አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
517 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እመጣልሻለው!

ወርቅ ስትይ ወርቅ ጨርቅ ስትይ ጨርቅ

አንባር ስትይ አንባር አልቦም ስትይ አልቦ

ምን ያላኩት አለ ምንድን ቅራቅንቦ

ላክ ያልሽኝን ሁሉ ስልክ ጃጅቻለሁ

አሁንም ና ስትይ ቦርቄልሻለው

ደሞ አንቺ ብለሽኝ እንዴት እቀራለሁ

ይዘህ ና ያልሽኝን ሁሉን ሸምቻለው

ታማኝ ሰው ካገኘው እልክልሻለው

ደሞ አንቺ ብለሽ ኝ እንዴት እቀራለው

አንድ ቀን አንድ ቀን ካልሽኝ ነገር ተርፎ

መሳፈርያ ሳገኝ እኔም እመጣለሁ።

🎴ኑረዲን ኢሳ.🎴


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍28
#ባራኪ
.
.
አንቺ ዳቦ ሆነሽ
ለበረከት ~ ቀርበሽ፣
እኔ ቄስ ብሆን
የነፍስ አባት ~ ቆራሽ፣
.
.
"ክቡርነትዎ አባ ቄሱ፣
በረከቱ ላይ ይቀድሱ፣
ቀድሰውም ይቁረሱ፣
ቆርሰውም
ለምእመናኑ ያዳርሱ፣"
.
.
ብባል ወስነው ቢፈርዱብኝ፣
መቁረሱ ግዴታ ~ ቢሆንብኝ፣
.
.
በመስቀሉ
ባርኬ ~ ቀድሼሽ፣
ሶስት ቦታ
ከፍዬ ~ ቆርሼሽ፣
እንዲህ ነበር የማከፋፍልሽ ፣
.
.
አንደኛው ለራስ ለቆራሹ፣
ሁለተኛው ለቄስ ለቀዳሹ፣
ሶስተኛው
ለነፍስ አባት
በፀሎቱ ምእመናንን ላስታዋሹ፣
.
.
እልና ሁለመናሽን
እከተዋለሁ ከኪሴ፣
ማንም እጅ አትገቢም
አንቺ ነሽ ~ የራሴ፣
.
.
ባንቺ የመጣ
አልፈራም ~ ኩነኔ፣
ገሀነም ልውረድ
እንጂ
ምንጊዜም ነሽ የኔ!!!

🎴ሀብታሙ ወዳጅ🎴


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍27🥰52😁2
#ቦጭቁኝ

እንደጉድ፤ ቦጭቁኝ

እኔ፤ ያ ምቀኛ

እኔ፤ ያ ጉረኛ

ጭንቅላተ፤ ደነዝ

እሱን ብሎ፤ ጎበዝ

ብላቹ ዘንጥሉ፤ እሙኝ በናታቹ

ከበዛው ወንጀሌ ትንሽ ላካፍላቹ

ታድያ ለመቼ ነው ጓደኝነታቹ።


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍26😁41🔥1
#ሞትኩልሽ

ያቺ  ....
ያኔ እንዲያ ላመልካት
የዳዳኝ መውደዴ
'ሞትኩልሽ' ያልኳት ልጅ
በህይወት አለች እንዴ??

አወይ ጊዜ ዳኛ
አወይ ወረት ክፉ
ባልተሰጣቸው መስክ
ቀን ከሌት ሲለፉ
ስንቶች ረገፉ  !!!

#Share and #subscribe my #YouTube

አረ ገባ ገባ እያላቹ 500 አስገቡት
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍182👏1😁1
አንዳንዶቻችን ከደስታ ይልቅ ሃዘንን፣ ከስኬት ይልቅ ችግር ላይ መቆዘም እንወዳለን።
እንዲህ ሆኜ...ተንከራትቼ...በዚህ ወጥቼ በዛ ገብቼ እያለን ችግሮቻችንን ሁሉ እንደከንቱ ውዳሴ ስንደጋግም፣ እንዲሁ ስናከብዳቸው እንውላለን ።

አዎ! እርግጥ ነው ሁሉም ሰው የራሱ የማይመቹ የህይወት መንገዶችን ያልፋል ነገር ግን ችግሩን አብዝቶ ስላወራው ብቻ ከችግሩ ነፃ ይሆናል ማለት አይደለም። ይልቅ ለችግሩ ተገዢ እየሆነ ይሄዳል እንጂ...ከዛም ባለፈ ችግሩን ማንነቱ አድርጎ ይቀበላል።

ወዳጄ ሆይ እስኪ አመስጋኝ እንሁን። ማታ ተኝቶ ጠዋት መንቃት በራሱ እኮ እራሱን የቻለ እድለኝነት፣  እራሱን የቻለ መመረጥ ነው። በጤንነት ብቻ መኖር በራሱ ድንቅ ነገር፣  ድንቅ ስጦታ ነው። በተሰጠን አመስጋኝ እንሁን የቀረው ነገር ወይም የኛ አይደለም ወይም ግዜውን ጠብቆ መምጣቱ አይቀርምና።

ፈጣሪ ሆይ

ካላየኃቸው እና ከማላቃቸው አደጋዎች ስላዳንከኝ ፣ በፈተና አፅንተህ ስላጠነከርከኝ ፣በፈተናዎች ወድቄ ስለተማርኩኝ

ክበሩን አንተ ውሰድ።

ስታበይ እንደመታበዬ ፣ስበድል እንደ በደሌ ፣ ስወድቅ እንዳወዳደቄ፣ ሰጠግብ እንዳጠጋገቤ በሆንኩት ልክ ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ስለምታኖረኝ

ክበሩን አንተ ውሰድ።

የሚያስፈልገኝን ሁሉ ስለምትሰጠኝ ፣ በመንገዴ ሞገስ ስለሆንከኝ ፣ ዙሪያዬ በመልካም ሰዎች ስላስከበብከኝ ።

አመሰግናለሁ፨

በረከቴ ስለሚታየኝ ፣ጤናዬ ስለሚታወቀኝ፣ 
ህያውነትህን ተጠራጥሬ ስለማላውቅ።

መልካም ቀን

#Share and #subscribe my #YouTube

አረ ገባ ገባ እያላቹ 500 አስገቡት
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏21👍93
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ዘጠኝ

ቤቱ!

ያ ቤቱ የእኔ ገነት ነበር፣ ቤቱን እወደዋለሁ። የእሱ የሆነውን ነገር ሁሉ እወዳለሁ፡፡ ዛሬም ድረስ ያ ቤቱ እንደ ሰው ይናፍቀኛል። ላፍቶ የሚባል ሰፈር ከተሠሩ የኮንዶሚኒዬም ሕንፃዎች በአንዱ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ነበር የሚኖረው። ንጹህ ቤት ... ሲበዛ ንጹህ፣ ሰላም ያለው ቤት ነበር። እንደ እሱ ቼልተኛ ነፍስ ካለው ወንደላጤ የማይጠበቅ። በተለይ በተለይ የ “ሲዲ ፕሌየሩ” ነገር፡፡ ስለዚህ ነገር ለጓደኞቼ ሁሉ አውርቼ አልጠግብም፡፡ ዞር ስል አካበደችው ይሉ ይሆናል፣ ግን እስከአሁን የትም አይቼው የማላውቀው “ሲዲ ፕሌየር'' እዚያ ቤት ነበር። ወደጎን ሁለት ሜትር የሚሆን ቦታ ይዞ በሞገስ የተቀመጠ፣ አራት ትልልቅ ስፒከር ያለው፣ ከትልቅነቱ ብዛት አንድ ላይ ለማስቀመጥ ቦታ ስላልበቃው አንዱን ስፒከር ለብቻው በመስኮቱ በኩል አስቀምጦታል፡፡ አንዳንዴ ይኼን “ስፒከር' እንደ ወንበር ሲቀመጥበት “እንዴ! ልትሰብረው ነው እንዴ?” ብዬ ጎትቼ አስነሰዋለሁ፡፡ እስቲ እዚያ ባዶውን የተቀመጠ ሰፋ እያለ፣ የቴፕ ስፒከር ላይ መቀመጥ ምን የሚሉት ነገር ነው? ተቀምጦ ቁም ነገር የሚሠራ አይመስልም!? በመስኮት ያንን ኮብል ስቶን የተነጠፈበት ደባሪ የመኪና ማቆሚያ ለማዬት፤ ሁልጊዜ እናቱ ገበያ እንደሄደችበት ሕፃን በመስኮት ውጭ ውጩን ማዬት ይወዳል፡፡ነፍሱ ምን እንደሚናፍቅ እንጃ። “ሲዲ ፕሌየሩ” 'ልጃችን ነገር ነበር የሚመስለኝ። እኔና እሱ ተጋብተን “ሲዲ ፕሌየር” የወለድን። መስኮ መስኮቱ ሰፊ ስለሆነ መጋረጃው ሲሰበሰብ ቤቱ በብርሃን ተጥለቅልቆ በረንዳ ይመስላ ስላል፤ ሁልጊዜ መጋረጃውን ጋርጄ መብራት አበራለሁ፤ እንደዚያ ሲሆን የሆነ "ኮዚ' ይሆናል። የመስኮ የመስኮት መጋሪ ጋሚመለከት ሰውም ም ይጨንቀኛል፡፡ መጋረጃ

የመጀመሪያ ቀን እቤቱ ስሄድ ዓይኔ ያረፈው እዚያ “ሲዲ ፕሌየር” ላይ ነበር። አለ አይደል ለሁሉ ነገር እንስፍስፍ ላለመባል “ይኼ ነገር ያምራል!” በሚል ልዩ? አስተያዬት ባልፈውም ስለ አብርሃም ቤት በሰብኩ ቁጥር ስለዚያ እቃ ያላሰብኩበት ጊዜ የለም፡፡ ድምፁ የማይታመን ነው፤ ስንት ዓመት የሰማኋቸው ዘፈኖች እሱ በት ስሰማቼው ተዓምር ይሆኑብኛል። ምንድን ነው? ማለቴ ባለ አንድ መኝታ ቤት ኮንዶሚኒዬም ውስጥ የሆነ ትልቅ የሙዚቃ ስቱዲዮ ውስጥ የሚገኝ ዓይነት የሙዚቃ ማጫወቻ እቃ መገኜቱ? እና... እኔ ሙዚቃ ሁሉ ነገሬ የሆንኩ - እኔ እዚያ 07號? መጀመሪያ የመሰለኝ፣ በቃ ለሙዚቃ የተለዬ ፍቅር ያለው ነበር፤ እየቆዬን የገረመ˘ ነገር ያንን የሚያክል “ሲዲ ፕሌየር” ጭራሽ ቤቱ ውስጥ እንደሌለ ዓይነት አያስታውሰውም ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ እንኳን “ሲዲ” በቤቱ አልነበረም። በቃ ዘፈን አያዳምጥም፣ ሃይማኖተኛ ሆኖ ነው እንዳልል መዝሙርም አያዳምጥም ...ባለ አምሳ ስምንት ኢንች ፍላት ስክሪን ቲቪ አለው፡፡ ግድግዳው ላይ የተሰቀለ፣ እሱንም ከፍቶት አያውቅም፡፡ ዝም ያለ ጉድ፡፡ “እና ቤት ዉስጥ ስትሆን ምን ትሠራለህ ?'' አልኩት ተገርሜ፣ “አነባለሁ ፣ እጽፋለሁ ፣ እና ምግብ እሠራለሁ ... !

" ምግብ!?"

“አዎ! ምግብ ...ደስ ይለኛል ምግብ መሥራት፣ ያን ያኽል ባለሙያ ባልሆንም...” እንደመደንገጥ አልኩ፡፡ ስለ ምግብ ማብሰል ሲነሳ ሁልጊዜ እደነግጣለሁ፡፡ ብዙም ስለ ምግብ ወሬ ማውራት አልፈለግሁም፡፡ ምክንያቱም የሙያ ነገር አይሆንልኝም ነበር። ምግብ ላይ ጥሩ ባለሙያ አልነበርኩም። ብዙ ደክሜ የሠራሁት ምግብ መንም ምንም አይልም፡፡ ወንድሞቼ ከእኔ የተሻለ ጎበዞች ነበሩ፡፡ እንደ ቀልድ ግብ መሥራት ትወዳለህ፣ መጻፍ ትወዳለህ... ሌላ ምን ትወዳለህ?'' አልኩት፣ ጨዋታ ለማስቀዬር፡፡

ሴት!" አለኝ ፡፡ አባባሉ ዳል ፎርማል ነገር እንደተናገረ ዓይነት ቀለል አድርጎ ነበር የተናገረው. ወይስ ኖርማል ነው? ከዚያም በኋላ በወሬ ወሬ ስናነሰው አይደብቅም እዚህ ቤት መ ት ግን እንቶን ብቻ ነው አለኝ። አመንኩት! የማለው ምክንያት አልነበረኝም፤ በፈለግሁት ሰዓት እንድሄድ የቤቱን ቁልፍ ሲሰጠኝ መቼም በራሱ ቢተማመን ነው። ያቺን ቁልፍ የሰጠኝ ቀን የገነት መግቢያ ቁልፍ የተሰጠኝ ያኽል በደስታ አብጄ ነበር፤ ዛሬ ላይ እሱን የሚያስታውስ እጄ ላይ ያለ ብቸኛ ቁስ ቢኖርያ ቁልፍ ብቻ ነው። ብዙ ሴቶች ማወቁ ደስ አላለኝም፡፡ መቼም ድንግል እንዲሆን ባልመኝም ይኼ ነገሩ ግን ደስ አይለኝም ነበር፡፡ ደግሞ እገረማለሁ አብረን በነበርንባቼው አራት ዓመታት፣ አንድም ቀን ከዚያ በፊት ስለሚያውቃቸው ሴቶች አውርቶልኝ አያውቅም፡፡ ለምን እንደሆን እንጃ እንዲነግረኝ እፈልግ ነበር፤ግን በቀጥታ ጠይቄው አላውቅም፡፡ እንዴት ሊረሳቼው ቻለ? እላለሁ በውስጤ - ልክ እንደሌሉ እንዳልተፈጠሩ እንዴት ረሳቼው? በሆነ አጋጣሚ በወሬ መካከል እንኳን እንዴት አንዷ ስላደረገቸው፣ ስለተናገረችው፣ ወይም አብረው ስለሄዱበት ቦታ አያነሳም? ...እኔንም እንደዚሁ ይሆን የሚረሳኝ? ታዲያ ከተለያዬን ከአራት ዓመት በኋላ መጽሐፍ አሳተመ ሲባል ተጣድፌ ገዛሁ፤ እኔን ራሴን የሆነ ቦታ በሆነ መንገድ ጽፎኝ ከሆነ ለመፈለግ፡፡ያ ያሳለፍኩት ጊዜ በዉስጤ የፈጠርኩት ቅዠት እንዳልነበር ምስክር ፍለጋ፡፡ ሳያዉቀኝ በፊት የጻፈኝ የመሰለኝ ሰው ካወቀኝ በኋላ ረስቶኛል፡፡ ስሜን ከእነ ቤት ቁጥሬ ይጻፍልኝ ማለቴ አልነበረም፤ ግን ደራሲዎች ባለፉበት መንገድ ስላዩት ዛፍ አይጽፉም? ስለቀኑ ደመናማነት አይጽፉም? መንገድ ዳር ስለተቀመጡ ጫማ ሰፊዎች አይጽፉም? ቡናቼዉ ዉስጥ ስለገባችዉ ዝንብ አይጽፉም? ከነዚያ እንደ አንዱ መንገደኛም ቢሆን ሲያልፍ አላዬኝም?! የሆነ ሆኖ "ሲዲ ፕሌየሩ" የቤቱ ልብ ነበር- ለእኔ። ለዚያ ነው የምወዳቼውን “ሲዲዎች ሁሉ እሱ ጋ የማስቀምጣቼው የነበረው፡፡ ያ ቤቱ ከረብሻዬ ሁሉ የምደበቅበት ዋሻዬ ነበር፡፡ እና የረሳሁት ነገር

“ኪችኑ' ውስጥ ትልልቅ ምግብ ቤቶች የሚጠቀሙበት ዓይነት የኤሌክትሪክ “ስቶቭ ነበረው፡፡ “ደግሞ ይኼ ምን ይደርግልኻል?" አልኩት ተገርሜ፡፡ በትክክል የምን ኤምባሲ እንደሆነ እንጃ ብቻ እዚያ የሚሠራ ጓደኛው ኤምባሲ ዕቃ ሲቀይር "ሲዲ ፕሌሩን እና ስቶቩን” ገዝቶ እንዳመጣለት ነገረኝ። ያንን “ስቶቭ” የጎሪጥ ነበር የማዬው ሙያ ስለሚባል፣ እኔ ስለማልኖርበት ሌላ የሴት ዓለም ያስታውሰኛል። የተበደልኩበት ሌላ ጉዳይ... የሴት ልጅ ሙያ የሚሉት ነገር አልነበረኝም፤ ምግብ ማብሰል፤ ቡና ማፍላት፤ ጓዳ ውስጥ ጉድጉድ ማለት... ምንም! መርመጥመጥ ምን ያደርግልሻል እየተባልኩ ነው ያደግሁት፡፡ እሺታን እንደ እምቢታ! እናም አግባኝ አልኩት መልሱ የሚገርም ነበር “እሺ!'' ነበር ያለው “እሺ!'' ፊቱ ላይ ምንም የተለዬ ስሜት አልነበረም፡፡ አልተገረመም፣ ፈገግ አላለም፣ አላዘነም፣ ቅሬታ ወይም ማንገራገር አልነበረም፣ ምንም የለም “እሺ!'' አባባሉ፣ ለእኔ ብቻ የሚገባ “እምቢ!'' ነበር፡፡ በደስታ ይፍለቀለቃል ብዬ አስቤ ነበር፤ ያቅፈኛል ብዬ አስቤ ነበር፤ መቼ እናድርገው? ብሎ ይጠይቀኛል ብዬ ነበር፤ እኔም ከነገ ዛሬ እጠይቅሻለሁ ብዬ ሳስብ ቀደምሽኝ ብሎኝ እንሳሳቃለን ብዬ አስቤ ነበር፤ ከዚህ ሁሉ ሐሳብ አልፌ ለአባቴ እንዴት እንደምነግረው እያሰብኩ ነበር ጥያቄዬን ያነሳሁት። እሺ! በሚል መጠቅለያ እምቢታውን አቀበለኝ፡፡ ብዙ ሴት ጓደኞቼ ለጋብቻ ሲጠዬቁ አይቻለሁና የሚገባኝ አንድ እውነት አለ፤ ወንዶች ሥጋቼው ለአንድ ደቂቃ ተንበርክኮ ለጋብቻ እንዲጠይቀን ነፍሳችን
👍47🥰3😱32
ለዓመታት ተንበርክካ ትለምናቼዋለች። እኔ ቃል አውጥቼም ልመናው አልተሳካልኝም። ተስፋ መቁረጥ የሚባለው ነገር ያኔ ነው የገባኝ፤ የሆነ ብዙ የሸክላ ሰሃን ከተደረደረበት እየወረደ እንደሚንኮታኮት ዓይነት ውስጤ የነበረ ደስታ፣ ተስፋ፣ ሳቅ እምነት፣ ጉጉት ሁሉም ወርዶ ተንኮታኮተ። በአንድ ጊዜ ሥጋ ብቻ ሆንኩ፡፡ በዶ መንፈስ፣ በዶ ነፍስ ...በቃ ሥጋ ... ከዚያን ቀን ጀምሮ እሱ ጋር የምተኛው ራሴን ስለጠላሁ ለመቅጣት ነበር።መቆሸሽ ነው የሚሰማኝ፡፡ ተራ መሆን ነው የሚሰማኝ፡፡ ቢሆንም ሌላ ወንድ የሚባል ነገር በጭራሽ አስቤ አላውቅም ነበር፤ እንደዚያው በዶ እንደሆንኩ ቀስ በቀስ መሞት ነበር ምኞቴ- አይገባውም፤ የገረመኝ ልዩነቱ እይገባውም፡፡ እኔ ለእሱ ሰውነት ብቻ ነበርኩ፡፡ እንደ “ሲዲ ፕሌየሩ'' እዚያ የተቀመጥኩ፣ እንደ ቴሌቪዥኑ እዚያ ግድግዳው ላይ የተሰቀልኩ፣ እንደ ስልክ፣ እንደ አበባ ማስቀመጫ፣ እንደ ጀበና፣ በዙሪያው ካሉ ነገሮች እንደ አንዱ ዕቃ ነበርኩ፡፡ ቆይ እኔ ግራ የገባኝ፣ ሴት በአገሩ ሞልቷል ቆንጆ ቆንጆ ሴት ያውም ግጥም፣ ደራሲ፣ ነፍሴ ምናምን የሚሉ ይኼን ሁሉ ዓመት ለምንድን ነው? እኔ ጋር የቆዬው?!...ካላፈቀረኝ ለምን?! በቃ ጨረስን። ልክ በዚህ ተስፋ ቢስ ባዶነት ውስጥ ሆኜ ነበር ሕይወቴን የቀያዬረ መርዶ (መርዶ ልበል እንጂ) የገጠመኝ፡፡ እንደ ነጠላ፣ ከመኻል እጥፍ የሚያደርገኝ የሆድ ቁርጠት ድንገት ነበር የጀመረኝ፡፡ ቀለል አድርጌ ባዬውም በየሰዓቱ እየደጋገመ አላስቆም አላስቀምጥ አለኝ፡፡ ይኼ ሲገርመኝ፣ ከየትም የቡና ሺታ ሲሼተኝ ሊያስመልሰኝ ይተናነቀኛል፡፡ በጭራሽ እርግዝና ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ አንዳንዴ እንዘናጋለን፡፡ ወደ ሦስት ዓመት አብረን ስንቆይ እንዲህ ዓይነት ነገር ስላላጋጠመኝ ማርገዝ የሚባል ነገር መኖሩንም ሳልዘነጋው አልቀረሁም፡፡

እውነቱን ለመናገር እሱም ጥንቁቅ ነበር ። የዚያን ጊዜ እንዴት ይኼ ነገር ለፈጠር እንደቻለ አልገባኝም፡፡ ጓደኛዬ : ሃይሚን ስለሚያስቸግረኝ ሕመም ነገርኳት ሳታንገራግር ነበር እየጎተተች ወስዳ ያስመረመረችኝ፡፡ እንዴት በዚያ ፍጥነት ገባት? እላለሁ እስከ ዛሬ፡፡ የአንድ ወር ከዐሥራ አምስት ቀን ፅንስ ሆዴ ውስጥ ተቀምሱ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ያዘንኩት ለአባቴ ነው፡፡ ለአባቴ ብቻ፡፡ “አስወጪው! ከዚህ ውሻማ አትወልጅም!'' አለችኝ ሃይሚ፡፡ጥሎባት አትወደውም፣ ያው በእኔ ምክንያት ነው፡፡ አላንገራገርኩም፤ ግን ልነግረው አልፈለግሁም ነበር። ምንም እንኳን ራሴን እግሩ ሥር ብጥል ስላረገዝኩ አግባኝ ወደሚል ተራነት ራሴን ማውረድ አልፈለግሁም፡፡ እኔን ያልፈለገ ወንድ፣ ልጅ እንደ ሽጉጥ ተደቅኖበት የሚገባበት ትዳር ምን ዓይነት ነው? እናም ለማስወረድ ወሰንኩ፡፡ ማስወረድ ማለት ልክ እንደሆነ ሕመም ውስጣችን ያለውን ፅንስ አውጥቶ ጥሎ ወደ 'ኖርማል' ሕይወት መመለስ ነበር የመሰለኝ፤ ቀላል የተወሰነ ሕመም ያለው የሰዓታት ሥራ። በዚያ ላይ የጓደኛዬ የሃይሚ ግፊት ተጨምሮበት ነገሩን ሁለት ጊዜ እንኳን አላሰብኩበትም። ለአባቴም፣ ለአብርሃምም ፊልድ እንደምወጣ ነግሪያቼው ሃይሚ ጋር ፅንስ ወደማስወጣበት ክሊኒክ ሄድን፡፡ የገጠመኝ ነገር ካሰብኩት ፈጽሞ የተለዬ ነበር፡፡ ስቃዩ _ አይነገርም፣ዘላለም የሚመስል ረዥምና የማያቋርጥ _ ስቃይ፡፡ ዶክተሩ መቋቋም እስኪያቅተው፣ ጩኸቴና መወራጨቴ ቀላል አልነበረም፡፡ ምንድን ነው የዘጠኝ ወር ልጅ ነው የሚወጣው ወይስ እንዳሉት ሁለት ወር ያልሞላው ፅንስ? ...ያንን ሕመም ሳስታውስ እስከ ዛሬ ልቤ ላይ የሚሰማኝ ማቅለሽለሽ አለ፡፡ ከውስጤ የሚወጣው ፈሳሽ፣ ደም ብቻ ሳይሆን ቀስ በቀስ እኔ ራሴ እየሟሟሁ የምፈስ ነበር የመሰለኝ። ከእያንዳንዱ የሰውነት ክፍሌ ፈሳሽ ነገር ሁሉ ወጥቶ፣ ቆዳዬ እንደ ቅጠል የደረቀ መሰለኝ፡፡ ሰው ሳልሆን አጥበው የጠመዘዙት የሆነ ልብስ ነገር ፤ እንደዚያ ነው የተሰማኝ ፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍456
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዶ/ር ሶፊያ ከታዲዬስ ጋር ላላት የቁርስ ግብዣ ቀጠሮ ለመዘጋጀት በለሊት ነው የተነሳችው፡፡ ስለእሱ እና ስለልጆቹ ስታሰላስል ስላደረች በቂ እንቅልፍ አልተኛችም፡፡ቀለል እንዲላት ሻወር ወሰደች ፡፡ ልብሷን በመለባበስ ላይ እያለች ሞባይሏ ጠራ.የማታውቀው ቁጥር ነው፡፡አነሳችው፡፡፡

<<ሄሎ>>

‹‹ሄሎ ሰላም አደርሽ?››

‹‹እግዜያብሄር ይመስገን ...ይቅርታ ግን ማን ልበል አላወቅኩህም፡፡››

‹‹አላዓዛር እባላለሁ፡፡››

‹‹አላዓዛር..አላዓዛር››

‹‹የሰላም ስዕል አስተማሪ፤የታዲዬስ…፡፡››

‹‹አወቅኩህ፤አንተ ቁምነገረኛ ነህ፡፡››

‹‹በጣም እንጂ ፤ ይሄው ሰማይና ምድሩ ከመላቀቁ ደወልኩልሽ››

‹‹በጣም አመሰግናለሁ፤ እንደውም በጣም ስፈልግህ ነበር፡፡ >>

ውስጡን ሞቀው‹‹... እኔ እንደፈለግኳት እሷም ስትፈልገኝ ነበር ማለት ነው ? >> ሲል ተኩራራ፡፡

‹‹ለምንድን ነበር የፈለግሺኝ፤በሰላም ነው?››

‹‹አይ ሰላም ነው፤ስለታዲዬስ አንዳንድ ነገሮችን ልጠይቅህ ነበር?››

‹‹ለምሳሌ ምን?››

‹‹ማኛውንም ነገር ፤ለምሳሌ ያንን የመሰለ ቪላ ቤት ከየት አመጣው?››

‹‹ውርስ ነው፡፡እናቱ ይርጋጨፌ አካባቢ ትልቅ የቡና መሬት ነበራቸው፡፡ ባለሀብት ነበሩ ፡፡ ሲሞቱ ቤቱንም ፤ የቡና ማሳውንም መጠኑን የማላውቀው ጥሬ ብርም እንዳወረሱት አውቃለሁ፡፡እሱ ደግሞ በነሰላም ላይ ኢንቨስት እያደረገው ነው፡፡››

‹‹ቆይ አንድ ያልገባኝ ነገር ታዲያ ይሄ ሁሉ ንብረት ካለው ለምን የሊስትሮ መስራት አስፈለገው?››

‹‹ቆይ ስለታዲዬስ ምንም አታውቂም ማለት ነው?>>

‹‹አዎ እውቂያችን አጭር ነው፡፡በጣም ሚስጥራዊ ሰው ሆኖብኛል፡፡››

አላዓዛር የዶክተሯ አካሄድ አላማረውም‹‹ዘመድሽ አይደለም አይደል?››

‹‹አዎ አይደለውም፡፡በአጋጣሚ ነው የተዋወቅኩት፡፡ከዛ በኃላ ግን ፈፅሞ ልረሳው አልተቻለኝም፡፡››

‹‹ማለት ፍቅር ቢጤ ማለትሽ ነው?››

‹‹እንደዛ ማለት እንኳን ይከብደኛል፤አይ አይደለም…..እኔ በባለፈ ህይወቴ ብዙ ያልተጠናቀቀ የፍቅር ጣጣ ያለብኝ ሰው ነኝ፤ግን ተረዳኝ አላዓዛር በታዲዬስ በጣም ተስቤበታለሁ ...እና ጥያቄዬን መልስልኝ፡፡ የገንዘብ ችግር ከሌለበት ለምን ሊስትሮ ይሰራል?››

‹‹ዶ/ር ..ታዲዬስ ማይሰራው የስራ አይነት የለም፡፡ሲያሰኘው የሆቴል አስተናጋጅ ይሆናል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ የትልቅ መስሪያ ቤት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡ስራን የሚሰራው ለገንዘብ ሳይሆን በውስጡ ላለው ፍልስፍና ሲል ነው፡››

‹‹ቆይ ስለትምህርት ደረጃው ልትነግረኝ ትችላለህ?››

‹‹ሁለት ዲግሪ 3 ዲፕሎማ እና ቁጥራቸውን የማላውቀው ሰርተፍኬት በተለያየ ሞያዎች አለው፡፡››

‹‹ስለታዲዬስ እኮ ነው የምጠይቅህ? >>

‹‹እኔም ስለእሱ ነው እያወራሁሽ ያለሁት፡፡››

‹‹ቆይ ግን..››ቀጣዩን ጥያቄ ካማጠናቀቋ በፊት የአላዓዛር ስልክ ተቋረጠ፤ሳንቲም ጨርሶ ነው ብላ በማሰብ መልሳ ደወለችለት፤ ጥሪ አይቀበልም ይላል፡፡

‹‹ብሽቅ አለች››ጥያቄቿን ከማጠናቀቋ በፊት የስልኩ መቋረጥ አበሳጭቷታል፡፡ልብሷን ለብሳ ካጠናቀቀች በኋላ በቀጠሮዋ መሰረት 2 ሰዓት ሲሆን ግቢ ውስጥ ያለውን መኪናዋን በማስነሳት ታዲዬስ ሊስትሮ ወደሚሰራበት ቦታ አሸከረከረች፡፡አገኘችው፡፡ስላምታ ተለዋወጡ፡፡

‹‹በቀጠሮችን መሰረት መጥቻለሁ›› አለችው ፡፡

‹‹መሄድ እንችላለን ››ብሎ ቀድሟት ወደ መኪናው አመራ፡፡

‹‹ዕቃህንስ… ?ማን ይጠብቅልሀል?››

‹‹ችግር የለውም፡፡››

‹‹ማለት መፅሀፎቹን አይሰርቁህም?››

‹‹መፅሀፍ የሚሰርቅ ሰው ሰረቀ አይባልም፡፡››

‹‹እንዴት ?››አለችው መኪናው ውስጥ ገብታ ሞተሩን እያስነሳች፡፡

‹‹ከዚህ የሚወስደው ወይ ለማንበብ ነው አልያም ለሚያነብ ሰው ለመሸጥ ነው፡፡ በሁለቱም መንገድ አውቆም ይሁን ሳያውቅ እውቀትን እያስፋፋ ነው፤ስለዚህ ሊመሰገን ይገበዋል፡፡››

‹‹ትገርማለህ..እሺ ቁርሱ የት ይሁን ?>>

‹‹ጋባዥ አንቺ አይደለሽ የፈለግሺው ቦታ፡፡›› ተስማምታ አሽከረከረች፤ ወደ ሀይሌ ሪዞርት ወሰደችው ፡፡ህንጻውን አልፈው ከጓሮ ሀይቁ ዳር ከሚገኝ አንድ መቀመጫ ላይ ፊታቸውን ወደሀይቁ አዙረው ጐን ለጐን ተቀመጡ፡፡
ወዲያው አስተናጋጁ መጣና የሞቀ ሰላምታ ካቀረበላቸው በኃላ የታዘዘውን ቁርስ መዝግቦ ሲመለስ የሆቴሉ ስራ‐አስኪያጅ በቦታው ተተካና ለታዲዬስ የወዳጅነት የሞቀ ሰላምታ አቅርቦለት ከእሷ ጋርም ተዋውቆ ተመለሰ፡፡

‹‹ታዲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?››

‹‹አልፈልግም፡፡>>

‹‹እውነቴን እኮ ነው፡፡››

‹‹እውነትሽን እንደሆነ አውቃለሁ..ይህ ቁርስ እስኪመጣ 15 ደቂቃ ይፈጃል..ይህቺን ጊዜ በዝምታ ፀሀይ እየሞቅኩ ማሳለፍ ነው የምፈልገው››አላት ዓይኖቹን ወደ ሀይቁ እየላከ፡፡እሷም በኩርፊያ እና በንዴት መካከል ሆና ዝምታውን ተቀላቀለች፡፡የጥዋቷ ፀሀይ ከወደ ምስራቁ የምትረጨው ጨረር ሀይቁ ላይ ሲያርፍ በአከባቢው ሊነገር የማይችል የቀለማት ህብረ ቀለም እና ልዩ የሆነ ስሜትን በሰውነት ውስጥ ይረጫል፤የጥዋቱ ቀዝቃዛ
አየርም እንደዛው ለውስጥ ሰላምን ያጓናፅፋል፡፡በንዴት ጀምራው የነበረውን ዝምታ ቀስ በቀስ በደሰታ ታጣጥመው ጀመር፡፡ልክ ታዲዬስ እንደገመተው ከ15 ደቂቃ በኃላ ቁርሱ ቀረበ እና መመገብ ጀመሩ፡፡

አንድ ጉርሻ ጠቅልላ ወደ አፏ እየላከች‹‹እሺ አሁን ጥያቄዬን መጠየቅ የምችል ይመስለኛል፡፡››አለችው፡፡

‹‹የምታደርጊውን ነገር ሁሉ በጽሞና ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ስትበይ ዝም ብለሽ ብይ፤ሁሉ ነገር በማስተዋል ሲያጣጠጥሙት ነው እርካታ የሚያጐናጽፈው፡፡›.

‹‹ይሄማ ሰይጣን አለበት››ስትል በውስጧ ደመደመችና እንዳዘዛት በዝምታ መብላት ጀመረች፡፡

በልተው ካጠናቀቁ <<አሁን የፈለግሽውን ጠይቂኝ ..15 ደቂቃ መጫወት እንችላለን፡፡››

‹‹ግራ ገባት፡፡ በአእምሮዋ ታጭቀው የነበሩት ጥያቄዎች ሁሉ ተበታትነው የት እንደገቡባት አታውቅም..…ዝም ብላ አፏ ላይ የመጣለትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡››

‹‹ትናንት እራት የበላንበት ቤትም ሆነ እዚህ ያሉ ሰራተኛች ከስራ‐አስኪያጆቹ ጭምር በጣም ይቀርቡሀል፤ይወዱሀል፡፡››

አዎ እዚህ በአስተናጋጅነት ..የማታው ቤት ደግሞ በስራ‐አስኪያጅነት ሰርቼ ስለነበር ነው ፤ሌላ ሚስጥር የለውም፡፡››

‹‹በሞያው ሰልጥነሀል?››

‹‹አዎ በሆቴል ማነጅመንት ዲፕሎማ አለኝ፡፡››

‹‹ሌሎች ሁለት ዲግሪዎችም እንዳሉህ ሰምቼያለሁ፡፡›.

‹‹በምን ፊልድ››

‹‹ሲቪል ኢንጂነሪንግ እና ሶሾሎጂ›.

‹‹የምትገርም ነህ፤ታዲያ በተማርክበት ሞያ ደህና የተባለ ስራ መስራት ስትችል...››

አላስጨረሳትም‹‹ደህና የሚባል ስራ የለም፤ሁሉም ስራዎች በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡እስቲ ለሊት ተነስተው አስፓልቱን
የሚያጸዱ የፅዳት ሰራተኛች ባይኖሩ የከተማችን መንገዶች እንዴት አስጠሊታ
ይሆኑ እንደነበር አስበሽ ታውቂያለሽ?

በየበረንዳው የጀበና ቡና አፍልተው በርካሽ የሚሸጡ ወጣት ሴቶች ባይኖሩ ስንቱ ቡና ሱሰኛ ቀኑ ተበላሽቶበት እንደሚውል አልመሸ
ታውቂያለሽ.?ቁራሊዬ ባይኖር ሰፈራችን ባልባሌ ኮተቶች ምንያህል ተጨናንቆ እንደነበር ገምተሻል?ድንጋይ ፈላጩ
፤ግንበኛው እና አናፂው ባይኖር ኢንጂነሩ
ይሄንን ህንፃ ማነፅ እንደማይችል አታውቂም.?
👍86👏53😱3👎2
አየሽ እኔ ስራን የምሰራው ለብር አይደለም እያንዳንዱን የህይወት ዘርፍ ለማጣጣም እንዲያመቸኝ ነው፡፡ሳይት ኢንጂነር
ሆኜ ሰርቼያለሁ፤የሆቴል ማናጀር ሆኜያለሁ፤ተሸካሚ ሆኜ ሰርቼ አውቃለሁ፤ ዌይተርም ነበርኩ፤ አስተማሪም ሆኜ ሰርቼያለሁ..ብዙ ብዙ ነገር፡፡ይሄንን የማደርገው ከነዛ የስራ ዘርፎች የሚገኘውን የህይወት ልምድ ቀጥታ ለማግኘት ስል ነው፡፡››

‹‹የሚገርም ነው!!!የወደፊት እቅድህን ልትነግረኝ ትችላለህ?››

‹‹የወደፊት ዕቅዴ ህዝብና መንግስትን ማሳቀቅ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹አየሽ... ሰሞኑን የተዋወቅሻቸው አምስት ልጆቼን በየተሰጥኦዋቸው የመጨረሻው ስኬት ላይ እንዲደርሱ ማገዝ ነው ዋና የህይወት ግቤ፡፡…ያ ሲሆን ደግሞ እነዚህ ልጆች ከበረንዳ ኑሮ ከቆሻሻ ላይ ተነስተው የሀገሪቱ ምርጥ ሰው ሆነው ሲገኙ..መንግስትም ሆነ ማንም ገንዘብ አለኝ የሚል ግለሰብ ስንቱ ምጡቅ
አዕምሮ ያለው ትውልድ በየቆሻሻው ባክኖ እንደቀረ ማሰብና መቆጨት ይጀምራል፡፡ከዛም ከአንድ ሺ መካከል አንድ ሰው እንኳን የእኔን ልጆች ስኬት ተመልክቶ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ቢነሳ ጎዳና ባክኖ የሚቀር አንድ ህፃን እንኳን አይገኝም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ በአጠቃላይ እኔ ይሄንን አድርጌያለሁ ... እናንተስ ?...ለማለት ነው..፡፡የተግባር ስብከት ለመስበክ፡፡››

ቀጣይ ምን እንደምትጠይቀው እያሰላሰለች ሳለ የእሱ ስልክ ድምፅ አሰማ፡፡

<ሄሎ ሰላም::>>

<<ሄሎ>>

<<ምን?>>

‹‹መጣሁ...በቃ ሄለን ሞባይሉን ስጫትና ከኋላ ትከተለው ..ደውዬላት ያሉበት ድረስ ሄዳለሁ፡፡›› ስልኩን ዘጋው፡

‹‹ምነው? ምን ሆንክ?››

‹‹ሙሴ ከግቢ ወጥቷል ...ሂሳብ ክፈይና እንሂድ፡፡››ከቦርሳዋ ብር አወጣችና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ በመነሳት ወደመኪናው አመራች ፡፡እሱም ተከትሏታል፡፡ የተፈጠረው ችግር አልገባትም፡፡

ከግቢው ወጥተው መንገድ እንደያዙ‹‹አልገባኝም..ሙሴ ከግቢ መውጣቱ ችግር አለው?››

‹‹አዎ..ሙሴ ትንሽ ክትትል የሚፈልግ ልጅ ነው፤ከግቢ የሚወጣው ብዙውን ጊዜ የሆነ ነገር ለመስራት አስቦ የሆነ ቁሳቁስ ሲያጣ ፍለጋ ነው፡፡››

‹‹ከየት ነው የሚፈልገው?››

‹‹ከየመንገዱ.፤ከየቆሻሻ መጣያው...የፈለገውን እሲኪያገኝ ድረስ ሲባዝን ነው የሚውለው..ካጣ ደግሞ ስለሚ።በሳጭ ያመዋል፡፡››

‹‹ምንድነው የሚያመው?››

‹‹የሚጥል በሽታ አለበት፡፡ሙሴ ተአምራዊ የሆነ የፈጠራ ብቃት አለው፡፡ ይሁን እንጂ በዛው ልክ ታማሚ፤ከሰው የማይግባባ፤የትምህርት ለመማር የሚያዳግተው የተለየ ልጅ ነው፡፡››

‹‹ቆይ ..አንድ የማይገባኝ ነገር እንዲህ የተለየ የፈጠራ ብቃት እያለው ትምህርት ለመማር እንዴት ይከብደዋል?››

‹‹በዚህ አለም የትምህርት ስርዓት ስትማሪ በካሪኩለሙ በተቀመጠው ልክ ካልተጓዝሽ ደደብ ነሽ፡፡››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ማለቴ ሰነፍም ከሆንሽ…በጣምም ከመጠን ያለፈ ጎበዝ ከሆንሽ በተመሳሳይ ‹ደደብ ነሽ >ነው የምትባይው...ምክንያቱም ሰነፍ ስትሆኚ የእውነት አንቺ አታውቂም ...በጣም ጎበዝ ስትሆኚ ደግሞ አንቺ ባወቅሺው መጠን
ካሪኩለሙም አስተማሪዎችሽም አያውቁም፡፡

የዛን ጊዜ ታዲያ መቼስ ማንም ቢሆን አስተማሪው አያውቅም ማለት ስለማይደፍር አንችኑ ደደብ ነሽ ይልሻል..ያሸማቅቅሻል፡፡

ሙሴን ያጋጠመው እንደዚህ አይነት ሁኔታ
ነው፡፡ለምሳሌ ሁለተኛ ክፍል ሆኖ አንድ ዶሮ ሲደመር ሶስት ዶሮ ስንት ይሆናል ? የሚል ጥያቄ ፈተና ላይ ቀረበለት፡፡ለዚህ ጥያቄ

አስተማሪው ከእሱ የሚጠብቀው መልስ አራት
ዶሮ የሚል ነበር፡፡እሱ ግን ‹መደመር አይቻልም> ብሎ መለሰ፡፡ ኤክስ አገኘ፡፡‹ አልተሳሳትኩም›ብሎ ክርክር አስነሳ << ..አንዱ ዶሮሴት..ሌላው ወንድ..አንዱ ጥቁር ሌላው ቀይ..አንዱ 5 ኪሎ ሚመዝን ሌላው 3 ኪሎ
ሚመዝን ሊሆን ይችላል፤ታዲያ እንዲህ በስም ካልሆነ በስተቀር በምንም የማይመሳሳሉ
የተለያዩ ነገሮች አንድ ላይ ጨፍልቆ አምስት ዶሮዎች ማለት ትልቅ ስህተት ነው ብሎ ሀሳቡን አብራራ፡፡ከእኔ በስተቀር ማንም ሀሳቡን
ሊረዳው የፈለገ ሰው አልነበረም፣አስተማሪዎቹ
ሳይቀሩ እንደጅል ነበር የቆጠሩት፡፡››

‹‹እውነትም እንክብካቤ የሚገባው ልጅ ነው››አለች ዶ/ር ሶፊያ በሙሴ ሁኔታ ውስጧ ተነክቶ፡፡ ታዲዬስም ሄለን ጋር ደወለ የሚገኙበትን ቦታ ነገረችው፤ ተቃርበዋል፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ  በጣም ቀንሳችኋል እስካሁን የተወሰነ ሰው ነው #Sebscribe ያደረገው ከዚ ፖስት በኋላ አንድ 20 ሰው እጠቦቃለው ሃሳባችን ከሞላ ጠዋት በክፍል 33 እንገናኛለን አመሰግናለው።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10412🥰1😱1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዶ/ር ሶፊያ ከታዲዬስ ጋር ላላት የቁርስ ግብዣ ቀጠሮ ለመዘጋጀት በለሊት ነው የተነሳችው፡፡ ስለእሱ እና ስለልጆቹ ስታሰላስል ስላደረች በቂ እንቅልፍ አልተኛችም፡፡ቀለል እንዲላት ሻወር ወሰደች ፡፡ ልብሷን በመለባበስ ላይ እያለች ሞባይሏ ጠራ.የማታውቀው ቁጥር ነው፡፡አነሳችው፡፡፡ <<ሄሎ>> ‹‹ሄሎ ሰላም አደርሽ?›› ‹‹እግዜያብሄር…»
#የካፊያ_ምች

ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣቺኝ ጥርቅም ዕቅፍ አርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የዕድሜ ልክ ልክፍቴን ያኔ አስለከፈቺኝ፡፡

መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የኔ ልብ በሷ የሷ በኔ ጠፋ
የስማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን ውሃ ጠማኝ ውሃ እየዘነበብን።

ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ የዘመን ሕመሜን ያን ዕለት ታመምኩኝ፡፡

አሁን አሁን ታዲያ!

ደመናው ሲጠቁር ነጐድጓድ ሲያጓራ ነፋስ ሲያስገመግም ክረምቱን ሊጣራ ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ፣ ምች ተሳልሜ፡፡

🎴ተፈሪ ዓለሙ🎴

#Share and #subscribe my #YouTube

አረ ገባ ገባ እያላቹ 500 አስገቡት
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍38🥰17👏4
#አንችን_ነበረ

አበስኩ ገበርኩ ብያለሁ
በጾም ጡትሽን አይቻለሁ.

በማማት ስወድቅ ስነሳ
ባንቺ ባየሁት አበሳ.

ልቤ ተሰብሮ ካልቀረ
መስቀልስ አንቺን ነበረ !!!

#Share and #subscribe my #YouTube

አረ ገባ ገባ እያላቹ 500 አስገቡት
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍18😁17🔥1
#ማንን_ትተኪያለሽ

ምን መሆን ትሺያለሽ
ማንን ትተኪያለሽ
ብለው ለጠየቁኝ

እነሆ ብያለሁ

እኔስ የምፈልግ ልቤ የሚመኘው ለኔ ብላ የኖረች እናቴን መሆን ነው።

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
31👍11🥰7👏3
#ልማዱ_ሁኖበት

ሰው ''እንዴት ነህ'' ብሎ ሰውን ይጠይቃል

ሰውም በምላሹ

"ደና ነኝ'' በሚል ቃል ህመም ይደብቃል ።

እንዴት ነህ.......ደህና ነኝ!!"

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍196🔥3👏3
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሁሴን ኢትዬጵያን ለቆ ከሄደ ሁለት ወራት አለፈው፡፡ትንግርት ሙሉ ለሙሉ የስራ አስኪያጅነቱን ቦታ ለመለማመድ ደፋ ቀና እያለች ስለነበር ብቸኝነቱ ብዙም አልከበዳትም፡፡ በዛ ላይ እንደ ጓደኛም እንደ እህትም የምትንከባከባት ፎዚያ ከጎኗ አለችላት፡፡ስራውም ቢሆን አልከበዳትም..፡፡

ሁሴን ትንታግ የሆኑ ጋዜጠኞችን ነው አደራጅቶላት የሄደው ፡፡እነሱን መምራት፤መምራት እንኳን አይባልም ማስተባበር ብዙም አልከበዳትም፡፡

ትንግርት ዛሬ በጥዋት ተነስታ ወደ ቢሮዋ ገብታለች፡፡ የወጪ ሰነዶች፤የተገዙ ዕቃዎች ዝርዝሮች የመሳሰሉትን የቀረቡላትን ሪፖርቶች በጠቅላላ በዝርዝር አየችና የሚፈረመውን ፈርማ የሚሰረዘውን ሰርዛ ጨረሰችና.. በሚቀጥለው ቀን እሁድ ለሚታተመው ጋዜጣ የተዘጋጁ ፅሁፎችን በየደርዛቸው ማንበብ
ጀመረች፡፡ቅር ያለት ቦታ ቆም ትልና መልሳ ታነበዋለች፤ካልተዋጠላት በማስታወሻዋ አስፍራ ወደ ሚቀጥለው ትሸጋገራለች፤ እንዲህ እንዲህ እያለች ጨርሳ ቀና ስትል ሁሉም ሰራተኞች ገብተው የአለት ስራቸውን ተያይዘውት ነበር፤ዋና አዘጋጁን ኤልያስን ጠራችው፡፡ ወደእሷ ተጠጋና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡

‹‹ምነው ጥቁርቁር አልሽ ?ሁሴን ናፈቀሽ እንዴ?››

‹‹ገና ሶስት ወር ሳይሞላው እስክጠቁር ድረስ ሚናፍቀኝ ይመስልሀል?››

‹‹ለምን አይመስለኝም፤ የሚያፈቅሩት ሰው ለአንድ ቀንም ቢሆን ከፊት ዞር ሲል ማንገብገቡ የት ይቀራል?››

‹‹ባክህ እሱ ለእንደናንተ ዓይነቱ ነው፡፡ አሁን የሀዋሳውን ልጅ እንዴት እንደምናገኘው ነው ግራ የገባኝ?ባለፈው አይደል ላይ ልጆቹ ሲወዳደሩ ያየሁት እና ትናንትና ድጋሚ በደቡብ ቴሌቨዥን አየሁት ያልኩህን ፤ሁኔታው በጣም ነው ያስደመመኝ፡፡እንዲህም የሚያስብ ሰው አለ እንዴ.?ብዬ እራሴን ደጋግሜ እንድጠይቅ ነው ያደረገኝ፡፡ፈጽሞ ከአዕምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም፡፡

‹‹እሱስ እኔም በጣም ነው ያስደመመኝ… የልጆቹ ብቃትማ አፍ ያስከፍታል፡፡››

‹‹አንድ ነገር አስቤያለሁ፡፡››

‹‹ምን አሰብሽ?››

‹‹ታሪኩን በጋዜጣችን መዘገብ፡፡››

‹‹ቴሌቭዥኑን እንደምንጭነት ተጠቅመን?››

‹‹አይደለም... ቦታው ላይ በመሄድ ልጁንም ከነልጆቹ በማግኘትና በጥልቀት በማጥናት፤ቃለ መጠየቅ በማድረግ ፤ዶክመንተሪ በመስራት፡፡››

‹‹እሱ ትክክል ነሽ.. ከፈለግሽ አድራሻውን ላገኝልሽ እችላለሁ፡፡››

‹‹በእውነት ..እንዴት?››

‹‹ኢንተርቪውን የሰራው ጋዜጠኛ የማውቀው ልጅ ነው፡፡ደውዬለት አድራሻውን እንዲሰጠኝ ቀጠሮም እንዲያሲዝልን ማድረግ እችላለሁ፡፡››

‹‹አይ ጭንቅላት ነበረ እኮ!!! ይህቺ ሀገር አልተጠቀመችብህም እንጂ፡፡››በማለት ከአንጀቷ አሞገሰችው፡፡

‹‹ያው ባልሽ እና አንቺ እየተፈራረቃችሁ ጥፍጥፍ አድርጋችሁ እየተጠቀማችሁብኝ አይደል..?››

‹‹በላ አሁንኑኑ ደውልለት፡፡››

<<አሁን??>>

<<አዎ አሁን>>

በገረሜታ ሞባይሉን ከኪሱ አወጣና ደወለለት፤ሁኔታውን በዝርዝር አስረዳው፤ከአደራ ጋር ውለታውን ጠየቀና በመሰናበት ስልኩን ዘጋ፡፡

‹‹ከተሳካ አሪፍ ምሳ ግብዣ አለህ›፡፡›አለችው፡፡

‹‹ለእኔ ሳይሆን ሀዋሳ ስትሄጂ ጓደኛዬን በመጋበዝ ለውለታው ታመሰግኚልኛለሽ፡፡››

‹‹ቃሌን ሰጥቼሀለሁ›› አለችው፡፡

ከሁለት ቀን በኃላ መልሱ መጣ‹‹ተሳክቷል››አላት ኤልያስ ተንደርድሮ ከውጭ ወደ ቢሮ እየገባ ነው የሚናገረው፡፡

‹‹አትለኝም..!!››በደስታ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡

‹‹አዎ አልኩሽ ሁሉ ነገር ዝግጁ ሆኗል፡፡››

‹‹በጣም ደስ ብሎኛል፡፡››

‹‹እኔም..እና መቼ ልትሄጂ ነው?››

‹‹አይ አብረን ነው የምንሄደው፡፡አንተ ለጋዜጣው የሚሆን ዘገባ ትሰራለህ….እኔ ደግሞ ይሄንን ሰውዬ ገፀ ባህሪ አድርጌ አንድ ምርጥ መፅሀፍ መፃፍ እፈልጋለሁ፡፡ ተዘጋጅ ነገ በጥዋት እንሄዳለን፡፡››

<<ነገ ነገውኑ>>

‹‹አዎ... የሚሰራ ስራ እጅህ ላይ ካለ ለሌሎቹ አስተላልፍ..ለሶሰት ቀን ሀዋሳ ነን፡፡››

‹‹ተቀብያለሁ ኮማንደር ››አላት ቅፅበታዊ ውሳኔዋ አስገርሞት፡፡

በማግስቱ ትንግርት መኪናዋን እያሽከረከረች ከኤልያስ ጋር ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ሀዋሳ ከተማ ደረሱ፤እንደደረሱ የኤልያስን ጓደኛ ጋዜጠኛውን አገኙት፡፡

‹‹እሺ ለመቼ ልቅጠርላችሁ?›› አላት ትንግርትን፡፡

‹‹ከተቻለ አሁኑኑ ባገኘው ደስ ይለኛል፡፡››

‹‹ከተመቸው ልደውልለት >>አለና ሞባይሉን አወጥቶ ታዲዬስ ጋር ደወለለት...

ስልኩ ሲደወል ታዲዬስ እና ዶ/ር ሶፊያ ሰሜን ሆቴል ምሳ እየበሉ ነበር..ዶ/ር ሀዋሳ ለስራ ከመጣች አንድ ሳምንት ያለፋት ቢሆናትም ታዲዬስና ልጆቹ ዙሪያ ስትሽከረከር በራሷ ፍቃድ እስከዛሬ ቆይታለች ..ዛሬ ግን የግድ መሄድ አለባት፡፡ታዲዬስን ለመጨረሻ ጊዜ ልትሰናበተው ነው በስንት ጭቅጭቅ ለዚህ የምሳ ግብዣ በማሳመን አሁን አብራው ያለችው፡፡

‹‹ማን ነው የደወለልህ?››

‹‹ከአዲስአበባ የመጡ እንግዶች ናቸው፤ቢቀላቀሉን ቅር አይልሽም ብዬ ነው እዚህ የቀጠርኳቸው› .አላት፡፡

<<ችግር የለውም..እነሱ እስኪመጡ ካወራን ይበቃናል፤ከዛ ወደማልቀርበት ሀገሬ ጉዞ እጀምራለሁ፡፡››

‹‹ጥሩ ዕቅድ ነው፡፡››አላት፡፡

‹‹በናትህ ግን፤ ቢያንስ በቀን አንዴ መደዋወል አለብን፡፡››

‹‹በቀን አንዴ!!!››

‹‹ምነው ችግር አለው?››

‹‹እንዴ በየቀኑ ተደዋውለን የምናወራው ርዕስ ከየት እናመጣለን?››

<< ደግሞ መደወል እንጂ የሚወራ ርዕስ ይጠፋል?››

‹‹አዎ..እኔ በየቀኑ እየደወልኩ ፍሬ ቢስና ተደጋጋሚ ሀሳብ እያላዘንኩ ያንቺንም የእኔንም ወርቅ ጊዜ አላባክንም..በዛ ላይ ስልኩም በሳንቲም ነው የሚሰራው፡፡››

‹‹እኔ እኮ ነኝ የምደውልልህ?››

‹‹አንቺ ደወልሽ እኔ ምን ለውጥ አለው? ለማንኛውም በሳምንት አንድ ቀን ከተደዋወልን
ወዳጅነታችንን ለማቆየት በቂ ይመሳለኛል፡፡››

‹‹እንዴ!!! በሳምንት አንድ ቀን... ጨካኝ ነህ፡፡››

‹‹ጭካኔን እዚህ ላይ ምን አመጣው?››

‹‹ትቀልዳለህ?ስሜት የለህም እንዴ? ናፍቆት የሚባል ነገር በልብህ አይበቅልም ማለት ነው?>>

‹‹ኧረ ንግግርሽን አጠጠርሽው፡፡እኔ ቀላል ነገር ነው የተናገርኩት፡፡ስልክን አግባብ ለሆነ ነገር በስርዓት መጠቀም አለብን ብዬ የማምን ሰው ነኝ፡፡ምክንያት እየፈጠርን በየሰከንዱ እዚህም እዛም እየደወልን ገንዘባችንንም ጊዜያችንንም ከማባከናችንም በላይ የምንደውልለትንም ሰውዬ ጊዜውን እናባክንበታለን፡፡ደግሞ ሰውዬው የማውራት ፍላጎት አለው ወይ?

ሚመች ቦታ ላይ ላይሆን ቢችልስ?ስራ ላይ ይሆን እንዴ?ትዝ አይለንም፡፡መጫኛ የሚያህል ውል የሌለው ፍሬከርስኪ ወሬያችንን እንተረትራለን..እንዲህ አይነት ነገር አይመቸኝም፡፡ለማንኛውም በሶስት ቀን አንዴ እንደዋወላለን፤ከዛ በላይ የተለየ ነገር ካለሽ በመልዕክት ልትልኪልኝ ትችያለሽ ..በቃ፡፡››

‹‹በየቀኑ ብደውልልህስ?››

‹‹አላነሳልሽም፡፡››

<<እንዴ.!!!>>

በዚህ ጊዜ የታዲዬስ ሞባይል ዳግመኛ ጮኸች፡፡አነሳ፡፡ እንግዶቹ ናቸው እጁን ወደላይ አንጠልጥሎ ያለበትን ቦታ ጠቆማቸው፡፡ ትንግርት፤ኤልያስ እና ጋዜጠኛው ወደእነሱ ተጓዙ፡፡ ዶክተር ሶፊያ ጀርባውን ሰጥታቸው ነው የተቀመጠችው፡፡ደረሱ

‹‹ታዲዬስ›.አለችው ትንግርት ፊት ለፊት የምታየው ፈርጣማ ወጣት በቲቪ ካየችው ምስል ጋር አልገናኝ እያላት ...በዚህ ጊዜ ዶ/ር ሶፊያ ልብን የሚሰነጥቅ አስደንጋጭ ድምፅ ነበር በጆሮዋ የገባው፡፡ በደመነፍስ አንገቷን ጠምዝዛ ዞር አለችና ‹‹ትን..ግር.ቴ.......››አለች፡፡
👍9812😁4👏1
ትንግርት ታዲዬስን ለመጨበጥ በአየር ላይ የዘረጋችው እጇን እንዳንከረፈፈች ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ ዶ/ር አዞረች፡፡በህይወቷ መቼም ፊት ለፊት አገኛታለሁ ብላ ለሰከንድ እንኳን አስባ የማታውቀውን ሰው ፊት ለፊት ስታይ አፏን ከፈተች.. ለደቂቃዎች ሁለቱም ደንዝዘው በፀጥታ ተፋጠጡ፡፡ ሶስት ወንዶች ግራ ገባቸው፡፡

በመጋባት ጠየቀ::

‹‹እጅግ በጣም እንተዋወቃለን ››ብላ ስትናገር እና ጠረጴዛ ላይ ያለውን የለስላሳ ጠርሙስ አንስታ ዶክተሯ ጭንቅላት ላይ ስትከሰክሰው አንድ ነበር፡፡በሰከንዶች ቅፅበት በአከባቢው ከፍተኛ ግርግርና ድንጋጤ ተከሰተ፡፡.ዶ/ር ሶፊያ መላ ፊቷ በደም ተሸፍኖ እራሷን ስታ ተቀምጣበት ከነበረበት ወንበር ወደ ኃላዋ ተገነደሰች፡፡

<< ምን ነካሽ አብደሻል እንዴ…?››ኤልያስ
‹‹እንዴ ምነካሽ ?እኛን እንኳን አታከብሪም?››ጋዜጠኛው አመነጫጨቃት፡፡ ታዲዬስ ዶ/ር ሶፊያን በክንዶቹ አቅፎ ግራ በመጋባት ትንፋሿን ያዳምጣል፡፡

ከ5 ደቂቃ በኃላ ታዲዬስ እና ኤልያስ ዶ/ር ሶፊያን ለህክምና ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች በአፋጣኝ ደርሰው ወንጀለኛዋን ትንግርትን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አመሩ፡፡


ይቀጥላል


ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ነው በጣም አመሰግናለው
አሁንም #Sebscribe   ያለደረጋቹ እያደረጋቹ #ትንግርት እስከሚያልቅ 500 ##Sebscriber እጠብቃለሁ በቅድምያ ለሁላችሁሜ አመሰግናለሁ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6915🤔6😱6
#የፍቅር_ቀዶ_ጥገና

በሰው ልጅ ልብ ውስጥ፣ ባ'ዳም ዘር ሰብእ ና ያ'ውሬነት ቅጥያ መቼ ይጠፋና ቀንድ፣ ጭራ፣ ክራንቻ ኩንቢና ሽሆና ልቤ ይህን አምኖ ማክዳን መሰለ ወደ ፍቅር ገብቶ ቅጥያውን ጣለ፡፡

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9👏1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ትንግርት ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ ከታሰረች ከአንድ ሰዓት በኃላ የዕለቱ ተረኛ መርማሪው ፖሊስ ዘንድ እንድትቀርብ ተደረገ፡፡

‹‹ሙሉ ስምሽን ብትነግሪኝ?››መርማሪው ብዕሩን መዝገቡ ላይ ቀስሮ ጠየቃት፤ነገረችው፡፡

‹‹በምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋልሽ ታውቂያለሽ?››

‹‹አዎ አውቃለሁ፡፡››

‹‹እስቲ የተፈጠረውን በዝርዝር አስረጂኝ?››

ዝም አለች፡፡ትንግርት ዶ/ር ሶፊያ ጋር ባላሰበችው ቦታ ባልታሰበ አጋጣሚ ስትገናኝ እራሷን የመሳት ያህል ስሜቷ ጡዞ አቅሏን ስታ ነበር፡፡ በወቅቱ ምን እንደተከሰተ ምን እንዳደረገች በትክክል አታስታውስም፡፡.

‹‹ምንም የማስታውሰው ነገር የለም?››

‹‹የሰራሽውን ወንጀልማ ማስታወስ አለብሽ ፡፡››

‹‹ምንም ወንጀል አልሰራሁም አላልኩም፤እያንዳንዱን ድርጊት አስታውሼ ግን ልዘረዝርልህ አልችልም፡፡››

‹‹ግድ የለም የምታስታውሺውን ያህል ንገሪኝ፡፡ ዶ/ር ሶፊያ በምትባል ግለሰብ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰሺባታል ፡፡ግለሰቧ አሁን በህያወት እና በሞት መካከል ትገኛላች፡፡››

‹‹እኔም እሷ ከዓመታት በፊት ባደረሰችብኝ ጥቃት ለሦስት ጨለማ ዓመታት በህይወት እና በሞት መሀከል ተንጠልጥዬ ስቃትት ነበር፡፡ ስለዚህ ብትሞት እንኳን በእኔ ላይ የፈፀመችብኝን በደል በማካካስ ስርየት
አያስገኝላትም፡፡>>

‹‹እስቲ በደለችኝ የምትያቸውን ነገሮች ንገሪኝ?››

‹‹አልችልም::››

‹‹የምርመራ ስራዬን አስቸጋሪ እያደረግሺብኝ ነው፡፡››

‹‹ይገባኛል ...ግን አሁን ምንም ልነግርህ አልችልም ፤ጊዜ እፈልጋለሁ፡፡››

መርማሪው ፖሊስ ለተወሰነ ደቂቃዎች በዝምታ አሰላሰለና ‹‹እንግዲህ የተጠቂዋ ሁኔታ እስኪለይለት ማረፊያ ቤት ትቆያለሽ ፡፡ ዛሬ ቅዳሜ ነው ሰኞ ፍርድ ቤት እንድትቀርቢ እናደርጋለን፡፡ፍርድ ቤቱ ምን አልባት ዋስ ሊፈቅድልሽ ይችላል፡፡››በማለት ወደ ማረፊያ ቤቱ እንድትመለስ አደረገ፡፡

ኤልያስ የዶክተር ሶፊያን የህክምና ሁኔታ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ትንግርትን ሊያያት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ፡፡ፖሊሶቹን አስፈቅዶ ወደ እሷ ተጠጋ፤ከአጥሩ ወደዚያና ወደዚህ ሆነው መስኰት በመሰለች ክፍተት መነጋገር ጀመሩ፡፡

‹‹ሀይ ትንግርት ...እንዴት ነሽ?››

‹‹ሠላም ነኝ፡፡››

‹‹ፖሊሶቹ አናገሩሽ?››

‹‹አዎ ..…ማናገር አናግረውኛል፤አልተጋባባንም እንጂ፡፡››

‹‹አይዞሽ ..አንድ መቶ ሃለቃ ወዳጅ አለኝ፤ሁኔታውን ለእሱ አስረድቼዋለሁ፡፡ እንዲያናግራቸው አድርገን በዋስ ምትወጪበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡››

‹‹አይዞህ አትጨነቅ ምንም አልሆንም፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ... ምንድነው የተፈጠረው? ከልጅቷስ ጋር የት ነው ምትተዋወቁት?››

‹‹ኤልያስ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ማውራት አልፈልግምም…አልችልምም፡፡››

‹‹ተይ እነጂ ትንግርት፤ችግር ውስጥ እኮ ገብተሻል፤ ሁኔታውን ካላወቅን እንዴት ልንረዳሽ እንችላለን?››

‹‹ምንም ዓይነት እርዳታ አልፈልግም፡፡ እሷ ሞታ እኔ እዚሁ እስር ቤት ለዘላለም ብበሰብስ እንኳን ደስተኛ ነኝ፡፡››አለችው እየተንዘረዘረች፡፡

‹‹ያን ያህል?››

‹‹ከዚያም በላይ፡፡አሁን ከዚህ በዋስ ብታስፈተኝ እንኳን ቀጥታ ወዳለችበት ሆስፒታል ሄጄ እስትንፋሷን እስከመጨረሻው ማቋረጥ ነው ምፈልገው፤አዎ እንደዛ ነው የማደርገው፡፡››

‹‹ኤልያስ ግራ ገባው ፡፡ትንግርትን በእንዲህ ዓይነት የቂመኝነትና የክፋት ባህሪ ውስጥ ወድቃ አጋጥሞት አያውቅም፡፡እሷን በአዛኝነቷ፤በትእግስተኝነቷ፤ ለሰው ባላት ሀሳቢነት : የሰውን ልጅ ቀርቶ እቤቷ የገባች አይጥ በወጥመድ ተይዛ ብታገኛት በሀዘኔታ ከወጥመዱ አላቃ ከነ ህይወቷ ወደ ጐሬዋ እንድትመለስ የምትፈቅድላት ሰው እንደሆነች ነው የሚያውቀው፡፡ታዲያ እንዴት እንዲህ ልትቀየር ቻለች? ፡፡የዚህን ዓይነት የገዘፈ አውሬነት እንዴት በውስጧ ተሸሽጐ ሊኖር ቻለ? ያቺ ልጅስ ምን ያህል ብትበድላት ነው ይሄን ያህል ልታስቆጣት የቻለችው?››

‹‹እሺ ፎዚያን ምን ልበላት ...በስልክ እያጨናነቀቺኝ ነው?..

‹‹እንዴ!!! ነገርካት እንዴ?››

‹‹አዎ ነግሬያታለሁ... ስታጨናንቀኝ ምን ላድርግ?››

‹‹ሰላም ነች በላት፡፡››

‹‹እሱማ ብያታለሁ..ግን ካልመጣሁ እያለቺኝ ነው፡፡››

‹‹በቃ ከመጣች ከእኔ መኝታ ቤት ካለው ኮመዲኖ ታችኛው መሳቢያ ውስጥ ሁለት ጥቁር ልባስ ያላቸው ዲያሪዎች አሉ..እነሱን ይዛልኝ ትምጣ፡፡››

‹‹እሺ ነግራታለሁ፡፡››አላት፡፡

ብዙ ማውራት ቢፈልጉም ተረኛ ፖሊስቹ ከዛ በላይ ሊፈቅዱላቸው ስላልቻሉ እሷ ወደ ማረፊያዋ እሱ ደግሞ አንዳንድ ነገሮችን ለመመካከር መቶ ሃለቃ ጓደኛው ወዳለበት ቦጋ አመራ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ 5 ሰው #subscribe ካደረገ ቀጣዩ ክፍል ማታ 3 ሰአት ላይ ይለቀቃል

#Share and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8721👏4👎3🥰2
ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?

የኔ ውብ ከተማ -

ሕንጻ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፤

የኔ ውብ ከተማ -

መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፣

የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው

ሕንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢፀዳ ቤቱ

የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ?

🎴በዓሉ ግርማ🎴
👍3614👏2