🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_17
ይኸው አንድ ዓመት ተፈርዶበት ግማሹን አገባዷል፡፡ እንግዲህ በዚሁ ክቡር ነው በሚለው የሌብነት ስራው ለእናትና አባቱ ቤት መሥራት ዓላማው እንደነበርና ያንን ቀደም ሲል እንዳሳካ፣ ወደፊት ለራሱ የሚሆን መኖሪያ ቤትና መቋቋሚያ ገንዘብ እንዳገኘ ይህን የሚወደውን ሥራ እንደሚለውጥ ነገረኝ:: የሚገርመው መው ሚስቱን ያገባው ሳትወድ በግድ
አባቷን በሽጉጥ አስፈራርቶ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ታዲያ ባለቤቱ በየጊዜው ጥሩ ጥሩ ምግብ እየያዘች ትመጣና አልቅሳ ትሄዳለች፡፡ ምንም እንኳን እንደካቦአችን ዘወትር እየመጣች የምታለቅስልኝ ቆንጆ ሚስት እንድትኖረኝ የታደልኩ ባይሆንም፤ አለሚቱ ግን አልፎ አልፎ ምግብ ይዛ ትጠይቀኝና አለቃቅላ ትመለስ ነበር፡፡ ለመጠባበቂያ ብዬ ያስቀመጥኩትን ገንዘብ ከሳጥን እያወጣች እንድትጠቀም ነግሬያት ስለነበርና አልፎ አልፎም የመሥሪያ ቤት ጓደኞቼ እየመጡ ገንዘብ ስለሚሰጡኝ ችግሩ ብዙም አልጠናብኝም ነበር:: ነገር ግን በመጡ ቁጥር "ምን ሆነህ ታሰርክ? እንዴት ነው በቅርቡ የመፈታት ተስፋ አለህ?" ወዘተ.. ለሚለው ተደጋጋሚና አስቸጋሪ ጥያቄያቸው ለጊዜው መልስ ስለማላገኝለት አእምሮዬን ክፉኛ ያስጨንቀው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ በተለይ አንዳንዶቹ ባይመጡ ይሻለኝ ነበር። ጠበቃዬ በየመሀሉ እየመጣ ጠቃሚ ነው ያለውን መረጃ ለማሰባሰብ በተለመደው መልኩ በጥያቄ ያጣድፈኛል፡፡ ይሁን እንጂ ከእኔ የሚያገኘው መረጃ እንዳሰበው ስለማይሆንና ብዙም ልረዳው ዝግጁ ስላልነበርኩ አልፎ አልፎ መበሳጨቱ አልቀረም፡፡ “ስማ አቶ አማረ! እኔም እንደ ኤልሳ በአንተ ንጽህና ላይ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ግን የእኛ ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም:: ለዳኞች እውነቱን ፈልቅቀን ማሳየትና ማሳመን መቻል አለብን:: ለዚህ ደግሞ አንተ አእምሮ ውስጥ ያለውን እውነት ምንም ሳትቀያይርና ሳታድበሰብስ ልትነግረኝ ይገባል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ እኔ አንተን ወክዬ በመቆም ተከራክሬ ማሸነፍ እችላለሁ:: አለበለዚያ ግን ንፁህ ሆነህም ቢሆን የአንተ ንጽህና እያነሰና እየመነመነ ከሄደና ባንጻሩ ደግሞ አንተን ወንጀለኛ የሚደርጉ ነገሮች ጎልተው ከወጡ ባንተ ላይ ሊፈረድ ይችላል፡፡'' አለኝ:: እንደነገረኝ ከሆነ አልማዝ እኔን ትታ ሌላ በመውደዷ የተነሳ ገድሏት ሊሆን ይችላል ተብሎ በፖሊሶች በኩል እንደሚጠረጥሩኝና እስካሁን ድረስም አልማዝን ገድሎ ይሆናል ሊባል የሚችል ከእኔ የተሻለ ሌላ ተጠርጣሪ አለ ተብሎ እንደማይታሰብ ገለጸልኝ፡፡ ስለዚህም ይህንን ግምትና አስተሳሰብ ለመለወጥ ከእኔ ብዙ እንደሚጠበቅብኝም ሊያስረዳኝ ሞከረ፡፡ እኔ ግን ሌሎች ይህንን በማሰባቸው አልፈረድኩባቸውም፡፡ ምክንያቱም እነሱ እኔ ለእሷ ያለኝን ፍቅር እንዴት ሊረዱ ይቻላቸዋል? በእኔ ሕሊና ውስጥ ለአልማዝ ፍቅር እንጂ ለጥላቻ የሚሆን ቦታ የለም፡፡ ጊዜያዊ ስሜቴ በአንዳንድ ሁኔታዎች የተነሳ ላይ ላዩን ቢጠላትም ውስጤ ግን ይወዳታል፡፡ እንኳን ሳትበድለኝ ቀርቶ ምንም ያህል በደል ብትፈጽምብኝ ያንን አጋጠማት የተባለውን ሁኔታ ለእሷ በፍፁም አልመኘውም:: የጥንት ጥላቻዬም ቢሆን የመጥላት ሳይሆን
የፍራቻዬ መገለጫ ነው፡፡ ያም የሌላ ሳይሆን እያስታወስካት ከመሰቃየት ይልቅ ጥላቻን እየራገብኩ ከፍቅር ለመራቅ የማደርገው ግብግብ ነበር። ያም ሆነ ይህ ታሪካችን ይኸው መሆኑንና የመከላከያ ምስክር ይሆኑኛል ያልኳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር፤ የጮኛውን የኤልሳን ስም ጨምሬ ስጠሁትና ተለያየን፡፡ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች የሚሰሙበት ቀን ደርሶ ወደ ፍርድ ቤት አመራሁ፡፡ምስክሮቹ በየተራ እየወጡ የእኔን ገዳይነት ቆመው ያዩ ወይም መግደያ ያቀበሉ እስኪመስል ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ እየማሉ መሰከሩ። ሲገድላት አይተናል ማለት ቢቀራቸውም ከአነጋገራቸው እንደተረዳሁት ስለመግደሌ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ አልነበራቸውም። አቃቤ ሕግ የሚፈልገውን ጠቦት አግኝቶ ለማረድ ቢላ ያቀበሉት ያህል ተሰምቶት በድል አድራጊነት በቁሙ ተፍነከነከ፡፡ ቢላው እጁ ገብቶለታል፤ ነገር ግን በእኔ ደም መጨማለቅ ያልፈለገ ይመስል ዳኛው ይህንን የሕሊናና የፍርድ ሃላፊነት እንዲወስዱለት ለማድረግ፣ በደሌንና ጭካኔዬን ከምስክሮች አፍ በሚፈልገው መልኩ በጥያቄ እያውጣጣና እያጣጣመ እሱ ግን እንደጲላጦስ ከደሙ ንፁህ ለመሆን እያመቻቸ ያቀርብላቸዋል:: ፍርድ ቤቱ ውስጥ የተቀመጡት ሰዎች ዓይኖች እሳት ሆነው የሚያቃጥሉ ቢሆን ኖሮ ጨርቄን አልፎ አጥንቴን አመድ ያደረገው ነበር፡፡ ሁሉም በሆዱ ያቺን የተማረች ምስኪን ጭካኔ በተሞላው መንገድ ስገድላት ይታየዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ጭካኔ ፈፅሞ እንዴት ራሱን አያጠፋም? አሁን ይህንን ሁሉ በደል ፈፅሞ ነፃ መውጣት ያምረው ይሆናል እኮ? አይገርምም! እያለ በውስጡ ሳያሰላስል አልቀረም:: አንዳንዱ ሩህሩህ ደግሞ “ ፊቱን እንኳን ሲያዩት ገዳይ አይመስልም፣ ግን ምን እንዲህ አስጨከነው? ምናልባት ማን ያውቃል የከፋ በደል አድርሳበት ሊሆን ይችላል" ብሎ አስቦም ሊሆን ይችላል:: ያም ሆነ ይህ እውነቱን ግን የምናውቀው እሱ አንድየ አምላክና እኔ ብቻ ነን። የእኔን እውነት ደግሞ የሚሰማ ወይም ለመስማት የሚጓጓ ጆሮ ተፈልጎ የሚገኝ አይደለም:: አምላክ ደግሞ በእውነት ውስጥ ሰርጾ እንጂ መቼም ቢሆን እንዲህ በገሀድ መሬት ወርዶ ስለማይመሰክር እውነት በአደባባይ እስከምትታይ ድረስ ዞሮ ዞሮ እውነት የሚባል ነገር ያው ሌሎች እንደሚያስቡትና እንደሚገምቱት በመሆኑ ወደድኩም _ ጠላሁም የእኔን ወንጀለኝነት መቀበል የግድ ነው፡፡ ብዙ የውሸቶች ዓይነቶች በሰፈኑባት በዚህች ዓለም ውስጥ ውሸቶች ተደጋግመው ሲሰሙ "እውነት" ይሆናሉ እንዲሉ፣ ጥቂቱ እውነት ካለም ወይ ይደበቃል ወይ ጠፍቶ ይቀራል፣ አሊያም ራሱ ውሸት ይሆናል።
ከአቃቢ ሕግ ምስክሮች መሃል የዶ/ር አድማሱ ስም ሲጠራ ክው ብዬ ደነገጥኩ፡፡ አዎ እዚህ ወንጀለኛ መቆሚያ ሳጥን ውስጥ መቆሜ የማይቀር መሆኑን ባውቅ ኖሮ መግባት የነበረብኝ ይህንን ሰው ገድዬ መሆን ነበረበት:: በፍቅራችን መሀል ገብቶ ለእኔና ለአልማዝ መለያየት ብሎም ለእሷ ሞትና ለእኔም እንዲህ መስቃየትና መንከራተት ከዚህ ሰው ውጪ ሌላ ቀዳሚ ተጠያቂና ምክንያት ሊኖር አይችልም:: ባለፉት ዓመታት ብዙ ግዜ ይህንን ከይሲ መበቀል እፈልግና ፈርቼ እተወው ነበር። ፍርሀቴና ስጋቴ ላለመታሰር ቢሆንም እነሆ ያሰብኩትን ሳልፈፅም ግን መታሰሬ አልቀረም:: እኔ ወኔ ኖሮኝ ልገድለው ባልችልም እሱ ግን ሁለት ጊዜ ገድሎኛል፡፡ በመጀመሪያ ፍቅሬን ነጠቀኝ፣ ቀጥሎም በዚሁ የተነሳ ወንጀለኛ ሳልሆን ወንጀል እንደሰራሁ ተቆጥሬ በማላውቀው ነገር ለእስር ዳረገኝ:: ይህ አልበቃ ብሎት ይኸው ደግሞ ዛሬ ቀሪውን የድህነትና የመከራ ሕይወቴን እንኳ በሰላም እንዳልኖር በሐሰት ሊመሰክርብኝ መጣ። ዶ/ር አድማሱ የሚመስክረው እውነትና እውነት ብቻ መሆኑንና ከእኔ ጋር ዝምድናም ሆነ ጠብ የሌለው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ቀርቦለት ከማለ በኋላ ውሸትና ውሸት ብቻ መናገሩን ተያያዘው፡፡ አቃቤ ሕጉ እንደተለመደው በልበ-ሙሉነት ቆሞ ጥያቄውን ይጠይቅ ጀመር። እኔ ወንጀለኛ መሆኔን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነገር ባገኘ ቁጥር ወደ ዳኛው እየዞረና ጥያቄውን ደጋግሞ እየጠየቀ ዳኛው ሳይስሙት እንዳያልፉ ለማድረግ ይሞክራል፡፡ “እሺ ዶ/ር አድማሱ እርሶ እሷን ወደ ቤት እየወሰዱ ሲያስጠኑ፣ እሱ እንደሚቀናና እርሶ ጋ እንዳትመጣ እንደሚጨቀጭቃት ከነገረችዎ ለመሆኑ ከእሱ ከተለየች በኋላ እንዳይበቀላት አትፈራም ነበር?"፡፡ ዶክተሩ የሚፈልገውን ጥያቄ ያገኘ ይመስል በጥድፊያ ከአፉ ላይ ቀበል