አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
517 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ስለ_አድዋ_አጭር_ማስታወሻ

ነገ አድዋ ነው የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የልደት ቀን፡፡ አድዋን ሳስብ ብዙ ነገሮችን አስባለሁ የተራራ ጫፎች እንደ ጦር ተስለው ይታዩኛል፡፡ ድራጎንን ገድሎ ብሩታይትን ከፍርሃት ነፃ ያወጣው ሰይፍ ነጸብራቅ #ምኒልክ መዳፍ ውስጥ ይታየኛል፡፡

አድዋ የነፃነት ቀን እንደሆነ አልጠራጠርም ነጭ ቡጢ በጥቁር መዳፍ የከሸፈበት፣ ብርቱ የንቀት ቋጥኝ የተደረመሰበት፣ አንገት በሃፍረት ከመዘለስ የዳነበት ቦታ እንደሆነ አልዘነጋም፡፡ አድዋ እኮ ግዑዝ ተራራ አይደለም ገበየሁን ያህል የጦር ሳተና ውጦ ጭጭ ያለ ጨለማ፣የእምየን ትዕግስት ተፈታተነ፣ የባራቴሪን ትዕቢት ትቢያ ያደረገ የነጭን ሴራ የበታተነ ሞገድ ነው፡፡ አድዋ የተራራ ሰንሰለት ብቻ አይደለም #የጣይቱን የሴትነት ብልሃት ያንጸባረቀ መስተዋት፣ የባልቻን ያህን ድፍረት ያሰናዳ ፣ የአባ መላን ብልሃት የሸረበ፣ለወገን ሃይል ወኔን ያቀበለ፣የባሻ አውአሎም ምስጢረኛ፣ ጀግኖችን በደም አጥምቆ የሀገር ፍቅር ማተብን ያሳሰረ መንፈስ ነው አድዋ፡፡ አድዋ ለኢትዮጵያውያን በዓል ብቻ አይደለም.. .ሳንባን በኩራት ወጥሮ ደረት የሚያስነፋ አየር፣ አንገትን ከመዘለስ ታድጎ ቀና የሚያደርግ ምርኩዝም ጭምር ነው፡፡

አድዋ የሰላም ወዳድ ትውልድና ህዝብ ቋሚ ምስክር አርማ ነው ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ የጣይቱ ንግግር መጥቀስ በቂ ነው

“እኔ ሴት ነኝ፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡" ተጨማሪ ካስፈለገ አያልቅም

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፤ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ሀበሻ" የሚለው ስነ ቃላዊ ግጥም ውስጥ የምንይልክን ብሎም የኢትዮጵያውያንን ሰላም ወዳድነት ማሳያ ነው በግጥሙ ውስጥ በግልጽ እንደተመለከተው #ምኒልክ ባያነሳ ጦር አይደለም የተባለው . . .ጋሻ ነው፡፡ ጋሻ ደግሞ ራስን ለመከላከል እንጂ ጠላትን ለማጥቃት የሚውል መገልገያ አይደለም፡ እናም ሀበሻ በአዘቦት "የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል. ." እንደሚለው ምኒልክ ክተት አውጆ ጋሻውን አነሳ፣ ሀገሬው አልገዛም ባይ፣ አሻፈረኝ ባይ፤ በየጎራው ላይ" እያለ ባለትዳሩ ምሽቱንና ልጁን፣ ያላገባው ኮረዳና አጎጠጎቴውን (የከንፈር ወዳጁን) ተሰናብቶ ተከትሎት አድዋ ላይ ተገናኙ እናም አድዋ ከገፊዎች ሳይሆን ከተገፉት ጎራ ቆመ ግዑዝ መልክዓ ምድር ብቻ አይደለም፤ የሀበሻ የልብ ወዳጅም ጭምር ነው፡፡ .ስለዚህም አድዋ"
፨፨
የአድዋን በዓል ስናነሳ በቅድሚያ ከሚጠቀሱት ቋሚ ቅርሶች አንዱ የአፄ ምኒልክ ሐውልት ነው፡፡ ሐውልቱን ያሠሩት ንግሥት ዘውዲቱ ሲሆኑ የቆመው የአባታቸው የአፄ ምኒልክ ማስታወሻ እንዲሆን ታስቦ ነው፡፡

የሐውልቱን ንድፍ ያወጣው ጀርመናዊ አርክቴክት ሀርቴል ስፔንግለር ነበር፡፡ ሐውልቱም የተቀረፀው ጀርመን ሀገር ሲሆን የተሰራውም ከነሐስ ነው፡፡ ሐውልቱ ከጀርመን ሃገር ተሠርቶ ከመጣ ወዲህ የሚቆምበት ቦታ በዝግጅት ላይ እያለ ንግሥት ዘውደቱ በድንገት መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡ ነገር ግን የተጀመረውን ሥራ የንግሥቲቱን አልጋ የወረሱት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንዲጠናቀቅ በማድረግ በንግሥናቸው በዓል ዋዜማ ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም. በታላቅ ክብር በንጉሠ ነገሥቱ ተገለጠ፡፡

ከሐውልቱም ግርጌ ዘመን የማይሽረው ጥቅስ የተቀረፀ ሲሆን እንዲህም ይነበባል፡-

‹‹ከትልቅ ወይም ከትንሽ ቢሆን መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው፡፡››

ሃውልቱ በዳግም ፋሽስታዊ ወረራ ወቅት በማርሻል ግራዚያኒ ወርዶ ተቀብሮ የነበረ ቢሆንም ከነፃነት በኋላም ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ

እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ቀድሞ በነበረበት ቦታ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም. እንዲቆም ተደርጓል፡፡

እምየ ምኒልክ ከአድዋው ድል በኋላ ብዙ መሰረተ ልማት በመዘርጋትና ስልጣኔን በማስገባት የሰላም ጊዜ ጀብደኝነታቸውን አስመስክረዋል፡ከነዚህ አንዱ ለሆነው የባቡር ፕሮጀክት ህዝቡ አንድ አንድ ጠገራ ብር ለማዋጣት ማቅማማቱን ሲሰሙ ታህሣሥ 29 ቀን 1900 ለመምህር አካለ ወልድ በፃፉት ደብዳቤ ላይ ይህን ብለው ነበር "ስለምድር ባቡር ሥራ ገንዘብ አውጡ ባልነው ሰው አለቀሰ ብለው የላኩብኝ ደብዳቤ ደረሰኝ… ይህስ ከእንቅልፌ ለምን ቀሰቀሳችሁኝ እንደማለት ያለ ነው እንጂ በጭራሽ አንዳንድ ብር አውጡ ቢባል የሚጎዳ ሆኖ አይደለም።" እኔም እላለሁ ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅስ መሪ ይብዛልን . . . ለመንቃት ግን አናመንታ፡፡

የአድዋ ዝክሬን የማጠቃልለው አፄ ምኒልክ ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን በጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ ሲሆን እንዲህ ይነበባል

"የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት። በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ። አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፣ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ'' አኔም ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ፡፡

🔸ዋግሹም ካሳ🔸


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍346😁2