አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
516 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዶ/ር ሶፊያ በማግስቱ ከምሽቱ 12፡3ዐ ላይ መኪናዋን እያሽከረከረች ታዲዮስ ቤት ደረሰች፡፡ሦስት ኩርቱ ፔስታል ሙሉ ስጦታ ይዛለች ፤ለአምስቱም ልጆች ፡፡በመከራ እየተንገዳገደች ነበር ዕቃዎቹን ተሸክማ በረንዳው ላይ ማድረስ የቻለችው፡፡መሬት አስቀመጠችውና በራፉን አንኳኳች፡፡ ሃያ አምስት ዓመት የሚሆነው ባለ ሹሩባ ፀጉር መልከ መልካም…»
#ፍቅር_የመሸባት_ሀገር


እዛ ሰው ይሞታል፣ እዛ ደም ይፈሳል
እዚህ ይጨፈራል ፣ እዚህ ይደነሳል
እዛ ሰው ያለቅሳል፣እዚህ ሳቅ ይነግሳል።
፨፨፨
እዛም እኛዎች ነን፣አዚም እኛ ባዮች
የደላን እኛው ነን ፣ እኛው ተበዳዮች
አንድነትን ሰብከን፣የምንሆን ብዙዎች፡፡
እኛው ነን የሞትነው፣እኛው ነን ቀባሪ
እኛው ነን ሙሾ አውራጅ፣እኛው ነን ጨፋሪ
አንድ ነን እያልን ፣ ልዩነት ፈጣሪ፡፡
፨፨
እዛ እኛ ስንሞት፣ እዚ እኛ ስንጨፍር
እዛ እኛን ስንቀንስ፣እዚ እኛን ስንደምር
ሙሾን ከደስታ ጋር የምንደባልቀው
እኛው እያነባን ፣ እኛው የምንስቀው
እኛው ለነፃነት ፣ ታግለን የምናልቀው
እኛው ባርነትን፣ፈቅደን የምንሞቀው
እዚ እየረሳን ፣ እዛ ም'ናፍቀው
ፍቅር መሽቶብን ነው፡፡
፨፨
እንዲህ ነው ሚኖረው....
ፍቅር የመሸበት፣ሀቅ ያልገባው ሀገር
እዛ እኛ ሙሾ አውራጅ ፣ እኛ አዚ ምንጨፍር፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢20👍11👏43🔥2
#እኔና_ጊዜ

ጊዜ አጥቼ እንጂ፣ ፍቅሬን ለማስረዳት
የሰማንያ ሚስቴን፣ በጣም ነው ምወዳት፡፡

ተወጥሬ እንጂ፣ ሀገሬን በማልማት
መቼ ዝም እል ነበር?፣ ልጄ ‘በራብ’ ሲሞት፡፡

ቸኩዬ ነው እንጂ፣ ስሮጥ ለቁም-ነገር

ሁለት ሰው ገጭቼ፣ አላመልጥም ነበር!!!

በተለይ በተለይ…
ጊዜ አጣሁኝ እንጂ፣ ጥቂት ፋታ ባገኝ ስለ ጊዜ ጥቅም፣ የምለው ነበረኝ !!!

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😁25👍8🥰5
ካንተ ቤት......
ቋንጣ ተሰቀለ
ሻኛ ተቆረጠ፣ ወይን እየተጠጣ፣
፨፨
ያ’ዳም ዘር ወንድምህ
ያለ ሁዳዴ ፆም በ’ራብ የ’ተቀጣ፡፡
፨፨
ይገርማል
አንተ ማለትኮ...
አንተ ማለት ጥጋብ ያለልክ ሠልቃጭ፣
እሱ ማለት ደግሞ...
እሱ ማለት ሚስኪን ካንተ ቤት ቀላዋጭ፣
፨፨
እንዲህ ነው ተፈጥሮ እግዜሩ  ሲያዳላ፣
አንዱ ፆሙን ሲያድር ሌላኛው ሲበላ፡፡
፨፧
በተራበች ነፍሱ
........ቀልቡ እየዋለለ፣
ድህነት ሰቅዞት
.......ሳይበላ እየዋለ፣
ሂወት ጨክናበት
ቆዳ ምላሽ ሊያገኝ
..........በጌቶቹ ቅዬ ፍሪዳ እየጣለ፣
ለሁዳዴው ፆም ፍቺ
በግ ሲጠባ ያድራል ቢለዋ እየሳለ፣
፨፨
እንዲህ ነው ተፈጥሮ እግዜሩ ሲያዳላ፣
አንዱ ፆሙን ሲያድር ሌላኛው  ሲበላ፡፡
፨፨
ትቀምሰው ያጣች ነፍስ ቁራሽ ንጣይ ቅምሻ፣
በጣር ሲቃ ታንቃ ስታጣ መድረሻ፣
ፍርድ አጥተን ከሰማይ የ'ግዜር እጅ መንሻ፣
ሠው የሠው አገልጋይ ሠው የመንደር ውሻ፣
ሲ..ጎ..መ..ጅ ይኖራል በ.በ.ሊ.ቶ.ች ጉርሻ፡፡



👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍242😁2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል ሠባት


“አበባም ይሁን ድንጋይ፣ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው!”

ማኀደረ-ሰላም!

አገባሁ!! ድል ባለ ሰርግ ዮናስ የሚባል ከአሜሪካ የመጣ ሰው አገባሁ፡፡ አስተያዬት ሰጪዎች ግን ለባለቤቴ የሚሉት “አፈስክ” ነው። አስተፋፈሱ የየቅል ይሁን እንጂ፧ እኔም ባለቤቴ ያገባኝ ሳይሆን ያፈሰኝ ነው የሚመስለኝ፡፡ በሆነ ግዴለሽ መዳፍ! እንደ አልባሌ ነገር የትም ተበታትኜ ከተደፋሁበት አፋፍሶ ያገባኝ ነው የሚመስለኝ። ለራሴ ቢቀፈኝም ከወዳደቅሁ እኔ ገጣጥሞ፣ በወጉ ያልተቃኜች በድን ሚስት የምትባል ፍጥረት የሠራ ነው የሚመስለኝ፡፡ በድፍን አዲስ አበባ ከላፍቶ እስከ ሜክስኮ፣ ከቦሌ እስከሃያሁለትና መገናኛ፣ ከተበታተንኩበት ለቃቅሞ የገጣጠመኝ ልክ እንደተሰበረ ብርጭቆ፣ ከነስንጥቄ ተጠጋግኜ የሆነ ደግ ሰው ቤት የተቀመጥኩ፣ ውስጤ ፍቅር የማይቋጥር እንዲሁ ቅርስ ነገር ...የዕድለ ቢስነት መታሰቢያ ቅርስ። ታዲያ መልስ ሲባል ባሌ አልፈልግም ብሎ ወደ አባቴ ቤት የሚመልሰኝ መስሎ ነበር የተሰማኝ፡፡ባደረገዉ...!

ብዙ ሰዎች ሲሉ እንደሰማሁት ትዳር የአዲስ ሕይወት ጅማሬ፣ ያለፈ ታሪካችንን አጀንዳ ዘግተን ለአዲስ ነገ “ሀ” ብለን ርምጃ የምንጀምርበት ምዕራፍ መስሎኝ ነበር፡፡ ግን ለእኔ እንደዚያ አልነበረም፡፡ ያለፈ ታሪኬን፣ ትዝታዬን፣ ሕመሜንና ደስታዬን ሁሉ ልክ እንደ ልብስና ሌላ ሌላ ኮተቴ ሁሉ በአእምሮዬ ሻንጣ አጭቄ ነበር ወደ አዲሱ ቤት ያዘገምኩት፡፡ ያው አዲስ አበባ ይባል እንጂ ሩቅ ነበር ለእኔ፡፡ ሰሚት ወደ ሚባል ሰፈር፡፡ አሜሪካ ይሁን አንታርቲካ፣ ሰሚት ይሁን ቃልቲ፣ ከምወዳት ሰፈሬ ሜክሲኮ ከራቀ ሩቅ ነው፤ ሩቅ ነበር ለእኔ። ስደት በርቀት ካልተለካ በስተቀር ስደት ነበር ለእኔ፡፡ ልደታን ወረድ ብዬ ካላዬሁ ያዛጋኛል፡፡ የዋቢ ሸበሌ ሆቴልን አጥር ታክኬ ካላለፍኩ ዓለም ምልክት የሌላት ምድረበዳ ትመስለኛለች፡፡ በ'ኮሜርስ' ዙሪያ ካላንዣበብኩ አዲስ አበባ የዋልኩ አይመስለኝም፡፡ ብሔራዊ ቲአትር በር የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችንና የቲያትር “ፖስተሮችን” ካላዬሁ፣ የዕለት መዝሙረ ዳዊቱን ሳይደግም እንደወጣ ሃይማኖተኛ ቅር ቅር ሲለኝ ይውላል፤ ስንት የማናውቀው ሱስ አለብን!? እትብት የሚባለው ነገር በሥጋ እንጂ በነፍስ አይቆረጥም መሰል!? የተወለድንበት ሰፈር ላይ ያለ የማይታይ የመንፈስ ችካል ላይ ተቋጥሮ፣ በረዥም ክር ከእኛ ጋር የተሳሰረ ነገር ነው፤ የትም ብንሄድ ይስበናል፡፡ ሻንጣዬን ከፍቼ ልብሶቼን ቦታ ቦታ ሳሲይዝ፣ አእምሮዬም በሰፊው ተከፍቶ አሮጌ ትዝታዬን በአዲሱ ቤቴ ውስጥ እንደ ፎቶ መደርደር ጀመረ፡፡ እያንዳንዱን ልብስ ለብሼ፣ ምን እንዳደረኩ አውቃለሁ፡፡ እያንዳንዷን ቀሚስ እንዴት እንደገለብኩ፣ ሱሪዎቼን በእብደት ቁልቁል እንዳንሸራተትኳቼው አውቃለሁ፡፡ ከምንወዳቼው ጋር ስንት ጊዜ ልብሳችንን አውልቀን ስንት ጊዜ ለብሰናል?...ማነው የቆጠረው? በደመነፍስ ስንት ዓይነት ፈጣን አወላለቅ ተምረናል፡፡ ገና ቀጠሮ ስንይዝ፣ ውዶቻችን ልብሳችንን ለማውለቅ እንዳይቼገሩ ቀለል ያለውን አልመረጥንም? ልብስ ብዙ ብዙ ነገር ነው፡፡ ቢታጠብም የማይለቅ አሻራ፣ ከመተቃቀፎቻችን የቀረ ጠረን ሁሉ ዘላለማዊ ነው፤ ልብሶቼን እወዳቸዋለሁ፡፡ ውድ

ቅርስ እንደሚሰበስቡ ሰዎች፣ የእኔ ሰብስቦች ልብሶቼ ነበሩ። ውድ ሆነው አይደለም የተለዬ “ብራንድ” ያላቼው ወይም በአድናቆት የት አገኘሻቼውን የሚባልላቸው አልነበሩም። ለፋሽን ግድ የለኝም፣ለውበትም ያን ያኽል አልጨነቅም፡፡ምቾታቸው ድሎቴ ነው: ውስጣቼው ኑሪያለሁ ከቤቴ፣ ከሕይወቴ፣ ከአገሬም በላይ ልብሶቼ ውስጥ ኖሪያለሁ፣ መደበቂያዎቹ ነበሩ። የእኔ የራሴ ባንዲራዎች ነበሩ፡፡ ልብሶች ተራ ነገር አይደሉም፣ የግል ባንዲራዎቻችን ናቸው፡፡ አገር ባንዲራውን፣ ሰው ልብሱን ከጣለ ምን ቀረው? ሁለቱም እብደት ነው፡፡አረጄ ብለን የምንወረውረው ልብስ፣ ልብስ ብቻ አይደለም፤ የዕድሜ አሻራችን ጭምር እንጂ፡፡ ካለነገሩ አይደለም የለበስነውን ልብስ ተመሳሳይ ሌሎች ለብሰውት ስናይ ውስጣችን በቅሬታ የሚሞላው? ሌሎች ባንዲራችንን የነጠቁን ስለሚመስለን ነው፡፡ ግድግዳው፣ ጣሪያው፣ መኝታ ቤቱ፣ ሳሎኑ፣ መታጠቢያ ቤትና ማብሰያ ቤቱ ሁሉ ቁጥር ስፍር በሌለው ትዝታዬ ተሞልቶ፣ ገና ሳምንት ሳይሞላኝ አዲሱ ቤት ዕድሜ ልኬን የኖርኩበት አሮጌ ዋሻ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከምንም በላይ ያመመኝ እና ያደከመኝ፣ ደስተኛ መስዬ ለመታዬት አደርገው የነበረው ጥረት ነበር። እንዴት ሰው ዕድሜውን በሙሉ ሌሎችን ለማስደሰት እና ተቀባይነት ለማግኘት ሲባዝን ይኖራል? ...እኩል ምድር፣ እኩል ሰብአዊ ክብር፣ ተሰጥቶን እንዴት ነው አንዱ ለማኝ አንዱ ተለማኝ የሚሆነው!? ባለቤቴ በአዲስ ትዳር ናውዞ ሲሟዘዝ፣ አብሬው መሟዘዝ፣ ሲስቅ- መሳቅ፣ በስሜት ሲግል፣ እሳት ላይ ቢጥዱት የማይሞቅ ቀዝቃዛ ሥጋዬን የሞቀ ለማስመሰል መጣር፣ ባል~ ባል ለመሆን ሲደክም፣ ሚስት - ሚስት ለመምሰል መፍገምገም- ብዙ ማስመሰል፤ግን ብዙ መቀጠል አልቻልኩም።

እስከ መቼ ነው እንዲህ የምኖረው!? ያልኩት ገና በሳምንቱ ነበር፤ በተጋባን በሳምንቱ። የቤተዘመዱ ዕልልታ እንኳን፣ ካንዱ ቤት ሌላው ቤት ግድግዳ የሚነጥር የገደል ማሚቱው አልጠፋም ነበር። እልልልል ሲባል አእምሮዬ ይኼ እልልታ ለማነው? ይላል። ባለቤቴ ጋር የተዋወቅነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የመጀመሪያ ድግሪዬን ሥሠራ ነበር። የዛሬን አያድርገውና ጥርስ የማያስከድን ተጫዋች ልጅ ነበር። በግሩፕ ከነበረ ጓደኝነት እንደ አንዳቼው ከማዬት ባለፈ በግል እንኳን ያን ያኽል ቅርበት አልነበረንም፡፡ እንዲያውም ጓደኛዬ ሃይሚ “ይኼ ወሬኛ መጣ''እያለች እንድንርቀው ስለምትገፋፋኝ ብዙም አልቀርበውም ነበር። ልንመረቅ እንድ ዓመት ሲቀረን፣ ምን ሰይጣን ሹክ እንዳለው እንጃ፣ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ሱዳን ተሰደደ ተባለ፡፡ ወሬው ከዬት እንደመጣ አላስታውስም። ሁልጊዜ ከክላስ በኋላ የማይጠፋባት ፎቶ ኮፒ ቤት የሆነ ነገር ኮፒ ላደርግ ስሄድ እግረ መንገዴን እዚያ ያገኜሁትን ጓደኛውን “ዮኒ የት ሄዶ ነው?'' ብዬ ጠየቅሁት፤ እሱም እንዳላወቀ ነገረኝ፤ ያኔ ከአንድ ሰሞን ያለፈ ወሬ አልነበረም፤ በቃ ተረሳ። እሱ እንደገና ከተገናኜን በኋላ፣ እንደነገረኝ ከሆነ ለዓመታት ብዙ ብዙ ችግር እሳልፎ አሜሪካ ገባ፡፡ አሁን ኑሮው እዚያዉ አሜሪካ ነው፡፡ ገና ሳንጋባ በግልጽ እንደነገረኝ፣ ታክሲ ይነዳል፣ የጽዳት ሥራ ይሠራል። በዚሁ ታታሪነቱ ለቤተሰቦቹም ለራሱም ተርፏል፡፡ ዮናስ ከሰርጋችን አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነበር ስድስት ኪሎ ውልና ማስረጃ ድንገት የተገናኜነው፡፡ የዚያን ቀን ግጥጥሞሸ ይገርመኛል፣ አለቃዬ የሆነ ፋይል እንድታመጣለት ሰናይት የምትባል ቢሮ የምትጋራኝ ሠራተኛ ሊልክ ወደ ቢሯችን ይመጣል። በአጋጣሚ ወጥታ ስለነበር ሲጨናነቅ ሳዬው “በዚያው የምሄድበት ጉዳይ ስላለኝ እኔ አመጣልሀለሁ" ብዬው ፋይሉን ላመጣ ሄድኩ፡፡

ታዲያ ፋይሉን ተቀብዬ ስወጣ ከእንግዳ ማስተናገጃው አካባቢ ስሜ ከኋላ ሲጠራ ሰምቼ ዞር ብል፣ የጠራኝ ሰው ከስንትና ስንት ዓመት በፊት የማውቀው ዮናስ ሆኖ አገኜሁት። እውነቱን ለመናገር መጀመሪያ አላስታወስኩትም _ ነበር፣ ከዕድሜው በላይ ትልቅ ሰው መስሏል፤ ሲናገር ነው ያስታወስኩት፡፡ ከኮሌጅ ጀምሮ ሲናገር ዓይኑን በከፊል ከደን የሚያደርገው ነገር ነበር፡፡ ባልሳሳት ወደ ዐሥራ አምስት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ሳንተያይ ቆይተን ነበር፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ነገራችን ሁሉ ፍጥንጥን
👍466😢2
ያለ ነበር፡፡ ያ ጊዜ የአብርሐም ነገር ያንገሸገሸብኝ፣ ሕይወትም ስልችት ብሎኝ ሥጋዬ በደመነፍስ የሚንገላወድበት ጊዜ ነበር፡፡ የሆነውን ሁሉ ከእኔ እኩል ትሰማ የነበረችው ጓደኛዬ ሃይሚ እንኳን ልንጋባ መሆኑን ያወቀችው ነገሩ ሁሉ አልቆ ለሚዜነት ስጠይቃት ነበር፡፡ አደነጋገጧ ሁሉ ትዝ ይለኛል፤ ረዘም ላለ ጊዜ ሳንገናኝ ቆይተን ምሳ ልጋብዝሸ ብዬ ቀጠርኳትና "አንድ ጥሩ አንድ መጥፎ ዜና አለኝ" አልኳት

“በናትሽ ዛሬ ጥሩ ሙድ ውስጥ አይደለሁም፣ ስለዚያ አብርሃም ስለሚባል ሰውዬሽ ምንም እንዳታወሪኝ አለችኝ'' በምሬት እየተንገሸገሸች፤

“አንዱ ስለ እሱ ነው"

“መጥፎው ዜና ስለ'ሱ ከሆነ ንገሪኝ!” ተሳሳቅንና

“ተለያዬን” አልኳት።

“ማለት?”

“በቃ ከዚህ በኋላ የእኔና የሱ ነገር አበቃ”

“ለስንተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?" አለች፣ እያሾፈች፡፡

“ይኼ ከምር ነው!”

“እሱ ነው ያለሽ?''

“አይ! እኔ ነኝ!" “ያንችን እንኳን ተይው፤ እስከሚደውልልሸ ነው!!" “እሺ! ሁለተኛው ዜና.. ላገባ ነው ! " አልኳት። ቀና ብላ አይታኝ በሳቅ ፈረሰችና... “ማሂ! አሁን ፈቃድ ጠይቂ እና ሁለት ሰባት በራሴ ወጭ ጸበል እንሄዳለን!” “እውነቴን ነው አባባ ይሙት!" በአባባ ከማልኩ እንደማልቀልድ ታውቃለች፡፡ የያዘችውን ሹካ ከእጇ ላይ ጥላ... “ቆይ! ቆይ! አባባ ይሙት ነው ያልሽው?. የምታገቢው? ባል ከሰማይ ዘነበ በዚህ ፍጥነት?” ሌላው ሁሉ ይቆዬንና ማንን ነው "ያው በይው! ታውቂዋለሽ ፤ ከአሜሪካ የመጣ ልጅ ነው!" "እኮ! ማነው ደግሞ እሱ?" “ዮናስ! ኮሌጅ እያለን ትምህርቱን አቋርጦ ሱዳን የሄደ ልጅ... የሆነ ተጨዋች ልጅ፣ ረሳሽው?'' አፍጥጣ ስታዬኝ ቆይታ በረዥሙ ተነፈሰች። “ሱዳን የሄደው ልጅ ከአሜሪካ መጣ? እና ሊያገባሽ ነው? አንችም እሺ አልሽው እ!?'' አለችና በሽሙጥ ከንፈሯን ጠመም አድርጋ መለሰችው፡፡ ፊቷ ግን በብስጭት ተቀያይሮ ነበር። በረዥሙ ተንፍሳ የነበርንበትን ሬስቶራንት ዙሪያ በዓይኗ ቃኜችና የሆነ ነገር ልትናገር ገና ከንፈሯን ስታላቅቅ … … “ምንም አስተያዬት ምክር አልፈልግም፤ በቃ ሚዜዬ ነሸ፣ ካልፈለግሸ ደግሞ የራስሸ ጉዳይ!''አልኳት፡፡ ዝም አለች፤ዝምታዋ ግን መልሶ እኔን አስደነገጠኝ። ይኼን የተናገርሽው አንች ነሸ? በሚመስል ግርምት ትክ ብላ አዬችኝ፤ ወዲያው ዓይኖቿ ድንገት በዕንባ ተሞሉ። ተነስቼ ጠረጴዛውን ዞርኩና ከኋላዋ አቅፊያት ማለማመጥ ጀመርኩ። ገፋ አድርጋኝ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደች። ግራ ገብቶኝ

ወገቤን ይዠ ቆምኩ። እንደተመለሰች ኮስተር ብላ አስተናጋጁን ጠራቸዉና ሒሳባችንን ከፍላ “እንሂድ!” ብላ ቦርሳዋን አነሳች። በብልግናዬ ራሴን እየረገምኩ ተከተልኳት።በጭራሽ እንደገና አገኛታለሁ አላልኩም ነበር፤ ግን ማታ ደወለች። 15 ስልኩን ከማንሳቱ የይቅርታ መዓት አዥጎደጎድኩበት “እስቲ ዝም በይ! የደወልኩት የሚያስፈልግሽ ነገር ካለ እንድትነግሪኝ ነው፤ ሌላውን ከሰርግሽ በኋላ እናወራለን አለችኝ፤ ስልኩን እንደዘጋሁ አለቀስኩ። ሃይሚ ሚዜዬ ሆና ባገባም፤ ባልገባኝ ምክንያት እስከ ዛሬ ስለ ዮናስም ሆነ ስለ ሁኔታው አንድም ቃል ተንፍሳ አታውቅም፡ይኼ የእርሷ ባሀሪ አልነበረም። በጣም ወሬ ከመውደዷ የተነሳ አብርሃም ጋር እንደነበርኩ የማይጠየቅ ነገር ሁሉ ነበር የምትጠይቀኝ። “ሃይሚ አትባልጊ" ብዬ ካልተኮሳተርኩ በስተቀር በጭራሽ ጥያቄዋን አታቆምም። አሁን ግን “ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም” ሆነ። እንዲያውም ከዚያ በኋላ የሌላትን ባሕሪ ቁጥብ ሆና ቀረች፡፡ በቀን ዐሥር ጊዜ የምትደውለው ልጅ ካገባሁ በኋላ ጠፋች፡፡ አልፎ አልፎ ለዚያውም ጉዳይ ሲኖራት ነበር የምንደዋወለው። እቤት የምትመጣውም የሆነ ዝግጅት ኖሮ ስጠራት ብቻ ነበር፤ ለዚያውም አትቆይም። ዮናስ ለሰርጋችን፣ የሦስት ወር ፈቃድ ወስዶ ነበር ከአሜሪካ የመጣው። እያንዳንዷን ቀንና ሰዓት በስስት ሲቆጥርና ከዚህ ጊዜው ላይ እያንዳንዷን ሰከንድ እኔን ለማስደሰት ባለ በሌለ አቅሙ ሲጥር፣ ለእኔ ግን ሦስት ወር እንደዘላለም ነበር የራቀብኝ፡፡ ቶሎ አልቆ ወደመጣበት እስኪመለስ ጓጉቼ ነበር፤ ለሌላ ነገር አይደለም ወደዚያ ጠቅልሎ እስኪወስደኝ ድረስ ብቻዬን መሆን ነበር ፍላጎቴ፡፡ አሜሪካ ሄጃ ኑሮዬን ለመቀዬር አይደለም!... እዚሀስ ኑሮ ምናለኝ? እንዲያውም እዚያ በበርሚል ይታለባል ከሚሉት የሰማይ ላም፣በስኒም ቢሆን እዚህ እጄ ላይ ያለው ወተት ሳይሻል ይቀራል!? መሄድ ነው የምፈልገው...መሄድ። ከዚህች አገር መራቅ። ከትዝታዬ መሸሽ።

ተወልደን ካደግንበት ምድር የሚያፈናቅሉን ጠላት ብለው የፈረጁን ብቻ አይደሉም፤ አፈቀርናቼው ብለን አፈር እንዳይነካቼው ራሳችንን ከጫማቼው ሥር ያነጠፍንላቼው ጭምር እንጂ፡፡ እንዲያውም ይኼኛው ስደት ያማል፤ እየገፉን በልባችን ይዘናቼው እንሰደዳለን፡፡ ፈጣሪ በቸርነቱ ካልገላገለን ዕድሜ ልካችንን ነፍሳችንን የሚያነቅዙ ነቀዝ ተፈቃሪዎች፡፡ ተምሪያለሁ፡፡ በአካውንቲንግ ሁለተኛ ድግሪዬን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይዤ፣ በአዲተርነት እየሠራሁ ነበር፡፡ የገንዘብ ችግር አልነበረብኝም። የረባ ነገር ባላደርግ እንኳን ለራሴ በምፈልገው ልክ እኖራለሁ፡፡ የደረሰብኝ ነገር _ ስም የሌለው መዘበራረቅ ነው፡፡ ይኼ ነገር ወደ አእምሮ ሕመም ከፍ እንዳይል ስፈራ ነው የቆዬሁት፡፡ ብዙ ሴቶች በቀላሉ እንደ ቀልድ የሚያልፉት ነገር እንደሆነ አውቃለሁ፤ እኔ ግን አልቻልኩም፡፡ ከፍጥረቴ ልፍስፍስ ሆኜ ይሆናል፡፡ ወይም እኔ የተጋጨሁት ድንጋይና እነሱ የተጋጩት ድንጋይ ጥንካሬው ተለያይቶ አላውቅም...ብቻ ተጎድቻለሁ። ማልቀስ አልፈልግም፤ግን ሙሉ ቀን፣ ሙሉ ሌሊት ዕንባዬን አፍኜ መኖር ስቃይ ነው የሆነብኝ፡፡ ብቻዬን የምሆንበት አጋጣሚ ባገኝ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት አልቅሼ እንዲወጣልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ አንዲት ጠብታ ዕንባ ውስጤ እንዳትቀር አድርጌ ማልቀስ፡፡ አንዳንዴ እመኛለሁ፣ ፋርማሲ ውስጥ የሚያስለቅስ መድኃኒት ይኖራቼው ይሆን? ልክ የእንቅልፍ ክኒን እንደሚባለው በቃ የሚያስለቅስ፡፡ ዕንባ የሚያፈስ አይደለም፣ ከልብ ስቅስቅ አድርጎ የሚያስለቅስ፣ ውስጤ ያለውን እልኽ፣ የበታችነት፣ መገፋት፣ መጠላት፣ እንደ ጨው አሟሙቶ የሚያወጣ ዕንባ የሚያጎርፍ መድኃኒት፡፡ ሴት ደግሞ ዕንባ ቸገራት? የሚል አይጠፋም፡፡ እዚህ አገር ሴት ልጅ ከመበደሏ በላይ የሚያመመው ማልቀሻ አገር ማጣቷ ነው። ድፍረቱ የለኝም እንጂ የሆነ ሆቴል ክፍል ይዠ እስኪበቃኝ ባለቅስ ደስታዬ ነበር፡፡ ሰው ክፍል ይዞ መፋቀር ብቻ ነው እንዴ!? ክፍል ይዞ ቢያለቅስ፣ ኡኡ... ቢልስ!? ...ያም ስሜት ይኼም ስሜት፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍464👎2🔥2😢1
#አድዋ

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።

#እጅጋየሁ_ሽባባው

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍24🥰7🤩1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ታዲዬስ ባለፈ ህይወቱ አንዴ አግብቶ ነበር፤ካገባት ሴት ውጭም ፍቅረኛ አለችው፤እስኪ በህይወቱ ውስጥ ስለነበሩና አሁንም በልብ ስፍራ ይዘው ስለሚገኙ ሁለት ሴቶች ታሪክ እንመልከት፡፡

ከሰባት አመት በፊት ታዲዬስ በምህንድስና ሞያ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ በኤም.ኤች አማካሪ ድርጅት በሪዘዳንት ኢንጂነርነት ተቀጥሮ እየሰራ የነበረ ወጣት መሀንዲስ ነበር፡፡ በወቅቱ በማታው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሳይኮሎጂ መማር ከጀመረ ሁለት አመት አልፎት ነበር፡፡ ተከራይቶ ሚኖረው ከደራራ ሆቴል በጀርባ በኩል ያለውን መንገድ ተሸግሮ ከሚገኙ ቤቶች መካከል በአንድ ነው፡፡የተከራያት ቤት ባለሁለት ክፍል ስትሆን የቤቱ ባለቤት አቶ ቂጤሳ የተባሉ አዛውንት ናቸው፡፡አዛውነቱ የሚኖሩት ከብቸኛ
ሴት ልጃቸው ጋር ነው፡፡በጊቢው የሚኖር ሌላ ሰው አልነበረም፡፡

ታዲዬስ ከስራ ሲመጣ በስራ ጉዳይ ከሰዎች ጋር ሲጨቃጨቅ ስለዋለ ዝልፍልፍ ብሎ ነበር፡፡ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ እስኪዘረር ነው የቸኮለው፡፡የውጭውን የቆርቆሮ በር ከፍቶ ገባ ፡፡ የአቶ ቂጤሳ ብቸኛ ልጅ መርጊቱ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ስትክዝ አጋጠመው፡፡

‹‹..ሰላም ዋልሽ?››አላት፡፡

‹‹አልመለሰችለትም፡፡›› ብዙም አልደነቀውም፡፡ እንኳንም እንዲህ በደበታት ቀን ይቅርና በሰላሙም ቀን ያን ያህል ሚነገርለት ቅርርብ አልነበራቸውም፡፡ እንደውም ከእሷዋ ይልቅ በተሻለ ሁኔታ ከአባቷ ከአቶ ቂጤሳ ጋር ይግባባል፡፡አልፏት ትልቁን ቤት ዞረና ወደ ተከራየው ሰርቢስ ቤት አመራ፡፡ገብቶ አልጋው ላይ አሪፍ ከማለቱ በራፉ በቀሰስተኛ ሁኔታ ተንኳኳ፡፡መርጊቱ ነበረች፡፡

‹‹ሰላም ነሽ.. ፌናን፡፡››

‹‹ሰላም ነኝ...መፅሀፎችህን ልመልስልህ ነበር፡፡››ተመለከታት፡፡ በእጆቿ ሶስት መፅሀፎች ይዛለች፤ከእሱ የተዋሰችው ሁለት መፅሀፍ ብቻ ነው ‹‹ሶስት አድርጋ ለምን ትመልስልኛለች?››ግራ ገባው ፡፡በዛ ላይ ሁኔታዋ ጉስቅል ብላለች፤ ስታለቅስ እንደቆየች በአይኖቿ መቅላትና በጉንጮቿ ቲማቲም መምሰል ተረዳ፡፡

‹‹ምነው ..ሰላም አይደለም እንዴ?››

‹‹አይ ሰላም ነው..መጽሀፍህን ልመልስልህ ነው፡፡እነዚህ ካንተ የተዋስኳቸው ናቸው..ይሄ ደግሞ ራሴ የምወደው መፅሀፍ ነው እንደማስታወሻ ይሁንልኝ፡፡››

ተቀበላት..ፊቷን አዙራ ለመሄድ ከተንቀሳቀሰች በኃላ መልሳ ቆመች <<ታዲ..>>ብላ ጠራችው..ደነገጠ ፡፡እንደዚህ በቁልምጫ ጠርታው አታውቅም፡፡

‹‹እዚህ ሀገር እስካለህ አባዬን አደራ፡፡..››

‹‹እንዴ!! ምን ማለትሽ ነው?››

<< አንተ በጣም ጥሩ ሰው ነህ...ይሄንን ውለታ ዋልልኝ››እንባዋ ዝርግፍ ብሎ ፊቷን አጠበው፡፡ ታዲዬስ ከተቀመጠበት ተነሳና ክንዷን ይዞ ወደ ቤት በማስገባት ከአልጋው ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጣትና እሱ ከአልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ‹‹ምን ሆነሻል..እስኪ ንገሪኝ?››አላት፡፡

‹‹አይ የሚነገር አይደለም፤ብቻ ሀገር ለቅቄ ልሄድ ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ወዴት..?አባትሽ ያውቃሉ?››

‹‹ኧረ በፍጽም..አንተ ብቻ ነህ የምታውቀው፡፡››

‹‹እሺ የት ነው የምትሄጂው?››

‹‹የእውነቱን ንገሪኝ ካልክ ወዴት እንደምሄድ እኔም አላውቀውም፤ግን መሄዴ ግድ ነው፡፡››

‹‹መርጊቱ....እባክሽ እስኪ እንደወንድምሽ ወይም እንደ ሚስጥረኛ የሴት ጓደኛሽ አይተሸኝ ንገሪኝ?››

‹‹አይ ታዲ.. ያለሁበትን ሁኔታ እንኳንስ በአንደበቴ ለሌላ ሰው ላወራ፤ ለእራሴም መልሼ መናገር ይዘገንነኛል፡፡››

‹‹ለሆነ ሰው ካልተናገርሽማ ለችግርሽ መፍትሄ አታገኚም፡፡ይሄውልሽ እኔ የምትነግሪኝን ታሪክ ሰምቼ ልፍርድብሽ፣ልታዘብሽ ወይንም ላፌዝብሽ ፈልጌ አይደለም…ግን አንቺ መፍትሄ አልባ መስሎሽ ድፍን ያለብሽን ነገር ምን አልባት መውጫ መንገዱ ለእኔ ይገለፅልኝ ይሆናል፡፡››

‹‹አርግዤ ነው፡፡››

<<አርግዤ?>>


«አዎ!>>

‹‹በቃ ስላረገዝሽ ብቻ ነው አቅመ ደካማ አባትሽን ጥለሽ ለመኮብለል የወሰንሽው?››

«አልገባክም እኮ...::>>

‹‹ኧረ በደንብ ገብቶኛል..ካልሆነ እኮ ማስወረድ ትቺያለሽ፡፡››

‹‹ሞክሬያለሁ...ውርጃውን ከሞከርኩት እንደምሞት ተነገረኝ፡፡›› እየነፈረቀች ብሶቷን ተነፈሰች ፡፡

ተረጋግታ ዝም እስከምትል በትዕግስት ጠበቃት፡፡እሷም ትንፋሽ ወስዳ ንግሯን ቀጠለች‹‹.... እና ታዲዬስ ነገ በለሊት አባዬ በተኛበት ሹልክ ብዬ እሄዳለሁ...አደራ አጽናናው፤ደግሞ አሁን የነገርኩህን እንዳትነግረው..፡፡‹ትምህርት ጨርሳ ስራ መያዝ ባለመቻሏ ሰሞኑን ስትበሳጭ ነበር፤ስራ ፍለጋ ይሆናል ወደ ሌላ ሀገር የሄደችው በለው

‹‹ቆይ ተነጋግረን እኮ አልጨረስንም..ልጁ ቢወለድ ምን ችግር አለው?፤አባቱ እንኳን እምቢ ቢል ሰርተሸ ታሳድጊዋለሽ፡፡››

‹‹አልገባህም ያልኩህ እኮ ለዚህ ነው፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ያረገዝኩት ባለፈው ከአሜሪካ መቶ ከነበረው ከአባዬ ታናሽ ወንድም ነው፡፡››በዚህ ጊዜ ነበር መርጊቱ ምን አይነት አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች ታዲዬስ የተረዳው::

<< የዛን ጊዜ አዲስ አበባ ይዞኝ ሄዶ እንደነበር ታስታውሳለህ አይደል..?ታዲያ አንድ ቀን በየጭፈራ ቤት እያዞረ ማላውቀውን መጠጥ ሲያጠጣኝ ካመሸ በኃላ ሁለታችንም ስክር ብለን ወደ ቤርጎ መግባታችንን አስታውሳለሁ..ከዛ ጥዋት ስነቃ እኔም ሆንኩ አጎቴ ዕርቃናችንን ተቆላልፈን ተኝተን ነበር፡፡ በርግጌ ተነስቼ የሆነውን ስመለከት ጭኔም አንሶላውም በደም ነጠብጣብ እርሷል፡፡አጎቴ
ሳየው በእርካታና በደስታ ይፍነከነካል፡፡ በጊዜው ባብድ ምንም መለወጥ ምችለው ነገር አልበነበረም፡፡አየህ እሱ ሆነ ብሎ አስቦ አቅዶ ያደረገው ነገር ነበር፡፡

በጣም የሚገርመው ግን በማግስቱም፣በሚቀጥለዉ ቀንም እሰከሚሄድ ድረስ በተመሳሳይ ደጋግመን በሀጥያቱ እራሳችንን አጨቀየን፡፡ ይሄው ውሎ አድሮ መዘዙ ተመዞ ለእኔ ለብቻ ተረፈ፡፡››

‹‹ለእሱ ማርገዝሽን ለምን አትነግሪውም..ምን. አልባት እኮ?››

አላስጨረሰችውም‹‹…እርሳው ፡፡ ላንተም እንዴት እንደነገርኩህ ግራ ገብቶኛል፡፡በፍፁም አላረገውም ፤ አጎቴን ልጅ ፀንሼልሀለው ብዬ ልነግረው አልችልም፡፡ደግሞ በህይወት ዘመኔ ከእሱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዲኖረኝ  አልፈልግም፤በል ለማንኛውም ቻው››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ጎንበስ ብላ ግንባሩን ስማ ወደ መውጫዋ አመራች፡፡

ታዲዬስ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ደመ ነፍሱ ሹክ አለው፡፡ የቤቱን ደጃፍ ተሻግራ ከመውጣቷ በፊት እጇን ይዞ አስቆማትና ‹‹መርጊቱ አንቺም አንድ ውለታ ዋይልኝ?››ሲል ጠየቃት፡፡

ገርሟት አፍጥጣ አየችውና <<እኔ በዚህ ጊዜ ላንተ ውለታ?››

‹‹አዎ ለእኔ፡፡››

‹‹እሺ ምን ላድርግልህ?››

‹‹ነገ እሁድ አይደል?››

«አዎ۰::>>

‹‹በቃ ነገ ዋይና ሰኞ ትሄጂያለሽ፤በሰንበቱ አባትሽንም ማሳቀቅ ጥሩ አይደለም፡፡››

‹‹ምንም ለውጥ እኮ የለውም፡፡››

‹‹አውቃለሁ፤ለእኔ ስትይ አንድ ቀን ...>>

ለደቂቃ በቆመችበት ካሰላሰለች በኃላ ‹‹እሺ እንዳልክ›› አለችው፡፡

‹‹አመሰግናለሁ...የሰጠሸኝን አደራ እንድወጣ ከፈለግሽ የሰጠሁሽን አደራ ፈፅሚ፡፡››

‹‹እሺ አልኩህ እኮ፡፡አንድ ቀን አይደል አንተን ደስ ካሰኘህ ግድ የለም እውላለሁ፡፡››ብላው ወጥታ ሄደች፡፡
👍889
በጊዜው ታዲዬስ እሷን ከሸኘ በኃላ እረፍት አላገኘም…፡፡በምን ዓይነት መንገድ ይህቺን ልጅ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሊረዳት እንደሚችል በቀላሉ ሊገለጽለት አልቻለም፡፡ እንዲሁ በሀሳብ ሲባዝን አምሽቶ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን የቻለው፡፡ሞባይል ስልኩን አነሳና ያሰበውን ወደተግባር ለመቀየር ያግዙኛል ወዳላቸው ሶስት ሰዎች ጋር  በተከታታይ የደወለው፡፡እቅዱን ለሁሉም በዝርዝር አስረዳና በእፎይታ እራሱን ለእንቅልፍ አሳልፎ ሰጠ፡፡

በማግስቱ ማለዳ 12 ሰዓት ነበር የአቶ ቂጤሳ ቤት በሶስት ሰዎች የተንኳኳው፡፡ድምፁን ሰምታ በድንጋጤ በመበርገግ በሩን ለመክፈት መኝታዋን ለቃ በራፍ ላይ ቀድማ የተገኘችው መርጊቱ ነች፡፡ ይሄ ያልተለመደ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው?ማን ሞተ..…?‹‹ተልባ ቆይዋ እያለች..ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት››የሚለው ሀገራዊ ብሄል በአዕምሮዋ ተሰነቀረ፡፡እሷን ማን ቀደማት?የትኛው ዘመድ ነው ከእሷ ጋር ፉክክር የገጠመው…?ማነው ቀድሟት የሞተው?ምን አለ አንድ ቀን ዘግየት ብሎ ቢጠብቋት ወይም ምን አለ አንድ ቀን ፈጠን ብትል? በሰከንዶች ሽርፍራፊ ይሄን ሁሉ እያሰላሰለች በራፉን ስትከፍት ሶስት ጎልማሳ ወንዶች በራፉን ሞልተው ቆመዋል፡፡

‹‹ምንድ ነው? ምን ተፈጠረ?››

‹‹ተረጋጊ ሰላም ነው፡፡››

‹‹በዚህን ሰዓት የምን ሰላም?››

‹‹ኧረ ሰላም ነው ፤ አባትሽን ማናገር ፈልገን ነው፤ቤተክርስቲያን ሳይሄዱ ልንደርስባቸው ስለፈለግን ነው በማለዳ የመጣነው፡፡

በድንጋጤ የሚንቀጠቀጠው ሰውነቷ ሳይረጋጋ ከበራፉ ገለል አለችና እንዲገቡ ፈቀደችላቸው፡፡

‹‹ግቡ ..ይቅርታ ቤቱ ግን እንደተዝረከረከ ነው፡፡››

‹‹አረ ግድ የለም፤ይልቅ አባትሽን ቀስቅሺልን፡፡››

‹‹እሺ ››ብላ ዞር ስትል አቶ ቂጤሳ ተነስተው ከመኝታ ቤታቸው በመውጣት ሳሎን ደርሰው ነበር::

መርጊቱ ትታቸው ወደ መኝታ ቤት ገባችና ጆሮዋን ግድግዳ ላይ ለጥፋ ማዳመጡን ቀጠለች፡፡

‹‹ሰዎች ምነው በሰላም ነው? አረ ቁጭ በሉ፡፡››

በተርታ ተገትራው የነበሩት ሶስት ሰዎች በአክብሮት እጅ እንደመንሳት አሉና ‹‹የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር መቀመጥ አንችልም፡፡››

‹‹እኮ ቁጭ በሉና ትናገራላችሁ፡፡››

‹‹ኧረ ግድ የለም ቆመን ይሻላል፡፡››

‹‹እሺ ምን እግር ጣላችሁ?››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን እንድትሰጡን ልንጠይቅ ነው፡፡››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን?››አቶ ቂጤሳ ቃሉን መልሰው ደገሙት፡፡መኝታ ክፍል ሆና ስታዳምጥ የነበረችው መርጊቱ የምትሰማው ነገር የተዓምር ያህል አስደነገጣት፡፡ማን ነው
ላኪው? መቼስ እዚህ ቤት ከእኔ ሌላ ሌላ ሴት የለም፡፡የትኛው አፍቃሪዬ ነው እኔን ሳያማክር ለጋብቻ ሚስኪኑ አባቴ ጋር የላከው? በፍቅር የሚጎመዣትና ስትወጣ ስትገባ የሚለክፏትን አንድ ሶስት ወንዶች በምናቧ መጡላት፡፡ከእነሱ መካከል አንድ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች፡፡ አሳቃትም፣ አሳዘናትም፡፡ሁለቱም ስሜት እኩል ነው የተሰማት፤አንድ ላይ ተዋህዶ አንድ ላይ ተጨፍልቆ፡፡መቼስ እርጉዝ መሆኗን እያወቀች ብትፈልግ እንኳን ይሄንን የጋብቻ ጥያቄ መቀበል አትችልም፤በሀጥያት ላይ ሌላ ሀጥያት አትጭምርም፡፡ጆሮዋን የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ እንደለጠፈች ሳሎን የሚካሄደውን ትዕይንት መከታተል ቀጠለች፡፡

‹‹ለመሆኑ ልጁ ማን ነው?››አባቷ ጠየቁ፡፡

‹‹እኮ ማ ነው? የእሱንና የቤተሰቦቹንም ማንነት ንገሩኝ?››

ያው እርሷ ባያውቁም ልጃችንና ልጆት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ፤ያው አሁን መምጣታችን ነገሩን ሁሉ በእርሷ ፍቃድ እንዲሆን ስለፈለግን ነው፡፡››

‹‹ሰዎች ለምን የጠየቅኳችሁን አትመልሱም..? ልጁ ማን ነው?››ጋሽ ቂጤሳ ትግስት አጠራቸው፡፡

መርጊቱ ደግሞ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የምትሰማው ነገር ግራ አጋባት‹…እንዴ እንዲህ አይነት ውሸት አለ እንዴ?ማነው እንዴህ በድፍረት አይን ያወጣ ውሸት አሲዞ ሽማግሌዎችን የሚልክ?እሱ ተዋርዶ እነሱንም የሚያዋርድ?›› ተንደርድራ ወጥታ ለሽማግሌዎቹም ለአባቷም ምንም አይነት ፍቅረኛ እንደሌላትና ማንንም ማግባት እንደማትፈልግ ነግራቸው ነገሩን ለማሳጠርና ሁሉንም ከድካም ለመገላገል ወሰነችና ወደ ሳሎን ሳሎን ለመግባት መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ አንድ እግሯን ስታነሳ ‹‹ጌታዬ ልጁ ታዲዬስ  ነው፡፡››የሚል ድምጽ ከሽማግሌዎቹ ሰማች... ባለችበት ደንዝዛ ቆመች፡፡

‹‹ታዲዬስ….ታዲዬስ የቱ?››

‹‹ታዲዬስ መሀንዲሱ ..እዚሁ እርሶ ቤት የሚኖረው፡፡››

አቶ ቂጤሳ ከመደንገጣቸው የተነሳ በተቀመጡበት እጆቻቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ጫኑና አንገታቸውን ወደ መሬት ደፍተው ማሰላሰል ጀመሩ፡፡‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል?››አንድ ቀን እንኳን የረባ ጫወታ ሲጫወቱ፣ሲቀላለዱ ወይም ሲላፉ አጋጥሞቸው አያውቅም፡፡ሁለቱም እርስ በርስ ከመሳሳብ ይልቅ የመገፋፋት ባህሪ ነበር ዘወትር የሚያታይባቸው፡፡እንዴት ከእሷቸው በዚህን መጠን ግንኙነታቸውን መሰወር ቻሉ?

‹‹እሺ ያላችሁትን ሰምቼያለሁ፤ጉዳዩን ከልጅቷም ከዘመድ አዝማድም ጋር ልማከርበትና መልሱን ለሳምንት ልስጣችሁ፡፡››
በደመነፍስ እግሯን እየጎተተች በጓሮ በር ወጥታ ወደ ታዲዬስ ክፍል አመራች፤አንኳኳች፤ ከፈተላትና ወደ መኝታው ተመለሰ፡፡ ምንም ሳትናገር ወደውስጥ ገባችና በራፉን ዘጋችውና ወደ አልጋው በመውጣት ከውስጥ በመግባት ዝም ብላ ከጎኑ ተኛች፡፡ በአድናቆትና በዝምታ ተመለከታት፡፡ በጣም ደንግጣለች፤ በእንቅልፍ ልቧ እየተጓዘች የመጣች ትመስላለች፡፡ዝም ብሎ አይኖቾ እንባ ያመነጫሉ፡፡ከሃያ ደቂቃ የዝምታ ጊዜ በኃላ << ታፈቅረኝ ነበር እንዴ?››በማለት ያልጠበቀውን አደናጋሪ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ግራ ተጋባ‹‹ምን አልሺኝ?››

‹‹ታፈቅረኝ ነበር ወይ ?ሳትዋሽ ንገረኝ፡፡››

‹‹በፍቅር እኮ ውሸትም ይሉኝታም አይገባም፤ፈጽሞ አፍቅሬሽ አላውቅም፡፡››

ሰውነቷ በደቂቃዎች እንደበረዶ ቀዘቀዘባት‹‹ታዲያ ለምን?አስበኸዋል ግን? ሰው ያፈቀረውን እንኳን ለማግባት ሞራል ባጣበት ጊዜ አንተ የማታፈቅራትን ለዛውም እርጉዝ የሆነችን ሴት ለማግባት መስዋዕትነትን ለመክፈል የፈለከው ?ነው ወይስ የውሸት ድራማ እየተጫወትክ ነው፡፡?››

‹‹የውሸት አይደለም፤ የእውነት ነው የማገባሽ..ማለቴ እንጋባለን፤አብረን እንኖራለን፡፡…ያለምንም ግንኙነት፤ልጅሽን ወልደሽ ሁኔታዎች ከተስተካከሉ በኃላ አልተስማማንም ብለን እንፋታና አንቺም የፈለግሽውን ማለት የሚያፈቅርሽንና የምታፈቅሪውን ታገቢያለሽ፤ እኔም እንደዛው፡፡››

‹‹እኮ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ለምን ለመግባት ፈለክ?እኔ ምን አድርጌልህ አውቃለሁ? አንድ ቀን እንኳን ልብስህን ልጠብልህ ወይም ቤትህን ላፅዳልህ ብዬህ አላውቅ፡፡››
ስለተደረገልሽ ብቻ አይደለም የሆነ ነገር ማድረግ ያለብሽ፡፡ደግሞም ላንቺ ብዬ አይደለም፤ ለአባትሽ ስል ነው፡፡አንቺ እንዳልሽው በዚህ ዕድሜያቸው ጥለሻቸው ብትጠፊ እርግጠኛ ነኝ ለአንድ ወር በህይወት አይቆዩም፤በመጨረሻ ዕድሜያቸው ለእሳቸው ይሄ አይገባቸውም፡፡››


ይቀጥላል

ዛሬ በጠዋት ተከስተናል ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ እስከማታ የተወሰነ ሰው #Sebscribe ካደረገ በክፍል #31 እንገናኛለን #Shareም አይረሳ  አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12012😱5😢2
#ስለ_አድዋ_አጭር_ማስታወሻ

ነገ አድዋ ነው የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የልደት ቀን፡፡ አድዋን ሳስብ ብዙ ነገሮችን አስባለሁ የተራራ ጫፎች እንደ ጦር ተስለው ይታዩኛል፡፡ ድራጎንን ገድሎ ብሩታይትን ከፍርሃት ነፃ ያወጣው ሰይፍ ነጸብራቅ #ምኒልክ መዳፍ ውስጥ ይታየኛል፡፡

አድዋ የነፃነት ቀን እንደሆነ አልጠራጠርም ነጭ ቡጢ በጥቁር መዳፍ የከሸፈበት፣ ብርቱ የንቀት ቋጥኝ የተደረመሰበት፣ አንገት በሃፍረት ከመዘለስ የዳነበት ቦታ እንደሆነ አልዘነጋም፡፡ አድዋ እኮ ግዑዝ ተራራ አይደለም ገበየሁን ያህል የጦር ሳተና ውጦ ጭጭ ያለ ጨለማ፣የእምየን ትዕግስት ተፈታተነ፣ የባራቴሪን ትዕቢት ትቢያ ያደረገ የነጭን ሴራ የበታተነ ሞገድ ነው፡፡ አድዋ የተራራ ሰንሰለት ብቻ አይደለም #የጣይቱን የሴትነት ብልሃት ያንጸባረቀ መስተዋት፣ የባልቻን ያህን ድፍረት ያሰናዳ ፣ የአባ መላን ብልሃት የሸረበ፣ለወገን ሃይል ወኔን ያቀበለ፣የባሻ አውአሎም ምስጢረኛ፣ ጀግኖችን በደም አጥምቆ የሀገር ፍቅር ማተብን ያሳሰረ መንፈስ ነው አድዋ፡፡ አድዋ ለኢትዮጵያውያን በዓል ብቻ አይደለም.. .ሳንባን በኩራት ወጥሮ ደረት የሚያስነፋ አየር፣ አንገትን ከመዘለስ ታድጎ ቀና የሚያደርግ ምርኩዝም ጭምር ነው፡፡

አድዋ የሰላም ወዳድ ትውልድና ህዝብ ቋሚ ምስክር አርማ ነው ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ የጣይቱ ንግግር መጥቀስ በቂ ነው

“እኔ ሴት ነኝ፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡" ተጨማሪ ካስፈለገ አያልቅም

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፤ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ሀበሻ" የሚለው ስነ ቃላዊ ግጥም ውስጥ የምንይልክን ብሎም የኢትዮጵያውያንን ሰላም ወዳድነት ማሳያ ነው በግጥሙ ውስጥ በግልጽ እንደተመለከተው #ምኒልክ ባያነሳ ጦር አይደለም የተባለው . . .ጋሻ ነው፡፡ ጋሻ ደግሞ ራስን ለመከላከል እንጂ ጠላትን ለማጥቃት የሚውል መገልገያ አይደለም፡ እናም ሀበሻ በአዘቦት "የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል. ." እንደሚለው ምኒልክ ክተት አውጆ ጋሻውን አነሳ፣ ሀገሬው አልገዛም ባይ፣ አሻፈረኝ ባይ፤ በየጎራው ላይ" እያለ ባለትዳሩ ምሽቱንና ልጁን፣ ያላገባው ኮረዳና አጎጠጎቴውን (የከንፈር ወዳጁን) ተሰናብቶ ተከትሎት አድዋ ላይ ተገናኙ እናም አድዋ ከገፊዎች ሳይሆን ከተገፉት ጎራ ቆመ ግዑዝ መልክዓ ምድር ብቻ አይደለም፤ የሀበሻ የልብ ወዳጅም ጭምር ነው፡፡ .ስለዚህም አድዋ"
፨፨
የአድዋን በዓል ስናነሳ በቅድሚያ ከሚጠቀሱት ቋሚ ቅርሶች አንዱ የአፄ ምኒልክ ሐውልት ነው፡፡ ሐውልቱን ያሠሩት ንግሥት ዘውዲቱ ሲሆኑ የቆመው የአባታቸው የአፄ ምኒልክ ማስታወሻ እንዲሆን ታስቦ ነው፡፡

የሐውልቱን ንድፍ ያወጣው ጀርመናዊ አርክቴክት ሀርቴል ስፔንግለር ነበር፡፡ ሐውልቱም የተቀረፀው ጀርመን ሀገር ሲሆን የተሰራውም ከነሐስ ነው፡፡ ሐውልቱ ከጀርመን ሃገር ተሠርቶ ከመጣ ወዲህ የሚቆምበት ቦታ በዝግጅት ላይ እያለ ንግሥት ዘውደቱ በድንገት መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡ ነገር ግን የተጀመረውን ሥራ የንግሥቲቱን አልጋ የወረሱት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንዲጠናቀቅ በማድረግ በንግሥናቸው በዓል ዋዜማ ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም. በታላቅ ክብር በንጉሠ ነገሥቱ ተገለጠ፡፡

ከሐውልቱም ግርጌ ዘመን የማይሽረው ጥቅስ የተቀረፀ ሲሆን እንዲህም ይነበባል፡-

‹‹ከትልቅ ወይም ከትንሽ ቢሆን መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው፡፡››

ሃውልቱ በዳግም ፋሽስታዊ ወረራ ወቅት በማርሻል ግራዚያኒ ወርዶ ተቀብሮ የነበረ ቢሆንም ከነፃነት በኋላም ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ

እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ቀድሞ በነበረበት ቦታ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም. እንዲቆም ተደርጓል፡፡

እምየ ምኒልክ ከአድዋው ድል በኋላ ብዙ መሰረተ ልማት በመዘርጋትና ስልጣኔን በማስገባት የሰላም ጊዜ ጀብደኝነታቸውን አስመስክረዋል፡ከነዚህ አንዱ ለሆነው የባቡር ፕሮጀክት ህዝቡ አንድ አንድ ጠገራ ብር ለማዋጣት ማቅማማቱን ሲሰሙ ታህሣሥ 29 ቀን 1900 ለመምህር አካለ ወልድ በፃፉት ደብዳቤ ላይ ይህን ብለው ነበር "ስለምድር ባቡር ሥራ ገንዘብ አውጡ ባልነው ሰው አለቀሰ ብለው የላኩብኝ ደብዳቤ ደረሰኝ… ይህስ ከእንቅልፌ ለምን ቀሰቀሳችሁኝ እንደማለት ያለ ነው እንጂ በጭራሽ አንዳንድ ብር አውጡ ቢባል የሚጎዳ ሆኖ አይደለም።" እኔም እላለሁ ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅስ መሪ ይብዛልን . . . ለመንቃት ግን አናመንታ፡፡

የአድዋ ዝክሬን የማጠቃልለው አፄ ምኒልክ ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን በጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ ሲሆን እንዲህ ይነበባል

"የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት። በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ። አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፣ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ'' አኔም ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ፡፡

🔸ዋግሹም ካሳ🔸


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍346😁2
ዋ ! አድዋ !
(ሎሬት ፀጋዬ ገ /መድኅን

አድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥጉዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
አድዋ …
በአንቺ ብቻ ህልዉና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና …
ዋ !
አድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነቱዋ
በሞት ከባርነት ስርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ እለት
አድዋ …
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
አድዋ ..
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
አፅምሽ በትንሳዔ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ህዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘዉ መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው በለው በለው በለው
ዋ …አድዋ !…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው በለው
ዋ …አድዋ …
አድዋ የትናንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና ::
ዋ ! . . . . .ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ . . . ..

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍25🥰32
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ የድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!

ዓድዋ! የኢትዮጵያውያን ሕያው የድል አሻራ!

ዓድዋ! የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት!                                                        
                                 
💚💛❤️🙏


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍159
#ያልተኖረ_ዓድዋ

ወድቀንማ ነበር

የጋራ ሞት ሞተን

የተዋጋነውን

መኖር ነው ያቃተን።😢

🔘ኢዛና መስፍን🔘


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢22👍9🥰1
#እኔ_እና_ቤቴ

‘ቤቴ’ የኪራይ ናት፡
ከወር ደመወዜ፣ በወር ምታስከፍል፤
‘እኔ’ ስደተኛ፡
በገዛ ሀገሬ፣ ‘ለገዛ ወገኔ’፣ ለቤት የምከፍል፤
ይኸው በኑሯችን፡
‘ቤቴ’ን አላምናትም፣ እርሷም አታምነኝም፣
አብረን እንኑር እንጂ፡
‹በየኔ ነው ስሜት›፣ ከቶ አንገናኝም፡፡
በእርሷ አልፈርድባትም፡
ድሮስ ስደተኛን፣ ማን አምኖ ያኖራል?
በእኔም አትፍረዱ፡
የራስ ያልሆነን ቤት፣ ማን አምኖ ይኖራል?
ይህን እናውቃለን፡
ፈጽሞ እንደማንችል፣ መኖር ተለያይቶ፣
እንዴትስ ይኖራል?
ቤት ሰው አልባ ሆኖ፣ ሰውም መኖሪያ አጥቶ፤
ዘመናችን ይህ ነው፡
አብረው እየኖሩ፣ አለመተማመን…
ቆይ ግን ምን ነክቶናል?
መለያየት ማንችል፣ አብሮነት ያመመን?

🎴መላኩ አላምረው🎴

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍25👏1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ስምንት

ሰው ክፍል ይዞ መፋቀር ብቻ ነው እንዴ!? ክፍል ይዞ ቢያለቅስ፣ ኡኡ... ቢልስ!? ...ያም ስሜት ይኼም ስሜት፡፡

ይኼ ሁሉ የሆነው በዚያ በተረገመ ልጅ ምክንያት ነው፡፡ በዚያ በተረገመ ልጅና በተረገምኩ እኔ ምክንያት። ችግሬ ለመናገር በጣም ቀላል ነው፤ ለመኖር ነው የሚከብደው፡፡ በዓለም ላይ እንዳሉ ብዙ ሚሊዮን ሴቶች የማፈቅረውን ሰው ትቼ (ምን እተዋለሁ! በልቤ ተሸክሜ) የማላፈቅረውን ሰው አገባሁ “ወንድን በወንድ ነው መርሳት" በሚል የጓደኞቼ ምክር ጭምር፤ ይኼው ነው ታሪኬ፡፡ በደፈናው ሲታይ በቃ ይኼው ነው? ያስብላል አይደል? ....እኔም እንዲህ ዓይነት ታሪክ፣ ልብወለዶች እና ፊልሞች ላይ ስንት ጊዜ አነበብኩ፣ አዬሁ እና ለምን እንዲህ አያደርጉም? ለምን __ እንደዚያ አይሠሩም? ብዬ _ ምክርና _ ግሳጼ _ ወረወርኩ ...በመምከር ውስጥ ተመካሪውን ደካማ አድርጎ የማዬት ስስ መታበይ አለ፤ ሲኖሩት ግን ሌላ ዓለም ነው፡፡ ሰው በቁሙ ሕልምና ገሃድ የሆነ ሕይወት እንዴት በአንዴ ይኖራል? ባሌ ዮናስ፣ እጄን ሲነካኝ “ፍቅረኛ እንዳለኝ አታውቅም!?''ብዬ በጥፊ ማጮል ያምረኛል፡፡ እዚህ ሌላ ወንድ አግብቼ፣ እዚያ ትቼው መጣሁ ያልኩት ሰው ጋር ፍቅር ውስጥ ነኝ። ትንፋሽ የሚያሳጣ- ፋታ የማይሰጥ ዕልኽ፣ መገፋት፣ አለመፈለግ እና መናቅ የተቀላቀለበት ፍቅር ውስጥ ነኝ፡፡ ከፍቅሬ እኩል ደግሞ አምርሬ እጠለዋለሁ፡፡ የማፈቅረው ሰው አብርሃም ይባላል ደራሲ ነው፡፡ አራት ዓመታት አብረን በፍቅር ቆይተናል፡፡ እና ለምን ተለያያችሁ? ብባል መልስ የለኝም። ስላልፈለገኝ አልል ነገር ለእኔ ሲንሰፈሰፍ ለጉድ ነበር...ብቻ አይገባኝም፤ የሰው ልጅ ምን ዓይነት ውስብስብ ፍጥረት እንደሆነ አይገባኝም፡፡ የሚገባኝ በዚህ ውስብስብ ፍጥረት ቀጥ ያለ የዋህ ባሕሪዬ መሰባበሩ ነው፡፡ ሌላው ይቅርና ይወድሻል ወይስ አይወድሽም? ብባል መልስ የለኝም፡፡ አላውቅም፤ የእውነት አላውቅም፡፡ እዚህ ክንዱን አንተርሶ ያስተኛኝ ባሌ እቅፍ ላይ ሥጋዬን ትቼ፣ ነፍሴ ከምታፈቅረው ሰው ጋር ስትዛብር የምታድር ከንቱ አፍቃሪ ነኝ፡፡ ባሌ እላዬ ላይ በፍቅርና ወሲብ ናውዞ ሲቃትት፣ ያውልኽ ሥጋዬ ብዬ በነፍሴ ወደ ወደድኩት ሰው የምኮበልል ባተሌ ነኝ፡፡ እንዲያ ሲሆን ያላለቀስኩበት ጊዜ የለም፡፡ ባለቤቴ ጥሩ ሰው ነው፤ ይኼን

ጥሩነቱን እንደ ስኒከር ጫማ፣ ስልክና ላፕቶፕ፣ ከአሜሪካ ይዞት የመጣው ሳይሆን፤ ዩኒቨርስቲም እያለን አብሮት የነበረ፣ ከዚያም በፊት አብሮት ያደገ ገራገርነት ነው፡፡ ቤተሰቦቹ በሙሉ ጥሩዎች ናቸው፡፡ ምን ዋጋ አለው... እኔ ላይ ጣለው፡፡ እንዳንዴ የምለው ሰጣ “በጣም ጥሩ ሰው ነሀ!” እለዋለሁ በፍጹም የዋሀነት “ጥሩነቴን አይቶ አንችን ሰጠኝ" ይለኛል፡፡ ይኼ አባባል የክፉዎች መፎክር መሆኑን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው። “ፍቅረኛዬ” አብርሃም ያረገኝን ሁሉ ከደረገኝ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ ስንለያይ እንደዚያ ነው ያለኝ “በጣም ጥሩ ልጅ ነሽ" የይሁዳ አሳሳም ቃል ለብሶ ሲገለጥ እንዲህ ነው፡፡ ምን ማለት ነው ጥሩ ሰው ነሽ?... ስበድልሽ ዝም ብለሽ ተበድለሻል፣ ስሰብርሽ ያለ ድምፅ ተንኮታኩተሽ ወድቀሻል...ስለዚህ አመሰግናለሁ ነው? ...ለምን የበደሉን ያደንቁናል?...ለምንስ የሚያደንቁን ይበድሉናል!? ባሌ ዕረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሊመለስ ሲዘጋጅ፣ በመለያዬታችን እንደ ሴት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ በማልቀሱም ብቻ ሳይሆን ሰርጋችን ሁለት ቀን ሲቀረው ያደረኩትን አውቃለሁና በጸጸት አብሬው አለቀስኩ፡፡ በእርግጥ ከዚያም በፊት ከጋብቻችን በፊት፣ለጋብቻ ጠይቆኝ እሺ ካልኩበት ቀን ጀምሮ እሱ ለሰርግ ሲዘጋጅ እኔ ታማኝ አልነበርኩም፡፡ አንዳንዴ ዮናስ ጋር ተኝቼ አብርሃም ከደወለልኝ እየተጎተትኩ ሄጄ በሰዓታት ልዩነት እሱም ጋር እተኛለሁ። ባከንኩ። ተዝረከረኩ። ቆሸሽኩ። ታዲያ እገረም የነበረው፤ ለዓመታት የወደደውን ያለ እሱ ማንም ነክቶት የማያውቀውን ገላዬን ሌላ ወንድ እንደነካው እንዴት አያውቅም እያልኩ ነበር። የመጨረሻዋ አለመታመን ግን እንደ ደረቀ እንጨት ቅስሜን ቀሽ አድርጋ የሰበረች አለመታመን ነበረች፡፡ አለመታመኔ ደግሞ ሰይጣን አሳሳተኝ የሚባል ዓይነት ድንገተኛ ነገር አልነበረም፡፡ ሰይጣን ራሱ ጅራቱን ሸጉቦ እና ጉዴን ላለመስማት ጆሮውን በሁለት እጁ ደፍኖ፣ የፈረጠጠበት አለመታመን ነበር፡፡ የሚያንገበግበኝ ያ የመጨረሻው ነው፡፡ አለመታመንም ዓይነትና ደረጃ ይኖረው ይሆን?...እንጃ! በስድስት ሚዜ እና በአንድ ሾፌር መኻል እንደ ነፋስ አልፎ አመንዝሮ መመለስ።

ፈጣሪ ራሱ ከማመንዘሬ በላይ፣ ለማመንዘር የሄድኩበትን መንገድ በግርምት መዝግቦ የሚያስቀምጠው ነው የሚመስለኝ፡፡ ሰርጌ እሑድ ሆኖ አርብ ቀን ጸጉር ቤት ከሚዜዎች ጋር ሄድን፤ ጸጉሬን የሚያጥበት ልጅ የራስ ቅሌን በጣቶቹ 'ማሳጅ ሲያደርገኝ ነበር አእምሮዬ በአንዴ በናፍቆት የተሞላው። አብርሃም ከጡቶቼ ቀጥሎ ጸጉሬን የሚወደው ይመስለኛል፤ እንደዚያ ብሎኝ አያውቅም ግን - ይመስለኛል፡፡ ሁልጊዜ ጎን ለጎን ተቀምጠን ወይም ተኝተን፣ በጣቶቹ ጸጉሬን ማበጠር የሚወደው ነገር ነበር። በጸጉሬ መጫወት... ዓይኖቹን ጨፍኜ ጣቶቹ በጸጉሬ ውስጥ ሲሽሎከለኩ የሚሰማኝ ደስታ ...ስንት ቀን በዛው እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወስዶኛል...እና ጸጉሬን የሚያጥበኝ ልጅ ጣቶቹ በጸጉሬ ውስጥ ሲርመሰመሱ፣ እንደ ወተት የሚንጥ ናፍቆት ሞላኝ፡፡ ቀስ በቀስ አልነበረም. በአንዴ። ምንድን ነው እንደዚያ ያደረገኝ? አንገቴን ወደፊት ቀና አደረግሁ:: “እሳመምኩሽ?'' አለኝ ልጁ፡፡ አላሳመመኝም ቀድሜ የታመምኩ እኔ‐ በሽታዬን ነው Pyha:: ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ሚዜዎቼ እዚያና እዚህ የሚወራወሩት ቀልድ እና ሳቅ ሳይሆን፤ የትዝታ ጅረት ነበር በመላ አካሌ የሚፈሰው... የሚጮኸው። በቃ የመጨረሻሽ ነው የሚል ድምፅ ነው በጆሮዬ የሚያንሾካሹከው። ጸጉሬን ተሰርቼ እንደጨረስኩ ቀጥ ብዬ ወጣሁና ራቅ ብለው በሰልፍ ከቆሙት ላዳ ታክሲዎች ወደ አንዱ ሄጄ..ላፍቶ ኮንዶሚኒዬም አልኩት፤ መንገድ ጀምሬ ነበር ለአብርሃም የደወልኩለት...ቤት ጠብቀኝ ብዬ....ወደ ቤቱ በቀረብኩ ቁጥር ልቤ ደረቴን ሰንጥቃ የምትወጣ እስኪመስለኝ ጭንቀቴ የተለዬ ነበር። ሰውነቴ በሙቀት ይቃጠላል፣ለራሴ እያበድኩ እስኪመስለኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፍቶኝ ነበር። ባለታክሲውን አዙረU መልሰኝ ለማለት ሁለት ሦስት ጊዜ እየቃጣሁ ከአፌ ቃል ማውጣት አልቻልኩም። የኮንዶሚኒዬሙን ደረጃ ስወጣ፣ እግሬ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ በሩን ሲከፍትልኝ ተዝለፍልፌ መውደቅ ነበር የቀረኝ፣ በውስጤ እባክህ አይሆንም በለኝ እላለሁ ... እባክህ ....እንደዚያ እያልኩ ግን እቅፉ ላይ ወደቅሁ፡፡ እኔስ እሺ በቃ የመጨረሻው

የሴትነት ክብሬን አለቅልቄ የደፋሁ ከንቱ ሆኜ ነው፤ አራት ዓመት አብሮ የቆዬ ፍቅረኛ የፈለገ ወንድ ቢሆን የቱንም ያኽል ስሜታዊ፣ ሰርጓ ሁለት ቀን የቀረው ሙሽራ መጥታ እግሯን ስለከፈተችለት እንዴት ዘው ይላል!? ያውም የማያፈቅራት ሴት። ማንንም ለመውቀስ አይደለም፤ በልቤ “አይ! አይሆንም” እንዲለኝ ግን ምኞቴ ነበር፡፡ አልዋሽም እንደዚያ ቢለኝ፣ ያንንም ከመገፋት ቆጥሬ የሰርጌ ቀን ማታ ባሌን አስተኝቼ ልሄድ እችል ይሆናል ...
👍404
ምክንያቱም አእምሮዬን አላምነውም፤ ምክንያቱን በትክክል ባላውቀውም የሆነ ዓይነት የአእምሮ ችግር ሳያጋጥመኝ አልቀረም፡፡ ወይም ጓደኛዬ ሃይሚ አንደምትለው አስደግሞብኛል፡፡ አልጋው ውስጥ ሆኜ የምታገለው ዕንባዬ ጋር ነበር፡፡ በሕይወቴ እንደዚያን ቀን አፍሬ አላውቅም፤ በኃፍረት እንዳቀረቀርኩ ልብሴን ለባብሼ ወጣሁ። ሚዜዎቼ በግርምት _ እያዩኝ፣ የት እንደሄድኩ ለማወቅ በጥያቄ አፈጠጡብኝ “ቤተክርስቲያን” አልኳቼው፡፡ አሁንም ዓይናቼውን ከእኔ ላይ አልነቀሉም ውሸቴ አላረካቼውም ይሆናል፡፡ “የማስገባው ስእለት ነበር ድንገት ትዝ አለኝ" ሁሉም ወደጥፍርና ጸጉር ወሬያቼው ተመለሱ፡፡ ጓደኛዬ ሃይሚ ግን ዓይኖቿን አጥብባ በጥርጣሬና ትዝብት አዬችኝ “ እውነቴን ነው” አልኳት ቆጣ ብዬ “ሆሆ! ታዲያ ምን አስጮኸሽ?'' ካለችኝ በኋላ በትንሽ ብልቃጥ ሽቶ እያቀበለችኝ “በይ ይኼን እንኪ ላብ ላብ ሸትተሻል" ብላኝ ተነስታ ሄደች። በጣም እንደተናደደች ታስታውቅ ነበር፡፡ ወደ ደረቴ ጎንበስ ብዬ እጄን በየተራ እያነሳሁ የራሴን ጠረን ለማሽተት አነፈነፍኩ...ከጡቶቼ መኻል፣ ከብብቴም ግራና ቀኝ እሱ ጋር ስተኛ ሁልጊዜም እንደምሼተው የሆነ ደስ የሚለኝ የላብ ጠረን ከሰውነቴ ይተን ነበር። ዮናስ ጸጉር ቤት መጥቶ አነሳንና ሚዜዎቼን በየቤታቼው አድርሰን ስንመለስ ድንገት መኪናዋን ወደሆነ ሰፈር አስገባት። ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ “የት እየሄድን ነው?” አልኩት። “እየጠፋን” ብሎኝ ጨለማው ውስጥ መኪናውን አቆመ፣ መብራቱን አጠፋ፣ በሩን ከፍቶ ወረደና በእኔ በኩል ዙሮ ከፈተልኝ። ዓይን ቢወጉ በማይታይበት ጨለማ ወረድኩ፤ የኋለኛውን በር ከፍቶ ግቢ አለኝ ፤ ገባሁ። እሱም ተከትሎኝ ገባና ልክ እንደ እብድ ሰፈረብኝ። በጭራሽ ያልጠበኩት ነገር። ሻወር

እንኳን አልወሰድኩም። “እንዴ ኸረ ሰው ያዬናል” አልኩ ደንግጨ። አንስቶ ታፋው ላይ አስቀመጠኝ። እንደዚያ ቀላል መሆኔን አላውቅም ነበር። ቀሚሴን ወደ ላይ ሰብስቦ ትንፋሹ እየተቆራረጠ “ዋው ፓንት አለበሺም?!'' ሲለኝ ደነገጥኩ። ግራ ገባኝ ...እጄን በቀስታ ልኬ ሰውነቴን ነካሁት፤ ፖንት አለበስኩም:: ዮናስ ወደ እብደት በተጠጋ ስሜት ነገሩን ቀጥሏል። መኪናው ምንም ካለመመቸቱም በላይ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እልኅና ኃይል የተሞላበት ስለነበር ማሕፀኔ ላይ እና የታጠፈ ጉልበቴ ላይ ሕመም እየተሰማኝ ነበር። ግን እሱ ሌላ ዓለም ውስጥ ስለነበር አላስቆምኩትም። _ እንደዚያ __ አነር _ ሲሆን ዓይቼው አላውቅም። ጥርሴን ነክሼ ቻልኩት። እየታምመኩ ለሌሎች ምቾትና ደስታ ማሰብ ትልቁ የሕይወቴ ድክመት ነበር፡፡ ይኼን የመኪና ውስጥ ጉዳይ ከተጋባን በኋላ እንደገና ሞክሮት በቁጣ ቀልቡን ገፍፌ መኪናውን ካስገባበት ጨለማ አዙሮ ወደ ቤት ሄደናል። ሁልጊዜ በተለይ ማታ፣ መኪና ውስጥ ብቻችንን ከሆንን ሌላ ነገር ያምረዋል። ከመኪና ምን አለው ሰውዬው? “ሮማንቲክ'' መሆኑ ነው? የዚያን ቀን የሚያደርገውን አድርጎ _ እቤት _ አድርሶኝ _ “የማይረሳ _ ጊዜ” ብሎኝ ከተመለሰ በኋላ የመኪናውን ጉዳይ ረስቼ ሐሳቤ ሁሉ ስለ ፖንት ነበር። ከአብርሃም ቤት ስመለስ የሆነ ነገር ታክሲ ውስጥም ሆኜ ቅፍፍ ሲለኝ እንደ ነበር ትዝ አለኝ፣ ምክንያቱ ግን አልገባኝም ነበር፡፡ በእርግጠኝነት ፓንቴን እሱ ቤት ረስቼ ነው የተመለስኩት፤ ምክንያቱም ስሄድ ያ የመቅፈፍ ስሜት አልነበረም፤ ወይም እኔ እንጃ ከቤት ስወጣ አለበስኩም ይሆናል ...ዝርክርክ ብዬ ነበር፡፡ ዝርክርክ ሙሽራ፡፡ የኛ ሙሽራ ፖንት የላትም፣ እግዚአብሔር አይወዳትም፤... እራሴ ላይ በሰርግ ዜማ አላገጥኩ፤ መራር ቀልድ። ይኼ ሁሉ አራት ዓመት አብሬው ከቆዬሁት ፍቅረኛዬ ጋር ያደረግሁት የለዬለት እብደት ነበር። ምናልባትም የመጨረሻው። ከዚያ በፊት ይኼን እብደቴን መተው

ከሆነ ከባድ የአደንዛዥ ዕፅ (ሄሮይን ምናምን) ሱሰኝነት እንደመላቀቅ ዓይነት ከባድ ትግል ጠይቆኛል። ሰባት ጊዜ ብወድቅም፣ ሰባት ጊዜ እነሳለሁ በሚል (ሲተረት ሰምቼ) የጀመርኩት የመውደቅ - መነሳት ትግል ነፍሴንም ሥጋዬንም እንዳልነበር አድርጎ አድቅቆኝ፤ ይኼው ለሰባት መቶኛ ጊዜ ይሁን ለሰባት ሚሊዮነኛ ጊዜ አሁንም ያንደፋድፈኛል፡፡ እያንዳንዱ መውደቅ ውስጥ ጠባሳ አለ። ውድቀታችን ቁጥር ብቻ አይደለም፤ ወድቆ መነሳትን እንደ ጀግንነት የሚነግሩን ሁሉ በእያንዳንዱ ውድቀት የማይጠገን የዋሀነት፣ዳግም የማይነጻ ንጹህ ቅንነት እንደሚጣል አልነገሩንም፡፡ ስኬት ብቻውን ጥንካሬ አይደለም። ነፍስን ጥሎ በሥጋ ሰማይ ቢደረስ ምንድን ነው ትርጉሙ!? ይኽ መውደቅ- መነሳት ከውጭ አይታይ እንጂ፤ በደላው ሥጋዬ ሥር ያለች ነፍሴን እንደ ልማደኛ ሰካራም ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጸጉሯ በጠባሳ ሞልቷታል (እንዲያውም ነፍሴ ጥፍራም ትመስለኛለች፡፡) ቢጨንቀኝ ጸለይኩ፣ ወደ ቤቱ ልሄድ እግሬን ሳነሳ ግደለኝ ብዬ ለአምላኬ ጸለይኩ፣ አልገደለኝም፡፡ እግርና እጄን አሳስረው ብዬ ለመንኩ፣ እንዲያውም ወደ እሱ ቤት ስሄድ ለወትሮም የሚንከረፈፉ እግሮቼ እንደሚዳቋ እግሮች ይፈጥኑ ነበር፡፡ ገነት የት ነው ቢሉኝ? ከሜክሲኮ ተነስቶ፣ በቄራ፣ በቡልጋሪያ፣ በገብርኤል አድርጎ፣ መብራት ኃይልን አልፎ ላፍቶ የሚባል ሰፈር ነው እላለሁ፡፡ የታክሲ ረዳቶቹ ላፍቶ! ላፍቶ! ሲሉ ክንፋቼውን ለሥራ አልመች ብሏቼው ነቅለው ያስቀመጡ ወደ ገነት ሕዝብ የሚጋብዙ መልአክት ይመስሉኛል፡፡ ወደ እሱ ቤት ስሄድ ለወትሮው በሰልፍ የማይገኝ ታክሲ እንደግል መኪና መጥቶ ፊቴ ይቆማል''ሰካራም እንዲወድቅ፣ሰይጣን ምንጣፍ ያመቻችለታል'' እንደሚሉት ወደሱ ቤት ስሄድ መንገዱ አልጋ በአልጋ ይሆናል፤ መዳረሻዬም የሰው ልብ አልነበረም አልጋ ነበር፡፡ ፍቅራችን እንደ በሽተኛ ከአልጋ ወርዶ አያውቅም፡፡ አንዳንዱ ፍቅር አልጋ ላይ ተጀምሮ አልጋ ላይ ያበቃል፡፡አፈቅረዋለሁ ስለዚህ ሰውነቴ፣ ልቤ፣ ሐሳቤ፣ ጊዜዬ ሁሉ የእሱ ነበር፤ ያለኝን ብቻ አይደለም የሌለኝን ሁሉ ልሰጠው እመኝ

ታዲያ ሁልጊዜ አስባለሁ እንዴት ነው ሳያፈቅረኝ የሚተኛኝ? ... መተኛት ሲባል፤ አራት ዓመት ሙሉ ልክ እንደመጀመሪያ ቀን ዓይነት በጉጉት በናፍቆት በስሜት የሚደረግ መተኛት!...እንደዚያ ይቻላል ወይ!?... ወይስ እያፈቀረኝ ለማግባት ያልፈለገበት ምክንያት ነበር? ...ስለ ወንዶች አላውቅም ...የመጀመሪያዬ ነበርና የማይገባኝ ብዙ ነው፡፡ አሁንም እራሴን እወቅሳለሁ ምን ይሆን ያጠፋሁት? እያልኩ... አፍ አውጥቼ “አግባኝ” አልኩት፡፡ ያቺ ቃል ትጸጽተኛለች፡፡
👍325👎2
ትዳር ወግ ማዕረግ የሚባለው ነገር ናፍቆኝ አልነበረም፣ እውነቱን ለመናገር እንደ ትዳር የምፈራውም የምጠላውም ነገር የለም። የራሴን ቤተሰቦች ጨምሮ በዙሪያዬ ካዬሁትና ከሰማሁት፣ አንድም ጤነኛ ትዳር አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ አግባኝ ያልኩት አንድ ቀን ትቶኝ የሚሄድ- የሚተወኝ መስሎኝ ስለፈራሁ ነበር፡፡ ያንን ሁሉ ደስታዬን ይዞ ቻው እንዳይለኝ ፈርቼ። ኃይሎጋ ይባል አይባል፣ ሰርግ ይኑር አይኑር፣ ቀለበት ጣት ላይ ይሰካ አይሰካ፣ልጅ ይወለድ አይወለድ ጉዳዬ አልነበረም፤ የምፈልገው እሱ ጋር መሆን ብቻ ነበር፡፡ በቃ አግብቼሻለሁ ቤቴ ኑሪ ቢለኝ ሰተት ብዬ ነበር የምገባው። ፍጹም ደስተኛ ነበርኩ- ከእሱ ጋር። ይሁንና ስለጋብቻ እሱ ጋር ያወራነው ሁለት ቃላት ብቻ ነበሩ፤ ሁለት ቃላት፣ አግባኝ! አልኩት፡፡ እሺ! አለ፡፡ በቃ! አፍ አውጥቼ ያንን ከተናገርኩ፣ የተሰማውን መናገር አልነበረበትም!? የሆነ ነገር ማለት አልነበረበትም!? ለመስክ ሥራ በየክፍለ ሐገሩ ስዞር ከአዲስ አበባ ይልቅ ናፍቆቴ እሱ ነበር፤ ራሴን ረስቼ ነበር። ካለ'ሱ ምኔም ምኔም ለብቻ አይታዬኝም፡፡ ለእኔ ያቺ ባለ አንድ መኝታ ቤት የኮንዶሚኒዬም ቤቱ ዓለሜ ነበረች፡፡ ወይኔ ቤቱ !!!


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍256
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹እኔ ከቤት ወጥቼ ስለጠፋሁበት ያን ያህል የሚያዝን ይመስልሀል?››

‹‹ልጠፊ ቢሆንማ ምን አልባት አንድ ቀን ተመልሳ ትመጣለች በሚል ተስፋ አንቺን ለመጠበቅ ሲሉ ብቻ ህይወታቸውን በጥንካሬ ያቆዮታል፤ከሞትሽ ግን ለመኖር ምን ምክንያት ይኖራቸዋል?፡፡››

‹‹እንዴ!!!... ሞታለሁ መች አልኩህ?››

‹‹ባትይኝም ዕቅድሽ እራስሽን ለማጥፋት እንደነበረ አውቃለሁ፡፡››

‹‹እንዴ በምን አወቅክ…?ይሄ እኮ በውስጤ ብቻ ያቀድኩት የብቻ ሚስጥሬ ነበር፡፡›› በገረሜታና ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እንዴት እንዳወቅኩ አትጠይቂኝ ..ግን እርግጠኛ ነበርኩ፡››

‹‹ለማንኛውም በጣም አስደንቀኸኛል፤ደግሞም በጣም አመሰግናለሁ፤ ለእኔ መልዓኬ ነህ፡፡ሁል ጊዜ ስላንተ ሳስብ የተቋጠረ ፊትህና የተዘጋ አንደበትህ ሳይሆን የውስጥህ ቅንነት ነበር የሚታየኝ፤በትክክል ነበርኩ ...ልዩ ሰው ነህ ››አለችው፡፡

ፊቷን ወደ እሱ አዙራ በማቀፍ ብትስመውና ብትውጠው ደስ ይላት ነበር ፤ግን አልቻለችም ፡፡ …ሊረዳት እንጂ ሊያፈቅራት እንዳልፈለገ ትዝ ስላላት..ፈራች፡፡ ቢሆንም የሆነች ብጣቂ የህይወት ተስፋ በልቧ ሲበቅል ይታወቃታል፡፡

ከሦስት ወር በኃላ ታዲዬስና መርጊቱ ቀለል ባለ ዝግጅት በስርአቱ 8ዐ ተፈራርመው ተጋቡ፡፡አባትዬው የግል ዕቃቸውን ጠቅልለው ታዲዬስ ተከራይቶበት የነበረበት ቤት ሲገቡ፤ በተቃራኒው ደግሞ ታዲዬስ ዕቃውን ሸክፎ አባ ወራ ሆኖ ትልቁ ቤት ገባ፡፡
አንድ ቤት መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራቶች እየተገባደዱ ነው፡፡በዚህ ጋብቻ እንደ አቶ ቂጤሳ ደስተኛ የሆነ የለም፡፡መርጊቱ እርግዝና እየገፋ ሲመጣ የታዲዬስ እንክብካቤ እየጨመረ መጣ፡፡ አንድ ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን ማንኛውንም ነገር ያለስስት ያደርግላታል፤ከአንድ ነገር በስተቀር፡፡ታዲዬስና መርጊቱ እስከአሁን አንድ መኝታ ቤት ውስጥ ቢያድሩም አልጋ ላይ እና መሬት ተለያይተው ነው የሚተኙት፡፡

ይሄ ሁኔታ ደግሞ ለመርጊቱ ይበልጥ ከብዷታል፡፡እንዴት ወንድ ልጅ ያለምንም ጥቅም አንዲት ምኑም ያልሆነችን ሴት ለዛውም ለማያፈቅራት ሴት እንዲህ መስዋዕት ይከፍላል?››

ፍራሹን ከተጣጠፈበት ፈታና ወለሉ ላይ ዘረጋው፤አንሶላና ብርድልብስ አቀበለችው፡፡ አነጠፈና ከጨረሰ በኃላ ተጋደመ..፡፡እሷም ከበላዮ ካለው አልጋ ወጥታ ከውስጥ ገብታ ከተኛች በኃላ ‹‹መብራቱን ላጥፋው?››

አለችው፡፡

‹‹አጥፊው፡፡››

አጠፋችው፡፡

‹‹...ውይ ፌናን ሳልነግርሽ፤ነገ አዲስአባ መሄድ ፈልጌያለሁ..ነገና እሁድን እዛ ውዬ ሰኞ እመለሳለሁ፡፡››

‹‹እሺ››አለችው፡፡

ቅር ያላት ስለመሰለው‹‹አትፈሪም አይደል?››አላት፡፡

‹‹ምን ያስፈራኛል..ካልሆነ አባዬ እዚህ እንዲተኛ አደርጋለሁ..ግን በሰላም ነው?››

‹‹አይ ሰላም ነው…ጓደኛዬ ናፍቀኸኛል ስላለችኝ ነው፡፡››

«...ማ ርብቃ?>>

‹‹አዎ..በዛ ላይ እኔም አምሮኛል..ሁለት ወር ሊሞላኝ እኮ ነው፡፡››ታዲዬስ ስለ እሱና ርብቃ ግንኙነት ከዚህ ቀደም ነግሯታል ፡፡

‹‹ርብቃ ማለት የታዲዬስ ጓደኛም፤ፍቅረኛም ነች፡፡በወቅቱ ሶስት ዓመት ያስቆጠረ የፍቅር ታሪክ ነበራቸው፤ሲነፋፈቁ ይደዋወሉና ይገናኛሉ፡፡ ለሁለት ሶስት ቀን ጣፋጭ የፍቅር ጊዜ ያሳልፉና መልሰው ይለያያሉ፡፡ሁለቱን የሚያቆራኛቸው የጋራ ነገር ፍቅራቸው እና ጓደኝነታቸው ነው፡፡

በጭለማው ውስጥ ለረጅም ደቂቃ ስለእሱና ስለርብቃ በዝምታ ስታሰላስል ከቆየች በኃላ‹‹ታዲ.... >> አለችው፡፡

<<አቤት>>

‹‹መሬት ልተኛ?››

‹‹አልተመቸሽም? ምነው ልቀይርሽ እንዴ?››

‹‹አይ!! ካንተ ጋር ለመተኛት ፈልጌ ነው፡፡››

‹‹ነይ ..ምን ችግር አለው፡፡››አላት…..ማብራቱን ሳታበራ ተንሸራታ ወረደችና ከጎኑ ተጋደመች፡፡

<<ታዴ...::>>

<<አቤት>>

‹‹ከርብቃ ጋር ግን የምትጋቡ ይመስልሀል?››

‹‹አይመስለኝም፡፡››

<< ከተፋቀራችሁ ለምን አትጋቡም?››

‹‹የተፋቀረ ሰው ሁሉ ይጋባል እንዴ..…?››

‹‹አዎ ሰው ከተፋቀረ ምን ይፈልጋል…?በአሁኑ ጊዜ የጠፋው እኮ በሁለት ወገን ሚከሰት ተመጣጣኝ ፍቅር ነው፡፡››

‹‹ችግሩ ሁለታችንም ለጋብቻ ጉጉት የለንም፡፡ ርዕሱንም አንስተን አውርተንበት አናውቅም፡፡ እኔ እንጃ ብቻ እንደዛ ሚሆን አይመስለኝም ››ወደ እሱ ዞረችና አቀፈችው፡፡እሱም አቀፋትና ተኛ ፤ቀድሞ እንቅልፍ ወሰደው .. እሷ ግን መአት ግትልትል ሀሳብ ስታስብ ለሊቱ ከተጋመሰ በኃላ ነበር እንቅልፍ ያሸነፋት፡፡ .

ታዲዬስ እንደተለመደው ከአንድ ወር ቆይታ በኃላ ጓደኛውን ርብቃን ጥየቃ ወደ አዲስአበባ ሄደ፡፡ ናፍቃው፡፡ ኮልፌ የሚገኛው ቤቷ ሲደርስ እሷ አልነበረችም፡፡ግን አልተመለሰም የሳሎኑን በራፍ ተጠጋና ዙሪያውን በዓይኑ ቃኘ፡፡የእግር መጥረጊያ ምንጣፉን ገለጥ በማድረግ ቁልፉን አገኘው፡፡ከፍቶ ገባ፡፡በሩን መልሶ ዘጋውና ያነገበውን መለስተኛ ሻንጣ ጠረጴዛ ላይ አኑሮ ወደ ሶፋው በመሄድ ጋደም አለ፡፡ ርብቃን ለምን እንደሚያፈቅራት ዘወትር ሲያስብ ግራ ይገባዋል፡፡ምን አልባት እንደ እሱ ሚስጥራዊ፣እንደእሱ በፀጥታ የተሞላች፣እንደእሱ ገለልተኛ ስላልሆነች ይሆናል፡፡ክፍተቱም ከእሷ ጋር ሲሆን ተደፍኖ ስለሚያገኘውም ሊሆን ይችላል፡፡ግን ለምንድነው እንደሌሎች ሴቶች ለጋብቻ ፍቅር የሌላት?ለምንድነው እስከዛሬ አግባኝ ብላ ያልጠየቀችው? ይሄም ይገርመዋል፡፡
መገረሙ ሳያበቃ እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ መርጊቱ ነጭ ቀለም ያለው እስከ እግር ጥፍሯ የሸፈናትን ቀሚስ ለብሳ ከብዙ ሰው መካከል እየተሹለከለከች ወደ እሱ ትመጣለች፤ አባቷንም ትጠጋለች፡፡ አልፋ ፡፡ ወደእሱ ትጠጋለች።

‹‹ምነው መርጊቱ፤ ፈለግሺኝ?>>ይጠይቃታል፡፡

‹‹አዎ..እዚህ ካንተ እና ከአባዬ ጋር መኖር ከብዶኛል...እናቴ ጋር ብሄድ ይሻለኛል፡፡.››ትለዋለች፡፡

<እና?>>

‹‹እናማ እሷ ጋር ሄጄ ልኖር ነው፡፡››

‹‹እናትሽ የት ነው ያለችው?››

‹‹እሱን አላውቅም..ግን ልትወስደኝ መጥታለች፡፡…ያችዋትና እየጠበቀችኝ ነው››ብላ እናቷ ወዳለችበት አቅጣጫ ትጠቁመዋለች፡፡እይታውን ወደ ጠቆመችው
አቅጣጫ መልሶ ሲያይ እናትዪዋን ይመለከታታል፡፡ግርም ይለዋል፡፡እናትና ልጅ ምንም ልዩነት የላቸውም፡፡ በመልክ፣በአለባበስ፣ በቁመት፣ በሰውነት መጠን፣ብቻ የእናትዬው ፀጉር ድፍን ነጭ ሲሆን አጠገቡ የቆመችው መርጊቱ ፀጉር ደግሞ ከጥቁርነት ገና ወደ ነጭነት ለመቀየር የጀመረ ዓይነት ነው፡፡

‹‹እና ምን ልርዳሽ?›› ይላታል፡፡

አዲስ የሰው እጅ ያልነካው እስር መቶ መቶ ብር አንድ ላይ አስር ሺ ብር ይመስለዋል ወደ እሱ እየዘረጋችለት ‹‹ይሄንን በአደራ አስቀምጥልኝ፤ ይውልህ ይሄን ብር ለማግኘት ብዙ መከራ አሳልፌያለሁ፤ብዙ ተሰቃይቼያለሁ፡፡በካዝናህ ውስጥ ካንተ ወርቅ እና ዕንቁዎች ጋር አስቀምጥልኝ፡፡አንድ ቀን ተመልሼ ከመጣሁ ትመልስልኛለህ፡፡ ካልሆነም እኔን ፍለጋ መምጣትህ ስለማይቀር ያን ጊዜ ታስረክበኛለህ፡፡››

‹‹እንዴ!! ይሄን ሁሉ ብር ለምን ለአባትሽ አትሰጪያቸውም?እሷቸው ከእኔ በተሻለ በእምነት ያስቀምጡልሻል..በፈለግሽ ጊዜም መልሰው ይሰጡሻል፡፡››.

‹‹አይ አባዬ እኮ አሁን አርጅቷል፤ይሄንን ብር በሌባ እንዳይዘረፋ ነቅቶ መጠበቅና ማቆየት የሚችል ይመስልሀል..?ተው ተው ይሄንን አድርግልኝ ብዬማ ጭንቅ ውስጥ አልከተውም…አንተው ትሻለኛለህ፡፡››

‹‹ካልሽ እሺ..››በማለት ይቀበላታል፡፡

‹‹ግን ከባድ አደራ ነው ፡፡ የጣልሺብኝ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ብር ቤቴ ገብቶ አያውቅም፡፡››
👍7816👏3🤔2
‹‹ግድ የለህም፤ አደራህን እንደምትወጣ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው..በል ቻው እማዬን ብዙ አስጠበቅኳት››ብላ ጉንጩን ስማው ትሄዳለች፤ እየራቀች... እየራቀች፣እናቷ የቆመችበት ቦታ ስትደርስ እናትዬው እንደ ህፃን ልጅ ከመሬት አንስታ ካቀፈቻት በኃላ በነጭ ቀሚሷ ውስጥ የደበቀችውን ነጭ ክንፍ ትበትንና አርገፍግፋ አድርጋ በመዘርጋት ወደላይ ትበራለች፤መርጊቱን እንዳቀፈች ከሰማየ ሰማያት በራ ከደመናው ውስጥ ገብታ ትሰወራለች፡፡

የበራፉ መንጓጓት ነበር ከእንቅልፉ ያባነነው ፡፡ በርግጎ በመነሳት ቁጭ አለ፡፡ሰውነቱ ላብ በላብ ሆኗል፡፡

ተለጠፋበት ጉንጮቹን አገላብጣ እየሳመች‹‹እንዴ ስትመጣ እኮ ትደውልልኛለህ ብዬ ነው?››አለችው ርብቃ፡፡

‹‹ምቹ ቦታ እንዳልሆነሽ አውቄ ነው ያልደወልኩልሽ፡፡››

‹‹ፀጉር ቤት ነበርኩ፤ ፀጉሬን እየተሰራሁ›› ከፀጉር ቤት እማ ከወጣሽ ቆየሽ…መጠጥ ቤት ከሆነ ወንድ ጋር የነበርሽ ነው ሚመስለው››

‹‹ምን…? አይተኸኛል እንዴ?››

‹‹አይ አላየሁሽም.. ግን አንደኛ ስትስሚኝ ትኩስ መጠጥ ሸቶኛል፡፡ሁለተኛ እንዲህ ንቁ የምትሆኚው ከወንድ ጋር ከጠጣሽ ብቻ ነው››

‹‹የሆንክ ምትገርም ጠንቋይ ነገር ነህ..ግን ንፍቅ ብለኸኛል፡፡››

‹‹አውቃለሁ.. እኔንም ንፍቅ ብለሽኛል፡፡አንቺም ብቻ ሳትሆኚ ወሲብም በጣም አምሮኝ ነበር ግን::>>

<<ግን ምን?>>

‹‹ተመልሼ መሄድ አለብኝ፡፡››

<<መቼ ለምን.?>>

<<አሁን ተኝቼ መጥፎ ህልም አየሁ...ህልም እንኳን ማለት ይከብዳል፤ብቻ ከቻልሽ አውቶቢስ ተራ ድረስ ሸኚኝ፡፡››

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ?አስራ አንድ ሰዓት እኮ ሆኗል፤እደርና ለሊት ትሄዳለህ፤እኔ እንደውም የቅዳሜውንና የእሁዱን እረፍት ተኝተን በጣፋጭ ሁኔታ እናሳልፋለን ብዬ ስቋምጥ ነው የሰነበትኩት፡፡››

‹‹ነገርኩሽ..መሄድ አለብኝ፤ያልሽውን አንቺ የምትፈልጊውን ነገር እኔም ፈልገው ነበር ››.በማለት ከተቀመጠበት ተነሳና ሻንጣውን ያዘ::

‹‹...እንግዲያው አስር ደቂቃ ጠብቀኝ አብረን እንሄዳለን፡፡››ብላው ውሳኔውን ሳትጠብቅ አልፋው ወደ መኝታ ቤቷ ገባች፡፡ቆሞ ጠበቃት፡፡ልብሷን ቀያይራ የተወሰነውን ደግሞ በቦርሳዋ ይዛ ወጣች፡፡ቤቱን ቆልፈው ወደ መነኻሪያ ተጓዙ ..አምቦ ሲደርሱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡

ቤት ደርሰው አንኳኩ፡፡አቶ ቂጤሳ ነበሩ ‹‹ማን ልበል?›› እያሉ የከፈቱት፡፡

‹‹እኔ ነኝ››ድምፁን ስትሰማ መርጊቱ ከመቀመጫዋ ተነሳችና በፍጥነት በራፍ ላይ ደረሰች፡፡

‹‹ምነው ምን ሆንክ?››ተርበተበተች፡፡

...መላ አካሉን አይታ ሰላም መሆኑን እስክታረጋግጥ አልተረጋጋችም‹‹ምንም አልሆንኩ፤ ኧረ ሰላም ነኝ››እያለ ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባ፡፡ ርብቃም ከኋላ ተከተለችው፡፡ሁሉም ሰላምታ ከተለዋዋጡ በኃላ ወንበር ይዘው ተቀመጡ፡፡የመጡበትንም ምክንያት ሰበብ ፈጥረው አሳመኗቸው፡፡

አባትዬው ልረፍ ብለው ወደ ክፍላቸው ሄዱ ፡፡ መርጊቱ እራት አቀረበችላቸውና እነሱ እየበሉ ሳለ ወደ መኝታ ቤት በመሄድ እሷ የምተኛበትን አልጋ ንጽህ አንሶላ ቀይራ በስርዓት አነጠፈችና ታዲዬስ ይተኛበት የነበረውን ፍራሽ እየጐተተች ወደ ሳሎን ስታወጣ ‹‹እንዴ ምን እያረግሽ ነው..?እኔ አነጥፈዋለሁ >>ብሎ ምግቡን ጥሎ ተነሳ፡፡ ተቀብሎ አስተካከሎ አነጣጠፈው፡፡ ርብቃ የተበላበትን ዕቃ አነሳሳች፡፡

‹‹ፍራሹን እዚህ ያነጠፍሽው እኛ መኝታ ቤት አልጋው ላይ እንድንተኛ አስበሽ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን እዚህ ይመቸናል፡፡›› ብሎ ቀድሞ ተኛበት፡፡ብትከራከርም የሚሰማት አላገኘችም፡፡ምርጫ ስላልነበራት ደህና እደሩ ብላ ወደ መኝታ ቤቷ ገባችና ተኛች፡፡

ርብቃ የለሊት ልብሷን ቀይራ ከጎኑ ሄዳ ተኛች፤ በሹክሹክታ ንግግር‹‹ዝም ብለህ ነው ስትቃዥ አክለብልበህ ያመጣኸኝ፡፡ እሷ ሙሉ ጤነኛ ነች፡፡››አለችው፡፡

በስጋት ተውጦ‹‹እናያለን፡፡›› አላት፡፡

አቀፈችው፤ዳበሰችው፤በመከራ ነበር ከገባበት የተደበተ ስሜት ውስጥ አውጥታ ስሜቱን በማነቃቃት ፍቅር እንዲሰሩ ማድረግ የቻለችው፤ጨርሰው ርብቃ እንቅልፍ እንደወሰዳት ተነሳና ወደመኝታ ቤት ሄደ፡፡
በራፉን ገፋ ሲያደርገው ተከፈተ፡፡ መብራቱ አልጠፋም መርጊቱ አልተኛችም ነበር፡፡

ስታየው ፊቷ በራ ‹‹‹ምነው እንቅልፍ እንቢ አለሽ?እንዳልተኛሽ ተሰምቶኝ ነው የመጣሁት፡፡››

‹‹እኔ እጃ ውስጤን ፍርሀት ፍርሀት ሲለኝ ነው የዋለው››አልጋው ላይ ወጣና ከጎኗ ተኛ ፡፡
‹‹ግን በመምጣትህ እንዴት ደስ እንዳለኝ አትጠይቀኝ፤ ቀኑን ሙሉ ምነው አትሂድ ባልኩት እያልኩ ስማረር ነበር የዋልኩት፡፡››

‹‹ለምን ..በሰላም?››

‹‹እኔ እንጃ፤ ብቻ ከአጠገቤ እንድትኖር ፈለኩ..፡፡››ወደ እሱ ዞራ አቀፈችውና ‹‹ይሄ ልጅ ሲወለድ ባንተ ስም ነው የሚጠራው፤አባቱ ነህ፡፡የእውነት አባቱ እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ ማለቴ የእውነት አግባኝ እያልኩህ አይደለም፡፡ ጥለሀኸኝ ብትሄድ ወይንም እኔ ጥዬህ ብሄድ እንኳን ልጁን እንዳትሰጠኝ፡፡ባንተ እጅ እንዲያደግ እፈልጋለሁ፡፡እርግጥ ያልወለዱትን ልጅ ማሳደግ ይከብዳል፡፡ቢሆንም ላንተ ምንም የሚያቅትህ ነገር የለም ፡፡>>

‹‹ተቀብዬለሁ...የሰጠሽኝን ልጅ እንደ አባት ሆኜ ሳይሆን አባት ሆኜ አሳድጋለሁ፡፡ግን ወንድ ሳይሆን ሴትም ልትሆን ትችላለች?››አላት፡፡

‹‹ትሁን ሴትም ወንድም ቢሆን ያንተው ነው፡፡ ለእኔ እግዜር ካለ ሌላ ወልዳለሁ፡፡ይሄንን ልነግርህ ነበር መሰለኝ እንዳገኝህ የጓጓሁት፤አሁን እፎይታ ተሰማኝ ..እንቅልፌም መጣ... አመሰግናለሁ፡፡›› ብላ ግንባሩን ሳመችውና ‹‹ከተኛው በኃላ ቀስብለህ ሂድ›› አለችው፡፡

ወደ ራሱ አስጠግቶ አቀፋትና‹‹ ዛሬ ካንቺ ጋር ነው የምተኛው፤ዝም ብለሽ ዘና ብለሽ ተኚ፡፡›› አላት፤ ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት ፡፡ ከለሊቱ 8 ሰዓት ገደማ አስፈሪ የመቃተት
ድምፅ ነበር ከእንቅልፉ ያባነነው ፡፡መርጊቱ
እየተንቆራጠጠች ነበረ፡፡ወዲያው ስልክ
ደወለ‹‹ ቶሎ በል ተነስና ታክሲዋን ይዘህ ና›› አባትዬው ተቀሰቀሱ፡፡ በ15 ደቂቃ ውስጥ ሆስፒታል አደረሷት፡፡ከአንድ ሰዓት በኃላ በነጭ ጨርቅ የተጠቀለለች የምታምር ለጋ ህጻን ነርሷ ለታዲዬስ አስታቀፈችው፡፡ወዲያው
የመርጊቱ ሬሳ ከማዋለጃ ክፍል ወደ ሬሳ ማቆያ ክፍል ሲዘዋወር ተመለከተ ፡፡ አባት በእሪታ ግቢውን አደበላለቁት፡፡ርብቃ በእንባ
ታጠበች፡፡ታዲዬስ በከፍተኛ ሀዘን ውስጡ ገብቶ ተንኮታኮተ፤እንደእነሱ ግን በእንባ መታጠብ አላሰኘውም፡፡ የሆን ጭር ያለ ቦታ፤ማንም ማይደርስበት ስፍራ ሄዶ መሸሸግ አማረው፡፡ መርጊቱ ከቀበረ በኃላ በማግስቱ
ህፃኒቷን ይዞ ከአምቦ ወጣ ፤ የወለድኳት ልጄ ነች ብሎ ሀዋሳ ወስዶ ለእናቱ ሰጣት፡፡እሱም ኑሮውን ጠቅልሎ ወደ ሀዋሳ አዘዋወረ፡፡ይሄንን ያደረገበት ዋና ምክንያት ሚጡን የማሳደጉን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ለእናቱ በማስረከብ ዳር ቆሞ ሊመለከት ስላልፈለገ ነው፡፡የእውነት
አባት ለመሆን …፡፡የሚጡ ጨቅላና ጀማሪ ልብ ከታዲዬስ ጎልማሳ ልብ ጋር እንዲህ ባለ የህይወት ገጠመኝ ነበር ሊጋመድ የቻለው....ከዛሬ ሰባት አመት በፊት፡፡ዛሬ እናቱ ብትሞትም እሱ ግን ሰላም ፣ሙሴ፣ሄለንና ሀሊማን በተለያየ ገጠመኝ ከየጎዳናው በመሰብሰብ ወደቤቱ ወስዶ ከሚጣ ጋር እንደልጅ የሚያሳድጋቸው ልጆቹ ናቸው፡፡

ይቀጥላል

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10620👏5
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ‹‹እኔ ከቤት ወጥቼ ስለጠፋሁበት ያን ያህል የሚያዝን ይመስልሀል?›› ‹‹ልጠፊ ቢሆንማ ምን አልባት አንድ ቀን ተመልሳ ትመጣለች በሚል ተስፋ አንቺን ለመጠበቅ ሲሉ ብቻ ህይወታቸውን በጥንካሬ ያቆዮታል፤ከሞትሽ ግን ለመኖር ምን ምክንያት ይኖራቸዋል?፡፡›› ‹‹እንዴ!!!... ሞታለሁ መች አልኩህ?›› ‹‹ባትይኝም ዕቅድሽ እራስሽን…»