር ሞክራለች። እሷ ራሷ የለበሰችው ቀሚስ ልዩ አይነት ስሜት እንዲሰማት አድርጓታል…በህይወቷ መቼ ቀሚስ ለብሳ እንደነበረ አታስታውስም፡፡ ምን አልባት ከቤተሰቦቾ ጠፍታ ከወጣች በኃላ ቀሚስ ጨርሱኑ ለብሳ አታውቅም ይሆናል…ሴት መሆኗ እንዲሰማት አትፈልግም…ጠንካራ ታጋይ ሆና ልጇን ማሳደግና ህይወትና ማሸነፍ ብቻ ነው እቅዷ ..ቀሚስ መልበስ ለስላሳ የሚያደርጋት ይመስላታል…በምን ምክንያት እንደዛ ልታስብ እንደቻለች አታውቅም..ግን ደግሞ ትክክል ነበረች፡፡ ይሄው ዛሬ የተለየ ስሜት እየተሰማት ነው…ሴትነቷ ጎልቶ እየበራ ነው…ይሄ ደግሟ ለሚመለከቷት ሰዎች ብቻ ሳይሆን… ለራሷም በደንብ ታውቋታል፡፡ አዲስአለም የሚካኤልን  እጅ በመያዝ አጋቢው ፓስተሩ የሚላትን ጥምረታቸውን የሚያበስሩ ውብ ቃላትን  ጥርት ባለ ድምፅ ስትደግም ይሰማል… ።

በመከራህም ሆነ በደስታ ጊዜ… ላልለይህ ቃል እገባለው፡፡
በሀዘንህም ሆነ በደስታህ …ጊዜ ከጎንህ ልሆን  ቃል እገባለው፡፡
በጤንነትህም ሆነ በህመምህ ጊዜ …ከጎንህ ላልለይ ቃል እገባልው፡፡

ቀላበቱን አውጥቶ አጠለቀላት እሷም አጠለቀችለት፡፡እርስ በርስ እንዲሳሳሙ ተደረገ….ፀደይ  በምታየው ነገር ሁሉ አንሳፋፊ አይነት  አስካሪ  ስሜት እየተሰማት ነው፡፡

እሷ ከረጅም ጊዜ በፊት ነው በደስታ ማመን ያቆመችው፣ ነገር ግን እዚህ ውብ ቦታ ላይ ሆና አዲስአለም እና ሚካኤል ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ባልና ሚስት መሆናቸውን በፓስተሩ ሲታወጅ ስትሰማ  ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ደስታ ተገፋፍታ ከጣሪያ በላይ ‹‹…እልልልልል….›› ስትል አዳራሹን አናጋችው..በዙሪያዋ ያሉ ሚዜዎችና አጃቢዎች ተቀላቀሏት…ዘፈኑና ጭፈራው ቀጠለ..፡፡
///
ዘሚካኤል አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ወንበር ከያዘ ደቂቆች አልፈውታል፡፡በአይኑ እየፈለጋት ነው፡፡‹‹በፈጣሪ ስም ወዴት ሄዳሽ ነው?››አጉረመረመ፡፡

ቢፌ የተዘረጋበትን የተንቆጠቆጠ የድግስ አዳራሽ ውብ ሆኖ ይታያል፣  የሰርጉ ድግስ አሁን በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው እና ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ እንግዶች በግዙፉ አዳራሽ ሽር ብትን እያሉ እና እየተዝናኑ ነበር።

‹‹አንድ ባልና ሚስት እንዴት በዚህ መጠን ብዙ ጓደኞች እና ወዳጆች ሊኖራቸው ቻለ?››ሲል አሰበ ፡፡ እና  ደግሞ ሁሉም  ወደ እሱ ለመቅረብ እና ከእሱ ጋር ውስን ቃላትን ለመለዋወጥም ፈልገው ሲቁነጠነጡ ታዘበ ። እሱ ግን ቀልቡም አይኑም እየተንከራተተ ያለው አንዲትን ሴት ለማየት ነው ።ድንገት ከመድረክ ላይ ከሙሽሮቹ ጀርባ ሆና ተመለከታት፡፡ ግን ወዲያው ተሰወረችበት ፡፡‹‹ዘሚካኤል አረ እራስህን ሰብስብ ››ሲል ራሱን ገሰፀ…ፊቱን ወደግድግዳ አዞረና በእጁ የያዘውን መጠጥ እየተጎነጨ ዘና ለማለት ሞከረ። ቢያንስ  እንደዛ በማድረጉ በአይኖቻቸው   ሲያሳድዱት የነበሩትን ጎረምሳ ልጃገረዶችን መገላገል ችሏል ፡፡

‹‹ወደዚህ ተንደርድሬ እንድመጣ ያደረገኝ  ምንድን ነው?››እራሱን ጠየቀ፡፡ትላንት አመሻሹ ላይ ወደ ዱባይ የመብረር እቅድ ነበረው፡፡ትኬት ሁሉ ቆርጦ ነበር፡፡ከአምስት ቀን በኃላ የሚጀመርና ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚካሄድ የሙዚቃ ድግስ አለው፡፡ከአምስት ቀን አስቀድሞ የሚጎዘው…ቀደም ብሎ ከአካባቢው ሁኔታና የአየር ጻባይ ጋር ለመለማመድና   ለዝግጅቱ ትኩረት ለመስጠት ስለፈለገ ነበር፡፡እና በፕሮግራሙ መሰረት ሻንጣውና ሸክፎ ወደቦሌ መጓዝ ጀምሮ ነበር..ግን በመንገዱ ላይ የሚያያቸውን ቢል ቦርዶች ሁሉ የልጅቷን ምስል የያዙ እየመሰሉት ሲደነግጥና ፈፅሞ ሊቆጣጠረው የማይችል ስሜት ውስጡ ሲያሸብረው..ወዲያው ስልኩን አውጥቶ ለኤጀንቱ ነበር የደወለው፡፡

‹‹ሄሎ ይቅርታ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆነ ዛሬ መብረር አልችልም››አለው፡፡

‹‹ምነው..ምን ተፈጠረ?››

‹‹እያመመኝ ነው…አሁን ቦሌ አየር ማረፊያ እየተቃረብኩ ነበር..ግን ወደቤቴ ልመለስ ነው…በረራውን ለሌላ ቀን እንዲሸጋገር አድርግ፡፡››

‹‹ለመቼ ለነገ ላድርገው….?››

‹‹ነገ እንደሚሻለኝ በምን አውቃለው…?ምናልባት ተነገ ወዲያ››

‹‹አውቀሀል …?ዝግጅቱ 5 ቀን እኮ ነው የቀረው››
👍7111🥰1
‹‹ሶሪ… ስልኩን ልዘጋው ነው… ከዚህ በላይ ማውራት አልችልም››በማለት ስልኩን ዘጋውና ሹፌሩን ወደቤት እንዲመልሰው አዘዘው፡፡እያደረገ ስላለው ነገር እሱም እየገባው አይደለም…‹ይህቺ ልጅማ የሆነ አስማታዊ ጥበብ ከንፈሯ ላይ አለ፤እንዴት እንዴት እየሆንኩ ነው?››እራሱን ታዘበ….ወደቤት ተመልሶ ለሊቱን ሙሉ ሲገረምና ስለእሷው ሲያስብ አደረ..በጥዋት ተነሳና አምሮና ተሸቀርቅሮ…ልጅቷ የሰጠችውን የሰርግ ጥሪ ካርድ ካስቀመጠበት ቦታ አንስቶ ኪሱ በመክተት ማንም እንዳያገኘው ስልኩን ጠርቅሞ ዘግቶ ግዙፉን ሀመር መኪና እራሱ እያሽከረከረ ወደአዳማ መንዳት ጀመረ፡፡የሆነ ሃይል  ሙሉ ልቡን  ተቆጣጥሮ  አእምሮው የማይፈቅደውን ነገር በግድ እያሰራው እንዳለ ነው እየተሰማው ያለው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe እያደረጋጁ ቤተሰቦች  500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍617
አትሮኖስ pinned «#አላገባህም ፡ ፡ #ምዕራፍ_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ /// ‹‹ እንዴት ናችሁ.?.የሴት ወሬ ላይ ነበራችሁ መሰለኝ….በመምጣቴ ምቾት አልተሰማችሁም››አለ፡፡ ‹‹እንዴ ባልዬው የሴት ወሬ ደግሞ ምንድነው?››ስትል አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡ ‹‹ያው ወንዷችን ማማት ነዋ››ሲል በፈገግታ መለሰላት፡፡ ‹‹አንተ እንደዚህማ አትለንም….በዚህ ፀባይህ ላላገባህ እችላለው…የደገስከው ድግስ  ብላሽ…»
#አላገባህም


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ዘሚካኤል ከሰዓታት በፊት የሰርጉን ስፍራ ለቆ መሄድ ነበረበት። ነገር ግን ከፀአዳ ተለይቶ መራመድ አልቻለም። ከሳምንት በፊት በእንጥልጥል የተወውን ጉዳይ መቋጫ ማበጀት አለበት፡፡በልቡ ጭራበት የሄደችው ሲኦል እሳት እየተንበለበለች መላ ሰውነቱ ትኩሳት እንደለቀቀችበት ነው…እንዴትም አድርጎ እንዴት  እሱን  ማስተካከል ያስፈልገዋል. ዛሬ ማታ።

ፀአዳ ለዘሚካኤል ቃል በገባችለት መሰረት ወደእሱ ለመሄድ ከውስጥ ወደአዳራሹ በተመለሰች ጊዜ በብዙ ውብና አማላይ ሴቶች ተከቦ ሲያውካካ ተመለከተችውና  ከመንገዱ  ለመራቅ ወሰነች - ባየችው ነገር ክፍት ነው ያላት…እንደዛ የማድረግ መብት የላትም ..ግን   ከማንም ለመፎካከርና እሱን ሻሞ ለመሻማት ምንም አይነት እቅድ የላትም..እና እግሯና ወደኃላ ጎተተችና  የአስተባባሪነቱን ስራዋን በትኩረት መስራቷን ጀመረች፡፡እራሷን ማሞኘት አልፈለገችም።

እሱ በእጁ ይዞ የነበረውን ባዶ ብርጭቆ በአጠገቡ በሚያልፈው አስተናጋጅ ትሪ ላይ አስቀመጠና ዓይኑን ወደ ህዝቡ መሀከል አንከራተተ። የሙሽሮቹ ዋና ተጠሪ እንደመሆኗ   መጠን መጥፋት አልቻለችም። ግን   እሱን ከእይታዋ ለማስወገድ እየሞከረች እንደሆነ ያስታውቅባታል፡፡‹‹እንደዛ እንድታደርጊማ አልፈቅድልሽም››ሲል ፎከረ፡፡ይሄ በእሱ ልምድ  አዲስ ተሞክሮ ነበር።አንድ በሆነ አጋጣሚ ከንፈሩን የቀመሰች ሴት መልሳ ልታገኘው መከራዋን ስታይና ስትንሰፈሰፍ ነበር የሚያውቀው፣ከከበቡት ልጃገረዶች በዘዴ ተለየና  እሷን ለማግኘት መጣር ጀመረ፡፡

ፀደይ ግራ በመጋባት ያለአላማ ከወዲህ ወዲያ ስትሽከረከር . ድንገት አይን አዲስ ወደእሷ ጠራቻት‹‹እ ምን ፈለግሽ?››

‹‹እኔ ምንም አልፈለኩም… ለምን ከእሱ ትደበቂያለሽ ?››

‹‹ አልተደበቅኩም›› አለች ፀአዳ፡፡

‹‹እሺ እንደዚያ ከሆነ፣ ለምንድነው ከእሱ ጎን ሆነሽ አንድ ብርጭቆ ሻምፓኝ የማትጎነጪው?ምንድነው የሚያስፈራሽ?››

‹‹እንደምታይው እሱ ብቸኛ ሰው አይደለም….ሁሉም ሰው የእሱን እዚህ ሰርግ ላይ ስለመገኘት ነው  የሚያወራው -..እና ወደሰርግ አዳራሹ ከገባበት ደቂቃ አንስቶ በሰው በተለይ በሴቶች እንደተከበበ ነው››

‹‹እና ውድድሩን አላሸንፍም ብለሽ ሰጋሽ …?አዎ  ከባድ ውድድር እንዳለብሽ እኔም ገምታለው።ግን እኮ ይሄንን ለመሰለ ጠንበልል አማቼ… መፋለም መቻል በራሱ እድል ነው?››

‹‹አረ በካሽ…እኔ ፀደይ ነኝ፡፡ ወንድ ለማግኘት ከሌላ ሴት ጋር የምናጠቀው። እንደው እንዳልሺው ፊልሚያ ውስጥ ልግባ ብልስ እሱ ፍላጎት ከሌለው የሚሆን ይመስልሻል…?እናስ ከእነዛ ከከተመዋ አማላይና ስብር ቅንጥስ ከሚሉ ወዳጆችሽ ጎልቼ በአይኑ የምገባ ይመስልሻል...›› በብስጭት ተንዘረዘረች፡፡

‹‹ገባሽ እኮ ..ቀድመሽ በከንፈሩ ገባሽ….ይልቅ አትንቀርፋፊ..በሰርጌ ቀን ካንቺ ጋር ከዚህ በላይ መዳረቅ አልችልም..ባሌ አየጠራኝ ነው፡፡ቻው››ብላት በቆመችበት ጥላት ሄደች፡፡

ፀደይ ለተወሰነ ደቂቃ ድንዘዝዝ አለች‹‹…ምን ላድርግ?››እራሷን ጠየቀች..፡፡ምንም ያህል ችላ ልትለውና ልትርቀው ብትሞክርም ልቧ ግን ልክ እንደማግኔት ወደእሱ እየጎተታት ነው…ወደአለበት  ሄዳ ከሰውዬው ጋር ለመነጋገር ድፍረት አልነበራትም።ፊቷን አዙራም ከእሱ ርቃ ለመሰወር ብትጥርም ከዚህ የበለጠ ተጫማሪ ሳዕታትን ከእሱ ተደብቃ መቆየት እንደማትችል ልቧ ያውቃል፡፡ድንገት ስታየው ብቻውን ሆኖ ስላየችው  ወደኋላ ተመለሰችና ቅዱስን ከሞግዚቷ ተቀብላ በማቀፍ እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ወደእሱ ሄደች፡፡

‹‹እንዴት ነሽ…?መምጣትሽን በናፍቆት ስጠብቅ ነበር››ከአንደበቷ የሚወጡት ቃላት ልቧን በቀላሉ ማቅለጥ አቅም ነበራቸው፡፡

‹‹አልደበረህም አይደል?››

‹‹በመጠኑ…ግን በጣም የሚፈልጉትን ነገር ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥም ሆነው መጠበቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው….እና አልከፋኝም››አላት፡፡

ዝም አለች…ምን እንደምትል ግራ ተገባች‹‹ከወንድምህ ልጅ ከቅዱስ ጋር ላስተዋውቅህ።››አለችው

ዘሚካኤል  በተራው በዝምታ ተዋጠና  ህፃኑን በትኩረት ማየቱን ቀጠለ። የሆነ የማያውቀው መከፋት ስሜት ውስጡን ሲያተረማምሰው ተሰማው፡፡ህፃኑን እቅፉ የተንጠለጠሉትን ውብ ጉንጮቹን እያገላበጠ ቢሰመው ደስ ይለው ነበር፤አዎ እንደዛ አይነት ፍላጎት ነበር የተሰማው፡፡ግን ከተቀመጠበት መነቃነቅ ሆነ እጆቹን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡እንዲህ መሆን የለበትም ነበር፡፡እሱ በቤተሰቡ ላይ ያን አይነት መአት ከመድረሱ በፊት በጣም ሰው ወዳጅ በተለይ ዘመድ ለተባለ ሰው ልቡ ትርክክ የሚል በፍቅር የሞላ ልጅ ነበር፡፡ከክስተቱ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ነው የሆነው፡፡ከዘመድ ጋር መነካካት መርዝ እንደመጎንጨት የሚያንገፈግፈው ነገር ሆኖል…ቢሆንም እንዲህ በጮርቃ ህፃን ላይ እንኳን የተለየ አቋም ሊኖረው አይገባም  ነበር፡፡

‹‹አይዞህ አትጨናነቅ..በሂደት ጥሩ አጎቱ ትሆናለህ››አለችው፡፡

‹‹ልጁን በተመለከተ እንደጨነቀኝ እንዴት አወቀች?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡

‹‹አሁንም ብቻህን ጥዬህ ልሄድ ነው..ግን አልቆይም..ህፃኑን ለእናቱ አስረክቤ መጣሁ…››

በረጅሙ ተነፈሰ‹‹አዎ እንደዛ ይሻላል..አታስቢ ስለአንቺ እያሰብኩ ጠብቅሻለሁ፡፡››አላት፡፡

ፈገግ አለችለትና ህፃኑን ቅዱስን አቅፋ ተነስታ ሄደች፡፡ከኃላ አይኑን ተክሎ ተመለከታት..አቋሞ ልዩ ነው፡፡ተረከዘ ሎሚ የምትባል አይነት ነች..እንዲህ አይነት እግር ያላት ሴት ከድሮውም በጣም ነው የምትማርከው…ደግሞ ከሁሉም በላይ እሱ ጋር ከሚመላለሱት ሴቶች ተቃራኒ በሆነ መልኩ ምንም አይነት መዋቢያና መኳኳያ አትጠቀምም…ለምን እንደሆነ ሊገባው አልቻለም…ብትጠቀም እኮ የበለጠ ውብ ትሆን ነበር?››ሲል አሰበ፡፡‹‹ግን አንኳንም አልተጠቀመች››ሲል ደመደመ፡፡

ልጁን ለሞግዚቷ አስረክባ ብቻዋን  ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ የወንድሙን ሚስት አስከትላ መጣች፡፡

አዲስአለም ‹‹ዘሚካኤል… በመምጣትህ በጣም ደስ ብሎናል … ዛሬ ማታ ቤታችን በተዘጋጀው የእራት ግብዣ  ላይ ብትገኝ እንዴት ደስ ይለናል መሰለህ …ግን ምቾት የማይሰማህ  ከሆነ እንረዳሀለን….እዚህ ስለመጣህ እራሱ በእውነት በጣም ደስተኛ አድርገሀናል….ሰርጋችንም የማይረሳና የታደመው ሰው ሁሉ መቼም የሚያስታወስው እንዲሆን አድርገሀል ።››

ዘሚካኤል ደቂቃ ወስዶ እንደማሰብ ሲያደርግ ፀአዳ ጣልቃ ገብታ‹‹እባክህ እሺ ብለህ ቆይ…አይዞህ እንደአሁኑ  ጣል ጣል አናደርግህም…ቃል እገባልሀለው››አለችው፡፡

ንግግሯን ስታጠናቅቅ አዲስአለምም ሆነች ዘሚካኤል አፍጥጠው እየተመለከቷት ነበር…‹‹ምንድነው የሚያስቀበጥረኝ ?››ስትል በውስጧ እራሷን ወቀሰች፡፡

ዘሚካኤል መናገር ጀመረ‹‹እሺ እቆያለው››ሲል ተናገረ፡፡

አዲስአለም ፊት በደስታ በራ‹‹አመሰግናለው..በቃ አሁን ጥያችሁ ልሂድ …አብረሽው ቆይና ይዘሽውን ነይ››አለችና ተመልሳ ሄደች፡፡

ፀአዳ ከእፍረቷ ሳትላቀቅ በዝግታ ተቀመጠችና፡፡‹‹እሺ ትላለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››አለችው፡፡

‹‹እውነቱን ለመናገር እኔም እሺ እላለው የሚል ግምት አልነበረኝም….ቃልሽን አምኜ ነው እሺ ያልኩት››አላት፡፡

‹‹ማለት የምን ቃል?››

‹‹እንደእስካሁኑ  ብቻህን በመተው እንድትደበር አላደርግህም…ከመጀመሪያው እስከፍጻሜው ከጎንህ አልለይም…›ብለሽ  የገባሽልኝን ቃል ነዋ››

‹‹አንተ ይሄን ሁሉ መቼ ነው የተናገርኩት.››

‹‹.አሁን ከደቂቃዎች በፊት››

‹‹ይሁን..ለማንኛውም ማትቆጭበት ውሳኔ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው››
👍639🥰2
‹‹እኔም…አሁን ዝግጅቱ አልተጠናቀቀም እንዴ?..ይሄን ቦታ መልቀቅ ፈልጋለው፡››

‹‹ተጠናቋል …ከ10 ደቂቃ በኋላ እንወጣለን››

‹‹ጥሩ….አንቺ ከፊት ለፊቴ አስካለሽ ከ10 ሰዓትም በሃላ ቢሆን ግድ የለኝም፡፡››

ሳታስበው ‹‹እንደወንድምህ አይደለህም…››አለችው፡፡

‹‹ማለት?››

‹‹እሱ አንደበተ ቁጥብ ነው..በምንም አይነት መንገድ ሰውን በውሸት አይሸንግልም››አለችው፡፡

‹‹በውሸት…ለምን እዚህ የመጣው ይመስልሻል?››

‹‹ይሄ ምን ጥያቄ አለው..የወንድምህ ሰርግ ላይ ለመገኘት ነዋ፡፡››

‹‹ተይ እንጂ….በዛ ውድቅት ለሊት በከንፈርሽ ካደነዘዝሺኝ በኋላ ካንቺ ውጭ ስለሌላ ነገር ማስብ አልቻልኩም..ትናንት ማታ ወደዱባይ መብረር ነበረብኝ ..ትኬት ቆርጬ ወደኤርፖርት ሁሉ መሄድ ጀመሬ ነበር..ከዛ ነው ሀሳቤን ቀይሬ  የመጣሁት…ለምን?፡፡››

‹‹በል አሁን  ሰው እየተንቀሳቀሰ ነው ተነስ እንሂድ አለችው…..››እንዳለችው የሆቴሉ ዝግጅት አልቆ ሙሽሮቹን ተከትሎ ሰው ሁሉ እየወጣ ነው፡፡ግን የጀመረውን ንግግርም ልታቋርጠው ስለፈለገች  ነው አጋጣሚውን ተጠቀመችበት፡፡መቀመጫውን ለቆ ተነሳና ክንዷን ጨብጦ ወደመውጫው መጓዝ ጀመረ….በትክክልም መራመድ አቃታት፡፡ከአዳራሹ ውጭ ወጥተው ወደሀመር መኪናው ሲያመሩ ጎዳናው ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በገረሜታና በመደነቅ ሲያቸው ነበር..አንዳንዱም እጆቻቸውን በደስታ እያውለበለቡ ሰላም ይሉት ነበር፡፡የዘሚካኤል ባለግርማ ሞገስ  ሀመር  መኪና ከሌሎች መኪኖች መሀከል ሆኖ  ጎልቶ ይታያል።፡፡የሙሽሮችን ሊሞዚን ተከትሎ ከኃላ እያሽከረከረ ነው፡፡እሷ ከጎኑ ገቢና ሆና  ባልተረጋጋ ስሜት አንዴ የሰርጉን ድባብ ወዲያው ደግሞ በቀጣይ ከእሱ ጋር ስለሚሆነው ነገር ታሰላለስላለች፡፡

እሱ የዚህን ያህል በጣም ታዋቂ እንደሆነ አታውቅም ነበር! እሷ እምብዛም ሙዚቃ አድማጭና ፊልም ተከታታይ አይደለችም፡፡ ስለእሱ ያወቀችው የሚካኤል ወንድም በመሆኑ ነው ..ስለእሱ የተወሰነ መረጃም መሰብሰብ የጀመረችው በዛ ጉዳይ ነው፡፡አሁን ግን እዚህ ሰርግ ላይ ከተገኘ በኋላ እያንዳንዱ ሰው ከህጻናት እስከ አዛውንቶች እሱን ለማየት ሲንጠራሩና ሰላም ለማለት ሲራኮቱበት ስታይ በጣም ነው የተገረመችው፡፡እና ደግሞ በጣምም ነው ያስፈራት፡፡
ቀኝ እጁን ዘርግቶ ትከሻዋን እየነካካ‹‹ቀኑን ሙሉ አልበላሁም እና  ርቦብኛል››አለ በረጋ መንፈስ።

‹‹እንዴ ምሳ ግብዣ ኮ ብፌ ነበረ››

‹‹ባክሽ የእኔ ቀልብ አንቺ  ማግኘት ላይ ስለነበረ ...በወቅቱ ትዝ አላለኝም..አሁን አንቺን ሳገኝሽ ነው እንደራበኝ ያወቅኩት ››አላት፡፡ ..

ምላሽ ስትሰጠው የድምጻን መንቀጥቀጥ  መቆጣጠር አልቻለችም። የአዲስአለምና የሚካኤል መኖሪያ ቤት ለራት ድግስ የተዘጋጀውን ቢፌ  ብቻ ሊውጥ ያሰበ አይመስልም …አይነ ውሀውን ስታስተውል ረሀቡ የምግብ ብቻ አይመስልም…፡፡  ለምን እንደዛ እንደተሰማት  አታውቅም?

እስከምሽቱ  ሁለት ሰዓት ድረስ እነ አዲስአለም ቤት የራት ግብዠው ላይ አብረው አሳለፉ…በጣም አስደሳችና ዘና ያለ ምሽት ነው ያሳለፉት ከዛ ሙሽሮቹን በስነስርዓት ተሰናበተና ፀአዳ ሆቴል ድረስ ትሸኘኝ በማለት ይዞት ወጣ..እሷም ያለምንም ማንገራገር ነበር ተከትላው ወጥታ መኪናው ውስጥ የገባችው፡፡ቀጥታ ቀደም ብሎ ወደያዘው ሀይሌ ሪዞርት ነዳው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ክፍያችን እሱ ብቻ ነው  500 subscribers Please 🙏

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1076
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_21


ሕይወትን በወህኒ ቤት ከፖሊስ ጣቢያ የሚለያት ነገር ቢኖር፣ እዚህ ያለው እስረኛ ከጥቂቱ በቁጠሮ ቤት ካለውና ካልተፈረደበት በስተቀር፣ ምን ይፈረድብኝ ይሆን? በዋስ እፈታ ይሆን? ምን ያገኙብኝ ይሆን? ወዘተ ከሚለው ጭንቀት መገላገሉ ነው:: እያንዳንዱ እስረኛ የተፈረደበትን የእስራት ቀናት በልቡ ውስጥ ጽፎ አንድ ቀን በአደረ ቁጥር አንድ ቀን እየቀነስ የመውጪያ ቀኑን ከማስላት ውጪ ሌላ የሚያስጨንቀውና የሚያሳስበው ነገር የለም:: አብዛኛው እስረኛ ትምህርቱን የሚማር ስለሆነ ከዚህ ሲወጣ ስንተኛ ክፍል አጠናቆ እንደሚወጣ ያውቀዋል:: ዩንቨርስቲ አቋርጠው ወይም ዩንቨርስቲ አጠናቀው ሥራ ላይ እያሉ በተለያየ ምክንያት የታሰሩ ምሁራን ምንም ባይከፈላቸውም እስረኛውን ለማስተማር ከልባቸው ይጥራሉ፡፡ ለጥናት የሚሆን ግዜ በሽበሽ ስለሆነ ከልቡ ለመማር ለደፈረ ሰው የሕይወቱን

አቅጣጫ ሊለወጥ የሚችል ዕውቀት አግኝቶ እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም.. ትምህርት ያገኙ ተራ ሌቦች ያገኙት ዕውቀት በመጠኑም ቢሆን በአነጋገራቸውና በባህርያቸው ውስጥ ለውጥ እያመጣ መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ በብዙ መልኩ ከመጣሁበት ፖሊስ ጣቢያ ጋር ሲነፃፀር ብዙ ነገሩ እዚህ ለየት ይላል፡፡ የቤቱ ንጽህና የተጠበቀ ነው፣ ሁሉም ነገር ስርዓት አለው፣ የሚወራው ወሬም ቢሆን ብስለት አለው፡፡ እስረኛውም አብዛኛውን ጊዜውን በማውራት ሳይሆን በመማር፤ በማንበብ፣ የተለያዩ ስራዎችን በመስራትና በመጻፍ ያላልፋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወህኒ ቤት የተለያዩ የሌብነትና የቅጥፈት ባህርያትን ተክኖ ለመውጣት አመቺ ቦታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ራሱን ለውጠ ጥሩ ዜጋ መሆን ለማይፈልግ አሥረኛ በወንጀል ሙያ ለመሰልጠን ምርጥ ኮሌጅ ነው:: በአልባሌ ሰበብ ከሰው ጋር ተጣልቶ ወይም ሳያስበው የሰው ገንዘብ ጠፍቶበት ለተፈረደበት እስረኛ ፍላጎቱ ካለው ሙያውን ለማስፋት ጥሩ የማስልጠኛ ኮሌጅ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እዚህ የማይቻል ነገር የለም:: ውጪ ያለውን ሁሉንም ነገር "ማግኘት ወይም ማድረግ" ይቻላል:: ሌላው ቀርቶ ከሴት ጋር ፍቅር መጀመር ይቻላል:: የኳስ ጨዋታ ወይም ትርዒት በሚቀርብበት ወቅት በሩቅ እየተያዩ መከሳከስ ነው:: መጀመሪያ እንደተያዩ መተፋፈር፣ ቀስ በቀስ በዓይን ሰላምታ መለዋወጥ፣ መሳሳቅና መሽኮርመም ወዘተ የተለመዱ የፍቅር ጨዋታዎች ናቸው:: እንደዚህ ባለ ሁኔታ የተገኘች ፍቅረኛ "አይኑካ ትባላለች፡፡ ታዲያ በአካል ተገኛኝቶ የልብን መወጣት ስለማይቻል የዓይኑካ ፍቅር ከሌላው ፍቅር ይልቅ የጠነከረ ነው፡፡ እኔ ለእንደዚህ ዓይነት ፍቅር ቦታ አልነበረኝም:: የማያት ሴት ስለሌለኝ የሚያዩኝ ሴቶች ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም:: ደግሞ ለእንደኔ ዓይነቱ በፍቅር መነሻ ሃያ ዓመት ተፈርዶበት ወህኒ የተወረወረ እስረኛ፣ ዳግም ላፍቅር ማለት አዲስ እርግማንን ማስተናገድ ነው:: አላርፍ ካልኩ ደግሞ ከዚህ በኋላ ፍቅር ሊያስከትለው የሚችለው መዘዝ በመሬት ላይ የሚያልቅ ሳይሆን ሲዖልም ተከትሎኝ ሊሄድ የሚችል ነውና የምመኘው አልነበረም። ሁለተኛው የይግባኝ ቀጠሮ ብዙም የሚወራለት ነገር አልነበረውም:: ጠበቃዬ ባቀረበው ይግባኝ ላይ የአባዲና የምርመራ ውጤት መምጣቱን ተከትሎ አለኝ የሚለውን ማስረጃ ከሁለት ወር ተኩል በኋላ እንዲያቀርብ በመወሰን አሰናበቱን፡ ዳኞቹ የአባዲናን የምርመራ ውጤት ከተመለከቱ በኋላ የሰው ማስረጃ እንዲያቀርብ በመፍቀዳቸው ጠበቃዬ አንድ ያገኘው ነገር በመኖሩ ነው የሚል ግምት ስላሳደረብኝ ይበልጥ መፅናናት ጀመርኩ፡፡ ጠበቃዬ ለፍ/ቤቱ ያቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት በማግኘቱ ዞር ብሎ እያየኝ ፈገግ ስላለ

መደሰቱን ገመትኩ:: ዳሩ ግን እኔም ሳይታወቀኝ ፈገግ ብዬ ስለነበር መሳቁ አፀፋ ለመመለስ እንጂ በሌላ ላይሆን ይችላል የሚል ስሜትም አደረብኝ፡ በጊዜ ላይ ጊዜ እየጨመረ እነሆ እስር ከተፈረደብኝ ከስድስት ወር በላይ ሆነኝ:: ግን በእነዚህ ወራት ውስጥ ወንጀለኛ አለመሆኔን ሊያረጋግጥልኝ የሚችል መረጃ አለመገኘቱን ሳስብ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያንዣብብብኛል። ዳሩ ምን ያደርጋል! እኔ ውስጥ ያለውን እውነት ለማውጣት ባያዳግተኝም እውነት መሆኑን ለማሳመን ግን አቅሙ ስለሌለኝ ሌላው በእኔ ቦታ ሆኖ እንዲያሳካልኝ ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝምና የቀጠሮ ቀናት በመጡ ቁጥር ዛሬ እውነት ትወጣ ይሆናል እያልኩ ከመጠበቅ በቀር ላደርገው የምችል ነገር አልነበረኝም። ካለፉት ቀጠሮዎች በተለየ መልኩ ዛሬ ተስፋ ያደረኩባት የቀጠሮ ቀን ደርሳ ወደ ፍርድ ቤት ሄድኩ፡፡ ይህቺ ዕለት ከሁሉም በላይ የዘገየችብኝ ቀን በመሆኗ እያንዳንዱ ቀን የወር ያህል ሆኖ ነበር የተሰማኝ። ብዙ ተስፋ የጣልኩባት ቀን በመሆኗ ነው መስለኝ ከፖሊስ መኪናው ላይ ወርጄ ወደ ፍርድ ቤቱ ሳመራ እግሬ መብረክረክ ጀመረ:: ይህቺ ቀን የእኔን የሕይወት አቅጣጫ የምትወስን ከመሆኗም በላይ የመጨረሻ የተስፋዬ ማለምለሚያ ወይም የተስፋዬ መድረቂያ ቀን ነበረች። ማን እንደነገራቸው ባላውቅም ከሌላው የይግባኝ ቀጠሮ ቀን በተለየ መልኩ አንዳንድ የመ/ቤቴ ሠራተኞችም መጥተዋል፡፡ ይህም የመፈታት ተስፋ እንዳለኝ የሚያመላክት ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰውዬ ከተፈታ ይታዘበናል በሚል ስሜት የፍርዱ ሁኔታ ያለበትን ደረጃ ሲስሙ አንዳንዶች ወህኒ ቤት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: መፈታት አለመፈታቴ አንድ ነገር ሆኖ ቢያንስ ለተወሰነች ጊዜ ቢሆን እንኳ ወንጀለኛ አለመሆኔን የሚያምን ሰው ማግኘት ትልቅ ደስታ ፈጠረብኝ:: ዳሩ ድከሙ ቢላቸው ነው እንጂ እኔ ማንንም የምቀየምበት ምክንያት አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም እኔ ለሌላው ሳደርገው ከነበረው አንፃር እያንዳንዱ ስው ለእኔ ያደረገው እጅግ ቢበዛብኝ እንጂ የሚያንስብኝ አልነበረም፡፡ ዛሬ ፍ/ቤት የምቀርበው ሁለት አማራጭ ይዤ ነው፡፡ ጠበቃዬ በእርግጥም ጠቃሚ መረጃ ይዞ መጥቶ ከሆነና ነፃ ካወጣኝ አሰየው፡፡ ነገር ግን እንደጠረጠርኩት እኔን ለተጨማሪ የእስር ዘመን ለመዳረግ ሴራ እየገመደብኝ ከሆነ ግን፣ ጮኬም ሆነ አልቅሼ ውስጤ ያለውን ጥርጣሬ ዳኞች ለጥቂት ደቂቃ እንዲሰሙ በማድረግ፣ ቢቻል ራሴን ነፃ ማውጣት ካልተሳካም *የቻልኩትን ሞክሬአለሁ" በማለት ከወደፊት ፀፀት ራሴን ነፃ ማድረግ ነው፡፡

የቀጠሮው ሰዓት ደርሶ ሣጥኔ ውስጥ ገብቼ ድራማውን እንደተለመደው ለመመልከት በተዘጋጀሁበት ወቅት ዳኛው ጠበቃዬ አለኝ የሚለውን የሰው ማስረጃ እንዲያቀርብ ስለአዘዙ ፖሊሱ “ዶ/ር አድማሱ" ብሎ ሲጣራ ክው ብዬ ደነገጥኩ፡፡ ዶክተሩ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ጥርሱን እየገለፈጠና በጥላቻ ዓይን እየተመለከተኝ ወደ መመስከሪያው ቦታ ሲራመድ ንዴቱ ፈንቅሎ ሊወጣ ደረሰ:: መቼም ይኼ ክፉ ሰው በምንም ዓይነት መንገድ እስሬን ለማጠናከር ካልሆነ በስተቀር እኔን ለማስፈታት የሚሆን ማስረጃ ሊኖረው አይችልም:: ጠበቃዬ ሆን ብሎ ወንጀሌን ለማጠናከር የሚያደርገው መሆኑ ስለገባኝ እጅግ ጠላሁት፡፡ ጠበቃዬ እኔ እንዳልፈታ የሚሸርበው ሴራ ለእጮኛው የሚያበረክተው ገፀ በረከት ነውና ብዙም ባልናደድበት፤ ይህንን ሰውዬ አምጥቶ እኔን ለማናደድ የሚያደርገው ድርጊት ግን እጅግ በጣም አበሳጨኝ:: ያም ሆነ ይህ አንዱ አማራጭ ካልተሳካ ሌላውን መሞከሬ ስለማይቀር ራሴን አረጋግቼ አባላንጣዬ ጋር ፊት ለፊት በጥላቻ ዓይን መተያየቱን ተያያዝነው:: ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ማድረግ የማይታሰብ ነው፡፡ ምንም ያህል ብናደድ ያለኝ አንድ አማራጭ እዚሁ ቆሜ ነድጄ እስከማልቅ ድረስ ውስጥ ውስጡን መቃጠል ነው፡። መሃል ዳኛው ከሁለቱ ዳኞች ጋር
👍375
ከተነጋገሩ በኋላ፣ “ዶ/ር አድማሱ የመጡበትን ምክንያት ያውቃሉ?'' ብለው ሲጠይቁ፣ ዶ/ሩ ኮስተር ብሎ፤ “አላውቅም ጌታዬ" በማለት መለሰ፡፡ እየተርበተበ ጌታዬ ሲል ተገረምኩ፡፡ እሱ እዚያ ዩንቨርስቲ ውስጥ የሁሉም ጌታ ስለነበር ከውስጡ የጌትነት ስሜቱ ጠፍቶ በአንዴ ራሱን ማውረዱ ገረመኝ:: ያ ሁሉ ተማሪ ከእሱ ርህራሄን አግኝቶ ለማለፍ ሲል እሱ እንዳለው ይሆንለታል፤ ይሽቆጠቆጥለታል፡፡ ከተፈተነው ተማሪ ውስጥ ቢያንስ አንድ ሦስተኛው በእሱ ትምህርት መቀጣቱ/መውደቁ/ ስለማይቀር ሲያየው ይበረግጋል፡፡ በእሱ ትምህርት ለማለፍ ትምህርቱን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም:: እያንዳንዷን የተናገራትን ቃልና በመሃሉም አስሎም ከሆነ ይህንኑ ጭምር እየጠቀሱ መጻፍ የግድ ነው:: የተናገራት ቃል ከሌለች፤ "የታለች የእኔ ወርቃማ ቃል Where is my golden word/" በማለት የቅጣት በትሩን ስለሚያሳርፍ የግዴታ እሱ ሲያስተምር ቃላቶች እንዳያመልጡ ሁሉም ተማሪ ጆሮውን አሹሎ ያዳምጣል፡፡ አንድ ነገር ሳያስቀር የተናገረውን በሙሉ ይጽፋል፣ በፈተና ግዜም የተናገረውን በሙሉ በመጻፍ ይመልሳል:: እሱ ሲራራላት የታየች ተማሪ ብትኖር አልማዝ ብቻ ሳትሆን አትቀርም:: ያም ቢሆን ለእሷ አዝኖ ወይም እራርቶ ሳይሆን እኔና እሷን በማለያየት እሷን

ለራሱ ለማድረግ ሲል ያደረገው የመጠቀሚያ ዘዴ ነበር:: ዳኛው ወደ ጠበቃዬ ዞር ብለው፣ “ጥያቄ ካለህ ቀጥል'' አሉ:: ጠበቃዬም፤ “ዶ/ር አድማሱ፤ አቶ አማረን ያውቋቸዋል" ብሎ ጠየቀው:: “ተከሳሹን ማለትዎ ከሆነ አዎ አውቀዋለሁ" በማለት መለሰ፡፡ ጠበቃዬ፤ “እንግዲህ እርሶን የፈለግንዎት አቶ አማረ የተከሰሰበትን ወንጀል አስመልክቶ የምስክርነት ቃልዎን እንዲሰጡን ነው” ሲል፣ ከመቀመጫው በመነሳት፤ አቃቤ ሕግ “ተቃውሞ አለኝ' አለ፡፡ “ምንድነው ተቃውሞህ? ተናገር!" አሉ ዳኛው:: “ክቡር ፍ/ቤት፣ ዶ/ር አድማሱ ቀደም ሲል በዚሁ ጉዳይ ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ስለሆነ አሁን ሌላ የሚለውጡት የምስክርነት ቃል ስለማይኖር ጥያቄውም አግባብ ስላልሆነ ተቀባይነት እንዳይኖረው እጠይቃለሁ" አለ፡፡ ዳኛው ግን ሀሳቡን ስላልተቀበሉት ዶ/ር አድማሱ ጥያቄውን እንዲመልስ አዘዙ፡፡ ጠበቃዬም ቀጠለ፡፡ “ሟቿን ወ/ት አልማዝ አስፋውን ያውቋታል?'' በማለት ጠየቀ። ዶ/ር አድማሱ የተሰላቸ በሚመስል ሁኔታ፤ “አዎ አውቃታለሁ'' አለ፡፡ “ትውውቀችሁ በምን ላይ የተመሰረተ ነበር?” “ይህንን እኮ ቀደም ብዬ ተናግሬዋለሁ፡፡ አሁን ደግሞ መጠየቁ ለምን አስፈለገ?'' በማለት ዶ/ሩ በንዴት መልክ መለሰ፡፡ ዳኛው ጣልቃ ገብተው፤ “ዶ/ር አድማሱ፤ የተጠየቁት ጥያቄ ምንም ያህል ቢደጋገም የመመለስ ግዴታ ስላለብዎ ሳይሰለቹ መልስ ቢሰጡ የተሻለ ነው" አሉ:: ዶ/ር አድማሱ ግን ቶሎ ለመመለስ አልደፈረም፡፡ እርግጥ ይህንን ለመናገር ጉሮሮውን ቢተናነቀው የሚያስደንቅ አልነበረም፡፡ ይህ ኃጢያት እንጂ እንደ ጀብዱ የሚወራ አልነበረምና። እሱ በፈፀመው ስህተት እኔና አልማዝ ተለያየን፡፡ ጣጣው በዚህም ሳያበቃ ለእሷ ሕይወት መጥፋትና ለእኔ መታስር መንስኤ

ሆነ፡፡ ታዲያ ይኼ እንዴት ሆኖ ሳይተናነቅ በቀላሉ ከጉሮሮ ይውጣ? ያም ሆነ ይህ እየተናነቀውም ቢሆን መናገር የግድ ነውና፤ "ቀደም ሲል ተማሪዬ ነበረች፡፡ ትምሀርቷን ከጨረስች በኋላ ደግሞ ፍቅረኛሞች ነበርን" አለ:: ለምን እንደዋሽ ይገባኛል፡፡ ተማሪ ሆና አማገጣት እንዳይባል ጊዜውን ለማራቅ መሞከሩ ነበር። ጠበቃዬም ቀጠል አድርጎ፤ “ሟች የእርሶ ፍቅረኛ ከመሆኗ በፊት የአቶ አማረ ፍቅረኛ እንደሆነች ያውቁ ነበር?' ብሎ ሲጠይቀው ዶ/ር አድማሱ በንዴት፤ “ይህንን እኮ ከዚህ በፊት ተናግሬያለሁ!'' በማለት ሳያስበው በፊት እንዲያርመው የተነገረውን ስህተት ደገመው፡፡ ዳኛው በፊት የተናገሩትን ላለመናገር ፈልገው ሳይሆን አይቀርም ሌላ ቃላት ከመወርወር ይልቅ ዝም ብለው ያዩት ጀመር፡፡ ለአፍታ ያህል ዝም ካለ በኋላ፣ “እውቃለሁ፤ ነገር ግን ይህንን ያወቅሁት ከእሷ ጋር ከተዋወቀን በኋላ ነግራኝ እንጂ ከዚያ በፊት አላውቅም ነበር" አለ፡፡ ምስኪን! ውሀ ውስጥ እንደገባች አይጥ መውጪያ ሲያጣ አዘንኩለት:: ይግባኙ ውጤት ቢኖረውም ባይኖረውም በዚህ ሁሉ ሰው ፊት እንዲህ እንደ ጨው እየሟሟ ሲሄድ በማየቴ ደስ አለኝ:: ጠበቃዬ ቀጠል አድርጎ፤ “መቼም ሟች ይህንን ከነገረችዎት፣ ከአቶ አማረ ጋር እንዴት እንደተለያየች ሳትነግሮት አትቀርምና በምን ምክንያት ነበር የተለያዩት?'' ብሎ ሲጠይቅ፤ አቃቤ ሕግ ትንሽ ትንፋሽ እንዲሰበስብ እረፍት ለመጠየቅ በሚመስል መልኩ፤ “ተቃውሞ" አለ፡፡ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ዳኛው ዕድል ሰጡት:: እሱም ጊዜ ለመግዛት በሚመስል መልኩ እየተንቀረፈፈ፤ “ይህ ጥያቄ ተጠያቂውን የሚመለከት ሳይሆን አቶ አማረ ሊመልሰው የሚገባ ጥያቄ በመሆኑ አግባብነት የለውም" በማለት ተቃወመ:: ጠበቃዬም ከተል አድርጎ፤ "ክቡር ፍርድ ቤት፤ የምጠይቀው ጥያቄ ለማቀርበው ማስረጃ አስፈላጊዬ ስለሆነ ጥያቄውን እንዲመልስ ቢፈቀድ" ሲል፣ ዳኛው ተቃውሞውን ውድቅ አድርገው ዶ/ር አድማሱ መልስ እንዲሰጥ አዘዙ። "እኔ የማውቀው ነገር ቢኖር አቶ አማረ ደካማ ተማሪ ስለነበር ለትምህርቱ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያጠና በተደጋጋሚ ብትነግረውም ምክሯን ተቀብሎ ውጤቱን ማሻሻል ስለተሳነውና በዚሁ የተነሳ ከትምህርት ቤት

በመባረሩ የተለያዩ ይመስለኛል:: በኋላም እሷ ትምህርቷን መቀጠል ስለፈለገችና እሱም የሚመጥናት ዓይነት ግለሰብ ሆኖ ስላላገኘችው ግንኙነቷን ማቋረጧን ነግራኛለች" በማለት እኔን በማጥላላት በጠበቃዬ ላይ ቁጭቱን ለመወጣት የፈለገ በሚያስመስል መልኩ መልስ ሰጠ፡፡ አነጋገሩም ሆነ አስተያየቱ ሆን ብሎ የእኔን ስሜት ለመጉዳት ያደረገው ስለነበር እጅግ በጣም ተናደድኩ፡፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል? በሕግ ቁጥጥር ሥር ሆኖ መናገር ወይም መማታት በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩ ልሳደብበት የከፈትኩትን አፌን ቀስ ብዬ ገጠምኩት፡፡ አባቶቻችን "ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ" ይሉ የለ! ጠበቃዬ ቀጠል አድርጎ፧ “የሚዋደድ ሰው መቼም በዚህ የተነሳ እስከመጨረሻው መቆራረጥ ስለማይችል ሟች ሌላ ምክንያት ነግራዎት ከሆነ ቢነግሩን" ሲል ጠየቀ፤ “እኔ ይህንን በሚመለከት አንዴ የጠየቅኋት ቢሆንም እሷ ጥያቄውን የመለሰችልኝ በንዴት መልክ ስለነበርና ዳግም ስለእሱ እንዳልጠይቃት ስለነገረችኝ፣ ከዛ በኋላም ጠይቄያት ስለማላውቅ ምንም ልለው የምችለው ነገር የለም'' በማለት መለሰ፡፡ “ማለት እነርሱን በማለያየት እሷን የግልዎ ለማድረግ በእርሶ በኩል አልሞከሩም?" ብሎ ሲጠይቅ፣ ዶ/ር አድማሱ ክው ብሎ ቀረ፡፡ በዚህ ጊዜ አቃቤ ሕግ እንደተለመደው፧ “ተቃውሞ" በማለት ትንፋሽ እንዲሰበስብ ዕድል ሰጠው:: ሲፈቀድለትም፤ “ጥያቄው መስካሪውን በማያውቀው ነገር ሆን ተብሎ እንደጥፋተኛ ለመፈረጅ የተጠየቀና ክብርሩንም የሚነካ ነው፡፡ በመሆኑም ክቡር ፍ/ቤቱ ይህን ጥያቄ እንዳይቀበለው እጠይቃለሁ" አለ:: ዳኛውም አቃቤ ሕጉን ላለማስከፋት በሚመስል መልኩ ጠበቃዬ ሌላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ አዘዙ:: ዶ/ር አድማሱ ጥያቄውን ሲጠየቅ የሚናገረው ጠፍቶት መርበትበት ሲጀምር _ አቃቤ ሕግ ጣልቃ ገብቶ ስላስቆመው እጅግ በጣም ተናደድኩ። ለመናገር የፈለገ ቢሆንም አፉን ከፍቶና ደንግጦ ስለነበር የሚመልሰውን መልስ ለመስማት ጓጉቼ ነበር። እኛን ለመለያየት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረምና በልበ ሙሉነት የሚመልሰው መልስ እንደማይኖረው እርግጠኛ ነበርኩ። ጠበቃዬ ግን ለዚህ ብዙም ሳይጨነቅ የእኔን ጉዳይ ከሚመለከትበት
👍311
ፋይል ውስጥ አንድ ደብዳቤ አውጥቶ ለዳኛው እንዲሰጥለት አደረገ፡፡ ዳኛውና አቃቤ ሕጉ የየራሳቸውን ፋይል እያወጡ ተመለከቱ፡፡የዚሁኑ ደብዳቤ ኮፒ ዶ/ር አድማሱም እንዲያነበው ተሰጠው፡፡ ዶክተሩ ከንፈሩ እየተርበተበተ በጸጥታ አንብቦ ከጨረሰ በኋላ፤

እና ይህ ደብዳቤ ከእኔ ጋር ምን ያገናኘዋል?'' በማለት ጮኸ ተናገረ:: ጠበቃዬ መልስ ሳይሰጥ በተረጋጋ መልኩ ሌላ ደብዳቤ እንዲሰጠው አደረገ፡፡ ዶ/ሩ ወረቀቱን እንደያዘ ጠበቃዬንና ዳኞቹን በየተራ አያቸው:: ፊቲ በላብ ተደፍቆ ደብዳቤውን ማንበብ ተያያዘው:: እንደጨረሰም : “ይህም ደብዳቤ ቢሆን ከእኔ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፣ ይልቁንም መጠየቅ የምትፈልገው ነገር ካለ ለምን በቀጥታ አትጠይቀኝም?" ሲል፣ ጠበቃዬ “ይህ መጀመሪያ ላይ ያነበቡት ደብዳቤ አቶ አማረ ለአልማዝ ከእንግዲህ ወዲህ እሱ ለእሷ ስለማይመጥን በፍቅር መቀጠል እንደማይፈልግና ይልቁንም ቢጤዋን ፈልጋ እንድታገባና የተሻለ ኑሮ እንድትኖር በመመኘት የጻፈውና ለመለያየታቸው መንስኤ ነው የተባለ ደብዳቤ ነው:: ሁለተኛው ደብዳቤ ደግሞ ወ/ት አልማዝ የጻፈችውና ከእሱ ጋር መቀጠል እንደማትችልና ሌላ ሚስት አግብቶ ቢኖር የተሻለ መሆኑን አስመልክቶ ጻፈችው የተባለ ደብዳቤ ነው፡፡ እንዲህ ይላል ብሎ ለችሎቱ ማንበብ ጀመረ፤ “ይድረስ ለውድ ጓደኛዬ ለአማረ አስረስ፡፡ በመጀመሪያ ለጤናህ እንደምን ሰንብተሃል:: እኔ እግዚአብሄር ይመስገን በጣሙን ደህና ነኝ:: ዛሬ የምጽፍልህን ይህን የመጨረሻ ደብዳቤዬን ስታነብ ትንሽም ቢሆን ማዘንህ እንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ:: ነገር ግን የመጨረሻው ሐዘን ይበልጥ ሊከፋ ስለሚችል ከአሁኑ መወሰን ነበረብኝና መወሰኔ አልቀረም:: እንደምታውቀው አብረን ያሳለፍናቸው የፍቅር ዘመናት ለእኔም ሆነ ለአንተ እንዲህ በቀላሉ የሚረሱ አይደሉም:: ግን ይኼ ትዝታ መቆም እንዳለበት ተሰምቶኛል:: እንደምታውቀው እኔ በዚህ አለም ላይ ካንተ የተሻለ ዘመድም ሆነ መከታ ይኖረኛል ብዬ አልገምትም:: ለዚህም ነው አብረን በነበርንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ አንተ ሁሌም አጠገቤ ስትሆን ደስታ፣ ስትርቀኝ ሐዘን ይፈራረቅብኝ የነበረው :: ይሁን እንጂ ጊዜ ግዜን እየወለደ ሲሄድ ሕይወትን በአሰብነው መንገድ ልንመራት አልቻልንም:: እሷ በፈለገችው መንገድ እየመራችን ሳንወድ በግድ መለያየታችን ቁርጥ ሆነ:: አሁንም ጊዜ ግዜን እየወለደ ሲሄድ የማይረሳ ነገር የለምና ሁሉም ነገር ሙሉ በሙሉ ባይረሳም እንደጥንቱ ግን ሊሆን አልቻለም። አሁን ስለፍቅር ወይም ስለትዳር ከማውራቴ በፊት ራሴን ማሸነፍ እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው:: መማር አለብኝ፡፡ ብዙ ነገር የማወቅ ፍላጎቴም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መጥቷል፡፡ ከዩንቨርስቲውም በጥሩ ውጤት ተመርቄ የዶ/ር አድማሱ እርዳታና አስተዋፅኦ ተጨምሮበት ዛሬ በትምህርቴ በጥሩ ደረጃ ላይ እገኛለሁ:: ከዚህ የሚበልጥ ትልቅ ነገር የለምና ይህንን

እንደጨረስኩ ለማስትሬቴም ለመማር ወስኜአለሁ:: ግን አንተ እኔን በመጠበቅ ሕይወትህ እንዲበላሽ አልሻም:: የራስህን ሕይወት በሚመስልህ መንገድ ብትመራ የተሻለ ነው፡፡ እኔ ከእንግዲህ ወዲያ አብዛኛውን ጊዜዬን በትምህርት ስለማላልፍ ያንተ ባለቤት ልሆን በምችልበት ደረጃ ላይ አይደለሁም:: የእኔን መጨረሻ እኔ ራሴም አላውቀውም:: ስለወደፊቱ ቃል ገብቼ ቃሌን ልጠብቅ አልጠብቅ እርግጠኛ ሳልሆን ላንተ ቃል መግባቱንም አልሻም:: የወደፊቱን የሚያውቀው ጌታ ብቻ ነውና:: ስለዚህ እኔ የራሴን ውሳኔ ወስኛለሁ:: ውሳኔዬንም በምድር ላይ ሊያስቀይረኝ የሚችል ኃይል ባለመኖሩ በዚህ በኩል እንዳትደክም እመክርሃለሁ:: ለጊዜው ላስከፋህ እንደምችል ባውቅም ወደፊት ግን ጥቅሙን ትረዳለህ ብዬ በማሰቤ በሥራዬ አልተፀፀትኩም:: ሁልጊዜ ላንተ ጥሩ ነገር በማሰቤ ሳላውቅ ላሳዝንህ ብችልም፣ አንተን ለመጉዳት ሆን ብዬ የማደርገው አይደለምና እንዳትቀየመኝ:: ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ደብዳቤ ባትፅፍልኝ ደስ ይለኛል፡፡ የእኔን ሰላማዊ ሕይወት ከመረበሽ ውጪ የሚለውጠው ነገር የለምና አትድከም፡፡ የራስህን ምርጫ በጊዜ ውሰድ። በተረፈ ምን ጊዜም አልረሳህም:: ለአንተ ያለኝ ፍቅር እንዳለ እንዲቆይ ከፈለግህም _ ሃሳቤን ለማስለወጥ አትሞክር፡፡ ሁሌ የማይለይህ አምላክ ክአንተ ጋር ይሁን፡፡ ውድ ጓደኛህ አልማዝ ታፈሰ" ብሎ አንብቦ እንደጨረሰ ጥያቄ ለመጠየቅ ሲዘጋጅ፣ ዶ/ሩ ከአፉ ነጥቆ፤ “ታዲያ ይህ እኔን ምን ይመለከታል? ከእኔ ጋር ባልተያያዘ ነገር ነው ጊዜዬን የምታጠፋው" አለ። በይግባኙ ወቅት አዳዲሶቹ ተጨማሪ ማስረጃዎች ለፍ/ቤቱና ለአቃቤ ሕጉ ቀርበው ስለነበር ወረቀቶቹ እዚያም ቢሆን ተነበው ይዘታቸው ታውቋልና ጠበቃዬ ፈገግ እንደማለት ብሎ፤ "ዶ/ር፧ እርሶም እንዳዩት ሁለቱም ደብዳቤዎች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው አቶ አማረ ጻፈው በተባለው ደብዳቤ ውስጥ ለመለያየታቸው እንደምክንያት በሟች ዲያሪ ውስጥ የተጻፈው አቶ አማረ ቢጤውን ለማግባት መወሰኑ ሲሆን፤ በዚህ ደብዳቤ ደግሞ ለመለያየታቸው ምክንያቱ ሟች ትምህርቷን መቀጠል መፈለጓ ከመሆኑ በስተቀር ደብዳቤው እምብዛም ልዩነት አልነበረውም። ከዚህ በላይ ደግሞ ሁለቱም ደብዳቤዎች ላይ ያለው የእጅ ጽሑፍ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ደብዳቤዎቹ ያለ ጥርጥር ከእርሶ ውጪ በማንም እንዳልተጻፉ ለእርሶም ሆነ ለማንም ትክክለኛ ጉዳይ አጣሪና ለሐሰት አሳዳጅ ሰው ግልጽ ነው፡፡" ሲል ዶ/ር አድማሱ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ፧

“በፍፁም ሀሰት ነው! ሀስት ነው!' እያለ ጮኸ፡፡ ፍርዱን ሲከታተል የነበረው ሁሉ ያልጠበቀውን ነገር በመስማቱ እርስ በእርሱ የሹክሹክታ ወሬ ጀመረ፡፡ እነሆ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ሁሉ ዘመን ሲያስጨንቀኝ የነበረውና ያንን ሁሉ ገጽ ሳነብ ልፈታው ያልቻልኩት እንቆቅልሽ ተፈታ:: በንዴትም ሳላስበው "ወይኔ! ወይኔ! ወይኔ! ሰውየው፤ ቆይ አገኝሀለሁ!'' ብዬ ጮህኩ፡፡ ሳላስበው ተጨማሪ ወንጀል እየፈፀምኩ መሆኔን እንኳን ማሰብ ተስኖኝ ነበር:: ዳኛው በንዴት ሥነሥርዓት በማለት ጠረጴዛውን በያዙት መዶሻ መታቱት:: ዶ/ር አድማሱ ግን እየደጋገመ “ሀሰት ነው'' አያለ ሲጮህ ጠበቃዬ! “ዶ/ር አድማሱ "አጉል መፍጨርጨር ለመላላጥ ነው" እንደሚባለው እውነቱን ለማስተባበል ባይሞክሩ ጥሩ ነው፡፡ ይኸ የእርሶ የእጅ ጽሑፍ እንደሆነ በአባዲና ፖሊስ ምርመራ ተረጋግጧል” ሲል፣ አቃቤ ሕግ ተስፋ በመቁረጥ አንገቱን ደፋ፡፡ ጠበቃዬ ዶ/ሩ እንዲረጋጋ ይመስላል ጥያቄውን ለአፍታ ያህል ቆም በማድረግ ፋታ ከሰጠውና ፊቱን በመሀረብ ጠርጎ መጨረሱን ከተመለከተ በኋላ ሌላ አንድ ደብዳቤ አውጥቶ በችሎቱ በኩል አሰጠው:: ዶ/ሩ ደብዳቤውን አንብቦ እንደጨረሰ፤ “እና ታዲያ ምን ላድርገው? ይኼ የእኔ የእጅ ጽሑፍ አይደለም፤ የአልማዝ የእጅ ጸሑፍ ነው” አለ፡፡ “አዎ ልክ ነዎት፤ ይህ ጽሑፍ የእርስዎ የእጅ ጽሑፍ ሳይሆን የአልማዝ የእጅ ጽሑፍ ነው:: በዚህ እሷ ጻፈችው በተባለውና እርሶ በጻፉት ደብዳቤ መካከል ያለው ልዩነት ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም እርሶም እያረጋገጡት ነውና ክርክሩን አቁመው ይልቁንም ይህ አልማዝ እራሷን እንደገደለች የሚገልፅውን ደብዳቤ እንዴት እንደጻፈችው ቢገልፁልን የተሻለ ነው” ሲል ጠየቀ
👍364🔥1
። ዶ/ሩ ከዚህ በላይ እውነትን መጋፈጥ እንዳቃተው ፊቱ ላይ ይነበባል፡፡ ወጥመድ ውስጥ የገባች አይጥ ሆኖ ግራ ቀኙን ቢያይ ምንም ማምለጪያ እንደሌለው አወቀ፡፡ ፊቱ ይበልጥ ፍም መሰለ፡፡ ለጥቂት ሴኮንዶች በዝምታ ከተዋጠ በኋላ፣ ንዴት በተናነቀው ሁኔታ ድምፁን ሁሉም እስኪሰማው ከፍ አድርጎ፤ “አዎ ገድያታለሁ" አለ፡፡ ችሎቱ በአንድ ጊዜ በታዳሚው ጫጫታ ታወከ፡፡


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍374😱3
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_22


“አዎ ገድያታለሁ!" አለ፡፡ ችሎቱ በአንድ ጊዜ በታዳሚው ጫጫታ ታወከ፡፡ እኔ ፍጹም ያልጠበቅሁትን ነገር በመስማቴ በቁሜ ደረቅሁ፡፡ ዳኛው በመዶሻቸው ፀጥታውን አስከበሩ፡፡ ጠበቃዬም፤

"ይህንንማ አውቄዋለሁ፤ ግን ለምን?" ሲለው፡፡ ፊቱ ላይ አንዳችም የመፀፀት ስሜት ሳይታይበት፤ "ለእሷ ሞት ያንሳት እንደሆነ እንጂ የሚበዛባት አይደለም:: አሁንም ሁለተኛ ተነስታ ዳግመኛ ብገድላት እንኳን በእኔ ላይ የፈፀመቺውን በደል የሚያካክስ አይደለም:: ከሁሉ አስበልጬ እየወደድኳት፣ እሷን አጥቼ መኖር እንደማልችል እያወቀች፣ ፍቅሬን ረግጣው ለመሄድ ሞከረች:: ከራሴ በላይ እሷን የተሻለች ሰው ለማድረግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ለጥሩ ነገር ላበቃት ብችልም የእኔ ድካም፣ የእኔ ውለታ፣ ለእሷ ምንም አልነበረም:: ሁሌ ጊዜ ከእኔ ይልቅ የምትናፍቀው ይህንን ደደብ ነበር:: ዳሩ ግን እሷ የእናትነትና የአባትነት ፍቅርን አይታ ስለማታውቅ ለፍቅር ስለፍቅር የሚያስብ ህሊና አልነበራትምና አልፈርድባትም:: እኔ ግን ተስፋ ሳልቆርጥ አንድ ቀን ታፈቅረኝ ይሆናል እያልኩ የቻልኩትን ሁሉ ብጥርም እሷ ግን ለእኔ በድኗን እንጂ መንፈሷን ሳትሰጠኝ ለሶስት ዓመታት በአንድ ቤት ውስጥ አብረን የይስሙላ ህይወት ኖርን:: ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አንድ ቀን ትወደኝ ይሆናል፣ ልጅ ስንወልድ ታፈቅረኝ ይሆናል እያልኩ ተስፋ ሳልቆርጥ በእሷ የምወደድበትን ቀን በናፍቆት መጠባበቁን ተያያዝኩት:: ግን ምን ያደርጋል! ልፋቴ ሁሉ የእምቧይ ካብ ነበር፡፡ ምንም ያህል ብጥር፣ ምንም ያህል ጥሩ ነገር ብሰራ ሕሊናዋ ውስጥ አልገባ አልኩኝ። በእሷ አባባል እኔን በወንድምነት እንጂ በፍቅር ሊቀበል የሚችል ልቦና አልነበራትም፡፡ ወሬዋ ሁሉ ስለአማረ ነበር፡፡ ዓይኖችዋ ማየት የሚፈልጉትና የሚመኙት እኔን ሳይሆን በእኔ ውስጥ አሻግረው የሚያዩት እሱኑ ነበር። ሌላው ቀርቶ አልጋ ላይ በፍቅር ጨዋታ ወቅት የምትጠራው የእኔን ስም ሳይሆን የእሱን ስም ነበር፡፡ የእኔ የራሴ ብቻ ላደርጋት የወስንኩትን ሁሉ እንደፈላ ውኃ አተነነችው፡፡ይህ ደግሞ እጅግ በጣም አተከነኝ:: ስለዚህ ቀናሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ብቸኛው መፍትሄ አሷን ከእሱ ጋር ማለያየት ብቻ ነው ብዬ ስላሰብኩ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አንድ መላ ፈጠርኩ። በመጀመሪያ ቢያንስ እሷ ደብዳቤ እየጻፈችለት እሱ መልስ የማይሰጥ ከሆነ ተስፋ ቆርጣ ትተወው ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ አማረ የሚጽፋቸውን ደብዳቤዎች ከፖስታ ቤት ሳጥናችን ውስጥ ቀድሜ እያወጣሁ ማቃጠሉን ተያያዝኩት፡፡ በተቻለ መጠንም እንዳይደርሳት አደረኩ፡፡ እሷ ግን ተስፋ ባለመቁረጥ ትጽፍለት ነበር፡፡ "ባይመቸው ነው እንጂ ሲመቸው ይጽፍልኝ ይሆናል" እያለች በተደጋጋሚ ትሞክር ነበር። በመጨረሻ ግን ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝና እነዚህ የምታሳየኝን ሁለቱም ተስፋ ያስቆርጣሉ ያልኳቸውን ደብዳቤዎች ጽፌ በእሱና በእሷ ስም በተለያየ ጊዜ አሽጌ ላኩኝ፡፡ ይህንንም እንዳታውቅብኝ የተቻለኝን ሁሉ

አደረኩ፡፡ ይኸ በእርግጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተሳክቶልኛል፡፡ እሷም ሆነች እሱ ድርጊቱን በእውነትነት ስለተቀበሉት ሁለቱም ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህም ቢሆን ሊዘልቅ አልቻለም፡፡ እንዴት ልታውቅ እንደቻለች ባይገባኝም ወደ መጨረሻ አካባቢ ሁለቱም ደብዳቤዎች በእኒ እንደተጻፉ በማወቋ ይበልጥ ጠላችኝ፡፡ ይህንን ሁሉ ያደረግሁት ለፍቅሯ ስልና እጅግ በጣም ስለምወዳት ነበር። እሷን ለማንም ቢሆን አሳልፌ መስጠትን ህሊናዬ የሚቀበለው ጉዳይ አልነበረምና እውነታውን ተቀብዬ አርፌ መቀመጥ አልቻኩም:: ልቤን ሰብሮ እጅግ ተስፋ ያስቆረጥኝ ግን ዘወትር በምታነበው መጽሐፏ ውስጥ ያገኘሁት የደብዳቤ ረቂቅ ነበር፡፡ ተጽፎ ያልተላከውን ለጓደኛዋ ኤልሳ የተጻፈውን ደብዳቤ እንዳነበብኩ ክፉኛ አንቀጠቀጠኝ፤ አሁንም ቢሆን ያንገሸግሸኛል፡፡ ኮፒውን አስቀርቼ ደጋግሜ ስላነበብኩት በቃሌ አጥንቼዋለሁ ማለት ይቻላል፡፡ እንዲህ እኳ ነው ያለችኝ፡፡ "ዶ/ር አድማሱ ራስ ወዳድ ነው፡፡ እኔ ለእሱ ከወንድምነት ያለፈ ፍቅር እንደሌለኝና መቼም ቢሆን የእሱ ዘላቂ ፍቅረኛ ልሆን እንደማልችል እያወቀ ለእኔ ደስታ ሳያስብ ለራሱ ፍላጎት ብቻ በመጨነቅ የእኔ ሕይወት አበላሽቶ በእኔ መደሰት መፈለጉን ሳስብ ይበልጥ እንድጠላው ያደርገኛል:: እኔ ለአማረ፣ አማረ ለእኔ ምን ያህል ፍቅር እንዳለን እያወቀና በሚያደርገው እኩይ ተግባር ሁለታችንም ምን ያህል ልንጎዳ እንደምንችል እየተገነዘበ፣ በሁለታችን ደስታ ማጣት የራሱን ደስታ ለመግዛት ሲሞክር ማየት ምንጊዜም ቢሆን የሚያናድድ ተግባር ነው:: በዚህም የተነሳ ለእኔ ከእሱ ጋር ተመልሶ አብሮ መኖር ቀርቶ ማሰቡም ሆነ መሞከሩ ራሱ የማይቻል ሁኔታ ነው፡፡ እርግጥ ነው ዶ/ር አድማሱ፣ ለእኔ ያለውን ፍቅርና በዚህም የተነሳ ያደረገልኝን ነገር ሁሉ ምንግዜም የምረሳው አይደለም:: በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው:: አንድ የምተማመንበት ዘመዴ እሱ ነው ብዬ ስላመንኩ ሳላቅማማ ያለኝን ሁሉንም ነገር አሳልፌ ልሰጠው ሞከርኩ፡፡ ግን ገላዬን እንጂ ጥልቅ ፍቅሬን ልሰጠው አልቻልኩም፡፡ ውጪያዊ አካሌ እንጂ ነፍሴ ከሱ ጋር ልትሆን አልቃጣችም:: በተለይ አሁን ከአማረ ጋር እንዴት እንደተለያየን ካወቅሁ በኋላና ያለ በደሉ በደለኛ አድርጌ መለያየቴን ስገነዘብ ፀፀቱ በፍጹም አላስቀምጥ አለኝ፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እስካሁን አላግባብ ሳብጠለጥለው መኖሬን ሳስብና ከሁሉም በላይ ደግሞ ዶ/ር አድማሱ ያደረገውን ነገር ሁሉ እያወቅሁ፣ በምንም ተአምር ተመልሼ የእሱ ፍቅረኛ ሆኜ ልኖር እንደማልችል ይታየኛል፡፡ አርግጥ እሱ ለእኔ ካለው ፍቅር የተነሳ ያደረገው መሆኑን ስለማውቅ ጥፋቱን ሁሉ ይቅር ልለው እችላለሁ፣ ሆኖም እላይ

በጠቀስካቸው ምክንያቶች የተነሳ ዳግም የእሱ ፍቅረኛ ለመሆን ግን በምንም ሁኔታ አይቻለኝም:: የበደልኩትን ፍቅረኛዬን ፈልጌና እግሩ ላይ ወድቂ ይቅርታ ለመጠየቅ ወደ አንቺ እየመጣሁ ነው:: ቢያንስ ዳግም ባያፈቅረኝ እንኳ ይቅር ካለኝ ይበቃኛል" ይላል፡፡ ይህንን ደብዳቤ እንዳነበብኩ ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ፡ ከጽሑፉ ምሬት የተነሳ ሳልወድ በግድ ደጋግሜ አነበብኩት፤ በቃሌም አጠናሁት፡፡ ይህን በሕልሜም በውኔም ይሆናል ብዬ ያልጠበኩትን ነገር በራሷ የእጅ ጽሑፍ ሳነብ ውስጤ እሳት የተለኮሰበት ያህል ነደደ፡፡ ግን መጨከን አልቻልኩም፡፡ በዚሁ የተነሳ ጥላኝ ለመሄድ በተነሳችበት ዕለት ጨክኜ ላሰናብታት አልቻልኩም፡፡ ጽኑ ፍቅሬን እየገለጽኩላትና የወደፊቱን አስደሳች የሚሆን ሕይወታችንን በልዩ ልዩ መልክ እያብራራሁላት እንድትቀር ለመንኳት፡፡ እሷ ግን እምነቴንና ተስፋዬንም በእሷ ላይ ማሳደሬን በተደጋጋሚ ነግሬያት ሳለ ታደርገዋለች ብዬ በሙሉ ልቤ ሳላምን ጥላኝ ሄደች፡፡ ይህንን ሁሉ ውለታና ለእሷ ያለኝን ፍቅር ከምንም ሳትቆጥር ጥላኝ ወደ እዚህ እርኩስ ለመሄድ ወሰነች:: ለመንኳት፣ እግሯ ላይ ተንበርክኬ ቅሪ እያልኩ እያለቀስኩ ተማፀንኳት፣ ከእሷ ወዲያ ሕይወት ለእኔ ትርጉም እንደሌለው እና በእኔ ላይ በምትፈፅመው ነገር የኋላ ኋላ ከምትፀፀት ብትቀር እንደሚሻል ደጋግሜ ነገርኳት፡፡ አንጀት ካላት በማለት እንድትራራልኝ ጣርኩ፡፡ ለእሷ ግን ይህ ሁሉ መማፀን ምንም ዋጋ አልነበረውም:: እነዚህ ሁለት ደብዳቤዎች በእኔ መጻፋቸውን በማወቋ እጅግ አድርጋ ጠላቺኝ:: አፍ አውጥታ ለምን ይህንን እንዳደረኩ ግን ልትጠይቀኝ አልፈለገችም፡፡ ነገር ግን ይህ ድርጊቴም ቢሆን በእኔ ላይ እንዲህ የከፋ ጥላቻን ሊያስከትል የሚችል መሆን አልነበረበትም:: ምንም
👍452👏2🥰1😱1
እንኳን ድርጊቴ ጥሩ ባይሆንም ለእሷ ካለኝ ፍቅር የተነሳ እሷን ላለማጣትና ያንን የመሰለ ችሎታ ያላት ወጣት በአልባሌ ፍቅር ተተብትባ እንዳትቀር ያደረኩት መሆኑን ስለምታውቅ ይህንን ያህል የሚያስጨክን ነገር አልነበረም፡፡ እሷ ግን በተቃራኒው ልክ ትልቅ ወንጀል እንደፈፀምኩባት አድርጋ ሸሸችኝ፤ ጥላኝም ሄደች። በነጋታው ቤቱ ወና ሆነብኝ፡፡ ገና ከመሄዷ ብቸኝነት አስጨነቀኝ፡፡ ሌላ አማራጭ አልነበረኝምና ወደ እሷ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ግን ስሄድ በውስጤ ሁለት አማራጮችን ይዤ ነበር፡፡ ልመናዬን ሰምታ ከተመለሰች፤ ያፈጸመችብኝን በደል ሁሉ ረስቼ አብሬ ለመኖር፣ ይህ የማይሳከ ከሆነ ግን ተበቅዬ ለመምጣት፡፡ የምጠብቀው ካልተሳካም በማለት ለሁለተኛ አሰከፊ አማራጭ ተዘጋጅቼና ስልት አዘጋጅቼ እሷን ፍለጋዬን ጀመርኩ፡፡ በመጀመሪያ ድሬደዋ ካገኘኋት ብዬ ስፈልጋት አመሸሁ፡፡ ያላሰስኩት ሆቴል አልነበረም፤ ላገኛት ግን አልቻልኩም፡፡ በኋላ ግን ኤልሳ አዲስ አበባ

የሚገኘው ደብረወርቅ የተባለ ሆቴል ውስጥ አልጋ እንደያዘችላት የነገረችኝ ትዝ አለኝ፡፡ በነጋታው የአውሮፕላን ቲኬት ቆርጬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ገባሁ። እንደገባሁም ሆቴሉ ድረስ ሄጄ ስጠይቅ፣ አልጋ እንደተያዘላት ነገር ግን እስከዚያ ሰዓት ድረስ እንዳልመጣች አስተናጋጁ ነገረኝ፡፡ መሸት እስከሚል ከተማውን እየዞርኩ ስናፈስ ቆይቼ ስመጣ ከተሾመ ጋር ስታወራ አየሁዋት:: እሷ ባታየኝም እኔ ግን ጥግ ላይ ተቀምጬ ሁኔታቸውን ሁሉ መከታተል ጀመርኩ፡፡ ግን ያንን ሳይ አለመምጣቴን ተመኘሁ፡፡ በምንም ታምር እኔን በተሾመ ትለውጣለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ያን ያህል ካልሄድኩ ብላ ድርቅ ስትል፣ ደብዳቤ ላይ ባነበብኩት መሰረት ያቺ ኤልሳ ከዚህ ከደደብ ከአማረ ጋር ልታስታርቃት ፈልጋ የቀጠረቻት መሰለኝ እንጂ ወደዚህ የመጣችው በምንም ታምር ተሾመን ለማግኘት ነው ብዬ አልጠረጠርኩም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ይህንን ሳይ እሱ የተባረረ ጊዜ እሳት ጎርሳና እሳት ለብሳ ቢሮዬ ድረስ በመምጣት ያባረርኩት እኔ መሆኔንና አለመሆኔን የጠየቀችኝ ትዝ አለኝ፡፡ ግን ለምን? በወደድኳት ምን በደልኳት? ምን መጥፎ ነገር አድርጌ ነው እንዲህ የጠላችኝ? ለምንስ እኔን እንደጣዖት የማመልካትን ትታ ይኸን ባገኛት ቁጥር የሚቀጠቅጣትን ሰው መረጥች? ከእርሷ ተለይቼ ለአንዲት ደቂቃ እንኳን መቆየት እንደማልችል እያወቀች ለምን ጥላኝ ለመሄድ ወስነች? ከእኔ ምን አጣች? ከእነ ተሾመና አማረ ያገኘችውና ከእኔ ግን ያጣችው ምን ነገር ኖሮ ነው ጀርባዋን የሰጠችኝ? ነው ወይስ መውደዴን እንደወንጀል ቆጠረችው? በማለት ተማረርኩ፡፡ ለእሷ መንሰፍሰፌ ወንድነቴን አሳንሶና እኔነቴን አዋርዶ ያሳየብኝ መሰለኝ፡፡ ከተሾመ ተሰናብታ አስተናጋጁን ቢራ ክፍሏ ድረስ ይዞላት እንዲመጣ አዝዛ ወደ ክፍሏ እንደገባች የተዘጋጀሁበትን ሁለት አማራጮቼን ይዜ አስተናጋጁ ተከትዬ ወደተከራየችው ክፍል አመራሁ፡፡ _ ለእሱ በሩን ስትከፍትም ወደ ውስጥ ገብቼ በሩን ከኋላዬ ዘጋሁ፡፡ ያልጠበቀችው ነገር ስለነበር ስታየኝ ደነገጠች፡፡ ግባ ውጣም ሳትለኝ አልጋዋ ላይ ወጥታ ቁጭ አለች፡፡ ትንሽ ቆየት ብላም ለምን እንደመጣሁና እንዴት እዚህ አልጋ እንደያዘች እንዳወቅሁ ጠየቀችኝ፡፡ ተስፋ ሳለቆርጥ፣ ከእሷ ተለይቼ መኖር እንዳልቻልኩና እሷ ስትሄድ ቤቱ ወና እንደሆነብኝ በመንገር፣ ለፈጸምኩት በደል ሁሉ ይቅርታ አድርጋ ወደ ቤታችን እንድትመለስ እያለቀስኩና ጉንጯን እየሳምኩ ለምንኳት፡፡ ሁሉንም ነገር እንዳልተፈጸመ _ አድርጋ የደሰታ ሕይወታችንን እንኳ ባይሆን የደስታ ህይወቴን እንድቀጥል ዕድል እንድትሰጠኝና ከዚህ በኋላም ምንም እሷን የሚያስከፋ መጥፎ ነገር እንደማላደርግ ቃል እየገባሁ እንድትመለስ ተማጸንኳት፡፡

እሷ ግን እዚህ የመጣችው አማረን ፍለጋ መሆኑንና ያለ በደሉ በደለኛ አድርጋ መለያየቷን ስታውቅ ፀፀቱ በፍጹም አላስቀምጥ ስላላት ይቅርታ ለመጠየቅ እንደመጣች በድፍረት ነገረችኝ:: በዚህ ሳታበቃ በፊቷ ላይ ምንም የርህራሄ ገጽታ ሳይታይባት፣ እኔ ያፈጸምኩትን በደል ሁሉ እያወቀች በምንም ተአምር ተመልሳ የእኔ ፍቅረኛ ሆና መኖር እንደማይቻላት በመግለጽ መራራውን ሐቅ ሳልወድ በግድ ጋተችኝ :: ከዚህ በኋላ ግን መወሰን ነበረብኝና ወሰንኩ፡፡ ጊዜ ሳላጠፋ ቀደም ያወጣሁትን የበቀል ስልት ተጠቅሜ የማይቀረውን ርምጃዬን ሲል ወሰድኩ፡፡ አልጋዋ ላይ አጋድሜ በትራስ አፈንኳት፤ አየር አሳጣኋት፡፡ ትራሱን ከላይዋ ላይ ለማላቀቅ ብትሞክርም አልቻለችም፡፡ ቀስ በቀስ መተንፈስ እያቃተኝ ሄደ:: በመጨረሻም ተደሰትኩ እንጂ አላዘንኩም፡፡ ለዘላለም አሸለበች፡፡" የምሰማው ነገር ሁሉ በውኔ ሳይሆን በህልሜ መሰለኝ:: እሱ በእኔ ላይ ለፈፀመው በደል ተጠያቂ ሆኖ እያለ አላግባብ ያደረሰብኝ በደልና እንግልት ምንም ሳይመስለው በችሎት መኻል ይህ ደደብ ብሎ ሲጠራኝ ስሰማ በጣም አዘንኩ፡፡ በመግደሉ አለመፀፀቱም እጅግ ደነቀኝ፡፡ እኔ እንዲያ የምሳሳላትን ፍቅሬን በጭካኔ ገድሎ እና ይህም አልበቃም ብሎት ዳግም ተነስታ ቢያገኛት እንኳን ከመግደል እንደማይመለስ ሲናገርና በመግደሉ በመፀፀት ፋንታ ሲኩራራ መስማት እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ የእናትና አባት ፍቅር ማጣቷ በህይወቷ ላይ ጥሎት ያለፈውን ጠባሳ እያወቀ፣ ይህንኑ እንደጥፋት ቆጥሮ ሲወነጅላት በመስማቴም አዘንኩ፡፡ ከዚህ አልፎ ተርፎ ይህንን ሁሉ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ ወንጀሉን ደብቆ በሰላም ለመኖር ሲል ራሷን የገደለች ለማስመሰል በማሰብ ሬሳዋን ሰቅሎ የክፍሏ የበር ቁልፉን ከደጅ ቆልፎ መሄዱን ሲተርክ ስሰማ የጭካኔው ደረጃ ዘገነነኝ:: በተለይ እሱ በጻፈው የሐሰት ደብዳቤ የተነሳ ራሷን እሱ ቤት ውስጥ ለማጥፋት በወሰነችበት ዕለት እሱ በወንጀሉ እንዳይጉላላ በማሰብ እራሷን እንደገደለች በመጥቀስ የጻፈችውን ደብዳቤ እስከዚያ ሰዓት ድረስ አስቀምጦ በወቅቱ ራሱን ከወንጀል ነፃ ለማድረግ እንደተጠቀመበት ስሰማ፣ ጨካኝና አልማዝ እንዳለችው ራስ ወዳድ ነው ብዬ ደመደምኩ፡፡ ግን ቆየት እያልኩ ሁኔታውን ሳየው በውስጤ ይንተከተክ የነበረው ንዴት ጠፍቶ በቦታው ሐዘን ተተካ፡፡ ፍቅሬም ልክ አሁን ገና የሞተች ያህል ተሰምቶኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩላት:: ስሜቴ ተመሰቃቀለ፡፡ ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለእሱም አዘንኩለት፡፡ ያን የመሰለ ምሁር በእርግጥ ጤነኛ ቢሆን ኖሮ ይህንን ሁሉ ወንጀል ባለፈፀመ፣ ከፈፅመ በኋላ ከመፀፀት ይልቅ እንዲህ በመግደሉ ባልተኩራራ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ፀጥታ ሰፈነበት:: ዳኛውም ፈዘው ቀሩ። ጠበቃዬ ለብዙ ወራቶች የደከመበት ጉዳይ እንዲህ ተሳክቶለት በሚፈልገው መልኩ በአሸናፊነት ሲጠናቀቅ እያየና እየሰማ በመደሰት ፋንታ በሰማው ነገር የደነገጠ መሰለ። ዋና ተዋናዩ ዶ/ር አድማሱ ግን ድራማውን መተወን ጀመረ:: ጥሩ ገድል ፈፅሞ የመጣ አርበኛ እስኪመስል ድረስ እያንዳንዱን ያደረገውን ድርጊት አንድም ሳያስቀር ተርኮ ጨረሰ:: ዳኛው በእኔ ላይ ሊፈረድ የነበረውን ፍርድ በእሱ ላይ አጠናክረው ፈርደው፣ የእሱን ነፃነት ለእኔ አጎናጽፈው፣ ውሳኔያቸውን ወስነውና ጠረጴዛውን በመዶሻቸው ጠልዘው ችሎቱን ዘጉ፡፡ የመዶሻ አመታታቸውም ለየት ያለ ድምፅ ነበረው:: ጠረጴዛውን ሳይሆን ወንጀለኛውን የመቱ ያህል ሳይሰማቸው አልቀረም፡፡ ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ከሳጥኑ ውስጥ ነፃ ሰው ሆኜ ወጣሁ፡፡ ወዳጆቼ ሁሉ በደስታ ስከሩ፡፡ የሚያውቁኝ ብቻ ሳይሆኑ ችሎቱን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በልዩ ፈገግታ "እንኳን ደስ አለህ" አሉኝ:: እኔ ግን የምናገረው ጠፍቶኝ እምባዬ እንደጎርፍ ይወርድ ነበር፡፡ ለእኔ አልማዝ የሞተችው ገና
👍323😢3😁1
አሁን ነው:: ከሁሉም በላይ ካለጥፋቷ ይህንን ሁሉ ዘመን እንደ ጥፋተኛ ቆጥሬያት፤ በጥላቻና በከሀዲነት ፈርጄያት መቆየቴ ውስጥ ውስጡን አንገበገበኝ:: እውነቱን ለማወቅ እንኳን አንድም ጥረት ሳላደርግ በመኖሬ በተዘዋዋሪም ቢሆን ለሞቷ ተጠያቂ ነበርኩና ነፃ ነህ ብባልም ውስጤ ግን ነፃ የመሆን ስሜት በጭራሽ አልነበረውም። ከችሎቱ እንደወጣን በተገኘው ድል እጅግ የረኩና የተደሰቱት ኤልሳና ጠበቃዬ በደስታ ሰክረው ተቃቅፈው ተሳሳሙ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ በፖሊስ ታጅቤ ከችሎቱ እንደወጣሁ፣ አንድ ሰው ከኋላዬ ጠራኝ፡፡ በሀሰት የመሰከረብኝ የሆቴሉ አስተናጋጅ ነበር፡፡ ብልጭ አለብኝ፤ "አሁን ደግሞ ምን ቀረህና ነው ስሜን የምትጠራው?" ብዬ አምባረቅሁበት፡፡ እሱ ግን ትህትና በተሞላው ሁኔታ፤ "ይቅርታ ያድርጉልኝ ጌቶች፡፡ እስቲ ተመልክቱ! ሰውዬው ከእርስዎ ጋር በጣም ይመሳሰላል፡፡ በሀሰት ለመመስከር ብዬ ሳይሆን መልካችሁ ተመሳስሎብኝ ተሳስቼ ነው" አለኝ፡፡ ይህንን ስሰማ አልማዝ መመሳሰላችንን አስመልክቶ የምትነግረኝ ትዝ ስላለኝ ለማረጋገጥ ዶ/ር አድማሱን አሻግሬ ማየት ጀመርኩ፡፡ በእርግጥም እኔኑ ነበር የሚመስለው፡፡ ዶ/ር አድማሱ በእኔ ምትክ በእኔው ካቴና ታስሮ ወደ መኪና ሲገባ አዘንኩለት፡፡ በፍ/ቤቱ ውሳኔ መሠረት ነፃ ሆኜ የምለቀቀው ወህኒ ቤት ወርጄ የመለቀቂያ ወረቀት ከተቀበልኩ በኋላ በመሆኑ ወደ ወህኒ ቤት ከሚወርደው ከዶ/ር አድማሱ ጋር ማዶ ለማዶ ተቀምጠን ተጓዝን፡፡ በእሱ ፊት ላይ የጥላቻ

ገፅታ ቢታይበትም እኔ ግን በሀዘን ስሜት ተመለከትኩት:: የነበረኝ ጥላቻ ሁሉ የት እንደገባ ባላውቅም የድሮው የእኔን እየወደድኩ የተጠላሁ አድርጎ የማየት ስሜት በእሱ ላይ ተገልጾ በማየቴና ይህንን ወንጀል እንዲፈፅም እንደገፋፋው በመረዳቴ አዘንኩለት፡፡ እየወደዱ አለመወደድ፣ እያፈቀሩ አለመፈቀር ከባድ ነውና ቢያሳዝነኝ የሚደንቅ አልነበረም:: ግን በመግደሉ ከመፀፀት ፋንታ መደሰቱንና ዳግም ለበቀል ያለውን ስሜት ሳጤነው፤ እጁ በደም ታጥቦም ቢሆን የሚጠራ አለመሆኑን ሳስብ ደግሞ ጭካኔው ያንገፈግፈኛል:: ዶ/ር አድማሱ ዓይኑን ከእኔ ላይ ሳይነቅል ግንባሩን አጨማዶ በንዴትና በጥላቻ ዓይን ያየኛል:: ግን ለምን እንዲህ ጠላኝ? እኔ እኮ ተስፋ ቆርጬ እሷን ለእሱ ትቼ፣ ሐሳብ ብቻ ታቅፌ የኖርኩና ከሐሳቤ ጋር እየታገልኩ እብደት ጠርዝ ላይ ቆሜ የይስሙላ ሕይወት ከመኖር ውጪ እሱን ለመጉዳትም ሆነ አልማዝን ለመበቀል አንድም ያደረኩት ነገር አልነበረም፡፡ እንደ እኔ ግምት እሷ ለእኔ እንዲህ የፀና ፍቅር አላት ብዬ አስቤም ሆነ አልሜ ስለማላውቅ ይህንን ሁሉ ዓመታት ላገኛት ከመመኘት ይልቅ እንዳላገኛት ስሸሽ የነበርኩ ሰው በመሆኔ ለእሱ ምንም አስጊ አልነበርኩበትም፡፡ ታዲያ ይህ ሆኖ እያለ ለምን ይህንን ያህል ሊጠላኝ ቻለ? እያልኩ ባለቀለት ጉዳይ መጨነቅ ጀመርኩ፡፡ በሁለተኛው ቀን ለመፈታት ስሜ ሲጠራ ከጓደኞቼ የመለያያው ቀን መድረሱን ተረዳሁት:: ጓደኞቼ የእስር ቤት ወጉ ሆኖ ተለይቻቸው ስሄድ ቅር ቢላቸውም፣ በመፈታቴ ደግሞ ተደስተዋል፡፡ እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ ልክ ከቤተሰቦቹ እንደሚለያይ ሰው ሆዴን ባር ባር አለው፡፡ እምባዬም መውረዱን ቀጠለ:: እርግጥ ለአለፉት አራት ዓመታት ገደማ ቀንና ሌሊት ሳልለያቸው በየቀኑ ለሀያ አራት ሰዓታት አብሬ እየበላሁና እየጠጣሁ ያሳለፈኩ በመሆኔ እንደቤተሰብ ባያቸው የሚደንቅ አልነበረም፡፡ ከእነዚህ ጎደኞቼ ጋር ያሳለፍኩት አራት ዓመት፣ ምናልባት ቀን ትምህርት ቤት እየተማርኩና ከጓደኞቼ ጋር እየተጫወትኩ ያሳለፍኳቸው ሰዓታት እንዲሁም ዩንቨርስቲ ስማርና በስራ ላይ ሆኜ ያሳለፍኳቸው ጊዜያት ተቀንሰውበት ከሚቀረው ከቤተሰቦቼ ጋር ካሳለፍኩት ዓመታት ጋር ቢነጻጸር፣ ቢያንስ አንድ ስድሰተኛውን ሊሆን ስለሚችል ባለቅስ የሚበዛብኝ አልነበረም፡፡ ከወህኒ ቤት የመለቀቂያ ወረቀቴ ተዘጋጅቶ እንደተሰጠኝ ከግቢው ወጣሁ፡፡ ከእስር መፈታቴ ቢያስደስተኝም ወዴት ነው የምሄደው እያልኩ መጨነቅ ጀመርኩ፡፡ ቤት እንደሆነ የለኝም:: ሕይወቴ በብቸኝነት የተሞላ ስለነበር ደፍሬ የምሄድበት ጓደኛም አልነበረኝም:: አልቤርጎም እንዳልይዝ

ገንዘብ የሚባል ነገር ካየሁ ሰነባብቼአለሁ:: ያለኝ አማራጭ የቀድሞ አከራዮቼ ጋ ሄጄ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ እነሱ ጋ መጠለል ብቻ ነው እያልኩ እየተጨነቅሁ አግቢው ስወጣ፣ ኤልሳና ጠበቃዬ በር ላይ ሲጠብቁኝ አገኘኋቸው፡፡ በቀጥታ ወደ እነሱ በጥድፊያ በመሄድ በሁለቱም የጋራ እቅፍ ውስጥ ገብቼ አንደበት ሊገልጸው ከሚችል የፍቅር ስሜት በላይ በሆነ ሁኔታ ተሳሳምን፡፡ ተያይዘንም በኤልሳ መኪናም ወደ እሷ ቤት አመራን፡፡ ኤልሳ ጋር ለሶስት ዓመታት ያህል ሊረሳ የማይችል ሕይወት አብረን አሳልፈን ስለነበር የእሷ ውለታ ብዙም አልከበደኝም ነበር። ለእኔ እንቆቅልሽ የሆነብኝና የከበደኝ ነገር ቢኖር ያለምንም ክፍያ እንደዚህ የደከመው የእጮኛዋ የጠበቃዬ ውለታ ነበር። ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ውለታውን ለመመለስ የሚያስችል አቅም ስላልነበረኝ ላደርገው የምችለው ነገር አመሰግናለሁ ማለት ብቻ ስለነበር ከልብ በመነጨ ስሜት "አመሰግናለሁ" አልኩት፡፡ ለእኔ ያደረጉትን ነገር ሳይና ደስታቸውን ስመለከትና መሰረት በሌለውና ሁለቱም በማያውቁት ነገር እነርሱን መጠርጠሬን ሳስብ፣ ነፃ ወጥቼ እንኳን የወንጀለኝነት ስሜት እንዲሰማኝ አደረገኝ፡፡ ውስጤ በዚህ እንደተጎዳ በደስታና በፀፀት ስሜት እያለቀስኩ፤ “ግን ለምን? ለምን ለእኔ ምንም ለማልጠቅም ምስኪን እንዲህ መድከም አስፈለገህ?'' አልኩት፡፡ “እኔ ላንተ ብዬ ሳይሆን ፍትህ ተጓድላ እንዳትቀር በመፈለግ ያደረኩት ተግባር ነው:: ትላንትም ሆነ ዛሬ ካንተ በላይ የተደሰትኩት እኔ ነኝ፡፡ ደስታዬ አንተ በመፈታትህ ብቻ ሳይሆን ሐቅ ተዳፍና ባለመቅረቷና አሸናፊ ሆና ስትወጣ በማየቴ ነው:: በሠራሁትም ሥራ ገንዘብ አላግኝ እንጂ የጥሩ ተግባር ዝናና የመንፈስ እርካታ አግኝቼበታለሁ፡፡ ዝናና በራስ መተማመን ካለ ደግሞ ያለምንም ጥርጥር ገንዘብ ተከትሎ ይመጣል" አለኝ:: ቀጠል አድርጎም በመቀለድ መልክ፤ “ከዚህ በላይ ደግሞ ከኤልሳ ጋር በቅርቡ ስለምንጋባና ይህንን በድል ከተወጣሁ ጥሎሽ እንደማልጠየቅ ስለተነገረኝ በተዘዋዋሪም ቢሆን ክፍያ ተከፍሎኛል ማለት ይቻላልና አትጨነቅ” በማለት ከት ብሎ ሳቀ፡፡ እኔም ከልቤ ፈገግ አልኩ፡፡ ቀስ በቀስ የነፃውን ሰው ዓለም _ እየለመድኩት መጣሁ:: አለቆቼ ያላግባብና ያለጥፋቴ ባሳለፍኩት የእስር ዓመታት እጅግ በጣም ስላዘኑ ወደ ሥራ እንዲመልሱኝ ስጠይቃቸው ምንም ሳያንገራግሩ ወዲያው አስገቡኝ፡

ትንሽ ቆይቼም የራሴን ቤት ተከራይቼ ሠራተኛዬ ቀድሞ አከራዮቼ ዘንድ አስቀምጣ የሄደችውን መጻሕፍትና እነ ኤልሳ የሰጡኝን አንድ አልጋ፣ አንድ ወንበርና አንድ ጠረጴዛ ይዤ እንደ አዲስ ጎጆ ወጪ ኑሮዬን "ሀ" ብዬ ጀመርኩ:: ከዚህ ውጪ አለኝ የምለው አንድ ታሪካዊ ንብረት ቢኖር ከፖሊስ ጣቢያ ያመጣሁት ዲያሪ ነበር:: በአልማዝ ፋንታ የቀረኝ ነገር ቢኖር ይኼው የእሷ የእጅ ጽሑፏ ነው:: ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ደግሜ ደጋግሜ አነበብኩት። ባነበብኩት ቁጥርም የማነበው የእሷን የእጅ ጽሑፍ ሳይሆን ቁጭ ብላ የምታወራኝ ያህል ሆኖ ይሰማኛል:: ታሪኩ በመደምደሙና ፍጻሜውም እንዲሁ የታወቀ በመሆኑ እንደበፊቱ ለማንበብ ባያጓጓኝም፣ ቀደም ብዬ ሳነበው በነበረ ጊዜ አልፈታ ያሉኝ እንቆቅልሾች እንዲህ በቀላሉ በእውነት ኃያልነት ሊፈቱ ይችሉ እንደነበር ሳስብና ለዚህ ሁሉ ጊዜ ይህንን ለመረዳት አለመቻሌን ሳስታውስ፤ ዶ/ር አድማሱ "ያንን ደደብ…" ብሎ
👍32👎21
የተናገረው ምናልባት ትንሽም ቢሆን እውነትነት ሳይኖረው አይቀርም ብዬ ማሰቤ ግን አልቀረም፡፡ ያም ሆነ ይህ! ሁሉ ነገር ባልጠበቁትና ባልገመትኩት መንገድ ተጠናቀቀ፡፡ እኔ እንደተመኘሁት ሳይሆን ሕይወት በፈለገችበት አቅጣጫና መንገድ ያለማንም ከልካይ እንዳሻት ተጓዘች፡፡ የእኔ የመከራ ሕይወትም ያለፈው ውስብስብ ታሪክን ሰንቆ ሕይወት ወደ መራችው ለመሄድ ኋላ ኋላ ድክ ድክ እያለ መከተሉን ቀጠለ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ፣ ቅደም ተከተሉ እና በግብግቡ ውስጥ የነበሩት አያሌ ድርጊቶችና ፈተናዎች አንድም ሳይዛቡ፣ እነሆ የአልማዝ ሕያው ዲያሪ እስከ ኅልፈተ ሕይወቴ ድረስ በሕሊናዬ ውስጥ ተቀርጾ ይኖራል፡፡ በእጄ በያዝኩት ዲያሪ ውስጥ ደግሞ የአልማዝ ፍቅርና ምኞት፣ ተስፋና ትዝታ፣ ዓላማ እና ግብ እየተዋሀደበት የእኔና የእሷ ያልተጻፈ የሕይወት ጥምር ዲያሪ ፍሰት ይቀጥላል...

ተፈፀመ።

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
🥰47👍285