አትሮኖስ
283K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
513 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል ሠባት


“አበባም ይሁን ድንጋይ፣ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው!”

ማኀደረ-ሰላም!

አገባሁ!! ድል ባለ ሰርግ ዮናስ የሚባል ከአሜሪካ የመጣ ሰው አገባሁ፡፡ አስተያዬት ሰጪዎች ግን ለባለቤቴ የሚሉት “አፈስክ” ነው። አስተፋፈሱ የየቅል ይሁን እንጂ፧ እኔም ባለቤቴ ያገባኝ ሳይሆን ያፈሰኝ ነው የሚመስለኝ፡፡ በሆነ ግዴለሽ መዳፍ! እንደ አልባሌ ነገር የትም ተበታትኜ ከተደፋሁበት አፋፍሶ ያገባኝ ነው የሚመስለኝ። ለራሴ ቢቀፈኝም ከወዳደቅሁ እኔ ገጣጥሞ፣ በወጉ ያልተቃኜች በድን ሚስት የምትባል ፍጥረት የሠራ ነው የሚመስለኝ፡፡ በድፍን አዲስ አበባ ከላፍቶ እስከ ሜክስኮ፣ ከቦሌ እስከሃያሁለትና መገናኛ፣ ከተበታተንኩበት ለቃቅሞ የገጣጠመኝ ልክ እንደተሰበረ ብርጭቆ፣ ከነስንጥቄ ተጠጋግኜ የሆነ ደግ ሰው ቤት የተቀመጥኩ፣ ውስጤ ፍቅር የማይቋጥር እንዲሁ ቅርስ ነገር ...የዕድለ ቢስነት መታሰቢያ ቅርስ። ታዲያ መልስ ሲባል ባሌ አልፈልግም ብሎ ወደ አባቴ ቤት የሚመልሰኝ መስሎ ነበር የተሰማኝ፡፡ባደረገዉ...!

ብዙ ሰዎች ሲሉ እንደሰማሁት ትዳር የአዲስ ሕይወት ጅማሬ፣ ያለፈ ታሪካችንን አጀንዳ ዘግተን ለአዲስ ነገ “ሀ” ብለን ርምጃ የምንጀምርበት ምዕራፍ መስሎኝ ነበር፡፡ ግን ለእኔ እንደዚያ አልነበረም፡፡ ያለፈ ታሪኬን፣ ትዝታዬን፣ ሕመሜንና ደስታዬን ሁሉ ልክ እንደ ልብስና ሌላ ሌላ ኮተቴ ሁሉ በአእምሮዬ ሻንጣ አጭቄ ነበር ወደ አዲሱ ቤት ያዘገምኩት፡፡ ያው አዲስ አበባ ይባል እንጂ ሩቅ ነበር ለእኔ፡፡ ሰሚት ወደ ሚባል ሰፈር፡፡ አሜሪካ ይሁን አንታርቲካ፣ ሰሚት ይሁን ቃልቲ፣ ከምወዳት ሰፈሬ ሜክሲኮ ከራቀ ሩቅ ነው፤ ሩቅ ነበር ለእኔ። ስደት በርቀት ካልተለካ በስተቀር ስደት ነበር ለእኔ፡፡ ልደታን ወረድ ብዬ ካላዬሁ ያዛጋኛል፡፡ የዋቢ ሸበሌ ሆቴልን አጥር ታክኬ ካላለፍኩ ዓለም ምልክት የሌላት ምድረበዳ ትመስለኛለች፡፡ በ'ኮሜርስ' ዙሪያ ካላንዣበብኩ አዲስ አበባ የዋልኩ አይመስለኝም፡፡ ብሔራዊ ቲአትር በር የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችንና የቲያትር “ፖስተሮችን” ካላዬሁ፣ የዕለት መዝሙረ ዳዊቱን ሳይደግም እንደወጣ ሃይማኖተኛ ቅር ቅር ሲለኝ ይውላል፤ ስንት የማናውቀው ሱስ አለብን!? እትብት የሚባለው ነገር በሥጋ እንጂ በነፍስ አይቆረጥም መሰል!? የተወለድንበት ሰፈር ላይ ያለ የማይታይ የመንፈስ ችካል ላይ ተቋጥሮ፣ በረዥም ክር ከእኛ ጋር የተሳሰረ ነገር ነው፤ የትም ብንሄድ ይስበናል፡፡ ሻንጣዬን ከፍቼ ልብሶቼን ቦታ ቦታ ሳሲይዝ፣ አእምሮዬም በሰፊው ተከፍቶ አሮጌ ትዝታዬን በአዲሱ ቤቴ ውስጥ እንደ ፎቶ መደርደር ጀመረ፡፡ እያንዳንዱን ልብስ ለብሼ፣ ምን እንዳደረኩ አውቃለሁ፡፡ እያንዳንዷን ቀሚስ እንዴት እንደገለብኩ፣ ሱሪዎቼን በእብደት ቁልቁል እንዳንሸራተትኳቼው አውቃለሁ፡፡ ከምንወዳቼው ጋር ስንት ጊዜ ልብሳችንን አውልቀን ስንት ጊዜ ለብሰናል?...ማነው የቆጠረው? በደመነፍስ ስንት ዓይነት ፈጣን አወላለቅ ተምረናል፡፡ ገና ቀጠሮ ስንይዝ፣ ውዶቻችን ልብሳችንን ለማውለቅ እንዳይቼገሩ ቀለል ያለውን አልመረጥንም? ልብስ ብዙ ብዙ ነገር ነው፡፡ ቢታጠብም የማይለቅ አሻራ፣ ከመተቃቀፎቻችን የቀረ ጠረን ሁሉ ዘላለማዊ ነው፤ ልብሶቼን እወዳቸዋለሁ፡፡ ውድ

ቅርስ እንደሚሰበስቡ ሰዎች፣ የእኔ ሰብስቦች ልብሶቼ ነበሩ። ውድ ሆነው አይደለም የተለዬ “ብራንድ” ያላቼው ወይም በአድናቆት የት አገኘሻቼውን የሚባልላቸው አልነበሩም። ለፋሽን ግድ የለኝም፣ለውበትም ያን ያኽል አልጨነቅም፡፡ምቾታቸው ድሎቴ ነው: ውስጣቼው ኑሪያለሁ ከቤቴ፣ ከሕይወቴ፣ ከአገሬም በላይ ልብሶቼ ውስጥ ኖሪያለሁ፣ መደበቂያዎቹ ነበሩ። የእኔ የራሴ ባንዲራዎች ነበሩ፡፡ ልብሶች ተራ ነገር አይደሉም፣ የግል ባንዲራዎቻችን ናቸው፡፡ አገር ባንዲራውን፣ ሰው ልብሱን ከጣለ ምን ቀረው? ሁለቱም እብደት ነው፡፡አረጄ ብለን የምንወረውረው ልብስ፣ ልብስ ብቻ አይደለም፤ የዕድሜ አሻራችን ጭምር እንጂ፡፡ ካለነገሩ አይደለም የለበስነውን ልብስ ተመሳሳይ ሌሎች ለብሰውት ስናይ ውስጣችን በቅሬታ የሚሞላው? ሌሎች ባንዲራችንን የነጠቁን ስለሚመስለን ነው፡፡ ግድግዳው፣ ጣሪያው፣ መኝታ ቤቱ፣ ሳሎኑ፣ መታጠቢያ ቤትና ማብሰያ ቤቱ ሁሉ ቁጥር ስፍር በሌለው ትዝታዬ ተሞልቶ፣ ገና ሳምንት ሳይሞላኝ አዲሱ ቤት ዕድሜ ልኬን የኖርኩበት አሮጌ ዋሻ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከምንም በላይ ያመመኝ እና ያደከመኝ፣ ደስተኛ መስዬ ለመታዬት አደርገው የነበረው ጥረት ነበር። እንዴት ሰው ዕድሜውን በሙሉ ሌሎችን ለማስደሰት እና ተቀባይነት ለማግኘት ሲባዝን ይኖራል? ...እኩል ምድር፣ እኩል ሰብአዊ ክብር፣ ተሰጥቶን እንዴት ነው አንዱ ለማኝ አንዱ ተለማኝ የሚሆነው!? ባለቤቴ በአዲስ ትዳር ናውዞ ሲሟዘዝ፣ አብሬው መሟዘዝ፣ ሲስቅ- መሳቅ፣ በስሜት ሲግል፣ እሳት ላይ ቢጥዱት የማይሞቅ ቀዝቃዛ ሥጋዬን የሞቀ ለማስመሰል መጣር፣ ባል~ ባል ለመሆን ሲደክም፣ ሚስት - ሚስት ለመምሰል መፍገምገም- ብዙ ማስመሰል፤ግን ብዙ መቀጠል አልቻልኩም።

እስከ መቼ ነው እንዲህ የምኖረው!? ያልኩት ገና በሳምንቱ ነበር፤ በተጋባን በሳምንቱ። የቤተዘመዱ ዕልልታ እንኳን፣ ካንዱ ቤት ሌላው ቤት ግድግዳ የሚነጥር የገደል ማሚቱው አልጠፋም ነበር። እልልልል ሲባል አእምሮዬ ይኼ እልልታ ለማነው? ይላል። ባለቤቴ ጋር የተዋወቅነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የመጀመሪያ ድግሪዬን ሥሠራ ነበር። የዛሬን አያድርገውና ጥርስ የማያስከድን ተጫዋች ልጅ ነበር። በግሩፕ ከነበረ ጓደኝነት እንደ አንዳቼው ከማዬት ባለፈ በግል እንኳን ያን ያኽል ቅርበት አልነበረንም፡፡ እንዲያውም ጓደኛዬ ሃይሚ “ይኼ ወሬኛ መጣ''እያለች እንድንርቀው ስለምትገፋፋኝ ብዙም አልቀርበውም ነበር። ልንመረቅ እንድ ዓመት ሲቀረን፣ ምን ሰይጣን ሹክ እንዳለው እንጃ፣ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ሱዳን ተሰደደ ተባለ፡፡ ወሬው ከዬት እንደመጣ አላስታውስም። ሁልጊዜ ከክላስ በኋላ የማይጠፋባት ፎቶ ኮፒ ቤት የሆነ ነገር ኮፒ ላደርግ ስሄድ እግረ መንገዴን እዚያ ያገኜሁትን ጓደኛውን “ዮኒ የት ሄዶ ነው?'' ብዬ ጠየቅሁት፤ እሱም እንዳላወቀ ነገረኝ፤ ያኔ ከአንድ ሰሞን ያለፈ ወሬ አልነበረም፤ በቃ ተረሳ። እሱ እንደገና ከተገናኜን በኋላ፣ እንደነገረኝ ከሆነ ለዓመታት ብዙ ብዙ ችግር እሳልፎ አሜሪካ ገባ፡፡ አሁን ኑሮው እዚያዉ አሜሪካ ነው፡፡ ገና ሳንጋባ በግልጽ እንደነገረኝ፣ ታክሲ ይነዳል፣ የጽዳት ሥራ ይሠራል። በዚሁ ታታሪነቱ ለቤተሰቦቹም ለራሱም ተርፏል፡፡ ዮናስ ከሰርጋችን አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነበር ስድስት ኪሎ ውልና ማስረጃ ድንገት የተገናኜነው፡፡ የዚያን ቀን ግጥጥሞሸ ይገርመኛል፣ አለቃዬ የሆነ ፋይል እንድታመጣለት ሰናይት የምትባል ቢሮ የምትጋራኝ ሠራተኛ ሊልክ ወደ ቢሯችን ይመጣል። በአጋጣሚ ወጥታ ስለነበር ሲጨናነቅ ሳዬው “በዚያው የምሄድበት ጉዳይ ስላለኝ እኔ አመጣልሀለሁ" ብዬው ፋይሉን ላመጣ ሄድኩ፡፡

ታዲያ ፋይሉን ተቀብዬ ስወጣ ከእንግዳ ማስተናገጃው አካባቢ ስሜ ከኋላ ሲጠራ ሰምቼ ዞር ብል፣ የጠራኝ ሰው ከስንትና ስንት ዓመት በፊት የማውቀው ዮናስ ሆኖ አገኜሁት። እውነቱን ለመናገር መጀመሪያ አላስታወስኩትም _ ነበር፣ ከዕድሜው በላይ ትልቅ ሰው መስሏል፤ ሲናገር ነው ያስታወስኩት፡፡ ከኮሌጅ ጀምሮ ሲናገር ዓይኑን በከፊል ከደን የሚያደርገው ነገር ነበር፡፡ ባልሳሳት ወደ ዐሥራ አምስት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ሳንተያይ ቆይተን ነበር፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ነገራችን ሁሉ ፍጥንጥን
👍466😢2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ስምንት

ሰው ክፍል ይዞ መፋቀር ብቻ ነው እንዴ!? ክፍል ይዞ ቢያለቅስ፣ ኡኡ... ቢልስ!? ...ያም ስሜት ይኼም ስሜት፡፡

ይኼ ሁሉ የሆነው በዚያ በተረገመ ልጅ ምክንያት ነው፡፡ በዚያ በተረገመ ልጅና በተረገምኩ እኔ ምክንያት። ችግሬ ለመናገር በጣም ቀላል ነው፤ ለመኖር ነው የሚከብደው፡፡ በዓለም ላይ እንዳሉ ብዙ ሚሊዮን ሴቶች የማፈቅረውን ሰው ትቼ (ምን እተዋለሁ! በልቤ ተሸክሜ) የማላፈቅረውን ሰው አገባሁ “ወንድን በወንድ ነው መርሳት" በሚል የጓደኞቼ ምክር ጭምር፤ ይኼው ነው ታሪኬ፡፡ በደፈናው ሲታይ በቃ ይኼው ነው? ያስብላል አይደል? ....እኔም እንዲህ ዓይነት ታሪክ፣ ልብወለዶች እና ፊልሞች ላይ ስንት ጊዜ አነበብኩ፣ አዬሁ እና ለምን እንዲህ አያደርጉም? ለምን __ እንደዚያ አይሠሩም? ብዬ _ ምክርና _ ግሳጼ _ ወረወርኩ ...በመምከር ውስጥ ተመካሪውን ደካማ አድርጎ የማዬት ስስ መታበይ አለ፤ ሲኖሩት ግን ሌላ ዓለም ነው፡፡ ሰው በቁሙ ሕልምና ገሃድ የሆነ ሕይወት እንዴት በአንዴ ይኖራል? ባሌ ዮናስ፣ እጄን ሲነካኝ “ፍቅረኛ እንዳለኝ አታውቅም!?''ብዬ በጥፊ ማጮል ያምረኛል፡፡ እዚህ ሌላ ወንድ አግብቼ፣ እዚያ ትቼው መጣሁ ያልኩት ሰው ጋር ፍቅር ውስጥ ነኝ። ትንፋሽ የሚያሳጣ- ፋታ የማይሰጥ ዕልኽ፣ መገፋት፣ አለመፈለግ እና መናቅ የተቀላቀለበት ፍቅር ውስጥ ነኝ፡፡ ከፍቅሬ እኩል ደግሞ አምርሬ እጠለዋለሁ፡፡ የማፈቅረው ሰው አብርሃም ይባላል ደራሲ ነው፡፡ አራት ዓመታት አብረን በፍቅር ቆይተናል፡፡ እና ለምን ተለያያችሁ? ብባል መልስ የለኝም። ስላልፈለገኝ አልል ነገር ለእኔ ሲንሰፈሰፍ ለጉድ ነበር...ብቻ አይገባኝም፤ የሰው ልጅ ምን ዓይነት ውስብስብ ፍጥረት እንደሆነ አይገባኝም፡፡ የሚገባኝ በዚህ ውስብስብ ፍጥረት ቀጥ ያለ የዋህ ባሕሪዬ መሰባበሩ ነው፡፡ ሌላው ይቅርና ይወድሻል ወይስ አይወድሽም? ብባል መልስ የለኝም፡፡ አላውቅም፤ የእውነት አላውቅም፡፡ እዚህ ክንዱን አንተርሶ ያስተኛኝ ባሌ እቅፍ ላይ ሥጋዬን ትቼ፣ ነፍሴ ከምታፈቅረው ሰው ጋር ስትዛብር የምታድር ከንቱ አፍቃሪ ነኝ፡፡ ባሌ እላዬ ላይ በፍቅርና ወሲብ ናውዞ ሲቃትት፣ ያውልኽ ሥጋዬ ብዬ በነፍሴ ወደ ወደድኩት ሰው የምኮበልል ባተሌ ነኝ፡፡ እንዲያ ሲሆን ያላለቀስኩበት ጊዜ የለም፡፡ ባለቤቴ ጥሩ ሰው ነው፤ ይኼን

ጥሩነቱን እንደ ስኒከር ጫማ፣ ስልክና ላፕቶፕ፣ ከአሜሪካ ይዞት የመጣው ሳይሆን፤ ዩኒቨርስቲም እያለን አብሮት የነበረ፣ ከዚያም በፊት አብሮት ያደገ ገራገርነት ነው፡፡ ቤተሰቦቹ በሙሉ ጥሩዎች ናቸው፡፡ ምን ዋጋ አለው... እኔ ላይ ጣለው፡፡ እንዳንዴ የምለው ሰጣ “በጣም ጥሩ ሰው ነሀ!” እለዋለሁ በፍጹም የዋሀነት “ጥሩነቴን አይቶ አንችን ሰጠኝ" ይለኛል፡፡ ይኼ አባባል የክፉዎች መፎክር መሆኑን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው። “ፍቅረኛዬ” አብርሃም ያረገኝን ሁሉ ከደረገኝ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ ስንለያይ እንደዚያ ነው ያለኝ “በጣም ጥሩ ልጅ ነሽ" የይሁዳ አሳሳም ቃል ለብሶ ሲገለጥ እንዲህ ነው፡፡ ምን ማለት ነው ጥሩ ሰው ነሽ?... ስበድልሽ ዝም ብለሽ ተበድለሻል፣ ስሰብርሽ ያለ ድምፅ ተንኮታኩተሽ ወድቀሻል...ስለዚህ አመሰግናለሁ ነው? ...ለምን የበደሉን ያደንቁናል?...ለምንስ የሚያደንቁን ይበድሉናል!? ባሌ ዕረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሊመለስ ሲዘጋጅ፣ በመለያዬታችን እንደ ሴት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ በማልቀሱም ብቻ ሳይሆን ሰርጋችን ሁለት ቀን ሲቀረው ያደረኩትን አውቃለሁና በጸጸት አብሬው አለቀስኩ፡፡ በእርግጥ ከዚያም በፊት ከጋብቻችን በፊት፣ለጋብቻ ጠይቆኝ እሺ ካልኩበት ቀን ጀምሮ እሱ ለሰርግ ሲዘጋጅ እኔ ታማኝ አልነበርኩም፡፡ አንዳንዴ ዮናስ ጋር ተኝቼ አብርሃም ከደወለልኝ እየተጎተትኩ ሄጄ በሰዓታት ልዩነት እሱም ጋር እተኛለሁ። ባከንኩ። ተዝረከረኩ። ቆሸሽኩ። ታዲያ እገረም የነበረው፤ ለዓመታት የወደደውን ያለ እሱ ማንም ነክቶት የማያውቀውን ገላዬን ሌላ ወንድ እንደነካው እንዴት አያውቅም እያልኩ ነበር። የመጨረሻዋ አለመታመን ግን እንደ ደረቀ እንጨት ቅስሜን ቀሽ አድርጋ የሰበረች አለመታመን ነበረች፡፡ አለመታመኔ ደግሞ ሰይጣን አሳሳተኝ የሚባል ዓይነት ድንገተኛ ነገር አልነበረም፡፡ ሰይጣን ራሱ ጅራቱን ሸጉቦ እና ጉዴን ላለመስማት ጆሮውን በሁለት እጁ ደፍኖ፣ የፈረጠጠበት አለመታመን ነበር፡፡ የሚያንገበግበኝ ያ የመጨረሻው ነው፡፡ አለመታመንም ዓይነትና ደረጃ ይኖረው ይሆን?...እንጃ! በስድስት ሚዜ እና በአንድ ሾፌር መኻል እንደ ነፋስ አልፎ አመንዝሮ መመለስ።

ፈጣሪ ራሱ ከማመንዘሬ በላይ፣ ለማመንዘር የሄድኩበትን መንገድ በግርምት መዝግቦ የሚያስቀምጠው ነው የሚመስለኝ፡፡ ሰርጌ እሑድ ሆኖ አርብ ቀን ጸጉር ቤት ከሚዜዎች ጋር ሄድን፤ ጸጉሬን የሚያጥበት ልጅ የራስ ቅሌን በጣቶቹ 'ማሳጅ ሲያደርገኝ ነበር አእምሮዬ በአንዴ በናፍቆት የተሞላው። አብርሃም ከጡቶቼ ቀጥሎ ጸጉሬን የሚወደው ይመስለኛል፤ እንደዚያ ብሎኝ አያውቅም ግን - ይመስለኛል፡፡ ሁልጊዜ ጎን ለጎን ተቀምጠን ወይም ተኝተን፣ በጣቶቹ ጸጉሬን ማበጠር የሚወደው ነገር ነበር። በጸጉሬ መጫወት... ዓይኖቹን ጨፍኜ ጣቶቹ በጸጉሬ ውስጥ ሲሽሎከለኩ የሚሰማኝ ደስታ ...ስንት ቀን በዛው እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወስዶኛል...እና ጸጉሬን የሚያጥበኝ ልጅ ጣቶቹ በጸጉሬ ውስጥ ሲርመሰመሱ፣ እንደ ወተት የሚንጥ ናፍቆት ሞላኝ፡፡ ቀስ በቀስ አልነበረም. በአንዴ። ምንድን ነው እንደዚያ ያደረገኝ? አንገቴን ወደፊት ቀና አደረግሁ:: “እሳመምኩሽ?'' አለኝ ልጁ፡፡ አላሳመመኝም ቀድሜ የታመምኩ እኔ‐ በሽታዬን ነው Pyha:: ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ሚዜዎቼ እዚያና እዚህ የሚወራወሩት ቀልድ እና ሳቅ ሳይሆን፤ የትዝታ ጅረት ነበር በመላ አካሌ የሚፈሰው... የሚጮኸው። በቃ የመጨረሻሽ ነው የሚል ድምፅ ነው በጆሮዬ የሚያንሾካሹከው። ጸጉሬን ተሰርቼ እንደጨረስኩ ቀጥ ብዬ ወጣሁና ራቅ ብለው በሰልፍ ከቆሙት ላዳ ታክሲዎች ወደ አንዱ ሄጄ..ላፍቶ ኮንዶሚኒዬም አልኩት፤ መንገድ ጀምሬ ነበር ለአብርሃም የደወልኩለት...ቤት ጠብቀኝ ብዬ....ወደ ቤቱ በቀረብኩ ቁጥር ልቤ ደረቴን ሰንጥቃ የምትወጣ እስኪመስለኝ ጭንቀቴ የተለዬ ነበር። ሰውነቴ በሙቀት ይቃጠላል፣ለራሴ እያበድኩ እስኪመስለኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፍቶኝ ነበር። ባለታክሲውን አዙረU መልሰኝ ለማለት ሁለት ሦስት ጊዜ እየቃጣሁ ከአፌ ቃል ማውጣት አልቻልኩም። የኮንዶሚኒዬሙን ደረጃ ስወጣ፣ እግሬ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ በሩን ሲከፍትልኝ ተዝለፍልፌ መውደቅ ነበር የቀረኝ፣ በውስጤ እባክህ አይሆንም በለኝ እላለሁ ... እባክህ ....እንደዚያ እያልኩ ግን እቅፉ ላይ ወደቅሁ፡፡ እኔስ እሺ በቃ የመጨረሻው

የሴትነት ክብሬን አለቅልቄ የደፋሁ ከንቱ ሆኜ ነው፤ አራት ዓመት አብሮ የቆዬ ፍቅረኛ የፈለገ ወንድ ቢሆን የቱንም ያኽል ስሜታዊ፣ ሰርጓ ሁለት ቀን የቀረው ሙሽራ መጥታ እግሯን ስለከፈተችለት እንዴት ዘው ይላል!? ያውም የማያፈቅራት ሴት። ማንንም ለመውቀስ አይደለም፤ በልቤ “አይ! አይሆንም” እንዲለኝ ግን ምኞቴ ነበር፡፡ አልዋሽም እንደዚያ ቢለኝ፣ ያንንም ከመገፋት ቆጥሬ የሰርጌ ቀን ማታ ባሌን አስተኝቼ ልሄድ እችል ይሆናል ...
👍404
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ዘጠኝ

ቤቱ!

ያ ቤቱ የእኔ ገነት ነበር፣ ቤቱን እወደዋለሁ። የእሱ የሆነውን ነገር ሁሉ እወዳለሁ፡፡ ዛሬም ድረስ ያ ቤቱ እንደ ሰው ይናፍቀኛል። ላፍቶ የሚባል ሰፈር ከተሠሩ የኮንዶሚኒዬም ሕንፃዎች በአንዱ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ነበር የሚኖረው። ንጹህ ቤት ... ሲበዛ ንጹህ፣ ሰላም ያለው ቤት ነበር። እንደ እሱ ቼልተኛ ነፍስ ካለው ወንደላጤ የማይጠበቅ። በተለይ በተለይ የ “ሲዲ ፕሌየሩ” ነገር፡፡ ስለዚህ ነገር ለጓደኞቼ ሁሉ አውርቼ አልጠግብም፡፡ ዞር ስል አካበደችው ይሉ ይሆናል፣ ግን እስከአሁን የትም አይቼው የማላውቀው “ሲዲ ፕሌየር'' እዚያ ቤት ነበር። ወደጎን ሁለት ሜትር የሚሆን ቦታ ይዞ በሞገስ የተቀመጠ፣ አራት ትልልቅ ስፒከር ያለው፣ ከትልቅነቱ ብዛት አንድ ላይ ለማስቀመጥ ቦታ ስላልበቃው አንዱን ስፒከር ለብቻው በመስኮቱ በኩል አስቀምጦታል፡፡ አንዳንዴ ይኼን “ስፒከር' እንደ ወንበር ሲቀመጥበት “እንዴ! ልትሰብረው ነው እንዴ?” ብዬ ጎትቼ አስነሰዋለሁ፡፡ እስቲ እዚያ ባዶውን የተቀመጠ ሰፋ እያለ፣ የቴፕ ስፒከር ላይ መቀመጥ ምን የሚሉት ነገር ነው? ተቀምጦ ቁም ነገር የሚሠራ አይመስልም!? በመስኮት ያንን ኮብል ስቶን የተነጠፈበት ደባሪ የመኪና ማቆሚያ ለማዬት፤ ሁልጊዜ እናቱ ገበያ እንደሄደችበት ሕፃን በመስኮት ውጭ ውጩን ማዬት ይወዳል፡፡ነፍሱ ምን እንደሚናፍቅ እንጃ። “ሲዲ ፕሌየሩ” 'ልጃችን ነገር ነበር የሚመስለኝ። እኔና እሱ ተጋብተን “ሲዲ ፕሌየር” የወለድን። መስኮ መስኮቱ ሰፊ ስለሆነ መጋረጃው ሲሰበሰብ ቤቱ በብርሃን ተጥለቅልቆ በረንዳ ይመስላ ስላል፤ ሁልጊዜ መጋረጃውን ጋርጄ መብራት አበራለሁ፤ እንደዚያ ሲሆን የሆነ "ኮዚ' ይሆናል። የመስኮ የመስኮት መጋሪ ጋሚመለከት ሰውም ም ይጨንቀኛል፡፡ መጋረጃ

የመጀመሪያ ቀን እቤቱ ስሄድ ዓይኔ ያረፈው እዚያ “ሲዲ ፕሌየር” ላይ ነበር። አለ አይደል ለሁሉ ነገር እንስፍስፍ ላለመባል “ይኼ ነገር ያምራል!” በሚል ልዩ? አስተያዬት ባልፈውም ስለ አብርሃም ቤት በሰብኩ ቁጥር ስለዚያ እቃ ያላሰብኩበት ጊዜ የለም፡፡ ድምፁ የማይታመን ነው፤ ስንት ዓመት የሰማኋቸው ዘፈኖች እሱ በት ስሰማቼው ተዓምር ይሆኑብኛል። ምንድን ነው? ማለቴ ባለ አንድ መኝታ ቤት ኮንዶሚኒዬም ውስጥ የሆነ ትልቅ የሙዚቃ ስቱዲዮ ውስጥ የሚገኝ ዓይነት የሙዚቃ ማጫወቻ እቃ መገኜቱ? እና... እኔ ሙዚቃ ሁሉ ነገሬ የሆንኩ - እኔ እዚያ 07號? መጀመሪያ የመሰለኝ፣ በቃ ለሙዚቃ የተለዬ ፍቅር ያለው ነበር፤ እየቆዬን የገረመ˘ ነገር ያንን የሚያክል “ሲዲ ፕሌየር” ጭራሽ ቤቱ ውስጥ እንደሌለ ዓይነት አያስታውሰውም ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ እንኳን “ሲዲ” በቤቱ አልነበረም። በቃ ዘፈን አያዳምጥም፣ ሃይማኖተኛ ሆኖ ነው እንዳልል መዝሙርም አያዳምጥም ...ባለ አምሳ ስምንት ኢንች ፍላት ስክሪን ቲቪ አለው፡፡ ግድግዳው ላይ የተሰቀለ፣ እሱንም ከፍቶት አያውቅም፡፡ ዝም ያለ ጉድ፡፡ “እና ቤት ዉስጥ ስትሆን ምን ትሠራለህ ?'' አልኩት ተገርሜ፣ “አነባለሁ ፣ እጽፋለሁ ፣ እና ምግብ እሠራለሁ ... !

" ምግብ!?"

“አዎ! ምግብ ...ደስ ይለኛል ምግብ መሥራት፣ ያን ያኽል ባለሙያ ባልሆንም...” እንደመደንገጥ አልኩ፡፡ ስለ ምግብ ማብሰል ሲነሳ ሁልጊዜ እደነግጣለሁ፡፡ ብዙም ስለ ምግብ ወሬ ማውራት አልፈለግሁም፡፡ ምክንያቱም የሙያ ነገር አይሆንልኝም ነበር። ምግብ ላይ ጥሩ ባለሙያ አልነበርኩም። ብዙ ደክሜ የሠራሁት ምግብ መንም ምንም አይልም፡፡ ወንድሞቼ ከእኔ የተሻለ ጎበዞች ነበሩ፡፡ እንደ ቀልድ ግብ መሥራት ትወዳለህ፣ መጻፍ ትወዳለህ... ሌላ ምን ትወዳለህ?'' አልኩት፣ ጨዋታ ለማስቀዬር፡፡

ሴት!" አለኝ ፡፡ አባባሉ ዳል ፎርማል ነገር እንደተናገረ ዓይነት ቀለል አድርጎ ነበር የተናገረው. ወይስ ኖርማል ነው? ከዚያም በኋላ በወሬ ወሬ ስናነሰው አይደብቅም እዚህ ቤት መ ት ግን እንቶን ብቻ ነው አለኝ። አመንኩት! የማለው ምክንያት አልነበረኝም፤ በፈለግሁት ሰዓት እንድሄድ የቤቱን ቁልፍ ሲሰጠኝ መቼም በራሱ ቢተማመን ነው። ያቺን ቁልፍ የሰጠኝ ቀን የገነት መግቢያ ቁልፍ የተሰጠኝ ያኽል በደስታ አብጄ ነበር፤ ዛሬ ላይ እሱን የሚያስታውስ እጄ ላይ ያለ ብቸኛ ቁስ ቢኖርያ ቁልፍ ብቻ ነው። ብዙ ሴቶች ማወቁ ደስ አላለኝም፡፡ መቼም ድንግል እንዲሆን ባልመኝም ይኼ ነገሩ ግን ደስ አይለኝም ነበር፡፡ ደግሞ እገረማለሁ አብረን በነበርንባቼው አራት ዓመታት፣ አንድም ቀን ከዚያ በፊት ስለሚያውቃቸው ሴቶች አውርቶልኝ አያውቅም፡፡ ለምን እንደሆን እንጃ እንዲነግረኝ እፈልግ ነበር፤ግን በቀጥታ ጠይቄው አላውቅም፡፡ እንዴት ሊረሳቼው ቻለ? እላለሁ በውስጤ - ልክ እንደሌሉ እንዳልተፈጠሩ እንዴት ረሳቼው? በሆነ አጋጣሚ በወሬ መካከል እንኳን እንዴት አንዷ ስላደረገቸው፣ ስለተናገረችው፣ ወይም አብረው ስለሄዱበት ቦታ አያነሳም? ...እኔንም እንደዚሁ ይሆን የሚረሳኝ? ታዲያ ከተለያዬን ከአራት ዓመት በኋላ መጽሐፍ አሳተመ ሲባል ተጣድፌ ገዛሁ፤ እኔን ራሴን የሆነ ቦታ በሆነ መንገድ ጽፎኝ ከሆነ ለመፈለግ፡፡ያ ያሳለፍኩት ጊዜ በዉስጤ የፈጠርኩት ቅዠት እንዳልነበር ምስክር ፍለጋ፡፡ ሳያዉቀኝ በፊት የጻፈኝ የመሰለኝ ሰው ካወቀኝ በኋላ ረስቶኛል፡፡ ስሜን ከእነ ቤት ቁጥሬ ይጻፍልኝ ማለቴ አልነበረም፤ ግን ደራሲዎች ባለፉበት መንገድ ስላዩት ዛፍ አይጽፉም? ስለቀኑ ደመናማነት አይጽፉም? መንገድ ዳር ስለተቀመጡ ጫማ ሰፊዎች አይጽፉም? ቡናቼዉ ዉስጥ ስለገባችዉ ዝንብ አይጽፉም? ከነዚያ እንደ አንዱ መንገደኛም ቢሆን ሲያልፍ አላዬኝም?! የሆነ ሆኖ "ሲዲ ፕሌየሩ" የቤቱ ልብ ነበር- ለእኔ። ለዚያ ነው የምወዳቼውን “ሲዲዎች ሁሉ እሱ ጋ የማስቀምጣቼው የነበረው፡፡ ያ ቤቱ ከረብሻዬ ሁሉ የምደበቅበት ዋሻዬ ነበር፡፡ እና የረሳሁት ነገር

“ኪችኑ' ውስጥ ትልልቅ ምግብ ቤቶች የሚጠቀሙበት ዓይነት የኤሌክትሪክ “ስቶቭ ነበረው፡፡ “ደግሞ ይኼ ምን ይደርግልኻል?" አልኩት ተገርሜ፡፡ በትክክል የምን ኤምባሲ እንደሆነ እንጃ ብቻ እዚያ የሚሠራ ጓደኛው ኤምባሲ ዕቃ ሲቀይር "ሲዲ ፕሌሩን እና ስቶቩን” ገዝቶ እንዳመጣለት ነገረኝ። ያንን “ስቶቭ” የጎሪጥ ነበር የማዬው ሙያ ስለሚባል፣ እኔ ስለማልኖርበት ሌላ የሴት ዓለም ያስታውሰኛል። የተበደልኩበት ሌላ ጉዳይ... የሴት ልጅ ሙያ የሚሉት ነገር አልነበረኝም፤ ምግብ ማብሰል፤ ቡና ማፍላት፤ ጓዳ ውስጥ ጉድጉድ ማለት... ምንም! መርመጥመጥ ምን ያደርግልሻል እየተባልኩ ነው ያደግሁት፡፡ እሺታን እንደ እምቢታ! እናም አግባኝ አልኩት መልሱ የሚገርም ነበር “እሺ!'' ነበር ያለው “እሺ!'' ፊቱ ላይ ምንም የተለዬ ስሜት አልነበረም፡፡ አልተገረመም፣ ፈገግ አላለም፣ አላዘነም፣ ቅሬታ ወይም ማንገራገር አልነበረም፣ ምንም የለም “እሺ!'' አባባሉ፣ ለእኔ ብቻ የሚገባ “እምቢ!'' ነበር፡፡ በደስታ ይፍለቀለቃል ብዬ አስቤ ነበር፤ ያቅፈኛል ብዬ አስቤ ነበር፤ መቼ እናድርገው? ብሎ ይጠይቀኛል ብዬ ነበር፤ እኔም ከነገ ዛሬ እጠይቅሻለሁ ብዬ ሳስብ ቀደምሽኝ ብሎኝ እንሳሳቃለን ብዬ አስቤ ነበር፤ ከዚህ ሁሉ ሐሳብ አልፌ ለአባቴ እንዴት እንደምነግረው እያሰብኩ ነበር ጥያቄዬን ያነሳሁት። እሺ! በሚል መጠቅለያ እምቢታውን አቀበለኝ፡፡ ብዙ ሴት ጓደኞቼ ለጋብቻ ሲጠዬቁ አይቻለሁና የሚገባኝ አንድ እውነት አለ፤ ወንዶች ሥጋቼው ለአንድ ደቂቃ ተንበርክኮ ለጋብቻ እንዲጠይቀን ነፍሳችን
👍47🥰3😱32
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስር


“በቃ ጨረስን!'' አለ ዶክተሩ፡፡ ያ ቃል በዚያ ቅጽበት እፎይታ የሚሰጥ ቃል ነበር። ሲቆይ ግን ምንጊዜም ጆሮዬ ላይ የሚያቃጭል ረባሽ ቃል ሆኖ ቀረ... እስከ ዛሬ! ምንድን ነው መጨረስ?...ጨረስን! ...እኛ ማነን? ...እኔና ዶክተሩ ...ምን የጋራ ጉዳይ ኖሮን ነው “ጨረስን” የሚለኝ?... በሕይወታችን ውስጥ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች አሉ፤ ችግሮቹ፣ ጠባሳዎቹ የእኛ ሆነው ሌሎች በሙያቼው አልያም በገንዘባቼው ብቻ አግዘውን እጃቼውን ታጥበው ሲሄዱ እኛ ዕድሜ ልካችንን ተሸክመናቼው የምንኖራቼው፡ ዶክተሩ እንዳለው አላለቀም ነበር፤ እንዲያውም ጀመረ። በዶነት ከአእምሮዬ ወደ ሰውነቴ ወረደ፣የተሟላ ባዶነት! በአካልም በመንፈስም! ውስጤ እንደ ፊኛ በአየር የተሞላ ይመስል ቀለለኝ።ሰዎች ሁሉ የሆነውን የሚያውቁ ባደረግሁት ነገር የናቁኝ መስሎ ይሰማኝ ጀመር። በሬዲዮ ይሁን በጋዜጣ ወይም በጨዋታ መኻል ስለ ማስወረድ ስለ እርግዝና ሲወራ፣ የአገር ድብርት ይጫነኛል፣ መንፈሴ ይረባበሻል፡፡ በመንፈሳዊ ትምህርትም ሆነ ስብከት፣ ስለማስወረድ ኃጢያትነት ሲነገር ነፍሴ በእሳት ጅራፍ ትገረፋለች፤ ደግሞ ማድመጥ ስለጀመርኩ ነው መሰል ወሬው ሁሉ፣ ስብከቱ ሁሉ፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ሁሉ ማስወረድ የሚል ቃል የተሞላ ሆነብኝ፡፡ የሆነ ከባድ ሚስጥር እንደያዘ ሰው ወሬዬ ሁሉ በጣም በጥንቃቄ ሆነ፡፡ እንኳን ወሬ ሳወራ ስስቅ በጥንቃቄ ነበር፡፡ ምንድን ነው ከውስጤ ያወጡት? እስከምል ሁሉም ነገሬ ተወስዶ ነበር፡፡ እንደሆነ ባዶ በርሚል ምናምን፣ ወደ ውስጤ ብጮኽ የገደል ማሚቱ የሚያስተጋባ እስኪመስለኝ ኦና ሆኜ ነበር! ሃይሚ በብዙ ልታጽናናኝ ትሞክራለች “እንትናን ታውቂያታለሽ? ያቺ እንኳን የእንትና ገርል ፍሬንድ? እንትን እንኳን የምትሠራው?...እሷ ሦስት ጊዜ ነው ያስወረደችው፣ ተራ ነገር'ኮ ነው፡፡ እንትናስ? አሁን አግብታ እንግሊዝ የሄደችው? በአራት ወሩ አስወጥታለች ...'' አንዳንድ ነገሮች አሉ ዐሥር ጊዜም ተሠሩ፣ አንድ ጊዜ ዋጋቼው እኩል የሚሆን፤ ሃይሚ ያልገባት ይኼ ነው። ቁጥር ምንድነው? ሁለት ወር ይሁን፣ ዘጠኝ ወር ፅንስ ምን ልዩነት አለው? ሰኞ ልሙት ዓርብ፣ ሟች ያው ማኅደረ ሰላም ነኝ፡፡ የመሞቻ ቀን መቅደምና መዘግዬት የሟችን ማንነት አይቀይረውም።

ብደጋግመው እላመደው ይሆናል እንጂ፤የነገሩን መሠረታዊ እውነት አልቀይረውም:: እውነቱ ግን ተፈጥሮ፣ ወላ እግዚአብሔር ውስጤ በአደራ ያስቀመጡትን ፅንስ ገድዬዋለሁ፡፡ ምክንያቴ ምን ነበር?... ማሳደግ ስለማልችል?...አይደለም! የጤና እክል ስላለብኝ?... አይደለም!... ራስ ወዳድነት ነው፡፡ ሳላገባ ወለድኩ እንዳልባል፣ ከማያፈቅረኝ ሰው ወለድኩ እንዳልል ...አባቴ እንዳያዝን!...አዎ አባቴ እንዳያዝን ልጄን መግደል! ወይም እኔ እንጃ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በጋዜጣ፣ በየመድረኩ “በሕገ-ወጥ መንገድ ፅንስን ማስወረድ ...በሕጋዊ መንገድ ፅንስን ማስወረድ ..." እየተባለ ሲነገር ግርም ይለኛል፡፡ የተፈጥሮን ሕግ የሚጻረር ሕጋዊነት እንዴት ያለ ነው? ከዚህ አጋጣሚዬ የተረዳሁት የትኛውም ሕጋዊነት ከከፋ የጤና ስጋት ሴቷን ይታደግ ይሆናል፤ ከማስወረድ በኋላ ከሚኖረው የሥነ-ልቦና ጉዳት የሚታደግ ሕግ ግን የለም።ነገሩን ቀለል ለማድረግ የሚጠቀሙበት ብዙ መንገድ በኋላ የደረሰብኝን ከባድ የሥነ-ልቦና ጉዳት እንዳልገምት አድርጎኝ ነበር፡፡ ከማስወረዴ በፊት ጓደኛዬ ሃይሚ ስታጽናናኝ ያለችኝን አልረሳም “ፅንስ እንጂ፣ ልጅ አይደለ!?...'' ፅንስ ማስወረድ የሚለው አገላለጽ፣ ልጅ ማስወረድ ሆኖ እንዳይታዬኝ ማን ነበር የቃል ጨዋታ የቀመረው...? እንዲያዉም ፅንስ ማቋረጥ እኮ ነዉ ያሉኝ፡፡ እንግዲህ ሰዉ ሳይሆን ሰዉ የሚሠራበትን ሂደትን ነዉ ያቋረጥነዉ አይዟችሁ መሆኑ ነዉ፡፡ፊልም ወይንም “ሶፍትዌር' ምናምን ስንጭን ሳይጨርስ ብናቋርጠዉ “አቦርት' ሆነ እንደሚለን የኮምፒዩተር ቋንቋ፣ ከመሐፀንናችን ልጆቻችንን ስናስወርድ አንድ ቀላል ሂደት ያቋረጥን እንዲመስለን “አቦርሽን' የሚል ተመሳሳይ ቃል አስታጠቁን፡፡ ተቀብለን ፅንስ ማቋረጥ እንላለን፡፡ እንኳን ፅንስ ጠብታ ደማችን ዉስጥ ሙሉ ባይሎጂካል ማንነታችን እንዳለ የነገሩን እነሱ አልነበሩም? ሙሉ ማንነቴ ነዉ የተወሰደዉ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ የሃይማኖት ሰዎችን እና የመንፈሳዊ ወሬ በሩቁ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ እግዚአብሔር ብዬ መጥራት አፌ ላይ ከበደኝ፡፡ በምድር ላይ እንደ እኔ ዓይነት ኃጢያተኛ ያለ መስሎ እስከማይሰማኝ ራሴን ተጸዬፍኩት፣ ጠላሁት፡፡ ከሁሉም

ልቤን የሰበረው፣ ከሕፃንነቴ ጀምሮ አንድ ዓመት እንኳን አልፎኝ የማያውቅ ልማድ ነበረኝ፣ አባቴ ጋር ሆነን ለጥምቀት የልደታን ታቦት መሸኜት “ለልደታ ሴት ልጅ ከሰጠሽኝ በየዓመቱ ላንቀር ብዬ ተስያለሁ" ይላል የአንድ ዓመት ልጅ ሆኜ ነው አቅፎ የወሰደኝ፤ ያኔ ነበር የጀመርነው፡፡ ወንድሞቼ ጋር እንኳን አይሄድም። የሁሉም ዓመት ፎቶ አለን፤ ለአባቴ የተለዬ ትርጉም የሚሰጡ ፎቶዎች፡፡ አቤት እነዚያን ፎቶዎች ሲመለከት ፊቱ ላይ የሚበራው ብርሃን! ...ያ የአባቴ ኩራት ነበር፡፡ በዚያ ዓመት የጥምቀት በዓል ሊከበር ቀናት ሲቀሩት፣ ከባድ የመንግሥት ሥራ አለብኝ በሚል ሰበብ አባቴን አሳምኜ የዕለቱ ዕለት ሃይሚ ቤት ሳለቅስ ውዬ፣ ሳለቅስ አደርኩኝ፡፡ ያን ያኽል ሃይማኖተኛ ባልሆንም ልደታን እወዳታለሁ፡፡ ስመለስና የልደታን ጉልላት ሳይ፣ ማረፊያ ሜዳው ላይ የትም ዞሬ ወደ ሰፈሬ እንደ ደረሰ አውሮፕላን መንፈሴ ለእረፍት ይንደረደራል፡፡ አንዳንዴ በዚያ በኩል ሳልፍ፣ ዝም ብዬ ገብቼ ግቢው ውስጥ ቁጭ ስል ይሰማኝ የነበረው ሰላም ልዩ ነበር። ያጣሁትን ሰላም የምፈልገው እዚያ ልደታ ግቢ ነበር፣ ያንን ሁሉ ነው ከውስጤ ፅንስ ነው ብዬ ያስወጣሁት፤ ከነኃጢያታችሁ፣ ከነሸክማችሁ ኑ! መባሉን እየሰማሁ ባድግም፣የራሴ ሸክም ክፉኛ ወደ ኋላ ጎትቶኝ ልደታን በሯን መርገጥ ፈራሁ፡፡ በዚያ ሳልፍ ጉልላቷን ቀና ብዬ ማዬት እንኳን ከበደኝ። ፍርሃቴ ቀላል አልነበረም፤ ጭል ጭል የሚል እምነቴ ከማሕፀኔ በግዴለሽነት በነፈሰ ነፋስ ድርግም ብሎ ጠፋ። ጨለማ ነበር የዋጠኝ፡፡ ይኼ ሁሉ ዶክተሩ “ጨርሰናል!'' ካለባት ቅጽበት የጀመረ የነፍሴ ረብሻ ነበር።

ማቄን ጨርቄን ሳልል ...

በዚያ ስቃይ ውስጥ እያለፍኩ አብርሃምን አልራቅሁትም። በደወለልኝ ቁጥር ተንደርድሬ እቤቱ ነበርኩ፡፡ ወደ ቤቱ ስሄድ እንደ አክርማ ልቤ ለሁለት ይሰነጠቃል፣ ወደ ኋላዬ በመመለስና ወደሱ በመሄድ፤ ስቃዩ በአካል በስለት የመሰንጠቅ ያኽል

የሚያም ነበር፡፡ አስታውሳለሁ አንድ ቀን በጭራሽ ቤቱ መሄድ የለብኝም ብዬ ወሰንኩ፤ በደወለልኝ ቁጥር እሱ አልጋ ላይ የምገኘው ሴተኛ አዳሪ ነኝ ወይ አልኩን እልኽ ከእግር ጥፍሬ ጀምሮ እስከ ራስ ጸጉሬ አንቀጠቀጠኝ... በጭራሽ! አልኩ! ሲደውል ግን ወደ ላፍቶ የሚሄድ ታክሲ ላይ ራሴን አገኜሁት... ወደ እሱ ቤት፡ ከራሴ ጋር ትግል ጀመርኩ። እዚሀ ወርጄ መመለስ አለብኝ...እዚያጋ...እያልኩ ላፍቶ ደርሽ ወረድኩ፡፡ ቆሜ የኮንዶሚኒዬሙን ግራጫ ሕንጻ ለደቂቃዎች ተመለከትኩ፣ ምንድነው እዚያ ብሎኬት ክምር ውስጥ ያለው? ተመለከትኩ! ራሴ ጋር ግብግብ ገጠምኩ፤ እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አሸንፌ የሚመለስ ታክሲ ውስጥ ዘልዬ ገባሁ። አቤት የተሰማኝ እርካታ!...ከሆነ አውሬ ያመለጥኩ ያኽል፣ ከንፈሬ እየተንቀጠቀጠ ዕንባ ተናንቆኝ ነበር፡፡ ልክ ሜክሲኮ ደርሼ ስወርድ ግን ስልኬ ጮኸ፣ አብርሃም ነበር፣
👍359
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አንድ


በገጽ 113 እና 114 መካከል ምን ተደብቋል?

ጓደኛዬ ሃይሚ የማታውቀው ገጣሚና ደራሲ የለም (ገጣሚና ደራሲ ይለያያል ወይስ አንድ ነው? እኔ እንጃ! ብቻ እንደዚያ ነው የሚሉት) እንደ እሷ ድንገት ተነስቶ ግጥም የወደደ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ የግጥም ዝግጅት አለ በተባለበት ሁሉ አዲስ ጸበል ፈልቋል እንደተባለ በሽተኛ መሮጥ ነበር ሥራዋ፤ ወደ እንደነዚህ ዓይነት ቦታዎች ስትሄድ የምትዘንጠው አዘናነጥ ሰርግ ቤት ያስንቃል፡፡ አጭር ናት፣ ራሷም እንደምትለው መልክ አላደላትም፤ ውበቷ ዓይኖቿ፣ጥርሷና እግሯ ላይ ያቆማል፤ ሳቋ በግድ ያስቃል፣ ዓይኖቿ አያርፉም፡፡ ሁልጊዜ ነፍሷ የሆነ ነገር እንደፈለገ ነው፡፡ ትውውቃችን ገና ከሕፃንነታችን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር፤ አውቃታለሁ እላለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት የሚሉት ጋብዛኝ እዚያው በጸበልሽ ብያታለሁ። ግጥም፣ ልብ-ወለድ የሚሉት ነገር ምኑም አይስበኝም፡፡ ነገሩ ማንበብ ላይ ሰነፍ ሆኜ አልነበረም፤ እንዲያዉም ግለ-ታሪኮችንና በሙያዬ ዙሪያ የተጻፉ መጽሐፍትን፣ አሳድጄ ነበር የማነበው። ልብ-ወለድ፣ በአጋጣሚ እንኳን በሬዲዮ ሲተረክ ከሰማሁ ለወራት _ ከአእምሮዬ_አይወጣም፡፡ ታሪኩን ሳወጣና ሳወርድ፣ በቁም ነገር ሳዝንና ስደሰት እሰነብታለሁ፡፡ እንደ ፈጠራ ሥራ ቀለል አድርጌ ማዬት አልችልም። ያንን ስሜት ደግሞ አልወደውም። ሃይሚም ብትሆን ከእኔ ብዙም አትለይም ነበር፤ እንዲያውም እውነቱን ለመናገር ንባብ ላይ ብዙም አልነበረችም፡፡ ይኼ የግጥም ፍቅሯ ድንገት የሆነ ጊዜ የጀመረ ነበር። ከ “ኤለመንተሪ” እስከ “ሀይስኩል” በኋላም አብረን ኮሌጅ ስንማር ስለ ልብስ እና ጌጣጌጥ እንጂ ስለ ግጥም ስታወራ ሰምቻት አላውቅም ነበር። ታዲያ እንዲህ እንዲህ ያለው ቦታ ጋብዛኝ አልሄድም ስላት “ኋላ ቀር” ትለኛለች፡፡

አንድ ሁለት ጊዜ የሙዚቃ ዝግጅት እንድንሄድ ለምኛት እንቢ ስላለችኝ “ኋላ ቀር እዚያ ሄደሽ የሽማግሌዎች ተረት ስሚ" ብያታለሁ።አንዳንዴ ጓደኝነታችን ይገርመኛል፡፡ በጋራ የምንወደው ነገር “ፒዛ” ብቻ ይመስለኛል፡፡ እኔ ወድጄው ያልጠላችው፣ እሷ ወዳው ያልጠላሁት ነገር የለም። ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እቤቷ ከሰበሰበቻቼው መጽሐፎች የሚበዙትን የደራሲያኑ ፊርማ ያለባቼው ስለነበሩ እንደ ቅርስ ነበር የምታያቼው፡፡ ለሰው አታውስም፣ በበኩሌ መጽሐፍ የደራሲው ፊርማ ኖረበት የመጽሐፍ አዟሪው፣ ልዩነቱ አይገባኝም ነበር። ሃይሚ ስለ ማንበብ ጥቅም ብዙ ብዙ ስትለኝ ምን እንዲህ ቀዬራት? እያልኩ በግርምት አያታለሁ፡፡ በተለይ አንድ ሰሞን ወደ ስብከት የሚቀራረብ “ዲስኩር† ነበር _ የምትደሰኩርብኝ፡፡ _ ታዲያ በአንገቴ ገመድ ቢገባ ከቤቴ አይወጡም የምትላቼውን መጽሐፍት፣ ካላነበብሽ እያለች ስትሰጠኝ ጉዱን ልዬው ብዬ ልብ ወለድ ማንበብ ጀማመርኩ። አንዳንዱን በጣት የሚቆጠር ገጽ እንኳን ሳላነብ እመልስላታለሁ፤ አንዳንዶቹን በስንት ትግል ዐሥራ አምስት ቀንም፣ ወርም ወስዶብኝ እጨርሳቼዋለሁ። እንዲህ ስንነታረክ ነበር አንድ መጽሐፍ ያዋሰችኝ፡፡ ያንን መጽሐፍ በጣም ነበር የወደድኩት፤ ታሪኩን ከመውደዴ የተነሳ በሦስት ቀናት ነበር አንብቤ የጨረስኩት። ሃይሚ ያንን መጽሐፍ ስታውሰኝ በጣም እንደወደደችው እና ሁለት ጊዜ እንዳነበበችው አጋና ነግራኝ ነበር፡፡ የመጽሐፉ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የደራሲው ፊርማ እና “ከአክብሮት ጋር ለሃይማኖት ዳኛቸው የተሰጠ” የሚል ጽሑፍ በጥቁር እስክርቢቶ ተጽፎበታል፤ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ስለ አንዲት በአደጋ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዋን ስላጣች ሴት ነበር፡፡ ይህቺ ሴት የአምስት ዓመት ልጇንም _ ነበር _ የረሳችው፤ ልጅቱ ሕፃን ናትና ችግሩን አትረዳም፡፡ እናቷን እንደወትሮው ለመቅረብ የማታደርገው ጥረት የለም፡፡ እናት ግን በየቀኑ ትረሳታለች ፤ በዚያ ላይ በጣም ቁጡ እናት ሆና ነበር...መጽሐፉ ሲበዛ አሳዛኝ በመሆኑ ላለማልቀስ እየታገልኩ ነው ያነበብኩት፡፡ እስካሁን ያ ታሪክ ድርሰት

ነው ቢሉኝ አላምንም፤ የሆነ ነፍሴ ውስጥ ተሰንቅሮ ቀርቷል።ያቺ ሕፃን እኔ ነኝ፤ የተረሳሁ፣ የሚገፋኝን፣ የረሱኝን ሁሉ እግራቼው ሥር እየወደቅሁ እንዲወዱኝ የመማጸን፤ እኔ ነኝ። ሰልነግረው የተረዳኝ ሰው ያገኜሁ መሰለኝ፡፡ ደራሲዉ እኔ ራሴ የሆንኩ መሰለኝ፤ የሆነ ተናግሬም፣ አልቅሸም ልገልጸው የማልቾል ነገሬ ላይ ደርሶ ነክቶኛል። መቼም ትንሽ ማወቅ ዕዳ ነው፤ ከዚያ በኋላ ስለ መጽሐፍ በተወራ ቁጥር የማነሳው ያቺን መጽሐፍ ሆነ፡፡ እንድ ነገር ግን ገረመኝ ፣ ስለመጽሐፉ ሳይሆን ስለጓደኛዬ ሃይሚ ... ያዋሰችኝ መጽሐፍ ገጽ 113 እና 114 ከላይ የተጣበቁ ነበሩ፣ ሕትመት ላይ የሚፈጠር ነገር ነው፡፡ ብዙ አዳዲስ “ሪፈረንስ' መጽሐፍት ስገዛ አጋጥሞኝ ያውቅ ስለነበር የገጾቹ መያያዝ አላስገረመኝም፤ የገረመኝ ሃይሚ እንዳለችው ይኽን መጽሐፍ ሁለት ጊዜ ካነበበችው እንዴት ገጾቹን አላላቀቀቻቼውም...?ያላነበበችውን መጽሐፍ ለምን ታደንቃለች....? አራት ጣቶቼን በመኻል አስገብቼ እንደ ክብ ትቦ በተጣበቁት ገጾች መኻል አጨነቆርኩ፤ ምናልባት ሌላ ኮፒ ይኖራት ይሆናል ብዬ በቀስታ በምላጭ አላቅቄ ማንበቤን ቀጠልኩ። ለሃይሚ መጽሐፉን እንደወደድኩት ነገርኳት ስለ ታሪኩ ብዙ አወራኋት “አዎ! አስገራሚ ነው'' ከማለት ውጪ ብዙም ዝርዝር አላወራችኝም። እኔ ግን ማውራቴን ማቆም አልቻልኩም፤ የጥያቄ መዓት አዥጎደጎድኩባት መልስ የለም፡፡ እንዲያውም ለአባቴ ሰጥቼው አንብቦ ወደደው... ብዙ ብዙ አወራንበት፡፡ ለሃይሚ መጽሐፉን ከመለስኩላት በኋላ ሥራዬ ብዬ ሔጄ ለራሴ ገዛሁ፡፡ ልብ-ወለድ መጽሐፍ ስገዛ የመጀመሪያዬ ነበር፤ ምናልባት የመጨረሻዬም!! አንድ ዓርብ ቀን ታዲያ ጓደኛዬ ሃይሚ ደወለችልኝና... “የምትወጂው ደራሲ ነገ ጧት የመጽሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ይመጣል ለምን አንሄድም?'' አለችኝ...

“ኧረ! ባክሽ?'' አልኩ ሰፍ ብዬ... በመሠረቱ ደራሲውን እወደዋለሁ የሚል ቃል ከአፌ አልወጣም ነበር! የት አውቄው? “እውነት! ቶማስ ጋር “ቤስት' ናቸው ያስተዋውቀናል እንዲያውም እኔን ትጠይቂዋለሽ”... ቶማስ ከምታደርቂኝ ስለዚያ መጽሐፍ ያለሽን ጥያቄ ሁሉ የሃይሚ ፍቅረኛ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሁፍ ተመርቆ እስካሁን አንድ ስንኝ እንኳን ያልጻፈ ነጭናጫ ልጅ፣ በሕሪው ስለሚያስጠላኝ አልወደውም፤ ሃይማ ምኑን እንደወደደችው እስከ ዛሬ ይገርመኛል፡፡ ለወትሮው እንዲህ ዓይነት የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት ይሁን፣ ስብሰባ የሚባል ነገር ባልወድም፣ የዚያን ቀን ግን ደራሲውን ለማዬት ጓጓሁ፤ ምናልባት ውስጤ አድንቆት ይሆናል እንጃ! ብቻ ውስጤ ሊያገኜው ፈለገ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ጧት ከሃይሚ ጋር ተያይዘን ሄድን፡፡ እዚህ ራስ ሆቴል፣ አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ በሰው ተሞልቷል። መድረኩ ላይ የባሕል የሙዚቃ ተጫዋጮች የባሕሩ ቃኜን ዘፈን ይጫወታሉ(ይልቅ ይኼ ደስ አለኝ) እንደፈራሁት አልነበረም፡፡ እንዲያውም ደስ የሚል ዝግጅት ነበር፡፡ የተለያዩ ሰዎች መድረክ ላይ እየወጡ ግጥም ያነባሉ፡፡ መጽሐፍ ያሳተመውን ሰውዬ እንኳን ደስ ያለህ ይላሉ፡፡ ፕሮግራሙ ወደማለቁ ሲቃረብ ወጣትና ንጹህ ልብስ የለበሰ፣ በሥርዓት ፂሙን የተስተካከለ ልጅ ወደ መድረክ ሲወጣ ሃይሚ በክንዷ ጎሼም አድርጋኝ “እሱ ነው!!' አለችኝ፡፡ ሰው እንደዚያ አፍጥጨ ዓይቼ አላውቅም፡፡ ትልቅ _ ሰውዬ ነበር የጠበቅሁት፣ መላጣ መነጽር የሚያደርግ ምናምን፡፡ ግጥም አነበበ፣ እውነቱን ለመናገር ግጥሙ አልገባኝም። የአዳራሹ ሰው ሲያጨበጭብ አብሬ
👍355
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ሁለት


ረብሻ ሁለት!

ከሰርጋችን በኋላ ባለቤቴ ረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሲመለስ ቤተሰቦቹ ቤት ነበር አስቀምጦኝ የሄደው። የሚያምር ትልቅ ግቢ፣ በአበቦች የተዋበ፣ ከዋናው “ሺላ ነጠል ብሎ በሰርቪስ ስም የተሠራ ሌላ ባለ ሦስት ክፍል 'ቪላ' ውስጥ ለብቻዬ ነው የምኖረው፡፡ ቤተሰቦቹ (እናቱና ሁለት እህቶቹ) ሲበዛ ጥሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ዋና ሥራቼው እኔን መንከባከብ እስኪመስለኝ አፈር አይንካሽ ብለው ነበር የያዙኝ። ከገባሁ በኋላ ሥራ አቁሜ ስለነበር ውሎዬ ቤት ነው። “ምን ጎድሎ በየገጠሩ ትንከራተቻለሽ?'' ብሎ ነበረ ባሌ ሥራ ያስቆመኝ፡፡ በዚያ ላይ ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወዲያው “ፕሮሰስ'' እንደሚጀምርልኝ ስለነገረኝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሥራ ማቆሜ አይቀርም በሚል የቤት እመቤት ሆንኩ። እውነቱን ለመናገር እኔም ወደ ውጭ መውጣት፣ ሰው ጋር መገናኜት በራሴ ምክንያት ጠልቼ ነበርና ሥራዬን ማቆሜ አላስከፋኝም። ታዲያ በሰበብ አስባቡ (እነሱ በፍጹም ቅንነት ብቼኝነት እንዳይሰማኝ በማሰብ) እሀቶቹ፣ አልያም እናቱ ከአጠገቤ አይጠፉም ነበር፡፡ በጭራሽ ብቻዬን መሆን አልቻልኩም፡፡ እሱም ባልከፋ፤ ሰብሰብ ሲሉ በአንድም በሌላም መንገድ “የሴት ልጅ ሙያ'' ስለሚሉት ነገር ሳያነሱ ያልፋሉ ማለት ዘበት ነበር። ስለ ጠላ መጥመቅ፣ ስለ ዶሮ ወጥ ጣዕም፣ ስለ እንጀራ ዓይን፣ ስለ ዳቦ ኩፍ ማለት፣ ስለ በርበሬ መቀንጠስ፣ ስለምናምን መደለዝ ይኼ ትንሽ ሳያማርረኝ አልቀረም፡፡ በተለይ የባለቤቴ እናት! ከሃያ ዓመት በፊት ሰው ቤት ሄደው ስለቀመሱት የማይረባ ዶሮ ወጥ ሳይቀር አንስተው ያማርራሉ «ሴት ልጅ እንዴት የግዜር ዶሮ ወጥ መሥራት ያቅታታል? አሁን ማን ይሙት ዶሮ እንደዚያ ይበለታል?» ይላሉ በግርምት። ጉድዎትን አልሰሙ፣ እላለሁ በውስጤ! ይህች ጥሩ ሴትዮ እንጀራ መጋገር አላውቅበትም ብላቼው ራሳቼውን ስተው የሚወድቁ ነው የሚመስለኝ፤ እጄን ታጥቤ ሲቀርብልኝ ከመብላት ባለፈ ዶሮ ይገንጠል፣ ይፈጭ ግድ አይሰጠኝም ብላቼው ደግሞ በቀጣዩ ቀን ቀብር የምንውል ይመስለኛል።

እውነቴን ነው፤ እኛ ቤት ምግብ በሕይወት ለመሰንበት ከመበላቱ ውጭ እንዲሀ ትልቅ ርዕስ ሆኖ አያውቅም። ሠራተኛችን ጽጌም ብትሆን ከእናቴ ብትሻልም ምግብ ላይ ያን ያኽል የምትደነቅ አልነበረችም። ምስኪን የገጠር ሴት ናት። ከተማ እንደገባች እኛ ቤት ተቀጠረች፤ የከተማ ምግብ የሚባለውን ሙያ እናቴ ናት እንግዲህ ያሰለጠነቻት። ይኼን ሳስብ ሳቅ ይቀድመኛል። ጓደኛዬ ሃይሚ እግር ጥሏት ስበላ ከደረሰች አንዴ ጎርሳ ትተወውና “ከእናንተስ ቤት ምግብ የእኛ ቤት ርሃብ ይሻላል'' ትለኛለች። በተለይ በሠራተኛችን ጽጌ እንጀራ እንደቀለደች ነው “ጽጌ እኮ እንጀራ ሆኖባት ነው እንጀራ የምትጋግረው'' ትልና እንስቃለን። የሆነ ሆኖ የባሌ ቤተሰቦች ከዬት እንዳገኟት እንጃ በደግ ቀን የቀጠሩልኝ ሠራተኛ በዚህ ባለሙያ ቤተሰብ መኻል ከመዋረድ አድናኛለች። ይኼንንም ችዬ ታዲያ በጣም ያማረረኝ ሲበዛ ሃይማኖተኞች መሆናቼው ነበር። ጧት ማታ ቤተክርስቲያን እንሂድ ንዝናዚያቼው ማቆሚያ የለውም፡፡መጀመሪያ እማማ (የባለቤቴ እናት)... “ያይኔ አበባ!” ይሉኛል (እንደዚያ ነው ሲጠሩኝ፣ አቤት ይኼ ስም ሲያስጠላኝ! የሆነ ሰው አምጥቶ እዚህ ግቢያቼው ውስጥ የተከለኝ፣ ከትንሽ ጊዜ በኋላ የምጠወልግና ጠርገው የሚጥሉኝ የሆነ ከንቱ አበባ የሆንኩ መስሎ ነው የሚሰማኝ፡፡) “ነገ የዓመቱ ሚካኤል ነው በጧት ይቀሰቅሱሻል ልጆቹ፤ ቤተስኪያን እንሄዳለን" “አይ! እኔ አልሄድም እማማ'' ደንገጥ ብለው አዩኝ፡፡ አደነጋገጣቼው ጾታዬ'ኮ ወንድ ነው ያልኳቸው ዓይነት ነበር ፡፡ “ምነው! ያውም ለክብረ በዓሉ ከቤተስኪያን የሚያስቀር ...?'' ድንገት የመጣልኝን ሰበብ ወረወርኩ “ፔሬድ ላይ ነኝ'' አልገባቼውም፡፡ ትልቋ ልጃቼው እየሳቀች “ንጹሀ አይደለሁም! ማለቷ ነው" አለች፡፡ የዚያን ቀን በዚህ አለፍኩ፡፡ ከዚያ በኋላ የነበረው የዬቀን ጥያቄ ግን ማቆሚያ አልነበረውም፡፡

ቤታቼው ውስጥ መንፈሳዊ መዝሙር ካልሆነ ምንም ዓይነት ዘፈን አይከፈትም፡፡ ሬዲዮ እንኳን ሲከፍቱ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ታዲያ አፍ አውጥተው ባይናገሩትም እኔ ዘፈን ስከፍት ፊታቼው ላይ የማዬው ግራ መጋባት ይረብሸኝ ነበር፡፡ የሆነ መብረቅ ላስመታቼው የተላክሁ ዓይነት ዓይናቼው ማረፊያ ያጣል፡፡ ቀስ በቀስ የራሴን ፍላጎት ቶቼ፣ የእነሱን ለማክበር ከሙዚቃ እየራቅሁ፣ ከመዝሙሩም ሳልቀረብ ዝምታ ውስጥ እየተነከርኩ መጣሁ። ይኼ ደግሞ ድብርቴን አባብሶት ግቢው እስር ቤት እስኪመስለኝ በጭንቀት ልሞት ደረስኩ፡፡ አንዳንዴ አባቴ ጋር ሄጄ አድር ነበር፡፡ በተለይ የባሌ እናት ይኼ ነገር ፈጽሞ ደስ አይላቼውም፡፡ ምንድን ነው ይኼ ሁሉ ነገር? እላለሁ ለራሴ... ምን ውስጥ ነው የገባሁት? ታዲያ አባቴ ቤት ስሄድ እዚያ ሜክሲኮ “ላፍቶ ላፍቶ” የሚል የታክሲ ረዳት ጥሪ “ማኅደረ ሰላም'' ከሚለው ስሜ እኩል ይጎትተኛል፡፡ አምላኬ ርዳኝ ስንቴ አልኩ!

ረብሻ ሦስት!

የስልክ ሰው አይደለሁም፡፡ ሰው በስልክ ዐሥር ደቂቃ ከሚያወራኝ፣ በአካል ሙሉ ቀን ቢያወራኝ እመርጣለሁ፡፡ባለቤቴ፣ በየቀኑ አንዳንዴም በቀን ሁለትና ሦስት ጊዜ ከአሜሪካ ይደውልና ረዢም ሰዓት ሊያወራኝ ይሞክራል... ቀን፣ ሌሊት፣ ጧት፣ ማታ አይልም፤ ይገባኛል...ሚስቱ ነኝ፣ ሌላ የሚያገኝብኝ አማራጭ የለውም፣ ይናፍቅ ይሆናል፣ ግን ሁሉም ነገር ዞረብኝ፤ ስልክ አልወድም።ይኼን ባህሪዬን የሚያውቁኝ ሁሉ ያውቃሉ፣ “ውይ እሷና ስልክ'' ነው የሚባለው፡፡ ሌሊት ከእንቅልፌ መንቃት አልወድም፣ አባቴ እንኳን እኔ ከተኛሁ እንዳይቀሰቅሰኝ ቤት ውስጥ በጥፍሩ ነበር የሚራመደው፣ ረዘመ ከተባለ ያውም የሥራ ጉዳይ ከሆነ ዐሥር ደቂቃ ካወራኹ ራስ ምታት ይጀምረኛል፡፡ ጓደኛቼ “ቴክስት" ቢልኩልኝ እመርጣለሁ፡፡ የሆነ ጊዜ ባለቤቴ አንድ ሰዓት ሙሉ ያወራኝ ቀን ሲዘጋው አለቀስኩ፤ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ፊቴን የጋለ ጆርዬን በቀዝቃዛ ፎጣ ሸፍኜ አለቀስኩ ጩኺ! ጩኺ! አለኝ፣ ርግማን ነው ይኼ! ምንም ምንም በነፍስም በሥጋም የሚቀራረብ ነገር የሌለን ሰዎች ምን ዓይነት ነገር ነው ያገናኜን? ባሕሪው ጥሩ ይሁን አይሁን የራሱ ጉዳይ።

ለምሳ ወጥቼ ነው ብሎ በደረቅ ሌሊት ይደውላል፤ አእምሮዬ ሌሊት ነውና ስለምሰ ማሰብ አይችልም። ባሌ በሌሊት ምሳ የሚበላ ፍጥረት ነው? አይ! አሜሪካ የምለ ሰዓት ነው እላለሁ ለራሴ፣ ይሁና በዚህ ሰዓት የሆነ ነገር እያላመጠ የሚያወራ ሰው በእንቅልፍ ልብ መስማት ያቅለሸልሻል፡፡ ስልኬን ከዘጋሁ በቤት ስልክ ዋናው ቤት ደውሎ ደህና አይደለችም እንዴ? ይላል እየተንጋጉ መጥተው በደረቅ ሌሊት በሬን ያንጓጓሉ፡፡ የሩቅ ትዳር ርግማን ነው፣ ዝም ብሎ ሲያወራ ሬዲዮ ይመስለኛል፡፡ ስሜን የሚጠራ የሆነ ዜና አንባቢ…“ማሂዬ የኔ ማር!” አጠራሩ ይዘጋኛል፡፡ የAND3 መራራቅ በወሬ ሊሞሉ መጣር፤ እንዲያውም ሌላ ነገር ያምረዋል፣ በስልክ ስለ ሴክስ ማውራት ምናምን፤ በራሴ አዝናለሁ በምርጫዬ ድድብና ራሴን ረግመዋለሁ። አዲስ አበባ የተቀመጠ የከሰል _ ፍም፣ _ አሜሪካ በረዶ ላይ ተቀምጦ ሊሞቅ እንደሚታገል ሰው ምን ምስኪን አለ? እንዲህ ዓይነት ሕይወት...
👍353
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ሶስት


እናትሽ የት ሄደች?

እናቴ ቆንጆ፣ ዘናጭ፣ ሳቂታና ደስተኛ ሴት ነበረች፡፡ በዚያ ዕድሜዬ እንደዚያ ነበር የማስበው፡፡ በጥቁር ቆዳዋ ላይ የሚያምሩ ነጫጭ ጥርሶቿ ያስደነግጣሉ፡፡ እንደ ወንዝ ድንጋይ ለስላሳና ጽድት ያለ ወደ ጥቁረት የሚወስደው ቆዳ ያላት፣ ሌሎች

ሰዎች ጋር ስትቆም ረዥም ቁመቷ የተለዬ ሞገስ የሚሰጣት- ቆንጆ ሴት፡፡ ሦስት ልጅ ወልዳ እንኳን ንክች ያላለ ውበት። አዲስ የወጣ ዘፈን የማያመልጣት፣ ፓናሶኒክ ቴፓችን ከጧት እስከማታ ካልተከፈተ የሚጨንቃት፣ እኔና ሁለት ታናሽ ወንድሞት ምንም እናውራት ምን “እስቲ ልቤን አታንሸራቱኝ ሂዱ ለአባታችሁ ንገሩት” የምትል፣ ከዘፈን ሌላ እኛን መስማት የሚደክማት፤ ሙሉ ቀን ስንዘፍን ብንውል ግን በፈገግታ የምትመለከተን እናት ነበረች። እናቴን ለመቅረብ በስምንት ዓመቴ እዚያ ፓናሶኒክ ቴፕ ሥር ራሴን ደቅኘ ያልሸመደድኩት የዘፈን ግጥም አልነበረም፡፡ ዘፈን ወደ እናቴ መድረሻ ድልድይ ነበር “ውይ የድምፅዋ ማማር ደግሞ'' ትልና የቀለበት መዓት በተደረደረባቼው ለስላሳ ጣቶቿ ጉንጭና ጉንጨን ይዛ ከንፈሬን ትስመኛለች፤ የእጇ ልስላሴ_እስካሁን ይታወሰኛል፣ የእናት እጅ እንዴት እንደዚያ ይለሰልሳል!? “ተይ! ይኼን ከንፈር መሳም'' ይላታል አባባ ደስ አይለውም። “እንዴ ምናለበት?'' ትልና እንደገና ከንፈሬን እሟ እሟ...እልኅ በሚመስል አሳሳም: ፡አባባ በቅሬታ ፊቱን ወደ ሌላ ቦታ ያዞራል ወደ መስኮት፣ ወደ ወንድሞቼ ወደሚያነበው ነገር፣ እዚያ ጥግ ላይ ወደተቀመጠው የሸክላ ሰሃን እና ብርጭቆ ወደታጨቀበት ትልቅ ቡፌ፣ ወይም ወደ ላይ ወደ ኮርኒሱ፡፡ መከራከር አይወድም። የአባባ ዓይኖች ሲሸሹ እናቴ በድል አድራጊነት ድምፅዋን ከፍ አድራጋ በጣም የምትወደውን ዘፈን “ይላል ዶጁን” እያንጎራጎረች የምትሠራውን ትሠራለች። ብዙ ጊዜ የምትሠራው በእስክርቢቶ ካሴት ማጠንጠን ነበር፤አባባ ጋር ብዙ አያወሩም፤ ስልቹ ነበረች፡፡ አባባን በተደጋጋሚ የምትጠይቀው ጥያቄ “እስቲ እስክርቢቶ ስጠኝ" የሚል ነበር። ካሴት ለማጠንጠን፤ እንዲያውም አባባ ከአባትነትም፣ ከባልነትም በላይ የሆነ የእስክርቢቶ ማስቀመጫ ዕቃ መስሎ ሳይታያት አይቀርም፡፡ እውነቱን ለመናገር ለእኛም ለልጆቿ ያን ያኽል ፍቅር ነበራት ብዬ አላስብም፡፡ በተለይ እኔ እንደ እናት ልቀርባት የምደክመው ድካም አሁን ላይ ሳስታውሰወ ያመኛል፡፡

እስከ አሁን በሕይወቴ የሚከተሉኝ ድክመቶች ከእርሷ ግዴለሽ ባሕሪ የተፈለፈሉ ቫይረሶች ይመስሉኛል፡፡ ፈሪ፣ ግራ የምጋባ፣ ሰው አብዝቼ የምለማመጥ እና በራሴ የማልተማመን ነኝ። ሰዎች ሁሉ የሚሰለቹኝ፣ የማይወዱኝ እና የሚርቁኝ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም የእርሷ ጦስ ነው፡፡ ለማሳበብ ሳይሆን ይኼ የተለማማጭነት ባሕሪዬ፣ ስሜቱ እሷን ለመቅረብ ከምታገልበት ስሜት ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ሰዎች ትንሽ ፊታቼውን ዞር ያደረጉብኝ ከመሰለኝ ጭንቀት ሊገድለኝ ይደርሳል፡፡ እቤታችን የነበሩትንና እናቴ ጋር የተነሳናቼውን ፎቶዎች በሙሉ ተመልሼ ሳያቼው፣ ወገቧን ለማቀፍ ተንጠራርቼ፣ ትከሻዋ ላይ በመለማመጥ ተደግፌ.... እነዚያን ፎቶዎች ሳያቼው ያመኛል፡፡ አባባን የምወደው እሱም ቢሆን እንደ አባት ስለቀረበኝ አልነበረም፣ እናቴን ለመቅረብ ልክ እንደ እኔ በዓይኑ፣ በንግግሩ፣ የምትናገርና የምትሠራው ልክም ሆነ ስሕተት በማዳነቅ ሊቀርባት ሲሞክር፣ ሲለማመጥ ሳዬው አሳዝኖኝ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በቤታችን 'ቤሳቤስቲን' ስሜት ከሌላት ስስታም ሴት የፍቅር ለማኞች ነበርን!! ያቺን ሴት ለማስደሰት የማልፈነቅለው ድንጋይ አልነበረም፤ እሷ ግን ሁልጊዜ የመስኮታችንን መጋረጃ በትንሹ ከፈት አድርጋ ወደውጭ መመልከት ነበር ሥራዋ፡፡ ያንን መስኮት አብዝታ ነበር የምትወደው፡፡ በተለይ አባባ ከሌለ ቴፑን ድብልቅልቅ አድርጋ ከፍታ፣ በመስኮት ዐሥር ጊዜ ወደ ውጭ ከማዬት በስተቀር ሥራ እልነበራትም፡፡ አባባም ቢኖር ባለፈች ባገደመች ቁጥር ዓይኗን ወደ መስኮት መወርወሯ አይቀርም ነበር፡፡ በመስኮት አስተያዬቷ የሆነ የሚያጓጓ ነገር ነበረው፤ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ቁመቴ መስኮቱ ጋ ስለማይደርስ ወንበር ጎትቼ ያዬቸውን ለማዬት ብዙ ጊዜ እሞክር የነበረው... ምንም የለም፣ ምንም! ከዚያ አስቀያሚ ጋራዥ በስተቀር፡፡ እኛም ሆንን አባባ ምን እንብላ፣ ምን እንልበስ ግድ የሌላት ሴት ነበረች፡፡ አልፎ አልፎ ሠራተኛችን ዘመድ ጥዬቃ ብላ ስትሄድ፣ እናቴ እየተማረረች ወደ ኩሽና ትገባለች፡፡ አንዱ ዕቃ ጠፋ ስትል፣ ሌላኛው ተደፋ እያለች ስታማርር ብዙ ሰዓት ቆይታ እሀል ውሃ የማይል ነገር ሠርታ ብሉ ትለናለች፤ አንበላም፤ እንዲያውም እሷ

ምግብ ስትሠራ የሚደፋው ይበዛል፡፡ ጓዳው ባልታጠበ ዕቃ ይሞላል፡፡ በዚያ ላይ ፊቷን በቁጣ ጥላው ነው የምትውለው። በሠራተኛ ነው ያደግነው፤ አብራን የኖረች እንደ እናት የምናያት ሠራተኛ ነበረችን፡ ታዲያ ደጋግሜ ምንም እንደሌለ ባረጋግጥም እናቴ በዚያ መስኮት ምንድን ነው የምታዬው? እያልኩ እጓጓ ነበር፤ እሷ ስትቆም ታይቶ እኔ ብቅ ስል የሚጠፋ አንዳች ተአምር ምንድን ነው!? ቆይቶ በዕድሜ ከፍ ስል ነው- ተክሌ ጋራዥ መኪና ሊያሠሩ የሚመጡ የከባድ መኪና ሹፌሮችን ትመለከት እንደነበር የገባኝ፡፡ በዚያ ዕድሜ እነዚያ ወንዶች ጋር የነበራት ነገር ባይገባኝም፣ አንዳንዶቹ እቤታችን ድረስ መጥተው በመስኮት በኩል ያወሯትና ይሳሳቁ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ በሚያማምሩ የፕላስቲክ ማሸጊያዎች የታሸጉ ከረሜላና ቸኮሌቶች በብዛት ያመጡላት ነበር። ከጅቡቲ ነው ያመጣነው ሲሉ ስለምሰማ በዚያ ዕድሜዬ፣ ጀቡቲ ከረሜላና ቸኮሌት የሚዘንብባት አገር ትመስለኝ ነበር። እናቴ ጣፋጭ ነገር በጣም ነበር የምትወደው። ቡና ጨምሮ መረር የሚል ነገርና የሚያቃጥል ምግብ ደግሞ በሩቁ ነው የምትሸሸው። ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ቤታችን አልጫ ወጥ የሚዘወተረው፡፡ እኔም እስከ ዛሬ ቡና አልወድም። ያንን ሾፌሮቹ የሚያመጡላትን ጣፋጭ ለእኔም እያፈሰች ትሰጠኛለች። በቦርሳዬ ዉስጥ እየደበቅሁ ትምህርት ቤት እወስድና ሃይሚ ጋር ሆዳችን ከበሮ እስከሚያክል እናሻምዳለን። አንዱ ሾፌር ያመጣው ሳይጋመስ ሌላው ስለሚያመጣ ያ የጣፋጭ ጎርፍ ዘላለም የሚያልቅ አይመስልም ነበር። በተለይ የማልረሳው “ጥቁር ዕንቁ” የሚላት ሰውዬ ነበር፡፡ የሸሚዙ ቁልፍ ተከፋፍቶ ደረቱ ላይ ችፍግ ያለ አስቀያሚ ጸጉሩ የሚታይ፤ በተራመደ ቁጥር እንደ ጸናጽል የሚንሿሿ ባለዘለበት ቡትስ ጫማ የሚያደርግ፡፡ ሁልጊዜ ቤታችን ካሉት ወንበሮች አባባ የሚወደውን ባለ ስፖንጅ ወንበር ታወጣለትና በር ላይ፣ መስኮቱ ሥር ይቀመጣል፡፡

እናቴ ወደ ቤት ትመለስና ከወገቧ በላይ በመስኮት ብቅ ብላ ገበያ እንደጠረረበት በለ ሱቅ የመስኮቱን ደፍ ተደግፋ ድምፃቼውን ቀንሰው ያወራሉ- ይሳሳቃሉ። እንዲህ ሲያወሩ ታዲያ እቤት ሆኜ ከኋላዋ አያታለሁ፡፡ እግሯ አያርፍም፤ በነጠላ ጨማዋ ትጫዋታለች ፣ ሽፍን ጫማ ብታደርግ እንኳን የአንድ እግር ጫማዋን አውልቃ (ብዙ ጊዜ የቀኟን) እግሯ በጫማዋ ይጫዎታል፤ ወይም በረዣዥምና በሚያምሩ የእግሯ ጣቶች ምንጣፉ ላይ የማይታይ የሐሳብ ሥዕል ትሥላለች፤ ወይም በቀኝ እግሯ ጣቶች የግራ እግሯን ከተረከዟ ከፍ ብሎ እስከ ጉልበቷ ያለውን ክፍል ትነካካለች፤ እኔም ይኼ ነገር ለምዶብኝ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቢሮዬም ይሁን ሌላ ቦታ ስቀመጥ፣ ጫማዬን አወልቅ ነበር፡፡ ብዙ ባሕሪዋ ሳልፈልግ ውስጤ ተቀምጦ ራሴን እንደ እሷ ሳደርግ የማገኝበት ጊዜ ነበር፡፡ ታዲያ ሁልጊዜ ወሬዋን ስትጨርስ የአንድ እግሯ ጫማ ስለሚጠፋት
👍453😁2🔥1🥰1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አራት


አልተዘዋወረችም!

እናቱ ትታን ብትጠፋም አልጠላኋትም፤ እንዲያውም ሰው በሌለበት በናፍቆት አለቅስ ነበር፡፡ በተለይ ጠዋት አባባ ወደ ሥራ ከሄደ በኋላ ፣ወንድሞቼ ለጨዋታ አወጡ? ሠራተኛችን እዚያው ሰፈራችን ወዳለ ጉሊት ገበያ ስትሄድ ቤቱ በጸ ይሆንብኛል። ይኼ ሰዓት የእናቴ መንፈስ ቤቱን የሚናኝበት ነው። በዚህ ሰዓት ነበር ሙዚቃ ከፍታ፣ ቤቱ በሽቶ ጠረን ተሞልቶ፣ በቅመም ያበደ ሻይዋን ይዛ መስኮቱ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ የምትቀመጠው፣ ባታወራኝም አብራኝ የምትሆነው። ዝምተኛ ነበረች፤ በዓይኖቿ ብቻ የምታወራ፣ እና ዓይኖቿን ከእኔ የምታሸሽ። ሁለቱ ታናናሽ ወንድሞቼ የእናቴ መጥፋት ለምን ግድ እንዳልሰጣቼው እስካሁንም ድረስ አላውቅም፡፡ የበለጠ የገፋችኝ እኔ ግን ለምን በናፍቆቷ እንደተጎዳሁ ዛሬም ድረስ አይገባኝም፡፡ ክፉኛ ትናፍቀኝ ነበር፡፡ እናቴ ጠረኑ በሚያውድ ሽቶና በብዙ ጣፋጭ የተከበበች ገነት ነበረች- ለእኔ። ያ ገነት ሁልጊዜ ውብ ዜማ ከውስጡ ይፈልቅ ነበር፡፡ የሠራሁትን ኃጢአት እንጃ ወደዚያ ገነት እንዳልገባ ብከለከልም በልጅነት እግሮቼ ዳር ዳሩን ስዞር ነው የኖርኩት። በስንተኛው ዙር ያ የመገፋት ቅጥር _ እንደሚፈርስ ባላውቅም _ አንድ ቀን በእናቴ የፍቅር እቅፎች ውስጥ እንደምወድቅ አስብ ነበር... ቅጥሩ ሳይሆን ተስፋዬ ፈራረሰ። በናፈቀችኝ ቁጥር እዘፍናለሁ፡፡ ታዋቂ ዘፋኝ ብሆን ተመልሳ የምትመጣ ይመስለኝ ነበር፡፡ አባባ ግን ስዘፍን ከሰማ ይቆጣል፤ ማቆም አልቻልኩም፡፡ ውሎዬ ሁሉ ልክ እንደ እናቴ ቴፕ ሥር ሆነ። በቁጣም በምክርም ብሎኝ ብሎኝ አልሰማ ስል ያንን ፓናሶኒክ ቴፕ ዬት እንዳደረሰው እንጃ ድራሹን አጠፋው፡፡ ቤታችን : ጭር አለ፤ የሚያስፈራ ጭርታ፡፡ ቤት እንደ ሰው ይሞታል ለካ፤ ቤታችን ሞተ፡፡ ዩኒቨርስቲ ገብቼ እስክመረቅ እቤታችን ቴፕ አልነበረም፡፡ አንዳንዴ እናቴ ትታቼው ከሄደቻቼው ጥቂት ካሴቶች አንዱን ይዠ ጎረቤት ቤት እሄድና ክፈቱልኝ እላለሁ፡፡ብዙ ጊዜ

ባለጋራዡ ክፍሌ ቢሮ(ቢሮ አይበለው መቆሸሹና መዘበራረቁ) እሄድና የብረትና የቅጥቀጣ ድምፅ ጋር እየታገልኩ ዘፈኔን እዬሰማሁ ቁጭ እላለሁ። በዚያ እናታችን ትታን በሄደችበት ዓመት ብዙ ነገር ተዘበራረቀብኝ፡፡ በተለይ የትምህርቴ ነገር እንዳልነበር ሆነ፡፡ ሆኖ የማያውቀውን በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በክፍሉ ውስጥ ከነበርነው 55 ተማሪዎች 47ኛ ወጥቼ አባባን እንደ ሴት አስለቀስኩት፡፡ አልተቆጣኝም አቅፎኝ አለቀሰ፡፡ ሠራተኛችን ጽጌ ታዲያ እንደ ፎካሪ ሰሎን ውስጥ እየተንጎራደደች "የምን ማልቀስ ነው? ልጁ ሁሉ እየወደቀ እየተነሳ ነው ትልቅ ደረጃ የሚደርስ፤ ለወደፊቱ ሁሉንም በልጣ አንደኛ ነው የምትሆን!“ ትላለች፡፡ በየመኻሉ ግን እሷም ዕንባዋን ትጠርግ ነበር፡፡ ሪፖርት ካርዳችን በተሰጠን ማግስት አንድ ሰከራም የክፍል ኃላፊ መምህራችን ከነበርኩበት ጎበዝ መደዳ እስነስቶ ሰነፍ መደዳ አስቀመጠኝ “ድሮም ዘፈን ስታበዥ ነው ነገር የተበላሼው!” ከሚል ስላቅ ጋር... ተነስተሽ ካልዘፈንሽ እያለ እንዳላስቼገረኝ... ፊቱ ላይ የነበረው ጥላቻና ንቄት ባሰብኩት ቁጥር ያበሳጨኛል። በዓመቱ መጨረሻ ሪፖርት ካርዴን ስቀበል፣ ልክ ልብ ድካም እንዳለበት ሰው የልጅ ደረቴን ድንገተኛ ውጋት ሰቅዞ ያዘኝ፤ ተዝለፍልፌ የምወድቅ ነበር የመሰለኝ። በቀሪ ዘመኔ ሁሉ አእምሮዬ ውስጥ እንደትራፊክ መብራት ደምቀው በሚያበሩ ቀያይ ፊደላት የተጻፈ ቃል ካርዱ ላይ ታትሞ ነበር “አልተዘዋወረችም'' ይላል፡፡ የሆነ ነገሬ ላይመለስ የተመታው በዚያ ሰይፍ በሆነ ቃል ነበር፡፡ ውዳቂነት፣ ከሰው ማነስ፣ አለመፈለግ፣ አለመሳካት፣ አለመቻል ይኼ ሁሉ በእናቴ የግዴለሽነት ሲሪንጅ ቀስ በቀስ ደሜ ውስጥ ሲሰርግ የነበረ የበታችነት ስሜት፣ በአደባባይ በመላ መምህራኖቼ እና ቦትምህርት ቤቴ ታውቆ የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ትምህርት እንደ ቀደሙት ዓመታት በፍቅር አዲስ ነገር ለማወቅ የምጓጓበት ነገር ሳይሆን፤ ፍርኃት፣ ጭንቀት እና አባቴን ላለማሳዘን፣ በሰው ፊት ላለመዋረድ፣ ጓደኞቼ እንዳይርቁኝ ለመለማመጥ የሙጥኝ ብዬ የያዝኩት የገደል ጫፍ ገመድ ነበር፤ ትግል!!

ከዚያ በኋላ ጎበዝ ተማሪ ሆኜ ከምማርበት ክፍል፣ እስከ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት እስከ ማስመዝገብ ብደርስም ያ ቃል ያንኮታከተው በራስ መተማመኔ ግን፣ እስከ መጨረሻው አልተመለሰም፡፡ በማንኛውም የሕይወቴ ክፍል አንድም ቀን ይሳካልኛል፣ እችላለሁ የሚል እምነት ኖሮኝ አያውቅም፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ ከውድድር እርቃለሁ። ከዚያ የልጅነት ዕድሜዬ እስከ ኮሌጅ የፈተና ውጤት በሚነገርበት ቀን ልቤ ላይ የሚሰማኝ የሚያፍን ጭንቀት አለ፡፡ ውጤት ሲባል ብርክ ይይዘኛል። ከኮሌጅ ከተመረቅን በኋላ ሃይሚን ጨምሮ ብዙዎቹ ጓደኞቼ ያውም ከእኔ ያነሰ ውጤትም፣ ብቃትም : ያላቼው ልጆች በታላላቅ ድርጅቶች በጥሩ ክፍያ ሲቀጠሩ፣ ሥራ ሲቀያይሩ እኔ መጀመሪያ ከተቀጠርኩበት ቢሮ ንቅንቅ አላልኩም። ሥራ እንድቀይር፣ በየሚሠሩበት የውጭ ድርጅት ዕድሌን እንድሞክር ገፋፍተውኝ- ገፋፍተውኝ ሲደክማቼው፣ ሁሉም የራስሽ ጉዳይ ብለው ተውኝ። ያ “አልተዘዋወረችም!'' ያስፈነደቃት ብቸኛ ፍጥረት ጓደኛዬ ሃይሚ ነበረች፤ በደስታ አቅፋኝ ዘለለች፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ገና አንደኛ ክፍል ስንገባ፣ ክፍል ደግማ ስለነበር እኩል መሆናችን አብረን እንድንቀጥል ዕድል ይሰጠናል ከሚል ንጹህ የጓደኝነት ፍቅር ነበር፡፡ ከፍ ስል- በዕድሜ ስበስል ታዲያ ያቺን አልተዘዋወረችም እያስታወስኩ በብዙ ሐሳብ እብሰለሰላለሁ። እንደ ቀልድ በወላጆቻችን፣ በመምህራንና ጓደኞቻችን የምትወረወር የቃል ዘር፣ ተራ ቃል ሆና አታልፍም፤ ከእኛ በላይ አድጋ ዛፍ ትሆናለች፤ ማንም ሰው ተጠልሎ የሚኖረው ውስጡ ተተክሎ ባበቀለ የቃል ዛፍ ጥላ ሥር ነው። በቀሪ ዘመናችን ሁሉ የዕድሜ ልክ ፍርኃት፣ አልያም ብርታት ጥለውብን የሚያልፉ ቅጽበቶች የሚበዙት መፈልፈያቼው ቃል ነው። ይኼን ይኼን አጥብቄ ስለማስብ ለንግግሬ በጣም ጥንቁቅ ነበርኩ፡፡ ከዚያ ክፉ ቃል በኋላ በእርግጥ በሒሳብና

በእንግሊዝኛ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ብቻ፣ በሕይወት ፈተና ወደተሻለ ከፍታ እንደማያሻግር ሕይወት ራሱ አስተማረኝ፡፡ በሥራ፣ በፍቅር እና ሌላም ማኅበራዊ ግንኙነቶቼ ያ ማኅተም፣ የእኔ ጠባሳ ብቻ እንዳልሆነ ተረዳሁ፡፡ በስንትና ስንት ጉድ የሕይወት ስንክሳር እንደ ቤተሰብ፣ እንደ አገር፣ እንደ ሃይማኖት “አልተዘዋወርንም” የሚል ማኅተም ኑሯችን ላይ አርፎብናል!! ለመስክ ሥራ ወጥቼ ያንን ውብ መልከዓ ምድር ስቃኝና የሕዝቡን መጎሳቆል ስመለከት፣ አገሬ ራሷ በየሜዳና ሸንተረሯ ላይ በማይታይ ቀለም “አልተዘዋወረችም!!” የሚል ማኅተም የታተመበት ይመስለኛል፡፡ እንደ አገር _ ስንት የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያጋጥመን እንዲህ ፈራረስን? እላለሁ። ምን ያኽልስ በጎርፍ ተጥለቀለቅን? መቼስ ነበር እሳተገሞራ ምድራችን ላይ የፈነዳው? የትኛውስ ወረርሽኝ ነበር ለዓመታት ሕዝባችንን የፈጄው? በየዐሥርና ሃያ ዓመት የሚያጋጥመን ድርቅ በዚያ ሁሉ ዓመታት በመረትነው ምርት የማይመከት ሆኖ ነው ወይ በርሃብ ሕዝባችን የሚያልቀው? ይኼ ሁሉ የተፈጥሮ መርገምት እዚህ ግባ የሚባል ጉዳት የማድረስ አቅም አልነበረውም!! ታዲያ ምንድን ነው እንዲህ ያጎሳቆለን? ምን ነበር ዓይናችንን ሸብቦ ሌሎች ከሩቅ ያዩትን እኛ ከቅርብ እንዳናይ የጋረደን? ይኼን ሁሉ ጦር ያማዘዘን...
👍373🥰2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አምስት

አደባባይ!

በአንድ የጷግሜ ማለዳ ስርቅርቅ የሚል የሴት አባውዴ ድምፅ ከእንቅልፌ አነቃች፡፡ በዚያ ውብ ድምፅ የባለቤቴን እናት እያሞገሰች ነበር።

ጓዳሽ ለሁሉ ክፍት እንዳ'ደባባይ፣ ደግነትሸ መብራት ባለም የሚታይ፣
ፊትሽ የማይጠቁር የመጣው ቢመጣ፣ ቸርነትሽ አይነጥፍ ቢወጣ ቢወጣ፣..."

ከዚያች የአባውዴ ግጥም በላይ የባለቤቴን እናት የሚገልጽ ምንም ነገር የለም። ያ ግጥም የባለቤቴ እናት ፎቶ ነበር፡፡ ከባሌ ዮናስ ቤተሰቦች ቤት እንደ አደባባይ ሰው አይጠፋም፡፡ የአክስትና አጎቶቹ፣ የሩቅና የቅርብ ዘመዶቹ ብዛት ለጉድ ነበር፡፡ ጭር አለ ከተባለ በሳምንት ሁለት እና ሦስት እንግዳ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ታዲያ ባለቤቴ “በተቸገርንበት ሰዓት አንድኛቼውም አልነበሩም'' ይለኛል:: ወልጄ አንድ ዓመት አልፎኝ እንኳን፣ የአራስ ጥዬቃ እያሉ የሚንጋጉት ዘመዶቻቼው ብዛት ይገርመኝም ይጨንቀኝም ነበር፡፡ ለይቶለት እንግዳ ተብሎ የሚመጣው ይቅርና “በዚህ ሳልፍ ሰላም ልበላችሁ ብዬ ..." ብሎ ጎራ ካለ በኋላ ግማሽ ቀን ቆይቶ የሚሄደው ሰው ብዙ ነበር፡፡ እናቲቱም እንግዳ ይወዳሉ። እንግዳ በመጣ ቁጥር አንድ ቀን ፊታቼው ላይ ቅሬታ ዓይቼ አላውቅም። ለእሳቼው ሁሉም ሰው የመድኃኒዓለም እንግዳ ነው። እህቶቹም በእናታቸው ወጥተው ነው መሰል ሽር ጉድ ብለው እንግዳ ማስተናገድ ይችሉበታል፡፡ የሚገርም ትህትና ያላቼው ሁለት እህቶች አሉት፡፡ እናታችንን ትተን አንሄድም ብለው እስከአሁን ያላገቡ፤ ታዲያ እናቲቱ “ግቢው ሰፊ፣ ባትሄዱ እንኳን እዚህ አምጧቼው እና ኑሩ፤ አንቺ በዚያ በኩል ቤት ብትሠሪ አንቺኛይቱ በዚህ

እንዳለሁላችሁ ወለድ ወለድ አድርጉ!” ይላሉ። ታዲያ ይኼን፣ ይኼን ሳይ፣ ወደ ኋላ ተመልሼ የራሴን ሕይወት እታዘባለሁ። እኛ ቤት እንግዳ ተብሎ ሰው የመጣበት ጊዜ ትዝ አይለኝም፡፡ በጣም አልፎ አልፎ የሠራተኛችን የጽጌ አባት ይመጡ ነበር። እሳቼውም አይቆዩም፣ ወይ ከገጠር ለሕክምና አልያም ለሆነ ጉዳይ ከተማ ብቅ ሲሉ፣ እግረ መንገዳቼውን ነበር ልጃቼውን ለማዬት እቤታችን ጎራ የሚሉት። ተሸማቀው በር ሥር ያለች ወንበር ላይ እንደተቀመጡ፤ የሚበሉም ከሆነ በልተው፣ ቡናም _ ከተፈላላቼው ጠጥተው፣ ይሄዳሉ። ከፍ ስል የሰው ናፍቆቴን ለመወጣት እንደሆነም እንጃ በጣም ብዙ ጓደኞች ነበሩኝ። ደመወዜ የሚያልቀው _ በሰርግ፣ በልደትና በክርስትና ስጦታ በየጓደኞቼ ቤት ስዞር ነበር፡፡ ቆይቼ የተረዳሁት ነገር፣ ጓደኞቼን በስጦታ ልገዛቼው እየታገልኩ እንደነበር ነው፡፡ ዛሬ ላይ አንዳቼውም የሉም፣ ዛሬ እዚህ አደባባይ ላይ :: ታዲያ አሁን ላይ የባሌ ቤተሰቦች፣ ዘመድ አዝማድ ነን የሚሉ በዙሪያዬ የሚያንዣብቡ እናቶች ያስጠሉኛል፤ ያው''አንችም እናት እኛም እናት''በሚል ሒሳብ ስለጡጦ፣ ስለዳይፐር፣ ስለምናምን ሊያወሩኝ ሲጀምሩ ሰበብ ፈጥሬ ከወሬያቼው ርቃለሁ፡፡ በጣም ጥልቅ ቢሆንም ለራሴ ብቻ የገባኝ አንድ ነገር፣ አንዳንድ ሴቶች ስለ ልጅ ጸጋነት ከሚያወሩት በላይ በመውለድ አደገኛ መቀዣበር ውስጥ ይገባሉ፡፡ እና ወጣት ሴቶች ቶሎ ወልደው ወደዚህ የመቀዣበር ዓለም እንዲዘፈቁ ሳያሰልሱ ይመክራሉ “ውለጅ እንጂ!'' ሲሉ እኔ “ያዬሁትን ደስታ እይ'' ማለት ብቻ አይደለም፣ “የቀመስኩትን ፍዳ አንችም ቅመሽ'' የሚል ምቀኝነትም ውስጡ ያለ ይመስለኛል፡፡ እና ስለወለድኩ ብቻ ጓደኛቼው ሊያደርጉኝ ይፈልጋሉ፣ ወሪያቼው ይደክመኛል፡፡ አንድኛቼውም ስለ ድሮ ፍቅረኛቼው አያወሩም፤ ከእናታቼው ማሕፀን ሲወጡ ባሎቻቼው በማቀፊያ እየተቀበሉ _ ወደየቤታቼው የወሰዷቼው ይመስል... ስለ ትላንት፣ ስላለፉበት ሕይወት ቢሞቱ አያወሩም፡፡

እኔ ስለ ትዳር፣ ስለ ላጅ ልቤ አርፎ ማውራት አልቾልም :: ገና ነኝ፣ ያልተዘጋ የሕይወት ሒሳብ በልቡ አልነነ ታት ለመንገድ መሳሳም፣ በየጢሻው መጓተት፣ በ Rot ቤቱ ጨለማ መጎነታተል ልቤ ይሸል፡፡ ገና ነኝ ሥጋዬ እንጂ፣ ነፍሴ ለእናትነት አልተዘጋጀችም፤ ጨዋ ሚስት አይደለሁም፡፡ ምናለ ዳይፐርና ምናምናችሁን ይዛችሁ ወደዚያ ብትሄዱልኝ፡፡ የሚሰትር ነገር ይሰትራቼውና “እንዲህ በወጣትነት በትዳር መሰተር መባረክ ነው!” ይሉኛል፡፡ ነፍሶብኛል፣ውስጤ አውሎ ነፋስ አለ፣ እንደ ፊኛ ውስጤን ሞልቶ አቅልሎኛል፣ ወደነፈሰበት እንድንሳፈፍ አድርጎኛል፣ ይኼ ባል የሚባለው ሰውዬ የነፋስ ጣት ላይ ነው ቀለበቱን ያጠለቀው፡፡ አንዳንዴ ልጄን ለሆነ ሰው መስጠት ያምረኛል፣ ወይም ልጄን ለባሌ እናት ሰጥቼ፣ በዚያው ፍርድቤት ጎራ ብዬ የፍች ወረቀት ማስጻፍና በሰው ልኬለት ወደዚህ ቤት አለመመለስ። ሐሳቤ ያስደነግጠኝና ዜማን እንስቼ ጥብቅ አድርጌ አቅፋታለሁ፤ ሁልጊዜም ውስጤ ይቅርታ ይጠይቃታል፡፡ ይቅርታ ስላት አባባ ትዝ ይለኛል:: ላገባ ሁለት _ ሳምንት ሲቀረኝ አባባ አድርጎት የማያውቀውን «እስኪ ዛሬ ራት ልጋብዝሸ!» አለኝ፡፡ ደስ ብሎኝ ተያይዘን ወጣን፡፡ ራት በልተን፣ ስናወራ “ማኅደሬ መቼም ላንችም፣ ለወንድሞችሽም ያለፈው ጊዜ ቀላል አልነበረም፤ ከዚያች ሴት ስለወለድኳችሁ ይቅርታ አድርጊልኝ፡፡ ሰው ነኝና ወድጃት ነበር፤ ግን ሁኔታዋን ከጅምሩ እያዬሁ፣ እናተንም መውለዴ ራስ ወዳድነቴ ጭፍን ቢያደርገኝ ነው"አለኝ፡፡ እኔም ገና ካሁኑ ከባለቤቴ ስለወለድኳት ሳይሆን፣ በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሆኜ ስለወለድኳት ይቅርታ ይላል ውስጤ፡፡ በእግሮች መካከል... ፈጣሪ ሴትን ልጅ ድንግል አድርጎ የፈጠራት ለምንድን ነው? ምናልባት ከምታገባው ወንድ ውጭ ሄዳ እንዲህ ዓይነት መዘበራረቅ ውስጥ እንዳትገባ ልዩ የተፈጥሮ ማስጠንቀቂያ ይሆን!? ድንግልና ከልባችን እና ከአእምሯችን ጋር የተያያዘ

የሴትነታችን ማዕከል ይሆን? ወይስ ዙሪያችንን እንደ መንፈስ የከበበን የማይታይ ስስ መስተዋት? ለምን ሴቶች ብቻ ተለይተን እንደዚያ ተፈጠርን? 'ኦዲተር' ነበርኩና አንድ ነገር አውቃለሁ፤ የከበረ ነገር የተቀመጠበት ካዝና ምንጊዜም በጥብቅ ማኅተም የታሸገ ነው፡፡ ምን ችግር አለው ማንስ ቢከፍተው? ይሉት አጉል ፈሊጥ ከዬት የመጣ ጅል ሐሳብ ነው?! ከጋብቻ በፊት ወሲብ ምንም ችግር የለውም ያሉኝ አሁን የት ናቸው!? እውነት ነው የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም፤ ግን ስንደናበር የደፋነውን ውሃ መደፋቱ ልክ ነበር ማለት የጅል ሙግት፣ መራርም ቀልድ ነው፡፡ በተለይ የሚያሳዝነው እንደፈለገ የሚረግጥ ወንድ እግር ሥር ብርጭቋችንን ከከበረ መደርደሪያው አውርደን _ ማስቀመጣችን፤ ጎንበስ ብሎ እንኳን ምን ተሰበረ? ምንስ ተደፋ ለማይል ደንታ ቢስ- ሂያጅ! ከጋብቻ በፊት ወሲብ፣ ከጋብቻ በፊት ዕልል ያልተባለለት ጋብቻ መሆኑን እንዴት አልነገሩኝም!? ጉዳዩ የአምስት ደቂቃ ያበደ የሥጋ ፍላጎት ብቻ ነው እንዴ!? የሚተኛን ወንድ በእግራችን መኻል አልፎ የሚሄድ መንገደኛ ነው? የሴት ልጅ እግሮች የከተማ መግቢያ ላይ እንደተተከለ የእንኳን ደህና መጣችሁ 'ቅስት' ናቸው፤ በዚያ አልፎ ወደልባችን ከተማ የሚገባ ጸጉረ ልውጥ መቼ እንደሚወጣ ማን ያውቃል ?...
👍385👏1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ስድስት


ባምንም ባላምንም ተደፍሪያለሁ!

መደፈር ጉልበተኛ እጅ እና እጅን ይዞ፣ በጉልበቱ በፈለቀቃቼው እግሮች መኸራ ገብቶ፣ ኃጢያቱን መድፋት ብቻ አይደለም፡፡ ለምኖ፣ ተለመማምጦ፣ እባክህ ብሎ፣ እግር ሥር ወድቆ መደፈርም አለ፡፡ እንደ እኔ እነደ እኔ አብሮ መተኛት ሳይፈልጉ በፍቅር የመገደድ፣ በክብር በገንዘብ የመገደድ፣ በትዳር የመገደድ (ሚስት ነሽ ታዲያ ምን ትሆኝ? ተብሎ) የመገደድ ዓይነቱ ብዙ ነው። ዕድሜሽ አመለጠሽ ቶሎ ውለጂ ተብሎ፣ ልብ ያልከጀለውን በጀርባ ተንበልብሎ መቀበል፤ ሕግ መደፈር የማይለው ብዙ ነው ዓይነቱ፤ ለዚሀ ዓይነቱ ችሎት አይቆምም፡፡ ሕዝቡም ይላል “ወደሽ ከተደፋሽ፣ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” ወደው ከተደፉልን አይዟችሁ ብሎ ማንሳት ጽድቅ፣ መርገጥም መብት ነው ሲሉን፡፡ በወደውናል ሰበብ ስንቶቹን ረገጥን፣ በስንቶቹ ተረገጥን? የእግራችን ዳና ወደውን በጎነበሱልን ልብ ላይ ሕያው ሆኖ ታትሟል “የወደዱትን ቢያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ'' በሚል ብሒል ትተናቼው ስንሄድ ለሌላዋ ባል ሆነው፤ ትተውን ሲሄዱ ለሌላው ሚስት ሆነን፣ ያልታደለ ባል በልባችን ጫካ ማንም ያልሄደበት መንገድ ሊመሠርት ደፋ ቀና ይላል። ሁሉም ልብ ገጣባ፣ እግር የለመደ መንገድ፣ ባል ይሁን ውሽማ፣ “ቦይ ፍሬንድ' ይሁን ምን፣ ያው ተራማጅ ነው የሚሉ የደከማቼው ሚስቶች። ሴት ልጆቻቼውን “ከወንድ ተጠንቀቁ!” እያሉ የሚመክሩ! “ተጠንቀቁ! ወንዶች ቀጣፊ ፍጥረቶች ናቸው" ወንድ ልጆቻቼው ይኼን ቁጭ ብለው ይመዘግባሉ፣ እኩል ከከሬሜላ ጋር መጥምጠውት ያድጋሉ፣ እናም ከፍ ሲሉ.. “ቀጣፊ የሆንኩት ፈልጌ አይደለም፣ ወንድ አድርጎ የፈጠረኝን አምላክ ጠይቁት! ካላመናችሁ እናቴንም ጠይቋት ሁለተኛ ምስክር ናት'' ይላሉ፡፡ አይሄድም ወይ ይኼ ሰው? ባለቤቴ ዮናስ ረፍት ብሎ ከአሜሪካ ከመጠ በኋላ፣ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ እዚሁ ቆዬ፡፡ አትሄድም እንዴ? ብዬ በግልጽ ባልጠይቀውም(ምን አላት ከመሄዴ? እኔን ነው አሜሪካን የወደደችው? እንዳይል ፈርቼ) ውስጤ ግን ይዞኝ ከዚህ አገር

ይሸሻል ብዬ የተደበቅሁበት ሰውዬ፣ በማላውቀው ምክንያት ከአሜሪካ እየሸሸ እኔ ውስጥ መደበቅ መጀመሩ አስገርሞኝም ግራ አጋብቶኝም ነበር “ሲትዝን ስለሆንኩ ችግር የለውም ቆይቼ እሄዳለሁ” ይላል፣ ሰልጠይቀው። እናቱና እህቶቹ በመቶ ት ደስ ብሏቼው እንዲያውም ረፍቱን አራዝሞ እንዲቆይ ይነዘንዙታል፤ እኔስ? እላለሁ በውስጤ እኔስ? በቃ እዚህ ግቢ እየተብሰለሰልኩ ዕድሜዬን ልፍጅ ...12 አንድ ቀን ታዲያ ራት ይዞኝ ወጣና በምሽቱ መርዶ አረዳኝ “ማሬ በቃ እዚሁ አገሬ ላይ ለመኖር ወስኛለሁ።" “ምን ማለት ነው እዚሁ ...?" “እዚሁ ኢትዮጵያ ነዋ!'' “እየቀለድክ ነው?'' “ኖ! ቀልድ አይደለም፣ የምመጣበት አሳማኝ ሰበብ አጥቼ እንጂ፣ ካሰብኩበት ቆይቻለሁ፡፡ አሁን አንቺ አለሽ፣ የአብዬ አለች (ልጃችንን)ምን አደርጋለሁ እዚያ? አእምሮዬ _ እንደ _ አሸን የሚፈላ እንግሊዝኛ ቃል ለመተርጎም ሲታገል መዋል ሰልችቶታል፡፡ ለመኖር መስማት አለብኝ፣ መረዳት አለብኝ፡፡ አገሬ ላይ መላ ሰውነቴ ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ጸጉሬ ቋንቋዬን ይረዳል... የኔ ነዋ! እዚያ ምን አለኝ? ባሀላቼው፣ ቋንቋቼው፣ ሳቃቼው፣ ለቅሷቼው፣ ሰላምታቼው፣ ፍቅርና ጥላቻቼው፣ ለእኔ የመኖርና ያለመኖር ትግል ነው፡፡ አስቤ እስቃለሁ፣አስቤ አዝናለሁ የምረዳቼው ቋንቋቼው በገባኝ ልክ ብቻ ነው፤ የሚያውቁኝ በምሠራው ሥራና ራሴን መግለጽ በቻልኩበት ልክ ነው፤ ሳንተዋወቅ የምንተዋወቅ መስለን እንኖራለን። ይከፍሉኛል - አገለግላለሁ።ሌላ ሕይወት የለም። ብሞት አያዝኑም፣ሌላ ሰው ይቀጥራሉ። ብደሰት ደስታዬ አያስደስታቼውም። የምለውን ካልኖርሽው አትረጂውም፤ አጉል ፍልስፍና ሊመስልሽ ይችላል።'' በግርምት ዝም ብዬ አዬዋለሁ፤ ፊቱን በአንዴ ያጥለቀለቀው ምሬት ያንን ሁሉ ሳቅና ፈገግታ በምኔው ሸፈነው? እያልኩ እገረማለሁ ...

“…እንዴት እንደማስረዳሽ አላውቅም፣ ጧት የስልክ 'አላርም' እያንባረቀ፣ ሰውነቴን ጨርሶታል። ስንት ቀን ነው እንቅልፍ አስክሮኝ በጉልበቴ እየዳህኩ ወደ መታጠቢያ ቤት የሄድኩት? ሁሉም ነገር ይቅርብኝ አገሬ መጥቼ አንዲት ፍራሽ ብቻ ያለችባት ቤት፣ ማንም ሳይቀሰቅሰኝ እስኪበቃኝ ለመተኛት ተመኝቻለሁ። በእንቅልፍ እጦት የተጥመለመለች ነፍሴ ቀኗን የምትገፋው በቡናና ቀዝቃዛ ውሃ ምርኩዝ ተደግፋ እያነከሰች ነበር:: ከሩቅ በቅዳሴና አዛን ድምፅ እንደ እናት አባብሎ የሚቀሰቅስ አገር ላደገ ሰው፣ የአላርም'ጩኸት ቀውስ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ የጠላት ድምፅ ነው. ምን ትዘፈዘፋለህ? የአባትህ ቤት መሰለህ? ለባርነት ነው ያመጠንህ ተነስ ግርድናህን ጀምር' የሚል የፈረንጅ ድምፅ ነው። ጽዳት ሥራዬ ነው...ዶላር የማገኝበት፣ ቤተሰቦቼን ያንደላቀኩበት ሥራዬ ነው፤ ግን እገረማለሁ የቆሻሻም ዓይነት አለው፡፡ ቆሻሻ ሁሉ ቆሻሻ እንዳይመስልሽ፡፡ የቤት ጥራጊያችንን ተመልከች፣ ቄጤማው፣ የዳቦ ፍርፋሪው፣የጫት ገረባው፣ ሲሞላልን የተራረፈ ምግብ... የፈረንጅ ቆሻሻ ገራገር አይደለም፤ ሽታው እንደ ብረት የጠጠረ ክርፋት ነው፤ ቆሻሻ ሁሉ ቆሻሻ አይደለም። የቆሻሻቼውን ጭካኔ የሚነግርሽ የበሽታቼው ክፋት ነው፤ዳማከሴ የማይፈውሰው መርገምት። ዓለም አሻግሮ በጉጉት የሚያዬው ዘመናዊ ሕክምናቼውና ጥበባቼው የማያድነው መቅሰፍት ነው፡፡ “አሰለቼሁሽ መሰል በምሬት?'' “አይ! እዬሰማሁህ ነው" አልኩ፡፡ እውነቴን ነበር እንደዚያን ጊዜም ሰምቼው አላውቅም። በረዥሙ ተነፈሰና ሩቅ እያዬ በትካዜ ሥራዬ...ቀን ታክሲ እነዳለሁ፣ ማታ Oሥራ ሁለት ፎቅ ያለው ሆስፒታል ውስጥ ከሌሎች መሰሎቸ ጋር ጽዳት እሠራለሁ፡፡ እዚያ ኢራቅና አፍጋኒስታን ሽብርተኛ ተዋጉ _ ለሚሏቼው ወታደሮቻቼው _ ሜዳሊያ ቢሰጡም፣ የአሜሪካ ሕዝብ በዕለት ከዕለት ኑሮው ከሚያመርተው ቫይረስ እና

ጀርም አንገት ላንገት ተናንቆ፣ ከእልቂት የሚጠብቀው ስደተኛው የጽዳት ሠራተኛ ነው- እኔና ወገኖቼ። እንደ ዘይት የረጋ ሺንታቼውን፣ እንደ ወተት ከነጣ የመጸዳጃ ቤት ሰሃኖቻቸው ላይ ማጽዳት ነው ሥራዬ፤ በላስቲክ ጆንያ የሞላ የምግብ ትራፊና አፍ ማበሻ ወረቀታቼውን ማንሳት ነው ሥራዬ፤ የሚቀረና የፕላስቲክ ቡና መጠጫ ኩባያቼውን መሰብሰብ ነው ሥራዬ፤ ቡና እንዴት እንደዚያ ይቀረናል? ቡና ሲባል፣ እጣንና ሉባንጃ የሚያስታውሰው አእምሮዬ ዛሬ ላይ ቡና ሲባል፣ ያንን ክርፋት ነው በምሬት የሚያስታውሰው፡፡ ከዓመት ዓመት ፀሐይ የማይደርስበት ቀዝቃዛ ስሚንቷቼውን በበረኪና ማጠብ ነው ሥራዬ፣ አገሬ ላይ መኖር እፈልጋለሁ፤ ሕዝቡ ደግ-ሆነ ክፉ ግድ የለኝም፡፡ ኑሮው ተወደደ- ረከሰ ግዴለኝም። ከስደት የከፋ መንፈስን ሽባ የሚያደርግ ክፋት የለም፡፡ ድህነት ወለል ላይ ቆሜ ሸቅብ ስመለከት፣ ገንዘብ የሰማይ ጥግ መስሎኝ ነበር፤ እጄ ላይ ሲገባ የሰው መንፈስ እንደህዋ ወሰን የለሸ መሆኑ ገባኝ፤ በገንዘብ የማይሰፈር ረቂቅ ነገር! ይኼን ለሰው ባወራ ጥጋበኛ እባላለሁ አውቃለሁ፤ ድህነት አንዱ የሚነጥቀን ነገር ትክክለኛ ፍርድን ነው። ስንቱ ሥጋው በርሃብ በሚረግፍበት አገር መንፈሴ፣ ነፍሴ ብል መሞላቀቅ ተደርጎ እንደሚታይ አውቃለሁ፡፡ እህቶቼ ተምረው ለወግ ማዕረግ በቅተውልኛል፡፡ ብር ከሆነ እግዚአብሔር ይመስገን የሚበቃኝን ያኽል ይዣለሁ፤ባይበቃም በረከት ከላይ ከሰማይ መሆኑን ካመንኩ ቆይቻለሁ፡፡ ምን አደርጋለሁ እዚያ...? ወደዚህች ምድር የመጣነው በእንግድነት ነው፤ ጭራሽ እንግዳ ሆነን ወደሌሎች ምድር እንሄዳለን፡፡ ስደት
👍416🔥2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ሰባት


“እያንዳንዱ ጓደኝነት ውስጥ ትንሽ ትንሽ ጠላትነት አለ!”

ሃይማኖት!

እንደ እኔ መልኳ ብዙም ለማይስብ ሴት፣ ጥሩ አፍቃሪ ማግኜት ከረዥም ዛፍ ላይ በአጭር ቁመት ፍሬ ለማውረድ እንደመሞከር ነው “ሴትነት” ብቻውን በቂ አይደለም፤ ፍሬውን ማውረጃ አንዳች ዘንግ ያስፈልጋል፡፡ ፍሬው ላይ የሚደርስ የትምህርት ፣ የገንዘብ ፣ የጥሩ ምላስ፣ ባለቤት መሆን ያስፈልጋል፤ አልያም ቁመትን የሚያረዝም የጥሩ ቤተሰብ መሰላል ላይ መቆም፡፡ ይኼን ዘንግ በእጄ እስክጨብጥ ስንቱ ያስጎመጄኝ ፍሬ የወፍ ሲሳይ ሆነ፡፡ ተስፋ አስቆራጭ መልክ ነው ያለኝ፡፡ በዚያ ብኩለው በዚህ አስቀያሚነቱ እየባሰበት የሚሄድ፡፡ ምንሽ ነው የሚያስጠላው? ቢሉኝ አላውቅም፤ ግን እንዲሁ መልኬ ቆሜ እያዩኝ እዚያው በቆምኩበት የሚረሳ ዓይነት ነው፡፡ ሰው ካልታወሰ ምኑ ይፈቀራል? የመፈቀር ተቃራኒው መጠላት አይደለም፤ መረሳት ነው፡፡ ማንም የሚያፈቅረውን አይረሳም፤ እኔ ግን ሰዎች አእምሮ ውስጥ በትዝታ መዝገብ እንዳልጻፍ የተረገምኩ ይመስለኛል፡፡ በዚህ እና በሌላ ሌላ ብዙ ምክንያቶች ስለ ራሴ ከማሰብ ይልቅ፣ ስለሌሎች ጉዳይ በማያገባኝ ገብቼ መፈትፈት እወዳለሁ፡፡ ሌሎች ላይ ለመድረስ ሳይሆን ከራሴ ለመሸሽ።

አብሮ አደግ ጓደኛዬ ማኅደረን ጨምሮ የሚቀርቡኝ ሁሉ “ለግጥምና ሥነ-ጽሑፍ ሟች ነሽ' ይሉኛል፣ አይደለሁም። የሚሞትለት ነገር ጠፋ እንዴ? እንዲያውም ግጥም የሚሉትን ነገር አልወድም፤ ምኑም አይጥመኝም፡፡ ግጥም በተለይ ረዥም ግጥም፣ የጅል ለቅሶ ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ ገጣሚዎች በአቀራረባቼው እና ቀለል አድርገው በሚያነሱት ሀሳብ ያስቁኛል፣ ሳቅ ማን ይጠላል? በተለይ እኔ ሳቅ በሁለት ምክንያት እወዳለሁ...የመጀመሪያው ሳቅ ያው ሳቅ ስለሆነ ነው፣ ሁለተኛው ግን ጥርስሽ ያምራል ስለሚሉኝ ስስቅ እኩል ሁለት ደስታዎችን ስለማጣጥም ነው፤ በአንድ የሳቅ ጠጠር፣ ሁለት የደስታ ወፍ እንደማውረድ። የሆነ ሆኖ እንደዚያ ዓይነት ግጥሞችን፣ ፍቅረኛዬ ቶማስ ዝርው፣ተራ፣ ገለባ ናቸው ይላቼዋል፡፡ እሱ ራሱ ዝርው ተራና ገለባ የሆነ ልጅ ነበር፡፡ “ትንሽ ካላሳሰቡሽ ምኑን ግጥም ሆኑ?'' የሚለው ነገር አለ (ግድ ካላሰብኩ ብሎ ነገር!) አስበን የምንደርስበትን እዚያው አስበው ፍሬ ነገሩን ከነገሩን ምን አደከመን? ዘመናችን የጥድፊያ ነው፣ ቁጭ ብሎ ለመቆዘም ፋታ አይሰጥም። ሥራችን ነው ካሉ፣ እዚያው ቆዝመውም ይሁን ተጨንቀው፣ ሊሉን የፈለጉትን በአጭርና በግልጽ ቋንቋ ይንገሩን። ቢሆንም ፍቅረኛዬ ቶማስ የተመረቀው በሥነ-ጽሑፍ ምናምን ነውና በዚህ ጉዳይ ገፍቼ አልከራከረውም፡፡ ለነገሩ በምንም ጉዳይ አልከራከረውም። ቶማስ ውስጡ የተቀበረ ቁጭት አለበት፣ ሰዎች ሲጨበጨብላቼው ይበሳጫል። አንዳንዴ ደግሞ ስም የሌለው ገጣሚ በታዋቂዎቹ መካከል ግጥም ሲያቀርብ እና ከተመልካቹ ቀዝቀዝ ያለ ጭብጨባ ሲቼረው፣ ቶማስ ረዢምና ደማቅ ጭብጨባ ያጨበጭባል፣ ሊቆም የሚያዘግመው ጭብጨባ እንደገና ነፍስ ይዘራል፡፡ ቶማስ ለታዋቂ ገጣሚያን ጥላቻ እንዳለበት እረዳለሁ። ገጣሚያን ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ታዋቂ ሰው ያበሳጨዋል፤ በተለይ ኢትዮጵያዊ፣ ግን ለምን ብዬ አልጠይቀውም ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ግጥም እንደሚጽፍ ቢነግረኝም፣ በሦስት ዓመት ቆይታችን አንድም _ መስመር ጽፎ ዓይቼ አላውቅም፡፡ _ አይደለምና / ግጥም፣ መደበኛውን መጻፍና ማንበብ መቻሉ እስኪያጠራጥረኝ፣ እጁ ላይ ብዕርም መጽሐፍም ዓይቼ አላውቅም፤ ግድ አይሰጠኝም፡፡

ቶማስ ጋር እንዴት ፍቅረኞች ሆንን? በፍቅሩ ወድቄ ነው? አይደለም፡፡ ፍቅረኛ የሆንበት ብቼኛ ምክንያት ታክሲ ውስጥ ገብቼ ጎኑ ስቀመጥ ገና በወጉ እንኳን ተደላድዬ ሳልቀመጥ “ኦህ! ጥርስሽ እንዴት ያምራል!'' ስላለኝ ብቻ ነው፡፡ ዞር ብዬ አዬሁት፣ ብጉራም ነው እንጂ መልኩ ደህና ነው “አመሰግናለሁ” ብዬ ልዘጋው እቺል ነበር፡፡ ግን በሕይወቴ እንደ ፀሐይ ግርዶሽ በስንት አንድ ጊዜ ያውም ከማያውቀኝ ወንድ የሚሰነዘር አድናቆት እንደ ተራ ነገር ማለፍ የምችል ልጅ አልነበርኩም። አድናቆት ያሳሳኛል፤ የሚያደንቁኝ ሰዎች ጻድቃን ነው የሚመስሉኝ፡፡ ፈገግ ብዬ፣ “ገና ከመግባቴ ...የት አዬኸው ጥርሴን?'' አልኩት፡፡ ይኼ ፈገግታዬ ድፍረት ሰጥቶት ወሬ ጀመርን፡፡ እና ልክ እንደፈላስፎች በቀልድ የሌለውን ፂም እየጎተተ “ታክሲ ውስጥ ከመግባትሽ በፊት ጓደኛሽ ጋር ስትሰነባበች ፈገግ ብለሽ አልነበረምን?'' አለ፡፡ የእውነት አሳቀኝ። እጁን ዘርግቶ “ቶማስ እባላለሁ' አለኝ፡፡ ጨበጥኩት፤ የሴት እጅ እንኳን እንደዚያ አይለሰልስም፡፡ የእጁ ልስላሴ የተለዬ ምቾት ይፈጥራል፡፡ እንዲህ ተዋወቅን፡፡ የዚያን ቀን ስልኬን ሲጠይቀኝ አልከለከልኩትም፤ ግን ይደውላል ብዬ አላስብኩም ነበር፡፡ ላግኝሽ ሲለኝ አልከለከልኩትም፣ግን ቀጥሮኝ ይቀራል ብዬ ፈርቼ ነበር። ልሳምሽ ሲለኝ አልከለከልኩትም፣ ልተኛሽ ሲለኝ አልከለከልኩትም...አብረን የተኛን ቀን አለቀሰ፡፡ እስካሁንም ያ ነገር አንጀቴን ይበላኛል፡፡ እዚህ የጡት ዘር ያልፈጠረበት ባዶ ደረቴ ላይ ተለጥፎ አለቀሰ፡፡ ምንም ነገር ከልክዬው አላውቅም፡፡ እንደማያፈቅረኝ አውቃለሁ፣ እኔም አላፈቅረውም ነበርና ግድ አልነበረኝም። ሥራ አልነበረውም፤ ሳውቀው ጀምሮ ሥራ አልነበረውም። ሥራ ሲፈልግም አይቼው አላውቅም፤ እሱም ያን ያኽል አሳስቦኝ አያውቅም፡፡ እንዲያውም የሻይ እያልኩ በየወሩ የተወሰነ ብር እሰጠው ነበር፡፡ ይኼ ነገር ውለታ ሆኖበት ይሁን ወይም ሌላ መሄጃ ስለሌለው እንጃ እስከ መጨረሻው ከእኔ ጋር ነበር፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነጽሑፍ ተመርቆ ለሦስት ዓመት ሥራ ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ እንዴት እንደሚኖር ለራሴም ይገርመኛል፡፡ግን ጠይቄው አላውቅም፡፡ እየቆዬ ሲገባኝ እሱም ከእኔ በባሰ ሁኔታ የተገፋና በራስ መተማመኑ የተንኮታኮተ ልጅ ነበር፡፡ ልዩነታችን ይኼን መገፋታችንን የተቀበልንበት መንገድ ላይ ነበር፡፡ እኔ ወደ ውስጤ ኖርኩት፤ እሱ በጥላቻ፣ በጠብ፣ በማማረር እና ሌሎችን በማናናቅ ኖረው። መሠረታዊ ችግራችን ግን ያው መገፋት ነበር፡፡ ከጓደኛዬ ማኅደረ ሰላም ፍቅረኛ አብርሃም ውጭ ቶማስን የሚወደው ይቅርና አብሮት ለደቂቃዎች መቀመጥ የሚፈልግ አንድም ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ የሰው ዘር በሙሉ ክንፍ ያለው መልአክ ነው ብላ ልትከራከር የሚቃጣት ጓደኛዬ ማኅደረ እንኳን ቶማስን አትወደውም ነበር፡፡ “አልፈሽ ልትወጂው ብትሞክሪ እንኳን ዙሪያውን በእሾህ አጥር የታጠረ ልጅ ነው፣ በዬት ሽንቁር አልፈሽ እንደወደድሽው እንጃልሽ'' ትለኛለች፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ጋር ነው የኖርኩት። “በፍቅር”፡፡ የሆነ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት ላይ እንደ ፍቅረኛ ክንዴን ይዞ የወሰደኝ ቶማስ ነበር። ለእኔ ይኼ ማለት ብዙ ነገር ነው፡፡ ለቅሶ ቤት ይውሰደኝ፣ ሰርግ ቤት ጉዳዬ አልነበረም፤ ሳያፍርብኝ እጄን ይዞ ሰው መኻል የሚገኝ ሰው ከጎኔ መኖሩ ብቻውን የሚሰጠኝ ስሜት የተለዬ ነበር። ከዚያ በኋላ ብዙ የሥነ-ጽሑፍና የግጥም ዝግጅቶች ላይ ቶማስ ጋርም ይሁን ብቻዬን እገኝ ነበር። እንዲሁ የግጥም ምሽቶች ላይ መገኜት የሆነ ዘመናዊነት ነገር አለው አይደል?! የሥዕል ኤግዝቢሽን፣ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ምናምን? በተለይ “ምሽት'' የሚለው ደስ ይላል። "Maslow's hierarchy of needs" እንደሚነግረን የሰው ልጅ የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን ካገኜ በኋላ ጥጋብና ብርዱን ከመከላከል ባለፈ የመታዬት፣ የመወደድ ፍላጎቱን ለማርካት ይታትራል። ምንም ደሃ አገር ብንኖር
👍418
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ስምንት

አባቶች!

ንጹህና የሚቀዘቅዝ ክፍል ነበር፣ አብረን ከገባን በኋላ፣ አልጋ ላይ ተቀምጦ በእጁ አልጋውን መታ መታ እያደረገ ነይ እዚህ አለኝ፡፡ ቀስ ብዬ ሄጄ ተቀመጥኩ.. ይጣደፋል ክፉኛ ይጣደፋል፡፡ በበኩሌ በአጓጊ _ ሕልም ውስጥ እንዳለሁ ዓይነት ነገሮች ሁሉ ድንገት ባንኜ የሚቋረጡ እየመሰለኝ ነበር፡፡ በዝምታ አድርጊ የሚለኝን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ ጓጉቻለሁ፣ አውቃለሁ ምን እንደሚሆን፣ ጣቴን የምጠባ ሕፃን አይደለሁም፡፡ ከሆነም እዚህ ሰው ጋር መሆኑ የተለዬ ተአምር ነበር- ለእኔ፡፡ እንዲያውም በመኻል “አይ ይቅርብን' ብሎ ተነስቶ እንዳይሄድ እየፈራሁ ነበር፡፡ አጠቃላይ ለነገሩ አዲስ መሆኔና ድንገተኛ ነገር መሆኑ ከፈጠረብኝ መደነባበርና ጭንቀት ውጭ፣ ይኼ ሰው ምንም ቢያደርገኝ ምንም ቅሬታ አልነበረኝም፡፡ይኼ ቆንጆ ሰውዬ፣ ሀብታም ሰውዬ፣ ሳቂታ ሰውዬ፣ ቆንጆ ሚስት ያለችው ሰውዬ፣የሰፈሩ ሰው ሁሉ የሚያከብረው እና የሚወደው ሰውዬ፣ ምንድን ነው እኔ ጋር የሚሠራው “ጫማሽን አውልቂና ከፍ ብለሽ ተቀመጭ፣ አይዞሽ አትፍሪ"...እንዳለኝ አደረግሁ። ጉርድ ቀሚሴ ያጋለጠውን እግሬን እያዬ እና የሸሚዙን ቁልፍ እየፈታ... "ይኼ እግርሽ እንዴት እንደሚያምር ሰዎች አልነገሩሽም...'' አለኝ፡፡ አቀርቅሬ ዝም አልኩ፡፡ ሸሚዙን አውልቆ ወደ ጎን ወርወር አደረገና እጁን የተጋለጠ ጉልበቴ ላይ አሳረፈ ቀስ አድርጎ ወደ ራሱ ሳበኝ ... ደረቱ ላይ ተለጠፍኩ። እጁን ልኮ ከማነሳቼው ብዛት ለመቆንጠጥ እንኳን የሚያስቸግሩ ጡቶቼን ሲነካካኝ፣ ባለ በሌለ ኃይሌ ታፋዬን ገጥሜ ትንፋሼን ዋጥኩ፡፡ ልብሴን ቀስ በቀስ ሲያወልቅልኝ፣ በዝምታ ነበር የተባበርኩት፡፡ ተንጠራርቶ መብራቱን አጠፋው እፎይታ ተሰማኝ፡፡ አንሶላው ደስ የሚል ሽታ አለው፡፡ ከዚያ በኋላ የሆነው ሁሉ ፈጣንና ግራ አጋቢ ሕልም ነበር ሕመም፣ ደስታ፣ የማላውቀው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበር የሚሰማኝ፡፡ በዓለም ላይ እንደ እኔ የሚፈቀር ሰው ያለ መስሎ አልተሰማኝም። ወንዶች ይጸዬፉኛል ብዬ አስብ ነበር፣ እንደዚህ ዓይነት ቆንጆ

ሀብታም፣ አገር ያደነቃት ውብ ሚስት ያለችው ሰውዬ ከንፈሬን፣ ጉንጨን፣ አንገቴን ሲስመኝ ዕንባዬ እየፈሰሰ በሁለት እጆቼ እስከቻልኩት ተጠምጥሜበት ሳላስበው? “ጋሽ ዓለምነህ'' አልኩት:: “ወይዬ! የኔ ጣፋጭ” እንዲሁ ነበር ያለኝ “የእኔ ጣፋጭ!"... “እግባኝ!” አልኩት። ጨለማ ነውና መልኩን ባላዬውም ትንታ ከምትመስል አተነፋፈሱ ሳቁ ያመለጠው ይመስለኛል። ዛሬ ላይ ሳስበው የሚያሳፍረኝም የሚያስቀኝም፣ ነገር ነው ይኼ... ቃሉ ራሱ “አግባኝ!'' ጨርሶ ሲነሳ መብራቱን አበራና የአልጋ ልብሱን ገልቦ የሆነ ነገር ተመለከተ፣ ሰውነቴን በእጄ ሸፈንኩ፡፡ “አመመሽ እንዴ?” “አይ! ደህና ነኝ!'” አልኩ እውነታው ግን፣ የሆነ ነገር ውስጤ የቀረ ዓይነት ኃይለኛ የማቃጠልና ታፋና ታፋዬ መገጣጠሚያ ላይ ሕመም እየተሰማኝ ነበር፡፡ “ሃሃሃሃ… የዛሬ ልጆች እሳቶች!'' እያለ ወደ ሻወር ገባ፡፡ ምን ማለት ነው እሳቶች!? ወደ ሻወር እንደገባ በፍጥነት አንሶላውን ገለጥኩና ሲባል የሰማሁትን ብር አምባር ነገር ፈለግሁ፡፡ አንሶላው ላይ ምንም ዓይነት ደም አልነበረም፤ የሆነ የተሳሳተ ነገር አለ? አልኩ ለራሴ፡፡ የሰማሁት እንደዚህ አልነበረም፣ ደም መኖር አለበት፣ ደም! ፊልሙ፣ መጽሐፉ፣ ወሬው ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገር ያደረገች ሴት፣ ነጭ አንሶላ ጋር ትፋጠጣለች አላሉኝም፡፡ ከዚያ በፊት ወንድ የሚባል ባላውቅም፣ ምንም ደም አልነበረም፤ ጋሽ ዓለምነህ እንዳላመነኝ ያወቅሁት ቆይቶ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ለወራት ነክቶኝ አያውቅም፡፡ እንዲያውም መንገድም ላይ ሲያዬን አልፎን ነበር የሚሄደው።

የሆነውን ሁሉ በውስጤ አፍኜ እንደገና ላዬው እጓጓ ነበር፡፡ እንዲያውም ይኼን ሁሉ ያደረገ እሱ እያለ ለዓይን ያስጠላችኝ ሚስቱ እትዬ ሆህተ ነበረች፡፡ ሳያት እና ለሁሉ ደግሞ ሁልጊዜ “እንደም? ዋልሽ? ሃይሚዬ” ትለኛለች፡፡ ልክ ባጠገቧ እንደ ዳልሁ። እንደ ማንም ሕፃን ነበር የምታዩኝ፡፡ በየኋት ቁጥር ወደ አእምሮዬ የሚመጠወ ልፍ ዓለምነህ ጋር አጉል ነገር እያደረጉ “የኔ ጠፋጬ!'” ሲላት ነው። ለመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተኙ ደም ዓይታ ይሆን? መሆን አለበት፣ እንዲህ እያልኩ አስባለሁ፡፡ እንዳንድ ማታ፣ ባልና ሚስቱ ተያይዘው በሰፈር ሲያልፉ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁለቱም ሰላም ይሉኛል፡፡ ታዲያ እፈራለሁ ድንገት እትዬ ሆሀተ ጠርታኝ “ሃይማኖት! የሚነግረኝ ነገር እውነት ነው ባሌ ጋር ተኝተሻል?'' የምትለኝ፣የምታሳስረኝ፣ ሰፈር ውስጥ የምታዋርደኝ፣ እንደዚያ እንደዚያ ዓይነት ሐሳብ ውስጤ እየገባ እንደ ብርድ ያንዘፈዝፈኛል፡፡

አንዴ ታዲያ ጋሽ ዓለምነህ ከትምህርት ቤት ስንመለስ አገኜንና፣ የተወውን መሸኜት ትዝ ያለው ይመስል ግቡ አለን፣ ገባን፡፡ ስለትምህርት ምናምን እያወራን ማኅደረን ሜክሲኮ አወረዳትና ብቻችንን ስንቀር ያለምንም ዙሪያ ጥምጥም ምን አለኝ ...

“ይች ...ቦይ ፍሬንድ አላት?''

"ማን?"

“ማኅደረ” ያላሰብኩት ጥያቄ:: “ኧረ! እኛ እንደዚህ ዓይነት ነገር አናውቅም'' “ሃሃሃ.. ያንችንማ አዬነው ...አሁን የሷን ንገሪኝ'' እንዳቀረቀርኩ “የላትም'' አልኩ፡፡ “ጥሩ! ነገ ከክላስ ስትወጡ፣ የሆነ ሰበብ ሰጥተሽ ብቻዋን እንድትሄድ አድርጊያት''

“구?” “ወደ ቤቷ ነዋ!'' አለ ቆጣ ብሎ፡፡ “እሺ!'' ነበር መልሴ፡፡ የዐሥረኛ ክፍል ቁጣ! በቀጣዩ ቀን ማኅደረን “ከትምህርት ቤት ስንመለስ ቤተክርስቲያን ፕሮግራም ስላለኝ አልጠብቅሽም” አልኳት፡፡ ቀደም ብዬ ስወጣ፣ ታክሲ መቆሚያው ጋር ከመድረሱ በፊት የጋሽ ዓለምነህ መኪና ቆማ አዬኋት። መንገዱን ተሻግሬ፣ በሩቁ አንድ የቆመ መኪና ኋላ ሰው የምጠብቅ መስዬ ቆምኩ። ማኅደረ ወደ ታክሲ መጠበቂያው አቀርቅራ ስትጣደፍ ጋሽ ዓለምነህ በቀስታ መኪናውን እያሽከረከረ ደረሰባትና ጠራት። የኋለኛውን በር ለመክፈት ሞክራ፣ ጎንበስ ብላ የሆነ ነገር ተናገረችና ወደ ከፈተላት የጋቢና በር ገባች፡፡ ውስጤ የቀረች ተስፋና መፈቀር ዕንባ ሆና ተንጠፈጠፈች፡፡ ወደ ጦር ኃይሎች ብረሪ ብረሪ አለኝ፡፡ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት መሮጥ አማረኝ፣ ያቺን ሚስቱን “ባልሽ ማኅደረ ጋር ሊተኛ ይዟት ሄደ” ብሎ ነገር ማቀራቀር አማረኝ፡፡ ከታክሲ እንደወረድኩ እቤቴ አልሄድኩም፣ ልደታ እስኪወጣልኝ ተነፋረቅሁ፤ ቅናት አንገበገበኝ፡፡ ቤተክርስቲያን ገብቼ ወደ ማታ አካባቢ ማኅደረ በብስጭት ብው ብላ እቤት መጠች ፤ የማውቃት ማኅደረ አልነበረችም። “አንቺ! ያ ልክስክስ ሰውዬ ልሸኝሽ ብሎ አስገብቶ ጡቴን አልነካኝም መሰለሽ!'' ብላ ተአምር የነገረቺኝ ያኽል አፈጠጠችብኝ፡፡ “ማነው? አልኩ'' እንዳላወቀ፡፡

“ጋሽ ዓለምነህ ነዋ! ከሱ ብሎ ጋሽ!'' “ምን!? ይኼ ጨምላቃ! ጠርጥሬ ነበር” ብዬ አጋነንኩ እንደማያውቅ:: “አንቺማ ነግረሽኝ ነበር፣ እኔ ነኝ እንጂ ፉዞ፤ አሁኑኑ ሄጄ ለሚስቱ ነው የምነግራት... ነይ እንሂድ!” ብላ መንገድ ጀመረች፡፡ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ማኅደረ እንደዚያ ተቆጥታ ዓይቻት አላውቅም። “እንዴ! ቆይ የሆነውን ንገሪኝ እንጂ ከዚያ እንወስናለን'' አልኳት፡፡ “...ስወጣ አግኝቶ ልሸኝሽ አለኝ፣ እንዲያውም ሃይሚም የለችም ብቻዬን ከመሄድ ገላገለኝ ብዬ ደስ አለኝ። ከኋላ ልገባ ስል ጋቢና ግቢ አለኝ፣ አገር ሰላም ብዬ ዘው! ትንሽ እንደሄድን 'ዛሬ ብቻችንን ተገናኜኝ የኔ ቆንጆ' ብሎ በዛ ሰፌድ እጁ ጡቴን አላፈሰኝም መሰለሽ...
👍404😢2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ ዘጠኝ


ከአሟሟቱ የቀብሩ...!


ፍቅረኛዬ ቶማስ ሞተ፡፡ እንዲህ በቅርብ የማውቀው ሰው ሲሞት የመጀመሪያዬ ስለነበር፣ ስለሞት አብዝቼ አሰብኩ። ስለ ቶማስም _ ሳምንቱን ሙሉ ማሰብ አላቆምኩም፡፡ ምናልባት በቁሙ ያላስተዋልኩት አንዳች በጎ ነገር ይኖረው እንደሆነ ብዬ፣ ከሞተ በኋላ ብዙ አሰብኩ፡፡ ስለ ሞተ ብዬ አንገቱ ረዢም ነው አልልም። ፍቅረኛዬ ስለነበርም ብዙዎች የሚያውቁን እንደሚያስቡት፣ የማይሆን የማይሆን ዓይነት ማለቃቀስ ውስጥ አልገባም። እውነታው ለሰው ባላወራም ቶማስ ቀናተኛ፣ ምቀኛ፣ የሰው ስኬት የማያስደስተው፣ ነገረ ሥራው ሁሉ አስፈሪ ነገር ነበር፡፡ የመጽሐፍት ምረቃ ላይ ታላላቅ ሰዎች(እሱ ባለስም ደላሎች የሚላቸው) ስለ ጸሐፊው በጎ በጎውን ሲናገሩ፣ ዓይኑ በንዴት ቀልቶ ፂሙን (አስቀያሚ ፂሙን) እየለቃቀመ ይነቅላል። ፂሙን በመንቀል ነበር የሚያስተካክለው። እሱ ለነቀለው እኔ ያመኝ ነበር፡፡ እንዳንዴ በሚነቅለው ቦታ ትንንሽ የደም ነቁጦች ብቅ ይሉ ነበር፡፡

“አያምህም?'” ስለው፣ “ያማል!ግን ስቃዩ ደስ ይለኛል” ይላል፣ ፍልስፍና መሆኑ ነው፡፡ ነብይ ነኝ ለማለት ሳይሆን፣ ፈጠነም ዘገዬ እንደሚሞት ቀልቤ ነግሮኝ ነበር፤ ግን አሟሟቱ እንዲህ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም፡፡ አንድ ቀን ወይ የሆነ ሰው አጥፍቶ ይጠፋል፤ አልያም ራሱን ያጠፋል፤ ብዬ ነበር የምጠብቀው፡፡ ምናልባትም እኔን ይገለኛል የሚል ሐሳብ ነበረኝ፤ ግን አልፈራም ነበር፡፡ ሐሳቡን ፊት አልስጠው እንጂ በውስጤ በጣም ጥልቅ በሆነ የአእምሮዬ ክፍል፣ ትንሸ ለሰሚው ግራ የሆነ አነጋጋሪ አሟሟት መሞት እፈልግ ነበር፡፡ አለ አይደል “የሚያፈቅራት ልጅ በቅናት ተነሳስቶ ገደላት” መባል፡፡ ቶማስ የሞተው ምንም በሌለበት በተባራሪ ጥይት ተመትቶ ነው አሉ። መጠጥ ቤት ውስጥ፡፡ ከአምሳ በላይ ሰው በታጨቀበት መጠጥ ቤት በተነሳ ተራ የሁለት ሰዎች ጸብ አንዲት ጥይት ተተኮሰች፣ ቶማስን ገደለችው፡፡ ስሰማ ደንግጨ አለቀስኩ፣ ደንግጨ ነው። የሚያውቁት ሰው ሲሞት ያስደነግጣል፣ እንኳን አንሶላ ተጋፈዉ። በዚህ ሁሉ ውስጥ ታዲያ የሰውን ዘር ጠልቶ የሚኖር ቶማስ፣ ሞቶ እንኳን ባሕሪው ያስፈራኝ ነበር፡፡ በዚያ ልክ ሰዎችን መጥላት፣ ያውም እንደሚለው በግሉ ምንም ያልበደሉትን፣ ከዚያ በፊት ዓይቷቼው እንኳን የማያውቃቼውን 中午:: ስለ ቶማስ ሳስብ እፈራለሁ፡፡ ሰዎች በልብስ እና መኪናቼው፣ በስልጣን እና ውበታቼው ሸፋፍነውት፣ ውስጣቼው ግን እንደ ቶማስ በጥላቻ ያበደ ቢሆንስ? እያልኩ እፈራ ነበር፡፡ ሴቶች ቆንጆ በመሆናቼው ይጠላቼዋል፤ ወንዶች በሴት በመፈቀራቼው ይጠላቼዋል፤ ሕፃናትን ሳይቀር ሳቃቼው ፍንደቃቼው ያበሳጨዋል፡፡ ሁሉንም ሕፃናት ዲቃላ ነበር የሚላቸው፡፡ በዚህ ሁሉ ጥላቻው መኻል አብርሃምን ይወደው ነበር “ጅል ነው'' ይለዋል።

“ጽሑፍስ ላይ?” እለዋለሁ፡፡ የማጥላላበት ሙያዊ ስድብ ከእሱ ለመዋስ በጉጉት “የእኔ 'ታይፕ' አይደለም፤ ግን አሪፍ ይጽፋል።ይቀረዋል! ግን ጠብ፣ ትቾት አይፈራም ብዙም መታዬት ምናምን አይወድም። ሴት ይወዳል፣ ሴቶች ደግሞ “ይሻፍዱለታል'' ምክንያቱም ሴት ይወዳል። ሁላችንም ሴት እንወዳለን፤ ሴቶች መልሰው የሚወዱትን ግን ጥቂቶችን ብቻ ነው፡፡ 'ባዮሎጂው' አይገባኝም'' እንዲህ ሲል ፊቱ ላይ የቅናት ቅሬታ ያንዣብብ ነበር፡፡ታዲያ ቅር ይለኛል... ምንም ሳይሆን ሴትነቴን፣ ገንዘቤን፣ ጊዜዬን ሰጥቼዋለሁ፤ ለምን የሌላ ወንድ በሴቶች መወደድ ያስቀናዋል!? እኔ ሴት አይደለሁም? የቀብሩ ቀን ምን ገረመኝ? መጀመሪያ የገረመኝ አካሄዴ ነበር። ምንም ይሁን ምን ቶማስ ፍቅረኛዬ ነበር። በውስጤ ልጥላው እንጂ ለአንድም ሰው ስለ እሱ ክፉ ተናግሬ አላውቅም፤ ሥራ ሳይኖረው፣ ከሰው የሚያኗኑር ባሕሪ ሳይኖረው፣ አብሬው ኖሪያለሁ። ይኼ ደግሞ እንዴት ብታፈቅረው ነው? ሲያስብለኝ የኖረ ነገር ነበር። እና ድንገተኛ ሞቱን ስትሰማ አንድ ነገር ትሆናለች ብሎ ከጎኔ የሚሆን ሰው እንዴት ይጠፋል? ይኼም ቢቀር፣ ወግ አለ ባህል አለ፤ አነሰም በዛም ከምቀርባቼውና ግንኙነታችንን ከሚያውቁ ጓደኞቼ አንድ እንኳን ሰው አብሬሽ ልሂድ አለማለቱ ገረመኝ። የሁሉም ይቅር የማኅደረ ነገር ነው የደነቀኝ፤ ደውዬ የቀብሩን ቀን ነግሪያት አይመቼኝም ብላ ቀብሩ ላይ አልተገኜችም። ሁለተኛው የገረመኝ ነገር የቀብሩ ቦታ ነበር፡፡ እዚያ አብርሃም የሚኖርበት ሰፈር መንገድ ዳር የታክሲ ፌርማታው እዚህ ሆኖ፣ ቀብሩ እንደ መድረክ ከፍ ያለ ቦታ መንገዱን ተሻግሮ፣ በግራ በኩል እዚያ። ወደ ቀብሩ ለመሄድ፣ ከፍያለዉ መሬት ወደ አስፖልቱ እንዳይንሸራተት በተገነባው የድጋፍ ግንብ መኻል ያለውን የድንጋይ ደረጃ በመጠቀም ነው። ብዙ ጸሐፊ ጓደኞች ስለነበሩት፣ የቀብር ኮሚቴ የተባሉት እነሱ ናቸው። ዘመድ የለው! ምን የለው። በሕይወት ዘመኔ አንድም ሰው ያላለቀሰበት ቀብር ያንን አዬሁ። ብዙዎቹ እኔ እንዳለቅስ ጠብቀው ነበር ይመስለኛል ዕንባዬ ከዬት ይምጠ?! ነገረኛ ነውና መንገድ ዳር እንቅበረው ብለው እንደሆን እንጃ፤ ብቻ እዚያ ቀበሩት፡፡

ከቀብር መልስ ቶማስ ዘመድ የለውም ነበርና ሁልጊዜ በሄደበት የሚይዛትን ማንገቻዋ የነተበ የቆዳ ቦርሳ አምጥተው ሰጡኝ (ውርስ መሆኑ ነው) ማታ ቁጭ ብዬ ስበረብር ምን አገኜሁ? ብዙ ቀይና ሰማያዊ እስክርቢቶዎች፤ ሁለት ምንም ሳይጻፍባቼው ያረጁ ማስታወሻ ደብተሮች (አልፎ አልፎ ርዕስ ነገር ተጽፎ ተሰርዟል) በዚህ ሁሉ ጊዜ የጻፈው አንድ ነገር የለም፤ የባከነ! ፍተሻዬን ስቀጥል፣ ከአንደኛው ማስታወሻ ደብተር ውስጥ ተጣጥፋ የተቀመጠች ቁራጭ ወረቀት አገኜሁ፤ ዘረጋግቼ በላይዋ ላይ የተጻፉትን ሁለት ቃላት አነበብኩ “የማኅደረ ከንፈር..” ይላል! የማኅደረ ከንፈር ምን?... ሰው ሞኝ ነው ቶማስ ምንም ሳይጽፍ ሞተ ይላል፣ ከዚህ ወዲያ ምን ይጻፍ?! ልክስክስ! ከመቃብሩ አውጥቼ በጥርሴ ብዘለዝለው ደስታዬ ነበር። አንዳንድ ሴቶች አሉ እንደ ዳሌ፣ እንደ ጡት፣ ዝምታና ትህትናቸውን ወንድ ለማማለል የሚጠቀሙበት። የእርሷ ጥፋት ይሁን አይሁን ግድ አልሰጠኝም ብቻ ማኅደረን ከነፍሴ ጠላኋት፡፡ ቶማስ በተቀበረ በሳምንቱ፣ አብርሃም አንድ ግጥም መድረክ ላይ አንብቦ፣ “ለጓደኛዬ ቶማስ መታሰቢያ ይሁን” አለ፡፡ እውነቱን ለመናገር በግጥሙ ምን እንዳለም አልሰማሁም፤ መታሰቢያ ነው ሲል ነበር የገባኝ። አንዳንዶች ታዲያ እያጨበጨቡ ወደኔ ዞር ዞር አሉ ... ግድ አልቅሺ ነው!? ወጉ አይቅር ብዬ እንዳዘነ ሰው አቀረቀርኩ፡፡ሳቀረቅር ጫማዬን በትኩረት ተመለከትኩ፤ ለምንድን ነው ሁልጊዜ ፍላት ጫማ የማደርገው? ብዬ ያሰብኩት እና ለመጀመሪያ ጊዜ ተረከዘ ረዥም ጫማ መግዛት እንዳለብኝ የወሰንኩት በዚያች ምሸት ነበር፡፡ አበበ ጠላ ጠጣ! ዮናስ እና ማኅደር ተጋቡ እያልኩ ለራሴ ደጋግሜ የምናገረው ስለሚገርመኝ ነው። ባል ተብዬው እዚያ ንግድ ሥራ ኮሌጅ እያለን ትምህርቱን አቋርጦ ሱዳን እንደሄደ ነበር የሰማሁት፡፡ በዬት በዬት ዞሮ አሜሪካ እንደገባ እንጃለት፡፡ ማህደረ ጋር እንዴት እንደተገናኙ እዴት እስከ ጋብቻ እንደደረሱም አላውቅም፡፡ አንድ ቀን እንኳን ስሙን አንስተነው አናውቅም፤ ለእኔ ተአምር ነበር፡፡ይኼ ዮናስ የሚባል ልጅ
👍466
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ


ማነሽ ባለ ሳምንት?

ያኔ ነው ስለ አብርሃም አጥብቄ ማሰብ የጀመርኩት።እንግዲህ በዚያ ሰሞን በፍቅረኛው ማኅደረ ተክዷል (መካድ ከተባለ) ከአሜሪካ በመጠ ሰው ተፈንግሏል፤ በዚያ ላይ የእኔም ፍቅረኛ፣ የሱም ጓደኛ የሆነ የጋራችን ሰው ደግሞ ሞቶብናል፣ የሚያቀራርብ የጋራ ጉዳይ አለን ብዬ፣አጉል ዓይነት ተስፋ በልቤ አደረ፡፡ እንደዚያ እንዳልጠላሁት፤ ከመሬት ተነስቼ ደወልኩና ወሬ ጀመርኩት፡፡ ለቶማስ ስላደረገው ነገር ሁሉ አመሰገንኩት፤ በጣም ቁም ነገረኛ መሆኑንም አጋንኜ አዳነቅሁ፤ በአካል አግኝቼው ለማመስገን ቡና እንድንጠጣ ጠዬቅሁት “እንዲያውም ላገኝሸ ሳስብ ነበር የደወልሽው” አለ። ምናልባት ስለ ማኅደረ አንዳንድ ወሬ ለመስማት ፈልጎ ይሆናል ብዬ አሰብኩ። እሱ ግን "ቶማስ የጻፈው የሆነ ነገር እጅሽ ላይ ይኖር ይሆን? ግጥም ወይም ልብወለድ? ለማስታወሻ ይሆን ዘንድ ከሌሎች ሥራዎች ጋር ላሳትምለት አስቤ ነበር" አለኝ። ስለ ባዶዎቹ ማስታወሻ ደብተሮች

ምንም ሳልል “ቦርሳውን ሰጥተውኛል፤ አቀብልሃለሁ- አንተው ታዬዋለህ'' አልኩትና ለመገናኜት ቀጠሮ ያዝን፡፡ ያቺን የማኅደረ ከንፈር...ቁራጭ ወረቀት ለብቻ አውጥቼ አስቀመጥኩና ቦርሳውን ልወስድለት አዘጋጄሁ።የዚያን ጥልማሞታም ቶማስ ጉዳይ ወደዚያ ጨርሶ፣ የዚያኑ ቀን እየጎተተ እቤቱ ቢወስደኝ እና ልተኛሽ ቢለኝ እምቢ አልልም ነበር። ደግሞ ተጎትቶ ለመተኛት! እንዲያውም እውነተኛው ማጽናናት በሆነልኝ ነበር(ባላዝንም)። የቀጠሯችን ቀን ጸጉሬን ተሰርቼ፣ አዲስ ቀሚስ ገዝቼ እና የመጨረሻ ራሴን አሳምሬ (እኔን ማሳመር _ቢከብድም) ቀጠሯችን ቦታ ቀድሜ ደርሼ ስጠብቀው ምን ተፈጠረ? ከርዝመቷ -ቅላቷ፣ ከቅላቷ- የሰውነቷ ቅርጽ፣ ልብ ከሚያስደነግጥ ሴት ጋር ሰበር ሰካ እያለ መጣ። ማነሽ ባለ ሳምንት? አልኩ። ከዚህ በፊት የሆነ ቦታ ባያትም የት እንዳዬኋት ጠፋብኝ። የልጅቱ የተጋነነ ቁንጅና የሆነ የሚረብሽ ነገር ነበረው፡፡ ከገባች ጀምሮ ሬስቶራንቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሰበብ እየፈለጉ ሊያይዋት ሲጣጣሩ እታዘባለሁ፡፡ አንዱ የሆነ ነገር የወደቀበት መስሎ ዞር ይልና ከኋላዋ አዬት፤ ሌላው 'ባዝ ሩም' ደርሶ ሲመለስ ፊቷን በቁሙ ሸምድዶጽ ያልፋል፤ 'በዝ ሩም' የሚመላለሰው ወንድ ምነው በረከተ እላለሁ? (የተቀመጥነው ወደ በዝ ሩም መሄጃው ጋር ነበር) ከሕፃንነቴ ጀምሮ አልታይም እንጂ፤ እንደ ስውር ካሜራ አካባቢዬ ላይ የምትፈጠር ነገር ከዓይኖቼ አታመልጥም፡፡ ያኔም ምን እየሆነ እንዳለ ገብቶኛል፡፡ ወንዶች ከምንድን ነው የተሠሩት?! ድምፃቼው የጎላ የወንድ ሳቆች ከኋላችን ... ትኩረት ለመሳብ መሆኑ ነው። አለባበሷ አስገራሚ ነበር፡፡ከግራ ወደ ቀኝ ተላላፊ ጋውን የመሰለ አጭር፣ ጥቁር ቀሚስ፣ ወገቡ ላይ በባለ አበባ የፈረንጅ መቀነት ሸብ የተደረገ፤ ቀበቶውን ጫፉን ይዛ ብትስበው፣ ቀሚሷ ግራናቀኝ ተከፍቶ ራቁቷን የምትቀር ነበር የምትመስለው፡፡ ማን ነው ወንድ ያንን ሸብ የተደረገ ቀበቶ ሳብ አድርጎ ለመፍታት የማይመኝ!? እፍ አውጥቶ የሚጣራ ቀሚስ! ተቀምጣ እግሯን ስታነባብር ቀሚሷ እስከታፋዋ በከፊል ከፈት አለ፤ በጥቁር ቀሚስ እንደዚያ ዓይነት ዓይን ላይ የሚያበራ ጭን። በዚያ ቁመት ላይ፣ ከቁም ሣጥን የላይኛው ክፍል ዕቃ ሳወርድ የምቆምበትን ዱካ

የሚያክል ተረከዝ ረጅም ጫማ ተጫምታለች፡፡ ሰው ቁመት በቃኝ አይልም ይሆን? የካቶቿ ጥፍሮች ጥፍር ቀለም አልተቀቡም።ግን ንጹህ ሆነው የሚያንጸባርቁ ነበሩ? እንደ ብዙዎቹ አብርሃም ጋር እንደማያቼው ሴቶች ክንዱን ይዛ አትተሻሽም፡፡ አብረው ሲራመዱም፣ ሲቀመጡም ራሷን የቻለች ዘናጭ። አረማመዷ ትሁት የሆነ እምባገነን ነበር፤ ምናልባት ሌሎች ግርማሞገስ ያለው የሚሉት ሳይሆን አይቀርም፤ ቀና ብላ ብቻዋን መኝታ ቤቷ ያለች ማንም የማያያት ዓይነት፣ ጡቶቿ እረጋ ብለው ግራና ቀኝ ይንቀሳቀሳሉ፣ ቁመቷ ጋር _ ስለሚመጣጠኑ አይጋነኑ እንጂ ጡቶቿ ትልልቆች ነበሩ። እንደ ብዙ ቀይ ሴቶች በቅላት የተድበሰበሰ ቁንጅና ሳይሆን ልቅም ያለ ውብ ፊት ያላት ሴት ነበረች። አፍንጫዋ አንድ አገር ዓይኗ ሌላ አገር ቢገኝ ለየብቻው ቆንጆ እየተባለ የሚደነቅ። ይሀች ቆንጆ እንደ ብራ መብረቅ ፊቴ ስትወድቅ፣ ኩሌ ከቅንድቤ ላይ ልትረግፍ ምንም አልቀራትም። ለቅሶ እንድረስ ብሎ ነውና ያመጣት፣ ብዙ ባትስቅም ስንተዋወቅ ፈገግ ባለችበት ቅጽበት የጥርሶቿን ውበት ዓይቻለሁ። የሆነ ሴት አውል ወንድ ከሄዳቼው ሴቶች ሁሉ ቆንጆ ቆንጆ ነገራቼውን ወስዶ እቤቱ የሠራት ነበር የምትመስለው፡፡ እኔ ጋር ቢተኛ ኖሮ ከእኔ ምኔን ወስዶ ይሰጣት ነበር? እላለሁ። “አዚዛ” አለችኝ፣ ከፍ ባለ ትህትና፡፡ “ሃይማኖት” አልኩና፣ ሳልወድ በግዴ ባሏ የሞተባት ምስኪን መስዬ ለቅሶ እንዲደርሱኝ ተመቻቼሁ። አቤት የልባችንና አፋችን መራራቅ፣ አውርተን ሳቀረቅር ረዣዣምና ውብ ጣቶቿ እጄ ላይ አረፉ፡፡ ደንግጨ እጄን ላሸሽ ነበር- ማጽናናቷ ነው፣ጠንካራና የሚቀዘቅዝ መዳፍ፡፡ ውስጤ የነበረው ብቼኛ ፍላጎት፣ ቶሎ ተለያይተን ቤቴ ሄጄ ማልቀስ ነበር፡፡ እንኳን የያዙት፣ ገና የተመኙት ተስፋ ሲሞት አያስለቅስም!? እሱ ግን ምን ዓይነት ሴት አውል ነው!? ልክስክስ!! ማን ነበር ስሟን ያለችኝ ... አዚዛ! ልክ እንደ ማስቲካ ልጥጥ ብሎ ነፍስ ጋር የሚጣበቅ ስም አዚዛ!!!

ወደ ቤቴ ስመለስ ሳላስበው እንደ አዚዛ ተራመጅ ተራመጅ የሚለኝ መንፈስ ነበር: ቀና ብዬ ማንንም ሳልደገፍ፣ ማንንም ሳልፈራ፣ አጉል ጨዋ ጨዋ ሳልጫዎት፣ ቀና ማለት አማረኝ - ቀና ማለት፡፡ ማን ነው ቀና ማለትን ለቆንጆ ብቻ የሰጠው?, እንዲህ እያሰብኩ ቀና ከማለቴ ዓይኖቸ በዕንባ ተሞልተው መንገዴ ብዥ አለብኝ፤ መልሼ አቀረቀርኩ። ዕምባዬ እንደ ድንገተኛ ምጥ መንገድ ላይ ይታገለኛል? ርምጃዬን አፈጥናለሁ! በዬት በኩል ቀና ይባላል?!

የሴቶች እኩልነት ሲባል...

በየቴሌቪዥን እና ሬዲዮው የሴቶች እኩልነት ሲሉ እኔ የሚታዬኝ ብቸኛ ነገር፣ በእኔና በማኅደረ መካከል የነበረው የእኩልነት ትግል ነበር። ይኼ ውድድር መኖሩን ማኅደረን ጨምሮ ማንም አያውቅም፤ አሸነፍኩም ተሸነፍኩም የውስጤ ድልና የውስጤ ውድቀት ነበር። ተወዳዳሪ እኔ፣ ተመልካች እኔ፣ ዳኛም እኔ የሆንኩበት የዕድሜ ልክ ውድድር ውስጥ ነበር የምኖረው። ዕድሜ ልኬን የተወዳደርኩት ማኅደረ ጋር እኩል ለመሆን፣ ከቻልኩም ለመብለጥ ነበር፤ የተዳላላት ልጅ ናት፡፡ ተፈጥሮ አዳልቶላታል፤ ማኅበሰቡ አዳልቶላታል፤ ወንዶች አዳልተውላታል፣ አጠገቧ ቆሜ ተረስቻለሁ፡፡ የመጡት ሁሉ ከፊቷ የተዘረጋሁ እኔን እንደ ምርቃት 'ሪቫን' በቸልተኝነት መቀስ ቆርጠው እሷን ሲያከብሩና ሲያሞግሱ ነው የኖሩት፡፡ ማኅደረ ውድድር መኖሩን እንኳን ሳታውቅ ስታሼንፈኝ ነው የኖረችው። የራሴ እናት ሳትቀር “እንደ ማኅደረ ጎብዥ፣ እንደ ማኅደረ ቁጥብ ሁኚ፣ እንደ ማኅደረ ንጹህ ሁኚ!" ስትለኝ ነው የኖርኩት፡፡ ታዲያ በእኔ ጉብዝና ሳይሆን በሁኔታዎች ማኅደረን ያሸነፍኩባቼዉ አጋጣሚዎች ነበሩ። ድሎቼን ደጋግሜ በመቁጠር የማገኜውን እርካታ ከሌላ ከምንም ነገር አላገኜውም።

ድል አንድ!
👍488🔥1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ አንድ


“ዓሣውም እኛ፣ መረቡም እኛ!!” ዮናስ! በዚህች ምድር ፣የመኖሬ ምክንያት የምትለው ዋናው ነገርሀ _ ምንድን ነው? ብባል ቤተሰቤ ነው ባይ ነኝ፡፡ እንዲያው ለአፌ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ነፍሴ ውስጥ ያስቀመጠው የቤተሰብ ፍቅር፤ ለአፍታ እንኳን የማይናወጥ እንደ አለት የጸና ተራራ ነው፡፡ ሌት ከቀን ሐሳቤ እናቴና ሁለት ታናናሽ እህቶቼ ናቸው፡፡ እነዚሁ ነበሩ ቤተሰቦቼ፤ እርጋታ እና እምነቷ እንደ ባሕር ውሃ ጥልቅ የሆነው እናቴ፣ በደስታ ከልክ በላይ የማትፈነድቅ፣ በሐዘንም ሆነ በችግር የማትልፈሰፈስ ደግ እናት ናት፡፡ ማንም ሰው የቱንም ያኽል ከባድ ችግር ቢያወራት መደምደሚያዋ አንድና አንድ ነው “መድኃኒዓለም ያውቃል!'' እህቶቼ አዜብና ማሪያም ሰምራ ዛሬ አድገው የእማማ እርጋታ ተጋባበቼው እንጂ፤ በልጅነታቼው በብስጭት ጸጉሬን የሚያስነጩኝ እሳቶች ነበሩ፡፡ ቢሆንም ታዲያ ጨዋነታቼውን አገር የመሰከረላቼው ልጆች ናቸው፡፡ ዛሬ አዜብ ነርስ ስትሆን፣ ማሪያም ሰምራ ደግሞ ዳኛ ሆናለች፡፡ ሁለቱም ከእህትነት ይልቅ ልጆቼ ነው የሚመስሉኝ፡፡ ደስታም ሆነ ሐዘኔ፣ የሕይወት ውሳኔዬም ሆነ ስኬትና ውድቀቴ፣ ሁሉ በቤተሰቤ ዙሪያ ብቻ የሚያጠነጥን ነው። ያለኝን ሁሉ ነፍሴንም ቢሆን ለቤተሰቤ ሰጥቼ በምድር ላይ አለ የሚባል ደስታ ባጎናጽፋቼው ደስታዬ ነው፡፡ ይሁንና የበዛውን የወጣትነት ዘመኔን በስደት ተለይቻቼው ኖርኩ፤ ድፍን 14 ዓመታት። ይኼን ምርቃትም እርግማንም ልለው ይቸግረኛል። በመሰደዴ ቤተሰቦቼ እንደ አቅማ

የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ጥሪያለሁ፤ በዚህም ያሰብኩትን ያኽል በይሆንም የበኩሌን ጠጠር የወረወርኩ ይመስለኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስደት እነዚያን ወርቃማ የወጣትነት ዘመናት አብሪያቼው እንዳላሳልፍ አድርጎኛል። ሁሉን ወዶ አይሆንምና፣ እግዚአብሔርን ለሆነው ሁሉ እያመሰገንኩ ቀሪ ዘመነ ላይ ማተኮርን ብቻ መረጥኩ፡፡ ባላተኩርስ ያለፈውን ሕይወት ምን ላደርገው እችላለሁ?! ይኼን የቤተሰብ ፍቅር የወረስኩት ምናልባትም ከአባቴ ይሆናል፡፡ አባቴ ጥላሁን (ነፍሱን በገነት ያኑራትና!) ለዓይን የማይሞላ፤ ከሰውነቱ ይልቅ ባሕሪው ያስከበረው ሰው ነበር፡፡ እንደ _ ስሙ ለቤተሰቡ የእውነትም ጥላ የነበረ ብርቱ ሰው፡፡ ከሥራ በስተቀር ለእንቶፈንቶ እና ላረባ ነገር ጊዜውን ሳያባክን ይህችን ዓለም ተሰናበተ። ሥራ ሱስ የሆነበት አባት ነበር፡፡ ጧት ከቤት ይወጣል፤ ወደ ሥራ ቦታው መርካቶ ይሄዳል፤ ማታ ከሥራ ይወጣል ወደ ቤቱ ይመለሳል፡፡ የሕይወት ምልልሱ ቢታይ እንደ ሸማኔ ድር ሥራ ቦታውና እቤቱ በተተከሉ ሥውር ሚስማሮች ላይ ሲጠመጠም የኖረ ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ ታዬ ከተባለ ወይ ቤተክርስቲያን፣ አልያም የታመመ ሊጠይቅና የሞተበትን ሊያጽናና ሲሄድ ነው። የአባባ የቤተሰብ ፍቅር “ነበር” ተብሎ ብቻ የሚታለፍ አልነበረም፡፡ አባቴን ባስታወስኩ ቁጥር፣ በወቅቱ ያላስተዋልኩትን ጉዳይ በጥልቀት አስባለሁ። አባትነት ስለሚባለው ነገር። እኛን ልጆቹን ባለፈ ሕይወታችን ተጠንቅቆ አሳድጎናል፤ የልጅነት ባሕሪያችን የተጋነነ አምሮት ውስጥ አስገብቶን የማይሆን ነገር ካልጠዬቅን በስተቀር፣ ማድረግ የሚገባውን አጉድሎብን አያውቅም፡፡ ይኼም ብቻ አልነበረም፤ ስለ ቤተሰቡ የወደፊት ዕጣ ፋንታ አርቆ ያዬ፤ ማዬት ብቻ ሳይሆን ነጋችንን እንደ ምቹ አልጋ አንጥፎልን ያለፈ ሙሉ አባት ነበር። በዚህ አርቆ አስተዋይነቱ ሞቶ እንኳን በእያንዳንዱ ሕይወታችን አብሮን አለ፡፡ አለ ስል “በመንፈስ ዛሬም አብሮን አለ" እንደሚሉት የልማድ ንግግር አይደለም፡፡ እንዲህ በአካል በእጆቼ አልዳስሰው እንጂ፤ በመንገዴ ሁሉ ኅልውናው ይሰማኛል፡፡

ዛሬ ላይ የቤታችን በረንዳ ላይ ስቆም አባባ ከሥራ ሲመጣ የነበረው ነገር ሁሉ ይታወሰኝና የማላውቀው ቁዘማ ውስጥ እገባለሁ። ሁሌ ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ የያኔውን የግቢያችንን የቆርቆሮ በር ገርበብ አድርጎ ይገባል፡፡ በጨለማው ውስጥ በዛፎቹ ጥላ መኸል ነጭ ጋቢው እንደ ጨረቃ ከሩቅ ይታያል፡፡ ሁልጊዜም በሩን እንዳለፈ ያስላል ኡሁ! ኡሁ! ያቺ ሳል መጥቻለሁ የምትል መጥሪያ መሆኗ ::٥٠ל በእርግጥ አባባ ከአባትነት ፍቅሩ እኩል ቅጣቱም አብሮ የሚታውስ ባሕሪው ነበር: በተለይ ለእኔ! አንዳንዴ ከሌሎች አባቶች ጋር ሳስተያዬው ትንሽ ግራ የሚሆንብኝ ነገር ነበር፤ እንደ ባህልም ይሁን እምነት፣ ብቻ የሚበዛው የአገራችን ወላጅ ሴት ልጆቹ ላይ ቁጥጥሩ ጠበቅ ይላል፡፡ የአባባ ባሕሪ ግን በተቃራኒው ነበር፡፡ ሁለቱ ሴት እህቶቼ ያን ያኽል ቁጥጥር የማይበዛባቼው እንዲያውም ያጠፉትን ቢያጠፉ ከናካቴው የአባባ እጅ ተነስቶባቼው የማያውቅ ቅንጡዎች ነበሩ። እኔ ላይ ግን ቁጥጥሩም ሆነ አጥፍቼ ስገኝ ቅጣቱ የማያፈናፍን ነበር፡፡ ምክሩም ቂጣ የቀላቀለ! ለእህቶቼ አንድ ነገር አላካፍልም ካልኩ ሙሉውን ቀምቶ ይሰጣቼውና የምክር ነጎድጓዱን ያወርድብኛል “ስግብግብና ራስ ወዳድ ሰው አባት አይሆንም:: ይኼን አየር ተመልከት ይላል ወደማይታዬው አየር በእጁ እየቀዘፈ፤ የፈጣሪ አባትነት የቸረን ነው፡፡ ይኼን ውሃ ተመልከት ፀሐዩን፣ መሬቱን፣ ተራራውን ሁሉ የአባትነት ስጦታ ነው። አባትነት ሙሉ ለሙሉ ያለህን መስጠት ካልሆነልህም ማካፈል ነው፡፡ መስጠት ባይሆንልህ ማካፈል ልመድ። ስግብግብ ሰው ቤት አይሠራም፤ ባክኖ ይቀራል፡፡ ስግብግብ ሰው ምቾቱን ይወዳልና ፈሪ ነው፤ ፈሪ እንኳን ቤተሰቡን ራሱን አይታደግም፡፡ ፈሪ ሕይወት የዘረጋችለትን ጥርጊያ መንገድ ትቶ፣ ጢሻ ለጢሻ ሲዳክር እንኳን ከሌላው ከራሱ ሲደበቅ ይኖራል፡፡ ወንድ ሁን ይኼን እዚህ ከእህቶችህ ጀምር!!” ታዲያ ይኼን ይኼን ሸሽት ይመስለኛል ወደ እናቴ መጠጋት አበዛ ነበር፡፡ በእናታች፣ የጓዳ ሥራና ምክር የሚሰላቹት እህቶቼ ደግሞ ወደ አባቴ ያዘነብላሉ፡፡ ለምክሩ

እናቴም አትተናነስ፤ ልዩነቱ የእማማ ምክር ምንግዜም ወጥእንጨት ይቀድመዋል፡፡ ለሀቶቼ ሰው የሆኑት በእማማ ወጥ እንጨት ነው ብል አላጋነንኩም! “የፈለገ ብትማር ብትሰለጥን፤ እግሯ ከጓዳዋ የተነቀለ ሴት ጥላ ቢስ ናት፡፡ ባሎቻችሁ ቢታገሱ ልጆቻችሁ አይምሯችሁም፤ ሙያ ልመዱ'' ትላቸዋለች፡፡ መኻል አዲስ አበባ ተወልደውና አድገው ጠላ መጥመቅ፣ ጠጅ መጣልና እንዝርት ማሾር የሚችሉ እሀቶች የኖሩኝ በእናቴ ምክንያት ነው፡፡ እህቶቼ ታዲያ ከትምህርት ቤት ሲወጡ፣ በዚያው መርካቶ አባቴ ጋ ወደ ሱቅ ሄደው ማታ አብረውት ወደ ቤት ይመለሳሉ፡፡ ወደ መርካቶ ሲሄዱ “አባባን እናግዘው'' =ነበር ሰበባቼው፤ ወይ ማገዝ! ያማራቼውን ሲበሉና ሲጠጡ ውለው ራት እንኳን = እስኪዘጋቼው ጠግበው ነበር የሚመጡት፡፡ አባባ ያቀብጣቼው ነበር፡፡ እኔ እግር ጥሎኝ ሱቅ ከሄድኩ ግን ወገቤ እስኪቆረጥ ጣቃ ስጠቀልልና ስደረድር ነበር ውሎዬ፡፡ ብዙውን ጊዜ እኔ እናቴ ሥር ስርመጠመጥ አመሻለሁ (አባባ ነው መርመጥመጥ የሚለው) አባቴ ካረፈ በኋላ፣ ለእህቶቼ መሸሻ መደበቂያቼው እኔ ሆንኩ፡፡ አባባ በመንፈስም፣ በአካልም አዘጋጅቶኝ ነበርና ጨርሶ ይዣቼው ባልወድቅም እንደ አባባ ሆኜላቼዋለሁ ብዬ ግን አላስብም፡፡ ቢሆንም “ዋርካ በሌለበት እንቧጮ አድባር ይሆናል'' እንደሚባለዉ የቤታችን አድባር የሆንኩት ገና በወጣትነቴ ነበር። የዐሥራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ፡፡ ያኔ ይኼ ሁሉ ከመሆኑ በፊት፣ አባባ ዘመድ ወዳጆቹ ሁሉ “ይኼ ነገር ትንሽ አልራቀም?'' እያሉት ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ ሰፊ ቦታ ገዛ፡፡ ከኖርንበት ከደመቀው ገዳም ሰፈር ለቅቀን ወደ አዲሱ ሰፈራችን ተሰደድን፡፡ አዲስ በገዛው ቦታ ላይ አቅሙ
👍363🥰1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ ሁለት

ፎቶ ኮፒ!

ቀጥሎ ምንድን ነው የሚሆነው? መሬታችንን እየሸረፍን ሸጠን አጨብጭበን ከመቅረታችን በፊት ምን ላድርግ? ነበር የዬቀኑ ሐሳቤ፡፡ ንግድ አሰብኩ፣ ግን እርግጠኛ ባልሆንኩበት ነገር ያቺን የመሬት ብር ደፍሬ መንካት አስፈራኝ፡፡ ከቤት ኪራይ የምናገኜው ገቢ ያን ያኽል የሚያወላዳ አልነበረም።እንዲያውም ከትምህርት ቤት ክፍያና ከታክሲ የሚያልፍም አልነበረም፡፡ ምናልባት አጋንኜው ይሆናል ግን ወደ ችግር እየተንደረደርን እንደነበር ነው በወቅቱ ይታዬኝ የነበረው። እማማን ላማክራት ስሞክር “አትጨነቅ መድኃኒዓለም ያውቃል'' ከማለት ያለፈ ምንም ነገር

ከአፏ አይወጣም ነበር፡፡ የእሷን ያኽል አማኝ ስላልሆንኩ ይሁን ወይም የአባቴ ሱቅ በግፍ ሲወሰድ መድኃኒዓለም ዝም ስላለ፣ ብቻ አባባሏ የባሰ ያስጨንቀኝ ነበር እንጂ ተስፋ አልሰጠኝም፡፡ እንዲሁ በጭንቀት ሌላ ሁለት ዓመታት ነጎዱ፡፡ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በዋናው በር በኩል መንገዱን ተሻግሮ ሁለት ወጣት ወንድማማቾች የከፈቷት ፎቶ ኮፒ ቤት ነበረች፡፡ የኮሌጁ ተማሪ “ሃንድአውት" ኮፒ የሚያደርግባት፡፡ እውነቱን ለመናገር ወጣትና መልከመልካሞቹ ወንድማማቾችም ተጨዋችነታቼው ጋር ተዳምሮ ብዙውን ተማሪ የሚስብ አንዳች ነገር ነበራቸው፡፡ ከሁለት ዓመታት በላይ ደንበኞች ስለነበርን እንግባባለን፤ እንዲያውም ቅርርባችን የጓደኝነት ቅርጽ ይዞ ነበር፡፡ ለመድኃኒዓለም ዝክር ጠርቻቼው እቤታችን ከመጡ በኋላ ደግሞ እማማ የምትጠምቀው ጠላ ጋር በፍቅር ወድቀው ነበር፡፡ እሷም በተጠመቀ ቁጥር “ለነዚያ ልጆች ውሰድላቼው' ትላለች፡፡ በአምስት ሊትር ጀሪካን እወስድና ክላስ ስጨርስ እዚያች ቤት ተቀምጠን ጠላችንን እያንቃረርን የሞቀ የወጣትነት ወሪያችንን እናደራ ነበር፡፡ አንዳንዴ ተማሪ ሲበዛ የፎቶ ኮፒ ሥራቼውን አግዛቼው ስለነበር ቤተኛ ነበርኩ፡፡ የሆነ ቀን የሦስተኛ ዓመት ትምህርት እንደጀመርኩ አካባቢ ታናሽዬው ድንገት ከዚያች ሱቅ ጠፋ፤ የት ሄደ አልኩት? ታላቁን፤ ፊቱ ላይ ሐዘን እንዳጠላበት “የለም ባክህ” አለኝ፡፡ በሆነ ነገር ተጣልተው ይሆናል ብዬ ችላ አልኩት፡፡ ታናሸዬው ሞገደኛ ነገር ነበር፤ ይሁንና በተከታታይ ለሳምንት አካባቢ ጠፋ፡፡ ይኼ ሲገርመኝ ታላቅዬው እንድታግዘኝ ብሎ እዚያች ፎቶ ኮፒ ሱቅ ውስጥ አንዲት ልጅ ቀጠረ፤ የዚያን ጊዜ ግን ጠበቅ አድርጌ ጠየቅሁት “አሮን የት ሄደ?'' አሮን ነበር ስሙ። ልክ የተሳሳተ ነገር የጠየኩ ይመስል ኮስተር ብሎ “ና ቡና እንጠጣ” አለና እያጣደፈ ይዞኝ ወጥቶ ቴሌ ባር ወሰደኝ፡፡ ግራ ቀኝ ተገላምጦ ሰው አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ድምፁን ቀንሶ “ከአገር ወጣ” አለኝ፡፡ "ήλης Φ?" “አዎ! እንግሊዝ'' አለና እንደገና ዙሪያውን ቃኜት አደረገ፤ ምን ግራ ቀኝ አገላመጠው ብዬ መጀመሪያ ገርሞኝ ነበር፡፡ በኋላ ቀስ በቀስ አኪያሄዱን ሲነግረኝ ነገሩ ሕገወጥ

እንደሆነ ገባኝ፡፡ ይሁንና ልክ እንደመገለጥ የሆነ አዲስ ተስፋ አጫረብኝ። ለካ መሄድም አለ የሚል፣ ለካስ ዓለም ሰፊ ናት፣ ከኩሪያችን መውጣትም ይቻላል የሚል... እዚህ እጅ በእጅ ከመፋለም ራቅ ብሎ በዶላር ሚሳኤል ድሀነትን በጅምላ ማደባዬት ይቻላል የሚል ተስፋ። ከዚያን ቀን ጀምሮ ከአጀማመሩ እስከመዳረሻው ወሪያችን ይኼው ስደት ሆነ፡፡ አልፎ አልፎ ስለቤተሰቦቻችንም ጉዳይ አወራን። በተለይ እኔ በጥያቄ መቆሚያ መቀመጫ ስላሳጣሁት እስኪሰላች ወሬውን ከረምንበት። እኔም ፈጽሞ በአእምሮዬ የሌለ ነገር እንደ መንፈስ ገብቶብኝ፣ ቆሜም ተኝቼም ሐሳቤ ወደውጭ መሄድ ሆነ። ከብዙ ብዙ ወሬና ማጣራት በኋላ ይኼው ልጅ አንዲት መንግሥት ቢሮ ውስጥ የምትሠራ፣ ዕድሜዋ አምሳውን የተሻገረ ዘናጭ ሴት ጋር አስተዋወቀኝ (ማወቅ እንኳን አላውቃትም አገናኜኝ ማለቱ ይቀላል) በሷ በኩል ነበር፣ ከአዲስ አበባ እስከ እውሮፓ፣ ከዚያም አሜሪካ ድረስ በተዘረጋ ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ጉዞው የሚፈጸመው። ሴትዮዋ የመጣችው በወቅቱ ዘመናዊ በነበረ ቀይ 'ቶዮታ ላንድ ክሩዘር' መኪና ሲሆን፤መኪናውን የሚነዳው ወጣት ልጅ አንድም ነገር የማይናገር ግኡዝ ነገር ነበር፤ ልጁ ምንም የተለዬ እንቅስቃሴም ንግግርም ስላልነበረው መኪናው በራሱ የሚሄድ ነበር የሚመስለው። ከዋቢሸበሌ ሆቴል በር ላይ አሳፍረውን ወደ ፒያሳ እየተጓዝን፣ እዚያው መኪናው ላይ ስለሁኔታው በዝርዝር አስረዳችኝ። አነጋገሯ አጠር አጠር ያለና ግልጽ ነበር። ዝርዝሩ ሁለት አማራጮች ነበሩት ፈጠን ባለ ንግግር እንዲህ ስትል አብራራችልኝ "ጉዞው ከመነሻው እስከ መድረሻው ሕገወጥ ነው፤ ለጓደኛም ይሁን ለቤተሰብ ዝርዝር ጉዳዮችን ባትናገር ጥሩ ነው፤ በመንገድ ላይ ተይዞ መመለስም ሊኖር ይችላል፡፡ የተያዝከው በእኛ ስሕተት ከሆነ ገንዘብሀን ሙሉውን እንመልሳለን፤ ለመጓጓዣም ሆነ ለምግብ የምታወጣውን እንከፍላለን፤ ያ ብቻ ሳይሆን እንደገና አመቻችተን ጉዞሀን እንድትቀጥል እናደርጋለን፡፡ እስከ አሁን አንድም ሰው ተይዞ የተመለሰብን የለም። እንዲሁ እንድታውቀው ነው፤ ስሕተቱ የእንተ ከሆነ ግን

ገንዘብ በንመልስም ማስተካከል የሚቻል ስሕተት ከሆነ እንደገና ለመርዳት እንሞክራለን፤ ያም ሆኖ ግን ግዴታ አይኖርብንም!” የአንተ ስሕተት ማለት፣ ሰዓት አለማክበር፣ በቀጠሮው ቦታ አለመገኘት፣ እንድታርፍበት ከሚነገርሀ ቦታ ውጭ ወጥቶ በፖሊስ መያዝ፣ ሌሎች ሰዎች ጋር መጠላት፣ ክፍያን በአግባቡ አለመክፈል፣ በተለይ ክፍያና ሰዓት፣ አለችና “በተረፈ እምነትህን እኛ ላይ ጣለው። የቤተሰቦችህን አድራሽ ትነግረናለህ የደረስክበትን በየጊዜው እናሳውቃቼዋለን...ጉዞው ምን ያኽል ጊዜ እንደሚወስድ በትክክል ማወቅ አይቻልም። መንገድ ላይ በየአገራቱ እንደሚኖረው ሁኔታ ይወሰናል፡፡ ዋናው ነገር የትኛውም አገር ምንም ይፈጠር ከጎንህ ነን'' ካለች በኋላ “ታዲያ አሜሪካ ስትገባ እንዳትረሳኝ...ሽቶ እወዳለሁ እንድትልክልኝ" ብላ ፈገግ አለች፡፡ ይኼ የመጨረሻ ንግግሯ አሜሪካ እንደተነሳሁ የምደርስባት ቅርብ፣ ሀዋሳ፣ ቢሾፍቱ ነገር እንድትመስለኝ አድርጎኝ ነበር በወቅቱ፡፡ መልሰው ዋቢሸበሌ በር ላይ አውርደውን እንደገና ወደ ፒያሳ አቅጣጫ ተፈተለኩ። ያቺን ሴት ስሟን እንኳን አላውቀዉም፤ ሴትዮዋ ነበር የምንላት። ከዚያ የመኪና ውስጥ ማብራሪያ በኋላ ስደት መረጥኩ፡፡ ልቤ ቀድሞ ተነስቶ ነበርና ውሳኔዬ የዚያን ቀን ውጤት ብቻ ነው ማለት አልችልም። የወጣትነት ችኩል ስሜትም ይሁን፣ አልያም ተስፋ ያደረግሁት ነገር፣ ብቻ እነዚሀን ወደ ውጭ አገር እንወስድሃለን ያሉ ሰዎች አምኛቼው ነበር፡፡አሜሪካ ደግሞ የተስፋዬ ምድር ነበረች። ይኽ ዉሳኔ ለእኔ ቀላል አልነበረም፤ በተለይ እናቴንና ሁለት እህቶቼን ትቼ መሄድ ሙዳ ሥጋ ከሰውነቴ ላይ የመቦጨቅ ያኽል ነበር ሕመሙ። ከሸጥነው መሬት ላይ የተወሰነ ብር አንስቼ በድፍረት እግሬን ሳነሳ፣ የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን ላጠናቅቅ አንድ ዓመት ብቻ ቀርቶኝ ነበር፤ ቢያንስ ጨርሰውና ሒድ እያሉኝ ጣጥዬው መንገዴን ጀመርኩ፡፡ የእናቴ የመጨረሻ ቃል ዕንባ በሚያደናቅፈው ድምፅ “መድኃኒያለም ከፊትህ ይቅደም!'' የሚል ነበር፡፡ ያኔ በቼልታ አሜን ብዬ ርምጃዬን አፈጠንኩ። ከዚያ በኋላ ግን ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ ምርቃቷ ትዝ ሲለኝ፣ በሙሉ

ልቤ፣ ከነፍሴ በወጣ ስሜት አሜን፤ ያላልኩበት ጊዜ የለም፡፡ መቼስ ምርቃት እንደ ምግብና ቁሳቁስ መጠቀሚያ ጊዜው አያልፍ! ስደትን እንዲሀ ከፎቶ ኮፒ ቤት ኮፒ አደረግኋት።

እኔን! እየተባልን አድገን...
👍415
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ ሶስት

ዓሣውም እኛ፣ መረቡም እኛ!!

ገበያ የሚመስል እስር ቤት ውስጥ ከሱዳን፣ ከማሊ፣ ከሱማሊያ፣ ከኤርትራና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በመጡ ስደተኞች መኻል ራሴን አገኜሁት፡፡ የእስረኛውን ብዛት መገመት በራሱ ያዳግታል፡፡ ሁካታው እና መርመስመሱ ግራ ያጋባል፡፡ እስር ቤቱን እስር ቤት ሊያስብለው የሚችለው ነገር ዙሪያውን አጥር መኖሩና የታጠቁ

ጠበቂዎች በየማማው ላይ መቆማቼው ነበር፡፡ በተረፈ ዙሪያውን የታጠረ ሜዳ ማለት ይቀላል፡፡ እገሩ ሞቃት ስለሆነ ውጭ ለውጭ ውለን፣ ሲመሻሽ የ'ዩኒሴፍ' አርማ ባለባቼው ዐሥራ አንድ ረዣዥም ዳሶች ውስጥ እንገባለን፡፡ ዳሶቹ ግራና ቀኝ ክፍት ሆነው በረዣዥም _ የብረት _ ምሰሶዎች የተወጠረ የሸራ ጣራ ብቻ ያላቼው፣ የፀሐይ መከላከያዎች ናቸው፡፡ በውስጣቼው ባለ ሁለት ርከን ተደራራቢ የብረት አልጋዎች፣ ግራና ቀኝ በመደዳ ተዘርግቶባቼው መኻላቼው መተላለፊያ መንገድ ነው። የሚበዛው ስደተኛ የለበሰው ደረቱ ላይ የ'ዩኒሴፍ' አርማ ያለበት ነጭ'ቲሸርት'ነበር፡፡ ገና አጥሩን አልፌ እንደገባሁ፣ አንድ በሳቅ የሚፍለቀለቅ ወጣት ከዬት እንደመጣ ሰላዬው ፊቴ ተጋረጠ፡፡ ነጭ 'ቲሸርት'ና ደማቅ ሰማያዊ የጨርቅ ቁምጣ ለብሷል፤ ከቆዳ የተሠራ ሰንደል ጫማ ተጫምቶ፣ እጁ ላይ ርካሽ የፕላስቲክ ሰዓት አሥሯል፡፡ ቁመቱ ረዥም ስለነበር አንጋጥጨ ነበር የማዬው፡፡ ጥርት ባለ እንግሊዝኛ ሰላምታ አቀረበልኝና መልሶ “እንግሊዝኛ ትሰማለህ?'' አለኝ፡፡ አጠያየቁ ጨዋነት የተሞላበት ነበር።

“እሞክራለሁ ግን ማውራት አልፈልግም፣ ከቻልክ የማርፍበትን ቦታ በማሳዬት እርዳኝ'' አልኩት፡፡ ዝዬ ነበር! ያ መዛል ሁሉንም የጨዋነት ድንበር የሚያስጥስ ቁጣ ውስጥ አስገብቶኛል፡፡ ወጣቱ ልጅ ግን ፈገግታው ሳይቀንስ፣ “ኦ! ሸክስፒር ራሱ እንዳንተ አያወራም!'' “እዚህ ታሥሯል?''
"ማን?"

“ሸክስፒር” ተሳሳቅን::
"ከየት ነህ"

“እኔ እንጃ!'' “ይገባኛል እኔ ራሱ ከማሊ መምጣቴን ያስታወስኩት እዚህ እስር ቤት ገብቼ የሙስጠፋን ሻይ ከጠጣሁ በኋላ ነው! ሃሃሃሃሃ! ና እዚያ ጋ አለ እጋብዝሀለሁ! በዚያውም ታርፋለህ!'' ቀልጣፋ ነገር ነው፡፡ ዝም ብዬ ተከትዬው ሄድኩ፡፡ አንድ ጥግ ላይ በተነጠፈ ሰሌን የሚመስል ምንጣፍ ላይ እግሩን አጣጥፎ ተቀመጠ፤እኔም እንደሱ ተቀመጥኩ፡፡ አንድ አፍንጫው እንደ ወፍ ማንቁርት የረዘመ ሽማግሌ በትንንሽ የፕላስቲክ ፍንጃል የሞሮኮ ሻይ አቀረበልን። በዚያ እስር ቤት ውስጥ ብቼኛ ቆዳው ፈካ ያለ ሰው ይኼው ባለ ሻይ ቤት ነበር፤ ሞሮኳዊ ነው፡፡ እውነትም ሻዩን ስንጠጣ ነቃ አልኩ፡፡ አጠገቤ የተቀመጠውን ጋባዠን ረስቼ በግርምት የሚተራመሰውን ሕዝብ ስመለከት፣ “እዚህ ብዙ አያቆዩህም፣ በፊት ስድስት ወር ያቆዩ ነበር፣ አሁን ስደተኛው ሲበዛ ከሁለት ሳምንት፣ ቢበዛ ከወር የበለጠ አያቆዩም፤ አስፈላጊውን መረጃ ሰብስበው ጊዚያዊ ዶክሜንት ይሰሩልህና …." “ከዚያ በኋላ ምን ያደርጉናል?'' አልኩት ደንግጨ፡፡ “በፕሬዝደንቱ የግል አውሮፕላን አውሮፓ ወይም አሜሪካ ይልኩሃል ሃሃሃሃሃሃሃ!” “ ብሎ በራሱ ቀልድ ሳቀ፡፡ ቀጠል አድርጎ “ሁለት ምርጫ አለህ፣ ኤርትራዊ ወይም ኢትዯጵያዊ መሆንህን ከተናገርክ ሱዳን ድንበር ወስደው ይጥሉሃል'' “እንዴ ? ሱዳናዊ ሳልሆን?” “እና ምናዊ ነህ?” “ኢትዮጵያዊ!” “አዬህ ሻዩ ሠራ፤ አገርህን ማስታወስ ጀመርክ ሃሃሃሃሃ!"አብሬው ሳቅሁ፡፡ ወደ አገርህ መልሰው ለመላክ ይፈራሉ፤ ዓለም አቀፍ ሕግ ጣሳችሁ ምናምን እንዳይባሉ፡፡

ማንኛውም አገር አስጠጉኝ ብሎ የመጣበትን ስደተኛ፣ ያለፈቃዱ ወደ አገሩ መመለስ አይችልም። ስደተኞቹ ራሳቼው ካልፈለጉ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ ከባድ ወንጀሎችን ሠርተው እየሸሹ ካልሆነ በስተቀር፣ ያላቼው አማራጭ ወይ አገራቼው ላይ ማቆዬት፣ አልያም ወደሚቀበልህ ሦስተኛ አገር መላክ ነው። ሱዳን ደግሞ በአካባቢው ካሉ አገራት ተመላሽ ስደተኞችን በሰፊው የምትቀበል አገር ስለሆነች የመጀመሪያ ምርጫቼው ናት።''
"በቃ"?
“ሁለተኛው አማራጭጮ'' አለና ግራ ቀኝ ገልመጥ ብሎ ወደ እኔ ሰገግ አለ:: ይችን ግራ ቀኝ : መገላመጥና ማስገግ ኢትዮጵያ እያለሁ : አውቃታለሁ፤ለመጀመሪያ ጊዜ ስለስደት ያሰብኩት፣ በዚች መገላመጥ የታከለበት ወግ ነበር:: በሹክሹክታ እንዲህ አለኝ “የማውቃቼው ሰዎች አሉ፣ ትንሸ ሳንቲም ካለህ ለአንድ ዓመት እዚሁ እንድትቆይ ይረዱሃል፡፡” “አንድ ዓመት እዚህ እስር ቤት?'' አልኩ ሳላስበው ድምፄን ከፍ አድርጌ ዙሪያውን የሚተራመሰውን እስረኛ እዬተመለከትኩ፡፡ “ሽሽሽሽ...! መጀመሪያ ነገር እስር ቤት አይደለም፤ ጊዚያዊ የስደተኞች ማቆያ ካምፕ ነው፡፡ እስር ቤት ከፈለግህ ግን ከዚህ 12 ኪሎሜትር የሚርቅ ጥሩ እስር ቤት አላቸው፡፡ ከፖሊስ ጋር ግብ ግብ የፈጠረ ስደተኛ ወይም አዚህ አገር ሌላ ወንጀል የሠራን ብቻ ነው ወደዚያ እስር ቤት የሚልኩት። እዚህ ስልህ እዚህ ማቆያው ውስጥ ማለቴ አይደለም፤ ስደተኞችን የሚያቆዩባት የወደብ ከተማ አለች፤ ታንጂር ትባላለች፣ ከዚህ ሰባት ሰዓት ብቻ ነው የምትርቀው በመኪና፣ በእርግጥ ሕጋዊ አይደለም ግን ሕግ የሚያስከብሩት እንዳላዩ ካለፉህ ያው ሕጋዊ ልትለው ትችላለህ” “እሺ! ተስማማሁ እንበል፤ እና ሰዎችሀን በምንድን ነው የማገኛቼው?''

ቀላል ነው፤ ዩኒሴፍ በየዐሥራ አምስት ቀኑ አንዴ ለዐሥር ደቂቃ ብቻ ስልክ ያስደውላል፡፡ ስደተኞች ቤተሰብ ወይም ጠበቃ ምናምን እንዲያናግሩ፤ እዚህ እስር ቤቱ ውስጥ ስልክ ይፈቅዳል፤ ለቤተሰብ ልደውል ነው ብለህ ትመዘገብና በዚህ ስልክ ደውል፣ ብሎ ቁራጭ ወረቀት ከኪሱ አዉጥቶ ሰጠኝ፤ ፍጥነቱ ይገርማል፡፡ እጆቹ ከሚናገረው ቃል ጋር እኩል ነው የሚሠሩት፤ በቼልታ ወረቀቷን ተቀበልኩት፡፡ ወዲያው ነበር ደላላ መሆኑ የገባኝ፤ ካለነገሩ አልተንከባከበኝም፡፡ “ሱለይማን ነው የላከኝ በላቼው''ብሎ እግረመንገዱን ለትውውቅ እጁን ዘረጋልኝ፡፡ “ዮናስ!” ብዬ የዘረጋልኝን እጁን ጨበጥኩት። ቀጠል አድርጌ "እእ... የምከፍለው ብር ግን. . . " ከማለቴ ከአፌ ነጥቀኝና፣ “ፈልግ! ብዙ ውድ አይደለም፤ "በዚያ በኩል ስፔን ቅርብ ነዉ፡፡እየቀለድኩ እንዳይመስልህ ቅርብ ነዉ፡፡ሞሮኮ ላይ ቆመህ እጅህን ስፔን ጠረፍ ላይ የምትዝናና ቆንጆ ከኋላዋ ቸብ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ሃሃሃሃ!"ሳቁ ያምራል፡፡ በዚያ በኩል ስፔን ቅርብ ነው፤ እየቀለድኩ እንዳይመስልህ ቅርብ ነው፡፡ አንዳንዶች በዋና ይሻገሩታል!ሃሃሃሃሃ!” የኑግ ልጥልጥ የመሰለ ፊቱ ላይ በሥርዓት የተደረደሩ ትንንሽ ነጫጭ ጥርሶቹ የሆነ ጥሩ ሰው ያስመሰሉት ፍጥረት ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ያው ደላላ ነው፤ ያውም በሕገወጥ የሰው ዝውውር ሰንሰለት ውስጥ የሚሠራ፡፡ ይኼ ማለት ሳቁ ሌሎች ለቅሶ ላይ የተመሠረተ ፍጥረት ማለት ነው። ስደተኛ ከእስር ቤት በር ላይ እያጠመደ፣ ለእንደገና ስደት የሚያመቻች፡፡ ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ወደ አገሬ መመለስ ውርደት ሆነብኝ፡፡ እንደገና ሌላ ስደትም ገና ሳስበው አንገሸገሸኝ፤ እንደተከዝኩ... “ብር የለኝም፡፡ ያለኝን በሙሉ እነዚያ የተረገሙ ፖሊሶች ወስደውብኛል'' አልኩት በሚነጫነጭ ድምፅ። “አትዘንባቼው”
👍275
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ አራት

ብር፣ አምባር...ሰበረችልዎ!

ትንሸ ስረጋጋ እና አገሩን ስለምድ፣ እኔም ሰው ነኝና ስፈራ ስቼር አልፎ አልፎ ወደ እነዚያ መሸታ ቤቶች ጎራ ማለት ጀመርኩ፡፡ በሕይወት ዘመኔ ከእናቴ ጠላ ውጭ አልኮል መቀማመስ የጀመርኩት እዚያ ነበር፡፡ እንደ እኔ ሊሰደዱ ሞክረው ገንዘብ ያጠራቼው፤ ወይም በማይወጡት ሱስና ዕዳ የተዘፈቁ፤ ያቺን ለማሟላት ሴተኛ አዳሪ የሆኑ የበርካታ አገራት ሴቶች በመሸታ ቤቶቹ ውስጥ ነበሩ፡፡ የሚበዙት ተስፋ ቆርጠው እዚያው በሴተኛ አዳሪነት ሕይወታቼውን የሚገፉ ናቸው፡፡ ከብዛታቼው

የተነሳ አንድ ዓሣ- ዓሣ የሚሸት ጎስቋላ ወንድ ወደ ቡና ቤቶቹ ሲገባ እምስት - ስድስት ሴቶች ይከቡታል፡፡ እነዚያ በሌላው ዓለም ቢሆን እግራቼው ተስሞ ለጋብቻ የሚጠየቁ ቆነጃጅቶች እንዲሀ ሲሆኑ ማዬት፣ እስኪለምዱት አንዳች ግርምት ያጭራል። እኔም ይኼው ነበር የገጠመኝ፡፡ ሴቶች አንዳች አስማተኛ ፍጡራን ናቸው። በዚያ ሲኦል ውስጥ እንኳን ወንድነት፣ ሰው የመሆን፣ የመፈቀር ስሜት፣ እንዲሰማን ያደርጉናል፡፡ ለሕይወት እንድንሳሳ ያደርጉናል፡፡ የቆረጥናትን ተስፋ በሴቶች ፈገግታና የሽቶ ጠረን መልሰን እንቀጥላታለን፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነበር ዛናታ የምትባል ሴት ጋር የተዋወቅሁት፡፡ መጀመሪያ እንዳዬኋት ኢትዮጵያዊ መስላኝ ነበር፡፡ የቀይዳማ መልኳ፣ የሚዘናፈል ጸጉሯ እና በዚያ ሥራ ውስጥ ሆና እንኳን የሚያስታውቅበት ዓይን አፋርነት የኢትዮጵያ ሴቶች ዓይነት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ እዚያ ቤት ስመላለስ ሴቶቹ አይተውኝ ምንም ጠብ እንደማይለኝ ስላወቁ ለብቻዬ ትተውኝ ነበር፡፡ የዚያን ቀን ግን ማፍጠጤ ጠርቷት መሰለኝ ፈገግ ብላ ወደተቀመጥኩበት መጣች፡፡ ለዚያ ሥራ በተለማመደችው የወንዶችን ስሜት የሚያነሳሳ አረማመድ ሰበር ሰካ ስትል ትልቅ መቀመጫዋና መካከለኛ ጡቶቿ የተለዬ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። በተለይ ግን ጥርሷ! እንደዚያ ዓይነት የጥርስ ንጣት የትም ዓይቼ አላውቅም፡፡ የማላውቀው አገር ልሳን በሚጫነው እንግሊዝኛ... “ምነው ብቻህን?'' አለችኝ፡፡ እንደ ቀልድ ፈገግ ብዬ “እግዚአብሔር_ከነፍጥረቱ ብቻዬን ተወኝ” አልኳት፡፡ አልሳቀችም፤ ዝም ብላ አዬችኝና ኮስተር እንዳለች በማላውቀው ቋንቋ የሆነ ነገር ተናገረች። ግራ መጋባቴን አውቃ በእንግሊዝኛ "እግዚአብሔር_እኔን ልኮልኻል የምትፈልገውን ተናገር" ብላ ባንዴ መኮሳተሯ ወደ ሳቅ ተቀዬረ፡፡ “ምንኛ ነው መጀመሪያ የተናገርሽው?'' “ፈረንሳይኛ፡፡”

“ትችያለሸ?” “ከአረብኛ ቀጥሎ አፌን የፈታሁበት ነው።” “አረብኛም ትናገሪያለሸ?!'' “እንደ ትልቅ ዕውቀት አትዬው፣ በሁሉም ቋንቋ አንድ የረባ ነገር ተናግሬበት አላውቅም!” ተሳሳቅን፡፡ ቢራ እንድትጠጣ ጋበዝኳት፤ አልኮል እንደማትጠጣ ነገረችኝ እና ለእኔ ቢራ፣ ለእርሷ ቀዝቃዛ የሎሚ ጭማቂ ይዛ መጣች፡፡ ከተፋፈገው ክፍል ወጥተን፣ ነፋሻው የቡና ቤቱ አሮጌ የእንጨት በረንዳ ላይ ተቀመጥን። ስትቀመጥ አያታለሁ፣ ቀሚሷን ሰብሰብ አድርጋ በሥርዓት ነበር የተቀመጠችው። ሁለታችንም ዝም ብለን ተቀመጥን፡፡ ጨለማ በዋጠው ውቂያኖስ ላይ አልፎ አልፎ ቀይ መብራቶች ቦግ እልም ይላሉ፤ የባሕር ላይ ድንበር ጠባቂ ጀልባዎች ናቸው: ከመራቃቸው የተነሳ ድምፃቼው የማይሰማ አውሮፕላኖች በጥቁሩ ሰማይ ላይ አብሪ ኮከብ መስለው ያልፋሉ። ዛናታ እንደ ዓመታት ፍቅረኛ ራሷን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ፣ በዝምታ ተቀምጣለች፡፡ ጠረኗ ደስ የሚል የሽቶ፣ የሎሚና የዚያ አገር ሜንት ሲጋራ ድብልቅ ጠረን ነበረው። በቀስታ አቅፌ ጸጉሯን መነካካት ጀመርኩ፣ ልቤ ደረቴን ቀዳ ልትወጣ ደርሳለች... ድንገት ቀና ብላ “ቤቴ ቅርብ ነው ከፈለግህ መሄድ እንችላለን” አለችኝ፡፡ በአክብሮት እንደማልፈልግ ነግሪያት ተሰነባብተን ወደ ዋሻዬ አመራሁ። ዞሬ ሳያት ቆማ እያዬችኝ ነበር። እስከዚያ ዕድሜዬ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም ነበርና ክፉኛ ፈርቼ ነበር፡፡ በዚያ ልክ ሴት ጋር ስጠጋጋም የመጀመሪያዬ ነበር። ከዚያች ምሽት በኋላ ወደዚያ መሸታ ቤት እግር አበዛሁ፡፡ ዛናታ ባዬችኝ ቁጥር እየተፍለቀለቀች ትመጣለች፤ ቢራዬን ይዠ የሎሚ ጭማቂዋን እየተጎነጨች እናወራለን፡፡ የሆነ ነገር ገብቷታል፤ እንደ እንስሳ በሚያደርጋቼው ወንዶች መኻል ሰው ሰው ሳልሸታት አልቀረሁም፡፡ የሰውነት ሽታ፣ ከሚቀረናው የዓሣ ሽታም በላይ የሰውን

ነፍስ ዘልቆ ይሰማል መሰለኝ!? ብቻ በየምሽቱ እየተገናኜን ወዳጅነታቸንም እየጠነከረ ሄደ፡፡ አንድ ማታ መጠጋጋታችን ወደ ድንገተኛ መሳሳም አለፈ፡፡ እጅግ ጥልቅና ረዥም መሳሳም ነበር። ሎሚ-ሎሚ የሚል መሳሳም። እናም በሚስለመለሙ ውብ ዓይኖቿ እያባበለች ወደ ቤቷ ስትጋብዘኝ እንቢ የማለት ወኔዬ ከዳኝ፡፡ የሴት ልጅ ሰውነት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የዚያን ሌሊት ተዋወቅሁ፡፡ “እኔ አላምንም የመጀመሪያህ ነው?'' አለች እየተፍለቀለቀች! ዝም ብዬ አዬኋት። “እንዳትዋሽ!'' አለች ሊፈነዳ ያሰፈሰፈ ሳቋ ፊቷ ላይ እንደተዘጋጁ፤ በአወንታ ራሲን ነቀነቅሁ፤ ከንፈሬን ስማኝ... አውቄ ነበር፤ _ አውቄ ነበር.... እያለች በሳቅ ተፍለቀለቀች። ድንገት ሳቋን አቁማ... “አገራችሁ ሴት የለም?'” አለችና የሚያምሩ ጥርሶቿ ብርሃናቼውን ረጩ፤ እንደ ተአምር አዬችኝ፡፡ ልክ እንደ ሕፃን ልጅ በዝምታ ጉንጯን ጉንጨ ላይ ለጥፋ ቆዬችና “ሲገርም” አለች ለራሷ፤ ምን እንደገረማት አልገባኝም፡፡ እናም ዛናታ ጋር ያበደ ፍቅር ውስጥ ገባሁ፡፡ አንድ እሷ ነበረች ሙሉ ከተማውን፣ ውሃውን፣ መንገዱን የሞላችው- ለእኔ፡፡ እሷ ጋር ስሆን በስደት አገር ውስጥ ለብቻዬ የተከለለ ሕጋዊ ደሴት ላይ ያረፍኩ መስሎ እስኪሰማኝ ሰላም እሆን ነበር፡፡ እቤቷ _ በሄድኩ ቁጥር ከእሷ እኩል ቤቷ ይገርመኛል፡፡ እግሬ ከኢትዬጵያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥርዓት የተደራጄ ቤት ውስጥ ስገባ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ የቤቷ ንጽህና ገረመኝ፡፡ የቤት ዕቃዎቹ ወደ ሆነ ሕይወት መለሱኝ፡፡ ትንሽ ሕያው ሙዚዬም ነገር። የምኖረው ሌሎች ዘጠኝ ስደተኞች ጋር በምጋራው ጠባብ አሮጌ ክፍል ውስጥ የተገኜውን ነገር እያነጠፍኩ ነበርና የተሰማኝ ስሜት ልዩ ነበር፡፡ የእኔን እንኳን መኖሪያ ከማለት መደበቂያ ዋሻ ማለት ይቀላል፡፡ ማንኪያ፣ ሹካ፣ መጥበሻና ብርጭቆ ዝም ብለው ቁስ አይደሉም። ከነመኖራቼውም ትዝ የማይሉን የቤት እቃዎች ሰውን ተከትለው ባረፈበት የሚረጉ፣ ሰውን በክብር ለማስተናገድ የተሰለፉ፣ ሕያው ቁሶች ናቸው፡፡ ቤት እንዲህ የሚናፈቅ ነገር ነው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ የተደረደሩትን እቃዎች እያዬሁ ዕንባዬ በዓይኖቼ እንደሞላ ትዝ

ይለኛል።ይኼ እንዴት ሊገለጽ ይችላል!? ከአንድ ወር በኋላ ይመስለኛል፣ ዘናታ ጠቅልዬ ከእሷ ጋር እንድኖር ጠዬቀችኝ፤ አላንገራገርኩም!! ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ... ተማርኩ ሰለጠንኩ ብዬ “የአበሻ ወንዶች አምባ ገነን ባሕሪ የፈጠረው ተረት!” እያልኩ ያጣጣልኩት አባባል ነበር። ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ ሲሉ። የዚያችን ቀን ምሽት ገጠመኝ ባስታወስኩ ቁጥር ግን አባባሉ እንደ በዓል መድፍ አርባ ጊዜ ይጮኸብኛል። ዛናታ ቤት ጠቅልዬ የገባሁ ሰሞን ሁለታችንም ዓለምን ረሳን፤ ራሳችንን ረሳን፤ ስደተኝነታችንን ረሳን፤ ፖሊስ ጋር የአይጥና ድመት ድብብቆሸ እየተጫዎትን የምንኖር ምስኪኖች መሆናችንን ረሳን፤ ፍቅር _ ነፃነት ነው...
👍497😁1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ አምስት

ድቅድቅ ባለው ጨለማ ከጀልባዋ የሞተር ድምፅ እና ከውሃው መንቦራጨቅ በስተቀር ምንም ነገር በማይሰማበት ባሕር ላይ ለሦስት ሰዓታት ያኸል ተጉዘን፣ የታሪፋ ወደብ የሚባለው የስፔን ግዛት ስንቃረብ፣ ጀልባችንን የሚነዳት ስደተኛ ሞተሯን አጠፋት፤ ልምድ ያለው ሰው ይመስላል፡፡ ጨለማው ውስጥ ከሩቅ የወደቡን መብራት እያዬን በዝምታ በመዓበሉ እየተገፋን ስንጠጋ፣ ከወደቡ አካባቢ ድንገተኛ የሆነ ከባድ የተኩስ ድምፅ ተሰማ፤ ወዲያው በሰማዩ ላይ እንደ ጅራታም ኮከብ የሚበር _ ነገር እየተምዘገዘገ ወደ እኛ አቅጣጫ መጥቶ ሰማዩ ላይ እንደ ርችት ፈነዳና የብርሃን ዝናብ በላያችን ላይ ዘነበ፡፡ እካባቢው በደማቅ ብርሃን ሲጥለቀለቅ ዓይኖቻችንን ጨፍነን መንጫጫት ጀመርን፡፡ በበኩሌ ያለቀልን ነበር _ የመሰለኝ። ወዲያው ሌላ ተኩስ ተከተለ፣ ይኼንኛው ለደቂቃዎች እንደ ፀሐይ ከበላያችን ቆሞ ባሕሩን ቀን አስመሰለው። ወዲያው ሁለት ትልልቅ ደማቅ ብርቱካናማ ቀለም ያላቼው የሞተር ጀልባዎች ውሃውን እየሰነጠቁ ወደ እኛ በፍጥነት ሲበሩ ተመለከትን፡፡ የእኛን ጀልባ ሲቆጣጠር የነበረው ስደተኛ “ማንም ሰው እንዳይንቀሳቀ የስፔን ድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ናቸው ጀልባችን ተበላሽቷል በሉ” አለና ከጀልባዋ ኋላ የተንጠለጠለውን መቅዘፊያ ሞተር ነቅሎ ወደ ውሃው ውስጥ ወረወረው፤ ከዚያም መኻላችን ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ጀልባዎቹ እንደደረሱ በድምፅ ማጉያ ፖሊሶቹ መናገር ጀመሩ፡፡ “ፖሊሶች ነን፣ ማንም ሰው ወደ ውሃው እንዳይዘል ጥልቅና ቀዝቃዛ ነው!''
“ጀልባው ላይ ሕፃናት አሉ?''

"እርጉዝ ሴቶች ...?"
“የታመመ ?"
“አካል ጉዳተኛ. . .?"
“የጦር መሣሪያ የያዘ. . .?"

ጀልባችሁ ውስጥ ውሃ ገብቷል?... ከጥያቄው በኋላ ወፍራምና ረዥም ገመድ ቁልቁል ወረወሩልን፤ ጀልባችን ከእነሱ ዘመናዊና ግዙፍ ጀልባ ጋር አቆራኜናት፤ በቀስታ እየተጎተትን ወደ ወደቡ ተጓዝን። በዚህ ሁኔታ የአውሮፓን ምድር ለመርገጥ በቃሁ።

ስሄድ አገኜኋት ስመለስ አጣኋት...

አውሮፓ ገብቼ ስዳክር፣ በኋላም በብዙ ውጣ ውረድ ወደ አሜሪካ ስሻገር፣ ዘናታን በልቤ ተሸክሚያት ነበር፡፡ ያኔ ስፔን መድረሴን በስልክ ሳሳውቃት ደስታዋ በቃል የሚገለጽ አልነበረም፡፡ ለአራት ወራት አካባቢ በሰጠችኝ ስልክ ተገናኝተን የደረስኩበትን ስናወራ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ያ እንደዋወልበት የነበረው ስልክ መሥራት አቆመ። ብዙ ደከምኩ፡፡ ብዙ ቀናት፣ ወራት፣ ዓመታት ነጎዱ... ዛናታ የውሃ ሽታ ሆነች፡፡ ከሞሮኮ መጣ የተባለን ስደተኛ ሁሉ እያሳደድኩ ስለ ዛናታ ያልጠዬኩበት ጊዜ አልነበረም። ሰው ነን እና ከዓይናችን የራቀን ምስል ልባችን ቢያደበዝዝብንም በሆነ በሆነ ቀላል የሚመስል ትዝታ፤ ፍቅር የራሱን ቀለም የሚያድስበት የሚደምቅበት ጊዜ አለ፡፡ ከአምስት ዓመታት የአሜሪካ ኑሮ በኋላ የዛናታ ነገር እንደገና ውስጤን ያንገበግበው ጀመረ፡፡ ምናልባት በገንዘብም፣ በስሜትም ስረጋጋ፤ ሁሉ ነገር ሞልቶ ሰው ሰው የሚሸት ነገር ሲጠፋ፤ ባዶነት በውስጤ እንደ ውቂያኖስ ተንጣሎ መንፈሴ የሆነ አድማስ ማረፊያ መሬት ስትፈልግ ያኔ ትናንቴን ፍለጋ ውስጤ ተነሳስቶ ይሆናል፡፡ አገራት ጦርነት ላይ ሲሆኑ ከታሪክ ይልቅ የቅጽበቱ ውጊያ እንደሚያሳስባቼው፣ ግለሰብም በሕይወት ጦርነት ሲዘፈቅ ታሪኩን ለጊዜው ዘንግቶ ይቆያል፡፡ ድል ሲያደርግ ወደ ነበረው ይመለሳል፡፡ ወደ ትዝታዬ... ፍቅር፣ በጎነት ወዳሳዬችኝ ያቺ ሴት በትዝታ ተመለስኩ። ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ ቤተሰቦቼን ካዬሁ በኋላ ያቀናሁት ወደ ሞሮኮዋ ታንጂር ነበር፡፡ ያለ ስጋት በቱሪስት 'ቪዛ' በእነዚያ መንገዶች ስራመድ "መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ አይባልም ደርሶ...!" የሚሉት ብሒል ነበር ግዝፈቱ የሚሰማኝ፡፡ ከተማዋ

ስሄድ እንደነበረችው እንደዚያው ናት፡፡ ሁሉም ነገር እንዳለ ነበር፡፡ ወደ እነዚያ መሸታ ቤቶች ሰቀና፣ እግሮቼ እየተንቀጠቀጡ ሐሴት፣ ናፍቆት እና ፍርኃት በተቀላቀለበት ስሜት ነበር። የመሸታ ቤቶቹ ቁጥር በጣም ጨምሯል። ሰውም የዚያኑ ያህል በዝቶ ነበር። ይሁንና የዚያን ምሽት አንድም ዛናታን እውቃታለሁ የሚል ሰው ማግኘት አልቻልኩም፡፡ እነዚያ በዓይን የማውቃቼው ሴቶች አንድኛቼውም አልነበሩም። እንኖርበት ወደነበረው ቤት አቀናሁ፣ ሰፈሩ በሙሉ ፈርሶ ትልቅ መጋዘን የሚመስል ነገር ተሰርቶበታል፡፡ በብዙ ፍለጋ፣ ከሦስት ቀናት በኋላ አብራት ትሠራ የነበረች ናይጀሪያዊት ሴት አገኜሁ፤ አላስታወሰችኝም፡፡ ሴትዮዋ በዚህ ፍጥነት ትልቅ ሴትዮ መስላለች፡፡ ጥያቄዬ አሰልችቷት ነበር፡፡ መጠጥ ስገዛላት ተረጋጋች። ከብዙ ምልክትና ማብራሪያ በኋላ ግን ትዝ አላት፡፡ ሞቅ ብሏት ንግግሯ እየተደነቃቀፈ ስለነበር ማስታወሷን ተጠራጥሬ ነበር፡፡ ሊያልቅ የተቃረበ ሲጋራዋን በላይ በላዩ እየሳበች ጭሱን አንዴ ወደ ላይ፣ አንዴ ወደ ጎን በዘፈቀደ ታንቦለቡለዋለች። በጭሱ ውስጥ በቸልታ አዬችኝና፣ በረዥሙ ተንፍሰ "ያቺ ቆንጆ ልጅ... አስታወስኳት ቆንጆ ጥርሶች የነበሯት...ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ አረብኛ ትናገር ነበር ... ወንዶች በጣም ይወዷት ነበር፤ አስታወስኳት። እንደገና ፊቷ የተቀመጠውን ብርጭቆ አንስታ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠችውና በመጠጡ ምሬት ፊቷን አጨፈገገች፡፡ ትዕግስት በሚፈታተን እርጋታ አዲስ ሲጋራ አዉጥታ ለኮሰች፡፡ “የሆነ ጊዜ ተጣልተን አሮጊት ብላ ሰድባኛለች...ሁሉም እንደዚያ ነው የሚለኝ፡፡ ዕድሜዬን ላቆመው አልችልም!" አለች በቅሬታ፡፡ ድንገት ኮስተር አለችና "ምኗ ነህ ግን?'' አለችኝ፡፡ “ጓደኛዋ ነበርኩ ከተለያዬን ቆዬን፣ ላገኛት ከሩቅ ቦታ ነው የመጣሁት”

“ከየት”
ፈራ ተባ እያልኩ “ከአሜሪካ”

ሁለት እጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ “ዕድለኛ ልጅ ነች፤ ሞታ እንኳን የምትፈለግ! እኔ ቆሜ ፈላጊ የለኝም'' አለች። “ሞታ ነው ያልሽው?'' አልኩ በድንጋጤ። ሲጋራ በያዘ እጇ ወደተንጣለለው ባሕር እየጠቆመችኝ “ከአራት ይሁን አምስት ዓመት በፊት ተገድላ እስከሬኗ ውሃ ላይ ተጥሎ ተገኜ፡፡ በዚያ ምክንያት እነዚያ ውሻ ፖሊሶች ሰብስበው አስረውን ነበር። ብዙ ሰው ጋር ትጣላ ነበር በጣም ወጣት ነበረች ደግሞ...' አለች፡፡ ሁኔታዋ ተራ ነገር ያወራች ነበር የሚመስለው፣ የያዝኩት የቢራ ጠርሙዝ ከእጄ አምልጦኝ መሬት ላይ ሲወድቅ፣ ናይጀሪያዊቷ ሴት ምንም ሳይመስላት “መሄድ አለብኝ! አሮጊት ብሆንም ቀድማኝ ሞተች...ይቅርታ ደነገጥክ መሰለኝ?''ብላኝ ተነስታ ሄደች:: በቃ! ያቺ ውብ እና ለእኔ ብቻ ደግ አድርጎ የፈጠራት ሴት መጨረሻዋ እንደዚያ ሆነ፡፡ የቀረኝ ብቼኛ ነገር ትዝታዋ እና ከእጄ ላይ አውልቄው የማላውቀው የሰጠችኝ 'ብራዝሌት' ነበር፡፡ ናይጀሪያዊቷ ተነስታ ስትሄድ፣ አዳዲስ ወጣት ሴተኛ አዳሪዎች መጥተው ከበቡኝ። ተነስቼ በመካከላቸው አለፍኩና ከቡና ቤቱ ወጥቼ ቁልቁል ወደ ባሕሩ ዳርቻ ተጓዝኩ... ጀልባዎች ወደሚቆሙበት፣ አሁንም ጀልባዎች በመደዳ ታሥረው ይወዛወዛሉ፡፡ ሁለት ሰዎች መረብ ይጠቀልላሉ፣ መልካቼው በደንብ አይታዬኝም፡፡ ባሕሩ ዳርቻ ላይ ቆሜ እስኪበቃኝ አለቀስኩ! ከንቱ ዓለም!! ምናልባት እርሰ በእርስ እየተቀናኑ ለዱርዬ ትንሽ ሳንቲም ሰጥተው እህቶቻቼውን የሚያስገድሉ ሴቶች ሲሳይ ሆና ይሆናል፡፡ ወንጀል፣ ወሲብ፣ ሕገወጥ የሰው ዝውውር፣ ዕፅ፣ ባጥለቀለቃት በዚያች ትንሽ መንደር እንዲህ ዓይነት ነገር የተለመደ ::חל ከዚያ ሁሉ መንከራተት በኋላ አሜሪካ እጇን ዘርግታ አልተቀበለችኝም ነበር፡፡ ቢሆንም የመንከራተት ታሪኬ አብቅቶ እንደ ሰው የምታይበት ኑሮ መጀመሬ ልዩ
👍493😢3
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ ስድስት

እንግዲህ አንደ ጓደኛዋ ሃይማኖት አባባል ከሆነ፤ የማኅደረ ዝምተኝነት እና ከሰው መለዬት እንደ በሽታ የተጠናዎታት እናታቼው ትታቼው ከሄደች በኋላ ነበር። ከወንድሞቿም በላይ በእናቷ መጥፋት ክፉኛ የተጎዳቸው ማኅደረ ናት እንጂ ከዚያ በፈት ተጫዋች፣ ተግባቢ እንዲያውም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እያሉ አስተማሪ ወጣ ሲል፣ ተማሪዎች ፊት ቆማ ካልዘፈንኩላችሁ የምትል ደፋር ልጅ ነበረች፡፡ የእናቷ መጥፋት መንፈሷን ሰበረው፡፡ ጓደኛዋ ይኽን ነገር ለምንም ትንገረኝ ለምን፣ ቤተሰብ የሚለው ነገር የሁሉ ነገሬ አልፋና አሜጋ ነውና ለማኅደረ ልክ የሌለው ሐዘን ተሰማኝ፡፡ እናቷ ትታት የጠፋችና በዚህች ምድር አባት ብላ በሙሉ ልቧ የተደገፈቻቼው ሰው ምናልባትም ትክክለኛ አባቷ ያልሆኑ ምስኪን። ጓደኛዋ እንኳን የእውነት ጓደኛዋ አይደለችም፡፡ ለማኅደረ የነበረኝ ስሜት ከልክ ያለፈ ሐዘን ነበር። ከመጀመሪያውም ከወደድኩት ባሕሪዋ ጋር ምናልባት ይኼ ይኼ ነገር ተደማምሮ ማኅደረን እንደ ጓደኛዬ ማዬት እና መቅረብ የጀመርኩበት ጊዜ ነበር፡፡ ያውም በራሴ የቤተሰብ ጉዳይ በተጨናነቅሁበት ለራሴ የሚታዘንልኝ በነበርኩበት ወቅት፡፡ በሴት ጉዳይ ይዘፈንበት ይለቀስበት የማላውቅ ወጣት ነበርኩና ደፍሬ አልገፋሁም፤ ጨክኜም አልራቅኋትም፡፡ አንዳንድ ማኅደረ ጋር ለመቀራረብ የማደርጋቼው ነገሮች ነበሩ። ከጓደኞቼ ፎቶ ኮፒ ቤት የሚያስፈልጋትንም የማያስፈልጋትንም ሁሉ በነፃ ኮፒ እያደረግሁ እወስድላት ነበር፡፡ እሷ ግን እያንዳንዷን ሳንቲም አስባ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትመልስልኝ ነበር፡፡ ያው ተዘዋዋሪው እዚያ የተማሪዎች ካፌ ላይ ስንጠጣ የእኔን ሒሳብ ተንደርድራ የምትከፍለው ነገር መሆኑ ነው፡፡ ለምን ቀድማ ሒሳብ እንደምትከፍል ለእኔ ቢገባኝም፣ ለሌሎቹ ጓደኞቻችን ግን በመካከላችን የተለዬ ቅርበት የተፈጠረ የሚያስመስል ነገር ነበር፡፡ በአሽሙር ፈገግታ፣ በጥቅሻ፣ በክንድ ጉሸማ፣ ወዘተ፣... ግፋበት የሚሉኝ ጓደኞቼ በወቅቱ እንደዚያ ስታደርግ ደስ የማይል ስሜት እንደሚሰማኝ አያውቁም ነበር፡፡ማኅደረ ጋር አሳለፍኩ የምለው ረዥም ጊዜ አሁን ጨርሶ በማላስታውሰው ምክንያት ሰፈሯ ድረስ የሸኜሁባትን ቀን ነው። ምን እንዳወራን አላስታውስም፣ ሰዓቱ እንኳን ትዝ አይለኝም፣

የማስታውሰው ብቼኛ ነገር አንድ ዙሪያውን በወዳደቀ አሮጌ መኪናና የመኪና 19 የተሞላ አሮጌ ጋራዥ ጋ ስንደርስ መለያዬታችንን ነው። መንገዱ ከዚያ ጋራዥ በሚወጣ የተቃጠለ ዘይት የተበከለ ከባድ የብረት ቅጥቀጣ ድምጽ የነበረበት፣ አካባቢውም የሚቀፍ ዓይነት ነበር፡፡ ከጋራዡ አለፍ ብለው፣ እንደሱቅ መንገዱን ተከትለው የተሠሩ ግቢ የሌላቼው የቁጠባ ቤቶች ነበሩ። ከእነዚያ ምርጊታቼው የረገፈና የጣራቼው ቆርቆሮ የዛገ አሮጌ የቁጠባ ቤቶች መካከል ማኅደረ ወደ አንደኛው ስትገባ አስታውሳለሁ፡፡ ለምን እንደሆን እንጃ ያም እይታ አሳዝኖኛል፡፡ ከሁለት ዓመታት በላይ በዚያ ስሜት ውስጥ ቆይቻለሁ። በመጨረሻ አቅሌን ስቼ ለስደት ስዘጋጅ ከእነዚያ ሁሉ ጓደኞቼ ይልቅ ማኅደረ የጠዬቀችኝን ዛሬ ላይ አስታውሰዋለሁ። ወደ አምስት የምንሆን ልጆች ከክላስ በፊት ሰብሰብ ብለን ተቀምጠን በየአፋችን ስናወራ፤ ከጎኗ ነበር የተቀመጥኩት፣ ዞር ብላ አይታኝ፣ “ዮኒ ሰሞኑን ልክ አትመስልም ደህና ነህ?'' “ደህና ነኝ” አልኩ፤ እየሳቅሁ! ለቅጽበት ትክ ብላ አይታኝ ወደ ሌሎቹ ጨዋታ ተመለሰች፡፡ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ይመስለኛል ተሰደድኩ፡፡ የማኅደረ ነገር በዚያው አለቀለት፡፡ እንደው በሆነ በሆነ አጋጠሚ ለቅጽበት አስታውሻት ካልሆነ በስተቀር ሙሉ መልኳ ጭምር ከአእምሮዬ ጠፍቶ ነበር፡፡ እንደገና ማኅደረን ያገኜኋት ከ14 ይሁን 15 ዓመታት በኋላ ነበር፡፡ ሌላ ሰው ሆኜ ሌላ ሰው ሆና፡፡ የዛሬ ሰባት ዓመት ቤተሰቦቼን ጥዬቃ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ነበር። በዚያውም አባታችን ያወረሰን ቦታ ላይ ወደ አገሬ ስመለስ የምኖርበት ያልኩትን ቤት እያሠራሁ ስለነበር ምን እንደደረሰ ለማዬት። የተወሰነ ጊዜ እንደቆዬሁ ታናሸ እህቴ ማሪያም ሰምራ ጋር የሆነ ውክልና ጋር የተያያዘ ነገር ለመጨረስ ስድስት ኪሎ ወደሚገኝ አንድ መሥሪያ ቤት ሄድን፤ ሁሉም ነገር ግራ ስለሚገባኝ እህቴ እንሂድ ያለችብኝ ቦታ ሁሉ እንደ ሕፃን ልጅ እየተከተልኩ ከመሄድና ፈርም ስትለኝ ከመፈረም ውጭ ሌላ ሥራ አልነበረኝም፡፡ ቢሮክራሲው ያሰለቼኝ ነበር፡፡

የዚያን ቀን እህቴ የምታደርገውን አድርጋ ለፊርማ እስክትጠራኝ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጨ ከዚያ ከዚህ ስትሯሯጥ አያታለሁ፡፡ የትላንትና ማሪያም አድጋ እንዲህ ከሩቁ ሳያት ግርምት ይሞላኛል፡፡ መኻል ላይ ዐሥራ አራት ዓመታት ክፍተት ስለነበር ያች ትንሿ እህቴ አድጋ ሳይሆን በትልቅ ቆንጆ ወጣት ሴት ቀይረው የጠበቁኝ እስኪመስለኝ፣በግርምትና በስስት አያታለሁ፡፡ ትርምሱን እታዘባለሁ፡፡ በጫጫታው እገረማለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ ሁሉ ነገር እንደነበረ መሆኑ እየገረመኝ ይኼን ትርምስ የናፈቀ አእምሮዬ በጉጉት እያንዳንዱን ነገር ይቃርማል፡፡ በዚህ ቅጽበት ነበር ፊት ለፊ ከቆመው የመስተዋት ግርዶሸ ጀርባ ካሉት በርካታ ቢሮዎች የአንዱ በር ተከፍቶ በወረቀት የተሞላ ቢጫ ፋይል ያቀፈች ሴት ብቅ ያለችው፡፡ አእምሮዬ ለቅጽበት የት እንደሚያውቃት ከማሰብ ውጭ ለማስታወስ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም፡፡ ረዘም ያለች ፣ረዥም ጸጉሯ ወደ ኋላ ታሥሮ የተለቀቀ ጠይም ሴት፤ ለራሴ ማኅደረ አልኩ፡፡ ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ እንኳን ከልጅነት ወደ አዋቂነት ከተሸጋገረ አጠቃላይ ለውጥ ውጭ የተጋነነ ለውጥ አልነበራትም፤ ውስጤ በደስታ ሲዘል ይታወቀኛል፡፡ ተነስቼ ወደ ፊት ሄድኩና ደንበኛ ለማስተናገድ በተሠራው የመስተዋቱ ክብ ቀዳዳ በኩል ጎንበስ ብዬ በጎላ ድምፅ ጠራኋት “ማኅደረ!'' ድንገት ዞረችና ወደ እኔ ሳይሆን ወደሚተራመሰው ሕዝብ የጠራትን ሰው ፍለጋ ዓይኞቿን አንከራተተች። እጄን አውለበለብኩላት፣ ግራ በመጋባት አዬት አደረገችኝና ወደ እኔ መጥታ በትህትና “አቤት!” አለችኝ፡፡ ፊቷ ላይ ምንም ዓይነት ማስታወስ አይታይባትም ነበር (በዚህ ትንሽ ቅሬታ እንደተሰማኝ አስታውሳለሁ ያን ያኽል አርጅቼ ይሆን? ከሚል ሐሳብ ጋር ) ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ በፈገግታ ጠፋሁብሸ? አልኳት፡፡ ትንሽ የኃፍረት ፈገግታ ፊቷ ላይ እየታዬ ወደ ቀኝ በኩል ተራመደች፣ በዚያ በኩል መስተዋት ስላልነበር በግልጽ መተያዬት እንችል ነበር። እናም ትንሽ አዬችኝና “እምምም ዮኒ እንዳትሆን ብቻ?'' ብላ በሳቅ ስትፍለቀለቅ ነፍሴ በሐሴት ተሞላች። ከሆነ ዓይነት ሞት በኋላ የሚያውቁኝ ሰዎች ወዳሉበት ዓለም በትንሣኤ የተመለስኩ

እስኪመስለኝ ውስጤ በደስታ ዘለለ፡፡ ያቀፈችውን ፋይል የሆነ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችና፣ ሌላ በር ከፍታ ወደ እኔ መጣች ተቃቅፈን በሳቅ አውካካን፡፡ ከውስጥ መስተዋቱ ያንጸባርቃል ለዚያ ነው፤ አለች ይቅርታ ባዘለ ድምጽ። አንተ! አንቺ! እየተባባልን በግርምት ስንተያይ ቆዬን፡፡ እንዲህ ነበር ከጸጉር በቀጠነች አጋጣሚ ማኅደረን ዳግም ያገኜኋት፡፡ የዚያን ቀን እህቴ ጋር አስተዋወቅኋቼው፡፡ ታዲያ ስንወጣ እህቴ ምን አለችኝ?... “የፊቷ ጥራት ሲገርም!... ንኪው ንኪው ብሎኝ ነበር...'' ወይ ይኼ ፊት! አልኩ በውስጤ።
👍40👏3🥰1