🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_16
ኤልሳ ተሰናብታኝ ከፖሊሱ ጋ ተከታትለው እየወጡ ላለ ውስጤ ሆኖ ስለሚያስጨንቀኝ የአልማዝ አሟሟት ልጠይቃት ፈልጌ ስሟን ተጣራሁ፡፡ ዞር ስትል እምባ ከዓይኖችዋ ይወርድ ስለነበር አማራጭ አልነበረኝምና፤ "አይ ተዪው" አልኳት፡፡ ቀጥ ብላ ቆማ በርህራኄ ዓይን አየችኝ፡፡ እነሱ እንደወጡ ምርመራው ክፍል _ ውስጥ የቀረነው እኔና ጠበቃው ብቻ ነበርን:: ፊት ለፊቴ ተቀምጦ ዓይን ዓይኔን ሲያይ ምን ብዬ እንደማነጋግረው ሳወጣና ሳወርድ፣ እሱ ራሱ ዝምታውን ጥሶ፤ “አቶ አማረ፤ እኔ ሣሙኤል ገድሉ እባላለሁ፡፡ የኤልሳ ጓደኛ ነኝ፣ ማለትም እጮኛዋ ነኝ፡፡ እሷ ላንተ ያላት ፍቅር ልዩ ነው፡፡ በንፁህነትህና ባልፈጸምከው ወንጀል እንደታሰርክ ምንም ጥርጣሬ የሚባል ነገር የላትም:: ባልሰራኸው ሥራ እንደተከሰስክ ስለምታምንም አንተን መርዳት ትፈልጋለች:: በቀደም ዕለት ብቻህን ያለ ጠበቃ መቆምህን እንዳየች በጣም አዝና እኔ እንድቆምልህ ስለጠየቀችኝ፣ ጥብቅና ልቆምልህ ተስማምቼያለሁ:: እርግጥ ነው ከዚህ በላይ ደግሞ እኔ ላንተ ጥብቅና ለመቆም የወሰንኩት ኤልሳ ባንተ ንጽህና ላይ ያላትን እምነት በመረዳቴና በመጋራቴ ነው:: እኔ ለማልረታበት ነገር ጥብቅና መቆም አልፈልግም:: ስለዚህ ፍቃድህ ከሆነ እኔ ጠበቃህ ለመሆን ዝግጁ ነኝ' አለኝ፡፡ ጠበቃዬ ዕድሜው በግምት አርባ ዓመት አካባቢ የሚደርስ በመሆኑ ከኤልሳ ጋር ሲተያይ በጣም ይልቃታል፡፡ ኤልሳ የእኔ እኩያ በመሆኗ ዕድሜዋ ከሰላሳ ዓመት አይበልጥም፡፡ እርግጥ ቦርጫምና ወፍራም በመሆኑ ምክንያት ምናልባት ልጅ ሆኖ ነገር ግን በዚሁ የተነሳ ጠና ያለ ሊመስል ይችላል፡፡ በተረፈ መልከመልካምና ከእሷ በትንሹ ፈገግ ያለ ጥቁር ፊት አለው፡፡ ሲያወራ በየመሀሉ ፈገግ ስለሚል ሁኔታው ሁሉ የሚከብድ ዓይነት አይደለም፡፡ እኔኑ ለመርዳትና ጥብቅና ሊቆምልኝም መጥቶ ፍቃደኛ መሆኔን በትህትና ሲጠይቀኝ በማየቴ ለሰው አክብሮት ያለው በመሆኑ ጨዋ ሰው ነው ብዬ ደመደምኩ፡፡
“እንግዲህ እኔ ጥብቅና የምቆምልህ አንትን ወክዬ በመሆኑና እውነቱንም ማወቅ ስላለበኝ፣ የሆነውን ነገር ሁሉ ሳትደብቅ ንገረኝ" በማለት የተለያዩ ጥያቄዎችን ያዥጎደጉድብኝ ጀመር። እንዳንዶቹን ጉዳዮች እኔ ራሴ የማላውቃቸው ስለነበሩና እንዲያውም በተቃራኒው እኔ ኤልሳን ልጠይቃት የተዘጋጀሁበት ጥያቄ ስለነበር ራሴው ተመልሼ ተጠያቂ ስሆን ደነገጥኩ:: የጠየቀኝም የማላውቀውን ታሪክ ነበርና ብዙ አውጥቼና አውርጀ:: “እውነት ለመናገር ከሆነ፣ የምትጠይቀኝን ነገር እኔ ራሴ አላውቀውም፡፡ የአልማዝንም ሞት የሰማሁት እዚህ እስር ቤት ውስጥ ነው:: ከትምህርት ቤት ከተባረርኩ ጀምሮ አይቻት አላውቅም” አልኩት:: ግራ በተጋባ ሁኔታ ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆየና፤ “ማለት እዚህ ስትመጣ ለምን እንደመጣህ አታውቅም ነበር ማለት ነው" አለኝ:: ሆን ብዬ ላለመናገር የማደርገው ነገር ስለመሰለው በአመላለሴ ቅር መሰኘቱ ከፊቱ ላይ ይነበብ ነበር፡፡ ያለኝ አማራጭ ሁኔታውን በዝርዝር ማስረዳት ብቻ ስለነበር እንዴት እዚህ እንደመጣሁ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሬ ዘክዝኬ ነገርኩት:: የሚፈልገውን መረጃ ፅፎ ከጨረሰ በኋላ በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት እንደሚመጣ ነግሮኝ ተሰናብቶኝ ወጣ፡፡ በሦስተኛው ቀነ ቀጠሮ ስሜ እንደተጠራ በፖሊስ ታጅቤ ዳኞች ፊት ቀረብኩ:: የእጄ ላይ ሰንስለት ተፈትቶ ሳጥኔ ውስጥ ገባሁ:: ጠበቃዬ ከፊት ለፊት ከአቃቤ ሕጉ በተቃራኒ ቆሞ ባለበት አንገቱን ጎንበስ በማድረግ ሰላምታ ስጠኝ፡፡ ኤልሳ ከፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ ተቀምጣ በማዘን መልክ አንገቷን ወደ ጎን ዘንበል አድርጋ ትመለከተኛለች:: ጥቂት የመስሪያ ቤት ጓደኞቼም ጥግ ላይ ተቀምጠዋል:: መሃል ዳኛው በያዙት መዶሻ ጠረጴዛውን ጠልዘው "ፀጥታ” ካስጠበቁ በኋላ፤ የክሱን ዝርዝር ልክ ስገድል እዚያ የነበሩ በሚመስል መልኩ በንባብ ማሰማት ጀመሩ፡፡ እስር ቤት ውስጥ እያለሁ ለአንድም ደቂቃ ቢሆን አለወንጀሌ መታሰሬን አስቤ እና ተበሳጭቼ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ዛሬ እዚህ ሳጥን ውስጥ ገብቼ ስቆም የሆነውን ነገር በፀጋ መቀበል ተስኖኝ ተበሳጨሁ፡፡ ንፁህ የፍቅር ሰው እንደወንጀለኛ ስንት ነፍሰ ገዳይ ገብቶ በተፈረደበት ሳጥን ውስጥ ገብቼ ካለጥፋቴ ስወነጀልና ያልፈፀምኩት የወንጀል ታሪክ ሲተረክ ብሎም ባልፈፀምኩት ወንጅል ሊፈረድብኝ እዚህ መምጣቴን ሳስብ እምባ ተናነቀኝ። ነገር ግን ማልቀሱ ከፍርሐት የመነጨ እንጂ ባልፈፀምኩት ወንጀል በመታሰሬ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ስለማይኖር እንደምንም ታግዬ መለስኩት፡፡ ይህንንም ሁኔታ ሳስብ በዚች ዓለም ላይ ምን ያህሉ ሰው እንደእኔ ያለኃጢአቱ ተወንጅሎ እዚህ ሳጥን ውስጥ ቆሞ በግፍ ተፈርዶበት ይሆን በማለት ማሰላሰል ጀመርኩ።
ዳኛው ምን እንደሚሉ ባይገባኝም ያ አቃቤ ሕግ የጠቀሰውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር ተጠቅሶ ጭካኔ በተሞላው መንገድ የፈፀምኩት ግድያ ድራማዊ በሆነ አቀራረብ ይተረክ ጀመር፡፡ እኔ በጉጉት ስጠባበቅ የነበረው አልማዝ እንዴት እንደሞተች ለማወቅ ነበር። ግን ምን ያደርጋል የዚያችን ከራሴ በላይ የምወዳትንና የምሳሳላትን የውድ ፍቅረኛዬን አሟሟት በንባብ ስሰማ ምነው ይህንንስ ባልሰማሁት ኖሮ ማለቴ አልቀረም። እንካን ሰው የሚጎዳ ድርጊትን ማድረግ ቀርቶ አንድም ቀን ከአፋ ክፉ ቃል ወጥቶ የሚያውቅ ፍቅረኛዬ የተገደለችበትን ጭካኔ የተሞላበት አገዳደል እንደስማሁ ራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ ድምፅ እያሰማሁ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ በሁኔታው ቢደናገጥም፣ እኔ እንዲያ የምሆነው ግን የሚያጋጥመኝን የቅጣት ውሳኔ መጠን ፈርቼ እንጂ ለእሷ ሲል ነው የሚያለቅሰው ብ እንደማያስብ እርግጠኛ ስለነበርኩ ብዙም ደንታ ሳይሰጠኝ ለቅሶዬን ቀጠልኩ፡፡ ዳኛው ልቅሶዬን እንዳቆም አዘው ትረካቸውን ቀጠሉ፡፡ ዩንቨርስቲ ውስጥ ተዋደን በፍቅር ስንኖር እኔ በትምህርቴ በመድከሜ የተነሳ መባረሬን፣ ከዛ በኋላ እሷ እዛ በቆየችበት ወቅት ዶ/ር አድማሱ ከተባለ የዩንቨርስቲ መምህር ጋር ተዋዳ ፍቅር መጀመሯን፣ በዚህም የተነሳ ከእኔ ጋር ቅራኔ ውስጥ በመግባቷ መለያየታችንን፡፡ ከዛም እኔ በቂም በቀል ተነሳስቼ አመቺ ጊዜና ቦታ ጠብቄ ሕይወቷን በማጥፋቴ በመግደል ወንጀል ተከስሼ መቅረቤን በመግለፅ ድራማውን አጠናቀው መጋረጃውን ዘጉ፡፡ ለእኔ ታሪኩ የተፈፀመ ድርጊት ሳይሆን የሆነ አንድ ልብ ወለድ ታሪክ በድራማ መልክ ተሰርቶ የማይ እስከሚመስለኝ ድረስ ፈዝዤ አዳመጥኩ:: ፍቃደኛነቴ ሳይጠየቅ በቲያትሩ ውስጥ የምሳተፍና መሪ ተዋናይ ሆኜ ከአልማዝ ጋር እንደምንተውን ያህልም ሆኖ ተሰማኝ:: በመጨረሻም ጥፋተኛ መሆንና አለመሆኔን የእምነትና ክህደት ቃሌን እንድሰጥ መድረኩ ተለቀቀልኝ:: በምሰጠው መልስ ላይ ከራሴ ጋር ግብግብ ገጠምኩ:: ሁለት አማራጮች አሉ፣ እየተተወነ ያለው ድራማ፣ ድራማ ሳይሆን በእውነት የተፈፀመ ድርጊት በመሆኑ ድርጊቱን አምኖ ማረጋገጥ፣ አሊያም ትያትሩ ትያትር እንጂ ከዚህ ያለፈ እውነተኛ ድርጊት አለመሆኑን ማረጋገጥ፡፡ የቀረበው ትያትር እንጂ በውን የተፈፀመ ድርጊት አለመሆኑን ለማሳመን ደግሞ ድርጊቱን አለመፈፀሜን በተጨባጭ ማስረዳት አለብኝ፡፡ ነገር ግን አልገደልኩም ብዬ ለመናገር ድፍረቱን አጣሁ፡፡ ምክንያቱም ይህንን ቃል እየደጋገምኩ ተናግሬዋለሁ፤ ግን አንድ ሰው እንኳ ላሳምን አልቻልኩም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ዳኛው በማራኪ አነጋገር እንዲህ አጣፍጠው ወንጀለኛ መሆኔን ለዚያ ሁሉ ባለጉዳይና ታዛቢ ካቀረቡ በኋላ በዚያ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህ የተባለው ፍጹም ውሸት ነው ብሎ ለማሳመን