አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...«እየው» አሉት ወደ ጆሮው ጠጋ በማለት «እሙዬን ራሴን አሞኛልና
መድሃኒት ግዢልኝ ብዬ ወደ ከተማ ልልካት ነው። እሷ ከሄደች በኋላ የምነግርህ ነገር አለኝ። በል ቶሎ ተኛ፡፡» አሉት እያዋከቡት።

“ምንድነው እሱ?» አላቸው አስራት ዓይኑን ዓይናቸው ላይ ትክል አደርጎ።
«ብኋላ እነግርህ የለ! አሁን ተኛ፣» አሉትና ወደ ጓዳ ገባ ብለው ጋቢ
አምጥተወ ሰጡት፡፡ በል ቶሎ በል!ካሉ በኋላ አሁንም ወደ ጆሮው ጠጋ ብለው «እሙዬ ምን ሆንክ ታለችህ ድንገት ቁርጠት ተነሳብኝ ብለህ ቅልስልስ እያልክ ንገራት።
አሉት ጣደፍ ጣደፍ እያሉ።
አስራት ግራ እየገባው ጋቢውን ለብሶ ቁጭ ብሎበት በነበረ መደብ ላይ ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡ በጆሮው ግን የእናቱን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ያዳምጣል፡፡
የሔዋን እናት የአስራትን አተኛኘት ካረጋገጡ በኋሳ ወደ ጓሮ ዞሩ። ልክ እንደ ታመሙ" ሁሉ ሰውነታቸውን ድክምም፤ ዓይናቸውን ቅዝዝ፣ ፊታቸውንም
ጭምድድ አድርገው ከሔዋን አጠገብ ደረሱና በቀስታ እየተቀመጡ «እንዴት ይሻለኛል
እሙዬ ስላልተቀሳቀስኩበት ነው መሰለኝ ይኸ ራሴ ተነሳና ይፈልጠኝ ጀመር ያንን ኪኒንና የምትሉትን ነገር ግዛልኝ ልለው ወደ ቤት ብገባ አስራቴ ደሞ ሆዴን አመመኝ ብሎ ተኝቶ አገኘሁት።
አሉና ኧረ እዲያ» በማለት ብስጭትና ምሬታቸውን ለመግለፅ ሞከሩ።

«አመመሽ እማ?» አለቻቸው ሔዋን ሁኔታቸውን ሰለል እያደረገች፡፡ብታይ ጦሩን ይዞ ሽቀሽቀኝ፡፡ አሏት ራሳቸውን በሁለት እጃቸው ይዘው
ወደ መሬት በማጎንበስ።
«ምን ዓይነት ኪኒን ይሆን?»
«ይኽ እምብሮ ነው ምንትስ የምትሉት!
«አስፕሪን ይሆናል::»
«ይሆናላ! እኔ አላቀው፡፡ እንዳንዴ ሲያመኝ ይኸው አስራቴ ነበር
የሚገዛልኝ። እንግዲህ አባታችሁ እስከሚመጣ ልጠብቅና የሚያውቀው ተሆነ ይገዛልኛላ::"» አሏት በግማሽ ልባቸው ወደ ሔዋን ወረቀቶች ዓየት እያረጉ፡፡
«እኔ እገዛልሻለሁ እማ!» አለቻቸው ሔዋን።
«አዬ...ልጄ! መንገዱ ይርቅሻል። የኛ ሰፈር ደሞ ገጠር አይሉት ከተማ አጉል ነው።ከሱቅ እስቲደርሱ ድረስ ያለው መንገድ መች ቀላል ነውና።ክ
«ግድየለም እማ! መግዣውን ስጪኝ፡፡» አለቻቸው።
«ተበረታሽ ደግ የኔ ልጅ!» ብለው ከተቀመጡበት ተነሱና ነይ ቤት
እሰጥሻለሁ፡፡» እያሉ ወደ ቤት አመሩ፡፡ አስራት ጥቅልል ብሎ እንደተኛ ነው፡፡
የእናቱንና የሔዋንን ወደ ቤት መግባት እውቆ የሚደረገውን ለመከታተል ጆሮውን አቁሞ ሳለ ሔዋን ተናገረችው።
«አመመህ እንዴ አስራት!»
«አረ ቁርጠት ሊገለኝ ነው፡፡» አላት ገልበጥበጥ እያለ።
የሔዋን እናት ፈጥነው ወደ ጓዳ ገብተዋል። «ቆይ ተኔ መድሃኒት
እንሰጥሀለን፡፡ እስከዚያው ቻለው፡፡» እያሉ ይዘው የመጡትን ገንዘብ ለሔዋን ሰጧት፡፡ ተቀብላቸው ከቤት ስትወጣ እስከ ውጭ ድረስ ሸኟት፡፡
ጥቂት ርምጃዎች እስክትራመድ ድረስ በዓይናቸው ሲከታተሏት ከቆዩ በኋላ ፊታቸውን ወደ ግቢው በር ምልስ አድርገው እስከ ቁርጭምጭሚታቸው ይደርስ
የነበረ የአበሻ ቀሚሳቸውን እስከ ጉልበታቸው ድረስ ሰቀሰቁና ወደ ቤት ሳይገቡ ወደ ጓሮ
በሚወሰደው መተላለፊያ መንገድ ሮጡ። ከቦታው ሲደርሱ የሔዋንን የወረቀት አቀማመጥ ልብ ብለው ተመለከቱ፣ወረቀቷን ሲመልሱ
አቀማመጡ እንዳይጠፋባቸው ተጠነቀቁ። ከዚያም የጻፈችባትን ወረቀት ከማስደገፊያዋ ደብተር
ውስጥ ቀስ ብለው መዝዘው አወጧትና አሁንም በሩጫ ወደ ቤት ገሰገሱ።
“እስቲ ተነስ እስራቴ! አሉት ቶሎ ቶሎ እየተነፈሱ።
አስራት ከተሸፈነበት ገለጥ ብሎ ከፊትለፊቱ የቆሙ እናቱንና በእጃቸው የያዝዋትን ወረቀት እየተመለከተ «ምንድነው?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
«ቶሎ ተነስ! እሙዬ የጣፈችው ወረቀት ነው፡፡ ሳትመጣብን አንብበውና ከአስተቀመጠችበት ቦታ ልመልስ አሉት በተቻኮለ አነጋገር፡፡
አስራት ከተኛበት ቀና ብሎ ወሪቃቱን ተቀበለና አየት ሲያዩርግ ግጥም ደረድርበታለች፡፡ ከግጥሙ ዳርና ዳር ደግሞ የተለያዩ ቃላት ተሞነጫጭረውበታል።
አስቹ ሆዴ፣ የኔ ምስኪን.. ወዘተ የሚሉ፡፡ ወደ ዋናው ግጥም ከመግባቱ በፊት እነዚህን ቃላት አየት አየት ሲያደርግ ለካ ለሔዋን እናት ዘግይቶባቸው ኖሯል፡፡

“አንብበው እንጂ! አቃተህ እንዴ?» ሲሉ ጮሁበት፡፡ አስራት ግጥሞቹን ማንበብ ጀመረ።
እናቱም፣ ጀሮአቸውን አቁመው ያዳምጡ ጀመር።

«የኔ ሆድ አስቻለው አንተ የኔ ከርታታ!
ላመንከው ለመሞት የማታመነታ።
እመጣለሁ ብለህ ሄደህ እንደዋዛ፣
አንተም በዘያው ቀረህ የኔም አሳር በዛ፡፡
በእርግጥ ባትኖር እንጂ ፍጹም በሕይወት፣
አይጨክንም ነበር አስቹ የአንተ አንጀት።

የበላክን አውሬ ምነው ባገኘሁት፣
በውስጡ ባገኝክ እኔም በበላሁት።
ደምህን ከደሜ አጥንቴን ከአጥንትህ፤
አገናኝህ ነበር ነፍስ እንዲዘራብህ፡፡

የሳምከው ከንፈሬ ደርቋል እንደ ኩበት፤
እህል ውሃ ጠልቶ አንተ የሌለህበት፡፡

እንደው ሂጂ ሂጂ ብረሪ ይለኛል፣
እልም ያለው ገደል ባህሩ ይታየኛል።
ዛሬ ነገ አልኩ እንጂ ልቤ እየዋለለ፣
ስሜቴስ ይጮሀል በርቺ በርቺ እያለ።
ይጎነትለኛል የናፍቆት ሰቀቀን፣
አንተን ካላገኘሁ አይቀርም አንድ ቀን።»
«ኧ! ኧ! እስቲ እስቲ ድገመው!» አሉ የሔዋን እናት አሁንም ጆሮአቸውን ወደ አስራት ጣል አድርገው:: ዓይናቸው ፍጥጥ ማለት ጀምሯል፡፡
አስራት ቀስ ረጋ ብሎ ደግሞ አነበበላቸው: አንብቦ ከጨረሰም በኋላ እናቱ የሚሆኑትን ለማየት ቀና ብሎ በስጋት ዓይን ያያቸው ጀመር።
የሔዋን እናት ድንገት ጥርሳቸውን ግጥጥ፣ ፊታቸውን ክፍት አደረጉና
እንባቸውን እያዘሩ "እክክክክ..እክክክክ...እክክክክ" አሉ አንዳች የሀዘንና የስጋት
ስሜት ውስጣቸው ገብቶ በረብራቸውና፡፡ቀጠሉ አሁንም እጆቻቸውን በነጠላ ላይ ሸፍነው በወገባቸው ላይ በማሳረፍ ቀሚሳቸው በአየር ተንሳፎ
እስኪገለብ ድረስ በቆሙበት ላይ ወደ ግራ ቀኝ እየተወዛዙ «አንቲ» አሉ የጥሪ ያህል በረዘመ ድምፅ።
ሟቿን የአስቻለውን እናት መጥራታቸው ነው።«የጠጡት ጥዋ የለም? የካደሟት አድባር የለችም? የሳሙት ቤተክሲያን የለም፣? አረ አንድ በሉኝ! ኧረ በውቃቢዎ! ድረሱልኝ! ኧረ ልጆዎ ልጄን በላብኝ! ኧረ ልጄን አስመነነብኝ! ኧረ ምን አባቴን ልሁነው! እያሉ ዓይንና አፍንጫቸውን በነጠላቸው
እየጠራረጉ ልክ ሞታ ቀብረዋት ሀዘናቸው ገና እንዳልወጣላቸው አይነት ወያኔ ልጄን ወይኔ ልጄን እመዬ ምን ላርግሽ? እንደው ምን ልሁንልሽ? ልጄ! ልጄ! ልጄ! አሉ በተከታታይ።
“ምነው እማዬ! ምን ሆንሽ?» አላቸው አስራት ደንግጦ ።
በቃ እኮ እንግዲህ እኔም ልጄ በህይወት አለች ብዬ ተስፋ አላደርግም አንተም እህት አለችኝ ብለህ አታስብ! ልጂ ማምለጧ ነው። እሙዩ ተእንግዲህ ሰው አልሆነችም በቃ በቃ! በቃ በቃ! እህህህ።
«አረ ምንም አትሆን እማ»
«ኧረ ወዲያ አስራቴ በቃ ቁርጡን ነገረችን እኮ! በቃ ተናዘዘች እኮ!
«እሙዬ ገደል መግባቷ ነው እኮ! እ፤ህህህህህህ…"
«እንጠብቃታለና»
«አየየ... ጥበቃ! አየየ... ጥበቃ ዋልኝ! የሷ ነገር ተእንግዲህ ከበቃ
እኔም አብሬ ወደ ገደል ነው! እኔም ከእሷ ጋር ወደ ባህር ነው እህህህህህ» አስራት
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....ሸዋዬ በህዳር ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ ቆማ የመጀመርያው መንፈቅ ትምህርት አልቆ ለአጭር ጊዜ እረፍት ትምህርት ቤት የሚዘጋበትን የጥር ወር መጨረሻ በናፍቆት ትጠባበቃለች። ከብረ መንግስት የምትደርስበት ቀን ሳይቀር ተወስኗል።እቅዷ ከሔዋን
ወይም ከወላጆቿ ተቃውሞ ቢገጥመው ማሳመኛ ይሆናል የምታስበውን እያዘጋጀች ነው። ዘዴና ብልሀት በልቧ ይውጠነጠናል።

ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል እንዲሉ ወንድሟ አስራት ተስፋዬ ባላሰበችው ቀንና ሰአት ከቤቷ ከች ብሎ ያደረሳት ብሥራት ግን ሰጋትና ፍርሃቷን ሁሉ ከልቧ ውስጥ እንደ እድፍ አጠበው። ሔዋን የልብ ህመምተኛ ሆናለች በሰው ላይ ክፉ ደግ አለና መተሽ እያት ከማለት ውጭ ስለ ሔዋን ሁኔታ ምንም አይነት ፍንጭ ለሸዋዬ እንዳይሰጥ በተለይ በእናቱ አደራ የተባለው አስራት የልጅ ነገር ሆኖበት አንዳንድ ነገሮችን ማፈንዳቱ አልቀረም ሔዋን ዛፍ ስር ተቀምጣ መዋል ማዘውተሯን በሀሳብ እየተዋጠች ቤተሰቧን ማሳሰቧንና በተለይ በህመሟ ምክንያት አገር ብትቀይር የተሻለ መሆኑ መታመኑን ሁሉ አልደበቃትም።

የሔዋን አገር መቀየር አስፈላጊነት የታመነበት ስለመሆኑ መስማቷ ሸዋዬን ከምንም ነገር በላይ አስፈነጠዛት። ሔዋን አገር መቀየር ካለባት ቀላሉ ከክብረ መንግስት ወደ ዲላ ነው ይህ ደግሞ በቤተሰቦቿ ዘንድ ተፈጥሮ ይሆናል ብላ ከምታስበው ቅሬታ ነፃ የምትሆንበት አጋጣሚን ይፈጥራልና ወቅትና ጊዜ ያለ ሽማግሌ ሲያስታርቃት በመቅረቡ አምላኳን አመሰገነች፡፡ ወደ ክብረ መንግስት ልትሄድ በልቧ ይዛው የነበረውን የጊዜ ቀጠሮ አሳጠረችው፡፡ ወንድሟ አስራት
ከቤቷ በደረሰ በአራተኛው ቀን እንዲሆን አደረገችው:: በመሀል ያሉት ሁለት ቀኖችም የዝግጅት ጊዜ ሆነ::
ብሥራቱን ያካፈለቻችው በድሉና ማንደፍሮ በእነዚህ ሁለት ቀናት
አልተለዮትም፡፡ ወደ ክበር መንግስት አካሄዷን ሊያሳምሩ ሽርጉድ አሉ። አብረዋት
እየዋሉ አብረዋት አመሹ። በየገበያው ቦታ አብረዋት ዞሩ። አዘጋጇት፤ አዘገጃጇት ጠዋት ወደ ክበረ መንግስት ልትሄድ ሻንጣዋ የያዘውን ይዞ ማታውኑ ተቆለፈ
የማግስቷ ጀምበር ክብረ መንግስት የምታደርስ የልቧ መብራት ሆነች::

ልክ በዚያ ዕለት ምሽት ላይ ክብረ መንግስት ሌላ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው። የሄዋን አባትና እናት ሔዋን ወደ ዲላ መሄድ ያለ መሄድ ፍላጎቷን ለመጠየቅ ሊያነጋግሯት በተመካከሩበት መሠረት ውይይቱ ተጀመረ፡፡
«እሙዬ !» ሲሉ ጠሯት ለስለስ ባለ አነጋገር።
«አቤት እማ» አለቻቸው ሔዋን ከአጠገባቸው መደብ ላይ ገደም ብላ ሳለች። አባቷ ደግሞ ከባላቤታቸው ፊት ለፊት ምድጃኑ እጠገብ ተቀምጠው እሳት ይሞቃሉ።
«እንደው ይቺ ልብሽ ያስቸገረችሽ ይኸን አገር ጠልታብሽ ይሆን? እማስበው ባጣ ይህን ነገር በእሊናዬ አውጠነጥነው ጀመር ልጄ? አሏት ጉልበታቸውን በሁለት
እጆቻቸው ደገፍ በማድረግ ዓይን ዓይኗን እየተመለከቱ፡፡
«አዩ! እማ ቢቸግርሽ!»
«ቸገረኝ ልጄ! በጣም ችግረኝ፡፡»
«የት ልሂድ ታዲያ እማ»
«እውነትሽ ነው:: መሄጃማ ይቸግራል የኔ ልጅ፡፡» ካሉ በኋላ የሔዋን እናት ወደ አቶ ተስፋዩ ዞር በማለት «እንደው ወደ ዲላ ትሂድ ይሆን አቶ ተስፋዬ» ሲሉ ጠየቋቸው።
«ተሆነማ ወደዚያው ነው ኋላማ መይት ትሄደዋለች? ከዚያ ሌላ አገር አታውቅ አሉ አቶ ተስፋዬ አንገታቸውን ወደ እሳቱ ደፋ አድርገው፡፡
«ከማን ጋር ልኖር?»ስትል ሔዋን ጠየቀቻቸው፡፡
«በኔ ልብማ ከነዚያ ከነታፈሡ ጋር ትንሽ ተጨዋውተሽ ትመለሽ እንደሆን ብዬ ነዋ!»አሉ እናቷ ለስለስ ባለ አነጋገር።
«እህቷስ አለች አይደል! »አሉ አቶ ተስፋዬ ወደ እሳቱ እንዳቀረቀሩ።
«እንደገና ከእታ አበባ ጋር?» አለች ሔዋን ደንገጥ ብላ።
«እሷን ለሰበብ ተዚያ በኋላ ደግሞ ከእነዚያ ልጆች ጋር አንዳንድ ጊዜ
መጫወቱ ትንሽ ያፍታታሽና ልብሽም እየተወችሽ ትሄድ እንደሆነ ብዬ እኮ ነው፡፡»
አሉ እናቷ የሔዋንን ቁጣ ለመመለስ ረጋ ብለው።
«ተይ እማ! እንዲህማ አይሆንም::»
«ቀለብሽን ተሆነ እኔ እችላለሁ ሔዋኔ ከቶ የአንቺ ጤና ይመለስ እንጂ፣ደሞ ላንቺ ያልሆነ አዱኒያ ምን ሊያደርግልኝ! ላም ተሆነች ላም! በሬ ተሆነም በሬ ይሸጣል :: አይዞሽ!» አሉ የሔዋን አባት በቆራጥነት።
«እናንተ የማታወቁት ልላም ችግር አለ:: አለች ሔዋን፡፡
«ብትነግሪን አይፈታም?» አሏት እናቷ፡፡ ግን ትዝ ያላቸው ነገር አለ፤ ያኔ ታፈሡ በማትፈልገው ሰው ልታስደፍራት ያለቻቸው ነገር። ፈታ ብላ ብታወባና ሁኔታውን በግልጽ ቢረዱት ፈለጉ፡፡
«እኔና እት-አባበ አብረን መኖር አንችልም፡፡» አለች ሔዋን ነገሩን ደፈንፈን አድርጋ።
«ኧረ ተይ ሔዋኔ፣ በእትማማቾች መካከል ቂም ተያይዞ አይኖርም!» አሉ አባቷ አሻግረው መልከት እያሏት፡፡
«ከበድኳችሁ እንዴ አባዬ?»
«ለአንቺ ብለን ነው እንጂ እሙዬ ደሞ አንቺ ምን ትከብጅናለሽ የኔ ልጅ?»
አሏት እናቷ በማሳዘን ዓይነት አነጋገር፡፡
«እንግዲያው እዚሁ ብሆን ይሻለኛል፡፡» አለችና ሔዋን በረጅሙ ተነፈስች።

የሔዎን እናትና አባት ግራ ተጋቡ። ልጃቸው ወደ ዲላ ለመሄድ ፈቃደኛ አለመሆኗ ገባቸው። ከዚያ በኋላ ምንም ሳይነጋገሩ ጊዜው መሸ፡፡ እንደ ተዳፈጡ ተኙ፡፡ ሌሊቱ በሀሳብ ነግቶ ቀኑም በትካዜ አለቀ።

የደስታ ፈረስ ጋልባ ሶምሶማ ስትጋልብ የዋለችው ሸዋዬ ከቤተሰቦቿ ቤት የደረሰችው ከአመሻሹ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ በዚያ ሠዓት አባቷ
ከብቶቻቸውን ይዘው ከመስክ እየተመለሱ ነው። እናቷ ደግሞ ምናልባት ሔዋን ሸዋዬ ስትመጣ ሀሳቧን የቀየረች እንደሆነ ብለው ለወደፊቱ ግንኙነት እንዲያመች
የዘመድ ስልክ ቁጥር ሊያመጡ ወደ ከተማ ሄደው እየተመለሱ ገና በመንገድ ላይ ናቸው:: ሽዋዬና አባቷ በር ላይ ተገናኝተው በመሳሳም ናፍቆታቸውን አውጥተው እየተነጋገሩ ወደ ቤት ሲገቡ ሔዋን በጎሮ በር በኩል ወደ ቤት ስትገባ ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ።

"እማሃይዬ! አለች ሔዋን ሸዋዬን ስታይ ደንግጣ። የትናንት ማታው ወሬ መሰረቱ ምን እንደነበር ልቧ ጠረጠረ።
«እህትሽ መጣች ሔዋኔ!» አሉ አባቷ ቀድመው::
«ጠፋሁባት ይሆን?» በማለት ሽዋዬም ሳቅ እያለች ወደ ቤት ገባችና በሔዋን ላይ ጥምጥም ብላ ሳመቻት::
«አንቺ! አለቻት አጠገቧ ቆማ ከእግር እስከ ራሷ እየተመለከተቻት፡፡
«አቤት» አለች ሔዋን ወደ መሬት እንዳቀረቀረች::
«በቃ አንዲህ ሆነሽ ቀረሽ?»
ሔዋን ሽዋዩ ምን እያለች እንደሆነ አልገባትም፡፡ ጠቁራባት ይሁን
ከስታባት ብቻ ያየችባትን አካላዊ ለውጥ ገና ትነግራት እንደሆነ እንጂ ለጊዜው አለየላትም።
ሸዋዬ እንደ መናደድ ዓይነት እጆቿን ጨብ ጨብ ጨብ እያረገች ዋይ-ዋይ-ዋይ-ዋይ…አለች ደጋግማ:: በአባታቸው ግብዣ
ሁሉም በመደብ ላይ ተቀመጡ።

«ሔዋኔ ክብረ መንግስት እንዳላደገችበት ሁሉ ዛሬ ዛሬ አልስማማት ብሏል የሸዋ!» አሉ የሔዋን አባት የሸዋዬ ቁጭት መነሻው የሔዋን መጎሳቆል መስሏቸው።
«ለመሆኑ ያምሻል?» ስትል ሸዋዬ ሔዋንን ጠየቀቻት፡፡
«እል አልፎ ልቢን ያመኛል::
👍51
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...አስራ ስድስት ወራትን በክብረ መንግስት አሳልፋ ወዴ ዲላ የተመስሰችው ሔዋን ብዙ አካባቢያዊ ለውጥ ሊገጥማት እንደሚችል ገምታ ነበር፡፡ነገር ግን ከሽዋዬ ቤት በዘመናዊ የቤት እቃዎች መሞላትና ወንድ ወንድ ከመሽተት በቀር ሁሉም ነገር ያው ነው።በሸዋዬ ቤት የወንድ ኮትና ጃኬት ግድግዳ ላይ ተሰቅለው የወንድ ጫማ በአልጋ ሥር ተቀምጦና ትልቅ የወንድ ፎቶ ግራፍ ብፌ ላይ ስታይ ሸዋዬ ባል ያገባች መስሎ ተሰማት። በእርግጥም “ማንዴፍሮን ገና የገባች እለት ተዋወቀችው።
ማንደፍሮ መልኩ ጥቁር ፊቱ ጉሩድረድ ያለና አካሉ ግዙፍ
ከመሆኑ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጨብጣት የእጁ አከባበድ የሚያስፈራ ሆኖባት ቢሆንም እያደር ስትግባባው ግን ባህሪው ቀላል የሆነ ሰው ነው። ይስቃል
ይጫወታል። ቀልዶቹ ይጥማሉ፡፡ እየሰነበተች ስታየው እንዲያውም በእሱ መኖር ቤቱ ድምቅ ሲል መንፈሷም ዘና እያለ መጣ፡፡ «የኔ ፍልቅልቅ» በማለት እያጫወተም ይበልጥ ያፍለቀልቃት ጀመር።
ዲላ እንደገባች በአፍንጫዋ የገባው አየር በአስቻለው የሰቀቀን ትዝታ የተለወሰው ነበር፡፡ ሆዷን ባር ባር እያለው እንባዋም ያለ ገደብ ፈስሷል። ያም ሆኖም
በተለይ ታፈሡን፣ በልሁን መርዕድንና ትርፌን አግኝታቸው በጋራ አልቅሰውና አንብተው እፎይ ካሉ ወዲህ ከፊል የመንፈስ መረጋጋትም እያደረባት ሄደ። ሸዋዬም ለአባትና ለእናቷ የገባችውን ቃል ያከበረች መሰለች! ሔዋን በማንኛውም ሰዓት ወደ
ታፈሡ ቤት ሄዳ የቱንም ያህል ጊዜ ቆይታ ብትመለስ የት ነበርሽ ምን አስቆየሽ?” አትላትም፡፡ ለሔዋን ከምንም በላይ የተመቻት ይህ የሸዋዬ ቃል ማከበር ነው።

ለአንድ አስራ አምስት ቀናት ያህል በዚህ አይነት እንፃራዊ የመንፈስ
መራጋጋት ውስጥ የሰነበተችው ሔዋን ሦስተኛው ሳምንት ሲጀመር ግን ያ በሸዋዬ ቤት የመኖር ሥጋቷ የልቧን ግድግዳ ማንኳኳት ጀመረ፣ በድሉ አሸናፊ ማንደፍሮን እየተከተለ በዚያ ቤት ውስጥ ገባ ወጣ ማለት ጀመረ፡፡ ማንደፍሮ ስለ ሔዋን ብዙ ነገር ሲነገረው ከርሟል። ከአስቻለው ጋር የነበራት ግንኙነት፣ በድሉ ሔዋንን ለመቅረብ ያደረገዉ ጥረትና የሰጠችው ምላሽ፣ በአሁኑ ወቅት አስቻለው ስለሚገኝበት ሁኔታና ሌሎችም ሁኔታዎች በዝርዝር ተገልፀውለታል፡፡ ወደፈት
የበድሉንና የሔዋንን ጉዳይ እንዲጨርስም አደራ ተጥሎበታል፡፡
ምንም እንኳ በአስቻለውና በሔዋን መካከል የነበረው ግንኙነት በተዛባ ሁኔታ የተነገረው የተሳሳተ መንገድ እንዲከተል የተገፋፋ ቢሆንም ማንደፍሮ ግን
ሆዱን ፍርሃት ፍርሃት ይለው ነበር። ሁኔታው ምንም ይሁን ምን አንድ ነገር ተገንዝቧል። ሔዋን የምታፈቅረው ሰው አላት። ያ ሰው ለጊዜው በአካባቢው ባይኖረም በተስፋ እየጠበቀችው እንደሆነ ልብ ብሏል። የተጣለበት አደራ ደግሞ ይህን ተስፋ በጥሶ ሌላ እንዲቀጥል ነው። እናም ለህሊናው እየከበደው ውስጥ ውስጡን ይጨነቃል።
በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳዩ የበድሉ ነው፣ የሥራ ዋስትናው። እንዲሁም የሸዋዬም ጭምር ነው፤ የአፍላ ፍቅረኛው፡፡ በዚህና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እየተገፋፋ የተጣለበትን አደራ መወጣት የሚያስችሉ መላዎችን ሲፈጥር ሰንብቷል።አንድ ቀን በተለመደው
ሁኔታ በድሉና ማንደፍሮ በሽዋዬ ቤት ጫት ለመቃም አቅደው ከሸዋዬ ጋር በተደረገ ምክክር ቤቱ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከቤቷ ሲደርሱ ማንደፍሮ ከቤቱ ወለል ላይ ቆሞ ለየት ያለ ሀሳብ አቀረበ
«ዛሬ ከምንም ነገር በፊት አንድን ነገር መፈፀም አለበት።» አለ በዚያ ሰዓት ጓዳ ውስጥ ለነበረችው ሔዋን በሚሰማ ሁኔታ ድምፁን ከፍ በማድረግ።
«ምን?» አለች ሽዋዩ እንደማታውቅ ሆና፡፡
«ሔዋን የለችም እንዴ?» ሲል ማንደፍሮ እንደገና ጠየቃት፡፡
«አለች። ጓዳ ውስጥ ናት፡፡»
«ኑ ሁላችንም ወደ እሷ እንሂድ፡፡» አለና ማንደፍሮ ቀድሞ ወደ ጓዳ
ተራመደ። በድሉና ሸዋዬም ተከተሉት::
«የኔ ፍልቅልቅ» ሲል ጠራት ማንደፍሮ ሔዋንን፡፡
«አቤት» አለች ሔዋን ድንግጥ እያለች፡፡ የዚያን ዕለት ደግሞ የልብ
ህመሟ ዘወር ብሎባት ፍራሽ ላይ ጋደም ብላለች፡፡
«አንድ ጊዜ ብድግ ብትይ!»
ሔዋን በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ እንዳለ ተነስታ በዚያው ፍራሻ ላይ
ቆመችና ከፊት ለፊቷ የተኮለኮሉትን ሁሉ ተራ በተራ ታያቸው ጀመር፡፡
«ዛሬ ዛሬ ሁሉም ነገር ገብቶኛል፡፡» አለ ማንደፍሮ ሳቅ ብሎ። “ይህ ሰውዬ!» ሲል ቀጠለ ወደ በድሉ እያመለከተ ወደዚህ ቤት በመጣ ቁጥር ስሜትሽ ለምን እንደሚቀያየር ተረድቻለሁ። ያለ ፍላጎትሽ እየጎነተለ ሲያስቀይምሽ እንደቆየ ገብቶኛል።አሁን አሁን ጥፋት መሆኑን አምኖ ተቀብሏል፡፡ ይቅርታም ሊጠይቅሽ ተዘጋጅቷል።ይቅርታውን ተቀብለሽ እንድትታረቁና ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ እየተያየን እንድንኖር ፈልጌለሁ።» አላት።
ሔዋን ያላሰበችውና ያልጠበቀችው አቀራረብ ነበር። ለጊዜው ግን ድንግጥ ተብላ ወደ መሬት ከማቀርቀር በቀር ያለችው ነገር አልነበረም። ማንደፍር ወደ በድሉ ዞር አለና ቆጣ ባለ አነጋገር «በል እግሯ ላይ ውደቅ!» ሲል አዘዘው፡፡ በድሉ ኮቱን ወደ ኋላ መለስ አድርጎ በሔዋን እግር ላይ ወደቀ፡፡
«እልልልል» አለች ሽዋዬ። ማንደፍሮም ብቻውን አጨበጨበ። ለሔዋን ግን ትልቅ የእረብሻና የግርግር ጩኸት ወስጥ የገባች መሰላት፡፡ በድሉ በእግሯ ላይ ወድቆ ለአፍታ ሲቆይ ለመግደርደር ያህል እንኳ በቃ ተነስ አላለችውም። ሲበቃው ራሱ ተነሳ::
«ቀጥል!» አለ ማንደፍሮ ነገሩን በማሟሟቅ ዓይነት ፈንደቅ እያለ፡፡
በድሉ ቀኝ እጁን በኮቱ ኪስ አስገብቶ አንዲት በብልጭልጭ ወረቀት የተጠቀለለች ነገር አወጣ፡፡ ወረቀቱን ቀዶ ጣለ፡፡ ከማይካ የተስራች ነጭ ሙዳይ
ብቅ አለች፡፡ እሷንም ከፈታት። በቅድሚያ ጥጥ መሳይ ነገር ታየ። ቀጠለና በግምት አሥራ አራት ግራም የሚሆን የክርስቶስ የስቅለት ተምሳሌት ማጫዎች
የተንጠለጠለበት የወርቅ ሀብል አወጣና በአንገት ውስጥ ለማስገባት የተዘጋጀ በሚመስል ሁኔታ ከያዘ በኋላ ፈገግ እያለ ማንደፍርን አየት አደረገው::
«ቀጥላ! ምን ታየኛለህ?» አለ ማንደፍሮ፡፡ በድሉ እነዚያን አራት ገጣጣ ጥርሶቹን ገልፈጥ አድርጎ ወደ ሔዋን ጠጋ ሲል ሔዋን ግን ድንገት ጮኸች::
«አልፈልግም!»
«ተይ እንጂ የኔ ፍልቅልቅ አለ ማንደፍሮ እሱም ደንግጥ አያለ፡፡
«እምቢ! አልፈልግም» ሔዋን አሁንም፡፡ ፊቷን ክስክስ አድርጋ በድሉን በጥላቻ ዓይን ታየው ጀመር።
«አይ እንግዲህ!" አለና ማንደፍሮ ሔዋንን ወደ ራሱ ጎተት አደረገና ሁለት እጆቿን ያዝ በማድረግ «አጥልቅላት » አለው በድሉን።
በድሉ የሔዋን እጆቿ እንደተያዙለት ሀብሉን በአንገቷ ላይ የመጣል ያህል አስገብቶ ወደ ኋላው ፈግፈግ አለ።ማንደፍሮና ሸዋዬ አጨበጨቡ፡፡ ማንደፍሮ በሔዋን አንገት ላይ ያረፊቱን ሀብል በእጁ ያዝ አድርጎ ወርቁንም ሔዋንንም
ተራ በተራ እየተመለከተ«አንቺን ለመሰለች ቆንጆ የሚገባ ልዩ ስጦታ!» አላት።
ሔዋን ግን ዓይኖቿ በእንባ ሞሉ፡፡ ግንባሯን በከንዷ ጋርዳ ወደ መሬት
በማቀርቀር ታለቅስ ጀመር።
«ሔዋን እንዳንቀያየም» አላት ማንደፍሮ። ሔዋን መልስ አልሰጠችውም፡፡አሁንም አጎንብሳ ታለቅስ ጀመር፡፡
👍8😱1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....ጥቂት ቀናት አለፉ። አንድ ቀን ምሽት ላይ በልሁና መርዕድ በምህጻረ ቃል አምሆ ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ ከውጭ ወደ ቡና ቤቱ ሲገቡ በስተቀኝ በኩል በምትገኝ ብቸኛ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብለው ከአንዲት የቡና ቤቱ እስተናጋጅ
ጋር እየተቃለዱ ይጠጣሉ። ከጠረጴዛው ፊትለፊት ያለው ባንኮኒና የቡና ማሽን ብቻ
ስለሆነ ቦታው እንደ ልብ ለመጫወት አመቺ ነው። የቀልዳቸውና የጭውውታቸው
ማዕከልም የመርዕድ ዓይን አፋርነት ነው:: አስተናጋጇ ባህሪውን ቀደም ብላ ስለምታውቅ በነገር እየነካካች ታሳፍረው ይዛለች፡፡መቼም የአንተን ድንግል የምወስደው እኔ ነኝ፡፡» ትለዋለች ጉልበቱንና ጭኖቹን እያሻሸች።
«እስቲ እንደ ምንም ብለሽ ገላግይው::» በልሁ እየሳቀ፡፡
«አቦ ተይኝና ሌላ ወሬ አምጪ!» ይላል መርዕድ የአስተናጋጇን እጅ ከላዩ ላይ ለማንሳት እየሞከረ።
አይዞህ! ቦታውን እንደሆነ እኔው ራሴ አሳይሃለሁ፡፡» አስተናጋጇ አሁንም።
«እንዲህ ከመባል ሞት ይሻላል መርዕድ!» እያለ በልሁ ይስቃል::
እንዲህና እንዲያ እያሉ በመጫወት ላይ ሳሉ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ሁለት ሰዎች ተከታትለው ወደ ቡና ቤቱ ገቡና ግራ ቀኝ ተመለከቱ፡፡ ከበሩ
በስተግራ በኩል ያለው ዋናው ሳሎን በሰው ተሞልቷል። በቀኝ በኩል ያለችው ጠረጴዛ ደግሞ በእነበልሁ ተይዛለች። በቀጥታ ወደ ባንኮኒው በመጠጋት ጀርባቸውን ለእነበልሁ ሰጥተው ቆሙ:: ወዲያው ደግሞ በድሉ አሸናፊ ከውጭ መጥቶ
ተቀላቀላቸው:: እሱ ከመሀል ሌሎቹ ግራና ቀኝ በመሆን ፈንጠር ፈጠር ብለው ተደረደሩና የሚጠጡትን አዘዙ፡፡ ለሁሉም አረቄ ቀረበላቸው ::
በልሁ ግን ቅፍፍ ይለው ጀመር፡፡ እሱና በድሉ ቀድሞም ተዳፍጠው ነበር የኖሩት. ዜሬ ደግሞ ገና ሲገባ ገልመጥ አድርጎት ነበርና
እንዲሁም ከተማ ውስጥ አይቷቸው ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ገጥሟልና ጥርጣሬ ገባው መጠጥ አወሳሰዳቸውም አላምር አለው ግልብጥ ግልብጥ ያደርጉታል። በሹክሹክታም ሲወያዩ ያያቸዋል። ወደ ኋላቸው ዞር እያሉ ሲገላምጡት ያይ ጀመር
መርዕድና አስተናጋጇ የሚያወሩትን ትቶ እነ በድለን መከታተል ቀጠለ፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከምሽቱ ሁለት ሰአት አለፈ። የመደመጥ እድሉን እዚያው የተፈጠረበት አገር ረስቶ የመጣው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቡና ቤቱ ውስጥ ተከፍቶ ያለ ምንም አድማጭ ለራሱ ይጮሀል። ዜና እወጃውን ጨርሶ የግብርና ፕሮግራም ማስተላለፍ ጀምሯል።የመስኖ ስራ እንቅስቃሴ እያሳየ ገበሬዎች ያገኙትን ጠቀሜታ ይዘረዝራል።
በድለና ጓደኞቹ ከቴሌቪዥኑ ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ወሬ ማውራት ጀመሩ። ያም ቢሆን ከበልሁ ጀሮ ደረሰና እሱም በጥንቃቄ ያዳምጥ ጀመር፡፡ከበድሉ በስተቀኝ በኩል ከቡና ማሽኑ አጠገብ ቆሞ የሚጠጣው የበድሎ ጓደኛ "ስሚ አንቺ"
ሲል ጨራት ከባንኮኒ ውስጥ ቆማ የነበረችውን አስተናጋጅ።
«አቤት» አለችው።
የኢትዮጵያ ገበሬዎች ቴሌቪዥን ገዙ ወይስ እኔና አንቺን ገበሬ ለማድረግ ተፈልጎ ነው ይኸ ፕሮግራም የሚተላለፈው ? ሲል ጮክ ባለ ድምፅ ጠየቃት።
«እኔ ምን አወቄ?» አልች አስተናጋጇ።
«የከተማ ገበሬ ሞልቷሌ አትይውም!» አላት ሌላው የበድሉ ጓደኛ ከግራ በኩል ሆኖ ወደ ኋላ
ዞር ብሎ በልሁንም አየት አደረገው፡፡
«ይኽ ከየጓሮው ወፍ ዘራሽ ቡና የሚለቅመው?» ሲል የመጀመሪያው ተናጋሪ ጠየቀ።
«ሞፈርና ቀንበራቸውን ሰቅለው ወደ ከተማ የገቡ ገበሬዎች ስላሉ
ጎምዥተው እንዲመለሱ ይሆናል፡፡ አለና በድሉ ወደ ኋላው ዞር ብሎ በልሁን ገልመጥ ሲያደርገው ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ፡፡

«አሃ» አለ በልሁ፡፡ ነገሮች ሁሉ ይበልጥ እየገቡት ሄዱ። ሁኔታው የበለጠ ጆሮውን ጥሎ እንዲያዳምጥ አደረገው።
ከተማ ውስጥ ገብቶ ማውደልደል የጀመለ ገበሬ ምንም ቢሉት ምን
ቢያደርጉት ተመልሶ ገጠር አይገባም፡፡» አለ የመጀመሪያው ተናጋሪ የበድሉ ጓደኛ፡፡
እሱም በልሁን ዞር ብሎ ሲያየው አሁንም ከበልሁ ጋር ተገጣጠሙ::
«ወዶ ነው! ተጎዶ ይመለሳል፡፡» በማለት በድሉ ሲጨምር በልሁ
ሁለመናውን ይነዝረው ጀመር፡፡ በልሁ ጠብ ጠብ ሲሸተው ትንፋሽ ያጥረዋል፡፡እስኪጀምር ድረስ መላ ሰውነቱ ይንዘፈዘፋል። ዓይኑ ይፈጣል፡፡ ያ በሽታው ተነሳበት:: በዚያው ስሜት ውስጥ ሆኖ ምልልሳቸውን ማዳመጡን ቀጠለ፡፡
«ስሚ አንቺ!» ሲል ተጣራ በድሉ አሁንም እስተናጋጇን፡፡
«አቤት»
«ይህን ቴሌቪዥን ዝጊና «ቆይ ብቻ» የሚለውን ካሴት ክፈች፡፡ ይኸ ሴት አውል ሁሉ ልብ ቢገዘ» አለና አሁንም ዞር ብሎ በልሁን ገላመጠው ።
በዚህ ጊዜ በልሁ ለየለት፡፡ ተዘጋጅተው እንደመጡብትም በትክክል ተረዳ፡፡
ወዲያው በግራ ጣቱ ላይ ያጠለቃትን ባለ ፈርጥ ቀለበት ወደ ቀኝ ጣቱ አዛወራት፡፡
ጡንቻውን ማጠባበቅ ጀመረ። አንዲት የትንኮሳ ቃልና ግልምጫ ብቻ ቀረችው። ይጠባበቃትም ጀመር።
በድሉ አሁንም ቀጠለ፡፡ እንኳን የግብርና ወሬ መስማት የግብርና ባለሙያ ነኝ ባይ በከተማው ውስጥ ማየት አስጠልቶናል። አለና ብርጭቆዉን ብድግ አድርጎ
አረቄውን ጨለጠና ከመጠን በላይ ባንኮኒ እያንኳኳ «ቶሎ በይ ነዳጅ ጨምሪ ዛሬ የማነደው አለኝ» አለና አሁንም ወደ በልሁ ዞር አለ።
«ስማ አንተ» አለው በልሁ መርእድን
«ወይ» አለ መርእድ። መሰከረ እየሆነ ያለውን ነገርም ይከታተል ነበርና ደንግጦ መግቢያ ቀዳዳ አቷል
«ከተቀመጥክበት ንቅንቅ እንዳትል እሺ»
«ለምን ወጥተን አንሄድም?» አለ መርዕድ፡፡
«ጉዳዩን እስከምፈፅም" ጠብቀኝ» አለና በልሁ ከወንበሩ ላይ ተነስቶ
በቀጥታ ወደ ባንኒው አመራ፡፡ በበድሉ እና በቀኙ በኩል ባለው ጓድኛው መካከል ባንኮኒ ተደግፎ ቆመና «ጎበዝ» አላቸው ሦስቱንም ተራ በተራ እየተመለከተ፡፡
«የጨዋታችሁ ደስ አለኝና መጣሁ።» እያጋበዛችሁኝ ወይ እየጋበዝኳችሁ እንጫወት
ብዬ ነው::» አላቸው ዓይኑን ፈጠጥ ያለ ቢሆንም ነገር ግን ፈገግ ብሎ
«ታውቀናለህ?» አለው በድሉ በቁመት የሚበልጠውን በልሁን አንጋጦ እየተመለከተ፡፡
«ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ግን እንደማንተዋወቅ ገባኝ፡፡ ግን ደግሞ ሳንተዋወቅ እንለያይም።» ሲል መለሰለት በልሁ ረጋ ብሎ። «ተገድጄ ወደ አገሬ ልመለስ ነውና የወጪ ልበልህ፤ ጠጣ!» አለው አሁንም እያፌዘ።እስከዚህ ወቅት
ድረስ የበድሉ ጓደኞች ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ ግን በልሁን በግርምት ዓይን ይመለከቱታል።
«ነገር ፈልገሃል እንዴ?» አለ በድሉ አሁንም በልሁን እየተመለከተ::»
«ራሱ ፈልጎኝ ነው የመጣሁት።
አሁን ጠጣ! ካልጠጣህ ግን
እመታሀለሁ፡፡»
«ኣ?» ብሎ በድሉ ቀስቀስ ሊል ሲል በልሁ ድንገት አንገቱን አነቀወ። ገበሬ አይደለሁ ፊትህን ላርሰው ነው» አለና በመሀል ፊቱ ላይ ሀይለኛ ቡጢ አሳረፈበት፡፡ በፍጥነት ደገመው ከቀኙ በኩል ያለውን የበድለን ጓደኛ እንቅስቃሴ
ይከታተል ነበርና እውነትም ሲንቀሳቀስ አይቶት ኖሮ በቃሪያ ጥፊ ዓይነት በሀይል ሲሰነዝርበት ጆሮ ግንዱን አገኘው። ሰውየው ባላሰበው ሁኔታና ሀይል ስለተመታ
ከመርዕድ እግር ስር ወድቆ ጥቅልል አለ። መርዕድ በዚያው ጀመረው። በወደቀበት
👍12
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..ሔዋን የልብ ህመሟ ከመቼውም ጊዜ ብሶባት ፍራሽ ላይ ድፍት ብላ
መዋል አዘውትራለች።በበልሁ በጢ ፊቱ የተጠረማመሰው በድሉ አሸናፊ አልጋ ላይ ከዋለ አስራ አንድ ቀን ሆኖታል፡፡ እዚሁ ቀን ላይ ሆኖ ሲቆጠር “ማንደፍሮ በአንድ ሳምንት ያህል ተረኛ ሆኖ በተመደበበት ከአዋሳ ይርጋለም መስመር ላይ ለመስራት ከቤቱ ከወጣ ሶስት ቀናት አልፎታል።
እለቱ እሁድ ነው፣ ከሰአት በኋላ፡፡ ሸዋዬ ቤትዋ ውስጥ ለብቻዋ ቁጭ ብላ ጫት ትቅማለች።
ነገር ግን የጎረሰችውን ጫት ማላመጥ እስከምትረሳ ድረስ
በሃሳብ ተውጣ ፍዝዝ ትክዝ ትላለች። በበድሉ ላይ የደረሰው ውርደት ከእሱ ይበልጥ እሷን አሳፍሯታል። ዛሬ በማውጠንጠን ላይ ያለችው ሃሳብም ይህንኑ
ሀፍረትና ውርደት ስለምታካክስበት መንገድና ሁኔታ ነው።
መነሻ ያደረገችው ከራሱ ከበድሉ የመነጨ ሀሳብ ነው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተኛበት አልጋ አጠገብ ቁጭ ብላ ስታፅናናው በነበረችብት ወቅት በድሉ
አንድ ነገር ተናግሯታል ሸዋዬ! በእህትሽ ምክንያት ደሜ ፈስሷል፡፡ ቅሌት ደርሶብኛል። መካሻዬም እሷው ናት:: የመጣው ይመጣል እንጂ አልተዋትም። ወይ
እንደኔ ትዋረዳለች። አለያም እስከ መጨረሻው በእጄ ትገባለች። ለዚህ ደግሞ የአንቺን የአላሰለሰ ጥረት እጠብቃለሁ የሚል፡፡ የዛሬው ህሳብና ትካዜዋም በዚሁ
ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ከበድሉ የዛቻ ቃሎች በተግባር ተፈጽሞ ማየት የምትፈልገው ሔዋን ጥቅልል ብላ በእሱ እጅ መግባቷን ብቻ ነው::
ሸዋዬ ያለማወላወል በአንድ ሀሳብ ፀንታለች። ሔዋን ከበድሉ እጅ እስከ ወዲያኛው ትገባ ዘንድ አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ከእሱ መፀነስ ይኖርባታል። ይህ ከሆነ መንገዶች ሁሉ ያጥራሉ፡፡ ሔዋን አስቻለውን በተስፋ የመጠበቅ ሀሳቧ ይቀየራል ቢመጣ እንኳን መሸሹን ትመርጣለች። አስቻለው ራሱም ዘወር ብሎ ሊያያት አይሞክርም አንዴ ከወለደች የልጅ አባት ያስፈልጋታልና በድሉን መራቅ አትፈልግም ምርጫዋም እሱና ብቻ ይሆናል። ማርገዟ ያሳፍራትና ከነታፈሡና ከነበልሁም ትርቃለች እንዲያውም ጭራሽ እንዳያውቁባት ወደ ቤተሰቦቿ ወደ ክብረ መንግስት ልሂድ ከሰል ትችላለች ያኔ በድሉም ወደዛው መመላለስ ይጀምራል በዚያው ከቤተሰቦቿ ይተዋወቅና እጁንም መዘርጋት ይጀምራል። ይሄ ደግሞ ለሸዋዬ ድርብ ድል ይሆናል "እኔም ለዚህ ብዬ ነበር" ለማለት ያበቃታል ይህንም ወርቃማው መላ ብላ ሰይመዋለች።

ይህን ወርቃማ መላ ለፍሬ ለማብቃት ግን በድሉ ከሔዋን ጋር
የሚፈፅመው የወሲብ ግኑኝነት
በተጠና ወቅትና ሰዓት መሆን እንዳለበት ታምናለች ለዚህ መሰረት የሆናት ደግሞ በወር አበባ አቆጣጠር የሚታወቅ
የእርግዝና ወቅት ነው። እንደ ሔዋን ለመውለድ ሳይሆን ላለመውለድ ስትል ራሷ
ስትጠቀምበት ኖራለችና እውቀቱ አይቸግራትም የሚያስፈልጋት የሔዋንን የወር አበባ ዙር ማወቅ ብቻ ነው በየስንት ቀን እንደማታየት ካወቅች በየትኛው ቀን ግኑኝነት ብትፈፅም መፀነስ እንደምትችል ታውቀዋለች።በዚህ ሰአት ሔዋን ይፈፀምባት ዘንድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ወስናለች። ሔዋን ጩኸት ብታሰማ
እንኳ በተያያዥ ሊነሳባት የሚችለውን ውግወት ጆሮ ዳባ ልበስ ልትለው ቆርጣለች።
የሔዋንን የወር አበባ ዙር ለማወቅ ግን ተቸግራለች፡፡ እሷን እራሷን
አትጠይቃት ነገር ሰሞኑን ተኳርፈዋል። በሌላ በኩል በትክክል ላትነግራት ትችልና
ጥረቷ ሊመክን ይችላል። አስተማማኝ እንዲሆንላት ሐኪም ማማከር እንደሚሻል ታይቷታል። ለዚህ ስኬት ደግሞ የሔዋንን የልብ ህመም መነሻ ማድረግ ፈለገች ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባርናባስ ወይሶ ታወሳት። እሱ ደግሞ የውጭ ሀገር ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ሥራው ከተመለሰ
ሰምብቷል። ከመጣም ተገናኝተዋል፡፡ ባል ማግባቷን ሰምቶ ተነጋግረውበታል፡፡ ባርኔ አልተከፋም እንዲያውም እንኳን ደስ ያለሽ ብሏታል በተገናኙ ቁጥር መቃለዳቸውን አልተውም። እናም የሔዋንን የልብ ህመም በማስመርመር ሂደት ምናልባት የወር አበባሽ ጋር ግንኙነት ካለው በሚል ሰበብ በሚቀርበው ሀኪም በኩል የወር አበባ ቀን መምጫ ዙር ሊያስጠናላት እንደሚችል ገመተች። ይህን ዘዴ ለራሱ ለበድሉ ብታካፍለው ከእሷ በተሻለ
ከባርናባስ ጋር ተመካክሮ ሲያሳካው እንደሚችል አሰበች፡፡ የዚያን ዕለት ልትነግረው ወሰነች።
ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ከቤቷ ወጣች፡፡ በቀበሌ ዜሮ ሦስት የመጨረሻ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው የበድሉ መኖሪያ ቤት ማምራት ጀመረት:
ቀኑ መሽት ብሎ ለዓይን መያዝ ጀምሯል፡፡ ወደ በድሉ ቤት በመሄድ ላይ ሳለች ልክ አስፋልቱ ላይ ስትደርስ ድንገት ሳታስበው ባርናባስን ከሩቅ አየችው
አስፋልቱን ይዞ ከታች ወደ ላይ ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን እሷ ወደነበረችበት አቅጣጫ ይመጣል:: ከበድሉ በፊት ለእሱ ስለ ውስጥ አሳቧ በዚያ አጋጣሚ ትንሽ ፍንጭ ልትሰጠው ወደደች፡፡ መንገድ ዳር ቆማ ጠበቀችው። ባርናባስ ልክ አጠገቧ ሲደርስ ከሰዎቹ ነጠል ብሎ ወደ እሷ እንዲመጣ በእጇ ጠቀሰችው፡፡ ባርናባስም ጥሪዋን ተቀበሎ ወደ እሷ ጠጋ እያለ
«የሽዋ፣ በጨለማ መንገድ ዳር ምን አቆመሽ?» ሲል ጠየቃት እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ።
ቸግሮኝ::» አለችው እንደመሽኮርመም እያለች።
«ምነው? ምን ገጠመሽ? አላት ባርናባስ። ሞቅ ስላለው አፉ ተያይዟል።
«ከቸገረኝ እንኳ ቆይቷል፡፡ ድንገት በሩቅ ሳይህ ግን ላማክርህ ፈልጌ ነው፡፡
«ምንድነው ችግሩ?።»
«ባክህ ያቺን እህቴን ልቧን እያመማት ተቸግሬአለሁ።» ምናልባት በደንብ ሊከታተላት የሚችል አንተ በተለይ የምትቀርበው ሀኪም ካለ አደራ ትልልኝ እንደሆነ ብዬ ነው።»
«እሱ ምን ይቸግራል ይዘሻት ነያ»
«ቢሮህ ውስጥ ምን ጊዜም ትኖራላህ እያደል?»
«የት እሄዳለሁ፡፡» ካለ በኋላ
ባርናባስ እጇን ያዝ አድርጎ «ድሮ እንኳ ወደ ዜሮ አምስት ቀበሌ ጎራ እል ነበር! ዛሬ ግን ማንዴ አስለቀቀኝ» በማለት ሳቅ ብሎ ሸዋዬንም አሳቃት።
«ሁሉም በጊዜው ሆኗል በቃ!» አለች ሸዋዬ እንደ መሽኮርመም እያለች።
«በቃ ! በቃ? አላት ባርናባስ አሁንም ወልገድገድ እያለ፡፡
«አብቅቶ»
«ታዲያ ያቺን ቆንጆ እህትሽን እንዴት አድርጌ ልጠይቃት?»
«እንዴ እሷን መጠየቅ ማን ይከለክልሀል?»
«አሁን እችላለሁ? ወይስ ስውየሽ ይኖር እንደሆን ብሎ ነገሩን ተወት
ሲያደርግ ሸዋዬ ቀጠለች።
«አሁን መሸ ጓደኞችህም ጥለውህ ሂዱ»
«እነሱን ተያቸው እባክሽ!» አለና እውነት ሰውየሽ ከሌለ ልጠይቃት
በጣም በጣም ናፍቃኛለች፡፡» ሸዋዬ የበርናባስሀሳብ አልከበዳትም ማንደፍሮ የለምና ዓይን ለዓይን አይጋጩባትም። በሌላ በኩል እግረ መንገዷን
ሔዋን ወደ ሐኪም ቤት እንድትሄድ ሊገፋፋት እንደሚችል ታያት፡፡
«ከበረታህ እንሂድ፡፡ እንደውም ቀኑን ሙሉ እንደተኛች ነው የዋለችው»
«ሰውየው ግን አይኖርም? አየሽ ምናልባት» ብሎ አፍ አፏን ሲጠባበቅ ሸዋዬ ቀጠለች፡፡ ለነገሩ ሰሞኑን አይኖርም የስራ ተራው ይርጋለም አዋሳ መስመር ሳይ ነው።» አለችና ግን ቢኖርም የኔና የአንተን ጉዳይ የት ያውቃልና
ይጠራጠራል ብለህ ሰጋህ?»
«አለመኖሩ ጥሩ!»
👍13
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የእልሁን ያህል ወለል ላይ የተጋደመ ፊቷን በጫማው ረግጦ ድፍጥጥ ካደረጋት በኋላ እዚያው እንደተዘረረች ትቷት ወደ በር አመራ።.
«ዘወር በል!» አለ ማንደፍሮ በር ላይ ተኮልኩሎ ሁኔታውን ይመለከት የነበረው ሰው ሁሉ።
ሳሎን ውስጥ መግባት የጀመሩትም በር ላይ የተኮለኮሉትም ሰዎች ግርር ብለው ወደ ውጭ ወጡ፡፡
ማንደፍሮ ግቢ ውስጥ እየተጯጯህ ይርመሰመስ የነበረው ህዝብ መሀል
እየተራመደ «ማንደፍሮ ገና ዛሬ ተደፈረ ተደፈረ ተደፈረ!» ካለ በኋላ “ዋይ ዋይ ዋይ" እያለ
ከግቢ ወጣ። ግራ ቀኝ ሳይመለከት ቀጥታ ወደ ከተማ ሄዴ፡፡ያ በወያዘሮ ዘነቡ ግቢ ውስጥ ይተረማመስ የነበረ ሕዝብ ሁሉ እየተጋፋ ወደ ሸዋዬ ቤት ገባ፡፡ ርቃነ ሥጋዋን ወለል ላይ ተጋድማ ስታለከልክ ላያት ሁሉ
የምትተርፍ አትመስልም ነበር። የወሳንሳ ተሸክመው አልጋዋ ላይ አጋደሟት፡፡ወይዘሮ ዘነቡ እፈቷ ቆመው «ኧረ እስቲ ውሃ! ኧረ እስቲ ውሃ!» እያሉ ጮሁ፡፡ ውሃ
በፍጥነት ቀረበላቸውና በአፍና በአፍንጫዋ ይወርድ የነበረ ደሟን ሲያጥቡ በነበረበት ወቅት ድንገት ሳታስብ ሔዋን ከተፍ አለች:: በትርምስምሱ ደንግጣ እንዳልነበረ ሁሉ ጭራሽ ወደ ቤት ገብታ የሸዋዬን ሁኔታ ስታይ የባሰ በመረበሽ «ወይኔ ጉዴ! እት አበባ ምንድነው?» እያለች በድንጋጤ ትርገበገብ ጀመር።
በዚህ ሰዓት ሸዋዬ በሌባ ጣቷ ወደ ሔዋን እያመለከተች ድክምክም ባለ ድምፆ «ያዙል...ኝ! ይቺን ሰው ያዙልኝ! ጎረምሳዋን ቤቴ ውስጥ ደብቃ ያስገደለችኝ እሷ ናት! ያዙልኝ!» እያለች ጥሪ ታስተላልፍ ጀመር፡፡
ሔዋን ክው ብላ ደነገጠች። በአካባቢው የነበሩትን ሰዎች አየት አየት እያረገች ወደኋላ ታፈገፍግ ጀመር። ከሔዋን የበለጠ
በውሃ ያጥቧት የነበሩት ወይዘሮ ዘነቡ ከመደንገጥ በተጨማሪ ንድድ አላቸውና፡
«ኣ! ምን እያልሽ ነው አንቺ?» አሏት በቁጣ።
ሸዋዬ ግን አሁንም «ያዙልኝ! እሷ ናት ያስገደለችኝ! ያዙል..ኝ»
ማለቷን ቀጠለች።
ሔዋን ጉዳዩ ስላልገባት ይበልጥ እየደነገጠች ሄደች። ከቤት ወጣችና ግቢ ውስጥ ቆም ብላ ስታዳምጥ ሸዋዬ አሁንም ያዘልኝ እያለች ስትናገር ስትሰማ ጭራሽ ከግቢው ወደ ውጭ ወጣች። ደግነቱ ማንም ሊይዛት አልቃጥም እሷ ግን ደንግጣና ፈርታ ገልመጥ ገልመጥ እያለች በቀጥታ ወደ ታፈሡ ቤት ገሰገሰች፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ንዴታቸው ባሰ፡፡ ያጥቧት የነበረቱን ትውት አደረጉና ወደ ውጭ እያተራመዱ በዙሪያቸው ለተሰበሰበው ሕዝብ በሚሰማ ድምፅ።
ጎረቤቶቹ የሆናችሁ ወገኖቼ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይቺን መዘዘኛ ሴት ዛሬውኑ ከቤቴ አውጡልኝ ቶሎ በሉ ዕቃዋን አውጡልኝ ቶሎ በሉ ለእናቷ ልጅ እህቷ ያላዘነች ነገ ለኔም አትመለስ ቀጣፊ ናት ወልወልዳ ናት የተረገመች» አሉ
በማከታተል፡፡ ለዚያች ዕለት እንኳ ቢለመኑ እሻፈረኝ አሉ፡፡ በአካባቢው የተከበሩ ናቸውና ልመናቸው ተከበረ።
በቦታው በርካታ ወጣቶች ስለነበሩ የሸዋዬን ዕቃ አንድ ባንድ እየለቀሙ ወደ ውጭ ማውጣት ጀመሩ። ተባባሪው በርካታ ስለነበር
የሸዋዬን የማውጣት ስራ አፍታ
አላቆየም፡፡ ሁሉም ከአጥር ውጪ ወጣ:: ወይዘሮ እልፍነሽ ዕቃዋን
ደረደሩላት በመፍቀዳቸው ከእሳቸው ግቢ ውስጥ እየገባ ተቆለለ፡፡ ራሷ ሽዋዬም በሰዎች
እቅፍ ተይዛ ወደ እሳቸው ቤት ተወሰደች።
ዝቅዝቅ የዶሮ ሸክም እንዲሉ የሔዋንና የአስቻለውን ፍቅር አፍርሳ የራሷን ቤተ ልትገነባ ደፋ ቀና ስትል የነበረች ሸዋዬ ህልሟ ሁሉ ከንቱ ሆነ።
ድሮም የውሸት ቤት ነበርና እነሆ በአንድ ቀን ፈረሰ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከሶስተ ወር በኋላ ነው ፤ የጥር እና የካቲት ወራት መጋጠምያ
ሳምንት። በደንባራ በቅሎ እንዲሉ ወትሮም ግርግር የማይለያት ዲላ ከተማ ሰሞኑን ደግሞ በባስ ግርግር ውስጥ ሰንብታለች፣ የክፍለ ሀገሩ ስፖርት ሻምፒዮና ሲካሄድባት ሰንብቷል ። ከመላ የሲዳሞ ክፍለ ሀገር በርካታ ስፖርቱኞች መጥተው
ይርመሰመሱባታል፡፡ በተለይ በፈስቲቫሉ ማጠናቀቂያ ቀናት ስፖርተኞች በቡድን በቡድን እየሆኑ የመደባደብ አዝሚያሚያ ስለጀመሩ የፀጥታ ጥበቃውም በዚያው ልክ ተጠናክሯል በከተማዋ ውስጥ ያሉ ፖሊሶችና ሌሎች አጋር የፀጥታ ሐይሎች
በተጠንቀቅ ሆነው የከተማዋን ፀጥታ ይጠብቃሉ፡፡
ልከ ሻምፒዎናው በተጠናቀቃበት ቀን ፡ምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ
የተፈራው ሁከት የተነሳ መሰለ።
ከአንደኛ መንገድ በላይ ወደ አውራጃው አስተዳደር ፅህፈት ቤት መሄጃ አካባቢ ድንገት የእሪታና ኡኡታ ድምፅ ተሰማ። ወዲያው ደግሞ አንድ ጥይት ተተኮሰ። በርካታ የፀጥታ ሀይሎች ወደ አካባቢው መሮጥ ጀመሩ:: ስፖርተኞች የተጣሉ የመሰለው ህዝብና ሌሎች ስፖርተኞችም ወደዚያው ይጎርፍ ጀመር። ለዚያውምበሩጫና በጫጫታ ታጅቦ።
በርካታ ሰው እቦታው ሲደርስ ግን የጠቡ ዓይነትና መነሻው የተለየ ሆኖ ተገኘ የተጣሉቶ ስፖርተኞች ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ናቸው መነሻው በአንዲት ሴት ምክንያት መሆኑ ይወራል ሰዎቹ ለድብድብ መጋበዛቸውን እንደ ቀጠሉ
ናቸው። አንዲት በዕድሜ ጠና ያሉ ሴት ደግሞ ከአንድ ቤት በር ላይ ቆመው ይለፈልፋሉ፡፡ «ያቺ ነውረኛ እኔ ደግሞ ደህና ሰው መስላኝ አንገት ደፊ አገር አጥፊ አሉ! ሆሆይ! የድሀ ቤቱን ልታስፈርሰው!» ይላሉ። ከሴትዮዋ አነጋገር በመነሳት አንድ ፖሊስ ጠጋ አላቸውና ‹‹ምንድነው ችግሩ የኔ እናት?» ሲል ጠየቃቸው።
አሪ በገዛ እጄ ጎትቼ ያመጣሁት ችግር ነው ልጄ ከሁለት ወር በፊት
ሳይሆን አይቀርም፤ አንዲት ሴትዮ መጥታ ቤት አከራይኝ ብላ መጣች፡፡ እኔ ደሞ ጨዋ መስላኝ አክራየኋት። ለካ ጋለሞታ ኖራ ይኸው ሁለት ወንዶችን በአንድ ጊዜ ቀጥራ ሰው ታፋጃለች::» አሉና እንደ እንዝርት በሚሾር ምላሳቸው እየተንጣጡ፡፡
«ጋለሞታዋ የታለች? » ሲል ጠየቃቸው ፖሊሱ::
ሴትዮዋ ከቆሙበት ቤት በታች ቀጥሎ ያለውን ክፍል በእጃቸው እየጠቆመው «እዚህ ቤት ውስጥ ናት ስራዋ አሳፍሯት ሳይሆን አይቀርም ቤት ዘግታ
ትነፋረቅልሀለች::» አሉት:: ፖሊሱ ወደ ተጠቆመው ቤት በር ጠጋ አለና እያንኳኳ
«ክፈች አንቺ! አለ።
«እምቢ! አንክፍትም!» የሚል ምላሽ ሰውስጥ ተሰጠው::
«ነገርኩሽ ብቻ! ፖሊስ ነኝ ክፈች!»
በሩ ተከፈተ፡ ሁለት ሴቶች ቆመው ያለቅሳሉ፡፡ ፖሊሱ በር ላይ ቆሞ ወደ ውስጥ እያየ ማንኛሽ ነሽ ጋለሞታዋ?» ሲል ጠየቀ::
«እዚህ ጋለሞታ የለም» አለች ከሁለቱ አንዷ፡፡ ሌላዋ አሁንም አጎንብሳ ታለቅሳለች እኒያ ላፍላፊዋ ሴትዮ ፖሊሱን ተከትለው ወደ በሩ ጠጋ ብለው ያዩ ነበርና
ነበርና ለፖሊሱ በእጃቸው እየጠቆሙ፡ «ይቺ አጎንብሳ የምትነፋረቀዋ ናት የማትረባ የቆንጆ በለል!» ካሉ በኋላ ወደ ኋላ መለስ እያሉ፡ «ይቺን ሁለት እጆቸን የፊጥኝ አስሮ አርባ መግረፍ ነበር እንጂ..»እያሉ ወደ መጡበት አቅጣጫ ተመለሱ።
ሕዝቡ ከዚያም ከዚህም እየጎረፈ አካባቢው በመደበላለቅ ላይ ነው፡፡
ፖሊሱ የተጠቆመችውን ጋለሞታ በቁጣ
«ነይ ውጪ” አላት በር ላይ እንደ ቆመ
«ለምን?» አለኝው በፍርሀት እየተንቀጠቀጠች፡፡
ፖሊሱ እንደ መናደድ አለና ገባ ብሉ በበይለኛ ጥፊ አንዴ አጮላት፡፡እንድና ከኋላ ዞሮ ወደ በሩ ይገፈትራት ጀመር፡ የቤቱን በር ወጣ እንዳለች ፖሊሱ አሁንም በሀይለኛ እርግጫ መቀመጨዋ ላይ ሲያሳርፍባት ወጀ ላይ ነጥራ.
👍18👎1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


.....የምትለቀቀውማ እንደ ነገሩ ሁኔታ ዋስ ጠርተህ ነው» አለው መርማሪው ፖሊስ፣ ነገሩ የዕለት ግጭት በመሆኑ ብዙም ርቀት በማይሄድ ምርመራ እንደሚጠናቀቅ መርማሪው
ያስባል። የጠረጴዛ ደወል
አቃጨለና ረዳቱ ፖሊስ ሲቀርብለት ዓለሙን ወስዶ መብራቴ ባዩ የተባለ ሌላ
እስረኛ እንዲያቀርብለት አዘዘው።
ረዳቱም የተባለውን ፈፀመ፡
መብራቴ ባዩም በዕድሜው ብዙ አልገፋም ፣ ከሠላሳ ብዙ አያልፈውም፡፡ቀጠን ያለ ቀይ ዳማ ቢጤ ነው። መካከለኛ ቁመት አለው፡፡ ፀጉሩ አጠር፣ ከወደ አፉ
ሞጥሞጥ፣ ዓይኖቹ አነስ እነስ ያሉ ናቸው። እሱም በተመርማሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ መርማሪውን በፍርሀት ይመለከተው ጀመር።
መርማሪው ፖሊስ ልክ በዓለሙ ላይ እንዳደረገው ሁሉ መብራቴን
መሠረታዊ መረጃዎችን እየጠየቀ ከመዘገበ በኋላ፡ «ከዓለሙ መርጋ ጋር ከአሁን በፊት ትተዋወቃላችሁ?» ሲል በቅድሚያ ጠየቀው።
«አይቸውም አላውቅ::»
«ምን አጣላችሁ ታዲያ?»
«እኔ ቀድሜ ገብቼ ባለሁበት ቤት መጥቶ ካልወጣህ ብሎ ሊያሳገድደኝ ሞከረ። አልወጣም ስለው በተቀመጥኩብት በጥፊ አቃጠለኝ ከዚያ በኋላ ነው
በደመነፍስ እጆቹን ይዤ ድረሱልኝ ብዬ የጮኩት።» አለው አይኖቹን እያቁለጨለጨ።
«በተጣላችሁበት ቤት ውስጥ ለምን ነበር ቀድመህ የገባኸው?»
«ቤቴ ነዋ!»
«ቤቴ ስትል? ሴትዮዋ ሚስትህ ናት?»
«ያው እንደ ሚሲቴ ናተ።»
«ለምን ያህል ጊዜ አብራችሁ ቆይታችኋል?»
«አረ ብዙ ነው።»
«እኮ በግምት?»
«ከአስራ አምስት ቀን በላይ አብረን አድረናል። ግን በተከታታይ
አደለም አልፎ አልፎ ነው፡፡ ከተዋወቅን ግን ቆይተናል፡፡»
«ወዳጅህ ስሟ ማን ይባላል?»
እየተገረመ ጠየቀው።
«ስሟ?»አለና መብራቴ ወደ ጣሪያ አንጋጠጠ፡፡ ግን ጠፋበት፡ ለማሰላሰል ሞከረና ሲያቅተው «ረሳሁት።» አለ የድንጋጤ ስሜት እየተነበበበት፡፡
«አሥራ አምስት ቀን ሙሉ የአቀፍካት ወዳጅህን» በማለት መርማሪው እየተገረመ ጠየቀው።
«በድንገት ስለሆነ የተገናኘነው ስሟ ይረሳኛል።»
መርማሪው ፖሊስ ጥርጣሬ ገባውና መብራቱን ትኩር ብሎ ተመለክተው።
መብራቴ የበለጠ የእፍረትና የድንጋጤ ስሜት ይነበብበት ጀመር።
«ዋሽተሃል አይደል?» አለው መርማሪው በትኩረት እየተመለከተው፡፡
«አጥፍቻለሁ ጌታዬ» አለ መብራቱ ሽቁጥቁጥ እያለ»
የመርማሪው ፖሊስ ልብ አሁንም እየተከረጢረ ሄደ ሆኖም ቃል
በያዘበት ወረቀት ላይ ከአስፈረመው በኋላ «የአንተንና የዓለሙን ጉዳይ በቀላሉ
ላለፈው አስቤ ነበር፡፡ ነገር ግን ተጠራጥሬአለሁ፡፡ የሁለታችሁንም ጉዳይ እንደገና
ኑነየው አልቀርም:: እለና ወደ እስር ቤት እንዲሄድ አሰናበተው፡፡
የመርማሪው ፖሊስ ጥርጣሬ ቀላል አልነበረም። ዓለሙን በሚጠይቅበት ወቅት ያያቸው ነነበሩ ሁኔታዎች እንደገና ትዝ አሉት። በስካር መንፈስ በአንዲት
ሴተኛ አዳሪ የተጣሉ መስለውት በእርግጥም ዋስ እያስጠራ በቀላሉ ሊሸኛቸው ነበር
አሳቡ:: አሁን ግን በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ምርመራ ሊያደርግ ወሰነ። ለማንኛውም አለ በሆዱ
እስቲ ጋለሞታ የተባለችው ሴት ሌላ አጠራጣሪ ፍንጭ የምታወጣ
ከሆነ በቅድሚያ እሷን ላናጋግራት፡፡” አለና በረዳቱ ፖሲስ እንድትጠራ አደረገ።
ጋለሞታዋ ተጠርታ ወደ መርማሪው ፖሊስ ቢሮ በር ላይ ስትደርስ ሁለመናዋ በፍርሀት ይንቀጠቀጣል፡፡ እንባዋ ከዓይኗ ላይ እንደ በረዶ ይረግፋል።
መልኳ ደግሞ ይህ ቀረሽ የማትባል ወብ ናት። ዓይኖቿ እንደ ንጋት ኮከብ ያበራል። በዕድሜዋ ገና ወጣት ልጃገረድ ትመስላለች። “ጋለሞታ በሚለፈው የሴትነት መገለጫ አንዳች አመልካች ነገር አይታይባትም። ከንፈሮቿ እምቦጦች ይመስላሉ፡፡ የአፍንጫዋ አቀማመጥ ለቄንጥ የተሰራ ይመስላል። የቀይና ነጭ
ቡራቡራ ድሪያ ለብሳ በጡቶቿ ተገትሮ የአንጀቷን ድራሽ አጥፍቶታል።የመርማሪው ቢሮ በር ላይ ደርሳ ምን እንደምትባል ትዕዛዝ እየጠበቀች ሳለች
መርማሪው ፖሊስ ግን ይህንን ገፅታዋን ሲያይ ድንገት ተዘናግቶ ኖሮ ፐ! ይችስ ታደብድባለች አለ በሆዱ። ወዲያው ደግሞ «ምን ያስለቅስሻል?» ሲል ፈገግ ብሎ ጠየቃት ሁኔታዋ ሁሉ እያስገረመው። ግቢ ቁጭ በይ ማለቱን እንኳ እረሳው፡፡
«ፈርቼ» አለችው እንዳቀረቀረች::
«የሰራሽው ስራ አሳፈረሽ!»
«አረ እኔ ምንም አልሰራሁም!»
«እስቲ ግቢና ቁጭ በይ አላት» በእጁ አገጩን ያዝ አድርጎ አሁንም በትኩረት እየተመለከታት። ጋለሞታዋ ቁጭ አለችና አሁንም በፍርሃት ስሜት አቀርቅራ መሬት መሬት ታይ ጀመር።
«ምን አድርገሽ ነው የታሰርሽው?» ሲል ጠየቃት መርማሪው ፖላስ ቀስ እያለ ሊያግባባት ፈልጎ።
«ምንም» አለችና ለቅፅበት ያህል ቀና ብላ አየችው፡፡
«ዓለሙንና መብራቱን የት ነው የምታውቂያቸው?»
«እነማናቸው እነሱ?» አለች አሁንም፡፡ ለቅፅበት ያህል ቀና ብላ አይታው እንደገና እንጋቷን ደፋች::
«ጭራሽ አታወቂያቸውም?»
«አረ እኔ እንደዚህ የሚባሉ ሰዎች አላውቅም።»
«ሁለቱም ወዳጃችን ናት እያሉ እኮ ነው፡፡» አለና መርማሪው ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ለምላሿ ጓጉቶ ይጠባበቃት ጀመር፡፡
"ኣ"አለችና እሁንዎ ቀና ብላ አየት አረገችው፡፡
«ከማናቸውም ጋር አብረሽ አድረሽ አታውቂም?»
«እኔ ከወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም፡፡»
«አንድም ቀን?»
«አንድ ቀን ብቻ ከምወደው ሰው ጋር አድሬ አውቃለሁ፡፡ ግን ከንፈሬን ስሞታል እንጂ ሌላ ምንም አላደረገኝም::»
«ማነው እሱ ደግሞ?» ሲል ጠየቃት መርማሬው።
«እሱ እዚህ አገር የለም፣ ኤርትራ እሚባል አገር ከሄደ ቆይቷል፡፡»
«ኦ!» አለ መርማሪው ፖሊስ አንዳች የማያውቀው ስሜት መላ ሰውነቱን ድንገት ወርር እያረገው፡፡ «ማን ይባላል?» ሲል እንደገና ጠየቃት::
«አስቻለው ፍስሀ»
«አስቻለው ፍስህ ?» ሲል ደግሞ ጠየቃት፡፡
«አዎ፡፡» አለችውና እሷም ድንግጥ ብላ ቀና ብላ ታየው ጀመር፡፡
«እንዴ!» አለና «መርማሪው እንደገና አትኩሮ ያያት ጀመር። ስሜቱ እያደር ተለዋወጠ፡፡ አንቺ ስምሽ ማን ይባላል?» ሲል ጠየቃት የምትሰጠው መልስ ቀድሞ እያስፈራው።
«ሔዋን ተስፋዬ::»
«ምን?» ሰምቶ እንዳልሰማ፡፡
«ሔዋን ተስፋዬ እባላለሁ።»
መርማሪው ፖሊስ ፍዝዝ ብሎ ቀረ፡፡ የያዘው እስኪርቢቶ ከእጁ ላይ ሾልኮ ሲወድቅ ፈጽሞ አልታወቀውም፡፡ ዲላ ከተማ እየኖረ ስለመሆኑ እንደ አዲስ
ታወቀው፡፡ በሀሳብ ጥቅልል ብሎ አስመራ ከተማ ገባ፡፡
መርማሪው ፖሊስ የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ይባላል። በሲዳሞ ክፍለ ሀገር በሀገረ ማሪያም ከተማ ተወልዶ ያደገ ነው። እዚያው በፖሊስነት ተቀጥሮ
እስከ ምክትል አሥር አለቅነት የደረሰና እሱም እንደ አስቻለው ፍሰሀ የዘመቻ ግዳጅ ተወስኖበት
ወደ ግንባር ዘምቶ በኤርትራ ምራባዊ የጦር ግንባሮች ለተከታታይ አምስት ዓመታት ሲዋጋ የቆየ ነው:: በጦር ግንባር የፈጸመው ጀብዱ የሀምሳ አለቅነት ማዕረግ ካገኘ በኋላ በቀጣይ የውጊያ ወቅት በደረሰበት ቁሰለት የተዋጊነት
ብቃቱ ቀንሶ ወደነበረበት የፖሊስ ሰራዊት አባልነቱ እንዲመለስ ተወስኖለት ወደ ሲዳም የተመለሰና ጊዜያዊ ምደባ ዲላ ውስጥ በመርማሪነት እየሰራ ያለ ፖሊስ ነው።
👍2
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....ወደ ሲዳሞ በስተርጅና ዕድሜዬ ብቅ ማለት አስባለሁ፡፡» ካለ በኋላ ወደ ሃምሳ አለቃው ቀና በማለት ፈገግ እያለ
«ግን ደግሞ ከሀገሬ በፊትእኔ ቀድሜ ካረጀሁ » አለው
«አልገባኝም::»
«የሀገር እርጅና፡፡»
አስቻለው ወደ መሬት አቀረቀረና ራሱን ወዘወዘ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ከንፈሩን ነከሰ፡፡ ስሮቹ በግንባሩ ላይ ተገተሩ። ፊቱ ተከፋ፡፡
«አስረዳኛ የኔ ወንድም አለው»
የሃምሳ አለቃ ክንዶቹን አቆላልፎ
ጠረጴዛውን በመደገፍ አስቻለውን እየተመለከተ።
«ሀገር በገዳዮቿ መዳፍ ወስጥ እስከ ገባኝ ድረስ ምናልባት እንደ ሰው አትቀበር እንደሆነ እንጂ ማርጀት ቀርቶ ልትሞትም ትችላለች» አለ አስቻለው ፊቱ ክፍት እያለውና ጣሪያ ጣሪያ እያየ፡፡
«ስትል?» ሲል ጠየቀው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ፡ የአስቻለው አነጋገር ሚስጥሩ ለጊዜው ባይገባውም ግን ደግሞ በውስጡ ብዙ ነገር ስለመሆኑ ከወዲሁ ገምቷል።
«አየህ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ቀጠለ እስቻለው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ የህዝብና መንግስት ከተኮራረፈ ምድርና ሰማያዋም ይቀያየማሉ። ያኔ ከዜጎቿ ልብ
ውስጥ ተስፋ ይጠፋል፡፡ ተስፋ የሌለበው ሕዝብ ጭካኔ ይወልዳል።በተለይ ደሃ ከጨከነ
ጠላት የሚያደርገው የገዛ ሀገሩን ነው፡፡ አምባገነኖች የቱንም ያክል
ጡንቻቸው ቢፈረጥም ድሀን ማስተዳደርና መቆጣጠር አይችሉም፡፡ እንዲያውም
በቁጣው እነሱንም ያጠፋቸዋል፡፡ ያኔ ገዢና ተጎዢ አይኖርምና 'ጥፋት ይነግሳል::በዚህ ጊዜ ሀገር መታመም ትጀምራለች። ታዲያ ይህ ከሆነ ሀገር አልሞተችም፣?
የሃምሣ አለቃ ሲል ጠየቀው።
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ባላሰበውና አስቦትም በማያውቅ የተለየ እሳቤ ወስጥ ገባ፡፡ አንዳች አስፈሪ ስሜት ውስጥ ገባ። አንዳች አስፈሪ ስሜት መጣበት እስከዛሬም እንደ ሰው ስለመኖሩ ተጠራጠረ። ፍርሀትና ጭንቀትም አደረበት። በረጅሙ ተነፈሰና
«አስደነገጥከኝ አስቻለው» አለው፡፡
«ሊያስፈራም ሊያስደነግጥም ይችላል ሃምሣ አለቃ። በአሁኑ ሠዓት ሀገራችን ታማለች። ህመም ደግሞ በቶሉ ያስረጃል፡፡ ከሐገሬ በፊት እኔ ካረጀሁ ያልኩህም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ አለና አስቻለው የሃምሳ አለቃን ትኩር ብሎ
ተመለከተው።
«ይህ ገባኝ አስቻለው አለና የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ እንቆቅልሽ የሆነብኝ ግን ለምን ከዚያ ወዲህ ወደ ዲላ ላለመሄድ እንደነሰንክ ነው፡፡ ምናልባት
ይህም ምስጢር ይኖረው?» ሲል ፈራ ተባ እያለ ጠየቀው።
«ምስጢር የለውም፡፡ እኔ ግን መሄድ አልፈልግም::»
«አይመስለኝም አስቻለው፣ ይህ ውሳኔህ ምስጢር ሳይኖረው አይቀርም፡፡አይዞህ ምስጢር ቢኖረውም በበኩሌ እጠብቅልሃለሁና ንገረኝ፡፡» አለው።
«ወታደር አይደለህ! ለምስጢርማ ማን ብሎህ» አለና አስቻለው ፈገግ አለ፡፡
«ሙያዬ ስለሆነ ሳይሆን ባአንተ በመታመን።»
አስቻለው ጭንቅ አለው። የሃምሳ አለቃው ጥያቄ ከልቧ የመነጨ መሆኑ ይገባዋል ግን ደግሞ የሆዱን ምስጢር ለማንም ላለመናገር ወስኗል የሃምሳ አለቃው ልመና ግን መንፈሱን ወጥሮ ያዘው።ወደ ጣርያ ወደ መሬት ጎንበስ ቀና ካለ በኋላ
በቅድምያ በረጅሙ ተነፈሰ።
የሀምሳ አለቃውንም አየት ሲያደርገው በፊቱ ላይ የጭንቅ ስሜት አነበበበት። መጨነቁም ስለ እሱ መሆኑ ገባው። ከዚያ በኋላ ፍንጭ ሊሰጠው ፈለገ።
«አየህ ሃምሳ አለቃ! እኔ በአሁኑ ሰዓት ወደ ዲላ ብሄድ ያለ ጊዜዋ
የምትረግፍ አበባ አለች፡፡» አለና እንባው ከዓይኑ ላይ ዝርግፍ አለ፡፡
«እንዴት»
«አበባ የምልህ በእርግጥ ተክል አደለችም። ሔዋን ተስፋዬ የምትባል የሰው ልጅ ናት:: የምወዳት የምትወደኝ፣ የምሳሳላት የምትሳሳልኝን የመጀመርያ ፍቅረኛዩና እጮኛዬ ነበረች፡ ልንጋባ ሁለት ወር ሲቀረን ነበር እኔ ድንገት ወደዚህ ወደ አስመራ የመጣሁት።አሁን ግን ይህው እንደምታየኝ ግማሽ አካሌ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ያለ ጊዜዋ ትረግፋለች የምልህም ያቺ አበባ እንዲህ ሁኜ ብታየኝ
የሚፈጠርባት፣ የስሜት ስቃይ ስለማውቅ ነው፡፡ እንደኔ እግሯ ባይቆረጥ እንኔ ፊቷ ባይጠበስ! እንደኔ ጆሮዋ ባይበላሽ፣ እንደኔ ዓይኗ ባይጠፋ እኔን በዚህ ሁኔታ
ካየች ግን በንዴት በቁጭት በብስጭትና በፀፀት የአእምሮ ህመምተኛ ትሆንብኛለች ብዬ እሰጋለሁ። ታዲያ ይህን እያወኩ ሄጄ የዚያችን አበባ ህይወት ላበላሸው ሃምሳ አለቃ?» አለውና በጉንጩ ላይ ይንቆረቆር የነበረ እንባውን በእጁ መዳፍ ሙሉ ሙዥቅ አድርጎ ጠረገው።
«አታልቅስ የኔ ወንድም!» አለው ሃምሣ አለቃ እሱም ዓይኑ በእንባ
እየሞላ።
«እኔማ ገና ብዙ ብዙ አለቅሳለሁ ሀምሳ አስቃ! እኔ ዕድለ ቢሱ ያቺን እድለ ቢስ አድርጊያት ቀርቻለሁ:: ስለ ሔዋን ተስፋዩ ገና ብዙ አለቅሳለሁ::በህይወት እስካለሁ ልረሳት አልችልምና ሳለቅስ እኖራለሁ፡፡» አለና አስቻለው
አሁንም እህህህህ …! በማለት መላ ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በለቅሶ ሲቃ ተርገፈገፈ።
“ምናልባት ትጠየፈኛለች ብለህ ሰግተህ ይሆን የኔ ወንድም?» ሲል ሃምሣ አሐቃ የራሱንም አይን እየጠረገ ጠየቀው።
«ፍጹም ሀምሳ አለቃ! የኔዋ ሔዋን መልኳ አበባ እንደሚመስል ሁሉ
ትጠየፈኛለች ብዬ አይደለም፡፡ የኔዋ ሔዋን እንዲህ ያለ ተፈጥሮ የላትም። በራሴ በኩል ግን ከእንግዲህ እኔ ለእሷ አልገባም ብዬ ወስኛለሁ።» አለ እያለቀሰ።
“ታዲያ እሷ እየጠበቀችህ ቢሆንስ?»
«ተስፋ እንድትቆርጥ ብዩ የበኩሌን አንድ ርምጃ ወስጃለሁ። የምትኖረው በኔ ደመወዝ ስለነበር እንዲቋረጥባት ብዬ የመንግስት ስራ ለቅቄ በአንድ የፈረንጆች
ግብረ ሰናይ ድርጅት ክሊኒክ ውስጥ በአስተርጓሚነት ተቀጥሬአለሁ::»
«ምናልባት ርሀብ ላያሽንፋት ቢችልስ?»
«ይህ እኔንም ያሰጋኛል። ግን ልጅ ናትና ከመቆየት ሀሳቧን ብትቀይር
እያልኩ እጓጓለሁ:: በዚያ ላይ ደግሞ ገና እኔ እዚያው እያለሁ ሊድሯትና ሊያገቧትም እያሰቡ የሚያንዣብበ ሰዎች ነበሩና በእነሱ ጫና ተሸንፋ አዲስ
ህይወት ብትጀምር እያልኩም እፀልያለሁ::»
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ የአስቻለውን ምኞትና ሃሳብ ሲሰማ ቆይቶ ወደ ዲላ ላለመሄድ የወሰኑበት ምክንያት ሲገባው በራሱ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቁስል አመመውና ለአስቻለው ይገልፅለት ዘንድ ስሜቱ ገፋፋው።
«ስማ እስቻለው፡፡» አለው ፍዝዝ ትክዝ ብሎ እየተመለከተው እኔም እንዳተው ተገድጄ ወደዚህ ሀሄገር የመጣሁ ነኝ መጥቼ የፈፀምኩት ነገር ቢኖር ሰው መግደል ነው።እላዬ ላይ የምታየው የሃምሣ አለቅነት መአረግ የተሰጠኝም ሰው በመግደሌ ነው። የገደልኩት ደሞ የሀገሬን ልጆች ወንድሞቼን ነው ሶስት አራት ገድዬ ከሆነ በዛው መጠን በርካታ ዘመድ አዝማዶቻቸውን አስለቅሻለሁ አሳዝኛለሁ በዚህ ስራዬ ደግም ተሸልሜበታለሁ። ታድያ እኔ ይሄን ያህል የህሊና እዳ ተሸክሜ ወደ ሃገሬ ልገባ ስቸኩል አንተ ልታክም መተህ ራስክ ከቆሰልክ ልትረዳ
መጥተህ ራስህ በተጎዳህ ልትጠግን መጥተህ ራስክ ከተሰበርክ ምን የህሊና የፀፀት አለብህና ምን የሚያሳፍር ነገር ሰርተሃልና ከዚህ አይነት አሳዛኝ ውሳኔ ላይ ልትደርስ ቻልክ?» ሲል ጠየቀው።
«ሀሳብህን አደንቃለሁ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ጀመረ አስቻለው «ልዩነቱ ግን አንተ የገደልካቸው ኢትዮጵያውያን ሞተው አርፈዋል። ቤተሰቦቻቸውም እርማቸውን አውተው ተገላግለዋል።ፀፀቴ ያለው በአንተ ልብ ብቻ ነው።
👍10
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...እንደ ሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከትዝታ ጋር የተቀላቀለ አይሁን እንጂ መርዕድ እሽቴም በደረቅ ጭንቀት ተወጥሮ ነው ያረፈደው የጀመረው ደግሞ ጠዋት ሁለት ሰዓት በፊት፡፡ መኖሪያው በዜሮ ሁለት ቀበሌ የታችኛው ጥግ ሲሆን የሚያስተምረው ደግሞ የዲላ ከተማ የላይኛው ጫፍ
በሆነ ቀበሌውስጥ በማገኘው
የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ሔዋንና ትርፊ የተከራዬት መንገዱ ላይ በመሆኑ ሲወጣም ሲወርድም ጎራ እያለ ይጠይቃቸው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ግን ወደ ሥራው ሲሄድ ያ ቤት በጠዋት ከውጭ ተዘግቶ አየው ወዴት እንደሄዱ የጎረቤት ስዎችን ሲጠይቅ ማታ ሲሆንና ሲባል ያመሸው ሁሉ ሁሉ የዝርዝር ተነገረው።
በሰማው ወሬ የተሰማው ድንጋጤ ጭራሽ ራስ ምታት ለቀቀበት። ዛሬ
ቢቸግረው ወደ በልሁ ቢሮ ሮጠ፡፡ ነገር ግን ዘንግቶ ነበር እንጂ በልሁ
ለመስክ ስራ ወጥቷል መስሪያ ቤት ደርሶ ይኸው ሲነግረው ያለ ውጤት ተመለሰ።
እንደገና ወደ ታፈሠ ቤት ላሮጥ አሰበ፡፡ ግን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ክፍለ ጊዜ አስተምሮ ሌሎቹን ክፍለ ጊዜያት ነፃ እንደሆነ አስታወሰና በአንድ ፊት ስራውን
አጠናቆ ለመሄድ ወስኖ እየተጨነቀም ቢሆን ወደ ትምህርት ቤት አመራ፡
ልክ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሥራውን ጨርሶ ወደ ታፈሡ ቤት
በመገስገስ ላይ ሳለ አስፋልቱን አቋርጦ ሊያልፍ ሲል ከይርጋ ጨፌ አቅጣጫ ትመጣ የነበረች ቶዮታ መኪና ደጋግማ ክላክስ ስታደርግ ሰማ። ዞር ብሎ ሲመለከት የበልሁ የመስክ መኪና ናት:: በክላክስ ያስጠራውም ራሱ በልሁ ኖሯል፡፡ በአለበት ላይ ቆሞ መኪናዋን ጠበቀ።
«ዛሬ ስራ የለም እንዴ?» ሲል ጠየቀው በልሁ አጠገቡ ሲደርስ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ መርዕድን እየተመለከተ፡፡
«እስቲ ና ውረድ!» አለ መርዕድ ፊቱ በድንጋጤ ጭምትርትር እንዳለ።በልሁም የመርዕድ ሁኔታ ገና ሲያየው እስደንግጦታል። «ምነው? ምን ሆነካል?
«ችግር አለ፡፡»
በልሁ ከመኪናዋ ላይ ዱብ ብሎ ወደ መርዕድ በመጠጋት ምንድን ነው ችግሩ? ሲል ጠየቀው።
«ሔዋን ታስራለች!»
«ምን አድርጋ?»
መርዕድ ከሰው የሰማውን በሙሉ ነገረው::
«ያምሀል እንዴ አንተ ሰው?»
«የነገሩኝን ነው እኔ የምነግርህ?»
“ከታሰረች ጠይቀሃታል?»
« አሁን ወዚያው እየሄድኩ ነበር፡፡»
ለነበሩበት ቦታ ፖሊስ ጣቢያው ቅርብ ነው፡፡ በልሁ ሾፈሩን ወደ ቤቱ እንዲሄድ አሰናበተውና ከመርዕድ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያው ገሰገሱ፡፡ እርምጃቸው
ፈጣን ስለነበር ከአምስት ደቂቃ በላይ አልወሰደባቸውም።
ትርፌ ገና በጠዋት ለሔዋን ቁርስ ይዛ እንደሄደች አልተመለሰችም ኖሯል፡እንዲያውም በእስረኞች ግቢ እንድትገባ ተፈቅዶላት ኖሮ ፊት ለፊት ሔዋን ጋር አብረው ተቀምጠው በልሁና መርዕድን ከሩቅ ሲያዩአቸው ተንጫጬ «በልሁ! መርዕድ! በልሁ! መርዕድ!» በማለት።
በልሁና መርዕድ ጣቢያው በር ላይ እንደ ደረሱ አንድ ፖሊስ ጠጋ
አላቸውና ««ከእናንተ ወስጥ በልሁ ተገኒ የሚባል ማነው?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
«እኔ!» አለው በልሁ በሌባ ጣቱ ወደ ራሱ እያመለከተ፡፡
«ሃምሳ አለቃ ይፈልጉሃል።»
«በሰላም?»
«አላወቅሁም አለና ፖሊስ ወደ እነ ሔዋን ዞር ብሎ አየት አደረገና ፊቱን ወደ በልሁ በመመለስ ከልጅቷ ጋር ሳይገናኝ ወደኔ አምጡት ነው ያሉት» አለው።
«ቢሮው የት ነው?» አለ በልሁ ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
«ተከተለኝ! አለና ፖሊስ በልሁን ከፊት ከፊት እየመራ ወስዶ ካሃምሳ አለቃው ቢሮ አስገባው፡፡
የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ጆሮግንዶቹን በእጆቹ ይዞ
ጠረጴዛው ላይ በማቀርተር ሀሳብ ውስጥ ገብቶ ሳለ ፖሊስ በልሁን ይዞ በመድረስ «አቶ በልሁ
እኒህ ናቸው አለው፡፡ ሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ለካ በልሁን ከተማ ውስጥ በዓይን ያወቀው ኖሯል:: እንዲያውም በአለባበስ፣ በተክለ ሰውነቱና አጠቃላይ አቋሙ
ያደንቀው የነበረ ሰው ሆኖ ሲያገኘው ‹‹በልሁ ተገኒ ማለት አንተ ኖረሀል እንዴ?
እያለ ብድግ ብሎ ጨበጠው::
«አዎ ነኝ» አለ በልሁ ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
«ቁጭ በል እስቲ! ሁለቱም ፊት ለፊት ተቀመጡና ተፋጠጡ፡፡
«የተበሳጨህ ትመስላለህ!» አለው የሃምሣ አለቃ፡፡
«አዎ እጅግ በጣም ተናድጃለሁ፡፡
«ምነው?»
«የማትታሰር ሰው አስራችኋላ» አለው በልሁ ቁጭ እንዳለ በቀኝ
ሽንጡን በመያዝ ሃምሳ አለቃውን እየተመለከተ።
«ወንጀል ፈጽማ እንሆነስ» አለ ሃምሳ አለቃው ፈገግ እያለ።
«የተባለው ከሆነ አላምንም።» አለና በልሁ የሃምሳ አለቃውን ጠረጴዛ መታ መታ እያደረገ «ቀድሞ ነገር የተሰራ ሁሉ ወንጀለኛ የአሰረ ሁሉ ዳኛ ነው ብዬ ማመን ከተውኩ ቆይቼአለሁ።» አለው።
«አይፈረድብህም»
«አሁን ለምን ፈለከኝ።» ሲል በልሁ ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ ጠየቀው።
«ለብርቱ ጉዳይ !» አለና ሃምሳ አለቃ በረጅሙ ተንፍሶ "ግን አቶ በልሁ አሁን የምነግርህ ጉዳይ ሔዋን ለምትባል ልጅ ፈፅሞ መነገር የለበትም ባይሆን
ለአንተና ለቅርብ ጓደኞችህ ከነገርኳችሁ በኋላ አስባችሁበት የሚሆን ነገር ነው።"
«ምንድነው እሱ?»
«አስቻለው ፍስሀ የሚባል ጓደኛ እንደነበረህ ሰማው።»
«አሁንም አለኝ::»
«አብራችሁ ያላችሁ አይመስለኝም።»
«ከልቤ አይወጣምና ምንጊዜም አብረን የምንኖር ይመስለኛል»
«በአካል ማለቴ ነው፡፡»
«ክፉዎች አለያይተውናል፡፡ አሁን የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ
አላውቅም።» ካለ በኋላ በልሁ «ለአንተ ማን ነገረህ? ሲል ጠየቀን
«በህይወት አለ ብልህ ታምናለህ?
«የት አገር?»
«እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡»
«ኦ?» አፉ ተከፍቶ ቀረ ዓይኖቹ በሃምሳ አለቃው ላይ ተተከሉ
«እስቲ ከሚቀርበህ ሰዎች ጋር በመሆን ተሰባሰቡልኝና ስለ እሱ ሁኔታ በጋራ ላናጋገራችሁ፡፡ እኔ የማውቀው ነገር አለኝ፡፡
«ዛሬ ማታ ቢሆንስ?»
«ይቻላል»
«ቦታና ሰአት ወስነው ተለያዩ፡፡»
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ፖሊስ ሆኖ ከተቀጠረ ጀምሮ አሁን
ያጋጠመውን ዓይነት አስደሳች ሥራ እግኝቶ አያውቅም። የሔዋንና በእሷ ምክንያት ተጣላን ያሉ ሰዎችን ጉዳይ እንደ የመንግስት ተቀጣሪነቱ ሳይሆን ልክ እንደ ራሱ
ገዳይ በተለየ ስሜትና ትኩረት ሊከታተለው ወሰነ።
የስራው የመጀመሪያ ዕቅድ የሔዋንን ድንግልና በሐኪም ማረጋገጥ ነበር።በእርግጥም ፈፀመው ሔዋን ያልተሟሸ ገላ ባለቤት ሆና አገኛት። የምስክር
ወረቀቱንም በእጁ ያዘ፡፡ ለምርመራው የሚያወመቹ በርካታ ፍንጮችን ከእነበልሁ አግኝቷል፡፡ የምርመራው ሂደት በዚያው አቅጣጫ እንዲጓዝ አድርጎ እቅድና
ስልቱንም ቀይሶታል፡፡ ስለ አስቻለው ሁኔታ ታፈሡን በልዑንና መርዕድን ሲያነጋግር ባመሽበት ሶስተኛ ቀን ላይ ዓለሙ መርጋንና መብራቴ ባዩን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ከቢሮው አስቀረባቸውና «ልብ ብላችሁ አድምጡኝ» ሲል ሀምሳ አለቃ አስጠነቀቃቸው፥ ዓለሙና መብራቴ ከፊቱ ተቀምጠው የሚሆኑት ሁኔታ በራሱ ውስጣቸውን ያስነብበዋል።
«ሔዋን ተስፋዬ የምትባል ሴት ወዳጃችሁ እንደሆነች ቃል በሰጣችሁበት ወረቀት ላይ ፊርማችሁን አኑራችኋል ነው ወይስ እይደለም?» ሲል ጠየቃቸው።
👍12🔥1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በድሉ ከመደንገጡ የተነሳ በዓይኑ መግቢያ ቀዳዳ የሚፈልግ ይመስል ወደ ላይ ወደ ታች፣ ወደ ቀኝ ወደ ግራ ዓይኑን እያማተረ ይቁነጥነጥ ጀመር።
«በምን ተገናኝታችሁ ነው ያስደበደበችህ?
«እወዳታለሁ!»
«ለምን ወደድከኝ ብላ አስደበደበችህ?»
«መሰለኝ::»
«ስለዚህ ልትበቀላት ፈለክ?»
«የራሷ እህት ናት የገፋፋችኝና መላውን የፈጠረችልኝ::»
«ስሟን ጥራታ!»
«ሸዋዬ::» አለና በድሉ እነዚያን ገጣጣ ጥርሶቹን የባስ ግጥጥ አደረጋቸው፡፡
ላብ ላብ ብሎት ጭንቀቱ ይታወቅበታል።.
“ 'ተደበደበ ሰው ቢደበድብ ወይም ቢያስደበድብ ድርጊቱ ወንጀል ቢሆንም ነገር ግን ስም አለው:: «ግን ወንድ አደባደበች» ብሎ ማስወራቱ ምንድንነው
ዓላማው? ሲል ጠየቀው፡፡
«ስሟን ለማጥፋት::»
«ማለት?»
«ልጅቷ አስመራ ሄዶ የቀረ እጮኛ' አላት፡፡»
«እሺ»
«እዚህ ያሉት ጓደኞቿ ግን ከማንም ጋር እንዳትገናኝ ይጠብቋታል፡፡
እሷም ትፈራቸዋለች። ወንድ አደባደበች ተብሎ ከተወራባት ግን እነሱ ያርቋታል፡፡እሷም ተስፋ ትቆርጥና የኔን ጥያቄ ትቀበላለች ብዬ በማሰብ ነው፡፡» አለና በድሉ
በተቀመጠበት ላይ ተቁነጠነጠ፡፡
«ስማ » አለው የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር።
«አቤት»
«እዚሁ እንዳለህ የሴራ መሀንዲስህን አስጠራታለሁ፡፡ እጥር ምጥን ባለ ቃል
ሁሉን ነገር እንደተናገርንክ ትነግራታለህ። ነገር አደፋፍናለሁ ካልክ ጠብክ ከመንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር በግል እንደሚሆን እወቅ!!»
«ኧረ እነግራታለሁ!»።
ሃምሳ አለቃ ረዳቱን በደውል ጠራና እንደቀረበለት ሽዋዬን እንዲያመጣ አዘዘው። ረዳቱ ሸዋዬን ወዲያው አቀረባት። በበድሉ ፊትለፊት
እንድትቀመጥ ታዝዛ አለፍ ብላ ተቀመጠች፡፡ ከመርማሪው ፖሊስ ይልቅ በድሉን በፍርሀት ዓይን ታየው ጀመር።
«ቀጥላ!» አለ ሃምሣ አለቃው በድሉ ላይ በማፍጠጥ::
በድሉ ከተቀመጠበት ብድግ አለና ወደ ሽዋዬ ጣቱን ቀስሮ «የቀይ ሽብሩን ጉዳይ ሙልጭ አድርጌ ተናግሬያለሁ፡፡ ብትዋሽ ውርድ ከራሴ!» አላትና ተመልሶ ቁጭ አለ። የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቀይ ሽብር የሚለውን ቃል ሲሰማ መላ ሰውነቱን አንቀጠቀጠው፡፡ አጠገቡ ያሉት ሰዎች ነፍሰ ገዳዮች መስለው ታዩት። ልክ በቀይ ሽብር ጊዜ እንደተፈጸመው ሁሉ እሱም እነዚህን ሰዎች ዘቅዝቆ ቢለበልባቸው ደስ ባለው ነበር። ግን ደሞ ጨካኞች የፈፀሙትን የጭካኔ ተግባር መድገም የባስ አረመኔነት መሆኑን ይገነዘባልና በቁጭት ራሱን ወዝውዞ ተወው።
ወድያው ረዳቱን በደውል ጠራ። በድሉን ወደ እስር ቤት አስወሰደና ሸዋዬን ብቻዋን አገኛት።
ሽዋዬ በዕለቱ አጠር ያለ ሰማያዊ ጉርድ ቀሚስና ቡናማ ሹራብ ለብሳለች፡፡
ቀላ ያለች ስካርፍ አንገቷ ላይ ጣል አድርጋለች:: ሳታስበው ታስራ በማደሯ ፀጉሯ አላበጠረቾም፣ አልተቀባባችም:: አመዷ ወጥቷል፡፡ ማንደፍሮ ሜዳ ላይ የደፈጠጠው ፊቷ ጠባሳው አልጠፋም፡፡ ተዥጎርጉራለች። ያ አጭር ፀጉሯ ተንጨፍሯል፡፡
ቀጫጭን እግርቿን ስታክካቸው አድራ መስመር ሰርተዋል። በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ ብሎ የሴትነት ጥላዋ ተገፏል። ታስጠላለች::
«መምሀርት ሸዋዬ!» ሲል ጠራት የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ሁለት እጆቹ ላይ አገጩን አስደግፎ ዘንበል ብሎ እየተመለከታት፡፡
«አቤት!»
«ሙያሽን ምን ያህል ትወጅዋለሽ?»
«በጣም እወደዋለሁ፣ አከብረዋለሁ፣ ተማሪዎቼም በጣም ይወዱኛል::»
«ምን እያስተማርሻቸው እንደሆነ ስለሚገባቸው ይሆናላ!» አላት በምፀት።
«ትንትን ብትንትን አድርጌ ነው የማስተምራቸው»
የሃምሳ አለቃው በረጅሙ ተነፈሰና ወደ ጠረጴዛው ጎንበስ አለ።
ራሱን ወዝወዝ አድርጎ ብዕርና ወረቀቱን ከአመቻቸ በኋላ «እስቲ እኔም እንደተማሪዎችሽ እንድወድሽ ስለ ቀይ ሽብሩ ጉዳይ ትንትን ብትንትን አድርጎአል ንገሪኝ፡፡» አላት።
ሽዋዬ የደረቀ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች ወደ ላይ ወደ ታች በማየት ከተቅበጠበጠች በኋላ «ቀይ ሽብሩኮ» ብላ ልትጀምር ስትል እንደገና ወደ ሃምሳ አለቃው
ዞር ብላ «በድሉ ነግሮህ የለ?»
አለችው።
ሀምሳ አለቃው በሸዋዩ አስተሳሰብ እንደ መገረም ብሎ ድንገት ፈገግ እንደ ማለት አለና እሱ ብቻ ሳይሆን ዓለሙም መብራቴም በሰፊው ዘርዝረውታል ግን መጀመርያ ሀሳቡን ያፈለቅሽው አንቺ ስለሆንሽ ከባለቤቷ መስማት ፈልጌ ነው::
እግረ መንገዴን ምን ያህል እውነተኛ እንደሆነሽ ለማወቅ ፈልጌ ነው፡፡» ብሎ አየት ሲያደርጋት ሸዋዬ ቀጠለች።
«እኔ እኮ ውሽት አላቅም!» አለችው ቀበጥበጥ እያለች
«እኔስ መች ወጣኝ? በይ እውነቱን ንገሪኝ።»
«ቀይ ሽብር ማለት ያው ቀይ ሽብር ማለት ነው አለችው አይኖቿን በዓይኖቹ ላይ እያንከባለለች።
«ነገርኩሽ አንቺ ሴትዮ አላት ተናዶ፡፡ ምኗ ደነዝ ናት በሆዱ።
«ምን ልበል ታዲያ?» ሽዋዬ ድንግጥ አለች። ተጨነቀችም።
«ዝርዝር ሂደቱን ንገሪኝ ነው ያልኩሽ አለና «ቀይ ሽብርስ ምን አስፈለ»
«ሔዋን አስቸገረችኝ::»
«ምን አድርጊኝ ብላ?
«በቃ! እሷ እያለች ባልም ትዳርም ሌኖረኝ አልቻሉም፡፡»
«ነጠቀችሽ ወይስ አፋታችሽ?»
«ሁለቱንም።»
«እንዴት እያረገች?»
«መጀመሪያ በልቤ የወደድኩትን ሰው ውስጥ ለውስጥ ሄዳ በጎን
ጠለፈችብኝ፡፡» እንደገና ብላ ልትቀጥል ስትል ሃምሣ አለቃ ቀደማት።
«የነጠቀችሽ ሰው ማን ይባላል?»
«አስቻለው ፍሰህ ይባል ነበር፡፡»
«እንዴ!» አለ ሃምሣ አለቃ በመገረምም በመደነቅም ዓይነት ትኩር ብሎ ሸዋዬን ሲመለከታት ከቆየ በኋሳ አስቻለውን ትወጂው ነበር?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ነፍሴ እስክትወጣ!»
ሃምሣ አለቃ ግራ ገባው፡፡ ልክ ሔዋንን ያነጋገረ ዕለት እንደሆነው ሁሉ እስኪርብቶውን ወረቀት ላይ ጣል አደረገና ጉንጮቹን ደግፎ ወደ ጠረጴዛው አቀረቀረ፡፡ በዚያው ሀሳብ ውስጥ እንዳለ ሸዋዬ በልቤ የወደድኩትን… ያለችውን አስታወሰና ቅናት ከአጎመነበሰበ ቀና በማለት
«እሺ፣ ደግሞ ከማን አፋታችሽ?» ሲል ጠየቃት።
««ያን እንኳ ባናወራው ይሻላል::»
«ለምን?»
«ደስ አይልማ!»
«ሀምሣ አለቃ የሸዋዬ ባዶነት አስገረመውና አሁንም ጎንበስ ብሎ እንደ መሳቅ አለና። እንደገና ቀና ብሎ “ታዲያ ለኔ የሚያስደስተኝ ደስ የማይለውን ነገር ማወቅ መሆኑን አጣሽው? ወይስ ፖለስ ጣቢያ ውስጥ መሆንሽን ረሳሽው አለና ወረቀቶች ብድግ አድርጎ «ታሪክሽ ሁሉ እኮ እዚህ ላይ ተዘርዝሯል መደበቁ ያዋጣሽ መሰለሽ?» አላት። በእርግጥ ስለ ፍቺ ነገር የተጠቀሰ ነገር አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሸዋዬን ለማስፈራራትና ለማስወትወት ተጠቀመበት፡፡
«ሰዎቹ ያንንም አውታዋል? »አለች ሽዋዬ ደንግጣ ብላ፡፡
«በእነሱ ላይ ጨምሮ ቀድሉ አጋልጦሻል::»
«ቅሌታም ነው።»
የሀሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ድንገት ቂቂቂቂቂ...» ብሎ ሳቀ፡፡ ሸዋዬ ፊደል ከመቁጠሯ በቀር
ምንም እንዳልተማረች ታስበው፡፡፦ እውቀት" ሥርዓትም አጣባት።
በዚያ ምትክ የክፋትና የተንኮል ሰው መሆኗን በውል ተገነዘበና
«ጊዜዬን እትግደያ መምህርት ሸዋዬ!» ሲል ቆጣ ብሎ ተናገራት፡፡ በዚያኑ ልክ
👍15🥰1😁1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...'መወለድ ቋንቋ ነው' ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተደጋግሞ እንደታየው ሰዎች አብረው እስካልበሉና እስካልጠጡ ክፉ ደጉን በጋራ
እስካልተካፈሉ እንዲሁም እስካልተረዳዱ እስካልተደጋገፉ ድረስ የዘር ግንድና የደም ትስስርን ብቻ መሰረት በማድረግ እህቴ! ወንድሜ! አክስቴ! እቴቴ... ወዘተ መባባል ብቻ ከሆነ በርግጥም 'መወለድ' የሚለው ቃል ከቋቋነት ያለፈ ፋይዳ ሲኖረው አይታይም።
በተቃራኒው እንኳንስ መወለድ
የአንድ ወንዝ ውሃ እንኳ አብረው ሳይጠጡ ነገር ግን በአንድ ከተማ ወይም በአንድ አካባቢ አብረው በመኖራቸው ብቻ ስሜት ፍላጎታቸውና አመለካከታቸው ተገጣጥሞ ጥብቅ ቤተሰባዊ ትስስርን ሲፈጥሩ ይታያሉ ለዚህ
ደግሞ የከስቻለው፣ የበልሁ የታፈሡ የመርእድ ከልብ የመነጨ ፍቅር አይነተኛ ምስክር ነው።
ለእነዚህ የፍቅር ቤተሰቦች ትውውቅ መሰረት የሆነው የታፈሡኔ የባለቤቷ ጋብቻ ነበር፡፡ ታፈሡ በወሎ ከፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ውስጥ
ከካቤ እስከ ጃማ ድረስ በተዘረጋው ወይናደጋማ ቦታ ላይ ከትመሰረተ ሰፊ ቤተሰብ ትወለዳለች፡፡ ባለቤቷ ደግሞ በጎጃም ክፍለ ሀገር ደጀን አካባቢ
የተወሰደ ቢሆንም አባቱ መምህር ስለነበሩ በስራ ምክንያት ብዙ በቆዩባት በመሀል ሜዳ ከተማ
ለብዙ አመታት የቆየ ነው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን
በዚያው ከተማ አጠናቆ በኋላም በተግባረእድ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት በምህንድስና ሙያ ሰልጥኖ ትምህርቱን ሲጨርስ ለስራ ተመድቦ ወደ ደሴ ነበር የሄደው።
በዚሁ ጊዜ ተይዩ ታፈሡ እንግዳሰው የአንደኛና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በወረኢሉ ልዕልት የሺመቤት ትምህርት ቤት አጠናቃ ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደሴ በሚዋኘው ዝነኛው የወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ለመማር ትሄዳለች፡፡ ሁለቱ በአንድ ሰፈር ያኖሩ ነበርና በዚያው ሰበብ ያተያያሉ፡ : በሃደት ይተዋወቃሉ፡፡ ቀስ በቀስ ይቀራረባሉ።የኋላ ኋላ ይዋደዱና በመጨረሻም ይጋባሉ።
ታፈሡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ጨርሳ አዲስ አበባ በሚገኘው የኮተቤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ትገባለች፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ ባለቤቷ በዝውውር ወደ ዲላ ይሄዳል፡፡ ታፈሡም የኮሌጅ ትምህርቷን ስታጠናቅት በጋብቻ ሰበብ ወደ ባለቤቷ እንድትሄድ ተደርጎ እሷም በዲላ
አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ትመደባለች፡፡
አስቻለው ተወልዶ ያደገው በመሀል ሜዳ ከተማ እንደ መሆኑ
የተማረውም እዚያው ነው፡፡ እሱ ልጅ በነበረበት ወቅት የታፈሡ ባለቤት በዚያ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲከታተል ያውቀው ነበር፡፡ እሱ ራሱም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በነርስነት ሙያ ሰልጥኖ ሲመረቅ ለስራ ተመድቦ ወደ ዲላ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ ገና ዲላ ከተማ የገባ ዕለት የታፈሡን ባለቤት መንገድ ላይ ያየዋል፡፡ ፈራ ተባ እያለ ያነጋግረዋል፡፡ የትና እንዴት እንደሚያውቀው ያስረደዋል። የታፈሱ ባለቤት የአስቻለውን ለአገሩ እንግዳ መሆን በመረዳቱ ወቸ ቤቱ ይወስደዋል። ከታፈሡ ጋር ያስተዋውቀዋል ታፈሡ ለአስቻለው ትመቸዋለች። አዘውትሮ ወደ ቤቷ እንዲመጣ ታደርገዋለች። እሱም እየተመላለሰ መጠየቁን ይቀጥላል።በዚያው እየተግባቡና እየተዋደዱ ይሄዳሉ። ታፈሡ የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ ክርስትናውን ለአስቻለው ትሰጠዋለች፡: አበ ልጆችም ይሆናሉ፡፡
በሌላ መንገድ ደግሞ በልሁና መርዕድ ትውውቅ እየፈጠሩ ነብር
መርዕድ ወደ እጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ከመዛወሩ በፊት ከዲላ በስተደቡ በሚገኘው በጩጩ ገብርኤል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ያስተምር
ነበር፡፡ በልሁ ደግሞ አዘውትሮ ወደ መስክ ስራ የሚሄደው በዚያ መስመር ስለነበር፣ በልሁ መርዕድ መምህር መሆኑን ስለሚያውቅ በአጋጠመው ጊዜ ሁሌ
ስለነበርና መርዕድም ብዙ ጊዜ ከዲላ ከተማ ወደ ስራው የሚሄደው በእግሩ ስለነበር
በልሁ መርእድ መምህር መሆኑን ስለሚያውቅ በአጋጠመዉ ጊዜ ሁሉ ለመስክ ስራ በሚጠቀምባት መኪና ላይ ያሳፍረዋል፡፡ በዚያው እየተግባቡ ይሄዳለ፡: መርዕድ በተፈጥሮው ተጫዋች በመሆኑ ለበልሁ በጣም እየተመችው
ይሄዳል ጫትም አብረው መቃም ይጀምራሉ።
በልሁና አስቻለው በከተማ ውስጥ በዓይን ይተዋወቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ደግሞ አስቻለው ከአንድ የዲላ ከተማ ነዋሪ ጋር ሆኖ በአንድ ቡና ቤት ውስጥ
ሻይ እየጠጡ ሳለ በልሁ ድንገት ይደርሳል፡፡ ያ ካአስቻለው ጋር የነበረ ሰው በልሁን በደንብ ያውቀው ኖሮ ቁጭ ብሎ" ሻይ እንዲጠጣ ይጋብዘዋል፡፡
በልሁም ቁጭ ይላል፡፡ ከአስቻለው ጋር የነበረው ሰው ለመሆኑ ሁለታችሁ ትተዋወቃላችሁ? ሲል ሁለቱንም ተራ በተራ እያየ ይጠይቃቸዋል፡፡ በዓይን ይሉታል። ሰውየው አስቻለውና በልሁን በቅደም ተከተል እየጠራ አንተ መንዜ፣ አንተ ቡልጌ፣ በትውልድ ስፍራ እኮ ጎረቤቶች ናችሁ ይላቸዋል፡፡
በልሁና አስቻለው ፈገግ ፈገግ በማለት እንደገና እየተጨባበጡ እንደ አዲስ የስም ትውውቅ ያደርጋሉ፡፡ ከዚያ በኋላ፤ መንገድ ላይ በተገናኙ ቁጥር ጠበቅ ያለ ሰላምታ መለዋወጥ ይቀጥላሉ፡፡
አንዳንዴም ሻይ ቡና መገባበዝ ይጀምራሉ::

ከወራት በኋላ ሁለቱን የበለጠ የሚያቀራርብ አጋጣሚ ተፈጠረ አንድ ምሽት ላይ በልሁ በአንድ ቡና ቤት ውስጥ በተለምዶ ባለጌ ወንበር ተብላ በምትጠራ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብሎ ይጠጣል አንዳት የቡና ቤቱ አስተናጋጅ አጠገቡ ቆም እያለች ታጫውተዋለች። በቡና ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብለው ይጠጡ የነበሩ አራት ጎረምሶች ልጅቷን እየፈለጉ በልሁን መተናኮል ይጀምራሉ በልሁ ግን ንቋቸው ዝም ብሎ ልጅቷን ያጫውታል ቆየት ብለው ከጎረምሶቹ መሀል መስከር የጀመረው አንዱ ልጅቷን በሀይል ጎትቶ ሊወስድ ወደ ልጅቷና በልሁ መራመድ ሲጀምር ድንገት አስቻለው ይደርሳል።
በልሁ ከተቀመጠበት ባለጌ ወንበር ላይ ወርዶ ጎረምሳውን ሊመታ ሲል አስቻለው ይይዘውና ወደ ጎረምሳው ዞሮ ብሎ 'አንተ እረፍ እንጂ' ይለዋል። ጎረመሳው ግን 'ምን አገባህ' ብሎ በአስቻለው ላይ ያፈጣል። አስቻለው ደግሞ ሲያስጠነቅቀው ያ ጎረምሳ ጭራሽ ይጠገዋል።በዚህ ጊዜ ጎረምሳው የተማመነባቸው ጓደኞቹ አስቻለውንና በልሁን ሊመቱ ግር ብለው ወደ እነሱ ይመጣሉ።ድብድብ ይጀመራል አስቻለውና በልሁ ከወንበር ወደ ወንበር ከጠረጴዛ ወደ ጠረጴዛ እየዘለሉ እነዚያን ጎረምሶች አመድ ያደርጓቸዋል ሁሉንም ይዘርሯቸዋል በድብድቡ ምክንያት የቡና ቤቱ ብርጭቆዎች እንዳሉ ይሾቃሉ ወንበሮች ይሰባበራሉ ይጮሀል ፖሊስ ይደርሳል በልሁና አስቻለው ታስረው ያድራሉ በፖሊስ። በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ሲያድሩ እንቅልፍ አልወሰዳቸውም ነበር።ሲያወሩና ሲጫወቱ ይነጋል።
ጠዋት በዋስ ሲለቀቁ ወደ አስቻሴው ቤት ነበር የሄዱት ለእንቅልፍ አረፍ ሊሉ በልሁ አስቻለው ቤት ሲገባ በቅድምያ አይኑ ያረፈው በአስቻለው አልጋ ፊት ለፊት ለጫት መቃምያ የተነጠፈች በምትመስል ፍራሽ ላይ ነበር።
ጫት ትቅማለህ እንዴ?» ሲል እስቻለውን ይጠይቀዋል፡፡
«እንደውም»
«ፍራሿ ታድያ»
«ባልቅምም ሲቃም ደስ ስለሚለኝ አንዳንዴ የስራ ባልደረቦቼ እየመጡ ይቅሙበታል።
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በልሁ ቅስሙ ስብር አለ ከሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ የተሰጠው ምልክትና አድራሻ ያ መናፈሻ ብቻ ነበር።ሃምሳ አለቃ እራሱ በአስመራ ከተማ ውስጥ ከዚያ መናፈሻ በስተቀር ሌላ አካባቢ ብዙም አያውቅም። የአስመራ ቆይታው አጭር ስለ ነበርጰተዘዋውሮ አላየውም።
“ምን ይሻለኛል ታዲያ የኔ ወንድም" ሲል በልሁ ጭንቅ እያለው ሹፌሩን ጠየቀው።
«እኔ እንጃ!» አለና ሾፌሩ ለአፍታ ያህል ቆየት ብሎ ወዴ በልሁ ዞር በማለት «እዚያ የሚሰራ ሰው ነበር የሚፈልጉት?» ሲል ጠየቀው
«እዚያ አዘውትሮ የሚገባ ወንድሜን ነበር፡፡»
«ታዲያ አንዱ ጋ አረፍ ብለው ያፈላልጉታ»
በልሁ ለአፍታ ያህል ፀጥ ብሎ ሲያሰላስል ቆየና እስቲ ጥሩ ማረፍያ ወደምትለው ሆቴል ውሰደኝ።አለው የበልሁ ተክለ ሰውነታዊ ገፅታና በራሱ
አንደበት 'ጥሩ ማረፊያ' በማለት በተናገረው ቃል መሰረት ጥሩ ኗሪ
እንደሆነ የገመተው ሾፈር «ወደ ኮምፒሽታቶ ያሻልዎታል» አለው፡፡
«ኮምፒሽታቶ ምንድነው?ሲል በልሁ ጠየቀው በልሁ ቃሉ የተለየ ትርጉም ካለው ብሎ በማሰብ።
መሀል ከተማ ላይ የሚገኝ ቦታ ነው ጥሩ ጥሩ ሆቴሎችም የሚገኙት በዚያው አካባቢ ነው።» አለ ሹፌሩ።
«እሺ እንሂድ!»
በእርግጥ በልሁም የገንዘብ ችግር የለበትም፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ወላጅ አባቱ እስቲ ብትኖርበትም ብትሽጠውም ቦታ መያዝ ደግ ነውና ቤት ለመስራት ሞክር በማለት ከሰጡት በርካታ ገንዘብ ላይ ግማሽ ያህሉን በመንገድ ሻንጣው ውስጥ አድርጐ ይዞት ሄዷል።አስቻለውን በመፈለግ ሂደት ታሪካዊቷን የአሥመራ ከተማ ለማየት ይጓጓ የነበረው በልሁ ገና ከጅምሩ መንፈሱ በስጋት በመወጠሩ በሚጓዝበት
ጎዳና ግራና ቀኙ ያሉትን የከተማዋን ቦታዎች እንኳ ልብ ብሎ ሳያይ ያ ባለ ታክሲ ተጉዞ ተጉዞ ከአንድ ኣካባቢ ሲደርስ ዳር ይዞ በመቆምም «ኮምፒሽታቶ
ማለት ይህ ነው!» አለው፡፡
«ወደ አንዱ ሆቴል ጠጋ ብታደርገኝ
«ይቻላል» አለና ሾፌሩ ከመንታ መንገዱ ወደ ቀኝ ታጠፈና ኒያላ
ሆቴል» ከተባለ ሆቴል በር ላይ አደረሰው፡፡
በልሁ የታክሲ አገልግሎት ክፍያውን ከምስጋና ጋር ከፈልና የልብስ ሻንጣውን ትከሻው ላይ አንግቶ ወደ ሆቴሉ የእንግዳ መቀበያ ክፍል አመራ፡፡አልጋ ሲጠይቅ መኖሩ ተነገረው፡፡ አንድ አስተናጋጅ ከፊት ከፊት እየመራ
ወሰደውና ክፍሉን አሳየው፡፡ ከፍሉ ንፁህና ግሩም የሚባል አልጋ አለው በልሁ የክፍሉን በር ዘግቶ አልጋው ላይ አረፍ በማለት ስለገጠመኑ ችግር ያሰላስል ጀመር፡፡ ማሰቡ ግን መላ አላስገኘሰትም፡፡ ይልቁንም የባሰ ጭንቅ ጭንቅ ይለው ጀመር፡፡
በምሀል አንድ ነገር ትዝ አለውና ከዚያው ጋር በተያዘ ሌላም ነገር ቆጨው በመሠረቱ አስቻለው አካል ጉዳተኛ ነው፡፡ ብዙ መጓዝ ስለማይችል ቤት የሚከራየው በሚሰራበት አካባቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ስራዬ መናፈሻ ውስጥ
የሚያዘወትር ከሆነም ቤቱም ሆነ መሥሪያ ቤቱ በዚያው አካባቢ ከመሆን እንደማያልፍ ገመተና ያንን ባለ ታክሲ በመናፈሻው አካባቢ ማረፊያ ወደዚያ አድርሰኝ ሳይለው በመቅረቱ ነበር ቁጭቱ፡፡ ሆኖም አሁንም ሳይዘገይ ጥሩ ሀሳብ እንደ መጣላት አስቦ ጭንቀቱ ከፈል ሲልለት ሀሳቡን ሰብሰብ አደረገና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሊገባ ፈለገ፡፡ የሚለብሰውን ፒጃማ አዘጋጀና ሊታጠብ ገባ።
ታጥቦ አበጥሮ ሲያበቃ ምግብ አሰኘው፡! ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ሄዶ ከበላ በኋላ በቀጥታ ከሆቴሉ ቅጥር ግቢ ወጣ፡፡ ሰዓቱ ከአስራ ሁለት እለፍ ብሏል፡፡ የመንገድ መብራቶች በርተዋል፡፡ ከሆቴሉ በስተግራ አቅጣጫ ተራመደና መንታውን መንገድ አቋርጦ ወደ ምዕራብ አቅጣፍ ደራመድ
ጀመር፡፡ የምሽት የአስመራ ውበት ማራኪ ነው፡፡ አየሩም ሞቅ ያለ፡፡
መብራቶቸ የደመቁ፡፡ የከተማዋ ከቀማመጥ ማራኪ፡፡ መንገዶች ንፁህና የተስተካከሉ፡: በልሁ በሁሉም የአስመራ ገፅታ እየተደሰተ በግምት እስከ ሶስት
መቶ ሜትር ከተጓዘ በኋላ በስተቀኙ በኩል አንድ በበረንዳው ላይ በርካታ ወንበሮች የተደረደሩበት፣ በሰው ብዛት ሞቅ ደመቅ ያለ ሆቴል አየና ጎራ
አለበት፡፡ ሰው አልባ የነበረች ጠረጴዛ አግኝቶ ቁጭ እንዳለ አንዲት ወፈር ያለች ጠይም ጎፈሬ አስተናጋጅ ቀረብ ኣለችውና፡-
«እንታይ ክዕዘዝ» አለችው፡፡
«ትግሪኛ አልችልም፡፡» አላት በልሁ ቀና ብሎ በፈገግታ እያያት
«ዋይ! ይቅርታ የኔ ወንድም!» ብላ አስተናጋጇ በፈገግታ ኣየት
ካደረገችው በኋላ «ምን ልታዘዝ ማለቴ እኮ ነው፡፡» አለችው::
በልሁ በልጅቷ ትህትናና ፈገግታ ደስ ብሎት እሱም ፈገግ በማለት
«ቢራ አምጪልኝ» አላት፡፡
አስተናጋጇ ቢራውን ይዛ መጥታ በብርጭቆ ሞላችለትና ከአጠገቡ ራቅ ብላ የግድግዳ ጥግ ደገፍ ብላ ቆመች፡፡ በልሁ ልጅቷ ያሳየችውን ትህትና አስታውሶ ሁኔታዋ ደስ ስላለው በልቡ ስላለው ጉዳይም ሊያወያያት ፈልገና ሊጠራት አሰበ፡፡ ነገር ግን በዚያች ቅጽበት ማጣደፉ ለሌላ ነገር ይመስላል በማለት ለጊዜው ተወት አረገው፡፡ የመጀመሪያውን ቢራ ጨርሶ ሁለተኛውን
ስታቀርብለት ግን እንደ ምንም ጨከነና፡-
«የኔ እህት ላነጋግርሽ እፈልግ ነበር!» ሲል ጠየቃት፡፡
«ምን?» አለችው አስተናጋጇ ጠጋ ብላ፡፡
«ቁጭ ማለት አትችይም?»
«እችላለሁ፡፡ብላው ቁጭ ልትል ወንበር ሳብ ስታደርግ በልሁ
ቀደማት:: እየጠጣሽ ነዋ»
አስተናጋጅዋ ሳቅ እያለች ወደ ውስጥ ገባችና ለራሷም ቢራ ይዛ
በመምጣት ከፊትለፊቱ ቁጭ አለች፡፡
«አስመራ፡ ከተማዋም ሰዎቹም በጣም ደስ ትላላችሁ» አላት በልሁ ፈገግ ብሎ እየተመለከታት፡፡
«አይደል?" አለች አስተናጋጇም እንደ መሽኮርመም እያደረጋት።
«በእውነት ታምራላችሁ፡፡»
«እናመሰግናለን::»
በልሁ አስተናጋጇን እያጫወተ ትንሽ ሳያሳስቃት ከቆየ በኋላ ወደ ዋና ጉዳዩ ተመለሰ፡፡ «አንድ ነገር ብጠይቅሽ ታውቂ ይሆን?» ሲል ጠረጴዛውን ደገፍ ብሎ ዓይን ዓይኗን እያየ ጠየቃት፡፡
«ምን?»
«እዚህ አስመራ ወስጥ 'ሰሪዬ መናፈሻ' የሚባል ሆቴል እንዳለ ሰምቻለ። የት አካባቢ ይሆን?»
«ያ የተዘጋው»
«ሲሉ ሰማሁ፤ ግን ለምን እንደተዘጋ ታውቂያለሽ?»
«ኧረ እኔም አላውቅም!» አለችና አስተናጋጇ በልሁን ለየት ባለ
እስተያየት ታየው ጀመር፡፡ በእርግጥ በልሁም የአስተያየቷ መለወጥ ገብቶታል።
«ምነው? መጠየቄ ቅር አለሽ እንዴ? ሲል ጠየቃት፡፡
«አይ እሱ እንኳ ብላ ንግግሯን ቆረጥ ስታደርገው በልሁ ጣልቃ ገባ።
«ቅር ካለሽ ጥያቄዬን አነሳለሁ፡፡» አለና ብርጭቆውን ብድግ አድርጎ ቢራውን ተጎነጨ
«የሸዋ ሰዎች እኮ አትታመኑም፡፡» ብላ አስተናጋጁ የቅንድቧ ስር
አሾልካ በልሁን አየት አደረገችው፡፡
«የሽዋ ሰው መሆኔን በምን አወቅሽ?» አላት በልሁ እንደመገረም ብሎ ለነገሩ አልተግባቡም፡ በልሁ የሸዋ ሰው ሰትለው የደብረ ብርሃን ተወላጅ
መሆኑን ያወቀች መስሎት ነው፡፡ እሷ ግን ቀደም ሲል ትግሪኛ አልችልም ስላላትና ለበርካታ የአስመራ ሰው ትግሪኛ የማይችል ሁሉ የሸዋ ሰው እንደያነ ተደርጎ ስለሚገመት ነው።
«ትግሪኛ አልችልም አላልከኝም?አለችው ፈገግ እያለች፡፡
«ትግሪኛ የማይችል ሁሉ የሸዋ ሰው ነው እንዴ» ሲል ጠየቃት
👍103👎1